You are on page 1of 9

1

SOS HERMANN GMENER SCHOOL, BAHIR DAR


AMHARIC SECOND ROUND MODEL EXAMINATION
FOR GRADE -10, APRIL , 2010/2018
NUMBER OF ITEMS: 80 SUBJECT CODE: --
TIME ALLOWED: 1:30 HOURS
GENERAL DIRECTIONS:
THIS BOOKLET CONTAINS AMHARIC EXAMINATION. THE SUBJECT CODE FOR THIS
EXAMINATION IS ---. PLEASE COPY THIS CODE ON YOUR ANSEWR SHEET WHERE IT
READS SUBJECT CODE. THEN, BLACKEN THE CORRESPONDING BOXES IN THE
COLUMNS BELOW EACH NUMBER.

THE EXAMINATION CONTAINS 80 MULTIPLE CHOICE QUESTIONS. ATTEMPT ALL THE


QUESTIONS. FOLLOW THE INSTRUCTIONS ON THE ANSWER SHEET AND THE
EXAMINATION PAPER EXACTLY. USE ONLY PENCIL TO MARK YOUR ANSWERS.

THERE IS ONLY ONE BEST ANSWER FOR EACH QUESTION. CHOOSE THE BEST
ANSWER FROM THE SUGGESTED OPTIONS AND BLACKEN THE LETTER OF YOUR
CHOICE ON THE ANSWER SHEET. YOUR ANSWER MARK SHOULD BE HEAVY AND
DARK, COVERING THE ANSWER SPACE COMPLETELY. PLEASE ERASE ALL
UNNECESSARY PENCIL MARKS COMPLETELY FROM YOUR ANSWER SHEET.

YOU WILL BE ALLOWED TO WORK FOR 1:30 HOURS. IF YOU FINISH BEFORE TIME IS
CALLED, YOU MAY GO BACK AND REVIEW. WHEN TIME IS CALLED, YOU MUST
IMMEDIATELY STOP WORKING, LAY YOUR PENCIL DOWN, AND WAIT FOR FURTHER
INSTRUCTIONS.

ANY FORM OF CHEATING OR AN ATTEMPT TO CHEAT IN THE EXAMINATION HALL WILL


RESULT IN AN AUTOMATIC DISMISSAL FROM THE EXAMINATION HALL AND
CANCELLATION OF YOUR SCOR(S)
DO NOT TURN THIS PAGE UNTIL YOU ARE TOLD TO DO SO.

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
2

መመሪያ ፩፡- ከዚህ ቀጥሎ የተለያዩ ዓይነት ጥያቄዎች ቀርበዋል፤ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን

መልስ ምረጡ፡፡

1. የሶስተኛን ሰው ንግግር ለመግለጽ የሚገለግል የስርዓተነጥብ ዓይነት ምንድን ነው?


