You are on page 1of 36

የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ

የ2ኛ መ/አመት ትምህርት

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ
ከኤክሴል አካዳሚ
ጋር በመተባበር የተዘጋጀ
ሚያዚያ 2012 ዓ.ም
አዘጋጅ ፡- መ/ርት ማህሌት ሌንዲዶ
ሞባይል : +251 912 81 54 43
ምዕራፍ ስድሰት
በረሃማነት

የደን ውድመት

የቃላት ጥናት

መነጣጠል እና ማጣመር

መነጣጠል፡- ማጣመር ማለት አንድን ሙሉ ቃል ወይም ሀገር በተናጠላዊ ሂደቶች ወይም


አነስተኛ የቃላት ክፍልፋዮች ነጥሎ የማንበብ ሂደት ነው፡፡

ማጣመር፡- ማጣመር ማለት ደግሞ አነስተኛ ክፍልፋዮች ወይም ፊደሎች ተነጣጥሎ


የቀረበውን ቃል ወይም ሀረግ በአንድ ላይ አጣምሮ መናገር፡- ማንበብ መይም መፃፍ
ሂደት ነው፡፡

ምሳሌ
 እየጨመሩ  እየጨመሩ
 አመለከቱ-አቸው  አመለከቱአቸው
 እየ-ተመናመነ  እየመናመነ

- ከላይ የቀረበውን ነጥሎ እና አጣምሮ የማንበብ ሂደትን ስትመለከቱ ሁለቱ


ምሳሌዎች ስንመለከት ምንም ዓይነት ልዩነት የፊደል ቅርፅ ለውጥ አይታይም ነገር
ግን በአንደኛውም ማለትም ‹‹አመለከቱ-ኣቸው›› የሚለው ግን ‹‹ ቱ›› በሚለው
ተነባቢ ድምፅ ውስጥ ‹‹ኡ›› አናባቢ ድምፅ ነበረች ‹‹ቱ›› ይህም ተነባቢ ድምፅ
‹‹ኣ›› ተነባቢ ሲወስድ ወደ ‹‹ቷ›› ይቀየራል፡፡ ስለዚህ በመነጣጠል እና በማጣመር
ሂደት ጊዜ ሁል ጊዜ እንዳለ አጣምሮ ማንበብ (መፃፍ ብቻ) ሳይሆን የተነባቢ
ድምፅ ውስጥ አናባቢ ስርዓትን በማስተዋል ያስፈልጋል፡፡
ተግባር 1

የሚከሉትን ተነጣጥለው የቀረቡ ቃላት በምሳሌ መሰረት ካነበባችሁ በኃላ እንደገና


አጣምራችሁ በመፃፍ አንብቡ፡፡

ሀ. ሽማግሌ-ዎች-ኣችን

ለ.መታረስ-ኣቸው-ን

ሐ.አ-ድንቅ-ኸው-ል-ኣት-ኣል

መ.ት-ነግር-ኸኝ-ኣል-ኸህ

ሠ.አውርዳ-ብ-ን-ኣል-ኸች

ረ.አብልተው-ኣቸው-ኣል

መፅሐፍ

ድርሰት መፃህፍ

የድርሰት ክፍሎች

ከአደረጃጀት አኳያ ሲታዩ ማንኛውም ጥሩ ድርሰት በሶስት ክፍሎች የተደረጃ ነው፡፡


እነርሱም፡- መግቢያ፣ ሃተታና መደምደሚያ ናቸው፡፡

1. መግቢያ፡- መግቢያ ከቃሉ መረዳት እንደሚቻለው ወደ ዋናው ፅሁፍ መተላለፊያ በር


ነው፡፡ ድርሰት የአንባቢ ልብ (ቀልብ) በመሳብ እያግባባ ለመንደርደር ወደ ዋናው
አካል (ሀተታ) ክፍል ማድረስ እንዲችል በጥንቃቄ መፃፍ ይኖርበታል፡፡ ጥሩ መግቢያ
ያልተንዛዛ እና ግልፅ ሆኖ አንባቢው ሊያነበው የተዘጋጀውን ፍሬ ነገር ሊያጓጓ በሚችል
መልኩ በማስተዋወቅ እና ዋና ዋና ነጥቦችን በመጠቆም በሀተታው ክፍል ይለቃል፡፡
2. ሀተታ(ዋና አካል)፡- ይህ የድርሰት ክፍል ጭብጦች በማስረጃነት የሚተነተኑትን እና
ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎችን የሚቀርብበት የድርሰቱ ዋና አካል ነው፡፡ የሀተታ ክፍል
አንቀፆች ብዛት የሚወሰነው የአርስተ ነገሩ ስፋት እና ነጥብ ፤የሚቀርቡ ማስረጃዎች
ብዛትና የፀሀፊው ሃሳቦች አስፋፍቶ የማቅረብ ችሎታ የመሳሰሉትን ይመለከታል፡፡
ዋናው ነገር በተቻለው መጠን የተሰጠውን (የተመረጠውን) ርዕስ ተዓማኒ መረጃዎችና
ማራኪ የሆነ የአፃፃፍ ዘዴ ለአንባቢው መቅረብ መቻል አለበት፡፡
3. መደምደሚያ፡- በዚህ ድርሰት ክፍል በዋናነት በሀተታዊ(በዋነው አካል) ክፍል በስፋት
ተብራርተው (ተተንትነው) የቀረበውን ጭብጦች አጠር ባለ መልኩ በማሳሰብ ውጤቱን
ቁልጭ አድርጎ ማሳሰብ ነው፡፡
የአንቀፅ ባህሪያት
- የአንቀፅ ባህሪያት የሚባሉት አንድነት፣ ግጥምጥምነት፣ ብቁነት ናቸው፡፡
1. አንድነት፡- አንድንት በአንቀፅ ውስጥ የሚቀርቡት ሀሳቦ ሁሉ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ
በማተኮር እንዳለበት ያመለክታል፡፡
2. ግጥምጥምነት፡- ይህ የአንቀፅ ባህሪ ደግሞ አንድ አንቀፅ ውስጥ የሚቀርቡ ሀሳቦች
እንደተጠበቀ ሆኖ ሰንሰለታዊ ቁርኝታቸው ተጠያቂው ፍላጎታቸው እየተከታተለ
መሆን እንዳለበት ያሳያል፡፡
3. ብቁነት፡- የአንቀጹ አንድነትና ግጥምጥምነት እንደተጠበቀ ሆኖ ሃሳቦች ጥልቀትና ስለ
ብስለት ብቃቱን የጠበቀ መሆን እንዳለበት ያመለክታል፡፡

የድርሰት አይነቶች
የድርሰት አይነቶች ከሚባሉት መካከል የሚከተሉትን ተመልከቱ፡፡

1. ተራኪ ድርሰት
ተራኪ ድርሰት በጣም ከተለመዱት አራት ዋና ዋና የድርሰት አይነቶች አንዱ
ነው፡፡የቀሩት ሶስቱ ደግሞ (መስታወታዊ)፣ ገላጭ (አስራጅ) ድሰትና አመዛዛኝ ድርሰት
በመባል ይታወቃሉ፡፡

* ተራኪ ድረሰት ድጊቶችንና ስንሠለታዊ እውነቶችን የድርጊት የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን


ጠብቆ ‹‹ እንዲህ ሆ፣ እንዲህ እንዲህ ተደረገን፣ እያለ ሚተርክልን ፅሁፍ ነው፡፡ ታሪኩን
የሚነግረንም እራሱ የድርጊቱ ተካፋይ ሊሆን ይችላል፡፡ አለበለዚያም ድጊቱን
የተመለከተ፣በልምድ ያገኘው ወይም ከሌላ ሰምቶ የጊዜ ቅደም ተከተልን መሰረት አድርጎ
ያቀርባል፡፡
ለምሳሌ፡- ’’ የአድዋ ጦርነትን’’ የሚመለክት ፅሁፍ በጊዜ ቅደም ተከተል ቢቀርብ ተራኪ
ድርሰት ይባላል፡፡
2. ስዕላዊ ድርሰት

ስዕላዊ ድርሰት የአንድን ነገር ምስልና ገፅታ በቃላት አማካኝነት ስሎ ለማቅረብ የሚሞክር
የድርሰት አይነት ነው፡፡ በዚህ የድርሰት አይነት ደራሲው የሚጠቀምባቸው ቃላት በሰው
አእምሮ ውስጥ ምስል መፍጠር የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ በዚህ የድሰት አይት የአንድን
ነገር ሁኔታ በዓይን እንዳዩትና በእጅ እንደዳደሱለት በጆሮ በቅርብ ሆነው እንደሰሙት
በጠቅላላው ግዙፍ አድጎ የሚቀርብ የድርሰት አይት ነው፡፡

ምሳሌ፡-

ለጠረጴዛው ጎኗን ሰጥታ እግሮቿን አነባብራ ተቀምጣለች፡፡ ክንዷን ጠረጴዛው ላይ


አዘስደግፉ መፃፉ ላይ ጋደም ብላለች፣አውራ ጣቷ ክብ አገጯ ስር ገብቶ በሌላ ጧቷ
ጉንጯን እንደ ማከላ እያለች ትተክዛለች፤ሀሳብ የያዘው ወይም የተገረነ ሰው ትመስላለች፡፡

3 አስረጅ ርገላጭ/ድረሰት

አሰውረጅ ድረሰት ከድሰት አይነቶች አንዱ ሲሆን የአንድን ነገር ምንነት፣አገኛኘት፣


ባህሪያት፣ ዓይነት፣መጠን፣ቅርፅ፣አሰራር፣ ጠቀሜታ፣ጉዳት ወዘተ. የሚያብራራ የድርሰት
አይነት ነው፡፡

ለምሳሌ፡- ስለ ‹‹ዶሮ ወጥ›› አሰራ የሚገልፅ ፅሁፍ በአስራጅ ድርሰት ምሳሌነት መውሰድ
ይቻላል፡፡

4. አመዛዛኝ ድርሰት

አመዛዛኝ ድርሰት አከራካሪ ስለሆኑ ጉዳዮች የሚፅፍ፣አንባቢን/አድማጩን/የአንድን ጉዳዩ


እውነትነት ወይም ሐሰትነት ለማሳመን ለአንድ ወገን ቆሞ አንድን ጉዳዩ በአንድ መልኩ
ብቻ በመቃወም ወይም በመደገፍ ሊፅፍ የሚችልበት፣ወይም ለሁለቱ ሀሳቦች የቆመ
በመምሰል ጉዳዩን በመደገፍ በመቃወም አቅርቦ በመጨረሻም ማስረጃው ያደለበትን
አጠናክሮ በመተቸት አንዱን በማጠናከር ወደ አንዴ ውሳኔ የሚደርስበትና ለማሳመን
የሚጥርበት የድርሰት አይነት ነው፡፡

