Professional Documents
Culture Documents
በብንያም ከድር
ታህሳስ 2013
አ.አ
ማውጫ
1.የአማርኛ ቋንቋ ሆሄያት እና ብዛታችው...............................................................................................................3
1
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
4. በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ የሚገኙ የባዕድ ሀገራት ቃላቶች ትክክለኛ የግዕዝ ፍቺያቸው.................................................5
5.ስነ ድምፅ.........................................................................................................................................................7
6. ምንባብ አንድ..................................................................................................................................................7
8. ምንባብ ሁለት...............................................................................................................................................11
9.የስም እርባታ..................................................................................................................................................14
10.የቅፅል አይነቶች............................................................................................................................................15
11.ግስ..............................................................................................................................................................16
13. መስተዓምር፡-..............................................................................................................................................18
14. ምዕላድ.......................................................................................................................................................19
15 የምስረታ ምዕላድ.........................................................................................................................................20
16.ምንባብ ሶስት...............................................................................................................................................21
17. አ.ነገር........................................................................................................................................................24
20.ሥነፅሁፍ.....................................................................................................................................................30
21.ግጥም.........................................................................................................................................................32
22.የግጥም አይነት.............................................................................................................................................33
23.ቲያተር........................................................................................................................................................33
24. ዘይቤ..........................................................................................................................................................34
25.ቅኔ..............................................................................................................................................................38
26.አንቀፅ.........................................................................................................................................................38
2
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ
መ ሙ ሚ ማ ሜ ም ሞ ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ ጰ ጱ ጲ ጳ ጴ ጵ ጶ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ ጸ ጹ ጺ ጻ ጼ ጽ ጾ
ሰ ሱ ሲ ሳ ሴ ስ ሶ ፀ ፁ ፂ ፃ ፄ ፅ ፆ
ሸ ሹ ሺ ሻ ሼ ሽ ሾ ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ
ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ ፐ ፑ ፒ ፓ ፔ ፕ ፖ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ቶ
ቸ ቹ ቺ ቻ ቼ ች ቾ
ኀ ኁ ኂ ኃ ኄ ኅ ኆ
ነ ኑ ኒ ና ኔ ን ኖ
ኘ ኙ ኙ ኛ ኜ ኝ ኞ
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ
ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ
ወ ዉ ዊ ዋ ዌ ው ዎ
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ
ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ
የመጀመሪያ ፊደላት ብዛት 34 ሲሆን አጠቃላይ ሁሉም ፊደላት ብዛት 238 ናቸው
ማሳሰብያ
የአማርኛ ቋንቋ ከግዕዝ 24 ፊደላትን ወስዷል እነሱም
ሀ፣ለ፣ሐ፣መ፣ሠ፣ረ፣ሰ፣ቀ፣በ፣ተ፣ኀ፣ነ፣አ፣ከ፣ወ፣ዐ፣ዘ፣የ፣ደ፣ገ፣ጠ፣ጸ፣ፀ፣ፈ፣ፐ ናቸው፡፡
ጰ ከግሪክ
ፐ እና ቨ ከእንግሊዘኛ
ኸ፣ዠ፣ጀ፣ጨ፣ቸ፣ሸ፣ኘ፣የ ከኩሽ ቋንቋ የተወሰዱ ፊደላት ናቸው፡፡
3
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ስለዚህ አማርኛ የራሱ የሆኑ ፊደላት የሉትም ሁሉንም ፊደሎች ከ ግዕዝ ከኩሽ ቋንቋዎች ከግሪክ እና
ከእንግሊዘኛ የወሰዳቸው ናቸው፡፡
ሀ ፣ ሐ፣ ኸ፣ ኀ ሠ፣ ሰ አ፣ ዐ ጸ፣ ፀ
የሆሄያት ስያሜ
70 ፸ ሰባ 80 ፹ ሰማንያ 90 ፺ ተሰዓ
ማስገንዘቢያ
ከ 10 -19 ለመፃፍ አስርን ከፊት አስቀድሞ ከ አንድ እስከ ዘጠኝ ያሉትን ቁጥሮች ማስከተል ነው፡፡
ከ 20-90 ያሉትን ለመፃፍ ከ 20 እስከ 90 ያሉትን ከፊት አስቀድሞ ከ አንድ እስከ 9 ያሉትን ቁጥሮች
ማስከተል፡፡
ከ 100 -900 ለመፃፍ ከ 1-9 ያሉትን ቁጥሮች አስቀድሞ መቶን ማስከተል፡፡
ከ 1000- እስከ 9000 ለመፃፍ ከ 10-90 ያሉ ቁጥሮችን በማስቀደም 100 ማስከተል ነው፡፡
ከ 10 ሺህ እስከ 90 ሺህ ያሉትን ለመፃፍ ከ 1-9 በማስቀደም አስርሺን መጻፍ፡፡ ወ.ዘ.ተ
4
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ሰው ከገነት ከተባረረ በኋላ በአምላኩ ቃል የተገባለት 5500 ዘመን በኋላ ተመልሶ መጥቶ እንደሚያድነው ነው
እነሆ የሰው ልጅ ከዳነ ዘንድሮ 2012 ዓመታት ተቆጠሩ
5500 አመታት ሲቆጠሩ ዓመተ ዓለም ይባላል
2012 ኣመታት ሲቆጠሩ ዓመተ ምህረት ይባላል
ስለዚህ ዘመንን ለመስራት የሚከተለውን መንገድ እንጠቀማለን
7512- (4 x 1878)
3.2 መባቻ
(7512 + 1878) ÷ 7
9390 ÷ 7
4. በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ የሚገኙ የባዕድ ሀገራት ቃላቶች ትክክለኛ የግዕዝ ፍቺያቸው
