You are on page 1of 41

በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ስምንተኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የክፍል ውስጥ


አመራር ሁኔታ ትንተና

በ ሸዋነሰሽ እምየው ዶዮ

አማካሪ ዶ/ር ታደሰ ሰንቤቦ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲስ፣ የቋንቋዎች ጥናት፣ የጋዜጠኝነትና


ኮሚዩኒኬሽን ኮሌጅ የአማርኛ ቋንቋ፣ ስነፅሁፍና ፎክሎር ትምህርት ክፍል
የባችለር ዲግሪ ማሟያ ጥናት

ፍቼ ሰላሌ

ሐምሌ 2011 ዓ.ም


የሠንጠረዥ ማውጫ
ሠንጠረዥ 1 በመረጃ ሰጪነት የተሳተፉት ተማሪዎች አጠቃላይ መረጃ.......................... 14
ሠንጠረዥ 2 ተማሪዎችን በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎ የሰጡት ምላሾች ........................ 15
ሠንጠረዥ 3 የአማርኛ ቋንቋ መምህራኑን የጊዜ አጠቃቀም በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎች
የተሰጡ ምላሾች፡፡ ....................................................................................................... 15
ሠንጥረዥ 4 መምህራኑ ወደ መማሪያ ክፍል ሲገቡ ያለው ሁኔታ በተመለከተ የቀረበ ጥያቄ
................................................................................................................................. 16
ሠንጠረዥ 5 በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚቀርበውን ይዘት በተመለከተ የቀረበ መጠይቅ.. 17
ሠንጠረዥ 6 የመምህሩ የትምህርት አቀራረብ ሁኔታ በተመለከተ የቀረበ መጠይቅ ......... 17
ሠንጠረዥ 7 በትምህርት ሂደቱ ጊዜ ተማሪዎች ለመምህራናቸው የሚያቀርቡት ጥያቄ
ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ለቀረበ ጥያቄ የተሰጡ ምላሾች............................................. 18
ሠንጠረዥ 8 በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚከስቱ የስርዓት ችግሮችን ለመከላከል የመምህሩን
ሚና በተመለከተ የቀረቡ ጥያቄዎች .............................................................................. 19
ሠንጠረዥ 9 የተማሪዎች ተሳትፎ በተመለከተ የቀረበ ጥያቄ ......................................... 21
ሠንጠረዥ 10 በመረጃ ሰጪነት የተሳተፉት መምህራን አጠቃላይ መረጃ ........................ 22
ሠንጠረዥ 11 ለመምህራኑ ስራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ..... 22
ሠንጠረዥ 12 የመማሪያ ክፍለ እና የተማሪዎችን ጥር ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር
ያለውን ተፅኖ በተመለከተ በቀረበ ጥያቄ የተሰጠ ምላሾች ............................................... 23
ሠንጠረዥ 13 የተማሪዎች ተሳትፎን በተመለከተ ለቀረበ ጥያቄ የተሰጠ ምላሾች ............ 24

i
የስዕል ማውጫ
ስዕል 1 :ፆታ ስርጭት ................................................................................................ 14
ስዕል 2፡የአብዲሳ ኣጋ የ 2011 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ክፍለ ጊዜ ተሳትፎ
................................................................................................................................. 24

ii
ዋና ማውጫ

ገፅ
የሠንጠረዥ ማውጫ ...................................................................................................... i
የስዕል ማውጫ ............................................................................................................. ii
ዋና ማውጫ ................................................................................................................. iii
አጠቃሎ ....................................................................................................................... v
ምስጋና........................................................................................................................ vi
ምዕራፍ አንድ ............................................................................................................... 1
1. መግቢያ ................................................................................................................... 1
1.1 የጥናቱ ዳራ ........................................................................................................ 1
1.2. ሰበበ ጥናት........................................................................................................ 3
1.3 የጥናቱ ዓላማ ..................................................................................................... 3
1.4 የጥናቱ ጠቀሜታ ................................................................................................ 3
1.5 የጥናቱ ወሰን...................................................................................................... 4
1.6 ያጋጥሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሔዎች .................................................... 4
ምዕራፍ ሁለት.............................................................................................................. 5
2. ክለሳ ድርሳናት ......................................................................................................... 5
2.1 ጊዜ ንድፈ ሀሳባዊ ቅኝት ..................................................................................... 5
2.1.1. ለመማሪያ ክፍል ውስጥ የስርዓት መጓደል ምክንያቶች ................................... 6
2.1.2 በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች መንስኤያቸውን መፈለግ ............... 8
2.1.3. በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮቸን መቆጣጠር ................................ 9
2.1.4. በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች የሚወሰዱ እርምጃዎች ................ 9
2.2. የተዛማጅ ፅሁፎች ቅኝት .................................................................................. 10
ምዕራፍ ሦስት ............................................................................................................ 12
3 የጥናቱ ዘዴ እና አካሄድ .......................................................................................... 12
3.1 ትምህርት ቤቱ ናሙና አወሳሰድ ........................................................................ 12
3.1.1 የክፍል ደረጃ ናሙና አወሳሰድ..................................................................... 12
3.1.2. የተማሪዎ እና መምህራን ናሙና አወሳሰድ ................................................. 12
3.2 የመረጃ መሰብሰቢያ መረጣ ................................................................................ 13
3.2.1 ምልከታ ..................................................................................................... 13
3.2.2 የፅሁፍ መጠይቅ ........................................................................................ 13
3.2.3 ቃለ መጠይቅ ............................................................................................. 13

iii
3.3የመረጃ አተናተን ................................................................................................ 13
ምዕራፍ አራት ............................................................................................................ 14
4 መረጃ ትንተና ...................................................................................................... 14
4.1 ከተማሪዎች በፅሁፍ መጠይቅ የተገኘ መረጃ ትንተና ........................................... 14
4.2 ከመምህራን በቃለ መጠይቅ የተገኙ መረጃዎች ትንተና .................................... 22
ምዕራፍ አምስት ......................................................................................................... 25
5. ማጠቃለያ እና የመፍትሄ ሃሳቦች ............................................................................ 25
5.1. ማጠቃለያ ........................................................................................................ 25
5.2 የመፍትሔ ሀሳቦች ............................................................................................ 27
6.ዋቢ መጽሐፍት ....................................................................................................... 28
አባሪ አንድ ................................................................................................................. 29
አባሪ ሁለት ................................................................................................................ 31
ደብዳቤዎች ................................................................................................................. 34

iv
አጠቃሎ
ይህ ጥናት በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስምንተኛ
ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የክፍል ውስጥ አመራር ሁኔታ ትንተና በሚል ርአስ
የተሰራ ነው።በመሆኑም አብይ አላማ አድርጎ የያዝው በትምህርት ቤቱ ስምንተኛ ክፍሎቸ
ያለውን የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አቀራረብ ሁኔታን መተንተን እና ለቸግሮቹም ማቃለያ
ይሆኑ ዘንድ የመፍትሄ ሃሳቦችን ይዟል።

ጥናቱ በገላጭ የምርምር ዘዴ የተካሄደ ሲሆን የናሙና አወሳሰድም እድል ሰጪ የናሙና


አወሳሰድ ዘዴን መሰረት ያደረገ ነው።እንዲሁም መረጃዎች በምልከታ በፅሁፍ መጠይቅ እና
በቃለ መጠይቅ ነው የተሰበሰቡት።

የተሰበሰቡት መረጃዎች አይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴን መሰረት በማድረግ በሰንጠረዥ


የተተነተኑ ሲሆኑ የምልከታ ውጤቶችም የፅሁፍ መጠይቁን ተአማኒነት ለማረጋገጥ ሲባል
የተሰበሰብ ስለሆነ እንደተመሳሳይነታቸው አብረው ተተንትነዋል።

በትምህርት ቤቱ አብዛኞቹ ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የማይጥሩ


መሆኑን ከሚያቀርቡት ይዘት ጋር ተዛማጅ የሆኑ የማስተማሪያ ስልቶች እንደማይጠቀሙ
ከቡድን ይልቅ የተማሪዎችን የግል ተሳትፎ እንደሚያበረታቱ ሁሉንም ተማሪዎች በእኩል
እንደማያሳትፉ ተግባራትን በጊዜ ከፋፍለው እንደማይሰሩ ተማሪዎች እንዲሳትፉ
እንደማያበረታቱ እና የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎች ምቹ ሁኔታ እንደማይፈጥሩ
ጥናቱ ያሳያል።

በመጨረሻም ጥናቱ የትምህርት ቤቱን መምህራን ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ


ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቢተጉ፣ ለሚያቀርቡት የትምህርት ይዘት ምቹ የሆነ የማስተማሪያ
ዘዴን ቢጠቀሙ፣ የክፍል ውስጥ መስተጋብራቸው ሁሉንም ተማሪ ያማከለ ቢሆን፣ተግባራትን
በጊዜ ከፋፍለው ቢያሰሩ እና ተማሪዎችን ቢያሳትፉ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸውን
ክፍሎች የትምህርት ቤቱን የመማሪያ ክፍሎች ሁኔታ ምቹ እንዲሆኑ በተቻለ አቅም ቢጥሩ
ምቹ የሆነ የመማሪያ ክፍልን መፍጠር እንደሚቻል ይገልፃል።

v
ምስጋና
ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በእግዚአብሔር ፍቃድ ነውና አመሰግነዋለሁ።

በመጀመሪያ ተስፋ ቆርጠን ሳለ ይህንን የትምህርት እድል ላመቻቸልን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የአማርኛ ቋንቋ፣ ስነፅሁፍና ፎክሎር ትምህርት ክፍል ምስጋናይዬ ከፍ ያለ ነው። ሲቀጥል
የዚህ ስራ ውጤት ከጅማሬው እስከ ፍጻሜው እንዲሳካ ከፍተኛ እገዛ ላደረጉልኝ ለዶ/ር ታደሰ
ሰንቤቦ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው። እንደዚሁም ጽሁፉን በማረም ለረዳችኝ ልጄ ለዶ/ር ነፃነት
አያሌው፣ፅሁፉን በመጻፍ ለተባበረችኝ ለወ/ሮ ስናፍቅሽ ደቀቦ ፣ ለውድ ባለቤቴ አያሌው አበበ፣
ለልጆቼ ቶማስ አያሌው፣አሸናፊ አያሌው፣ሄኖክ አያሌው እና ናኦል አያሌው ለሰጣችሁኝ
ሞራል ና ድጋፍ ፈጣሪ በጤና እና በፍቀር ያኑርልኝ። እንደዚሁም ትብብራችሁ ላልተለየኝ
የአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና የ 2011
ዓ.ም ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

vi
ምዕራፍ አንድ

1. መግቢያ

1.1 የጥናቱ ዳራ
የክፍል ወስጥ አመራር ማለት መምህሩ በመማር ማስተማር ተግባር ጊዜ በመማሪያ ክፍል
ያሉትን ሁኔታዎች በአጠቃላይ የሚዳስሱ የመምህሩ ሚናዎች ናቸው:: በጥሩ የክፍል አመራር
ችሎት ያልታጀበ የማስተማር ተግባር የትምህርቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ አያስችልም፡፡
በመሆኑም ለትምህርቱ ስኬታማነት ከትምህርቱ በቂ እውቀት በተጨማሪ መምህሩ ጥሩ
የክፍል አመራር ችሎት ሊኖረው ይገባል፡፡ በክፍል አመራር ዙሪያ የተለያዩ ሙሁራን የተለያዩ
ብያኔዎች ሰጥተዋል፡፡ ከተሰጡት ብያኔዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

እማርጀት (2003 151) አርቪን ኤስ ኪንግን በመጥቀስ እንደ ገለፀው “የክፍል ውስጥ አመራር
ዋንኛ አላማው ህግና ስርዓትን አቀናጅቶ በመያዝ እና በመተግበር እንከኖችን ለመከላከል እና
ለመቅረፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማጠናከር ነው። እንደ እማርጀት ገለፃ የክፍል አመራር
እንደ ዋና አላማ አድርጎ ሊይዝ የሚገባው ጉዳይ የትምህርቱን አላማ ከግብ ማድረስ ነው።

ሰይድ እንዲሪስ (998 1) ቱባን አልቤርቶን እና ቴርማንን በመጥቀስ እንደገለፀው የክፍል


ውስት አመራር ትምህርቱን የሚያነቃቃ ድባብ ለመፍጠር የመምህሩ ጊዜን፤ ቦታን፣ቁሳቁሶችን
የተማሪውን ሚናና ባህሪ በህብር የመምራት ችሎታ ነው፡፡ እንደ ብያኔው የክፍል ውስጥ
አመራር ማለት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳካት ሲባል መምህሩ በክፍል ውስጥ
ሊተገብራቸው የሚገቡ ተግባራትን ሁሉ ያካተተ ነው፡፡

