You are on page 1of 88

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት

(ለማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች የማሰልጠኛ ማንዋል)

አዘጋጆች፡- ደሳለው ጌትነት

ሐይማኖት ጌታቸው

አርታዒ፡- ኤርሚያስ ፀጋዬ

ጥር 2009 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

i
ማውጫ
አርዕስት ገፅ

መግቢያ............................................................................................................................ 1
የስልጠናው ዓላማ ............................................................................................................. 4
ክፍል አንድ ...................................................................................................................... 5
1.የልማታዊ ጋዜጠኝነት ንድፈ ሃሳብና የማህበረሰብ ሚዲያ ................................................... 5
1.1 የማህበረሰብ ሚዲያ ምንድን ነው? ...................................................................................... 6
1.2 ልማታዊ ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነው? .................................................................. 7
ክፍል ሁለት ..................................................................................................................... 9
2.የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት .................................................................................. 9
2.1 ዜና ........................................................................................................................... 9
2.1.1 ዜና ምንድን ነው?............................................................................................................. 9
2.1.2 የዜና ዓይነቶች ................................................................................................................. 11
2.1.3 የዜና ጠቀሜታዎች ......................................................................................................... 13
2.1.4 የዜና ጥንካሬዎችና ድክመቶች........................................................................................ 14
2.1.5 የዜና መመዘኛ እሴቶች .............................................................................................. 15
2.1.6 የዜና አላባውያን .............................................................................................................. 22
2.2 የዜና ምንጮች .................................................................................................................... 27
2.2.1 ዜና ከየት ይገኛል? ...................................................................................................... 27
2.2.2 የዜና ምንጮች............................................................................................................. 28
2.2.3 የዜና ምንጮች አያያዝ ................................................................................................ 30
2.2.4 መረጃ እንዴት ይገኛል? .............................................................................................. 32
ሀ. ምልከታ ............................................................................................................................ 32
ለ. ቃለ መጠይቅ .................................................................................................................... 39
ሐ. ምርምርና ጥናት.............................................................................................................. 48
2.3 የዜና አፃፃፍ ስልት.............................................................................................................. 48
2.3.1 የዜና ቋንቋ................................................................................................................... 49
2.3.2 መሪ አንቀፅ (Lead) .................................................................................................... 52
2.3.3 የአርስተ ዜና አፃፃፍ .................................................................................................... 53
2.3.4 የዜና መዋቅር .............................................................................................................. 54

i
2.3.5 የሬዲዮ የዜና አፃጻፍ ፎርማቶች ................................................................................. 57
2.3.5 የሬዲዮ ዜና አፃጻፍ ደንቦች ......................................................................................... 63
3. የሬዲዮ ፕሮግራም ...................................................................................................... 65
3.1 የሬዲዮ ፕሮግራም ማለት ምን ማለት ነው? .................................................................... 65
3.2 የሬዲዮ ፕሮግራም ዓይነቶች .............................................................................................. 65
3.2.1 የማስተማርያ ፕሮግራም ............................................................................................. 65
3.2.2 የማሳወቂያ ፕሮግራም................................................................................................. 66
3.2.3 የመዝናኛ ፕሮግራም ................................................................................................... 66
3.3 የሬዲዮ ፕሮግራም ባህርያት .............................................................................................. 67
3.4 የሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት ................................................................................................ 68
3.4.1 የቅድመ-ዝግጅት ምዕራፍ............................................................................................ 69
3.4.2 የዝግጅት ምዕራፍ ....................................................................................................... 73
3.4.1 የድህረ ዝግጅት ምዕራፍ ............................................................................................. 74
ዋቢ መፅሐፍት ............................................................................................................... 75
አባሪ፡- የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮፖዛል አዘገጃጀት ................................................................. 76

ii
መግቢያ

የጋዜጠኝነትን ፅንሰ-ሃሳብ በተለያየ መልኩ የሚተረጉሙ ብዙ አካላት አሉ፡፡ ይኸውም


ከጋዜጠኝነት ጋር ባላቸው ቅርበትና ለጋዜጠኝነት ካላቸው አመላካከት የመነጨ ነው፡፡
ለጋዜጠኝነት የተለያየ ትርጓሜ ቢኖረውም ትርጉሞቹ የተወራረሰ ባህሪ አላቸው፡፡
ከነዚህም ትርጉሞች ውስጥ አንዳንዶቹን ለመጠቃቀስ የሚከተለው ትርጓሜ አንዱ ነው፡፡
ጋዜጠኝነት ማለት መረጃዎችን ከምንጮቻቸው የመሰብሰብ፣ በዜና፣ መጣጥፍና ሃተታ
መልክ በማዘጋጀት በብዙሃን መገናኛ የማሰራጨት ሙያዊ ጥበብ ነው፡፡ ብዙሃን መገናኛ
ስንል ሰሌዳ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችን፣ በራሪ ወረቀቶችን፣ የቢሮ ውስጥ
ህትመቶችን፣ ጋዜጣ፣ መፅሔት፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣መፅሐፍ፣ ፊልምና የመሳሰሉትን
ያጠቃልላል፡፡ ይህም ማለት ጋዜጠኝነት በነዚህ ብዙሃን መገናኛ አማካኝነት መረጃን
ከመረጃው ባለቤት ወደ አንባቢው፣ አድማጩ ወይም ተመልካቹ በተለየ አዘገጃጀት
የማቅረብ ጥበብ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት የሚለውን ቃል መጀመሪያ አካባቢ የሚያገለግለው
ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን በጋዜጣ አትሞ ማውጣት ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት
ጋዜጠኝነት በጣም ሰፊ የሆነ አውድ አለው፡፡ ይኸውም ከብሮድካስትና ዌብሳይት ሚዲያ
መጀመር ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡

በሌላ መልኩ ጋዜጠኝነት መረጃን ቆፍሮና እውነታውን አጣርቶ ሁነቶችን፣ ጉዳዮችንና


ሂደቶችና ከብዙሃኑ ህዝብ በጋዜጣ፣ በመፅሔት፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣በኢንተርኔት
እና በመሳሰሉት ማዳረስ የሚቻልበት የሙያ ዘርፍ ሲሆን በዋናነት መረጃን የመሰብሰብ፣
የማጠናከር፣ የመፃፍ፣ አርትዖት ሥራ የመስራት፣ ፎቶግራፍ የማንሳት፣ የህትመት
የዲዛይን ሥራን እና የማሰራጨት ሥራዎችን አካቶ የያዘ ሙያ ነው፡፡

ህብረተሰቡ መረጃ የማድረስ ዓላማ በመያዝ ጋዜጠኝነት ግለሰቦችን፣ ድርጅቶችን፣


ተቋማትን፣ መንግስትንና የንግድ ተቋማትን እንዲሁም ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ላይ
ትኩረት አድርጎ ሽፋን የሚሰጥ ሙያ ነው፡፡

በህንድ አገር የጋዜጠኝነት አባት በመባል የሚታወቁት ፕሮፌሰር ፓታን ዳሊ ሰፒ


ስለጋዜጠኝነት ሲናገሩ፡-

1
ጋዜጠኝነት ሰውን ልጅ ሰብዓዊ መብት የሚያስከብር፣ የታመነ
የዲሞክራሲ ስርዓት አራማጅ እንዲሁም የፍትህ ርትዕ ጠበቃና የህዝብ
ድምፅ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት በነፃ ሃሳብን የመግለጫ መሳሪያ፣ እንዲሁም
የህሊናን ነፃነት ማዳበሪያ ፍቱን ማስተላለፊያ መሳሪያ በመሆኑ
በህብረተሰብ የሙያ ዝርዝሮች ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ መያዝ የሚገባው
ተግባር ነው፡፡

እንደህንዳዊው ፕሮፌሰር ጋዜጠኝነት ከምንም በላይ ከራስ ጥቅም በፊት የማህበረሰባዊ


ጥቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ድምፅ አልባ ለሆኑ
የማህበረሰብ አካላት ድምፅ መሆን መቻል ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና
ለህግ መከበር ከፍተኛ የሆነ ሥራ የሚሰራ የሥራ መስክ ነው፡፡

የጋዜጠኝነት ዋነኛ የስራ ማሳያ የሆኑት የብዙሃን መገናኛዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ብዙሃን
መገናኛዎች ህዝባዊ የሆኑ ጉዳዮችን በመረጃና በአስተያየት ተቀሽረው የሚቀርቡበት
ነው፡፡ ጋዜጠኝነት መረጃን ጥሩውን ከድፍርሱ፣ ምርቱን ከእንክርዳዱ በመለየት
መረጃዎችን፣ አስተያየቶችን እና ሁነቶችን ከህብረተሰቡ ለህብረተሰቡ የማሰራጨት ስራ
ነው፡፡

ጋዜጠኝነት ሁነቶችን፣ ሃሳቦችን፣ መረጃዎችን እና ተቃርኖዎችን በየአውዳቸው


እየመረጠ የማስቀመጥና የማቅረብ ተግባርን የያዘ ሙያ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት
የድርጊቶችንና አስተያየቶችን እውነትን፣ ውክልናቸውንና ጠቀሜታቸውን በመገምገም
የሚቀርብበት የሙያ ዘርፍ ሲሆን የማያቋርጥ ሂደትም ጭምር ነው፡፡ የማያቋርጥ
ሂደት ሲባል ደግሞ ዓለም እስካለች ድረስ የመረጃ ፍሰት ከአንዱ የዓለማችን ክፍል ወደ
ሌላው የሚያደርገው ጉዞ ስለማይነጥፍ በመሆኑ ነው፡፡

በአጠቃላይ ጋዜጠኝነት ለዜና፣ ለመጣጥፍና ለሃተታ የሚሆኑ ጉዳዮችን ከምንጫቸው


የማሰባሰብ፣ የማዘጋጀትና በበራሪ ፅሁፎች፣ በሚበተኑ ወረቀቶች፣በጋዜጦች፣
በመፅሔቶች፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በማህበራዊ ድረ ገፅ የብዙሃን መገናኛዎች
የማሰራጨት ሙያዊ ሂደት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የጋዜጠኝነትን ትርጉም ከብዙሃን
መገናኛ ጋር በተለይም ከብሮድካስት የሚዲያ ዘርፍ ጋር አያይዘው ያዩታል፡፡ ለዛም ነው
አንድ ግለሰብ ጋዜጠኛ ነኝ ሲል በቀጥታ ከቴሌቪዥን ወይም ከሬዲዮ ተቋም እንደመጣ

2
አድርገን የምንወስደው፡፡ ነገር ግን ጋዜጠኝነት ሁልጊዜም ከብዙሃን መገናኛ ጋር ብቻ
ማሰብ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው፡፡ ምክንያቱም ብዙሃን መገናኛ የመረጃ ማስተላለፊ መንገድ
እንጂ በራሱ የጋዜጠኝነት ሙያ አይደለም፡፡ ስለዚህ በበራሪ ወረቀቶች፣ በማስታወቂያ
ሰሌዳዎች፣ በመስሪያ ቤት ህትመቶች ወዘተ የሚሰራጩ መረጃዎች በጋዜጠኝነት ዘውግ
ውስጥ ይከናወናሉ፡፡

በሬድዮ የሚደረግ የጋዜጠኝነት /የሚዲያ / አተገባበር በድምፅ የሚደረግ የቃላት ጨዋታ


ነው፡፡ በታሪካዊ አመጣጣቸው ሲታዩ ቴሌቭዥን ሬድዮን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ እንዲህ
በመሆኑም ብዙ የብዙኅን መገናኛ ጠቢባን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቴሌቭዥን እየተወደደ
በመሄዱ ሬድዮ የመሞት እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ብዙ
የጋዜጠኝነት አጥኝዎች ፍላጎታቸው ወደ ቴሌቭዥን እያጋደለ የመሄድ አዝማምያ
አሳይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የጠቢባኑ መላምት ሳይሆን ቀርቶ ሬድዮ እስከ አሁን በጣም
ተወዳጅና ተደማጭ የብዙኅን መገናኛ ዓይነት ነው፡፡ በተለይ ሬድዮ የኤሌክትሪክ
መብራት ሀይል ባላገኙ የገጠር አከባቢዎች በጣም ተፈላጊና ተመራጥ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ሬድዮ የሚያዳምጡበት ምክንያት ምን እየተደረገ ምን እየሆነ እና ነገሮች


ምን እንደሚመስሉ በአፋጣኝ ለማወቅ ሲፈልጉ ነው፡፡ ሬድዮ አንድ ድርጊት ሲፈፀም
ወይ ሲከወን ወድያው በፍጥነት /in speed/ ለአድማጮች ያደርሳል፡፡ ይህ አንዱ
የሬድዮ ባህርይ ነው፡፡ ሬድዮ እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ተመራጭ ከሚያደርጉት
ነገሮች አንደኛ ከቦታ ወደ ቦታ ይዞ ለመንቀሳቀስ /being portable) ሁለተኛ ሬድዮን
እያዳመጥክ ሌላ ተጓዳኝ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ ሌላው የሬድዮ እንደ ብዙኅን መገናኛ
ተመራጭ የሚዲያደርገው የሰው ሃይል ብዛት ቆጣቢነቱ ነው፡፡ ይህ ሲባል በሬድዮ
ለሚደረግ የመረጃ ስርጭት አንድ ሰው ከስልክ በሚመጡ ብዙ ሃሳቦች ሊያስተናግድ
ይችላል፡፡ የካሜራ የመብራት ባለሞያዎች ላያስፈልጉ ይችላሉ፡፡

ይህ የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ማንዋል ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች


አሉት፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ስለማህበረሰብ ሬዲዮ ጠቅላላ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ
ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ለማህበረሰብ ሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አሰራር ላይ
ዝርዝር ገለፃ ይሰጣል፡፡

3
የስልጠናው ዓላማ

የዚህ ሥልጠና ዓበይት ግቡ የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎችን የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራሞችን


ሙያዊና ስኬታማ በሆነ መንገድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ማስቻል ሲሆን ሰልጣኞች ይህንን
ስልጠና ሲያጠናቅቁ የሚከተሉት ክህሎቶች ይኖሯቸዋል፡፡

 የማህበረሰብ ሬዲዮ ምንነትን ያውቃሉ፤


 ለማህበረሰብ ሬዲዮ የሚሆን ዜናን ያዘጋጃሉ፤
 የመረጃ ምንጮችን አያያዝ ያውቃሉ፤
 የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን ይለያሉ፤
 የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን ተጠቅመው መረጃን ይሰበስባሉ፤
 የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮፖዛሎችን ማዘጋጀት ይችላሉ፤
 ሬዲዮ ፕሮግራሞችን ያቀርባሉ፤
 ዜናና ፕሮግራሞችን በስቱዲዮ ውስጥ ማንበብ ይችላሉ፤

4
ክፍል አንድ

1. የልማታዊ ጋዜጠኝነት ንድፈ ሃሳብና የማህበረሰብ ሚዲያ

በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን የብዙሃን መገናኛ ተቋማት ዋነኛ የልማት ደጋፊ እንደሆነ
ይታመናል፡፡ ልማት ማለት ምን ማለት ነው የሚለው ጉዳይ የተለያዩ ዓይነት
ትርጓሜዎች ቢሰጠውም አሜሪካዊ ምሁር ሮጀርስ (1976) ልማት ምን እንደሆነ
የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቷል፡፡

ልማት ማለት በማህበረሰቡ ውስጥ ማህበራዊ ለውጥ የሚያመጣ አሳታፊ


የማህበራዊና የማቴሪያል ልቀት በማምጣት አብዛኛውን የማህበረሰብ
ክፍል በአካባቢው ላይ ተቆጣጣሪና ከአካባቢው ተጠቃሚ የሚያደርግ
ሂደት ነው፡፡

ከሮጀርስ ትርጉም መረዳት የሚቻለው ልማት ማለት ሂደት ነው፤ ልማት ማለት
ማህበራዊ ለውጥን ያመጣል፣ ልማት ማለት አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል
ይጠቅማል፣ ልማት ማለት መሻሻል ነው፡፡

ልማትን በተመለከተ ለረዥም ጊዜ ሁለት ዓበይት አስተሳሰቦች ብቻ ነበሩ፡፡ ይኌም


ዘመናዊነት (Modernaization paradigm) ና ጥገኝነት (Dependecy paradigm)
ናቸው፡፡ ሁለቱ ፅንፍ አስተሳሰቦች ልማትን በማምጣት ድሃ የዓለማችን ክፍሎችን
ማሳደግ የሚቻልበት ሁኔታ በተለያየ መንገድ ቀይሰዋል፡፡ የዘመናዊነት አስተሳሰብ ለድሃ
አገሮች መሰረታዊ ችግራቸው ኋላቀርነታቸው ሲሆን ማደግ የሚችሉት ምዕራባውያን
አገሮች በሚሰጧቸው እርዳታ ዝግመታዊ በሆነ መልኩ ይለማሉ የሚል ነው፡፡ በአንፃሩ
የጥገኝነት አስተሳሰብ አራማጆች የሚሉት የደሃ ሃገሮች ችግር የምዕራባውያን ቅኝ
ግዛትና ጭቆና ነው ስለሆነም መፍትሄው የእነሱን እርዳታ መቀበል ሳይሆን ከእነሱ ጋር

5
ያለውን ግንኙነት በማቋረጥ ለራስ መስራት ነው ይላሉ፡፡ በዚህ መሃል የሁለቱ ፅንፍ
የወጣ አስተምህሮ ዓለማችን በግሎባላይዜሽን ዘመን አንዱ ለአንዱ አስፈላጊ ስለሆነ
የሚያስሄድ ስላልሆነ ሶስተኛ አማራጭ “ሌላው አስተምሮ” የሚል የሶስተኛ ዓለም
ሃገራት ፈጠሩ፡፡ ይህ አስተምሮ ልማትን ማየት የሚፈልግበት ዕይታ ልማት መጀመር
ያለበት ታች ካለው ተራ ህዝብ ሲሆን የሃገሩን ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሥነ-ምህዳሩን
በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ ስለዚህ ይህንን አማራጭ በመያዝ ማህበረሰብን
ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ሲሰሩ በዋናነት የሚከተሉት ማህበረሰቡን
ያሳተፈና ተጠቃሚ የሚያደርግ አካሄድን መሆን ይኖርበታል፡፡ ተራውን የማህበረሰብ
ክፍል ለማሳተፍ ደግሞ የመረጃ ተደራሽነት በዘልማዳዊው ሚዲያ አስቸጋሪ ስለሚሆን
የማህበረሰብ ሚዲያ ወይም የማህበረብ አገልግሎት የሚሰጡ የሬዲዮ ጣቢያዎች
በየአካባቢው መኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.1 የማህበረሰብ ሚዲያ ምንድን ነው?


በአሁኑ ሰዓት የማህበረሰብ ሚዲያ በተደራሽነቱና በሚሰጠው አገልግሎት
ከመንግስታትና ከልማት ድርጅቶች በሰፊው ዕውቅናን እያተረፈ ይገኛል፡፡ ምክንያም ይህ
የሚዲያ ዘርፍ በዋናነት ድምፅ አልባ የነበሩትን ደሃና የተገለሉ/ የተረሱ የማህበረሰብ
ክፍሎችን ድምጽ የሚሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ የማህበረሰብ ሚዲያ የለውጥ አካል ሲሆን
በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ-ልቦናዊ ለውጦች እንዲመጡ
ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ ይህ ሚዲያ ለአካባቢው ተራ የማህበረሰብ ክፍሎች
የውይይት መድረክን በመክፈት ድምጻቸው እንዲሰማ በማድረግ ያገለግላል፡፡ ይህ ሚዲያ
የሚቋቋመው ለማህበረሰቡ ሲሆን የሚያስተዳድረውም የሚደግፈውም ራሱ ማህበረሰቡ
ነው፡፡ የማህበረሰብ ሚዲያ አካባቢያዊነት፣ የብዙሃን ተሳትፎ፣ እና የለውጥ ተምሳሌት
መሆን የሚታወቅባቸው ባህርያቶቹ ናቸው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አሰራር ደግሞ የማህበረሰብ ሚዲያ ማለት


ለትርፍ ያልተቋቋሙ የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን አገልግሎት ሲሆን በህዝቡ ፍላጎትና
ይሁንታ በመቋቋም የአንድ የተወሰን ቦታ ላይ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ፍላጎት
በማንፀባረቅ በእነሱው የሚቋቋምና የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡ ይህም ማለት
የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለቤቱም፣ ሰራተኞቹም፣ አስተዳደሮችም ራሱ የማህበረሰቡ አካላት
ማለት ነው፡፡

6
የማህበረሰብ ሬዲዮ አራቱ መርሆች ብሎ ጃን ሰርቪያስ (2007) ያስቀመጣቸው
የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ባለቤትነቱ የማህበረሰቡ ነው፤


2. የሚሰጠው አገልግሎት ለማህበረሰቡ ነው፤
3. ህዝብን አሳታፊ መሆን አለበት እና
4. ለትርፍ የማይሰራ ተቋም

የማህበረሰብ ተሳትፎ የማህበረሰብ ሚዲያ ቁልፍ ተግባር ሲሆን በሌሎች የሚዲያ


አማራጮች ድምፃቸውን ማሰማት ያልቻሉትን የማህበሰብ ክፍሎች እንዲናገሩ እና
እንዲወያዩ ማስቻል አለበት፡፡ ስለዚህ የማህበረሰቡ ክፍሎች ከአድማጭ ወደ ተሳታፊ
ይቀየራሉ ማለት ነው፡፡

የማህበረሰብ ሬዲዮ በኢትዮጵያ በሚያስገርም ፍጥነት ከመንግስትና ከግሉ ሚዲያ በኋላ


ተነስቶ በአሁኑ ሠዓት 30 የሚደርሱ የሬዲዮ ጣቢያዎች ከመንግስት ፈቃድ አግኝተው
በሥራ ላይ ናቸው፡፡ የማህበረሰብ ሬዲዮ አሰራር መመሪያ ቁጥር 04/2004 መሰረት
በኢትዮጵያ የተለያዩ የማህበረሰብ ሬዲዮ አገልግሎቶች በመከፈት ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ
የሬዲዮ ጣቢያዎች የልማታዊ ጋዜጠኝነትን ሥራ እንዲያከናውኑ በማሰብ ነው
የሚቋቋሙት፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

 የማህበረሰብ ሬዲዮ ምንድን ነው?


