You are on page 1of 7

የ 2013 ዓ/ም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ወረዳ አቀፋዊ የአማረኛ ሞዴል ፈተና

መመሪያ አንድ፡- ከተራ ቁጥር 1-47 ለቀረቡት ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ትክክለኛ አማራጭ የያዙት ፊደል
በመምረጥ መልሱ
1. ኢትዮጵያዊ መሆን ደስ ይላል፡፡ በተሠመረበት ቃል ውስጥ ያለው ቅጥያ ምንን ያመለክታል ሀ. ፆታ
አመልካች ለ. መደብ አመልካች ሐ. ብዙ ቁጥር አመልካች መ. ወገን አመልካች
2. ልጁ ለሚለው ቃል ባለቤት አመልካች ማን ነው?
ሀ. ሩ ለ. አ ሐ. ኡ መ. ኦ
3. “ኦች” የሚለውን አብዥ ቅጥያ የሚወሰድ ቃል የቱ ነው?
ሀ. ዶሮ ለ. ላም ሐ. በሬ መ. ጎማ
4. ከሚከተሉት ውስጥ ስማዊ ሀረግ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የገብስ ጠላ ለ. በድንገት መጣ ሐ. በጣም ብርቱ መ. በጣም ገና
5. የልቦለድ አለባዊያን የሆነው የቱ ነው?
ሀ. መቼት ለ. ታሪክ ሐ. ትልም መ. ሁሉም
6. ከሚከተሉት ውስጥ የግጥም ባህሪያት ውስጥ የማይካተተው የቱ ነው?
ሀ. ቁጥብነት ለ. የቃላት ምርጫ አለመኖር ሐ. ዜማ መ. ምት
7. ጠበቀ የሚለው ቃል በ 1 ኛ መደብ ብዙ ቁጥር ሲራባ ነው?
ሀ. ጠብቃችኋል ለ. ጠበቃችሁ ሐ. ጠብቀናል መ. ጠበቁ
8. ሮቤል ቶሎና በሚለው ዓ.ነገር ውስጥ የተሠመረበት ቃል የቃል ክፍል ነው?
ሀ. ግስ ለ. ቅፅል ሐ. ተወሳከ ግስ መ. ስም
9. ከሚከተሉት ጊዜ አመልካች ግሶች ውስጥ ኢ ሃላፊ ጊዜን የሚያመለክተው የትኛው ነው?
ሀ. ግስ ለ. ቅፅል ሐ. ተወሳከ ግስ መ. ስም
10. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. መምህራኖች ለ. ቃላት ሐ. ካህናት መ. ቤቶች
11. ዝናቡ ካበራ ወደ ቤታችን እንሄዳለን፡፡ በሚለው ዐ.ነገር ውስጥ ጥገኛ ሀረጉ --------ነው፡፡
ሀ. ዝናቡ ለ. ወደቤታችን ሐ. ዝናቡ ካበራ መ. ወደ ቤታችን እንሄዳለን
12. ማስተዋል አስቸጋሪ ልጅ አይደለችም፡፡ የተሠመረበትን ቃል ተክቶ የሚገባው ተወላጠ ስም የትኛው ነው?
ሀ. አንቺ ለ. እሳቸው ሐ. እሷ መ. እናንተ
13. ከሚከተሉት ቃላት መካከል እዲስ ቃል ሊመሰረትበት የማይቻለው ቃል የትኛው ነው?
ሀ. ቆፈረ ለ. ደግ ሐ. ሰው መ. ሆኖም
14. ትምህርቷን በሚገባ ስለአጠናች በፈተናው ጥሩ ውጤት አመጣች፡፡ በሚለው ዐ.ነገር ውስጥ መደበኛ ሀረጉ
-----------ነው፡፡
ሀ. ትምህርቷን በሚገባ ለ. ስለአጠናች ሐ. በፈተናው ጥሩ ውጤት አመጣች
15. አቶ አለሙ የከተማው ከንቲባ በመሆን ተሰየሙ በሚለው ዐ.ነገር ውስጥ ለተሠመረበት ቃል አወዳዊ ፍች
-----------ነው?
ሀ. ተሾሙ ለ. ስም አገኙ ሐ. ተመረቁ መ. ተመኙ
16. ምራቁን የዋጠ ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር በፍች የሚስማመው የቱ ነው?