“የክፍል አመራር ለመማር ሂደቱ አመቺ ሁኔታዎችን የመፍጠር ተግባር እንጂ ማስተማር
ልንለው አንችልም።” ክለርክ ድየል (2003: 111) እንደ ክለርክ ገለፃ ማስተማር ያለ ጥሩ
የክፍል አመራር ችሎታ ተግባራዊ ሊሆነ አለመቻሉን ያሳያል።

በአጠቃላይ በክፍል አመራር ዙሪያ ብዙ የተባለ ቢሆንም ያሲን አህመድን በመጥቀስ ሰይድ
እንዲሪሰ (1998፤ 1) ያለውን ሁሉንም ለማካተት ይሞክራል፡፡ የክፍል አመራር ለመማር
ማስተማር ሂደቱ ጥሩ ሁኔታን የመፍጠርና የመጠበቅ ጉዳይ ነው፡፡ ከብያኔው ለመረዳት
እንደሚቻለው የክፍል ውስጥ አመራር ማለት ለመማር ማስተማር ሂደቱ አመቺ ሁኔታዎችን
መፍጠር እና በመሀል የሚከሰቱ ችግሮች ካሉም እንዳይከሰቱ መቆጣጠርን እና ከተከሰተም
የመከላከል ሁኔታዎች ሁሉ የሚያካትት ተግባር ነው።

1
ለመማሪያ ክፍል ውስጥ ስርዓት መጓደል መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ምክንያቶች
ይጠቀሳሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. የመምህሩ በራስ መተማመን ማነስ

እማርጀት (2003 1) ጆንን በመጠቀስ እንዳለው:: “አንዳንድ ጊዜ የሚፈጠሩ ችግሮችን


ለመቆጣጠር በራስ መተማመን ስለሚያንሰኝ እቸገራለሁ:: በመሆኑም ተማሪዎች ብዙን ጊዜ
ትኩረታቸው በሌላ ነገሮች ይሰረቃል፡፡ » ከዚህ ገለፃ እንደምረዳው መምህሩ በራስ መተማመን
ማጣት የመማሪያ ክፍሉን ስርዓት ሁኔታ ይወሰናል ማለት ነው፡፡

ለ በክፍል ውስጥ የተማሪዎች ቁጥር መብዛት

ሰይድ (1998፣7) ያሲን አህመድን በመጥቀስ እንደገለፀው በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ
የተማሪዎች ቁጥር መብዛት በመማሪያ ክፍሉ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ
ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

ሒ በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ ወደ ክፍል መግባት

መምህራን በሚያስተምሩት ትምህርት ይዘት ዙሪያ በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ ወደ መማሪያ ክፍል


ውስጥ ከገቡ የመማር ማስተማር ተግባር ለመፈፀም እንከኖች ይገጥሟቸዋል፡፡ ከእነዚህም
እንከኖች ውስጥ ገለፃን ለመስጠት በራስ መተማመን ማነስ፣የተማሪዎች ፌዝ፣መሰላቸት እና
የፀጥታ ሁኔታ ይገኙበታል።

በአጠቃላይ የክፍል ውስጥ ስርዓት መጓደል በተለያዩ መንስኤዎች ሊከሰት መቻሉን ከላይ
ለአብነት በተጠቀሱት መንስኤዎች መረዳት ይቻላል። በመሆኑም አንድ መምህር መማሪያ
ክፍል ከመግባቱ በፊትም ሆነ ከገባ በኋላ የሚፈጽማቸው ማንኛውም ተግባራት እጅግ ጥንቃቄ
ብተሞላበት እና አላማውን መሰረት ያደረጉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ስለ ክፍል ውስጥ አመራር ሁኔታ እና ለክፍል ውስጥ ስርዓት መጓደል መንስኤዎች ከላይ
ለመጥቀስ እንደተሞከረው ሆኖ ስለ አጥኝው በተግባር ልምምድ በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና
መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሄደበት ወቅት ያስተዋላቸው ትግባራት ከአማርኛ
ቋንቋ ትምህርት አንጻር ሲታይ አንዳንድ ችግሮችን በትምህርቱ ላይ የሚያሳድሩ መሆናችውን
ማስተዋል ተችሏል። በመሆኑም ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስምንተኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የክፍል ውስጥ
አመራር ሁኔታ ለመተንተን የተዘጋጀ ነው::

2
1.2. ሰበበ ጥናት
አንድ የቋንቋ መምህር ካለው በቂ የቋንቋ እውቀት በተጓዳኝ ጥሩ የክፍል ውስጥ አመራር
ችሎታ ከሌለው የመማር ማስተማሩ ስራ የተሟላ ሊሆን አይችልም፡፡ በመሆኑም አጥኚው
በተግባር ልምምድ በሄደበት ትምህርት ቤት ያስተዋላቸው አንዳንድ ችግሮች መንስኤዎቻቸው
ምን እንደሆነ ለማወቅ እና ከምን እንደሆነ ለመረዳት ሲል የጥናትና ምረምር ፅሁፉን በነዚህ
ርእስ ጉዳይ ላይ እንዲሰራ ካነሳሱት ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ናችው፡፡

1.3 የጥናቱ ዓላማ


የጥናቱ ጥቅል አላማ በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ስምንተኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የክፍል ውስጥ አመራር ሁኔታ መፈተሽና
መተንተን ሲሆን፣

የጥናቱ ዝርዝር አላማዎች ከላይ የተጠቀሰውን ዋና አላማ መሠረት በማድረግ የተጠቀሱ

ናቸው፡፡

 በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚከሰቱ የተማሪዎችን ተሳትፎ ማነስ ምክንያቶች ምን


እንደሆኑ መለየት እና መተንተን።
 በቋንቋ ትምህርት ክፍል ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ የስርዓት ጉድለቶችን እንዴት
መከልከልና ከተፈጠሩም በኃላ እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የመፍትሔ ሀሳብ
ማስቀመጥ
 ተማሪዎችን በቋንቋ ትምህርት ላይ ተነሳስተው እንዲያጠኑ የሚያደርጓቸውን
ምክንያቶች መለየት፡፡

1.4 የጥናቱ ጠቀሜታ


ይህ ጥናት የሚከተሉትን ፋይዳዎች ያስገኛል፡፡

 በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያሉትን የቋንቋ መምህራን በቋንቋ ትምህርት ጊዜ


የሚያጋጥሟቸው ችግሮች እንዴት መፍታት እዳለባቸው እገዛ ያደርጋል::
 የቋንቋ ትምህርቱ እውቀት በጥሩ የክፍል አመራር ችሎታ ካልታጀበ ትምህርቱ ጎደሎ
እንደሚሆን ይጠቁማል፡፡
 የቋንቋ መምህራን እንሚያቀርቡት የቋንቋ ትምህርት ይዘት ምን ዓይነት ሚና
ሊኖራቸው እንደሚገባ ይተነትናል።
 ለተመሳሳይ ስራዎች እንደ መረጃ /ማጣቀሻ/ ሊውል ይችላል።

3
1.5 የጥናቱ ወሰን
አጥኚው ጥናቱን ለማድረግ የመረጠው ቦታ በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። በዚህም ትምህርት ቤት ወስጥ ካጋጠሙት ችግሮች ውስጥ
ከወጪ፣ ከጊዜ፣ ከሰው ኃይል እና ከጉዳዩ አንገብጋቢነት አንፃር በማየት በትምህርት ቤቱ
በስምንተኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የክፍል ወስጥ አመራር ሁኔታ ትንተናን
መርጧል፡፡

1.6 ያጋጥሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሔዎች


አጥኚው ጥናቱን በሚያደርግበት ጊዜ የሚከተሉትን ችግሮች አጋጥመውታል።

 መረጃዎችን ለማሰባሰብ ሲባል በተደጋጋሚ ለሚደረገው የምልከታ ሂደት በአንዳንድ


መምህራን በኩል ፈቃደኛ አለመሆን፣
 እንደሚታወቀው የጽሁፍ መጠይቁ ከበርካታ ክፍሎች ነው የተሰበሰበው፡፡ በዚህን ጊዜ
ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል እጥረት አጋጥሟል፡፡
 ለጥናታዊ ፅሁፍ ይሆን ዘንድ ተብሎ የተሰጠው በጀት በቂ አለመሆን፡፡

የተወሰዱ መፍትሔዎች

ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ከዚህ በታች በተገለጸው መልኩ ለማቃለል ተሞሯል፡፡

 የጥናቱ አላማ ምን እንደሆነ በመንገርና መረጃዎችንም በተደጋጋሚ የሚሰበሰብበት


ምክንያት የተገኙትን መረጃዎች ታአማኒነት ለማረጋገጥ ሲባል እንደሆነ በመግለፅ
ለማከናወን ተችሏል፡፡
 መረጃ በሚሰበሰብበት ጊዜ በት/ቤቱ የታወቁ መምህራን ካሉት መምህራን በተደረገ እገዛ
የሰው ኃይል እጥረትን መቅረፍ ተችሏል።
 ለጥናታዊ ፅሁፉ ገንዘቡን በማብቃቃት ላጋጠመው ችግር እንደመፍትሔ ተጠቅሞ
ማከናወን ችሏል፡፡

4
ምዕራፍ ሁለት

2. ክለሳ ድርሳናት
2.1 ጊዜ ንድፈ ሀሳባዊ ቅኝት
የአመራርነት እውቀት የማያስፈልግበት የስራ መስክ እንደሌላ ብዙ ጊዜ በባለሙያዎች
ይነገራል፤ ይፃፋልም፡፡ አመራርነት በህዝባዊና መንግስታዊ አምራች ወይም አገልግሎት ሰጪ
ድርጅቶች ሁሉ አስፈላጊነቱ የታመነበት ነው። እንዲሁም በአንዳንድ የስራ መስኮች የስራ
መዳከምና አክሳሪነት ካስከተሉ ምክንያቶች አንዱ የአመራርነት ድክመት እንደሆነ በየጊዜው
ይሰማል፡፡ በዚህ ዋናው መፍትሄ ደግሞ ሙያው በየደረጃው እንዲሰርጽ ማድረግ ነው፡

የክፍል ውስጥ አመራር ከአመራር አይነቶች አንዱ ነው፡፡ መምህራን የመማር ማስተማር
ተግባርን ከግብ ለማድረስ ወይም ወጤታማ ለማድረግ አላማን ወስነው ለትምሀርቱ
የሚያስፈልጉትን ማቴሪያል በመማር ማስተማር ተግባር በቅልጥፍና እና በጥራት ወደ
ሚፈለገው ግብ የማድረስ ሂደት ነው፡፡

የክፍል አመራርን የተለያዩ ምሁራን በተለያየ መንገድ ይገልፁታል፡፡ ከእነርሱም መካከል


ለአብነት ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፡፡

የክፍል ውስጥ አመራር ጥሩ የክፍል ሁኔታን የመፍጠር እና በመማሪያ ክፍል ውስጥ


የሚከናወኑትን ተግባራት በአግባቡ የማቀናጀት ተገቢውን የማስተማሪያ ዘዴ የመጠቀም ፣
የመማሪያ ክፍሉን የማደራጀት እንዲሁም ተማሪዎችን እንዴት በጋራ መስራት እንደሚችሉ
ማስተባበርን ያካትታል፡፡ (ጂኤን፣2001፣506)

ኢሎት (2000፡ 377) የክፍል ውስጥ አመራርን እዲህ ሲል ገልፆታል፡፡ «የመማር


ማስተማርሩን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ ስንል የምንጠቀማቸው ስርዓቶች እና ደንቦች
ናቸው»፡፡ እንደ ኢሎት ገለፃ በመማሪያ ክፍል ውስጥ በመማር ማስተማር ሂደት
የሚተገበሩትን ህግና ደንቦችን በአጠቃላይ የክፍል አመራር እንላቸዋለን፡፡

“የክፍል ውስጥ አመራር ዋንኛ አላማው ህግና ስርዓትን አቀናጅቶ በመያዝ እና በመተግበር
አና እንዲሁም እንከኖችን በመከላከል እና በመቅረፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማጠናከር
ነው።” አማርጀት (2003፡ 151)፡፡ ከዚህ ብያኔ ለመረዳታ እንደሚቻለው የክፍል ውስጥ
አመራርነት የመማር ማስተማር ሂደቱን ወጤታማ ለማድረግ ሲባል የመማሪያ ክፍል ህግና
ደንቦችን በአግባቡ መጠቀም ወይም እንዲተገበሩ ማድረግ የሚለውን ሀሳብ ያስጨብጣል፡፡

