Professional Documents
Culture Documents
ከድቶሻል
ከድቶሻል ሃገሬ አድምጪልኝ ልንገርሽ
ከአፍሽ ያጎረሽው ያ ያመንሽው ልጅሽ
ሲበላ የኖረው ከማጀት ከጓዳሽ
ዛሬ ቆሞ ሲሄድ ሁሉን ነገር ሲያውቀው
ምነው እንዲህ ሆነ ማንስ አስተማረው
ማን ሲገል አይቶ ማንን ተከተለ
መቼ ተመርዞ መችሽ ደም ለመደ
ንገሪኝ ሃገሬ መች ነው ያመለጠሸ
ከጉያሽ ፈልቅቆ መች ነው የሮጠብሽ
መሬትሽ ሲታረስ ሲዘራበት ያኔ
ዘር ማለት ይሄ ነው የሰው ዘር የለውም አላልሽውም እንዴ
እናልሽ ሃገሬ
የልጅሽ ለውጡን ግዜውን ባናውቅም
የሆነው ሆነና ዛሬ አንቺን አያውቅም
ሰው መሆን እረስቶ አውሬ ሆኖልሻል
ሰው በላ አራዊት ቤተሰብ አፍርቷል
ልንገርሽ እምዬ ልጅሽ እረስቶሻል
ከአንድ ሆድ የወጣን ወንድሙን ይደፋል
እናም ባንቺ መሬት የደም ጎርፍ ይወርዳል
እናት ማቅ ለብሳለች ልጇቿም ታርደዋል
ልጅም እናት የለው እንባው ደርቆልሻል
በይ ስሚኝ ሃገሬ አድምጪኝ ልንገርሽ
ከድቶሻል ያልጅሽ
አንቺ እንደው ሃገሬ ክፉ ነው አትይም
የእናት ሆድሽ ችሎ ገፍተሸ አጥይውም
ግና እናት አለሜ ልጅሽ ማለት ይህ ነው
እውነታው ይሄ ነው የእናት ጡት ነካሽ ነው
፶/አ ዳኛቸው ፈንታሁን
ከአውቶ መካኒክ B
ዳግም ቃል ገብተናል
ይለፍ ይረግጥ ዳንኪራ
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይደሰት ይኩራራ
ለአንድነት ቃል ገብተናል በህብረት ልንሰራ
አብረን እንገስግስ ከዘመኑ ጋራ
ገበሬው ከማሳው ሁሉም በየሙያው
ወዛደሩ ሳይቀር ላፍታ ከፋብሪካው
ቀን ከሌሊት መስራት ነው የድህነት መፍቻው
በእጥረት ብቻነው ሀገር የምትለማው
የሀገር መከታ ዙሪያውን ጠባቂ
አኩሪ ጀግኖች አለን ጠላት አስጨናቂ
በየመሸገበት አንገቱን አናቂ
ሠላም የሰነቀ እድገትን ናፋቂ
እምየ ምድርሽን ጠላቶች ቢራቡ
ከሰሜን ከደቡብ ከምስራቅ ከምዕራቡ
አይሆንላቸውም ከንቱ ነው ሃሳቡ
የጀግኖች ዳር ድንበር ይፋጃል ወሰኑ
በእብሪት ተውጠው ጀግናን የደፈሩ
ትዕግስት ባይገባቸው እነሱ አፈሩ
ጥቃት የማይወደው ከትውልድ ከዘሩ
ድንበር ላይ ስላለ የጦር ሜዳ ሃገሩ
ሠላምሽን ገፎ ውድቀትሽን የሚሻ
የጀግናው ሞት አለ የትቤት ማርከሻ
በየአጋጣሚው ተመስክሮለታል
ድንቁን ብቃታችን ህዝቡ አውቆለታል
ይበልጥ ልንሰራም ዳግም ቃል ገብተናል
፶/አ ዳኛቸው ፈንታሁን
ከአውቶ መካኒክ B