 የማህበረሰብ ሬዲዮ አገልግሎቱ ለማን ነው?
 የማህበረሰብ ሬዲዮ ከሌሎች የሬዲዮ ወይም የሚዲያ ተቋማት
በምን ይለያል?

1.2 ልማታዊ ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነው?


ጋዜጠኝነትና ልማት እንደጓድ፣ እንደአቀጣጣይ ወይም ደግሞ እንደተች/ቃፊር ያለ ግንኙነት
አላቸው፡፡ የልማታዊ ጋዜጠኝነት ፅንሰ ሃሳብ በምዕራብ ሃገራት የዜና አሰራር ላይ ደስተኛ
ያልሆኑ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች በ1980ዎቹ ላይ የፈጠሩት የሚዲያ ፍልስፍና ነው፡፡ እንደ
ሚዲያ ንድፈ ሃሳቦች ሚዲያ ብሄራዊ ልማት እንዲፋጠን የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ
ልማቶችን በማቀናጀት ከፍተኛ ሥራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ልማታዊ

7
አጀንዳዎችን በትልቁም ሆነ በትንሹ በጥልቀት እየፈተሸ ይሰራል፡፡ የልማት ፕሮጀክቶችን
ተገቢነት እና አካሄድ ላይ የመደገፍ ሥህተቶች ካሉም የማጋለጥ ሥራ ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ
ልማታዊ ጋዜጠኝነት የሚያተኩረው ልማት ተኮር የሆኑ ዜናዎችን መረጃ በመሰብሰብ
ለማህበረሰቡ ማድረስ ላይ ነው፡፡ የልማታዊ ጋዜጠኝነት ቁልፍ ተግባራት (አጋራዋል፣ 1980)

1. በዕቅድና በትግበራ መካከል ያለውን ልዩነት መዘገብ፤ በማኅበረሸቡ ላይ ያለውን


ተፅዕኖም ማጋለጥ፤
2. በዕለት ከዕለት ዜናዎች ሳይሆን በዘላዊ የልማት ሂደቶች ላይ ማተኮር
3. ከመንግስት ነፃ ሆኖ ለመንግስት ገንቢ አስተያየቶችን መስጠት
4. ለሃገር ግንባታ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ
5. ደሃና ተራ የማህበረሰብ ክፍሎችን አቅም ማጎልበት

የቡድን ውይይት

ውድ የዚህ ስልጠና ተካፋዮች የማህበረሰብ ሬዲዮ የልማታዊ ጋዜጠኝነት


ማሳያ የልማት አጋር ነው ሲባል ምን ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ በቡድን
ተወያይታችሁ አብራሩ፡፡

በዚህ የማህበረሰብ ሬዲዮ የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄ መመለስ


የሚቻልበትን መንገድ በመነጋገር አብራሩ፡፡

ማጠቃለያ

የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ማህበረሰቡ ድምጹን የሚያሰማባቸው፣ ሃሳቡን


የሚያስተናግድባቸው፣ የማህበረሰቡን ችግር በጋራ በመወያየት የሚፈታባቸው ራሱ
ህዝቡ የሚያቋቁማቸውና የሚሰራባቸው ሲሆኑ አሰራራቸውም ሆነ አገልግሎታቸው
ህዝባዊ ነው፡፡ ስለሆነም በሌሎች የሚዲያ ተቋማት ላይ አየር ላይ ለመዋል
ያልቻልሁትን የአካባቢው ማህበረሰብ ድምፆች ያሰማል፡፡

8
ክፍል ሁለት

2. የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት

2.1 ዜና

2.1.1 ዜና ምንድን ነው?

የመወያያ ጥያቄዎች

 ዜና ምንድን ነው?
 በየቀኑ ምን ያህል ዜና ትሰማላችሁ?
 ዜና ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም?

ዜና ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ሁሌም ለጋዜጠኝነት ሙያ ቅርብ የሆነ ሰው


ወይም ደግሞ ዘወትር ምሽት በጉጉት ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን የሚከታተል ሰው
በቀላሉ ይመልሰዋል፡፡ በርካታ ቤተሰቦች በዜና ሰዓት ህጻናትን ዝም በሉ ወይም ከሌሎች
ሰዎች ጋር ያወሩበት የነበረውን ጉዳይ ቆም አድርገው በትኩረት የሚከታተሉት
የብዙሃን መገናኛ ገፀ በረከት ዜና ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ዓለማችን እንዴት ዋለች?
ለሚለው ጉዳይ በቂ መልስ የሚሰጠው ዕለታዊ ዜና ስለሆነ ነው፡፡

በማንኛውም የብዙሃን መገናኛ ማለትም በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔት


ወይም በኢንተርኔት ዜና ከሌሎች የብዙሃን መገናኛ በተሻለ አስፈላጊና የአድማጭ
ተመልካችን ቀልብ መግዛት የሚችል የጋዜጠኝነት ዘውግ ነው፡፡ ስለሆነም ጥራት ያለው
የዜና ዝግጅት ደግሞ አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን ዓለማችን በሉላዊነት ምክንያት በጠበበችበት
ሰዓት ቴክኖሎጂ በየቀኑ እንደአሸን በሚፈላበት ወቅት ብዙ ምርጫ ያለውን አንባቢ፣
አድማጭ ወይም ተመልካች ይዞ መገኘትና መዝለቅ ትልቅ ችሎታ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ
በዚህ ውድድር በበዛበት የብዙሃን መገናኛ ሥራ ውስጥ በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና
ልምድ ያካበቱ ጋዜጠኞች ዜናን መስራት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው
ምን ያህሉ ሙያዊ ጋዜጠኞች ጥራት ላለው ዜና ትኩረት እንደሚሰጡ ነው፡፡

9
አያሌ የጋዜጠኝነት ምሁራን “ዜና” ለሚለው ቃል የተለያዩ ትርጎሞች ይሰጡታል፡፡
የትርጉማቸው መሰረተ ሃሳብ አንድ ቢሆንም የአተረጓጉም ዘይቤያቸው ግን በመጠኑ
ልዩነት አለው፡፡ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የዜና አቻ ትርጉም ነው የሚባለው “News”
የሚለውን ቃል ከቁም ትርጉሙ ሌላ ሁለት ዓበይት ቁምነገሮች ያንፀባርቃል፡፡ አንደኛው
የቃሉ ዝርዝር ፊደላት N (North) ሰሜን, E (East) ምስራቅ, W (West) ምዕራብ እና
S (South) ደቡብ ማለት ነው ይላሉ፡፡ ስለዚህ “News” በሚለው ቃል ውስጥ ያሉት
አራት ፊደላት አራቱን መልክዓ ምድራዊ የዓለም ማዕዘናት ይጠቁማሉ ማለት ነው፡፡
ሁለተኛው “News” (ዜና) ከሚለው ቃል የሚገኘው ቁም ነገር ጋዜጣ “Newspaper”
ለሚለው የእንግሊዘኛ ቃል መነሻ ወይም መሠረት መሆኑ ነው፡፡ ብዙዎቹ የሙያው
ምሁራን ዜናን ዜና የሚያደርገው በዜና መልክ መዘጋጀቱ ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰቡ
መሰራጨቱ ነው ይላሉ፡፡

የኦክስፎርድ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት ዜና ማለት አዲስ፣ መሳጭ፣ እውነትና


ያልተለመዱ ክስተቶች ዘገባ ነው ይላል፡፡ ይህም ማለት አብዛኛው ጋዜጠኛ ስለዜና
ያለውን ግንዛቤ ማካተት የሚችል ይመስላል፡፡ ዜና ስለአንድ የህብረተሰብን ትኩረት
በብርቱ ሊስብ ስለሚችል ወይም በህዝብ ህይወት ላይ ተፅዕኖ ስላለው ክስተት ለጋዜጣ፣
ለዜና መፅሔት፣ ለዜና አገልግሎት፣ ለሬዲዮና ለቴሌቪዥን፤ በአጠቃላይ ለብዙሃን
መገናኛ የሚዘጋጅ ዘገባ ነው፡፡ ሌላው በኦክስፎርድ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ
ካለው ትርጓሜ የምንረዳው ዜናን ዜና የሚያደርገው አዲስነቱ ነው፡፡ ሁልጊዜም ሠዎች
ከለመዱትና ከሰለቻቸው ውጭ የሆነን ጉዳይ ጆሮ ሰጥተው ስለሚያዳምጡ ነው፡፡
ለዚያም ነው የዜና ቋንጣ የለውም እየተባለ በወቅቱ አየር ላይ ወይም ህትመት ላይ
ያልዋሉ ጉዳዮች እንደዜና የማይቆጠሩት ወይም የማይቀርቡት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
ዜና ሁሌም በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡

ሌላው የጋዜጠኝነት ትርጓሜ ደግሞ የታሪክ የመጀመሪያ ንድፍ ነው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ


በችሎላ የሚዘጋጅ ሥነ-ፅሁፍ ነው ይላሉ፡፡ ስነ-ፅሁፍም ሆነ የታሪክ ፅሁፍ በአንድ
ወቅት የዜና አካል የነበረ ስለሆነ ነው ይህንን ትርጓሜ የሚሰጡት፡፡ ለምሳሌ በአንድ
ወቅት በሃገራችን ተከስተው ያለፉ ጉዳዮች ዛሬ ላይ ታሪክ ቢሆኑም በወቅቱ ግን
በየብዙሃን መገናኛዎቹ ዋነኛ የዜና ዘገባዎች ነበሩ፡፡ በቅርብ ታሪካችን ውስጥ ያሉትን
ለመጥቀስ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ ምርጫ 97፣ የኢትዮጵያ ሚሊኒየም፣ የጠቅላይ

10
መለስ ዜናዊ ህልፈተ-ህይወት አሁን ላይ ታሪክ ቢሆኑም በወቅቱ ግን የተመረጡ
ዜናዎች ነበሩ፡፡

ዜና ሰውን የሚያስደነግጥ፣ የሚያስገርም ወይም የሚያስደንቅ፣ የሚያስደስት ወይም


የሚያሳዝን የአዳዲስ ኩነቶች መገለጥ፣ የአዳዲስ ድርጊቶች መፈፀም፣ መታወጅ፣ ወይም
የአንድ ክስተት ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዜና ማለት ሰው ሲሰማው
እውነታቸውን ነው እንዴ? በማለት በታላቅ አግራሞት እና መደናገጥ የሚቀበለው ወሬ
ወይም መረጃ ነው፡፡ አንድ አባባል አለ፤ “ውሻ ሰው በላ” እና “ሰው ውሻ በላ” የሚሉ
ሁለት ጉዳዮች ቢቀርቡ ዜና የሚሆነው “ሰው ውሻ በላ” የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም ዜና
ማለት ያልተለመደና ሲሰሙት አግራሞች የሚያጭር መሆን ስላለበት ነው፡፡

ዜና ማለት ሰዎች ናቸው የሚል ትርጉምም ይሰጠዋል፡፡ ሰዎች


የሚናገሩት፣ ሰዎች የሚሰሩት ሁሉ ዜና ነው፡፡ ስለዚህ ከሰዎች
ንግግር፣ተግባር፣ ዕቅድ፣ ሥራ፣ ግጭት እየወሰድነ የምናቀርበው
ስለሆነ ዜና ማለት ሰዎች ማለት ነው የሚል ትርጉም ለዜና
ይሰጠዋል፡፡ በአጠቃላይ ዜና የአንድን ሁነት የመንገር ጥበብ ነው፡፡

2.1.2 የዜና ዓይነቶች

ዜና ሁሌም በተመሳሳይ መልኩ አይፃፍም፡፡ ይኸውም የዜናው ዓይነትና በምን መልኩ


ቢቀርብ ይሻላል ከሚለው አንጻር ነው የሚታየው፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን ዜናዎች
ተመልከቱ፡፡

1. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ፡፡

2. ኢትዮጵያን ላለፉት 38 ዓ.ም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በትግልና በአመራር ሲመሩ


ነበር፡፡ በተለይም ባለፉት 21 ዓመታት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው
አገልግለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ካሳለፍነው የግንቦት ወር ጀምረው
ህመም ስለተሰማቸው ለህክምና ውጪ ሲመላለሱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
ትናንትና ማታ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ አረፉ፡፡

ዜና በሁለት መልኩ ሊፃፍ ይችላል፡፡ ይኸውም በቀጥታና በተዋዛ መልኩ፡፡

11
1. የቀጥታ ዜና (Hard News)

የቀጥታ ዜና አንድን ድርጊት በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወዲያኑና በወቅቱ


የሚዘገብ የዜና ዓይነት ነው፡፡ የቀጥታ ዜና የሚጀምረው በድርጊቱ ውስጥ በጣም
ጠቃሚ በሆነው ጉዳይ ሲሆን ነገሮችን በትኩሱ ማቅረብ ዋነኛ መለያው ነው፡፡
አቀራረቡም የተከሰተውን ጉዳይ ቀላል፣ ግልፅ፣ ቀጥተኛና እውነተኛ በሆነ መልኩ
ያቀርባል፡፡ የቀጥታ ዜና በአብዛኛው ኩነት-ተኮር (Event-oriented) ነው፡፡ ኩነቱን
በተመለከተ ቀጥተኛ የሆነ የዜና አቀራረብ መንገድ ይጠቀማል፡፡ በርካታ ኩነቶች በቀጥታ
የዜና አቀራረብ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ለምሳሌ ያህል መፈንቅለ
መንግስት፣ ሹምሽር፣ ምርጫ፣ የፖሊስ ሪፖርት፣ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ ግድያ፣
መንግስታዊ ስብሰባዎች፣ ህዝባዊ መድረኮች፣ የአየር ንብረት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዋጋ
ጉዳይ (ገበያ ነክ ዜናዎች)፣ .. ወዘተ ናቸው፡፡

የቀጥታ ዜና በሚፃፍበት ጊዜ መረጃን ማዛባት፣ በተገቢው ቦታ አለማስቀመጥ፣ ወይም


የተሳሳተ ነገር መጨመር ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡ ምክንያቱም በዜናው መንስኤ ከፍተኛ
የሆነ ህዝባዊና አገራዊ አደጋ ስለሚያስከትል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ድምዳሜ
መስጠት፣ አሉባልታዎችን ማካተት፣ የግል አመለካከትንና ያልተጣሩ ተባራሪ ወሬዎችን
ማካተትም አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የቀጥታ ዜናዎች በአድማጭ ተመልካች ላይ
ያላቸው ተፅዕኖ ከፍተኛ ስለሆነ ነው፡፡

2. የተዋዛ ዜና (Soft News )

የተዋዛ ዜና ወይም ዋዘኛ ዜና ከቀጥታ ዜና ጋር ሲወዳደር በዜና አፃጻፉ የተለየ የራሱ


የሆኑ ባህርያት አሉት፡፡ ይኸውም ለሁነቶች እና ለጊዜ ትኩረት አይሰጥም፡፡ ይልቁንም
ለሰው ስሜት ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነውው፡ በአብዛኛው ጊዜ ለብዙዎቹ እንደ
አማራጭ የሚቀርብ የዜና ዓይነት ነው፡፡ የተዋዛ ዜና ተዋዝቶ የሰውን ስሜት በሚነካ
መልኩ የፀሐፊው ችሎታ እና አቅም ተጨምሮበት የሚፃፍ ዜና ሲሆን ለመስማት፣
ለማንበብ ወይም ለማየት ማራኪ፣ አጓጊ እና አስደሳች ሆኖ የሚቀርብ ነው፡፡ የተዋዛ
ዜና በአድማጭ ላይ እዚህ ግባ የሚባል ተፅዕኖ ማሳደር ባይችልም እንኳ በዕለት ከዕለት
ህይወት ውስጥ ያለውን የማህበራዊ ሁኔታና የሁኔታዎች ለውጥ ለማወቅ ይረዳል፡፡

12
ለምሳሌ ያህል ግለታሪኮች፣ የመዝናኛ ወሬዎች፣ ባህላዊ ወጎችና የመሳሰሉት የሚጠቀሱ
የተዋዛ ዜና ሁነታዎች ናቸው፡፡

በቡድን በቡድን ሆናችሁ አንድ ቀጥተኛ ዜናና አንድ ደግሞ የተቃዛ ዜና


ጻፉ፡፡

2.1.3 የዜና ጠቀሜታዎች

በርካታ የዘርፉ ተመራማሪዎች ሠዎች ለምን ዜናን ይከታተላሉ የሚለውን ጥያቄ


ለመመለስ በርካታ ጥናት አካሂደዋል፡፡ አንዳንዶቹ የተፈጠረውን ለማወቅ፤ ሌሎች ደግሞ
የሚፈጠረውን ወይም ይፈጠራል ተብሎ የሚጠበቀውን ለማወቅ ዜናን ይከታተላሉ፡፡
የዜና ዘገባ በተወሰ ጊዜ የተለያዩ ዘርፈ-ብዙ መረጃዎችን መስጠት ስለሚያስችልም የራሱ
የሆነ አውንታዊ ሚና አለው ምን እንኳ ይህንን የሚቃወሙ ባይጠፉም፡፡

የሰው ልጆች ለምን ዜናን ይከታተላሉ ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሆኑ ዋና ዋና


ምክንያቶችን እንደሚከተለው ለማየት ተሞክሯል፡፡

1. በሰውና በንብረት ላይ ከሚደርስ አደጋ ለመጠንቀቅ፡፡ በዜና አማካኝነት በሰውና


በንብረት ላይ በጦርነት፣ ግጭት፣ በተፈጥሮ አደጋ፣ በወረርሽኝ፣ በተመረዙ
ምርቶች ወዘተ አማካኝነት የሚደርሱ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት
የማስጠንቀቂያ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ስጋት ላይ
የጣለው የኢቦላ ወረርሽኝ ብዙሃን መገናኛዎች የሚሰጡት የማስጠንቀቂያ ዜና
ለዚህ ምርጥ ምሳሌ ነው፡፡

2. ምን እንደተፈጠረና ሊፈጠር እንደሚችል መንገር፡፡ በዜና በዓለም ላይ ምን


እየተካሄደ እንዳለና ሊፈጠር የሚችል ጉዳይ እንዳለ በዜና አውታሮች አማካኝነት
ማወቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የልማት ዘገባዎች፣ የመድኃኒት መፈብረክ፣ በጤና፣
በትምህርት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚወጡ ልማቶችንና
ለውጦችን በተመለከተ የመንገር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ መንግስት
ለመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሬ አደረገ እና መንግስት ለመንግስት

13
ሠራተኞች ከሃምሌ ጀምሮ የደመወዝ ጭማሬ ሊያደርግ ነው የሚሉ ዜናዎች
የዜናን የመንገር ጠቀሜታ ያሳያሉ፡፡

3. ለሰው ልጅ ነፃነት ስጋት የሆኑ ነገሮችን ማጋለጥ፡፡ ለሰው ልጅ ስጋት የሆኑትን


ጉዳዮች ማለትም ኢ-ፍትሃዊነት፣ ሙስና፣ ሽብርተኝነት፣ ሰብዓዊ መብት ረገጣ፣
የጉልበት ብዝበዛ፣ ፖለቲካዊ ጭቆና ወዘተ ዓይነት ጉዳዮች ለሰው ልጅ ነፃነት
ስጋት በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዜና የማጋለጥ ተግባር
ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ በዜና የማጋለጥ አገልግሎት ዜና እንዲከታተሉ
የሚያደርግ ምክንያት ነው፡፡

