Professional Documents
Culture Documents
ስ.አ ገጽ 1
ወንዱ አሥራ ሁለት ሆነን አንዲት ልጅ ወደን፣
እሷ ትስቃለች እኛ ተጨንቀን፡፡
ሴቷ አስራ ሁለት ሆነን አንድ ልጅ ወደን፣
እሱ ይጫወታል እኛ ተጨንቀን፡፡ በማለት ይገጥማሉ፡
3. ቀረርቶና ፉከራ፡- ቀረርቶና ፉከራ የጀግንነት መገለጫ፣ የጠላትና የፈሪ መተንኮሻ ስልቶች ናቸው፡፡ አብዛኛውን
ጊዜ የሚከውኑት በጦርነት ዋዜማና በጦርነት ጊዜ በአውደ ዓመት ባዕለትና በደል በዝቶ ልብ ሲሸፍት ነው፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች በለቅሶ ጊዜም ይከወናል፡፡
ምሳሌ፡-
ቀረርቶ አረምን ካረሙ ከስሩ ነቅሎ ነው፣
ከቆረጡትማ ያው መተካቱ ነው፡፡
ኧረ ጥራኝ ጫካው ኧረ ራኝ ዱሩ፣
ላንተም ይሻልሃል ብቻ ከማደሩ፡፡
እኛን ስለከፋን ብናንጎራጉር፣
እኒህ ጥጋበኞች እንባል ጀመር፡፡
እንኳን ምታ ብለው ልከው ሰደውት፣
በወገብ ላይ ሆኖ ያኮራል ጥይት፡፡
ፉከራ “አካካ ዘራፍ . . .
በሮች ጥቋቁር ገበሬው ሙጫ፣
ማን ይለቀዋል እርፍ ቢንጫጫ፡፡
መጋና ጎሹ የሄዱበት፣
ያረገርጋል የእርሻ መሬቱ፡፡”
አጃቢ “እውነት ነው!”
4. የልጆች ጨዋታ፡- የልጆች ጨዋታ እንደ ጨዋታው ዓይነት እንደ ባሕሉ፣ እንደ ልጆቹ እድሜ ይለያያል፤
ይከወናልም፡፡ በአብዛኛው በእንቅስቃሴ የታጀበ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እቴሜቴ የሚለውን ምሳሌ፡- እቴሜቴ የሎሚ
ሽታ፣
ያ ሰውዬ ምናለሽ ማታ፣
ምንም ምንም ምንም አላለኝ፣
ትዳሩን ፈቶ ልውሰድስ አለኝ፣
አይወስድሽም ትዳሩን ፈቶ፣
ምሎልሻል ጋሻ ጦር ደፍቶ፣
ማላ ማላ የጎበዝ ማላ፣
ጉሽ ይላታል እንደ ጉሽ ጠላ፡፡ . . .
የባሕል ዘፈኖች፡- ዘፈን በተለያየ ጊዜና ቦታ፣ በተለያዩ ሰዎች ሊቀርብ ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ በቡድን
አንዳንዴም በተናጥል የሚቀርብበት ጊዜ አለ፡፡ በተለያዩ ወቅቶና በተለያዩ ሁኔታዎች
በቡድንም ሆነ በተናጥል ከሚቀርቡ ውስጥ የሠርግ እና የክብረ በዓላትን ዘፈኖች
እናያለን፡፡
የሠርግ፡-
ስ.አ ገጽ 2
ምሳሌ፡- ሙሽራዬ አይበልሽ ከፋ፣
ሁሉም ይዳራል በየወረፋ፣
ባልንጀሬ ሥሪ ጉልቻ፣
ከእንግዲህ የለም የእናት እንጎቻ፡፡
ሸኝቸው መጣሁ ሸኝቸው፣
የብር አለንጋ ሰጥቸው፡፡
የክብረ በዓላት፡-
በጥምቀት (ታቦት ስንሸኝ)
እየው ሎሌው ሲምር
ሎሌው ሲያምር
የሚካኤል ደብር
እየው ሎሌው ሲያገሳ
ሎሌው ሲያገሳ
የሚካኤል አንበሳ . . .
