You are on page 1of 23

ልጁን

አንሱ፣
ምጡን እርሱ።

%
ወልደው ሳያበቁ
በሰው ልጅ አይስቁ።

%
ሥራን ሲፈልጉ፣
ጉልበትን አያባልጉ።

%
አህያን ሥጋ ጭነህ፣
ጅብን ንዳ ብለህ።

%
አንዱ ባንዱ ሲስቅ፣
ጀንበር ጥልቅ፤

%
የአፍ ዘመድ፣
ከገበያም አይገድ።

%
የጉም ሌባ!
ጉሙ ሲለቅ የት ትገባ?
%
ባለጌና የቆቅ አውራ፣
ያለበትን ያወራ።

%
የበደለ ይካስ፣
የቀማ ይመልስ።

%
የተደረገላትን ረድኤት ትታ፣
የተሠራላትን ውለታ ዘንግታ፣
%
ወደሽ ከተደፋሽ
ቢረግጡሽ አይክፋሽ።

%
የኃጥኡ ዳፋ፣
ጻድቁን ያዳፋ።

%
ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል፣
ስስታም ሲበላ ይታነቃል።

%
ጊዜ አለው ለሰው፣
ዕድሜ ካላነሰው።

%
በምክራቸው ተጎዱበት፣
በሰይፋቸው ተመቱበት።

%
ባፍ ይጠፉ፣
በለፈለፉ።

%
ብናስር እናጠብቃለን፣
ብንመታም እናደቃለን።

%
ውሸት ዓለምን ዞሮ፣ በመጨረሻ ወደ ዋሾው ይመለሳል።

-- የአባቶች ምሣሌ
%
ሥነ ጹሁፍ ሁለት ጊዜ የሚነበብ ኪነጥበብ ሲሆን ጋዜጣ ግን አንድ ጊዜ ብቻ ታይቶ የሚታለፍ ነው።

-- ሳይረል ኮኖሊይ
%
ታሪክ የሌሊት ቅዥት ስለሆነ በእርሱ ቀስቃሽነት እነቃለሁ።

-- ጄምስ ጆይስ
%
ታማኝነት እንደትሮይ የምስጢር መሣሪያ ነው።

-- ሎርድ ኪኒዮር
%
ማየቱን ታያለህ፣ ግን አትገነዘብም

-- ሰር አርተር ዶየል
%
በተሰጥኦ የምንጠቀመው ከመቶው በአንዱ ብቻ ነው።
በብርቱ ጥረት ግን ዘጠና ዘጠኝ ከመቶውን መሸፈን እንችላለን።

-- ቶማስ ኤልባ ኤዲሲን


%
በሚጠፋ ገንዘብ፣ የሚሞት ከብት ይገዛበታል።

%
እንኳንስ እናቴ ሞታ፣ እንዲሁም ለቅሶ ለቅሶ ይለኛል።

%
ጆሮ ለባለቤቱ ባዕድ ነው።

%
ድል አድራጊነት የሚገኘው ገምቶ ከመነሳት ከፍላጐትና እነዚህን በተግባር
ለማሣየት ከሚደረገው የአሠራር ስልት ነው።

-- ቶማስ ኤልባ ኤዲሲን


%
ጊዜን ከምንም ነገር አስበልጠን እንፈልገዋለን። ነግር ግን በአግባቡ ሣይሆን
እጅግ በከፋ ሁኔታ እንጠቀምበታለን።

-- ዊልያም ፔን
%
ዘለሰኛ፦
ጐበዝና ፈሪ፣ ሁለት መልክ ይዘሽ፤
ጥርስሽ ሰው ገደለ ከንፈርሽ ሲሸሽ።

%
ዘለሰኛ፦
ያባቴ ነው ብሎ፣ ይፋጃል በርበሬ፤

ያባቱን ያጣ ሰው፣ አይሆንም ወይ አውሬ?


%
ዘለሰኛ፦
እኔ አላውቅም እንጂ፣ ጥዶ መጋገር፤
አንቺስ እህል እህል፣ ብለሽን ነበር።

%
ዘለሰኛ፦
ለኔ የት ታወቀኝ፣ ወዳጄስ ጠላቴ፤
እንዲያው ኡኡ፣ ሲባል ሁሉም መጡ ደጄ።

%
መዲና፦
የማናውቀውን ሌብነት፣
ልንሠርቅ ገብተን ከሰው ቤት፣
ይቅርብህ ጓዴ እንውጣ፣
የሚጠብቀን መጣ።

%
መዲና፦
ጠላ ጠምቄ ለሰንበት፣
አንስቼው ነበር በቡይት፣
ዞሬ ባየው አጣሁት፣

ሰውን ጠጣው መሬት?


%
የምሕረት ዝናብ
ለዚህ ሕዝብ እዘኑ፣ ባፍሪካ ቀንድ ላለው፤

ከቶ መቼ ይሆን፣ ኑሮን የሚኖረው?


መኪና መንዳቱ፣ ሽክ ማለቱ ቀርቶ፤

መቼ ነው የሚያድረው «በቀን ሦስቴ» በልቶ?