5
ክፍል ውስጥ አመራር ትምህርቱን የሚያነቃቃ ድባብ ልመፍጠር የመምህሩ ጊዜን ቦታን
ቁሳቁሶችን የተማሪውን ሚና እና ባህሪ በህብር የመምራት ቸሎታ ነው።(ቱባ አንሲ ድህረገጽ)
እነደ ቱባ ገለፃ የክፍል አመራርነት በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚገኙትን ተግባራት በአጠቃላይ
ለትምህርቱ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥሩ አድርጎ የመምራት ሂደት ነው፡፡

በአጠቃላይ በክፍል አመራር ዙሪያ ብዙ የተባለ ቢሆንም የሲንግ (1995፣ 181) ራይነት እና
ሀርመርን በመጥቀስ የገለፀወ ሁሉንም ለማካተት ይሞክራል፡፡

የክፍል ወስጥ አመራር ማለት የመምህሩን፡

1. መማርያ ክፍሉን ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታን እንዲፈጥር የማድረግን


2. በመማር ማስተማር ሂደቱ ወስጥ ለሚኖሩት ተግባራት አመቺ የማስተማሪያ
ስልቶችን የመምረጥ እና የመጠቀም እና
3. የመማር ማስተማር ሂደቱን ስኬታማነት ከትምህርቱ አላማ አንፃር የመፈተሽ እና
የመገምገም ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡

2.1.1. ለመማሪያ ክፍል ውስጥ የስርዓት መጓደል ምክንያቶች


በመማሪያ ክፍል ውስጥ ጥሩ የሆነ የመማር ማስተማር ተግባር እንዳይኖር ሊያደርጉ የሚችሉ
ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ችግሮች ከተከሰቱ የራሳቸው የሆነ መንስኤ / ምክንያት /
እንደሚኖራቸው ይታወቃል፡፡ አትክሊስ (1995፣ 181) ሀርመርን በመጥቀስ የሚከተሉተን
አካላት በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚከሰቱ የስርዓት ጉድለት መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ
ይገልፃቸዋል፡፡

ሀ. መምህር

ሊ ተማሪዎች

ሒ ተቋመ /ትምህርት ቤቱ

ሀ. መምህር

ሀርመር እንደሚለው አንድ መምህር ያለው አመለካከት እና ስብዕና በመማሪያ ክፍሉ ወስጥ
አንዳች ፋይዳን ያስገኛል ወይም በከፍሉ ወስጥ የሚፈጠር የስርዓት ጥሰት መሰረት ሊሆን
ይችላል፡፡ በመሆኑም ይላል ሀርመር የሚከተሉትን ተግባራት በፅናት በመከተል
የሚፈጠረውን ችግሮች መቅረፍ ይቻላል፡፡

ሀ. ወደ መማሪያ ክፍል ሲገባ በቂ ዝግጅት ማድረግ፡፡

6
ለ. እቅድ አዘጋጅቶ በእቅድ መመራት፡፡

ሒ ተማሪዎችን አለማስፈራራት /ዛቻን አለመጠቀም/::

መ. ድምፅን መጥኖ መጠቀም::

ሠ. ለሁለም ተማሪዎች እኩል አመለካከት መያዝ በተማሪዎች መካከል አለማዳላት፡፡

ረ. ለተማሪዎ ቀና አመለካከት መኖር ወይም በተማሪዎች ሁኔታ አለመረበሽ፡፡

ለ ተማሪዎች

ሀርመር እንደገለፀው በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች በሁለተኛ ደረጃ


በምክንያትነት የወሰደው ተማሪዎችን ነው፡፡ እንደ ሀርመር ገለፃ ቀጥሎ የተዘረዘሩት በተማሪዎ
በኩል የሚፈጠሩ ችግሮች ወይም የስርዓት ጉድለቶች አንደ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ
ያምናል፡፡

ሀ. የሰዓቱ፡ ሁኔታ

ተማሪዎች በጠዋት ወይም ከሰአት በኋላ በሚኖረው ሞቃታማ ስዓት ወይም ከአድካሚ የስራ
ቆይታ በኋላ በመማሪያ ክፍል ውስጥ ከተገኙ ለመማሪያ ክፍሉ ስርዓት መጓደል መንስኤ
ይሆናል፡፡

ለ. ተማሪዎቹ ለትምህርቱ ያላቸውን አመለካከት

ተማሪዎች ለመምህሩ ፣ ለትምህርቱ እና ለመማር ማስተማር ሂደቱ ያላቸው አመለካከት ምን


ይመስላል፡፡ ይህ ሁኔታ በአሉታዊ መልኩ ከሆነ በተማሪዎች በኩል ለሚነሳው የስርዓት
መጓደል በር ከፋች ይሆናል፡፡

ሐ. ተማሪዎቹ እውቅናን መሻት

በጉርመስና ወቅት የሰው ልጅ በተለያዩ ነገሮች መታወቅን ይሻል ወይም ሊታወቅበት የሚችሉ
ነገሮችን ይፈልጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ተማሪዎችን ከቁጥጥር ውጪ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል::

መ. ተማሪዎች በጋራ በመሆን ሌሎችን ሊረብሹ ይችላሉ፡፡

ሐ. ተቋሙ/ትምህርት ቤቱ

አንድ ተቋም/ትምህርት ቤቱ/ ስነ ስርዓትን በተመለከተ የራሱ የሆነ ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል።
ይህ ካልሆነ ግን መምህራኑ ፖሊሲው እንዲዘጋጅ ግፊት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

7
አስቸጋሪ /ከባድ/ የሆነ የስነ ስርዓት ጉድለቶች በትምህርት ቤቱ ባለስልጣናት አማካኝነት
ሊገደቡ/ሊታገዱ/ ይችላሉ፡፡

2.1.2 በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች መንስኤያቸውን መፈለግ


በመማሪያ ክፍል ወስጥ ችግሮች መኖራቸው ከታወቀ ለተፈጠሩ የስርዓት ችግሮች
መንስኤያቸው ምን እንደሆነ ማወቅ ያሻል። ምክንያቱም የችግሮቹ መንስኤ ከታወቀ ችግሮችን
በቀላሉ መከላከል ወይም መቆጣጠር ይቻላል ማለት ነው፡፡

ኢሎት (2000፣390) የመማር ማስተማሩን ሂደት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጥያቄዎች


በመገምገም የችግሮቹ መንስኤ መለየት ይቻላል፡፡

ሀ. የመማሪያ ክፍሉ ለተማሪዎቹ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል?

በመማሪያ ክፍል ውስጥ የተማሪዎች እይታ የሚጋረድ፣ የአቀማመጥ ምቾትን የሚነሳና


ሌሎች እንቅፋት ነገሮችን መኖራቸውን ማጤን፡፡

ለ ህግና ስርዓቶቹ ግልፅ ናቸው?

አንዳንድ አስቸጋሪ የሆኑ ባህሪያትን ያማከለ ነው የወጣው ህግ ወይም አንድ እና ከአንድ በላይ
የሆኑ ህጎችን መተግበር አለባቸው፡፡

ሒ ተማሪዎች እየሰሩት ያሉትን ስራ በጥንቃቄ እየተቆጣጠሩ ነው?

የተስጡት መመሪያዎች በሁሉም ተማሪዎች ዘንድ ግልፅ መሆናቸውን እና ተማሪዎች


በሚሰሯቸው ስራዎች እንደሚጠየቁባቸው መረዳታቸውን ማጤን፡፡

መ. ጥሩ እና መጥፎ በመባል የተለዩት ባህሪያት ወጤትን አስገኝቷል?

አስራርን መለስ ብሎ በመቃኘት ለተማሪዎች የተሰጡት ማበረታቻ እና ቅጣቶች ወጤታማ


መሆናቸውን። እንዲሁም በተማሪው ላይ በጭፍኑ እርምጃ እንዳልተወሰደባቸው ማጤን::

ሠ. ችግሮችን ገና በእንጭጩ ማግኘት ትችሏል?

በራስ የሆነ የመቆጣጠር ስልትን ተጠቅሞ ችግሮች ከተከሰቱ በፍጥነት ለማስወገድ መጣር
ተገቢ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ችግሩ እያደገ ሄዶ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን
ይፈጥራል፡፡

8
ሬ የማስተማር ሂደቱ ለተማሪዎቹ ተስማምቷቸዋል?

ማስተማሩ ሂደት ተማሪዎች በትምህርት ሂደቱ ማለትም በመመሪያው በመማር


አለመደናገራቸውን እንዲሁም ከአንድ ተግባር ወደ ሌላ ተግባር በሚደረግ ሽግግር ወቅት
ተያያዥነት ባለው መልኩ መሆኑን ማጤን ያሻል።

በአጠቃላይ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን የኢሎትን ስድስቱን በክፍል ወስጥ ለምከሰቱ ችግሮች
መንስኤ መፈለጊያ መጠይቆች በመጠቀም መምህራን የችግሮችን መንስኤ በቀላሉ ሊያገኙ
ይችላሉ፡፡ ችግሮች ከተገኙ ደግሞ ለችግሮቹ መፍትሄ መፈለጉ እምብዛም ከባድ ሊሆን
አይችልም፡፡

2.1.3. በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮቸን መቆጣጠር


አትከሊስ (995:192) ሀርመር ጠቅሶ እንደገለጸው «መምህራን የክፍል ውስጥ ስርዓትን
ለመቆጣጠር ሲሉ በተማሪዎች አካላዊ ወይም ስሜታዊ ጉዳትን ሊያደርስ የሚችል ተግባር
መፈፀም ያለባቸውም::» ሀርመር እንደሚለው «የመምህራን ችግሮችን የመቆጣጠር ብቃት
ከመምህራኑ ማንነት ጋር ሊለያይ ይችላል፡፡»

2.1.4. በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች የሚወሰዱ እርምጃዎች


አትክሊስ (1995፡193) የክፍል ውስጥ ችግሮችን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች
በሚከተለው መልኩ አስቀምጧቸዋል፡፡

ሀ. ችግሮችን በፍጥነት ማስወገድ

ችግሮችን በቶሎ ካልተወገዱ ወይም ሳይወገዱ ከቆዩ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡


በመሆኑም ችግሮቹን በፍጥነት ማስወገድ ለስራዓት ብልሹነት አይነተኛ መፍትሔ ነው፡፡

ሊ በመማር ማስተማር ሂደቱ ውስጥ የስርዓት ችግር ከተከሰቱ ዝም ማለት፡፡

መምህራን በመማር ማስተማር ሂደት ትግበራ ወቅት ችግሮች ከተከሰቱ ለችግሮቹ እልባት
ለማግኘት የማስተማር ሂደቱን በማስቆም ለጥቂት ደቂቃዎች ዝምታ በማስፈን የችግሩን
መፍትሔ አማርጠው ችግሩን ማስቆም/መከላከል / ይችላሉ፡፡

ሔ ችግር ፈጠሪ የሆነ ተማሪዎች ለያይቶ ማስቀመጥ፡፡

በመማሪያ ክፍል ውስጥ ተማሪዎች በጋራ/በጥንድ/ በመሆን የትምህርት ሂደቱን ሊያወውኩ


ይችላሉ፡፡ በዚህን ጊዜ መምህራን ችግር ፈጣሪ የሆነ ተማሪዎችን አብረው ከተቀመጡበት
በማለያየት ለየብቻ እንዲሆኑ አልያም ከነበሩበት ቦታ ወደ ሌላ መለወጥ እና በማስቀመጥ
መፍትሄን ሊያስገኙ ይችላሉ፡፡

9
መ, የተለያዩ የአሰራር ዘዴዎችን መጠቀም

ትምሀርት ሁል ጊዜ በተመሳሳይ የማስተማሪያ ስልት ሊተገበር የማይችል ተግባር ነው።


በመሆኑም መምህራን እንደየትምሀርት ይዘቱ ተዛማጅነት ያለው የማስተማሪያ ዘዴና የአሰራር
ስልት ቀርፀወ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ካደርጉም በተማሪዎቹ ዘንድ አላስፈላጊ ከሆነ
መደናገር እና መሰላቸት የሚነሳውን የከፍል ወስጥ ችግር መከላከል ይችላሉ፡፡