ሀ. አስተዋይ ለ. ጭምት ሐ. አዋቂ መ. ሁሉም
17. ከሚከተሉት አንዱ ቃላዊ ስነፅሁፍ በመባል ይታወቃል፡፡
ሀ. ስነቃል ለ. ግጥም ሐ. ኢልቦለድ መ. ልቦለድ
18. ሰውየው ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ ሆዱ ቆረጠ፡፡ ለተሠመረበት ቃል አውዳዊ ፍቺ የትኛው ነው?
ሀ. ቀነጠሰ ለ. በጠሰ ሐ. ቀጠፈ መ. ወሰነ
19. ከሚከተለው ውስጥ አንዱ ሌሎችን አካቶ የሚይዘው የትኛው ነው
ሀ. ድምፅ ለ. ምዕላድ ሐ. ቃል መ. የለም
20. ህፃኑ ልጅ ሰነፍ ወይም ጎበዝ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚለው ዐ.ነገር የተገለፀበት ጊዜ
ሀ. የአሁን ለ. የትንቢት ሐ. የሀላፊ መ. ለናሐ
21. “መጣ” የሚለው ቃል የ 3 ኛ መደብ በብዙ ቁጥር በአሉታዊ ቅርፅ ሲረባ /ሲፃፍ/
ሀ. አልመጣችም ለ. አልመጡም ሐ. አልመጣችሁም መ. አልመጣም
22. ያአንደኛ ደረጃ የወጣው ልጅ ትናንት ተሸለመ፡፡ በሚለው አ.ነገር ውስጥ ጠቋሚ መስተዓምሩ ማነው?
ሀ. አንደኛ ለ. ያ ሐ. ደረጃ መ. ትናንት
23. በተራ ቁጥር 22 ጥያቄ ላይ በተሠጠው አ.ነገር ውስጥ ደረጃ አመልካች መስተዓምሩ ማነው
ሀ. ያ ለ. ትናንት ሐ. ደረጃ መ. አንደኛ
24. በአንድ ትንፋሽ የሚነበብ የግጥም ክፍል ምን ይባላል፡፡
ሀ. ስንኝ ለ. አንጓ ሐ. አርኪ መ. ሀረግ
25. ቤት ã ሰብ የሚለውን በመነጣጠል የቀረቡትን የቃል ክፍሎች አጣምረን ስናነብ የምናገኘው ቃል
ሀ. ቤተሰቡ ለ. ቤተሰቧ ሐ. ቤተሰብ መ. ቤትስብ
26. ነበሯቸው የሚለውን ቃል ተዋቃሪዎች በምዕላድ ነጣጥለን ስናነብ የሚኖረው ክፍፍል በትክክል
የሚያሳየው የትኛው ነው?
ሀ. ነበሯ-አቸው ለ. ነበሯ -ኡ-ኦቸ-ው ሐ. ነበር -ኡ-ኣቸው መ. ነ-በር- አቸው
27. “ወንድሞችሽ” የሚለው ቃል ተዋቃሪዎች በምዕላድ ነጣጥለን ስናነብ የሚኖረው ክፍል በትክክል
የሚያሳየው የትኛው ነው?
ሀ. ወንድም-ኦች-ሽ ለ. ወንድም -ሽ- ኦች ሐ. ወንድ- ም -ኦች ሽ መ. ወ-ንድም-ኦች-ሽ
28. ዮሐናስ በሚገባ አጠና፡፡ የሚለው ቃል ወደ አሉታዊ ቅርፅ ሲቀየር? ሀ. ዮሐናስ በሚገባ አጥንቷል ለ.
ዮሐናስ በሚገባ ያጠናል ሐ. ዮሐናስ በሚገባ አላጠናም መ. ሀናለ
29. ከሚከተሉት ዘይቤዎች ውስጥ ተነፃፃሪ ዘይቤ የሆነ የቱ ነው?
ሀ. ይልቃል እንደግ በግ የዋህ ነው ለ. ሆድና ጀርባ ሐ. ልብ ገዛ መ. በሬ ወለደ
30. ከሚከተሉት ውስጥ ነባራዊ ሀቅ ሆነው የቱ ነው?
ሀ. ወተት አልወድም ሐ. ሰኞ ቀን ደስ አይለኝም
ለ. ፀሐይ በምስራቅ ትወጣለች መ. ሁሉም ሰው ማር ይወዳል
31. ታናሽ እህቴ ዛሬ ትመጣለች፡፡ በዓ.ነገሩ የተካተተው የጊዜ ተወሳከ ግስ የትኛው ነው?
ሀ. ታናሽ ለ. እህቴ ሐ. ዛሬ መ. ትመጣለች
32. ተደመመ፣ ተገረመ፣ ተላበሰ ፣ ተሰረቀ፣ በሚሉት ቃላት በመዝገበ ቃላዊ የፊደል ተራ አደራደር መሠረት
ሲፃፍ ?
ሀ. ተላበሰ ፣ ተሰረቀ ፣ ተደመመ፣ ተገረመ ሐ. ተላበሰ ፣ ተሰረቀ ፣ተገረመ፣ተደመመ
