You are on page 1of 191

ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሒሳብ
የተማሪ መጽሐፍ
6ኛ ክፍል
አዘጋጆች
ግርማ ቶላ
ፅጌ መንገሻ
ታደሰ ረታ

ኤዲተሮች
ቦኪ ቶላ
ግርማ ተሾመ
ሚሊዮን በየነ
ተርጓሚዎች
ድሪባ ኃይሌ
ታየ በላይነህ
ደረጀ ድሪርሳ

ገምጋሚዎች
ጥላሁን አለሙ
ሀይሌ ዲጋ
ባኔ ቶሎሳ

ግራፊክስ
ታደሰ ድንቁ

i
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

© የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ፣ 2014/2024፡፡


ይህ መጽሐፍ በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ እና በአሰላ መምህራን
ትምህርት ኮሌጅ ትብብር በ2014/2024 ተዘጋጀ፡፡

የዚህ መጽሐፍ የባለቤትነት መብት በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከኦሮሚያ


ትምህርት ቢሮ ፈቃድ ውጪ በሙሉም ሆነ በከፊል ማሳተምም ሆነ
አባዝተው ማሰራጨት በህግ ያስጠይቃል፡፡

ii
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ማውጫ
አርዕስት ገጽ

ምዕራፍ 1፡ የሙሉ ቁጥሮች ተካፋይነት …………………….…1


1.1. ተጋማሽ እና ኢ-ተጋማሽ ቁጥሮች. ……………………………………2
1.2. የተካፋይነት ፅንሰ ሃሳብ፡- የተካፋይነት ደንቦች ……………………….3
1.3 ተካፋዮች እና አካፋዮች ……………………………………………....11
1.4 ትልቁ የጋራ አብዢ (ትጋአ) እና ትንሹ የጋራ ብዜት (ትጋብ) ፅንሰ
ሃሳብን ስራ ላይ ማዋል ...……………………………………………29

ምዕራፍ 2፡ ክፍልፋዮች፣ አሥርዮሾች እና መቶኛ ……………33


2.1. ክፍልፋይ ቁጥሮችን በዝቅተኛ ሒሳባዊ ቃል ማስቀመጥ ................ 34
2.2. ክፍልፋዮችን ወደ አሥርዮሾችና መቶኛዎች መቀየር.................... 40
2.3. አሥርዮሾችን ወደ ክፍልፋዮች እና መቶኛዎች መቀየር ................ 48
2.4. መቶኛን ወደ ክፍልፋዮችና አሥርዮሾች መቀየር ......................... 52
2.5. ክፍልፋዮችን ማወዳደር እና በቅደም ተከተል ማስቀመጥ .............. 54
2.6. የመቶኛ ፅንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ ማዋል .................................... 64

ምዕራፍ 3፡ የክፍልፋዮች እና አሥርዮሾች ስሌት…………….70


3.1 ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን መደመር....................................... 71
3.2 ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን መቀነስ......................................... 76
3.3. ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን ማባዛት ....................................... 79
3.4 ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን ማካፈል........................................ 83

ምዕራፍ 4፡ መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች እና


ወደረኝነት.. ............................................................... 89
4.1. መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ክለሳ............................... 90

iii
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.2. መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮችን በመተካት


መፍትሔ መፈለግ ............................................................... 94
4.3. ባለአንድ እርምጃ መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገርን
መፍትሔ መፈለግ ................................................................ 98
4.4. ወደረኝነት .........................................................................103
4.5. የወደረኝነት ፅንሰ ሀሳብን ስራ ላይ ማዋል ................................111

ምዕራፍ 5፡ የጠለል ምስሎች እና ጥጥሮች .………………..121


5.1. ዘዌዎች.............................................................................122
5.2. ጐነሦስቶች ........................................................................136
5.3. ጐነአራቶች ........................................................................143
5.4. ክቦች ................................................................................147
5.5. ጥጥር ምስሎች ..................................................................150
5.6. የጠለልና የጥጥር ምስሎች ፅንሰ ሃሳብን ስራ ላይ ማዋል ............156

ምዕራፍ 6፡ የዳታ አያያዝ………………………………….. 161


6.1. ዳታ የሚሰበሰብበትን ጥያቄዎች ማዘጋጀት እና ዳታን መሰብሰብ....162
6.2. ዳታን በሠንጠረዥ ማቀናጀት .................................................165
6.3 ግራፎችን መስራትና መግለፅ ..................................................169
6.4 አማካይ ዋጋ፣ተደጋጋሚ ዋጋ እና መሃል ከፋይ ዋጋ...................178
6.5 የዳታ አያያዝ ፅንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ ማዋል .............................183

iv
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ

1
የሙሉ ቁጥሮች ተካፋይነት

የመማር ውጤቶች፡ በዚህ ምዕራፍ ትምህርት ሂደት እና ማጠቃለያ ላይ፡-


• የሙሉ ቁጥሮች ተካፋይነት ደንብን ትጠቀማለህ/ሽ፡፡
• የተሰጡትን ሙሉ ቁጥሮች በብቸኛ አካፋዮች ትተነትናለህ/ሽ፡፡
• ለተሰጠ አንድ ሙሉ ቁጥር ብቸኛ አካፋዮችን ትለያለህ/ሽ፡፡
• ተጨባጭ ኘሮብሌሞችን ለመፍታት የሙሉ ቁጥሮችን አካፋይ እና
ተካፋይን ትጠቀማለህ/ሽ፡፡

መግቢያ

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የሙሉ ቁጥሮችን ተከፋይነት ትርጓሜ እና ያለ ቀሪ

ለ2፣ ለ3፣ ለ4፣ ለ5፣ ለ6፣ ለ8፣ ለ9 እና ለ10 መካፈል መቻላቸውን


የሚታረጋግጥበትን/ጪበትን ደንቦች ትማራለህ/ሽ፡፡ በተጨማሪም ስለ ብቸኛና
ተተንታኝ ሙሉ ቁጥሮች፣ የተሰጠን ሙሉ ቁጥር በብቸኛ አካፋይ ቁጥሮች
መተንተን እንዲሁም አካፋይ እና ተካፋይ ሙሉ ቁጥሮችን በመጠቀም የሙሉ
ቁጥሮች ትልቁ የጋራ አካፋይ እና ትንሹ የጋራ ተካፋይ አፈላለግ
ትማራለህ/ሽ፡፡ በመጨረሻም ትልቁን የጋራ አካፋይ እና ትንሹ የጋራ ተካፋይ
ቁጥሮችን ሥራ ላይ ማዋልን ትማራለህ/ሽ፡፡

1
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.1 ተጋማሽ እና ኢ-ተጋማሽ ቁጥሮች

መግቢያ
በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ስለ ተጋማሽ እና ኢ-ተጋማሽ ቁጥሮች በመማር
በሙሉ ቀጥሮች ተካፋይነት ጽንሰ ሃሳብ ርዕስ ስር ትጠቀምበታለህ/ሽ፡፡

ትግበራ 1.1
የአንድ ተምህርት ቤት የአራት ክፍሎች ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው
ሠንጠረዥ ውስጥ ተሰጥተዋል፡፡ በእያንዳንዱ ክፍል ያሉት ተማሪዎች
ብዛት ከፍተኛ ስለሆነ ትምህርት ቤቱ አንዱን ክፍል ሁለት ቦታ መክፈል
ፈለገ፡፡
ክፍል የተማሪዎች ብዛት
ሀ 79
ለ 86
ሐ 106
መ 95

ከእነዚህ ክፍሎች መካከል ሁለት እኩል ቦታ መከፈል የሚችሉት ክፍሎች


የትኞቹ ናቸው? ሁለት እኩል ቦታ መከፈል የማይችሉት ክፍሎች የትኞቹ
ናቸው? ለምን?
ከዚህ በላይ ካለው ትግበራ የሚከተሉትን ዐቢይ ሃሳቦች መረዳት ይቻላል፡፡
ተጋማሽ ቁጥር ማለት የአንድ ቤት ድጂት 0፣ 2፣ 4፣ 6፣ ወይም 8 የሆነ
እና ለሁለት ያለቀሪ መካፈል የሚችል ቁጥር ማለት ነው፡፡
ኢ-ተጋማሽ ቁጥር ማለት የአንድ ቤት ድጂት 1፣ 3፣ 5፣ 7፣ ወይም 9 የሆነ
እና ለሁለት ሲካፈል ቀሪው 1 የሆነ ቁጥር ማለት ነው፡፡

2
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 1
28፣ 420፣ 4564፣ 10002፣ እና የመሳሰሉት ተጋማሽ ቁጥሮች ናቸው፡፡
41፣ 45፣ 683፣ 2207፣ 55669 እና የመሳሰሉት ደግሞ ኢ-ተጋማሽ ቁጥሮች
ናቸው፡፡

አስተውል/ዪ
መ የትኛውም ሙሉ ቁጥር ከሆነ፡-
ሀ. 2መ ተጋማሽ ሙሉ ቁጠር ነው፡፡
ለ. 2መ + 1 ኢ-ተጋማሽ ሙሉ ቁጥር ነው፡፡

1.2 የተካፋይነት ፅንሰ ሃሳብ፡- የተካፋይነት ደንቦች

መግቢያ

በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር የተካፋይነት ምንነት እና ምልክት፣ እንዲሁም የሙሉ

ቁጥሮች የተካፋይነት ደንቦች ትማራለህ/ሽ፡፡

ትግበራ1.2
ረጅሙን የማካፊል ዘዴ በመጠቀም ከዚህ በታች የተሰጡትን ቁጥሮች ያለ ቀሪ
ለ4 መካፈላቸውን አረጋግጥ/ጪ፡፡
ሀ. 892 ለ. 6,123 ሐ. 12,834 መ. 3,246

አንድ ሙሉ ቁጥር ለሌላ ሙሉ ቁጥር ተካፍሎ ቀሪው ዜሮ ከሆነ፣


የተሰጠው ቁጥር ተካፋይ ሲሆን የተካፈለበት ቁጥር ደግሞ አካፋይ ይባላል፡፡
ለምሳሌ:- 16 ÷ 4 = 4፣ ቀሪው 0 ስለሆነ፣ 16, የ4 ተካፋይ ወይም 4 የ16
አካፋይ ነው እንላለን፡፡

3
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትርጓሜ 1.1
ሀ እና ለ ሙሉ ቁጥሮች ከሆኑ፣ ለ ≠ 0 እና ሀ ያለ ቀሪ ለ ለ የሚካፈል
ከሆነ፣ ለ የሀ አካፋይ ነው፡፡

በምልክት ለ|ሀ የምንለው አንድ ሙሉ ቁጥር ጠ፤ ለጠ = ሀ የሚገኝ ከሆነ


ብቻ ነው፡፡ ምልክት ለ ∤ሀ ማለት ለ የሀ አካፋይ አይደለም ማለታችን ነው፡፡
ወይም ለ ሀን አያካፍልም ማለታችን ነው፡፡

ምሳሌ 2
ሀ. 3 × 4 = 12 ስለሆነ፣ 3|12 ወይም 4|12 እንላለን፡፡
ለ. 5 × 200 = 1000 ስለሆነ፣ 5|1000 ወይም 200|1000 እንላለን፡፡
ሐ. 7 ∤ 34 ማለት 7፣ 34ን አያካፍልም፡፡ ወይም 34 የ7 ተካፋይ
አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሙሉ ቁጥር “ጠ” የእኩልነት ዓረፍተ
ነገር 7ጠ = 34 እውነት የሚያድርግ ስለሌለ ነው፡፡

አንድ ሙሉ ቁጥር ለሌላ ሙሉ ቁጥር ይካፈላል የምንለው በማካፈል ሂደት


ውስጥ ድርሻው መቁጠሪያ ቁጥር ሆኖ ከአንድ የሚበልጥ ወይም አንድ ሲሆን
እና ቀሪው 0 ከሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ 81 ለ 3 ይካፈላል፡፡

በሌላ አገላለፅ 3 የ81 አካፋይ ነው፡፡ ምክንያቱም 81 ÷ 3 = 27 ስለሆነ


ነው፡፡ ከዚህ በላይ ከተሰጠው ትርጓሜ እንደምትረዳው/ጂው ሙሉ ቁጥር ሀ
ለሙሉ ቁጥር ለ፣ ለ≠0 ሰለ መካፈል መቻሉ መጠየቅ ማለት በማካፈል ሂደት
ውስጥ የ ሀ ÷ ለ ቀሪው ዜሮ መሆኑን መጠየቅ ማለት ነው፡፡

ትግበራ 1.3
ሀ. 2,567,278 ያለ ቀሪ ለ2፣ ለ3፣ ለ4፣ ለ5፣ ይካፈላልን?
ለ. 739,344 ያለ ቀሪ ለ6፣ ለ8፣ ለ9፣ ለ10፣ ይካፈላልን?

4
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የዚህን ትግበራ መልስ ለማግኘት ብዙ ዲጀቶች ያለውን ቁጥር አንድ በአንድ


አካፍሎ ለማረጋገጥ ረጅም ጊዜ ልወሰድ ይችላል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተሰጡ የተካፋይነት ደንቦችን በማወቅ ሥራህን/ሽን


በአጭር እና ቀላል በሆነ መንገድ መስራት ትችላለህ/ሽ፡፡
ደንብ 1፡ ለ2 መካፈል መቻል

አንድ ሙሉ ቁጥር ያለ ቀሪ ለ2 የሚካፈለው የአንድ ቤት ድጂቱ ተጋማሽ


ቁጥር ከሆነ ነው፡፡ የአንድ ቤት ድጂቱ 0፣ 2 ፣ 4 ፣ 6 ወይም 8 ከሆነ ነው፡፡

ምሳሌ 3
ሀ. 350፣ 12,482፣ 68,564፣ 125,806፣ 998 የአንድ ቤት ድጂቶቻቸው
ተጋማሽ ቁጥር ስለሆኑ ለ2 ይካፈላሉ፡፡

ለ. 351፣ 12,483፣ 68,565፣ 807፣ 999 የአንድ ቤት ድጂቶቻቸው


ኢ-ታጋማሸ ቁጥሮች ስለሆኑ ለ2 አይካፈሉም፡፡
ደንብ 2፡ ለ3 መካፈል መቻል
አንድ ሙሉ ቁጥር ያለ ቀሪ ለ3 የሚካፈለው የቁጥሩ ድጂቶች ድምር ያለ
ቀሪ ለ3 ሚካፈል ከሆነ ነው፡፡

ምሳሌ 4
ሀ. 523,248 ውስጥ የድጂቶቹ ድምር፡-
5 + 2 + 3 + 2 + 4 + 8 = 24 ነው፡፡ 24 ደግሞ ለ 3 ይካፈላል፡፡ ስለዚህ
523,248 የ3 ተካፋይ ነው፡፡
ለ. 682 ውስጥ የድጂቶች ድምር፡- 6+8+2 = 16 ፡- 16 ያለቀሪ ለ3 መካፈል
አይችልም፡፡ ስለዚህ፣ 682 የሦስት ተካፋይ አይደለም፡፡

5
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ደንብ 3፡ ለ4 መካፈል መቻል


አንድ ባለ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ድጂቶች ያለው ቁጥር ለ4 መካፈል
የሚችለው በመጨረሻዎቹ ሁለት ድጂቶች የሚፈጠረው ቁጥር ለ4
የሚካፈል ከሆነ ነው፡፡
ምሳሌ 5
ሀ. 523,248 የ4 ተካፋይ ነው፡፡ ምክንያቱም በመጨረሻዎቹ ሁለት ድጂቶች
የሚፈጠረው ቁጥር፣ 48 ለ 4 ያለ ቀሪ ስለሚካፈል ነው፡፡
ለ. 7,613 የ 4 ተካፋይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በመጨረሻዎቹ ሁለት
ድጂቶች የሚፈጠረው ቁጥር፣ 13 ለ4 ስለማይካፈል ነው፡፡
ደንብ 4፡ ለ5 መካፈል መቻል
አንድ ሙሉ ቁጥር ያለቀሪ ለ5 የሚካፈለው የአንድ ቤት ድጂቱ 0 ወይም 5
ከሆነ ብቻ ነው፡፡

ምሳሌ 6
ሀ. 24,860 እና 6,365 የአንድ ቤት ድጂት ቁጥር በቅደም ተከተል 0
እና 5 ስለሆኑ ለ5 ይካፈላሉ፡፡
ለ. 126,792 የ5 ተካፋይ አይደለም፡፡ ለምን?
ደንብ 5፡ ለ6 መካፈል መቻል
አንድ ሙሉ ቁጥር ለ6 የሚካፈለው ቁጥሩ ለ2 እና ለ3 የሚካፈል ከሆነ ብቻ ነው፡፡

ምሳሌ 7
ሀ. 193,128 ተጋማሽ ቁጥር ነው፡፡ ስለዚህ ለ 2 ይካፈላል፡፡ የቁጥሩ
ድጂቶች ድምር፣ 1+ 9 + 3 + 1 + 2 + 8 = 24፣ ለ3 የሚካፈል ስለሆነ
በደንብ 5 መሠረት ለ6 ይካፈላል፡፡
ለ. 964 ለ6 ይካፈላልን? ለምን?
ሐ.1,233 የ6 ተካፋይ ነውን? ለምን?

6
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ደንብ 6፡ ለ8 መካፈል መቻል


አንድ ሙሉ ቁጥር ለ8 ይካፈላል የምንለው የቁጥሩ የመጨረሻዎቹን 3 ድጂቶች
የሚወክል ቁጥር ለ8 የሚካፈል ከሆነ ነው፡፡

ምሳሌ 8
ሀ.193,128 የ8 ተካፋይ ነው፡፡ ምክንያቱም የመጨሻዎቹ ሦስት ድጂቶች
ቁጥር 128 ለ8 ስለሚካፈል ነው፡፡
ለ. 32,614 የ8 ተካፋይ ነውን? ለምን?

ደንብ 7፡ ለ9 መካፈል መቻል


አንድ ሙሉ ቁጥር ለ9 ይካፈላል የምንለው የቁጥሩ ድጂቶች ድምር ለ9
የሚካፈል ከሆነ ነው፡፡

ምሳሌ 9
ሀ. 62,487 የ9 ተካፋይ ነው፡፡ ምክንያቱም የቁጥሩ ድጂቶች ድምር
6 + 2 + 4 + 8 + 7 = 27 ስለሆነ፣ 27 ለ9 ያለ ቀሪ ይካፈላል፡፡ ስለዚህ
62,487 የ9 ተካፋይ ነው፡፡
ለ. 193,128 የ9 ተካፋይ አይደለም፡፡ ለምን?

ደንብ 8፡ ለ10 መካፈል መቻል


አንድ ሙሉ ቁጥር ለ10 የሚካፈለው የአንድ ቤት ድጂቱ 0 ከሆነ ነው፡፡

ምሳሌ 10
ሀ. 7,680 እና 42,830 የአንድ ቤት ድጂቶቻቸው 0 ስለሆኑ ሁለቱም ለ10
ይካፈላሉ፡፡
ለ. 36,782 የ10 ተካፋይ ነውን? ለምን?

7
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የቡድን ሥራ 1.1
ከባለ ሁለት ድጂቶች ቁጥር ያለ ቀሪ ለ7 እና 8 ሊካፈል የሚችል ቁጥር የቱ
ነው?

መልመጃ 1.1
1. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ2፣ ለ3 እና ለ5 ይካፈላሉን? ለምን
እንደሆነ አብራራ/ሪ፡፡
ሀ. 14 ለ. 25 ሐ. 12,568 መ. 5,648,532
2. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ4 ይካፈላሉን? ለምን?
ሀ. 824 ለ. 53,690 ሐ. 956,456 መ. 9,485,672
3. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ8 ይካፈላሉን? ለምን?
ሀ. 33,586 ለ. 851,696 ሐ. 45,689,256 መ. 9,974,520
4. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ6 ይካፈላሉን? ለምን?
ሀ. 45,962 ለ. 78,95,616 ሐ. 6,581,232 መ. 8,888
5. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ7 ይካፈላሉን? ለምን?
ሀ. 84 ለ. 672 ሐ.8,876 መ.274,855
6. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ9 ይካፈላሉን? ለምን?
ሀ. 909 ለ.2,568 ሐ.79,065 መ. 8,469,123

7. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ10 ይካፈላሉን? ለምን?


ሀ. 86,970 ለ. 89,455 ሐ. 659,482 መ. 100,010
8. እስቲ የኦሮሚያ ልማት ማህበርና ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት በሆነ
ዓመት ውስጥ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ብዛት 384 ነበር እንበል፡፡
የተማሪዎች ብዛት እኩል በሆነ፤
ሀ. 6 ረድፍ መሰለፍ ይችላሉን? ለ. 9 ረድፍስ?
ሐ. 5 ረድፍስ? መ. 3 ረድፍስ?

8
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

9. አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ 948 መቀመጫዎች


አሉት፡፡ ከተማሪ ወላጆች ጋር ውይይት ለማድረግ ቢፈለግ ሁሉንም
መቀመጫዎች እኩል በሆነ ስድስት ረድፍ ማስቀመጥ ይቻላልን? ለምን?
10. ቁጥር 62_1 ያለ ቀሪ ለ3 የሚካፈል ከሆነ፣ በጐደለው ቦታ መግባት
የሚችሉትን ድጂቶች ዘርዝር፡፡

የድምሮች እና የልዩነቶች)፣ የብዜቶች ተካፋይነት


1. የድምሮች(የልዩነቶች) ተካፋይነት
ትግበራ 1.4
ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ ውስጥ የተሰጠውን ባዶ ቦታ ሙላ/ዪ፡፡
በ5ኛ ረድፍ ላይ ያለው መልስ ከ3ኛ እና 4ኛ ረድፎች ጋር በማስተያየት
ተመልከት/ቺ፡፡ በ5ኛ ረድፍ ውስጥ "አዎን" የሚሆነው መቼ ነው? ይህ
ማለት የሁለቱ ቁጥሮች ድምር ለ2 የሚካፈለው መቼ ነው?
ሀ ለ2 ለ ለ2 (ሀ+ ለ) ለ2 (ሀ – ለ) ለ2
ሀ ለ ይካፈላልን? ይካፈላልን? ይካፈላልን? ይካፈላልን?

15 4 አይካፈልም አዎን አይካፈልም አይካፈልም

18 16
23 21
14 12

አስተውል/ዪ
የድምሮች ወይም የልዩነቶች ተካፋይነት
ሁለት ሙሉ ቁጥሮች፡- ሀ እና ለ ሁለቱም ለመቁጠሪያ ቁጥር ”መ” የሚካፈሉ
ከሆነ፣
ሀ. የሁለቱም ድምር፣ ሀ + ለ ለ”መ” ይካፈላል፡፡

9
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለ. ሀ ≥ ለ ከሆነ፤ የሁለቱ ልዩነት ሀ — ለ ለ”መ” ይከፈላል፡፡ ይህ ማለት


በምልክት፡-
ሀ. መ|ሀ እና መ|ለ ከሆነ፣ መ|(ሀ+ለ)፡፡
ለ. መ|ሀ እና መ|ለ ከሆነ፣ መ|(ሀ — ለ)፣ሀ  ለ፡፡
ምሳሌ 11
3|27 እና 3|9 ስለዚህ 3|(27+9) እና 3|(27—9)

2. የብዜቶች ተካፋይነት
“12 × 16” ለ12 እና ለ16 ይካፈላል፡፡ ከዚህም ሌላ ይህ ብዜት ለ3 እና ለ4
እንደሚከፈል ሳናካፍል ማረጋገጥ እንችላለን፡፡
12 × 16 = (4 × 3) × 16
= 4 × (3 × 16)
= 3 × (4 × 16)
12 × 16 =12 × (4 × 4)
= (12 x 4) x 4
12 ×16 የሚካፈለው ለ12 እና ለ16 ብቻ አይደለም፡፡ ለሌሎች
ተካፋዮቻቸውም ይካፈላል፡፡

የብዜቶች ተካፋይነት
የ መ ተካፋይ ለሌላ ተካፋይ ቁጥር ወ የሚካፈል ከሆነ፣ (መ > ወ) መ ለወ
ይካፈላል፡፡

ምሳሌ 12
600 ለ4 ተካፋይ ነውን? ለምን?
መፍትሔ፡
600 = 6 ×100

10
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

100 የ4 ተካፋይ እንደሆነ ታውቃለህ/ቂያለሽ፡፡ ምክንያቱም 100 = 4×25 ስለሆነ


ነው፡፡ ስለዚህ፣ 600 የ4 ተካፋይ ነው፡፡

መልመጃ 1.2
1. የተካፋይነትን ሀሳብ በመጠቀም ከዚህ በታች ያሉትን ዓረፍተ ነገሮች
ትክክል ከሆነ እውነት ትክክል ካልሆነ ደግሞ ሐሰት ብለህ/ሽ መልስ/ሺ፡፡
ሀ. 6 | 80 ለ. 4 | 15,000
ሐ. 5 | (120 + 200) መ. 4 | (140 + 25)
ሠ. 3 | (261 − 132) ረ. 6 | (444 − 108)
2. ጠ + የ፣ ያለ ቀሪ ለ”ዘ” መካፈሉን ወይም ያለመካፈሉን ለይ/ዪ፡፡
ሀ. ጠ = 600፤ የ = 78፤ ዘ = 3
ለ. ጠ = 98፤ የ = 30፤ ዘ = 6
ሐ. ጠ = 42፤ የ = 224፤ ዘ = 7
3. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮች ለ7 ይካፈላሉን? ለምን?
ሀ. 98 ለ. 97 ሐ. 672 መ. 71,512
4. የብዜት ተካፋይነትን በመጠቀም ከዚህ በታች ያሉትን እውነት ወይም
ሐሰት ብለህ/ሽ መልስ/ሺ፡፡
ሀ. 7 | (21 × 18) ለ. 18 | (21 × 18)
ሐ. 4 | (21 × 18) መ. 3 | (21 × 18)

1.3 ተካፋዮች እና አካፋዮች


መግቢያ
ባለፈው ንዑስ ርዕስ ሥር የሙሉ ቁጥር የተካፋይነት ደንቦች እንዲሁም የድምር
ወይም የልዩነት ተካፋይነት ደንቦች ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር
የተካፋይ እና የአካፋይ ትርጓሜ እንዲሁም እንዴት እንደምንፈልጋቸው
ትማራለህ/ሽ፡፡

11
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትግበራ 1.5
1. የ2፤ የ3፤ የ5፤ የ7 የመጀመሪያዎቹን አምስት(5) ተካፋዮች ዘርዝር/ሪ፡፡
2. የ18 እና የ24 ሁሉንም አካፋዮች ዘርዝር/ሪ፡፡
1.3.1 የአካፋዮች እና የተካፋዮች ክለሳ
ቁጥሮችን ስናባዛ የተባዙት ቁጥሮች እያንዳዳቸው አካፋዮች ሲባሉ የተገኘው
ውጤት ደግሞ ብዜት ወይም ተካፋይ ይባላል፡፡

በዚህ መሰረት 28 ÷ 4 =7 እና 28 ÷ 7 = 4 ይሆናል፡፡ ስለዚህ፣ 28 ያለ


ቀሪ ለ4 እንዲሁም ለ7 ይከፈላል፡፡ በዚህ ውስጥ 4 እና 7 የ 28 አካፋዮች
ሲሆኑ፣ 28 ደግሞ የ4 እና 7 ተካፋይ ነው፡፡

ትርጓሜ 1.2
ሀ እና ለ የመቁጠሪያ ቁጥር አባሎች ከሆኑ፣ ሀ የለ ተካፋይ ነው የሚባለው
የመቁጠሪያ ቁጥር በ፣ ሀ =ለ × በ እውነት የሚያደርግ ካለ ብቻ ነው፡፡
ነገር ግን ሀ = ለ × በ እውነት የማይሆን ከሆነ፣ ሀ የበ ተካፋይ
አይደለም፡፡

ምሳሌ 13
91 የ13 ተካፋይ ነው፡፡ ምክንያቱም 13 × 7 = 91 ስለሆነ ነው፡፡
91 የ12 ተካፋይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሙሉ ቁጥር ሐ የእኩልነት
ዓረፍተ ነገር 12 × ሐ = 91 መፍትሔ የሚሆን ስለሌለ ነው፡፡
የአንድን ሙሉ ቁጥር ተካፋዮች ለማግኘት ቁጥሩን በሌሎች ሙሉ ቁጥሮች
ወይም በራሱ በማባዛት ነው፡፡

12
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለምሳሌ፡- የ6 ተካፋዩችን ለማግኘት፣ 6ን በሙሉ ቁጥሮች ከዚህ በታች


በተሰጠው ሠንጠረዥ መሰረት ታባዛለህ/ሽ፡፡
ሙሉ ቁጥር የ6 ተካፋዮች(ብዜቶች)
0 06 = 0
1 1 6 = 6
2 2  6 = 12
3 3  6 = 18
4 4  6 = 24
5 5  6 = 24
6 6  6 = 36
. .
. .
. .
16 16  6 = 96
17 17  6 = 102
18 18  6 = 108
ከዚህ በላይ ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የ6 ተካፋዮች ያለ ገደብ ይቀጥላሉ፡፡
ስለዚህ፣ የ6 ተካፋዮች(ብዜቶች) 0፣6፣12፣18፣24፣36፣42፣48፣54፣ …

አስተውል/ዪ
ከዚህ በላይ ባለው ሠንጠረዥ መሰረት የተካፋዮች በህርያት ከዚህ በታች
እንደሚከተለው መግለፅ ትችላለህ/ያለሽ፡፡
ማንኛውም ሙሉ ቁጥር የ1 ተካፋይ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ 1x5 = 5፣ 1 x 20 = 20፣1 x 35 = 35 እና የመሳሰሉት የ1 ተካፋዮች
ናቸው፡፡

1. ዜሮ ያልሆነ ማንኛውም ሙሉ ቁጥር ለራሱ ተካፋይ ነው፡፡

ለምሳሌ፣ 15 = 15 x1፣ 230 = 230 x 1 እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

13
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2. ዜሮ የማንኛውም ሙሉ ቁጥር ተካፋይ ነው፡፡ ነገር ግን የዜሮ አካፋይ


አይደለም፡፡
ለምሳሌ፡- 0 = 56 x 0፣0 = 679 x 0 እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
3. ማንኛውም ሙሉ ቁጥር 1 እና ከአንድ በላይ አካፋዮች አሉት፡፡
ምሳሌ 14
የ21 አካፋዮች፤- 1፤3፤7፤21 ናቸው፡፡
የ18 አካፋዮች፤- 1፤2፤3፤6፤9፤18 ናቸው፡፡
የ5 አካፋዮች፤- 1፤5 ናቸው፡፡
የ1 አካፋይ 1 ብቻ ነው ፡፡

መልመጃ 1.3
1. ከዚህ በታች የተሰጡት ትክክል ከሆኑ እውነት፤ ትክክል ካልሆኑ ሐሰት
በማለት መልስ/ሺ፡፡ ለመልስህ/ሽ ምክንያት ስጥ/ጪ፡፡
ሀ. 14 የ3 ተካፋይ ነው፡፡
ለ. 14 የ2 ተካፋይ ነው፡፡
ሐ. 74 የ8 ተካፋይ ነው
መ. ኢ-ታጋማሽ ቁጥር ለ2 ይካፈላል፡፡
ሠ. ለ9 የሚካፈል ሙሉ ቁጥር ለ3 ይካፈላል፡፡
ረ. ለ3 የሚካፈል ሙሉ ቁጥር ለ9 ይካፈላል፡፡
ሰ. ለ6 የሚካፈል ሙሉ ቁጥር ለ3 ይካፈላል፡፡
ሸ. ለ8 የሚካፈል ሙሉ ቁጥር ለ4 ይካፈላል፡፡
2. ሀ. በ43 እና በ92 መኸከል የሚገኙ ለ7 የሚካፈሉ ሙሉ ቁጥሮችን
ዘርዝር/ሪ፡፡
ለ. በ43 እና በ92 መኸከል የሚገኙ ለ7 የማይካፈሉ ሙሉ ቁጥሮችን
ዘርዝር/ሪ፡፡
ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ መሰረት ሀ የ ለ ተካፋይ ከሆነ፣

14
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

"√" ምልክት በመጠቀም ካልሆነ ደግሞ በ”x” በመጠቀም በተሰጠው ቦታ ላይ


በመጻፍ ለይ/ዪ፡፡

ሀ 33 97 524 95,000 262,895 0 1 0 40 39


ለ 11 7 4 10 5 13 69 0 8 9
ምልክት ′√′
ወይም ’X’
4. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች ሁሉንም አካፋዮቻቸውን ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 29 ለ. 35 ሐ. 45 መ. 36
1.3.2 ብቸኛ እና ተተንታኝ ቁጥሮች
ትግበራ 1.6
ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ ውስጥ ባዶ ቦታ ሙላ/ዪ፡፡
ቁጥር አካፋዮቸ የአካፋዮቸ ብዛት
1 1 1
2 1, 2 2
3 1, 3 2
4 1, 2, 4 3
5
6
7
8 4
9 1, 3, 9
10
11 2

ከዚህ ትግበራ ምን ትገነዘባለህ/ሽ?

15
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 14 እና ከዚህ በላይ ያለው ትግበራ 1.5 ከወሰድን አንዳንድ ሙሉ


ቁጥሮች ሁለት አካፋዮች ብቻ ሲኖራቸው፣ የቀሩት ሙሉ ቁጥሮች ከሁለት
በላይ አካፋዮች አሏቸው፡፡ አንድ አካፋይ ብቻ ያለው ቁጥር 1 ብቻ ነው፡፡
በዚህ ላይ በመመርኮዝ የሙሉ ቁጥሮችን እንደሚከተለው
እንከፍላለን/እንመድባለን፡፡

ትርጓሜ 1.3
1. ከ1 የሚበልጥ ሙሉ ቁጥር ሁለት አካፋዮች ብቻ ካሉት ብቸኛ ቁጥር
ይባላል፡፡ ሁለቱ አካፋዮቹ 1 እና እራሱ ብቻ ናቸው፡፡
2. ከ1 የሚበልጥ ሙሉ ቁጥር ከሁለት በላይ የተለያዩ አካፋዩች ካሉት ተተንታኝ
ቁጥር ይባላል፡፡
3. 0 እና 1 ብቸኛም፣ተተንታኝም ቁጥሮች አይደሉም፡፡

ምሳሌ 15
የ2 እና የ5 አካፋዮችን ተመልከት/ቺ፡፡

2 = 1 2
ስለዚህ፣ 1 እና 2 የ2 አካፋዮች ናቸው፡፡
2 = 2 1
5 = 1 5
ስለዚህ፣ 1 እና 5 የ5 አካፋዮች ናቸው፡፡
5 = 5 1
ስለዚህ፣ 2፣ 3፣ 5፣ 7፣ 11፣ 13፣ 17፣ 19፣ 23፣… ብቸኛ ቁጥሮች ናቸው፡፡
12 = 1  12
12 = 2  6
12 = 3  4
ስለዚህ, የ12 አካፋዮች 1፣2፣3፣4፣6፣12፣ ናቸው፡፡
12 = 4  3
12 = 6  2
12 = 12  1
ስለዚህ 4፣6፣8፣9፣10፣12፣14፣15፣16፣18፣20፣21፣… ተተንታኝ ቁጥሮች
ናቸው::

16
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 1.4
1. ከዚህ በታች ያሉት ዓረፍተ ነገሮች ትክክል ከሆኑ፣ እውነት ትክክል
ካልሆኑ ሐሰት በማለት ከነምክንያቱ መልስ/ሺ፡፡
ሀ. ብቸኛ የሆነ ትንሹ ሙሉ ቁጥር 2 ነው፡፡
ለ. 1 አንድ አካፋይ ብቻ አለው፡፡
ሐ. ተጋማሽ ብቸኛ ሙሉ ቁጥር 2 ነው፡፡
መ. ማንኛውም ከአንድ የሚበልጥ ሙሉ ቁጥር ቢያንስ ሁለት አካፋዮች
አሉት፡፡
ሠ. ሙሉ ቁጥሮች 0 እና 1 ብቸኛም ተተንታኝም አይደሉም፡፡
ረ. ትንሹ ብቸኛ ሙሉ ቁጥር 1 ነው፡፡
ሰ. የ180 ብቸኛ አካፋዮች 2፣3፣ እና 5 ናቸው፡፡

2. ከዚህ በታች ያሉት ቁጥሮች ብቸኛ፣ ተተንታኝ ወይም ሁለቱም


አይደሉም በማለት ላይ/ዪ፡፡
1፣7፣9፣17፣39፣123፣777፣0፣1,028፣12,889፣10,567
3. በ50 እና በ90 መኻከል የሚገኙ ብቸኛ ሙሉ ቁጥሮችን ዘርዝር/ሪ፡፡
4. በ20 እና በ100 መካከል የሚገኙ ተተንታኝ ሙሉ ቁጥሮችን ዘርዝር/ሪ::
5. በብቸኛ አካዮች ቅርንጫፍ ላይ የጐደለውን አካፋይ ሙላ/ዪ፡፡

17
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.3.3 በብቸኛ ቁጥሮች መተንተን


መግቢያ
በንዑስ ርዕስ 1.2.1 ሥር ብቸኛ ሙሉ ቁጥሮች እና ተተንታኝ ሙሉ ቁጥሮች
የሆኑትን ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ንዑሰ ርዕስ ሥር ደግሞ ተተንታኝ ሙሉ
ቁጥርን እንዴት በብቸኛ አካፋዮች መተንተን እንደሚቻል ትማራለህ/ሽ፡፡

ትግበራ 1.7
1. 125 በብቸኛ አካፋዮች ብዜት ሲገለፅ የትኛውን ይሆናል?