አድጎ የሚታየው እንደ ዘመኑ ሰው፤

ከርዳታ ሚወጣው ጎጆ ሚቀልሰው?


መቼስ ነው መንፈሱ፣ የሚላበስ ደስታ፤

ፈውስን የሚያገኘው፣ ድኖ ከበሽታ?


ሁላችን ተጎዳን፣ ጉስቁልናው ከፋ፤
ክፋይ አየለና፣ ድህነት ተስፋፋ።
በግርግር ሁከት፣ ዕድሜያችን ነጎደ፤
ለመጪውም ትውልድ ፣ ጦሳችን ወረደ።
በፖለቲካ ጦስ፣ በጥቂቶሽ ሴራ፤

ሞልቶ የተረፈን፣ ቸነፈር... መከራ።


እስከመቼ ድረስ፣ እንኑር በሰቀቀን?
ኧረ እናንተ ሆዬ፣ ናፈቀን፣ ጥሩ ቀን።
አንዳችን ከአንዳችን፣ ሀቀን ተሰራርቀን፤
ልባችን ሳያጣው፣ እውነትን ደብቀን።
እፎይ ለማለቱ፣ አንዴም ሳንታደል

ሁልጊዜ በሀዘን፣ ሁልጊዜ በበደል?


ዝንተ ዓለም እንኑር፣ በሀዘን ሰቆቃ?
ተለመኑ ሰዎች፣ እባካችሁ ይብቃ።

የጎሪጥ ተያይቶስ፣ እንዴት ይዘለቃል?


መሪር ነው እንደኔ፣ መኖር ያስጨንቃል።
ተጠላልፈን ኑሮን፣ ከምናወሳስብ፤
ተው ስለ ሥራ፣ ስለ ዕድገት እናስብ።
ተንኮል መተብተቡ፣ እባካችሁ ይቅር፤
በፍትህ እንዳኝ፣ ይግዛን እንጂ ፍቅር
ስንቀብር ከመሞት፣ መጠፋፊያ እንጂ፤
መልካሙን ቀን አይተን፣ ኖረን እንሙት እንጂ።
ዕድሜ ልካችንን፣ ዘወትር ስንዋጋ፤
ከቶ ሳናጣጥም፣ የተፈጥሮን ፀጋ።
አድጎ ለወግ መድረስ፣ መሳምን ልጅ ወልዶ፣

እንለፍ ሳናየው፣ ወይ ነዶ! ወይ ነዶ!


በዓለም ላይ እየኖርን፣ እንድናገኝ ትርጉም፤
መች ይጠራ ይሆን፣ ይህ የአሣራችን ጉም።
ዳግም ተጠየቁ፣ ፖለቲከኞቹ፤
በሕዝብ ስም ለሕዝብ፣ ሕዝብን አማሾቹ።
በሥርዓት ካልኖሩ፣ በውል ተመካክሮ፤
ካልተሸናነፉ፣ ብዙ ተከራክሮ፤

ይጣፍጣል ሕይወት? እንዲህ ነወይ ኑሮ?


እሾሁ ይነቀል፣ እግዜርም በል ፍረድ፣
መናቆር ይወገድ፣ ባገር ላይ ዕርቅ ይውረድ።

አቅቶናል እኛስ... እባክህን አምላክ፣


ፍቅርን የሚያበቅል፣ የምህረት ዝናብ ላክ!!
-- ማንልበል ከ(አ/አ)
%
ጀምበር አትጠልቅም

ይነጋል... ትወጣለች ፀሐይ


ይረፍዳል... ትገርራለች ፀሐይ
ይመሻል... ትጠልቃለች ፀሐይ፤
ነግቶ እስከምትወጣ...፤
ይብላኝ ለበደለ፣ የኑሮም ጣም ላጣ፤
እጁን እንደዘበት፣ ለበደል ሰንዝረዋት፤
ልቦና ጥበቡን ኃይልና ጉልበቱን፣
ግፍ እየዘራባት፤
ሞቱ ሞት አብቅሎ፣
ግፉ ግፍን ወልዶ፣
ራሱን ሲጥለው፣ ታጋይ በሌለበት
ጀምበር አትጠልቅም፣ ቀኗ የመጣች ለት።

-- ከመልካም መዓዛ
%
ሠይጣን ሠለጠነ

ሠይጣን ሠለጠነ- ቀንዶቹ ነቃቅሎ፣


ጭራውንም ቆርጦ፣

ከሰው ልጆች ጋራ- አንድነት ተቀምጦ።


ሊኖር ነው ጨምቶ፣

ከሰው ልጆች ጋራ- ሊጋባ ተጫጭቶ።


ሠይጣን ሠለጠነ፣
ዘመናዊ ሆነ።

ፊደል ቆጠረና- ዳዊትም ደገመ፣


በስመ አብ ብሎ- ውዳሴ ማርያምን
መልካ መልኩን ሁሉ- አጠና ፈጠመ።
ከዚህም በኋላ- ጾ ጸሎት ጀመረ፣
በመጨረሻውም- አቡን ተክሌ አጥምቀው
ክርስትና አነሱት- ግና ተቸገረ።
እንዲያው በየዕለቱ፣

