You are on page 1of 5

አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ የተዘጋጀ የ 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና

መመሪያ አንድ :- ለሚከተሉት ቃላት ተመሳሳይ ፍቺ የያዘዉን መርጠህ/ሽ በመልስ መስጫ ላይ አጥቁር/ሪ
1. ተፈወሰ፡- A. ተገለጠ C. ረዳ
B. ተረዳ D. ዳነ
2. ገራ፡- A. አሰለጠነ C. ገለጠ
B. አሳወቀ D. ገደለ
3. አፈላማ :- A. አፈቀላጤ C. አፈ ጮሌ
B. የከብት ጥፋት ዕዳ D. አፈ ጉባኤ
4. አፋፍ፡- A. መሐል C. ከፍታ ላይ
B. ቤት ዉስጥ D. አፍ
5. ወጠነ :- A. ሳለ C. ወጣ
B. ወጠረ D. አቀደ
መመሪያ ሁለት፡-ከዚህ ቀጥሎ ለቀረቡት ቃላት ተቃራኒ ፍቺ የያዘዉን ፊደል በመምረጥ መልስ/ሽ
6. አቀበት፡- A. ረግረግ C. ወጣ ገባ
B. ሸለቆ D. ቁልቁለት
7. ሩሩህ፡- A. ስስታም C. ጨካኝ
B. ክፉ D. ገብጋባ
8. ወጠነ፡- A. ጀመረ C. አጠናቀቀ
B. ወሰነ D. አቀደ
9. ተከለ፡- A. ከለለ C. ጠወለገ
B. ነቀለ D. ሰጠ
10. ማርዘም፡- A. መደርደር C. መቀነስ
B. መጨመር D. ማሳጠር
መመሪያ ሦስት፡- ቀጥሎ በቀረቡት ዐ.ነገሮች ዉስጥ የተሰመረባቸዉን ቃላት ወይም ሐረጎች አገባባዊ ትርጉም ምረጥ/ጪ
11. ከዚህ ሥፍራ መራቅ ይሻላል፡፡
A. ሁኔታ C. ቦታ
B. ፍራቻ D.ጉራጉር/ስርቻ
12. እሱ ሁል ጊዜ በሆነ ባልሆነ ነገር ከሰዉ ጋር ይጋጫል
A. ይጣላል C. ይጠላል
B. ይታረቃል D. ይላተማል
13. ላንቺ ስል የማልሆነዉ ነገር የለም፡፡
A. ምስል C. ብዬ
B. ሁኔታ D.ስለት
14. የተዳፈነን ነገር መቀስቀስ አያስፈልግም፡፡
A. ማነቃቃት C. ማጭበርበር
B. ማነካካት D.ማነሳሳት
15. ስለ አትሌት ደራርቱ ሲወሳ መስማት ያስደስታል
A. ሲበሰር C. ሲተረክ
B. ሲነገር D.ሲዘመር
16. ደበላ ጥሩ ዉጤት ስላመጣ ፊቱ ፈካ
A. ጠቆረ C. ተደሰተ
B. ተረበሸ D. ተደናገጠ
17. ቶላ በሰራዉ ስራ ተፀፀተ
A. አዘነ C. ተገረመ
B. ኮራ D.ተደሰተ
18. ሐዊ ቡናዉ ሲሰክን ቀዳችዉ

/
የናፍያድ ት ቤት
አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ የተዘጋጀ የ 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና

19.
A. ሲገነፍል C. ሲንተከተክ
B. ሲጠል D. ሲፈላ
መመሪያ አራት፡- በትዕዛዙ መሰረት ትክክለኛዉን መልስ ምረጥ/ጪ
20. “አነበበ” ብሎ “ንባብ” ካለ ፃፈ ብሎ ______________ ይላል፡፡
A. አፃፃፍ C. መፃፍ
B. ፁሑፍ D.ፀሐፊ
21. “ነፃ” ብሎ “ነፃነት” ካለ “ሰዉ” ብሎ ______________ ይላል፡፡
A. ሰዋዊነት C. ሰዉነት
B. ሰዋዊ D.ሰዎች
22. “ፈለሰፈ” ብሎ “ፍልስፍና” ካለ “ደነቆረ” ብሎ ____________ ይላል
A. ድንቁርና C. ተደናቁሯል
B. ተደናቆረ D.ይደናቆራል
23. ቅጥያ የሌለዉ ቃል የትኛዉ ነዉ?
A. ሲመጣ C. ቅርስ
B. ሰዎች D.ቀጥተኛ
24. የሚጠብቅ ድምፅ ያለዉ ቃል የትኛዉ ነዉ?
A. መንፈቅ C. ዘመን
B. ነባር D. ለዉጥ
25. ድርብ ቃል ያልሆነዉ የትኛዉ ነዉ?
A. ቤተ መፃህፍት C. ማስተዋወቅ
B. ሥራ ፈት D.አቃቤ ህግ
26. አረፍተ ነገር ያልሆነዉ የትኛዉ ነዉ?
A. እያየ ዝም አለ C. ምሳዉን በላ
B. ት/ቤት ሄዶ D.ልብሱን ለበሰ
27. ጫልቱ ጎበዝ ተማሪ ናት፤ _____________ አስተማሪዎቿ ይወዷታል፡፡
A. ስለዚህ C. ይሁን እንጂ
B. ቢሆንም D.ነገር ግን
28. ብዙም አልተማረም _______________ በአስተሳሰቡ በሳል ነዉ፡፡
A. በመሆኑም C. ስለሆነም
B. ነገር ግን D.ስለዚህም
29. ልጁ ትምህርቱን ተግቶ _______________ ጥሩ ዉጤት አመጣ፡፡
A. ቢያጠናም C. ስላጠና
B. ስላላጠና D.ካጠናም
30. የሰዉየዉን ንግግር በሚገባ ያዳመጥኩ _____________ ብዙ ቁም ነገር አላገኘሁበትም
A. ስለሆነም C. ነገር ግን
B. ስለሆነ D.ቢሆንም
31. ዝናቡ እየዘነበ ______________ በፍጥነት መራመድ አለብን
A. ስለሆነ C. ግን
B. ነገር ግን D.ሲሆን
መመሪያ አምስት፡- ከዚህ ቀጥሎ ለቀረቡት ዓረፍተ ነገሮች ተስማሚዉን ሥርዓተ ነጥብ በመምረጥ መልስ/ሽ
32. ወደ ፊት ምን መሆን ትፈልጋለህ/ሽ
A. ፣ C.?
B. ፡፡ D. ፤
33. ገመቹ ጎበዝ ተማሪ ነዉ

/
የናፍያድ ት ቤት
አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ የተዘጋጀ የ 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና

A. :: C. ፤
B. ፣ D. ፡
34. ፈተናዉ ተቃርቧል ስለዚህ በርትቼ አጠናለሁ በሚለዉ ዐ.ነገር ውስጥ ተቃርቧል ከሚለዉ ቃል ቀጥሎ የሚገባዉ
ሥርዓተ ነጥብ _____________ ነዉ
A. ፣ C. ::
B. ፤ D. !
35. ከዚህ ቦታ ብትንቀሳቀስ ወዮልህ __________________
A. : C. !
B. :: D. ፣
36. ያሰብንበት ለመድረስ በዕቅድ መኖር ተገቢ ነዉ _______________
A. ፤ C.?
B. ፣ D. ::
መመሪያ ስድስት፡- ከታች ለቀረቡት ፈሊጣዊ አነጋገሮች ትክክለኛዉን ትርጉም በመምረጥ መልስ/ሽ
37. ሂያጅ ፡- A. የማይደክመዉ C. ቅናተኛ
B. አመንዝራ D. ሀሜተኛ
38. ቅጠል በጣሽ ፡- A. የባህል መድሐኒተኛ C. የልጆች ጫዋታ
B. ደን ጠባቂ D. ሳይንባዊ ሐኪም
39. ለአይን ያዘ፡- A. ጨለምለም አለ C. አይኑ ታወረ
B. ነጋ D. ወጋገን ታየ
40. ቆርጦ ቀጥል A. አዋቂ C. ዉሸታም
B. አትክልተኛ D.ሐቀኛ