ሀ. 5 × 25 ለ. 5 × 3 ሐ. 53

2. ከዚህ በታች ያሉት ሙሉ ቁጥሮችን በብቸኛ አብዢ ዛፍ ግለፅ/ጪ፡፡

ሀ. 38 ለ. 92 ሐ. 250 መ. 400

አንድ ተተንታኝ የሆነ ሙሉ ቁርን እንደ ብቸኛ ሙሉ ቁጥሮች ብዜት


መግለፅ ይቻላል፡፡ አንድ ተተንታኝ ሙሉ ቁጥርን እንደ ብቸኛ ሙሉ ቁጥሮች
ብዜት ለመግለፅ በመጀመሪያ ቁጥሩን በአካፋዬቹ ብዜት በመግለፅ ጀምር/ሪ፡፡
ሁሉም አካፋዬች ብቸኛ ቁጥሮች እስኪሆኑ ድረስ ቀጥል/ዪ፡፡ (አካፋዬቹ ብቸኛ
ቁጥሮች እስኪሆኑ ድረስ ሂደቱ ይቀጥላል)፡፡

ምሳሌ 16
ሀ. 18 = 2  9 = 2  3  3

ለ. 24 = 2 12 = 2  2  6 = 2  2  2  3
ሐ. 50 = 2 × 25 = 2 × 5 × 5

መ. 120 = 2  60 = 2  2  30 = 2  2  2 15 = 2  2  2  3  5
አንድ የተሰጠ ሙሉ ቁጥር እንደ ብቸኛ አካፋዮቹ ብዜት የተፃፈ ከሆነ፣
በብቸኛ አካፋዮች ተተነተነ እንላለን፡፡

18
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 17
ከዚህ በታች የሚታዩት የአብዢ ዛፍ በተለያየ መንገድ 72ን በብቸኛ
አካፋዮች ትንተና ያሳያሉ፡፡ እነዚህም የአካፋዮች ወይም ዛፎች ይባላሉ፡፡

72 72 72 72

36 9 8 3 24 4 18
2
3 3 2 4 9
2 18 4 6 2 2 2
2 2 3 3
2 9 2 2 3
2
3 3

በሁሉም አብዢ ዛፎች በመጨረሻ ቅርንጫፎች ላይ ያሉት ብቸኛ ቁጥሮች


አቀማመጣቸው የተለያየ ቢሆንም ተመሳሳይ ናቸው፡፡

ምሳሌ 18
180 እና 126ን በብቸኛ አብዢ ዛፍ ዘዴ በመጠቀም ተንትን/ኚ፡፡

180 126

10 18 2 63

2 5 2 9 3 21

3 3 3 7

ስለዚህ በብቸኛ አብዢ ቁጥሮች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡፡


ሀ. 180 = 22 x 32 x 5
ለ. 126 = 2 x 32 x 7

የርቢን ምልክት በመጠቀም በብቸኛ አካፋይ የተገለፀ ቁጥርን መፃፍ ይቻላል፡፡

19
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሀ. 72 = 2  2  2  3  3 = 2  3
3 2

ለ. 12 = 2  2  3 = 2  3
2

ሐ.
መ.

መልመጃ 1.5
1. ከዚህ በታች የተሰጡት ቁጥሮችን በብቸኛ አካፋዮች ተንትን/ኚ፡፡

ሀ. 28 ለ. 142 ሐ. 49 መ. 83
2. ከዚህ በታች የተሰጡ ቁጥሮችን በብቸኛ አብዢ ዛፍ በመጠቀም አካፋዮች
ብቸኛ አከፋቻቸውን ፈልግ/ጊ፡፡ የሚቻል ከሆነ በርቢ ምልክት ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. 15 ለ. 46 ሐ. 122 መ. 154

3. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች ሁሉንም አካፋዮቻቸውን ፈልግ/ጊ፡፡


ሀ. 21 ለ. 75 ሐ.180 መ. 200
4. ትልቁን ብቸኛ ሙሉ ቁጥር፡-
ሀ. ከ50 በታች የሆነ ቁጥር ፈልግ/ጊ፡፡

ለ. ከ60 በታች የሆነ ቁጥር ፈልግ/ጊ፡፡

ሐ. ከ70 በታች የሆነ ቁጥር ፈልግ/ጊ፡፡

5. የጎደለውን አካፋይ ሙላ/ዪ፡፡ 2 4  ( )  5 = 720

20
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.3.4 የጋራ አካፋዮች

መግቢያ
በንዑስ ርዕሰ 1.2.1 ሥር እንዴት የሙሉ ቁጥር አካፋይን መፈለግ
እንደምትችል/ዪ ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር ደግሞ የሁለት
ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሙሉ ቁጥሮች የጋራ አካፋይ እንደሚትፈልጉ እና
ትልቁ የጋራ አካፋይ (ትጋአ) እንዴት እንደምትፈልግ/ጊ ትማራለህ/ሽ፡፡

ትግበራ 1.8
1. ሀ. የ24 እና 32 አካፋዮችን ፈልግ/ጊ፡፡

ለ. የ24 እና 32 የጋራ አካፋዮችን ፈልግ/ጊ፡፡

ሐ. የ24 እና 32 ትልቁን የጋራ አካፋይ ፈልግ/ጊ፡፡

2. ሁለት ሙሉ ቁጥሮች አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ናቸው የሚባሉት መቼ


ነው?
• የሁለት ወይም ከሁለት በላይ ሙሉ ቁጥሮች በጋራ ያላቸው አካፋዮች
የጋራ አካፋዮች ይባላሉ፡፡
• ከጋራ አካፋዮች ትልቁ የጋራ አካፋይ (ትገአ) ይባላል፡፡
• ሁለት ሙሉ ቁጥሮች ከ1 የተለየ የጋራ አካፋይ ከሌላቸው ቁጥሮቹ
አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 19
የ24 አካፋዮች ፈልግ/ጊ፡፡
መፍትሔ፡
1x24 = 24 ስለሆነ 1 እና 24 የ24 አካፋይ ናቸው::
2x12 = 24 ስለሆነ 2 እና 12 የ24 አካፋይ ናቸው::
3x8 = 24 ስለሆነ 3 እና 8 የ24 አካፋይ ናቸው::

21
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4x6 = 24 ስለሆነ 4 እና 6 የ24 አካፋይ ናቸው::


ስለዚህ የ24 አካፋዮች ፡- 1፣2፣3፣4፣6፣8፣12 እና 24 ናቸው::

ምሳሌ 20
የ36 እና የ60 የጋራ አካፋዮች እና ትልቁ የጋራ አካፋይ በመተንተን ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
የ36 አካፋዮች፡- 1፣2፣ 3፣ 4፣ 6፣ 9፣ 12 ፣ 18፣ 36 ናቸው፡፡.
የ60 አካፋዮች፡- 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5 ፣ 6፣ 10፣ 12፣ 15፣ 20፣ 30፣ 60 ናቸው፡፡.
የ36 እና የ60 የጋራ አካፋዮች፡ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 6፣ 12 ናቸው፡፡.
የ36 እና የ60 የጋራ አካፋዮች 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 6፣ 12 ናቸው::

12 ትልቁ የጋራ አካፋያቸው ነው፡፡ ይህም ሲፃፍ ትጋአ(36፣ 60) =12 ነው፡፡

ምሳሌ 21
የ180 እና የ126 ትልቁ የጋራ አብዢ በብቸኛ አካፋዮች አበዢ ዛፍ ዘዴ
በመጠቀም በብቸኛ ቁጥሮች ብዜት በመተንተን ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ

የ180 እና የ126 ብቸኛ የጋራ አካፋዮች፡- 2 እና 3 ናቸው፡፡

ስለዚህ ትልቁ የጋራ አብዢ 2 x 32 = 18 ነው፡፡

22
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 22
ቬን ዲያግራምን በመጠቀም የ180 እና 126 ትልቁን የጋራ አብዢ በብቸኛ
ቁጥሮች ትንታኔ ዘዴ ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
180 ብቸኛ አካፋዮች፡- 2×5 ×2×3 ×3
126 ብቸኛ አካፋዮች፡- 2×3×3 ×7
የ180 ብቸኛ አብዢዎች በስተ ግራ በኩል ያለው ክብ ውስጥ እና የ126 ብቸኛ
አካፋዮች ደግሞ በስተቀኝ ባለው ክብ ውስጥ ፃፍ/ፊ፡፡ የ180 እና 126
ትልቁን የጋራ አብዢ የምናገኘው የክቦቹን የጋራ ቁጥር በማብዛት ነው፡፡

የ180 እና የ126 ትልቁ የጋራ አብዢ፡- 2 x 3 x 3 = 18 ነው፡፡

ከዚህ በታች የተሰጠውን ምስል ተመልከት/ቺ፡፡

180 ብቸኛ 126 ብቸኛ

አካፋዮች አካፋዮች

ምስል 1.1
ትርጓሜ 1.4
ሁለት ሙሉ ቁጥሮች ከአንድ የተለየ የጋራ አብዢ ከሌላቸው እነዚህ ቁጥሮች
አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 23
ሀ. 45 እና 64 አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ናቸው፡፡

ለ. 21 እና 35 አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ናቸው፡፡

23
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
ሀ. የ45 አካፋዮች ፡- 1፣ 3፤5፣ 9፣ 15፣ 45 ናቸው፡፡
ለ. የ64 አካፋዮች፡- 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 8፣ 16፣ 32፣ 64 ናቸው፡፡
የ45 እና 64 የጋራ አብዢ 1 ነው፡፡
ስለዚህ 45 እና 64 አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ናቸው፡፡
ለ. የ21 አካፋዮች፡- 1፣ 3፣ 7 ናቸው፡፡
የ35 አካፋዮች፡- 1፣5፣7 ናቸው፡፡
የ21 እና 35 የጋራ አካፋዮች፡- 1፣7
የጋራ አብዢ ከ1 የተለየ ነው፡፡
ስለዚህ 21 እና 35 አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች አይደሉም፡፡
መልመጃ 1.6
1. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች የጋራ አካፋዮቻቸውን ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 54 እና 56 ለ. 138 እና 180 ሐ. 220 እና 330 መ. 36 እና 47
2. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች ትልቁን የጋራ አብዢ (ትጋአ)
በመተንተን ፈልግ/ጊ፡፡

ሀ. 24 እና 50 ለ. 44 እና 74 ሐ. 44 እና 74 መ. 70 እና 80

3. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች ብቸኛ የአብዢዎች ቅርንጫፍ


በመጠቀም ትልቁን የጋራ አብዢ(ትጋአ) ፈልግ/ጊ፡፡

ሀ. 46 ፣86 ለ. 33 ፣ 99 ሐ. 23 ፣ 40 መ. 16 ፣ 26

4. ቬን ዲያግራምን በመጠቀም የ120 እና የ135 ትልቁን የጋራ አብዢ


(ትጋአ) ፈልግ/ጊ፡፡
6. 14 እና 15 አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ናቸውን? ለምን?

24
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.3.5 የጋራ ተካፋዮች

መግቢያ
በንዑስ ርዕስ 1.2.1.ሥር ስለሙሉ ቁጥሮች ተካፋዮች እና አካፋዮች
ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚሁ ንዑስ ርዕስ ሥር የጋራ ተካፋዮች እና ትንሹን የጋራ
ተካፋይ እንዴት እንደምትፈልጉ ትማራለህ/ሽ፡፡

የቡድን ሥራ 1.2
ለዚህ ቡድን ሥራ እርሳስና እስክሪብቶ አዘጋጅ/ጂ፡፡

1. ከጓደኞቻችሁ ጋራ በመሆን ከዚህ በታች የተሰጡትን ሥሩ፡፡


ሀ. በደብተራችሁ ላይ ከ1 እስከ 50 ያሉ ሙሉ ቁጥሮችን ፃፉ፡፡

ለ. እስክሪብቶአችሁን በመጠቀም ሁሉንም የ6 ተካፋይ (ብዜት) ስር

አሰምሩ፡፡

ሐ. እርሳስ በመጠቀም ሁሉንም የ8 ተካፋይ (ብዜት) ስር አስምሩ፡፡

2. በሚቀጥሉት የመወያያ ነጥቦች ላይ ተወያዩ፡፡


ሀ. በእርሳስና እስክሪብቶ(በሁለቱም) የተሰመረበት ቁጥር የትኛው ነው?

ለ. እነዚህን ቁጥሮች እንዴት ትገልፃላችሁ?

ሐ. በእርሳስና በእስክሪብቶ (በሁለቱም) ከተሰመረባቸው ቁጥሮች ውስጥ

ከሁሉም ትንሹ የቱ ነው?ይህንን ቁጥር ምን ትሉታላችሁ?

ትርጓሜ 1.5
ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ለሆኑ መቁጠሪያ ቁጥሮች የጋራ ተካፋያቸው
ለተሰጡት ቁጥሮች ሁሉ ተካፋይ ቁጥር ነው፡፡

25
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 24
የ4 እና 5 የጋራ ተካፋይ/ዮች ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ፡
የ4 ተካፋዮች፡ 4፣8፣12፣16፣20፣24፣28፣32፣36፣40፣44፣48፣...

የ5 ተካፋዮች፡ 5፣10፣15፣20፣25፣30፣35፣40፣...

የ4 እና 5 የጋራ ተካፋዮች፡ 20፣40፣... ናቸው፡፡

ትርጓሜ 1.6
የሁለት ወይም ከሁለት በላይ ለሆኑ መቁጠሪያ ቁጥሮች ትንሹ የጋራ ብዜት
(ትጋብ) ነው፡፡

ምሳሌ 25
የ7 እና 3 ትንሹ የጋራ ብዜት (ትጋብ) በመተንተን ፈልግ/ጊ፡፡
መፍትሔ፡
የ7 ተካፋዮች፡ 7፣14፣21፣28፣35፣42፣49፣56፣…
የ3 ተካፋዮች፡ 3፣6፣9፣12፣15፣18፣21፣24፣27፣30፣33፣36፣39፣42፣…
የ7 እና የ3 የጋራ ተካፋዮች፡ 21፣42፣…

የ7 እና የ3 ትንሹ የጋራ ተካፋይ/ብዜት 21 ነው፡፡

ለተሰጡት ሙሉ ቁጥሮች ትንሹን የጋራ ተካፋይ ለመፈለግ በትንተና ዘዴ


በመጠቀም የጋራ ከሆኑ ተካፋዮች ትንሹን ቁጥር በመውሰድ ይሆናል፡፡

ከዚሁ በመቀጠል በብቸኛ ቁጥሮች ትንታኔ በመጠቀም ከሁለት እና ከሁለት


በላይ ለሆኑ ቁጥሮች ትንሹን የጋራ ተካፋይ/ብዜት እንዴት እንደምፈለግ
ትማራለህ/ሽ፡፡

በብቸኛ አካፋይ ቁጥሮች ትንተና በመጠቀም ትንሹን የጋራ ተካፋይ(ትጋተ)


ለመፈለግ፡-

26
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

i. የተሰጠውን ሙሉ ቁጥር በብቸኛ አካፋይ ሙሉ ቁጥሮች መተንተን፡፡

ii. የጋራ ብቸኛ አካፋይ ቁጥሮች ካሉ ትልቅ ርቢ ያለውን ቁጥር


መውሰድ ፡፡ የጋራ ያልሆነውንም መውሰድ፡፡

iii. በሁለተኛ እርምጃ ያገኘኸው/ሺውን ቁጥሮች በማበዛት ትንሹን የጋራ


ተካፋይ (ብዜት) መፈለግ ትችላለህ/ሽ፡፡

ምሳሌ 26
ብቸኛ አካፋዮች ትንተና ዘዴ በመጠቀም የ10 እና 12ን ትንሹን የጋራ
ተካፋይ(ትጋብ) ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ፡
i. 10 = 2  5
12 = 2  2  3 = 2 2  3
ii. 2 2  3  5 የጋራ አካፋይ ካለ ትልቁን ርቢ መውሰድ
እንዲሁም የጋራ ያልሆነውን መውሰድ ነው፡፡

iii. 2 2  3  5 = 60 (በሁለተኛ እረምጃ መሰረት ያገኘነውን የጋራ


ቁጥሮች አባዛ/ዢ)፡፡
ስለዚህ የ10 እና የ12 ትንሹ የጋራ ብዜት 60 ነው፡፡

ምሳሌ 27
በብቸኛ አካፋይ ትንተና ዘዴን በመጠቀም የ18፣ 24 እና 32 ትንሹን የጋራ
ብዜት ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
i. 18 = 2  3
2

24 = 23  3
32 = 2 5

27
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ii. 2 5  32 ብቸኛ የጋራ አካፋይ ካለ ትልቁን ርቢ መውሰድ፡፡

iii. 2 5  32 = 288 ስለዚህ፣ የ18 ፣ 24 እና የ32 ትንሹ የጋራ ብዜት 288


ነው፡፡
መልመጃ 1.7
1. ከዚህ በታች ለተሰጡት የጋራ ተካፋዮቻቸውን ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 5 እና 7 ለ. 15 እና 18 ሐ. 25 እና 30 መ. 45 እና 50
2. ከዚህ በታች የተሰጡ ቁጥሮችን በብቸኛ አካፋይ ቁጥሮች ተንትን/ኚ፡፡
ሀ. 58 ለ. 85 ሐ. 90 መ. 72

ሠ. 110 ረ. 135 ሰ. 250 ሸ. 420

3. ከዚህ በታች የተሰጡ ጥንድ ቁጥሮችን በብቸኛ አካፋዮች

በመተንተን ትንሹን የጋራ ብዜት ፈልግ/ጊ፡፡


ሀ. 15 እና 18 ለ. 14 እና 16 ሐ. 23 እና 25 መ. 7 እና 9
4. ከዚህ በታች የተሰጡት ጥንድ ቁጥሮች በብቸኛ አካፋይ ትንተና
ዘዴ በመጠቀም ትንሹን የጋራ ተካፋይ(ትጋተ) ፈልግ/ጊ፡፡

ሀ. 22፣27 ለ. 65፣86 ሐ. 130፣144 መ. 60፣80


5. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች በብቸኛ አካፋይ ትንተና ዘዴ በመጠቀም
ትንሹን የጋራ ተካፋይ ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 3፣5 እና 8 ለ. 9፣18 እና 33
ሐ. 45፣ 55 እና 49 መ. 78፣170 እና 108
6. የሁለት ቁጥሮች ትንሹ የጋራ ብዜት የሁለቱ ቁጥሮች ብዜት የሚሆነው
መቼ ነው?

28
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.4 ትልቁ የጋራ አብዢ (ትጋአ) እና ትንሹ የጋራ ብዜት (ትጋብ)


ፅንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ ማዋል
መግቢያ
በንዑስ ርዕሶች 1.2.4 እና 1.2.5 ስር ትልቁ የጋራ አካፋይ (ትጋአ) እና ትንሹ
የጋራ ተካፋይ (ትጋብ) ትርጓሜያቸውና እንዴት እንደሚሰሉ ተምረሃል/ሻል፡፡
በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ትልቁ የጋራ አብዢ(ትጋአ) እና ትንሽ የጋራ
ብዜት(ትጋብ) ቀመር እንደምትጠቀም/ሚ እና ሥራ ላይ እንዴት
እንደሚውል ትማራለህ/ሪያለሽ፡፡

ምሳሌ 28
ሦስት እናቶች ወይዘሮ መገርቱ፣ ወሮ ኩለኒ እና ወይዘሮ ጃለኔ ጡት
የሚያጠቧቸው ህፃናት አሏቸው፡፡ ወይዘሮ መገርቱ በ18 ደቂቃ ልዩነት፣
ወይዘሮ ኩለኒ በ24 ደቂቃ ልዩነት እና ወይዘሮ ጃለኔ ደግሞ በ48 ደቂቃ
ልዩነት ህፃኖቻቸውን ያጠባሉ፡፡ ሶስቱም እናቶች በተመሳሳይ ጊዜ ጡት
ማጥባት ቢጀምሩ ሶስቱም እናቶች ከስንት ደቂቃ በኋላ በተመሳሳይ ጊዜ
ህፃናቶቹን ጡት ያጠባሉ?

መፍትሔ
1. የ18 ተካፋዮች: 18፣36፣54፣72፣90፣108፣126፣144፣ …
የ24 ተካፋዮች: 24፣48፣72፣96፣120፣144፣168፣ …
የ48 ተካፋዮች: 48፣96፣144፣192፣240፣288፣ …
የ18፣ የ24 እና 48 ትንሹ የጋራ ተካፋይ 144 ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሶስቱም
እናቶች በተመሳሳይ ጊዜ ማጥባት ቢጀምሩ ከ144 ደቂቃ በኋላ ተመልሰው
በተመሳሳይ ጊዜ ህፃናቶቻቸውን ያጠባሉ፡፡

29
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 1.8
1. አንድ ቅድመ አንደኛ ደረጃ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአንድ ቅጥር
ጊቢ ውስጥ ሲሆኑ፣ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ክፍለ ጊዜ ርዝመት 30 ደቂቃ
ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ክፍለ ጊዜ ርዝመት ደግሞ 40 ደቂቃ ነው፡፡ የተለያዩ
ሁለት ደወሎች ለሁለቱም የትምህርት ደረጃ ይደወላሉ፡፡ ትምህርት
የሚጀርበት ስዓት 3 ሰዓት ከሆነ፣ ሁለቱም ደውሎች በተመሳሳይ ጊዜ
የሚደወሉት ስንት ሰዓት ላይ ነው?
2. በፊንፊኔ ከተማ ውስጥ የአውቶቢሶች መነሻ ቦታ ከመርካቶ ተመሳሰይ
ሰዓት ነው፡፡ የመጀመሪያው ከተነሳበት ቦታ የሚመለሰው በ12 የቂቃ
ልዩነት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በ18 ደቂቃ ልዩነት ከተነሳበት ቦታ
ይመለሳል፡፡ እነዚህ አውቶብሶች ከተነሱበት ተመልሰው የሚገነኙበት
ከስንት ደቂቃ በኋላ ነው?
3. ሦስት ደውሎች፣ ደ1፣ደ2፣ደ3 በተመሳሳይ ጊዜ ተደወሉ፡፡ የመጀመሪያው
ደወል (ደ1) በ6 ሰኮንድ ልዩነት ይደወላል፡፡ ሁለተኛው ደወል(ደ2) በ9 ሰኮንድ
ልዩነት እና ሶስተኛው ደወል(ደ3) ደግሞ በ12 ደቂቃ ልዩነት ይደወላል፡፡
ከስንት ሰኮንድ በኋላ ሶስቱም ደውሎች አንድ ላይ ይደወላሉ?

የምዕራፍ 1 ማጠቃለያ
1. ሀ እና ለ ሙሉ ቁጥሮች ሆነው ለ ≠ 0 ከሆኑ፣ለ የሀ አካፋይ ወይም ለ ሀን
ያካፍላል በምልክትም ለ|ሀ የምንለው ሙሉ ቁጥር ጠ ኖሮ፣
ለጠ =ሀ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ለ ∤ ሀ ማለት ለ የሀ አካፋይ አይደለም
ወይም ለ ሀ ን አያካፍልም ማለት ነው፡፡
2. የሙሉ ቁጥሮች ተካፋይነት ደንብ
I. አንድ ሙሉ ቁጥር ያለ ቀሪ ለ2 የሚካፈለው የአንድ ቤት ድጂቱ ተጋማሽ
ቁጥር ከሆነ ነው፡፡ (የአንድ ቤት ድጂቶች 0፣2፣4፣6 ወይም 8 ከሆነ ነው፡፡

30
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

II. አንድ ሙሉ ቁጥር ያለ ቀሪ ለ5 የሚካፈለው የአንድ ቤት ድጂቱ


0 ወይም 5 ከሆነ ብቻ ነው፡፡
III. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ 10 የሚከፈለው የአንድ ቤት ድጅቱ 0 ከሆነ ብቻ
ነው፡፡
IV. ማንኛው ባለ ሁለት እና ከሁለት በላይ ድጂቶች ያለው ቁጥር ለ4
የሚካፈለው የመጨረሻዎቹ ሁለት ድጂቶች የሚፈጠረው
ቁጥር ለ4 የሚከፈል ከሆነ ነው፡፡
V. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ8 ይካፈላል የምንለው የቁጥሩ የመጨረሻዎቹ
ድጂቶችን የሚወክል ቁጥር ለ8 የሚካፈል ከሆነ ነው፡፡
VI. አንድ ሙሉ ቁጥር ያለ ቀሪ ለ3 የሚካፈለው የቁጥሩ ድጂቶች ድምር
ለ3 የሚካፈል ከሆነ ነው፡፡
VII. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ9 ይካፈላል የሚንለው የቁጥሩ ዲጂቶች ድምር
ለ9 የሚካፈል ከሆነ ነው፡፡
VIII. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ2 እና ለ3 ያለ ቀሪ የሚካፈል ከሆነ ለ6
ይከፈላል፡፡
3. ሁለት አካፋዮች ብቻ ያሉት መቁጠሪያ ቁጥር ብቸኛ ቁጥር ይባላል
4. ሁለት እና ከሁለት በላይ አካፋዮች ያሉት የመቁጠሪያ ቁጥር ተተንታኝ
ቁጥር ይባላል፡፡
5. ሙሉ ቁጥሮች 0 እና 1 ብቸኛም ተተንታኝም አይደሉም፡፡
6. የሁለት ወይም ከሁለት በላይ መቁጠሪያ ቁጥሮች ትልቁ የጋራ አካፋይ
(ትጋአ) ካሏቸው የጋራ አካፋዮች ትልቁን ማለታችን ነው፡፡
7. የሁለት ወይም ከሁለት በላይ መቁጠሪያ ቁጥሮች ትንሹ የጋራ ተካፋይ
(ብዜት) ወይም (ትጋብ) ማለት ከቁጥሮቹ የጋራ ተካፋዮች ውስጥ ትንሹን
ማለት ነው፡፡
8. የሁለት መቁጠሪያ ቁጥሮች የጋራ አካፋይ ከአንድ የተለየ ካልሆነ ቁጥሮቹ
አንፃራዊ ብቸኛ ቁጥሮች ይባላሉ፡፡
9. አንድን የተሰጠ ቁጥር እንደ አካፋዮች ብዜት የሚንፅፍበት ዘዴ የአካፋዮች

31
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትንተና ይባለል፡፡ ሁሉም አካፋዮች ብቸኛ ቁጥሮች ከሆኑ ደግሞ በብቸኛ


ቁጥሮች ትንተና ዘዴ ይባላል፡፡

የምዕራፍ 1 የክለሳ መልመጃ


l g a al

1. ከዚህ በታች የተሰጡት ዓረፍተ ነገሮች ትክክል ከሆነ፣ እውነት ትክክል


ካልሆነ ደግሞ ሐሰት በማለት መልስ/ሺ፡፡
ሀ. 3 | 9 ለ. 32 | 6 ሐ. 3 የ21 አካፋይ ነው፡፡
መ. አንድ መቁጠሪያ ቁጥር ለ9 የሚካፈል ከሆነ፣ ለ3 መካፈል
ይችላል፡፡
ሠ. አንድ መቁጠሪያ ቁጥር ለ4 የሚካፈል ከሆነ፣ ለ8 መካፈል ይችላል፡፡
ረ. ማንኛውም ብቸኛ ቁጥር ኢ-ታጋማሽ ነው፡፡
2. ከመቶ በታች የሆኑ ሁሉንም የ20 ተካፋዮች ዘርዝር፡፡
3. 48ን በ3 የተለያዩ የአካፋዮች አበዢ ዛፍ ዘዴ ፃፍ/ፊ፡፡
4. ከዚህ በታች ከተሰጡት ቁጥሮች የ3፣የ4፣እና የ9 ተካፋዮች የሆኑትን ለይ/ዪ፡፡
ሀ. 123,452 ለ. 1,114,500 ሐ. 2,199,456 መ. 31,020,417
5. ለ2፣ለ4፣ለ5፣ለ6፣እና ለ12 መካፈል የሚችል ትንሹ መቁጠሪያ ቁጥር
የቱ ነው?
6. 260ን በብቸኛ አብዢዎች ትንተና ፃፍ/ፊ፡፡
7. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች ትልቁን የጋራ አካፋይ(ትጋአ) ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 48 እና 56 ለ. 60እና75
8. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች ትንሹን የጋራ ተካፋይ(ትጋብ) ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 8 እና 14 ለ. 3 እና 7 ሐ. 15 እና 20

32
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ

2 3 = 1 = 0.4
6 2
4 = 2 = 0.2
10 5

ክፍልፋዮች፣አሥርዮሾች እና መቶኛ
የመማር ውጤቶች፡ በዚህ ምዕራፍ ትምህርት ሂደት እና ማጠቃለያ ላይ፡-
• የክፍልፋዮችንና የአሥርዮሾችን ምንነት በመረዳት፣ሁለቱም አንድን
ቁጥር በተለያዩ መንገዶች የሚገልፁ መሆናቸውን ትገነዘባለህ/ሽ፡፡
• ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን የማወዳደርና በቅደም ተከተል የማስቀመጥ
ችሎታን ታዳብራለህ/ሽ፡፡
• ከክፍልፋዮች እና አሥርዮሾች ጋር ተያያዙ የቃላት ኘሮብሌሞች ላይ
ትሰራለህ/ሽ፡፡
• የተጨባጭ ኘሮብሌሞችን መፍትሔ ለመፈለግ የክፍልፋዮችንና
የአሥርዮሾችን ፅንሰ ሐሳብ ትጠቀማለህ/ሚያለሽ፡፡
• የመቶኛን ጽንሰ ሃሳብ ሥራ ላይ ታውላለህ/ሽ፡፡

መግቢያ
በ4ኛ ክፍል ውስጥ ስለ ክፍልፋዮች ዓይነት፣ ክፍልፋዮች እና አሥርዮሾችን
ማስላት እንዲሁም ስለ መቶኛ ተምረሃል/ሻል፡፡
ይህ ምዕራፍ ስለ ክፍልፋዮች በማስታወስ ክፍልፋይ ቁጥሮችን እንዴት ወደ
አሥርዮሾች እና መቶኛ፣ አሥርዮሾችን ወደ ክፍልፋይ ቁጥሮች እና መቶኛ
እንዲሁም መቶኛን ወደ ክፍልፋይ ቁጥሮች እና አሥርዮሾች መቀየር እንዴት
እንደምትችል/ዪ ትማራለህ/ያለሽ፡፡ በተጨማሪም ክፍልፋይ ቁጥሮችን

33
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ማወዳደር እና በቅደም ተከተል ማስቀመጥ እንዲሁም መቶኛን በተጨባጭ


ሥራ ላይ ማዋል ትማራለህ/ሽ፡፡

2.1. ክፍልፋይ ቁጥሮችን በዝቅተኛ ሒሳባዊ ቃል ማስቀመጥ

መግቢያ
በዚህ ርዕስ ሥር አንድን ክፍልፋይ ቁጥር እስከ መጨረሻ እንዴት በዝቅተኛ
ሒሳባዊ ቃል መግለፅ እንዲሁም አንድን ክፍልፋይ ቁጥር እንዴት በተመጣጣኝ
ክፍልፋይ ቁጥር መግለፅ እንደምትችል/ዪ ትማራለህ/ሽ፡፡
በዚህ ንዑስ ርዕስ ውስጥ ክፍልፋይ ቁጥሮች አንድ ነገርን እንደሚገልፁ
ትገነዘባለህ/ሽ፡፡ በ5ኛ ክፍል ሒሳብ ትምህርት ውስጥ ስለ ክፍልፋይ ቁጥር
የተማርከውን/ሽውን ታስታውላለህ/ያለሽ? ለማስታወስ እንዲረዳህ/ሽ ከዚህ
በታች የተሰጠውን ትግበራ ሥራ/ሪ፡፡

ትግበራ 2.1
1. ክፍልፋይ ቁጥር ምንድነው?
3
2. በክፍልፋይ ቁጥር ውስጥ ላዕሉ የቱ ነው? ታህቱስ?
14
3. ክፍልፋይ ቁጥሮች ውስጥ የትኛው፡-

ሀ. ሕገኛ ክፍልፋይ ቁጥር ነው?


ለ. ሕገኛ ክፍልፋይ አይደለም?
ሐ. ድብልቅ ክፍልፋይ ቁጥር ነው?

7
4. 3 ወደ ሕገኛ ያልሆነ ክፍልፋይ ቁጥር ቀይር/ሪ፡፡
10

34
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

15
5. ወደ ድብልቅ ክፍልፋይ ቁጥር ቀይር/ሪ፡፡
4
3
6. ከዚህ በታች የተሰጡት ክፍልፋይ ቁጥሮች ውስጥ የትኛው ከ ጋር
4
እኩል ይሆናል?
ጠ 6
7. = ከሆነ፣ የ”ጠ” ዋጋ ስንት ይሆናል?
6 36

ክፍልፋይ ቁጥር ለአንድ የሙሉ ነገር ክፋይ የተሰጠ ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
አንድ ዝርግ ሣህን (ዕቃ) ከዚህ በታች እንደተመለከተው ቁርስ የሚቀርብበት
አራት እኩል የተከፈሉ ክፍሎች አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክፍል አንድ አራተኛ
ወይም ከአራት ክፍሎች ውስጥ አንድ እጅ ነው፡፡

ትርጓሜ 2.1

ሀ እና ለ ሙሉ ቁጥሮች ሆነው ለ ≠ 0 ከሆኑ ማለት አንድን ሙሉ ነገር ለ

እኩል ቦታ ተከፍሎ ከእነዚህ ”ሀ” ክፋዮች የሚገልፅ ነው፡፡ በክፍልፋይ ቁጥር



ውስጥ “ሀ” ላዕል ሲባል፣ “ለ” ታህት ይባላል፡፡

35
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 1
1
ክፍልፋይ ቁጥር ማለት አንድ ሙሉ ነገር እኩል በሆኑ ሦስት ገሚሶች
3
የተከፈለ ሲሆን፣ ከሶስቱ ገሚሶች ውስጥ አንድ ክፋይ ማለት ነው፡፡
2
የክፍልፋይ ቁጥር ማለት አንድ ሙሉ ነገርን እኩል በሆኑ አምስት ገሚሶች
5
የተካፈለ ሲሆን ከአምስቶቹ ገሚሶች ውስጥ ሁለት ገሚሶች ማለት ነው፡፡
ክፍልፋይ ቁጥሮች፣አሥርዮሽ እና መቶኛ ላይ የሚደረግ ሥራ የዚህ ምዕራፍ
ትኩረት ነው፡፡ የአንድ ቁጥር ትንተና ሂደት ክፍልፋይ ቁጥሮችን ወደ
ዝቅተኛ የሆነ ሒሳባዊ ቃል ለመቀየር ይረዳል፡፡ የአንድ ሙሉ ክፋይ ክፍልፋይ
ቁጥሮች ማቆሚያ በሌላቸው ብዙ ክፍልፋይ ቁጥሮች ሊገለፅ ይችላል፡፡
እንደነዚህ ያሉ ክፍልፋይ ቁጥሮች ተመጣጣኝ ክፍልፋይ ቁጥሮች ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 2
2 3 4 1
ከዚህ በታች በምስል 2.1 የሚታዩት ፣ ፣ ክፍልፋይ ቁጥሮች ከ ጋር
4 6 8 2

ተመጣጣኝ ክፍልፋይ ቁጥሮች ናቸው፡፡

1
ክፍልፋይ ቁጥር በቀላል ሒሳባዊ ቃል ተቀመጠ እንላለን፡፡
2
ምክንያቱም የላዕል እና የታህት የጋራ አካፋይ ከ1 ውጪ የላቸውም፡፡

36
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2
ክፍልፋይ ቁጥር በቀላል ሒሳባዊ ቃል ተቀመጠ አንልም፡፡ ምክንያቱም
4
የላዕል እና ታህት ሁለቱም ለሁለት ስለሚካፈሉ ወይም የጋራ አካፋያቸው
ከ1 ውጪ ሌላ 2 ስላለው ነው፡፡ አንድ ክፍልፋይ ቁጥር በቀላል ሒሳባዊ ቃል
ተፃፈ የምንለው የላዕል እና የታህት ትልቁ የጋራ አካፋይ(ትጋአ) 1 እንደሆነ
መግለፅ ማለት ነው፡፡ ይህን የሚናደርገው ደግሞ ላዕልና ታህትን በትልቁ
የጋራ አብዢ (ትጋአ) በማካፈል ነው፡፡

ትርጓሜ 2.2

ክፍልፋይ ቁጥር ከሆነና ትልቁ የጋራ አካፋይ ትጋአ(ሀ፣ለ)1 ከሆነ፣

በቀላል ሒሳባዊ ቃል የተቀመጠ ክፍልፋይ ቁጥር ይባላል፡፡ ከዚህ


ትርጓሜ የምንረዳው አንድ ክፍልፋይ ቁጥር በቀላል ሒሳባዊ ቃል
ተቀመጠ የምንለው የላዕልና የታህት ትልቁ የጋራ አካፋይ(ትጋአ) 1 ሆነ
ማለት ነው፡፡

አንድን ክፍልፋይ ቁጥር በቀላል ሒሳባዊ ቃል ለመግለፅ፡-


• የላዕልና የታህት ትልቁ የጋራ አካፋይ(ትጋአ) መፈለግ፡፡
• ላዕልና ታህቱን ለትልቁ የጋራ አካፋይ(ትጋአ) ማካፈልና
የተገኘውን ክፍልፋይ ቁጥር መፃፍ ነው፡፡

ምሳሌ 3
12
በቀላል ሒሳባዊ ቃል ፃፍ/ፊ፡፡
45

37
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
እርምጃ 1፡- የ12 እና 45 ትልቁ አካፋይ ፈልግ/ጊ፡፡
የ12 አብዢዎች: 1፣2፣3፣4፣6፣12
የ45 አብዢዎች: 1፣3፣5፣9፣15፣45
የ12 እና 45 የጋራ አብዢዎች: 1፤3
የ12 እና 45 ትልቁ የጋራ አብዢ 3 ነው፡፡
እርምጃ 2: ላዕልና ታህትን ለ3 አካፍል/ዩ፡፡
(የ4 እና 15 የጋራ አካፋይ ከ1 ውጪ ሊሆን
አይችልም)
12 4
ስለዚህ በቀላል ሒሳባዊ ቃል ሲፃፍ ይሆናል፡፡
45 15
12 4
ክፍልፋይ ቁጥሮች እና ተመጣጣኝ ክፍልፋይ ቁጥሮች ይባላሉ፡፡
45 15
ተመጣጣኝ ክፍልፋይ ቁጥሮችን ለማግኘት የተሰጠውን ክፍልፋይ ቁጥር
ላዕልና ታህቱን በተመሳሳይ ቁጥር ማባዛት ወይም ማካፈል ነው፡፡
ምሳሌ 4
2 4 8 2
ተመጣጣኝ ክፍልፋይ ቁጥሮች ፣ እና ውስጥ በቀላል ሒሳባዊ
3 6 12 3
አገላለፅ የተቀመጠ ነው፡፡ ምክንያቱም የላዕልና የታህት የጋራ አካፋይ ከ1
ውጪ የለውም፡፡

ማንኛውም ሙሉ ቁጥር እንደ ክፍልፋይ ቁጥር መፃፍ እንደሚቻል


4 12 60
ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ይህም 4 = ፤ 12 = ፤ 60 =
1 1 1
የተቀሩትንም በዚሁ መልክ መግለፅ ይቻላል፡፡

38
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4 8 12 16 20
4= = = = = = ... ተመጣጣኝ ክፍልፋይ ቁጥሮች
1 2 3 4 5
60 120 180 240 300
60 = = = = = = ... ተመጣጣኝ ክፍልፋይ ቁጥሮች
1 2 3 4 5
2 3 4 5 6 20 60 240
1= = = = = = = = = ...
2 3 4 5 6 20 60 240

መልመጃ 2.1
1. ከዚህ በታች ያሉትን ክፍልፋዮች በቀላል ሒሳባዊ ቃል ፃፍ/ፊ፡፡

32 28 2 6
ሀ. ለ. ሐ. መ.
40 49 4 10
5 18 3 7
ሠ. ረ. ሰ. ሸ.
6 30 12 20
2. ከዚህ በታች የተሰጡት ሰዓቶች ስንት የአንድ ቀን ክፋዮች ይሆናሉ?
በቀላል ሒሳባዊ ቃል ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. 9 ሰአት ለ. 16 ሰአት ሐ. 20 ሰአት
3. ከዚህ በታች የተሰጡትን ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች በቀላል ሒሳባዊ ቃል የጠን
ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
15 ጠ 16 4 20 ጠ
ሀ. = ለ. = ሐ. =
45 3 28 ጠ 36 9