ምሳሌ፡-
ብዙ የስነ-ትምህርት ተመራማሪዎች የመማር ማስተማር ዘዴ ትምህርት ‹‹ ሳይንስ›› ነው
ሲሉ ሌሎች ደግሞ‹‹ አርት›› ነው ይሉታል፡፡ ‹‹ አርት›› ነው የሚሉት ተመራማሪዎች
የመማር ማስተማ ዘዴ ምንም ህግ የለውም ይላሉ፡፡ ‹‹ የተማረ ያስተም›› እንደሚሉት
አይነት ነው፡፡

አስተዋፅኦ(ቢጋር)
አንድን ድርሰት መፃፍ ከመጀመራችን በፊት ሶስት ዋና ዋና ተግባራን እከናውናለን፡፡

እነዚህ ተግባራ ርእስ መምረጥ፣የተመረጠን ርዕስ መወሰን ወይም ማጥበብና አተዋፅኦ


(ቢጋር) ማዘጋጀት ናቸው፡፡

 አስተዋፅኦ (ቢጋር) ዋናውን ፅሁፍ ለመፃፍ፣መንገድ ቀያሽ ወይም ትልም ነው፡፡


በተለዩም ለልቦለዶችና ለሌሎች ረጃጅም ፅሁፎች በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው፡፡

የአስተዋፅኦ(የቢጋር) ጥቅሞች
 ዓላማን ግልፅ ለማድረግ ሐሳብን ከአላማ ጋር ለማዛመድ ያግዛል፡፡
 ድርሰቱ ከመፃፉ በፊት የሐሳቡን ቅንጅት ለማየትና ለማስተካከል ይጠቅማል፡፡
 መልዕክትን ለማስተላለፍ ራሱን የቻለ መሳያ በመሆን ያገለግላል፡፡
 ፅሁፉ በሚፃፍበት ጊዜ ከዋና ሀሳብ እ3ንዳንወጣ ይረዳል፡፡
 አስተዋፅኦ(ቢጋር) እንዴት ሊነደፍ ይችላል? የሚከተለውን ተመልከቱ፡፡

ስርወ ቃላትና ቅጥያዎች

1. ስረወ ቃል (ዋናቃል፣ግንድ)
1.1 ዋና ቃል ትርጉም አለው
1.2 ብቻውን መቆም ይችላል
2. ቅጥያዎች
2.1 ብቻቸውን መቆም አይችም፡፡
2.2 በዋና ቃል ውስጥ የተለያየ ቦታ ሊገኙ ይችላሉ፡፡
ሥርወ ቃላትና ቅጥያዎች

ወደ ሌላ ዝቅተኛ ቅንጣት ሊሸራረፍ የማይችል ባለትርጉም የድምፅ ልሳናት ቅንጅት


ስረወቃል (ዋና ቃል) ይባላል፡፡ ያለምንም ተጨማሪ ቅጥያ ራሱን ችሎ ይቆማል፤የተሟላ
ትርጉምም ይሰጣል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ዋና ቃል አልፎም ነፃ ምዕላድ እየተባለ ይጠራል፡፡

ቅጥያ (ምዕላድ) ማለት ደግሞ በስረወቃላት(በዋና ቃል) ላይ እየተጨመረ የቃቱን


መሰረታዊ ፍቺ የሚያስለውጥ ሆኔ ወይም ሆኔጣት ሁሉ ቅጥያዎች (ምዕላዶች) በመባል
ይታወቃሉ፡፡ ቅጥያዎ(ምዕላዶች)አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ችለው አይቆሙም፤ ከቃላት
ጋር ካልተጣመሩ የተሟላ ትርጉም አይሰጡም፡፡ ነገር ግን ከቃላት ጋር ሲጣመሩ የቃላቱን
መሰረታዊ ፍቺ ሊያጠቡ፣ ሊያሰፉ፣ ሊያስለዉጡ፣ ሊያስፈርሱ፣ ወዘተ የሚችሉ የቋንቋ
ቅንጣቶች ናቸው፡፡

. ‹‹ የደኖች መመናመን ›› በሚል ርዕስ ከላይ በቀረቡት ገለፃዎችና ምሳሌዎች መሰረት


መግቢያ፣ዋና አካልና ማጠቃለያ (መደምደሚያ) ያለው ድርሰት በትረካ ስልት ለመፃፍ
የሚያስችል የቢጋር (አስተዋፅኦ) በማዘጋጀት ድርሰት ፃፉ፡፡

ሰዋሰው

ተግባር 2

 የዓ/ነገር አይነቶች (በአገልግሎት)


ዓ/ነገሮች ከአገልግሎታቸው (ከስልት) አንፃር ሐተታዊ፣ ጥያቄዊ፣ትእዛዛዊና አጋኗዊ የዓ/ነገር
አይነቶች በሚሉ ስር ይመደባሉ፡፡ የእያንዳንዱን ልዩንት እንመልከት፡-
ሐተታዊ ዓ/ነገር
 ሐተታዊ ዓ/ነገር አይነት ሀሳብን ለመግለፅ በቀጥታ የሚነገር፣ በአነጋገርና በአፃፃፍ ስልቱ
የመጠየቅ (ምላሽ) የመጠበቅ ባህሪ የሌለው የዓ/ነገር አይነት ሲሆን አዎንታዊና አሉታዊ
ዓ/ነገሮችን ይይዛል፡፡
ሀ. አዎንታዊ ሐተታ ዓ/ነገር
ምሳሌ፡- ቤዛ ጎበዝ ተማ ነው፡፡
በረከት ስዕል መሳል ይወዳል፡፡
ለ. አሉታዊ ሐተታ ዓ/ነገር
ይህ ዓ/ነገር በአፍራሽ ማለትም በአሉታ የሚነገር የዓ/ነገር ስልት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ምሳዬን አልበላሁም፡፡
ልጅቷ በጣም አስቸጋሪ አይደለችም፡፡
ትዕዛዛዊ ዓ/ነገር
ትዕዛዛዊ ዓ/ነገር በትዕዛዝ መልክ የሚቀርብ የዓ/ነገር ስልት ነው፡፡ ትዕዛዙ በትዕትና
አነጋገርና በመግባባት መልክ ሊሆን ይችላል፡፡
ምሳሌ፡- ያልኩህን ፈፅም!
ስራህ ቦታ በቶሎ ድረስ!
ጥያቄያዊ ዓ/ነገር
ጥያቄያዊ ዓ/ነገር በጥያቄ መልክ የሚቀርብ የዓ/ነገር ሰልት ነው፡፡ መልስ የሚሻ የዓ/ነገር
አይነት መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡
ምሳሌ፡- - ምን እየሠራህ ነው?
- የልደትህ ቀን መቼ ነው?
የጥያቄያዊ ዓ/ነገር ማስረጊያው የጥያቄ ምልክት መሆኑን አትዘንጉ፡፡
አጋኗዊ ዓ/ነገር
አጋናኝ ዓ/ነገር የማጋነን፣የመደሰት፣የመደንገጥ ወዘተ ስሜት የሚነገርበት የዓ/ነገር አይነት
ነው፡፤ የአነጋገር ስልቱ የተናጋሪውን ስሜት የሚጎላ በመሆኑ ለየት ይላ፡፡
ምሳሌ፡- እልልል! እሰይ! ልጄ መጣች፡፡
ይኸውላችሁ ዋ! ያልኩት አልቀረም፡፡
ዓ/ነገርን ወደ አሉታዊና መጠይቃዊ ቅርፅ መቀየር
- የሚከተሉትን ዓ/ነገሮ በምሳሌው መሰረት ወደ አሉታዊና ወደ መጠይቃዊ ዓ/ነገሮ
ለውጣችሁ ፃፉ፡፡
ምሳሌ፡- ትህትና ከዛፍ ስራ ቆማለች፡፡
 ትህትና ከዛፍ ስር አልቆመችም፡፡
 ትህትና ለምን ከዛፍ ስር አልቆመችም?
 ትህትና ከዛፍ ስር ለምን ቆመች?
ሀ. ችግኝ በመትከል ብቻ ደንን መንከባከብ ይቻላል፡፡
ለ. የሰዎ ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት ብቻ ደኖች ይወድማሉ፡፡
ሐ. ከመንደሩ በቅርብ ርቀት ጫካ አለ፡፡፡
መ. እልፍነሽ ጥሩ ውጤት አስመዝግባለች፡፡
 ከላይ የቀረቡ ዓ/ነገሮችን በምሳሌው መሰረት ወደ አሉታና መጠይቃዊ ዓ/ነገሮች ለውጣችሁ
ፃፉ፡፡
የግንዛቤ ማመሳከሪያ ቅፅ
. ከዚህ በታች በምዕራፍ ስድሰት የቀረበውን ትምህርት ምን ያህል እንደተረዳችሁ
የምታመሳክሩበት ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡ በእያንዳዱ የማመሳከሪ ነጥብ ትይዩ ስለተረዳችሁት
እርግጠኛ ከሆናችሁ/ /፣ እርግጠኛ ካልሆናችሁ የ/ ? / ፣ሙሉ በሙሉ ካልተረዳችሁ ደግሞ
የ/x / ምልክቶችን በማድረግ መልሶ ገለፃውን ወይም ማስታወሻውን እና ምሳዎን በትኩረት
በማንበብ ለመረዳት ሞክሩ፡፡
ተ.ቁ የማጠናከሪያ ነጥቦች  ? x
1 የመነጣጠልና የማጣመርን ምንነት
ተረድቻለሁ
2 የድርሰት ክፍሎችን ለይቻለሁ
3 የአንቀፅ ባህሪያትን አውቄያለሁ
4 የድርሰት አይነቶችን አውቄያለሁ
5 የአስተዋፅኦ(ቢጋር) ምንነት ተረድቻለሁ
6 የአስተዋፅኦ(ቢጋር) ጥቅሞች
አውቄያለሁ
7 የአረፍተ ነገሮች አይነቶችን
(ከአገልግሎት) አንፃር ለይቻለሁ
ምዕራፍ 7
የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ
የቃላት ጥናት
መነጣጠልና ማጣመር
ተግባር 1
የሚከተሉትን ቃላት ነጣጥላችሁና አጣምራችሁ አንብቡ፡፡
ነጣጥሎ ማንበብ አጣምሮ ማንበብ
ሀ ግንዛቤ-ያቸው-ን ግንዛቤቸውን
ለ ሱቅ-በ-ደረት-ኤ-ነት ሱቅበደረቴነት
ሐ አሳሳቢ-ነት-ኡ-ን አሳሳቢነቱን
መ ቀስ-ኣ-ቀስ-ኦች ቁሳቁሶች
ሠ ህገ-መንግስት-ኡ-ም ህገመንግስቱም