ሀ. ትዕምርተ ስላቅ ለ. ትዕምርት ጥያቄ ሐ. ትዕምርተ አንክሮ መ. ትዕምርተ ጥቅስ
2. ከሚከተሉት መካከል የስራ ደብዳቤ ውስጥ ብቻ የሚገኝ የቱ ነው?
ሀ. ቀን ለ. ቁጥር ሐ. መግቢያ መ. ሐተታ
3. ከሚከተሉት መካከል የስነቃል ዘርፍ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ.አፈታሪክ ለ. ሐተታ ተፈጥሮ ሐ. የልብወለድ መጻህፍት መ. ቃላዊ ግጥሞች
4. ከሚከተሉት መካከል አንዱ የስነጽሁፍ ጥበባዊ ብቃት መመዘኛ አይደለም፡፡
ሀ. በጽሁፍ መስፈሩ ሐ. ማራኪና ሳቢ በሆነ መንገድ መቅረቡ
ለ. በአገላለጹ አምሮ መቅረቡ መ. የሰውን ልጅ ሕይዎት ማሳየቱ
5. ከሚከተሉት መካከል ምዕላድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ሰው ለ. ሰውነት ሐ. ሰዎች መ. ሰዋዊ
6. ከሚከተሉት መካከል የምክንያትና ውጤት ትስስር የሌለው ሃሳብ የቱ ነው?
ሀ. ቋንቋ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ተናጋሪ ሲያጣ እሱም አብሮ ይጠፋል፡፡
ለ. በርትቶ የሚያጠና ተማሪ ተገቢውን እውቀት ይቀስማል፡፡
ሐ. የሰው ልጅ ቋንቋ ና የእንስሳት አንድነትም ልዩነትም አላቸው፡፡
መ. ለስኬት ጥረት ወሳኝነት አለው፡፡
7. በስነቃል ክዋኔ ጊዜ የተደራስያን ተግባር ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ምላሽ መስጠት ለ. ማዳመጥ ሐ. የሚከውነውን አካል ማጀብ መ. ስነቃሉን
መምራት
8. ማንኛውም ቋንቋ ምሉዕ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?
ሀ. ሙሉ በሙሉ ራሱን የቻለ ነው ማለት ነው፡፡
ለ.ከሌሎች ቋንቋ ቃላት በመዋስ ጉድለቱን ይሞላል ማለት ነው፡፡
ሐ. የሌላን ቋንቋ ቃል ይተረጉማል ማለት ነው፡፡
መ.የተናጋሪውን ማህበረሰብ ባህል መግለጽ ይችላል ማለት ነው፡፡
9. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ስማዊ ሐረግ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ትናንት ያየኋት ቀይ መኪና ሐ. እንደ እህቷ በጣም ቀልጣፋ
ለ. ከወንድሙ ጋር መ. ትህትናዋ የሚማርከው አስተናጋጅ
10. የአንቀጽ ቅርጽ የሚወሰነው በምን መነሻነት ነው?
ሀ. አንቀጹ በሸፈነው ሃሳብ ሐ. ኃይለቃሉ በሚገኝበት ስፍራ
ለ. በአንቀጹ መዘርዝር ዓረፍተነገሮች አማካኝነት መ. በዓረፍተነገሮች ብዛት
11. አንድ ጸኃፊ የአንድን ሃሳብ እውነትነት ወይም ሐሰትነት በማስረጃ በማስደገፍ ለማሳመን በመጣር የሚጽፍ
ከሆነ የድርሰቱ ዓይነት ምን ይባላል?
ሀ. ተራኪ ድርሰት ለ. አመዛዛኝ ድርሰት ሐ. ስዕላዊ ድርሰት መ. ገላጭ ድርሰት
12. በዓረፍተነገሮች ውስጥ የቃላቶች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በሚለው ዓረፍተነገር ውስጥ ስህተት እንዲኖር ያደረገው
ቃል የትኛው ነው;
ሀ. ሚና ለ. ከፍተኛ ሐ. ቃላቶች መ. ዓረፍተነገረ
13. በተራ ቁጥር‹‹ 12›› የተጠቀሰው ስህተት ዓይነት ምንድን ነው?
ሀ. የተሳቢ ለ. የቁጥር ሐ. የመደብ መ. የቃላት ምርጫ
14. ከሚከተሉት መካከል በውይይት አቀራረብ ጊዜ የሚከናወን ተግባር የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ስለ ርዕሱ ዋናዋና ሃሳቦችን መያዝ ሐ. ርዕሱን በሚገባ መረዳት
ለ. የርዕሱን ዓላማ ባጭሩ ማስቀመጥ መ. የርዕሱን ወቅታዊነት መገምገም

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
3

15. በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ የሚገኙትን የውሰት ቃላት በተመለከተ ምን ማለት ይቻላል?
ሀ. በጦርነት የገቡ መሆናቸውን ሐ. ከሐይማኖት አገባብ ጋር የተዋረሱ መሆናቸውን
ለ. በንግድ አማካኝነት የተገኙ መሆናውን መ. ሁሉም