4. ገመቹ ከ20 የሒሳብ ሙከራ ጥያቄዎች ውስጥ 15 መለሰ፡፡


ሀ. በትክክል የመለሳቸውን ጥያቄዎች በክፍልፋይ ስጻፍ ስንት ይሆናል?
ለ. የተሳሳተውን ጥያቄዎች በክፍልፋይ ስጻፍ ስንትይሆናል?
5. ከዚህ በታች ከተሰጡት ክፍልፋዮች ውስጥ በቀላል
ሒሳባዊ ክፍልፋይ የተቀመጠው የቱ ነው?
3 39 35 48
ሀ. ለ. ሐ. መ.
9 65 49 85

39
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.2 ክፍልፋዮችን ወደ አሥርዮሾችና መቶኛዎች መቀየር


መግቢያ
በርዕስ 2.1 ሥር አንድን ክፍልፋይ እንዴት በቀላል ሒሳባዊ ቃል መፃፍ
እንደምትችል/ይ ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ርዕስ ሥር ደግሞ አንድን የተሰጠ
ክፍልፋይ እንዴት ወደ አሥርዮሾችና መቶኛዎች መቀየር እንደምትችል/ይ
ትማራለህ/ሽ፡፡
ክፍልፋይ ቁጥሮች የአንድን ሙሉ ነገር ክፋይ ለመግለፅ የሚረዳን ነው፡፡
የአንድን ሙሉ ነገር ክፋይ ለመግለፅ የሚረዳን ሌላ ቁጥር አሥርዮሽ ነው፡፡

ትግበራ 2.2
1. ከዚህ በታች የተሰጡት ክፍልፋዮች ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡
i. ላዕልን ለታህት በማካፈል ያገኘውን/ሺውን መልስ ፃፍ/ፊ፡፡
1 1 45 4 55
ሀ. ለ. ሐ. መ. ሠ.
4 2 2 5 4
ii. በ(i) የተሰጡ ከ ”ሀ - ሠ” የተሰጡ ክፍልፋይ ጥያቄዎችን
ካልኩሌተር በመጠቀም ከላይ ያገኘኸውን/ሽውን መልስ ጋር
በማስተያየት ተመልከት/ቺ፡፡
iii. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች እውነት ወይም ሐሰት
በማለት መልስ/ሺ፡፡
2 1 3 3
ሀ. = 0.4 ለ. = 0.25 ሐ. = 0.15 መ. = 0.003
5 8 20 100

በአሥርዮሽ ውስጥ ከነጥብ በፊት እንዳሉት ቁጥሮች ከነጥብ በኋላ ያሉ


ድጂቶች የቁጥር ቤት አላቸው፡፡

40
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 5
የሚከተለውን ምስል ተመልከት/ቺ::

የቡድን ሥራ 2.1
6529.3124 በቁጥሮች ቤት ፃፍ/ፊ፡፡

አንድን አሥርዮሽ ቁጥር ከነጥብ በኋላ ወደ ፈለግነው ድጂቶች ለማጠጋጋት


ከዚህ በታች የተሰጡ ደንቦችን ተከተል/ዪ፡፡ በተሰጡ አሥርዮሾች ውስጥ ከነጥብ
በኋላ የተሰጡትን ድጂቶች ውሰድ/ጂ፡፡ ማጠጋጋት የተፈለገው ድጂት 5 እና
ከ5 የሚበልጥ ከሆነ ደግሞ ወደሚጠጋበት ድጂት 1ን በመደመር በማጠጋጋት
በስተቀኝ ያሉ ቁጥሮችን ደግሞ እንተዋለን፡፡ ነገር ግን የሚጠጋጋው ድጂት ከ5
ያነሰ ከሆነ የሚጠጋጋበት ድጂት በስተቀኝ ያሉ ድጂቶችን በመተው የቀሩትን
እንወስዳለን፡፡

ምሳሌ 6
አሥርዮሽ ቁጥር 5.6274 ወደ መቶኛ ቤት አጠጋጋ/ጊ፡፡
መፍትሔ
የሺኛ ቤት ውስጥ የሚገኝ ቁጥር 7 > 5 ስለሆነ በመቶኛ ቤት ባለው
ጂት ላይ1ን በመደመር ከመቶኛ ቤት በኋላ ያሉ ድጂቶችን በመተው እንፅፋለን፡፡
ስለዚህ ቁጥር 5.6274 ወደ መቶኛ ቤት ሲጠጋጋ 5.63 ይሆናል፡፡
ይህም ማለት 5.6274 ቁጥር በማጠጋጋት ከ 5.63 ጋር እኩል ነው ወይም
5.6274 ≅ 5.63 ይሆናል፡፡ ምልክት“ ≅ ” በማጠጋጋት እኩል ነው ማለት
ነው፡፡

41
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 7
0.23241 ወደ ሺኛ ቤት አጠጋጋ/ጊ፡፡

መፍትሔ
ወደ ሺኛ ቤት ለማጠጋጋት በአሥር ሺኛ ቤት ያለውን ቁጥር ተመልከት/ቺ፡፡
በ አሥር ሺኛ ቤት ውስጥ ያለው ቁጥር 4 < 5 ስለሆነ ከሺኛ ቤት በኋላ
ያሉ ድጂቶች 41 በመተው የቀሩትን እንፅፋለን፡፡ ስለዚህ 0.23241 ወደ ሺኛ
ቤት ሲጠጋጋ 0.232 ይሆናል፡፡ ስለዚህ በማጠጋጋት 0.23241 = 0.232
ወይም 0.23241 ≅ 0.232 ይሆናል፡፡

መልመጃ 2.2
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን አሥርዮሽ ወደ አሥረኛ ቤት አጠጋጋ/ጊ፡፡
ሀ. 0.2468 ለ. 0.2768 ሐ. 0.278
2. ከዚህ በታች የተሰጡትን አሥርዮሾች ወደ መቶኛ ቤት አጠጋጋ/ጊ፡፡
ሀ. 4.6588 ለ. 3.6966 ሐ. 12.3449
3. ከዚህ በታች የተሰጡትን አሥርዮሾችን ወደ ሺኛ ቤት አጠጋጋ/ጊ፡፡
ሀ. 6.12834 ለ. 6.12874 ሐ. 10.34368

I. ክፍልፋይን ወደ አሥርዮሽ መቀየር

ክፍልፋይን ወደ አሥርዮሽ ለመቀየር ረጅም የማካፈል ዘዴን በመጠቀም


የክፍልፋዮን ላዕል ለክፍልፋዩ ታህት ማካፈል ነው፡፡


አንድ ክፍልፋይ በ መልክ ከተሰጠህ/ሽ በረጅም የማካፈል ዘዴ “ሀ” ን ለ”ለ”

በማካፈል ሊኖሩ የሚችሉ ቀሪዎች ከ”ለ” የነሱ 0፣1፣2፣3፣------፣ለ-1


ይሆናል፡፡ በረጅም የማካፈል ዘዴ ቀሪው 0 ከሆነ፣ የማካፈሉ ሂደቱ ይቆማል፡፡
የሚገኘውም አሥርዮሽ ቁጥር አክታሚ አሥርዮሽ ይባላል፡፡

42
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 8
ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡

3 5
ሀ. ለ.
5 8

መፍትሔ
ሀ. ለዕሉን ለታህት አካፍል/ዩ፡፡

ለ. ላዕሉን ለታህት አካፍል/ዩ፡፡

በማካፈል ሂደት ውስጥ ከ3ኛ እርምጃ በኋላ ማካፈሉ ቆሟል፡፡ ምክንያቱም


ቀሪው 0 ነው፡፡ ስለዚህ 0.625 አክታሚ አሥርዮሽ ነው፡፡

43
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በዚህ ምሳሌ ሀእና ለ ውስጥ ቀሪው 0 ነው ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ



በክፍልፋይ ውስጥ በረጅም የማካፈል ዘዴ “ሀ” ለ “ለ” ስናካፍል ቀሪው

0 ሳይሆን የማካፈል ሂደቱ በመቀጠል ተመሳሳይ ተደጋጋሚ ቁጥር ሊሰጠን


ይችላል፡፡ የነዚህ አይነት አሥርዮሽ ተደጋጋሚ አሥርዮሽ ይባላል፡፡

ምሳሌ 9
7
ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡
3

መፍትሔ
ተደጋጋሚ አሥርዮሽ ነው፡፡
ይህንን አሥርዮሽ ከነጥብ በኋላ ወደ አንድ
ድጂት ብናጠጋጋ 2.3 እናገኛለን፡፡ ይህንን
አሥርዮሽ ከነጥብ በኋላ ወደ ሁለት ድጂት
ብናጠጋጋ 2.33 እናገኛለን

ይህንን አሥርዮሽ ከነጥብ በኋላ ወደ 3 ድጂት


ብናጠጋጋ 2.333 ይሆናል፡፡

7 .
ስለዚህ = 2.3333... = 2. 3 ነው፡፡
3

መልመጃ 2.3
1. ካልኩሌተር በመጠቀም ከዚህ በታች የተሰጡት ክፍልዮችን ወደ አሥርዮሽ
ቀይር/ሪ፡፡
2 7 6 5
ሀ. ለ. ሐ. መ.
3 9 11 6

44
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2. በ1ኛ ተራ ቁጥር ላይ ያገኘሀውን/ሺውን አሥርዮሽ ከነጥብ በኋላ ወደ


ሁለት ድጂት ቁጥር(ወደ መቶኛ) በማጠጋጋት ፃፍ/ፊ፡፡
3. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡
2 5 7 8
ሀ. ለ. ሐ. መ.
5 6 25 125
4. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ወደ አሥርዮሽ በመቀየር አክታሚ
አሥርዮሽ ወይም ተደጋጋሚ አሥርዮሽ በማለት ላይ/ዪ፡፡
1 1 6 3
ሀ. ለ. ሐ. መ.
3 5 11 4
5. ከዚህ በታች ከተሰጡት አሥርዮሾች ውስጥ የ4 ድጂት የቤት ዋጋን
ተናገር/ሪ፡፡
ሀ. 1.412 ለ. 0.014 ሐ. 5.842 መ. 10.341
6. ከዚህ በታች የተሰጡት ድብልቅ ክፍልፋዮችን ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡
2 3 1 1
ሀ. 3 ለ. 5 ሐ. 6 መ. 7
3 4 2 5

II. ክፍልፋዮችን ወደ መቶኛ መቀየር


የቡድን ሥራ 2.2

1. በቡድን በመሆን መቶኛ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከተወያየችሁ በኋላ


የቡድን መሪያችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ ይግለፅ፡፡ በመቶኛ ምልክት አሳዩ፡፡
2. ከዚህ በታች የተሰጡ ክፍልፋዮችን ወደ መቶኛ በመቀየር በመቶኛ ምልክት
አሳይ/ዪ፡፡

1 2 7 5
ሀ. ለ. ሐ. መ.
8 5 4 6

45
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትርጓሜ 2.3
መቶኛ ማለት የአንድ ክፍልፋይ ታህት መቶ ከሆነ ነው፡፡


በምልክት በ 𝟏𝟎𝟎
= ሀ% ሲፃፍ ስሆን ሲነበብ ሀ መቶኛ ይባላል፡፡

አንድን የተሰጠ ክፍልፋይ ወደ መቶኛ ሲቀየር የክፍልፋዮን ታህት 100


ማድረግ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ የክፍልፋዮን ላዕልና ታህት አመቺ በሆነ
ተመሳሳይ ቁጥር ማባዛት አለብህ/ሽ፡፡ አንድን አሥርዮሽ ቁጥር ወደ መቶኛ
100
ለመቀየር የተሰጠውን አሥርዮሽ ቁጥር ወይም 100% ማባዛት
100
አለብህ/ሽ፡፡

ምሳሌ 10
ከዘህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ወደ መቶኛ ቀይር/ሪ፡፡
1 5 1
ሀ. ለ. ሐ.
2 8 4

መፍትሔ
1
ሀ. ወደ መቶኛ ለመቀየር ታህቱን 100 ማድረግ አለብህ/ሽ፡፡ ይህን
2
ለማድረግ ክፍልፋዮ መቀየር ስላለበት፣ ላዕሉንና ታህቱን በተመሳሳይ ቁጥር
ማባዛት ያስፈልጋል፡፡ 2 በ50 ሲባዛ ብዜቱ 100 ስለሚሆን ላዕልና ታህቱን
1 50 50 1
በ50 አባዛ/ዢ፡፡ ይህም  = = 50% (ሀምሳ መቶኛ) ፡፡ ስለዚህ
2 50 100 2
ወደ መቶኛ ሲቀየር 50% ይሆናል፡፡


በሌላ መንገድ፣ በ ን በማባዛት ወደ መቶኛ ስንቀይር፡-

46
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1 ነ ?
× = ፡፡ ታህቱን በመውሰድ 2× ነ =100
2 ነ 100

ነ = 100 ÷ 2 = 50
1 1 50 50
ስለዚህ =  = = 50%
2 2 50 100
5 ? 5 100 500 500
ለ. = ,  = = % = 62.5%
8 100 8 100 8  100 8
5
ስለዚህ ወደ መቶኛ ሲቀየር 62.5 % ይሆናል፡፡
8
1 ? 1 100 100
ሐ. = 100 × 100 = 4 % =25%
4 4
1
ስለዚህ ወደ መቶኛ ሲቀየር 25% ይሆናል፡፡
4
በሌላ መንገድ ክፍልፋይን ወደ መቶኛ ለመቀየር

ክፍልፋይን ወደ መቶኛ ለመቀየር ሌላ መንገድ አለ፡፡ ይህም የተሰጠውን


ክፍልፋይ ላዕል ለታህት ካካፈልን በኋላ የተገኘውን አሥርዮሽ በ100 በማባዛት
በመጨረሻ ላይ % ማስቀመጥ ነው፡፡

ምሳሌ 11
1
ወደ መቶኛ ቀይር/ሪ፡፡
8

መፍትሔ
ላዕል ለታህት አካፍል (1÷ 8) ድርሻውን በ100 አባዛ/ዢ፡፡ በመጨረሻ
% አሰቀመወጥ፡፡
1÷ 8 = 0.125
0.125 × 100 = 12.5
ስለዚህ 0.125 = 12.5% ነው፡፡

47
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 2.4
1. ከዚህ በታች የተሰጡ ክፍልፋዮችን በመቶኛ ፃፍ/ፊ፡፡
29 1 5 5
ሀ. ለ. ሐ. መ.
100 5 20 4
7 2 5 130
ሠ. ረ. ሰ. ሸ.
20 25 1000 650
2. 50 ኳሶችን ከያዘ ሳጥን ውስጥ 27ቱ አረንጓዴ ቀለም ተቀብቷል፡፡ አረንጓዴ
የተቀቡት ኳሶች የኳሶቹን ስንት በመቶኛ ነው?
3. ብዛታቸው 30 ከሆኑ የ6ኛ ሀ ክፍል ተማሪዎች መኻከል 16ቱ ሴቶች
ናቸው፡፡ የሴት ተማሪዎች ብዛት በመቶኛ ስንት ነው?
4. በአንድ ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ 72 አትክልቶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ
ውስጥ 36ቱ አቮካዶዎች ናቸው፡፡ ካሉት አትክልቶች ውስጥ የአቮካዶዎቹ
ብዛት በመቶኛ ስንት ይህናል?

2.3 አሥርዮሾችን ወደ ክፍልፋዮች እና መቶኛዎች መቀየር

መግቢያ
በርዕስ 2.2. ሥር ክፍልፋዮችን ወደ አሥርዮሽ እና መቶኛ እንዴት መቀየር
እንደምትችል/ይ ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ንዑስ ርዕስ ደግሞ አክታሚ አሥርዮሽን
እንዴት ወደ ክፍልፋዮችና መቶኛ መቀየር እንደሚቻል ትማራለህ/ሪያለሽ፡፡

ትግበራ 2.3
1
ከዚህ በታች ከተሰጡት አሥርዮሾች ውስጥ ከክፍልፋይ ጋር እኩል
20
የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. 0.2 ለ. 0.02 ሐ. 0.002 መ. 0.05

48
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

አክታሚ አሥርዮሽን ወደ ክፍልፋይ ለመቀየር የድጂቶች ቤትን ፅንሰ ሀሳብ


ማስታወስ ያስፈጋል፡፡
አክታሚ አሥርዮሽን ወደ ክፍልፋይ ለመቀየር
i. ከአሥርዮሽ ነጥብ በሰተግራ ያሉ ድጂቶች ሙሉ ቁጥሮችን መፃፍ፣
ii. ከአሥርዮሽ ነጥብ በስተቀኝ ያሉ ድጂቶች በቤታቸው ላይ በመመስረት
የክፍልፋዩን ታህት 10፣100፣1000፣10000፣… እንዲሆኑ መፃፍ፣
iii. ክፍልፋዮቹን በመደመር ወደ ተቃለለ ክፍልፋይ መቀየር፡፡

ምሳሌ 12
ከዚህ በታች የተሰጡ አሥርዮሾችን ወደ ክፍልፋይ ቀይር/ሪ፡፡
ሀ. 26.108 ለ. 0.0049

መፍትሔ
ሀ. ዘዴ 1፡ በትንተና

ዘዴ 2፡ 0.0049 ውስጥ ከአሥርዮሽ ነጥብ ወደ ቀኝ ያሉ ድጂቶች 4 ስለሆኑ በአሥር


ርቢ 4 ኃይለ ቁጥር(እክስፖነንት) ባለው ወይም በ 10,000 ላዕሉን እና ታህቱን
አባዛ/ዢ፡፡

49
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

10,000 49
ይህም 0.0049 = 0.0049  =
10,000 10,000

መልመጃ 2.5
ከሀ እስከ ሠ ያሉ አሥርዮሾችን፣

i. በትንተና ዘዴ ወደ ክፍልፋይ ቀይር/ሪ፡፡

ii. በአሥር ርቢ ዘዴ በማባዛት ወደ ክፍልፋይ ቀይር/ሪ፡፡


ሀ. 0.35 ለ. 0.81 ሐ. 0.9 መ. 0.06 ሠ. 0.6

እስካሁን አክታሚ አሥርዮሽን ወደ ክፍልፋይ መቀየር ተምረሃል/ሻል፡፡ በመቀጠል


ደግሞ አክታሚ አሥርዮሾችን ወደ መቶኛ መቀየር ትማራለህ/ሪያለሽ፡፡

አስተውል/ዪ
100
አክታሚ አሥርዮሾችን ወደ መቶኛ ለመቀየር አሥርዮሹን በ ማባዛት ነው፡፡
100
በ100 በማባዛት በመጨረሻ ላይ በ % ማስቀመጥ ነው፡፡

ምሳሌ 13
ከዚህ በታች የተሰጡ አሥርዮሾችን ወደ መቶኛ ቀይር/ሪ፡፡

ሀ. 0.36 ለ. 0.852 ሐ. 0.025 መ.12.6

መፍትሔ
100 36
ሀ. 0.36 = 0.36  = = 36%
100 100
100 85.2 1 1
ለ. 0.852 = 0.852  = = 85.2% = 85 % ( = 0.2 ስለሆነ)::
100 100 5 5
100 2.5
ሐ. 0.025 = 0.025  = = 2.5%
100 100
100 1260
መ. 12.6 = 12.6  = = 1260%
100 100

50
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 14
የሬክታንግል ስፋት ሞዴልን በመጠቀም አሥርዮሽ 0.64 በመቶኛ ግለፅ/ጪ፡፡

መፍትሔ
64
0.64 = = 64%
100
64 16
= ,
100 25
16
ስለዚህ = 64%
25

መልመጃ 2.6
ከዚህ በታች የተሰጡትን አሥርዮሾች ወደ መቶኛ ቀይር/ሪ፡፡
ሀ. 0.35 ለ. 0.6 ሐ. 0.001 መ. 0.08
ሠ. 0.125 ረ. 12.56 ሰ. 24.001 ሸ. 1.001

51
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.4 መቶኛን ወደ ክፍልፋዮችና አሥርዮሾች መቀየር

መግቢያ
በርዕስ 2.3 ስር አሥርዮሾችን ወደ ክፍልፋዮችና ወደ መቶኛ እንዴት መቀየር
እንደምትችል/ዪ ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ርዕስ ስር ደግሞ መቶኛን ወደ ክፍልፋይና
ወደ አሥርዮሽ እንዴት መቀየር እንደምትችል ትማራለህ/ያለሽ፡፡

ትግበራ 2.4
1. ከዚህ በታች የተሰጡ መቶኛዎችን ወደ ክፍልፋዮች ቀይር/ሪ፡፡ ክፍልፋዮቹን
በቀላል ሒሳባዊ ቃል ፃፍ/ፊ፡፡

ሀ. 70% ለ. 65% ሐ. 92%


መ. 12% ሠ. 22.6% ረ. 10.5%
2. ከዚህ በታች የተሰጡ መቶኛዎችን ወደ አሥርዮሾች ቀይር/ሪ፡፡
ሀ. 75% ለ. 65% ሐ. 92%
መ.15% ሠ. 37.8% ረ. 46%
3. ከዚህ በታች ለተሰጡት ቁጥሮች አሥር መቶኛቸውን ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 90 ለ. 30 ሐ. 86

መቶኛ ማለት የክፍልፋዩ ታህት መቶ የሆነ ክፍልፋይ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ


መቶኛን ወደ ክፍልፋይ ለመቀየር በዚህ መልክ መፃፍ ይቻላል፡፡ መቶኛ ወደ
አሥርዮሽ ለመቀየር በመጀመሪያ በ መልክ መፃፍና ላዕልን ለ100
ማካፈል ነው፡፡

ምሳሌ 15
ሀ. 40% ወደ ክፍልፋይ ቀይር/ሪ፡፡
ለ. 40% ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡

52
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
ሀ.

ለ. 40
40% = = 40  100 = 0.4
100

ምሳሌ 16
2
ሀ. 16 % ወደ ክፍልፋይ መቀየር
5
2
ለ. 16 % ወደ አሥርዮሽ መቀየር
5
መፍትሔ

(ላእሉን ለ100 ማካፈል)


በሌላ በኩል በቀጥታ መቶኛን ወደ አሥርዮሽ ለመቀየር የመቶኛ ምልክት
”%” ከቁጥሩ አጠገብ በመተው ከቀኝ ወደ ግራ ሁለት ድጂቶችን በመውሰድ
የአሥርዮሽ ነጥብ ማስቀመጥ ነው፡፡

መልመጃ 2.7
1. እያንዳዳቸውን ከሀ—ሸ ያሉትን ክፍልፋዮች ወደ ተቃለለ ክፍልፋይ ቀይር/ሪ፡፡

ሀ. 39% ለ. 38% ሐ. 50% መ. 75%


ሠ. 5% ረ. 98% ሰ. 35% ሸ. 16%
2. እያንዳዳቸውን ከ ሀ—ሸ ያሉትን መቶኛ ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡

53
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሀ. 18% ለ. 99% ሐ. 9% መ. 2%
ሠ. 20% ረ. 50% ሰ. 23.2% ሸ. 61.78%
3. ከዚህ በታች የተሰጠውን ሠንጠረዥ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ሙላ/ዩ፡፡
መቶኛ ክፍልፋይ አሥርዮሽ
1%
0.1
1
4
50%
1.0

2.5 ክፍልፋዮችን ማወዳደር እና በቅደም ተከተል ማስቀመጥ

መግቢያ
በዚህ ርዕስ ሥር ክፍልፋዮችን እንዴት እንደምታወዳድር እና በቅደም
ተከተል እንደምታስቀምጥ/ጪ ትማራለህ/ያለሽ፡፡ ክፍልፋዮችን ማወዳደር ማለት
የትኛው ክፍልፋይ ትልቅ ወይም ትንሽ እንደሆነ መለየት ማለት ነው፡፡
ክፍልፋዮችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ማለት ደግሞ ከትንሽ ወደ ትልቅ
ወይም ከትልቅ ወደ ትንሽ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡

ትግበራ 2.5
1. ከተቀባው የስፍራ ስፋት ጋር ተመጣጣኝ የሆነን ክፍልፋይ ፈልግ/ጊ፡፡

54
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2. ከዚህ በታች ለተሰጡት ክፍልፋዮች ተመጣጣኝ ክፍልፋዮችን ፈልግ/ጊ፡፡


1 4 1
ሀ. ለ. ሐ.
4 6 5

3 6 9
3. ፣ እና ለምን ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች ሆኑ?
4 8 12

4. የጠን ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡

1 3 4 ጠ 8 1
ሀ. = ለ. 5 = 10 ሐ. =
3 ጠ 64 ጠ

ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች የአንድ ሙሉ ክፋይ ተመሳሳይ የሆኑ ገሚሶች


የሚያሳዩ ክፍልፋዮች ሆነው፣ ነገር ግን አገላለፃቸው በተለያየ ሁኔታ የተሰጠ
ነው፡፡ እኩል የሆነ መጠን የሚያሳዩ ክፍልፋዮች ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች
ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 18
4 1
ከዚህ በታች የተሰጡ የሬክታንግላዊ ስፋት ሞዴሎች ክፍልፋይ ከክፍልፋይ
8 2
ጋር ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች መሆናቻውን ያሳያል፡፡ አንድን ቁጥር የሚተኩ ክፍልፋዮች
ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 19
4
ከክፍልፋይ ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ 3 ክፍልፋዮችን ፈልግ/ጊ፡፡
8

55
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
4 2 8
ዘዴ 1፡  = (ላዕልና ታህትን በተመሳሳይ ሙሉ ቁጥር ማብዛት)
8 2 16
ዘዴ 2፡ ላዕልና ታህትን በተመሳሳይ ቁጥር ማካፈል፡፡ ለምሳሌ ለ2 ማካፈል
42 2
=
82 4
22 1
=
42 2

8 2 1 4
ስለዚህ፣ ፣ ፣ ፣ ሦስቱም ን የሚገልፁ ናቸው፡፡
16 4 2 8

ምሳሌ 20
1 2 3 4 5 9
= = = = = እና የመሳሰሉት ክፍልፋዮች ተመጣጣኝ ናቸው፡፡
3 6 9 12 15 27

1 2 3 4
= = = ተመጣጣኝ ክፍልፋዮች ናቸው፡፡
5 10 15 20

መልመጃ 2.8
1
1. ሬክታንግላዊ የስፋት ሞዴልን በመጠቀም ከ ጋር ተመጣጣኝ የሆኑ ሁለት
3
ክፍልፋዮችን ፈልግ/ጊ፡፡
2. ከዚህ በታች በተሰጠው ምስል ላይ በመመሥረት ተመጣጣኝ ክፍልፋይ
ለመግለፅ የጐደሉትን ቁጥሮች ሙላ/ዪ፡፡

56
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3. ከዚህ በታች የተሰጠውን ፓተርን በመከተል ባዶ ቦታ ሙላ/ዪ፡፡


1 2 3
= = =_______ = ______ = ________ .
4 8 12

4. የ “ጠ”ን ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
1 ጠ 1 ጠ 3 6 ጠ 8
ሀ. = ለ. 3 = 12 ሐ. = መ. 5 = 10
2 8 ጠ 8

የተመጣጣኝ ክፍልፋዮች ትርጓሜ እና የተመጣጣኝ ክፍልፋዮች ምሳሌ


ተምረሃል/ሻል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ክፍልፋዮችን እንዴት እንደምታወዳድር/ሪ
እና ቅደም ተከተላቸውን እንዴት እንደምታስቀምጥ/ጪ ትማራለህ/ሪያለሽ፡፡
ትግበራ 2.6
1
1. ቶላ እና ዱሬቲ መጠናቸው እኩል የሆነ ምግብ አሏቸው፡፡ ቶላ ውን
2
3
በላ፣ ዱሬቲ ደግሞ ውን ከበላች፤ ከሁለቱ ትንሽ ምግብ የበላው ማነው?
4
7
2. በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ካሉት ተማሪዎች መካከል ሴቶች እና
9
5
ወንዶች ከሆኑ፣ አብላጫ ቁጥር ያለው ፆታ የቱ ነው? ለምን?
9
3. ከዚህ በታች የተሰጡ ክፍልፋዮችን > ፣ < ወይንም = ምልክቶችን
በመጠቀም አውዳድር/ሪ፡፡
4 7 2 1
ሀ. ____ ለ. ____
6 8 4 2

3 5 4 4
ሐ. ____ መ. ____
8 8 7 8

4. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች የ < ን ምልክት በመጠቀም


ከትንሽ ወደ ትልቅ ፃፍ/ፊ፡፡

2 2 2 3 4 5 6 1 1 1 1
ሀ. ፣ ፣ ለ. ፣ ፣ ፣ ሐ. ፣ ፣ ፣
13 11 15 5 7 6 7 2 4 5 7

57
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

5. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች የ >ን ምልክት በመጠቀም ከትልቅ ወደ


ትንሽ ፃፍ/ፊ፡፡
1 3 1 1 1 2 1 3
ሀ. ፣ ፣ ፣ ለ. ፣ ፣ ፣ ሐ.1 2 ፣1 4 ፣1 5 ፣2 4
1 3 1 1
2 4 3 5 10 12 12 15

ምሳሌ 21
5 3
የሬክታንግላዊ ስፋት ሞዴሎችን በመጠቀም እና ን አወዳድር/ሪ፡፡
8 8
መፍትሔ
5
8
3
8

5 3
ከየሬክታንግላዊ ስፋት ሞዴሎቹ የምትረዳው/ጂው  መሆኑን ነው፡፡
8 8
ምሳሌ 22
1 1
ወይስ ይበልጣል? የቁጥር መስመርን በመጠቀም አሳይ/ዪ፡፡
4 2

0 1 2 3 1
4 4 4

0 1 1
2

መፍትሔ
1 1
ከላይ በቁጥር መስመሩ ላይ የምትገነዘበው/ዊው  መሆኑን ነው፡፡
2 4

58
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 23
ቀጥሎ ያሉትን ክፍልፋዮች ከትንሽ ወደ ትልቅ በቅደም ተከተላቸው
2 1 7
አስቀምጥ/ጪ፡፡ ፣ ፣
3 2 12

መፍትሔ
ዘዴ 1፡ የቁጥር መስመርን በመጠቀም

ዘዴ 2፡ ታህታቸው ተመሳሳይ የሆነ ተመጣጣኝ ክፍልፋዮችን ፈልግ/ጊ፡፡ ይህ


እንዴት ይሆናል?

መፍትሔ
2 4 8 1 6 6
 =  =
3 4 12 2 6 12
ታህታቸው እኩል ስለሆነ ላዕላቸውን በማወዳደር ከትንሽ ወደ ትልቅ መፃፍ፡፡
6 < 7 < 8፡፡
6 7 8
, ,
12 12 12

1 7 2
, ,
2 12 3
1 7 2
ስለዚህ ከትንሽ ወደ ትልቅ በቅደም ተከተል ሲጻፉ፤ ፣ ፣ ይሆናል፡፡
2 12 3

59
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትግበራ 2.7
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን አሥርዮሾች > ወይንም < ወይንም =
በምልክቶችን በመጠቀም አወዳድር/ሪ፡፡
ሀ. 4.362 _____3.362 ለ. 2.489 _____2.3999
ሐ. 6.648 _____6.692 መ. 0.6685_____ 0.6679
2. ከዚህ በታች የተሰጡትን አሥርዮሾች ከትንሽ ወደ ትልቅ በቅደም

ተከተል አስቀምጥ/ጪ፡፡

ሀ. 0.39፣ 0.42፣ 0.35 ለ. 0.43፣ 0.432፣ 0.48፣ 0.438


ሐ. 1.3፣ 2.52፣ 0.35፣ 0.3

ዘዴ 3፡ አሥርዮሾችን በመጠቀም
ክፍልፋይን ወደ አሥርዮሽ መቀየር

1
= 0 .5
2
7
= 0.583
12
2
= 0.667
3
አሥርዮሾችን ለማወዳደር በመጀመሪያ በአሥርዮሾች ውስጥ ከአሥርዮሽ ነጥብ
በስተግራ ያሉትን ቁጥሮች አወዳድር/ሪ፡፡

ከአሥርዮሽ ነጥብ በስተግራ ትልቅ ቁጥር ያለው አሥርዮሽ ይበልጣል፡፡


ከአሥርዮሽ ነጥብ በስተግራ ያሉ ሙሉ ቁጥሮች እኩል ከሆኑ ከአሥርዮሽ
ነጥብ በስተቀኝ ያሉ ቁጥሮችን አወዳድር/ሪ፡፡ በመጀመሪያ የአስረኛ ቤት
ድጂቶችን አወዳድር/ሪ፡፡ ትልቅ ድጂት ያለው አሥርዮሽ ትልቅ ይሆናል፡፡
የአሥርዮሽ ቤት ድጂቶች እኩል ከሆኑ የመቶኛ ቤት ድጂቶችን አወዳድር/ሪ፡፡
ትልቅ ድጂት ያለው አሥርዮሽ ትልቅ ይሆናል፡፡ የመቶኛ ቤት ድጂቶች እኩል

60
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ከሆኑ የሺኛ ቤት ድጂቶችን አወዳድር/ሪ፡፡ ትልቅ ድጂት ያለው አሥርዮሽ


ትልቅ ይሆናል፡፡ በዚህ መልክ እስከምትለይ/ዪ ድረስ ሂደቱን ቀጥል/ዪ፡፡ ከዚህ
በላይ በተሰጠው ማብራሪያ መሰረት አሥርዮሽን በዘዴ 3 ስር ባለው
ማወዳደር፡፡ ከአሥርዮሽ ነጥብ በስተግራ ያለው ሙሉ ቁጥር በሦስቱም ውስጥ
0 ስለሆነ እኩል ናቸው፡፡ ወደ አስረኛ ቤት እለፍ/ፊ፡፡ በአስረኛ ቤት ውስጥ
6 > 5 ስለሆነ፣ 0.67 ትልቅ ነው፡፡
በመቀጠል 0.5 እና 0.583 አወዳድር/ሪ፡፡ የአስረኛ ቤት ድጂቶች እኩል ናቸው፡፡
በመጨረሻ ወደ መቶኛ ቤት ድጂቶች እለፍ/ፊ፡፡ 8 > 0 ስለሆነ 0.583 > 0.5
2 7 1
ይሆናል፡፡ ስለዚህ 0.667 > 0.583 > 0.5 ይሆናል፡፡ ይህ ማለት  
3 12 2
ይሆናል፡፡
ከዚህ በላይ ከተሰጡት ዘዴዎች ምን ትረዳለህ/ጂያለሽ?
ምሳሌ 24
ከ6.326 እና 6.327 ቁጥሮች ትልቁ የቱ ነው?
መፍትሔ
በተሰጡት አሥርዮሾች ውስጥ ከአሥርዮሽ ነጥብ በስተግራ ያለው ቁጥር
እኩል ነው፡፡
ስለዚህ ከአሥርዮሽ ነጥብ በስተቀኝ ያሉ ቁጥሮችን አወዳድር/ሪ፡፡ በአሥርዮሽ
ቁጥሮች 6.326 እና 6.327 ሁለቱም ውስጥ የአስረኛ ድጂት 3 ስለሆነ
በሁለቱም አሥርዮሽ ውስጥ የመቶኛ ቤት ዲጂት እኩል ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ሺኛ
ቤት ድጂት እለፍ/ፊ፡፡
6.326 ውስጥ የሺኛ ቤት ድጂት 6 ሲሆን በ6.327 ውሰጥ ደግም የሺኛ ቤት
ድጂት 7 ነው፡፡ 7 > 6 ስለዚህ፣ 6.327 > 6.326 ይሆናል፡፡
በሌላ መልኩ ታህታቸው ተመሳሳይ ያልሆኑ ክፍልፋዮችን ለማወዳደር ከዚህ
በታች የተሰጠውን ደንብ ተጠቀም/ሚ፡፡
ሀ፣ለ፣ሐ እና መ መቁጠሪያ ቁጥሮች ከሆኑና ከሆነ፣

61
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

7 4
ሀ×መ > ለ×ሐ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ  ፡፡ ምክንያቱም 7 x 5 > 8 x 4
8 5
(35 > 32) ስለሆነ ነው፡፡

መልመጃ 2.9
1. ቀጥሎ የተሰጡትን የሬክታንግላዊ ስፋት ሞዴል በመጠቀም ከታች
የተሰጡ ጥንድ ክፍልፋዮችን በ > ፣< ወይም = ምልክት አወዳድር/ሪ፡፡

2. ቀጥሎ የተሰጡትን የቁጥር መስመሮችን በመጠቀም ከታች የተሰጡትን


ጥንድ ክፍልፋዮች > ፣< ወይም = ምልክቶችን በመጠቀም አወዳድር/ሪ፡፡

3. ከዚህ በታች የተሰጡትን ጥንድ ክፍልፋዮችን ምልክት > ፣< ወይም =


በመጠቀም አወዳድር/ሪ፡፡

62
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4. ከዚህ በታች የተሰጡ ክፍልፋዮችን ከትንሽ ወደ ትልቅ በቅደም ተከተል


ፃፍ/ፊ፡፡

1
5. ቶለሣ በቅርጫት ውስጥ የሚገኘውን ብርቱካን በላ፡፡ ጫልቱ ዳግሞ
4

3
በቅርጫት ውስጥ የሚገኘውን ብርቱካን በላች፡፡ ከሁለቱ የበለጠ
12
ብርቱካን የበላው ማነው?
6. ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ እንደተመለከተው ሁለት ተማሪዎች
እያንዳንዳቸው ወላጆቻቸውን በእርሻ የሚረዱትን የጊዜ መጠን ያሳያል፡፡
ይበልጥ ወላጂን የረዳ/ች ማነው? ባይሳ ከባይሴ የበለጠ ወይንስ ያነሰ ጊዜ
ወሰደ? አብራራ/ሪ፡፡

ተማሪዎች ጊዜ
4
ባይሳ ሰአት
12
3
ባይሴ ሰአት
4

7. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ከትልቅ ወደ ትንሽ በቅደም ተከተል


ፃፍ/ፊ፡፡

63
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.6. የመቶኛ ፅንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ ማዋል

መግቢያ
በዕለት ተለት ኑሮአችን የመቶኛን ፅንሰ ሃሳብ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ገንዘብን
ጨምሮ ለስሌት እንጠቀምበታለን፡፡ ስለዚህ በመቶኛ ማስላት በእለት ተለት
በምንተገብራቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ለምሳሌ፡- ለማንኛውም ምጣኔ፣ የባንክ ወለድ፣ የግብር ምጣኔ፣ የውልደት ምጣኔ፣


የዋጋ ጭማሪ፣ የሽያጭ ዋጋ ቅናሽ እና የመሳሰሉትን ለማስላት በአብዛኛው በመቶኛ
ይገለጻሉ፡፡

ምሳሌ 25
.

18 የ24 ስንት መቶኛ ነው?

መፍትሔ
ድርሻ ነ
=
ሙሉ 100

18  100
⟹ነ= = 75%
24
ስለዚህ፣ 18 የ24፤75 % ነው፡፡

ምሳሌ 26
የ150፣ 30 % ስንት ነው?

መፍትሔ
30 መቶኛ ነው፡፡ 150 ቤዝ ነው፡፡ የሚፈለገው በመቶኛ ነው፡፡

ድርሻ ነ
=
ሙሉ 100

64
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

30  150
በመቶኛ = = 45 የሆናል፡፡
100

ምሳሌ 27
12 የየትኛው ቁጥር 80% ነው?