ጨርሶ አላወቀም- ለማን እንደሆነ ፆምና ፀሎቱ።


ቢጨንቀው ጊዜና- ቆየና ሰንብቶ፣
ክርስቲያን ሆነ- አንድ ሰው አግኝቶ።
ተወዳጀውና ብሶቱን ነገረው- ሁሉንም ዘርዝሮ፣
በጣፈጠ ቋንቋ- በእውነት አሣምሮ።
«አትቸገር» አለው ክርስቲያን ወዳጁ
አፅናናው መልሶ፣

ሰይጣኑ ካሰበው- አለመጠን ብሶ።


«ይህስ ቀላልነገር- ችግርም የለው፣
እንደኛው ክርስቲያን- ሆንክ ማለት ነው።
-- «እስኪ ተጠየቁ»
ዮሐንስ አድማሱ፣
በሚል ርዕስ ከጻፈው መጽሐፍ የተወሰደ።

%
ግዛኝ ግዛኝ ብለው ሊሸጠኝ አሰበ።

%
በሬ ካራጁ ይውላል።

%
አትረፍ ያለው መነኩሴ መቁጠሪያውን ሸጦ ፍየል ይገዛል።
%
ጊዜ መስታዎት ነው

«ከጨርቁ ምን አለን» ባለ አንደበታቸው፤


«የአንድነት ዓርማችን» ሲሉ ሰማናቸው፤
ይመስገን ፈጣሪ፣ ቸር ላናገራቸው።

«ወራሪው ምኒልክ» ባለው ልሳናቸው፤


«ያለሞጣም ምኒልክ» ሲሉ አዳመጥናቸው፤
ፈጣሪ ይመስገን ሀቁን ላሳያቸው።

«የመቶ ዓመት ብቻ፣ ታሪክ ሆኖ ሳለ፤


የሦስት ሺ ዓመታት ታሪክ እየሣለ፤

የነፍጠኛው ሥርዓት፣ ሲያጭበረብር ኖረ»፤


ተብሎ በስድብ፣ እንዳልተነገረ፤

«የሦስት ሺ ዓመታት ፣ አኩሪ ገድላችን፣


ዛሬም ይደገማል በአንድነት ክንዳችን።»
ብለው ሲናገሩ፣ በአንክሮ አዳምጠናል፤
ከአንድ አፍ ሁለት ምላስ፣ በሂደት አይተናል።
ድንገት በቅሎ ሲገኝ፣ የአገር ባላጋራ፣
ዜጐች ለመወጣት፣የትውልድ ወር ተራ፤
በቁጭት ሲያሰሙ፣ ሽለላ ፉከራ፤

«የጀብደኞች መዝሙር» ሲሉ እንዳልነበሩ፤


ጊዜ መስተዎት ነው አየን ሲፎክሩ።
በገሀድ ብናይም፣ እንዲህ ሲለወጡ፤
ብሔራዊ እርቁን፣ የሚያበሻቅጡ፤
ለሆድ አሜን ያሉ፣ አሁንም አልታጡ።
መንታ ምላስ ይዘው፣ ከሚያተራምሱ፤
ሲሸሽ ከሚውለው፣ ሊደበቅ ከራሱ፤
ለኛ ሠናይ ነበር፣ ቢኖረን ቆይታ፤
መላ ውሎአቸውን፣ ለማየት በእርጋታ፤
ቀን ያወገዙትን፣ ሲያወድሱ ማታ።

-- ከእናት አገር ልጆች


%
ዝሆን ተሰብስቦ ሲጫወት ገበጣ፣
የኢትዮጵያ ጀግና ጅም አፍራሹ መጣ።

%
ጐበዝ ይሙት ፈሪ ይኑር ቢሻው፣
አተላ መሸከም ይችላል ትከሻው።

%
ከቶ ለምን ይሆን ፈሪ ማጦንጦኑ፣
ቅጠል አይበጠስ ካልደረሰ ቀኑ።

%
ቢያዝኑለት ያለቅስ፣
ቢስሙት ይነክስ።

%
በወሰኑት ፍልሚያ ተረቱ፣
በቆረጡት አርጩሜ ተመቱ።

%
በቅሎ እንዳሰገሩት፣
ሎሌ እንደነገሩት።

%
በተለሙ ያርሷል፣
በጀመሩ ይጨርሷል።

%
ባጭር ታጥቆ፣
ጋሻ ነጥቆ፣
ዘገር ነቅንቆ፣
ይዋጓል አጥብቆ።

%
ግፈኛማ ባሪያ፣ ምን ነፅነት አለው፤
የሰው ልጅ ነፃነት እልቡ ውስጥ ነው።
ዋና አውቃለሁ ብዬ እንዲያ ስፎክር፣
ሀገሬ ምን ይለኝ ጠልቄ ብቀር?
%
ሁሉ በሽተኛ ሁሉ ራሴን ባይ?
በቤታችን ደህና መጥፋቱ ነው ወይ?
-- ከብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ አማርኛ ቅኔ የተወሰደ
%
እሾህ አጣሪውን፣
ነገር ፈጣሪውን።