ሙሾ፡- የሙሾ ስንኞች ሲደረደሩ የሟችን ማንነት፣ ዕድሜና አጠቃላይ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡ መሆን
ይኖርባቸዋል፡፡
ምሳሌ፡- ለእናት ሞት
አትቅበሩኝ አለች ካንገቴ በላይ፣
ስወጣ ስገባ ልጆቼን እንዳይ፡፡
በጦርነት ለሞተ ጀግና
እርጥብ እርጥቡባ ተራራው ጋረደው
ደረቅ ደረቁ ነው ገብቶ የነደደው
ጎበዝ ይሙት ፈሪ ይኑር ቢሻው፣
አተላ መሸከም ይችላል ትከሻው፣
ፈሪ ጦንጣና ነው ዘላለም ይኖራል፣
ጀግና ብርሌ ነው ቶሎ ይሰበራል፡፡
እነዚህ ከላይ የቀረቡት ቃላዊ ግጥሞች የሥነ - ቃል በሆሄ የሆነውን አውዳዊነት፣ ክዋኔ፣ ተደራሲነት፣ ተለዋጭነት
ባሕሪቸው አድርገው ይተገበራሉ፡፡
ስ.አ ገጽ 3
ወጥ ረጋጭ ---------------------------------------- ባለጌ
በለስ ቀናው ---------------------------------------- ተሳካለት
ደመ መራራ ---------------------------------------- ነገር የሚገንበት
ኩታ ገጠም ---------------------------------------- ድምበርተኛ
አንጀቱ ራሰ ---------------------------------------- ተደሰተ
ህቅ አለ --------------------------------------------- ሞተ
ምሳሊያዊ አነጋገር፡- ምሳሌያዊ አነጋገር ወይም ተረትና ምሳሌ ከጥንት ጀምሮ የሚሠራበት፣ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ውበት
ያለው የአነጋገር ስልት ነው፡፡ አንድን ነገር በሚገባና በቀላሉ ለማስረዳት ሲፈልግ ተናጋሪ ሰው ሐተታ ሳያበዛ ከፍተኛ ቁም
ነገርና ጥልቀት ያለውን መልዕክት በጥቂቱ ምሳሌያዊ አነጋገር አማካኝነት ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር
ማለት አንድን ጉዳት አስመልክቶ ቀዳማይ አባቶችና እናቶች የሰነዘሩት ንግግር ሲሆን የዛሬውም ትውልድ ለሚደርጉት ነገር
ማስረጃና ምሳሌ አድርጎ የሚጠቀምበት ብርቱ የአነጋገር ስልትወይም ብልሃት ነው፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮች አሉ፡፡ እነሱም
ሴቶች ላይ፣ ሕፃናት ላይ እና አካል ጉዳተኞች ላይ የሚባሉ ናቸው፡፡ ጠንካራ ከሆኑ ምሳሌያዊ አነጋገሮች ስንመለከት፡-
የቃል ክፍሎች
በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ የሚገኙ የቃል ክፍሎች አምስት ናቸው፡፡ እነሱም ስም፣ ግስ፣ ቅጽል፣ ተውሳከ ግስ እና
መስተዋድድ ናቸው፡፡
ስም፡- ለማንኛውም ነገር በመጠሪያነት የሚያገለግል የቃል ክፍል ነው፡፡
ምሳሌ፡- ሰው፣ ፍቅር፣ ሀገር፣ መጽሐፍ፣ ከበደ . . . ወዘተ
ግስ፡- ድርጊትን የሚመለክት የቃል ክፍል ግስ ይባላል፡፡
ምሳሌ፡- ሄደ፣ ጻፈ፣ ተጫወተ፣ ሰበረ፣ ገነባ . . . ወዘተ
ቅጽል፡- ስምን የሚገልጽ የቃል ክፍል ቅጽል ይባላል፡፡