ሠ. የስርዓት ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች በቅርበት ማወያየት

እንዲህ አይነቱ ችግር ያለባቸወን ተማሪዎች በቅርበት ለማወያየት የችግራቸው መንስኤ ከምን
የመነጨ እንደሆነ በማየትና መፍትሔን በመስጠት ችግሩን መከላከል ይቻላል፡፡

ረ. በትምህርት ቤቱ ያለውን የስነስርዓት ህግን መጠቀም

አንዳንድ ችግሮች በመምህራን አቅም ብቻ ሊፈቱ የማይችሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዚህን ጊዜ


መምህራን በትምህርት ቤቱ የስነ ስርዓት ህግን መሰረት በማድረግ ለችግሮቹ መፍትሄ
ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

2.2. የተዛማጅ ፅሁፎች ቅኝት


«ማራኪና ወጤታማ የሆነ የመማር ማስተማር ተግባር ከክፍል አመራርና አደረጃጀት ጋር
በእጅጉ የተጣመረ ነው፡፡» ኢሎት (2000:379)፡፡ ከዚህ ሀሳብ ለመረዳት እንደሚቻለው የክፍል
ወስጥ አመራር ችሎታ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ስኬታማ ውጤትን ለማስመዝገብ
ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ያስረዳል፡፡ ለዚህም ሲባል ነው በተለያዩ ጊዜያት በክፍል አመራር
ዙሪያ ጥናት እና ምርምሮች የሚካሄዱት፡፡

ከዚህ ጥናታዊ ፅኁፍ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ስራዎች በ1998 በካሊስ ሀሰን እና በሰይድ
እንድሪስ ተሰርተዋል፡፡ ሁለቱንም ስራዎች ከዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር ያላቸው አንድነት እና
ልዩነት ለማሳየት ተሞክሯል፡፡

ካሊስ 1998 ከጅማ ዩኒቨርስቲ ከባዮሎጅ ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቀ|
ሲሆን። ለመመረቂያ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀው ጥናታዊ ፅሁፍም በጅማ ዞን በሰቃ ወረዳ በስቃ
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤ «በስቃ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክፍል ወስጥ አመራር
የሚያጋጥሙ ችግሮች» በሚል ርዕስ የቀረበ ነበር፡፡ ጥናቱ በዋናነት በትምህርት ቤቱ ያሉትን
የክፍል አመራር ችግሮች መመርመር እና የችግሮቹን መንስኤ በማወቅ የመፍትሄ ሀሳቦችን
ለመስጠት በአላማነት ሰንቆ የተነሳ ነበር። በመሆኑም ለጥናቱ ከተመረጡት አካላት መረጃዎቸን
በፅሁፍ መጠይቅ አማካኝነት በማስባሰብና የገላጭ የመተንተኛ ዘዴን ተጠቅሞ የችግሮችን

10
መንስኤዎች ተማሪዎች መሆናቸውን እና መምህራንም ተማሪዎች የባህሪ ለውጦችን
እንዲያመጡ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝቦ ጥናታዊ ፅሁፉን አጠናቋል።

የካሊስን ጥናታዊ ጽሁፍ ከዚህኛው የጥናታዊ ፅሁፍ ጋር ያላቸውን አንድነት እና ልዩነት


ሲነፃፀር የሚከተሉትን አንድነት እና ልዩነቶች ይኖራቸዋል፡፡ ሁለቱም ጥናቶች በተመሳሳይ
ክልል የተጠኑ መሆናቸው እና ሁለቱም በክፍል አመራር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መሆናቸው
ያመሳስላቸዋል፡፡ ነገር ግን የካሊስ ጥናት መሉ ትምህርት ቤቱን የሚያካትት መሆኑ፣ካሊስ
ለባውሉጅ ትምህርት ክፍል ያዘጋጀው መሆኑ፣ በዋናነት ችግሮችን መተንተን በመሻቱ፣
በመረጃ አስባሰቡና እንዲሁም በአመተ ምህረቱ በዋናነት ከዚህኛው ጥናታዊ ጽሁፍ ይለየዋል፡
ምክንያቱም ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ ለአማርኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል የሚዘጋጅ እና
በተወሰነ ትምህርት አይነትን የአተገባበር ሁኔታ ለመተንተን የተዘጋጀ መሆኑ እንዲሁም
መረጃዎች ከአንድ በላይ በሆነ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ተጠቅሞ ለመሰብሰብ እና ውጤት
ላይ ሊደርስበት የሚችል የ2011 ዓ.ም ስራ መሆኑ ነው::

ሰይድ እንድሪስ በ1998 ዓ.ም ለአማርኛ ቋንቋ ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል «በቦንጋ በጊንቦና
በሰጦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ እና አስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት
ክፍል አመራር ሁኔታ ትንተና በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ አዘጋጅቶ ነበር። የሰይድ ጥናታዊ
ፅሁፍም ከክፍል ውስጥ ስርዓትና ከተማሪዎች የትምህርት ተነሳሽነት ጋር ተዛማጅንት
ያላቸውን ጉዳዮች በማጥናት የመለየት እና የመፍትሄ ሀሳቦችንም የመጠቀም አላማ ያለው
ነው፡፡ ይህንንም ከግብ ለማድረስ ሲል መረጃዎችን በፅሁፍ መጠይቅ እና በምልከታ አማካኝነት
አሰባስቦ በመተንተን ችግሮቸን ለይቶ የመፍትሔ ሀሳቦችን ለመስጠት ሞክሯል፡፡

የሰይድ እንዲሪስን ጥናታዊ ፅሁፍ ከዚህኛው ጋር ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው በተመሳሳይ


የትህርት አይነት መስራታቸው፤ ማለትም በአማርኛ ቋንቋና ክፍለ ጊዜ መሆናቸው እንዲሁም
ሁለቱም የክፍል አመራር ሁኔታውን መተንተን መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ፅሁፎች
ከተዘጋጁበት ከሚጠነብት ቦታ አንፃር የተለያዩ መሆናቸው፤አንዲሁም የሰይድ ጥናት ከአንድ
በላይ ትምህርት ቤቶችን የሚያካልል መሆኑ እና ክ9-10ኛ ክፍል የሚጨምር መሆኑ እናም
የተጠናበት አመተ ምህረቱ አንፃር ከዚህኛው ጥናታዊ ፅሁፍ ጋር ልዩ ያደርጉታል፡፡

11
ምዕራፍ ሦስት

3 የጥናቱ ዘዴ እና አካሄድ
አጥኝው ለጥናቱ የመረጠው የምርምር ዘዴ ገላጭ የምርምር ዘዴን ነው። ይህ ዘዴ ክስተቶችን
ባለብት ተፈጥሮአዊ አካባቢ ለመመርመር እና ለችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ የሚያስችል
በመሆኑ ነው አጥኝው ይህንን ዘዴ የመረጠው።

3.1 ትምህርት ቤቱ ናሙና አወሳሰድ


ጥናቱ የተካሄደው በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በስምንተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን እና ተማሪዎ ላይ ነው። አጥኝው ለጥናቱ ይህንን
ትምህርት ቤት የመረጠበት ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

አጥኝው በማስተማር ስራ በትምህርት ቤቱ ቆይታ ስለነበረው ስለተማሪዎቹ አንፃራዊ የሆነ


ግንዛቤ ስላለው፡፡ እንደዚሁም ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በአንፃራዊ መልኩ የተሻለ ትብብር
አገኛለሁ ብሎ ስለሚገምት እና አመቺ ናሙና ለመውሰድ፡፡

3.1.1 የክፍል ደረጃ ናሙና አወሳሰድ


አጥኝው ጥናቱን 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው ያደረገው:: ይህንን ክፍል የመረጠበት
ምክንያትም የሚከተሉት ናቸው፡

የሚያስፈልገው የጊዜ የገንዘብ የሰው ሀይል እና ሌሎች ወጪዎችን አንፃር ሁሉንም


የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ማካለል ስለማይቻል፡፡

አጥኝው ለተግባር ልምምድ ወደ ትምህርት ቤቱ በሄደበት ጊዜ ልምምድ ያደረገው በ8ኛ


ክፍሎች ስልሆነ ከተማሪዎችም ሆነ ከመምህራኑ ጋር አብሮ ቆይታ አድርጓል ይህ ደግሞ
መረጃዎችን ለማግኘት ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር ነው፡፡

3.1.2. የተማሪዎ እና መምህራን ናሙና አወሳሰድ


በትምሀርት ቤቱ ሰባት የ8ኛ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም በአማካኝ ስልሳ ሁለት
ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን በድምሩ 496 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ይገኛሉ ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ ከተጠቀሱት 7 ክፍሎች ነሲብ የናሙና አወሳሰድ ዘዴን በመጠቀም
ከእያንዳንዱ ክፍል 2% ወይም አስር አስር ተማሪዎች ለመረጃ ሰጪነት ተወስደዋል።

መምህራኑ ከቁጥራቸው አንፃር አነስተኛ በመሆናቸው አጠቃላይ የናሙና አወሳሰድ ዘዴን


በመጠቀም በትምህርት ቤቱ ያሉትን ሶስቱንም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ለመረጃ
ስጭነት ተወስደዋል።

12
3.2 የመረጃ መሰብሰቢያ መረጣ
አጥኚው ለመረጃ መሰብሰቢያነት የተጠቀመው ሶስት ዓይነት የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን
ነው፡፡ እነርሱም ምልከታ ፣የዕሁፍ መጠይቅ እና ቃለ መጠይቅ ናቸው፡፡

3.2.1 ምልከታ
አጥኚው ጥናቱን ለማድረግ በመርጣቸው የ8ኛ ክፍሎች ካሉት አጠቃላይ ክፍሎች 30%
በሚሆኑት ወይም 3 ክፍሎች ለሶስት ያህል ጊዜያት በመግባት መደበኛ እና ኢ-መደበኛ በሆኑ
መንገዶች መረጃዎችን በምልከታ አስባሰቧል፡፡ መደበኛውን ምልከታ በሚያደርግበት ጊዜ
የአመራሩ ሁኔታ መሰረት በማድረግ የተዘጋጁ 30 ያህል ጥያቄዎችን በቅድመ ምልከት ቼክ
ሊስት አዘጋጅቶ ሁኔታዎችን እና ተግባራትን እየተከታተለ በሰንጠረኝt የሞላ ሲሆን ኢመደበኛ
ውን ግን ከመምህራኑ ጋር በመግባት ሁኔታዎችን እና ተግባራትን እየተከታተለ ማስታወሻ
የያዘበት ነው፡፡ በአጠቃላይ ይህንን የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴ ተጠቅሞ መረጃዎችን መሰባሰብ
የተፈለገበት ዋንኛ ምክንያቱ ከፅሁፍ መጠይቅ የሚገኘውን መረጃ ታአማኒነት ለማረጋገጥ
ሲባል ነው።

3.2.2 የፅሁፍ መጠይቅ


የጥናቱን አላማ መሰረት በማድረግ በጽሁፍ የተዚጋጁ መጠይቆችን በመጠቀም ከተማሪዎች
መረጃዎች ተስብስበዋል፡፡ እነዚህም የጽሁፍ መጠይቆች 15 ጥያቄዎችን የያዙ ሲሆን
ጥያቄዎቹም የመምህራኑንና የተማሪዎችን መማር ማረስተማር ሂደት ላይ ያሉትን ተግባራት
የሚዳስሱ ናቸው ጽሁፍ መጠይቆቹም በሚከተለው መልኩ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ዝግ ጥያቄዎች
(የምርጫ ጥያቄዎችን በመጠቀም እና ቅይጥ ጥያቄዎችን (የመረጃ ሰጪዎችን ከምርጫ
በተጨማሪ ልቅ መልሶችን ለሚሹ ጥያቄዎች መልክ የሰጡበት ነው።

3.2.3 ቃለ መጠይቅ
ይህ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ አጥኝው ከተጠቀመባቸው መረጃ ማሰባሰቢያዎች አንዱ ነው፡፡
በዚህም አማካኝነት ውሱን የሆነ ቃለ መጠይቆችን በመጠቀም ከመምህራን መረጃዎች
ተሰብስበዋል። እነዚህ የቃለ መጠይቅ መረጃዎች በመማር ማስተማር ሂደቱ ወቅት ያለውን
ምን እንደሚመስል እና በመማር ማስተማር ሂደቱ የመማር ክፍሎች የተማሪዎች ተሳትፎ
የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ካለ እንዲገልፁ የተደረገበት ነው፡፡ በዚህም አማካኝነት መረጃዎችን
በሚፈለገው መልኩ ማግኘት ተችሏል፡፡

