You are on page 1of 1

6 ኛ ክፍል ሂሳብ ፈተና

I. ትክክል የሆነውን እውነት ስህተት የሆነውን ደግሞ ሀሰት በማለት መልሱ::


1. ለ2 ተከፋይ የሆነ ማንኛውም ሙሉ ቁጥር ተጋማሽ ሙሉ ቁጥር ይላል፡፡
2. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ6 ተከፋይ የሚሆነው ሙሉ ቁጥሩ ለ2 ተከፋይ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
3. 1 ብቸኛም ተተንታኝም ሙሉ ቁጥር አይደለም፡፡
4. ሁሉም ሙሉ ቁጥር ለ1 እና ለራሱ ተከፋይ ነው፡፡
5. ማንኛውም ከ1 የበለጠ ሙሉ ቁጥር በብቸኛ ትንተና ሊገለፅ ይችላል፡
6. ለ8 ተከፋይ የሆነ ሙሉ ቁጥር ለ4 ተከፋይ ይሆናል፡፡
7. አንድ ክፍልፋይ በዝቅተኛ ሒሳባዊ ቃል ተፅፏል የሚባለው የጠሪው እና የቆጣሪው ትልቁ የጋራ አብዥ 1 ከሆነ ብቻ ነው፡፡
8. 64,207 ለ2 ተከፋይ ነው::
9. 531,377 ለ3 ተከፋይ ነው::
10. ሁለት ብቻ አብዥዎች ያሏቸው ሙሉ ቁጥሮች ብቸኛ ሙሉ ቁጥሮች ይባላሉ፡፡
II. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ::
11. ከየሚከተሉት ሙሉ ቁጥሮች ውስጥ የ 9 ብዜት የሆነው የቱ ነው? ሀ. 36 ለ. 40 ሐ. 53 መ. 37
12. ከየሚከተሉት ሙሉ ቁጥሮች ውስጥ ለ 4 ተካፋይ የሆነው የቱ ነው? ሀ. 2365 ለ. 4000 ሐ. 5327 መ. 6437
13. ከየሚከተሉት ሙሉ ቁጥሮች ውስጥ የ 24 እና 36 ትልቁ የጋራ አብዥ የቱ ነው?

ሀ. 6 ለ. 12 ሐ. 20 መ. 24

14. ከሚከተሉት ሙሉ ቁጥሮች ውስጥ የ4 እና የ6 ትንሹን የጋራ ብዜት የሆነው የቱ ነው? ሀ. 12 ለ. 8 ሐ. 10 መ. 24


72 12 9 9 10
15. በዝቅተኛ ሂሳባዊ ቃል ሲገለፅ _________ ነው፡፡ ሀ. ለ. ሐ. መ.
88 34 11 21 30
44
16. 100
ወደ ክፍልፋይ ሲቀየር ____________ ነው፡፡ ሀ. 36% ለ. 44% ሐ. 20% መ. 24%

17. የአንድ ደብተር ዋጋ 40 ብር ቢሆን እና 10% ቅናሽ ቢደረግ፣ አንድ ደብተር ለመግዛት ስንት ብር ያስፈልጋል?

ሀ. 36 ለ. 42 ሐ. 50 መ. 24

18. አቶ ደመቀ 6,000 ብር በባንክ አስቀምጠዋል፡፡ ባንኩ በአንድ ዓመት 7% ወለድ ሊከፍል ተስማምቷል፡፡ አቶ ደመቀ ከ4 ዓመት በኋላ ስንት

ብር በባንክ ይኖራቸዋል?

ሀ. 6700 ለ. 7680 ሐ. 7550 መ. 6740

19. 5.634 ወደ ሁለት አስርዮሽ ቤት ሲጠጋጋ __________ ነው፡፡

ሀ. 5.63 ለ. 5.75 ሐ. 5.60 መ. 5.614


20. ከሚከተሉት ሙሉ ቁጥሮች መካከል ከ27,452 ላይ ተደምሮ ቁጥሩን ለ9 ተከፋይ የሚያደርገው ሙሉ ቁጥር የቱ ነው?
ሀ. 1 ለ. 2 ሐ. 7 መ. 8

You might also like