You are on page 1of 9

በፍንፊኔ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2012 ዓ.

ም የትምህርት ዘመን የሁለተኛ መንፈቀ


ዓመት ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና፡፡

መመሪያ፡-

• መመሪያዎቹን በጥንቃቄ አንብቡ፡፡ስለፈተናው ጥያቄዎች ካላችሁ ፈተናው

ከመጀመሩ በፊት ፈታኙን /ፈታኟን/መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ፈተናው ከተጀመረ

በኋላ ምንም ዓይነት ጥያቄ መጠየቅ አይቻልም፡፡

• ይህ የአማርኛ ትምህርት ፈተና ነው፡፡ የተሰጠው ጊዜ 1 ሰዓት ሲሆን ከአንድ ስዓት

በላይ መስራት አይፈቀድም፡፡ ከተፈቀደው ጊዜ ቀድማችሁ ከጨረሳችሁ የሰራችሁትን

ፋተና በድጋሜ መፈተሽ ወይም ማረጋገጥ ትችላላችሁ፡፡

• እያንዳንዱ ጥያቄ አራት አማራጮች አሉት፡፡ ጥያቄዎቹንና ምርጫዎቹን በጥንቃቄ

ካነበባችሁ በኋላ መልሳችሁን በሚሰጣችሁ የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ አመልክቱ፡፡

መልሶቻችሁን ለማመልከት ከምርጫችሁ ሥር የሚገኘውን ሣጥን አጥቁሩ ወይም

አቅልሙ፡፡

❖ ለምሳሌ ፡- መልሳችሁ 3ኛው ምርጫ ከሆነ ከስሩ የሚገኘውን ሳጥን ከዚህ በታች በቀረበው

መልኩ አጥቁሩ፡፡

A B C D

• መልሳችሁን ለመቀየር ከፈለጋችሁ የመጀመሪያውን መልስ በደንብ አድርጋችሁ አጥፉ

ከዚያም የተቀየረውን መልሳችሁን አጥቁሩ፡፡

• ፈተናውን ለብቻችሁ መስራት ይኖርባችኀል፡፡በማንኛውም መንገድ ለማጭበርበር

ከሞከራችሁ ውጤታችሁ በሙሉ ይሰረዝባችኋል፡፡

• ለፈተናው የተፈቀደላችሁ ሰዓት ሲያልቅ ፈታኙ/ኟ/ እንድታቆሙ ይነግሯችኋል ወዲያውኑ ማቆም


ይኖርባችኋል፡፡
• ፈተናው እንዳለቀ መውጣት አይፈቀድም ፡፡ የፈተናው ወረቀቶች እስኪሰበሰቡ እና

ፈታኙ/ኟ/ ፍቃድ እስኪሰጧችሁ ድረስ መጠበቅ አለባችሁ፡፡

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 1
መመሪያ አንድ ፡- ለሚከተሉት ቃላት ተመሳሳያቸውን በመምረጥ የመረጣችሁትን ፊደል
በተገቢው ቦታ አጥቁሩ፡፡

