You are on page 1of 2

ኢንተለክቹዋል ትምህርት ቤቶች

ስም ____________________________
የመታ.ቁ _________________ ውጤት
የአምስተኛ ክፍል አማርኛ የእረፍት ጊዜ መልመጃ
ሀ) ከዚህ በታች ለቀረቡት ጥያቄዎች ትክክል የሚሆነውን መልስ ምረጡ ፡፡
____ ፩) አንድ ድርጊት ለምን እንደተከሰተ/እንደተፈጸመ የሚነገረን ነው፡፡

ሀ) ምክኒያት ለ) ውጤት ሐ) ሳቢ መ) ሁሉም


____ ፪) ዓይነትን ግብርን መጠንን ለመግለጽ በስም ላይ የሚጨመር ቃል

ሀ) ግስ ለ) ስም ሐ) ቅፅል መ) ቃል
____ ፫) ዛሬ ፈተና መፈተን ጀመርን፡፡ በዚህ ዓ.ገር ግሱ ________________ ነው፡፡

ሀ) ጀመርን ለ) ዛሬ ሐ) መፈተን መ) ሁሉም ግስ ናቸው፡፡

____ ፬) “-እኛ ” የሚል ቅጥያ ይጨመርባቸዋል

ሀ) መጣኝ ቁጥሮች ለ) ሁሉም ቁጥሮች ሐ) የቤት ቁጥሮች መ) ደረጃ አመልካች ቁጥሮች


____ ፭) ረጃጅም ስሞችን አሳጥሮ ለመጻፍ የምንጠቀምበት ስርአተነጥብ ____________ነው፡፡

ሀ) አንድነጥብ ለ) ሰረዝ ሐ) ይዘት መ) ሀ እና ሐ መልስናቸው፡፡

____ ፮) መጣ፣ሄደች፣ቆመ፣ተቀመጠች

ሀ) ሳቢ ግስ ለ) ኢሳቢ ግስ ሐ) ቅጽል መ) ሁሉም


____ ፯) እኛ ቤት ፀጉራም ድመት አለ፡፡ የስም ገላጩ ____________ ነው፡፡

ሀ) ፀጉራም ለ) ቤት ሐ) አለ መ)ድመት

____ ፰) ድርጊት የሚያርፍበትን ሁለት ስሞች የሚወስድ

ሀ) ሳቢ ግስ ለ) ቅጽል ሐ) ኢሳቢ ግስ መ) ቅጥያ


____ ፱) የዓረፍተ ነገር መጨረሻ የሚሆን ቃል

ሀ) ስም ለ) ቅፅል ሐ) ግስ መ) ተውሳከ ግስ
____ ፲) ምክኒያት የሚያስከትለው ነገር ነው፡፡

ሀ) መግቢያ ለ) ውጤት ሐ) ሐተታ መ) ሁሉም


____ ፲፩) ከሚከተሉት ውስጥ የደን ጥቅም ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ) የአየር ጠባይን ማስተካከል፣ ለ) የከርሰምድር ወሃ እንዳይቀንስ ማድረግ፣


ሐ) አፈር በነፋስ እንዳይጠረግ ማድረግ፣ መ)ንጹህ አየር እንዳይኖር ማድረግ፣
____ ፲፪) ዋንጫ መሰል በሆነው የዳሌ አጥንት ሥር የሚገኘው የሰውነት ክፍል የትኛው ነው?

ሀ) ሳንባ ለ) ልብ ሐ) ትልቅ አንጀት መ)እንጥል


____ ፲፫) "አሹቅ" ከየትኛው የእህል ዓይነት ይዘጋጃል?

ሀ) ከገብስ ለ) ከምስር ሐ) ከባቄላ መ)ከስንዴ


____ ፲፬) የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር የሚለው በትክክል አጥሮ ሲፃፍ____________ ይሆናል፡፡

ሀ) የኢ.ሠ.ማ ለ) የኢ.ሠ.ማ. ሐ) ኢ.ሠ.ማ መ)ኢ.ሠ.ማ.


____ ፲፭) የአንድን ነገር ስንትንት የሚያሳይ ቁጥር____________ ይሆናል፡፡

ሀ) መጣኝ ቁጥር ለ) ደረጃ አመልካች ቁጥር ሐ) ሙሉ ቁጥሮች መ)ሁሉም

You might also like