5
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
10. 1675---------------- 11. 709 ------------------ 12. 1267 --------------------13. 9876 -------------------
6
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
5.ስነ ድምፅ
ለማንኛውም ቋንቋ መሰረቱ ድምፅ ነው፡፡
የአማርኛ ቋንቋ ሁለት አይነት ድምፆቸ አሉት እነሱም ተነባቢ እና አናባቢ ይባላሉ፡፡
ተነባቢ ድምፆች
አማርኛ 30 ተነባቢ ድምፆች ያሉት ሲሆን 27 ተራ 3 ውስብስብ ናቸው፡፡
ከ 27 ተራ ተነባቢ ድምፆች መካከል 3 ቱ የተውሶ ድምፆች ናቸው፡፡ እነሱም /ፕ፣ጵ እና ፅ/ ናቸው፡፡
ክው፣ቅው፣ቅው የሚባሉት ድምፆች ውስብስብ ተነባቢ ድምፆች ይባላሉ፡፡
የአናባቢ እና የተነባቢ ቅንጅት
ፊደል ተነባቢ አናባቢ ቅንጅት
በ ብ ኧ ብኧ
ቡ ብ ኡ ብኡ
ቢ ብ ኢ ብኢ
ባ ብ ኣ ብኣ
ብ ብ እ ብእ
ቦ ብ ኦ ብኦ
ምሳሌ፡- 1. በር /ብኧር/
2. ጠርሙስ /ጥኧርምኡስ/
6. ምንባብ አንድ
------------------- በመጨረሻም በሰው አቆጣጠር በ 1770 ዓ.ም ተከታዩ ትዕዛዝ ደረሰን እስከዚህ ጊዜ ድረስ ማለትም የመጨረሻውን
6 ኛውን ክፍል ተግባራዊ አድረገን እስክናጠናቅቀቅና ተከታዩን ትዕዛዝ እስኪደርሰን ድረስ የመጨረሻ ጎላችን የትኛዋ አህጉር ውስጥ
የምትገኝ ምን የምትባል አገር እንደሆነች አናውቅም ነበር፡፡ ይህ ለኛ ገና አልተገለፀልንም ነበር፡፡ እናም ትእዛዙ ደረሰን አዲስቷን የምድር
መንግስት በዘመናዊ መልክ የመገንባት ስራችሁን ጀምሩ ተባልን፡፡
ይህ ማለት የቲዮሪው ትምህርት በሙሉ ወደ ተግባር ተለውጦ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኝበትና ወደ ሌላ አዲስ ስልጣኔ ሽግግር
መግባትና ማስቀጠል መቻል ተፈቀደልን ማለት ነው፡፡
ይህ ማለት በዚህ መፅሐፍ ውስጥ እንደሌሎቹ ያልተብራሩ በስም ብቻ የተጠቀሱና እኛ ድቅሎችና የሰው ልጅ ከስማቸው በቀር
አይነታቸውን እና መገኛ ቦታቸውን የማያውቃቸውን ነገሮችንም ሆነ በምድር እና በውስጧ ያሉ በርካታ ጠቃሚ የሆኑ ነገር ከምን ጋር
ሲጣመር እና ሲዋሀድ ምን እንደሚያስገኝ የዚያ ግኝት መጨረሻ ምን እንደሚሆን እና ሰዎች በምን መንገድ ጥቅም ላይ አውለው
ሊገለገሉበት እንደሚችሉ እየተሻሻለ ሄዶ የት እንደሚደርስና ሄዶ ሄዶ እንዴት ለልዑላችን ዋና አላማ ሊውል እንደተፈለገ ግልፅ ሆነልን
ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ጎላችንን እንድናውቅ ተፈቀደልን ማለት ነው! እናም እነዚህን ነገሮች የሚያብራሩ ቁጥራቸው የበዛ መንፍሳዊ
ጭፍሮች እንዳሉና እነሱን እንድንገናኝ ተነገረን፡፡ ቀጣይ ትዕዛዝ ያልኳችሁ ይህንን ነው፡፡ እንጠብቀውና እንፈልገው የነበረው ይህኑኑ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን የልኡላችን ጭፍሮች በስምና በስልጣን ለይተን እና አውቀን የትኛው መንፈሳዊ አካል በየትኛው ጉዳይ እንደተሾመ
ተረድተን የትኛው ለየትኛው እውቀትና ጥበብ ሊረዳን እንደሚችል ተገንዝበን ሁሉንም በየስማቸው እየጠራን ማዘዝ እና ለምንፈልገው
አላማ አማካሪ ማድረግ እንደምንችል ተነገረን፡፡ ነገር ግን እነሱንም ለማወቅ እና ለመገናኘት ተገናኝተንም እውቀታቸውን ለመካፈልና
ለመጠቀም እንቻል እንጂ ፈልገን የማግኘቱ ስራ ግን ለኛ ለንጉሳውያን ቤተሰቦች የተተወ የቤት ስራ ሆነ፡፡ የሰው ልጅ የመጀመሪያ
ፅሕፈት በሆነው ከሰው ልጅ ጋር በጥፋት ውሀ በዳነው የግዮን ምንጭ ባለበት አገር በአንድ ደብር የተቀመጠውን ሚስጥሩን ማንም
ባልፈታው በሄኖክ መፅሐፍ ሁሉንም እወቁት ሁሉንም ድረሱበት ይህ የእናንተ ስራ ነው በእናንተም መሰራት ያለበት ስራ ነው፡፡የእናንተ
7
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
የዘር ሀረግ የሚመዘዘው ከእነማን እንደሆነ የተዘረዘረበትም መፅሐፍ ስለሆነ የአያቶቻችሁን ቅድመ አያት ዋና ምንጭ የምታገኙበትም
ስለሆነ አግኙት ታሪክ እና ማንነታችሁን እዛ ስታገኙ ማን በምን ላይ እውቀት እንዳለው ማን በምን ላይ እንደተሾመ ከዚያ መፅሐፍ
ትረዳላችሁ ከአምስቱም የሄኖክ መፅሐፍት አግኙ የሚል ትዕዛዛ ነበር የደረሰን፡፡ ጎላችንን አወቅን ማለት ነው፡፡
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ሽግግሩ ገብተን አዲሲቷን የምድር መንግሰት ምስረታ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መንግድ ጀመርን፡፡ ስለ መፅሐፈ ሄኖክ
ከዚህ ቀደም በደንብ ተብራርቶላችኋል መፅሐፈ ሄኖክ፣ ሚስጠረ ሄኖክ፣ራዕየ ሄኖክ፣ ትንቢተነ ሄኖክ፣ነገረ ሄኖክ የሚባሉትን ናቸው
በእርግጥም ለኛ የጠቀመንና አሁን ለምንለው ነገር ሁሉ ሙሉ ምላሽ የነበረው ሚስጥረ ሄኖክ የሚለው ነው፡፡
ከዚያም የልዑላችን ታማኝ አገልጋይ የሖኑት አጠገባችሁ ያሉት ጳጳስ ቀደም ሲል እንዳብራሩላችሁ የእኔ ቅድመ አያት ተብላ
የምትታወቀው ነገር ግን እኔ እራሴ ከኛ ወገን የሖነውን ጀምስ ብሩስን በ 1770 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብና በቂ ስንቅ አስይዘን ላክነው፡፡
ሁሉንም የሄኖክ መፅሐፍት አገኛቸው በ 7 ዓመት ቆይታው መፅሐፈ ሄኖክን አዘበራርቆ ቀሪ ትቶላቸው ሌሎቹን ግን ቀሪ ሳይተው ይዞልን
መጣ በ 7 ዓመት ቆይታው በእኛ ትዕዛዝ ተምሮት እንዲመጣ በተደረገው የግዕዝ ቋንቋ፤ የግዕዝን የመጀመሪያ ፅሑፍ በቤተመንግስታችን
አብራራልን አቤት የጠደሰትነው ደስታ ----------!ያኔ እንደዛሬው ውስጥ አብርቶ ቋንቋን እንዲሁ መሞላት መቻልና በግዕዝ ልዑላችንን
እስከማምለክ የተደረሰበት ዘመን አልነበረም፡፡ እናም መፃህፍቱን አስረከበን፡፡ ሚስጥረ ሄኖክ ለጥያቄዎቻችን ሁሉ ምላሽ የሚሰጠንን
መንፈሳዊ ኣካለትን በስም ከመዘርዘር አልፎ ከፒራሚዳችን በላቲን ቋንቋ ተረቆ ከተሰጠን ቅድም ካያችሁት መፅሐፍ ጋር በማጣመር
ብቻ ያለማንም እገዛ በእኛ እውቀት ወደ ተግባር የምንለውጠው ጥበብ እስከ ማወቅ የደረሰ ሆነ፡፡
በእርግጥ ሄኖክ የበላይ አካሉ ተከታይ የሆነ እና ነ,ተነጥቆ ወደ ሰማይ የሄደ ነውና በመፅሐፉ የበላይ አካሉን እያሞገሰ እና የኛን ዘሮች እና
የልዑላችንን አላማ እያወገዘ ነበር የፃፈው፡፡ እኛ ግን በተቃራኒው በመፍታት ለወሳኝ ግብዓትነት ተጠቀምንበት፡፡
በሚስጥረ ሄኖክ ሁሉ በእጃችን ሁሉ በደጃችን ሲሆን የዘር ሀረጋችንን ከነሙሉ ታሪካችን በግልፅ አወቅንበት በጦርነቱ ስለተሰዉ
ዘሮቻችንም በጥልቀት ተረዳንበት፡፡ በራዕየ ሄኖክ እንዴት አድርገን ልኡላችንን በመጨረሻው ጦርነት እንደምናግዘው ተረዳን በራዕየ ሄኖክ
የበላይ አካሉ ልኡላችንን እንዴት አድርጎ በፍፃሜው ጦርነት ድል እንደሚነሳበት የተገለፀበትን ታሪክ መነሻ በማድረግ እንዴት መከላከል
እንዳለብንና እንዴት ልኡላችንን በእኛ እገዛ ለድል እንደምናበቃው ተገነዘብንበት፡፡ በትንቢተ ሄኖክ የበላይ አካሉ የመላዕክቱን ጭፍሮች
እንደሚያዘምት እና እንደሚያሰልፍ ተረድተን የራሳችንን አወቃቀርና አሰላለፍ እንዴት ማድረግ እንዳለብን ተገነዘብንበት፡፡
የሔኖክ መፅሐፍት ከኢትዮጵያ መጥተው እጃችን ከገቡ በኋላ በራሳችን መንገድ ተንትነን ጥቅም ላይ በማዋል ወደ አስደናቂ የሽግግር
ዘመን ተሻገርንባቸው የዘር ማንዘሮቻችንን ታሪክ መፅሐፉ እጃችን ሲገባ በስማቸው ሳይቀር ተዘርዝሮ ስናገኝማ በቤተ መንግስታችን
ታላቅ ፌሽታ ሆነ፡፡
ከኛ ጋር በመገናኘት የልኡላችን ትዕዛዝ የሚያሳውቁን የነበሩና በእኛ ለሚፈፀሙ ስራዎች ዝርዝር ትዕዛዝ ተቀብለው የሚያዙን
የልኡላችን ጭፍሮች ከዚህ ታሪካዊ መጽሐፍ ከመገኘት በኋላ የእነሱ በመልዕክተኝነት የማገልገል ቆይታ እንዳበቃና በቀጥታ ከዘሮቻችን
ጋር መገናኘት የምንችልበት መንገድ እንደተፈጠረ አወቅን፡፡ እኛም በቀጥታ ከዋና ዋና ከገዛ የዘር ሀረጎቻችን መናፍስት ጋር በነፃነት
እየተገናኘን የልኡላችንን ዓላማ የሚያሳካውን መንገድ ሁሉ በምንታዘዘው መሰረት በዘመናዊ መልኩ አዋቅረን ቀጠልንበት፡፡
በምንፈልገው ጉዳይ ላይ ማናቸውን ማዘዝና ማማከር እንዳለብን አውቀናልና ሁሉንም በስም እየጠራን የሚገባቸውን መስዋዕት
እያቀረብን ማዘዝ እና የተሰወረውን መግለጥ ገልጦም ወደ ተጨባጭ ነገሮች መለወጥ ማዘዝና የተሰወረውን መግለጥ ገልጦም ወደ
ተጨባጭ ነገሮች መለወጥ ቻልን፡፡ ከዚህ መፅሐፍ መገኘት በኋላ እየመነጠርን ያዘጋጀናትን ከተማ በቀደምት የዘሮቻችን መጠሪያ ስም
እየሰየምን በየኮከብና በምልክታቸው አርማ መሰረት የሕንፃዎች ግንባታ እያከናወንን ድንቅ አድርገን አሜሪካ የተባለችውን አገር
በመታሰቢያ ህንፃዎች አንቆጠቆጥናት ሰዎቻችንን አሰፈርን የጥበብ መፍለቂያ የሆነች የኛን የራሳችንም አገር ጨምረን በእንግሊዝ፣
በአሜሪካና በግዛታችን ካናዳ ሳይቀር ለዋና ዋናዎቹ የዘር ግንዶቻችን ሀውልት አቆምን ስልጣኔ ተቀጣጥሎ ቀጠለ፡፡ አዲስቷ የምድር
መንገስት ምስረታ በዘመናዊ መልክ ቀጥሎ ማንም ሕዝብ ዛሬም ድረስ ሳያውቀው ያማረና ቅርፅ የያዘ ሆኖ ታየ፡፡--------!አሉና እንደ
ህፃን ልጅ ፍልቅልቅ የሚል ገፅታ እያሳዩ በሳቅ እየተንከተከቱ መድረኩ ላይ እንደመዝለል አሉና ቀጠሉ፡፡