3.3የመረጃ አተናተን
በ 3 ዓይነት መንገድ የተሰበሰበትን መረጃዎች አይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴን በመጠቀም
የተገኙ መረጃዎችን እንደ ተመሳሳይነታቸው የመላሾችን ብዛት በሰንጠረኝ በማሳየት
የመላሾችን መጠን እና መልሶቸውን በመተንተን ካለው ውጤት በመነሳት በመረጃዎቹ ላይ
ማጠቃለያ እና የመፍትሔ ሀሳብ ተሰጥተዋል፡፡

13
ምዕራፍ አራት

4 መረጃ ትንተና
በዚህ ምዕራፍ የጥናቱን ዓላማ መሰረት በማድረግ በተለያዩ መንገዶች ወይም ዘዴዎች ከመረጃ
ሰጪዎች የተገኙ መረጃዎች ተተንትነው ይቀርባሉ

4.1 ከተማሪዎች በፅሁፍ መጠይቅ የተገኘ መረጃ ትንተና


ለዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ መረጃዎችን ከተማሪዎች በፅሁፍ መጠይቅ አማካኝነት ተሰብስቧል።
እንዲሁም የፅሁፍ መጠይቆችን ታአማኒነት ለማረጋገጥ ይረዳ ዘንድ ታስቦ የተዘጋጀ የምልከታ
ውጤትም አለ። ስለዚህ እንዚህን የመረጃ ውጤቶች በሚከተለው መልከ እያመሳከሩ
ለመተንተን ተሞክሯል፡፡
ፆታ

48% ወንድ
52% ሴት

ስዕል 1 :ፆታ ስርጭት


ሠንጠረዥ 1 በመረጃ ሰጪነት የተሳተፉት ተማሪዎች አጠቃላይ መረጃ

ተለዋዋጭ ብዛት በመቶኛ


ፆታ ወንድ 37 52.4
ሴት 33 47.6
ድምር 70
እድሜ ከ 14 - 18 62 88.2
ከ 18 በላይ 8 11.8
ድምር 70

ከሰንጠረዥ ለመረዳት እንደሚቻለው ለመረጃ ሰጪነት 70 ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን


ከእነዚህም ውስጥ 37(52.4%) የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ የቀሩት 33(47.6%) ሴቶች ናቸው::
እንዲሁም ከእድሜ አንፃር ሲታይም ከአጠቃላዩ 62 (88.2%) የሚሆኑት እድሜያቸው ከ14-
18 በመሆን እርከን ውስጥ የሚገኙ ሲሆን 8(11.8%) የሚሆኑት እድሜያቸው ከ18 አመት

14
በላይ የሆናቸው ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ለመረጃ ሰጪነት የተሳተፉት ተማሪዎች በአብዛኛው
እድሜያቸው ከ15-18 ባለው እርከን የሚገኙ መሆናቸውን እና በአማካኝ ሁለቱም ጾታዎች |
በእኩል መሳተፋቸውን ነው፡፡

ሠንጠረዥ 2 ተማሪዎችን በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎ የሰጡት ምላሾች

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


1 ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አዎንታዊ 41 58.3
ያለህ/ሽ አመለካከት አሉታዊ 29 41.7
ድምር 70 100
2 በአማርኛ ትምህርት ክፍለ ቀርቼ አላውቅም 38 54.7
ጊዜ ቀርተው ብዙ ጊዜ አልቀረም 23 33.5
በአብዛኛው እቀራለሁ 8 11.8
ድምር 70 100

ከዚህ ስንጠዝ እንደምናየው ከተጠየቁት ተማሪዎች 41(58.2%) የሆኑት ለአማርኛ ቋንቋ


ትምህርት አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው ሲሆን የቀሩት 29(41.7%) ተማሪዎች አሉታዊ
አመለካከት እንዳላቸው ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ እንዲሁም ከተጠየቁት ተማሪዎች 38(54.7%)
የሚሆነት በአማርኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ቀርተው የማያውቁ ሲሆን 23(33.5%) የሚሆኑት
ደግሞ ብዙ ጊዜ የማይቀሩና 8(11.8%) ተማሪዎች በአብዛኛው የሚቀሩ መሆናቸውን ያሳያል።
በአጠቃላይ በዚህ ሠንጠረዥ መሰረት ለመረዳት የተቻለው አብዛኞቹ ተማሪዎች ለአማርኛ
ቋንቋ ትምህርት አዎንታዊ አመለካከት ያላቸውን መሆኑን እና በአብዛኞቹ በአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት ክፍለ ጊዜ ቀርተው የማያወቁ መሆናቸውን ነው፡፡

ሠንጠረዥ 3 የአማርኛ ቋንቋ መምህራኑን የጊዜ አጠቃቀም በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎች


የተሰጡ ምላሾች፡፡

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ

እስማማለሁ 33 46.7
የአማርኛ ቋንቋ መምህርህ/ሽ ጊዜን አልስማማም 37 53.3
በአግባቡ ይጠቀማሉ? የተለየ 0 0

15
ይህ መረጃ እንደሚያሳየው የአማርኛ ቋንቋ መምህሩ ጊዜን በአግባቡ እንደማይጠቀሙ
37(53.3) የሚሆኑት ተማሪዎች ሲገልፁ 33(46.7%) የሚሆኑት ተማሪዎች መምህራኑ ጊዜን
በአግባቡ ይጠቀማሉ በሚለው ሀሳብ ተስማምተዋል፡፡

ከዚህ ሀሳብ ጋር በተያያዘ በምልከታ የተገኘው ውጤት ስንደሚያሳየው መምህራኑ ከሞላ


ጎደል በጊዜ ወደ መማሪያ ክፍለ የሚመጡ ቢሆንም እንኳ ተግባራትን በጊዜ ከፋፍለው
ማሰራትን እና ጊዜውንም በአግባቡ የመጠቀም ሁኔታቸው ሲታይ መሻሻል የሚገባው ነው።
በአጠቃላይ ከእነዚህ በሁለት አይነት መልኩ ከተገኙት መረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው
የአማርኛ ቋንቋ መምህራነ ጊዜን በአግባቡ እንደማይጠቀሙ ነው፡፡

ሠንጥረዥ 4 መምህራኑ ወደ መማሪያ ክፍል ሲገቡ ያለው ሁኔታ በተመለከተ የቀረበ ጥያቄ
ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ
መምህርህ/ሽ ወደ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ይይዛሉ 8 11.8
ክፍል ሲገቡ ለተማሪዎች ተገቢውን ሰላምታ |ያቀርባሉ 61 87.6
ለትምህርት አሰጣጥ ምቹ ሁኔታዎችን 17 23.6
ለመፍጠር ይጥራሉ
የተለየ 123

ይህ መረጃ እንደሚያሳየው የአማርኛ ቋንቋ መምህር ወደ ከፍል ሲገቡ ለተማሪዎች ተገቢውን


ስላምታ እንደሚሰጡ 61(87.6%) ሲሆን 17(23.6%) ያህል ተማሪዎች ደግሞ ለትምህርት
ሂደት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ይጥራሉ የሚል መልስ መስጠታቸውን እና እንዲሁም
በ 8(11.8%) ተማሪዎች መምህራኑ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ይዘው እንደሚገቡ ገልፀዋል።

እንዲሁም የምልከታ ውጤት እንደሚያሳየው መምህራኑ ወደ መማሪያ ክፍል እንደገቡ


ለመማር ማስተማር ሂደት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት አነስተኛ መሆኑን
እና ምንም ዓይነት የመርጃ መሳሪያ አለመጠቀማቸውን ማየት መቻሉን ነው፡፡ በአጠቃላይ
እነዚህ ተግባራት ማስተማር ሂደቱን ምቹ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ቢሆኑም
መምህራኑ ወደ መማሪያ ክፍል ሲመጡ /ሲገቡ/ ሰላምታ ከመስጠት በዘለለ ሌሎቹን
እንደማይተገብሩዋቸው ማየት ተችሏል።

16
ሠንጠረዥ 5 በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚቀርበውን ይዘት በተመለከተ የቀረበ መጠይቅ

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


አዎ ነው 31 44.1
የአማርኛ ቋንቋ መምህርህ/ሽ በከፊል
የሚያቀርቡት ይዘት የተማሪውን ነው 27 38.2
አቅም ያማከለ ነው? አይደለም 12 17.6
የአማርኛ ቋንቋ መምህርህ/ሽ የሚያቀርቡት ይዘት የተማሪውን አቅም ያማከለ ነው? በሚል
ለተጠየቁት ጥያቄ 31(44.1%) ተማሪዎ አዎ ነው ሲሉ፤ 27(38.2%) በከፊል ነው
ማለታቸውን እና የቀሩት 12(17.6%) ተማሪዎች አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ
እንምንረዳው መምህራነ የሚያቀርቡት ይዘት የተማሪውን አቅም ያገናዘበ እንደሆነ ነው፡፡

ሠንጠረዥ 6 የመምህሩ የትምህርት አቀራረብ ሁኔታ በተመለከተ የቀረበ መጠይቅ

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


1 መምህርህ/ሽ የተለያዩ አዎ 10 14.7
የማሰተማሪያ በከፊል 20 28.8
ዘዴዎችን ይጠቀማሉ? አይጠቀሙም 40 56.5
2 መምህርህ/ሽ የተለያዩ አዎ 8 11.8
የማሰተማሪያ በከፊል 26 36.5
ዘዴዎችን ይጠቀማሉ? በጭራሽ አያሰሩም 36 51.8
3 መምህርህ/ሽ የተለያዩ አዎ 12 16.5
የማሰተማሪያ በከፊል 28 40.6
ዘዴዎችን ይጠቀማሉ? አይቃኙም 30 42.9

ከሠንጠረዥ እንደምንረዳው በጥያቄ ቁጥር 1 በቀረበው ጥያቄ 40(56.5%) የሚሆኑት


ተማሪዎች አይጠቀሙም የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን 20(28.8%) የሚሆኑት በከፊል
ይጠቀማሉ ማለታቸውን እና ቀሪዎች 10(14.7%) ተማሪዎች መምህራኑ የተለያዩ
ማስተማሪያ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በምልክታ ጊዜ መምህራነ የሚያቀርቡት ይዘት ጋር ተዛማጅነት ያለው


የማስተማሪያ ዘዴ የማይጠቀም መሆኑን እና በአብ፣ ጊዜውን በመፃፍ እና ማብራሪያ/ገልፃ/
በመስጠት የሚሸፍኑ መሆኑን ለማየት ትቸሏል። ባጠቃላይ እነዚህ በሁለት አይነት መንገድ
የተሰበሰቡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት መምህራኑ በመማር ማስተማር ሂደቱ ጊዜ ከይዘቱ
ጋር ተዛማጅ የሆነ ይአማስተማሪያ ስልት አለመተግበራቸው ነው።

17
መምህራኑተማሪዎቸን በቡድን ወይም በጥንድ ያሰራሉ/ በሚለው ትያቄ 36(51.8%)
ተማሪዎች በጭራሽ አያሰሩም ሲሉ 26(36.5%) ተማሪዎች ብበከፊል ያሰራሉ ማለታቸውን
እና 8(11.8%) ተማሪዎች መምህራኑ በቡድን እና በጥንድ እንደማያሰሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የምልከታ ውጤቱ እደሚያሳየው ከፊሎቹ መምህራን ምንም የቡድን ስራ ሲያሰሩ


አለመታየቱን እና አንዳንዶቹ ሁሉንም ተማሪ ያማከለ ባይሆንም በጥቂት ቦታ ብቻ የተወሰነ
የቡድን እና የጥንድ ስራዎችን ሲያሰሩ ማየት ተችሏል፡፡ ነገር ግን ከላይ ከተማሪዎች የተገኘው
ውጤት እና እንዲሁም የምልከታውም ቢሆን የመምህራኑን የቡድን ስራ የማሰራት
ተግባራቸውን እጅግ ዝቅ ያለ መሆኑን ያሳያል።

