You are on page 1of 6

በአማርኛ እንዴት ታይፕ አደርጋለሁ?

አደርጋለሁ?
የአማርኛ ፊደላትን በኮምፒውተር ታይፕ ለማድረግ ተቀራራቢነት ያላቸውን የእንግሊዝኛ ፊደላትን
በመጠቀም መምታት ይቻላል። ይህም «phonetic» ይባላል። ፊደሉ በአማርኛ ምን አይነት ድምጽ
እንዳለው በማሰብ የእንግሊዘኛ ቁልፎቹን በኮምፒውተሩ ሰሌዳ ላይ በመጠቀም የመምታት ዘዴ ነው።

ለምሳሌ፦ «selam» የሚለውን ቃል ታይፕ ለማድረግ «ሰላም» ይሆናል።

አማርኛ ከእንግሊዝኛ የበለጠ ብዙ ድምጽ ወይም ፊደል ስላለው አንዳንድ ጊዜ የሚወክለውን ፊደል
መለየት ያዳግታል። በመሆኑም ተጨማሪ ህግ ያስፈልገዋል። ለምሳሌ ‹ጠ›ን ታይፕ ለማድረግ በእንግሊዘኛ
ለብቻው የተወከለ ፊደል ስለሌለው በተቀራታቢነት ‹t›ን እንጠቀማለን። ነገር ግን ‹t› በጣም የሚቀርበው
ለ‹ተ› ፊደል በመሆኑ ትልቁን (capital) ‹T›ን በመጠቀም የምንፈልገውን ፊደል ማለትም ‹ጠ›ን
እናገኛለን።

ለምሳሌ፦ «TienaysTlN» – «ጤናይስጥልኝ» ይሆናል።

ከላይ በተመለከተው ምሳሌ ላይ ትልቁን (capital) ‹N›ን በመጠቀም ‹ኝ› ፊደልን ማግኘታችን ያስተውሉ።
እንዲሁም ‹ie› በአንድነት በመጠቀም የ‹ጠ› አምስተኛ ፊደል ‹ጤ› አስገኝቶናል። በዚህ ሁኔታ
የሚፈልጉትን ቃል ለማግኘት በድምጽ ቅርበት ያለውን የእንግሊዘኛ ፊደል በመጫን፣ አልያም (capital)
ትልቁን ፊደል ይህም ካለሆነ ደግሞ የፊደሉን ቁልፍ ሁለት ጊዜ ደግሞ በመጫን ይሆናል።
ለምሳሌ፦ «sselam» – «ሠላም» ይሆናል።
«SSeHey» – «ፀሐይ» ይሆናል።

በመጨረሻ ልናስረዳ የምንፈልገው የ‹አጣቃሽ› ወይም “ ’ ” (apostrophe)ን ለየት ያለ ህግ ነው።


የአንዳንድ ቃላቶች አወቃቀር ሳድስ ሆኖ በአናባቢ ወይንም (vowel) ሲቀጠል የአጣቃሽ ምልክቱን
መጠቀም ግድ ይሆናል። አለበለዚያ ግን ከፊት ለፊት የመታነውን ‹ሳድስ› ፊደል ይቀይረዋል። ይህንን
ለማሳየት እንዲረዳ «ገብርኤል» የሚለውን ቃል ለመምታት ከ‹ር› ፊደል በኋላ አጣቃሹን ከዚያ ደግሞ
‹ኤ›ን በመጠቀም «gebr'El» በማለት እናስቀምጣለን። አጣቃሹን ባንጠቀም ግን ‹ር› ወደ ‹ሬ› ይቀየራል።

ለምሳሌ፦ «mel'ak» – «መልአክ» ይሆናል።


«m'eeraf» – «ምዕራፍ» ይሆናል።

ይህንን አጣቃሽ ምልክት ለአማርኛ (Ethiopic) ቁጥሮችም ጠቀሜታ አለው። በዚሁም መሰረት '1-፩
ይሆንና ሌሎቹም በዚሁ መልክ ያገኛሉ። እራሱ አጣቃሹን “ ’ ” ለመጠቀም ደግሞ ምልክቱን ሁለት
ጊዜ ደግሞ በመምታት ይሆናል። ይህ ዘዴ ለሌሎችም ምልክቶች (punctuation) ይጠቅማል። በዚሁ
ሁኔታ ይህንን ምልክት ‹;› በመሆን በመጀመሪያ ጊዜ ሲመታ ‹፤› የአማርኛ ፊደሉን (ምልክቱን)
ሲያስገኝ፣ ደግመው ሲመቱት ደግሞ የእንግሊዘኛውን ምልክት ‹;› ያስገኛል።