4. የህብረተሰቡን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ መሸሻል እንዲመጣ መርዳት፡፡


ስለኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ሥራ፣ ወዘተ ዓይነት ዜናዎች የህብረተሰቡን ኑሮ
እንዲሻሻል የሚረዱ ስለሆነ ዜና የኑሮ መሻሻል እንዲመጣ ጠቀሜታ አለው፡፡
ማንኛውም የብዙሃን መገናኛ የሚሰጣቸው ጥቅሞች አሉት፡፡ ይኸውም ማሳወቅ፣
ማስተማርና ማዝናናት ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ የማሳወቁ ሥራ የሚሰራው
በዜና ሲሆን ይህም የኑሮን ሁኔታ መሻሻል እንዲመጣ ወይም የመጣውን
ለማወቅ ዜናን ይከታተላሉ፡፡ ለምሳሌ የማዳበሪያ ዋጋን በተመለከተ የሚሰራጭ
ዜና በአርሶ አደሩ ህይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ስላለው ዜናን አፅንዖት
ሠጥተው ይከታተላሉ፡፡

5. ብልሹ የአኗኗር ዘይቤን እንዲሻሻሉ ያግዛል፡፡ ስለህዝብ ሰፈራ፣ የወንጀል


ድርጊት፣ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ አካባቢያዊ ጉዳዮች፣ የቤት ጉዳይ እና
የመሳሰሉት ዜናዎች የህብረተሰቡን የአኗኗር ችግሮችን እንዲቀርፉ
የሚነደፉትንና ሚከናወኑትን ተግባራት በዜና መከታተል ጠቃሚና የዜናን ሚና
ያመለክታል፡፡

2.1.4 የዜና ጥንካሬዎችና ድክመቶች

ዜና በጣም ከፍተኛ የሆነ ተፈላጊነት ያለው የጋዜጠኝነት ዘውግ ነውው፡ ይኸውም ሰዎች
ለተለያዩ ምክንያቶች ትኩረት ሰጥተው የሚከታተሉት ዘውግ፡፡ ዜና የራሱ የሆነ የአፃፃፍ
ስልት ያለው ሲሆን በቀጥታና በተዋዛ መል ይቀርባል፡፡ ዜና የራሱ የሆነ ጠንካራና
ደካማ ጎኖች አሉት፡፡

14
የዜና ጥንካሬዎች

 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መረጃን ይሰጣል


 አዲስና ተገቢነት ያለው መረጃ ያቀብላል
 የአድማጭ ተመልካችን አቅም ያጎለብታል
 ዕውቀትን ያሳድጋል
 ሚዛናዊነትን ያበረታታል
 አድማጭ ተመልካቾች ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ይረዳል

የዜና ድክመቶች (ውስንነቶች)


 በጣም አስፈላጊ ነገሮችን ብቻ ያቀርባል፤ ስለሆነም ብዙ ዝርዝር መረጃዎችን
አያደርስም
 በቦታና በጊዜ የተገደበ ነው፡፡ ይኸውም የምንፅፈው ለጋዜጣ ከሆነ በወረቀቱ ልክ
ለብሮድካስት ከሆነ ደግሞ በአየር ሰዓቱ ልክ የተገደበ ነው
 ብዙ ግብዓት ይፈልጋል በተለይም የቴሌቪዥን ዜና በርካታ የሰውና የንብረት
ግብዓቶችን ይፈልጋል፡፡

2.1.5 የዜና መመዘኛ እሴቶች

ዜና በምታዳምጡበት ጊዜ በጣም ጆሮ የምትሰጡት ይዘቱ ምን ሲሆን


ነው? የማታዳምጡትስ?

የተፃፉ ዜናች ሁሉ አይታተሙም ወይም አየር ላይ አይውሉም ምክንያቱም ዜና


መሠረታዊ የሆነ የዜና አፃፃፍ እሴቶችን አሟልቶ የቃፊሮችን (Gatekeepers) መመዘኛ
አሟልቶ የይታተም ወይም የይሰራጭ ይሁንታ ማግኘት አለበት፡፡ የቃፊሩን ይሁንታ
ያላገኘ ዜና አይታተምም ወይም አየር ላይ አይውልም ማለት ነው፡፡ ቃፊር ማለት
በዕየለቱ የሚቀርቡ ዜናዎች ላይ ከፍተኛ ዋሳኔ የሚሰጡ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ
ቃፊሮች የዜናውን ጥሩነት የሚመዝኑት ደግሞ ከዜና መመዘኛ እሴቶች አንፃር ነው፡፡

15
ነገር ግን እነዚህ እሴቶች በመጠቀም ዜናው በሚገመገምበት ሰዓት ከግምት ውስጥ
የሚገቡ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህመም ሁኔታዎች

1. የሪፖርተሩ የጀርባ ታሪክና ልምድ


2. የብዙሃን መገናኛ ተቋሙ መስፈርት
3. የገበያ ሁኔታ
4. የአድማጭ ተመልካች ፋላጎት ናቸው፡፡
ምንም እንኳ እነዚህ ሁኔታዎች ዜናን በዜና እሴቶች መሰረት የመመዘኑን ጉዳይ ተፅዕኖ
ቢያደርጉበትም በአብዛኛው ግን የሚታዩት ከእሴቶች አንፃር ነው፡፡ እነዚህም እሴቶች
እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

1. የጉዳዩ ቅርበት (Proximity)

ዜና በጂኦግራፊካል አቀማመጥ ወይም ለሰዎች ሥነ-ልቦና ቅርብ የሆነ ጉዳይ መሆን


አለበት፡፡ አንድ ሁነት በዜና መልክ እንዲቀርብ ከሚያደርገው ነገር አንዱ የጉዳዩ ቅርበት
ነው፡፡ የዜና ሁነቶች ለግለሰቦች ወይም ለአካባቢው የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
አንዳንዱ ተፅዕኖ በቀጥታ ይሆናል፡፡ አካባቢያዊ ወይም ሃገራዊ ዜናዎች ለሌሎች የዓለም
ክፍል ዜናዎች የተሻለ ተደማጭነት ወይም ተነባቢነት አላቸው ምክንያቱም የአድማጭ
ተመልካች ቀልብና ሃሳብ መግዛት ስለሚችሉ እና ተገቢነትና ተፅዕኖ ስላላቸው ነው፡፡
ነገር ግን አንዳንድ ሁነቶች የዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛን ትኩረት ይስባሉ፡፡ ያም
የሚሆነው የጉዳዩን ዓለምአቀፋዊነት ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከአካባቢያዊ ወይም
ብሔራዊ ዜናዎች በላይ ከአድማጮች ትኩረት አያገኝም፡፡ ምንም እንኳ ሉላዊነት
እየተስፋፋ ቢሄድም ብዙውን ጊዜ ሰዎች ስለአካባቢያቸው መስማት ወይም ማወቅ
ይፈልጋሉ፡፡ ለምሳሌ ስለተፈጥሮ አደጋዎች፣ ምርጫ፣ ሽብርተኝነት፣ የልማት ወሬዎች፣
ወዘተ በአካባቢው አድማጭ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጥባቸዋል፡፡

እስኪ የሚከተሉትን ሁለት ዜናዎች አወዳድሩ፡፡

1. አይ ሲ አይ ኤስ የተባለው የሽብር ቡድን በኢራቅና በሶሪያ የሚገኙ በርካታ


ንፁሃን ዜጎችን ገደለ፡፡

2. አል-ሸባብ በኢትዮጵያ ሱማሌ ድንበር መሸገ፡፡

16
ከነዚህ ሁለት ዜናዎች የትኛው ዜና የበለጠ ለኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት
አድማጭ ተመልካች ትኩረት ይሰጠዋል? ለምን?

አንዳንድ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ደግሞ የበለጠ ቅርብ የሚሆኑበት አጋጣሚ አላቸው፡፡
ለምሳሌ የነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ የታላላቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኪሳራ፣ የአስከፊ
ወረርሽኝ መከሰት፣ ወዘተ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት የዓለማችን አንገብጋቢ ዜናዎችን
መስራት የምንችለው ደግሞ ከአገራችን አውድ ጋር በማዛመድ ነው፡፡ ስለዚህ ዜናችን
ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችል ተገቢነት ያስፈልገዋል፤ ተገቢነት እንዲኖረው ደግሞ ቅርበት
ሊኖረው ይገባል፡፡

በአጠቃላይ አንድ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለሚገኝ ግለሰብ መጀመሪያ ስለደብረ
ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፤ ከዚያም ስለጎጃምና አካባቢው፤ ቀጥሎ ስለአማራ፣ ስለኢትዮጵያና
ስለአፍሪካ እያለ ስለተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ቢነገረው ትኩረት የመስጠት
ሁኔታውም በየደረጃው ከፍ እያለ የሚሄድበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

2. የባለጉዳዮች ታዋቂነት (Prominence)

አንዳንድ ጊዜ ስም በራሱ ዜና የሚሆንበት አጋጣሚ አለ፡፡ ታዋቂ የሆነ ሰው ትልቅ ዜና


መሆን ይችላል፡፡ ይኸውም የሚሰራው ሥራ ሳይሆን የሰራው ሰው ታዋቂነት መሰረት
ያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ በቀላሉ የሚያውቃቸው ሰዎች የያዘ ዜና ተመራጭ
ነው፡፡ ምክንያቱም በፖለቲካው፣ በስፖርቱ፣ በሙዚቃው፣ በመዝናኛው፣ በንግዱ ወዘተ
ዘርፎች ታዋቂነት ያላቸው ሰዎችን ጉዳይ ለዜና መጠቀሙ የዜና መመዘኛ እሴቱን
ስለሚጨምር ነው፡፡

ለምሳሌ፡

1. አቶ አበበ ተሰማ አረፉ፡፡

2. አትሌት ቀነኔሳ በቀለ ጉንፋን ይዞታል፡፡

የሚሉ ሁለት ዜናዎች ብትሰሙ የትኛውን ነው የበለጠ ጆሮ የምትሰጡት? መቼም


የአቶ ናንቦኒ ሞት ከቀነኔሳ ጉንፋን የበለጠ ቢሆንም አቶ ናንቦኒ ምን እንደሆኑ
ስለማናውቅ የቀነኔሳን ጉዳይ ነው ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጠው፡፡ ስለዚህ የታዋቂ

17
ሰዎችን የስኬት፣ የውድቀት፣ አስተዳደግ፣ ውሎና አዳር፣ ሽንፈትና ድል እንዲሁም
ውስጠ-ምስጢራቸውን ማወቅ ለሚፈልግ አድማጭ ተመልካች ያንን ይዞ መገኘት ትልቅ
የዜና እሴት ነው፡፡ በዜና ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ስም ካለበት ዜናው የዕለቱ ዜና ተደርጎ
ይቀርባል፡፡

እስኪ የሚከተሉትን ሁለት አርዕስተ-ዜናዎች በማንበብ ቀጥለው ያሉትን ጥያቄዎች


መልሱ፡፡

1. የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ ሃይማኖቱን ቀየረ፡፡

2. አቶ አበበ ከበደ ሃይማኖቱን ቀየረ፡፡

ከሁለቱ ዜናዎች የትኛውን ማዳመጥ ነው የምትፈልጉት? ለምን?

በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ አንዱን ዜና ከሌላው እንድናበላልጥ የሚያደርገን ምንድን


ነው?

3. ወቅታዊነት (Timeliness)

ዜናን ዜና የሚያሰኘው አዲስ ነገር ይዞ መገኘቱ ነው፡፡ በአገራችን የዜና ቋንጣ የለውም
ይባላል፡፡ ይህም ማለት አንድ ድርጊት እንደተከሰተ ወዲያውኑ መደበኛ የሆኑ የጋዜጠኛ
ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች በእንግሊዘኛ 5 W and H
questions በመባል ይታወቃሉ፡፡

 ምን ተከሰተ?
 ማን ፈፀመው?
 መቼ ተከፈተ?
 የት ተከሰተ?
 ለምን ተከሰተ? እና
 እንዴት ተከሰተ? የሚሉት ናቸው፡፡
ስለዚህ ድርጊቱ በተከሰተበት ፍጥነት፤ ቴክኖሎጂው እስከፈቀደ ድረስ ዜና በፍጥነት
ወቅቱን ጠብቆ መሠራት አለበት፡፡ የብሮድካስት ሚዲያ በተለይ ሬዲዮ በቀጥታ በቀላሉ
ነገሮችን ለማስተላለፍ ይረዳል፡፡ ወቅታዊነት በብሮድካስትና በህትመት የብዙሃን

18
መገናኛዎች እኩል አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንደብሮድካስት ሚዲያ በፍጥነት በህትመት
ውጤቶች ላይ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ይኸውም የህትመት መውጫ ቀን መጠበቅንና
ሁሉንም ሂደቶች ማለፍ ስለሚያስፈልግ ነው፡፡
ወቅታዊነት ማለት ዛሬ የሆነን ክስተት ብቻ መዘገብ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግ እስከዛሬ
ድረስ ተደብቀው የተቀመጡ መረጃዎችን እንደተገኙ ማቅረብን ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ
የቀዳማዊ ኃይለስላሴ አሟሟት እስካሁን ድረስ ግልፅ የሆነ ነገር የለውም፡፡ ነገር ግን
ከገዳዮቹ አንዱ አሁን ሊሞት ሲል የነበረውን ሂደት ቢናዘዝና መረጃ ቢወጣ
ወቅታዊነትን አያዛባም፡፡ ከወቅታዊነት ጋር በተያያዘ ግን ቶሎ ብሎ ዜናን ለማቅረብ
ያልተጣሩ መረጃዎችን ይዞ መውጣትም ይሁን ያልጠራ ፅሁፍ መስራ ተገቢ አይደለም፡፡

4. ተፅዕኖ አድራጊነት (Impact)

ተፅዕኖ ማት አንድ ስለአንድ ድርጊት የሚያትት ዜና ለህብረተሰቡ በሚሰጠው ጥቅም


ያለው አንድምታ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ህብረተሰቡ ከዜናው በኋላ ድርጊቱን
በተመለከተ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ ዜናው
በሚያሳድረው ተፅዕኖ አማካኝነት ነው ክንውኖች የሚካሄዱት፡፡ ዜናዎች የሚታተሙት
ወይም የሚሰራጩት ሊፈጥሩት የሚችሉት ተፅዕኖ ወይም ሊሰጡት የሚችሉት ፋይዳ
ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚዳስስ ዜና በሰፊው ተፅዕኖ
መፍጠር ስለሚችል ይዘገባል፡፡ ብዙ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ባሳደረ ቁጥር ብዙ ጠቃሚ
እሴቶችን የያዘ ዜና ይሆናል፡፡

5. አወዛጋቢነት (Controvesy)

አንድ ጉዳይ የሥነ-ልቦና፣ የሥነ-ምግባር ወይም ግብረገብነት ላይ ውዝግብ ሊፈጥር


ይችላል፡፡ ውዝግቡ ደግሞ ከራስ ጋር፣ ከግለሰቦች ጋር ወይም ከቡድኖች ጋር ሊሆን
ይችላል፡፡ ይህን ውዝግብ ደግሞ ዜናው ታትሞ ከወጣ ወይም አየር ላይ ከዋለ በኋላም
የሚቀጥል ይሆና፡፡ በዚህም የተነሳ ዜናውን የተመረጠ ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም
አወዛጋቢ ጉዳዮች በህይወታችን የተወሰነ ፋይዳ ስላላቸው ነው፡፡

19
ለምሳሌ፡- ሞሮኮ የ2015 የአፍሪካን ዋንጫ አላዘጋጅም አለች፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢቦላ
ወረርሽኝ መስፋፋት ነው፡፡ በሌላ በኩል የአፍሪካ ዋንጫ ኮንፌዴሬሽን ውድድሩን
የማታዘጋጅ ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንደሚጣልባት አስታውቋል፡፡

በዚህ ዜና ውስጥ ሞሮኮ ትክክል ናት አይደለችም፤ ኮንፌዴሬሽኑ ቅጣት ሊከብድ ይገባል


ወይም አይገባም በሚል ለውይይት ይጋብዛል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካታ ሰዎች ከግለሰብ
እስከ ቡድን ደረጃ በሁለት ጎራ ተከፋፍለው ስለሁኔታው እንዲነጋገሩ መድረኩ
ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለመነጋገሪያ እንዲሆን ስለሚያደርግ አወዛጋቢነት አንድ ጥሩ የዜና
እሴት ነው፡፡

6. ተገቢነት (Relevance)

ተገቢነት ለቅርበት የተሻለ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ ቅርበቱ ሲጠብ ዜናው በአንድ ሃገር
ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች ፍላጎት ማሟላት ይሳነዋል፡፡ ለምሳሌ የምርት ማዳበሪያ ዋጋ
መውረድ ለአርሶ አደሮች ጥሩ ዜና ነው፤ ተገቢነትም አለው፡፡ ለብረታ ብረት ኢንዱስትሪ
ባለሃብቶች ግን ተገቢነት የለውም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የብረታ ብረት ዋጋ ጭማሬ
ለኢንዱስትሪው ባሃብቶች ተገቢ ሲሆን ለአርሶ አደሮች ግን ምንም አይደለም፡፡ ይህም
የሚያሳየው የዜናዎች ጠቃሚነት በቅርበትና በተገቢነት የተወሰነ መሆኑ ነው፡፡

ስለ ተገቢነት ሲወራ ሁሌም መታወቅ ያለበት


የማህበረሰቡ የተለያየ ባህርይና ፍላጎት ነው፡፡ ስለዚህ
በአካባቢው የሚገኙ ተገቢ የሆኑ ማህበራዊ ፍላጎቶች
ቅድሚያ በዜናው ውስጥ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ትንግርት (Uniqueness)

የተለመዱ ሁነቶች ዜና ሊሆኑ አይችሉም፡፡ አንድ ክስተት ዜና ሊሆን የሚችለው


ለተለመደው ወይም ሰዎች ከለመዱት ውጭ ያለ ነገር ይዞ መቅረብ ሲችል ነው፡፡ ይህም
ማለት ልዩ የሆነና ያልተለመደ መሆን አለበት፡፡ የትም ቦታ ላይ ተከስቶ የማያውቅ
ወይም አልፎ አልፎ የሚከሰት ወይ ብርቅ የሆነ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያም ዜና
የሰዎች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ሳይሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የተለየና

20
ያልተለመደ ሲሆን የዜናውን እሴት በመጨመር የአድማጭ ተመልካችን ቀልብ መግዛት
ይችላል፡፡

ለምሳሌ፡-

1. አንዲት እናት ወንድ ልጅ በሠላም ተገላገለች፡፡

2. አንዲት እናት አራት ወንድ ልጆችን በሠላም ተገላገለች፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ዜናዎች የበለጠ የዜና እሴት ያለው ሁለተኛው ነው፡፡
ምክንያም የሰው ልጅ አይቀሬ የሆኑ ጉዳዮች ልደትና ሞት የተለመዱ ሲሆኑ በነዚህ
መካከል ግን ያልተለመዱ ሁኔታዎችን እንደ አራት ልጆች በሰላም መውለድ ዓይነት
ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ግን ዜና ይሆናል፡፡

8. ሰብዓዊነት (Human Interest)

ዜና የሰው ልጅ በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሌችም የህዝብ ጉዳዮች


የሚነካካ ከሆነ ጥሩ ዜና ነው ማለት ነው፡፡ ወደ ሰው ያዘነበለ የአፃፃፍ ስልት የሚጠቀም
ሲሆን ድርጊቶች ከሰው አኗኗር ጋር አያይዞ ይተነትናል፡፡ በዜናዎቹ ውስጥም የሰዎች
ቦታ ከፍተኛ ነው፡፡ ዜና አስደሳች እሴት የሚኖረው ከሁሉም እሴቶች ጋር የሰብዓዊ ነክ
ጉዳዮችን ይዞ መቅረብ ሲችል ነው፡፡

ለምሳሌ

1. በ 250 ሚሊዮን ብር የብረታ ብረት ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡

2. ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡

ከነዚህ ሁለት ዜናዎች የበለጠ ሰው ሰው የሚሸት ሁለተኛው ስለሆነ ከፍተኛ የሆነ


እሴት አለው፡፡ ምክንያቱም የፋብሪካው ካፒታል ሳይሆን በዚያ ካፒታል የተቋቋመው
ፋብሪካ ለማህበረሰቡ ምን ይፈይዳል የሚለው ስለሆነ ነው፡፡

21
9. ልብ ሰቀላ (Suspense)

የዜና የልብ ሰቀላ ተፈጥሮ የድርጊቱን ጠቃሚነት የተወሰነ በማሳየጥ አድማጭ


ተመነልካችን እያጓጉ እስከመጨረሻው ይዞ የመቆየት ተግባር ነው፡፡ ይህ ዓይነት አሰራር
አብዛኛውን ጊዜ የተዋዙ ዜናዎች ላይ ይበዛል፡፡ ይህ የዜና እሴት ከሌሎች እሴቶች ጋር
አብሮ የሚሄድ ሲሆን አድማጭን ስለአንድ ጉዳይ እርግጠኛ ሳይሆን እያዋዙና እያጓጉ
እስከዜናው ፍፃሜ ድረስ ይዞ መቆየት ነው፡፡