41. ቅስሙ ተሰበረ ፡- A. አንገቱን አቀና C. ደስ አለዉ


B. ተስፋ ቆረጠ D. ዉሸቱ ታወቀበት

መመሪያ ሰባት፡- በጅምር የቀሩትን ምሳሌዊ አነጋገሮች በተለምዶአዊ የሚያሟሉትን አባባሎች ምረጥ/ጭ
42. ዉሻ በቀደደዉ _________________ ፡፡
A. ጫጩቶች ይወጣሉ C. ሌባ ይገባል
B. ጅብ ይገባል D. ልጆች ይወጣሉ
43. ዞሮ ዞሮ ከቤት __________________፡፡
A. አውሬ በጫካ ዉስጥ C. ኖሮ ኖሮ ከመሬት
B. ማታ ማታ ዕረፍት D. ማታ ማታ ወደ ቤት
44. ደፋርና ጭስ ___________________ አያጣም፡፡
A. መሽሎኪያ C. መተላለፊያ
B. መዉጫ D. መንደርደሪያ
45. ከሞኝ ጓሮ ________________፡፡
A. ሞፈር ይቆረጣል C. ጎበዝ ገበሬ ያርሳል
B. እሸት ይበላል D. ጎበዝ ያርስበታል
46. የሰዉ ወርቅ _________________ ፡፡
A. አይወልቅ C. አያደምቅ
B. አይሰረቅ D. አይወድቅ
መመሪያ ስምንት፡- ከቀረቡት አማራጮች ልዩ የሆነዉን ቃል ምረጥ /ጭ
47. A. ሐብል C. የጣት ቀለበት
B. የጆሮ ጌጥ D. ሰዓት
48. A. ልጃገረድ C. ጎረምሳ

/
የናፍያድ ት ቤት
አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ የተዘጋጀ የ 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና

B. ኮረዳ D. ሴት
49. A. ብርቱካን C. ስንዴ
B. ገብስ D. አጃ
50. A. ባርኔጣ C. ቆብ
B. ፎጣ D. ኮፍያ
51. A. ላም C. ኮርማ
B. ወይፈን D. በሬ

ምንባብ አንድ
ገና በልጅነት አበባዋ ሲያምር
የዉበቷ ፀዳል መፍለቅለቅ ሲጀምር
ዉጥኗን አንግባ መንገድ ስትገባ
ቀጣፊዋ በሰልፍ ይቆማል ከባቢዋ
አንድም በማታለል አልያም በጉልበቱ
ሊያጨናግፋት ሲል ሊከታት ከአዘቅቱ
መሰናክል ሆኖ ይጋረጣል ፊቷ
በወጣትነቷ ስንት አለባት ሴቷ
መመሪያ ዘጠኝ ፡- ለቀረቡት ጥያቄዎች የግጥሙን ምንባብ ብቻ መሰረት በማድረግ ትክክለኛዉን መልስ ምርጥ/ጭ
52. የግጥሙ መልዕክት ምንድን ነዉ?
A. ሴት ልጅ በቀላሉ የምትታለል መሆንዋ
B. ሴት ልጅ በልጅነቷ ውብ /ቆንጆ/ መሆንዋ
C. ሴት ልጅ በልጅነቷ በርካታ ችግሮች እንደሚገጥሟት
D. ሴት ልጅ በልጅነቷ በርካታ እቅዶች ያላት መሆንዋ
53. “ዉጥኗን አንግባ መንገድ ስትገባ” የሚለዉ ስንኝ የሚገልፀዉ ሃሳብ ምንድን ነዉ
A. ልብሷን ለብሳ ወጣ ስትል C. አምራ ስትታይ
B. እቅድ አዘጋጅታ መተግበር ስትጀምር D. ስንቋን ሰንቃ ጉዞ ስትጀምር
54. ”ስንት አለባት ሴቷ” የሚለዉ ሐረግ የሚገልፀዉ ሐሳብ ምንድነዉ?
A. ሴት ልጅ በርካታ ችግሮች ያሉባት መሆንዋ
B. ሴት ልጅ ያሉባትን ችግሮች መጠን ይጠይቃል
C. ሴት ልጅ ሃብታም መሆንዋ
D. የሴት ልጅ ችግር ጥቂት መሆኑ
55. ግጥሙ ስንት ስንኞች አሉት
A. 6 C. 5
B. 7 D. 8
ምንባብ ሁለት
ኤድስ ሁሉንም የሥራ መስክ ገቢ የሚያቃዉስ ብዙ ወጪ የሚያስከትል በሽታ ነዉ፡፡ ኤድስ በግለሰብም ሆነ በሃገር ላይ
ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ አንድ የኤድስ በሽተኛ በመታመሙ በተደጋጋሚ ከሥራ ይቀራል፡፡ ፈዉስ ማግኘት ለማይችልበት
በሽታም የህክምና ወጪ ያወጣል፡፡ ለእነዚህ ነገሮች የሚወጣዉ ወጪ ለተቀረዉ ቤተሰብ ሊቀር የሚገባዉን እሴት
ያሟጥጣል፡፡ በተጨማሪም አንድ በሽተኛ በሚሞትበት ጊዜ ለብዙ ጊዜ ያካበተዉ እዉቀትና ልምድም አብሮት ይሞታል፡፡
በደሃ አገሮች ደግሞ አንድ ሰዉ ለማሰልጠን ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ የሚከተለዉ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡
መመሪያ አስር፡- በምንባቡ መሰረት ትክክለኛዉን መልስ ምረጥ/ጭ
56. በኤድስ በሽተኛ ላይ የሚደርሰዉ ጉዳት ምንድን ነዉ?
A. የህክምና ወጪና ከስራ መቅረት
B. የመድሃኒት በዉድ ዋጋ መግዛት
C. ምንም ጉዳት እንደደረሰበት የሚገልፅ ነገር የለም
D. ጉዳት ሊደርስም ላይደርስም ይችላል
57. የምንባቡ ፍሬ ሐሳብ ምንድን ነዉ?

/
የናፍያድ ት ቤት
አማርኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ የተዘጋጀ የ 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ትምህርት ሞዴል ፈተና

A. በኤድስ የሚሞት ሰዉ እዉቀቱን ለሌሎች ያስቀራል


B. ኤድስ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያስከትላል
C. በኤድስ በሞተ ሰዉ ምትክ ሌላዉን በቀላሉ አሰልጥኖ መተካት ይቻላል
D. በኤድስ መሞት ሲቀር የቀብርና የእዝን ወጪ ይቆማል
58. አንድ የኤድስ በሽተኛ በሚሞትበት ጊዜ
A. የተለያዩ ወጪዎች ይቀንሱለታል C. ያካበተዉ ልምድና እዉቀት አብሮ ይሞታል
B. የቤተሰቡ ኑሮ እንዳይቃወስ ያደርጋል D. ሊሆን የሚችለዉ ነገር በምንባቡ አልተገለፀም
59. ‹‹ያሟጥጣል›› የሚለዉ ቃል ፍቺ ምንድን ነዉ
A. ያበዛል C. ይጨምራል
B. ይቀንሳል D. ይጨርሳል
60. ኤድስን በሚመለከት ትክክለኛዉ ሐሳብ የትኛዉ ነዉ
A. ኤድስ ሁሉንም የሥራ መስክ ገቢ ያቃዉሳል
B. ኤድስ ወጪ የማያስከትል በሽታ ነዉ
C. ኤድስ በግለሰብም ሆነ በሐገር ላይ የሚያደርሰዉ ጉዳት የለም
D. ትክክለኛዉ ሐሳብ አልተገለፀም
61. በኤድስ በሽተኛ ላይ የሚደርሱ ወጪዎች የትኞቹ ናቸዉ
A. የህክምና የቀብርና የዕዝን ወጪ C. የምግብ፣ የመጠጥና የልብስ ወጪ
B. የትምህርትና የተለያዩ ሥልጠናዎች ወጪ D. ምንም ወጪ እንደ.ሚደርስበት አልተገለፀም

/
የናፍያድ ት ቤት

You might also like