%
ማሩን አመረረ፣
ወተቱን አጠቆረ።

%
ግፍ ሲናኝ
ኩበት ሰጥሞ ድንጋይ ይዋኝ።

%
ከመጠን በላይ በመሥራቱ የሞተ ሰው መኖሩን አላውቅም። ነገር ግን ከጭንቀት ብዛት ብዙ ሰዎች ሞተዋል።

-- ዶ/ር ቻርለስ ማዩ
%
ከምንም ነገር የበለጠ ደስታ የሚሰጠን የምንመቀኛቸው ሰዎች ችግር ላይ ወድቀው ማየት ነው።

-- የጀርመኖች ምሣሌ።
%
የነፃነቶች እናት የሆነው የፕሬስ ነፃነት ቁጥጥርና እግድ የሚደረግበት በፈላጭ ቆራጭ መንግሥት ብቻ ነው።

-- ጆርጅ ማስን
%
ያደግሁባት መሬት፣
ማነው ሜዳ ናት ያላት፣
ልናገር እኔ የማውቃት፣
አገሬ ጋራ ናት።

%
ተፈረደብህ ብዙ ዓመት
በራስሕ ጥፋት እሥራት፣
የኔ ወንጀል ቢቀልም፣
በወሬ አልፈታም።

%
ንጉሥ የሰጡኝ ታላቅ ዕቃ፣
ላገር ለምድር የሚበቃ፣
አድጦኝ ወድቆ እስኪሰበር፣

ስይዘው ቀሎኝ ነበር!


%
መጠራጠር
ያደርሣል ከቁም ነገር።

%
አፍ ቀለም ሲነዳ፣
ልብ ዕቃ ያሰናዳ።

%
ካልቀመሰ፣
የደገመው ባሰ።

%
የአፍ ዘመድ
ከገበያም አይገድ።

%
የኑሮህን ዕቅድ አስቀድመህ ንደፍ።
እንግዲህ በዚያ መሠረት ላይ ነው ሕይወትህን የምትመራ።

-- ማርክ ትዌይን
%
በአጋጣሚ ወም በእድል ካልሆነ በስተቀር በምድር ላይ የተሟላ ሰላም የለም።

-- ጄኔራል ዳግላስ ማካርተር።


%
እደር ያሉት እንግዳ፣
እራቱ ፍሪዳ።
%
የተቀማጭ
ምላሱ ምላጭ።

%
ማዕረገ ቢስ፣
እራቱ ገሚስ።

%
በአፍ ይጠፉ፣
በለፈለፉ።

%
በሬ ያርሣል፣
አህያ ምርቱን ያፍሣል።

%
አስቀድሞ የተናገረን ሰው ይጠላዋል፣
አስቀድሞ ያሸተን ወፍ ይበላዋል።

%
ሥራን ሲፈልጉ፣
ጉልበትን አያባልጉ።

%
ከሰዎች መጥፎና መልካም ነገር መቀሰም ይቻላል። የተሻለውን መርጦ መያዝ ግን የኔ ፋንታ ነው።

%
ምንም ሣይኖራቸው ሁሉንም አለን ብለው ከሚኮሩና ባዶ ሆነው እራሳቸውን ምሉዕ አድርገው ከሚገምቱ ሰዎች ጋር
መኖር ሰለቸኝ።
አልበርት ኦሸዋይዘር

%
የፍትሕ ማስተባበር ተግባር የመንግሥት ጠንካራ ዋልታ ነው

-- ጆርጅ ዋሽንግተን
%
እግዚአብሔር ትክክለኛ መሆኑን ሳሰላስል ለአገሬ በጣም እሰጋለሁ

-- ቶማስ ጃፈርሰን
%
ረሀብተኛ ውሻን አንስተህ ሀብታም ካደረግኸው አይነክስህም። በሰውና በውሻ መካከል ያለው ልዩነት ይኸው ነው።

-- ማርክ ትዌይን
%
እምነትና ክብርን በማዋረድ፣ ዕውነትንም በመጣል የሚገኘው ከፍተኛ ማዕረግ ለባሹን የማያሞቅ ነጠላ ነገር ነው።

-- ጆን ቴይለር
%
ጋዜጠኛ ሊከለልበት የሚገባው ብቸኛ ጥግ ቢኖር አንድ ብቻ ነው። እርሱም «የዕውነት ጥግ»
-- ሪዚያ ባቲ (የፓኪስታን ጋዜጠኛ)
%
እንደሰው ያለ አህያ ባላውቅም፤ እንደ አህያ የሚያስቡ ሰዎች ግን አጋጥመውኛል።