2.1.6 የዜና አላባውያን

አንድ ዜና ተወዳዳሪና ኃላፊነት የተሰማው ለማድረግ በተሻለ አቀራረብ መቅረብ አለበት፡፡


ይኸውም አድማጭ ተመልካች በሚፈልገውና በሚጠብቀው መልኩ ቢቀርብ በጣም
ተመራጭ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ዜና የሚሰራው ለይስሙላ ሳይሆን የያዝነውን መረጃ
በትክክለኛ መልኩ በመቅረብ ነው፡፡ ለአድማጭ ተመልካች ጥሩ ጣዕም ያለው ዜናን
ለማዳረስ መካተት ያለባቸው አስፈላጊ ንጥረ-ነገሮች ሊሟሉለት ይገባል፡፡ እነዚህ የዜና
ቀመሞች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. እውነትነት (Accuracy)
2. ሚዛናዊነት (Objectivity)
3. ምልዑነት (Completeness)
4. ግልፅነት (Clarity)
5. ምንጭን መለየትና መግለፅ (Source Identification and Attribution )

22
እውነትነት

ምንጭን
መለየትና ሚዛናዊነት
መግለፅ

ግልፅነት ምልዑነት

1. እውነትነት

በጋዜጠኝነት የዕለት ተዕለት ሥራ ውስጥ እውነትን የመሻት ፍላጎት አስፈላጊ ነው፡፡


እውነት መናገር ደግሞ ለጋዜጠኝነት ሥራም ሆነ ለዜና ጥንቅር አልፋና ኦሜጋ ነው
መርህ ነው፡፡ እውነትን መናገር ሁልጊዜ የዜና ተግባር መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን
እውነት ያልሆነ መረጃን ማስተላለፍ ከፍተኛ የሆነ ችግር ያጋጥማል፡፡ አንድ እውነትን
የገደፈ ዜና ከተሰራጨ የሚከተሉት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡

 ታማኝነትን ያሳጣል
 አድማጭ ተመልካችን ያሳጥል ወይም ምርጫቸውን እንዲቀይሩ ያደርጋል
 አላስፈላጊ የሆኑ ብዥታዎችን ይፈጥራል
ስለዚህ ከነዘህ እና መሰል ችግሮች መፈጠር በፊት ዜናውን የሚያዘጋጀው ጋዜጠኛ ጊዜ
ወስዶ ያሉትን መጃዎች ደግሞ ደጋግሞ ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም የጋዜጣ
ወይም የሬዲዮ ወይም ማንኛውም ዜና በተቻላቸው መጠን እውነት የሆነውን ነገር ነው
መዘገብ ያለባቸው፡፡ እውነትነት መጓደል ከሁለት በኩል ሊከሰት ይችላል፤ ከፀሐፊውና
ከመረጃ ምንጩ፡፡ በእውነት ላይ የተመሰረተ ዜና የማይሰሩ ጋዜጠኞች እንደመንስኤ
የሚቆጠረው ደግሞ ትኩረት ባለመስጠር (በእንዝህላልነት)፣ በስንፍና፣ ባልተሟላ
መረጃ፣ በተዛባ መረጃ እና በተባራሪ ወሬዎችና አሉባልታዎች ላይ ተመርኩዘው
መስራታቸው ነው፡፡ ነገር ግን መታየት ያለበት በነዚህና መሰል መንስኤዎ ምክንያት
እውነት ያልሆነ ነገር መዘገብ በጣም ከፍተኛ የሆነ ችግር መፍጠሩ ነው፡፡

23
2. ሚዛናዊነት

ጋዜጠኞች እንደማንኛውም ሰው ናቸው፡፡ ስለሆነም ሙሉ በሙሉ ከአንድ ጉዳይ ፍፁም


ነፃ እና የተገለሉ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ሚዛናዊ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም
የመሆኑ ጉዳይ ጋዜጠኛው ሥራውን ሲሰራ ከራሱ የግል ስሜትና ጥቅም ተነሳስቶ
ለራሱ በሚመቸው መልኩ መስራት ሳይሆን ጉዳዩን ከተለያየ አቅጣጫ መመልከት
ይገባዋ፡፡ ብዙውን ጊዜ አንድን ጉዳይ ከተለያየ አቅጣጫ መመልከት ተገቢም አዋጭም
ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሪፖርተሮች አንድን የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ እንዲዘግቡ ቢላኩ
ይዘውት የሚመለሱት መረጃ ሁሉም ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህም ማለት
አንዳንዱ በምስክሮች ላይ ያተኩራል፣ ሌላው በተከሳሽ፣ ሌላው በከሳሽ፣ ሌሎች ደግሞ
በአቃቢ ህጉ፣የተወሰኑት ደግሞ በጠበቃውና በዳኛው ላይ ያተኮረ ዜና ይዘው ይመጣሉ፡፡
ስለዚህ የውስንነት ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ ሚዛናዊ ለማድረግ መሞከር ተገቢ ነው፡፡

ጥሩ ልምድ ያካበቱ ሪፖርተሮች ከግል እይታቸው እና እምነታቸው ውጭ ዜና


ይፅፋሉ፡፡ ይህም ሚዛናዊ ሆነው እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ጋዜጠኞች ፍትሃዊና ሚዛናዊ
በሆነ መል ዜናን ካልሰሩ እውነትን ማዛባታቸው አይቀርም፡፡ እውነት ሲዛባ ደግሞ
የአድማጭ ተመልካች እምነትን ማጥት ያስከትላል፡፡ ሰው መሆን በራሱ ራሳችንን ዜና
ውስጥ ጨምረን እንድናስብ ቢያደርገንም እንኳ እንደጋዜጠኛ ግን ዜና በሚሰበሰብበት
ጊዜ ነፃና ሚዛናዊ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ ሚዛናዊነት ከምንሰራው ሥራ ጋር
በተያያዘ በሂደቶች ውስጥ የምናደርገው መንገድ እንጂ ዉጤቱ ላይ አይደለም፡፡

ለምሳሌ፡- መንግስትና ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እየጨቆኑ


መሆኑን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡

በዚህ ዜና ውስጥ ከመንግስት፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር


በምናደርጋቸው ቆይታዎች በተመሳሳይና ሚዛናዊ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ነገር ግን
ጋዜጠኛው የመንግስት ደጋፊ ወይም በመንግስት የሚዲያ ተቋም ውስጥ የሚሰራ
ስለሆነ ብቻ የተቃዋሚዎችን ጉዳይ ከፀረ-ሠላም አካላት ወይም ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር
አያይዞ መናገር ከጋዜጠኛ የማይጠበቅ ነው፡፡

24
3. ምልዑነት

ዜና ከተለያየ አቅጣጫ ያሉትን ጉዳዮች በመያዝ ምልዑ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡


አብዛኛውን ጊዜ በጋዜጣና በመፅሔቶች ላይ ለሚወጣ ዜና ነገሮችን ከብዙ አቅጣጫ
በማየት ማቅረብ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የጋዜጣውና የመፅሔቱ የህትመት ቀን
እስኪደርስ ብዙ የማጣራት ተግባራት ማከናወን ስለሚቻል ነው፡፡ ይኸውም የሌሎች
የህትመት ውጤቶችን፣ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዘገባዎችንና ትንታኔዎችን፣ በኢንተርኔት
ለላይ የሚለቀቁ መረጃዎችን በማየትና የመረጃ ምንጮችን በማነጋገር የተጠናከረ ምልዑ
ሥራ ይዘው መውጣት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል በብሮድካስት ሚዲያ ሁሌም አወዛጋቢ
በሆኑ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ነገሮችን አሟልቶ መቅረብ ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም
ብሮድካስት ሚዲያ በዋናነት ከጊዜ ጋር ስለሚሰራ ነው፡፡ ሚዛናዊነትና እይታ በጣም
አስፈላጊ ስለሆኑ በዜና ውስጥ ከተካተቱ ዜናው ምልዑ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን
ሁሌም ከሰዓት ጋር በተያያዘ ጉዳይ ግፊት ስላለ ፍጥነትና ቅልጥፍና ይፈልጋል፡፡ አንድ
ዜና ምልዑ የሚሆነው እውነትና ሚዛናው ሲሆን ነው፡፡ ይህም ተግባራዊ የሚሆነው
የጉዳዩን ባለቤቶች ከተለያየ ጎን ይዞ መቅረብ ሲቻል ነው፡፡

4. ግልፅነት

ዜና መዘገብ ያለበት አጭርና ግልፅ በሆነ መልኩ ነው፡፡ በተለይም ለብሮድካስት ሚዲያ
መዘገብ ያለበት አንድ ጊዜ ተሰምቶ በቀላሉ ለአድማጭ ተመልካች በሚገባበት መልኩ
መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የብሮድካስት አድማጭ ተመልካቾች እንደገና ደግመው
የመስማት ዕድል የላቸውም ወይም ያልገባቸውን ነገር ከተለያዩ ነገሮች ላይ ለማጣቀስም
ሆነ ለማሰብ ጊዜ ስለሚያስፈልጋቸው ያንን ሲያደርጉ ሌሎች ዜናዎች ስለሚያልፉ ነው፡፡
ስለዚህ ዜናው ግልፅና በቀላሉ ለአድማጭ ተመልካች የሚገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ለዚህ ደግሞ የዜናው ፀሐፊዎች የሚመርጧቸው ቃላትና የዓረፍተ ነገር አወቃቀራቸው
ቀላልና ያልተንዛዛ መሆን አለበት፡፡ ይህም የአድማጭ ተመልካችን ሥራ ከማቅለሉ በላይ
ዜናውን ተደማጭ ያደርገዋል፡፡

25
5. ምንጭን መለየትና መግለፅ

ዜና በሚሰራበት ጊዜ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን እንጠቀማለን፡፡ እነዚህን የመረጃ


ምንጭ ግን እየለዩ መጠቀም ከጥሩ ዜና የሚገኝ አላባ ነው፡፡ ስለዚህ የዜና ምንጮችን
በግልፅና በአግባቡ መጠቀም ከጥሩ ዜና ይጠበቃል፡፡ የመረጃ ምንጭን በተመለከተ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቃል፡፡

 ትክክለኛው የመረጃ ምንጭ ማን ነው?


 የመረጃ ምንጩ ታማኝ ነውን?
 የትኛው የመረጃ ምንጭ የበለጠ ታማኝ ነው?
እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ከመለስን የመረጃ ምንጫችንን ለየን ማለት ነው፡፡ ከዚያ
ቀጥሎ እንዴት እንጠቀምበት የሚለው ጥያቄ መመለስ ነው፡፡
የመረጃ ምንጭ ሰዎች፣ ተቋማት ወይም የተለያዩ ሰነዶችና ዶሴዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ስለዚህ እውነትና ውሸቱን ለይተን ካየን በኋላ በምን መልኩ ልግለፃቸው (attribution)
የሚለው ወሳኝ ነው፡፡ ለመረጃ ምንጮች መጠቀስም ሆነ ክብር መስጠት ተገቢ የጥሩ
ዜና ጥንቅር አካል ነው፡፡ የመረጃ ምንጭን በአግባቡ መለየትና መጥቀስ የራሱ የሆነ
ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

 የዜናውን ታማኝነት ይጨምራል


 የዜናውን ግልፅነት ያሳድጋል
 የጋዜጠኞችን የህግ ጥያቄዎች ይከላከላል፡፡ ይህም ማለት የመረጃ ምንጩ
ከተጠቀሰ ጉዳዩ የሚሆነው የምንጩ እንጂ የጋዜጠኛው አይደለም፡፡
የመረጃ ምንጮችን በምንጠቀምበት ጊዜ በብሮድካስትና በህትመት ዜና ጊዜ የአጠቃቀም
ልዩነት አለው፡፡ ይኸውም በህትመት ዜናዎች እንደፈለግን በሰጡት መረጃ ፊት፣
መሃል፣ መጨረሻ ወይም እየተቀላቀለ መጠቀም ሲቻል በብሮድካስት ዜናዎች ግን
ሁልጊዜም ከመረጃው በፊት መቀመጥ አለበት፡፡ ምክንያም ደግሞ ዜናው የሚፃፈው
በንግግር መልኩ ስለሆነ ነው፡፡

26
2.2 የዜና ምንጮች

2.2.1 ዜና ከየት ይገኛል?

የመወያያ ጥያቄ

1. የመረጃ ምንጭ ምንድነው?


2. የመረጃ ምንጭ ከሪፖርተሮች ጋር ያለው ግንኙነት
እንዴት መሆን ይጠበቅበታል?

የመረጃ ምንጭ ማለት ማንኛውም ግለሰብ፣ ድርጅት፣ ተቋም ወይም ቡድን በትክክል
የተዋቀረ መረጃ ማቅረብ ወይም መስጠት የሚችል ነው፡፡ እነዚህ የመረጃ ምንጮች
ከጋዜጠኛው ጋር በሚኖራቸው ጊዜ ስለድርጅታቸው ወይም ስለራሳቸው ትክክለኛ መረጃ
የመስጠት አቅም ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተመሳሳይ ሪፖርተሩም የመረጃ ምንጮችን
አያያዝ በተመለከተ አግባብነት ያለው አካሄድ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህም ማለት በመረጃ
ምንጩና በጋዜጠኛው መካከል መልካም ግንኙነት ሊመሰረት ይገባል፡፡ ምክንያቱም
ያለመረጃ ምንጮች የጋዜጠኛነትን የዕለት ከዕለት የሥራ እንቅስቃሴ የተሟላ ማድረግ
ስለማይቻል ነው፡፡

በምዕራፍ አንድ የጋዜጠኝነት ትርጉም ላይ “መረጃን የሚሰበስብ፤ የሚያዘጋጅ፤ እና


የሚያሰራጭ ባለሙያ በማለት ጋዜጠኝነትን መተርጎማችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም
የመረጃ ምንጮቻችን በአግባቡ ካልተያዙና ግንኙነቱ መልካም ካልሆነ ጋዜጠኛው
የሚያሰባስበውም፣ የሚያዘጋጀውም ሆነ የሚያሰራቸው መረጃ አይኖርም ማለት ነው፡፡
ይህ ደግሞ የጋዜጠኝነትን ሥራ ያቆመዋል ማለት ነው፡፡

መረጃ ለጋዜጠንነት ሥራ በተለይም ለዜና ሥራ ደም ነው፡፡ ጋዜጠንነት አንድ የተገነባ


ሰው አድርገን ብንወስደው ዜናን ደግሞ እንደልብ ብንቆጥር መረጃው ደግሞ ደም ቢሆን
ጋዜጠኝነት በህይወት እንዲኖር ዜና መንቀሳቀስ አለበት፤ ዜና ደግሞ ብቻውን
መንቀሳቀስ ስለማይችል የግድ የሚያሰራጨው መረጃ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ የመረጃ
ምንጮቻችን ተዘጉ ማለት ለጋዜጠኝነት የሚቀርብ መረጃ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡
የተጀመረው መልካም ግንኙነት ደግሞ ሁሌም መቀጠል አለበት፡፡ መቀጠል ብቻ ሳይሆን

27
ተጠንክሮ መቀጠልም ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በጋዜጠኛውና በመረጃ ምንጩ መካከል
ያለውን ግንኙነት ለማሳደግ የሚከተሉት ተግባራት መከናወን ይገባቸዋል፡፡

ሀ. የተጀመረውን ግንኙነት ማጠናከር


ለ. የመረጃ ምንጮቻችን ምስጢር መጠበቅ
ሐ. ግላዊና ተቋማዊ ክብርንና ታማኝነት ማጠናከር
መ. ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸውን መረጃዎች ማረጋገጥ፣ መመዘንና መጠቀም
ሠ. ከምንጮች ጋር አብሮ የመስራት ችሎታን ማዳበር
ረ. ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን ጓደኛነት መመስረትና ማጠናከር

ከላይ በተዘረዘሩት ነገሮች ጋዜጠኞች የመረጃ ምንጭ መረባቸውን ማስፋፋት ይችላሉ፡፡


ሪፖርተሮች የአንድ የብዚሃን መገናኛ አምባሳደር መሆን አለባቸው ምክንያቱም እነሱ
የሚወክሉትን ኃላፊነት ወስደው የሚንቀሳቀሱት የተቋማቸውን ህልውና ነው፡፡
ሪፖርተሮች ከመረጃ ምንጮቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ምክንያት የብዙሃን
መገናናው ህልውና ሊቋረት ወይም ሊቀጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኞች
እንደአምባሳደርነታቸው ጤናማ የሆነ ግንኙነት የመመስረት፣ የማሳደግና የማጠናከር
ኃላፊነት አለባቸው፡፡

2.2.2 የዜና ምንጮች

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ዜና ከተለያዩ ምንጮች ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል


የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

ሀ. የሚዲያ ተቋሙ ሪፖርተሮች፡- ተቋማት በየቦታው የሚልኳቸውና የሚመድቧቸው


ትርፍ ጊዜ ወይም የሙሉ ሰዓት ጋዜጠኞች መረጃን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ይኸውም
የተመለከቱትን ነገር እንደዜና ምንጭ በመሆን መረጃን ለብዙሃን መገናኛ ተቋማት
ያቀብላሉ፡፡

ለ. አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የዜና ማዕከላት አገልግሎቶች፡- ጋዜጦችና የብሮድካስት


ተቋማት ዜናን ከተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ወይም የሃገር ውስጥ የዜና ማዕከል ሊያገኙ
ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሃገር
ውስጥ ዜናዎችን ከሃገር ውስጥ የዜና ማዕከላት ያገኛሉ፡፡ እነዚህም የዜና

28
ማዕከላትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)በ እና ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል
(ዋልታ) ናቸው፡፡ የውች ሃገር ዜናዎችን ደግሞ የቻይናው ሽንዋ፣ አጃንስ ፋራንስ
ፕሬስ፣ ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርንሽናል፣ ፓን አፍሪካን ኒውስ ኤጀንሲ (ፓና)፣
ሮይተርስ፣ ወዘተ የሚጠቀሱ ዋና ዋና የዜና ምንጮች ናቸው፡፡

ሐ. ኔትወርኮች፡- ይህ በኢትዮጵያ የተለመደ ባይሆንም በበለፀጉ ሃገሮች ብዙ


የብሮድካስት አገልግሎቶች መረጃን ከሚከፋፍሏባቸው ተቋማት በገመድ ወይም
በካርድ አማካንነት አማካኝነት መረጃን የመውሰድ ሁኔታ ነው፡፡ ከዚህም በጠጨማሪ
በኢንተርኮም (የውስጥ መስመር) አማካኝነት መረጃን ያገኛሉ፡፡

መ. ነፃ ጋዜጠኞች (freelancers)፡- እነዚህ ጋዜጠኞች ግለሰቦች ወይም በቡድን


ተደራጅተው ለዜና የሚሆኑ መረጃዎችን እየሰበሰቡ ዜና በመፃፍ በውል ለብዙሃን
መገናኛ ተቋማት የሚያሰራጩ ናቸው፡፡ ለሬዲዮ በፅሁፍና በድምፅ ሲቀርቡ
ለቴሊቪዥን ደግሞ ምስሉን ጨምረው ያቀርባሉ፡፡

ሠ. ከመስሪያ ቤት የሚወጡ ዜናዎች (furnished news)፡- እነዚህ ዜናዎች የሚወጡት


ከመስሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶች፣ ሲሆን በህዝብ ግንኙነቱ አማካንነት ይሰጣሉ፡፡
የሚዲያ ጥቆማና የፅሁፍ ስርጭት (ፕሬስ ሪሊዝ) የሚያካትት ነው፡፡ ይህ
በአብዛኛው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ለደንበኞቻቸውና ለባለድርሻ አካላት
የሚያሰራጩት የዜና ምንጭ ይሆናል፡፡

ረ. ኩነቶች፡- በየጊዜው የሚከሰቱና የሚካዱሄዱ ኩነቶች ለዜና ምንጭነተር ያገለግላሉ፡፡


የሚስቡና ያልተለመዱ ሲሆኑ ደግሞ የበለጠ የብዙሃን መገናኛን ቀልብ ይስባሉ፡፡
ለምሳሌ ጋዜጣዊ መግለጫ ጉባኤ፣ ምርቃት፣ ህዝባዊና ብሄራዊ በዓላት፣ አደጋዎችና
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆችወዘተ እንደኩነትነታቸው የመረጃነ ምንጭ ሆነው
ያገለግላሉ፡፡

ሰ. ህዝባዊ ትዕይንቶች፡- በርካታ ህዝብ የሚሳተፍባቸው ህዝባዊ ትዕይንቶች የዜና


ምንጭ ይሆናሉ፡፡ ሰላማዊ ሰልፎች፣ የተቃውሞ ሰልፎች፣ የድጋፍ ሰልፎች፣
ዘመቻዎች፣ ቅስቀሳዎች ዋና ዋና የህዝባዊ ትዕይት ዘርፍ ሲሆኑ የዜና
ምንችነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡

29
2.2.3 የዜና ምንጮች አያያዝ

መረጃ ምንጮችን በተገቢው መንገድ መያዝ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የመረጃ መ፣ንጮች
ስማቸው እንዳታወቅ የሚፈልጉ፣ ማንነታቸው እንዳይታወቅ የሚፈልጉ ወይም ደግሞ
ስማቸውንና ማንነታቸው በሚስጢር እንዲያዝላቸው የሚፈልጉ፣ ድምፃቸውና ምስላቸው
እንዳይቀረፅ የሚከለክሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን የመረጃ ምንጮች እንዴት መጠቀም
እንዳለበት የሚያውቅ ጋዜጠኛ ደግሞ በሥራው ከፍተኛ ትርፍ ያገኛል፡፡

 መረጃ እያላቸው መረጃ መስጠት የማይፈልጉ ሰዎች


ቢኖሩ ምን ታደርጋላችሁ?
 መረጃውን ሰጥተው ማንነታቸው እንዳይገለፅ
የሚፈልጉትንስ?

