You are on page 1of 3

ፉከራ

ቀድሞም አያቴ ሲዘምቱ አውቃለሁ ቀረርቶ


ኋላም አባቴ ሲገል አወቃለሁ ፈሪ ቁም ፈሪ ቁም መንታ ላሊበላ፣
ዛሬም ልጅየው ተደግሻለው ሲሸሽ የሞተ ሰው ተዝካሩ አይበላ፡፡
ጠላት ከመጣ አፈርሰዋለሁ እንደእውር አህያ እንዴት ጎድን ጎድን፣
ያባቴን ጋሻ አንስቼዋለሁ የማይሞት ሰው ላይሞት የሚሞት ሰው ላይድን፡፡

ፉከራ ቀረርቶ
ውጋው በሳንጃ በለው በሰደፍ በለው ሽንጡን ደሙ ይንዠርዠር
አገር ናትና ጎበዝ አትስነፍ፡፡ ሰው ስለገደሉ አይቀርም አገር፡፡
ኳኳ ሲል አውሽትራ ወዲህ ገምነን ወዲያ ገምነን ያልህበት እንደሆን
አጥንቱ ለጅብ ስጋው ላሞራ ፡፡ አንተም ትፈራለህ ካንበሳ ከዝሆን፡፡
*አውሽትራ(የጦር መሳርያ ስም እምቢ ብሎ እንደሆን ደም እያራወጠው
በምንሽር ጥይት ወገቡን ቁረጠው፡፡
ፉከራ ወዲያ ማዶ ገለህ ወዲህ ተሻገር
መድፍ መትረየስ ሲሸረሽረው፣ አገሩም ደም ይልመድ ወንዙም ይታፈር፡፡
አልቢን ምንሽር ሲያብጠሰጥሰው፣
አልሸሽም ብሎ ቆሞ ቆያቸው፣ ቀረርቶ
ዙሮ በጥይት ሰነጠቃቸው፡፡ ምን ያለው ሞኝ ነው ያጓት ጠላላ፣
ወንድሙን ሰው ገሎት እሱ አርሶ ሊበላ፡፡
ቀረርቶ ወንድሙን ሲከፋው ወንድሙን ካልከፋው፣
ለምን ዝም ትላለህ ሀገርህን ሲወረው፣ ጣሉለት ከፊቱ ደሙ እንዲከረፋው፡፡
ተነስ ያገሬ ልጅ ይህ የኛ እዳ ነው፡፡ የሰው ወንድም ገድሎ ቢገቡ ከደብር፣
እንኳን ባባቱ አገረ ባባቱ ሸለቆ፣ ያመጣል ወንድሙ ተስቦ እንደነብር፡፡
ምን አለ ቢሞቱት ወንድነቱ ታውቆ፡፡
ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
ቀረርቶ መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ
በያዝከው ወጥ አልቢን አርገው ገለል ገለል፣ አሻግሮ ገዳይ ዲብ አንተርሶ
በያዝከው ምንሽር አርገው ገለል ገለል፣ የዳኛው አሽከር ባልቻ አባ ነፍሶ፡፡
ሞት አይቀርምና በጀርባ መንጋለል፡፡
በለው በምንሽር በል፣ በለው በጓንዴ፣ ድገመው በዋንዛ፣
ባባት አገርና በሚስት የለም ዋዛ፡፡
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፣ ስለ አጤ ቴዎድሮስ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ፡፡ ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው፣
በሰራው ወጨፎ ባነሳው እርሳስ፣ ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው፣
ቆላ አንገረገበው ያን የባህር ገብስ፣ ምን ይሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው፡፡
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡ መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኸት በረከተ፣
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ፡፡
መብራቱን ዮሐንስ ለአሉላ ቢሰጠው፣ ጠላቶቹን ሁሉ አጭዶ እንደ ገብስ፣
እንደ ቀትር እሳት ቱርክን ገላመጠው፣ መቅደላ ተጣለው ራሱን በራስ፡፡
ጣልያን ወደቀ እያንቀጠቀጠው፣ እናትና አባቱ አላንድ አልወለዱ፣
አጭዶና ከምሮ እንደ ገብስ አሰጣው፡፡ አባ ታጠቅ ካሳ ያ ወንዱ ያ ወንዱ፡፡
…አባ ነጋ አሉላ የደጋ ላይ ኮሶ፣ ዳር እሰከ ዳር ይዞ የገዛው ንጉስ፣
በጥላው ያደክማል እንኳንስ ተቀምሶ፡፡ እንዲህን ለሱ ነው ጠበንጃ እሚጎርስ፡፡
ጣልያን ሰሐጢ ላይ እግሩን ቢዘረጋ፣
በብረት ምጣዱ በሰሐጢ አደጋ፣ ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም፣
አንገብግቦ ቆላው አሉላ አባ ነጋ፡፡ ዐርብ ዐርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም፡፡
አንተም ጌታ አይደለህ እኔም አልሆን ሎሌ፣
የኢየሩሳሌም ሰው ካልጫነ በርሞሌ፡፡
ሴሰኛውን ጎበዝ ያራቱን ማዕዘን ባል፣
የእሳት ምድጃችን ሳይዳፈን ቀርቶ፣ ታጠቅን ማን አምኖ ባል ብሎ ያገባል፡፡
ከትልቁ አዳራሽ ከጓዳው ተነስቶ፣
ብዙ ቤት በላብን የሚያጠፋው ጠፍቶ፡፡ ደረስጌ ያበራው የቋራው ፀሐይ፣
ተኝቷል መቅደላ ጠላት እንዳያይ፡፡
ኢትዮጵያ የተባለችው፣ የመቅደላን ጋራ መርጦ ቴዎድሮስ፣
አንደኛ እናትህ ናት ሰይፉን ልብስ አድርጎ ጦሩንም ትራስ፣
ሁለተኛ ዘውድህ ናት ቢርበው ጥይቱን አየነው ሲጎርስ፡፡
ሦስተኛ ሚስትህ ናት
አራተኛ ልጅህ ናት ጎጃም ራስ ሀይሉ ግድ የለም ግድ የለም፣
አምስተኛ መቃብርህ ናት አድዋ ራስ ሥዩም ግድ የለም ግድ የለም፣
አጤ ዮሐንስ 1887 ወሎ ራስ አመዴ ግድ የለም ግድ የለም፣
በዛች አውራ ጣቱ ያልፈረመ የለም፡፡
ካንድ አገር ብዙ ብር እየጠየቃችሁ፣
ላንድ ሰው ሶስት ሺህ፣ ላንድ ሰው ሁለት ሺህ
ብር እየሰጣችሁ፣
እኔስ አንድ ሰው ነኝ ይብላኝ ላገራችሁ፡፡ ,