 በዚህ በመነጣጠልና ማጣመር ሂደት የፊደል ገበታን መሰረት በማድረግ እናነባለን፡፡


ይኸውም ተደጋጋሚ ሆሄያትን በመተው በንግግር የድምፅ ልሳናት ብዛት የአማርኛ ቋንቋ
ድምፆችን ስንመድብ(ሰባት) አናባቢዎችና (27)ተነባቢዎ በሁለት ተመድበው እናገኛለን፡፡
እነዚህም፡’’ኸ፣ ኡ፣ ኢ፣ ኣ፣ ኤ፣ እ፣ ኦ’’ አናባቢዎች ሲሆኑ ተነባቢዎቹ ደግሞ፡- ‹‹
ሀ፣ለ፣መ፣ሰ፣ረ፣ሸ፣ቀ፣በ፣ተ፣ቸ፣ነ፣ኘ፣ከ፣ወ፣ዘ፣ዠ፣የ፣ደ፣ጀ፣ገ፣ጠ፣ጨ/፣ጰ፣ፀ፣ፈ፣ፐ፣ቨ’’ ናቸው፡፡ ስለዚህ
በነጣጥሎና አጣምሮ ማንበብ ሂደት ላይ በተነባቢ ድምፅ ውስጥ የአናባቢ የድምፅ ስርዓትን
ማስተዋል ይገባል፡፡
ምሳሌ፡- ’’ ሱቅ-በ-ደረት-ኤ-ነት ’’ በዚህ ነጣጥሎ ማንበብ ሂደት ጊዜ ’’ት’’ ድምፅ
ውስጥ ’’እ’’ አናባቢ ድምፅ በውስጡ ነበር፤ ከዚያም ’’ኤ’’ን በምትወስድበት ጊዜ
ወደ ‹‹ቴ›› ተለውጧል ስለዚህ ከላዩ የቀረበወን ሰንጠረዥ ይህንን መሰረት በማድረግ
በትኩረት አንብቡ፡፡
ቃላት
ለቃላት ተቃራኒ ፍቹ መስጠት
ተቃራኒ ፍቺ
ተቃራኒ ፍቹ ማለት አፍራሽ ማለት ነው፡፡ አንድ ቃል ለሚወክለው ነገር ተቃዋሚ
ወይም አፍራሽ የሆኑ ቃላትን በመፈለግ እያዛዱ ማጥናት ጠቃሚ ነው፡፡ ቃላትን
በሚገባ እንድናውቅ ይረዳናል፡፡
ስለመነሻው ቃል ትርጉም፣አገባብና ውክልና ጥርት ያለ ግንዛቤ እንድንጨብጥ
ከማስቻሉም ባሻገር ሀሳቦችን በአሉታዊ አማራጭ ለማስተላለፍ እንድንችል
ይረዳናል፡፡
ምሳሌ፡- ‹‹ አስተሳሰቡ ኋላቀር ነው›› የሚለውን ‹‹ አስተሳሰቡ አልተለወጠም›› ብሎ
በአማራጭ እንደመግለፅ አይነት ማለት ነው፡፡

በ‹‹ሀ›› ረድፍ ለሚገኙት ቃላትና ሐረጋት ተቃራኒ ፍቻቸውን በ‹‹ለ››


ረድፍ ካሉት በመምረጥ አዛምዱ፡፡
’’ሀ’’ ’’ለ’’
1. መጠበቅ ሀ.የተሻለ
2. የከፋ ለ.ማስቀጠል
3. ተጠቂ ሐ.ተጠቃሚ
4. ደንግጓል መ.ሸሯል
5. ማሰናከል ሠ. መጋለጥ
6. ህገወጥ ረ.ህገኛ
7. ፈነጠዘ ሰ.ተከፋ

መፃፍ
ድርሰት መፃፍ
በዋና መዘርዝ ሀሳችን ድርሰት መፃፍ
ተግባር 3
‹‹የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ አይነቶች›› በሚል ርዐስ ቢጋራ በማዘጋጀት
መግቢያ፣ሐተታና መደምደሚያ ያለው ድርሰት ፃፉ፡፡
ስርዓተ ነጥብ
 ስርዓተ ነጥቦች በወረቀት ላይ የሠፈረ ሀሳብ መልዕክቱ ግልጽ ሆኖ እንዲተላለፍ የጎላ
ድርሻ አላቸው፡፡ በመሆኑም መልዕክታችንን በሚገባ ለማስተላለፍ አጠቃቀማቸውን
በሚገባ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡
 በአማርኛ ቋንቋ ፅሁፎች ውስጥ የሚያገለግሉ ስርዓተነጥቦች በርካታ ናቸው፡፡ ቀጥሎ
የሚከተሉትን ተመልከቱ፡፡

1. ሁለት ነጥብ ከሠረዝ(፡-)


የአንድን ዓ/ነገር ሀሳብ ከማብቃቱ በፊት ዝርዝ ሀሳቦች የሚቀጥሉ መሆኑን ለማመልከት
ይገባል፡፡
ምሳሌ፡- የሰው ልጅ መኞቱ ብዙ ነው፡- ዋና ዋናዎቹ መኪና፣ቤት፣አልባሳት፣ሀብት
ናቸው፡፡

2. ትምዕርተ ስላቅ (i)


በፅሁፍ ውስጥ ከምፅት፣ከአሽሙር፣ከማሾፍ ጋር የተዛመዱ አነጋገሮችና ተዛማጅ ስቶች
መኖራቸውን ለማመልከት ይገባል፡፡
ምሳሌ፡- ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለi
ድንቄም አምሮብሽ ሞተሻልi

3. ነጠላ ሠረዝ(፣)
በዓ/ነገር ውስጥ በተከታታይ ተደርድረው የሚቀርቡትን ዝርዝር ቃላትና ሀረጎችን
ለመለየት ያገለግላል፡፡
ምሳሌ፡- ጥሩ ስ፣በቂ ገንዘብ፣ቆን ቤትና መኪና አለኝ፡፡
- ሌላው ደግሞ ምዕራፍንና የንዑሳን ምዕራፎን ቁጥሮች ለይቶ ለማመልከት ያገለግላል፡፡
ምሳሌ፡- ምዕ 9፣2

4. ድርብ ሠረዝ(፤ )
 በአያያዥ ቃላት የሚጣመሩ ዓ/ነገሮችን ለማስተሳሰር ያገለግላል፡፡
ምሳሌ፡- በጣም ደክሞኛል፤ ቢሆንም አልተኛም፡፡
 አቦካዶ ለጤና ጠቃሚ ነው፤ ስለሆነም መግዛት አለብኝ፡፡

5. ሶስት ነጥብ(…)
 ተቀንሶ የቀረ ተመሳሳይ ዝርዝ ሀሳብ መኖሩን ለማመልከት ይገባል፡፡
ምሳሌ፡- ቀልድና … ቤት ያጠፋል፡፡
 በአንድ ሰው አነጋገር ውስጥ የተቆራረጠ የደስታ፣የድንጋጤ፣የሲቃ ድምፆችና ቃላት
መኖራቸውን ለማሳየት ይጠቅማ፡፡
ምሳሌ፡- ልጄን… እኔን… እኔን… እናትሽን !

6. ቅንፍ()
 በዓ/ነገር ውስጥ የሚገቡ ተጨማሪ የቃላት ፍቺንና መረጃዎችን ለማመልከት ይገባል፡፡
ምሳሌ፡- ቢጋር(አስተዋፅኦ) ድርሰት ለመፃፍ ይረዳል፡፡

7. ትምዕርተ አንክሮ(!)
 የአድናቆት፣ድንገተኛ የሆነ የደስታ(የድንጋጤ) ስሜቶች ለመግለፅ ያገለግላል፡፡
ምሳሌ፡- ዘራፍ!በለው!ያዝልኝ!

8. ጥያቄ ምልክት(?)
 ከጥያቄያዊ የዓ/ነገር አይነቶች በስተመጨረሻ ይገባል፡፡
ምሳሌ፡- ይህ ሰው ማን ነው?

9. ትምዕተ ጥቅም (‹‹ ››)


 በአንድ ሰው ፅሁፍ ውስጥ የሌላ ሰው ሀሳብ የተጠቀሰ መሆኑን ለማሳየት ያገለግላ፡፡
ምሳሌ፡- የስራ ሃላፊው‹‹ የአመራ ክህሎትና የአፈፃጠም ብቃት›› የሚል ንግግር
አሰሙ፡፡
 የገፀባህሪያትን ንግግር ከታሪኩ ለመለየት ይጠቅማል፡፡
ምሳሌ፡- ናደው ድምፁን ክፍ አድጎ፣‹እምዬ!መድሃኒቴ!›› አለና እናቱን እቅፍ
አደረጋቸው፡፡

10. ነጠላ ትምህርተ ጥቅም (‹ ›)


 በጥቅስ ምልክት በሚወስድ ሀሳብ ወይም አባባል ውስጥ የሌላ ሰው ተጨማሪ ጥቅስ
(አባባል) ሲገባ በተጀመረው የጥቅስ ምልክት ውስጥ ለይቶ ለማመልከት ያገለግላ፡፡
ምሳሌ፡- ናደው ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ ‹‹ እናቴ‹ ልጄ አካላቴ፣ ሆዴ መድሃኒቴ› ትለኝ
ነበር›› በማለት ተናገረ፡፡
የአፃፃፍ ስርዓት
ስርዓተ ነጥቦችን በመጠቀም መፃፍ
ተግባር 4
የሚከተሉትን ዓ/ነገሮ ተገቢውን ሥርዓተ ነጥብ አሟልታችሁ ፃፉ፡፡
ሀ. ህፃናት በማንኛውም ስራ እንዳይቀጠሩ ተደንግጓል ነገር ግን ከአቅማቸው በላይ ስራ
ሲሰሩ ይታያሉ፡፡
ለ. ህፃኑ ሲደበደብ የት ነበርሽ
ሐ. የልጅ ባህሪ እንደ አሳዳጊ ነው ይላሉ ወይዘሮ አልታየ
መ. ወይንሸት አልማዝ መሀመድ ቢያድግልኝና አስቴር ስለ ህፃናት መብት ተወያዩ
ሠ. የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ይቁም
ረ. የሽመና ስራ ሸክም የታክሲ ረዳትነት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ የሚካሄድባቸው
የስራ ዘርፎች ናቸው፡፡