ለ. ተሰረቀ፣ ተላበሰ፣ ተገረመ፣ተደመመ መ. ተደመመ፣ ተገረመ፣ ተሰረቀ፣ ተላበሰ
33. ረጅሙ ስውዬ የአማረኛ መምህር ነው፡፡ በሙያ ሆኖ የገባው ስማዊ ሀረግ የትኛው ነው?
ሀ. ረጅሙ ለ. ሰውዬው ሐ. የአማረኛ መምህር መ. ነው
34. አስቴር በርካታ ልጆች አሏት፡፡ ሀናናን “በርካታ” ስራ ምን ሰራች፡፡ በዓ.ነገሩ ውስጥ የገባውን “በርካታ”
በተመለከተ ትክክል የሆነውን ምረጡ ?
ሀ. በመጀመሪያ ዓ.ነገር ላልቶ በሁለተኛው ደግሞ ጠብቆ ይነበባል
ለ. በሁለቱም ዓ.ነገር ጠብቆ ይነበባል ሐ. በመጀመሪያ ዓ.ነገር ጠብቆ በሁለተኛው ዓ.ነገር ላልቶ ይነበባል
መ. በሁለቱም ዓ.ነገር ላልቶ ይነበባል
35. አቶ ስዩም መረዋ ድምፅ ቢኖራቸውም የሙዚቃ ባለሙያ አይደሉም፡፡ ከስሩ ለተሰመረበት ቃል አውዳዊ
ፍቺ የትኛው ነው?
ሀ. ሳቢ ለ. ማራኪ ሐ. ያማረ መ. ሁሌም
36. በሩን የሰበረው በብዙ ምርመራ አመነ፡፡ የሚለው ዓ.ነገር ምድብ የትኛው ነው?
ሀ. ድርብ ለ. ነጠላ ሐ. ድብልቅ መ. ድርብርብ
37. ተማሪዎች በትምህርታቸው ጎበዞች ናቸው --- ቢሆንም ግን ጥሩ ውጤት አላስመዘገቡም በባዶ ቦታው
ሊገባ የሚገባውን ስርዐተ ነጥብ ምረጡ
ሀ. ፤ ለ፣ ሐ. ! መ.፡
38. ከሚከተሉት ውስጥ በክርክር መመሪያ ውስጥ አይካተትም፡፡
ሀ. ስለርዕሰ ጉዳይ ጠንቅቆ ማወቅ ሐ. የተከራካሪውን ስብዕና መንካት
ለ. መረጃ መሰብሰብ መ. የዳኘውን ውሳኔ ማክበር
39. ትናንት ራሱን የተፈነከተው ልጅ ከፍተኛ ታመመ፡፡ በዚህ ዓ. ነገር ውስጥ የሁኔታ ተወሳከ ግስ የትኛው
ነው?
ሀ. ትናንት ለ. የተፈነከተው ሐ. ልጅ መ. ከፍተኛ
40. ለማንኛውም ቶሎ መጣህ፡፡ የዚህ ዓ.ነገር ባለቤት የቱ ነው?
ሀ. እኔ ለ. እናተ ሐ. እሱ መ. አንቺ
41. ዛሬ ወይም ነገ እመጣ ይሆናል፡፡ በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ የምንን ጊዜ ይገልፃል?
ሀ. የትንቢት ለ. የሃላፊ ሐ. የሩቅ መ. የአሁን
42. ገረመው ንቁ አዕምሮ አለው -----------------ነገሮችን በቶሎ መገንዘብ ይችላል፡፡
ሀ. ስለዚህ ለ. ይሁን እንጂ ሐ. ግን መ. ነገር ግን
43. መታፈር ------ምሳሌዊ አባባሉን የሚያሟለው የትኛው ነው?
ሀ. ለመክበር ለ. በከንፈር ሐ. ለመብላት መ. ለመኖር
44. ህፃኑ ልጅ አልጋውን አነጠፈ፡፡ በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ ተሳቢው ማነው?
ሀ. ልጅ ለ. ለህፃኑ ሐ. አነጠፈ መ. አልጋውን
45. በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎች ሊያሳትፍ የሚችል የንግግር ክፍል የቱ ነው?
ሀ. ክርክር ለ. ውይይት ሐ. ጭውውት መ. የለም
46. ጨመረ ብለን ጭማሪ ካልን ሰበረ ለሚለው ቃል የምንመሰርተው ቃል የትኛው ነው?
ሀ. ሰብሮ ለ. ሰበራ ሐ. ሰባሪ መ. ሰበረ
47. ሰውየው ሆደሰፊ ነው፡፡ ለተሠመረበት ቃል ትርጉም
ሀ. ቶሎ የሚከፋው ለ. ታጋሽ ሐ. ሆዱን የሚቆርጠው መ. ሆዳም