መረጃ መስጠት የማይፈልጉ (reluctant) ምንጮች

ሰዎች መረጃ ከመስጠት ለምን ወደኋላ ይላሉ? ብዙውን ጊዜ ሰዎች መረጃዎችን


የማይሰጡት በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡

 በአለቆቻቸው በኩል የሚደርስባቸውን እርምጃና ከሥራ መፈናቀል በመፍራት


 ከህዝብ ግንኙነት ዌም ከቃል አቀባዩ መረጃውን እንዲሰሙ ስለሚፈልጉ
 ከዚህ ቀደም በሌላ ጋዜጠኛ በሥርዓት ሳስተናገዱ በመቅረታቸው ምክንያት
ላለመተባበር በመወሰናቸው
 የሚሰጡት አስተያየት ዌም መረጃ ጠቃሚ መስሎ ስለማይታያቸው
እነዚህን ምክንያቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት ጋዜጠኛው ለመፍታት የተለያዩ
ስትራቴጂዎችን ይመቀማሉ፡፡ ከነዚህ ስትራቴጂዎች መካከልም የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
 መረጃ በመስጠታቸው ምክንያት ምንም ዓይነት ችግር እንደማይደርስባቸው
የማሳመን ሥራ መስራት
 ጥያቄውን ከሚመለከተው አካል እንደጠየቁ በመንገር የተገኘውን መረጃ
ለማረጋገጥ ብቻ እንደምናናግራቸው በመንገር ማሳመን

30
 ከአሁን በፊት ስላስቀየማቸው ጋዜጠኛ ይቅርታ በመጠየቅ የራስን ስብዕና
ማስረዳት
 ምንጮች የነሱ መረጃ ጠቃሚ መስሎ ካልታያቸው በጣም ጠቃሚ የሆነ መረጃ
እንሱ ጋ እንደሚገኝ ሌለ፤ ሰው ላይ ያንን መረጃ ማግኘት እንደማይቻል
በማሳመነን መረጃ እንዲሰጡ ማድረግ

ማንነታቸው እንዳታወቅ ወይም በሚስጥር እንዲያዝላቸው የሚፈልጉ


(Anonymity & Confidentiality) ምንጮች

አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ማንነታቸው እንዳታወቅ ወይም በምስጥር እንዲያዝላቸው


በመረጃ መስጠት ሂደቱ መጀመሪያ፣ መሃል ላይ ወይም መጨረሻ ላይ ሊጠይቁ
ይችላሉ፡፡ ይኸውም መረጃውን ሲሰጡ የነሱን ማንነት እንዳይገለፅ ሲፈልጉ ጋዜጠኛው
ቃል እንዲገባ ያደርጋሉ ወይም ይጠይቃሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚሰጡትን መረጃ በጣም
ጠቃሚ ስለሚሆን በስማቸውና ማንነታቸው አለመገለፅ ላይ ከጋዜጠኛው ጋር
መስማማት አለባቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ዓይነት የዜና ምንጮችን ለመጠቀም እንዴት
መያዝ አለባቸው ለሚለው የሚከተሉት መንገዶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

1. ለሚጠይቁት ጥያቄ ውል በመስጠትና ቃል በመግባት ማረጋገጥ


2. እዲቀረፁ በማግባባት አስተያየታቸውን ለመጠቀም ማሳመን
3. በመቃወም እነሱን ትቶ በመሄድ ሌለላ የሚቀረፅ ሰው ፈልጎ በመቅረፅ መጠቀም
እነዚህን አማራጮች በምንወስድበት ጊዜ የሃገሪቱን ህግና አዋጆች ከግምት ውስጥ ያስገባ
መሆን ይጠበቅበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን የተለያዩ ሃረጎችን በመጠቀም ስማቸው
እንዳይጠቀስ የፈለጉትን የመረጃ ምንጮች እንደአማራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ለምሳሌ፡-
 ለከንቲባ ቅርብ የሆነ ምንጭ እንደተናገረው…….
 ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ የቢሮው ሠራተኛ እንደገለፁት…
 አንድ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካል እንዳሉት…..
ብዙውን ጊዜ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምንጮችም ቢኖሩ መረጃው በመቅርፀ-
ድምፅ እንዳይቀረፅ የሚፈልጉት ግን በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መረጃ እንዳይቀረፅ
የሚፈልጉትን ምንጮች በዜና ውስጥ በቀጥታ ጥቅስ ሳናስገባ በፅሁፉ ውስጥ ፍትሃዊ
በሆነ መልኩ ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡ ጋዜጠኛው ስማቸውንና ማንነታቸውን

31
ላለመግለፅ ከተስማማ ደግሞ ስምምነቱን ማክበር ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም ቃላችንን
ካላከበርነ ሌላ ጊዜ በፍፁም መረጃ ማግኘት ላይቻል ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ጋዜጠኝነት
የአንድ ቀን ሥራ ስላልሆነ የጋዜጠኝነት ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል፡፡

2.2.4 መረጃ እንዴት ይገኛል?

 መረጃ እንዴት ይገኛል?


 በየትኛው መንገድ የተገኘ መረጃ ነው ለሚዲያ ፍጆታ
የሚውለው?

መረጃን በተለያየ መንገድ እናገኛለን፡፡ ለዜና ግብዓት የሚሆነንን መረጃ ደግሞ


የምንፈልገው ሠላማዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ አስገድዶ እየደበደቡ መረጃን ማግኘት
የጋዜጠኝነት ሥራ አይደለም፡፡ ስለዚህ የጋዜጠኛ ሁነቶችን፣ ሁኔታዎችን፣ ዝግጅቶችን
በመመልከት ቃለመጠይቅ በማድረግ እና የራሱ የሆነ ጥናትና ምርምር በአንድ ጉዳይ
ላይ በማድረግ መረጃን ይሰበስባል፡፡ እነዚህ መንገዶች በውስጣቸው የተለያዩ ቴክኒኮች
አሏቸው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ እያንዳዳቸውን አንድ በአንድ እንመለከታለን፡፡

ሀ. ምልከታ

በአንድ ጉዳይ ላይ የተሻለ ሽፋን ለመስጠት ተመራጩ መንገድ ቦታው ድረስ በመሄድ

መመልከት (Observation) ነው፡፡ ምልከታ በጋዜጠኝነት ሥራ ውስጥ የዕለት ተዕለት

ተግባር መሆን ያለበት የመረጃ መሰብሰቢያ መንገድ ነው፡፡ ጋዜጠኛው በቦታው ተገኝቶ
ሁኔታዎችን መመልከት ካልቻለ የአንድ ዜና ጥንቅር ምልዑነት አስተማማኝ አይሆንም፡፡
ምክንያቱም ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት በሌሎች መንገዶች የሚሰበሰቡትን ጉዳዮች
በዓይን ተመልክቶ የማረጋገጥ ወይም ደግሞ ውድቅ የማድረግ ሥራዎችን ለማድረግ
ተጨማሪ ኃይል ስለሚሰጥ ነው፡፡

“ማየት ማመን ነው” እንደሚባለው በዜና አሰባስባችን ውስጥ ቦታው ድረስ በመሄድ
መመልከት የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት አለው፡፡ አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ
መመልከት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች፡-

 ሁኔታዎችን በቀላሉ ለመረዳት


 ጉዳዩን በቅርበት የበለጠ ለማረጋገጥ

32
 ከሚታየው ነገር ባሻገር ስላለው እውነት ለማወቅ
 ሠው በንግግር ሊገልፃቸው የማይችሉ ጉዳዮችን ለማግኘት ዕድል ይሰጣል
 ከባለጉዳዮች ጋር ቅርርብ መፍጠር ስለሚችል… ወዘተ
በሌላ በኩል አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት ያሉት ጉዳቶች፡
 ከፍተኛ የሆነ ወጪ ይጠይቃል (የማቴሪያል፣ የገንዘብና የጉልበት ወጪ)
 ጊዜ ይፈጃል
 ወደ ቦታው ለመግባት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መጋፈጥ ይጠይቃል
 ከጉዳዩ ባለቤቶች የሚደርሱ ክልከላዎችና ማስፈራሪያዎች ወዘተ ይገኙበታል፡፡

ምንም እንኳ አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት የራሱ የሆነ ጥቅሞችና
ጉዳቶች ቢኖሩትም ስለጉዳዩ ምልዑ የሆነ መረጃ ለመሰብሰብ መድረክ ስለሚከፍት
ተመራጭ መንገድ ያደርገዋል፡፡

ለምሳሌ፡- በቦረና አካባቢ 4.5 ሚሊዮን ህዝቦች ተርበዋል የሚል ወሬ ሰምታችሁ የመረጃ
ምንጫችሁ ምናልባትም የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡትን መግልጫ ጉባኤ ከአዲስ
አበባ ብትከታተሉ ወይም ከቦረና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚልከውን
ጋዜጣዊ መግለጫ ፅሁፍ እንደምንጭ ብትጠቀሙ ምናልባት የጉዳዩን ሁለትከመቶ
እንኳን በሚገባ መረዳት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የጉዳዩን አስከፊነት ሠዎች
ከሚነግሯችሁ በላይ ቦታው ድረስ ሂዳችሁ ብትመለከቱ የበለጠ መረዳት ስለምትችሉ
ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ አስር ሰዎች ሞተዋል ሲባል መስማትና አስር ሰዎች
በረሃብ አለንጋ ተገርፈው ቆዳቸው ከአጥንታቸው ተጣብቆ ሲሞቱ ማየት ለጋዜጠኛ
የበለጠ ትርጉም የሚሰጠው የትኛው እንደሆነ የታወቅ ነው፡፡

የምልከታ ዓይነቶች

መረጃን ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት ከድርጊቱ ድግግሞሽና ሂደት አንጻር በሁለት


ይከፈላል፡፡ እነሱም በተለያዩ ክፍሎች የአንድ ጊዜ ምልከታ (Episodic Observation)
እና ሥርዓታዊ ምልከታ (Systematic Observation) ተብለው ነው፡፡ የአንድ ጊዜ
ምልከታ የሚደረገው በተከታታይ በተጠናና በተደራጀ መደበኛ በሆነ መልኩ ሳይሆን
በኢ-መደበኛ ድንገት ቦታው ላይ በመገኘት የሚከናወን ነው፡፡ ሥርዓታዊ ምልከታ ደግሞ

33
መደበኛ በሆነ መልኩና በተደራጀ አካሄድ የሚደረግ ነው፡፡ እነዚህን የምልከታ ዓይነቶች
በውስጣቸው የተለያዩ የምልከታ ዓይነቶች ይዘዋል፡፡

የአንድ ጊዜ ምልከታ

የአንድ ጊዜ ምልከታ በራሱ ሶስት የተለያዩ የምልከታ ዓይነቶችን አካቷል፡፡ እነሱም

ሀ. ልማዳዊ ምልከታ (Conventional Observation)


ለ. ድብቅ ምልከታ (Unobtrusive Observation)
ሐ. አሳታፊ ምልከታ (Participant Observation)

እነዚህ ሶስቱ የምልከታ ዓይነቶች አንድ ድርጊት ሲፈጸም ወይም ክስተት ሲከሰት ቦታው
ላይ በመገኘት የሚከናወኑ የምልከታ ዓይነቶች ናቸው፡፡

ሀ. ልማዳዊ ምልከታ

ልማዳዊ ምልከታ አሳታፊ ያልሆነ የምልከታ ዓይነት ሲሆን የማህበራዊ


እንቅስቃሴዎችን ለማጥናት ወይም አሳታፊ ባልሆነ መልኩ መረጃን ለመሰብሰብ
ያገለግላል፡፡ የህብረተሰብ ሳይንስ ባለሙያዎች የሰዎችን ባህርይ ለማጥናት ይህንን
የምልከታ ዓይነት ይጠቀማሉ፡፡ ጋዜጠኞችም የህብረተሰብ ሳይንስ አካል እንደመሆናቸው
የሰውን ባህርይ ለማጥናት ልማዳዊ በሆነ፤ ራሳቸውን የድርጊቱ አካል ሳያደርጉ
ይጠቀሙበታል፡፡ ልማዳዊ ምልከታ ስብሰባዎችን በምንከታተልበት፣ ንግግሮችን
ስናዳምጥ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ስንመለከት፣ ኮንሰርቶችን ስንታደም፣ የጋዜጣዊ
መግለጫ ጉባኤዎችን፣ የምርቃት መርሃ-ግብሮችን፣ ዓመታዊ በዓላትን ወዘተ
በምንመለከትበት ወቅት የምንጠቀምበት የምልከታ ዓይነት ነው፡፡ ልማዳዊ ምልከታ
ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው የመረጃ ምንጮች የጋዜጠኛውን መኖር እያወቁ ነው፡፡
ይኸውም የመረጃ ምንጮች በጋዜጠኛ እይታ ውስጥ እንደሆኑ እያወቁ ነው
የሚካሄደው፡፡

የልማዳዊ ምልከታ ጠንካራ ጎኖች፡-

 ጋዜጠኛው ሥነ-ምግባር ጠብቆ የሰዎችን ግለኝነት መብት ሳይነካ እንዲሰራ


ያደርጋል፡፡

34
 የመረጃ ምንጩ ጋዜጠኛው እንዲያይለት የሚፈልገውን ነገር በሙሉ ለማሳየት
ይጥራል፣ ይኸውም የመረጃ አድማሱን ያሰፋዋል፡፡
 ጋዜጠኛው ራሱን የጉዳዩ አካል ስለማያደርግ በተቻለ መጠን ነፃና ሚዛናዊ ሆኖ
እንዲሰራ ይጠቅማል፡፡
 ጋዜጠኛው የጋዜጠኛ የሥራ መሳሪያዎችን (ካሜራ፣ መቅርፀ- ድምፅ፣ ማስታወሻና
ሌሎችንም) እንዲጠቀም ይረዳዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ልማዳዊ ምልከታ የራሱ የሆነ ድክመቶች አሉት፡፡ ልማዳዊ ምልከታ
በአንድ የተወሰነ ጊዜ ውስጥ ውስን የሆነን እንቅስቃሴ ለማየት የሚደረግ ስለሚሆን
በዋናነት በዛች ሰዓትም የመረጃ ምንጩ የጋዜጠኛውን መኖር እያወቀ በመካሄዱ
ምክንያት የተለያዩ ድክመቶች አሉት፡፡ የጋዜጠኛውን መኖር ስለሚያውቁ ትክክለኛ
ሥራቸውንና ሰብዕናቸውን እንዲደብቁ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ጋዜጠኛው የመረጃ
ምንጩ በወቅቱ በሚያሳየው ነገር ላይ እንዲወሰን ያደርገዋል፡፡
ለምሳሌ፡- የአባይ ግድብን ለመመልከትና ስለግድቡ መረጃ እንዲኖረን የሥራ ኃላፊዎችን
ማግኘት ስላለብን የምናገኘው በልማዳዊ ምልከታ ነው፡፡

ለ. ድብቅ ምልከታ

ድብቅ ምልከታ እንደልማዳዊው ምልከታ በአንድ የተወሰነ ቦታ ተገኝቶ አንድን ጉዳይ


ለተወሰነ ጊዜ መመልከት ሲሆን ብዙውን ጊዜ ሪፖርተሮች አንድ አዲስ ነገር ከተከሰተ
ብቻ የሚያደርጉት ነው፡፡ በልማዳዊው ምልከታ የሪፖርተሩን መኖር በመረጃ ምንጮች
የታወቀ ስለሚሆን ምንጮቹ ከመደበኛው ባህርያቸው ውጭ የሆነ ተግባርና እንቅስቀቃሴ
ስለሚያሳዩ ትክክለኛ ማንነታቸውን ማወቅ ስለማይቻል የድብቅ ምልከታ ይከናወናል፡፡
የድብቅ ምልከታ በዋናነት የመረጃ ምንጩ ሳያውቅ በድብቅ በመግባት መረጃ ሰብስቦ
የመውጣት ሂደት ነው፡፡

ለምሳሌ፡- አንድ ህፃናትን በጉዲፈቻ አሳድጋለሁ የሚል ሰው ሴት ህፃናትን


ወደቤቱ እያስገባ የመድፈር ሥራ ቢያደርግ ሰውየውን በልማዳዊ መንገድ
ለመከታተል ቢሞከር ልጆቹን ሲደፍርም ሆነ ሲያሰቃያቸው ማየት አይቻልም፡፡
ሰውየው በተቻለ መጠን ልጆቹን በአባትነት ስሜት ሲንከባከባቸው ነው
የሚታየው፡፡ ስለዚህ በቤት ሠራተኛ ወይንም የጥበቃ ሠራተኛ አማካኝነትና

35
እርዳታ ተደብቆ በመግባት መመልከት ይገባል፡፡ ስለዚህ የሰዎችን ድብቅ ማንነት
በድብቅ በማየት የህፃናቱን መደፈር መረጃ መሰብሰብ ይቻላል፡፡

የድብቅ ምልከታ የራሱ የሆነ ጥቅምም ተግዳሮትም አሉት፡፡ ጥቅሞችን በምናይበት ጊዜ


በልማዳዊ ምልከታ ማግኘት የማንችለውን መረጃ ማግኘት ያስችላል፡፡ ስውር ሴራዎችንና
የተደበቁ ወንጀሎችን ለማጋለጥ ይረዳል፡፡ በሌላ በኩል ግን የመረጃ መሰብሰቢያ የሆኑ
ቁሳቁሶችን (የቪዲዮ ካሜራ፣ የፎቶግራፍ ካሜራ፣ ማይክራፎን፣ መብራት፣ መቅርፀ-
ድምፅ፣ ማስታወሻ ወዘተ) መያዝ አስቸጋሪ ተግዳሮት ነው፡፡ ይህም የምንመለከተው
ሰው እንዳያውቅ ከሚደረገው እንቅስቃሴ ጋር ጋዜጠኛው መደበቅ ስላለበት በስውር
ስለሚገባና ስለሚወጣ እነዚህን ነገሮች መጠቀም አያስችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
የመረጃ ምንጭን የግለኝነት መብት በመጣስ የጋዜጠኝነት ህግና ሥነ-ምግባር መተላለፍ
እንደተግዳሮት ይወሰዳል፡፡

ሐ. አሳታፊ ምልከታ

አሳታፊ ምልከታ አንዳንድ ጊዜ “ራስህ ስራው” ምልከታ በመባል ይታወቃል፡፡ ይኸውም


ጋዜጠኛ በጉዳዩ ውስጥ ራሱን አስገብቶና የጉዳዩ ተሳታፊ በመሆን መረጃን
የሚሰበስብበት መንገድ ስለሆነ ነው፡፡ በአሳታፊ ምልከታ የጋዜጠኛውን መኖርና
አለመኖር የመረጃ ምንጮች ሊያውቁም ላያውቁም ይችላሉ፡፡ የመረጃ ምንጮች
የጋዜጠኛውን መኖር ካላወቁ የምስጢር ተመልካች (Undercover Observer) ይሆናል
ማለት ነው፡፡ ይህ የምስጪር ተመልካች ከድብቅ ምልከታ የሚለይባቸው የራሱ የሆኑ
መንገዶች አሉት፡፡ የምስጢር ተመልካች የጋዜጠኛው መኖር ባይታወቅም ከሚመለከተው
ጉዳይ ውስጥ ራሱን በማስገባት ይሳተፋል፤ በድብቅ ምልከታ ግን ጋዜጠኛው ተሳታፊ
አይደለም፡፡ ስለዚህ አንድ ጉዳይ ውስጥ ጋዜጠኛው ራሱን አስገብቶ ለመመልከት
ጋዜጠኛ መሆናችንን እና አለመሆናችንን ለመግለፅ የሚወሰነው በጉዳዩ ክብደትና ቅለት
ነው፡፡

