Professional Documents
Culture Documents
Grade 8AA S.study
Grade 8AA S.study
ከዚህ በታች ከተሰጡት የምርጫ ጥያቄዎች ትክክለኛዉን መልስ የያዘዉን ፊደል መርጠህ/ሽ በተሰጠዉ
መልስ መስጫ ላይ ፃፍ/ፊ
1. ከዚህ በታች ከተሰጡት ዉስጥ እዉነት የሆነዉ የትኛዉ ነዉ?
A. የአፍሪካ ስፋት ከኢስያ ስፋት ይበልጣል
B. የአዉስትራሊያ ስፋት ከአፍሪካ ስፋት ይበልጣል
C. የአፍሪካ ስፋት ከአዉሮፓ ስፋት ይበልጣል
D. የአዉሮፓ ስፋት ከኢሲያ ስፋት ይበልጣል
2. በአፍሪካ ዉስጥ እጅግ ከፍተኛ ርዝመት ያለዉ ተራራ የትኛዉ ነዉ?
A. ራስ ዳሽን C. ቱሉ ዲምቱ
B. ኪሊማንጃሮ D. ከመሩን
3. ስለ ኬክሮስ መስመር ትክክል የሆነዉ የትኛዉ ነዉ?
A. ለጊዜ ስለት ያገለግላል
B. በተጨባጭ መሬት ላይ የሚታይ መስመር ነዉ
C. ከሰሜን ወደ ደቡብ ተሰምሮ ይገኛል
D. ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ተሰምሮ ይገኛል
4. ከዚህ በታች ከተሰጡት ዉስጥ አንዱ በእርሻ በሚተዳደሩ ህዝቦች አሰፋፈር ላይ ተፅዕኖ
አያመጣም
A. የአየር ንብረት C. የመሬት አቀማመጥ
B. የማዕድን ሐብት D. አፈርና እፅዋት
5. አቅጣጫን ለማመልከት የሚያገለግል የካርታ ህደገ መረጃ የትኛዉ ነዉ?
A. ቀስት C. ርዕስ
B. የሕትመት ዘመን D. እስኬል (ሚዛን)
6. 1 ሳ.ሜ = 6 ኪ ሜ. የሚለዉ እስኬል (ሚዛን) ወደ ክፍልፋይ እስኬል ሲቀየር ትክክል የሆነዉ
የትኛዉ ነዉ?
A. 1፡6000 C. 1፡600,000
B. 1፡60,000 D. 1፡6,000,000
7. ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ማዕድናት ዉስጥ በበለጠ የገፅ ምድር ይዘት የሆነዉ
A. ብረትና ኒኬል C. ሲሊካና ማግንዥየም
B. ኒኬልና ማግኒዢየም D. ሲሊካና አሉሙኒየም
8. በኢትዮጵያ ዉስጥ በጥቅም ላይ እያዋለ ያለዉ የዝቅጠት አለት ማዕድን፡-
A. አሞሌ ጨዉ C. ወርቅ
B. አልማዝ D. አሸዋ
9. የዛይር ወንዝ ቆሪ ዕፅዋትና የዱር እንስሳት የሚወክለዉ የትኛዉ ነዉ?
A. ማሆጋኒ - አንበሳ C. ቁጥቋጦ- ጉሬዛ
B. ማሆጋኒ - ዝነጀሮ D. ቁጥቋጦ- አንበሳ
10. ምንጩ የታወቀ ዉሃ በካይ የትኛዉ ነዉ?