መፍትሔ
12 የመቶኛ ድርሻ ነው፡፡ 80 መቶኛ ነው፡፡ የሚፈለገው ሙሉ ወይም ቤዝ ነው፡፡

ሙሉ(ቤዝ) × 80 = 12 × 100
ሙሉ = 15 ይሆናል፡፡
ስለዚህ፣ 12 የ15 80% ነው፡፡

ምሳሌ 28
ሶሬቲ በአንድ ባንክ በነጠላ ወለድ ምጣኔ 5% የሚከፈላት የቁጠባ ሂሳብ
ከፈተች፡፡ ሶሬቲ 1000 ብር ብትቆጥብ ከአንድ አመት በኋላ የሚከፈላት ወለድ
ስንት ነው?

መፍትሔ
ሙሉ(ቤዝ)(ቤ) = 1000፣ ምጣኔ (ም) = 5%፣ የመቆያ ጊዜ (ጊ) 1 ዓመት፣
ተፈላጊው ፡- ነጠላ ወለድ(ወ)
ወ = ቤ × ም × ለ
ወ = 1000 × 5% × 1 = 50 ብር ይሆናል፡፡

65
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 2.10
1. 28 የ80 ስንት መቶኛ ነው?
2. የ180፣ 65 መቶኛ ስንት ይሆናል?
3. 36 የየትኛው ቁጥር 40% ነው?
4. ጫላ በወር ከሚያገኘው ደሞዝ ላይ 40% ይቆጥባል፡፡ የወር ደሞዙ 8000
ብር ከሆነ፣ በወር ምን ያህል ይቆጥባል?
5. ኦብሴ በመግዣ ዋጋ ብር 4,500 ላይ ተጨማሪ ግብር 675 ብር
በመጨመር ቴሌቪዥን ገዛች፡፡ ተጨማሪው ግብር በመቶኛ ስንት ነው?
6. አንድ ነጋዴ በ260 ብር የሚሸጥ ጫማን 25% ቅናሽ አድርጎ ቢሸጥ፤ ይህ
ነጋዴ ምን ያህል ብር ቀነሰ?
7. ቶላሣ አንድ ቋሚ ዋጋው 1500 ብር የሆነን ጃኬት ለመግዛት ፈለገ፡፡
ሳምንት ውስጥ የጃኬቱ ዋጋ በ33% ቢቀንስ የጃኬቱ የሺያጭ ዋጋ ስንት
ይሆናል?
8. ሶሬሣ በአንድ ባንክ በነጠላ ወለድ ምጣኔ 7% የሚከፈለው የቁጠባ ሂሳብ
ከፈተ፡፡ ሶሬሣ 6000 ብር ቢቆጥብ ከአንድ አመት በኋላ የሚከፈለው ወለድ
ስንት ነው?
9. ጋዲሴ 20 ሺ ብር ከአንድ ብድርና ቁጠባ ድርጅት ኮምፒዩተር ለመግዛት
ተበደረች፡፡ የወለድ ምጣኔ በአመት 9% ነው፡፡ ይህን ብድር ከፍሎ
ለመጨረስ 8 ወር ቢወስድባት ምን ያህል ወለድ ትከፍላለች?
10. ሀዊ የእርሻ ትራክተር ለመግዛት ከባንክ 1,000,000 ብር ተበደረች፡፡ የነጠላ
ወለድ ምጣኔ 15% ነው፡፡ ይህን ክፍያ ለመጨረስ 2 አመት ቢወስድባት
ምን ያህል ወለድ ትከፍላለች?

66
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፍ 2 ማጠቃለያ
1. ክፍልፋይ የአንድን ሙሉ ነገር ክፋይ ለመግለፅ የሚጠቅመን ቁጥር ነው፡፡
2. አንድ የተሰጠ ክፍልፋይ ህገኛ፣ ድብልቅ ወይም ህገኛ ያልሆነ ክፍልፋይ
ሊሆን ይችላል፡፡

3. አንድ በ መልክ የተሰጠ ክፍልፋይ በቀላል ሒሳባዊ ቃል የተፃፈ ነው

የሚንለው ትልቁ የጋራ አካፋይ ትገአ (ሀ፣ ለ) =1 ከሆነ ነው፡፡


4. አንድን ክፍልፋይ በተቃለለ መልክ ስፃፍ በትልቁ ጋራ አካፋይ/ትገአ/
ለዕልና ታህትን በማከፈል እንጠቀማለን፡፡
ሀ ሀ
5. ለ
ክፍልፋይ ከሆነ እና ትልቁ የጋራ አካፋይ ትገአ (ሀ፣ለ) =1 ከሆነ፣ ለ

የተቃለለ ክፍልፋይ ይበላል፡፡



6. በ የተገለፀ ክፍልፋይ ቢሰጥ እና በረጅም የማካፈል ዘዴ “ሀ”ን ለ”ለ”

በማካፈል ቀሪው 0 ከሆነ፣ የማካፈል ሂደቱ ይቆማል፡፡ የሚገኘው አስሪዮሽ


ቁጥር አክታሚ አሥርዮሽ ይባላል፡፡

7. በክፍልፋይ ውስጥ፣ “ሀ” ለ “ለ” ተካፍሎ ቀሪው 0 መሆኑ ቀርቶ

የማካፈል ሂደቱ ሳይቆም በተመሳሳይ የድርሻ ቁጥር ልቀጥል ይችላል፡፡


ይህ ዓይነት አሥርዮሽ ተደጋጋሚ አሥርዮሽ ይባላል፡፡
8. መቶኛ ታህቱ መቶ የሆነ ክፍልፋይ ነው፡፡
100
9. አንድን አክታሚ አሥርዮሽ ወደ መቶኛ ለመቀየር አሰርዮሹን በ
100
ማባዛት ነው፡፡ በመቶ በማባዛት በመጨረሻ ላይ % ምልክት ማስቀመጥ
ነው፡፡

67
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፍ 2 የክለሳ መልመጃ

1. ከዚህ በታች በተሰጡት ምስሎች ውስጥ የተቀቡትን ክፋዮች በክፍልፋይ


ግለፅ/ጪ፡፡

2. ከዚህ በታች የተሰጡ ክፍልፋዮችን በቀላል ሒሳባዊ ቃል ፃፍ/ፊ፡፡


6 15 24 49
ሀ. ለ. ሐ. መ.
8 18 9 343
123 23 155 45
ሠ. ረ. ሰ. ሸ.
66 45 220 99

3. ከዚህ በታች የተሰጡ ክፍልፋዮችን በአስሪዮሽ ፃፍ/ፊ፡፡


1 1 11 4
ሀ. ለ. ሐ. መ.
4 8 10 5
3 7 6 19
ሠ. 2 ረ. 4 ሰ. ሸ.
4 8 10 100

4. ከዚህ በታች የተሰጡትን መቶኛዎች ወደ ክፍልፋይ ቀይር/ሪ፡፡


ሀ. 29% ለ. 21.7% ሐ. 0.05% መ. 8%
ሠ. 100% ረ. 50% ሰ.0.2% ሸ.25%
5. ከዚህ በታች ያሉትን ክፍልፋዮች ወደ መቶኛ ቀይር/ሪ፡፡
60 12 8 76
ሀ. ለ. ሐ. መ.
25 20 10 100
6. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ከትንሽ ወደ ትልቅ በቅደም ተከተል
ፃፍ/ፊ፡፡

68
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

7. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ከትልቅ ወደ ትንሽ በቅደም ተከተል


ፃፍ/ፊ፡፡

8. የጐደለውን ቁጥር ሙላ/ዪ::


7 14 21 ? ? ? 2 ? 36 ?
ሀ. = = = = ለ. = = = =
12 ? ? 48 60 8 4 2 ? 60

69
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ 5 + 3 = 40 + 21 = 61

3
7 8 56 56

0.2  0.4 = 1  2 = 1  5 = 1
5 5 5 2 2

የክፍልፋዮች እና አሥርዮሾች ስሌት

የመማር ውጤቶች፡ በዚህ ምዕራፍ ትምህርት ሂደት እና ማጠቃለያ ላይ፡-


• ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን መደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛት እና ማካፈል
ላይ ችሎታህን/ሽን ታዳብራለህ/ሪያለሽ፡፡
• ከኑሮ ጋር የተያያዙ ተጨባጭ የቃላት ፕሮብሌሞችን መፍትሔ በመፈለግ
ውስጥ የክፍልፋዮችንና የአሥርዮሾችን ፅንሰ ሐሳብ ትጠቀማለህ/ሚያለሽ፡፡
• ሳይንሳዊ ምልክቶችን ትጠቀማለህ/ሚያለሽ፡፡

መግቢያ
ባለፋት የሒሳብ ትምህርት ምዕራፎች ውስጥ ስለ ክፍልፋዮችና አሥርዮሾች
ተምረሃል/ሻል:: በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ደግሞ ክፍልፋዮችና አሥርዮሾትን
መደመር፣ መቀነስ ፣ ማባዛትና ማካፈልን በጥልቀት ትማራለህ/ሪያለሽ፡፡

70
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3.1 ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን መደመር

መግቢያ
በዚህ ርዕስ ውስጥ ስለ ክፍልፋዮችና አሥርዮሾች መደመር ላይ ያለህን/ሽን
እውቀት ታዳብራለህ/ሽ፡፡ ክፍልፋዮች ተመሳሳይ ታህት ካላቸውና ከሌላቸው
እንዴት እንደሚደመሩና አሥርዮሾችን መደመር ትማራለህ/ሽ፡፡
ትግበራ 3.1
በቡድን ተወያዩበት፡፡
1. ሁለት ተመሳሳይ ታህት ያላቸው ክፍልፋዮች ቢሰጡህ/ሸ እንዴት
ትደምራለህ/ሸ? በቡድን ተወያዩበትና ለክፍላችሁ ግለፁ፡፡
2. ሁለት የተለያዩ ታህት ያላቸው ክፍልፋዮች ቢሰጣችሁ እንዴት
ትደምራላችሁ? በቡድን ተወያዩበትና ለክፍላችሁ ግለጹ፡፡
3. ከዚህ በታች ያሉትን ደምር/ሪ፡፡

ተመሳሳይ ታህት ያላቸው ክፍልፋዮችን ለመደመር የጋራ ታህትን በመውሰድ


ላዕላቸውን ደምር/ሪ፡፡ ታህታቸው የተለያዩ ክፍልፋዮችን ለመደመር፤
መጀመሪያ የተደማሪ ክፍልፋዮች ታህቶችን ማመሳሰል ያስፈልጋል፡፡ ይህን
ለማድረግ የታህቶቻቸውን ትንሹ የጋራ ተካፋይን (ብዜት) በመፈለግ
ይሆናል፡፡ ታህቶቻቸውን ካመሳሰልክ/ሽ በኋላ ክፍልፋዮቹን ደምር/ሪ፡፡

ምሳሌ 1
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ደምር/ሪ፡፡

70 30 19 60 40 4 6 5 2
ሀ. + ለ. + + ሐ. + መ. +
9 9 30 30 30 12 24 7 3

71
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
70 30
ሀ. + ክፍልፋዮቹ ተመሳሳይ ታህት ስላላቸው፤ የጋራ ታህትን
9 9

በመውሰድ ላዕላቸውን ደምር/ሪ፡፡

70 30 70 + 30 100
ሰለዚህ፣ + = =
9 9 9 9

19 60 40 19 + 60 + 40 119
ለ. በተመሳሳይ መልክ፡- + + = =
30 30 30 30 30
4 6
ሐ. 12
+ 24 የክፍልፋዮቹ ታህቶች የተለያዩ ሰለሆኑ በመጀመሪያ

የክፍልፋዮቹን ታህቶች አመሳስል/ዪ፡፡ ይህን ለማድረግ ትጋብ(12፣24)

ፈልግ/ጊ፡፡

የ12 ተካፋዮች 12፣ 24፣ 36፣ 48፣…

የ24 ተካፋዮች 24 ፤ 48 ፣ 72፣ …


ስለዚህ የ(12፣24) ትጋብ 24 ነው፡፡ ይህ ማለት ክፍልፋዮቹን

ለመደመር ታህቶቻቸውን 24 አድርግ/ጊ፡፡

4 6 4 2 6 1 8 6 14
+ = × + × = + =
12 24 12 2 24 1 24 24 24
በተመሳሳይ መልክ፡-

አስታውል/ዪ
ሀ ሐ ሀ ሐ ሀመ+ለሐ
1. እና ክፍልፋዮች ከሆኑ፣ + =
ለ መ ለ መ ለመ

ለ ለ ሀሐ+ለ
2. ሀ ድብልቅ ክፍልፋይ ከሆኑ፣ ሀ =
ሐ ሐ ሐ

72
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 2
የሚከተሉትን ደምር/ሪ፡፡

መፍትሔ
ሀ. ከዚህ በላይ ያለውን ‘አስተውል/ዪ’ መጠቀም ይቻላል፡፡

9 11 9  10 + 7  11 90 + 77 167
+ = = =
7 10 7  10 70 70

ለ. በመጀመሪያ ድብልቅ ክፍልፋዮችን በ ለ
መልክ መዳፍ፡፡
5 5 4  3 + 1  5 12 + 5 17
4 =4+ = = = እና
3 3 1 3 3 3

1 1 7  2 + 1  1 14 + 1 15
7 =7 + = = =
2 2 1 2 2 2
5 1 17 15 17  2 + 3  15 34 + 45 79
ስለዚህ፣ 4 +7 = + = = =
3 2 3 2 3 2 6 6

አሥርዮሾችን ለመደመር የአሥርዮሾች ነጥቦች በአንድ ረድፍ ላይ እንዲውሉ


በማድረግ ቁልቁል ጸፍ/ፊ፡፡ በመቀጠል ከቀኝ ወደ ግራ በተመሳሳ ቤት ውስጥ
ያሉትን ድጂቶች ደምር/ሪ፡፡ የሚደመሩት ድጂቶች ብዛት እኩል ካልሆኑ ትንሽ
ድጂት ብዛት ባለው ቁጥር ላይ በስተቀኝ ዜሮ ጨምር/ሪ፡፡ ይህን
የምታደርገው/ጊው የድጂቶቹን ብዛት እኩል ለማድረግ ነው፡፡
ምሳሌ 3
ከዚህ በታች ያሉትን ደምር/ሪ፡፡

73
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ

የድጂቶቹን ብዛት እኩል ለማድረግ 0 ን መጨመር ነው፡፡


ክፍልፋዮችን እና አሥርዮሾችን ለመደመር ከዚህ በታች የተሰጡትን
እርምጃዎች ተከተል/ዪ፡፡
1. አሥርዮሹን ወደ ክፍልፋይ ወይም ክፍልፋዩን ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡
2. አሥርዮሾቹን ወይም ክፍልፋዮቹን ደምር/ሪ፡፡
3. ያገኘኸውን/ሺውን መልስ በቀላል ሒሳባዊ ቃል ፃፍ/ፊ፡፡

ምሳሌ 4

መፍትሔ
በመጀመሪያ ክፍልፋዩን ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡ በመቀጠል ቁልቁልከቀኝ ወደ
ግራ በቁጥር ቤታቸው ደምር/ሪ፡፡
6712
= 0.6712
10,000
6712
0.385 + = 0.385 + 0.6712
10,000
0.385
+ 0.6712
1.0562

ወይም ደግሞ 0.385 ወደ ክፍልፋይ በመቀየር መስራት፡፡

385
0.385 =
1,000

74
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

6712 385 6712 385  10 + 6712 10562


ስለዚህ፣ 0.385 + = + = = = 1.0562
10,000 1,000 10,000 10,000 10,000

መልመጃ 3.1
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን ደምር/ሪ፡፡

2. ከዚህ በታች ያሉትን ድምሮች ፈልግ/ጊ፡፡ ዋጋቸውን በአሥርዮሽ እና ክፍልፋይ

ፃፍ/ፊ፡፡

3. ኦብሴ 448.75 ብር ለሥጋ፣ 424.85 ብር ለወተት፣ 682.35 ብር ለዘይት


ግዢ ከአንድ የቁጠባ ባንክ ወጪ አደረገች፡፡ በአጠቃላይ ስንት ብር ወጪ
አደረገች?
4. የትቤሶ መጠነቁስ 55.6 ኪ.ግ ከሆነ እና የበሪቴ ደግሞ 60.45 ኪ.ግ ከሆነ፣
የሁለቱ መጠነቁስ አንድ ላይ ምን ያህል ኪ.ግ ይሆናል?
5. ቦንቱ 475.75 ብር አላት፡፡ እፋ ደግሞ 350.25 ብር አለው፡፡ ሁለቱ አንድ
ላይ ስንት ብር አላቸው?

75
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3.2 ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን መቀነስ

መግቢያ
በዚህ ርዕሰ ስር ስለ ክፍልፋዮች እና አሥርዮሾች መቀነስ ላይ ያለህን/ሽን
እውቀት ታዳብራለህ/ሽ፡፡ ታህታቸው እኩል የሆኑ ክፍልፋዮች ወይም
ታህታቸው የተለያዩ ክፍልፋዮች ቢሰጥህ/ሽ እንዴት እንደምትቀንስ/ሽ
ትማራለህ/ያለሽ፡፡

ትግበራ 3.2
ከዚህ በታች ያሉትን አስላ/ይ፡፡

ክፍልፋዮችን ለመቀነስ የምንጠቀምበት ሂደት ክፍልፋዮችን ለመደመር


ከምንጠቀምበት ዘዴ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ታህታቸው ተመሳሳይ የሆኑ
ክፍልፋዮችን ለመቀነስ የጋራ ታህቱን ወስደህ/ሽ ላዕላቸውን ትቀንሳለህ/ሽ::
ታህቶቻቸው የተለያዩ ከሆነ፣ ደግሞ ትልቁ የጋራ ተካፋይ(ትጋብ) ዘዴን
በመጠቀም ታህቶቻቸውን በማመሳሰል ትቀንሳለህ/ሺያለሽ፡፡

ምሳሌ 5
ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች ቀንስ/ሺ፡፡

መፍትሔ

76
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሁለቱ ክፍልፋዮች ታህቶቻቸውን እኩል ስለሆኑ የጋራ ታህት በመወለድ


ላዕላቸውን ቀንስ/ሺ፡፡

351 299 351 − 299 52 13


ስለዚህ፣ _ = = =
200 200 200 200 50

ሁለቱ ክፍልፋዮች የተለያዩ ታህቶች ስላላቸው በመጀመሪያ


ታህቶቻቸውን እናመሳስላለን፡፡ ታህቶቻቸውን ለማመሳሰል አመቺ በሆነ ቁጥር
አባዛ/ዢ፡፡ ትጋት(12፣15) = 60 ስለሆነ የሁለቱን ክፍልፋዮች ታህቶች 60
አድርግ/ጊ፡፡
26 9 26 5 9 4 130 36 94 47
ስለዚህ፣ − =  −  = − = =
12 15 12 5 15 4 60 60 60 30
u
በመጀመሪያ ድብልቅ ክፍልፋዮችን በ ለ
መልክ ፃፍ/ፊ፡፡

8 8 6  7 + 8 50 5 5 2 2+ 5 9
6 =6+ = = እና 2 =2+ = =
7 7 7 7 2 2 2 2
የሁለቱም ክፍልፋዮች ታህቶቻቸው ተመሳሳይ ስላልሆኑ
መጀመሪያ ታህቶቻቸውን ማመሳሰል ነው፡፡
ታህቶቻቸውን ለማመሳሰል ምቹ በሆነ ቁጥር አባዛ/ዢ፡፡ ትጋብ(7፣2) =14 ስለሆነ፣
የሁለቱን ክፍልፋዮች ታህት 14 አድርግ/ጊ፡፡
8 5 50 9 50 2 9 7 100 63 37
6 −2 = − =  −  = − =
7 2 7 2 7 2 2 7 14 14 14
ከክፍልፋይ አሥርዮሽን ለመቀነስ ወይም ከአሥርዮሽ ክፍልፋይን ለመቀነስ
ከዚህ በታች የተሰጡትን እርምጃዎች ተከተል/ይ፡፡

1. አሥርዮሽን ወደ ክፍልፋይ ወይም ክፍልፋይን ወደ አሥርዮሽ ቀየር/ሪ፡፡


2. አሥርዮሾቹን ወይም ክፍልፋዮቹን ቀንስ/ሺ፡፡
3. ያገኘኅውን/ሺውን መልስ በቀላል ሒሳባዊ ቃል መልክ ፃፍ/ፊ፡፡

77
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 6

መፍትሔ
698
0.8672 − በመጀመሪያ ክፍልፋይን ወደ አሥርዮሽ ቀይር/ሪ፡፡
1000
ክፍልፋዮቹን ለመቀነስ የአሥርዮሽ ነጥቦች በአንድ ረድፍ በማድረግ ቁልቁል
ፃፍ/ፊ፡፡ ከዚህ በኋላ ከቀኝ ወደ ግራ በየቁጥር ቤታቸው ቀንሲ/ሺ፡፡ የድጂቶቹ
ብዛት እኩል ካልሆነ ትንሹ ድጂት ባለው ላይ በስተቀኝ 0ን ጨምር/ሪ፡፡
698 698
= 0.689 , 0.8672 − = 0.8672 − 0.698
1000 1000
0.8672
− 0.6980 ዜሮን የምንጨምረው የድጂቶቹን ብዛት እኩል ለማድረግ ነው፡፡
0.1692
ወይም ደግሞ 0.8672 ወደ ክፍልፋይ በመቀየር መስራት ይቻላል፡፡
8672
0.8672 =
10,000
8672 698 8672 − 10  698 8672 − 6980 1692
ስለዚህ፣ − = = = = 0.1692
10,000 1000 10,000 10,000 10,000

መልመጃ 3.2
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን ቀንስ/ሺ፡፡

78
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2. ከዚህ በታች የተጠየቁ ልዩነቶችን ፈልግ/ጊ፡፡ የተገኘውን ዋጋ በአሥርዮሽና


በክፍልፋይ ፃፍ/ፊ::

3. ቦንቱ 50.5 ኪ.ግ ቡና ገዝታ ነበር፡፡ 10.70 ኪ.ግ ለእናቷ፣ 18.80 ኪ.ግ
ደግሞ ለእህቷ ሰጠች፡፡ ምን ያህል ኪ.ግ ቡና የቀራታል?
2 1
4. ቤካ ውን የእርሻ ቦታውን በዕለተ ማክሰኞ አረሰ፡፡ ውን ደግሞ በዕለተ
5 2
ሐሙስ አረሰ:: ያልታረሰው የእርሻ ቦታ ምን ያህል ነው?

3.3 ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን ማባዛት


መግቢያ
በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር ስለ ክፍልፋዮችና አሥርዮሾች ማባዛት ያለህን/ሽን
እውቀት ታዳብራለህ/ሽ፡፡ ክፍልፋዮችን በክፍልፋይ እና አሥርዮሽን በአሥርዮሽ
እንዴት እንደምታባዛ/ዢ ትማራለህ/ሽ፡፡
ትግበራ3.3
ከዚህ በታች የተሰጡትን አሰላ/ይ፡፡

42 10 5 9
ሀ. × ለ. 3 × ሐ. 0.423 ×3 መ. 0.0324 × 0.2
12 12 7 2

መቁጠሪያ ቁጥሮችን በመቁጠሪያ ቁጥሮች እንደምታባዛው


ክፍልፋይን በክፍልፋይ ታባዛለህ/ሽ፡፡ እንዲሁም አሥርዮሽን በአሥርዮሽ
ታባዛለህ/ሽ፡፡ አሥርዮሽን በክፍልፋይ ወይም ክፍልፋይን በአሥርዮሽ
በምናባዛበት ጊዜ ሁለቱን አገላለፆች ማመሳሰል አለብህ/ሽ፡፡ ይህ ማለት

79
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ክፍልፋይን ወደ አሥርዮሽ ወይም አሥርዮሽን ወደ ክፍልፋይ መቀየር


አለብህ/ሽ፡፡
ክፍልፋይን በክፍልፋይ ለማባዛት ላዕላቸውን በላዕላቸው እና ታህታቸውን
በታህታቸው ታባዛለህ/ዢያለሽ፡፡
ምሳሌ 7
ከዚህ በታች የተሰጡትን አስላ/ይ፡፡

መፍትሔ
ሁለቱን ላዕላቸውን ማባዛት እንድሁም
ሁለቱን ታህታቸውን ማባዛት፡፡

አሥርዮሽን በአሥርዮሽ በሚታባዛበት/ዢበት ጊዜ የመቁጠሪያ ቁጥሮችን


በምናባዛበት ዘዴ የአሥርዮሹን ድጂቶች በአሥርዮሽ ድጂቶች
ታበዛለህ/ዢያለሽ፡፡ የአሥርዮሽ ነጥብ ቦታ ለመወሰን ከአሥርዮሽ ነጥብ በኋላ

80
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ያሉ የአሥርዮሽ ቁጥሮች ድጂቶች ብዛት ትወስደለህ/ሽ፡፡ የሁለት አሥርዮሽ


ቁጥሮች ማባዛት ሂደት ከዚህ በታች የተሰጡ እርምጃዎች አሉት፡፡.
እርምጃ 1፡- በተሰጡት አሥርዮሾች ውስጥ የአሥርዮሽ ነጥብ በመተው
ቁጥሮቹን መውሰድ::
እርምጃ 2፡- በእርምጃ 1 የተወሰዱ ቁጥሮችን አባዛ/ዢ::
እርምጃ 3፡- የአሥርዮሽ ነጥብ ቦታ ወሰን/ኚ፡፡

ምሳሌ 8
ከዚህ በታች የተሰጡ አሥርዮሾችን አባዛ/ዢ፡፡
ሀ. 0.624 × 0.04 ለ. 0.531× 0.021

መፍትሔ
ሀ. 0.624 × 0.04
እርምጃ 1፡- በተሰጡት ክፍልፋዮች ውሰጥ የአሥርዮሽ ነጥብ በመተው
ቁጥሮችን ውሰድ/ጂ፡፡ 624 እና 4
እርምጃ 2፡- በእርምጃ 1 ላይ የተወሰዱ ቁጥሮችን አባዛ/ዢ፡፡
624 × 4 = 2496
እርምጃ 3፡- የአሥርዮሽ ነጥብ ቦታ ወሰን/ኚ:: ይህ ብዜት ከአሥርዮሽ ነጥብ
በኋላ 5 ድጂቶች ሊኖሩት ይገባል፡፡ በአሥርዮሽ 0.624
ውስጥ ከአሥርዮሽ ነጥብ በኋላ ሦስት ድጂቶች አሉ፡፡ በ0.04
ደግሞ ሁለት ድጂቶች አሉ፡፡ ስለዚህ
ይሆናል::
ለ. 0.531× 0.021
እርምጃ 1:- በተመሳሳይ መልኩ እርምጃ 1፣ 531 እና 21
እርምጃ 2:- 531 × 21 = 11151
እርምጃ 3:- 0.531 × 0.021 = 0.011151

81
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 3.3
1. ከዚህ በታች ያሉት ክፍልፋዮች አባዛ/ዢ::

2. ከዚህ በታች ያሉትን አሥርዮሽ አባዛ/ዢ፡፡


ሀ. 0.76 × 0.64 ለ. 0.862 × 0.132 ሐ. 0.60 × 0.14
3. ከዚህ በታች የተሰጡትን አባዛ/ዢ፡፡

4. ከዚህ በታች የተሰጡትን ብዜቶች ፈልግ/ጊ፡፡ ዋጋቸውን በአሥርዮሽ እና


በክፍልፋይ ፃፍ/ፊ፡፡
5 1 3
ሀ. 8
× 0.4 ለ. 4
× 2.6 ሐ. 2 4 × 7.5

5. የአንድ ኪ.ግ ጤፍ ዋጋ 48.50 ብር ነው፡፡ የ100 ኪ.ግ ጤፍ ዋጋ ስንት


ብር ይሆናል?
6. አንድ ሮቶ 2000.5 ሊትር ውሃ ይይዛል፡፡ 100 ሮቶዎች ምን ያህል
ሊትር ውሃ መያዝ ይችላሉ?
6. 0.0355 በስንት ቁጥር ተባዝቶ 35.5 ይሰጣል?

82
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3.4 ክፍልፋዮችንና አሥርዮሾችን ማካፈል


መግቢያ
በዚህ ርዕስ ሥር ስለ ክፍልፋዮች እና አሥርዮሾች ያለህን/ሽን እውቀት
ታዳብራለህ/ሪያለሽ፡፡ ክፍልፋዮችን ለክፍልፋይ ፤አሥርዮሾችን ለአሥርዮሽ
እንዴት ማካፈል እንደምትችል/ይ ትማራለህ/ሽ፡፡.

ትግበራ 3.4
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን አስላ/ይ፡፡

.
ሐ. በ”ሀ” እና በ”ለ” ላይ ያገኘሀውን/ሺውን መልስ አወዳድር/ሪ፡፡ በዚህ
ላይ በመመስረት ክፍልፋዮችን ለክፍልፋይ ለማካፈል
የምንተገብራቸውን አጠቃላይ ሂደቶች ማስቀመጥ ትችላለህ/ሽ?
2. 0.250 ÷ 0.70 አስላ/ዪ፡፡
ክፍልፋዮችን ማካፈል በቀላሉ በአካፋዩ ተገላቢጦሽ ማባዛት ነው፡፡ ከ 0 የተለየ
ማንኛውንም ክፍልፋዮች ተገላቢጦሽ አለው፡፡ የክፍልፋዩ ተገላቢጦሽ ለማግኘት
5 7
የክፍልፋዩን ላዕልና ታህት ቦታ በመቀየር ነው፡፡ ለምሳሌ የ ተገላቢጦሽ
7 5
ነው፡፡
ሀ ሐ ሀ ሐ
ክፍልፋይ ለክልፋይ ማካፈል ማለት በ ተገላቢጦሽ ማባዛት ማለት
h መ h መ

ነው፡፡
ይህ ማለት፤

ምሳሌ 9
ከዚህ በታች የተሰጡትን አስላ/ዪ፡፡

83
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ

አሥርዮሽን ለአሥርዮሽ ለማካፈል በመጀመርያ ሁለቱንም አሥርዮሾች ወደ


ክፍልፋዮች ከቀየርክ/ሽ በኋላ በክፍልፋዮች የማካፈል ዘዴ ተጠቀም/ሚ፡፡
ምሳሌ 10
ከዚህ በታች የተሰጡትን አስላ/ይ፡፡

መፍትሔ

84
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሳይንሳዊ ምልክቶች
ሜርኩሪ ኘላኔት ከፀሐይ 57,910,000 ኪ.ሜ እንደምትርቅ ታውቃለህ/ያለሽ?
እንደነዚህ ያሉ ትላልቅ ቁጥሮችን በሳይንሳዊ ምልክት ተጠቅመን እንገልፃለን፡፡

ትርጓሜ 3.1
አንድ ቁጥር ከ በሳይንሳዊ ምልክት ተፃፈ የምንለው፡-
ከ = ሀ  10ነ ፣ 1  ሀ < 10፣ ነ ሙሉ ቁጥር፣ መልክ ከተገለፀ ነው፡፡

ምሳሌ 11
ከዚህ በታች የተሰጡትን ቁጥሮች በሳይንሳዊ ምልክት ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. 36,000,000 ለ. 387,000 ሐ. 141,710,000
መፍትሔ
ሀ. 36,000,000 = 3.6×107 ለ. 387,000 = 3.87×105
ሐ. 141,710,000= 1.4171×105
የቡድን ሥራ 3.1
ሜርኩሪ ከመሬት 9.17  107 ኪ.ሜ ርቃ ትገኛለች፡፡ ጁፒተር ደግሞ ከመሬት
በ 6.29  108 ኪ.ሜ ርቃት ላይ ትገኛለች፡፡ ለመሬት ቅርብ የሆነው
ኘላኔት የቱ ነው?

ምሳሌ 12
ከዚህ በታች የተሰጡ ቁጥሮችን በአሥርዮሽ ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. 4.5  108 ለ. 3.2375  10 2
መፍትሔ
ሀ. 4.5  108 = 450,000,000 ለ. 3.2375  10 2 = 323.75

85
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 3.4
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን ክፍልፋዮች አሰላ/ዪ፡፡

2. ከዚህ በታች የተሰጡትን አስላ/ዪ፡፡

3. ፉፋ 6.5 ኪ.ግ ቲማቲም በ195 ብር ገዛ፡፡ የአንድ ኪ.ግ ቲማቲም ዋጋ


ስንት ነው?
4. ቢፍቱ እና ጓደኞቿ ትላንትና 300.50 ብር እና ዛሬ 450.40 ብር አገኙ፡፡
ያገኙትን እኩል ቢካፈሉ ስንት ስንት ብር ይደርሳቸዋል?
5. ከዚህ በታች የተሰጡትን ቁጥሮች በሳይንሳዊ ምልክት ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. 8,600 ለ. 70,800 ሐ. 600,000 መ. 9,300,000
6. ከዚህ በታች የተሰጡትን ቁጥሮች በአሥርዮሽ ፃፍ/ፊ፡፡

86
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፍ 3 ማጠቃለያ

• በ ክፍልፋይ ውስጥ ሀ ላዕል ሲባል ለ ደግሞ ታህት ይባላል፡፡

• የአንድ ክፍልፋይ ላዕልና ታህት በተመሳሳይ መቁጠሪያ ቁጥር ቢባዙ
የክፍልፋዩ ዋጋ አይቀየርም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ክፍልፋዮች ተመጣጣኝ
ክፍልፋዮች ይባላሉ፡፡

• ለማንኛውም ሀ፣ለ፣ እና ሐ መቁጠሪየ ቁጥሮች ሀ ሐ
በሚሆንበት ጊዜ፡
ለ ለ ሀሐ+ለ
ሀ = ሀ+ =
ሐ ሐ ሐ

• ለማንኛዋም ሀ፣ለ፣ሐ፣ እና መ መቁጠሪያ ቁጥሮች ከዚህ በታች የተሰጡት


እውነት ይሆናሉ፡፡
ሀ ሐ ሀመ+ለሐ ሀ ሐ ሀ×ሐ

+መ = ለመ ለ
×መ= ለ×መ

ሀ ሐ ሀመ−ለሐ ሀ ሐ ሀ መ

−መ = ለመ ለ
÷መ=ለ×ሐ

አሥርዮሽን መደመርና መቀነስ ማከናወን የምንችለው አሰርዮሾችን ቁልቁል


በመፃፍ እና የአሥርዮሽ ነጥቦች በአንድ ረድፍ በማስቀመጥ በመደመርና
በመቀነስ ነው፡፡ እያንዳንዱ አሥርዮሽ ወደ ክፍልፋይ በመቀየር ከደመርን
ወይም ከቀነስን በኋላ የተገኘውን ውጤት ወደ አሥርዮሽ እንቀይራለን፡፡

የምዕራፍ 3 የክለሳ መልመጃ

1. ከዚህ በታች የተሰጡትን አስላ/ዪ፡፡

87
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2. ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ ውስጥ የተሰጡትን ጥንድ ቁጥሮች


ድምር (ሀ+ለ)፣ ልዩነተ (ሀ-ለ)፣ ብዜት(ሀ×ለ) እና ድርሻ (ሀ÷ለ)
ቀይር/ሪ፡፡

(ሀ፣ለ) + −  
ሀ  3
 3, 
 2
ለ  3 1
10 ,2 
 5 4
ሐ  55 
 0.657, 
 100 
መ (0.125,0.025)
1
3. ጫልቱ 2 ኪ.ግ ቀይ ሽንኩርት እና 0.75 ኪ.ግ ነጭ ሸንኩርት ገዛች፡፡
2
በአጠቃላይ ስንት ኪ.ግ ሽንኩርት ገዛች?
3
4. ቦና ለሦስት ቀናት በእግሩ ተጓዘ፡፡ በመጀመሪያው ቀን 3 ኪ.ሜ፤
4
በሁለተኛው ቀን 2.5ኪ.ሜ እና በሶስተኛው ቀን 6.875ኪ.ሜ ቢጓዝ፣
በአጠቃላይ በሶስቱ ቀናት ምን ያህል ኪ.ሜ ተጓዘ?
5. ከዚህ በታች የተሰጡትን በሳይንሳዊ ምልክት ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. 9,800 ለ. 300,000 ሐ. 2,180,000 መ. 89,000,000
6. ከዚህ በታች የተሰጡትን በአሥርዮሽ ፃፍ/ፊ፡፡

ሀ. 7.03 10 ለ. 6.55  10


5 9
ሐ. 8.07  10 4 መ. 9.99 107

88
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

,
ምዕራፍ ለጠ + ሀ > 0

4 ለ = ከሀ እና ሀ =

መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ


ነገሮች እና ወደረኝነት

የመማር ውጤቶች፡ በዚህ ምዕራፍ ትምህርት ሂደት እና ማጠቃለያ ላይ፡-


• እንደነ ጠ +ሀ >ለ ያሉ መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮችን
መፍትሔ የመፈለግ ችሎታህን/ሽን ታዳብራለህ/ሪያለሽ፡፡
• መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮችን ለማስላት የተለያዩ የዓረፍተ
ነገር ተለዋዋጭ ዳንቦችን ትጠቀማለህ/ሸ፡፡
• የርቱዕ ወደረኛ እና ኢ-ርቱዕ ወደረኛ ፅንሰ ሃሳብ ታስተውላለህ/ሽ፡፡
• የእለት ተለት ተጨባጭ ኘሮብሌሞችን ለመፍታት መሥመራዊ
የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች እና ወደረኝነት ትጠቅማለህ/ሽ፡፡

መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ከዚህ በፊት በባለአንድ ተለዋዋጭ የያለእኩልነት ዓረፍተ
ነገር ላይ የነበረህን/ሸን እውቀት ታዳብራለህ/ሽ፡፡ እንዲሁም የርቱዕ ወደረኛ፤
ኢ-ርቱዕ ወደረኛ እና የወደረኝነት ያዊት ፅንሰ ሃሳብን ትማራለህ/ሽ፡፡

89
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.1 መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ክለሳ


መግቢያ
ባለፋት ክፍሎች ውስጥ ስለ መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ርዕሰ ስር ሰለ መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ
ነገሮች ከማየትህ/ሽ በፊት የእኩልነት ዓረፍተ ነገርን በመከለስ ትገነዘባለህ/ሽ፡፡

ትግበራ 4.1
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን በቡድን ተወያዩበት፡፡
ሀ. የእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ለ. መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ሐ.ተመጣጣኝ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች
መ. ተለዋዋጭ
ሠ. የመስርያ ክልል
ረ. መፍትሔ
2. በተሰጠው የመስርያ ክልል ውስጥ ካሉት ቁጥሮች በ”ጠ” ቦታ
በመግባት የተሰጠውን የእኩልነት ዓረፍተ ነገር እውነት የሚያደርገው
የቱ ነው?
ሀ. ጠ − 8 = 10፣ የመስርያ ክልል፤ 10፣ 13፣ 15፣ 16፣ 18፣ 21
3 3 3
ለ. ጠ + = ፣የመስርያ ክልል፤ 0፣ 1፣ ፣ 5፣ 6
2 2 2

3. ከዚህ በታች ለተሰጡት በ “ጠ − ሀ = ለ” የእኩልነት ዓረፍተ ነገር መልክ


ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. አንድ ካልታወቀ ቁጥር ላይ 25ን ብንቀንስ ልዩነቱ 21 ይሆናል፡፡
ለ. እኔ አንድ ያልታወቀ ቁጥር እያሰብኩ ነው፡፡ ከዚህ ቁጥር ላይ 36
ቢቀነስ ውጤቱ 47 ይሆናል፡፡

90
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገርን ወደ ተመጣጣኝ መስመራዊ


የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ለመቀየር የሚረዱንን ደንቦች ማስታወስ፡-

ሀ. በመስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ላይ በሁለቱም በኩል እኩል


ቁጥር ብንደምር የሚገኘው መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ከመጀመሪያው መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ
ነው፡፡ ይህ ማለት ጠ = ሀ ከሆነ፣ ጠ + ለ = ሀ + ለ ይሆናል
(ለ ቁጥርን ይወክላል)፡፡
ለ. መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ላይ በሁለቱም በኩል እኩል
የሆነ ቁጥር ብንቀንስ የሚገኘው መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ከመጀመሪያው መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ጋርተመጣጣኝ
ነው፡፡ ይህ ማለት ጠ = ሀ ከሆነ፣ ጠ − ለ = ሀ−ለ ይሆናል(ለ ቁጥር
ይወክላል)፡፡
ሐ. መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገርን በሁለቱም በኩል 0 ባልሆነ ቁጥር
ቢባዛ የሚገኘው መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከመጀመሪየው
መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ነው፡፡ ይህ ማለት
ጠ = ሀ ከሆነ፣ ጠለ = ሀለ ይሆናል (ለ ቁጥርን ይወክላል)፡፡
መ. መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገርን በሁለቱም በኩል 0 ባልሆነ
ቁጥር ቢካፈል የሚገኘው መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ከመጀመሪየው መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ
ጠ ሀ
ነው፡፡፡፡ ይህ ማለት ጠ = ሀ ከሆነ፣ = (ለ ቁጥርን
ለ ለ

ይወክላል)፡፡

91
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 1
ከዚህ በታች ለተሰጡት የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች መፍትሔ ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ

ከሁለቱም በኩል 22 መቀነስ

በሁለቱም በኩል 6.9 መደመር

ትርጓሜ 4.1
ሁለት መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች በአንድ የመስርያ ክልል ውስጥ
ተመሳሳይ መፍትሔ ካላቸው፣ተመጣጣኝ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 2
ከዚህ በታች የተሰጡት ዓረፍተ ነገሮች ተመጣጣኝ መሆናቸውን ወይም
አለመሆናቸውን ላይ/ዪ፡፡
ሀ. ጠ + 5 = 8 እና ጠ + 3 = 6 ለ. ጠ — 4 = 7 እና ጠ — 3 = 9
መፍትሔ
ጠ + 5 = 8 እና ጠ + 3 = 6
ጠ + 5 — 5 = 8 — 5 እና ጠ + 3 — 3 = 6 — 3
ጠ= 3 እና ጠ = 3
ተመሳሳይ መፍትሔ ስላላቸው ተመጣጣኝ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡
ለ. ጠ — 4 = 7 እና ጠ —3 = 9

92
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ጠ — 4+ 4 = 7 + 4 እና ጠ —3+3 = 9+3
ጠ = 11 እና ጠ = 12
መፍትሔዎቻቸው እኩል ስላልሆኑ ተመጣጣኝ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች
አይደሉም፡፡

መልመጃ 4.1
1. ከዚህ በታች ለተሰጡት መፍትሔ ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 55 + የ = 92 ለ. 4.3+ የ = 6.2 ሐ. ጠ — 87 = 45
መ. 13.5 = ተ — 10.7 ሠ. 19.4 = ሰ — 13.8 ረ. የ+ 6.4 = 7.8
2. ከዚህ በታች ለተሰጡት መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች
ተመጣጣኛቸውን ፈልግ/ጊ፡፡

መ. የ - 4.7 = 8.4
3
3. ከዚህ በታች ለተሰጡት ዓረፍተ ነገሮች ከ 40፤ 0.4፤1.5፤ እና
ቁጥሮች
4
መካከል በ”ነ” ቦታ በመተካት ዓረፍተ ነገሩ እውነት ወይም ሐሰት
መሆኑን ለይ/ዪ፡፡

93
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.2 መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮችን በመተካት


መፍትሔ መፈለግ
መግቢያ
በሂሳብ ትምህርት ውሰጥ ተለዋዋጮች የማይታወቅ ነገርን ይወክላሉ፡፡ በዚህ
ርዕስ ስር ተለዋዋጮችን እና የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮችን በመጠቀም
የቃላት ኘሮብሌሞችን እንዴት እንደምትተካ/ኪ ትማራለህ/ያለሽ፡፡
እንዲሁም ከተሰጡት ዋጋዎች ወይም ቁጥሮች ውስጥ ለያለእኩልነት ዓረፍተ
ነገሮች መፍትሔ እንዴት እንደምትፈልግ/ጊ ትማሪለህ/ያለሽ፡፡

ትግበራ 4.2
1. ከዚህ በታች የተሰጡት የእኩልነት ዓረፍተ ነገርች ወይም የያለእኩልነት
ዓረፍተ ነገሮች መሆናቸውን ለይ/ዪ፡፡

2. ቀጥሎ ከተሰጡት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ኣውነት የሆነው የቱ ነው?