ከዚህ በታች የሚታየው ሰንጠረዥ ጠቅላላውን የአማርኛ ፊደላት፣ ቁጥሮችና ምልክቶች እንዴት ታይፕ
ማድረግ እንደሚቻል ያሳያል።
Amharic Typing Table
ዘመደ - ዘመደ - ዘመደ - ዘመደ - ዘ መ ደ -
ቤተሰብ ግ ዕ ዝ ካ ዕ ብ ሣ ል ስ ራ ብ ዕ ኃ ምስ ሳ ድ ስ ሳ ብ ዕ
ግዕዝ ካዕብ ሣልስ ራብዕ ኃምስ
ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ሆይ
he hu hi ha hie h ho
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ ሏ
ላዊ
le lu li la lie l lo lua
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ ሗ
ሐውት
He Hu Hi Ha Hie H Ho Hua
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ ሟ
ማይ
me mu mi ma mie m mo mua
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ ሧ
ሠውት
sse ssu ssi ssa ssie ss sso ssua
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ ሯ
ርእስ
re ru ri ra rie r ro rua
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ ሷ
ሳት
se su si sa sie s so sua
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ ሿ
ሻ-ሳት
xe xu xi xa xie x xo xua
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ ቈ ቊ ቍ ቋ ቌ
ቃፍ
qe qu qi qa qie q qo que qui quu qua quie
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧ
ቤት
be bu bi ba bie b bo bua
ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ ቯ
ቬ-ቤት
ve vu vi va vie v vo vua
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ ቷ
ታው
te tu ti ta tie t to tua
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ ቿ
ቻ-ታው
ce cu ci ca cie c co cua
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ ኈ ኊ ኍ ኋ ኌ
ኀርም
hhe hhu hhi hha hhie hh hho hue hui huu hua huie
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ ኗ
ነሐስ
ne nu ni na nie n no nua
ኘ ኙ ኚ ኛ ኜ ኝ ኞ ኟ
ኛ-ነሐስ
Ne Nu Ni Na Nie N No Nua
አ አ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ
አልፍ
a u i ea ie e o ea
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ ኰ ኲ ኵ ኳ ኴ
ካፍ
ke ku ki ka kie k ko kue kui kuu kua kuie
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ
ኻ-ካፍ
Ke Ku Ki Ka Kie K Ko
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ወዌ
we wu wi wa wie w wo
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዐይን
aaa uu ii aa iie ee oo
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ ዟ
ዘይ
ze zu zi za zie z zo zua
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ ዧ
ዠ-ዘይ
Ze Zu Zi Za Zie Z Zo Zua
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
የመነ
ye yu yi ya yie y yo
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ ዷ
ድንት
de du di da die d do dua
ጅ- ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ ጇ
ድንት je ju ji ja jie j jo jua
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ ጐ ጒ ጕ ጓ ጔ
ገምል
ge gu gi ga gie g go gue gui guu gua guie
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ ጧ
ጠይት
Te Tu Ti Ta Tie T To Tua
ጨ- ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ ጯ
ጠይት Ce Cu Ci Ca Cie C Co Cua
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ ጷ
ጰይት
Pe Pu Pi Pa Pie P Po Pua
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ ጿ
ጸደይ
Se Su Si Sa Sie S So Sua
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ፀጳ
SSe SSu SSi SSa SSie SS SSo
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ ፏ
አፍ
fe fu fi fa fie f fo fua
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ ፗ
ፕሳ
pe pu pi pa pie p po pua

፡ ። ፣ ፤ ፥ ፦ ' , ;
: :: , ; ,, :- ' ' ,,, ;;
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱
'1 '2 '3 '4 '5 '6 '7 '8 '9
፲ ፳ ፴ ፵ ፶ ፷ ፸ ፹ ፺ ፻ ፲፻ ፼
'10 '20 '30 '40 '50 '60 '70 '80 '90 '100 '1000 '10000
የተለያየ ቋንቋን ታይፕ የማድረግ ዘዴ

ዩኒኮድ የተሰኘው ዘዴ ከተፈጠረ በኋላ በርካታ የአማርኛ ፊደላትን በኮምፒውተር ለመምታት


አስችሏል። ይኸው ዩኒኮድ በተለያዩ ቋንቋዎች 461 የኢትዮጲክ ፊደላትን ለመጻፍ ያስችላል።
ይህም በጣም ብዙ ፊደላት ስለሆኑ በአማርኛ የታይፕ ሰሌዳ ላይ ያልተፈለገ ቃላትን ላለመፍጠር
ሲባል ይህ የዩኒኮድ ዘዴ አይሰራም። ነገር ግን እነኝህን የኢትዮጲክ ፊደላት መጠቀም አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ ይህንን የዩኒኮድ የታይፕ ሰሌዳን መጠቀም ይቻላል።

ዩኒኮድን ለመጠቀም ሁለት አይነት መንገድ አለው።

1. Ctrl + Alt + Yን በአንድነት በመምታት፣ ይህን ምልክት የታችኛው ታስክ ባር


ላይ እንዲመጣና ዩኒኮድን ለመተቀም ዝግጁ መሆኑን ያሳያል።
2. በታስክ ባሩ ላይ ይህንን ምልክት በመጫን ከዚያም ደግሞ ይህንን ምልክት
በተከታታይነት በመጫን የታይፕ ሰሌዳውን ለዩኒኮድ ማዘጋጀት ይቻላል።