መምሪያ ሁለት፡- ከ 48-53 የቀረቡት ጥያቄዎች በግጥሙ መሰረት መልሱ

ግጥም
ናፍቀህ የናፈቅህ፤
ብታስብ ያስበህ፤
ብትወድ የወደደህ ወዳጅ የለምና፤
ባካኙ ንብረቴ ልብ ከኔው ፅና፤
ልብ ካልኸው ልቤ ለልብህ ቁም ነገር
የወርቅ የእንቁ ምላሽ ሁኗል ድንጋይ ጠጠር፡፡
ምንጭ ፀጋዬ ገ/መድን እሳትወይ አባባ
48. ገጣሚው በግጥሙ ሊያስተላልፍ የፈለገው መልዕክት ምድን ነው?
ሀ. በሰው ማሳበብ ተገቢ ነው ሐ. ውድ የሆነ ጌጣጌጥ መግዛት ጥሩ ነው
ለ. ሰውን ከራስህ በላይ መውደድ አለብህ መ. ውድ የሆነው ህይወትህን ብትሰጥም ምላሹ የማይረባ ነው
ለዚህ ከራስ በላይ ለሰው መኖር ተገቢ አይደለም
49. ባካኙ ንብረቴ ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ገንዘቡን ለ. ብሩን ሐ. ህይወቱን መ. ሀብቱን
50. የግጥሙ አምስተኛ ስንኝ መነሻ ሀረግ የትኛው ነው?

ሀ. የወርቅ የእንቁ ምላሽ ለ. ልብ ካልኸው ልቤ ሐ. ባካኙ ንብረቴ መ. ብትወድ የወደደህ

51. ግጥሙ ስንት ስንኝ አሉት?