ትርጓሜ 4.2
መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ሀጠ + ለ > 0 ወይም ሀጠ + ለ ≥ 0
ወይም ሀጠ + ለ< 0 ወይም ሀጠ + ለ< 0 ወይም ሀጠ + ለ ≤ 0 ፣ሀ ≠ 0፣
መልክ የተፃፈ ነው፡፡

94
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 3
ከዚህ በታች የተሰጡ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች (I እስከ V) የተሰሰጡትን
በመጠቀም ከ”ሀ” ---- “ሠ” ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡
i. 4 > 8 ii. 6 < 8 iii. ጠ+ 3 < 6 iv. ጠ - 3 < ጠ v. ጠ- 3 > ጠ
ሀ. ከነዚህ ከተሰጡት የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ሁል ጊዜ
እውነት የሆነው የቱ ነው? የትኛው ሁል ጊዜ ሐሰት ነው?

ለ. በ (iii) ቁጥር ላይ፣ በ”ጠ” ቦታ 5ን ተካ/ኪ፡፡ የሚገኘው የያለእኩልነት

ዓረፍተ ነገር እውነት ነው?

ሐ. በ (ii) ቁጥር ላይ በ “ጠ” ቦታ 2ን ተካ/ኪ፡፡ የሚገኘው የያለእኩልነት

ዓረፍተ ነገር እውነት ነው ?

መ. በ (iv) ቁጥር ላይ በ”ጠ” ቦታ 3ን ተካ፡፡ የተገኘው የያለእኩልነት

ዓረፍተ ነገር እውነት ነው?

ረ. በ (v) ቁጥር ላይ በ”ጠ” ቦታ 3ን ተካ/ኪ፡፡ የተገኘው የያለእኩልነት

ዓረፍተ ነገር እውነት ነው፡፡


መፍትሔ
ሀ. ii በማንኛውም ጊዜ እውነት ነው፡፡ i ደግሞ ሁልጊዜ ሐሰት ነው፡፡

ለ. በ (iii) ቁጥር ላይ በ”ጠ” ቦታ 5 በመተካት 5 + 3 < 6 ወይም 8 < 6

እናገኛለን፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር ሐሰት ነው፡፡

ሐ. በ (iii) ቁጥር ላይ በ”ጠ” ቦታ 2 በመተካት 2 + 3 < 6 ወይም 5 < 6

እናገኛለን፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር እውነት ነው፡፡

መ. በ (iv) ቁጥር ላይ በ”ጠ” ቦታ 3 ስንተካ፣ 3 − 3 < 3 ወይም 0<3


4− 3 < 4 እናገኛለን፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር እውነት ነው፡፡ 4ን ብንተካ

95
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ወይም 1 < 4 እናገኛለን፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር እውነት ነው፡፡ ማንኛውንም


ቁጥር ብንተካ ጠ - 3 < ጠ ሁልጊዜ እውነት ነው፡፡
ሠ. በ (v) ቁጥር ላይ በ”ጠ” ቦታ 3 ን ብንተካ 3 − 3 > 3 ወይም 0 > 3
እናገኛልን፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር ሐሰት ነው፡፡ ሌላ ማንኛውም ቁጥር
ብንተካ የ ጠ −3 > ጠ ዓረፍተ ነገር እውነት የሚያደርግ
አታገኝም/ኚም፡፡ ስለዚህ ዓረፍተ ነገሩ ሁል ጊዜ ሐሰት ነው፡፡
አንዳንድ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ሁል ጊዜ እውነት ናቸው፡፡
አነዳንድ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ደግሞ ሁል ጊዜ ሐሰት ናቸው፡፡
አንዳንድ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች በተለዋዋጮች ቦታ ዋጋ ብንተካ
የተወሰኑትን ዓረፍተ ነገሮች እውነት ለሌሎቹን ደግሞ ሐሰት የሚያደርጉ
ናቸው፡፡

አስተውል/ዪ
የአንድ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር መፍትሔ አንድ ቁጥር በተለዋዋጭ ቦታ
ተተክቶ ዓረፍተ ነገሩን እውነት የሚያደርግ ነው፡፡

ምሳሌ 4
ከታች ከተሰጡት የመስርያ ክልሎች ውስጥ ቁጥሮችን በ”ጠ” ቦታ በመተካት ለ
“ጠ + 2 < 5” መፍትሔውን ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. የመስርያ ክልሉ ሙሉ ቁጥሮች ከሆኑ
ለ. የመስርያ ክልሉ የመቁጠሪያ ቁጥሮች ከሆኑ
ሐ. በ ሀ እና በ ለ ላይ የተገኙ መፍትሔዎችን በቁጥር መስመር ላይ
አሳይ/ዪ፡፡

መፍትሔ
ሀ. ጠ= 0፣ 0 + 2 < 5 ወይም 2 < 5 እውነት ነው፡፡

ጠ= 1፣ 1 + 2 < 5 ወይም 3 < 5 እውነት ነው፡፡

96
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ጠ= 2፣ 2 + 2 < 5 ወይም 4 < 5 እውነት ነው፡፡

ጠ= 3፣ 3 + 2 < 5 ወይም 5 < 5 ሐሰት

በመስሪያ ክልሉ ውስጥ ዓረፍተ ነገሩን እውነት የሚያደርጉ


0፣ 1 እና 2 ናቸው፡፡ ስለዚህ መፍትሔዎቹ፣ 0፣ 1፣ 2 ናቸው፡፡
ለ. በተመሳሳይ መልኩ በመስሪያው ክልል ውሰጥ ዓረፍተ ነገሩን
እውነት የሚያደርጉት 1 እና 2 ናቸው፡፡ ስለዚህ መፍትሔዎቹ፣1፣ 2
ናቸው፡፡
ሐ. በ ሀ እና ለ የተገኙ መፍትሔዎች በቁጥር መስመር ላይ ከዚህ
በታች ተመልክተዋል፡፡

መልመጃ 4.2
1. ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ ውሰጠ በ ሀ ረድፍ ውስጥ
2. እንደተሰራው በ”ጠ” ቦታ ተተክቶ ዓረፍተ ነገሩን እውነት ወይም ሐሰት
የሚያደርግ ቁጥር ፈልግ/ጊ፡፡
የያለዕኩልነት የተለዋዋጮች የያለእኩልነት ዓረፍተ ዓረፍተ ነገሩ
ዓረፍተ ነገር ዋጋ ነገሩ ከተተካ በኋላ እውነት ወይስ
ሐሰት?
ሀ ጠ− 3 > 4 ጠ= 4 4−3  4 ሐሰት
ለ ጠ+ 3 < 4 ጠ= 4
ሐ ጠ− 1
> 4 ጠ= 5
2

መ ጠ+ 2 < 3 ጠ=
1
2

97
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሠ ጠ+ 4 > 7
ጠ= 12
2
ረ ጠ − 3 < 0.56 ጠ = 3.3

3. ከዚህ በታች የተሰጡትን የቃላት ኘሮብሌሞች ወደ የያለእኩልነት


ዓረፍተ ነገር ቀይር/ሪ፡፡
ሀ. ቶለሣ የቦንቱ ታላቅ ነው
ለ. አንድ ቁጥር ከራሱ እጥፍ ሲቀነስ 4 ይበልጠል፡፡

4.3 ባለአንድ እርምጃ መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ


ነገርን መፍትሔ መፈለግ
መግቢያ
በዚህ ርዕስ ሥር መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር አንድ ተለዋጭ
ያለውና በአንድ እርምጃ መፍትሔ መፈለግ ያለህ/ሽን እውቀት
ታዳብራለህ/ሪያለሽ፡፡

ትግበራ 4.3
ከዚህ በታች ለተሰጡት የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ፃፍ/ፊ፡፡

ሀ. አንድ ክፍል ብያንስ 30 ሰዎችን መያዝ ይችላል፡፡

ለ. አንድ ክፍል ከ150 ሰዎች በላይ መያዝ አይችልም፡፡

አንዳንድን የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ከመስሪያ ክልል ውስጥ በተለዋጭ


ቦታ እያንዳንዱን ቁጥር በመተካት መፍትሔዎቹን ለመፈለግ ጊዜ ይወስዳል፡፡
ስለዚህ አንድን የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ቶሎ መፍትሔውን ለመፈለግ
የሽግግር ደንቦችን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

98
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 5
ከዚህ በታች ለተሰጡት የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከተሰጡት የመስርያ ክልል
ውስጥ መፍትሔዎቹን ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
ሀ. ከ ≤ ምልክት በስተግራ ያለው ቁጥር መቀነስ ስለሆነ በሁለቱም በኩል
0.56 ትደምራለህ/ሪያለሽ፡፡ ይህ ማለት

ስለዚህ የዚህ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር መፍትሔዎቹ፣ 0፣ 1፣ 2፣


3፣ 4፣ …፣ 82 ናቸው፡፡

ከ  ምልክት በስተግራ በኩል ያለው መደመር ስለሆነ በሁለቱም በኩል


40 ትቀንሳለህ/ሺያለሽ፡፡ ይህ ማለት፡-

ስለዚህ፣ የያለእኩልነቱ ዓረፍተ ነገር መፍትሔዎች፤ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣


…. ናቸው፡፡
ሐ. ጠ+0.30 > 60፣
ከ > ምልክት በስተግራ በኩል ያለው መደመር ስለሆነ ከሁለቱም በኩል
0.30 ትቀንሳለህ/ሽያለሽ፡፡ ይህ ማለት

ስለዚህ የያለእኩልነቱ ዓረፍተ ነገር መፍትሔዎች በከፊል ሲዘረዘሩ፤


63፣ 64፣ 65፣ … ይሆናሉ፡፡

99
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የቡድን ሥራ 4.1
ከዚህ በታች የተሰጠውን ጥንድ መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ላይ
በመወያየት በሁለቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ለክፍል ተማሪዎች
ግለፅ/ጪ፡፡
ግራ ቀኝ

ሠ. ከሀ እስከ መ የተሰጡትን ጥንድ መሰመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች


ውስጥ እውነት የሆነው የቱ ነው? የትኛው ሐሰት ነው?
ረ. በስተግራ በኩል ያለውን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ምን
ብናደርግ ነው በስተቀኝ ያለውን የምናገኘው?

መስራዊ ያለእኩልነት ዓረፍተ ነገርን ወደ ጠመጣጣኝ መለመረዊ


የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር የሚንቀይርበት ደንቦች
ሀ. የተሰጠን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር በሁለቱም አቅጣጫ
እኩል የሆነ ቁጥር በመደመር የሚናገኘው መስመራዊ ያለእኩልነት ዓረፍተ
ነገር ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል፡፡ ይህ ማለት ጠ < ሀ ከሆነ፣
ጠ+በ < ሀ + በ ይሆናል(በ ቁጥር ነው)፡፡

100
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለ. የተሰጠን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከሁለቱም ጎን እኩል


የሆነ ቁጥር ቀንሰን የሚናገኘው መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ከመጀመሪያው መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ
ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ጠ > ሀ ከሆነ፣ ጠ - ለ > ሀ - ለ ይሆናል(ለ
ቁጥር ነው)፡፡
ሐ. የተሰጠን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከዜሮ ውጪ
በሆነ ቁጥር ሁለቱንም ጎን እኩል በሆነ ቁጥር በማባዛት የሚገኘው
መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከመጀመሪያው መስመራዊ ያለ
እኩልነት ዓረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ነው፡፡ ይህም ማለት፣
ጠ > ሀ ከሆነ፣ ጠ × ለ > ሀ × ለ ይሆናል(ሀ ቁጥር ነው)፡፡
መ. የተሰጠን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከዜሮ ውጪ
በሆነ ቁጥር ሁለቱንም ጎን እኩል በሆነ ቁጥር በማካፈል የሚገኘው
መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከመጀመሪያው መስመራዊ
የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል፡፡
ጠ ሀ
ይህም ማለት ጠ > ሀ ከሆነ፣ > ይሆናል(በ ቁጥር ነው)፡፡
በ በ

ትርጓሜ 4.3
ሁለት የተሰጡ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች በተሰጠ የመስርያ ክልል ውስጥ
ተመሳሳይ መፍትሔዎች ካላቸው ተመጣጣኝ መስመራዊ የያለእኩልነት
ዓረፍተ ነገሮች ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 6
ከዚህ በታች የተሰጡትን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ተመጣጣኝ
መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን ላይ/ዪ፡፡
ሀ. ጠ + 5 < 8 እና ጠ + 3 < 6 ለ. ጠ – 4 > 7 እና ጠ – 3 > 9

101
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ

ስለዚህ የሁለቱም የያለእኩልነት መፍትሔዎቻቸው ስለሚመሳሰሉ ተመጣጣኝ


መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ዓረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡

ስለዚህ ሁለቱም የያለእኩልነት መፍትሔዎቻቸው ስለማይመሳሰሉ ተመጣጣኝ


መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ናቸው፡፡

መልመጃ 4.3
1. የመስርይ ክልሉ ሙሉ ቁጠሮች ከሆኑ፣ለሚከተሉት የያለእኩልነት ዓረፍተ
ነገሮች መፍትሔ ፈልግ/ጊ፡፡

2. ከዚህ በታች በተሰጡት መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች


ከመቁጠሪያ ቁጥሮች መካከል መፍትሔ ፈልግ/ጊ፡፡

102
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.4 ወደረኝነት
መግቢያ
በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር ሰለ ወደረኝነት ፅንስ ሀሳብን ትማራለህ/ሪያለሽ፡፡
የርቱዕ ወደረኝነት እና የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ልዩነቱ ታሳያለህ/ሽ፡፡ ከዚህም ሌላ
የርዕቱ ወደረኝነት እና የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት በግራፍ ታሳያለህ/ሽ፡፡
የሁለት የተለያዩ ነገሮች ዋጋ፣ የአንደኛው ሲጨምር ሌላኛውም አብሮት
እየጨመረ ከሄደ ወይም የሁለቱም ዋጋ በተመሳሳይ እየቀነሰ ከሄደ፤ ወይም
የአንዱ ዋጋ ሲጨምር የሌላኛው ዋጋ ደግሞ እየቀነሰ ከሄደ የእነዚህ ነገሮች
ዋጋዎች የወደረኝነት ዝምድና አላቸው እንላለን፡፡ ለምሳሌ፤ ብዙ ነገሮችን
ስትገዛ የምታወጣው ገንዘብ መጠን ይጨምራል፡፡ እንዲሁም አንድን ሥራ
የሚሰሩ ሰዎች ከበዙ ያንን ሥራ ለመጨረስ የሚወስድባቸው ጊዜ ይቀንሳል፡፡
የወደረኝነትን ዝምድና በሁለት መንገድ ልናይ እንችላለን፡፡
እነሱም፡-
i. የአንድ ዕቃ ዋጋ ሲጨምር፣ የሌለኛው ዋጋ የሚጨምር ከሆነ ወይም
የአንድ ዕቃ ዋጋ ሲቀንስ የሌለኛውም ዕቃ ዋጋ ሊቀንስ ይችላል፡፡
ii. የአንድ ዕቃ ዋጋ ሲጨምር፣ የሌለኛውም ዕቃ ዋጋ ሊቀንስ ወይም የአንድ
ዕቃ ዋጋ ሲቀንስ፣የሌለኛው ዕቃ ዋጋ ሊጨምር ይችላል፡፡

4.4.1 ርቱዕ ወደረኝነት


ትግበራ 4.4
የ = 3ጠ ከሆነ፣ የ የ ዋጋ ጠ ላይ የተመሠረተ ይሆናል፡፡ የጠ ዋጋ የሚቀያየር
ከሆነ፣ የ የ ዋጋም በዚያው መጠን ይቀያየራል፡፡
ሀ. የጠን ዋጋ፣ 0፣ 1፣ 2፣ 3፣ 4 ብትወሰድ/ጂ የ የ ዋጋ ምን ይሆናል?
1 1 1 1
ለ. የጠን ዋጋ፤ ፣ ፣ 9 ፣ 12 ብትወስድ/ጂ የ የ ዋጋ ምን ይሆናል?
3 6

103
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የአንድ እቃ ዋጋ ሲጨምር የሌለኛውም ዕቃ ዋጋ የሚጨምር ከሆነ ወይም


የአንዱ ዕቃ ዋጋ ሲቀንስ የሌለኛውም ዕቃ ዋጋ የሚቀንስ ከሆነ እነዚህ ነገሮች
ርቱዕ ወደረኝነት አላቸው እንላለን፡፡

ትርጓሜ 4.4
የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት አላቸው የምንለው ከዜሮ የተለየ ቁጥር
ከ፣የእኩልነት ዓረፍተ ነገር የ = ከጠ ን እውነት የሚያደርግ ካለ ነው፡፡ እዚህ
ላይ ከ የወደረኝነት ያዊት ይባላል፡፡
ምልክት፡- የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው በ የ ∝ ጠ መልክ
ይፃፋል፡፡

ምሳሌ 7
ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ መስራት ጠ የስኳር መጠን በኪ.ግ እና የ
የስኳሩ ዋጋ በብር ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መልስ/ሺ፡፡
ጠ 1 2 3 4 5
የ 30 60 90 120 150

ሀ. የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና አላቸውን?


ለ. የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው፣ ዝምድናቸውን በ
የ = ከጠ መልክ ፃፍ/ፊ፡፡
ሐ. (ጠ፤ የ) ጥንድ ቁጥሮችን በውቅር ጠለል ላይ አሳይ/ዪ፡፡ እነዚህን
ነጥቦች በመስመር አገናኝ/ኚ፡፡
መ. በዚህ ሠንጠረዥ ላይ እንደሚታየው የ ጠ ዋጋ እየጨመረ ሲሄድ
የ “የ” ዋጋም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ የ እና ጠ የርቱዕ
ወደረኝነት ዝምድና አላቸው እንላለን፡፡
ለ.

104
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የ = ከጠ = 30ጠ
የ = 30ጠ
ሐ. የቀጥታ መስመር ግራፍ
የ = ከጠ = 30ጠ
የ = 30ጠ

ምስል 4.2
ሐ. የቀጥታ መስመር ግራፍ
አስተውል/ዪ
የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው ሁለቱም አንድ ላይ የጨመሩ
ወይም እየቀነሱ ይሄዳሉ፡፡ ይህም የሁለቱን ንጥጥር በማየት ይታወቃል፡፡
የ ∝ ጠ ከሆነ እና ጠ1 እና ጠ2፣ የ ጠ ዋጋዎችና የ1 እና የ2 የ የ ዋጋዎች
ጠ1 ጠ2 የ1 የ2
ከሆኑ፣ የ1
=
የ2
ወይም
ጠ1
=
ጠ2
ይሆናል፡፡

ምሳሌ 8
ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምደና
አላቸው፡፡ የጠ1 እና የ1 ን ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
ጠ ጠ1 27 45
የ 9 የ1 22.5

105
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው፤

ስለዚህ እና ይሆናሉ፡፡

መልመጃ 4.4
1. የጠ እና የ ዋጋ ከዚህ ቀጥሎ በተሰጠው መሠረት ቢሰጥህ/ሽ የወደረኝነት
ያዊት እና እሱን የሚገልጽ ቀመር ፃፍ/ፊ፡፡
ሀ. የ እና ጠ የወደረኝነት ዝምድና ካላቸው፣, የ = 12 እና ጠ = 3
ከሆኑ፤
1 1
ለ. የ እና ጠ የወደረኝነት ዝምድና ካላቸው፣ የ = እና ጠ=
2 4
ከሆኑ፤
2. በተሰጠው ቀመር ላይ በመመስረት ከዚህ በታች ያለውን ሠንጠረዥ
ሙላ/ዪ፡፡

106
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3. ከዚህ በታች የተሰጡትን ኘሮብሌሞች በተጠየቀው መሰረት አሰላ፣ዪ፡፡


ሀ. የ እና ጠ የወደረኝነት ዝምድና አላቸው፡፡
ጠ = 20 ከሆነ፣ የ = 100፤ እና ጠ = 5 ከሆነ የ ን ፈልግ/ጊ፡፡
ለ. ነ እና ቀ የወደረኝነት ዝምድና አላቸው፡፡ ቀ = 3 ከሆነ፣ ነ = 39፤
እና ቀ = 8 ከሆነ፣ ነ ን ፈልግ/ጊ፡፡
4. አንድ መኪና በሰዓት 65ኪ.ሜ ይጓዛል፡፡ መኪና የሚጓዝበት
ፍጥነት መኪናው ከተጓዘበት ሰዓት ጋር እየተቀየረ ይሄዳል::
ከዚህ በታች የተሰጠውን ሠንጠረዥ ሙላ/ዪ፡፡ ግራፋን ሥራ/ሪ፡፡
ጊዜ (በሰአት) 1 2 3 4 5
ርቀት (ኪ.ሜ) 65
5. የአንድ ልብስ ዋጋ በቀጥታ ከልብሱ ርዝመት ጋር አብሮ እየተቀየረ
ይሄዳል፡፡ የ 5ሜ ልብስ ዋጋ 600 ብር ከሆነ፣ የ 6 ሜትር ልብስ ዋጋ
ፈልግ/ጊ፡፡
6. ቦንሣ በሰዓት በፈረስ 12 ኪ.ሜ የሚጓዝ ከሆነ፣ በ5 ሰዓት ውስጥ ስንት
ኪ.ሜ ይጓዛል?
7. አያንቱ ከ21 ሊትር ወተት ውስጥ 3ኪግ ቅቤ ብታወጣ፣ ከ48 ሊትር
ወተት ውስጥ ምን ያህል ኪ.ግ ቅቤ ታወጣለች?

107
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

8. አንድ ነጋዴ አንድ ኪ.ግ ቡና በ200 ብር ሸጠ እንበል፡፡ ከዚህ በታች


የተሸጠውን የቡና መጠን ጠ እና የተሸጠበት ዋጋ ብር የ ከሆኑ፣
የወደረኝነትን ያዊት ፈልግ/ጊ፡፡

4.4.2 ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት


ትግበራ 4.5
የጠ = 36 ከሆነ ከዚህ በታች ያሉትን ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. ጠ = 1 ከሆነ የ የ ዋጋ ስንት ይሆናል?
ለ. ጠ = 2 ከሆነ የ የ ዋጋ ስንት ይሆናል?
ሐ. ጠ = 3 ከሆነ የ የ ዋጋ ስንት ይሆናል?
መ. ጠ = 4 ከሆነ የ የ ዋጋ ስንት ይሆናል?
ሠ. ከ ሀ እስከ መ ባለው የ ጠ ዋጋ እየጨመረ ከሄደ የ የ ዋጋ ምን
ይሆናል?
ረ. ከሀ እስከ መ ያሉትን ጥንድ ቁጥሮችን አካፍል/ዪ፡፡ በሁሉም ቦታ አንድ
ዓይነት ቁጥር አገኘህ/ሽ?
ሰ. ከሀ እስከ መ ያሉትን ጥንድ ቁጥሮች አባዛ/ዢ፡፡ በሁሉም ቦታ አንድ
ዓይነት ቁጥር አገኘህ/ሽ?
ሸ. ከሀ እስከ መ ያሉትን ጥንድ ቁጥሮች በመጠቀም ግራፍ መስርት/ቺ፡፡
ይህን ግራፍ ከርቱዕ ወደረኝነት ግራፍ ጋር አመዛዝን/ኚ፡፡ ምን አይነት
ልዩነት አገኘህ/ሽ?
ሁለት ነገሮች ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና አላቸው የምንለው አንዱ
እየጨመረ ሲሄድ ሌላኛው እየቀነስ ወይም አንዱ እየቀነስ ሲሄድ ሌላኛው
እየጨመረ ከሄደ ነው፡፡

108
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትርጓሜ 4.5
ጠ እና የ ኢ-ርቱዕ የወደረኝነት ዝምድና አላቸው የምንለው ከ 0 የተለየ

ቁጥር ከ፤ ጠየ = ከ ወይምየ = ጠ ን እውነት የሚያደርግ ካለ ነው፡፡ እዚህ

ላይ ከ የወደረኝነት ያዊት ይባላል፡፡


1
ምልክት :- ጠ እና የ ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ካላቸው የ ∝ ጠ ብለን እንጽፋለን፡፡

ምሳሌ 9
ጠ 6 12 24 48 96

የ 24 12 6 3 3
2
ከዚህ በላይ ባለው ሠንጠረዥ የምናገኘው የጠ ዋጋ ሲጨምር የ የ ዋጋ
መቀነሱን ነው፡፡ የ የ ዋጋን ለ ጠ ስናካፍል የምናገኘው ቁጥር ተመሳሳይ
24 12 6 3 3
አይደለም፡፡ ይህ ማለት     ፤በሌላ በኩል ከዚህ በላይ
6 12 24 48 2
96
ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የ ጠ እና የ የ ዋጋ ጥንድ ቁጥሮች ስናባዛ
3
የምናገኘው ብዜት እኩል ነው፡፡ 6  24 = 12  12 = 24  6 = 48  3 = 96  = 144
2
ስለዚህ ጠ እና የ ኢ-ርቱዕ የወደረኝነት ዝምድና አላቸው፡፡ በዚህ ውስጥ
የወደረኝነት ያዊት ቁጥር 144 ነው

ምሳሌ 10
ቀጥሎ ለተሰጠው ሠንጠረዥ የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ግራፍ መስርት/ቺ፡፡
ጠ 1 2 3 4 5

የ 24 12 8 6 4.8

109
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ

24

ምስል 4.3

12

4.8
1 2 3 4 5
ምሳሌ 11
ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ ውስጥ ጠ እና የ የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት
ዝምድና ካላቸው የ ሀ፣ ለ እና ሐ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡

ሀ. ጠ 18 ለ ለ.
36 ጠ 19 ለ 6 3
የ 24 ሀ 8 6 2
የ ሀ 4.75 ሐ 38

መፍትሔ

110
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 4.5
1. ከዚህ በታች ካሉት ዝምድናዎች የየትኛው ሂደት ኢ-ርቱዕ ወደረኝነትን
ያሳያል?
ሀ. ስፋቱ 40ሜ2 የሆነ ሬክታንግል ወርድ እና ርዝመት
ለ. አንድ ሰው በባንክ ውስጥ ያጠራቀመውን ብር እና በባንኩ ህግ መሰረት
በየአመቱ የሚያገኘው/ታገኘው ወለድ፡፡
ሐ. የመኪና ፍጥነትና አንድ የተወሰነን ርቀትን ተጉዞ ለመጨረስ
የሚወሰድበት ሰዓት፡፡
2. ከሚከተለው ሠንጠረዥ ውስጥ የጠ እና የ ን ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት
የሚያሳየው የቱ ነው?

4.5 የወደረኝነት ፅንሰ ሀሳብን ሥራ ላይ ማዋል


መግቢያ
በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር የርቱዕ ወደረኝነት እና የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ጥቅም
ከእለት ተለት ኑሮ ጋር ያለውን ዝምድና ትማራለህ/ሪያለሽ፡፡

111
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.5.1 የርቱዕ ወደረኝነት ፅንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ ማዋል


• አንድ ቤተሰብ በወር በአማካይ የሚያወጠው ወጪ እና የቤተሰቡ አባላት፣
• የታወቀ ልብስ እና የልብስ ዋጋ፣
• የእንጨቱ ርዝመት እና ጥላው፣
• ሰው የሚለብሰው ልብስ እና መጠን፣
• አንድን ሥራ የሚሰሩ ሰዎች ብዛት እና ሥራውን ለመጨረስ
• የሚፈጅባቸው ሰዓት፣
• የሙዝ ብዛት እና ሙዙን ሊይዝ የሚችል ሣጥን፣
• በሁለት ከተሞች መሃከል ያለው ርቀት እና ርቀቱን ለመጓዝ የሚወሰደው
ሰዓት፣
• አንድ የሚሸጥ ነገር እና ትርፉ፣
• የአንድ ሰው ገቢና ሥራውን ለመስራት የወሰደበት ሰዓት፣
• ሆቴልን የሚጐበኙ ሰዎች ብዛት ከጨመረ፣ ገቢውም በዚያው ልክ
ይጨምራል፣
• በባንክ የሚቆጠበው ብር ሲጨምር ወለዱም ይጨምራል፣
• በቤት ውስጥ የምንጠቀመው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ከጨመረ የሚከፈለው
ገንዘብ ይጨምራል፣
የጠ ዋጋ ጠ1፣ጠ2 እና የ የ ዋጋ የ1፣ የ2 ከሆኑ፣ ጠ እና የ የወደረኝነት
ዝምድና ካላቸው፣ የ ∝ ጠ፤ ወይም

ምሳሌ 12
አንድ የመብራት ምሶሶ 7 ሜትር ይረዝማል፡፡ ጥለው ደግሞ 5 ሜትር
ይረዝማል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የጥለው ርዝመት 10 ሜትር ከሆነ፣
የምሶሶው ርዝመት ስንት ሜትር ይሆናል?

112
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
እስቲ የምሶሶውን ርዝመት ጠ እንበል፡፡ የምሶሶ ርዝመት ሲጨምር ጥላውም
ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ምሶሶው እና ጥላው የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና አላቸው
እንላለን፡፡

ስለዚህ የምሰሶው ርዝመት 14 ሜትር ይሆናል፡፡

ምሳሌ 13
የአንድ ካርታ እስኬል 1: 20000000 ተሰጠ፡፡ በማፑ ላይ በሁለት ከተሞች
መሃከል ያለው ርቀት 4ሳ.ሜ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ከተሞች በመሬት ላይ
ያላቸውን ርቀት ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
በማፑ ላይ ያለው ርቀት 4ሳ.ሜ ነው እስቲ፡፡ በመሬት ላይ ያለውን ርቀት ጠ
እንበለው፡፡

ስለዚህ በመሬት ላይ ያለው ርቀት 80,000,000ሳ.ሜ ነው፡፡

113
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 14
14ኪ.ግ ሽንኩርት 441 ብር ከሆነ፣ የ22 ኪ.ግ ሽንኩርትን ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
የሽንኩርቱ መጠነቁስ ከዋጋው ጋር ይጨምራል፡፡ ስለዚህ የሽንኩርቱ
መጠነቁስና ዋጋው የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና አላቸው፡፡ እስቲ የ22ኪ.ግ
የሽንኩርት ዋጋን ጠ እንበል፤

ስለዚህ የ22 ኪ.ግ የሽንኩርት ዋጋ 693 ብር ይሆናል፡፡

4.5.2 የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ፅንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ ማዋል

• የመኪና ፍጥነት ከጨመረ ቦታው ለመድረስ የሚወስድበት ሰዓት


ይቀንሳል፡፡
• ብዙ መኪናዎች በመንገድ ላይ ካሉ መንገዱ ይጣበባል፡፡
• ከፀሐይ በተራቀ ልክ የፀሐይ ብርሃን ይቀንሳል፡፡
• አንድን ሥራ የሚሰሩ ሰዎች ብዛት ከጨመረ ሥራውን ለመጨረስ
የምወሰድባቸው ጊዜ ያጥራል፡፡
• ጠንካራ እና በደንብ የሚሰሩ መምህራኖች ሲጨምሩ የሚወደቁ
ተማሪዎች ቁጥር ይቀንሳል፡፡

114
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

• የ ጠ ዋጋዎች ጠ1፣ጠ2 እና የ የ ዋጋዎች የ1፣ የ2 ከሆኑ ጠ እና የ


1
የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው፣ የ ∝ ጠ፣

ጠ1 የ2 ጠ2 የ1
ጠ2
=
የ1
ወይም
ጠ1
=
የ2
ይሆናል፡፡
ምሳሌ 15
አንድ አሽከርካሪ 72ኪ.ሜ በሰዓት ፍጥነት በመሄድ አንድ የተወሰነን ርቀት
ለመጨረስ 2፡45 ይወስድበታል፡፡ 90ኪ.ሜ ለመሄድ ስንት ሰዓት
ይወስድበታል?