ለምሳሌ፡- በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ሌላ ሃገር የሚያጓጉዙ ደላላዎችን በተመለከተ


መረጃ ለመሰብሰብ እንደ አንድ ተጓዥ ስደተኛ ሆነን ልንገባ እንችላለን፡፡ በዚህ ጊዜ
የእኛን ማንነት ደላላዎች ካወቁ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማወቁ ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ
ራሳችንን ደብቀን ምስጢራዊ ተመልካች እንሆናለን ማለት ነው፡፡

36
ምንም እንኳ ጋዜጠኛው ራሱን መግለፅ ከክህደትና አጭበርባሪነት ተግባር ነፃ
ቢያደርገውም ነገሮች ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ራሳቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ
ጋዜጠኛው ራሱን በሚስጢር ደብቆ መመልከት የተሸለ ታሪክ ይዞ እንዲመጣ
ያደርገዋል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ጉዳዩ ቀላልና ለማየት የማይከለከል ከሆነ ራሳቸውን
ጋዜጠኞች እንደሆኑ በመናገር መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በመስቀል በዓል የጉራጌን
የክትፎ አዘገጃጀት በተመለከተ ጋዜጠኛው አብሮ እየሠራ መመልከት በምስጢር
ከመመልከቱ የተሻለ ነው፡፡

አሳታፊ ምልከታ በልማዳዊ መንገድም ሆነ በድብቅ ከምናካሂደው ምልከታ አዲስ


አተያይ ይዘን እንድንመጣ ስለሚያደርግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ትክክለኛውን መረጃም
እንዲገኝ ያስችላል፡፡ ነገር ግን በተሳትፎ ጊዜ ሁልጊዜም ጋዜጠኝነታችንን መርሳት
የለብንም፡፡

ሥርዓታዊ ምልከታ

ከላይ በምልከታ ዓይነቶች አርዕስት ስር ለመግለፅ እንደተሞከረው በጣም መደበኛና


በተደራጀ መልኩ ለብዙ ተከታታይ ክፍሎች በትለ፤ለቅ አተያይ የሚደረግ የምልከታ
ዓይነት ሥርዓታዊ ምልከታ ይባላል፡፡ ስርዓታዊ ምልከታ አንድን ጉዳይ ሲከሰት ቦታው
ላይ ተገኝቶ መመልከት ሳይሆን ታስቦበትና በተከታታይ የሚደረግ ምልክት ነው፡፡ ይህ
ሥርዓታዊ ምልከታ በውስጡ አምስት የተለያዩ የምልከታ ዓይነቶችን አካቷል፡፡
እነርሱም፡-

ሀ. የህዝብ አስተያየትና የዳሰሳ ጥናት (Polls and Surveys)


ለ. የይዘት ትንተና (Content Analysis)
ሐ. ማህበራዊ አመላካቾች (Social Indicators)
መ. የመስክ ሙከራዎች (Field Experiment)
ሠ. አሳታፊ ምልከታ (Participant Observation)
የህዝብ አስተያየትና የዳሰሳ ጥናት፡- ስለአንድ ማህበረሰብ የህዝብ አስተያየቶች እየሰበሰቡ
የዳሰሳ ጥናት በማድረግ መረጃን መሰብሰብ ስለማህበረሰቡ ብዙ ነገር ለማወቅ
ይጠቅማል፡፡ ስለሆነም ስለአንድ ማህበረሰብ አንድ ቀን ብቻ በማየት ትክክለኛ መረጃን
መሰብሰብ ስለማይቻል በተቻለ መጠን ለረጅም ጊዜ ቦታው ላይ በመገኘት መከናወን

37
ይጠበቅበታል፡፡ ከዚያም በየቀኑ የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በማደራጀት መጠቀም ተገቢ
ነው፡፡ የህዝብ አስተያየቶችም ከቀን ቀን ስለሚለያዩ ሠፋ ያለ ጊዜ ወስዶ መመልከት
ይጠይቃል፡፡
የይዘት ትንተና፡- በአንድ ወቅት የተሰበሰቡትን ሰነዶችና መዛግብት በአንድ ጊዜ መርምሮ
ማስቀመጥ አይቻልም፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ 97 ወቅት የነበሩ የግል
ጋዜጦች ምን ዓይነት አቋም ነበራቸው በሚል ርዕስ የይዘት ትንተና ለማድረግ ብንፈልግ
የአንድን ጋዜጣ አንድ ህትመት ብቻ አይተን ፀረ-ኢህአዴግ ናቸው ልንል አንችልም፡፡
ሰፋ ላለ ጊዜ ሰፊ ናሙና ተወስዶ ሊሰራ ይገባል፡፡

ማህበራዊ አመላካቾች፡- ስለአንድ ማህበረሰብ መረጃ ለመሰብሰብ ጥናትን ትንተና


ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ስለማህበረሰቡ የስታትስቲክስ መረጃ በጣም
አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ ማህበረሰብ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ወደፊትስ ወደየት
እንደሚሄድ ለማወቅ አስፈላጊ የሆኑ ማህበራዊ አመለካከቶችን በተደራጀ መልኩ
መመልት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ የትምህርት ተደራሽነት
በተመለከተ ዜና መስራት ቢፈለግ በዋናነት የመረጃ ምንጭ የሚሆነው የስታትስቲክስ
መረጃዎችን ከድሮ እስከ ዘንድሮ መመልከት ነው፡፡

የመስክ ሙከራዎች፡- የኢቦላን መድኃኒት ሙከራዎች በተመለከተ በየቀኑ የጋዜጠኛው


ክትትል ያስፈልጋል፡፡ በአንድ ቀን ብቻ የኢቦላ መድኃኒት ተገኘ ሳይን እንዴት እየተሰራ
እነደሆነም ሪፖርተሩ በየቀኑ ደረስ ብሎ በመመልከት ያለውን ዕድገት ማወቅ
ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም የሙከራዎችን የመጨረሻ ውጤት ሳይሆን በየጊዜው ያሉትን
የአሰራር ሂደቶች ለማየት የመስክ ሙከራዎች አማራጭ የሌላቸው የመረጃ ምንጮች
ናቸው፡፡

አሳታፊ ምልከታ፡- ይህ አሳታፊ ምልከታ ከአንድ ክፍል ምልከታ የተለየ የሚያደርገው


ይህ በተደጋጋሚ፣ መደበኛ በሆነና በተደራጀ መልኩ ስለሚሄድ ነው፡፡ ይህ የምልከታ
ዓይነት ለብዙ ጊዜ በአንድ ጉዳይ ውስጥ የድርጊቱ አካል በመሆን እየሰሩ መረጃውን ይዞ
የመውጣት ሥራ ነው፡፡

38
የተግባር ልምምድ

 በከተማችሁ ውስጥ በተለያየ ቦታ ስትንቀሳቀሱ የምትመለከቱትን


ሁኔታ እንዴት ለዜና ወይም ለሬዲዮ ፕሮግራም ማብቃት
ይቻላል?
 ምልከታን ለዜና ፍጆታ መጠቀም ያለው ሙያዊ ፋይዳ
ምንድን ነው?
 በምልከታ የጋዜጠኝነትን ሙያ ማከናወን ያለው ተግዳሮት
ምንድን ነው?

ለ. ቃለ መጠይቅ

የውይይት ጥያቄ
1. ቃለ መጠይቅ ምንድን ነው?
2. ቃለ መጠይቅ በማን ይካሄዳል?
3. ቃለ መጠይቅ እንዴት ይካሄዳል?
4. ጋዜጠኛ የሚያደርገው ቃለ መጠይቅ ምን የተለየ ነገር አለው?

ቃለ መጠይቅ የመረጃ መሰብሰቢያ ሁለተኛው መንገድ ሲሆን እውነት፣ ወቅታዊነት፣


ተገቢ፣ ግልፅና ሳቢ መረጃዎች ይገኙበታል፡፡ ቃለ መጠይቅ የተለያዩ ትርጉሞች
ቢኖሩትም በአብዛኛው ተመሳሳይ የሆኑና ተመጋጋቢ ናቸው፡፡ ከብዙ ትርጉሞች መካከል
አንዱ የሚከተለው ነው፡፡

ቃለ መጠይቅ ማለት ሁለት ሠዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው በአንድ


ብርቱ ጉዳይ በተያያዘ በቃል የሚያደርጉት ልዩ የሆነ የኮሚኒኬሽን ሥራ
ነው፡፡

ከዚህ ትርጓሜ ውስጥ የሚከተለውን መረዳት እንችላለን፡፡

 ቃለ መጠይቅ ቢያንስ በሁለት ሰዎች መካከል የሚደረግ መሆኑን


 ቃለ መጠይቅ በቃል የሚደረግ ኮሚኒኬሽን መሆኑን
 ቃለ መጠይቅ ስለአንድ ብርቱ ጉዳይ የሚደረግ መሆኑን

ስለሆነም ቃለ መጠይቅ በሚደረግበት ሰዓት አንድን ጉዳይ ብቻ ማስተናገድ ተገቢ ነው፡፡


ከዚህም በተጨማሪ ቃለ መጠይቅ በቃል የሚደረግ ነው እንዲ በፅሁፍ መመለስ
የሚፈልጉትን ሰዎች ማስተናገድ ተገቢ አይደለም፡፡ ቃለ መጠይቅ በሚደረግበት ሰዓት

39
ሁለት መሰረታዊ ህጎች አሉት፡፡ አንደኛው በጥንቃቄ መስማት ነው፡፡ ይህም ቃለ
መጠይቅ የሚሰጠው ሰው የሚናገረውን ነገር በትክክል መስማት፣ ላልተብራሩ ነገሮች
ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ ወዘተ መሰረታዊ አሰራሮች ናቸው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ
እንግዳችንን/ መላሽን የማክበር ተግባር ነው፡፡ ይህም ሲባል መላሹ የሚሰጠው መልስ
ምንም ያህል ተገቢና አሳማኝ ባይሆንም እንኳን ሁልጊዜ የቃለ መጠይቅ ተሳታፊውን
ማክበር ይገባል፡፡

ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ከሌሎች ቃለ መጠይቆች በምን ይለያል?

ቃለ መጠይቅ በፖሊስ፣ በሥራ ቀጣሪዎች፣ በአባት፣ በነፍስ አባት፣ በጓደኛ ወዘተ


ሊከናወን ይችላል፡፡ ነገር ግን ለሥራ ውድድር የሚደረገው ቃለ መጠይቅም ሆነ ለፖሊስ
ቃል መስጠት ለጋዜጠኛ ከሚሰጥ ቃለ መጠይቅ የተለየ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ
የጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ የራሱ የሆነ አንድምታዎችና አቀራረቦች ስላሉት ነው፡፡ እነዚህ
ሁኔታዎች ደግሞ ቃለ መጠይቅን የተለየ ያደርጉታል፡፡ እነዚህም አንድምታዎችና
ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ሁልጊዜም ግብን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይኸውም ግቡ


ሁሌም የተሻለ መረጃ ይዞ መገኘት ነው፡፡ ለዚህም ዓላማውን ትኩረት አድርጎ
ይካሄዳል፡፡

2. የቃለ መጠይቁን ተነሳሽነት የሚወስደው ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወይም


ጋዜጠኛው መሆኑ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ የሚያደርግለትን ሰው ሂዶ
የሚጠይቀው እሱ/ሷ እንጂ ና ቃለ መጠይቅ ማድረግ እፈልጋለሁ ተብሎ
አይደለም፡፡

3. ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ሁሌም ባለሙያዎችን ይፈልጋል፡፡ ይህም ማለት ቃለ


መጠይቁን የሚያደርገው ማንም ሳይሆን ጋዜጠኛው መሆኑ ነው፡፡

4. በጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ተሳታፊዎች ማህበራዊ ልኬታቸውና ታማኝነታቸው


ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ በፖሊስ ቃለ መጠይቅ ማንኛውም ዓይነት ሰው

40
ተሳታፊ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ሁሉም ሰው ተሳታፊ
አይደለም ምክንያቱም በማህበረሰቡ ውስጥ የሚያሳየው አንድምታ ከግምት
ውስጥ ይገባል፡፡

5. ጋዜጣው ቃለ መጠይቅ ተጠያቂውን ሲመርጥ ትክክለኛውን ሰው እንጂ


ማንኛውንም አይደለም፡፡ ለምሳሌ ስለአንድ መስሪያ ቤት እንቅስቃሴዎች ለማወቅ
ጋዜጠኛው ሊያናግር የሚችለው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያውን ወይም ከላይ ያለ
ባለስልጣን እንጂ ሠፈርተኛውን ሊሆን አይችልም፡፡

6. የቃለ መጠይቁን ሁኔታ የተስተካከለ ነው፡፡ በጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ጋዜጠኛው


አካባቢውንና የሚሄድበትን ሁኔታ መስሎ መሄድ ይኖርበታል፡፡ አርሶ አደሮች ጋ
ሲሄድ በሱፍ ሸክ ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋ ደግሞ በከናቲራ መሄድ የለበትም፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የሚቀመጥበት ሁኔታ ቃለ መጠይቅ ከሚደረግለት ሰው ጋ
እኩል መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ማይክራፎኑን ለተጠያቂው ሰው አሳልፎ
መስጠት የለበትም፡፡

7. የቃለ መጠይቁ ምስጢራዊነትና ለህዝብ ይፋ የመሆን ጉዳይ የሚወሰነው


በጋዜጠናው ነው፡፡ በአብዛኛው ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ የሚደረገው ለህዝብ ይፋ
እንዲሆኑ የሚፈለጉ መረጃዎችን ይዞ ለመውጣት ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ
የህዝብን ኑሮ አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን በምስጢር ለጋዜጠኛው
ይነገሩና ለጋዜጠኛው በምልከታ እንዲያያቸው ሁኔታዎችን የማመቻቸት
ሥራዎች ይደረጋሉ፡፡ ስለዚህ የጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ብዙ ጊዜ ለህዝብ ይፋ
ሆኖ ነው የሚካሄደው፡፡

8. የቃለ መጠይቁ ፕሮቶኮል አስፈላጊ ነው፡፡ የጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ለአንድ ጉዳይ


ትክክለኛ የሆነ ሰው የሚያገናኝ ሲሆን ሁልጊዜም በትክክል ወቅታዊ የሆነን
ጉዳይ ከባለቤቱ እንዲገኝ ያደርጋል፡፡ ከዚህ ሌላ ሁሌም ባሳቻ ቦታ ሳይሆን
በትክክለኛ ቦታ የሚደረግ ነው፡፡

9. የቃለ መጠይቁ ማህበራዊ ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ መግባት አለበት፡፡ ጋዜጣዊ


ቃለ መጠይቅ ለጋዜጠኛውም ሆነ ለተጠያቂው ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡

41
ምክንያቱም አንድ ሰው ስለአንድ ጉዳይ በቴሌቪዥን፣ በጋዜጣ ወይም በሬዲዮ
ቃለ መጠይቅ አደረገ ማለት የሚያመጣው ማህበራዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡

10. የጋዜጠኛውና የቃለ መጠይቅ ተደራጊው የግንኙነት ርዝመት ወሳኝ ነው፡፡ ቃለ


መጠይቅ በአንዴ በሩጫ ተሂዶ የሚደረግ ሳይን ስለ ቃለ መጠይቅ ተደራጊው
ስለሚጠየቀው ጉዳይ በርካታ መረጃዎችን በመሰብሰብ የሚከናወን ነው፡፡
ስለሆነም በጋዜጠኛውና በቃለ መጠይቅ ተደራጊው መካከል ሊቆይ የሚችል
ግንኙነት ይፈጠራል፡፡

11. ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ቁጥብ ነው፡፡ ይኸውም የሚሰራው በጊዜና በቦታ ተወስኖ
ስለሆነ የሚደረገው ቃለ መጠይቅ በአንድ ጉዳይ ላይ ለሚኖረን የአየር ሰዓት
ወይም በሚኖረው የጋዜጣ ገፅ ስፋት ብቻ የሚወሰን ነው፡፡

12. ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ሁሌም የሚደረግበት ቦታ ዘፈቀደ መሆን የለበትም፡፡


በተገኘው ቦታ ሁሉ አይካሄድም፡፡ ሁሌም ጋዜጠኛውን ምላሽ ሰጪው
በሚደማመጡበት ፀጥታ ባለበት ቦታ ቢሆን ይመረጣል፡፡

የቃለ መጠይቅ ዓይነቶች

ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ከሚደረጉባቸው ጥቅሞች አንፃር በአራት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡-

ሀ. ለመረጃ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ (Informational Interview)


ለ. ለማብራሪያ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ (Interpretative Interview)
ሐ. ስሜትን ለማወቅ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ (Emotional Interview)
መ. የህዝብ ድምፅ (Vox-pop)

እነዚህን የቃለ መጠይቅ ዓይነቶች የሚደረጉባቸው ከሚሰጡት ጥቅም አንፃር ነው፡፡


ይኸውም ካለው ሁኔታና ከተፈጠረው ክስተት አንፃር ሊታዩ ይችለሉ፡፡

ሀ. ለመረጃ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ

ይህ የቃለ መጠይቅ ዓይነት የሚካሄደው አዲስ መረጃን ለማግኘት ነው፡፡ ስለዚህ


በተወሰኑ እውነታዎችና ኩነቶች ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ይህ የቃለ መጠይቅ

42
ዓይነት የምናደርገው በአንድ አካባቢ፣ ድርጅት፣ ቢሮ፣ ወዘተ የተፈጠሩ አዲስ ነገር
መኖሩን ቆፍረን በማውጣት ለአድማጭ ተመልካች የማቅረብ ሥራ ነው፡፡ ስለዚህ
ምንድን ነው እየተካሄደ ያለው? ምንድን ነው የተፈጠረው? የሚሉትን ጥያቄዎች ምላሽ
የማግኘት ዓላማ አለው፡፡

ለ. ለማብራሪያ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ

ስለአንድ ጉዳይ መረጃው ከደረሰን በኋላ የሚከናወን ነገር ቢኖር ስለመረጃው መጠየቅ
ሳይሆን ማብራሪያ፣ አመክንዮ ወይም አስተያየት መጠየቅ ነው፡፡ ስለዚህ ለዚህ ደግሞ
ለማብራሪያ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ ከጉዳዩ ባለቤት ጋር ይደረጋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት
መረጃ አለ እርስዎ ይህ ነገር እንዴት ሊፈጠር እደቻለ ሊያስረዱኝ ይችላሉ? የእርስዎ
አስተያየትስ ምንድን ነው? ለምን ተፈጠረ? እንዴት ተከሰተ? ለዚህ ሁሉ ነገር
ምክንያቱስ ምንድን ነው? ዓይነት ጥያቄዎችን በመጠየቅ ምላሽ ይገኝባቸዋል፡፡

ሐ. ስሜትን ለማወቅ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ

አትሌት ኃይለ ገብረስላሴ አሸንፎ አንደኛ ሲወጣ ጋዜጠኛው ሊጠይቀው የሚችለው


ጥያቄ አንደኛ በመውጣትህ ምን ተሰማህ? ሚለውን እንጂ ምን ሆነህ ነው? እንዴት
አንደኛ ልትወጣ ቻልህ? ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ የሰዎችን ስሜትና ያሉበትን ሁኔታ
የሚታወቅበት የቃለ መጠይቅ ዓይነት ስሜትን ለማወቅ የሚደረግ ነው፡፡ በዋናነት
ዓላማው የሰዎችን ስሜት ማወቅ እንጂ መረጃ ማውጣት ወይም ማብራሪያ መጠየቅ
አይደለም፡፡ ለምሳሌ የማሌዥያ አውሮፕላን መከስከስ ምክንያት የተጎጂ ቤተሰቦችን ቃለ
መጠይቅ የምናደርገው ለመረጃ ወይም ለማብራሪያ አይደለም፡፡ በጉዳቱ ምክንያት
የተሰማቸውን ስሜት ለህዝቡ ለማጋራት ነው፡፡

መ. የህዝብ ድምፅ ለመሰብሰብ የሚደረግ ቃለ መጠይቅ

ይህ የቃለ መጠይቅ ዓይነት የሚከናወነው መንገድ ላይ፣ ገበያ ውስጥ፣ በዓል ቦታ፣
ወዘተ የሚገኙ ሰዎችን አስተያየትና ሃሳብ ለማወቅ ነው፡፡ ለቃለ መጠይቅ የሚጠየቀው
ጥያቄ ደግሞ ተመሳሳይና ቀላል መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣
ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በአሶሳ ከተማ ሲከበር ጋዜጠኛው በዓሉን እንዴት አገኙት?
እያለ በርካታ ሠዎችን ሃሳብ ቢጠይቅ ይህ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡ በህዝብ ድምፅ ሚቀርቡ