ምሳሌ፡- ቀይ፣ ደግ፣ ሰባራ፣ ሞኝ . . . ወዘተ
ተውሳከ ግስ፡- ግስን የሚገልጽ የቃል ክፍል ተውሳከ ግስ ይባላል፡፡
ምሳሌ፡- ምንኛ፣ ክፉ፣ ገና፣ ቶሎ፣ ትናንተ . . . ወዘተ
መስተዋድድ፡- በራሳቸው ትርጉም የማይሰጡ ሌሎች የቃል ክፍሎ ጋር በመግባባት የተለያ አገልግሎት የሚሰጡ የቃል
ክፍሎች ናቸው፡፡
ስ.አ ገጽ 4
ምሳሌ፡- ከ፣ በ፣ ስለ፣ ከ - ጋር . . . ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ሐረግ
ሐረግ ማለት ትርጉም ያላቸው ሁለትና ከዚያ በላይ ቃላት ተቀናጅተው የሚፈጥሩት መዋቅር ሲሆን “ሐረግ”
የሚለውን ስያሜ ሊያገኝ የቻለው አግባብነት ያላቸው ቃላት እንደሰንሰለት ተያይዘው በመርዘም ሐረግ ስለሚሰመስሉት
ነው፡፡
የሐረግ ዓይነቶች
የሐረግ ዓይነቶች በቃላት ክፍሎች ልክ ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረት እኛ የቃላት ክፍሎን በአምስት ስለከፈልን የሐረግ
ዓይነቶችም አምስት ይሆናሉ፡፡
ስማዊ ሐረግ፡- ስማዊ ሐረግ የሚባለው የተለያዩ ስሞችን ቀኝ መሪ ያደረገ ሐረግ ነው፡፡
ምሳሌ፡- የላስቲክ ኳስ
ጥሩ የዶሮ ወጥ
ግሳዊ ሐረግ፡- ግሳዊ ሐረግ የተለያዩ ግሶችን ቀኝ መሪ ያደረገ ሐረግ ነው፡፡
ምሳሌ፡- ነጋዴ ነው፡፡
ዛሬ ጠዋት ገበያ ሄደች፡፡
ቅጽላዊ ሐረግ፡- ቅጽላዊ ሐረግ የሚባለው ቀኝ መሪ ቅጽል የሆነ ሐረግ ነው፡፡
ምሳሌ፡- በጣም ደግ
እንደ አባቱ የዋህ
ተውሳከ ግሳዊ ሐረግ፡- ተውሳከ ግሳዊ ሐረግ ተውሳከ ግስን ቀኝ መሪ ያደረገ የሐረግ ዓይነት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ቁልቁለቱን ቶሎ
ዛሬ ክፉኛ
መስተዋድዳዊ ሐረግ፡- መስተዋድዳዊ ሐረግ ቀኝ መሪም ግራ መሪም በመሆን የሚታይ የሐረግ ዓይነት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ስለ መጣ
ከ ዛፍ ላይ
የሕይወት ታሪክ
የሕይወት ታሪክ በተለያዩ መስኮች ማትም በፍልስፍና፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሥነ -
ጥበብና በሥነ - ጽሑፍ ወዘተ ዕውቅና ያገኙ የዓለማችንን ታላላቅ ሰዎች አስመልክቶ አስተዳደጋቸውን፣ ዝንባሌያቸውንና
ለዓለማችን ያደረጉትን አስተዋጽኦ በሚመለከት ሰፊ መረጃ መስጠት ነው፡፡
የሕይወት ታሪክ በሁለት ይከፈላል፡፡
1. የራስ የሕይወት ታሪክ
2. የግለሰብ የሕይወት ታሪክ
የራስ የሕይወት ታሪክ በራሱ በባለቤቱ የሚፃፍ ሲሆን የግለሰብ የሕይወት ታሪክ በሌላ ሰው የሚፃፍ ነው፡፡
የሕይወት ታሪክ አፃፃፍ ቅደም ተከተል
1. የባለ ታሪኩን ስም የትውልድ ስፍራና የትውልድ ዘመን
2. ስለ አስተዳደግ ሁኔታ
3. የትምህርት ደረጃ
4. የፈጸሟቸውን ጉልህ ተግባራትና ያበረከቷቸውን አስተዋጽኦዎ በቅደም ተከተል መዘርዘር
ስ.አ ገጽ 5
5. ተግባራቱ ያስገኙላቸው ጥቅሞች እና የመሳሰሉት
ስ.አ ገጽ 6