ሀ. 6 ለ. 7 ሐ. 10 መ. 12
52. ግጥሙ ስንት ሀረጎች አሉት?
ሀ. 12 ለ. 10 ሐ. 15 መ. 14
53. በግጥሙ ውስጥ በመጨረሻው ስንኝ ቤት የሆነው ሆሄ ማነው?
ሀ. ገ ለ. ቁ ሐ. ር መ. ና

መመሪያ ሦስት፡- 54-60 የቀረቡትን ጥያቄዎች ቀጥሎ በቀረበው ምንባብ “የሰሜን ተራራ ብሔራዊ
ፓርክ” መሰረት መልሱ

በኢትዮጵያ ከሚገኙ አንጋፋ ፓርኮች መካከል የሰሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ አንዱ ነው፡፡ ፓርኩ ከጎንደር
ከተማ በስተሰሜን 101 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ከደባርቅ ከተማ 32 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ
ይገኛል፡፡ የሰሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ 179 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት እንዳለው የሚገመት ሲሆን በፓርክነት
የተከለለው በ 1959 ዓ/ም ነው፡፡ በ 1962 ዓ.ም ደግሞ ህጋዊ እውቅና አግኝቷል፡፡ ከዘጠኝ አመታት በኋላ
በተባበሩት መንግስታት በትምህርት ሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኒስኮ/ አማካኝነት በአለም ቅርስነት መዝገብ
ላይ ተመዝግቧል፡፡

በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የሰሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ በቀዝቃዛ የአየር ንብረቱ ይታወቃል፡፡ ፓርኩ
ከባህር ወለል በላይ ከ 1900-3926 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ ተራራማ ቦታዎች የሚበዙበት የሰሜን ተራራ
ብሔራዊ ፓርክ ከፍተኛው የሙቀት መጠን ከ 12-18 ዲግሪ ሴሊሽየስ ይደርሳል፡፡ ዝቅተኛው ደግሞ ከ 3 አስከ 4
ዲግሪ ሴሊሽየስ ይደርሳል፡፡አመታዊ የዝናብ መጠኑም 1550 ሚሊ ሌትር እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

54. የሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ተራራ የተከለለው መቼ ነው?


ሀ. በ 1962 ለ. በ 1959 ሐ. በ 1958 መ. በ 1996
55. የሰሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ እውቅና ያገኘው ከስንት አመት በኋላ ነው?
ሀ. ከስምንት ለ. ከዘጠኝ ሐ. ከአስር መ.ከሰባት
56. ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ ከፍታው ከስንት አስከ ስንት ሜትር ነው?
ሀ. ከ 1900-3926 ለ. 900-4000 ሐ. 1800-3926 መ. 1900-3920
57. ፓርኩ ከደባርቅ ከተማ በስንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል?
ሀ. በ 30 ኪሎ ሜትር ለ. በ 32 ኪሎ ሜትር ሐ. በ 28 ኪሎ ሜትር መ. በ 31 ኪሎ ሜትር
58. የፓርኩ ስፋት ስንት ነው?
ሀ. 178 ካሬ ሜትር ለ. 179 ካሬ ኪ.ሜትር ሐ. 174 ኪሎ ሜትር መ. 173 ኪሎ ሜትር
59. የሰሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ የአየር ንብረት ሁኔታ ምን አይነት ነው?
ሀ. ቀዝቃዛ ለ. በርሃ ሐ. ቆላ መ. ወይና ደጋ
60. የሰሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ ዝቅተኛው የሙቀት መጠን ከስንት እስከ ስንት ነው?
ሀ. ከ 3-4 ዲግሪ ሴሊሽየስ ለ. ከ 4-3 ዲግሪ ሴሊሽየስ ሐ. ከ 2-3 ዲግሪ ሴሊሽየስ መ. ከ 3-2 ዲግሪ
ሴሊሽየስ

You might also like