43
ጥያቄዎች የባለሙያ ትንታኔ የማይፈልጉና ሁሉን ተሳታፊዎች እኩል ሊያሳትፍ
የሚችሉ ሊሆኑ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለዚህ የብኼሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንና
የኢትዮጵያን ህገ-መንግስት እንዴት ያዩታልቨ ብሎ የባለሙያ ትንታኔ የሚፈልግ ጥያቄ
መጠየቅ ስህተት ነው፡፡

የተግባር መልመጃ

አንድ የመኪና አደጋ ቢደርስና እንደ ጋዜጠኛ ጉዳዩን ልንሰራው ብንሄድ


የምናደርገው የቃለ መጠይቅ ዓይነት ምንድን ነው

 በአደጋው ጊዜ ከነበሩ የዓይን እማኞች ጋር


 ከፖሊስ መኮነኖች ጋር
 ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ጋር
 በአደጋው ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን ካጡ ሰዎች ጋር
በትራፊክ አደጋ መበራከት ምክንያት የህዝቡን አስተያየት ለማወቅ

የቃለ መጠይቅ የቴክኒክ ዓይነቶች

ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ከሚካሄዱባቸው ቴክኒኮችና ዝግጅቶች አንፃር በአምስት


ይከፈላሉ፡፡ እነሱም እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

ሀ. ያለቅድመ ዝግጅት የሚካሄድ ቃለ መጠይቅ (Spot Interview)

ይህ የቃለ መጠይቅ ዓይነት ጋዜጠኛው ሳይዘጋጅበት አንድ ክስተት በተከሰተበት ቦታ


ሂዶ የሚያደርገው ቃለ መጠይቅ ነው፡፡ ምናልባትም ወታደርና ጋዜጠኛ ሁሌም ዝግጁ
መሆን አለባቸው የሚባለው በዚህ ዓይነቱ የጋዜጠኝነት ሥራ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንድ
ሁኔታ እንደተፈጠረ ለምሳሌ የእሳት አደጋ፣ ጎርፍ፣ ግጭት ወዘተ ወዲያውኑ
ማስታወሻውንና መቅርፀ-ድምፁን ወይም ካሜራውን ይዞ ወደ ቦታው በመሄድ ምንም
ቀድሞ ያልተዘጋጀባቸው ጥያቄዎች ጠይቆ የመምጣት ቴክኒክ ነው፡፡

ለ. በቀጥታ የሚሰራጭ ቃለ መጠይቅ (Live Broadcasting Interview)

44
ይህ የቃለ መጠይቅ ዓይነት ጋዜጠኛው ተዘጋጅቶበት የሚሄድ ሲሆን በቀጥታ በሬዲዮና
በቴሌቪዥን የሚጠይቃቸውን ሠዎች ይዞ በመቅረብ ያለምንም የአርትኦት ሥራ
የሚያስተላልፈው የቃለ መጠይቅ ዓይነት ነው፡፡

ሐ. ከዋናው ቃለ መጠይቅ በፊት የሚደረግ ቃለ መጠይቅ (Background Interview)

አንድ ቃለ መጠይቅ ሲደረግ በዋናነት ስለሚደረገው ሰውና ስለጉዳዩ በቂ የሆነ ጥናትና


ዳሰሳ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኛው ከጉዳዩና ቃለ መጠይቅ ከሚደረግለት ሰው
ጋር በተያያዘ ቢያንስ ሰባ በመቶ የሚሆን ነገር አውቆ ነው መገኘት ያለበት፡፡ ስለዚህ
ከዋናው ቃለ መጠይቅ በፊት ሌላ ቃለ መጠይቅ ይከናወናል ማለት ነው፡፡

መ. በስልክ የሚደረግ ቃለ መጠየቅ (Telephone Interview)

ቃለ መጠይቅ በዋናነት ፊት ለፊት መካሄድ ቢኖርበትም የቀጠሮ ሰዓት ለማስያዝም ሆነ


አንዳንድ ያልተሟሉ መረጃዎችን ለመጠየቅ እንዲሁም የመረጃ ምንጩን በአካል
ማግኘት የሚቻል ካልሆነ በስልክ ቃለ መጠይቅ ይደረጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቃለ
መጠይቅ ተደርጎ ከመልስ በኋላ ግልፅ ያልሆኑና ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን
በተመለከተ መጠየቅ ይቻላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከስልክ በተጨማሪ በኢሜል፣ በፋክስ፣
በስካይፒ፣ በፌስቡክ እና በሌሎችም የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ሊካሄድ ይቻላል፡፡

ሠ. በቡድንና በፓናል የሚደረግ ቃለ መጠየቅ (Group & Panel Interview)

ቃለ መጠይቅ በሁለት ሠዎች መካከል የሚካሄድ ቢሆንም አንድ ጋዜጠኛ ከአንድ ቡድን
ጋር የሚያደርገውን የሁለትዮሽ ንግግር ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ አንድ ጋዜጠኛ ከአንድ
የፖለቲካ ፓርቲ የተለያየ ደረጃ አመራሮች ጋር በአንድ ጊዜ ቃለ መጠይቅ ቢያደርግ
ወይም ደግሞ ከአዲስ አበባ የመልሶ ማልማት ተነሺዎች ጋር ቃለ መጠይቅ ቢያደርግ
በቡድንና በፓናል የቃለ መጠይቅ ዓይነት አካሄደ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ዓይነት ቃለ
መጠይቅ በቡድንና በፓናል ሠፋፊ አውዶች ላይ የሚካሄድ የቃለ መጠይቅ ዓይነት
ነው፡፡

45
የስኬታማ ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ሂደቶች

ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ በዘፈቀደ መካሄድ ለበትም፡፡ ምክንያቱም በዘፈቀደ መንገድ


ከተካሄደ ስኬታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ የራሱ የሆነ ቅድም ተከተል ጠብቆ
በሂደት ሊሄድ ይገባዋል፡፡ እነዚህ ቅደም ተከተሎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ዓላማውን ማስቀመጥ፡- ቃለ መጠይቅ ለማድረግ የመጀመሪያው ሥራ ርዕሱን


መወሰን ብቻ ሳሆን በሁኔታዎችና በቃለ መጠይቅ ተደራጊው ላይ ጭምር ነው፡፡
ከዚያም በኋላ የርዕሱንና የቃለ መጠይቅ ተደራጊውን አግባብነት ከወሰኑ የቃለ
መጠይቁን ዓላማ በጠራ መል ለይተን ማስቀመጥ ይጠበቅብናል፡፡

2. ቃለ መጠይቁን ማግኘት፡- ቃለ መጠይቁን ለማድረግ ምንጫችንን ማግኘት በአግባቡ


ልንይዘው ይገባል፡፡ ይህም ማለት ስም ማስተዋወቅ፣ የቃለ መጠይቁን ዓላማ
መናገርና መቼ እንደሚደረግ ለቃለ መጠይቅ ተደራጊው በመንገር ቀጠሮ መያዝን
ያጠቃልላል፡፡

3. ማጥናት፡- ቃለ መጠይቁ ተፈቅዶ ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ ሊደረጉ የሚገባ ነገር ስለ


ምንጮችና ስለጉዳዩ ጥልቅ ዕውቀት እንዲኖር ከተለያዩ ነገሮች ስለጉዳዩ መረጃ
መቃረም ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለቃለ መጠይቁ ሲቀርቡ ምልዑና በራስ መተማመንን
ይጨምራል፡፡

4. ቃለ መጠይቁን ማድረግና መግባባትን መመስረት፡- ቃለ መጠይቁ ሲደረግ


በአድራጊውና በተደራጊው መካከል መልካም የሆነ ግንኙነት ሊኖር ይገባል፡፡ ስለሆነም
ጋዜጠኛው ራሱን ሚዛናዊ አድርጎ መረጃን መሰብሰብ አለበት፡፡ በተጨማሪም ቃለ
መጠይቅ የሚደረገውን ሰው ስሜት ዘና እንዲልና በተረጋጋ መል እንዲናገር
ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፡፡ ስለዚህ መግባባትን በመመስረት (establishing
rapport) የመጀመሪያ ሥራ የሚሆነው ምንጩ ዘና እንዲል ማድረግ ነው፡፡

5. የጥያቄ ስትራቴጂዎችን ማስቀመጥ፡- ብዙ ጊዜ የመጀመሪያ ጥያቄ ሊያበሳጭ


የሚችል ከሆነ የተሳካ ቃለ መጠይቅ ማድረግ አደጋች ነው፡፡ ስለሆነም ጥያቄዎችን
ጊዜ ወስዶ በትክክል ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ መሰደር ይኖርባቸዋል፡፡ ይም
የሚሆነው ከቀላል ወደ ከባድ፣ ከቀላል ወደ ውስብስብ እንዲሁም ከአውንታዊ ወደ

46
አሉታዊ መሆን አለበት፡፡ ቃለ መጠይቁ በዚህ መልኩ ጥያቄዎችን ማቅረብ ከቻለ
አርኪና ስኬታማ ይሆናል ማለት ነው፡፡

6. ቃለ መጠይቁን መዝጋት፡- ቃለ መጠይቁ የመዝጋት ሂደት ላይ እስካሁን በጋዜጠኛው


ጥያቄ ያልተዳሰሱ ጉዳዮች ካሉ ወይ ቀረ የሚሉትና የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ
ዕድል መስጠትና በተጨማሪም ቃለ መጠይቁን ውድ ጊዜያቸውን ሰውተው
በማድረጋቸው ከፍ ያለ ምስጋና በመቸር ይጠናቀቃል ማለት ነው፡፡

የጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ተግዳሮቶች

ጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ የሚካሄደው አልጋ በአልጋ በሆነ መልኩ አይደለም፡፡ ብዙ የሆኑ


እንቅፋቶች ማለፍ ይጠይቃል፡፡ እነዚህ እንቅፋቶች ደግሞ የጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ
ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ ከተግዳሮቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

 ለሁለቱም ተስማሚ የሆነ ጊዜ ማግኘት


 የቃለ መጠይቅ ተደራጊው የመቀረፅያ ያለመቀረፅ ጥያቄ
 የምንጩን ምስጢር ጠብቆ መቆየት
 እያዳመጡ ማስታወሻ መያዝ
 ተከታታይ የሆኑ ጥያቄዎች መብዛት ወዘተ ናቸው፡፡

የቃለ መጠይቅ የጥያቄ አጠያየቅ ቴክኒኮች

ቃለ መጠይቅ በሚደረግበት ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮች

 ተናጋሪውን በዓይናችን መከታተል


 መልሱን በሚገባ ማዳመጥ
 በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ መጠየቅ
 ጥያቄዎች ግልፅ ሆነው ለማቅረብ
 አጫጭር መልስ ለሚሰጡ ሰዎች ብዙ እንዲናገሩ ማበረታታት
 ምንጩን ማመስገን

47
እዚህ ከላይ የተጠቀሱት የቃለ መጠይቅ ቴክኒኮች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል
ደግሞ ቃለ መጠይቅ በሚደረግበት ጊዜ መጥፎ የሆኑ ላማዶች አሉ፡፡ እነዚህም መጥፎ
ልማዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
 የተዘጉ ጥያቄዎች ወይም አዎ ወይም አይደለም የሚል መልስ ያላቸውን ጥያቄዎችን
መጠየቅ
 ጥያቄ ያልሆኑ ዝም ብሎ መናገር ብቻ የሚያደርጉ ሰዎች
 ሁለትና ከዚያ በላይ ጥያቄዎችን በአንድ ጊዜ መጠየቅ
 ዝም ብሎ ራስን ብቻ መነቅነቅ
 የማያልቁ ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ተከትሎ መሄድ

እርስ በርሳችሁ ቃለ መጠይቅ ተደራረጉ፣ በሂደቱ ላይ


ያጋጠመ፣ችሁ ችግር ካለ ለውይይት አቅርቡት፡፡

ሐ. ምርምርና ጥናት

መረጃን በምርምርና ጥናት ለማግኘት የመጀመሪያው ተግባር ምልከታንና ቃለ


መጠይቅን አቀናጅቶ መጠቀም ነው፡፡ ምርምርና ጥናት ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ አለው
ምክንያቱም በአንዱ ያልተገኘውን መረጃ በሌላው ማግኘት ስለሚቻል ነው፡፡ ይህም
ማለት በምልከታ ያልተገኘው በቃለ መጠይቅ ወይም በቃለ መጠይቅ ያገኘውን መረጃ
ቦታ ድረስ በመሄድ ማረጋገጥ የመቻሉን ዕድል ስለሚፈጥር ነው፡፡

2.3 የዜና አፃፃፍ ስልት

ዜና ማለት አንድ አዲስ ክስተት፣ በአድማጮች ጠቃሚ የሆነና በብዙዎች ህይወት


አሉታዊ ይሁን አውንታዊ ለውጥ ወይም ጫና መፍጠር የሚችል ነው፡፡ ስለ የዜና
አፃፃፍ ስልት ስናወራ ዜና ለየትኛው የብዙኅን መገናኛ አውታር የሚል ጥያቄ መነሳቱ
የማይቀር ነው፡፡ የተለያዩ የዜና አፃፃፍ ስልቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የጋዜጣ፡ የሬድዮ፡
የመፅሔት እንዲሁም የኢንተርኔት ዜና አፃፃፍ ስልት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
48
የዜና አፃፃፍ ስልት ልዩነት የሚኖረው የድርጊት ልዩነት መኖሩ ሳይሆን የመገናኛ
ብዙሀን አድማጮችና አንባቢዎች ሁለመናቸው ልዩነት ስለሚኖር ነው፡፡ ይህ ሲባል
የጋዜጣ አንባቢዎችና የሬድዮ ዜና አድማጮች ሁለመናቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለዚ
የተለያዩ አንባቢዎችና አድማጮች በመኖራቸው የተለያየ የዜና አፃፃፍ ስልት ሊኖረን
ግድን ነው፡፡ ለምሳሌ የቴሌቭዥንና የሬድዮ ዜና አድማጮች በባህርያቸው ከጋዜጣ ዜና
አንባቢዎች በጣም ችኩል እንዲሁም ትእግስትና ጊዜ የሌላቸው ናቸው፡፡ ስለዚ የሬድዮና
የቴሌቭዥን ዜናዎች በጣም አጭርና ዝባዝንኪ የማይበዛባቸው ናቸው፡፡ የጋዜጣ ዜናዎች
ደግሞ ትንሽ ረዘም የማለት ባህሪ ይታይባቸዋል፡፡

ዜና የራሱ የሆነ የአፃፃፍ ስልት አለው፡፡ ዜና ስንፅፍና የልበ-ወለድ ወይም መጣጥፍ


ስንፅፍ ልዩነት አለው፡፡ ዜና ስንፅፍ ቀላል ያለ አገላለፅ፡ ቀለል ያሉና ለመረዳት
የማያስቸግሩ አእረፍተ ነገሮች እንጠቀማለን፡፡ በጣም አጫጭር አእርፍተ ለዜና አፃፃፍ
ተመራጭ ናቸው፡፡ ለዜና አፃፃፍ አጫጭር አእርፍተ-ነገሮች ተመራጭ የሚሆንበት
ምክንያት ለማንበብ በጣም ቀላል መሆናቸውና የአድማጭ ቀልብ ለመሳብ እንዲሁም
ለመረዳት የማያስቸግሩ መሆናቸው ነው፡፡

2.3.1 የዜና ቋንቋ

ስለ ዜና ቋንቋ ሲነሳ መቅረት የሌለበት አንዱ ትልቁ ቁምነገር ዜና በጣም አጭር


ያልተንዛዛና (brevity) ግልፅ (clarity) መሆን አለበት፡፡ አጭር ያልተንዛዛና ግልፅ ስንል
ዜና ሲፃፍ አጠር ያለ፣ አላስፈላጊ ቃላት፣ ሐረጎችና ቅጥያዎች ሳያካትት እንዲሁም
ግልፅ ጥያቄ በማያስነሳ መልኩ ሲቀርብ ይህ የዜና አፃፃፍ አንዱ የተመረጠ የዜና ቋንቋ
ያካተተ ነው ማለት ነው፡፡

ሁልጊዜ አጭር የዜና አፃፃፍ ይቅርና ማንኛው ዓይነት አጭር የፅሁፍ አቀራረብ በጣም
ተመራጭ፣ መሳጭ፣ ለመረዳት ቀላል፣ ለአድማጭ የማይሰለች ነው፡፡ ስለ የአጭር
ፅሁፍ ተመራጭነት አስመልክቶ አንዱ የ17ኛው ክ/ዘመን ፈረንሳዊው ብለይዝ ፓስካል
የሂሳብ ፈላስፋ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ ‘I have made this letter longer than usual,
only because I have not had the time to make it shorter.’ በአማርኛው
ሲተረጎም “ይህ የምፅፈው ደብዳቤ ከድሮው የተለየ ረዘም ያለ አድርጌዋለህ፡፡ እንዲህ
ያደረኩበት ምክንያት ለማሳጠር ጊዜ ስለሌለኝ ነው፡፡” ይህ ምሳሌ የሚያሳየን ነገር ቢኖር

49
አጭር ፅሁፍ ወይም አጭር ዜና ለመፃፍ የተካነ ቋንቋ ችሎታና ጊዜ እንደሚያስፈልገን
ነው፡፡ ስለ አጭር ዜና አፃፃፍ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ዜና በአጭሩ ተፃፈ ማለት
ማስተላለፍ ያለበት ፍሬ ጉዳይ (መልዕክት) ሳያስተላልፍ በቁንፅሉ መተው ማለት
አይደለም፡፡ ዜና በአጭር ቋንቋ ተፃፈ ማለት ሙሉ መልእክት ማስተላለፍ በሚችል
መልኩ በተመረጡ ሐረጎችና ቃላት ሳይንዛዛ ሲቀርብ ነው፡፡ ስለዚህ ዜና በአጭር የቋንቋ
አፃፃፍ ለማቅረብ ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ጥበብና ትዕግስት ይጠይቃል፡፡

የዜና አፃፃፍ በአጭር ቋንቋ በጥቂት ቃላት ማለትም ድርጊቶች፣ ድራማዎች፣ ቀለም
እንዲሁም የአንባቢው ፍላጎት ሳይሸራረፍ ለማቅረብ ተደጋጋሚ ልምምድ ያስፈልጋል፡፡
ጥሩ የዜና አፃፃፍ በጥሩ ቋንቋ ሲሆን በተቻለ መጠን በአጭርና ባልተንዛዛ አቀራረብ
ይፃፋል፡፡ እንዲህ በመሆኑም ጥሩ ቋንቋ የተጠቀመ የዜና አፃፃፍ ለመረዳት በጣም ቀላል
ነው፡፡ እንዲህ ሲባል ዜና ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የአረዳድ ደረጃ ልኬት መፃፍ አለበት
ለማለት አይደለም፡፡ ለማለት የተፈለገው ቀጥተኛና ማራኪ መሆን (direct and
snappy) አለበት ለማለት ነው፡፡ ጥሩ የዜና ንግርት በጥሩ ቋንቋ ሲፃፍ (news story)
አንባቢዎች ወይም አድማጮች የዜናው ጭብጥ ለመረዳት ሁለት ጊዜ ወይም ከዛ በላይ
የሚያነቡት የሚጨቃጨቁት ወይም የሚነታረኩበት ዓረፍተ-ነገሮችን መያዝ የለበትም፡፡

በአጭር ቋንቋ ዜና ለመፃፍ ምንም ዓይነት ቴክኒክ ወይም ቀመር (formula) የለም፡፡
ቢሆንም ግን ይህ ለመቻል ብዙ የልምምድ ጊዜ እንደሚያስፈልግ ማናችን አንስተዉም፡፡
ስለዚህ የተመረጠና የተሳካለት ጥሩ የዜና ቋንቋ ለመጠቀም ተሞክሮ ያላቸው የጋዜጣ
ዜናዎች በተከታታይ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ የቃላት ምጣኔ (word economy) ማወቅም
አንዱ መፍትሄ ሊሆን ይችላል፡፡

የዜና አፃፃፍ ቋንቋ የተለየ ሕግና ቀመር ባይኖረውም ዜና ሲፃፍ ከሌላ ዓይነት የቋንቋ
ፅሁፎች መለየት እንዳለበት በማወቅ አንድ ዜና በጥሩ ቋንቋ ስንፅፍ ግምት ውስጥ
መግባት ያለባቸው እና መካተት ያለባቸው ቋንቋ አጠቃቀም ክህሎት ይኖራሉ፡፡ በዚህ
ጉዳይ ቀጥሎ በሚቀርብ የዜና አፃፃፍ ቋንቋ በአጭር መቃኛት ያቻላል፡፡ የአፃፃፍና
የመገናኛ የአሰራር ስምምነት (House Style) እንዳለ ሁኖ፡፡