‹‹ አዎን! እያንዳንዱ የጥበብ ውጤት የቴክኖሎጂ ውጤት የሳይንስ ውጤት የምርምር ውጤት በልኡላችና በጭፍቹ የተገኙና በኛ
በባለተልዕኮቹ አማካኝነት ወደ ተግባር ተለውጠው ለውጤት የበቁና ለምደር ህዝብ እንዲደርሱ የሆኑ ናቸው! ይህ የዕውቀት ቀመር
በፒራሚዳችን እጅግ በተራቀቀ መንገድ በተግባር መተርጎም ከጀመረ ከ 7 ሺ ያህል አመታት ቢሆነውም ውጭ ያለውና ተጠቅልሎ
በልዑላችን ስራ መሆን እንዳለበት በታመነበት በኋላ ቀሩ የምድር ሕዝብ ዘንድ መታወቅና ወደ ተግባር እየተለወጠ ወደ ስልጣኔ ደረጃ
እንዲያደርሰው የተፈለገው ግን ቀስ በቀስ እና በዝግታ ነበር፡፡ እኛም ይሄን የእውቀት ቀመር ለአለም ሕዝብ ስናዳርስ ቀስ በቀስ እና
በዝግታ ነበር፡፡ እናም ከልዑላችንና ከተከታዮቹ ጎን ቆመን የእርሱን ረቂቅ ጥበብ እየተካፈልን ለአለም ህዝብ እያካፈልን እዚህ ደረስን
ሲሏቸው ተሰብሳቢዎቹ በጋራ ተነስተው አዳራሹን በጭብጨባ አደመቁት፡፡
ክብር ለልኡላችን ሲሊ አሜን አሉና ከልኡላቸውን አመስገነው ልቀጥል አሉና መሀል ላይ የነበረውን ግዙፍ ጥራዝ አንሸራተው ወስደው
ግድግዳ ላይ በመለጠፍ ግድግዳውን ሙሉ በሙሉ በሰፊው ስክሪን ለወጡት ከዛም እባካችሁ በየዘመናችሁ ተመራምራችሁ አለምን
መለወጥ የቻላችሁ የረቂቅ ግኝት ባለቤቶች የሖናችሁ በዘር ሀረግ ከኛ ወገን የሆናችሁና ያልሆነችሁ ነገር ግን በልዑላችን ምክንያት በዘር
ሀረግ ከማንም ጋር ሳትበላለጡ በእኩልነት ቤተሰብ መሆን የቻላችሁ የልዑላችን ታማኝ ልጆች የሆናችሁ አብረቅራቂውን ስጋ ለብሳችሁ
ያላችሁ ከልዕላችን ድል በኋላ የምንገናኝና እንደሌሎች ሹማምንት የምትሆኑ ሊቃውንቶች እና ሳይንቲስቶቻችን አንድ አፍታ ጎራ በሉና
ለተሰብሳቢዎች ታይታችሁ የምንለውን ነገር አጠናክራችሁ በዚያውም ወንድማዊ ሰላምታችሁን አቅርቡላቸው ካሉ በኋላ ፈገግ አሉና
ከሰፊው ስክሪን ዳር ላይ ሆነው እጆቻቸውን አጣምረው ቆመው መጠበቅ ጀመሩ ያይታመን ክስተት ነበር! ነገሩ ብታምኑ እመኑ
ባታምኑም ተውት! የሚባል አይነት ነው፡፡ እኒህ የሰይጣን ቁራጭ የሆኑ ጎባጣ አሮጊት የእንጊልዝ ንግሰት ይህን ብለው ጥጋቸውን
እንደያዙ የእንግሊዝ እና የአሜሪካን ዜግነት የነበራቸው የቀድሞ የግኝት ባለቤቶች ጥቁር በጥቁር ለብሰው ጥቁር ቦቲ ጫማ ተጫምተው
ግር ብለው እየተጋፊ በሰፊው ስክሪን ውስጥ መታየት ጀመሩ፡፡ ግፊያው መበተርታቱን የተመለከቱት ንግስቲቱ ጥቂቶች ትበቃላቹ
8
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ወንድሞች እባካችሁ አሉ ሊሰሟቸው አልፈለጉም ግፊያቸው ጠነከረ ትርምሱ በረታ በዚህ ጊዜ ንግስቲቱ ጠንከር አሉና በየተራ
እምጠራችሁ እና ለምናወራው ነገር ማጠናከሪያነት የፈለግናችሁ ብቻ ትመጣላችሁ አሉና ቶማስ ቅደም ቀጥሎ አሌክሳንደር ከዛ
አንስታይን ብለው ወደ ጥጉ ሄደው ቆሙ፡፡
9
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
መልመጃ 2
ሞት፣ ዕውቀት፣ ላም፣ ጀግንነት፣ ክፋት፣ ደብተር ፣መኪና፣ ተራራ ፣ፍሬ፣ ላም፣ አልጋ፣ ግመል፣ አንበሳ፣
ጅብ፣አዋሽ ድሬደዋ፣ጎንደር፣ካሳ፣መንጋ፣ዶሮ፣ሰላም፣ላፕቶፕ፣ራዲዮን፣ሳህን፣ብርጭቆ፣ማር፣ዘይት፣ስኳር
እስራስ፣መሶብ፣ፍራፍሬ፣ብርሀን፣ደብተር
8. ምንባብ ሁለት
አንዳንዴ ሀገር አርብ ላይ ትውላለች
አርብ አዳም እየዳነ ነው፤ ነገር ግን ክርስቶስ እየተገረፈ እና እየተሰቀለ ነው፤ ፀሐይ ጨልማለች ጨረቃ ደም ለብሳለች፤ ምድር
ትንቀጠቀጣለች፤ ሐዋሪያት ሸሽተዋል ፤ መፃጉ በሀሰት መስክሯል፤ ጲላጦስ የእውነት ፍርድ ለመፍረድ ተቸግሯል፡፡
በጥብሪያዶስ ባህር ሲበላ ‹ካልነገስክ› ያለው ሕዝብ ተገልብጦ ‹ካልተሰቀለ› እያለ ነው፡፡ ያቺ ቀን የክርስትና የመጨረሻዋ ቀን ትመስል
ነበር፡፡ የክርስቶስ ሆኖ የተገኘ ሁሉ ይቀጠቀጣል፡፡ ለዚህም ነበር ወጣቱን ማርቆስ ያባረሩት፡፡ ሀና እና ቀያፋ ጉልበት አግኝተል፡፡
የጭካኔያቸውን ልክ ሁሉ እያወረዱት ነው፡፡ ዮሐንስ ያለቅሳል፤ እመቤታችን በሐዘን ቆማለች፡፡ ሁሉም ነገር ያበቃና የተቆረጠ መስሏል፡፡
በዚህ መከከል ግን የሚነሱ ሙታን ነበሩ፤ የሚቀደድ የጥል መጋረጃ ነበር፤ ፈያታዊው ዜይማን ገነት እየገባ ነበር፤ የጲላጦስ ሚስት ስለ
እውነቱ እየመሰከረች ነበር፡፡ ሮማዊው መቶ አለቃ ስለ ክርስቶስ እውነቱን እየተናገረ ነበር፡፡ ግን እነዚህን ጣፋጭ ድምፆች ሌሎች የክፋት
እና የጨለማ ድምፆች ውጦዋቸው ስለነበር በቂ ሰሚ አላገኙም፡፡ በቂ ሰሚ ያገኙት በኋላ ነው፡፡ሀገርም እንዲህ ትሆናለች ፡፡ አርብ ላይ
10
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ስትሆን ፀሐይ የጨለመባት ጨረቃም ደም የለበሰችባት ትመስላለች፡፡ መድሐኒት አልባ ተስፋ የማታገኝ ሁሉም እንደጨለመ የማይነጋ
ህልም እንጂ እውን የሚባል ነገር የሚታይባት አትመስልም፡፡
ክፎዎች ሀይል አግኝተው ቅኖች የተሸነፉ ይመስላሉ፤ ወንጀለኞች ደስታ ተጎናፅፈው ንፁሐን መስቀል ስር ያለቅሳሉ፡፡ ትናንሽ
ጭላንጭሎች ደስታ ተጎናፅፈው ንፁሐን መስቀል ሥር ያለቅሳሉ፡፡ ትናንሽ ጭላንጭሎችን የሚያያቸው ጥቃቅን ብርቱ ድምፆችን
የሚሰማቸው ያጣሉ፡፡ ሁሉም የዋጠውን ጨለማ እንጂ የተሰቀለውን ብርሀን አያያም፡፡
ግን አርብ ያልፋል ፤ ቅዳሜ ይነጋል፤ እርሱም በዝምታ ይመሻል፤ እሁድም ይደርሳል፤ ትንሳኤም ይመጣል፤ አረብም በእሁድ ትተካለች፡፡
ከአርብ ወደ እሁድ ለመሻገር ግን እንደ እመቤታቸን እና ዮሐንስ ያሉ ፅኑአንን ይፈልጋል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ አርብ ላይ ናት ግን በቅዳሜ በኩል
ተሻግራው እሁድ እንደምትደርስ እናምናለን፡፡
መመሪያ አንድ፡- ከላይ በቀረበው ምንባብ መሰረት ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፈደል ምረጡ /የእውቀት ጥያቄዎች/
1. ትናንሽ ጭላንጭሎች ደስታ ተጎናፅፈው ንፁሐን መስቀል ሥር ያለቅሳሉ፡፡ ይሄንን ሀሳብ ሊተካ የሚችለው ሀሳብ የትኛው ነው
ሀ. የተፃፈውን ሁሉ አንብብ በሕሊና መዝገብ ከመመዝገብህ በፊት በህሊና ሚዛና አብጠርጥር
ለ. መስጠት እማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ
ሐ. የእብደት የመጀመሪያው ምልክት እራስን አዋቂ አድርጎ ማሰብ ነው
መ. መሆን ያለበት ሳይሆን መሆን የሌለበት ሆነ
2. እመቤታችን እና ዮሐንስ በምንባቡ ውስጥ ምን አይነት ሰዎች ናቸው
ሀ. የወደዱት የሚወዱ ለ. የጠላቸውን የሚወዱ
ሐ. የሚያፈቅሩትን የሚወዱ መ. ወደ ፍፅምና የተጠጋ ፍቅር ያለቸው
3. ከአርብ ወደ እሁድ ለመሻገር ግን እንደ እመቤታቸን እና ዮሐንስ ያሉ ይፈልጋል፡፡ ሲል ምን ማለቱ ነው
ሀ. ከሚታየው እውነታ ጀርባ ያለውን እውነታ የሚያይ
ለ. ከእውነታው ጀርባ ያለው ውሸትን ቀድሞ የሚያውቅ
ሐ. የሚታየውን እውነታ በተሻለ እውነታ የሚቀይር መ. መልስ የለም
4. በምንባቡ ውስጥ አርብ ምን አይነት ቀን ናት
ሀ. ክፉዎች የበለጠ የሚከፉበት ለ. እውነት የሚገለጥበት ሐ. ድሕነት ያለበት መ. ሁሉም
5. ከአርብ እና እሁድ የተሻለው ቀን የትኛው ነው
ሀ. አርብ ለ. እሁድ ሐ. ከጣት መካከል የሚሻለውን መምረጥ ይከብዳል መ. መ.የለም
6. እንደ ምንባቡ ሀሳብ የጥል መጋረጃ ሲል ምን ማለት ነው
ሀ. ፍቅር የበዛበት ለ. ፀብ የሌለበት ሐ. የኖረ ፀብ መ. ሀ እና ለ
7. ዛሬ ኢትዮጵያ አርብ ላይ ናት ሲል ምን ማለቱ ነው
ሀ. ችግር፣ሀዘን እና ሰቆቃ ብቻ የበዛባት ለ. በችግር እና በመከራ ውስጥ ተስፋ የሚታይበት
ሐ. የማያልፍ የሚመስሉ የሀዘን ጎርፍ ብቻ የሚታይባት መ. ሀ እና ሐ
8. በምንባቡ ውስጥ ቅኔ የሆነው ቀን የትኛው ነው
ሀ. ቅዳሜ ለ. እሁድ ሐ. አርብ መ. ቅዳሜ እና እሁድ
9. እንደ ምንባቡ ሀሳብ ቅዳሜ ምን አይነት ቀን ነው
ሀ. አሸናፊዎች የተሸነፉበት ለ. ፀጥታ የነገሰበት ሐ. የደስታ ጎርፍ የዘነበበት መ. ግርግር የበዛበት
10. ድህነት ያለ የማይመስል ነገር ግን ድህነቶች የሚበዙበት ዕለት የትኛው ነው
ሀ. ቅዳሜ ለ. እሁድ ሐ. አርብ መ. ቅዳሜ እና እሁድ
11
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
መመሪያ ሁለት፡- ለሚከተሉት ሰዋሰዋዊ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ/የዕውቀት ጥያቄዎ
11. ከሚከተሉት መካከል አንዱ ለምስረታ ቃል ምሳሌ አይሆንም
ሀ. ብልግና ለ. ሰውነት ሐ.ጉልበተኛ መ. ወታደሩን
12. ከሚከተሉት የቃል ክፍሎች መካከል ቅፅል ቀድሞት የሚገባው የቃል ክፍል የትኛው ነው
ሀ. መሰተዋድድ ለ. ግስ ሐ. ስም መ. መስተዓምር
13. ለቁጥር፣ለፆታ፣ለሙያ እና ለእምርነት የሚረባው የቃል ክፍል የትኛው ነው
ሀ. ተውሳከ ግስ ለ. ግስ ሐ. ስም መ. መስተዓምር
14. ቅፅሎች ለእምርነት ሲረቡ ተባዕት ፆታ እንዲኖራቸው የሚያደርገው ምዕላድ
ሀ. -ኡ ለ. -ኢት ሐ. ተባዕት ፆታ አይወስዱም መ. -ዋ
15. ምንም አይነት ቅጥያ ሳይጨመርበት ከግሱ እግሮች ውስጥ /ኧ/ን የሚጨምር የግስ አምድ የቱ ነው
ሀ. ተደራጊ አምድ ለ. አድራጊ አምድ ሐ. አስደራጊ አምድ መ. አዳራጊ አምድ
16. አድራጊ አምድ ላይ/ተ-/ የሚል ምዕላድ ሲጨመርበት የሚሆነው አምድ --------------- ነው
ሀ. ተደራጊ አምድ ለ. አድራጊ አምድ ሐ. አስደራጊ አምድ መ. አዳራጊ አምድ
17. ለመደብ፣ለፆታ፣ለቁጥር እና ለጊዜ የሚረባው የቃል ክፍል የትኛው ነው