16. ከሚከተሉት መካከል አንዱ የልብወለድን ጽሁፍ ባህሪያት አይወክልም፡፡


ሀ. ሙሉ ለሙሉ ከገሃዱ ዓለም የወጣ ነው፡፡ ሐ. ማህረሰቡን ሊተች ይችላል፡፡
ለ. የሚጻፈው በጊዜና በቦታ ተወስኖ ነው፡፡ መ. የደራሲው የምዕናብ ውጤት ነው፡፡
17. ከሚከተሉት ዐረፍተነገሮች አንዱ ትክክለኛ ሃሳብ አልያዘም፡፡
ሀ. ቋንቋ ለሰው ልጆች ብቻ የተሰጠ ጸጋ ነው፡፡ ሐ. እንስሳት ቋንቋ ስለሌላቸው በደመነፍስ
አይግባቡም ፡፡
ለ. ንግግር በድምጸ አልባ እንቅስቃሴ ይደገፋል፡፡ መ. የቋንቋ ክሂሎች አራት ናቸው፡፡
18. ከሚከተሉት መካከል ‹‹ትዳር ›› የሚለው ቃል በእማሬያዊ ፍችው የገባው በየትኛው ዓረፍተነገር ነው፡፡
ሀ. ትዳር ይዛለች፡፡ ሐ. የሞቀ ትዳር አለኝ፡፡
ለ. ትዳሩ ፈርሷል፡፡ መ. ትዳሩ ተናግቷል፡፡
19. የሰንጎ መገን ቤት የሚባለው የግጥም ቤት በሐረግ ስንት ስንኞች ያሉት ነው፡፡
ሀ. ስድስት ለ. አራት ሐ. ሶስት መ. አምስት
20. ከሚከተሉት መካከል የግጥም ባህርይ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ምዕናባዊነት ለ. ሙዚቃዊነት ሐ. ተጨባጭነት መ. ስድጽሁፋዊነት
21. የስነቃልን ባለቤት በተመለከተ የትኛው ትክክል ነው?
ሀ. ደራሲዎች በጋራ የፈጠሩት ነው፡፡ ሐ. ታላላቅ አባቶች በስምምነት የፈጠሩት ነው፡፡
ለ. የማህበረሰቡ የወል ሃብት ነው፡፡ መ. የታሪክ ምሁራን የፈጠሩት ነው፡፡
22. ከሚከተሉት መካከል በውይይት ወቅት የማይፈለግ ድርጊት የቱነው?
ሀ. የተወያይን ሃሳብ ማክበር ሐ. የተለየ ሃሳብን በውይይት አስደግፎ ማቅረብ
ለ. ውይይቱን በበቂ ማስረጃ ማጠናከር መ. ሃሳብ በሚሰጥበት ጊዜ ሁሉ በጭብጨባ ማድነቅ
23. ልብ ወለድ በሚጻፍበት ጊዜ ታሪኩ የሚያወራው ስለማን ነው ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ የትኛውን
የልብወለድ አላባ ይመለከታል፡፡
ሀ. ታሪክን ለ. ገጸባህሪያትን ሐ. መቼትን መ. አንጻርን
24. ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ቃላት መካከል ቅጽል የሆነው ቃል የትኛው ነው?
ሀ. ትኩስ ለ. እሸት ሐ. ድንገት መ. ዛሬ
25. በአንድ ዓረፍተነገር ውስጥ የዓረፍተነገሩ ባለቤት የሚገኝበት የሐረግ ዓይነት ምን ይባላል;
ሀ. ግሳዊ ሐረግ ለ. ቅጽላዊ ሐረግ ሐ. ግሳዊ ሐረግ መ. ስማዊ ሐረግ
26. ከሚከተሉት መካከል አሉታዊ ዓረፍተነገር የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. የት/ቤታችን ህንጻ ግንባታ እየተፋጠነ ነው፡፡ ሐ. እንኳን ደስ ያለህ
ለ. ልጁ አርፈዶ ስለመጣ አስተማሪው አላስገቡትም፡፡ መ. መቼ መጣህ
27. ለጤንነት የበለጠ ጠቀሜታ ያለው አትክልት ወይስ ስጋ ? የሚለው ዓረፍተነገር ለየትኛው የድርሰት ዓይነት ምሳሌ
ሊሆን ይችላል?
ሀ. ለተራኪ ለ. ለስዕላዊ ሐ. ለገላጭ መ. ለአመዛዛኝ
28. ሰዎች እቅድ አውጥተው ፣ጊዜና ቦታን በመወሰን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ የሚለዋወጡበትና ከጋራ
መግባባት ላይ የሚደርሱበት ክንውን ምንድን ነው?
ሀ. ክርክር ለ. ጭውውት ሐ. ውይይት መ. ትያትር
29. በአንድ ተውኔት የተሳሉትን ገጸ ባህሪት በመወከል መድረክ ላይ የሚተውኑ --------------- ይባላሉ፡፡
ሀ. ገጸባህሪያት ለ. መሪተውኔት ሐ. መሪ ተዋናይ መ. ተዋንያን
30. ውስን መቼትና ጥቂት ገጸባህሪያት የሚታዩበት የስነጽሁፍ ዘርፍ ምን ይባላል ?

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
4

ሀ. ተውኔት ለ. አጭር ልብወለድ ሐ. ረጅም ልብወለድ መ. ድራማ


ምንባብ
ሰው በተፈጥሮው የረሃብና የጥም ፣የበቀልና የመሳሰለው ፍልጎቱ ሁሉ እንዲፈጸምለት ይፈልጋል፤ነገርግን ማህበሩ
እያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፍላጎቱን ለመፈጸም ሲል ሌሎቹን ሰዎች እንዳይጎዳ የሚወስንበት የጽህፈትና
የልማድ ሕግ ሠራ፡፡ስለዚህ የተፈጥሮ ፍልጎቱን ለመፈጸም የማህበበሩን የጽህፈትና የልማድ ሕግ የተላለፈ
ነውረኛ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡

አንድ ሰው ከሌላው የሚያስቆጣ ነገር ቢደርስበትና ለቁጣው ምክንያት የሆነውን ሰው ለማጥፋት ቢወድ፣
በማህበሩ ህግ ቅጣት እንደሚያስከትል ስለሚያውቅ ቁጣውን ለማብረድ ፣ሌላ የሚበቀልበት አማራጭ መንገድ
መመፈለግ አለበት፡፡ስለዚህ የሰው ሰውነት የነጻነትና የጭቆና ውጤት ነው ማለት ይቻላል፡፡ይህ ነጻነትና ጭቆና
ማህበሩ በረጅም ዘመን ዕድሜው ከልማዱ፣ከወጉ፣ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ
ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በሱ ተመርቶ መኖር አለበት፤ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡
በጠቅላላው የማህበር ትምህርት እያንዳንዱ ሰው ሲወለድ ይዟቸው የሚወለደውን ጠቃሚ ውጥኖች ነጻነት
በመስጠትና በልዩልዩ መንገድ በመርዳት ጎጂዎቹነንም እንዲሁ በልዩልዩ መንገድ በመጠቆምና በማረም ሰውዬውን
ማህበራዊ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

እንዲህ ያሉት ሰዎች ደንበኛ አባልነታቸው ወደፊት ለሚመጣው ማህበር እንጅ ለሚኖሩበት ማህበር አይደለም፡፡
ምንም እንኳ የሰው ዘር የኑሮውንና የሕይዎቱን ደረጃ ለማሻሻል በሚያደርገው እርምጃ ተቀዳሚ መንገድ
ጠራጊዎች ቢሆኑም ለሚኖሩበት ማህበር አባሎች አይደሉም፡፡

የማህበሩ ትምህርት እያንዳንዱን ሰው ከሌሎች አባሎች ጋር መስሎና ተስማምቶ እንዲኖር ማህበራዊ እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡ሆኖም እያንዳንዱ አባል ከሌሎች ጋር መምሰልና መስማማት እንጅ መቶ በመቶ አንድ መሆን
አይችልም፡፡ስለዚህ ሰው ከሌሎች አባሎች የሚያስተባብረው የማህበሩ ትምህርት፣ ከሌሎች የሚለዩት
፣ከወላጆቹ የሚይዘው ማህበራዊ ከተፈጥሮ የሚያገኛቸው ስጦታዎች ስላሉት ልዩነቱን እንደያዘ ማህበራዊ
ይሆናል፡፡

መመሪያ ፪፡- ከላይ የቀረበውን ምንባብ መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት
አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
31. ሰው በተፈጥሮው እንዲፈጸምለት የሚፈልጋቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
ሀ. የረሃብ ፍላጎቱ ለ. ነጻ የመሆን ፍላጎቱ ሐ. የመበቀል ፍላጎቱ መ. ሁሉም
32. … ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ተወልዶ ውስጡ ሲገባ በእሱ መኖር አለበት ፡፡ በእሱ የተባለው ምንድን ነው?
ሀ. እያንዳንዱ ሰው ለ. የልማድና የጽህፈት ህጉ ሐ. ሐይማኖቱ መ. ነጻነቱ
33. በማህበሩ ህግ መሰረት ነውረኛ የሚል ስያሜ የሚሰጠው የትኛው ክፍል ነው?
ሀ. የማህበሩን ስርዓት ያስተዳደረ ሐ. የማህበሩን ስርዓት በእኩል ዐይን ያልተመለከተ
ለ. የማህበሩን ስርዓት የጣሰ መ. የማህበሩን ስርዓት ያከበረ
34. … ከማህበሩ ስርዓት አንድ ነቁጥ እንኳን አይተላለፍም፡፡ በሚለው ሃሳብ ላይ ለተሰመረበት ቃል አቻ የሚሆነው
ቃል ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው?
ሀ. ምልክት ለ. ስርዓት ሐ. ነጥብ መ. ትዕዛዝ
35. ማህበረሰቡ በረጅም ዘመን ዕድሜ ከልማዱ፣ ከወጉና ከህጉ አዋህዶና አስማምቶ የሰራው ምኑን ነው?
ሀ. ትክክለኛ እምነት የመያዝ ፍላጎቱ ሐ. ትክክለኛ አስተሳሰብ የመያዝ ፍላጎቱ
ለ. ነጻነቱና ጭቆናው መ. አመለካከቱና አስተሳሰቡ
36. አንድ ሰው የበቀል እርምጃ እንዳይወስድ የሚያግደው ምንድን ነው?
ሀ. ህሊናው ለ. የማህበሩ ስርዓት ሐ. እምነቱ መ. ቤተሰቡ
37. አንድን ግለሰብ አሁን ባለበትም ሆነ ወደፊት ለሚኖርበት ማህበረሰብ ጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉ የማን ኃላፊነት
ነው?
ሀ.የግለሰቦች ለ. የማበረሰቡ ሐ. የተፈጥሮ ፍላጎቱ መ. ነጻነቱ