ሌሎች ቋንቋዎችን እንዴት ታይፕ እንደሚደረግ ከዚህ በታች ይታያል።

Awngi/Blin/Kayla/Kufal/Quara/Qimant/Xamtanga
ጘ ጙ ጚ ጛ ጜ ጝ ጞ
Ge Gu Gi Ga Gie G Go
ⶓ ⶖ ⶔ ጟ ⶕ
Gue Guu Gui Gua Guie

Bench
ⶠ ⶡ ⶢ ⶣ ⶤ ⶥ ⶦ
xxe xxu xxi xxa xxie xx xxo
ⶨ ⶩ ⶪ ⶫ ⶬ ⶭ ⶮ
cce ccu cci cca ccie cc cco
ⶰ ⶱ ⶲ ⶳ ⶴ ⶵ ⶶ
ZZe ZZu ZZi ZZa ZZie ZZ ZZo
ⶸ ⶹ ⶺ ⶻ ⶼ ⶽ ⶾ
CCe CCu CCi CCa CCie CC CCo
Ge’ez
ይዘት ደረት ርክርክ ኅጺር፡ ድፋት ቅናት ጭረት ሒደት ቁርጥ
ርክርክ
᎐ ᎑ ᎒ ᎓ ᎔ ᎕ ᎖ ᎘ ᎙
_1 _2 _3 _4 _5 _6 _7 _8 _0

፧ ፠ ፨
? :+ :#
የግዕዝ ቁጥሮችም በዚሁ በዩኒኮድ ዘዴ በመጠቀም ታይፕ ማድረግ ይቻላል። ይህንንም በምናደርግ
ጊዜ ከፊት ለፊቱ አጣቃሹን “ ’ ” ታይፕ ማድረግ አያስፈልገንም። ይህኛው መንገድ በጥቂቱም
ቢሆን ቀላል ዘዴ ነው።

Me’en/Mursi/Suri
ሇ ⶀ ⶁ ⶂ ⶃ ⶄ ቇ ⶅ ⶆ ⶇ ኇ ⶈ ⶉ ⶊ
hoa loa moa roa soa xoa qoa boa toa coa hhoa noa Noa oa
ኯ ዏ ⶋ ዯ ⶌ ⶍ ⶎ ጏ ⶏ ⶐ ⶑ ፇ ⶒ
koa woa zoa yoa doa Doa joa goa Toa Coa Poa SSoa poa

Me’en/Mursi/Suri/Dizi & Historical Oromo/Sidama


ዸ ዹ ዺ ዻ ዼ ዽ ዾ ዿ
De Du Di Da Die D Do Dua

Sebatbeit
ⷀ ⷁ ⷂ ⷃ ⷄ ⷅ ⷆ
qye qyu qye qye qye qye qyo
ⷈ ⷉ ⷊ ⷋ ⷌ ⷍ ⷎ
kye kyu kyi kya kyie ky kyo
ⷐ ⷑ ⷒ ⷓ ⷔ ⷕ ⷖ
Kye Kyu Kyi Kye Kyie Ky Kyo
ⷘ ⷙ ⷚ ⷛ ⷜ ⷝ ⷞ
gye gyu gyi gya gyie gy gyo

ᎀ ᎁ ᎂ ᎃ
mue mui muie muu
ᎄ ᎅ ᎆ ᎇ
bue mue buie buu
ᎈ ᎉ ᎊ ᎋ
fue fue fuie fuu
ᎌ ᎍ ᎎ ᎏ
pue pue puie puu
Tigrinya
ቐ ቑ ቒ ቓ ቔ ቕ ቖ
Qe Qu Qi Qa Qie Q Qo
ቘ ቝ ቚ ቛ ቜ
Que Quu Qui Qua Quie
ዀ ዅ ዂ ዃ ዄ
Kue Kuu Kui Kua Kuie

የአማርኛ ሶፍትዌሩን ለመጫንና ለመጠቀም


ይህ ፋይል AmharicPowerPack7.exe ሶፍትዌሩን Tavultesoft Keymanንና ፎንቱን
(የኮምፒውተር ፊደላቱን) የያዘ ነው። የሶፍትዌሩ አጫጫን ዘዴም እንደሚከተለው ይሆናል፦
1. ሁለት ጊዜ ደግመው ይጫኑትና የአጫጫኑን ትዕዛዝ በሚገባ ይከተሉ
2. ሶፍትዌሩን በሚገባ ከጫኑ በኋላ “ፕሮግራም” ስር Tavultesoft Keymanንን ያገኛሉ።
ፕሮግራሙን ለመጀመር፦
በመጀመሪያ Start > ከዚያ All Programs
> ከዚያ Tavultesoft Keyman Desktop Light 7.1
> ከዚያ Keyman Desktop Light 7.1 ይጫኑ

3. በታስክ ባሩ በቀኝ በኩል የሚታየውን ይህን ምልክት መጫን


4. ይህን ሲያደርጉ የሚመጣው መስኮት ላይ የሚታየውን ይህንን ምልክት መምረጥ
5. የኢትዮጲክ ፊደልን (ፎንት) መምረጥና ታይም ማድረግ ይቻላል

You might also like