You are on page 1of 4

በአማርኛ እንዴት ታይፕ አደርጋለሁ?

ፊደል (አ) በአማርኛ ኪቦርድ፣ ለአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ብቻ ለሚውሉ ፊደላት ያገለግላል። የአማርኛ
ፊደላትን በኮምፒውተር ታይፕ ለማድረግ ተቀራራቢነት ያላቸውን የእንግሊዝኛ ፊደላትን በመጠቀም
መምታት ይቻላል። ይህም «phonetic» ይባላል። ፊደሉ በአማርኛ ምን አይነት ድምጽ እንዳለው በማሰብ
የእንግሊዘኛ ፊደላቱን በኮምፒውተሩ ሰሌዳ ላይ በመጠቀም የመምታት ዘዴ ነው።

ለምሳሌ፦ «selam» የሚለውን ቃል ታይፕ ለማድረግ «ሰላም» ይሆናል።

አማርኛ ከእንግሊዝኛ የበለጠ ብዙ ድምጽ ወይም ፊደል ስላለው አንዳንድ ጊዜ የሚወክለውን ፊደል መለየት
ያዳግታል። በመሆኑም ተጨማሪ ህግ ያስፈልገዋል። ለምሳሌ ‹ጠ›ን ታይፕ ለማድረግ በእንግሊዘኛ ለብቻው
የተወከለ ፊደል ስለሌለው በተቀራታቢነት ‹t›ን እንጠቀማለን። ነገር ግን ‹t› በጣም የሚቀርበው ለ‹ተ› ፊደል
በመሆኑ ትልቁን (capital) ‹T›ን በመጠቀም የምንፈልገውን ፊደል ማለትም ‹ጠ›ን እናገኛለን።
ለምሳሌ፦ «TienaysTlN» – «ጤናይስጥልኝ» ይሆናል።

ከላይ በተመለከተው ምሳሌ ላይ ትልቁን (capital) ‹N›ን በመጠቀም ‹ኝ› ፊደልን ማግኘታችን ያስተውሉ።
እንዲሁም ‹ie› በአንድነት በመጠቀም የ‹ጠ› አምስተኛ ፊደል ‹ጤ› አስገኝቶናል። በዚህ ሁኔታ የሚፈልጉትን
ቃል ለማግኘት በድምጽ ቅርበት ያለውን የእንግሊዘኛ ፊደል በመጫን፣ አልያም (capital) ትልቁን ፊደል
ይህም ካለሆነ ደግሞ የፊደሉን ቁልፍ ሁለት ጊዜ ደግሞ በመጫን ይሆናል።

ለምሳሌ፦ «sselam» – «ሠላም» ይሆናል።


«SSeHey» – «ፀሐይ» ይሆናል።

በመጨረሻ ልናስረዳ የምንፈልገው የ‹አጣቃሽ› ወይም “ ’ ” (apostrophe)ን ለየት ያለ ህግ ነው።


የአንዳንድ ቃላቶች አወቃቀር ሳድስ ሆኖ በአናባቢ ወይንም (vowel) ሲቀጠል የአጣቃሽ ምልክቱን መጠቀም
ግድ ይሆናል። አለበለዚያ ግን ከፊት ለፊት የመታነውን ‹ሳድስ› ፊደል ይቀይረዋል። ይህንን ለማሳየት
እንዲረዳ «ገብርኤል» የሚለውን ቃል ለመምታት ከ‹ር› ፊደል በኋላ አጣቃሹን ከዚያ ደግሞ ‹ኤ›ን
በመጠቀም «gebr'El» በማለት እናስቀምጣለን። አጣቃሹን ባንጠቀም ግን ‹ር› ወደ ‹ሬ› ይቀየራል።

ለምሳሌ፦ «mel'ak» – «መልአክ» ይሆናል።


«m'eeraf» – «ምዕራፍ» ይሆናል።

በጽሁፋችሁ ውስጥ አጣቃሽ ምልክትን ( ’ ) ከሳድስ ፊደል በኋላ መጠቀም ካስፈለገ፣ ምልክቱን ሁለት
ጊዜ እንደሚከተለው መምታት አስፈልጋል።