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
5

38. ሰው በተፈጥሮው ---------------------


ሀ. ግላዊ ነው ፡፡ ለ. ማህበራዊ ነው ሐ. ማህበራዊነትን ይዞ ይወለዳል፡፡ መ. በቀለኛ ነው፡፡
39. ነጻነትና ጭቆና የ-----------------ዘመን ውጤት ናቸው፡፡
ሀ. የረጅም ለ. የአጭር ሐ. የአንድ መ. የመቶ
40. የጽሁፉ ርዕስ ምን ሊሆን ይችላል፡፡
ሀ. ተፈጥሯዊ ፍላጎት ለ. የአስተሳሰብ ለውጥ ሐ. ተፈጥሯዊ ፍላጎትና ስነስርዓት መ. የተፈጥሮ
ስጦታ
መመሪያ ፫ ፡- ከዚህ ቀጥሎ የፈሊጥ፣የምሳሌያዊ አነጋገርና የቅኔ ጥያቄዎች ቀርበዋል፤እንደአጠያየቃቸው
መልሱ፡፡
41. እናንተ የአባቶቻችሁ ልጆች የአያቶቻችሁ ቅድመአያቶች ናችሁ፡፡ ተብሎ ቢገለጽ በየትኛው ዘይቤ የቀረበ ነው?
ሀ.በእንቶኔ ለ. በአያዎ ሐ. በሰውኛ መ. በምጸት
42. ሁሉአማረሽን----------------- በባዶ ቦታው ሊገባ የሚችለው አባባል ከሚከተሉት የትኛው ነው?
ሀ. ገበያ አውጧት ለ. ገበያ አታውጧት ሐ. ገበያ ላኳት መ. ገበያ ሰደዷት
43. በቅኔ ውስጥ ወርቅ የምንለው -----------------------ማለት ነው?
ሀ. በሰም የተሸፈነውን ለ. ዋና ሃሳቡን ሐ. ሚስጥሩን መ. ፈርጡን

44. ጥርሱን ነከሰ ለሚለው ፈሊጥ ተመሳሳይ የሚሆነው የትኛው ነው?


ሀ. ጥርሱን አደማ ለ. ዛተ ሐ. ደፈረ መ. ተተናኮለ
45. ሰማይን የሚያክል ብራና ተጽፎ ፣
ዐባይን የሚያክል ቀለም ተበጥብጦ፣
ውድህና ውዴ እዚያ ላይ ተጽፎ ፣
ያንን የሚያነበው የተማረ ጠፍቶ፣
ጎጃም ተሻገረ የብር ሳንቃ ገዝቶ፡፡ ይህ ግጥም የተጻፈበት የዘይቤ ዓይነት ከሚከተሉት የትኛው ነው?
ሀ. እንቶኔ ለ. አያዎ ሐ. ግነት መ. ተምሳሌት
46. የቸኮለ አፍሶ ለቀመ፡፡ ለሚለው አባባል የማይመሳሳለው የቱ ነው?
ሀ. ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል፡፡ ሐ. የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል፡፡
ለ. አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ፡፡ መ. ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ፡፡
47. ነገረ ውሽልሽል ማለት -------------- ማለት ነው፡፡
ሀ. ቁምነገር የሌለበት ለ.በደንብ የተሰራ ሐ. ቁምነገረኛ መ. መናኛ ስራ
48. ከአጋም የተጠጋች ቁልቋል ዘላለም--------------------፡፡
ሀ. ስትቀጥፍ ትኖራለች፡፡ ለ. ስታብብ ትኖራለች ሐ. ስታነባ ትኖራለች መ. አጋም አጋም ትሸታለች፡፡
49. ከተከለከለው ከጨፌ እየዋለች፣
አልታለብ ብላ ያቺስ ላም እምቢ አለች፡፡የዚህ ቅኔ ወርቅ ከሚከተሉት የትኛው ነው?
ሀ. ላሚቱ አልታለብ አለቸ፡፡ ሐ. እስላሟ ሃይማኖቷን ጣለች፡፡
ለ. ላሚቷ የሰው ክልል ጣሰች ፡፡ መ. የተጠየቀችውን እስላሟ ሴት ከለከለች ፡፡
50. ስሚ አንቺ እማማ ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆች የታፈርሽ ነሽ እኮ ፡፡ ብንል በየትኛው የዘይቤ ዓይነት
ተጻፈ፡፡
ሀ. ሰውኛ ለ. ተምሳሌት ሐ. እንቶኔ መ. ተለዋጭ
51. ‹‹ልጅ የጫረው እሳት ለጎረቤት ይተርፋል›› ቢባል ምሳሌያዊ አነጋገሩ የያዘው ትርጉም ከሚከተሉት
የትኛው ነው?
ሀ. ልጅ ያለ ልጅ ጨመረ፡፡ ሐ. የመልካም ልጅ ጎረቤት በብርድ አይጠቃም፡፡