በዚህ ሠንጠረዥ መምህራኑ በቡድን ስራ ጊዜ እየተዘዋወሩ ተማሪዎችን ይቃኛሉ? በሚል


ለቀረበላቸው ጥያቄ 30(42.9%) ተማሪዎች አይቃኙም ሲሉ፤ 28(40.6%) ተማሪዎች በከፊል
ይቃኛሉ ማለታቸውን እና 12(16.5%) ተማሪዎች አዎ ይቃኛሉ የሚል መልስ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል በምልከታ የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው መምህራኑ ፊትለፊት ወንበር አከባቢ
የተቀመጡትን ተማሪዎች የሚመሰርቱትን ቡድን እንጂ ወደ መሀል በመግባት እንደማይቃኙ
የተገኘው መረጃ ይጠቁማሉ፡፡ በአጠቃላይ መምህራኑ በመማር ማስተማር ሂደቱ ጊዜ
በአንፃሩም ቢሆን የተመሰረቱትን በድኖች እየተዘዋወሩ አለመቃኘታቸውን ለመገንዘብ ተችሏል።

ሠንጠረዥ 7 በትምህርት ሂደቱ ጊዜ ተማሪዎች ለመምህራናቸው የሚያቀርቡት ጥያቄ


ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ለቀረበ ጥያቄ የተሰጡ ምላሾች

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


1 ለተማሪዎች ያልገባቸውን ጥያቄ በተገቢ አዎ 14 20.6
መንገድ ያስረዳሉ? በከፊል 26 36.5
አያስረዱም 30 42.9

ለተማሪዎ ያልገባቸውን ጥያቄ በተገቢ መንገድ ያስረዳሉ? በሚል በቀረበው ጥያቄ የሰንጠረዡ
ውጤት እንደሚያሳየው 30 (42.9%) ተማሪዎች አያስረዱም ሲሉ 26(36.5%) ተማሪዎች
በከፊል ያስረዳሉ የሚል ምልስ የሰጡ ሲሆን የቀሩት 14(20.6%) አዎ ያስረዳሉ የሚል
ምላሽ መስጠታቸውን ነው። በአጠቃላይ ይሀ ውጤት እንደሚያሳየው መምህራኑ ተማሪዎችን
በተገቢ መንገድ የማያስረዱ መሆናቸውን ነው።

ከዚህ በተጨማሪ በምልከታ የተገኘው ውጤት ጥቂት መምህራን በመማር ማስተማር ሂደቱ
ከአንዳንድ ተማሪዎች የሚነሱትን ጥያቄዎች የጎደለው እርምት እንደሚስጡ ማየት ተችሏል።

18
ሠንጠረዥ 8 በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለሚከስቱ የስርዓት ችግሮችን ለመከላከል የመምህሩን
ሚና በተመለከተ የቀረቡ ጥያቄዎች

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


1 መምህርህ/ሽ ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ 40 57
አይሰጡም
የክፍል ውስጥ መስተጋብራቸው 45 64
ከጥቂት ልጆች ጋር ብቻ ነው
በጥቂት ተማሪዎች ጥፋት 33 47
ሁሉንም ይወቅሳስ
የተለየ 0 0
2 መምህርህ/ሽ የስርዓት አዎ ይጠቀማሉ 25 35.3
ችግሮች ሲከሰቱ ለመከላከል
አይጠቀሙም 45 64.7
የተለያዩ ዘዴዎችን
ይጠቀማሉ?
3 ለጥያቄ ቁጥር 2 ምላሽህ/ሽ ችግር በፈጠሩ ተማሪዎች ላይ 0 0
አዎ ይጠቀማሉ ከሆነ ምን አካላዊ እርምጃ ለመውሰድ
አይነት ዘዴዎችን ነው እንዲታረሙ ማድረግ
የሚጠቁሙት? ተማሪዎችን ከመማርያ ከፍል 12 16.7
በማስወጣት እና ወላጅ
አስመጥቶ እርምት እንዲወስዱ
ማድረግ
የአቀማመጥ ቦታቸውን 58 83.3
በማለዋወጥ
የተለየ

ከላይ በሰንጠረዡ የቀረበው መረጃ እንደሚያመለከተው የአማርኛ ቋንቋ መምህራኑ የክፍል


ወስጥ መስተጋብራቸው ከጥቂት ልጀች ጋር ብቻ ነው የሚል ምላሽ በ 64% ተማሪዎች
የተገለፀ ሲሆን 57% የሚሆኑት ተማሪዎች ደግሞ መምህራኑ ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሔ
እይስጡም ማለታቸውን እና 47% የሚሆኑ ተማሪዎች በጥቂት ተማሪዎች ጥፋት ሁሉንም
ይወቅሳሉ በማለት ገልፀዋል፡፡ በአጠቃላይ ከተገኘው መረጃ ለመረዳት እንደሚቻለው እነዚህ

19
የተጠቀሱት ጉዳዮች ለመማር ማስተማር ሂደቱ የተሳካ ይሆን ዘንድ በተገቢ ሁኔታ መፈፀም
ያለባቸው ሆኖ ሳለ መምህራኑ ግን በአግባቡ እየተገበሩዎቸው አይደለም።

ከዚህም ጋር በተያያዘ በምልከታ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በመማሪያ ክፍል ውስጥ


በትምህርት ሂደቱ ጊዜ የሚከስቱ ችግሮችን ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረት አነስተኛ መሆኑን
እና በመማር ማስተማር ሂደቱ ጊዜ ሁሉን ተማሪዎች በእኩል እንደማያሳትፉ በአብዛኛው
ተመሳስይነት ያለው ተግባራቱን ሲፈፅሙ ማየት ተችሏል። ነገር ግን በጥቂት ተማሪዎች
ጥፋት ሁሉንም ይወቅሳሉ የሚለው ሀሳብ የምልከታው ውጤት በደረሰበት መረጃ መሰረት
የሚቃረን ሆነ ለማግኘት ተችሏል፡፡

በዚህ ሰንጠረዥ በጥያቄ ቁጥር 2 ላይ መምህርህ የስርዓት ችግሮች ሲከሰቱ ለመከላከል


የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ 64.7% ተማሪዎች አይጠቀሙም
የሚል መልስ የሰጡ ሲሆን 35.3% የሚሆኑት ደግሞ አዎ ይጠቀማሉ በማለት ገልፀዋል።
ከዚህም ጋር በተመሳሳይ የምልከታው መረጃ እንሚያሳየው መምህራኑ በአብዛኛው በመማሪያ
ክፍል ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል የሚያደርጓቸው ጥረቶች እምብዛም አመርቂ
አለመሆናቸውን ማየት ተችሏል።

በጥያቄ ቁጥር 3 የቀረበው መረጃ እንደሚያሳየው መምህራኑ ችግሮችን ለመከላከል የተለያዩ


ዘዴዎን ይጠቀማሉ ካሉት ተማሪዎች 83.3% የሚሆኑት የአቀማመጥ ቦታቸውን በማቀያየር
የሚል መልስ ሰጥተዋል የቀሩት 16.7% ተማሪዎች ከክፍል በማስወጣት እና ወላጅ
በማስመጣት የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ከሰንጠረዥ መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ መረጃ
እንደምረዳው መምህራኑ ችግሮችን ለመከላከል ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎቹ በአብዛኛው
የሚያዘወትሩት ችግር የፈጠሩትን ተማሪዎች ቦታቸውን በማዘዋወር በማቀያየር/ መሆኑን
ነው።

እንዲሁም ይህንን መሰረት በማድረግ ለተማሪዎች በአንተ አስተያየት በክፍል ውስጥ የስርዓት
ችግር ለሚፈጥሩ ተማሪዎች እንዴት ከዚያ ተግባራቸው መከላከል ይቻላል ትላለህ/ትያለሽ?
በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ አብዛኞቹ ተማሪዎች ተማሪዎችን ምክር በመምከር ከጥፋታቸው
እንዲታረመ ማድረግ ይቻላል የሚል ሀሳብ የሰጡ ሲሆን እንዲሁም በአንፃሩ

ጥቂተ ተማሪዎቹ የረበሹትን ተማሪዎች ከመማሪያ ክፍል በማስወጣት ሌሎቱን እንዳይረብሽ


በማድረግ መከላከል ይቻላል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

20
ሠንጠረዥ 9 የተማሪዎች ተሳትፎ በተመለከተ የቀረበ ጥያቄ

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


1 አብዛኛው አዎ 10 14.1
ተማሪዎች በከፊል 27 38.3
የተስጣቸውን አይጥሩም 33 47.6
ተግባራት
ለመስራት
ይጥራሉ?
2 ለጥያቄ ቁጥር ለትምህርቱ ያላቸው ፍቅር አነስተኛ 18 25
1 መልስህ በመሆኑ
አይጥሩም ለአማርኛ መምህር ያላችው አመለካከት 13 18.7
ከሆነ አነስተኛ በመሆኑ
ምክንያታቸው መምህሩ በተደጋጋሚ ክትትል እና 44 62.5
ምን ቁጥጥር ስለማያደርጉ
ይመስልሀል/ሸ መምህሩ ተማሪዎችን ተግባራት 48 68.8
እንዲሰሩ ስለማያነሳሱ
የተለየ 0 0

በዚህ መረጃ መሠረት ተማሪዎች የተሰጣቸውን ተግባራት ለመስራት እንደማይጥሩ በ 47.6%


ተማሪዎች የተገለፀ ሲሆን በ 38.3% ተማሪዎች ደግሞ ተማሪዎ በከፊል እንደሚጥሩ እና በ
14.1% ተማሪዎች ደግሞ አብዛኛው የክፍላቸው ተማሪዎች በተሰጣቸው ተግባር ላይ
ለመስራት ይጥራሉ በማለት መልሰዋል፡፡ የተሰጡትን ምላሾች ስናይ በአብዛኛው ተማሪዎች
የማይጥሩ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚህ ጋር በተመሳሳይ ለመምህራኑ በቀረበላቸው የቃለመጠይቅ ተማሪዎቹ በከፊል ተሳትፎ


እንዳያደርጉ ገልጸዋል።

ከላይ ከተጠቀሰው ጥያቄ ጋር በማያያዝ ለቀረበው የተማሪዎች ተሳትፎ አለማድረግ እንደ


ምክንያት የሚሆኑትን በሚከተለው መልኩ አስቀምጠዋል። በ 68.8% መምህራን ተማሪዎች
ተግባራትን እንዲሰሩ ስለማያነሳሱ፣62.5% መምህራን በተደጋጋሚ ክትትል እና ቁጥጥር
ስለማያድርጉ 25% ለትምህርቱ ያላቸው ፍቅና አነስተኛ በመሆኑ እና 18.7% የሚሆኑት
ለአማርኛ መምህር ያላችው አመለካከት አነስተኛ በመሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ሀሳብ

21
አንደምንረዳው ለተማሪዎች ተሳትፎ ማነስ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም እንኳ በይበልጥ
የመምህራኑ ተማሪዎችን አለማነሳሳት እና በትደጋጋሚ ክትትል እና ቁጥጥር አለማድረጋቸው
ዋንኛ ምክንያት እንሆነ ያሳያል።

ክዚህ ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለመምህራኑ በቃለ መጠይቅ ጊዜ ለተማሪዎች ተሳትፎ ማነስ


ምክንያቶች፣ ምን እንድሆኑ ሲጠየቁ የአማርኛ ቋንቋ ለተማሪዎች ሁለተኛ ቋንቋ መሆኑን
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በተማሩበት አከባቢ የአማርኛ ቋንቋ ባለመነገሩ ቋንቋውን
እንዳይለምዱ ተፅዕኖ ማሳደሩን እና በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ጋር የተገናኙት ከ5ኛ ክፍል
ጅምሮ ስለሆነ ብዙም ቋንቋውን ለመልመድ እድል ባለማግኘታቸው እና የፍላጎት ማነስ
የሚሉትን ጠቅሰዋል፡፡

4.2 ከመምህራን በቃለ መጠይቅ የተገኙ መረጃዎች ትንተና

ሠንጠረዥ 10 በመረጃ ሰጪነት የተሳተፉት መምህራን አጠቃላይ መረጃ

ተለዋዋጭ ብዛት በመቶኛ


ፆታ ወንድ 1 33.3
ሴት 2 66.7
ድምር 3
እድሜ ሰርተፊኬት 0 0
ዲፕሎማ 0 0
ዲግሪ 3 100
ያገልግሎት ዘመን ከ 0-5 ዓመት 0 0
ከ 6-10 ዓመት 0 0
ከ 10 ዓመት በላይ 3 100
ከላይ በሰንጠረዡ እንደተመለከትንው ለቃለ መጠይቅ የተወሰዱት መምህራን በ 66.7% ሌቶች
መሆናቸው እና የትምህርት ደረጃቸው የሶስቱም መምህራን ድግሪ እንደሆንና በአገልግሎት
ዘመን ሲታዩም ከ10 አመት በላይ ያገለገሉ እንደሆነ መረጃው ያሳያል፡፡