1. ገመና A/ ገበታ B/ ድራማ C /ሚስጥር D/ ወሬ

2. ሁል ጊዜ A/ አልፎ አልፎ B/ አንዳንዴ C/ ቆይቶ D/ ዘወትር

3. ዋቢ A/ ወሬ B/ ዋስ C/ ጓደኛ D/ፍቅረኛ

4. መሻት A/ መጥላት B/ ማመን C/ መካድ D/መፈለግ

5. አፈላማ A/ የከብት ጥፋት ዕዳ B/ አፈ ጉባዔ C /ብልጥ D/ አፈ- ጮሌ

መመሪያ ሁለት፡- ከሚከተሉት ቃላት ተቃራኒያቸውን በመምረጥ በተገቢው ቦታ አጥቁሩ

6. ዘመድ A. ጎረቤት B ወዳጅ C/ ቤተሰብ D/ባዕድ/ባዳ/

7. አቀበት A/ ዳገት B/ ቁልቁለት C/ተራራ D/ ሜዳ

8. አዘነ A/ ተደሰተ B/ ተከፋ C/ተፀፀተ D/ አኮረፈ

9. እኩይ A/ ክፉ B/ መጥፎ C/ሰናይ D/ መሰሪ

10. ብልፅግና A/ ድህነት B/ እድገት C/ ስልጣኔ D/ ለውጥ

መመሪያ ሦስት፡-ከዚህ በታች በቀረቡት አረፍተ ነገሮች ውስጥ የተሰመረባቸውን ቃላት ወይም
ሃረጎች አገባባዊ ፍቺ በመምረጥ በተገቢው ቦታ አጥቁር/ሪ/

11. ሰራተኛዋ በአሰሪዋ ንግግር ደሟ ፈላ፡፡

A/ ተደሰተች B/ ተናደደች C/ አዘነች D/ ተስፋ ቆረጠች

12. ሱሪውን አጥሩ ላይ የነበረው ሚስማር ሸረከተው ፡፡

A/ አደቀቀው B/ ወጋው C/ ገረደፈው D/ቀደደው

13. ኩምሳ ልክ እንደገባ ዙሪያውን አማተረ፡፡

A/ ተመለከተ B/ ተሳለመ C/ ለካ D/ መተረ

14. ቡና ያገራችን ኢኮኖሚ እድገት የጀርባ አጥንት ነው ፡፡

A/ የሰውነት ክፍል B/ ወገብ C/ ዋልታ D/ ጀርባ

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 2
15. በኮሮና ምክንያት የሁለተኛው መንፈቀ ዓመት ትምህርት ተቋረጠ፡

A/ ተካሄደ B/ ተፈፀመ C/ ተደናቀፈ D/ተሳካ

መመሪያ አራት፡- በጅምር የቀረቡትን ምሳሌያዊ አነጋገሮች የሚያሟሉትን አባባሎች ምረጥ/ ጪ/

16. የቆጡን አወርድ ብላ -------------ጣለች፡፡

A/ የጇን B/ የብብቷን C/ የጀርባዋን D/የራሷን

17. የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ----------

A/ ፍልጥ B / ጭቃ C/ ብሎኬት D/ሰንበሌጥ

18. እውነትና ንጋት እያደር ---------------

A/ ይጠራል B/ ይቀላል C/ ይጠፋል D/ይናፍቃል

19. የጅብ ችኩል -------------- ይነክሳል ፡፡

A/ ጆሮ B /ጅራት C/ ቀንድ D/ እግር

20. የሰው ወርቅ -----------------

A/ ያምራል B/ አያደምቅ C / አያልቅ D/አይወሰድ

መመሪያ አምስት፡- ከዚህ በታች ለቀረቡት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል
በመምረጥ በተገቢው ቦታ አጥቁር/ሪ/

21. ከችግር ጋር ሲታገል የኖረ ሰው ቆዳው ይወፍራል ጅማቱ ይጠነክራል የተጣለበትን ሸክም መሸከም
ይችላል፡፡በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ መግባት ያለበት ስረአተ ነጥብ የቱ ነው?

A/ ‹‹ ›› B /፤ C/ ፣ D/.…

22. ተመሳሳይ ሙያ ወይም ተግባር እና ባህሪ ያላቸውን ዝርዘር ጉዳዮች ለመለየት የምንጠቀምበት ስርአተ
ነጥብ ------ይባላል፡፡

A/ ፣ B/ ፤ C/ ፡- D/ !

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 3
23. ትክክለኛ ስርአተ ነጥብን የተከተለ አረፍተ ነገር የትኛው ነው ?

A/ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ፡፡!”

B/ “እኔ ! ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ”፡፡

C/ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” አለች አህያ፡፡

D/ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች” አህያ፡፡

24. ጫላ ነጭ ፈረስ ገዛ ፡፡የዚህ አረፍተ ነገር ባለቤት -----------ነው ፡፡

A/ ገዛ B/ ነጭ C / ፈረስ D/ ጫላ

25. በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ መነሻ ሃሳብ በመስጠት የጋራ ሃሳብ የማመንጨት ሂደት -------ነው፡፡

A/ ውይይት B/ ክርክር C /ሙግት D/ ድርድር

26. ታታሪው ገበሬ ምርቱን በወቅቱ ይሰበስባል፡፡ የተሰመረበት ቃል ምንን ይገልፃል?