ሰዋሰው
የቃል ክፍሎች
 በዘመናዊ ሰዋሰው የቃል ክፍል በአምስት ይመደባሉ፡፡ እነርሱም፡-
ስም፣ ቅፅል፣ ግስ፣ ተውሳከ ግስና መስተዋድድ ናቸው፡፡

ሀ. ስም፡- መጠሪያ የሆነ ማንኛውም ቃል ስም ይባላል፡፡


ምሳሌ፡- አዳማ፣ፍቅር፣ወንበር ወዘተ

ለ. ቅፅል
ቅፅል የሚባለው የንግግር ክፍል በስም ላይ ተጨምሮ የስሙን
አይነት፣መጠን፣ቅርፅ፣ባህሪ ወዘተ የሚገልፅ ነው፡፡
ምሳሌ፡- አረንጓዴ ልብስ የለበሱ ወጣቶች መጡ፡፡ « አረጓዴ» የሚለዉቅፅል ነዉ፡፡

ሐ. ግሥ
- ድርጊትን (የመሆን ስሜትን) የሚገልፁ ቃላት ሁሉ ግስ ይባላሉ፡፡
ምሳሌ፡- በላ፣ዘመረ፣ጨፈረ ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
 ግሶች የዓ/ነገር መቋጫ (ማሠሪያ )ናቸው፡፡
መ. ተውሳከ ግስ
 በዓ.ነገር መዋቅር ውስጥ ከግስ በፊት እየገቡ የግሱን አፈፃፀም ከሁኔታ፣ከቦታ፣ከጊዜ
ወዘተ አንፃር ግሱን ይገልፃሉ፡፡
 የተውሳከ ግስ ትርጓሜም የግስ ጭማሪ ማለት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ልጁ ክፉኛ ታሟል፡፡ የተሠመረበት ቃል የቃል ክፍሉ ተውሳከ ግስ ነው፡፡

ሠ. መስተዋድድ
 በስም (ስም በሚመስሉ) ቃላት ላይ እየተጫነ ገብቶ በዓ/ነገር ውስጥ የንግግርን ዝምድና
የሚያሳይ ቃል መስተዋድድ ይባላል፡፡ መስተዋድድ ብቻውን ቢቆም ትርጉም
አይኖረውም፤ እንደሌሎ ቃላት አይረባም፡፡
ምሳሌ፡- - እሱ በዱላ መታኝ፡፡ የተሰረመረበት ፊደል መስተዋድድ ነው
o እሱ በወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ የተሠመረባቸው መስተዋድድ ናቸው፡፡

ተውሳከ ግሶችን በመጠቀም ዓ/ነገሮን መመስረት


በምሳሌው መሰረት ተውሳከግሶችን በመጠቀም ዓ/ነገሮችን መስርቱ፡፡

- ሁልገዜ
- አንዳንድ ጊዜ
- አልፎ አልፎ ትጠጣለች
- ሰሚራ
- ቶሎ
- ቸሩ - በፍጥነት ይጠጣል
- ከድር ና ለስላሳ
- በቀስታ ይጠጣሉ
- ቸርነት

ቸሩ ሁልጊዜ ለስላሳ ይጠጣል፡፡


ሰሚራ አንዳንድ ጊዜ ለስላሳ ትጠጣለች፡፡
ቸርነትና ከድር አልፎ አልፎ ለስላሳ ይጠጣሉ፡፡
ቀጥሎ ተውሳከ ግሳዊ ቃላትን በመጠቀም አምስት ዓ/ነገሮችን መስርቱ፡፡

1. ___________________________________________________ __________________

2. __________________________________________________________ ___________

3. ________________________________________________________________ _____

4. _____________________________________________________________________

5. _____________________________________________________________________

መናገር
በተሠጠ ርዕስ ተዘጋጅቶ ንግግር ማድረግ
የንግግር መመሪያ

ንግግር በቃልም ሆነ በፅሁፍ ሊቀርብ የሚችልና ሀሳብ አፍልቀን ለሌሎች


የምናስተላልፍበት ክሂል ሲሆን ከዝግጅት እስከ አቀራረብ ጥንቃቄ ይሻል፡፡

ሀ. የንግግር አዘገጃጀት መመሪያ

 የአድማጫችሁን እድሜውን፣የዕውቀት ደረጃው ወዘተ. ማወቅ፣የርእሱን ጥልቀት


መወሰን፣
 መረጃዎችን ከልዩ ልዩ ምንጮች ማሰባሰብ፣
 ካሰባሰብናቸው መረጃዎ ውስጥ ለንግግራችሁ ርእስ ይመጥናሉ የምትሷቸው ነጥቦች
መርጣችሁ መያዝ፣
 በጊዜና በቦታ ቅደም ተከተል ማደራጀት፣
 ፍሬ ሀሳቦን በአሃዝ ከፋፍሎ ለመለየት በሚያስችል መልክ ማደራጀት፣
ለ. የንግግር አቀራረብ መመሪ
 ለአድማጮች ንግግራችን በተገቢው ማቅረብ፣
 ንግግር በማቅረብ ሂደት ውስጥ የአድማጮችን ሁኔታ በዓይን በመቃኘት የንግግሩን
አቀራረብም ማራኪ እዲሆን መጣር፣
 በንግግር ማቅረብ ሂደት የመግቢ፣የዝዝርና ማጠቃለያ ሀሳብ እንዴት ያለ አቀራረብ
ሊኖረው እንደሚገባ አስታውሶ መተግበር፣
‹‹ የሕፃናት መብት ድንጋጌዎችና ተጨባጭ ሁኔታዎ›› በሚል ርዕስ ተዘጋጅታችሁ ንግገር
አድርጉ፡፡

ሰዋሰው

ጠቃሚ መስተአምር ፣ መስተፃምረና ወደረኛ መስተፃም

- ጠቃሚ መስተፃምመር በዓ/ነገር መዋቅር ውስጥ ከባለቤት ቀድሞ ሊመጣ ይችላል፡፡


ስለዚህ ጠቃሚ መስተኣም በዓ/ነገር ውስጥ ከተናጋሪ ጋር ያለውን ርቀት በማሳየት
የመቆም ተግባር አለው፡፡
ምሳሌ፡- እነዚያ ነርሶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓ/ነገር ውስጥ የተሠመረበት ጠቃሚ
መስተኣምር ይባላል፡፡

 መስተፃምር፡- መስተፃምር አንድን ዓ/ነገርን ግሱ እንዳያሳር አድርጎ ከሌላ ዓ/ነገር


ጋር እንዲጠጋ የሚያደርግ ነው፡፡
ምሳሌ፡- አበበ ከትምህርት ቤት መልስ ወደ ቤት ሄዶ ቤተሰቦቹን አገዘ፡፡
‹‹ሄዶ›› የሚለው መስተፃምር ነው፡፡

 ወደረኛ መስተፃምር ደግሞ ቃልን ከቃል፣ ሐረግን ከሐረግ፣ ዓ/ነገርን ከዓ/ነገር


ያያይዛል፡፡
ምሳሌ፡- አበበና ካሳ መፅሐፍ ማንበብ ይወዳሉ፡፡ የተሰመረበት ወደረኛ መዕተፃምር ነዉ፡፡

ቀጥሎ ጠቋሚ መስተፃምር የሚገኝባቸው አምስት ዓ/ነገሮች ፃፉ፡፡


1. ___________________________________________________ __________________

2. __________________________________________________________ ___________

3. ________________________________________________________________ _____

4. _____________________________________________________________________

5. _____________________________________________________________________
የህፃናት መብት
የቃላት ጥናት
መነጣጠልና መጣመር
ተግባር 1
- የሚከተሉትን ቃላት በመነጣጠልና በማጣመር አንብቡ፡፡
ነጣጥሎ ማንበብ አጣምሮ ማንበብ
ሀ እየ - ተደረገ - ል - ኣቸዉ እየተደረገላቸዉ
ለ መብት - ኦች -ኣቸዉ - ን መብቶቻቸዉን
ሐ ዓለም - አቀፍ - ኣዊ አለማቀፋዊ
መ ያ - አስ - ፈልግ - ኣቸዉ -ኣል ያስፈልጋቸዋል
ሠ ል -ዩ -አጋጥም -ኣቸዉ ሊያጋጥሟቸዉ
ረ ትምህርት - ቤት - ኦች - ን ትምህርት ቤቶችን
ሰ ልጅ - ኦች - አቸዉ -ን ልጆቻቸዉን
ሸ ህፃን - ኣት - ኣቸዉ - ን ልጆቻቸዉን
ቀ ይ - ፈፀም -ብ - ኣቸው -ኣል ይፈፀምባቸዋል

ሰዋሰው
ተውሳከ ግሶችን መለየት
ተግባር 2
በሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች ተውሳከ ግሶችን በመየት ፃፉ፡፡
ሀ. በቀለ አምና ሰባተኛ ክፈል ነበር፡፡
ለ. መሠረትና ሀዋ ነገወደ ኮምቦልቻ ይሄዳሉ፡፡
ሐ. ፈለቀች ሁል ጊዜ ስለህፃናት መብት ታስተምራለች፡፡
መ.መንግስቱ አልፎ አልፎ ወደ ጎንደር ይሄዳል፡፡
ሠ. ወይዘሮ እናኑ ትናንት ህፃናትን ለማነጋገር ፈልገው ነበር፡፡
ረ. ሀይሉ ቶሎ ቶሎ በመራመድ ካሰበው ቦታ ደረሰ፡፡
ሰ. ማህሌት አንዳንድ ጊዜ መዝሙር ትዘምራለች፡፡
ፈሊጣዊ አነጋገር