1)በኢጣልያ ወረራ ጊዜ የተገጠሙ(1928-1933)


እንኳን በእኛ ጊዜ ቢሆን በልጅ ልጅ፣
እንግዲህ አይመጣም የጣልያን ውራጅ፡፡
እነሱ በሰሩት በገዛ መድፋቸው፣
እነሱ ባመጡት በመትረጌሳቸው፣
አለቁ ጣልያኖች ባለማወቃቸው፡፡

2)በሱማሌና በኢትዮጵያ የወሰን ግጭት ጊዜ የተገጠሙ(1956-


1958)
ሱማሌ ጌሾ ጠጥታ አብዳለች ሰክራለች፣
ረመጥ ልትገባ ትገላገላለች፡፡
አወይ ማበድ አወይ መቅበጥ፣
በግመል ተጉዞ እዋጋለሁ ማለት፡፡
ድምፃዊ ይርጋ ዱባለ

3)በሱዳንና በኢትዮጵያ የወሰን ግጭት ጊዜ(1964)


ሱማሌ ጭኖ ነበር መልሶ አራገፈ፣
አንድ ሱዳን ቀርቷል የተክለፈለፈ፣
ይወድቃል ባዳፍኔ እግሩ ካላረፈ፡፡
አረ እናንተ ሆዬ ሁሉም ዋዛ ለምዶ፣
ሱዳን ሊበላ ነው ጎንደር እሳት ነዶ፡፡
አይጥ ጠላ ጠምቃ ሁለቱን ጠጥታ፣
ትገለገላለች ድመትን ልትመታ፡፡
ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ሲያስፋፋ፣
ፈጥኖ ደረሰበት ገና ሲያንቀላፋ፡፡
ድምፃዊ ይርጋ ዱባለ

You might also like