ሠንጠረዥ 11 ለመምህራኑ ስራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


ለሰራዎ ያሎት ፍቅር አዎንታዊ 3 100

አሉታዊ 0 0

22
ሰንጠረዡ እንደሚያመለክተው ለመረጃ ሰጪነት የተመረጡት መምህራን በሙሉ ለስራቸው
አዎንታዊ ፍቅር ያላቸው ናቸው፡፡

ሠንጠረዥ 12 የመማሪያ ክፍለ እና የተማሪዎችን ጥር ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር


ያለውን ተፅኖ በተመለከተ በቀረበ ጥያቄ የተሰጠ ምላሾች

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


1 የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎች ለመማር አዎ
ማስተማር ሂደቱ ምቹ ናቸው?
አይደለም 3 100
2 የተማሪዎች ቁጥር በትምህርት ክፍል ጊዜ አዎ
የአመራር ተፅዕኖ አሳድሯል?
አላሳደረም 3 100

በሰንጠረዡ የተጠቀሰው የተራ ቁጥር 1 መረጃ እንደሚያመለክተው የት/ቤቱ የመማሪያ


ክፍሎች በመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ አይደሉም ሲሉ ሁሉም መምህራን ገልፀዋል፡፡

በጥያቄ ቁጥር 1 የቀረበው ሀሳብ መሰረት በማድረግ መማሪያ ክፍሎቹ ያለባቸውን ችግሮቹ
ሲገልጽ የመቀመጫ ወንበሮቹ ሁኔታ፤ የከፍሉ ጥበት፣ በመማሪያ ክፍሎች በቂ የሆነ ብርሃን
አለመኖሩ፣ በተለይ ከሰዓት በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ሙቀት ያለው መሆኑ እና ወለሎቹ ምቹ
በሆነ ሁኔታ የተገነቡ አለመሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም ለዘረዘሯቸው ችግሮች ምን አይነት መፍትሔዎች ተጠቅመዋል? በሚል


ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ “በር እና መስኮቶች በመፋፈት አየር እንዲገባ በማድረግ
እንደዚሁም በተቻለ አቅም መቀመጫዎች ለአቀማመጥ ምቹ በማድረግ እና ሌሎችንም በአንፃሩ
ለመከላከል እንሞክራለን ማለታቸውን እና በኛ አቅም ልንከላከላቸው የማንችላቸው ችግሮችም
ለትምህርት ቤቱ አስተዳደሮች ሪፖርት አድርገናል” ብለዋል።

በዚህ ሰንጠረዝ ወስጥ ሌላው መልስ የተሰጠበት ጥያቄ የተማሪዎች ቁጥር በመማር ማስተማር
ሂደቱ ላይ የአመራር ተፅዕኖ አሳድሯል በሚል የተጠየቀው ነው:: ለዚህም ጥያቄ መልስ አዎ
አሳድሯል በሚለው መልስ የሚስማሙ መሆኑን ምርጃው ይጠቁማል።

ቀደም ሲል ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማለትም በተማሪዎች ቁጥር መብዛት የሚከሰቱትን ችግሮች


ለመከላከል ምን አይነት መፍትሄን ተጠቅመዋል በሚለው ከተማሪዎች ቁጥር መብዛትጋር
ተያይዞ ለሚመጡ ችግሮችን ለመከላከል እስከ አሁን እንደመፍትሄ ይሆናል ብለው
የሚያስቀምጡት ነገር እንደሌለ ገልፀዋል።

23
ሠንጠረዥ 13 የተማሪዎች ተሳትፎን በተመለከተ ለቀረበ ጥያቄ የተሰጠ ምላሾች

ተ.ቁ ጥያቄ አማራጮች ብዛት በመቶኛ


1 ተማሪዎች በአማርኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ አዎ 0 0
ተሳትፎ ያደርጋሉ? በከፊል 1 33.3
አያደርጉም 3 66.7
ይህ ስንጠረዥ እንደሚያሳየው ለመምህራኑ ተማሪዎች በአማርኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ
ተሳትፎ ያደርጋሉ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ 66.7% አያደርጉም የሚል መልስ ሲሰጡ
33.3% በከፊል ያደርጋሉ የሚል መልስ ሰጥተዋል። ስለዚህ የተገኙት መረጃዎን መሰረት
በማድረግ በት/ቤቱ የተማሪዎች ተሳትፎ ማነሱን ያሳያል።

ለመምህራኑ ለተማሪዎች ተሳትፎ ማነስ ምክንያት ምን ምን ናቸው? ተብለው ለተጠየቁት


ጥያቄ ሲመልሱ፤ በመምህራኑ የሚከተሉትን ሀሳቦች እንደምክንያት ይሆናሉ በማለት
ገልፀዋል። የአማርኛ ቋንቋ ሁለተኛ ቋንቋቸው ስለሆነ መናገር ስለሚፈሩ በአከባባያቸው
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በደንብ ስለማይነገር የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከ5ኛ ክፍል
የሚጀምሩ በመሆኑ ብዙም ቋንቋውን አለማዳበራቸው እና የተማሪዎቹ ፍላጎትም ማነስ ጭምር
ነው።ከዚህ ጋር በተያያዘም ለመምህራኑ ተማሪዎች እንዲሳተፉ ምን አይነት ማበረታቻዎችን
እንደሚጠቀሙ ሲጠየቁ የሰጡት መልስ በቋንቋው ሲናገሩ መፍራት እንደሌለባቸው እና ቋንቋ
በንግግር እና እርስ በርስ ተሳትፎ ብቻ ሊዳብር እንደሚችል በመንገር እና ቀላል እና አሳታፊ
ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦችን በማንሳት ተሳትፎአቸውን እንደሚያበረታቱ እና እንደሚያጠናክሩ
ገልፀዋል።

በአጠቃላይ በዚህ ምዕራፍ ከመረጃ ምንጮች የተገኙትን መረጃዎች ከላይ በተመለከተው መልኩ
ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ ስለሆነም በሚቀጥለው ምዕራፍ የጥናቱን አጠቃላይ ውጤት ምን
እንደሚመስል የሚገለፅበትና ለታዩት ችግሮቹም የመፍትሔ ሀሳብ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡

የተማሪዎች በአማርኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ተሳትፎ

አያደርጉም 66.7

በከፊል 33.3

አዎ 0

0 10 20 30 40 50 60 70 80

ስዕል 2፡የአብዲሳ ኣጋ የ 2011 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ክፍለ ጊዜ ተሳትፎ

24
ምዕራፍ አምስት

5. ማጠቃለያ እና የመፍትሄ ሃሳቦች


5.1. ማጠቃለያ
ይህ ጥናት በአብዲሳ ኣጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስምንተኛ
ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለ ጊዜ የክፍል ውስጥ አመራር ሁኔታ ትንተና በሚል
ርዕስ የተካሄደ ነው:: ስለሆነም ጥናቱ በዋናነት አላማ አድርጎ የያዘው በትምህርት ቤት
ስምንተኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አቀራረብ ሁኔታን መፈተሽ እና ተንትኖ ማሳየት
ነው::: ከዚህም ጋር በተያያዘ በአመራር ላይ ያሉትን ደካማ እና ጠንካራ ጎኖች ለይቶ በማሳየት
እና ችግሮችን በማውጣት ለችግሮቹ መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦችን ለመስጠት
ተሞክሮበታል፡፡

ለዚህ ጥናት እንደ መረጃ ምንጭነት የተወሰዱት የትምህርት ቤቱ ስምንተኛ ክፍል የአማርኛ
ቋንቋ መምህራኖች እና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው:: መምህራኑ በቁጥራቸው ትንሽ
በመሆናቸው እንዳለ የተወሰዱ ሲሆን ተማሪዎችን ግን ሙሉ በሙሉ ማካለል ስለማይቻል
ለናሙናነት ጥቂት ተማሪዎች ተወስደዋል።

ጥናቱን ለማካሄድ አጥኝው የተለያዩ የመረጃ ማሰባሰቢያ መሳሪያዎችን የተጠቀመ ሲሆን


እነሱም የፅሁፍ መጠይቅ፣ የቃለ መጠይቅ እና ምልከታ ናቸው፡፡ የፅሁፍ መጠይቁን ለመረጃ
ሰጪነት የተመረጡትን ተማሪዎች በመጠቀም መረጃ የተሰበሰበበት ሲሆን ፤ ቃለ መጠይቅ
በመጠቀም ከመምህራን መረጃዎች ተወስዷል፡፡ እንደዚሁም መምህራነ ለማስተማር
በሚገቡበት ጊዜ አስፈቅዶ በመግባት የመማር ማስተማር ሂደቱን በመከታተል ያለወን ሁኔታ
በማየት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ በተጠቀሱት የመረጃ ማሰባሰቢያ መሳሪያዎች የተገኙትን መረጃዎች አይነታዊ


የመረጃ መተንተኛ ዘዴን በመጠቀም ተተንትነው የተገኙትን መረጃዎች መሰረት በማድረግ
የተገኘውን ውጤት በሚከተለው መልክ ለማስቀመጥ ተሞክሯል።

በትምህርት ቤቱ የተሰበሰቡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ስምንተኛ ክፍሎች የአማርኛ


ቋንቋ መምህራን ለስራቸው ፍቅር ያላቸው መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ እንደዚሁም በስራው
አብዛኞቹ መምህራን ከአሰር አመታት በላይ ያገለገሉ መሆኑንም ከተገኙት መረጃዎች መረዳት

ተችሏል።

25
ምመህራኑ ለስራቸው ፍቅር እንዳላቸው የገለፁ ቢሆንም በመማር ማስተማር ሂደቱ ግን ይህን
ሊያሳይ የሚችል ሁኔታዎችን ሲፈፅሙ ማስተዋል አልተቻለም፡፡ ይህም ማለት በጊዜ ወደ
መማሪያ ክፍል አለመገኘት ለቋንቋ ትምህርት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የማይጥሩ

መሆናቸው እንደ እስፈላጊነቱ ተዛማጅ የሆኑ የመረጃ መሳሪያዎችን አለመጠቀማቸው


ከሚያቀርቡት ይዘት ጋር ተዛማጅ ሊሆን የሚቻል የማስተማሪያ ዘዴን አለመጠቀማቸው
ተጠቃሽ ደካማ ጎኖቻቸው ናቸው::

በመማር ማስተማር ሂደቱ ወስጥ ተማሪዎችን በግል እንደሚያሳትፉ እና የግል ስራዎችን


እንደሚያበረታቱ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ነገር ግን ለቋንቋ ትምህርት ግን እንዲህ
አይነቱ ተግባር የሚደገፍ አይደለም፡፡ በመሆኑም የተማሪዎችን የግል ተሳትፎ እንዳለ ሆና
በቡድንም እንዲሰሩ ማጠናከር ይኖርባቸዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ መምህራን ጥቂቶቹ
ተማሪዎችን በቡድን እና በጥንድ እንዲሰሩ የማያደርጉ መሆናቸውን እና ከሞላ ጎደልም ቢሆን
በጥንድ ወይም በቡድን የሚሰሩትን ተማሪዎች በመሀል በመግባት የሚያበረታቱ ናቸው::

በአጠቃላይ መምህራነ በመማርያ ክፍል ወስጥ የሚፈጸሙ የስርዓት ችግሮችን ለመከላከል


የሚያደርጓቸው ጥረቶች ከሚፈለገው በታች የሆነና ለችግሮች አፋጣኝ እርምጃ የማይወሰዱ
መሆኑን ከመረጃዎች ማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተማሪዎቹ ቋንቋውን በሚገባ መናገር አለመቻላቸው ለትምህርቱ


ያላቸውን ፍቅር አነስተኛ መሆኑ እና ለመምህሮቻቸው እምብዛም ክብር አለመስጠታቸው
በመማር ማስተማሩም ላይ እና በተሳትፎአቸው ማነስ ላይ አንዳች አሉታዊ ተፅዕኖን
አሳድሯል።

የመማሪያ ክፍሎች ስፋት ስለሚያንሳቸው ወይም ጠባብ በመሆናቸው በር እና መስኮታቸው


ወደ ክፍሎቹ በቂ የሆነ አየር እና ብርሃን የማያስገቡ በመሆኑ የመቀመጫው ሁኔታ እና
በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተመድበው የሚገኙት ተማሪዎች ቁጥር መብዛት ከታዩት ችግሮች
ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ያለውን የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የክፍል ውስጥ
አመራር ሁኔታ ሲፈተሽ ችግሮች እንዳሉበት ለማየት ተችሏል፡፡