A/ ስም ገላጭ B/ ግስ ገላጭ C/ ተገላጭ D/መስተዋድድ

27. /- ኦች / የሚለውን ቅጥያ ሊወስድ የሚችለው ቃል የቱ ነው?

A/ አፈር B/ ጸሐይ C/ ሰው D/ ዝናብ

28. ለጠላ ይጠመቃል ካለ ለጠጅ ……….ይላል

A/ ይወጣል B/ ይጣላል C/ ይፈላል D/ ይበጠበጣል

29 ሀቀኛ ሰው በማህበረሰቡ ዘንድ ምን ጊዜም ይከበራል፡፡የተሰመረበት ቃል……ይገልጻል?

A/ ስም B/ ግስ C/ የግስ ገላጭ D/ የስም ገላጭ

30. ለዶሮ ቄብ ካልን ለላም…….እንላለን

A/ ጊደር B/ ወይፈን C/ ጥጃ D/ እንቦሳ

31. የምክንያትና የውጤት ትስስርን የሚያመለክተው ዐ.ነገር የትኛው ነው?

A/ የአለም ኤድስ ቀን በየአመቱ ይከበራል፡፡ B/በለውጡ ምክንያት የሴቶች ተሳትፎ ጨምሯል::

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 4
C/ ራሳችንን ከኮሮና በሽታ እንጠብቅ፡፡ D/ የመረዳዳት ባህላችንን እናሳድግ፡፡

32. እየሰነጣጠቀ በሚለው ቃል ውስጥ የሚገኙት ቅጥያዎች የ……ና…..ናቸው?

A/ የመነሻና መድረሻ B/ የመድረሻ ና የመሀል C/ የመነሻ ና የመሀል D/ የመሀል ብቻ

33. ሲጠብቅና ሲላላ የተለያየ ትርጉም ሊሰጥ የሚችለው ቃል…….ነው?

A/ ፈረስ B/ አከለ C/ ጨመረ D/ አዛባ

34. እኔ ምሳዬን በላሁ፡፡ የሚለው ዐ.ነገር በስንተኛ መደብ የተገለጠ ነው?

A/ 1ኛመደብ ነጠላ B/ 2ኛ መደብ ነጠላ C/ 3ኛ መደብ ነጠላ D/ 4ኛ መደብ ነጠላ

35. ልጆቹ ትናንትና መጣ፡፡ የዚህ ዐ.ነገር ሰዋሰዋዊ ስህተት የ……ነው?

A/ የጾታ B/ የባለቤት C/ የቁጥር D/ የጊዜ

36. ከአያት ቅድመ አያት ሲወርድ ……..የቆየውን ባህላችንን እንጠብቅ

A/ ሲወጣ B/ የኖረውን C/ የነበረውን D/ ሲዋረድ

37. ክቡር ሊቀመንበር፥የተከበራችሁ ዳኞች……. ይህ የምን አጃማመር ስርአት ነው?

A/ የውይይት B/ የክርክር C/ የጭውውት D/ የንግግር

38. ልጅቷ ምሳዋን በልቶ ተኛ፡፡ የዚህ ዐ.ነገር ሰዋሰዋዊ ስህተት የ…..ነው?

A/ የመደብ B/ የጊዜ C/ የቅጥያ D/ የጾታ

39. ከስነ-ቃሎች ውስጥ በትረካ መልክ የሚቀርበው የትኛው ነው?

A/ ምሳሌያዊ አነጋገር B/ እንቆቅልሽ C/ ተረት D/ ፈሊጣዊ አነጋገር

40. የሚና ጨዋታ ከአራቱ የቋንቋ ክሂሎች የትኛውን ክሂሎት ያዳብራል?