ለምሳሌ፦ k'' – ክ’ ይሰጠናል

ከዚህ በታች የሚታየው ሰንጠረዥ ጠቅላላውን የአማርኛ ፊደላት፣ ቁጥሮችና ምልክቶች እንዴት ታይፕ
ማድረግ እንደሚቻል ያሳያል።
የአማርኛ ታይፕ መለማመጃ ሰነድ ከዚህ በታች በሚገኘው ሊንክ አማካኝነት ዳውንሎድ ማድረግ
ይቻላል፦
http://keyboards.ethiopic.org/docs/AmharicTypingPractice.docx
የአማርኛ ታይፕ ሰንጠረዥ
ዘመደ- ዘመደ- ዘመደ- ዘመደ- ዘመደ-
ቤተሰብ ግዕዝ ካዕብ ሣልስ ራብዕ ኃምስ ሳድስ ሳብዕ
ግዕዝ ካዕብ ሣልስ ራብዕ ኃምስ
ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
ሆይ
he hu hi ha hie h ho
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ ሏ
ላዊ
le lu li la lie l lo lua
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ ሗ
ሐውት
He Hu Hi Ha Hie H Ho Hua
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ ሟ
ማይ
me mu mi ma mie m mo mua
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ ሧ
ሠውት
sse ssu ssi ssa ssie ss sso ssua
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ ሯ
ርእስ
re ru ri ra rie r ro rua
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ ሷ
ሳት
se su si sa sie s so sua
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ ሿ
ሻ-ሳት
xe xu xi xa xie x xo xua
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ ቈ ቍ ቊ ቋ ቌ
ቃፍ
qe qu qi qa qie q qo que quu qui qua quie
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧ
ቤት
be bu bi ba bie b bo bua
ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ ቯ
ቬ-ቤት
ve vu vi va vie v vo vua
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ ቷ
ታው te tu ti ta tie t to tua
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ ቿ
ቻ-ታው
ce cu ci ca cie c co cua
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ ኈ ኍ ኊ ኋ ኌ
ኀርም
hhe hhu hhi hha hhie hh hho hue huu hui hua huie
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ ኗ
ነሐስ
ne nu ni na nie n no nua
ኘ ኙ ኚ ኛ ኜ ኝ ኞ ኟ
ኛ-ነሐስ
Ne Nu Ni Na Nie N No Nua
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ
አልፍ
a u i aaaa ie e o
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ ኰ ኵ ኲ ኳ ኴ
ካፍ
ke ku ki ka kie k ko kue kuu kui kua kuie
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ
ኻ-ካፍ
Ke Ku Ki Ka Kie K Ko
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ወዌ we wu wi wa wie w wo
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዐይን
aaa uu ii aa iie ee oo
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ ዟ
ዘይ
ze zu zi za zie z zo zua
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ ዧ
ዠ-ዘይ
Ze Zu Zi Za Zie Z Zo Zua
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
የመነ
ye yu yi ya yie y yo
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ ዷ
ድንት
de du di da die d do dua
ጅ- ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ ጇ
ድንት je ju ji ja jie j jo jua
ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ ጐ ጕ ጒ ጓ ጔ
ገምል
ge gu gi ga gie g go gue guu gui gua guie
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ ጧ
ጠይት
Te Tu Ti Ta Tie T To Tua
ጨ- ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ ጯ
ጠይት Ce Cu Ci Ca Cie C Co Cua
ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ ጷ
ጰይት
Pe Pu Pi Pa Pie P Po Pua
ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ ጿ
ጸደይ
Se Su Si Sa Sie S So Sua
ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ፀጳ
SSe SSu SSi SSa SSie SS SSo
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ ፏ
አፍ
fe fu fi fa fie f fo fua
ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ ፗ
ፕሳ pe pu pi pa pie p po pua
ስርዓተ ነጥቦችን ታይፕ ማድረጊያ
የኢትዮፒክ ስርዓተ ነጥቦች

፡ ። ፣ ፤ ፦ ፥ ፠ ፨
: :: , ; :- ,, :+ :#

‹ › « »
< > << >>

የኪቦርድ ስርዓተ ነጥቦች

ሁሉም የተለመዱ ስርዓተ ነጥቦች በኪቦርድዎ ላይ ይገኛሉ። አብዛኛዎቹ ስርዓተ ነጥቦች


እንደተለመደው አንድ ጊዜ ብቻ በመምታት ታይፕ ማድረግ ይቻላል። የኢትዮፒክ ምልክቶቹን
ለማግኘት አንዳንዶቹ የስርዓተ ነጥቦቹን ቁልፍ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የምንፈልገውን ምልክት
እስክናገኝ መምታት።

ቁጥሮችን ታይፕ ማድረግ

ሐሽ ማርክ (hash mark) እየተባለ የሚታወቀው ምልክት በግዕዝ ቁጥሮች ጥቅም ላይ ይውላል፤
ስለሆነም #1 ወደ ፩ ይለወጣል፤ እንዲህ እያለ ይቀጥላል። ይህ የቁጥር ምልክት ‘#’ በሰነድ ጽሁፍዎ
ላይ ከቁጥሩ በፊት ሲያስፈልግ፣ ይህንኑ የቁጥር ምልክት ‘#’ ሁለት ጊዜ ታይፕ ማድረግ።

የኢትዮፒክ ቁጥሮች

፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱
#1 #2 #3 #4 #5 #6 #7 #8 #9
፲ ፳ ፴ ፵ ፶ ፷ ፸ ፹ ፺ ፻ ፲፻ ፼
#10 #20 #30 #40 #50 #60 #70 #80 #90 #100 #1000 #10000

የአኅዝ ጥንቅሩ ዜሮ (0) ቁጥሮችን በመጨመር እስክ ፼፼ (100,000,000) ይቀጥላል።

You might also like