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
6

ለ. ታታሪ ልጅ ለጎረቤቱ በረከት ነው፡፡ መ. በልጅ የመጣ ጠብ ቶሎ አይበርድም፡፡


52. በበጋ እንዳይዘራ ጸሃይ እየፈራ ፣
በሐምሌ እንዳይዘራ ዝናብ እየፈራ፣
ልጁ ዳቦ ቢለው በጅብ አስፈራራ ፡፡ የሚለው ቃላዊ ግጥም ምንን ይገልጻል ?
ሀ. ፍቅርን ለ. ስንፍናን ሐ. ጥላቻን መ. ሙገሳን
53. መጨነቅ መጠበብ ለጠጅ ብቻ ነው፣
ለጠላ መድሐኒት ተወት ማድረግ ነው፡፡ የዚህ ቅኔ ህብረቃል ምን የሚለው ነው?
ሀ. ተወት ማድረግ ነው፡፡ ለ. መድሐኒት ሐ. ለጠላ መ. ለጠጅ ብቻ ነው፡፡
54. ህመሙን የደበቅ መድሐኒት የለውም፡፡ለሚለው አባባል ሊመሳሳል የሚችለው ከሚከተሉት የትኛው ነው?
ሀ. ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ፡፡ ሐ. ነጋሪ የሌለው ይታማ አይመስለው
ለ. ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም፡፡ መ. ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው፡፡
55. አስቴር ስራ ስትቀጠር የጠለፋ ዋስ እንድታቀርብ ተጠየቀች፡፡የተሰመረበት ፈሊጥ ፍች የትኛው ነው?
ሀ. ጓደኛ ለ. አለኝታ ሐ. ተያዥ መ. ጠበቃ
56. ጭራሽ ሰነፍ የሆነን ሰው መግለፅ ብንፈልግ የትኛውን ፈሊጣዊ አነጋገር መጠቀም እንችላለን?
ሀ. እጀ ሰባራ ለ. እጅ አጠረው ሐ. እጅ አደር መ. አጀ አመድ አፋሽ
57. ልጁ እንደእስስት ባህሪው ይቀያየራል፡፡ በሚለው አገላለፅ ውስጥ ለልጁና ለእስስት የጋራ የሆነው ባህሪይ የቱ ነው?
ሀ. እስስትነት ለ. ልጅነት ሐ. ተቀያያሪነት መ. ተንኮለኝነት
58. ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው ለሚለው አባባል የሚመሳሰለው የቱ ነው?
ሀ. ነገረኛ ዱቄት ከነፋስ ይጠጋል፡፡ ሐ. ወጥ ለሰሪው እህል ለዘሪው
ለ. ደባ ራሱን ስለት ድሱን መ. የግፍግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
59. ከኳስ ጨዋታ ውስጥ ጨዋታው ሲደራ፣
አይቀርም መድረሱ ፈጽሞ ግፍተራ፡፡ የዚህ ቅኔ ወርቅ የቱ ነው?
ሀ. ግፍተራ የሚባል ቦታ መጠራቱ አይቀርም፡፡ ሐ. መገፋፋት አይቀርም፡፡
ለ. ግፍ የሰራ ሰው ተራው መድረሱ አይቀርም፡፡ መ. መገፋፋት በፍጹም መኖር የለበትም፡፡
60. አሁን ምን ያደርጋል ነገር መለቃቀም፣
ባባቷ ያልሆነ ባያት ምን ልጠቀም፡፡የዚህ ቅኔ ህብረቃል የቱ ነው?
ሀ. ባባቷ ለ. ምን ልጠቀም ሐ. ባያት መ. መለቃቀም
መመሪያ ፬፡- ከዚህ ቀጥሎ ከቃላት ጋር የተያያዙ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፤በአጠያየቃቸው መሰረት
ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ ምረጡ፡፡
61. ወንድማማቾቹ በመፈቃቀር የኖሩ ቢሆኑም ፣ልሎች ካፈሩ በኋላ ግን ደመኛ ሆነዋል፡፡ የተሰመረበት ቃል ፍች
ምንድን ነው?
ሀ.ባላንጣ ለ. ባላንጋራ ሐ. ወዳጅ መ. ሀናለ
62. ከሚከተሉት ቃላት መካከል በእማሬያዊ ፍችው የገባው ቃል የቱ?
ሀ. ባለፈው በጎርፍ ተራቁቶ የነበረው መሬት አሁን ተራራ ሀኗል፡፡ ሐ. ልጅቷ መሬት ስለሆነች ለሰው ሁሉ
ትመቻለች፡፡
ለ. ልጃቸው አድጎ ሲጣሉ ሽማግሌ ሆኖ ያስታርቃቸውዋል፡፡ መ. የእህቴ ያገባችው ባል መልዓክ ነው፡፡
63. ከሚከተሉት መካከል ህቡዕ ለሚለው ቃል ሊመሳሳለወው የማይችል የትኛው ነው?
ሀ. ድብቅ ለ. ስውር ሐ. ሚስጢራዊ መ. ገሃድ
64. ከሚከተሉት መካከል ልዩ የሆነውን ቃል አውጡ፡፡
ሀ. ሴራ ለ. ምልሰት ሐ. ታሪክ መ. መቼት
65. ተረበኛ ለሚለው ቃል ሊመሳሳለው የሚችለው የትኛው ነው?
ሀ. ወገኛ ለ. ጉረኛ ሐ. መተተኛ መ. ቀልደኛ
66. ለተሾመ ይመሰከርለታል፤ለተሻረ ይመሰከርበታል ብንል የተሰመረባቸው ቃላት ምንን ይገልጻሉ፡፡