A/ መናገር B/ ማዳመጥ C/ መጻፍ D/ ማንበብ

41. ውድድሩ ፈታኝ …….. ማሸነፌ አልቀረም፡፡ በባዶ ቦታው መግባት ያለበት አያያዥ የቱ ነው?

A/ ስለዚህ B/ ስለሆነም C/ እንጂ D/ ቢሆንም

42. ያባቴ በሚለው ቃል ውስጥ የተዋጠው ድምጽ የቱነው?

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 5
A/ አ B/ የ C/ ተ D/ በ

43. የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት በምህጻረ-ቃል ሲቀመጥ……ይሆናል?

A/ የ.መ.ማ.ድ B/ ት.መ.ማ.ማ.ድ C/ የ.ት.ማ.ማ.ድ D/ ት.መ.ማ.ድ

44. ድሬደዋ ያደረሰን ባቡር ተበላሸ፡፡በሚለው ዐ.ነገር ውስጥ ሀረግ ሊሆን የሚችለው የትኛው ነው?

A/ ድሬደዋ B/ ባቡር C/ ያደርሰን ባቡር D/ ተበላሸ

45. የቋንቋ አገልግሎት ያልሆነው የትኛው ነው?

A/ እኩልነት B/ ማንነትን መግለጫ C/ መተንበያ D/ መግባቢያ

46. ከሚከተሉት ውስጥ ድርብ ቃል የሆነው የቱነው?

A/ አካባቢያችን B/ እያንዳንዳችን C/ መስሪያ ቤታችን D/ አይን-አዋጅ

47. ስለ አንድ ሀሳብ ብቻ የሚያብራራ፣ የሚያትትና የሚዘረዝር አነስተኛ የጽሁፍ

ክፍል……ይባላል?

A/ አንቀጽ B/ ሀረግ C/ ዐ.ነገር D/ ድርሰት

48. የህይወት ታሪክ አጻጻፍ በስንት ይከፈላል?

A/ 3 B/ 4 C/ 2 D/ 5

49 ድርሰትን ከመጻፋችን በፊት አስቀድመን የምንተገብረው ተግባር ምን ይባላል?

A/ መረጃ መሰብሰብ B/ አስተዋጽኦ መንደፍ C/ ማርቀቅ D/ መጻፍ

50. ሀለ-ቃል የያዘውን የሚተነትኑ፥የሚዘረዝሩና የሚያብራሩ ዐ.ነገሮች …….ይባላሉ?

A/ አንቀጽ B/ ዝርዝር ዐ.ነገር C/ መንደርደሪያ ዐ.ነገር D/ ዋና ዐ.ነገር

51. ማመልከቻ ከየትኛው የደብዳቤ አይነት ይመደባል?

A/የዘመድ B/ የጓደኛ C/ የፍቅረኛ D/ የስራ

52. በአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል በድምጽ፥በቃልና በአባባል ደረጃ የሚታይ ልዩነት ምን ይባላል?

A/ ዘዬ B/ ሰዋሰው C/ ግጥም D/ ስነ-ጽሁፍ

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 6
53. ከሚከተሉት አንዱ የቋንቋ ባህሪ አይደለም?

A/ ይወለዳል B/ ይበላለጣል C/ እኩል ነው D/ ምሉእ ነው

54. ዋና ዋና ሀሳቦችን በቃል፥በሀረግና በዐ.ነገር አሳጥሮ መጻፍ የ…….አያያዝ ዘዴ ነው?

A/ የዘገባ አያያዝ B/ የቃለ-ጉባኤ አያያዝ C/ የማስታወሻ አያያዝ D/ የመዝገብ አያያዝ

መመሪያ ስድስት፡- ምንባብ አንድ ከጥያቄ 55-57 ድረስ የቀረቡትን ጥያቄዎች በግጥሙ

መሰረት መልሱ፡፡

ባንድነት ተባበር፥ተው አትለያይ፥

ድር አንበሳ ያስራል፥ሲሆን አንድ ላይ፥

ከመሀልህ ይጥፋ፥ተንኮል መካሪው፥

ቸርነት ቅንነት፥ነው አሸናፊው፡፡

ህብረት ደመና ነው፥ያወርዳል ዝናም፥

የደረቀው ሁሉ፥እንዲለመልም፥

ሕብረት ብርሃን ነው፥የጸሀይ ጨረር፥

ሕብረት ጥሩ ነገር፥በመከባበር፥

አያጋጥምህም፥እንቅፋት ከእግር፡፡

/ ምንጭ ከ7ኛ ክፍል መማሪያ መጽሀፍ/

55. ግጥሙ ስንት ስንኞች ና ሀረጎች አሉት?