መፍትሔ
1. ሰዓት = 60 ደቂቃ
ጠ= 45 ደቂቃ
ጠ  60ደቂቃ = 1 ሰዓት  45 ደቂቃ

ስለዚህ 2 ሰዓት ከ 45 = 2.75 ሰዓት ነው::


ፍጥነት (ኪ.ሜ/ሰዓት) ሰዓት (ሰ)
72 2.75
90 ጠ

ፍጥነት ስጨምር ሰዓቱ ያንሳል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ኢ-ርትሁ ወደረኝነት


የወደረኝነት ዝምድና አሏቸው

115
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 16
ጠ እና የ የ ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና አላቸው ጠ = 10 ከሆነ የ=6
ይሆናል፡፡ ከዚህ በታች ካሉት ጥንድ ቁጥሮች ጠ እና የ በተገለጸው
የወደረኝነት ዝምድና ውስጥ የማይታቀፈው የቱ ነው?
ሀ.12 እና 5 ለ. 15 እና 4 ሐ. 25 እና 2.4 መ. 45 እና 1.3

መፍትሔ
ጠ እና የ ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ካላቸው ጠ × የ ከ ይሆናል፡፡

ሀ. 12  5 = 60 ለ. 15  4 = 60

ሐ. 25  2.4 = 60 መ. 45  1.3  60
ስለዚህ መ ሊሆን አይችልም፡፡

መልመጃ 4.6
I. ከዚህ በታች የተሰጡትን እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልስ/ሺ፡፡
1. ጠ እና የ የኢ-ርትዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው ጠየ = ከ፣ ከ > 0 ከሆነ፣
ከ የወደረኝነት ያዊት ነው፡፡
2. የሮምበስ የጐን ርዝመት እና ዙሪያው ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና አላቸው፡፡

3. ሁለት ነገሮች ጠ እና የ ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው

ቋሚ ቁጥር ነው፡፡
4. የ10 እስክሪብቶ ዋጋ 140 ብር ከሆነ፣ የ19 እስክሪብቶ ዋጋ 266 ብር
ይሆናል፡፡
5. አምስት ሰዎች አንድን ሥራ ሰርተው ለመጨረስ 10 ቀን ከወሰደባቸው
አንድ ሰው ደግሞ ሰርተው ለመጨረስ 20 ቀን ይወስድበታል፡፡

116
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ii. ከዚህ በታች የተሰጡትን በተጠየቀው መሰረት መልስ/ሺ፡፡


6. አንድ የመብራት ምሰሶ 14 ሜትር ይረዝማል፡፡ ጥላው ደግሞ 10
ሜትር ይረዝማል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የጥላው ርዝመት 15 ሜትር ከሆነ
የመብራቱን ምሰሶ ርዝመት ፈልግ/ጊ፡፡
7. አንድ መኪና በ25 ደቂቃ 14ኪ.ሜ ይጓዛል፡፡ በ5 ሰዓት ውስጥ
ስንት ኪ.ሜ ይጓዛል?
8. አንድ ዶላር በ40 ብር የሚመነዘር ከሆነ፣ 1000 ዶላር በስንት ብር
ይመነዘራል?
9. አንድ ኪ.ግ ቡና 200 ብር ከሆነ፣ 250 ግራም ቡና ስንት ብር ይሆናል?
10. በካርታ እስኬል መሰረት 1: 20,000 ነው፡፡ ከዚህ በታች ያሉትን
አሰላ/ዩ፡፡
ሀ. በካርታ ላይ 5 ሳ.ሜ ከሆነ በመሬት ላይ ምን ያህል ይሆናል?
ለ. በመሬት ላይ 800 ሜትር ከሆነ፣ በካርታ ላይ ምን ያህል ይሆናል?
11. የስድስት እስክሪብቶዎች ዋጋ 96 ብር ከሆነ፣ የ18 እስክሪብቶዎችን ዋጋ
ፈልግ/ጊ፡፡

117
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፍ 4 ማጠቃለያ
• በአንድ የመስርያ ክልል ውስጥ ተመሳሳይ መፍትሔዎች ያላቸው
መሰመራያዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ተመጣጣኝ መሰመራያዊ
የያለእኩልነት ዓረፍተነገሮች ይባላል፡፡
• የተሰጠን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር በሁለቱም አቅጣጫ እኩል
የሆነ ቁጥር በመደመር የሚናገኘው መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል፡፡ የተሰጠን መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር
ከሁለቱም ጎን እኩል የሆነ ቁጥር ቀንሰን የሚናገኘው መስመራዊ
የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገር ከመጀመሪያው መስመራዊ የያለእኩልነት
ዓረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል፡፡
• ጠ እና የ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው የ = ከጠ (ከ > 0)
ይሆናል፡፡ ከ የወደረኝነት ያዊት ይበላል፡፡
• የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ውስጥ ሁለቱ ተላዋዋጮች በአንድ ላይ
ይቸምራሉ ወይም ይቀንሳሉ፡፡
• የጠ ዋጋዎች ጠ1፣ጠ2 እና የ የ ዋጋዎች የ1፣ የ2 ከሆኑና ጠ እና የ
የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው፣
ጠ1 ጠ2 የ1 የ2
የ  ጠ፣ = ወይም = ይሆናል፡፡
የ1 የ2 ጠ1 ጠ2

• ጠ እና የ ኢ-ርቱዕ የወደረኝነት ዝምድና ካላቸው የጠ እና የ የ ብዜት


ቋሚ ቁጥር ይሰጠናል፡፡ ይህ ማለት ጠየ = ከ (ከ >0) ይሆናል፡፡ እዚህ
ውስጥ ከ ያዊት ይባላል፡፡
• በኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ውስጥ የአንድ ነገር ዋጋ ከጨመረ የሌለው
ዋጋ ይቀንሳል ወይም የአንድ ነገር ዋጋ የሚቀንስ ከሆነ የሌለው ዋጋ
ይጨምራል፡፡

118
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

• የጠ ዋጋዎች ጠ1፣ጠ2 እና የየ ዋጋዎች የ1፣የ2 ከሆኑና ጠ እና


1 ጠ1 ጠ2
የኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው፣ የ  ፣ = እንላለን፡፡
ጠ የ1 የ2

የምዕራፍ 4 የክለሳ መልመጃ

1. ከዚህ በታች ያሉትን አሰላ/ዩ፡፡

2. ከዚህ በታች መስመራዊ የያለእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች በተሰጠው መስሪያ


ክልል መፍትሔ ፈልግ/ጊ፡፡
1 1 2
ሀ. ጠ − < ፣ ጠ ሙሉ ቁጥር ነው ለ. ጠ + > 4፣ ጠ መቁጠሪያ ቁጥር ነው
4 5 3
7 12
ሐ. ጠ ≤ ፣ ጠ ሙሉ ቁጥር ነው መ. ጠ ≤ ፣ ጠ መቁጠሪያ ቁጥር ነው
2 10
3. የ እና ጠ ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው እና ጠ= 16 ሲሆን የ = 10
ይሆናል፡፡ ጠ = 40 ከሆነ፣ የ የን ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡ የወደረኝነት የዊት ቁጥር
ስንት ይሆናል?
4. ከዚህ በታች ያሉትን የወደረኝነት ዝምድና በግራፍ አሰይ/ዩ፡፡
.

5. ከዚህ በታች በተሰጠውን ሠንጠረዥ ውስጥ ያሉትን የፍደሎች ዋጋ


ሙላ/ዪ፡፡
ሀ. የ እና ጠ ርቱዕ የወደረኝነት ዝምድና አላቸው፡፡

ጠ 20 50 70 A B
የ 28 c D 42 126

119
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለ. የ እና ጠ ኢ-ርቱዕ የወደረኝነት ዝምድና አላቸው፡፡


ጠ 12 ሀ 30 32 በ
የ 32 16 ሐ መ 256

6. ጠ እና የ ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው እና ጠ = 13 ሲሆን፣


የ = 39 ይሆናል፡፡ ከዚህ በታች ያሉትን ጥንድ ቁጥሮች ርቱዕ
የወደረኝነት ዝምድና ያለው የቱ ነው?
ሀ. 1 እና 3 ለ. 17 እና 51 ሐ. 30 እና 10 መ. 6 እና 18
7. ጠ እና የ ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው እውነት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ቋሚ ቁጥር ነው፡፡

ለ. ጠ ×የ ቋሚ ቁጥር ነው፡፡
ሐ. ጠ — የ ቋሚ ቁጥር ነው፡፡
መ. ጠ + የ ቋሚ ቁጥር ነው፡፡
8. ጠ እና የ ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው እውነት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ቋሚ ቁጥር ነው፡፡

ለ. ጠ ×የ ቋሚ ቁጥር ነው፡፡
ሐ. ጠ — የ ቋሚ ቁጥር ነው፡፡
መ. ጠ + የ ቋሚ ቁጥር ነው፡፡

120
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ

5
የጠለል ምስሎች እና ጥጥሮች
የመማር ውጤቶች፡ በዚህ ምዕራፍ ትምህርት ሂደት እና ማጠቃለያ ላይ፡-
• ጉርብታም ዘዌዎች፣ ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች፣ ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች እና
ዝርግ አሟይ ዘዌዎችን ትማራለህ/ሽ፡፡
• በዘዌዎች እና ትይዩ መስመሮች መካከል ያለውን ዝምድና ትወስናለህ/ሽ፡፡
• ትይዩ መስመሮች በአቋራጭ መስመር ከተቋረጡ እና ከሚፈጠሩት ዘዌዎች
ጋር የተገናኙ ኘሮብሌሞች ታሰላለህ/ሽ፡፡
• ጎነ ሦስቶችን ትሠራለህ/ሪያለሽ፡፡
• ተጨባጭ እና ተመሳሳይ ሞዴሎችን በመጠቀም ሬክታንግላዊ ኘሪዝምን
ትገልፃለህ/ሽ፡፡
• ጎነ ሦስት እና ሬክታንግላዊ ኘሪዝም ጋር የተያያዘ ተጨባጭ ኘሮብሌሞችን
ታሰላለህ/ሽ፡፡

መግቢያ
ከዚህ ምዕራፍ ውስጥ በጥንድ ለሚገኙት ዘዌዎች ትርጓሜ ትሰጣለህ/ሽ፡፡
ትይዩ መስመሮች በአቋራጭ መስመር ከተቋረጡና ከሚፈጠሩት ዘዌዎች ጋር
የተያያዘ አብይ ቃላት ታጠናለህ/ሽ፡፡

121
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ማስመሪያ፣ ኘሮትራክተር እና ኮምፓስን በመጠቀም ጎነ ሦስቶችን፣ ጎነ


አራቶችን፤ እንደ ካሬ እና ሬክታንግል እንዲሁም ክብን ትገነዘባለህ/ሽ፡፡
በመጨረሻም ጥጥር ወለሎችን እንደ ኘሪዝም፣ ስሊንደር እና ፒራሚዶችን
በመማር ከተጨባጭ የዕለት ከእለት ኑሮአቹህ ጋር በማገናኘት ትማራለህ/ሽ፡፡

5.1 ዘዌዎች
መግቢያ
የዚህ ንዕስ ርዕስ ዋናው ዓላማ ተማሪዎች ዘዌዎች እና በጥንድ የተሰጡ
ዘዌዎች ያላቸውን ዝምድና እንድትማር/ሪ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ንዑስ ርዕስ ስለ
ዘዌዎች አምስተኛ ክፍል ምዕራፍ 8 ውስጥ ከተሰጠው የቀጠለ ነው፡፡ በዚህ
ንዑስ ርዕስ ሥር የመጀመሪያው ክፍል በተቋራጭ መስመሮች የሚፈጠሩትን
ጥንድ ዘዌዎች መማር ላይ ያተኩራል፡፡ የሚፈጠሩት ዘዌዎቹም ጉርብታም
ዘዌዎች፣ ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች፣ ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች እና ዝርግ አሟይ
ዘዌዎችን በቅደም ተከተል ትማራለህ/ሽ፡፡ በሁለተኛ ክፍል ደግሞ ትይዩ
መስመሮች በአንድ መስመር ሲቋረጡበየሚፈጠሩት ዘዌዎች ላይ የተኩራል፡፡

ትግበራ 5.1
1. አንድ መነሻ ነጥብ ያላቸውን ሁለት ጨረሮችን አገጣጥምህ/ሽ መስርት/ቺ፡፡
ከሁለቱ ጨረሮች አንዱን መነሻ ነጥቡ ሳይንቀሳቀስ የሚዞር እና ለሌለኛው
ጨረር ደግሞ በቦታው ይቆይ፡፡
ሀ. የሚዞረው ጨረር ቦታውን ከቀየርን የክፍተቱ ሥፍር ይጨምራልን?
ለ. የሚዞረው ጨረር በቦታው ለቀረው ጨረር ቀጤነክ ከሆነ የክፍተቱ
ስፍር ምን ያህል ይሆናል?
ሐ. የሚዞረው ጨረር እና በቦታው የቀረው ጨረር በተቃራኒ አቅጣጫ
ከሆኑ የክፍተቱ ስፍር ምን ያህል ይሆናል?
መ. የሚዞረው ጨረር አንድ ሙሉ ዙር ከዞረ የክፍተቱ ስፍር ምን ያህል

122
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ይሆናል?
2. በሁለት ጨረሮች እና በጋራ ነጥብ የሚፈጠረው ምስል የሚሰጠው
ስም ይኖራል?
3. በአከባቢህ/ሸ ከሚገኙ ነገሮች በጥያቄ 1 ላይ በተገለጹት ሁለት ጨረሮች እና
በጋራ ነጥብ ለሚፈጠረው ምስል ምሳሌ ስጥ/ጪ፡፡.
4. ከዚህ በታች ባለው ምስል 5.1 ላይ የተሰጡትን ምስሎች በፕሮትራክተር
በመስፈር፣ ሹል ዘዌ ፤ማዕዘናዊ ዘዌ፤ዝርጥ ዘዌ፤ዝርግ ዘዌ እና ጥምዝ ዘዌ
በማለት ለይ/ዪ፡፡

ምስል 5.1
5. ከዚህ በታች የተሰጡትን ዘዌዎች፡ ሹል ዘዌ፤ማዕዘናዊ ዘዌ፤ዝርጥ ዘዌ፤ዝርግ
ዘዌ፤ጥምዝ ዘዌ እና ክብ ዘዌ በማለት ለይ/ዪ፡፡
ሀ.120° ለ. 54° ሐ. 245° መ. 90°
ሠ. 300° ረ. 180° ሰ. 170° ሸ. 89°
6. በስተቀኝ ያለውን ምስል 5.2 በማየት ከሀ — ረ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሸ፡፡
ሀ. የ(∠ሐሠሀ) እና (∠ሐሠመ) የጋራ ጎን የቱ ነው?

123
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የ(∠ሐሠሀ) እና (∠ሐሠመ) የጋራ ነቁጥ አላቸው?


ለይ/ዪ፡፡
ለ. ∠ሐሠመ እና ∠መሠለ ስፍር ድምር ስንት ነው?

ሐ. ∠ሐሠሀ እና ∠መሠለ የጋራ ጎን አላቸው?

የጋራ ነቁጥ አላቸው?ለይ/ዪ::


መ. ∠ሐሠሀ እና ∠መሠለ እኩል ስፍር አላቸው?
ሠ. ∠ሐሠሀ እና ∠መሠለ ጥንድ ዘዌዎች የተለየ ይኖርሃል/ሻል?

ረ. በዚህ ምስል ነቁጥ ሠ ላይ ካሉት ጥንድ ዘዌዎች መካከል ከ <ሐሠሀ


እና <መሠለ የተለዩ ሆነው በስፍራቸው እኩል የሆኑ አሉ?

እስቲ 5ኛ ክፍል ስለ ዘዌዎች የተማራችሁትን በክለሳ መልክ እንመልከት፡፡


ዘዌ ሁለት አንድ መነሻ ነጥብ ባላቸው ጨረሮች የሚፈጠር ምስል ነው:: ዘዌ
የሚፈጥሩ ጨረሮች የዘዌ ጐኖች የሚባሉ ሲ ሆን የመነሻ ነጥብ ደግሞ የዘዌ
ነቁጥ ይባላል:: በምስል 5.4 ላይ ∠መአሐ ዘዌ ነው::

ምሳሌ 1

በምስል 5.4 የሚያሳየው አንድ መነሻ ነጥብ አ ባላቸው ጨረሮች፣ ጫረር አሐ


አሐ እና
እና ጨረር አመ የተፈጠረን ዘዌ ነው፡፡ ስለዚህ ̅̅̅̅ አመ
̅̅̅̅̅ የዘዌ ጐኖች

124
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

እና አ ደግሞ የዘዌ ነቁጥ ነው፡፡ የዘዌ ምልክቶች ∠ ወይም ^


ትጠቀማለህ/ሚያለሽ፡፡ ከዚህ በታች ያሉትን ተመልከት/ቺ:: ዘዌን በአንድ ነቁጥ
ወይም በሦስት ፊደሎች መሰየም ይቻላል፡፡

ምሳሌ 2
በምስል 5.5 ላይ የሚገኘውን ዘዌ
ሰይም/ሚ፡፡

መፍትሔ
በነቁጥ ፈ ላይ አንድ ዘዌ ብቻ ስለሚገኝ ዘዌውን ዘዌ ፈ ወይም ∠ፈ በማለት
መሰየም ይቻላል፡፡ በሌላ መንገድ ዘዌ አፈገ ወይም ዘዌ ገፈአ ብለን መሰየም
እንችላለን፡፡
በ5ኛ ክፍል ምዕራፍ 8 በተማርከው/ሺው መሰረት ዘዌዎችን ስፍራቸው ላይ
በመመርኮዝ ሹል ዘዌ፣ መዕዛናዊ ዘዌ፣ ዝርጥ ዘዌ፣ ዝርግ ዘዌ እና ጥሞዝ
ዘዌ በማለት መማርህን/ሽን አስታውስ/ሺ፡፡

i. ጉርብታም ዘዌዎች
ትርጓሜ 5.1
ሁለት ዘዌዎች የጋራ ጐንና ነቁጥ ኖራቸው የጋራ ውስጣዊ ነጥብ ከሌላቸው
ጉርብታም ዘዌዎች ይባላሉ፡፡

125
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 3
በምስል 5.6 ላይ ∠ሀመለ እና
መለ አላቸው፡፡
∠ለመሐ የጋራ ጐን ̅̅̅̅̅
መ ደግም የጋራ ነቁጥ ነው፡፡ ስለዚህ
∠ሀመለ እና ∠ለመሐ ጉርብታም
ዘዌዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ∠ሀመለ
እና ∠ሀመሐ ጉርብታም ዘዌዎች
አይደሉም፡፡ በተመሳሳይ
∠ሀመሐ እና ∠ለመሐ ጉርብታም ዘዌዎች አይደሉም፡፡ ለምን?

ii. ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች

ትርጓሜ 5.2
ሁለት ዘዌዎች የጋራ ነቁጥ ያላቸው እና ሁለተኛው ዘዌ ጐኑን በማርዘም
ጀርባ ጀርባ የሚፈጠር ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች ይባላሉ፡፡
በሁለት ተቋራጭ ቀጥታ መስመሮች ከሚፈጠሩት ዘዌዎች መካከል
ጥንድ ጉርብታም ያልሆኑ ዘዌዎች ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች ይባላሉ፡፡

ምሳሌ 4
በምስል 5.7 ስር ∠ሀለሐ እና
∠መለሠ ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች
ይባላሉ፡፡ ሌሎች ጥንድ ጀርባ ለጀርባ
ዘዌዎች ስም መጥራት
ትችላለህ/ያለሽ?

126
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

iii.ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች


ትርጓሜ 5.3
የሁለት ዘዌዎች ሥፍር ድምር 90° ከሆነ፣ እነዚህ ዘዌዎች ማዕዘናዊ አሟ ይ
ዘዌዎች ይባላሉ፡፡

ምስል 5
በምስል 5.8 ላይ በመመርኮዝ ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡

ምስል 5.8
ሀ. ∠ሀ እና ∠ሐ ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም
ሥ (∠ሀ) + ስ(∠ሐ) = 30° + 60° = 90° ስለሆነ ነው፡፡
ስለዚህ 30° ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ 60° ነው፡፡ የ15° ማዕዘናዊ አሟይ
ዘዌ ስንት ነው?

ለ. ∠መሠሰ እና ∠ሰሠረ ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም


ሥ(∠መሠሰ) + ሥ (∠ሰሠረ) = 65° + 25° = 90°

ትርጓሜ 5.4
α እና β’ ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች ከሆኑ α የ β ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ ነው፡፡
β ደግሞ የ α ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ ይባላል፡፡

127
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 6
የ 27° ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
እስት ጠን 27° ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ ነው እንበል፡፡
ስለዚህ ጠ + 27° = 90°
ጠ + 27° − 27° = 90° – 27 = 63°
ስለዚህ 63° የ 27° ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ ነው፡፡

iv.ዝርግ አማይ ዘዌዎች


ትርጓሜ 5.5
የሁለት ዘዌዎች ሥፍር ድምር 180° ከሆነ እነዚህ ዘዌዎች ዝርግ አሟይ
ዘዌዎች ይባላሉ፡፡

ለምሳሌ፡- 10° እና 170° ዝርግ አሟይ ዘዌዎች ይባላሉ፡፡ ምክንያቱም


100 + 1700 = 1800 ስለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን 130° እና 40° ዝርግ አሟይ
ዘዌዎች አይደሉም፡፡ ምክንያቱም 1300 + 400 ≠ 1800 ስለሆነ ነው፡፡

ትርጓሜ 5.6
ሁለት ዘዌዎች γ እና θ ዝርግ አሟይ ዘዌዎች ከሆኑ፣ θ የ γ ዝርግ አሟይ
ዘዌ እንድሁም γ የ θ ዝርግ አሟይ ዘዌዎች ይባላል፡፡

ምሳሌ 7
የ 63° ዝርግ አሟይ ዘዌ ፈልግ/ጊ፡፡

128
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መፍትሔ
እስቲ መ የ 63°, ዝርግ አሟይ ዘዌ እንበል::
መ + 63° = 180°
መ + 63° − 63° = 180° – 63° = 117°
ስለዚህ 117° የ 63° ዝርግ አሟይ ዘዌ ነው፡፡

ቲረም 5.1 ሁለት ቀጥተ መስመሮች


ቢቋረጡ ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች
ግጥምጥም ናቸው፡፡
የተሰጠው:- θ እና β ጀርባ ለጀርባ
ዘዌዎች ናቸው፡፡
የሚረጋግጥ፡- θ = β መሆኑን ነው፡፡

ማረጋገጫ
ዓረፍተ ነገር ምክንያት
1. θ + α = 1800 የዝርግ ዘዌ ስፍር
2. β + α = 1800 የዝርግ ዘዌ ስፍር

3. .θ + α = .β + α በመተካት

4. θ + α − α = β + α − α በሁለቱም አቅጣጫ  ን መቀነስ


5. θ = β እርምጃ 4

መልመጃ 5.1
1. ከዚህ በታች ያሉት ዓረፍተ ነገሮች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል
ካልሆኑ ሐሰት በማለት መልስ/ሺ፡፡
ሀ. የሹል ዘዌ ማዕዘናዊ አሟይ ሹል ዘዌ ነው፡፡
ለ. ጉርብታም ዘዌዎች ሁልጊዜ ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች ናቸው፡፡

129
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሐ. የሹል ዘዌ ዝርግ አሟይ ዝርጥ ዘዌ ነው፡፡


መ. የማዕዘናዊ ዘዌ ዝርግ አሟይ ዘዌ ማዕዘናዊ ዘዌ ነው፡፡
ሠ. የዝርጥ ዘዌ ዝርግ አሟይ ዘዌ ዝርጥ ዘዌ ነው፡፡
ረ. ሥፍሩ 270° የሆነ ዘዌ ማዕዘናዊ አማይ ዘዌ 70° ነው፡፡
2. ከዚህ በታች ከተሰጠው ምስል ላይ አራት ጥንድ ጉርብታም ዘዌዎችን
ዘርዝር/ሪ፡፡

3. ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተሰጠውን በባዶ ቦታ በትክክለኛ


መልስ ሙላ/ዪ፡፡
የዘዌ ስፍር ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ ዝርግ አሟይ ዘዌ
45°
74°
170°
10°
5. ከዚህ በታች በተሰጠው ምስል ላይ የጠ ን ዋጋ ፈልግ/ጊ::

5. ቀጥሎ በተሰጠው ምስል ∠መፐነ ዝርግ ዘዌ ነው፡፡ ሥ(∠መፐረ) = 1080

ከሆነ ሥ(∠ረፐነ) ፈልግ/ጊ::

130
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

6. በምስል 5.13 ውስጥ


θ = 120° ከሆነ β, γ, δ ን ፈልግ/ጊ፡፡

7. α እና β የዝርግ አሟይ ዘዌዎች ሥፍር ከሆኑ፣ የሚከተሉትን በባዶ


ቦታዎች በትክክለኛው መልስ ሙላ/ዪ፡፡
ሀ. α = 80° β = _______
ለ. α = ______ β = 40°

ሐ. α = β − 20° α = ______ β = ________


1
መ. α= 2
β α = ______ β = ________

8. γ እና θ ሥፍሩ 520 ለሆነ ዘዌ በቅደም ተከተል ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ እና


ዝርግ አሟይ ዘዌ ናቸው፡፡ γ እና θ ፈልግ/ጊ፡፡

ዘዌዎች እና ትይዩ መስመሮች


በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር በሁለት ትይዩ መስመሮች እና በአንድ አቋራጭ
መስመር ስለሚፈጠሩት ዘዌዎች ትማራለህ/ሽ፡፡
ትግበራ 5.2
1. በክፍልህ/ሽ ውስጥ ያሉትን ነገሮች በመመልከት ለትይዩ እና ተቀቋራጭ
መስመሮች ምሳሌ ሚሆኑትን አሳይ/ዪ፡፡
2. አብረህ/ሽ ከምትቀመጠው/ጪው ጓደኞችህ/ሽ ጋር በመወያየት በራሳችሁ
ስለትይዩ መስመሮች እና ተቋራጭ መስመሮችን በመግለጽ ፃፍ/ፊ፡፡

131
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3. ሁለት ትይዩ የሆኑ መስመሮችን በደብተርህ/ሽ ላይ በማስመሰል ሳል/ይ፡፡


4. የሳልከውን/ሺውን ትይዩ መስመሮች የማያቋርጥ ሌላ መስመር ሳል/ይ፡፡

ትርጓሜ 5.7
• አንድ ጠለል ላይ የሚገኙ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ መስመሮች
ትይዩ ናቸው የምንለው ምንም ያህል እየረዘሙ ቢሄዱ የማይቋረጡ ከሆኑ
ብቻ ነው፡፡
• አቋራጭ መስመር ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ መስመሮችን
በተለያዩ ነጥቦች ላይ የሚያቋርጥ መስመር ነው፡፡
ሁለት ቀጥታ መስመሮች ነ እና መ ትይዩ ከሆኑ በ ነ ∥ መ ምልክት
እንገልፃለን፡፡ ትይዩ ካልሆኑ በ ነ ∦ መ ምልክት ማሳየት ይቻላል፡፡

ለምሳሌ ትይዩ የሆኑ መስመሮች

ለምሳሌ ትይዩ ያልሆኑ መስመሮችን

ለምሳሌ ሁለት ትይዩ መስመሮች በአቋራጭ መስመር ከተቋረጡ ስንት


ዘዌዎች ይፈጠራሉ?

132
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 5.16 ላይ ቀጥታ መስመር ተ ቀጥታ መስመሮች ፐ እና ቀ ን


ያቋርጣል፡፡ ስለዚህ ተ አቋራጭ መስመር ይባላል፡፡
ዘዌዎች በሁለት ተቋራጭ ቀጥታ መስመሮች መሃከል የሚፈጠሩ ቀጥሎ
ባለው ምስል ላይ በ 1፣2. 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ እና 8 ቁጥሮች የተሰየሙት
የተለያየ ሰም አላቸው፡፡

ትርጓሜ 5.8
1. ሁለት ዘዌዎች ፍርቅ ውስጣዊ ዘዌዎች የምንላቸው ሁለት ቀጥታ
መስመሮችን በሚያቋርጥ መስመር በውስጥ በኩል ግራና ቀኝ
ሆነው የተለያየ ነቁጥ ላይ የሚኙ ከሆኑ ነው፡፡
2. ሁለት ዘዌዎች ተጓዳኝ ዘዌዎች ናቸው የምንላቸው ሁለት መስመሮች
በአቋራጭ መስመር ተቋርጠው በአንድ አቅጣጫ ተቋርጠው የተለያየ ነቁጥ
ኖሮአቸው አንዱ ዘዋ በሁለት ተቋራጭ መስመሮች በሚገኝ ሆኖ ሁለተኛው
ደግሞ ከሁለቱ መስመሮች ውጪ የሚኝ ከሆነ ነው፡፡
3. ሁለት ዘዌዎች ጥንድ ፍርቀ ውጪያዊ ዘዌዎች የምንላቸው ሁለት ቀጥታ
መስመሮች አቋራጭ መስመር አቋርጧቸው በውጪ በኩል ግራና ቀኝ
በቀጥታ መስመር ከቋርጧቸው እና የተለያዩ ነቁጥ ላይ የሚገኙ ከሆነ ነው፡፡

133
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በምስል 5.17 ላይ ሰ አቋራጭ መስመር ትይዩ መስመሮች መ እና ነ ን ሁለት


ነጥቦች ላይ ያቋርጣል፡፡
i. ጥንድ ዘዌዎች 3 እና 6 እንድሁም 4 እና 5 ጥንድ ፍርቅ ውስጣዊ
ዘዌዎች ይባላሉ፡፡
ii. ጥንድ ዘዌዎች 1 እና 8 እንድሁም 2 እና 7 ጥንድ ፍርቅ ውጫያዊ
ዘዌዎች ይባላሉ፡፡
iii. ጥንድ ዘዌዎች 1 እና 5፣ 3 እና 7 ፣ 2 እና 6 እንዲሁም 4 እና 8
ተጓዳኝ ዘዌዎች ይባላሉ፡፡
በምስል 5.18 ላይ ትይዩ መስመሮች መ1 እና መ2 በአቋራጭ መስመር
ቢቋረጡ የሚከተሉት እውነት ናቸው፡፡
i. የሚፈጠሩት ተጓዳኝ ዘዌዎች እኩል ስፍር አላቸው፡፡
ii. የሚፈጠሩት ጥንድ ፍርቅ ውስጣዊ ዘዌዎች እኩል ስፍር አላቸው፡፡
iii. የሚፈጠሩት ጥንድ ፍርቅ ውጫያዊ ዘዌዎች እኩል ስፍር አላቸው፡፡
iv. በአንድ ጐን የሚኙ ጥንድ ፍርቅ ውስጣዊ ዘዌዎች ድምር 1800
ይሆናል፡፡

በምስል 5.18 ላይ
𝜃 + 𝛽 = 1800 ይሆናል፡፡

መልመጃ 5.2
1. በምስል 5.19 ላይ ነ||መ፣ ፐ እና ቀ አቋራጭ መስመሮች ከሆኑ፣
𝛼, 𝛽, 𝛾 እና 𝜃 ሥፍር ፈልግ/ጊ፡፡

134
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2. ከዚህ በታች በተሰጠው ምስል ውሰጥ ቀጥታ መስመር ሀለ እና ሐመ


ቀጥታ መስመር ትይዩ ናቸው፡፡ ሥ(∠ለረሰ) =100° ከሆነ፣ ነቁጣቸው ረ
እና ሰ ላይ የሆኑትን ዘዌዎች ሥፍር ፈልግ/ጊ፡፡

3. በምስል 5.21 ላይ ሀለ ∥ ሐመ ነው
እንድሁም እንዲሁም ሀመ
̅̅̅̅̅̅ ∥ ሐለ
̅̅̅̅ ነው፡፡

ሰ(∠ሀለሐ) = 85° ከሆነ የቀሩትን


ጐነ አረት ዘዌዎች ስፍር ፈልግ/ጊ፡፡
4. በምስል 5.22 ላይ የ1፣2፣3 ዘዌዎችን ስፍር ፈልግ/ጊ፡፡

5. ከዚህ በታች ባለው ምስል ላይ መ እና ነ ትይዩ መስመሮች ከሆኑ የ ጠን


ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡

135
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

5.2 ጐነሦስቶች
መግቢያ
በ4ኛ ክፍል ምዕራፍ 6 የሂሳብ ትምህርት ውስጥ ሥራ ጐነ ሦስት በሦሶት
ዝግ ውስን ቀጥታ በመስመሮች ጠለል ላይ የሚፈጠር መሆኑን
ተምረሃል/ሻል፡፡ የጐነ ሦስት ትርጓሜ እና
ዓይነቶችንም ተምረሃል/ሻል፡፡ በዚህ ንዑስ
ርዕስ ስር ጐነ ሶስቶችን እንዴት
እንደምንመሰርት ትማራለህ/ያለሽ፡፡ በዚህ
ውስጥ የጐነ ሦስት ጎን ሰፍር ወይም
የአንዳንድ ዘዌዎች ሥፍር ከተሰጠህ/ሽ ኮምፓስ እና ማስመሪያ በመጠቀም ገነ
ሦስትን ትነድፋለህ/ሽ፡፡

ጐነ ሦስት መመስረት
የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች
ሀ. ማስማሪያ፣ ኘሮትራክተር እና ኮምፓስ
ለ. ካሬ ወረቀት
ሐ. ኢንተርኔት(ሶፍት ወር)፣ጂኦጀብራ

136
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ንድፍ 1
ጐነ ሦስት ሀለሐ የጐኖቹ ርዝመት፤ ሀለ = 4ሳ.ሜ፣ ለሐ = 6ሳ.ሜ እና
ሀሐ = 5ሳ.ሜ
ሀ. ማሰመርያ፣ ኘሮትራክተር እና ኮምፓስን በጠቀም መመስረት፡፡
1. ውስን ቀጥታ መስመር ለሐ = 6ሳ.ሜ መስርት/ቺ::

2. ነጥብ “ለ”ን እንደ እንብርት በመውሰድ ጥምዝ 5ሳ.ሜ ከነጥብ ለ የሚርቅ


ወደ ውስጥ መስመር ለሐ በኩል መስርት/ቺ፡፡

3. ነጥብ ሐን እንደ እንብርት በመውሰድ ከነጥብ ሐ 5ሳ.ሜ የሚርቅ ጥምዝ


በሁለተኛው ንድፍ ጋር የሚቋረጥ ንድፍ ሥራና ነጥቡን ሀ ብለህ
ሰይም/ሚ፡፡
4. ውስን ቀጥታ መስመር ሀለ እና ውስን ቀጥታ መስመር ለሐ ን
ማገናኘት፡፡

5. ∆ሀለሐ የሚፈለገው ጐነ ሦስት ነው፡፡

137
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትግበራ 5.3
1. ማስመሪያን እና ኮምፓስን በመጠቀም የጐኖቹ ርዝመት
ከዚህ በታች የተሰጠውን ጐነ ሦስት መስርት/ቺ፡፡
ሀ. 2፣ 3፣ 4 ለ. 6፣ 7፣ 12 ሐ. 5፣ 7፣ 8
መ. 4፣ 6፣ 7 ሠ. 3፣ 5፣ 7 ረ. 7፣ 8፣ 9
2. ከዚህ በታች የተሰጡት ዩኒቶች የአንድ ጎነ ሦስት የጐኖቹ ርዝመት መሆን
ይችላሉን? ለምን?
ሀ. 1፣ 2፣ 3 ለ. 6፣ 8፣ 12 ሐ. 2፣ 3፣ 5 መ. 3፣ 4፣ 6
3. ሀ፣ ለ እና ሐ የጐነ ሦስት የጎኖቹ ርዝመት ከሆኑ፤
ሀ. ሀ + ለ ከሐ ጋር አወዳድር/ሪ፡፡ ለ .ሀ + ሐ፣ ከለ ጋር አወዳድር/ሪ፡፡
ሐ. ለ+ሐ፣ ከሀ ጋር አወዳድር/ሪ፡፡
4. ሀ፣ለ እና ሐ የጐነ ሦስት የጐኖቹ ርዝመት ለመሆን ምን ዓይነት
መስፍርት ማሟላት አለባቸው?
ከዚህ በላይ ያለው ትግበራ 5.3 ከዚህ በታች ባለው በጣም አስፈላጊ በሆነው
የጂኦሜትሪ ሀሳቦች ይቋጫል፡፡
የጎነ ሦስት ጐኖችና ዘዌዎች ግንኙነት፤
1. የጎነ ሦስት ጐኖች ርዝመት ያላቸው ዝምድና ለማንኛውም ጐነ ሦስት
ውስጥ የሁለት ጐኖች የጐኖቹ ርዝመት ድምር ከሦስተኛው የጐን ርዝመት
ይበልጣል፡፡ ይህ ማለት በ፣ተ፣ቸ
የጐነ ሦስት የጐኖች ርዝመት ከሆኑ፣
በ + ተ > ቸ ፣ ተ + ቸ > በ
እና በ + ቸ > ተ ይሆናሉ፡፡

138
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 8
በምስል 5.27 ላይ ∆ሀለሐ ን
አስመልክቶ
ከዚህ በታች ያሉት እውነት ናቸው፡፡
i. ሀለ + ለሐ > ሀሐ
ii. ሀለ + ሀሐ > ለሐ
iii. ለሐ + ሀሐ > ሀለ

2. የአንድ ጐነ ሦስት የጐን ርዝመት ከሁለተኛው ጐን ርዝመት የሚበለጥ


ከሆነ የዘዌው ስፍር ከረዥሙ ጐን ፊትለፊት የሚገኘው ይበልጣል፡፡

ምሳሌ 9

በምስል 5.28 ላይ ሀሐ > ሀለ ነው፡፡


ስለዚህ ሥ(∠ሀለሐ) > ሥ(∠ሀሐለ)
ይሆናል፡፡

3. የአንድ የጐነ ሦስት የዘዌው መጠን ከሁለተኛው የዘዌው መጠን


የሚበልጥ ከሆነ፣ ከሰፊው ዘዌ ፊት ለፊት ያለው የጎን ርዝመት ከጠባቡ
ዘዌ ፊት ለፊት ካለው የ ጎን ርዝመት ይበልጣል፡፡ ምስል 5፡28
በምስል 5.29 ላይ
ሥ (∠መፐነ) > ሥ (∠መነፐ)
ነው፡፡ ስለዚህ መነ > መፐ ፡፡

መልመጃ 5.3
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን የጐነ ሦስት የጐኖች ርዝመት ማስመሪያና
ኮምፓስን በመጠቀም መስርት/ቺ፡፡
ሀ. 4ሳ.ሜ፣ 5ሳ.ሜ እና 8ሳ.ሜ ለ. 4ሳ.ሜ፣ 6ሳ.ሜ እና 8ሳ.ሜ
ሐ. 4ሳ.ሜ፣ 3ሳ.ሜ እና 6ሳ.ሜ መ.11ሳ.ሜ፣ 12ሳ.ሜ፣ እና 13ሳ.ሜ

139
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2. ከዚህ በታች ከተሰጡት ውሰጥ የጐነ ሦስት ጐን ርዝመት ሊሆን


የማይችለው የትኛው ነው?
ሀ. 3ሳ.ሜ፣ 4ሳ.ሜ፣ 7ሳሜ ለ. 2ሳ.ሜ፣2.5ሳ.ሜ፣ 3ሳ.ሜ
ሐ. 8ሳ.ሜ፣ 8ሳ.ሜ፣ 8ሳ.ሜ መ.15ሳሜ፣12ሳ.ሜ፣ 18ሳ.ሜ
ሠ. 5ሳ.ሜ፣ 10ሳሜ፣ 5ሳ.ሜ ረ. 10ሳ.ሜ፣ 20ሳ.ሜ፣ 30ሳ.ሜ
3. ከምስል 5.30 የ ጎነ ሦስት
ሀለሐ ትልቁን
ዘዌና ትንሹን ዘዌ ፃፍ/ፊ፡፡

4. ምስል 5.31 ላይ መሠረት


ትልቁንና
ትንሹን የጐን ርዝመት ፃፍ/ፊ፡፡
5. ጐነ ሦስት መነሀ (∆∠መነሀ) ውስጥ ሥ(∠መ) = 85° እና ሥ(∠ነ) = 50°
ከሆኑ፣ ረጅም እና አጭር የሆኑትን ጐኖች ፃፍ/ፊ፡፡

ንድፍ 2
ለ. 2 ጐኖቹ እና በሁለቱም ጐኖች መሃል የሚኘው ዘዌ ሥፍር የተሰጠን ጎነ
ሦስት መንዳፍ
የተሰጠ:- ሁለት ጐኖች ሀ እና ለ እንዲሁም መሃል ላይ የሚኘው ዘዌ ∠ሐ
የምትመሰርተው/ቺው: ሁለት ጐኖቹና በጐኖቹ መካከል የሚገኘው
ዘዌው የተሰጠን ጐነ ሦስት
1. ቀጥታ መስመር ለ ን በመመስረት፤ በምስሉ ላይ ነጥብ ደ ን መምረጥ፡፡