ፈሊጣዊ አነጋገር ሀሳብን ከተራ አገላለጥ ወጣ በማለት ሀሳብን ለየት ባለ፣በሚያመራምርና


ለዛ ባለው ሁኔታ የመናገር ወይም የመፃፍ ችሎታ ነው፡፡

ፈሊጥ ማለት የተለየ አነጋገር ወይም አገላለፅ ማለት ነው፡፡ ፈሊጣዊ አነጋገር እንደ
ምሳሌያዊ አነጋገሮች ማህበረሰባዊ መሰረት አላቸው፡፡ ፈሊጣዊ አነጋገር አብዛኛውን ጊዜ
ከአንድ እስከ ሶስት በሚደርሱ ቃላት ይዋቀራል፡፡ ነገር ግን ቃላቱ ቀድሞ ከነበራቸው
ቀጥተኛ ትርጉም የተለየ ፍቺ ይይዛሉ፡፡

ምሳሌ፡

1. ’’ ቀትረ ቀላል’’ ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ፍቺ ‹‹ ቀዥቃዣ ወይም ጥላቢስ›› የሚል


ነው፡፡
2. ’’ ሰለላ’’ ለሚለው ፈሊጣዊ ቃል ፍቺው ‹‹ የማይጠቅም፣የማይረባ፣ቀጭን ›› የሚል
ይሆናል፡፡

ተግባር 1

ከዚህ በታች ፈሊጣዊ ቃሎችና ሀረጎችን የሚያመለክቱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች


ቀርበዋል፡፡ ለእያንዳዱ ጥያቄ ተስማሚውን መልስ ምረጡ፡፡

1. ቅሌንጨርቄን አትበል
ሀ. አትስነፍ ለ. ወሬኛ አትሁን ሐ. ሰበብ አታብዛ መ. ነገር አታምጣ
2. ቤት ያፈራው ቀርቦለት ስላልመቸው ትቶት ሄደ፡፡ የተሠመረበት ትርጉም ምንድነው
ሀ. የተገኘውን ለ. የሌለውን ሐ. የጠፋውን መ. የከፋውን
3. እንዳንተ ሀሞተ ቢስ አላየሁም፡፡ ተመሳሳይ ፍቺ
ሀ. ፈሪ ለ. ሰነፍ ሐ. ቸልተኛ መ. ለስላሳ
4. ቤታቸው ኩታገጠም ነው፡፡ የተሠመረበት ተመሳሳይ ፍቹ፣
ሀ. ድንበርተኛ ለ. ሩቅ ለቁቅ ሐ. ማዶ ለማዶ መ. መጠነኛ
5. በነፍስ ወከፍ፣
ሀ. በግልፅ ለ. በተናጠል ሐ. በጥንድ መ. በጋራ
የክለሳ ጥያቄዎች
ለሚከተሉት ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊል ምረጡ፡
1. ’’ቆንቋና’’ የዚህ ቃል ተቃራኒ ፍቺ የሆነው የትኛው ነው
ሀ. ንፉግ ሐ. ስስታም
ለ. ቸር መ. መስጠት የማይወድ
2. ከሚከተሉት በትምህርተ ስላቅ(i) የቀረበ ሀሳብ የትኛው ነው?
ሀ. ብራቮ በጣም ደስ ይላል አቦ፡፡
ለ. በዚህ ሰዓት እዚህ ምን ትሰራለህ?
ሐ. የሰው ልጅ ምኞቱ ብዙ ነው፡፡
መ. ድንቄም አምሮብሽ ሞተሻል፡፡
3. በዘመናዊ ሰዋሰው የቃል ክፍሎች ስንት ናቸው
ሀ. 2 ለ. 3 ሐ. 4 መ. 5
4. በፍጥነት የቤት ስራውን ስለጨረሰ በትርፍ ሰዓቱ ተዝናና፡፡ የዚህ ዓ/ነገር ውስጥ
መስተፃምር የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. በትርፍ ለ. በፍጥነት ሐ. ስለጨረሰ መ. ተዝናና
5. ’’ ቀኝ እጅ’’ የዚህ ፈሊዊ አነጋገር ተመሳሳይ ፍቺ የትኛው ነው
ሀ. አለኝታ ለ. መከታ ሐ. ረዳት መ. ሁሉም
ምዕራፍ 8

የሴቶችን አቅም መገንባት


ስርዓተ ፆታና ትምህርት
የቃላት ጥናት
መነጣጠልና ማጣመር
ምዕላድ

ምዕላድ የምንለው ትርጉም አዘል የሆነና አነስተኛ ወደ ሆኑ ትርጉም አዘል ክፍሎች


ሊሸነሽን የማይችል የመጨረሻ ንዑስ አሀድ ነው፡፡ ‹‹ልብ›› የሚለውን ቃል ወስደን በምሳሌ
እንመልከት፡፡ ‹‹ ልብ›› በመጀመሪያ ትርጉም ያለው (አንድ የሰውነት ክፍልን
የሚያመለክት አሀድ ነው፡፡ ሁለተኛው ይህ አሀድ ወደ አነስተኛ ትርጉም አዘል ክፍች
ሊከፈል አይችልም፡፡ ስለዚህ እንደ ‹‹ ልብ›› የመሳሰሉት ምዕላዶች ራሳቸውን ችለው
ስለሚቆሙ ነፃ ምዕላድ ሲባሉ፣ ጥገኛ ምዕላዶች ደግሞ ‹‹ ልባችን;; በዚህ ቃል ውስጥ ያለው
‹‹-ኣችን›› የሚለው ነው፡፡

ውስብስብ ቃላትን በመነጣጠልና በማጣመር ማንበር

ተግባር 1
የሚከተሉትን ቃላት በመጀመሪ ነጣጥላችሁ፣በመቀጠልም የመድረሻ ጥያዎችን
ብቻ አንብቡ፡፡
ነጣጥሎ ማንበብር መድረሻ ቅጥያቸውን ማንበብ
ሀ. ይድረስ-ብ-ኣችው-ኣል -ኣል

ለ. ይቀንስ- ብ-ኣት-ኣል -ኣል

ሐ. ይኖር-ብ-ኸ-ኣል -ኣል

መ. ያግዝ-ኣችሁ-ኣል -ኣል
አስተውሉ፡- በዋና ቃል ውስጥ ቅጥያዎች በቃሉ በሶስት ቦታ ላይ ሊገኝ ይችላል፡፡
ይኸውም በቃል መነሻ፣በመሀል እና በመድረሻ ላይ ማለት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ‹‹ አልመጣም›› በሚለው ቃል ላይ ‹‹አል-›› መነሻ ቅጥያ ‹‹መጣ›› ዋና ቃል ‹‹-
ም›› ደግሞ መድረሻ ቅጥያ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ በቃሉ መካከል ላይ ይገኛል፡፡
ምሳሌ፡- ‹‹ አጫጭር›› በዚህ ቃል ላይ ደግሞ ‹‹ አጭር›› ዋና ቃል ሲሆን ‹‹-ጫ-›› ደግሞ
የመሀል (የውስጠ ግንድ) ቅጥያ ይባላል፡፡
 በተጨማሪም ምዕላዶች የእርባታ የምስታ በሚል በሁለት ይከፈላሉ፡፡
 የእርባታ ምዕላድ የሚባለው ቅጥያው በዋና ቃል ላይ ሲከሰት የቃሉን የቃል ክፍል
አይቀይርም፡፡
ምሳሌ፡- ‹‹ ቤት ›› እና ‹‹-ኦች›› ሲጣመሩ ‹‹ ቤቶች›› የሚል ይሆናል፤ በዚህ ቃል ውስጥ
‹‹-ኦች›› የሚለው አብዢ ምዕላድ ‹‹ ቤት›› በሚለው ነፃ ምዕላድ ላይ ሲመጣ የዋናውን
ቃል የቃል ክፍ ከስም ወደ ሌላ አልቀየረውም ነገር ግን አርብቶታል (ብዙ)
አድርጎታል፡፡
 ሁለተኛ ደግሞ የምስረታ ምዕላድ ነው፤ ይህ ደግሞ በዋና (በነፃ ምዕላድ) ወይም
ትርጉም ባላቸው ቃላት ላይ የሚከሰቱበት ጊዜ የነፃ ምዕላዱን የቃል ክፈል ከነበረበት
ወደ ሌላ የቃል ክፈል ይቀይራሉ፡፡
ምሳሌ፡- ‹‹ ልብ›› የሚለው ነፃ ምዕላድ ሲሆን ‹‹ -ኣም›› የሚለው ጥገኛ ምዕላድ
ሲጨመርበት ‹‹ ልባም ›› የሚል ይሆናል፤ ስለዚህ‹‹ ልብ›› የሚለው ነፃ ምዕላድ የቃል
ክፍሉ ስም ሲሆን‹‹ ልባም›› ደግሞ የቃል ክፍሉ ቅፅል ነው፤ ስለዚህ ከነበረበት የቃል
ክፍል ወደሌላ ክፍል ስለተለወጠ የምስረታ ምዕላድ እንለዋለን፡፡

ተግባር 2

የሚከተሉትን ከላይ በቀረበው ምሳሌ መሰረት የእርባታ ወይም የምስረታ


መሆናቸውን አብራርታችሁ ግለፁ፡፡

ዋና ቃል ቅጥያ ሲጣመር
ሀ. ተራራ -ኣማ _________________________
ለ. ሰማዩ -ኣዊ _________________________
ሐ. ልጅ -ኦች _________________________
መ. ጦስ -እኛ _________________________
ሠ. ትዕቢት - እኛ _________________________

መናገር
ሀሳብን በመደገፍ / በመቃወም መከራከር
ክርክር
- ክርክር በሁለት ሰዎ(ቡድኖች)መካከል ዳኛ እና ሊቀመንበር በመሰየም የሚቀርብ
ስርዓት ያለው ሙግት ነው፡፡

ሀ. የክርክር አዘገጃጀት መመሪያ


 ርዕስ መምረጥ፣ከተመረጠ ደግሞ ርዕሱን በሚመለከት ከጽሑፎች ወዘተ ሀሳብ ማሰባሰብ፣
 ከተሰበሰቡት መረጃዎች ጠቃሚዎቹን ለይቶና በቅደም ተከተል አስተካክሎ መያዝ
 ክርክር ከመደረጉ በፊት በቂ ልምምድ ማድረግ፣
 ከክርክሩ በፊት አለባበስና ፣ሰ፤ ነገሮችን ማስተካከል