26
5.2 የመፍትሔ ሀሳቦች
ምዕራፍ አራት የተተነተኑትን መረጃዎች መሠረት በማድረግ በዚህ ምዕራፍ መጀመሪያ ላይ
የማጠቃለያ ሀሳብ ለመስጠት ተሞክሯል። በመሆኑም በተሰጠው የማጠቃለያ ሀሳብ ውስጥ
ያሉትን ችግሮች መሰረት በማድረግ አጥኚው የሚከተሉትን የመፍትሔ ሀሳቦች ይሰነዝራል።

የአማርኛ ቋንቋ መምህራኑ፡

 የመማር ማስተማር ሂደቱን ከመጀመራቸው በፊት ለትምርት ሃደቱ ምቹ ሁኔታዎችን


መፍጠር ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ማለት የመማሪያ ክፍሎቹን በር እና መስኮቶች
በመክፈት በቂ የሆነ አየር እና ብርሃን ወደ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ በጥቁር ሰሌዳው
ላይ እንዲሁም ግድግዳው ላይ የተማሪዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ነገሮች ካሉ
ማስወገድ፡፡
 ለሚያቀርቡት የትምህርት ይዘት አመቺ የማስተማሪያ ዘዴን መጠቀም፣
 ተማሪዎችን በቡድን እንዲሰሩ ማድረግ እና እየተዘዋወሩ ቡድኖችን መቃኘት፣
 እንደ አስፈላጊነቱ አመቺ የመረጃ መሳሪያዎችን በመጠቀም ተማሪዎችን በቀላሉ
ለማስረዳት መሞከር
 የተማሪዎችን ተግባራት በቅርበት መከታተል እና መቆጣጠር
 የግል ችሎታቸውን እንደ አስፈላጊነቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ መጠቀም
 ችግሮችን በፍጥነት ማስወገድ ፣
 በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚከስቱ ችግሮችን ለመከላከል የምከር ዘዴን መጠቀም፣
 በሚያቀርቡት ይዘት ላይ ከሚደረግ በቂ ዝግጀት በተጨማሪ በራስ የመተማመን
ስሜትን ማጎልበት፣
 የተማሪዎችን ተሳትፎ ለመጨመር ችግሮቻቸውን በግል በመነጋግር ለመፍታት
መሞከር
 ቋንቋ በተደጋጋሚ ልምምድ ሊዳበር የሚቻል ነገር መሆኑን በመንገር የተማሪዎችን
ተሳትፎ እንዲቀጥል ማስቻል፡፡

እንደዚሁም የትምህርት ቤቱ ተጠሪዎች ወይም የሚመለከተው አካል የመማሪያ ክፍሎችን


በር መስኮት እና ወለል የመቀመጫ ወንበሮች እና ማስገደፊያ ጠረጴዛዎችን በተቻለ አቅም
ቢስተካከሉ በማጠቃለያ ሀሳብ ውስጥ የተዘረዘሩትን ችግሮች መቅረፍ ይቻላል፡፡

27
6.ዋቢ መጽሐፍት
Atklins J. (1995). Skills Development Methdology part 2 Addis Ababa: Adiss

Ababa University printing press.

Elliot et al. (1995). Educatuional Psychology Effective Teaching Effective


Learning (3d Ed.) Boston College: MC Grow-Hill Company.

Kallis Hassen. (2006). Challenges for Classroom Management in Seka High

School. (Unpublished)

Singh Amareget. (2003). Classroom Management, Aretlective Perspective


(2nded) New Dellhi Kaniska publisher distributer.

ሰይድ እንድሪስ፡፡ (1998)። በጊንቦ ቦስጦና በቦንጋ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ እና

አስረኛ ክፍሎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የክፍል አመራር ሁኔታ ትንተና፡፡(ያልታተመ)

ንጉሴ ሀብተየስና ብርሀኑ ብርቄ፡፡ (1991)፡፡ የስራ አመራር እና አስተዳደረር መርሆች ተግባሮች
እና ዘዴዎች፡፡ አዲስ አበባ፡ ሜጋ አሳታሚ ድርጅት፡፡

28
አባሪ አንድ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲስ፣ የቋንቋዎች ጥናት፣ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ኮሌጅ
የአማርኛ ቋንቋ፣ ስነፅሁፍና ፎክሎር ክፍለ ትምህርት

ለመምህራን የተዘጋጀ የቃለ መጠይቅ ቅፅ

የዚህ መጠይቅ አላማ በአበዲሳ ኣጋ አነደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ8ኛ ክፍሎች የአማርኛ
ቋንቋ ትምህርት አተገባበር ሁኔታን ለመተንተን የተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሁፍ መረጃን ለመሰብሰብ
ነው።

1. ፆታ ወ ____ ሴ _____

2. የመያ ደረጃ ሀ. ድግሪ__ ሊ. ዲፕሎማ ___ ሒ ሰርተፊኬት ___

3. በመምህርነት ለምን ያህል ጊዜ አገልግለዋል?

ሀ. 0-5 ዓመት

ሊ 6-10 ዓመት

ሒ ከ10 ዓመት በላይ

4.ለስራው ያልዎት ፍቅር

ሀ. አዎንታዊ___ ሊ አሉታዊ___

5. የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎች ለመማር ማስተማር ሂደት ምቹ ናቸው?

ሀ. አዎ ናቸው_______ ለ. አይደሉም________

6. ለጥያቄ ቁጥር 5 መልስዎ “አይደለም ከሆነ ምን ዓይነት ችግሮች አሉበት?

_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
__________________________________________።

7. በጥያቄ ቁጥር 6 ላይ ለዘረዘርዋቸው ችግሮች ምን ዓይነት መፍትሄዎችን ተጠቅመዋል?

29
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_______________________________________________________።

8. ተማሪዎች በአማርኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ተሳትፎ ያደርጋሉ?

ሀ. አዎ ያደርጋሉ________ለ. አያደርጉም______ ሐ. በከፊል ያደርጋሉ_____

9. ለጥያቄ ቁጥር 8 መልስዎ “አያደርጉም ከሆነ ምክንያቶቹ ምን ምንድናቸው?

_________________________________________________________________
____________________________________________።

10. ለተማሪዎች ተሳትፎ ምን ዓይነት ማበረታቻዎችን ይጠቀማሉ?

_________________________________________________________________
____________________________________________።

11. የተማሪዎቹ ቁጥር በትምህርቱ ክፍለ ጊዜው አመራር ላይ ተፅዕኖ ያሳድሯል ይላሉ?

ሀ.አዎ ያሳድራል __________ ለ. አያሳድርም_______________

12. ለጥያቄ ቁጥር 11 መልስዎ «ያሳድራል” ከሆነ ችግሮችን ለመከላከል ምን ዓይነት


መፍትሄዎችን ይጠቀማሉ?

_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
____________________________________።

30
አባሪ ሁለት
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲስ፣ የቋንቋዎች ጥናት፣ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ኮሌጅ
የአማርኛ ቋንቋ፣ ስነፅሁፍና ፎክሎር ክፍለ ትምህርት

በተማሪዎች የሚሞላ መጠይቅ

ይህ መጠይቅ አላማው በአበዲሳ ኣጋ አነደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ8ኛ ክፍሎች የአማርኛ


ቋንቋ ትምህርት የክፍል ውስጥ አመራር ሁኔታን ለመተንተን ለተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሁፍ
መረጃዎችን ለማሰባሰቢያነት የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች በቀረቡት ጥያቄዎች
ተገቢውን ምላሽ ይሆናል ያልከውን /ሽውን መልስ ከአማራጩ ፊት ለፊት ባለው መስመር
ላይ ምልክት አድርግ/አድርጊ፡፡

ለትብብርህ/ሽ ምስጋናዬ ከልብ ነው!

ማሳሰቢያ፡- በመጠይቁ ቅዕ ላይ ስም አይፃፍም::

ሀ. ጥቅል መረጃ የሚሹ መጠይቆች

1. ፆታ ወ________ ሴ___________

2. እድሜ ከ14-18 ____ ከ18 በላይ________

ለ ዝርዝር መረጃ የሚሹ ጥያቄዎች

1. ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያለህ አመለካከት

ሀ. አዎንታዊ _______ ለ አሉታዊ_____

2. በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለ ጊዜ

ሀ. ብዙን ጊዜ አልቀርም_____ ለ. ቀርቼ አላውቅም_____ሒ በአብዛኛው እቀራለሁ_______

3 የአማርኛ ቋንቋ መምህርህ/ሽ ጊዜን በአግባቡ ይጠቀማሉ?

ሀ. እስማማለሁ___________ ለ. አልስማማም_______ ሐ.የተለየ_________

4 መምህርህ/ሽ ወደ ክፍል ሲገቡ

ሀ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ይይዛሉ______ሊ ለተማሪዎች ተገቢውን ሰላምታ ይሰጣል____

ሐ.ለትምህርት አሰጣጥ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ይጥራሉ________

መ. የተለየ__________________________

31
5. መምህርሽ/ህ ተማሪዎችን በጥንድ እና በቡድን ያስራሉ?

ሀ. አዎ ያሰራሉ________ ሊ በከፊሉ ያሰራሉ__________ሒ በጭራሽ አያሰሩም_____

6 የአማርኛ ቋንቋ መምህርሽ/ህ የሚያቀርቡት ይዘት የተማሪውን አቅም ያማከለ ነው

ሀ. አዎ ነው _____ለ.በከፊል ነው______ሐ.አይደለም________

7. መምህርሽ/ህ የተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ?

ሀ. አዎ ይጠቀማሉ______ሊ በከፊል ይጠቀማሉ______ሒ አይጠቀመም_______

8. መምህርሽ/ህ

ሀ. የክፍል ወስጥ መስተጋብራቸው ከጥቂት ልጆች ጋር ብቻ ነው።________

ሊ ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ አይስጡም፡፡______________

ሒ በጥቂት ተማሪዎ ጥፋት ሁሉንም ይወቅሳሉ፡፡____________

መ. የተለየ________________________________

9. ተማሪዎች ያልገባቸውን ሐሳብ በተገቢ መንገድ ያስረዳሉ? _

ሀ.አዎ ያስረዳሉ_________ሊ በከፊል ያስረዳሉ____________ሐአያስረዱም_________

10. መምህርሽ/ህ በቡድን ስራ ወቅት ተማሪዎችን እየዞሩ ይቃኛሉ?

ሀ.አዎ ይቃኛሉ________ ሊ በከፊል ይቃኛሉ________ሒ አይቃኝም______________

11 መምህርሽ/ህ የስርዓት ችግሮች ሲከሰቱ ለመከላከል የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ።

ሀ. አዎ ይጠቀማሉ__________ ሊ. አይጠቀሙም_____________

12.ለጥያቄ ቁጥር 1 ምላሽህ/ህ «አዎ» ከሆነ ምን አይነት ዘዴ ነው የሚጠቀሙት

ሀ ችግር በፈጠሩ ተማሪዎች ላይ አካላዊ እርምጃ በመውሰድ እንዲታረሙ ማድረግ________

ለ ተማሪዎቹን ከመማሪያ ክፍል በማስወጣት ወላጅ በማስመጣት እርምት እንዲወስዱ

ማድረግ________________

ሔ የአቀማመጥ ቦታቸውን በማቀያየር____________________

መ. የተለየ_______________________

32
13.በአንተ /ቺ አስተያየት በክፍል ውስጥ የስርዓት ችግር ለሚፈጥሩ ተማሪዎች እንዴት ከዚህ

ተግባራቸው መከላከል ይቻላል ትላለህ/ትያለሽ?

_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________________________________________
_________________________________።

14. አብዛኛው የክፍልህ/ሽ ተማሪዎች የተሰጡአቸውን ተግባራት ለመስራት ይጥራሉ?

ሀ.አዎ ይጥራሉ_______ ሊ በከፊል ይጥራሉ_________ሐ. በጭራሽ አይጥሩም________

15. ለጥያቄ ቁጥር 14 ምላሽሀ/ህ «አይሰሩም» ከሆነ ምክንያታቸው ምን ይመስልሻልሃል?

ሀ. ለትምህርቱ ያላቸው ፍቅር አነስተኛ በመሆኑ_________________

ሊ. ለአማርኛ መምህር ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ በመሆኑ_______________

ሐ. መምህሩ በተደጋጋሚ ክትትል እና ቁጥጥር ስለማያደርጉ___________________

መ መምህሩ ተማሪዎች ተግባራትን እንዲሰሩ ስለማያነሳሳቸው________________

ሰ የተለየ______________________________________

33
ደብዳቤዎች

34

You might also like