ሀ. ተውሳከ ግስ ለ. ግስ ሐ. ስም መ. ቅፅል
18. ከጊዜ፣ ከቦታ፣ ከሁኔታ እና ከቁጥር አንፃር የሚጎላመሰው የቃል ክፍል የቱ ነው
ሀ. ተውሳከ ግስ ለ. ግስ ሐ. ስም መ. ቅፅል
19. ከሚከተሉት ድህረ ግንድ ቅጥያ የሆነው የትኛው ነው
ሀ. እንደ ለ. ኣችን ሐ. አስ መ. የ
20. ከሚከተሉት ቁጥር አመልካች ምዕላድ ያልሆነው የትኛው ነው
ሀ. እነ- ለ. -ኣን ሐ. -ኣት መ. -ነት
21. ከሚከተሉት ምዕላዶች መካከል ከቅፅል ጋር ሲገባ የምስረታ ከስም ጋር ሲገባ ደግሞ የእርባታ ምዕላደ የሚሆነው የትኛው ነው
ሀ. -አዊ ለ. -አማ ሐ. -አም መ. -ነት
22. ከሚከተሉት ለስማዊ ሀረግ አጎላማሽ መሆን የሚችለው ሀረግ የትኛው ነው
ሀ. ግሳዊ ሀረግ ለ. ዓ.ነገር ሐ. መስተዋድዳዊ ሀረግ መ. ተ.ግሳዊ ሀረግ
23. ለቅፅላዊ ሀረግ አጎላማሽ መሆን የሚችለው ሀረግ የትኛው ነው
ሀ. ግሳዊ ሀረግ ለ. መስተዋድዳዊ ሀረግ ሐ. ስማዊ ሀረግ መ. ቅፅላዊ ሀረግ
24. አንድ አ.ነገር ከመቋጨታችን በፊት የሚዘረዘሩ ነገሮች መኖራቸውን ለመግለፅ የሚጠቅመው ሥርዓተ ነጥብ የትኛው ነው
ሀ. ነጠብጣብ ለ. ድርብ ሰረዝ ሐ. ሁለት ነጥብ ከሰረዝ መ. ነጠላ ሰረዝ
25. ከሚከተሉት አንዱ ቃላትን አሳጥሮ ለመፃፍ የሚያገለግል ሥርዓተ ነጥብ የትኛው ነው
ሀ. እመጫት ለ. እዝባር ሐ. አግድም ሰረዝ መ. ትምህርተ አንክሮ
መመሪያ ሶስት፡- ለሚከተሉት ሥነፅሑፋዊ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ
26. ከግሪክ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትዕይንቱን ብቻ ሳይሆን ትዕይንቱ የሚከወንበትን ሕንፃ ጭምር የሚወክለው ቃል የትኛው ነው
ሀ. ድራማ ለ. ተውኔት ሐ. ቲያትር መ. ፊልም
27. ከሚከተሉት የሥነፅሁፍ ዘውጎች መካከል ገፀባህሪያቱ ምናባዊ ያልሆኑት በየትኛው ላይ ነው
ሀ. በመፅሐፍ ላይ ለ. በፊልም ላይ ሐ. በተውኔት ላይ መ. ሀ እና ለ
28. በሁካታ እና በሳቅ የተሞላ ሆኖ ብዙም ጥያቄ የማይነሳበት ዋናው የተነሳው ሀሳብ ያስቃል ወይስ አያስቅም የሚለው ብቻ
የሚታይበት የተውኔት አይነት የትኛው ነው
ሀ. ትራጀዲ ለ. ኮሜዲ ሐ. ድንቃይ መ. ቧልታይ
29. ከጠቀሜታ ቅርርቦሽ አንፃር አንዱን በሌላ የምንወክልበት የዘይቤ አይነት -------------- ነው
12
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
9.የስም እርባታ
ስሞች፡-
ለቁጥር
ለፆታ
ለሙያ/ተሳቢ/
ለእምርነት ይረባል፡
የአማርኛ ቃላቶች /-ኦች/ የሚል አብዢ ምዕላዶችን ሲወስዱ የግዕዝ ቃላቶች ደግሞ /-ኣን እና ኣት/ ይወስዳሉ፡፡
ምሳሌ ቃላት አብዢ ምዕላድ ቃላቶች
አያት -ኦች አያቶች
በሬ -ዎች በሬዎች
ምዕመን -ኣን ምዕመናን
ገዳም -ኣት ገዳማት
ለ. ስሞች ለፆታ ሲረቡ
ምሳሌ
ተባዕት ምዕላድ አንስታይን
1. ልጅ -ኢት ልጅት
2. ድመት -ኡኣ ድመቷ
3. በሬ ላም
4. ድንጉላ ባዝራ
5. ወይፈን ጊደር
ከ ምሳሌ 3 እስከ 5 ያሉ ቃላቶች ምንም አይነት ምዕላዶች ሳይጨመርባቸው ፆታን ያመለክታሉ፡፡
ሐ. ስሞች ለተሳቢ ሲረቡ
ተሳቢ አመልካች ምዕላድ /-ን/ ናት
ምሳሌ 1.
ስም ተሳቢ አመልካች ምዕላድ ስሙ ተሳቢ ከወሰደ በኋላ
1. ብንያም -ን ብንያምን
ምሳሌ 2
አበበ ብንያምን መታው፡- የተሰመረበት ቃል ስም ሆኖ ለተሳቢ ስለረባ ድርጊት ተቀባይ ሆኖ ይታያል፡፡
መ. ስሞች ለዕምርነት ሲረቡ
አንድን ስምየታወቀ እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው እምር አድራጊ ምዕላድ/-ኡ/ ናት
13
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ስም ምእላድ እምር
ምሳሌ በግ -ኡ በጉ
2. ቅፅል
ከስም በፊት ወይም በኋላ በመግባት ስምን ይገልፃል
10.የቅፅል አይነቶች
ተ.ቁ የባህሪ የመጠን ቅርፅ ቀለም ወገን
3 ደግ ብዙ ወልጋዳ ነጭ ጎንደሬ
4 ክፉ አያሌ ጠማማ ቢጫ
የቅፅል እርባታ
ቅፅሎች ለቁጥር ለሙያ ለእምርነት እና ለሙያ ይረባሉ
ቅፅሎች ለቁጥር ሲረቡ
ቅፅሎች ለቁጥር በሁለት አይነት መንገድ ይረባሉ
1. /-ኦች/ በመውሰድ የሚረቡ
ምሳሌ ነጠላ ምዕላድ ብዙ
1. ጅል -ኦች ጅሎች
2. ጠባብ -ኦች ጠባቦች
3. ጎበዝ -ኦች ጎበዞች
2. ተናባቢ እግር በመድገም የሚረቡ
ምሳሌ ነጠላ ምዕላድ ብዙ
1. ረዥም -ኣ ረዣዥም
2. ሰፊ -ኣ ሰፋፊ
3. ቀይ -ኣ ቀያይ
ቅፅሎች ለፆታ ሲረቡ
ቅፅሎች -ኢት እና -ኡኣ የሚሉ ምዕላዶችን በመውሰድ እራሳቸውን ለፆታ ያረባሉ፡፡
ምሳሌ ተባዕታይ ምዕላድ አንስታይ
1. ትልቅ -ኢት ትልቂት
2. ትንሽ -ኡኣ ትንሷ
3. ደግ -ኢት ደጊት
14
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
11.ግስ
በዓ.ነገር መጨረሻ ላይ የሚገኝ እና ባለቤት አመልካች ምዕላድ ያስከትላል፡፡
ምሳሌ 1. እሱ አንበሳ ገደል -ኧ
2. አንቺ በግ ገዛ -ሽ
3. እሷ ምሳዋን በላ -ች
4. እኔ ወተት ጠጣ -ሁ
5. አንተ ዛሬ ትመጣለ -ህ
የግስ አምድ
ሀ. አድራጊ አምድ፡-
ምንም አይነት ቅጥያ ሳይጨመርበት ከግሱ እግሮች ውስጥ/ኧ/ን በመጨመር ነው፡፡ አምዶቹም የተፈፀመ ድርጊትን የሚጠቀሙ
በመሆናቸው ሀላፊ አምዶች ናቸው፡፡
ምሳሌ ስር አድራጊ አምድ
ነገር ንኧግኧርኧ
ለወጠ ልኧውኧጥኧ
ለ. ተደራጊ አምድ፡-
አድራጊ አምድ ላይ /ተ-/ የሚል ምዕላድ በመጨመር የሚፈጠር ነው፡፡
ምሳሌ አድራጊ ተደራጊ
1. ሰበረ ተ-ሰበረ
2. ገደለ ተ-ገደለ
3. ወደደ ተ- ወደደ
ሐ. አስደራጊ አምድ፡-
በአድራጊ አምድ ላይ /አስ-/ የሚል ምዕላድ በመጨመር የሚፈጠር አምድ ነው፡፡
ምሳሌ አድራጊ አምድ አስደራጊ አምድ
1. ገደለ አስ-ገደለ
2. ለመነ አስ-ለመነ
3. ተከለ አስ-ተከለ
መ.አዳራጊ አምድ፡-
አድራጊ አምድን ወደ ማገዝ፣መርዳት ተግባር መቀየር ማለት ነው፡፡
ምሳሌ አምድ አዳራጊ አምድ
ፈለገ አፋለገ
ለመደ አላመደ
ለመነ አላመነ
የግስ እርባታ
ግሶች
ለመደብ
ለፆታ
ለቁጥር
ለጊዜ ይረባሉ፡፡
ቁጥር ግስ ጊዜ
መደብ ነጠላ ብዙ የአሁን ሀላፊ ትንቢት
1ኛ ፆታ እኔ በላ እየ-በላሁ በላሁ እበላለሁ
2ኛ ተባ አንተ በላ እየ-በላ-ህ በላ-ህ ት-በላለ-ህ
አን እንቺ በላ እየ-በላ-ሽ በላ-ሽ ት-በላለ-ሽ
3ኛ ተባ እሱ በላ እየ-በላ- በላ ይ-በላል
አን እሷ በላ እየ-በላ-ች በላ-ሽ ት-በላለ-ች
እኛ በላ እየ-በላ-ን በላ-ን እን-በላለ-ን
እናንተ በላ እየ-በላ-ችው በል-ኣችው ት-በላል-ኣቸው
እነሱ በላ እየ - በል-ኡ በል-ኣችው ይ-በል-ኣሉ
መልመጃ ሶስት
15
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
መመሪያ ሁለት፡- ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ሀሰት በማለት መልሱ
1. በዓ.ነገር ውስጥ ቅፆሎች የግስ ገላጭ በመሆን ያገለግላሉ-----------------
2. የተፀውኦ ስም -ኦች የሚለውን ምዕላድ ይወስዳል-------------------
3. አስደራጊ አምድ የሚመሰረተው ተደራጊ አምድ ላይ /-አስ/ የሚል ምዕላድን በመጨመር ነው፡፡-------------------
4. አስቴር ሽንኩርት አስተከለች፡፡ ይሄ ዓ.ነገር በተደራጊ አምድ የተመሰረተ ነው------------------
5. ስም በዓ.ነገር ውሰጥ ባለቤት እና ተሳቢ በመሆን ያገለግላል--------------
6. /-ን/ የሚለው ምዕላድ ተሳቢ አመልካች ምዕላድ ነው፡፡-------------------
7. የወል ስም እና የጥቅል ስም አንድ አይነቶች ናቸው፡፡--------------------
8. የስም ገላጭ ሁሉ ቅፅል መሆን ይችላሉ፡፡------------------------
መመሪያ ሶስት፡- የሚከተሉት ጥያቄዎች ከ ሀ ክፍል ወደ ለ ክፍል አዛምዱ
ሀ ለ
---------1. ጊደር ሀ. ስም
---------2. ወይፈን ለ. ቅፅል
---------3. ጎንደሬ ሐ. ግስ
---------4. ለመነ
---------5. ፎቅ
---------6. ቀይ
---------7. መምህር
---------8. አለ
---------9. ክፉ
---------10. ወልጋዳ
---------11. አልጋ
---------13. ነው
---------14. በግ
12. ተውሳከ ግስ
ተውሳከ ማለት በግዕዝ ጭማሪ ማለት ሲሆን ተውሳከ ግስ በግስ ላይ የሚጨመር ማለት ነው፡፡
ተውሳከ ግስ ከግሱ በፊት በመግባት ግሱን የሚገልፅ ነው፡፡
የተውሳከ ግስ ሌላይኛው መጠሪያ የግስ ገላጭ ነው
በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ተውሳከ ግስ ብዛታቸወ እጅግ በጣም ትንሽ ነው
በተፈጥሮ ተውሳከ ግስ ሆኑ ቃላት ጅልኛ ፣ክፉኛ፣ምንኛ፣ቶሎ ፣ገና እና ግመኛ ናቸው፡፡
ተውሳከ ግሶችን ከጊዜ፣ከቦታ፣ከሁኔታ እና ከቁጥር አንፃር ያጎላምሳለ
ምስሌ
16
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ተ.ቁ ተ.ግስ
4 ዘውትር መርካቶ
5 ቶሎ ግርጌ
ምሳሌ 1. ካሳ ዛሬ ይመጣል፡፡
2. ሰለሞን እባክፍ ከራስጌዬ አትቁም፡፡
3. ካሳ በድንገት ወደ ጎጃም ሄደ፡፡
4.ሰለሞን አራተኛ ክፍልን ስንቴ ወደቀ፡፡
5. መስተዋድድ፡-
የሚያዋድድ ወይም የሚያስማማ ማለት ሲሆን ቃላትን ከቃላት የሚያስማማ ማለት ነው፡፡
ምሰሌ፡- እንደ፣ አስ፣ ስለ፣ ወደ፣ በ፣ ከ፣ለ ፣እስከ ፣ወደ ፣ውስጥ፣ባሻገር ወዘ.ተ
13. መስተዓምር፡-
መጣኝ
ኢመጣኝ