ለ. የክርክር አቀራረብ መመሪ


 በክርክሩ መግቢያ ላይ ሰላምታ በመስጠት ርዕስን ለአድማጭ ማስተዋወቅ
 የክርክን ፍሬ ሀሳቦችን በቅደመም ተከተል ማቅረብ
 ክርክሩን ረጋ ባለና በልበ ሙሉነት ማቅረብ
 ተቃዋሚ የሚሰነዝረውን ሀሳብ በማስታወሻ በመያዝ ተገቢ ምላሽ መስጠት
 ለተከራካሪ፣ለአድማጭና ለዳኛ ተገቢውን አክብት መስጠት፣
 ክረክሩ ሲያበቃ ታዳሚዎችን አመስግኖ መሰናበት
 የዳኛን ውጤት በፀጋ መቀበል

ተግባር 1

ስርዓተ ፆዊ የስራ ክፍፍልን በመደገፍና በመቃወም ተከራከሩ፡፡


ሰዋስው
ጊዜ
ጊዜ፡- አንድ ድርጊት መቼ እንደተፈፀመ ወይም እንደሚፈፀም የሚገልፅ የግስ ባህሪ
ነው፡፡ ጊዜ በሶስት ይከፈላል፡፡ ክፍሎቹም የአሁን፣የኃላፊና የትንቢት ጊዜ ይባላሉ፡፡
1. የአሁን ጊዜ የሚባለው ድርጊቱ በሚከናወንበት ጊዜ ያለውን ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ደብዳቤ እየፃፈ ነው፡፡
2. የኃላ ጊዜ ድርጊቱ ተፈፅሞ ያለቀ መሆኑን ያመለክታል፡፡
ምሳሌ፡- መኪና ገዛ
3. የትንቢት ጊዜ ደግሞ ገና ያልተፈፀመና ወደ ፊት የሚፈፀም መሆኑን ይገልፃል
ምሳ፡- መሀመደም ነገ ወደ አዲስ አበባ ይሄዳል፡፡

የቅርብ ሀላፊ ጊዜና የሩቅ ሃላፊ ጊዜ


ተግ ር 1
የሚከተሉትን ጥንድ ቃላት በምሳሌው መሰረት በማርባት ፃፉ፡
ምሳሌ፡-
ሀ ለ
1. ይኖራል  ኖሯል
ይኖር ነበር  ኖሮ ነበር
2. ይፈልጋል  ፈልጓል
ይፈልግ ነበር  ፈልጎ ነበር
ሀ. ያገለግላል  _________________________
ያገለግል ነበር  _________________________
ለ. ይቀንሳል  _________________________
ይቀንስ ነበር  _________________________
ሐ. ይመክል  _________________________
ይመክር ነበር  _________________________
በቃላት ውስጥ የድምፆች መጥበቅና መላላት
በአማርኛ ጠባቂ ድምፆች የሚገኙት በቃል መሃከልና አልፎ አልፎ ደግሞ በቃል መጨረሻ
ላይ ነው፡፡ በቃል መጀመሪያ ላይ ያለ ድምፅ ጠበቆ አይነበብም፡፡ ለምሳሌ፡- ‹‹አጠና››
በዚህ ቃል ውስጥ ጠብቆና ላልቶ የሚነበበው ‹‹ጠ›› ነው

‹‹ጠ›› ጠብቆ ሲነበብ‹‹አነበበ፣ተገነዘ›› የሚል ትርጉም ሲኖረው ‹‹ ጠ›› ላልቶ ሲነበብ ደግሞ
‹‹ የእንጨት፣የእፅዋት አይነት›› የሚል ትርጉም አለው፡፡

ተግባር 1

የሚከተሉትን ቃላት ፊደሎች ሲጠብቁና ሲላሉ የሚኖራቸው የፍቺ ልዩነት


በምሳሌው መሰረት በዓ/ነገር አሳዩ፡፡

ምሳሌ፡- አደራ፡፡
ሲጠብቅ  ዓለማየሁ ድሩን አደራ

ሲላላ  ዓለማየሁ እህቱን አደራ አላት፡፡

ሀ. ባላት

ለ. ቁጥር

ሐ. መዳር

መ. በርካታ

ሠ. ነፃ

ረ. እንዳሉ
መፃፍ

ድርሰት መፃፍ

በማወዳደርና በማነፃፀር ስልት ድርሰት መፃፍ


ማወዳድ፡- በሁለት ተመሳሳይ ነገሮች መካከል ያለውን አንድነት ወይም ተመሳስሎ
መግለፅ ዳደር ሲባል ማነፃፀር ደግሞ በሁለት ተመሳሳይ ነገሮች መካከል ያለን ልዩነት
መግለፅ ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በበግና በፍየል መካከል አንድነትና ልዩነትን መግለፅ ማወዳደርና ማነፃፀር
ይባላል፡፡
ተግባር 1
- ቀጥሎ ‹‹ምዕራባውያንና ኢትዮጵያውያን እናቶች›› በሚል ርዕስ ቢጋር ወይም
አስተዋፅኦ በማዘጋጀት ከስርዓት ጾታ አንፃር በማወዳድና በማነፃፀር ስልት ድሰት ፃፉ፡፡

የክለሳ ጥያቄዎች
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ፃፉ፡፡
1. ምዕላድ ምንድ ነው?
2. የእርባታና የምስረታ ምዕላዶችን ምንነት ግለፁ፡፡
3. የክርክር ፅንሸ ኀሻብ ምንድ ነው እንዴት ይተገበራል?
4. ጊዜ ማለት ምንድነው በስንት ይመደባል?
5. ጠባቂ ድምፆችን በቃል ውስጥ እንዴት ለይተን እንገልፃለን?
6. ማወዳደርና ማነፃፀር ማለት ምን ማለት ነው?
ምዕራፍ 9
የአየር ንብረት
የአየር ንብረት ለውጥ

መፃፍ
ድርሰት መፃፍ
በምክንያትና በውጤት ስልክ ድርሰት መፃፍ ምክንያትና ውጤት
የአንድን ነገር ውጤት ከሱ በፊት በሚኖር ምክንያት ወይም መንስኤ ላይ የተመሰረተ
ነው፡፡ ተናጋረው ወይም ፀሐፊ ብዙውን ጊዜ የአንድን ነገር ውጤት ከምክንያቱ ጋር አብሮ
የሚገልፅበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ የምክንያትና ውጤት ግንኙነትን ስንመረምር አንድ
ምክንያት ብዙ ውጤቶን ሊያስገኝ ይችላል፡፡ ብዙ ምክንያቶችም እንዲሁ አንድ ውጤት
የሚስገኙበት ሁኔታ አለ፡፡በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ምክንያት ውጤትን ሊስገኝ፣በተገኘው
ውጤትና ለውጤቱ መገኘት ምክንያት በሆነው ነገር መካከልም ጥብቅ የሆነ ተጠያቂ
ግንኙነት አለ፡፡
ምሳሌ፡-
የኃይል እጥረት ለደኖች መመናመን ዋነኛ መንስኤ እየሆነ መጥቷል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል
ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ህዝቡ ደንን እየጨፈጨፈ ለማገዶነት ያውላል፡፡ የደኖች
በጨፍጨፍ መመናመን ደግሞ የአየር ንብረት መዛባትን ያስከትላል፡፡ በዚህ የተነሳ በቂ
የዝናብ መጠን ተገኝቶ በሰዎች፣ በእንስሳትና በሰብሎች ላይ ትልቅ ጉዳት ሊያደርስ
ይችላል፡፡ በዚህ አንቀፅ ውስጥ የተገኘውን የመንስኤና ውጤት ትስስር እንደሚከተለው
መለየት ይቻላል፡፡
ምክንያት ውጤት
- የሀይል እጥረት - የደኖች መመናመን
- የደኖች መጨፍጭፍ - የአየፍ ንብረት መዛባት
- በቂ ዝናብ አለመኖር ወይም - የሰዎች፣የእንስሳትና የሰብሎች ጉዳት
ከሚጠበቀው በላይ

ተግባር 1
የሚከተለውን የቢጋር ሰንጠረዥ መሰረት በማድረግ ‹‹ ሰው ሰራሽ የአየር ንብረት ለውጥና
ምክንያቶች ውጤቶች›› በሚል ርዕስ በምክንያትና ውጤት ስልት ደርሰት ፃፉ፡፡
-የደኖ -በከባቢ አየር የካርቦን የበረዶ መቅለጥ -የአየር ንብረት ለውጥ
መጨፍጨፍ፣ ሙቀት
ዳይ ኦክሳይድ መጠን የውቅያኖሶች -ያልተጠበቀ ዝናብና
-የኢንዱስትሪዎችና መጨመር
መጨመር ከፍታ መጨመር ፎርግ
--የተሸከርካሪዎች -የጋዞች ይሰት ምጥጥን የውሃ ትነት -የመሬት መጥለቅለቅ
ልቀት…. መዛባት መጠን መጨመር

ሰዋስው
የዓ/ነገር አይነቶች
ዓ/ነገር ማለት በስርዓተ ተቀነባብሪ ሙሉ ስሜትን ሊሰጥ የሚችል የቃላት ወይም የሐረጋት
ስብስብ ነው፡፡ ዓ/ነገሮች ነጠላ ዓ/ነገር እና ድርብ ዓ/ነገር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