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
7

ሀ. ተሿሚው አካል ተጠቃሚ ፣ከሹመት የወረደው ጥቅም ፈላጊ መሆናቸውን ይገልጻል፡፡


ለ. ተሿሚው አካል ሲጠቀም ፣ከሹመት የወረደው ይጎዳል ማለት ነው፡፡
ሐ. ተሿሚው አካል ተጠቃሚ ፣ከሹመት የወረደው ጠቃሚ ነው ማለት ነው፡፡
መ. ተሿሚው አካል ጠቃሚ ፣ ከሹመት የወረደው ተጠቃሚ ነው ማለት ነው፡፡
67. የልጅቷን ጥሮ ግሮ መኖር የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ለተሰመረበት ቃል በፍቺ የሚመሳሰለው የቱ ነው፡፡
ሀ. አታሎ ለ. ለፍቶ ሐ. ተንደላቆ መ. ዘንጦ
68. አቶ ደግአረገ ልበሙሉነቴ ጠቀመኝ ቢሉ፣የተሰመረበት ቃልአገባባዊ ፍችው ምንድን ነው?
ሀ. ጀግንነቴ ለ. ሚስጢር ጠባቂነቴ ሐ. ደፋርነቴ መ. ትዕግስተኛነቴ
69. ሾፌሩ በወያላውና በተሳፋሪው መካከል ላለው ያለመግባባት ደንታ ሳይኖረው የማሽከርከር ስራውን ተያይዞታል፡፡
ለተሰመረበት ቃል ተመሳሳይ የሚሆነው የቱ ነው?
ሀ. ግምት ለ. ግድ ሐ. ተሳትፎ መ. ክብር
70. አቶ ተኮላ ስለ ወንድማቸው ድንገት በሰሙት ወሬ አዝነዋል ፡፡ ብንል የተሰመረበትን ቃል ሊተካ የሚችለው
ከሚከተሉት የትኛው ነው?
ሀ. ድርቅ ብለዋል ለ. ልባቸው ተነክቷል ሐ. ቅቤ ጠጥተዋል መ. እፎይታ አግኝተዋል፡፡
መመሪያ፭፡ ከዚህ ቀጥሎ ክሂልን የሚጠይቁ ጥያቄዎች ቀርበዋል ፤ለእያንዳንዳቸው ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች
መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ ምረጡ፡፡
71. የቋንቋ ክሂሎች በቅደምተከተል ሲቀመጡ ከሚከተሉት የትኛው ትክክል ነው?
ሀ. መናገር ፣ማዳመጥ፣መጻፍ፣ማንበብ ሐ. ማዳመጥ፣መናገር፣ማንበብ፣መጻፍ
ሐ.ማዳመጥ፣መጻፍ፣መናገር፣ማንበብ መ. ማዳመጥ፣መጻፍ፣መናገር፣ማንበብ
72. ከክሂሎች መካከል በተፈጥሮ የምናገኛቸው ክሂሎች የትኞቹ ናቸው?
ሀ.ማዳመጥና መናገር ለ. መናገርና መጻፍ ሐ. መጻፍና ማንበብ መ. ማንበብናማዳመጥ
73. መልዕክትን ለመቀበያነት የምንጠቀምባቸው የክሂል ዓይነቶች የትኞች ናቸው?
ሀ. ማዳመጥና መናገር ለ. መጻፍና ማንበብ ሐ. ማዳመጥናማንበብ መ. ማንበብናመጻፍ
74. ትምህርትቤት ከገባን በኋላ የምንናገኛቸው የክሂል ዓይነቶች ከሚከተሉት የትኞቹ ናቸው?
ሀ. ማዳመጥና መናገር ለ. መናገርና መጻፍ ሐ. መጻፍና ማዳመጥ መ. ማንበብና መጻፍ
75. ‹‹ካልታረደ አይታይስባቱ ካልተናገረ አይታወቅ ብልሃቱ›› የሚለው ምሳሌያዊ አባባል ምንን ይገልጻል፡፡
ሀ. የንግግርን ትልቅነት ለ. የማዳመጥና የመስማትን ሐ. የማንበብን ትልቅነት መ. የመጻፍን አግባብነት