አገናዛቢ እና
ጠቋሚ መስተዓምር ተብለው የሚከፈሉ ሲሆን ስምን እና ቅፅሎችን ያጎላምሳሉ
ምሳሌ
1 አንድ ብዙ የ ካሳ እነዚህ
3 አስር መዓት ያ
4 ስምንት ጥቂት ይህ
5 መቶ ትንሽ
6 ሁለት መቶ ነፍ
7 አንድ ሺህ
14. ምዕላድ
ሊሸነሸን የማይችል የቋንቋ የመጨረሻ ቅንጣት አካል ነው
ምዕላድ ትርጉም ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል፡፡
ምዕላድ በሁለት ይከፈላል እነሱም፡- ነፃ ምዕላደ እና ጥገኛ ምዕላድ ይባላሉ፡፡
17
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ጥገኛ ምዕላ፡- ትርጉም የማይሰጥ ሲሆን ከነፃ ምዕላድ ጋር ሲጨመር ትርጉም ይሰጣል ወይም የቃል ክፍልን ከአንዱ ወደ ሌላው
ይቀይራል
ጥገኛ ምዕላድ በሶስት ይከፈላሉ እነሱም፡- ቅድመ ግንድ፣ውስጠ ግንድ እና ድህረ ግንድ ተብለው ይጠራሉ፡፡
ምሳሌ
1. እንደአስተማሪዎቻችን
እንደ- ፣ አስ- ቅድመ ግንድ ቅጥያ ሲሆኑ
ተማረ፡- ዋና ቃል/ስርወ/ ቃል ነው፡፡
-ኢ፣-ዎች፣-ኣችን የሚሉት ደግሞ ድህረ ግንድ ቅጥያዎች ናቸው፡፡
2. ቅጠላ ቅጠል
ቅጠል አንድ ስርወ ቃል ሲሆን ሌላይኛው ቅጠል ደግሞ ሁለተኛው ዋና ቃል ነው፡፡
እነዚህን ሁለት ዋና ቃሎች ያገናቸው ምዕላድ /-ኣ/ ናት ይህቺ ምዕላድ ደግሞ ውስጠ ግንድ ቅጥያ ትባላለች፡፡
ቅድመ ግንድ፣ውስጠ ግንድ እና ድህረ ግንድ ቅጥያዎች በአንድ ላይ በሁለት ይከፈላሉ እነሱም፡- የእርባታ እና የምስረታ ምዕላድ
ይባላሉ፡፡
1.የእርባታ ምዕላድ
አንድን የቃል ክፍል ወደ ሌላ የቃል ክፍል አይቀይሩም ነገር ግን አንድን ቃል ቅርጹን ይቀይሩታል፡፡
የእርባታ ምዕላድ የሚባሉት እራሳቸውን ለቁጥር ለመደብ ለፆታ እና ለእምርነት እንዲሁም ለባለንብረትነት ያረባሉ፡፡
የእርባታ ምዕላድ እራሳቸውን ለቁጥር ሲያረቡ
የእርባታ ምዕላዶች እራሳውን ከቃል በፊት እና በኋላ በመግባት ለቁጥር እራሳቸውን ያረባሉ፡፡
ከቃል በፊት በመግባት ለቁጥር እሚረቡ ምዕላዶች
15 የምስረታ ምዕላድ
አንድን የቃል ክፍል ወደ ሌላ የቃል ክፍል ይቀይራል፡፡
1. -ኣም ከስም ወደ ቅፅል ይቀይራል
18
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
19
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
16.ምንባብ ሶስት
በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም በልፋቴ ከካመቸሁት
ሀብት ያገኘውት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው አሁን በሕይወቴ የመጨረሻው ሰአት አከባቢ አልጋ ላይ ሆኔ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደኋላ ሳስበው
እኮራበት የነበረው ሀብትና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ
አንድ ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀትረው ትችላለህ እየተሰቃየህበት ያለውን በሽታ እንዲሸከምልህ ግን
ልትቀጥረው አትችልም
ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ዳግምም ሊገኙም ይችላሉ አንድ ጊዜ ካመለጠህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ ------- እሱም
ሕይወትህ ነው
አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚያደርግበት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው መፅሀፍ ትዝ ቢለው የመፅሀፉ ርዕስ ‹‹ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር››
የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም
በየትኛውም የሕይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበት ቅፅበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም
ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋር እና ለጓደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው ራስህን ተንከባከብ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ እያደግን ስንሄድና
የህይወት ትርጉም ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት---- ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል
በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ----- በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም
የአንድ ሚሊዮን ብር መኪና ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና የመንገዱን ርዝመት አይቀይረውም .አቅጣጫውም ያው አንድ ነው የምንደርሰውም ያው
እዚያው ቦታ ነው
ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም
ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ ከጓደኛችህ ከዘመዶችህ ጋር
በሚኖርህ ውብ ጊዜአት ብቻ ነው ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ በምትጫወተው ጨዋታ በምትዘምረው መዝሙር በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን
ታገኛለህ 5 ሊካዱ የማይችሉ የሕይወት እውነታዎች አሉ ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ
አስተምራቸው ሲያድጉየነገሮች ዋጋ ሳሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል ምግብህን እንደ መድሀኒት ውሰድ ካልሆነመድሀኒት እንደምግብ ትወስዳለህ የሚወድህ
ሰው በቀላሉ አይለይህም ከአንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችለበት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል ሰው ሆኖ በመፈጠርና
ሰው በመሆን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው ስትወለድ ውድ ነበርክ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ በመካከል ያለውን
ማስተካከል ያንተ ፈንታ ነው በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ ሩቅ ለመድረስ ከፈለክ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ
በዓለም ላይ ያሉስድስት ፈዋሽ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው
የፀሀይ ብርሀን፣ እረፍት፣ስፖርት፣ ጥሩ ምግብ፣በራስ መተማመን እና ጓደኛ እነዚህን አጥብቀህ ያዝ ደስተኛ ህይወትን አጣጥም
ምንጭ፡- ከማህበራዊ ድረ ገፅ የተወሰደ የያዘውን ፊደል ምረጥ
መመሪያ አምስት፡- ከላይ በቀረበው ምንባብ መሰረት ለሚከተሉትን ጥያቄዎች ትከክለኛ መልስ
29. የምንባቡ ርዕስ ሊሆን የሚችለው
ሀ. ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ለ. የነብስ ጥሪ ሐ. የመኖር ሚስጠር መ. መ.የለም
30. በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ----- በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም የሚለውን ሀሳብ ሊተካ የሚችለው የቱ ነው
ሀ. ወርቅ ወርቅነቱን የሚታወቀው በእሳት ሲፈተን ነው ለ. ሰው ሰውነቱን ካለረከሰው ሁሌም ውድ ነው
ሐ. ውድም ነገር ያለቦታው ርካሽ ነው መ. መ.የለም
31. የአንድ ሚሊዮን ብር መኪና ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና የመንገዱን ርዝመት አይቀይረውም ሲል ምን ማለቱ ነው
ሀ. ምንም ሀብታም ብንሆን እንጀራ በወጥ እንጂ በወርቅ አንበላም
20
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
44. በአ.ነግር ውስጥ ባለቤትም ተሳቢም መሆን የሚችለው የቃል ክፍል የትኛው ነው
ሀ. ተ.ግስ ለ. ቅፅል ሐ. ግስ መ. ስም
21
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
47. በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ከሁሉም አነስተኛ ቃላት ያለው የቃል ክፍል ማነው
ሀ. መስተዋድድ ለ. ተ.ግስ ሐ. ቅፅል መ. ግስ
ሀረግ
17. አ.ነገር
ከስማዊ እና ግሳዊ ሀረግ ጋር ተጣምሮ ይፈጠራል
ሙሉ ሀሳብን/ መልዕክትን/ ያስተላልፋል/
ቢያንስ በውስጡ ባለቤት እና ግስ መያዝ አለበት
22
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
የአ.ነገር አይነት
2. መጠይቃዊ ዓ.ነገር
3. ትዕዛዛዊ ዓ.ነገር
3. መጠይቃዊ ዓ.ነገር፡- ጥያቄያዊ ሀሳብ ያላቸው ሀሳቦችን የሚያነሳ ዓ.ነገር ነው እነዲሁም በዓ.ነገሩ መጨረሻ ላይ ጥያቄ
ምልክትን ይወስዳል
ምሳሌ ማን ጫማ ገዛልህ ?