2. ደ ን እንደ እምብርት ነጥብ በመውሰድ ርዝመቱ በ የሆነ ውስን ቀጥታ


መስመር መመስረት እና የውስን ቀጥታ መስመሩን ጫፍ ነጥብ አ
በማለት መሰየም፡፡

140
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


3. ነጥብ ደ ላይ ሥፍሩ ከ(∠መ) ሥፍር ጋር እኩል የሆነ ዘዌን
በመመስረት ውስን ቀጥታ መስመሩን መ በማለት ሰይም/ሚ፡፡

4. ሠ ን እንደመነሻ ነጥብ በመውሰድ በቀጥታ መስመር መ ላይ የውስን


ቀጥታ መስመር ርዝመት ከ ዩኒት የሆነ መመስረት፤ በመጨረሻም ይሀን
ውስን ቀጥታ መሰመር ጫፍ ፈ በማለት መሰየም::

5. ውስን መስመር ሠፈ መስርት/ቺ፡፡ Δመሠፈ የሚፈለገው ጐነ ሦስት


ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሁለት ዘዌዎችና በዘዌዎቹ መሃከል የሚገኝ ጐን የተሰጠን


ጐነ ሦስት መመስረት ይቻላል፡፡

141
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ንድፍ 3
የተሰጠ፤ ሁለት ዘዌዎች ረ እና ተ እና በሁለቱ ዘዌዎች መካከል የሚገኝ ጐን
ርዝመቱ ሀ ዩኒት የሆነ ጎነ ሦስት፡፡
የምትመሰርተው/ቺው፡- ሁለት ዘዌዎቹ እና በመሃከላቸው ያለው ጎን የተሰጠን
ጎነ ሦስት ፡፡
1. ቀጥታ መስመር ለ ን መመስረት እና ነጥብ ረ ን መምረጥ፡፡

2. ረ ን እንደ መነሻ ነጥብ በመወሰድ ርዝመቱ ሀ ዩኒት የሆነን ውስን ቀጥታ


መስመር መመስረት፡፡ በመጨረሻም ይሀን ውስን ቀጥታ መሰመር
በስተቀኝ ጫፍ ተ በማለት መሰየም::

3. ረ ን እንደመነሻ ነጥብ በመውሰድ በኮምፓስ ሥፍሩ ከ ∠ረ ስፍር ጋር


እኩል የሆነን ዘዌ መመስረት፡፡

4. ተ ላይ ስፍር ∠ተ የሆነን ዘዌ መስርት/ቺ፡፡

5. ጎነ ሦስት ረተሰ የተፈለገው ጐነ ሦስት ነው፡፡

142
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 5.4
1. ኮምፓስንና እርሳስን በመጠቀም ከዚህ በታች የተሰጡትን ጐነ ሦስቶችን
መስርት/ቺ፡፡
ሀ. ሀ = 5ሳ.ሜ, ለ = 6ሳሜ እና ሥ(∠𝐶) = 50°
ለ. ሀ = 3ሳ.ሜ፣ ለ = 4ሳ.ሜ እና ሥ(∠𝐶 ) = 30°
ሐ. ሀ = 7ሳ.ሜ፣ ለ = 7ሳ.ሜ እና ሥ(∠𝐶) = 80°
መ. ሀ= 10ሳ.ሜ፣ ለ = 11ሳ.ሜ እና ሥ(∠𝐶 ) = 100°
ሠ. ሀ = 3ሳ.ሜ፣ ለ = 4ሳ.ሜ እና ሥ (∠C) = 90°
2. ከዚህ በታች ሁለት ዘዌዎች መካከል የሚገኝ ጐን ተሰጥቷል፡፡ እነዚህን
ጐነ ሶስቶች መስርት/ቺ፡፡
ሀ. 60°፣ 70°፣ 4ሳ.ሜ ለ. 80°፣ 45°፣ 3ሳ.ሜ
ሐ. 55°፣ 75°፣ 5ሳ.ሜ መ. 110°፣ 50°፣ 6ሳ.ሜ
ሠ. 120°፣ 30°፣ 4ሳ.ሜ ረ. 90°፣ 45°፣ 3ሳሜ

5.3 ጐነአራቶች
መግቢያ
በዚህ ንዑስ ስር ካሬ እና ሬክታንግልን መመስረት እንዲሁም የካሬ እና
የሬክታንግልን ፀባዮችን ትማራለህ/ሽ፡፡

ሬክታንግልን መመስረት
የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች፡-

143
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሀ. ማስመሪያ፣ ኘሮትራክተር እና ኮምፓስ


ለ. ካሬ ወረቀት
ሐ. “ጂኦጀብራ” ከተገኘ፡፡
ለምሳሌ:- ሬክታንግል ሀለሐመ፤ ሀለ = 3ሳ.ሜ እና ለሐ = 5ሳ.ሜ
የሆኑትን ማስመሪያ፣ ኘሮትራክተር እና ኮምፓስን በመጠቀም
መስርት/ቺ፡፡
እርምጃዎች:
1. ለሐ = 5ሳ.ሜ መስርት/ቺ፡፡

.
2. ነጥብ ለ ላይ ስ(∠ጠለሐ) = 90° እንዲሆን በማድረግ ጨረር ለጠ ን
መስርት/ቺ፡፡

3. ነጥብ ለ ን እንደ እምብርት በመውሰድ ሬድየሱ ለሀ = 3ሳ.ሜ በማድረግ


ጨረር ለጠ ን ነጥብ ሀ ላይ የሚያቋርጥ ጥምዝ መስርት/ቺ፡፡

4. ነጥብ ሐ ን እንደ እምብርት በመውሰድ ሬድየሱ ሐመ = 3ሳ.ሜ በማድረግ


ጨረር ሐመ ን ነጥብ መ ላይ የሚያቋርጥ ጥምዝ መስርት/ቺ፡፡

144
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

5. ነጥብ ሀን እንደ እምብርት በመውሰድ ሬድየሱ ሀመ = 5ሳ.ሜ በማድረግ


በ4ኛ እርምጃ ላይ የተመሰረተውን ጥምዝ በነጥብ መ ላይ የሚያቋርጥ
መስመር መስርት/ቺ፡፡

ሀመ እና ሐመ አያይዝ/ዥ፡፡

6. ሀለሐመ የሚፈለገው ሬክታንግል ነው፡፡

በተጨማሪም ከዚህ በላይ ያሉትን እረምጃዎች በመጠቀም ካሬን መመስረት


ይቻላል፡፡

145
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የካሬ እና የሬክታንግል ጸባዮች


የካሬ ጸባዮች
ሀ. ጥንድ ፊትለፊት ያሉ ጐኖች ትይትና ግጥምጥም ናቸው፡፡
ለ. ትይዩ ዘዌዎች ግጥምጥም ናቸው፡፡
ሐ. ሰያፍ መስመሮች እኩል ሁለት ቦታ ይከፋፈላሉ፡፡
መ. ሁሉም ዘዌዎቹ ማዕዘናዊ ናቸው
ሠ. ሁሉም ጐኖቹ እኩል ርዝመት አላቸው፡፡

የሬክታንግል ጸባዮች
ሀ. ሁሉም ዘዌዎች ማዕዘናዊ ዘዌዎች ናቸው፡
ለ. ሰያፍ መስመሮቹ ግጥምጥም ናቸው፡
ሐ. ጥንድ ፊትለፊት ያሉ ጐኖቹ ትይዩና ግጥምጥም ናቸው፡፡

መልመጃ 5.5
1. ከዚህ በታች የተሰጡትን ዓረፍተ ነገሮች ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል
ካልሆኑ ሐሰት በማለት መልስ/ሺ፡፡
ሀ. ሁሉም ሬክታንግል ካሬ ነው፡፡
ለ. ካሬ ሬክታንግል ነው፡፡
ሐ. ሁሉም የካሬ ዘዌዎች ስፍር 90° ነው፡፡
መ. ሁሉም የሬክታንግል ዘዌዎች ስፍር 90° ነው፡፡
ሠ. ሁሉም የሬክታንግል ጐኖች እኩል ርዝመት አላቸው፡፡
ረ. ሁሉም የካሬ ጐኖች እኩል ርዝመት አላቸው፡፡
ሰ. ሁሉም የሬክታንግል ጐኖች ትይዩ ናቸው፡፡
2. ከዚህ በታች የጐን ርዝመቱ የተሰጠው ካሬ መስርት/ቺ፡፡
ሀ. 2ሳ.ሜ ለ. 3ሳ.ሜ ሐ. 40ሚ.ሜ
3. ከዚህ በታች ወርዱና ርዝመቱ የተሰጠውን ሬክታንግል መስርት/ቺ፡፡

146
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሀ. ርዝመቱ 2ሳ.ሜ እና ወርዱ 1ሳ.ሜ


ለ. ርዝመት 30ሚ.ሜ እና 20ሚ.ሜ

5.4 ክቦች
መግቢያ
በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር የክብን ትርጓሜ እና ከክብ ጋር የተያያዙ እንደነ
ሬድየስ፣ ድያሜትር እና አውታር ያሉትን ትማራለህ/ያለሽ፡፡ በተጨማሪም
የክብ ሬድየስ ከተሰጠ ክብ እንዴት እንደሚመሰረት ታስተውላለህ/ያለሽ፡፡

ትግበራ 5.4
1. ክብ ምንድን ነው?
2. የክብን ሬድየስ እንዴት ትገልፃለህ/ያለሽ?
3. ዲያሜትር ምንድን ነው? አውታርስ?
4. በሬድየስ እና በድያሜትር መካከል ያለውን
ግንኙነት ግለፅ/ጪ፡፡
5. በምስል 5.35 ላይ አ የክቡ እንብርት ከሆነ፣
i. የክቡን ሬድየስ ፃፍ/ፊ፡፡
ii. የክቡን ዲያሜትር ፃፍ/ፊ፡፡
iii. የክቡን አውታር ፃፍ/ፊ፡፡
6. በአከባቢያችሁ የሚገኙ የክብ ቅርፅ ያላቸውን ፃፍ/ፊ፡፡

ትርጓሜ 5.9
• በአንድ ጠለል ላይ የሚገኙና ከአንድ ከተሰጠ ነጥብ በእኩል ርቀት ላይ
የሚገኙ ነጥቦች ስብስብ ክብ ይባላል፡፡
• የተሰጠ ቋሚ ነጥብ የክቡ እምብርት ይባላል፡፡
• ከእምብርቱ እስከ ክቡ ድረስ ያለው ርቀት ሬድየስ ይባላል፡፡

147
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

• በክቡ ላይ የሚገኙትን ሁለትነ ጥቦች የሚያገኝ ውስን ቀጥታ መስመር


አውታር ይባላል፡፡
• በክቡ እምብርት ውስጥ የሚያልፍ አውታር ዲያሜትር ይባላል፡፡
ስለዚህ ዲያሜትር ከሁሉም የሚረዝም አውታር ነው፡፡
ኮምፓስን ተጠቅመህ/ሽ ክብን ስትስል/ይ፣ የኮምፓስህ/ሽ ጫፍ የሚያርፈው
በእምብርት ላይ ሲሆን፣ የኮምፓሱ እርሳስ ጫፍ የሚዞርበት ቅስት ደግሞ
ክብ ነው፡፡

ምሳሌ 11
ከላይ ባለው ምስል 5.36 ላይ መ የክቡ እምብርት፣ መረ
̅̅̅̅̅ ፣ ̅̅̅̅̅̅
መሐ እና መሠ
̅̅̅̅̅̅ የክቡ

ሬድየስ ሲሆኑ፣ ሀለ እና ̅̅̅̅ ሐረ


ሐረ የክቡ አውታሮች ናቸው፡፡ የክቡ አውታር ̅̅̅̅
በክቡ እምብርት ውስጥ ስለሚያልፍ ዲያሜትር ይባላል፡፡
ሐረ = መሐ + መረ
ዲ = ሬ + ሬ
ዲ = 2ሬ
ትግበራ 5.5
ዓላማ: የተሰጠህን/ሽን ሬዲየስ በመጠቀም ክብን መመስረት፡፡
የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች
ሀ. ማስመሪያ፣ ኘሮትራክተር እና ኮምፓስ
ለ. የካሬ ወረቀት
ሐ.“ጂኦጀብራ” ከተገኘ
ከዚህ በታች የተሰጠህ/ሽ የክብ ሬድየስ በመጠቀም ክብን መስርት/ቺ፡፡
ሀ. 2ሳ.ሜ ለ. 3ሳ.ሜ ሐ. 4ሳ.ሜ መ. 1ሳ.ሜ

148
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 12
ሬዲየሱ ረ = 5ሳ.ሜ የሆነን ክብ መስርት/ቺ፡፡

መልመጃ 5.6
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡
1. ሀ. የክብ ዲያሜትር 100ሚ.ሜ ከሆነ ሬድየሱ ስንት ይሆናል?
ለ. የክቡ ሬዲየስ 40ሳ.ሜ ከሆነ የዲያሜትሩ ርዝመት ስንት ይሆናል?
ሐ. የክቡ ሬድየስ 14ጠ ከሆነ የዲያሜትሩን ርዝመት ፈልግ/ጊ፡፡
መ. የክቡ ዲያሜትር 4ጠ + 2 ከሆነ የሬዲየሱን ርዝመት ፈልግ/ጊ፡፡

2. ከዚህ በታች ለተሰጡት ክቦች የተጠየቀውን ዳይሜንሽን ፈልግ/ጊ፡፡

3. ከዚህ በታች የተሰጡትን ሬድየሶች በመጠቀም ክብን መስርት/ቺ፡፡


ሀ. 2.5ሳ.ሜ ለ. 30ሚ.ሜ ሐ. 45ሚ.ሜ

149
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

5.5 ጥጥር ምስሎች


ትግበራ 5.6
1. የጥጥር ምስሎች ኘሪዝም እና ስሊንደር ከዚህ በታች ተሰጥተዋል፡፡
በቡድን በመሆን በአከባቢያችሁ ከሚገኙ ነገሮች ሁለት ሁለት ምሳሌዎችን
ስጥ/ጪ፡፡

2. በምስል 5.40 ላይ ያለውን ሬክታንጉለር ኘሪዝም በመጠቀም፤


የመሰረቶቹን፣ የገፀ ጐኖቹንና የጠርዞቹን ስም ለይ/ዪ፡፡

ትርጓሜ 5.10
ፕሪዝም ባለ 3 ዳይሜንሽን ጥጥር ምስል ሆኖ ሁለት ትይዩ እና ግጥምጥም
የሆኑ ጐነ ብዙ ገፆች ሲኖሩት፤ እነዚህ ገፆች መሰረቶች ይባላሉ፡፡ የጎን ገጾቹ
ሬክታንግሎች ናቸው፡፡

150
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የፕሪዝም መጠሪያው በመሰረቱ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡


ስለዚህ በኘሪዝሙ መሰረት ላይ በመመርኮዝ የተለያዩ የኘሪዝሞ አይነቶች፤
እንደ ሦስት ጐናዊ ኘሪዝም፣ ሬክታንግላዊ ኘሪዝም፣ ካሬ ኘሪዝም እና
የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ምሳሌ 13
ከዚህ በታች የተሰጠውን ኘሪዝም መሰረቱ ሦስት ጐን ስለሆነ ሦስት ጐናዊ
ኘሪዝም ይባላል፡፡

ከዚህ በታች የተሰጠውን ኘሪዝም መሰረቱ ሬክታንግል ስለሆነ ኘሪዝሙ


ሬክታንግላዊ ኘሪዝም ይባላል፡፡

አንድ ኘሪዝም መሰረቱ ክብ ከሆነ ፕሪዝሙ ስሊነደር ይባላል፡፡

151
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ትርጓሜ 5.11
ስሊንደር ማለት ሁለቱ መሰረቶቹ ክቦች የሆኑ ኘሪዝም ማለት ነው፡፡

ትግበራ 5.7
1. ፕራሚድ ምንድን ነው?
2. በቡድን በመሆን በአከባቢያችሁ ከሚገኙት ነገሮች ውስጥ ሁለት
የፕራሚድ ምሳሌዎችን ስጡ፡፡
3. በምስል 5.44 ላይ ነቁጥ፣ጠርዞች እና የፕራሚድን ገፆች በመለየት
ፃፍ/ፊ፡፡

ትርጓሜ 5.12
ኘራሚድ ጥጥር ምስል ሆኖ መሰረትና መሰረቱ ላይ የሌለ አፔዴክስ የሚባል
ነጥብ በመባል ይተረጐማል፡፡
ኘራሚድ ጥጥር ምስል ሆኖ ሁሉም ገፀ ጐኖቹ ጐነ ሦስቶች በአንድ ነጥብ
(አፔዲክስ) የሚገናኙ እና መሰረቱ ማንኛውም ጐነ ብዙ የሆኑ ነው፡፡
ጎነ ሶስቶቹ የሚነካኩበት ነጥብ የኘራሚዱ ነቁጥ ይባላል፡፡ይህ ነጥብ በመሰረቱ
ጠለል ላይ አይገኝም፡፡

152
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

አንድ ኘራሚድ ስሙን ከመሰረቱ ላይ ይወስዳል፡፡ ስለዚህ በመሰረቱ ቅርፅ ላይ


በመመርኮዝ ኘራሚዶች በተለያዩ አይነቶች ይከፋፈላል፡፡ እነሱም ሬክታንግላዊ
ኘራሚድ፣ ሦስት ጐናዊ ፕራሚድ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ትርጓሜ 5.13
መሰረቱ ክብ የሆነ ኘራሚድ ኮን ይባላል፡፡

153
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃ 5.7
1. በቀኝ በኩል የተሰጠው ሬክታንግላዊ ኘሪዝም ነው፡፡

ሀ. ነአለመ እና ሰፐቀረ የኘሪዝሙ


ምንድን ናቸው?
ለ. የኘሪዝሙን ጠርዞች ዘርዝር/ሪ፡፡
ሐ. የኘሪዝሙን ገነ-ገፆች ዘርዝር/ሪ፡፡
መ. የኘሪዝሙ ገፀ-ጐኖች ምስል ምንድን ናቸው?
2. በቀኝ በኩል የሚገኘው ምስል፡-
ሀ. ምን ይባላላ?
ለ. ስንት ገፀ ጐኖች አለው? ዘርዝር/ሪ፡፡
ሐ. የዚህ ምስል መሰረቶች ቅርፅ ምንድ ነው?
መ. የምስሉን ጠርዞች ዘርዝር/ሪ፡፡

3. አንድ ስሊንደር ስንት መሰረቶች አሉት? የስሊንደር መሰረቶች ቅርፅ


ምንድን ነው?
4. በቀኝ የሚገኘው ምስል፡-
ሀ. ይህ ጥጥር ምስል ምን ይባላል?
ለ. ስንት ገፀ ጐኖች አሉት?
ሐ. የመሰረቱ ሀለሐመ ቅርፅ ምንድን ነው?
መ. የገፅ ሀለአ ቅርፅ ምንድ ነው?
ሠ. የዚህን ጥጥር ምስል ነቁጥ ፃፍ/ፊ፡፡

154
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

5. ከዚህ በታች በተሰጡት ጥጥር ምስሎች ላይ በመመስረት ከሀ-መ ያሉትን


ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡

ሀ. የትኛው ምስል ስሊንደር ነው?


ለ. የትኛው ምስል ፒራሚድ ነው?
ሐ. የትኛው ምስል ፕሪዝም ይባላል?
መ. የትኛው ምስል ኮን ይባላል?
6. ምስሎቹን ከሚሰሩበት መረቦች ጋር አዛምድ/ጂ፡፡

i. ሀ ከ ____________ መረብ ተሰራ፡፡


ii. ለ ከ ____________ መረብ ተሰራ፡፡
iii. ሐ ከ ____________ መረብ ተሰራ፡፡

155
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

5.6. የ ጠለልና የጥጥር ምስሎች ጽንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ


ማዋል

ምሳሌ 14
የአንድ ጐነ ሦስት ቅርፅ ያለው መዝናኛ ቦታ የሁለቱ ጐኖች ርዝመት 30
ሜትር እና 20 ሜትር ነው፡፡ የመዝናኛ ቦታው ዙሪያ 76 ሜትር ከሆነ
የ3ኛውን ጐን ርዝመት አስላ/ዪ፡፡ መፍትሔ
እስቲ የ3ኛውን ጐን ርዝመት ጠ እንበለው፡፡
20ሜ + 30ሜ + ጠ = 76ሜ
50ሜ + ጠ = 76ሜ
= 26ሜ

ምሳሌ 15
ከዚህ በታች የተሰጠው ብርጭቆ ምን
ያህል ውሃ መያዝ ይችላል?

ምስል 5.52
መፍትሔ
የስሊንደር ይዘት V = πሬ2 ቁ
= π(2ሚ. ሜ)2 × 6ሚ. ሜ
= 12πሚሜ 3
ስለዚህ ይህ ብርጭቆ 12π ኪዩቢክ ሚ.ሜ ውሃ ይይዛል፡፡

መልመጃ 5.8
1. የወይዘሮ ሜቲ የእርሻ ማሳ ጐነ ሦስት ማዕዘናዊ ዘዌ ያለው እና የጐኖቹ
ርዝመት 30ሜ፣ 40ሜ እና 50ሜ ከሆኑ፡-
ሀ. የዚህን የእርሻ ማሳ ዙሪያ ፈልግ/ጊ፡፡

156
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለ. የዚህን የእርሻ ማሳ ስፋት ፈልግ/ጊ፡፡


2. ከዚህ በታች የተሰጠው ሬክታንግላዊ ኘሪዝም ወርድ 2ሳ.ሜ፣ ርዝመት
3ሳ.ሜ እና ቁመት 4ሳ.ሜ አለው፡፡ ይህን ሬክታንግላዊ ኘሪዝም ምን ያህል
ኪዩቢክ ዩኒቶች ይሞላዋል?

3. አንድ ሬክታንግላዊ ኘሪዝም ርዝመት፣ ወርድ እና ቁመት በቅደም ተከተል


6ሳ.ሜ 4ሳ.ሜ እና 8ሳ.ሜ ከሆነ የሬክታንግላዊ ኘሪዝሙን ይዘት ፈልግ/ጊ፡፡
4. የአንድ ሬክታንግላዊ ኘሪዝም ይዘት 240ሳ.ሜ3 ነው፡፡ ይህ ኘሪዝም
ርዝመቱ 8ሳ.ሜ እና ወርድ 5ሳ.ሜ ካለው የዚህን ሬክታንግላዊ ኘሪዝም
ቁመት ፈልግ/ጊ፡፡
5. አንድ የመኖሪያ ቤት ርዝመት 5ሜ እና ወርድ 4ሜ አለው፡፡ የዚህ ቤት
ቁመት 3ሜ ከሆነ በዚህ ቤት ውስጥ ያለውን አየር ይዘት አስላ/ዪ፡፡
6. አንድ መሰረቱ ካሬ የሆነ ቤት ወርድ 4ሜ አለው፡፡ የዚህ ቤት ይዘት
56ሜ3 ከሆነ የቤቱን ቁመት አስላ/ዪ፡፡
7. ከዚህ በታች ያለውን የምስል 5.55 ቅርፅ የሚመስል ብርጭቆ ምን
ያህል ወተት መያዝ ይችላል?

157
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፍ 5 ማጠቃለያ
1. ሁለት ዘዌዎች የጋራ ጐን ኖሯቸው የጋራ ውስጣዊ ነጥብ ካሌላቸው
ጉርብታም ዘዌዎች ይባላሉ፡፡
2. ሁለት ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች እኩል ስፍር አሏቸው፡፡ ይህ ማለት ሁለት
ጀርባ ለጀርባ ዘዌዎች ግጥምጥም ዘዌዎች ናቸው፡፡
3. ሁለት ዘዌዎች ሰፍር ድምር 900 ከሆነ ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች ይባላሉ፡፡
ሁለት ዘዌዎች ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች ከሆኑ እነዚህ ዘዌዎች የጋራ
ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌዎች ይባላሉ፡፡
4. ሁለት ዘዌዎች α እና β ዝርግ አሟይ ዘዌዎች የሚባሉት የስፍራቸው
ድምር 1800 ከሆነ ነው፡፡ α የ β ዝርግ አሟይ ዘዌ ይባላል፡፡
5. አንድ መስመር ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ መስመሮችን
የሚያቋርጥ ከሆነ አቋራጭ መስመር ይባላል፡፡
6. በአንድ ጠለል ላይ የሚገኙ መስመሮች ትይዩ መስመሮች የሚባሉት
እነዚህ መስመሮች የማይቋረጡ ከሆነ ነው፡፡
7. ሁለት ትይዩ መስመሮች በአቋራጭ መስመር ቢቋረጡ፡-
ሀ. ተጓዳኝ ዘዌዎች ግጥምጥም ናቸው፡፡
ለ. ፍርቅ ውስጣዊ ዘዌዎች ግጥምጥም ናቸው
ሐ. ፍርቅ ውጪያዊ ዘዌዎች ግጥምጥም ናቸው፡፡
መ. በአቋራጩ መስመር በአንድ ጐን የሚገኙ ጥንድ ፍርቅ ውስጣዊ
ዜዌዎች ዝርግ አሟይ ናቸው፡፡
8. በማንኛውም ጐነ ሦስት ውስጥ የሁለቱ ጐኖች ርዝመት ድምር
ከሶስተኛው ጐን ርዝመት ይበልጣል፡፡
9. የአንድ ጐነ ሦስት ጐን ርዝመት ከሁለተኛው ጐን ርዝመት የበለጠ
የሚረዝም ከሆነ በረጅም ጐን ትይዩ የሚገኝ ዘዌ ከአጭር ጐን ትይዩ
ካለው ዘዌ በሰፍር ይበልጣል፡፡
10. የአንድ ጐነ ሦስት የአንዱ ዘዌ ሰፍር ከሁለተኛው ዘዌ ስፍር ከበለጠ

158
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የትልቅ ዘዌ ትይዩ የሆነ ጐን ከትንሽ ዘዌ ትይዩ ከሆነው ጐን የበለጠ


ይራዝማል፡፡
11. የካሬ ጸባዮች
ሀ. ጥንድ ፊት ለፊት ያሉ ጐኖች ትይዩና ግጥምጥም ናቸው፡፡
ለ. ትይዩ ዘዌዎች ግጥምጥም ናቸው፡፡
ሐ. ሰያፍ መስመሮች እኩል ሁለት ቦታ ይከፋፈላሉ፡፡
መ. ሁሉም ዘዌዎች ማዕዘናዊ ዘዌዎች ናቸው፡፡
ሠ. ሁሉም ጐኖች እኩል ናቸው፡፡
12. የሬክታንግል ጸባዮች
ሀ. ሁሉም ዘዌዎች ማዕዘናዊ ዘዌዎች ናቸው፡፡
ለ. ሰያፍ መስመሮች ግጥምጥም ናቸው፡፡
ሐ. ጥንድ ፊት ለፊት ያሉ ጐኖች ትይዩና ግጥምጥም ናቸው፡፡
13. ክብ በአንድ ጠለል ላይ ከተሰጠ ቋሚ ነጥብ በእኩል ርቀት ላይ
የሚገኙ ነጥቦች ሰብስብ ነው፡፡ የተሰጠ ቋሚ ነጥብ የክቡ እምብርት
ይባላላ፡፡
14. ከእምብርቱ እስከ ክቡ ላይ የሚገኘው ነጥብ ርቀት ሬድየስ ይባላል፡፡
15. አውታር በክቡ ላይ ያሉ ሁለት ነጥቦችን የሚያገናኘ ውስን ቀጥታ
መስመር ነው፡፡
16. በክቡ እምብርት ውሰጥ የሚያልፍ አውታር ዲያሜትር ይባላል፡፡
17. ኘርዝም ባለ ሦስት ዳይሜሽን ጥጥር ምስል ሆኖ ሁለት ትይት እና
ተገጣጣሚ የሆኑ ጎነ ብዙ መሰረቶች አሉት፡፡ የጎን ገጾቹ ሬክታንግሎች
ናቸው፡፡
18. ሲሊንደር መሰረቶች ክብ የሆኑ ኘርዝም ነው፡፡
19. ኘራሚድ ጥጥር ምስል ሆኖ አንድ መሰረት እና መሰረቱ ላይ የሌላ
ኦፔዲክስ በሚባል ነጥብ ይተረጐማል፡፡
20. መሰረቱ ክብ የሆነ ኘራሚድ ኮን ይባላል::

159
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፍ 5 የክለሳ መልመጃ

1. ከዚህ በታች ለተሰጡት ዘዌዎች ማዕዘናዊ አሟይ ዘዌ ፈልግ/ጊ፡፡


ሀ. 60° ለ. 35° ሐ. 40° መ. 15°

2. ከዚህ በታች ለተሰጡት ዘዌዎች ዝርግ አሟይ ዘዌዎችን ፈልግ/ጊ፡፡


ሀ. 50° ለ. 35° ሐ. 45° መ. 65°
3. የአንድ ዝርግ አሟይ ዘዌ የዘዌውን እጥፍ በ600 ይበልጣል፡፡ ይህን ዘዌ
ፈልግ/ጊ፡፡
4. በምስል 5.56 ላይ በተሰጠው መሰረት፡-
ሀ. ጥንደ ዘዌዎች 1 እና 5 ምን ብለህ/ሽ ትሰይማለህ/ሚያለሽ?
ለ. ጥንድ ዘዌዎች 3 እና 5 ምን ብለህ/ሽ ትሰይማለህ/ሚያለሽ?
ሐ. ጥንድ ዘዌዎች 1 እና 3 ምን ብለህ/ሽ ትለይማለህ/ሚያለሽ?
መ. ዘዌ 7 እና ዘዌ 8 ጉርብታም ዘዌዎች ናቸው? ለምን
ሠ. ዘዌ 8 እና 4 ግጥምጥም ዘዌዎች ናቸው? ለምን?
ረ. ጥንድ ዘዌዎች 1 እና 7 ምን ብለህ/ሽ ትሰይማለህ/ሚያለሽ?

5. ከዚህ በታች ከተሰጡት ቁጥሮች ውስጥ የጐነ ሦስት የጐኖች ርዝመት


ልሆኑ የሚችሉ የትኞቹ ናቸው?
ሀ. 6፣ 7፣ 10 ለ. 7፣ 7፣ 14 ሐ.. 9፣ 9፣ 16
6. Δሀለመ ውስጥ ሀለ = 7ሳ.ሜ፣ ለሐ = 10ሳ.ሜ እና ሐሀ = 9ሳ.ሜ
ናቸው፡፡ ትንሹ ዘዌ የትኛው ነው?

160
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ

6
የዳታ አያያዝ
የመማር ውጤቶች፡ በዚህ ምዕራፍ ትምህርት ሂደት እና ማጠቃለያ ላይ፡-
• ቀለል ያለ ዳታን ለመሰብሰብ ጥያቄዎችን ታዘጋጃለህ/ሽ፡፡
• ዳታን በሠንጠረዥ ታቀናጃለህ/ሽ፡፡
• የዳታን ግራፍ ሰርተህ/ሽ፤ትርጓሜ ትሰጠዋለህ/ጭዋለሽ፡፡
• የዳታን አማካይ፣ መሃል አካፋይ እና ተደጋጋሚ ዋጋ ታሰላለህ/ያለሽ፡፡
• ተጨባጭ በሆነ የዳታን አያያዝ ፅንሰ ሃሳብ ኘሮብሌም ዳታን ማቀናጀት
እና ትርጓሜ መስጠትን ትጠቀምበታለህ/ሽ፡፡

መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ ሥር እንዴት ዳታን መሰብሰብ፣ ማቀናጀት እና በጥልቀት
መተንተን እና መግለፅ እንዴት እንደሚቻል ታያለህ/ሽ፡፡ ይህ ምዕራፍ አምስት
ንዕስ ርዕሶችን አጠምሮ የያዘ ነው፡፡ ዳታን እንዴት መሰብስብ እንደሚቻል፣
በሰጠረዥ ማቀናጀት፣ ትርጓሜ እና የግራፎች አወቃቀር፣ አማካይ፣ መሃል
ካፋይ እና ተደጋጋሚ ዋጋን ተጨባጭ በሆነ ሥራ ላይ መተግበርን
ትማራለህ/ሽ፡፡ ይህ ምዕራፍ ስለ ዳታ ያለህን/ሽን ግንዛቤ እንድታዳብር/ሪ
ያድርግሃል/ሻል፡፡

161
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

6.1 ዳታ የሚሰበሰብበትን ጥያቄዎች ማዘጋጀት እና ዳታን


መሰብሰብ
መግቢያ
ትክክለኛው ውሳኔ መስጠት የሚቻለው በትክክል የተሰበሰበ እና የተቀናጀ ዳታ
ካለ ነው፡፡ ስለዚህ እንዴት እንደሚሰበሰብ፣ እንደሚቀናጅ፣ እንደሚተነተን እና
እንደሚገለጽ ማወቅ አሰፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ስር ለዚህ ተግባር
የሚያገለግሉ ጥየቄዎችን ማዘጋጀት፤ ዳታን መሰብሰብ እና ግራፎችን
መተርጎምን ትማራለህ/ሽ፡፡

ትግበራ 6.1
ከጓደኛህ/ሽ ጋር ተወያዩበት፡-
1. ከዚህ በታች ያለውን ጥያቄ ለመለስ (√) ምልክት በመጠቀም በባዶ ቦታ
ላይ ሙላ/ዪ፡፡ ከዚህ በታች ካሉት ውስጥ የቱን ትወዳለህ/ሽ?
ሀ. ዳቦ ________ ለ. ሙዝ __________
ሐ. ወተት ________ መ. ኬክ_________
2. የእግር ኳስ መጫወትን ትወዳለህ/ሽ?
ሀ. አልወድም፡፡ ________ ለ. እወዳለሁ፡፡_______
3. በቀን ለጥናት የሚወስድብህ ሰዓት ምን ያህል ነው?
ሀ. ለ1 ሰዓት፡፡ ______ ለ. ለ2 ሰዓት፡፡______
ሐ. ለ3 ሰዓት፡፡______ መ. 3 ሰዓት፡፡____

ዳታን የምንሰበስብበት መንገዶች


ዳታን በተለያየ መንገድ መሰብሰብ ይቻላል፡፡
• ግራፍን በመጠቀም፡፡
• የመስክ ምልከታ ማድረግና የተገኘውን ውጤት መመዝገብ፡፡
• ሙከራን መሥራት፡፡

162
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

• ከዳታ መዝገብ ወይም ከዳታ ቤዝ” መሰብሰብ፡፡


• ከኢንተርኔት ላይ
መረጃ እንዴት እና የት እንደሚሰበሰብ ልዩ ትኩረት መስጠት
ያስፈልግሃል/ሻል፡፡
• ማግኘት የምትፈልገውን ነገር በግልፅ ማወቅ እና መረጃውን እንዴት
እንደምትፈልግ/ጊ ማወቅ አለብህ/ሽ፡፡
• አጭር እና ግልፅ የሆነ ጥያቄ መጠየቅ፡፡
• ለምትጠይቀው/ይው ጥያቄ የሳጥን ምልክት በማዘጋጀት መልስ
የሚሰጥበትን ቦታ አዘጋጅላቸው/ጂላቸው፡፡
• የምታዘጋጀው/ጂው ጥያቄ አንድ መልስ ያለው እና የማያሻማ መሆን
አለበት፡፡
የጭረት ምልክት/ታሊ ነገሮችን ለማቁጠር ያገለግላል፡፡
ይህ ምልክት ትናንሽ ቁም መስመር እያንዳንዱ አንድ ምድብን ይወክላል፡፡
ለምሳሌ ለአንድ |፣ለሁለት ||፤ ለሦስት ||| በመስራት እንጠቀማለን፡፡
ለአምስት ጭረት በመጠቀም እናሳያለን፡፡ ይህም በጠቅላላ መረጃ ውሰጥ
ያሉትን አምስቶች በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ ልኬት
በአንድ ሙከራ ውስጥ 7 ጊዜ ቢደጋገም || መልክ እናሳያለን፡፡
በዚህ ክፍል ውስጥ የጭረት ምልክትን በመጠቀም እንዴት መረጃን
እንደምንሰበሰብ እናያለን፡፡

ለአንድ ለሁለት ለሦስት ለአራት ለአምስት

|
አንድ ልኬት በአንዱ ሙከራ ውስጥ 8 ጊዜ ቢደጋገም በ መልክ
ማሳየት ይቻላል፡፡

163
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 1
1

ጫልቱ የምታስተምራቸውን ተማሪዎች የጫማ ቁጥር በመጠየቅ ከዚህ በታች


ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ ፅፋለች፡፡
35 34 37 35 36 37 36 35 36 36 35
34 35 36 38 37 34 36 35 36 34 36
35 37 36 37 35 37 36 34 38 37 38

ከዚህ በላይ ባለው ሠንጠረዥ ላይ በመመሥረት የሚከተሉትን መልስ/ሺ፡፡


ሀ. ተማሪዎች በብዛት ያጠልቁት የጫማ ቁጥር የቱ ነው?
ለ. ጥቂት ተማሪዎች ያጠለቁት የጫማ ቁጥር የቱ ነው?

መፍትሔ
ይህን ዳታ በቀላሉ ለመረዳት የመስመር ጭረት መጠቀም አለብን፡፡
የጫማ ቁጥር የተማሪዎች ብዛት በጭረት
መስመር
34

35

36

37
38

ስለዚህ፣ ከዚህ በላይ ባለው ሠንጠረዥ ላይ፡-


ሀ. ተማሪዎች በብዛት ያጠለቁት የጫማ ቁጥር 36 ነው፡፡
ለ. ጥቂት ተማሪዎች ያጠለቁት የጫማ ቁጥር 38 ነው፡፡

164
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የኘሮጀክት ሥራ
አብረህ/ሸ ከምትማረው/ሪው ተማሪዎች የቤተሰቦቻቸውን ብዛት ዳታ
በመሰብሰብ ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ ሙላ/ዪ፡፡
ከሰበሰብከወ/ሽው ዳታ ከዚህ በታች ያሉትን ሙላ/ዪ፡፡
የተማሪ ብዛት የቤተሰብ ብዛት በጭረት መስመር

ሀ. ብዙ ቤተሰብ ያላቸው ተማሪዎች ብዛት ስንት ነው?


ለ. እኩል ቤተሰብ ያላቸው ተማሪዎች ብዛት ስንት ነው?
ሐ. ትንሽ ቤተሰብ ያላቸው ተማሪዎች ብዛት ስንት ነው?