1. ነጠላ(ተራ) ኣ/ነገር፡- ከአንድ ስማዊ ሀረግና ከአንድ ግሳዊ ሐረግ ብቻ ይዋቀራል፡፡

ምሳሌ፡- ታፈሰ ሳር አጨደ፡፡


ስማዊ ሀረግ ግሳዊ ሀረግ
2. ድርብ (ውስብስብ)ዓ/ነገር ፡- ይህ ኣ/ነገር ከአንድ በላይ ማሰሪ አንቀፅ የያዘ ዓ/ነገር
ነው፡፡ ዋናው መለያው በውስጡ የያዘው የግስ መጠን ነው፡፡
ምሳሌ፡- ሀ. ልጁ ምሳውን በላ፡፡
ለ. ልጁ ወደ ት/ቤት ሄደ፡፡
እነዚህን ዓ/ነገሮች በማጣመር ወደ ድርብ(ውስብስብ) ዓ/ነገር መለወጥ ይቻላል፡፡
ምሳሌ፡- ሀ. ልጁ ምሳውን በልቶ ወደ ት/ቤት ሄደ፡፡
ለ. ልጁ ምሳውን እንደባ ወደ ት/ቤት ሄደ፡፡
ተግባር 1
የሚከተሉትን ጥገኛ ሐረጎች ከሚስማሟቸው ነጠላ ዓ/ነገሮች ጋር በማቀናጀት
የተስፋፋ ዓ/ነገሮችን ፃፉ፡፡
ጥገኛ ሐረጎች ነጠላ ዓ/ነገሮች
1. የአየር ንብረት ከተለወጠ ሀ. በሌሎች አካባቢዎ ዝናብ በመቀነሱ
2. የመሬት በአንድ ጆኦሎጂካዊ ድርቅ ይከሰታል፡፡
ዘመን ቅዝቃሴ ሲያኮማትራ ለ. የጎርፍ ማጥለቅለቅን ያስከትላሉ፡፡
3. አንዳንድ ነባር ዘሮች ከአዲስ ሐ. የተለያዩ ጉዳ ያደርሳል፡፡
የአየር ንብረት ጋር ለማስማማት መ.ሌሎች ነባር ዘሮች ግን ጠፍተዋል፡፡
የቅርፅና ይዘት ለውጥ ሲያደርጉ ሠ. በሌላ ጂኦሎጂካዊ መን ሙቀት
4. በአንዳንደን አካባቢዎች የውሃ ያነዳታል፡፡
ማጥለቅለቅ ሲደርሲ
5. በረዶዎች በመቅለጥ ከከባህሮች
ከተቀላቀሉ

ስማዊ ሐረጎችን በመሙያት መጠቀም


ስምን (ስማዊ ሀረግን) በመሙያነት የሚወስዱ የመሆን ግሶች ናቸው፡፡
ምሳሌ፡- እነዚያ ተማሪዎች ናቸው፡ ‹‹ ተማዎች›› የሚለው ስም ለመሆን ግስ መሙያነው፤
የመሆን ግሱ ደግሞ ‹‹ናቸው›› የሚለው ነው፡፡

ተግባር 2
ስማዊ ሐረጎችን በመሙያነት በመጠቀም አምስት አረፍተነገሮች በምሳሌው
መሰረት መስርቱ፡፡
6. ___________________________________________________ __________________

7. __________________________________________________________ ___________

8. ________________________________________________________________ _____

9. _____________________________________________________________________

10. _____________________________________________________________________
ተግባር 3
ጥገኛ ሐረጎችንና ስማዊ ሐረጎችን መለየት
ከሚከተሉት ዓ/ነገሮች ውስጥ ጥገኛ ሐረጎችንና እንደመሙያ ያገለገሉ ስማዊ
ሐረጎችን ለይታችሁ ፃፉ፡፡
ምሳሌ፡- ደን ስለተጨፈጨፈ የአየር ንብረት ተለውጧል፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- ደን ስለተጨፈጨፈ፤
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- የአየር ንብረት
ሀ. የአየር ንብረት ሲለወጥ የውሃ አካላት መጠን ይቀንሳል፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- _______________________________________
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- _______________________________________
ለ. የዓለምን ከፍተኛ አካል የያዙ የውሃ አካላት ናቸው፡፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- _______________________________________
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- _______________________________________
ሐ. የላይኛው የአፈር ክፍል በጎርፍ ከተጠረገ የምርታማነት ይቀንሳል፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- _______________________________________
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- _______________________________________
መ. ለከባቢ አየር መለወጥ የሚጠየቁት የበለፀጉ አገሮች ናቸው፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- _______________________________________
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- _______________________________________
ሠ. ይቺ ዛፍ ትንሽ ችግኝ ነበረች፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- _______________________________________
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- _______________________________________
ረ. ዛፎች ሊቆረጡ ካርቦን ወደ ከባቢ አየር ይለቀቃል፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- _______________________________________
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- _______________________________________
ሰ. ደን ሲለማ የአካባቢ ውበት ይጠበቃል፡፡
ጥገኛ ሐረገ፡- _______________________________________
እንደ መሙያ ያገለገለ ስማዊ ሐረጉ፡- _______________________________________
ተመሳሳይ ቃላት
ተመሳሳይ ፍቺ ማለት አንድ ቃል ሲታሰብ ተመሳሳይ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ
ቃላትን በመፈለግ የቀረበውን ቃል በመምረጥ መተርጎም ማለት ነው፡፡ ተመሳሳይ ሲባል
አንፃራዊ ተዛምዶ ያላቸውን ሀሳቦች የሚወክሉ ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-
ሀሩር ፡- ከፍተኛ የፀሐይ ሙቅት ማለት ነው፡፡
- የፀሐይዋ ሙቀት ከፍተኛ ነው፡፡

ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ለቀረቡት ቃላት ፍቺ በመስጠት በፍቺቸው ዓ/ነገር


መስርቱ፡፡

ተመሳሳይ
ተ.ቁ ቃል በተመሳሳይ ፍቺ የተመሰረተ
ፍቺ
አንዳንድ ቦታዎች ላይ ተላላፊ በሽታ
ሀ መስፋፋት መሰራጨት
በፍጥነት መሰራጨት ጀምሯል፡፡
ለ ለመግታት
ሐ መላቀቅ
መ መኖሪያ
ሠ ክምችት
ረ ምንጭ
ሰ በሚቀጣጠለው

የክለሳ ጥያቄዎች
ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ግለፁ፡፡
1. ስለምክንያትና ውጤት ምንነት አብራሩ፡፡
2. የዓ/ነገር አይነቶች ስንት ናቸው? ስማቸውን ፃፉ፡፡
3. ስለመሆን ግሶች እና ስማዊ ሐረጎችን እንደመሙያ የሚሉ ነጥቦችን አብራሩ፡፡
4. የቃላት ተመሳሳይ ፍቺ ማለት ምን ማለት ነው?
ምዕራፍ 10
ተውኔት
የተውኔት አላባውያት
የተውኔት አላባውያን የሚባሉት ገፀባህሪያት፣ ታሪክ፣ ትልም፣ ግጭት፣ ጭብጥና መቼት
ናቸው፡፡
ሀ. ገፀባህሪያት፡-
በአንነድ ተውኔት ውስጥ በፀሐፌ-ተውኔቱ የሚፈጠሩና በተፈጠሩበት ተውኔት ውስጥ
የሚያከናውኑት የስራ ድርሻ ያላቸው፣በገዓዱ ዓለም ሰውን መስለውና ሰውን ወክለው
እንደሰው በማናገርና የተለያዩ ተግባራን በመፈፀም የሚገለግሉ ናቸው፡፡ ገፀባህሪት
የሚናገሯቸው ሆነ የሚፈፅሟቸው ድርጊቶች ለአንባቢያን ሆነ ለተመልካቾች ሙሉ በሙሉ
ግልፅ ናቸው፡፡
ለ. ታሪክ፡-
በአንድ ተውኔት ውስጥ በንግግርም ሆነ በገፀባህሪት በድርጊት የሚከናወነው የአንድ
ተውኔት ታሪክ ነው፡፡ የተውኔት ታሪክ ሌሎችን አላባውያን ይይዛል ማለት ነው፡፡
ገፀባህሪት፣መቼት፣ትልምና ግጭት የሚፈጠሩት በአንድ ተውኔት ታሪክ ውስጥ ነው፡፡
ሐ. ትልም
ትልም ሌላው የተውኔት አላባ ነው፡፡ ገፀባህሪያት የሚፈፅሟቸው ድርጊቶች ምክንያትና
ውጤትን ተከትለው የሚካሄዱ እንደመሆናቸው፣ትልም በተውኔት ውስጥ የሚካሄዱትን
ነገሮች ምክንያትና ውጤት ያሳያል፡፡
መ. ግጭት
ግጭት በአንድ ተውኔት ውስጥ የሚገኘው ሌላው አላባ ግጭት ነው፡፡ በአንድ ተውኔት
ውስጥ ገፀባህሪት በሚያራምዱት ተግባር (በሚከናውኑት)ታሪክ እርስ በእርሳቸው ወይም ይን
ላድረግ ወይስ አላድርግ በሚል ከራሳቸው ጋር ይጋጫሉ፡፡ ማንኛውም የተውኔት ታሪክ
ያለግጭት ሊፈጠር አይችልም፡፡ ያለግጭት የሚፈጠር ታሪክ ተራ ታሪክ እንጂ የተውኔት
ታሪክ አይሆንም፡፡
ሠ. ጭብጥ
ጭብጥ ደራሰው በህብረተሰቡ ውስጥ ያየውን፣የታዘበውን፣የተገነዘበውን ማህበራዊ ጉዳይ
በማንሳት አመለካከቱን፣እውቀቱን መሰረት አድርጎ በተውኔቱ አንድ መልዕክት
ያስተላልፋል፡፡ ይህ ደራሲው እንዲተላለፍ የፈለገው ፍሬ ነገር ጭብጥ ይባላል፡፡
ጭብጥን ለይቶ ለማውጣትና ለመገንዘብ ከባድ ነው፡፡ በአንድ ቦታ ወይም አንቀፅ ላይ
ቁጭ ብሎ አናገኘውም፡፡ አንባቢ ታሪኩን አንብቦ ሲጨርስ በታሪኩ ከቀረቡ የተለያዩ የገፀ
ባህሪያት ንግግሮች መነሻነት ጭብጡን ፈልቅቆ ሊወጣና ሊገነዘብ ይችላል፡፡
ረ. መቼት
መቼት፡- ይህ አላባ የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፡፡ ቃላቱም
‹‹መቼ›› ‹‹የት›› የሚባሉት ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት የተውኔት መቼ ሲባል ታሪኩ
የተፈፀመበት ዘመንና ቦታ ማለት ነው፡፡

የአፃፃፍ ስርዓት
ስርዓተ ነጥቦችን በተገቢ ቦታ መጠቀም
የሚከተሉት ዓ/ነገሮች የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም ችግሮች አሉባቸው፡፡ ችግሮቹን
በመለየት ስርዓተ ነጥቦችን አስተካክላችሁ ዓ/ነገሮቹን እንደገና ፃፏቸው፡፡
ሀ. የተውኔት አላባውያን ገፀባህሪት ታሪክ መቼት ትልም(ምክንያት ውጤትና ግጭት ናቸው
ለ. ወይዘሮ ሐመልማል የታደሰ መኝታ ክፍል ተከፍቶ ሲያዩት ታደሰ እንደምን ዋልክ ልጄ
የት ጠፍተህ ውለህ ነው አሉ ወደ ውስጥ ገባ እያሉ፡፡
ሐ. ገፀባህሪያት ማለት ምን ማለት ነው?
መ. ዕድሜ ይስጥልን ለወደፊት እንደርስበታለን ደህና ይዋሉ አቶ ቦጋለ በማለት አቶ አየለ
ተሰናበቷቸው፡፡
ሠ. አልማዝ ከትምህት ቤት ውስጥ ታዋቂ ተዋናይ ናት፡፡
ረ. የተውኔት ፀሐፊ ፀሐፊ-ተውኔት በመባል ይታወቃል፡፡
ሰ. ጥሩተዋናይን ለመምረጥ የሚከተሉትን መስፈርቶች አስፈላጊ ናቸው፡፡
እነርሱም፡- የንግግር ችሎቻ
የማስታወስ ችሎታ
የማንበብ ችሎታ
የትወና ችሎታ
የመግባባት ችሎታ ናቸው፡፡