-- ሄንሪክ ሄደን
%
መለመን የለመደ ምላስ፣
በሕልሙ አቆማዳ ይዋስ።

%
ከተመቱ ማንጠርጠር፣
ጅብ ከሄደ አጥር ማጠር።

%
ቂል አይሙት፣
እንዲያጫውት።

%
ቅቤና ቅልጥም
ወዴት ግጥምጥም።

%
ሣይናገር ብልሀቱ፣
ሣይታረድ ስባቱ።

%
የኃጥኡ ዳፋ፣
ጻድቁን ያዳፋ።
%
አገር ያለ ምክር፣
ቤት ያለማገር።

%
እራትና መብራት፣
አማትና ምራት።

%
የሰው እምቢተኛነት
እሣትና ነፋስ መሬትና ሰማይ፣
አየርና ውሃ በቀልትና ድንጋይ፣
እነዚህ ፍጥረቶች እግዜር የሠራቸው፣
ሳያወላውሉ ሁሉም በባሕርያቸው፣
ጠባይ እንለውጥ ታከተን ሣይሉ፣
የተሰጣቸውን ሥራ ይሠራሉ።
ደግሞ ስናስተውል በመካከላቸው፣
መዋጋት፣ መጋደል፣ ጠብም የለባቸው።
እሣት ያቃጥላል፣ ነፋስም ይነፍሳ፣
በቀልት ይመግባል ውሃውም ያርሣል፣
መሬት ስትሸከም ጠፈር ይጋርዳል፣
እግዜር ያዘዘውን ቃሉን ሲፈፅሙ፣
ለማ፣ ጠፋ፣ ብለው እያጉረመረሙ።
ተሰብረው ቢወድቁ ተቃጥለው ቢነዱ፣
ልፋታቸው በዝቶ ቢደክሙ ቢጎዱ፣
ታዝዘው ይኖራሉ ጥንት እንደተሠሩ፣
ከፈጣሪ ጋራ ሣይከራከሩ።
ሕጉን በመከተል አምኖ እንዳይታዘዝ፣ይይጎትቶ ሊያመጣ በራሱ ላይ መዘዝ፣
ይህ የሰው ልጅ ብቻ አርፎ እንዳይገዛ፣

ምነው ከእግዜር ጋራ ክርክር አበዛ?


-- «ሰንደቅ ዓላማችን»
አቶ ከበደ ሚካኤል
ጋዜጣ ላይ መስከረም 6 ቀን 1935 ዓ.ም የወጣ
%
ለቀሣሚሽ ኑሪ

ፅጌረዳ አምሣል- ድንግል ነው ተፈጥሮሽ፣


ውበትሽን ሲያዩ- እጅግ ታጓጊያለሽ፣
የአይን ማረፊያ ነው- ምድራዊ አቀማመጥሽ፣
የመንፈስ እርካታ- የደስታ ምንጭ ነሽ።
ባዕዳን በሙሉ- አተኩረውባሻል፣
ተፈጥሮሽ ማርኮአቸው- በጣም ይመኙሻል፣
ፀዳል ውበትሽን- በረከትሽን አይተው፣
የአበራክሽ ክፋይ- ከጠላትሽ አድረው፣
አንቺ የውቦች ንግሥት- ፅጌረዳ አበባ፣
ሊቆርጥሽ ሊቀጥፍሽ- ሞልቷል የሚያደባ።
ቀሣሚሽ አልሚ ነው- ለእሱ ተሞሸሪ፣
ቀጣፊሽ አጥፊ ነው- ፀጋሽን ሰውሪ።
ፅጌረዳ! ደግሜ ልንገርሽ- ወዳጅሽን መርምሪ፣
ቀጣፊሽን ጥለሽ- ለቀሣሚሽ ኑሪ።
-- ሱልጣን ነጋሽ-መምህር
%
ፍርሃት የኛ ጌታ

ፍርሐት የገዛን- እና የፍርሐት ሀገር ዜጋ


በፍርሐት ብቻ መቼም- መውጫ መግቢያችን የተዘጋ።
ያለንበት ቤቱ ሁሉ- መላው አየሩ ተነፈገ፣
በውስጡም ያለነው እኛ- ሰውነታችን ጠወለገ።
ተው ልቀቀን ተው እባክህ- እንደምን እንሁን ያንተ ዜጋ፣
እስኪ ሙት እስኪ ጥፋ- ሕይወታችንን አትዝጋ።
እስከ አሁን ድረስ እስከ ዛሬ- እንዲያው ተክዘን ብናየው፣
ኧረ መቼ ነው ሰዓቱ?- ይህ ያንተ ጊዜ የሚያልፈው?
እስኪ ተጠየቅ እንጠይቅህ- ፍርሐት የኛ ጌታ፣
እኛን ብቻ ነው ወይስ አሉ- ያደረግሃቸው አውታታ?
ኧረ ምንድነ ነው ምሥጢሩ- ያገዛዝህ ውል መሠረቱ?
ከቶ ምንድን ነው ብልጠትህ- ይህ ሁሉ ፍጡር መራቆቱ?
ብርታት ድፍረትን ጥሎ- ወኔ መቁረጥን አሽቀንጥሮ፣
ላንተ ብቻ እንዲህ መገዛቱ- ዕራቁቱን ሆኖ ተዘርዝሮ።
-- «እስኪ ተጠየቁ»
ከተባለው ከዮሐንስ አድማሱ መጽሐፍ የተወሰደ