4. ትዕዛዛዊ ዓ.ነገር ፡- የትዕዛዝ ስሜት ያለው ሲሆን ቃል አጋኖ ስርዓተ ነጥብን ይወስዳል፡፡
በምሳሌ 1 ላይ ገዛ ብቻ የሚል ግስ ሲሆን ያለው በምሳሌ 2 ላይ ግን ሄዳ የሚል እና ጋገረች የሚል ግሶች አሉ ስለዚህ ምሳሌ
1 ተራ ዓ.ነገር ሲሆን ምሳሌ 2 ግን ውስብስብ ዓ.ነገር ነው፡፡
23
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
24
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
25
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ተመሳሳይ ተቃራኒ
1 ሬሳ በድን ደካማ
ተ.ቁ ቃላት ተመሳሳይ ተቃራኒ
2 ቄጤማ የሳር አይነት ልፍስፍስ
1 ሰርክ ዘውትር አልፎ አልፎ
3 ውሻ የእንስሳ ስም ልክስክስ
2 ተሰድረው ተስተካክለው ተመሰቃቅለው
4 እንግሊዝ የሀገር ስም ብልጥ
53 ሀኬት
ወስፌ ስንፍና
መስፊያ ጉብዝና
ቀጭን
64 በላ
ባህር ተመገበ
የተኛ ውሃ ጠጣሰፊ
7 እርግብ የእንስሳ ስም የዋህ
8 አንበሳ የእንስሳ ስም ጀግና ደፋር
9 እፉኝት የእባብ ዘር መርዘኛ እማራዊ እና ፍካራዊ ፍቺ
ምሳሌ
26
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
አውዳዊ ፍቺ
4. ከሰው ሰው የቃላት ፍቺ የተለያየ ነው፡፡ በአራቱ ምሳሌዎች ውስጥ ያሉ ቃላት ፋሲካ እና ፍቺ የሚሉት ቃላት
እንደገቡበት አረፍተ ነገር የተለያየ ፍቺ ስለሰጡ የተገኘው ፍቺ አውዳዊ ፍቺ ይባላል፡፡
አቻ ፍቺ
ተ.ቁ ቃላት አቻ ፍቺ
1 ሀሌታ ምስጋና
2 ህብር ስም
3 ህዳግ ጠርዝ
4 ለሆሳስ ቀስታ
5 ምንዳ ደሞዝ
6 ሲሳይ በረከት
7 ሲራክ ብልህ
8 በተሀ ለጋ ጠጅ
9 አንድምታ ትርጓሜ
10 ዘማዊ ሴሰኛ
11 ጃንደረባ ስልብ
12 ግልድም ሽርጥ
13 ጦማር ደብዳቤ
14 ፍስሀ ደስታ
27
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
15 ፍላፃ ቀስት
16 ፍኖት መንገድ
ላልቶ እና ጠብቆ
አንድ ቃል ጠብቆ እና ላልቶ ሲነበብ የሚሰጠው ፍቺን ይመለከታል፡፡
ምሳሌ
3 መላ ዘዴ በሙሉ/ሁሉም
9 ጥሬ ያልበሰለ ለፍቼ
10 ገላ ሰውነቴ ሰው ገላ
20.ሥነፅሁፍ
በቃልም ሆነ በፅሁፍ መልክ የሚቀርብ ሀሳብ ሲሆን ይሄ ሀሳብ የአንድ ማህበረሰብ ባህል ፣ወግ ፣ እምነት ፣ አስተሳሰብ
፣ፍቅር በደራሲ አማካኝነት ለተደራሲ የሚቀርበብት መንገድ ነው
ሥነ ፅሁፍ በሁለት ይከፈላል
1. ፅሁፋዊ ስነ ፅሁፍ
2. ቃላዊ ስነ ፅሁፍ
1. ፅሁፋዊ ስነ ፅሁፍ
ፅሁፋዊ ስነ ፅሁፍ ማለት የተፃፉ እና በብዕር ተከትበው በመፅሀፍ መልክ ወይም በኤልክትሮኒክስ መሳሪያዎች አማካኝነት ለተደራሲ
የሚቀርቡ ምናባዊ ፈጠራዎች አልያም እውነታዊ ክስተቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ፅሁፋዊ ስነ ፅሁፎች በሁለት መልኩ ሊቀርቡ ይችላል አንድም በግጥማዊ መልክ አንድም በዝርው መልክ
28
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
1. ልቦለድ
2. ግጥሞች
የልቦለድ አላባውያን
1. ታሪክ፡- በልቡለዱ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገውን አጠቃላ ነገር የሚይዝ ነው፡፡
2. ገፀባህሪያት፡- በልቦለዱ ውስጥ የሚተላለፈውን ሀሳብ ወክለውየሚንቀሳቀሱ የደራሲው ምናባዊ ፍጡራን ናቸው
3. ሴራ ፡- በገፀባህሪያት መካከል የሚፈጠረው ግጭት ከፍ እያለ ሲሄድ እና አለመግባባታቸው ሲከር የሚፈጠር ነገር ነው፡፡
የሴራ አይነት
4. ጭብጥ፡- በአንድ ልቦለድ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገው ፍሬ ሀሳብ ወይንም መልዕኩ ምንድን ነው የሚለውን የሚመልስ ነገር
ነው
5. ግጭት፡- በገፀባህሪያት መካከል የሚፈጠር አለመግባባት ነው፡፡
6. መቼት፡- ታሪኩ መቼ እና የት ተፈጠረ የሚለውን ይመልሳል፡፡
7. አንፃር፡- ማለት ታሪኩ እንዴት ይቅረብ የሚለውን ሀሳብ የሚተርክብት መንገድ ሲሆን ሶስት አይነት አንፃር አለ፡፡
ሀ. ሁሉን አቀፍ፡- በሶስተኛ መደብ የሚተረክ ሲሆን ተራኪው ሁሉንም ነገር በሚገባ ያውቃል ከተራኪው የሚደበቅ ሚስጥር
እሚባል ነገር የለም ስለዚህ የእያንዳንዱን ገፀባህሪያት ገበና አውጥቶ ለተደራሲያን ያቀርባል ወደፊት ምን ሊፈጠር ይችላል
የሚለውን ሀሳብ ሁሉ መገመት ይችላል፡፡
ሁሉን አወቅ አንፃር ድክመቱ ተደራሲያን ግምት እንዳይሰጡ ያደርጋል፡፡
ለ. ውሱን ሁሉን አወቅ አንፃር፡- የሚቀርበው በ 3 ኛ መደብ ሆኖ ተራኪው ሁሉንም የማወቅ እድል የለውም እውቀቱ
በአንፃራዊነት የተገደበ ነው፡፡ እንዲሁም በግል ስለሚፈጠር ነገር የመገመት ዕድል የለውም ትረካዎቹም የሚቀርቡት ከዋናው
ገፀባህሪ አንፃር ብቻ ሲሆን ንዑስ ገፀባህሪያትን ለማወቅ አዳጋች ይሆናል
ይሄ አንፃር ቀለል ያለ እና የተሻለ ነው በሚል ብዙ ደራሲን ይመርጡታል
ሐ. አንደኛ መደብ አንፃር
ተራኪው እኔ ወይም እኛ እያለ በአንደኛ መደብ ይተርካል፡፡
እኔ ወይም እኛ እያለ የሚተርከው ተራኪ ዋና ወይም ንዑስ ገፀባህሪ ሊሆን ይችላል፡፡
አጭር እና ረጅም ልቦለድ
አጭር ልቦለድ
በውሱን ቦታና ጊዜ ይወሰናል
የገፀባህሪያት ቁጥር ጥቂት ነው
ቅልብጭ ያለ እና ተደራሲያን አንዴ ሊያነቡት የሚችሉ ታሪክ አለው፡፡
ደራሲው ሶስቱንም አንፃር መርጦ መጠቀም ይችላል
ሴራው ተዓማኒ ፈጣን እና ወዲያውኑ የሚታይ ጥድፍ ጥድፍ ባይ ነው፡፡
ውሱን ቁጥብና በውጤት ላይ ያነጣጠረ ቋንቋና ገለፃ ይጠቀማል
አንድ ነጠላ ብቻ ጭብጥ አለው፡፡
ረጅም ልቦለድ
ሰፊ ቦታና ጊዜ ያካልላል
የገፀባህሪያት ቁጥር በርካታ ነው
ከልደት እስከሞት ካሻው ደግሞ ከልደት እስከ ሞት ያለ ታሪክ አለው፡፡
ደራሲው ሶስቱንም አንፃር መርጦ መጠቀም ይችላል
29
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
21.ግጥም
ዜማ አለው አጭር እና እምቅ ነው ቃላት ላይ ቁጥብነት አለው
በትንኝ ቃላት ብዙ መልዕክት ማስተላለፍ ይቻላል፡፡
የግጥም ባህሪያት
ተጨባጭነት
ቁጥብነት
ሙዚቃዊነት
ምናባዊነት
ተጨባጭነት፡- ያለ ምክንያት እማይገጠም ሲሆን ረቂቅ የሆነ ነገርን እንድናውቃቸው እና የበለጠ ተጨባጭ እንዲሆኑ የማድረግ
አቅም አለው፡፡
ቁጥብነት፡- በጥቂት ቃላት ብዙ ሀሳብ መግለፅ ይችላል፡፡
ሙዚቃዊነት፡- ግጥም ሲነበብ የራሱ የሆነ ዜማ አለው፡፡
ምናባዊነት፡- ግጥም ሲገጠምም ሆነ ሲነበብ በተደራሲያን አእምሮ ላይ ምስል የመከሰት አቅም አለው፡፡
የግጥም ሙያዊ ቃላት
1. ሀረግ፡- የአንድ ግጥም ግማሽ ስንኝ አካል ነው፡፡ በአንድ ትንፋሽ የሚነበብ ነው፡፡
ሀረግ በሁለት ይከፈላል እነሱም፡- መነሻ እና መድረሻ ሀረግ ይባላሉ
ምሳሌ፡- ወይ አዲስ አበባ/ ወይ አራዳ ሆይ፣
ሀገርም እንሰው/ ይናፍቃል ወይ፡፡
ከላይ የቀረበው ግጥም አራት ሀረጋት አሉት፡፡
2. ስንኝ፡- የግጥም አንድ መስመር ተሳክቶ ሲያልቅ ነው፡፡
ምሳሌ፡- ትመር እንደሆነ ምረር እንደ ቅል፣
አልመርም ብሎ ነው ዱባ ሚቀቀል፡፡
ከላይ የቀረበው ግጥም ሁለት ስንኞች አሉት፡፡
3. ቤት፡- በግጥም ስንኞች መጨረሻ ላይ የሚገኝ ሆሄ ነው
ምሳሌ፡- ማሽላና ስንዴ/ባንድ አድርገን ስንቆላ፣
እያረረ ሳቀ የባህር ማሽላ፡፡
ከላይ የቀረበው ግጥም የመጨረሻው ፊደላት ቤት ይባለሉ