አንብቦ መረዳት
የሚነበቡት ወይም ለማንበብ የሚመረጡት የፅሁፍ አይነቶች የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለሆነም
የፅሁፉ አይት ተስማሚ የሆነ የአንብቦ መረዳት ስልቶችን ቀጥሎ እንመለከታል፡፡

የንባብ ስልቶች(አይነቶች)
ሀ. በገረፍታ የማንበብ ስልት
የደብዳቤ፣ የማስታወቂያ፣ የዜና ወይም የርዕስ አንቀፅ ሀተታ፣ የስራ መመሪ፣ ማሳሰቢ፣ወዘተ
ፅሁፎችን በቀላሉ አንብቦ መረዳት ይቻላል፡፡ ከእንደዚህ አይነቶች ፅሁፎ በአንድ ጊጊ
የንባብ ፍጥነት ዋና ዋና ሀሳቦን ወይም የሚፈለገውን ጉዳይ ለይቶ መረዳት አያዳግትም፡፡

የአሰሳ ንባብ
በዚህ የንባብ ስልት የህይወት ታሪክ ዘገባዎች፣ተረቶች፣ልቦለድ ፅሁፎች የመሳሰሉትን
የማናነብበት ስልት ከላይኛው ይለያል፡፡ በእነዚህ አይነት ምንባቦች እምብዛም በጥልቀት
ማንበብና መመራመርን አይጠይቅም፡፡ ሆኖም ዋና ዋና ሀሳቦችና ዝርዝር መረጃዎችን
ለመለየት ተመልሶ ማሰስ መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ ስለሆነም ከፍጥነት ጋር የአሰሳ የንባ
ስልት በመጠቀም በትክል አንብቦ መረዳት ያስፈለልጋል፡፡
በጥልቀት የማንበብ ስልት(የዝግታ ንባብ)
በትኩረትና በተደጋጋሚ መነበብ የሚሹ የፅሁፍ አይነቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ፡- የትምህርት
ይዘቶች፣የአዳዲስ ንድፈ ሀሳቦች፣የፍልስፍና፣የታሪክ፣የምርም ፅሁፎ፣ረጃጅም ግጥሞች ወዘተ.
በገረፍታ የንባብ ስልት ጭብጦችን ወይም ተፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፍጥነት ማግኘት
ያዳግታል፡፡ በመሆኑም የንባብ ስልቱ የጥልቀት ወይም የትኩረት ንባብ ዘዴን የተከተለ
ለመሆን ይርበታል፡፡ ይህም ደጋግመን ማንበብ ይጠይቃል፡፡

በፍጥነት የማንበብ ስልት


ይህ የንባብ ስልት የንባብ ችሎታችንን(ክፍላችንን) ለማሻሻል የምናነብበት ሂደት ነው፡፡
ስለዚህ በዚህ ስልት በዋናነት የፅሁፉን ዋናና ዝርዝር ሀሳቦ መለየጥ ወይም በመገንዘብ ሳይ
ቃል በቃል፣ሐረግ ከሐረግ፣ዓ/ነገር ከዓ/ነገር ጋር በማያያዝ የንባብ ችሎታን ማሻሻል ነው፡፡
በመሆኑም በፅሁፉ ላይ በጣ እየተረማመዱ ቶሎ ቶሎ ማንበብ ይጠይቃል፡፡

ቅኔ
ቅኔ በቃልም ወይም በፅሁፍ በግጥም ወይም በዝርወ የሚነገር ወይም የሚፃፍ ድርሰት
ነው፡፡ ቅኔ መቀኘት ማለት አመራማሪ የሆነ የተደበቀ ነገር ያለው ግጥም መግጠም፣ሀሳብን
አመራማሪ (ምስጢት) አድርጎ ማቅረብ ማለት ነው፡፡ ቅኔ በግጥም ሲቀርብ አደራደሩ
ወይም የምጣኔ ማሳያ ምቱ ምንም ሳይዛነፍ ዜማውን ጠብቆ ቅርፅና ይዘቱ አስማምቶ
ከቀረበ ውበቱ በቀላሉ ይታያል፡፡ አንባቢን ወይም ቅኔ ፈቺውን ይስባል፡፡
ቅኔ የሚነገረው ወይም የሚፃፈው በሰምና ወርቅ ነው፡፡ ‹‹ ሰሙ›› ደራሲው ሊናገረው
ያሰበው ነገር የተሸፈነበት መጋረጃ ሲሆን፣ወርቁ ደግሞ አንድን ቃል ወይም ሐረግ
በማጥበቅና በማሳሳት ወይም አጠገቡ ካለው ከሌላ ቃል ጋር አያይዞ በማንበብና
በመመርመር የሚገኘው ምስጢር ወይም ፍሬነገር ነው፡፡
ቅኔው የተመሰረተበት ቃል ህብረቃል ይባል፡፡ ህብረቃሉ በፍቺ በሁለት ቦታ ተከፍሎ
አገባባዊ ትርጉም ሰም፣ ከአገባብ ውጪ የሆነው ፍቺ ደግሞ ወርቅ ይባላል፡፡ በዚህ መሰረት
የሚከተሉትን ቅኔዎች በምሳሌነት መመልከት አስፈላጊ ነው፡፡
ምሳሌ፡- ምነው ጌታዬ በደልከኝ፣
አጥፍቼም እደሁ ሳትመክረኝ፣
በሰው ፊት ቀጣኸኝ፡፡
ህብረ-ቃል፡- በሰው ፊት
ሰም፡- ሰው እያየ
ወርቅ፡- የሰው ፊት እንዳይ፣እንድለምን ወይም ተረጂ እንድሆን አደረከኝ፡፡
ተግባር 1
ቀጥሎ የቀረቡትን ቅኔዎች ህብረ-ቃል፣ ሰሙንና ወርቁን ከላይ በቀረበው
ምሳሌ መሰረት ፃፉ፡፡
ሀ. እዚያ ማዶ ሆና ትጣራለች እና፣
ናብላ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት የላት፡፡
ለ. ላሞቹ ደረቁ ጥጆቹ አብረው ዋሉ፣
አሁን የት ይገኛል ወተት ወተት ቢሉ፡፡
ሐ. እኛስ ሄደን ነበር ደህና አገር መስሎን፣
ተመልሰን መጣን ጉጉት በዝቶብን፡፡
መ. ሁልጊዜ በአሬራ ትበያለሽ ወይ፣
ምነው አንዳንድ ቀን ወጥ አትዪም ወይ፡፡
ሠ. እንሂድ እዛ ማዶ ፀሐይ የወጣበት፣
እነ እሜቴ መንደር ገና ጥላ አለበት፡፡

የግጥም አይነቶች
በአማርኛ ግጥም ውስጥ የሚዘተሩና የሚታወቁት የግጥም አይነቶች የወል ግጥም፣ሰንጎ
መገን ግጥ፣ ቡሄ በሉ ግጥም እና ድብልቅ ግጥም የሚባሉት ናቸው፡፡
1. የወልግጥም
የወልግጥም በሀረግ 6 ቀሰሞችን በስንኝ ደግሞ 12 ቀለሞችን በመጠቀም የሚደርስ
የግጥም አይነት ነው፡፡
ምሳሌ፡- አንቺ ብርድ ፈሪ/ክረምት አይወድልሽም፣በሀረፍ 6/6 ፣በስንኝ 12
ግቢ ከሆዴ ውስጥ መስከረም ይንጋልሽ፡፡
2. የሰንጎመገን ግጥም
የሰንጎ መገን ግጥም በሐረግ 5 በስንኝ 10 ቀለማትን በመጠቀም የሚደርስ ግጥም አይት
ነው፡፡
ምሳሌ፡- ውረድ እንውረድ ተባባሉና፣
አስደበደቡት አፈፉ ቆመና፡፡
3. የቡሄ በሉ ግጥም
የቡሄ ግጥም በሀረግ 4 በስንኝ ደግሞ 8 ቀለማትን የሚዝ የግጥም አይነት ነው፡፡
ምሳሌ ፡- እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል፣
አጋፋሪ ይደግሳል፡፡
4. ድብልቅ ግጥም
ከላይ የተጠቀሱት የስንኝ እና የሐረግ አይነቶች በግጥሞች ውስጥ ተደባልቀው ሲገኙ
የግጥሙ አይነት ድብልቅ ግጥም ይባላል፡፡
የክለሳ ጥያቄዎች
ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን
መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡

1. በልቦለድ ውስጥ እንዲተላለፍ የተፈለገው ዋና ፍሬ ነገር ምን ይባላል፡፡


ሀ. ትልም ለ. ግጭት ሐ. ጭብጥ መ. ገፀባህሪ
2. ዘመንና ቦታን የሚገልፅ የሁለት ቃላት ጥምረት ያለው የተውኔት አላባ የሆነው
የትኛው ነው
ሀ. ታሪክ ለ. ጭብጥ ሐ. ግጭት መ. መቼት
3. የንባብ አይቶች ስንት ናቸው
ሀ. 2 ለ. 4 ሐ. 3 መ. 5
4. ቅኔ የተመሰረተበት ቃል ምን ይባላል
ሀ. ሕብረቃል ለ. ሰም ሐ. ወርቅ መ. ሁሉም
5. በቅኔ ውስጥ ህብረቃሉን በማየት አገባባዊ ትርጉም -------- ይባላል፡
ሀ. ህብረቃል ለ. ሰም ሐ. ወርቅ መ. የለም
6. የግጥም አይነቶች ስንት ናቸው
ሀ. 4 ለ. 3 ሐ. 5 መ. 2

You might also like