6.2 ዳታን በሠንጠረዥ ማቀናጀት


መግቢያ
የአንድን ዳታ ዓላማ ከግብ ለማድረስ መረጃ ከሰበሰብን በኋላ በቀላሉ ለመገንዘብ
እንዲመች በተለያየ ሁኔታ ተደራጅቶ መቅረብ አለበት፡፡ ከነዚህ ሁኔታዎች
ውስጥ አንዱ የጭረት መስመሮች ሠንጠረዥ እና የድግግም ሠንጠረዥ
ናቸው፡፡ በሠንጠረዥ ከመግለፃችን በፊት የተሰጠውን ዳታ ገላጭ ለማሻሻል
በመጀመሪያ ከትንሽ ወደ ትልቅ ወይም ከትልቅ ወደ ትንሽ በቅደም ተከተል
ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ሠንጠረዥ መስርተህ እያንዳንዱን
የዳታ አባል ድግግሞሽ በጭረት መስመር እና በቁጥር በማስቀመጥ መግለፅ
ነው፡፡

165
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 2
ቶለሣ ስም የሚጠራቸውን ተማሪዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ የቀሩ
ተማሪዎችን ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ መዝግቧል፡፡

የቀሩ ተማሪዎች ብዛት የቀሩ ተማሪዎች


ዕለት
በጭረት መስመር ብዛት (ድግግሞሽ)

ሰኞ 5

ማክሰኞ 4
ረቡዕ - 0
ሐሙስ 2

ዓርብ 7

ከዚህ በላይ ባለው ሠንጠረዥ ላይ በመመርኮዝ ከዚህ በታች ያሉትን


ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡
ሀ. በየትኛው ቀን ብዙ ተማሪዎች ቀሩ?
ለ. ጥቂት ተማሪዎች የቀሩበት ዕለት መቼ ነው?
ሐ. ተማሪዎች ከትምህርታቸው ያልቀሩት በየትኛው ዕለት ነው?

መልመጃ 6.1
1. 40 ተማሪዎች በፊዚክስ የሙከራ ፈተና ከ 10 ያገኙት ውጤት ከዚህ
በታች ተሰጥቷል፡፡

9 2 4 8 7 6 6 5 5 3
5 10 6 4 8 2 7 6 3 8
8 4 9 5 3 9 10 6 9 7
8 5 6 7 10 7 5 5 7 7
ሀ. ይህንን ውጤት በድግግሞሽ ሠንጠረዥ በማደራጀት አሳይ/ዪ፡፡

166
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለ. ከዚህ ሠንጠረዥ ቀጥሎ የተጠየቁትን ፈልግ/ጊ፡፡


i. 7 እና ከ 7 በላይ ያገኙ ተማሪዎች ስንት ናቸው?
ii. 4 እና ከ 4 በታች ያገኙ ተማሪዎች ስንት ናቸው?
2. አንድ ነጋዴ በሳምንት ውስጥ የሸጣቸውን የአምፑሎች ብዛት ከዚህ በታች
በተሰጠው የተገለፀ ሲሆን ከሠንጠረዡ ላይ ቀጥሎ የተሰጡትን
ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡
ቀን በቀን የተሸጠ አምፑል
ሰኞ 13
ማክሰኞ 16
ረቡዕ 9
ሐሙስ 11
ዓርብ 14
ቅዳሜ 9
እሁድ 18
ሀ. በዕለት ዓርብ ስንት አምፑሎችን ሸጠ?
ለ. በየትኛው ዕለት ብዙ አምፑሎችን ሸጠ?
ሐ. በየትኞቹ ዕለታት እኩል አምፑሎችን ሸጠ?
መ. በየትኛው ዕለት ትንሽ አምፑል ሸጠ?
ሠ. አንድ ካርቶን 9 አምፑሎችን ማስቀመጥ የሚችል ከሆነ፣ በአንድ
ሳምንት ውስጥ ለተሸጡት አምፑሎች ስንት ካርቶን ያስፈልጋል?

3. በአምስት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ የእርሻ ትራክተር ብዛት ከዚህ በታች
በተሰጠው ሠንጠረዥ ውስጥ የተሰጠ ሲሆን ከ ሀ ̶ መ ያሉትን ጥያቄዎች
መልስ/ሺ፡፡

167
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ቀበሌዎች የትራክተሮች ብዛት


ቀበሌ ሀ 6
ቀበሌ ለ 5
ቀበሌ ሐ 8
ቀበሌ መ 3
ቀበሌ ሠ 6
ሀ. አነስተኛ ትራክተር ያለው የትኛው ቀበሌ ነው?
ለ. ብዙ ትራክተር ያለው የትኛው ቀበሌ ነው?
ሐ. ቀበሌ ሐ ያለው የትራክተር ብዛት ቀበሌ ለ ካለው የትራክተር ብዛት
በስንት ይበልጣል?
መ. በአጠቃላይ በአምስቱ ቀበሌዎች ውሰጥ ያለው የትራክተር ብዛት ስንት
ነው?
4. በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ በ8 ክፍሎች ውስጥ የልጃገረዶች ብዛት
ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ የተሰጠው ከሆነ፣ ከሀ-ሐ ያሉትን
ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡
ክፍሎች የተማሪ ብዛት
ሀ 24
ለ 20
ሐ 20
መ 16
ሠ 12
ረ 16
ሰ 12
ሸ 8
ሀ. በየትኛው ክፍል ውስጥ ጥቂት ልጃገረድ ተማሪዎች ይገኛሉ?

168
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለ. በ ሠ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ረ ውስጥ ካሉ


ተማሪዎች በስንት ያንሳሉ?
ሐ. በ ሸ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ምን ያህል ሴት ተማሪዎች ይገኛሉ?

6.3 ግራፎችን መስራትና መግለፅ

መግቢያ
የዳታ አያያዝ ከመረጃ መሰብሰብ፣ ማደራጀትና መግለፅ ጋራ የተያያዘ ነው ፡፡
በዚህ ርዕስ ውስጥ የቁም ግራፍና ፓይ ቻርትን በመጠቀም ዳታን መግለፅ
ትማራለህ/ያለሽ፡፡

የቁም ግራፍ
ቁም ግራፍ ሬክታንግላዊ ቻርቶች ያሉት ሲሆን ርዝመቱ ከሚወክለው ዋጋ
ጋር ተመጣጣኝ ነው፡፡
ቁም ግራፍ በምትሰራበት/ሪበት ጊዜ ከዚህ በታች የተሰጡትን ነጥቦች ትኩረት
ውስጥ ማስገባት አለብህ/ሽ፡፡
ሀ. የቁም ሬክታንግሎች እኩል ወርድ አላቸው፡፡
ለ. በቁሞቹ መሃከል ያለው ርቀት እኩል ነው፡፡
ቁም ግራፎች በብዙ መንገድ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
ሀ. ከግራፍ ላይ አስፈላጊውን መረጃ በማግኘት ግንዛቤ እናገኛለን፡፡
ለ. በግራፍ ላይ የምናገኘቸውን መረጃዎች በማመዛዘን አስፈላጊውን ግንዛቤ
ለማግኘት ይረዳል፡፡
ሐ. አብዛኛውን ጊዜ መረጃን ከግራፎች ላይ በማግኘት ኘሮብሌሞችን ለመፍታት
ይጠቅመናል፡፡

ምሳሌ 3
ከዚህ በታች ያለው ዳታ የ47 ተማሪዎች የልደት ቀናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

169
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የልደት ቀን የተማሪዎች ብዛት


ሰኞ 6
ማክሰኞ 8
ረቡዕ 7
ሐሙስ 8
ዓርብ 10
ቅዳሜ 3
እሁድ 5

ምስል 6.1

ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተሰጠው ዳታ ላይ ተመርኩዞ ከተሰራው


ግራፍ (ምስል 6.1) ላይ ከ ሀ እስከ ሐ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሽ፡፡
ሀ. ብዙ ተማሪዎች የተወለዱበት ዕለት የቱ ነው?
ለ. ጥቂት ተማሪዎች የተወለዱበት ዕለት የቱ ነው?
ሐ. ተመሳሳይ ብዛት ያላቸው ተማሪዎች የተወለዱባቸው ቀናት
የተኞቹ ናቸው?

170
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የቡድን ሥራ 6.1
ከዚህ በታች የተሰጡት ሁለት ግራፎች የ5ኛ እና የ6ኛ ከፍል ተማሪዎች
በአንድ ሳምንት ውስጥ በመማሪያ ክፍል የተገኙበትን ዕለታት ያሳያል፡፡

ከላይ ባሉት ምስል 6.2 እና 6.3 ላይ በመመርኮዝ ከታች ለተሰጡት ጥያቄዎች


መልስ ስጡ፡፡
ሀ. ከዚህ በታች በተሰጡት ዕለታት ስንት የ5ኛ ክፍል ተማሪዎች በመማሪያ
ከፍላቸው ተገኙ?
ሰኞ _________? ሐሙስ _________?
ረቡዕ__________ ? አርብ __________?
ለ. ከዚህ በታች በተሰጡት ዕለታት ስንት የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች

171
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በመማሪያ ክፍላቸው ተገኙ?


አርብ _________? ሐሙስ _________?
ረቡዕ__________ ? ማክሰኞ __________?
ሐ. ከዚህ በታች በተሰጡት ዕለታት የየትኛው ክፍል ተማሪዎች ይበልጥ
በብዛት ተገኙ?
ማክሰኞ _________? አርብ _________?
ረቡዕ__________ ? ሰኞ __________?

አስተውል/ዪ
ሀ. ቁም ግራፎችን በምትሰራበት/ሪበት ጊዜ መረጃውን በጭረት መስመር
መልክ ወይም በድግግሞሽ ሠንጠረዥ ማደራጀት አለብህ/ሺ፡፡
ለ. እነዚህ ግራፎች ቁም ወይም አግድም የተኙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ምሳሌ 4
ከዚህ በታች የተሰጠው ግራፍ በአንድ ቀበሌ ጐጥ ውስጥ የሚገኙ ልጆችን
እድሜ የሚያሳይ ነው፡፡

172
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ይህን ግራፍ በመጠቀም ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡


ሀ. ዕድሜያቸው 13 አመት የሆነ ልጀች ብዛት ስንት ናቸው?
ለ. ዕድሜያቸው ከ16 አመት በላይ የሆኑ ልጆች ስንት ናቸው?
ሐ. ዕድሜያቸው ከ13 አመት በላይ የሆኑ ልጆች ስንት ናቸው?
መ. ዕድሜያቸው 10 አመት የሆኑ ልጆች ስንት ናቸው?
ሠ. ዕድሜያቸው ከ14 አመት በታች የሆኑ ልጆች ስንት ናቸው?
ረ. በአጠቃላይ በዚህ ቀበሌ ጐጥ ውስጥ ስንት ልጆች ይገኛሉ?
መፍትሔ
ሀ. 10 ለ. 5 + 8 + 6 + 10 + 9 + 3 = 41 ሐ. 9 + 3 = 12
መ. 5 ሠ. 5 + 8 + 6 + 10 = 29 ረ. 5 + 8 + 6 + 10 + 9 + 3 = 41

ፓይ ቻርት (ክብ ግራፍ)


ፓይ ቻርት አንዳንድ ጊዜ ክብ ግራፍ ይባላል፡፡ ከቁም ግራፍ ጋር ትልቅ
ልዩነት አለው፡፡ በክብ ግራፍ ውስጥ አንድ የተሰጠ ሙሉ ነገር እንደ ሙሉ

173
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ክብ ስፋት (100% ወይም 3600) በመውሰድ ሊገለፅ ይችላል፡: ስለ ክብ ግራፍ


ለመረዳት ከዚህ በታች የተሰጠውን ትግበራ ሥራ/ሪ፡፡

ትግበራ 6.2
1. ክብን ከመሰረትክ/ሽ በኋላ እኩል 5 ቦታ በመከፋፈል የተለያዩ ቀለማትን
ቀባ/ቢ፡፡ እያንዳንዳቸውን ተከፋፍሎ የተለያየ ቀለም የተቀቡትን በመቶኛ
ግለፅ/ጪ፡፡
2. አንድን ክብ በመመስረት ከዚህ በታች በተሰጠው መሰረት ቀባ/ቢ፡፡
50% ቀይ ፤ 25% ቢጫ፤ 25% አረንጓዴ
3. ስለ ክፍልህ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተሰጠውን መረጃ ሠንጠረዥ
በመጠቀም ከሰበሰብክ በኋላ ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡
• የክፍላችሁ ተማሪዎች ብዛት
• የወንድ ተማሪዎች ብዛት
• የሴት ተማሪዎች ብዛት
ሀ. የወንድ እና የሴት ተማሪዎች ብዛት በመቶኛ ግለጽ/ጪ፡፡
ለ. ክብን በመመስራት የወንድ እና የሴት ተማሪዎችን መቶኛ
በመከፋፈል አሰይ/ዪ፡፡

አስተውል/ዪ
• የክብ ግራፍ መረጃን በመቶኛ መልክ ለመግለፅ ይረዳል፡፡
• የክብ ግራፍ ክፋዮች አጠቃላይ ድምር 100 መሆን አለበት፡፡
• በክብ ግራፍ ውስጥ የክብ ክፋዮች እንደ ቅስት ተወስደው በዲግሪ መግለፅ
ይችላሉ፡፡ በዚህ አገላለፅ ውስጥ የቅስቶች ስፍር ድምር በአንድ ላይ 3600
መሆን አለበት፡፡

174
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 5
ለአንድ ት/ቤት የተሰጠ ቦታ ከዚህ በታች እንደተገለፀው ሥራ ላይ ውሏል፡፡
45% ለእርሻ ፤20% ለመጫወቻ ሜዳ፤ 25% ለእግር ኳስ ሜዳ እና 10%
ለአበቦች መትከያ፡፡ ይህንን መረጃ ክብ ግራፍን በመጠቀም አሳይ/ዩ፡፡

መፍትሔ
የተሰጠውን መረጃ የሚተኩ ቅስቶች
ለመስራት የዘዌያቸውን ስፋት ከዚህ በታች
እንደተመለከተው ይፈለጋሉ፡፡
ሀ. የእርሻ ቦታ 45% የ 3600
45
=  360 0 = 162 0
100
ለ. የመጫወቻ ሜዳ 20% የ 3600
20
=  360 0 = 72 0
100
25
ሐ. የእግር ኳስ ሜዳ 25% የ3600 =  360 0 = 90 0
100
10
መ. የአበቦች መትከያ 10% የ3600 =  360 0 = 36 0
100
መልመጃ 6.2
1. ሀዊ የተማሪዎችን የሂሳብ ሙከራ ፈተና ውጤት ከ10 ያገኙትን
እንደሚከተለው መዝግባ ያዘች፡፡

4 1 7 6 1 3 8 7 2 4
5 1 3 7 7 8 9 7 5 1
3 2 1 8 9 3 7 10 2 6
8 9 10 3 7 6 2 5 8 10

175
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በዚህ ውጤት ላይ በመመሰረት:


ሀ. የድግግሞሽ ሠንጠረዥ አዘጋጅ/ጂ፡፡
ለ. የቁም ግራፍን ሥራ/ሪ፡፡
2. ከዚህ በታች የተሰጠው ግራፍ በ4 የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ
የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ብዛትን ያሳያል፡፡

በግራፉ ላይ በመመሰረት ከዚህ በታች የተሰጡ ጥያቄዎችን መልስ/ሽ፡፡


ሀ. በመማሪያ ክፍል ለ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ብዛት ስንት ነው ?
ለ. የበለጠ ተማሪዎችን የያዘው የትኛው የመማሪያ ክፍል ነው?
ሐ. የማመሪያ ክፍል ሐ ከመማሪያ ክፍል ለ በስንት ተማሪዎች
ይበልጣል?
መ. የትኛው መማሪያ ክፍል ጥቂት ተማሪዎችን ይዟል?
3. ቀጥሎ ያለው ሠንጠረዥ በአንድ ሱቅ የተሸጡ የተለያ ቀለማት ብዛት
በጋሎን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህንን መረጃ የሚያሳይ የቁም ግራፍ ሥራ/ሪ፡፡

የተሸጡት
ጭረት
የቀለም ዓይነት ቀለማች ብዛት
መስመር
በጋሎን
አንጓዴ 9

ብጫ 7

176
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሰማያዊ 5

ቀይ 8
4. ከዚህ በታች የተሰጠው ግራፍ በሆነ አከባቢ የሚገኙ የተለያዩ አይነት
ዛፎችን ርዝመት የሚያሳይ ነው፡፡

ይህን ግራፍ በመጠቀም ከዚህ በታች የተሰጡ ጥያቄዎችን መልስ/ሺ፡፡


ሀ. የጥድ ርዝመት ምን ያህል ነው?
ለ. ረጅሙ ዛፍ የቱ ነው?
ሐ. የአጭሩን ዛፍ ርዝመት እጥፍ የሆነው የየትኛው ዛፍ ርዝመት ነው?
5. ወይዘሮ ኦብሴ የወር ገቢያቸውን ከዚህ በታች እንደተገለፀው ሥራ ላይ
ለማዋል አቅደዋል፡፡ 20% ለቁጠባ፣ 35% ለምግብ፣15 % ለቤት ኪራይ፣
20% ለልጆቻቸው የትምህር ቤት ወጪ እና የቀረውን ለመጓጓዣ
ለማዋል አስበዋል፡፡
ሀ. በክብ ግራፍ የቁጠባ ዕቅዳቸው የሚተካ ቅስት ዘዌ ስፍር ስንት ነው?
ለ. በክብ ግራፍ የምግብ ወጪ ዕቅዳቸውን የሚተካ ቅስት ዘዌ ስፍር ስንት
ነው?

177
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሐ. በክብ ግራፍ የቤት ኪራይ ዕቅዳቸውን የሚተካ ቅስት ዘዌ ስፍር ስንት


ነው?
መ. በክቡ ግራፍ የልጆቻቸውን የትምህርት ወጪን የሚተካ ቅስት ዘዌ
ስፍር ስንት ነው?
ሠ. በክቡ ግራፍ የመጓጓዣን ወጪ የሚተካ ቅስት ስፍር ስንት ነው?
ረ. ወይዘሮ ኦብሴ ገቢያቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙ በክቡ ግራፍ
አሳይ/ዩ፡፡
ሰ. የወይዘሮ ኦብሴ የወር ገቢያቸው 13926 ብር ከሆነ፣ ለቁጠባ
የምታውለው ብር ስንት ነው?
6. የክፍል ጓደኞችህን የልደት ቀን መረጃ በመሰብሰብ ቁም ግራፍ ሥራ/ሪ፡፡

6.4 አማካይ ዋጋ፣ ተደጋጋሚ ዋጋ እና መሃል ከፋይ ዋጋ


መግቢያ
ከተሰበሰበው መረጃ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት መረጃውን የሚወክል ዋጋ
ማስላት ያስፈልጋል፡፡ ጠቅላላ መረጃን በመተካት ስለ መረጃው አስፈላጊ
መልእክት የሚያስተላላፍ የመሃል ልኬት ይባላል፡፡ ሦስት የታወቁ የመሃል
ዋጋ ልኬቶች አሉ፡፡ እነሱም አማካይ ዋጋ፣ ተደጋጋሚ ዋጋ እና የመሃል
ከፋይ ዋጋ ናቸው፡፡ ስለዚህ አንድ መረጃ፣ አማካይ ዋጋ፣ ተደጋጋሚ ዋጋ እና
መሃል ከፋይ ዋጋ መፈለግ በይበልጥ ስለ ዳታው አስፈላጊ የሆኑ መረጃን
ለማግኘት ይረዳሃል፡፡
ትግበራ 6.3
1. የክፍል ተማሪህን/ሽን የዕድሜ መረጃ በመሰብሰብ ከዚህ በታች የተሰጡትን
ጥያቄዎች መልስ/ሸ፡፡
ሀ. የክፍል ተማሪዎችህን/ሽን አማካይ እድሜ ፈልግ/ጊ፡፡
ለ. በክፍል/ሽ ውስጥ በጣም የተደጋገመው እድሜ ስንት ነው?

178
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሐ. የክፍል ተማሪዎችህ/ሽ መሃል ከፋይ እድሜ ፈልግ/ጊ፡፡


2. ቦንቱ ከመቶ በአሥር የትምህርት ዓይነቶች ያገኘቺው ውጤት ከዚህ
በታች ያለው ቢሆን፤ ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡ የቦንቱ
ውጤቶች 86፣ 91፣ 96፣ 86፣ 86፣ 71፣ 91፣ 93፣ 83፣ 85
ሀ. የቦንቱ አማካይ ውጤት ስንት ነው?
ለ. ይበልጥ የተደጋገመው የቦንቱ ውጤት የቱ ነው?
ሐ. የቦንቱን ውጤት ከትንሽ ወደ ትልቅ በመዘርዘር የመሃል ከፋይ
ውጤት ፈልግ/ጊ፡፡
3. ስምንት ተማሪዎችን በመጠየቅ የቤተሰቦቻቸው ብዛት መረጃ፡-
4፣5፣5፣4፣5፣5፣4፣6 ከሆነ፣ ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች መልስ/ሺ፡፡
ሀ. የዚህን ዳታ አማካይ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
ለ. ይበልጥ የተደጋገመው ቁጥር ስንት ነው
ሐ. የዚህን ቤተሰብ መረጃ ከትልቅ ወደ ትንሽ በመዘርዘር የመሃል አካፊይ
ፈልግ/ጊ፡፡

ከዚህ በላይ ባለው ትግበራ ላይ አማካይ ዋጋ ፣ የመሃል አካፋይ ዋጋ እና


ተደጋጋሚ ዋጋ ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ተገንዝበሃል/ሻል፡፡ ስለዚህ፣ ከዚህ
በታች የተሰጡትን የሀሳቡን ማጠቃለያ አስተውል/ዪ፡፡

አማካይ ዋጋ
የአንድ ዳታ ስብስብ አማካይ ዋጋ የምንለው በመረጃ ውስጥ ያሉ ሁሉንም
ቁጥሮች በመደመር በስብስቡ ውሰጠ ላሉ ቁጥሮች ብዛት በማካፈል ይሆናል፡፡
ይህም አማካይ ዋጋ

179
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 6
የዚህን ቁጥር አማካይ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡ 205, 136, 311, 257, 331 እና 224

መፍትሔ

ተደጋጋሚ ዋጋ
የተደጋጋሚ ዋጋ በአንድ መረጃ ስብስብ ውስጥ ከሚገኙት አባላት በይበልጥ
ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የታየ ዳታ ነው፡፡

አስተውል/ዪ
አንድ የተሰጠ ዳታ ከአንድ በላይ ተደጋጋሚ ዋጋ ሊኖረው ይችላል፡፡ እንድሁም
አንድ የተሰጠ መረጃ ተደጋጋሚ ዋጋ ላይኖረው ይችላል፡፡
ምሳሌ 7
ከዚህ በታች ለተሰጡት ዳታ ተደጋጋሚ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
ሀ. 36፣ 37፣ 38፣ 40፣ 30፣ 40፣ 35፣ 45፣ 40
ለ. 21፣ 37፣ 35፣ 41፣ 20፣ 23፣ 37፣ 45፣ 20
ሐ. 16፣ 13፣ 12፣ 18፣ 20፣ 22

መፍትሔ
እስቲ በመጀመሪያ የተሰጡትን ቁጥሮች በቅደምተከተል አስቀምጥ/ጪ፡፡
ሀ. 30፣ 35፣ 36፣ 37፣ 38፣ 40፣ 40፣ 40፣ 45 በተቀመጠው ቅደም
ተከተል መሰረት በብዛት ተደጋግሞ የተፃፈውን ቁጥር በቀላሉ መናገር
ትችላለህ/ያለሽ፡፡ ስለሆነም የተደጋጋሚ ዋጋ 40 ነው፡፡

180
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ለ. 20፣ 20፣ 21፣ 23፣ 35፣ 37፣ 37፣ 41፣ 45 በተቀመጠው ቅደም
ተከተል መሰረት በብዛት ይበልጥተደጋግሞ የተፃፋት ቁጥሮች 20 እና 37
ናቸው ስለዚህ ተደጋጋሚ ዋጋ 20 እና 37 ናቸው፡፡
ሐ. 12፣ 13፣ 16፣ 18፣ 20፣ 22 በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሰረት
በብዛት ተደጋግሞ የተፃፈ ቁጥር የለም፡፡ ስለዚህ የተደጋጋሚ ዋጋ
የለውም ማለት ነው፡፡

መሃል ከፋይ ዋጋ
የመሃል ከፋይ ዋጋ መጃመሪያ በቅደም ተከተል በማቀናጀት በተሰጠ መረጃ
ውስጥ በመሃል የሚገኝ ቁጥር ነው፡፡ የዳታው አባላት ብዛት ኢ-ተጋማሽ ቁጥር
ከሆነ፣ በመሃል ላይ የሚገኘው ቁጥር መሃል ከፋይ ይሆናል፡፡ ነገር ገን
የዳታዎቹ ብዛት ተጋማሽ ቁጥር ከሆነ፣ በመሃል ላይ የሚገኙ የሁለት ቁጥሮች
አማካይ መሃል ከፋይ ዋጋ ይባላል፡፡
አስተውል/ዪ
ሁል ጊዜ በቅደም ተከተል በተሰጠው ዳታ ውስጥ ከመሃል ከፋይ በፊትና በኋላ
የሚገኙ ቁጥሮች ብዛት እኩል ነው፡፡
ምሳሌ 8
በአንድ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ የሰዎች እድሜ ከዚህ በታች እንደተሰጠው
ከሆነ፣ የመረጃውን መሃል ከፋይ ፈልግ/ጊ፡፡
42፣ 59፣ 48፣ 43፣ 45፣ 43 እና 47

መፍትሔ
የመሃል ከፋዩን ለመፈለግ በመጀመሪያ የሰዎቹን እድሜ በቅደም ተከተል
ዘርዝር/ሪ፡፡ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሲዘረዘር፤ 42፣ 59፣ 48፣ 43፣ 45፣ 43፣ 47
ወይም ከትንሽ ወደ ትልቅ ሲዘረዘር፤ 42፣ 43፣ 43፣ 45፣ 47፣ 48፣ 59
የዳታዎቹ ስብስብ አባላት ብዛት 7 ነው፡፡ 7 ኢ-ታጋማሽ ቁጥር ስለሆነ
በመሃል ላይ የሚገኘው ቁጥር 45 ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ 45 መሃል ከፋይ ነው፡፡

181
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምሳሌ 9
ተማሪዎች የሂሳብ ሙከራ ፈተና ከ 40 ወስደው 33፤ 36፤ 38፤ 35፤ 33፤
39፤ 30፤ 33፤ 39፤ 36 ውጤት አመጡ፡፡ የዚህን ውጤት መሃል
ከፋይ ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ
የመሃል ከፋይ ለመፈለግ በመጀመሪያ የተማሪዎችን ውጤት በቅደም ተከተል
ማስቀመጥ ያስፈልጋ፡፡ ከትልቅ ወደ ትንሸ 39፣ 39፣ 38፣ 36፣ 36፣ 35፣
33፣ 33፣ 33፤ 30 የዳታዎቹ አባላት ብዛት 10 ነው፡፡ 10 ተጋማሽ ቁጥር
ስለሆነ መሃል ከፋይ ውጤት መሃል የሚገኙ ሁለት ቁጥሮች 35 እና 36
አማካይ ውጤት ይሆናል፡፡
35 + 36
ስለዚህ መሃል አካፋይ ውጤት = = 35.5
2

አስተውል/ዪ
የአንድ መረጃ መሃል አካፋይ ዋጋ ከተሰጡት መረጃ አባላት ውጪ ሊሆን
ይችላል፡፡

መልመጃ 6.3
1. በታህሳስ ወር በአንድ ሳምንት በሁለት ከተሞች ሀ እና ለ የተሰበሰበው
የሙቀት መጠን ከዚህ በታች በተሰጠው ሠንጠረዥ ውስጥ በድግሪ
ሴንትግሬድ ተቀምጧል፡፡ በዚህ ዳታ መሰረት አማካይ ዋጋ፣ መሃል ከፋይ
ዋጋ እና ተደጋጋሚ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
ከተማ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ሐሙስ አርብ ቅዳሜ እሁድ
ሀ 21 22 22 22 20 20 21
ለ 25 25 24 23 24 20 23
2. የ12 ተማሪዎች የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ፈተና ውጤት ከዚህ በታች

182
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ተሰጥቷል፡፡ ለዚህ ዳታ አማካይ ዋጋ፣ መሃል ከፋይ ዋጋ፣ እና ተደጋጋሚ


ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
88፣ 85፣ 93፣ 85፣ 73፣ 78፣ 59፣ 52፣ 86፣ 73፣ 99፣ 70

6.5 የዳታ አያያዝ ጽንሰ ሃሳብን ሥራ ላይ ማዋል


መግቢያ
በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር ስለ አማካይ ዋጋ፤መሃል ከፋይ ዋጋ እና ተደጋጋሚ
ዋጋ ተምረሃል/ሻል፡፡ አሁን ደግሞ የአማካይ ዋጋ፣ የመሃል ከፋይ ዋጋ እና
የተደጋጋሚ ዋጋን በመጠቀም ዕለት በዕለት የሚጋጥሙንን ተጨባጭ
ኘሮብሌሞችን ማሰላት ትችላለህ/ያለሽ፡፡
ምሳሌ 10
በአንድ ከተማ ውስጥ በታህሳስ ወር በመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ በየቀኑ
የተመዘገበ የሙቀት መጠን በሴንቲግሬድ 24፣ 18፣ 21፣ 27፣ 24፣ 20 እና
24 ከሆነ፣ ለዚህ ከተማ ሙቀት መጠን አማካይ ዋጋ፣ መሃል ከፋይ ዋጋ እና
ተደጋጋሚ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡

መፍትሔ

24 + 18 + 21 + 27 + 24 + 20 + 24 158
= = = 22.57
7 7
የመሃል ከፋይ ዋጋን ለመፈለግ የዚህን ሙቀት መጠን በቅደም ተከተል
አስቀምጥ/ጪ፡፡ ከትልቅ ወደ ትንሽ 27፣ 24፣ 24፣ 24፣ 21፣ 20፣ 18
ወይም ከትንሽ ወደ ትልቅ 18፣ 20፣ 21፣ 24፣ 24፣ 24፣ 27 እና የዳታው
አባላት ብዛት 7 ነው፡፡ 7 ኢ-ታጋማሽ ቁጥር ስለሆነ መሃል ያለው ቁጥር 24

183
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የመሃል ከፋይ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የመሃል ከፋይ ዋጋ 24 ነው፡፡ ተደጋጋሚ


ዋጋ ለማግኘት የተሰጡትን ቁጥሮች በቅደም ተከተል አስቀምጥ/ጪ፡፡
18፣ 20፣ 21፣ 24፣ 24፣ 24፣ 27 በዚህ ቅደም ተከተል ውስጥ ይበልጥ
የተደጋገመውን በቀላሉ መለየት ትችላለህ/ያለሽ፡፡ ስለዚህ የተደጋጋሚ ዋጋ 24
ነው፡፡

መልመጃ 6.4
1. ቶላ ለ3 ቀናት በመኪና ተጓዘ፡፡ በመጀመሪው ቀን በሰዓት 98ኪ.ሜ፣ በ2ኛው
ቀን በሰዓት 43ኪ.ሜ እና በ3ኛው ቀን በሰዓት 41ኪ.ሜ ቢጓዝ የአማካይ
ዋጋ፣ መሐል ከፋይ ዋጋ እና የተደጋጋሚ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
2. አንድ ተማሪ በወሰዳቸው 5 የሙከራ ፈተናዎች ያገኘው ውጤት ከዚህ
ቀጥሎ የተመዘገቡት ናቸው፡፡ ለዚህ ውጤት አማካይ ዋጋ፣ መሃል ከፋይ
ዋጋ እና ተደጋጋሚ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
የትምህርት ሒሳብ አፋን የአካባቢ እንግሊዘኛ
አይነት ኦሮሞ ገዳ ሳይንስ
ውጤት 9 10 9 8 7

3. በአንድ ጤና ጣቢያ የ10 ልጆች መጠነ ቁስ ስፍር ከዚህ በታች በተሰጠው


ሠንጠረዥ ውስጥ ተመዝግቧል፡፡ የልጆቹን መጠነ ቁስ አማካይ ዋጋ፣
መሃል ከፋይ ዋጋ እና ተደጋጋሚ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡
ህፃን ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሸ ቀ በ ተ
መጠነ ቁስ 13 16 19 21 26 29 22 30 28 25
(ኪ.ግ)

4. በእያንዳንዱ 6 መጠነ ቁስ ሣጥኖች ውስጥ የሚገኙ የክብሪት እንጨቶች


ብዛት ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ የክብሪት
እንጨቶች አማካይ ብዛት፣ መሃል ከፋይ እና ተደጋጋሚ ብዛት ፈልግ/ጊ፡፡

184
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ክብሪት ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ
የክብሪት እንጨት 44 43 45 48 47 49

የምዕራፍ 6 ማጠቃለያ
• ብዙውን ጊዜ በቁጥር የሚሰጡ የነገሮች ስብስብ መረጃ ይበላል፡፡
• ዳታ እንደ አጨማመሩ ወይም እንደ አቀናነሱ ሁኔታ ይቀናጃል፡፡
• የጭረት ቆጠራ ነገሮችን ለመቁጠር ያገለግላል፡፡ እነሱም እያንዳንዳቸው ትናንሽ
ከላይ ወደታች የተሰመሩ የአንድን ነገር ብዛት የሚተኩ ናቸው፡፡
• የጭረት ሠንጠረዥ መረጃን በሠንጠረዥ መልክ የሚየሳይ ነው፡፡ መረጃን
ቀለል ባለመልኩ ለማቅረብ ይረዳል፡፡
• አማካይ ዋጋ የሚባለው በመረጃ ውስጥ ያሉት ቁጥሮች ድምር ለቁጥሮች
ብዛት በማካፈል ነው፡፡
• መሃል ከፋይ ዋጋ የተሰጠውን መረጃ በቅደም ተከተል ከትንሽ ወደ ትልቅ
ወይም ከትልቅ ወደ ትንሽ በቅደም ተከተል በማስቀመጥ በመሃል ላይ የሚገኝ
ቁጥር ነው፡፡
• የአንድ መረጃ ተደጋጋሚ ዋጋ በተሰጠው ዳታ ውስጥ ይበልጥ የተደጋገመ
ቁጥር ነው፡፡ የተደጋጋሚ ዋጋ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል፡፡
• ቁም ግራፍ ሬክታንግላዊ ቁም ቻርቶች ሆነው ርዝመቱ ከሚወክላቸው ዋጋ
ጋር ወደር ያለው ነው፡፡ ቁም ግራፍ በምንመሰርትበት ጊዜ ከዚህ በታች
የተሰጡትን ነጥቦች በትኩረት እንመለከታቸዋለን፡፡
ሀ. ሬክታንግላዊ ቁሞቹ እኩል የሆነ ወርድ አላቸው፡፡
ለ. በቁሞቹ መሃከል ያለው ርቀት እኩል ነው፡፡
• ፓይ ቻርት አንዳንዴ ክብ ግራፍ ይባላል፡፡

185
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፍ 6 የክለሳ መልመጃ

1. በአንድ ወር ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን ከአንድ ከመሸጫ መጋዘን የተሸጠ


ስንዴ በኩንታል ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሠንጠረዥ ተቀምጧል፡፡
13 14 16 15 16 16 13 14 16 13
12 13 12 13 15 6 13 14 6 13
16 16 16 12 14 15 14 16 14 13

የዚህ መረጃ ድግግሞሽ ሠንጠረዥ በመመስረት አማካይ ዋጋ፣ መሃል ከፋይ


ዋጋ እና ተደጋጋሚ ዋጋ ስላ/ይ፡፡
2. የጉልበት ሥራ ለሚሰሩ 20 ሰዎች የቀን ውሎ አበል በብር ከዚህ በታች
ተመልክቷል፡፡
200 250 250 300 200 250 250 350 400 300
200 400 350 250 350 300 400 250 350 300

የጭረት መስመር ሠንጠረዥ በመስራት አማካይ ውሎ አበል፣ መሃል


ከፋይ ውሎ አበል እና ተደጋጋሚ ውሎ አበልን አሰላ/ዩ፡፡
3. የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በ8 የትምህርት ዓይነቶች ፈተና ወሰዱ፡፡
ተማሪዎቹ በአንደኛ ሴምስቴር ከመቶ ያገኙት ውጤት ከዚህ በታች
ተሰጥቷል
ተማሪ I: 92፣ 91፣ 98፣ 82፣ 85፣ 89፣ 90፣ 93
ተማሪ II: 59፣ 79፣ 62፣ 70፣ 86፣ 93፣ 63፣ 78
ተማሪ III: 78፣98፣99፣92፣86፣90፣91፣94
ሀ. የእነዚህን ተማሪዎች አማካይ ውጤት ፈልግ/ጊ፡፡
ለ. ለእያንዳንዱ ተማሪ መሃል ከፋይ ውጤት እና ተደጋጋሚ ውጤት
ፈልግ/ጊ፡፡

186
ሒሳብ 6ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሐ. የትኛው ተማሪ ትልቅ አማካይ ውጤት አገኘ/ች?


መ. የትኛው/ዋ ተማሪ ትንሽ አማካይ ውጤት አገኘ/ች?
ሠ. የትኛው/ዋ ተማሪ ብዙ የሚመሳሰል ውጤት አገኘ/ች?
4. ከዚህ በታች ለተሰጠው መረጃ አማካይ ዋጋ፣ መሃል ከፋይ ዋጋ እና
ተደጋጋሚ ዋጋ ፈልግ/ጊ፡፡፡
ሀ. 79፣ 77፣ 75፣ 70፣ 68፣ 66፣ 61፣ 56፣ 47፣ 45፣ 42፣ 38
ለ. 90፣ 91፣ 90፣ 85፣ 85፣ 82፣ 80፣ 76፣ 70፣ 65፣ 63
ሐ. 37፣ 37፣ 35፣ 34፣ 30፣ 28፣ 26፣ 26፣ 24፣ 22፣ 20፣ 17፣ 32
5. ከዚህ በታች የተሰጠው ሠንጠረዥ የአንድን ትምህርት ቤት ተማሪዎች
ብዛት በትምህርት ዘመን 2006 —2013 በየአመቱ የተመዘገቡትን ያሳያል፡፡
አመት 2006 2007 2008 2009 2010 2011 2012 201

የተማሪዎች 3
190
1050 1150 1300 1450 1500 1650 1700
ብዛት 0

ይህን መረጃ በቁም ግራፍ አሳይ/ዪ፡፡


6. አንድ የዱቄት ፋብሪካ በአንድ አመት ውስጥ ያመረተውን የስንዴ ዱቄት
ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ለሽያጭ ለ 5 ዞኖች አከፋፈለ፡፡
ዞን ሀ ለ ሐ መ ሠ
የዱቄት ብዛት 13,750 8,750 11,250 10,000 6,250
በኩንታል
ሀ. ከዚህ በላይ ለተሰጠው ዳታ ክብ ግራፍ ሥራ/ሪ፡፡
ለ. ለየትኛው ዞን ብዘት ያለው የስንዴ ዱቄት በኩንታል ተካፋፈለ?
ሐ. ለየትኛው ዞን አነስተኛ ብዛት ያለው የሰንዴ ዱቄት ተከፋፈለ?
መ. ይህ ፋብሪካ በአማካይ በአንድ አመት ውስጥ ለዘኖቹ ምን ያህል
የስንዴ ዱቄት በኩንታል አከፋፈለ?

187

You might also like