A. በንፋስ ኃይል የሚመጣ ቆሻሻ C. ከፋብሪካ ዉስጥ የሚለቀቅ ቆሻሻ
B. በጎርፍ ኃይል የሚመጣ ቆሻሻ D. በድብቅ የሚጣል ቆሻሻ
11. D.D.T በመጠቀም የሚፈጠር ቀጥተኛ ችግር የትኛዉ ነዉ ?
A. የንቦች እልቂት C. የአረም መብዛት
B. የአፈር መሸርሸር D. የዕፅዋት ጥፋት
/
የናፍያድ ት ቤት
የ 2012 የ 8 ኛ ክፍል ሕብረተሰብ ሞዴል ፈተና
/
የናፍያድ ት ቤት
የ 2012 የ 8 ኛ ክፍል ሕብረተሰብ ሞዴል ፈተና
/
የናፍያድ ት ቤት
የ 2012 የ 8 ኛ ክፍል ሕብረተሰብ ሞዴል ፈተና
/
የናፍያድ ት ቤት
የ 2012 የ 8 ኛ ክፍል ሕብረተሰብ ሞዴል ፈተና
A. እንግሊዝ C. ፈረንሳይ
B. ቻይና D. አሜሪካ
51. አንደኛዉ ዓለም ጦርነት የተካሄደበትን ዘመናት በትክክል የሚገልፅ የትኛዉ ነዉ?
A. ከ 1914 እስከ 1918 ዓ.ም C. ከ 1939 እስከ 1945 ዓ. ም
B. ከ 1929 እስከ 1933 ዓ.ም D. ከ 1917 እስከ 1923 ዓ.ም
52. ከሚከተሉት የፖለቲካ ድርጅቱንና የድርጅቱን መሥራች (መሪ) በትክክል ያዛመደ የትኛዉ ነዉ?
A. ሶሻሊዝም - አዶልፍ ሂትለር C. ኮሙኒዝም - አዶልፍ ሂትለር
B. ፋሽዝም - ቤኒቶ ሙሶሎኒ D. ናዚ - ቪ. አይ ሌኒን
53. ቀድሞ አሻንቴ ተብላ የምትታወቀዉ የአፍሪካ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ የትኛዉ ሀገር ናት?
A. ጋና C. ናይጄሪያ
B. ማሊ D. ካሜሩን
54. ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ፍፃሜ ተከትሎ የተከሰቱት ሁለት የፖለቲካ ጎራዎች (ቡድኖች) የትኞቹ
ነበሩ?
A. ካፒታሊዝምና ፋሽዝም C. ሶሻሊዝምና ናዚ
B. ካፒታሊዝምና ኮሙኒዝም D. ሊቤራሊዝምና ሶሻሊዝም
55. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፀጥታ ምክር ቤት ቋሚ አባል ያልሆነች ሀገር,
A. ጀርመን C. አሜሪካ
B. ቻይና D. እንግሊዝ
56. የሳሞሬ ቱሬ ፀረ-ቅኝ ግዛት ዉጊያ የትኛዉን ቅኝ ገዥ ሀገር በመቃወም ተካሄደ?
A. ጣሊያን C. እንግሊዝ
B. ፈረንሳይ D. ጀርመን
57. በ 20 ኛዉ ክፍለ ዘመን መግቢያ በተካሄደዉ የቅኝ ግዛት ይዞታ ፉክክር ሞሮኮ ላይ
የተፋለሙት ቅኝ ገዥዎች የትኞቹ ነበሩ?
A. እንግሊዝና ፈረንሳይ C. ጀርመንና ፈረንሳይ
B. እንግሊዝና እስፔን D. ጣሊያንና ቤልጂየም
58. በምሥራቅ አፍሪካ ማጅማጂ ተብሎ የሚታወቀዉ ፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል የትኛዉን ቅኝ
ገዥ አገር በመቃወም ተካሄደ?
A. ፈረንሳይ C. እንግሊዝ
B. ጀርመን D. ቤልጂየም
59. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመሰረተዉ በየትኛዉ ዓመተ ምህረት ነበር?
A. በ 1943 ዓ.ም C. በ 1946 ዓ.ም
B. በ 1944 ዓ.ም D. በ 1945 ዓ.ም
60. ከሚከተሉት አንዱ የአንደኛዉ የዓለም ጦርነት ዉጤት አይደለም?
A. የኦቶማን ቱርክ ኢምፓየር መፍረስ
B. የኦስትሪያ -ሀንጋሪ ግዛት መጠናከር
C. ቬርሳይል የሰላም ስምምነት
D. የዓለም መንግሥታት ማህበር (ሊግኦፍኔሽን) መመስረት
/
የናፍያድ ት ቤት
የ 2012 የ 8 ኛ ክፍል ሕብረተሰብ ሞዴል ፈተና
/
የናፍያድ ት ቤት