4. ቤት መምቻ፡- የመጀመሪያው ስንኝ የመጨረሻ ቃል ነው፡፡
5. ቤት ደፋ፡- የግጥሙ የመጨረሻው ስንኝ ተሳክቶ ሲያልቅ ነው፡፡
ምሳሌ፡- ምንሊክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ
30
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ቤት መምቻ፡- ጋሻ
ቤት ደፋ፡- አበሻ
6. አርኬ፡- በአንድ አይነት ቤት ወይም ድምፅ የተደረደሩ የስንኞች ስብስብ ነው፡፡
በግጥም ውስጥ ትልቁ ክፍል ነው
በአራት ነጥብ ይጠናቀቃል
7. ምጣኔ ፡- በግጥም ውስጥ የቀለማትን መጠን የምንለካበት ስልት ነው፡፡
ግጥም ምጣኔ ከሌለው ምቱ ይዛባል፡፡
ምት ከሌለው ደግሞ ዜማ አይኖረውም
8. ቀለም፡- በግጥም ውስጥ ጠብቀው የሚነበቡ ሆሄያት ቀለም ይባላል
ሳድስ ሆሄያት በቃል መጀመሪያ ከመጣ ቀለም ሆኖ ይቆጠራል፡፡
ሁለት ሳድሶች ተከታትለው ከመጡ እንደ አንድ ቀለም ይቆጠራል፡፡
ምሳሌ፡- ምነው ተቀየረ/የልጆች መንፈሱ
የጨዋታ ሱስ/የቡረቃ ምሱ
22.የግጥም አይነት
1. የወል ቤት፡- በሁለት ስንኘ በአራት ሀረጋት የተዋቀረ ሲሆን እያንዳንዱ ሀረጋት እኩል ሰድስት ስድስት ቀለማት አሉት፡፡
23.ቲያተር
ከግሪክ ቋንቋ የተገኘ ቃል ሲሆን ቲያትር የሚለው ቃል ትዕይንቱን ብቻ የሚወክል ቃል ሳይሆን ትዕይንቱ የሚከናወንበትን
ሕንፃ የሚወክል ቃል ነው፡፡
ድራማ
ድራማ የሚለው ቃል ከግሪክ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን በጥንታዊ ትርጉሙ ድርጊትና ተግባር የሚሉ ፅንሰ ሀሳቦችን ተሸክሟል፡፡
ተውኔት
ተውኔት የሚለው ስያሜ የተገኘው ተዋነየ ከሚለው ከእኛው የግዕዝ ቋንቋ ሲሆን ትዕይንታዊ የሆኑ እንቅስቃሴዎችንና
መዝናኛዎች ያመለክታል፡
ተውኔት የሚለው ስያሜ በመድረክ ላይ ለሚቀርበው ትርዒት ድራማን ወይንም ቴአትርን ወክሎ ግልጋሎት ይችላል፡፡
ለተደራሲያን በመድረክ ላይ የሚቀርብ ነው፡፡
31
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
24. ዘይቤ
በዕለት ተዕለት ግንኙነታችን ውሰጥ የምንጠቀማቸው ሲሆን ዘይቤዎች ለንግግሮቻችን ለዛ ለመስጠት ንግግሮቻችንን ውበት
ለመስጠት እንጠቀማቸዋለን፡፡
በንግግራቸውን ውስጥ ሆን ብሎ ማፈንገጥ ነው፡፡
የዘይቤ አይነቶች
1. ተለዋዋጭ ዘይቤ፡- የአንድን ነገር ባህሪ ለሌላ ነገር ሙሉ በሙሉ መስጠት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ልጅቷ ተርብ ነች፡፡ ልጁ አንበሳ ነው፡፡
2. አነፃፃሪ ዘይቤ፡- አንድን ነገር ከሌላ ነገር የምናነፃፅርበት መንገድ ሲሆን እንደ እና ይመስላል ያክላል የሚሉ ቃላቶችን ወስዶ
ያነፃፅራል፡፡
ምሳሌ ልጁ እንደ አንበሳ ይጮሃል ልጅቷ በሬ ታክላለች
3. ሰወኛ ዘይቤ፡- ሰው ያልሆኑ ነገሮች የሰውን ስሜት ተላብሰው ንግግር የሚያደርጉበት መንገድ ነው፡፡
ምሳሌ 1. መሬት እልል አለች
2. እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህይ
5. እንቶኔ ዘይቤ፡- አጠገብ የሌለን ነገር አጠገብ እንዳለ በማሰብ እና እንደሚሰማን በማሰብ ማወያየት ነው፡፡
6. ግነት ዘይቤ፡- ጥቂት እውነት ኖሮት አብዛኛው ነገር ውሸት የሆነ ነገር ነው
32
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
መልመጃ
መመሪያ 1፡- ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክከለኛ መልስ ስጡ
1. የተውኔት አይነቶችን ግለፁ
ሀ.------------------------------ ለ.-----------------------
ሐ.---------------------------- መ.------------------------
2. የግጥም አይነቶችን ግለፁ
ሀ.------------------------------ ለ.-----------------------
ሐ.---------------------------- መ.------------------------
3. ልቦለዶች መሰረታዊ ቴክኒኮች ግለፁ
ሀ.------------------------------ ለ.-----------------------
4. የልቦለድ አላባውያንን ግለፁ
ሀ.------------------------------ ለ.-----------------------
ሐ.---------------------------- መ.------------------------
ሠ.--------------------------- ረ.-------------------------
ሰ.----------------------------
5. የልቦለድ አንፃርን ጥቀሱ
ሀ.------------------------------ ለ.-----------------------
ሐ.----------------------------
መመሪያ 2. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ
1. ---------------በልቡለዱ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገውን አጠቃላ ነገር የሚይዝ ነው፡፡
2. ----------------በልቦለዱ ውስጥ የሚተላለፈውን ሀሳብ ወክለውየሚንቀሳቀሱ የደራሲው ምናባዊ ፍጡራን ናቸው
3. ---------------- በገፀባህሪያት መካከል የሚፈጠረው ግጭት ከፍ እያለ ሲሄድ እና አለመግባባታቸው ሲከር የሚፈጠር ነገር ነው፡፡
4. -----------------በአንድ ልቦለድ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገው ፍሬ ሀሳብ ወይንም መልዕኩ ምንድን ነው የሚለውን የሚመልስ
ነገር ነው
5. --------------- በገፀባህሪያት መካከል የሚፈጠር አለመግባባት ነው፡፡
6. ---------------ታሪኩ መቼ እና የት ተፈጠረ የሚለውን ይመልሳል፡፡
7. ------------------ ሀዘን ፣ ፍርሀት ፣ጭንቀት እና ስቃይ የተጋነነበት የተውኔት አይነት ነው፡፡
8. ------------------ የትራጀዲ ተቃራኒ ሲሆን ደስታ ሀሴት መዝናኛ በእጅጉ የሚስተዋለበት የተውኔት አይነት ነው፡፡
9. ------------------ እኩይ እና ሰናይ ገፀባህያት እንደየባህሪያቸው የሚፋለሙበት እና ሰናይ ገፀባህሪው ሲያሸንፍ የሚስተዋልበት
ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ተውኔት ሥነ ምግባርን ለማስተማር ይመረጣል፡፡
10. ------------ በፌዝ እና ቧልታዊ ትዕይንቶች የተሞላ ሲሆን በሁካታ እና በሳቅ የተሞላ ነው በዚህ ተውኔት ጥያቄ ላይጠየቀ
ይችላል ዋናው የነተሳው ሀሳብ ያስቃል አያስቅም የሚለው ብቻ ነው የሚታየው፡፡
መመሪያ 3 የሚከተሉትን ዘይቤዎች ትክክለኛ የዘይቤ አይነታቸውን ፃፉ
33
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
1. አንቺ እመብርህን---------------------------
2. የአንበሳ ደቦል የመሰለ ልጅ-------------------
3. ጠባይዋ ወርቅ ነው------------------
4. ሺ ቢታለብ ያው በገሌ አለች ድመት-----------------
5. የዳዊትን ብልሀት ይስጥህ------------------
6. ኪዳነምህረት ፈጥነሽ አቤት በይኝ----------------