%
አንዲቱን ቀዘባ
እንደ ሐምሌ ወራት ፊቷ ጭፍና ለብሶ፣
እንደ መኸር ድርቆሽ ልብሷ ተልከስክሶ፣
አየኋት ለየኋት እንዲቱን ቀዘባ፣
ዘንጠፍ ዘና ብላ እንደ መስክ አበባ።
ፊቷ ጭፍና ቢለብስ፣
ልብሷ ቢልከሰከስ፣
ግና ሥግው ሆኖ ውበት ተደብቆ፣
ታየኝ ተገለጠ ድንገት አሸብርቆ።
ልብሷ የባላገር አየረዋ ገጠር፣
ኩለንታዊ ውበት ይዛ የምትኖር፣
አየኋት ከመስኩ ወደ ገጠር ሄጄ፣
ተፈጥሮን ስፈልግ ተፈጥሮን ወድጄ፣
ነባይ አባይ ማለት በተፈጥሮ ቤት፣
አንዲቱ ቀዘባ አክሊል የውበት፣
ያልተዳደፈችው በሰው ሠራሽ ፈሊጥ ከንቱ ፈንደለላ፣
አየኋት ለየኋት የገጠረዋን ስንድቅ የገጠረዋን አፍላ።

-- «እስኪ ተጠየቁ»
ከሚለው ከዮሐንስ አድማሱ ግጥሞች የተወሰደ

ነሐሴ 1945 ዓ.ም


%
ይታየኛል
አንድ ነገር አየሁ፣ ተኝቼ በሕልሜ፤
ልንገርሽ እህቴ፣ ልንገርህ ወንድሜ።
መለያየት ይቅር፤
አንድነት ይጠንክር።
የሚል ድምፅ ሰማሁኝ፤
ተመስገን እያለሁኝ።
ብሔር ብሔረሰብ፣ ጐሳና ነገዶች፣
ባንድ ላይ ተነስተው፣ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች።
ያለፈው ይበቃ፣ ብለው ተመካክረው፤
ሲነሱ አየኋቸው፣ እጅና ጓንት ሆነው።
ሐሳብ ፍላጐቴ፣ ሕልምና ምኞቴ ይታየኛል ጐልቶ፤
በዘር በሃይማኖት አጉል ተለያይቶ፤
የሚለው ወገኔ፣ ሁሉም ልብ ገዝቶ፤
እኔ ያልኩት ይሁን፣ እኔን ብቻ ስሙኝም ማለቱን እረስቶ፤
ቂም በቀል ጥላቻ፣ ማስፋፋቱን ትቶ፤
ለሰላም ለፍቅር፣ ልባችን ተከፍቶ፤
ወገን ለወገኑ፣ ትህትና አሳይቶ፤
ያንድነትን ፅዋ፣ ሁሉም ተጐንጭቶ፤
በመልካም ሥራችን፣ እግዜር ተደስቶ፤
አምላክ በረዴቱ፣ እጆቹን ዘርግቶ፤
ባርኮና ቀድሶ፣ ሁላችን ነካክቶ፤
ያኮረፈ ሥቆ፣ ያዘነ ተፅናንቶ፤
የተቆጣ በርዶ፣ የጠበበ ሰፍቶ፤
መንግሥትም ለሰላም፣ እጆቹን ዘርግቶ፤
ሁኡልም ሰው በዘሩ፤ በታሪኩ ኮርቶ፤
ፀላየ ሠናይት፣ ከኛ እርቆ ጠፍቶ፤
ዳግም ላይመለስ፣ ምሎ ተገዝቶ፤
የውጪ ከፋፋይ፣ ከምድረዋ ላይ ጠፍቶ፤
ዳግም ላይመለስ፣ ምሎ ተገዝቶ፤
የውጬ ከፋፋይ፣ ከምድረዋ ላይ ጠፍቶ፤
ቅስሙ ተሰባብሮ፣ ካገራችን ወጥቶ፤
ርሃብ ድንቁርና፣ የርስ በርስ ጦርነት፣ ከኢትዮጵያ ጠፍቶ፤
ሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ ግብርና ተስፋፍቶ፤
ምርት ተትረፍርፎ በጐተራ ሞልቶ፤
መላው ኢትዮጵያዊ፣ እስቲጠግብ በልቶ፤
እግሩ ካደረሰው፣ በሰላም ተኝቶ፤
ክልል ሳይግደው፣ ከፈለግው ሠርቶ፤
ያለምንም ሥጋት፣ ኮርቶና ተዝናንቶ፤
ልቡ ካፈቀራት፣ ካሻው ጋር ተጋብቶ፤
ልጅ ወልዶ አሳድጐ፣ ቤተሰብ መስርቶ፤
አገር የሚረከብ፣ ትውልድን ተክቶ።