መመሪያ ፮ ቀጥሎ የቀረበውን ግጥም መሰረት አድርጋችሁ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች
መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡
የሞተው ወዳጄ እኔ የማልናፍቀው፣
ያነሳኛል አሉ ሲጨንቀው ሲጠበው፣
መቆያው ማደሪያው ከቤቴ ከደጄ
ምንድን ይሻ ይሆን ትልቁ ወዳጄ?
ታዲያ ምን ይሉታል እንዲህ ያለውን
ከመቃብር በታች ነፍስ የዘራውን፡፡
ምናልባት ሲቀበር ዐፈር አልባሾቹ፣
ኮረትና ድንጋይ አልጫኑት ከታቹ፡፡
ነፍስ እንዳለው ፍጡር እንዳልተቀበረ፣
ምነዋ ወዳጄ ብዙ ቀባጠረ?
መኖርም መሞትም አንዴ ጥርስን ነክሶ፣
ወይ በምግባር ከብሮ ወይ በምግባር ረክሶ፣
እንጅ እንደ ወዳጄ መች መቃብር ምሶ፣

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
8

እንጅ እንደ ወዳጄ መች ለራስ አልቅሶ፣


የቁም ሞትን ሙቶ በተንኮል ጨንብሶ፣
ካልሆነ በስተቀር የ‹‹ደንቆሮ››ለቅሶ፣
መልሶ መልሶ መልሶ መላልሶ፡፡
76. ግጥሙ የተጻፈው በየትኛው የግጥም ዓይነት ነው?
ሀ. የሰንጎ መገን ቤት ለ. የቡሄ በሉ ቤት ሐ . የወልቤት መ. የጸጋዬ ቤት
77. ተራኪው ስለ ሟቹ ስላለው አመለካከት ምን ማለት ይቻላል?
ሀ. እንደሚወደው መናገር ይቻላል፡፡ ሐ. እንደማያውቀው መናገር ይቻላል፡፡
ለ. እንደማይወደው መናገር ይቻላል፡፡ መ. እንደረሳው መናገር ይቻላል፡፡
78. ‹‹ደንቆሮ›› የሚለው ቃል በጥቅስ ምልክት የተቀመጠበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ. አባባል ስለሆነ ለ. የሟቹ ንግግር ስለሆነ ሐ. የተራኪው ንግግር ስለሆነ መ. ሟቹ የአዋቂ አጥፊ
ስለሆነ
79. ‹‹በተንኮል ጨንብሶ›› ማለት ምን ማለት ነው ?
ሀ. አይኑን አጨንቁሮ ለ. ውስጡን በተንኮል ሞልቶ ሐ. ራሱን አሞግሶ መ. ራሱን ጎድቶ
80. የግጥሙ መልዕክት ምንድን ነው?
ሀ. ሰው በጥሩ ስራው ይታወሳል፤ በመጥፎ ስራው ይረሳል፡፡
ለ. ክፉ ስራ ከሰሩ በኋላ ጸጸት አስፈላጊ አለመሆኑን፣
ሐ. ችግርን በጽናት መጋፈጥን፣
መ. ችግርን እንደችግርነቱ መጋፈጥን፡፡

የ 10 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ የሁለተኛው ናሙና መልስ 2010 ዓ.ም

1. መ 21. ለ 41. ለ 61. መ

2. ለ 22. መ 42. ለ 62. ሀ

3. ሐ 23. ለ 43. ሐ 63.መ

4. ሀ 24. ሀ 44. ለ 64. ለ

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን
9

5. ሀ 25. መ 45. ሐ 65. መ

6. ሐ 26. ለ 46. መ 66. ለ

7. መ 27. መ 47. ሀ 67.ለ

8. መ 28. ሐ 48. ሐ 68. ሐ

9. ሀ 29. መ 49. ሐ 69. ለ

10. ሐ 30. መ 50. ሐ 70.ለ

11. ለ 31. መ 51. መ 71. ሐ

12. ሐ 32. ለ 52. ለ 72. ሀ

13. ለ 33. ለ 53. ለ 73. ሐ

14. ለ 34. ሐ 54. ለ 74. መ

15. መ 35. ለ 55. ሐ 75. ሀ

16. ሀ 36. ለ 56. ሐ 76. ሐ

17. ሐ 37. ለ 57. ሐ 77. ለ

18. ሀ 38. ሀ 58. ለ 78. መ

19. መ 39. ሀ 59. ለ 79. ለ

20. መ 40. ሐ 60.ሐ 80. ሀ

ኤስ ኦኤስ ሔርማ ግማይነር ት/ቤት ባህርዳር፣የ 2010 ዓ.ም አማርኛ ቋንቋ ት/ት የ 10 ኛ ክፍል ናሙና ፈተና 2 አስናቁ
ኃይሉ በፍቅር የተመላ ቤት ለሁሉም ህጻን

You might also like