7. እንደ ሸማኔ መወርወሪያ----------------
8. ሰማይ ምድሩ ይደበላለቅብኛል-----------------
9. ገፅታዋ ጣረሞት ይመስላል--------------------
26.ስነ ቃል
የሥነቃል ተግባራት
1. የማዝናናት ተግባር፡- ሥነቃል የሚከወነው አዝናኝ በሆነ መንገድ ነው፡፡ በሥነቃል ጌዜ የሚገኘው ደስታ የምንገልፀው በሳቅ
ወይም በሲቃ ነው፡፡
በሰርግ ጫወታ፣በቀረርቶ፣እንቆቅልሽ እና በእንካ ሰላምታ ጊዜ ልንስቅና ልንዝናና እንችላለን፡፡
2. የማስተማር ተግባር፡- የሥነ ቃል አላማ በመጀመሪያ ማዝናናት ነው ከማዝናናት ቀጥሎ ደግሞ አንዳች ቁምነገርን ለተደራሹ
ማስተማር ነው፡፡ በተለየም ሥነቃል ላልተማሩ እና ላልሰለጡ ማህበረሰብ ብቸኛ የማስተማሪያ መንገድ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ለምሳሌ፡- በተረት ውስጥ ጅብ እና ጦጣ የሚሳሉበት መንገድ ተረቱን ለሚያዳምጡ ልጆች ከጦጣ ብልሀትን ከጅብ ደግሞ
በጉልበት ብቻ ማሰብ ጥቅም እንደሌለው ይማራሉ፡፡ በእንቆቅልሽም እንደዛው የሚጠይቀው ሰው ሲጠይቅ መላሹ ደግሞ
ያስባል ይመልሳል በዛ ውስጥ ብዙ ትምህርተችን ይማራል፡፡
34
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
3. የቁጥጥር ተግባር፡- በሥነ ቃል ማህበረሰቡን ሥነ ምግባር ማስተማር ይቻላል ሰዎች ከማህበረሰቡ አስተሳሰብ ውጭ ሲሆኑ በሥነ
ቃል ከማህበራሰቡ ያፈነገጠውን በማስተማር ይመለስበታል፡፡
4. የመቃወም እና ማሞገስ፡- በሥነ ቃል ጥሩ የሰራ ይሞገሳል ያጠፋም ይወቀሳል
ምሳሌ፡- ለምስለኔው ሙክት ለጭቃው ወጠጤ
እንዲህ ሆኘ ነወይ ባገር መቀመጤ/በኀይለስላሴ የተማረሩ
ምንሊክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ /ምንልክን ለማሞገስ/
የሥነ ቃል አይነቶች
የሥነቃል አይነቶች እንደየማህበረሱ ባህል እና አመለካከት የተለያዩ ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን የስነ ቃል አይነቶችን በሁለት መክፈል
ይቻላል እነሱም፡- በግጥማዊ እና በዝርው መልኩ የሚቀርቡ ናቸው፡፡
በግጥም መልኩ የሚቀርቡ የስነቃሎች አይነቶች
1. የክበረ ባዕላት ዘፈኖች
ምሳሌ፡- አየኸው ደመረ መስቀል ሲያበረ /2/
መስቀል አለ ወይ ቆሟል ወይ
አለ እንጂ ለምፅ ያነፃል እንጂ
ያው ቆሟል ድዊ ይፈውሳል
2. የሰርግ ዘፈኖች፡-
ምሳሌ፡- አንቺ ቤላ ቤላ ቤላ ቤላ
ነይ እንሂድ ሀረር ---ሀረር
ብርቱካን እነብላ ----ቤላ
3. ፉከራ፡-
ምሳሌ፡- ፈሪ ጨነቀው ተርበደበደ፣
ጥይት ዘነመ እሳት ወረደ፣
ውረድ እንውረደ ተባባሉና፣
አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና፡፡
4. እንካ ሰላምታ፣ልመና፣ሙሾ፣መነባነብ እና እሰጥ አገባ ግጥማዊ ስነቃሎች ናቸው፡፡
5. ምሳሌያዊ ንግግሮች እና እንቆቅልሾች ግጥማዊም ዝርውም ስነቃል ናቸው፡፡
በዝርው መልኩ የሚቀርቡ ስነቃሎች
1. ተረት፡- በሁለት ቡድኖች የሚከወን ሲሆን አንደኛው አድማጭ አንዱ ሰሚ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ አብዛኛው ጊዜ ተረት ለህፃናት
የሚቀር ሲሆን በተረቱ አማካኝነት ተረቱን የሚያዳምጡ ሰዎች ሥነ ምግባርን እንዲማሩ ይደረጋል
የተረት ገፀባህሪያት እንስሳት ሰዎች እኩይ መንፈሶች እና ሰናይ መናፍስት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
2. አፈ ታሪክ፡-በተፈጠረ ታሪክ ወይም በአንድ ሁነት ላይ የፈጠራ ታሪክ ተጨምሮበት የሚነገር ነው፡፡ ምሳሌ የአንድ ሰፈር
አሰያየም ወዘተ
3. ሀተታ ተፈጥሮ፡- ሰዎች የተፈጥሮን ሁኔታ በማየት ስለ አፈጣጠራቸው በራሳቸው ግምት መልስ የሚሰጡበት መንገድ ነው
ማለትም ሳይንሳዊ ለሆኑ ጥያቄዎች ኢሳይንሳዊ መልስ የሚሰጡበት ነው፡፡
ምሳሌ፡- በቅሎ ለምን ልጅ አልወለደችም የዝንጀሮ ቂጥ ለምን መላጣ ሆነ
35
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
25.ቅኔ
በልዩ ልዩ አይነት ግጥም የሚቀርብ ነው፡፡
ቅኔ ሶስት ክፍሎች አሉት እነሱም ሕብረ ቃል ሰም እና ወርቅ ናቸው
ሕብረ ቃል፡- ሰም እና ወርቅን በአንድ ላይ የሚይዝ ቃል ወይም ሀረግ ነው፡፡
ሕብረ ቃል፡- አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው በቅኔው የመጨረሻ ስንኝ ላይ ነው፡፡
ሰም ፡- የቅኔው ቀጥተኛ ፊቺ ነው
ወርቅ፡- የቅኔው ድብቅ ፍቺ ነው
ምሳሌ፡- 1. ሀረገሬ አታልቅሺ እኔ አሳይሻለው
ከጂማ መኖሩን ባይኔ አይቻለው
ሕብረቃል፡- ከጂማ
ሰም፡- ጅማ ከተማውን
ወርቅ፡- ከዳተኛ/ከጂ/
ምሳሌ፡- 2 አልተከልኩ እንኳ ከጓሮዬ
ዱባ ለመከራዬ
ሕብረ ቃል፡- ዱባ ለመከራዬ
ሰም፡- ለችግር የሚሆን ዱባ
ወርቅ፡- መከራ ድንገት ዱብ አለብኝ
ምሳሌ 3 ብሄድ በወለጋ ብሄድ በጎጃም
እንዳንቺ አይነት በቅሎ አይቼ አላውቅም
ሕብረ ቃል፡- በቅሎ
ሰም፡- እንዳንቺ አይነት ቆንጀ ተወልዶ አላየሁም
ምሳሌ 1 በጥቅሻ ይወድቃል እንኳንስ በጠጠር፡፡
26.አንቀፅ
አንቀፅ ማለት ተያያዥነት ያላቸው ዓ.ነገሮች ተገጣጥመው ስለ አንድ ፍሬ ሀሳብ ብቻ የሚያቀርቡበት ፅሁፍ ነው፡፡
የአንቀፅ ባህሪያት
1. አንድነት፡- በአንድ አንቀፅ ውስጥ የሚቀርቡ ሀሳቦች በሙሉ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ መሆኑን ያመለክታል፡፡
2. ግጥምጥምነት፡-የሚቀርቡት ሀሳቦች አንድነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሰንሰለታዊ ቁርኝነታቸውና ተጠየቅያዊ ፍሰታቸው የተስተካከለ መሆን
እንዳለበት ያመለክታል፡፡
3. ብቁነት፡- የሀሳባቦቹ ጥልቀትና ብስለት ብቃቱን የጠበቀ መሆን እንዳለበት ያመለክታል፡፡
4. ሀይለቃል፡- የአንቀፁ ዋና ሀሳብን የሚያመለክት ዓ.ነገር ነው፡፡
የሀይለ ቃል መገኛ እና የአንቀፅ ቅርፅ
ሀ. ሀይለ ቃል መነሻ ላይ ሲገኝ
ሀይለ ቃል
ዝርዘር ዓ.ነገር
ለ. ሀይለ ቃል መጨረሻ ላይ ሲገኝ
ዝርዝራ ዓ.ነገር
36
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
ሀይለ ቃል
ሐ. ሀይለ ቃል መሀከል ላይ ሲገኝ
ዝርዝራ
ሐይለ ቃል
ዝርዝር
ዝርዝር
ሀይለ ቃል
37
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
የሴራ አይነቶች
ጥብቅ ሴራ፡- ሴራው በተደራሲያን ዘንድ የእውነት እስኪመስል ድረስ ስሜትን በእጅጉ ይይዛል
ልቅ ሴራ፡- ምክንያትና ውጤቱ ጥብቅ አይደለም በአጠቃላይ ግጭቱ ተደራሲያንን አያሳምንም
ነጠላ ሴራ፡- የአንድ ሁነት ግጭት ብቻን ያመለክታል/ በአንድ ዘለላ ጉዳይ ላይ ብቻ ያጠነጥናል
ገፀባህሪያት፡-ፀሀፌ ተውኔቱ የሚቀርፃቸው ሆነው ተዋናዮቹ ህያዋን ናቸው፡፡
ሙዚቃ፡- በተውኔቱ ሊተላለፉ የሚፈለጉ ማንኛውንም አይነት ስሜት የምናጅብበት መንገድ ነው/የተውኔት ማጀቢያ ነው፡፡
ትዕይንት፡- የገቢር ክፍል ሲሆን የመድረክ እነፃውን፣ የተዋንያንን አልባሳት፣ የመድረኩን ገፅታ ይመለከታል በአጠቃላይ በገፀባህሪያት
38
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞጁል ለ አስረኛ ክፍል በብንያም ከድር ታህሳስ 2013
39