ኮርቶ 'ሚኖርባት ቅድስት ኢትዮጵያ፤


ገና ታበራለች፣ ደምቃ ትታያለች በዓለም ገበያ!!
-- ዋሲ ታደሰ
%
ቁጭ ብሎ መስቀል
ሰነፍ እረኛና ወያኔ አንድ ናቸው፤
ከሄደ በኋላ አምልጦ ከእጃቸው፤
ከሩቅ ለመመለስ ያልቃል ጉልበታቸው።
ቁጭ ብለው እንዳይሆን የሰቀሉት ዕቃ፤
ተነስተው ለማውረድ በቀን በጨረቃ።
አይቀሬ መሆኑን አስቸጋሪነቱ፣
አበው ነግረውናል ከጥንት ከጠዋቱ።
እንዲህ ተስማሚ ለዚህ ተምሳሌት፤
ኤርትራን እንጥቀስ የእኛን ጐረቤት።

ኋላ 'ሚመጣውን ችግር ሳይገምቱ፣


ተጨባጩን ነገር ሳይመለከቱ፣
እንደሰንበት ፀዲቅ እንደ ዳቦ ገምሰው፣
የወያኔ አለቆች ኤርትራን ለግሰው።
የኢትዮጵያን ሠፊ ሕዝብ ፈቃድ ሳይጠይቁ፣
በራሳቸው ሥልጣን በፊርማ ሲያፀድቁ።
ተነስተው ለማውረድ የማይቻላቸው፣
ቁጭ ብሎ ዕቃ መስቀል ነበር ተግባራቸው።
ያም ድኹር አሠራር ሰቆቃን አርግዞ፣
መጣ ወደ ሕዝቡ ጦርነትን ይዞ።
ችግሩን ለብቻ መፍታት ሲያቅታቸው፣
የድረሱልን ድምፅ መጣ ጩኸታቸው፣
ሕዝቡን እንደቁጢት በጐሣ በጣጥሰው፣
አንዱን ከሌላው ጋር እንደ ውሻ አናክሰው።
ለመኖር ያቀዱት የሸረቡት ሴራ፣
ጐልቶ ቢታየውም ቂሙ እንደተራራ፣
ስለማይታሰብ ኩርፊያ በሀገሩ።
የማይሣነው ሕዝብ ተነስቷል ለክብሩ።
ከዚያም ጋር ጐን ለጐን ለአገር አቀፍ ዕርቁ፣
የማሣነው ሕዝብ ጠበቅ ብሏል ትጥቁ።

-- ከአባ ኮስትር መንደር


%
«ዋሾዎች»
ዕውቅ ሠዐሊዎች፣
የፈጠራ፣ የቅርጻቅርጽ ጠበብቶች፣
ድንቅ የኪነት ሰዎች፣
የሕልም ዓለም ፍጡሮች።
ያልሳቀ ሰው አስቃችሁ፣
አለቅጥ አስፈንድቃችሁ፣
ያላዘነን አሳዝናችሁ፣

«በውሸት» አስለቅሳችሁ።
ደካማውን አጎልብታችሁ፣
ጀግናውን ፈሪ አርጋችሁ፣
የውሸት ጨዋታ መጫወታችሁ፣
ሁላችሁም ዋሾዎች ናችሁ።
ቀለም ተመቸን ብላችሁ፣
ዓይንን በውበት አታልላችሁ፣
ቋንቋ እናውቃለን ብላችሁ፣
በቃላት ተጨዋውታችሁ።
ተደራሲን በምናብ አማልላችሁ፣
የሌለ ዓለም በመፍጠራችሁ፣
ሁላችሁም ዋሾዎች ናችሁ።
የታለ ታዲያ በእውን ያ ውብ ዓላማችሁ፣
ነፃነት ለተጠሙት፣
አርነት መች አለበሳችሁ፣
ለተጨቆነውስ ክፍል፣

ደህና ቀን መች አወጣችሁ?
የመድረኩ ላይ ጀግንነት፣
የብራና ላይ ዕውቀት፣
የሸራው የወረቀት ውበት፣

የታለ በእውን የሚከሰት?


መች አለፈ ከሕልምነት፣
ከምናብ ጣጣ ቅዥትነት።

«ሊቃውንት አዋቆች ከሆናችሁማ፣


እስኪ ቀን ፍጠሩ ሳይመጣ ጨለማ፣»
ሲባለ እንደነበር ካ'በው ስንሰማ።
%
ብልህ በልቶ በሞኝ አፉን አበሰ።

%
አትቁም ያሉት ለማኝ ከሰጡት አንድ ነው።

%
የቤቴ መቃጠል ለትኋኑ በጀኝ።

%
ሆድን በጐመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል።

%
ሲሮጥ የመጣን አህያ አህያ አጥብቀህ ጫነው።
%
ሻማ እራሱ እየተቃጠለ ለሌሎች ብርሃን ይሰጣል።

%
አንበሣና አንዲት ጥጃ ጐን ለጐን ሊያርፉ ይችላሉ። ነገር ግን ጥጃዋን ጥሩ እንቅልፍ ሊወስዳት አይችልም።

-- ውዲ አለን
%
አደባባይ ቆሞ አበጀሁ ቢላችሁ፣

ይህን ባለ ጊዜ ምን ትሉታላችሁ?
%
አይጣል፣ አይጣል እያልን ስንለምነው፣

ሳናስበው ድንገት ጣለብን ምነው?