A/ 9፥12 B/ 9፥16 C/ 9፥18 D/ 9፥9

56. የመጀመሪያው አንጓ ቤት መድፊያ ቃል የሆነው የቱ ነው?

A/ መካሪው B/ አንድ ላይ C/ አትለያይ D/ አሸናፊው

57. የሁለተኛው አንጓ የመጨረሻ ስንኝ መድረሻ ሀረግ……..ነው?

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 7
A/ እንቅፋት ከእግር B/ ሕብረት ጥሩ ነገር C/ የጸሀይ ጨረር D/ የደረቀው ሁሉ

መመሪያ ሰባት፡- ምንባብ ሁለት ቀጥሎ የቀረበውን ምንባብ በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ
የቀረቡትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት መልሱ፡፡

በማህበረሰባችን ዘንድ “ ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቆሞ!” የሚል አባባል ዘወትር ይሰማል፡፡ይህ
ደግሞ ጊዜን ሳንጠቀምበት ሊያልፍ የሚችል፥ወደኋላ የማይመለስና ሊተካ የማይችል መሆኑን
ያመላክታል፡፡ ማድረግ የምንችለው ጊዜን መጠቀም ብቻ ነው፡፡ጊዜ መብረሩ አይቀርም፤ ጊዜ ሲበር
እንዳያመልጠንና ወደ አላማችን እንዲበር የማድረግ ጥበብ ሊኖረን ይገባል፡፡ጊዜን መምራት አንችልም፤ይህ
ማለት ደግሞ ቀኑን ማታ፥ማታውን ቀን፤ወይም ያለፈውን ጊዜ እንዲመለስ ማድረግ አንችልም ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ማለፉ የማይቀረው“ጊዜ” ታላቅ ስጦታ ነውና ተጠቅመንበት እንዲያልፍ ማድረግ ይገባናል፡፡

በሀገራችን ጊዜን በሚመለከት ከልማዳዊ አመለካከት ጋር የተያያዘውና “የሀበሻ ቀጠሮ” በሚል ጊዜን
በአግባቡ ከመጠቀም ጋር የተያያዘው የአስተሳሰብ ችግር ከፍተኛ እንቅፋት ሆኖብናል፡፡ይህ ልማዳዊ
አስተሳሰብ ደግሞ ለብዙ መቶ አመታት የተከማቸ ጉዳይ ነው፡፡በቀላሉ ላይቀረፍ ይችላል፤በመሆኑም ችግሩን
ለመቅረፍ ትኩረትና ጊዜ ይፈልጋል፡፡

58. ከልማዳዊ አመለካከት ጋር የተያያዘው “የሀበሻ ቀጠሮ” የሚለው አባባል ምንን ያመለክታል?

A/ ጊዜን በአግባቡ መጠቀምን B/ ሀበሻ በቀጠሮ ታማኝመሆኑን

C/ ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀምን D/ ቀጠሮ አከባሪ መሆናችንን

59. ሊተካ የማይችል ሲል ምን ማለቱ ነው?

A/ ለወደ ፊት ሊገኝ የሚችል B/ ሊመለስ የማይችል C/ ሊገዛ የሚችል D/ ቆሞ የሚጠብቅ

60. የዚህ ምንባብ ርዕስ ምን ሊሆን ይችላል?

A/ እቅድ B/ ተግባር C/ አላማ D/ ጊዜ

አዘጋጆች፡-መ/ርት ወላንሳ ተካበ

መ/ርት ፋጡማ ሰዒድ

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 8
ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና 2012ዓ.ም Page 9

You might also like