%
ተንሸራተተ አሉን እንዴት አድርጐ ይርጋ?
ከላይ በእንባ፣ በግፍ ጥንቱን የቆመ አልጋ።

%
ሃሣቡና ነገሩ፣
ጠባዬና ግብሩ።

%
ጥበብና ዕውቀትን፣
ማስተዋልና ዕውነትን፣

%
አጥር ጥሶ፣
ግድግዳ ምሶ።

%
መማለጃ እየበሉ፣
ወንድማቸውን እየበደሉ።

%
ደኃ አደግ
እሥር ቤት ነው የኛ ጽንሰት፣ የኛ ትውልድ ባጠቃላይ፣
የኛ ሕይወት የኛኑሮ፣ አስተዳደግ ከታች ከላይ፣
ሽብር እንጂ ሰላም አናውቅ፣ ጨለማ እንጂ ብርሃን አናይ፣
እስር ቤት ነው የኛ ደስታ፣ የኛ ፍቅር የኛ ሠናይ።
ልዩ ልዩ ድግሪ ድፋ፣ ዶክተር ተባል የምሁር ሠፈር፣
እስር ቤት ነው ያንተም እጣ፣ ያንተም ሕይወት፣ በኛ መንደር።
እረስ አምርት፣ ነግድ፣ ፍጠር፣ ሀብታም ተባል ባለፀጋ፣
እሥር ቤት ነው ያንተም ዕድል ሲቀየር አልጋ ባልጋ።
የትንናቱ ጅል ጦርነት በዘር ተቀየረ፣
ሶሻሊሽም ለኛ አልሆነም ዲሞክራሲም አልሠመረ።
ዛሬም የኛ መኖርያችን ዓለም በቃኝ ሆኖ ቀረ።
እናታችን ጀግና ፈሪ፣ ወላድ መሐን ናት ሾተላይ፣
አባታችን አንዱ ሆዳም፣ አንዱ ኮብላይ አንዱ አታላይ፣
እኛም ሕዝቦች ነን ሁሉን ቻይ፣ ነገር አድርባይ፣ ነገ ወላዋይ፣
የማርያም ልጅ እርዳን አንተ፤ አንዴ ውረድና ወይ ላክና ከላይ።

-- ከአያልነህ ሙላት
%
ሐኪሙ-ሐኪም አጣ
ያ-ዕውቀት መዘክር የትምህርት አባት፣
ችሎታውን ሁሉ በአይምሮው ይዞት፣
ዓለም አለቀሰ፣ በአስራት አሟሟት።

ሠላሣ- ዓመት በላይ ሲአክም ሲአስተምር፣


ብድር መላሽ ሣይኖር ተዘግቶበት በር፣
በሠራው ሆስፒታል በራሱ ሀገር፣
ዕንቁ እጁ ታሠረ የፕሮፌሰር።
የግል ጥቅም ክብርን ለሀገር ለውጦ፣
ከጐሠኞች ጋራ ፊት ለፊት ተጋፍጦ፣
እኔ ልሙት አለ ወገኑን አብልጦ።
ቀዳምዊ ሠርጀሪ አስራት ወልደየስ፣
ዕድሜ ልኩን ሁሉ ወገን ሲፈውስ፣
ምትኩን ለማፍራት ዕውቀት ለማውረስ፣

ሞት በሞት ቀደመው- ከዓላማው ሳይደርስ።


«ነፍጠኛ» ተብለህ ተከፍለህ በጐሣ፣
በሃረር፣ በባሌ፣ በአርሲ በአሶሳ፣
በግፍ የተጨረስክ አጥነትህ ይነሣ፣
ዋስ ጠበቃ ሆኖህ ለነፍሱ ሳይሳሳ፣
ለፍትህ ለነፃነት ሲወድቅ ሲነሳ፣
መጣ ተቀበሉት የኢትዮጵያ አንበሳ።
እናት ኢትዮጵያ አካልሽን ሊቆርጡ፣
ከላይና ከታች ሤራ ሲያረዋሩጡ፣
የአንድነት ጠላቶች ታሪክን ሲሸጡ፣
ያስራት ወንጀል ይህ ነው ሴራ ማጋለጡ።
ጐሰኛና ሆዳም በፈጠሩት ሴራ፣
አምስት ዓመት ሙሉ ልባቸው ሳይራራ፣

በጲላጦስ ችሎት «ኃጢያቱ» ሲወራ።


አሥራት በማለፉ ያረፉ መስሏቸው፣
ያብባል የአሥራት ደም፣
ይፈካል የአሥራት ደም ይህን ንገራቸው።

-- ከአለነ አሰፋ

You might also like