ጥሩ የዜና የአፃፃፍ ቋንቋ ለመጠቀም የሚከተሉት ጠቃሚ ነጥቦች ግምት ውስጥ


ማስገባት ይበጃል፡፡

50
 አጭር ቃል ወይም የድርጊት ግስ መጠቀም፡፡ (የምንጠቀመው የድርጊት
ግስ ምን እንደተፈፀመ፡ እንደተከናወነ፡ እንደተሰራ የሚገልፅ መሆን
አለበት፡፡ አንድ ድርጊት ለመግለፅ ግስ (action verb) ብቻ አስፈላጊ ነው፡፡
 አላስፈላጊ የድርጊት ግሶች ማስወገድ አለብን፡፡ ቃላት ለአብነት የስም ገላጭ
ወይም የድርጊት ግሶች ባልተፈለገ ቦታና ላልተፈለገ ማብራርያ መግባት
የለባቸውም፡፡ ለምሳሌ ነጭ ቀለም (white color) ነጭ በራሱ ቀለም መሆኑ
ስለ ሚታወቅ ነጭ ራሱ እንደ የስም ገላጭ ሁኖ መግባት የለበትም፡፡
 ምንም ለመግለፅ ወይም ለማመልከት የገቡ ቃላት መወገድ አለባቸው፡፡
ለምሳሌ የቃላት ድግግሞሽ መኖር የለበትም፡፡ ለምሳሌ
ሀ) የኢትዮጵያ ህዝቦች ባለፉት 20 ዓመታት ድህነት
ለማሸነፍ እልህ አስጨራሽ፣ አድካሚና መራራ ትግል
አሳልፏል
ለ) የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለያዩ ቦታዎች በንፁህ ውሃ
እጥረት ምክንያት መንከራተት፣ እንግልት፣ ላልተፈለገ
ወጪ እየተዳረገ መሆኑ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገለፁ

ከላይ በዜና መልክ ከቀረቡ ሁለት ፅሁፎች ተመሳሳይ ትርጉምና ግብር ያላቸው ቃላት
የመደጋገም ዕድል ታይተዋል፡፡ የቃላትና ሐረጎች አላስፈላጊ ድግግሞሽ መኖር
የለበትም፡፡ በ ‘ሀ’ ላይ ያለ የዜና ቋንቋ እልህ አስጨራሽና አድካሚ የሚሉ ሐረጎች
የትርጉምና የግብር ልዩነት የላቸዉም፡፡ በ ‘ለ’ ላይም መንከራተት፡ እንግልት አንድ
አይነት ትርጉም ያላቸው ቃላት ናቸው፡፡ ስለዚ የቃላት ድግግሞሹ ፋይዳ የለውም፡፡

ሞያዊ ቃላት (jargon) መጠቀምህና አለመጠቀምህ ወይም ከቻልክ ላለመጠቀም፡


ከተጠቀምክ ደግሞ ማብራራት እንዳለብህ አትርሳ ወይም አትርሺ፡፡ ለምሳሌ የኢኮኖሚ
ባለሞያ፣ የፖሊስ፣ የጤና ባለሞያ ወይም የግብርና ባለሞያ ሞያዊ ቃላት ስትጠቀም
ለአድማጭ ወይም ለአንባቢ ለመረዳት በሚቀል መልኩ ማብራራት ወይም በሌላ ቀለል
ባለ አገላለፅ መተካት አለበት፡፡

በዕየለቱ ኑሮአችን (ተደጋጋሚ የቋንቋ አጠቃቀማችን) የምናዘወትራቸው ቃላትና ሐረጎች


መጠቀም አለብን፡፡ ይህን ለመመስከርም የዜና አፃፃፍ ቋንቋ ምሁራን የዜና ቋንቋ
አቀራረብ ልክ ትንሽ ልጅ ሀሳቡ እንደሚገልፅ ግልፅ መሆን አለበት ይላሉ፡፡
51
ጠቅለል ባለ መልኩ የዜና ቋንቋ አፃፃፍ ክህሎትና ልምምድ የሚያስፈልገው ሲሆን
በተለያዩ የብዙኅን መገናኛ አውታሮች (ለሬድዮ፣ ለቴሌቭዥን፣ ለጋዜጣ፣ ለመፅሄት
እንዲሁም ለድረ-ገፅ (online news) ሲሆን መሰረታዊ የቋንቋ አጠቃቀምና ይዘት
ልዩነት ሊኖር ይችላል፡፡ ለምሳሌ ለሬድዮ የምንፅፋቸው የዜና ቋንቋ አጠቃቀም ለሬድዮ
በጣም የተመረጡና ገላጭ የሆኑ ቃላትና ሐረጎች መጠቀም ይጠበቅብናል፡፡ ለሬድዮ
አድማጮች ስለሆኑ በዓይናቸው መመልከት የማይችሉት ነገር በግልፅ የሚያሳይ ወይም
የሚያስረዳ ቋንቋ መጠቀም አለብን፡፡

2.3.2 መሪ አንቀፅ (Lead)


የዜና መሪ አንቀፅ አፃፃፍ የአንድ ዜና አወቃቀር የመጀመሪያ አንቀፅ በመጀመርያ ቦታ
(መስመር) ማሰቀመጥ እንደማለት ነው፡፡ መሪ አንቀፅ የራሱ የሆነ ማለት ራሱን የቻለ
አንቀፅ መያዝ ያለበት የዜና መግቢያ ነው፡፡ መሪ አንቀፅ እንደ አንቀፅ የአንባቢ ወይም
አድማጭ ቀልብ የሚስብና ዋና ዋና መረጃ የሚያካትት የዜና አካል ወይም መዋቅር
ነው፡፡ አንድ የዜና ወይም የፅሁፍ ንግርት መግቢያ (beginning) የመሀል (middle) እና
የመዝጊያ (ending) አንቀፆች ካሉት የመግቢያ አንቀፁ በዜና አተረÕጎም መሪ አንቀፅ
ይባላል፡፡

ብዙ ጊዜ ዜና የሚፅፋ ጋዜጠኞች በአንድ ነገር ይስማማሉ፡፡ ስለመሪ አንቀፅ ያላቸው


አረዳድና ጭብጥ፡፡ አንድ በጥሩና በአጥጋቢ መልኩ የተፃፈ መሪ አንቀፅ (lead) ከተቻለ
ሙሉ ወይም ዋና ዋና አምስት መጠይቆች መመለስ አለበት፡፡ እነኝህ አምስት
መጠይቆች ወይም በእንግሊዘኛው (5 WH Questions) የሚባሉ ናቸው፡፡ አምስቱ
መጠይቆች በአማርኛ ትርጓሜያቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1.ማን (who)
2. ምን (what)
3. መቼ (when)
4.የት (where)
5. ለምን (why)
6.እንዴት (how)

52
የነዚህ አምስት መጠይቆች አላማ በዜና መሪ አንቀፅ (lead) የእያንዳንዱ መጠይቅ
መልስ ተካትቶ እንዲቀርብና የመጠይቆች መልስ ተመልሶ እንዲፃፉ ነው፡፡ እንዲህ ሲባል
የግድ በማንም ዜና መሪ አንቀፅ የሚቀርብበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ እንደ ግዴታ
ሳይሆን እንደየ ሁኔታው ነው፡፡ አንድ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ግን በዜና ትርጓሜ
መሰረት ከአምስቱ መጠይቆች መቅረት የሌለበትና በርዕስ ዜና በመጀመርያ መመለስ
ያለባቸው መጠይቆች ማን (who) እና ምን (what) ናቸው፡፡ የዜና አንድምታዊ ትርጉም
ምን ተሰራ፣ ተከናወነ፣ ተደረገ እና ማን ሰራው ወይም እነ ማን ሰሩት ስለሆነ ማን
(who) እና ምን (what) የግድ መመለስ ያለባቸው ሁለት ዋና መጠይቆች ናቸው፡፡

2.3.3 የአርስተ ዜና አፃፃፍ /Headline Writing Techniques/

የአርስተ ዜና የዜና መግቢያ በመባል ይታወቃል፡፡ የአድማጩን ቀልብ በመሳብ ወደ


ዜናው እንዲያተኩር የሚያደርገው ማለት ነው፡፡ የአርስተ ዜና ማለት በቀላል አማርኛ
የዜና ዝርዝር ከመነበቡ በፊት ከዜና በፊት የሚቀርብ አንድ የዕለቱን ዓብይ ጉዳይ የያዘ
ዓረፍተ ነገር ነው፡፡

አርዕስተ ዜና ጠቅላላ የዜናው ንግርት እጥር ምጥን ባለ ዓረፍተ ነገር የሚያጠቃልል


ነጋሪ ጭብጥ ነው፡፡ በጋዜጠኝነት የቋንቋ አጠቃቀም ሳይንስ አዕርስተ ዜና ሲፃፍ
የተግባርን ክንዋኔ የሚያሳይ የገቢር ግስ (Active verb) ሊኖረው ይገባል፡፡ እንዲህ
የሚሆንበት ምክንያት ለአድማጭ ይሁን ለአንባቢ በቀላሉ ለመረዳት እንድያስችል ነው፡፡
አርእስተ ዜና የአንድ ዜና ጠቅላላ ንግርት አንባቢው ወይም አድማጩን ዜናውን
የመነበብ ወይም ያለመነበብ ወይም የመደመጥ ያለመደመጥ ዕድል የሚያስወስን ነው፡፡
በጥንቃቄና በጥሩ የቋንቋ አፃፃፍ አርእስተ ዜና የአድማጭ ወይም የአንባቢ ቀልብ
የመማረክ አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን የደከመና የተንዛዛ አርእስተ ዜና ግን አድማጮች
ወይም አንባቢዎች ያሳስታል፤ ያደናግራል እንዲሁም ሊቆረቁራቸው ሁሉ ይችላል፡፡

አንድ በጥሩ የዜና ቋንቋ አፃፃፍ የቀረበ አርእስተ ዜና / Headline/ በዜናው ንግርት/
Story/ ከሚሰጣቸው ጥቅሞችና አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. በቀኑ ምን ምን እንደተሰራ ያበስራል ስለጥቅሙም ያወሳል፡፡
2. ለአንባቢው ወይም ለአድማጩን በጣም ጠቃሚ ከሆኑ እውነታዎች እንዲመሰጥ
ያደርጋል፡፡

53
3. ለዜና ንግርት የአንድ ነገር ድርጊት አብሳሪነት በመሆን ዜና ተፈላጊ እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡
የአርስተ ዜና ለመፃፍ ክህሎትና ተመስጦ ያስፈልጋል፡፡ የምንፅፈው የአርስተ ዜና ስለ
ዜናው ጭብጥ ወይ ንግርት ፍሬ ነገር የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ The headline that
we write must give the essence of the story. ስለዚህ የዜና አርእስት ሲፃፍ
የዜና ንግርት /news story/ ዋና አንኳር ሀሳብ የሚያንፀባርቅ መሆን አለበት፡፡

2.3.4 የዜና መዋቅር

ሰዎች አከርካሪ እንዳላቸው ሁሉ ዜናዎችም መዋቅር አላቸው ሊኖራቸውም ይገባል፡፡


አንድ ዜና ያለመዋቅር ምንም መጨበጫ የሌለው የፍሬ ነገር ዝብርቅርቅ ይሆናል፡፡
ዜናዎች ተረጅነትና ትርጉም እንዲኖራቸው መዋቅር አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉም
በአንድ አይነት መንገድ መዋቅር የለባቸውም፡፡ ጥሩ ፀሃፊዎች ስለሚናገሩት ዜና ወይም
ታሪክ በጣም ተስማሚ የሆነውን ቅርፅ ይመርጣሉ፡፡ ለሬዲዮ ጋዜጠኝነት የተገለበጠ
ፒራሚድ የዜና መዋቅር ተመራጭ ያደርገዋል፡፡

የተገለበጠ ፒራሚድ

አብዛኛዎቹ ዜናዎች የዜናው ዋና ጉዳይ በሆነው ነገርና ከዛሬ መቶ ዓመት በፊት ጀምሮ
በሚሰራበት አወቃቀር ይጀምራሉ፡፡ የተገለበጠው ፒራሚድ የሚባለው ይህ አወቃቀር
በጣም አስፈላጊውን መረጃ ከላይ ያስቀምጣል፡፡ እንዲሁም እንደ አወቃቀር በጣም
አስፈላጊውን መረጃ ከላይ ያስቀምጣል፡፡ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነታቸው ቅደም
ተከተል ከላይ ወደታች ይወርዳል፡፡ የዚህ ዓይነቱ የዜና ቅርፅ ወቅታዊነት አስፈላጊ
በሚሆንበት ጊዜ ወይም ሰበር ዜናን ሲዘግቡ ጠቃሚ ነው፡፡ የአንድ ክስተት ሂደት
ለመዘገብ የመጀመሪያው ሰው ከሆንክ ለታዳሚዎቹ ምን እንደተከናወነ በዜናው
የመጀመሪያ የበላይ ጫፍ ላይ ታስታውቃቸዋለህ፡፡ ለምሳሌ ስለ ከባድ አውሎ ነፋስ
የሚሰራ ዘገባ በሞቱት ሰዎች ቁጥርና ክፉኛ ጉዳት የደረሰበትን ስፍራ በመግለፅ
ይጀምራል፡፡ የዚህን ዓይነት የዜና መዋቅር የማይቀበሉ ፀሐፊዎች “መግቢያውን ቀበሩ”

54
ተብለው ይወቀሳሉ፡፡ አቀራረባቸው ለታዳሚዎቻቸው የዜናውን ጠቀሜታ ለማግኘት
አስቸጋሪ ስለሚያደርጉት፡፡

በተገለበጠ ፒራሚድ መዋቅር ውስጥ መግቢያው ላይ ያለውን መረጃ በመግቢያው ስር


ያሉት ነጥቦች ደረጃ በደረጃ ያዳብሩታል፡፡

የአውሎ ነፋስ ዘገባን በሚመለከት ፀሐፊው መጥፎ ጥፋት የደረሰበትን ስፍራ ሊገልፅ
ይችላል፡፡ ከዛ ከተረፉት ሰዎች ወይንም ከአደጋው መከላከል ሰራተኞች መካከል የአንዱን
ጥቅስን ማስፈር ይችላል፡፡ ደጋፊ አንቀፆች ርዕሱን ሊያብራሩ ይችላሉ፤ ዝርዝር ነገሮችን
በመሙላትና ስለማዕበሉ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት፡፡ የማዕበሉ ዜና ስለ ዓለም አቀፍ
ዕርዳታ ጥረትና ለተረፉት ሰዎች ስለሚያስፈልግ የቅርብና የረጅም ጊዜ የዕርዳታ ፍላጎት
ሀሳብ ሊጨምር ይችላል፡፡ የተገለበጠ ፒራሚድ መዋቅር ዋናው ጥቅም የዜናው አዘጋጅ
ጠቃሚ ዜና ሳያጓድል ከፒራሚዱ በታች በኩል ያሉትን መረጃዎች በመቀስ መቁረጥ
መቻሉ ነው፡፡

ውድ የስልጠናው ተከታታዮች! ከዚህ ቀጥሎ አንድ ናሙና ዜና በማቅረብ ክፍሎቹንና


አጻፃፋቸውን በዝርዝር እናያለን፡፡

55
የአፍሪካ ህብረት Copy slug/ የዜና
መግለጫ ወይም መለያ
ጥር 22፣ 2009
(ኤፍ.ቢ.ሲ)

የቻዱ ሙሳ ፋቂ መሃማት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ። መሪ አንቀፅ

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ

ሙሳ ፋቂ መሃማት ህብረቱን ለቀጣይ አራት አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራት

የተመረጡት።

ሙሳ መሃማት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2003 እስከ 2005 የቻድ ጠቅላይ

ሚኒስትር ሆነው ችለዋል፡፡

ፖለቲካኛው ሙሳ ከ2007 እስከ 2008 ባለው ጊዜም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣

የማህበራዊና የባህል ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ሰርተዋል።

በዚያው ዓመት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ግለ

ታሪካቸው ያሳያል።

ሙሳ የአገሪቷን ሁለት ተቋማት በሚኒስትርነት የመሩና የቻድ የስኳር ኩባኒያንም

በዋና ዳይሬክተርነት መምራታቸው ታውቋል።

የፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ካቢኔ ዳይሬክተርና የ2001 ምርጫ ዘመቻ ኃላፊ

ሆነውም አገልግለዋል።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚና መሐመድ፣ ቦትስዋናዊቷ ፔሎኖሚ

ቬንሰን-ሞታይ፣የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አጋፒቶ ምባ ሞኩይ

እና ሴኔጋላዊው ዶክተር አብዱላዪ ባዚልይ ከሙሳ ፋቂ መሀመት ጋር ህብረቱን

በሊቀመንበርነት ለመምራት ተፎካክረዋል።

__________________________0__________________________

56
2.3.5 የሬዲዮ የዜና አፃጻፍ ፎርማቶች

የሬዲዮ ዜና ሲጻፍ ከሌሎች የብዙሃን መገናኛ ተቋማት በተለየ መልኩ የራሱን


ፎርማቶች ይዞ ይቀርባል፡፡ እነዚህ የሬዲዮ ዜና ፎርማቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡

1. Reader: ይህ የዜና ፎርማት አንድን የሬዲዮ ዜና ከመጀመሪያው እስከ


መጨረሻው በአንድ ሰው ያውም በዜና አቅራቢው ብቻ የሚነበብበት የዜና
ፎርማት ዓይነት ነው፡፡ ይህ ፎርማት ለአጫጭር ዜናዎች ያገለግላል፡፡

ተመድ ጥር 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ተመድ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቀ፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች

የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የመንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ

በተከሰተው ድርቅና ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ትናንት ማምሻውን ውይይት አካሂደዋል።

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ በተለይም ባለፈው ዓመት ከዓመታት በኋላ ያጋጠማትን ድርቅ በራሷ አቅም

በመመከት በሰውና በእንሰሳት ላይ ይደርስ የነበረውን ጉዳት መከላከል መቻሏ የሚወደስ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የጎረቤት አገራት ስደተኞችን ተቀብላ ማስተናገዷ የመንግሥታቱ ድርጅቱ በአዎንታ

እንደሚያየው ነው የተናገሩት።

በተያዘው ዓመት በኦሮሚያ፣ በደቡብና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም መንግሥት እያደረገ ካለው ጥረት

ባሻገር የዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ልማትን ማምጣት

የሚያስችሉ የልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፉም ነው ዋና ጸሃፊው የጠቆሙት።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው መንግሥት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በሰውና በእንሥሳት

ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አገሪቷ ባለፈው ዓመት የተከሰተውን ደርቅ ለመቋቋም ከፍተኛ በጀት መድባ ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ከድርቅ አደጋ

መታደግ እንደቻለች አስታውሰዋል።

57
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ይህን ለመቋቋም የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚን ለመገንባት እየሰራች መሆኑን ነው ያብራሩት።

በአሁን ወቅት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም መንግሥት 47 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መድቦ

የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን ድርቁን ለመከላከል ግን 948 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።

ሀገሪቱ ድርቅን ጨምሮ ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ

እንደሚያስፈልጋትም አስታውቀዋል።

በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ስቴቨን ኦሪን የተመራ ቡድን በሶማሌ ክልል የሦስት ቀናት ጉብኝት በማድረግ ድርቁ

ያስከተለውን ጉዳት በቅርበት ለመታዘብ ችሏል።

በአካባቢው መንግሥትና ሰብዓዊ ድርጅቶች ለድርቅ ተጎጂዎች ውኃ፣ ምግብና መድኃኒት እንዲሁም ለእንሥሳት መኖ

እየቀረበ መሆኑን ቡድኑ አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ህዘብና መንግሥት ድርቁን ለመቋቋም በቁርጠኝነት እየሰሩ ቢሆንም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከ 5 ነጥብ 6

ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከአደጋው ለመታደግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ሊያደርህ እንደሚገባ ስቴቨን ኦሪን ተናግረዋል።

መንግሥት በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች የከፋ ጉዳት እንዳይደርስባቸው የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከወዲሁ

እያደረገ መሆኑን ብሄራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

2. Voicer: የዕለቱ የዜና አቅራቢ የዜናውን መሪ አንቀፅ ካቀረበ በኋላ ዝርዝር


ሪፖርሩ ደግሞ በሌላ ሪፖርተር የሚቀርብበት የዜና ፎርማት ነው፡፡ በዚህ
ፎርማት ዜናውን ያጠናከረው ጋዜጠኛና የዕለቱ ዜና አንባቢ ድምጽ
ይስተናገድበታል፡፡

ተመድ ጥር 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ

እንዲያደርጉ ጠየቀ፡፡ የተመድ ከፍተኛ ባለስልጣናትም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮነን

ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

ለዝርዝሩ አበበ ከበደ

58
ተመድ ጥር 22፣ 2009 (አበበ ከበደ)

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች

የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የመንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ

በተከሰተው ድርቅና ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ትናንት ማምሻውን ውይይት አካሂደዋል።

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ በተለይም ባለፈው ዓመት ከዓመታት በኋላ ያጋጠማትን ድርቅ በራሷ

አቅም በመመከት በሰውና በእንሰሳት ላይ ይደርስ የነበረውን ጉዳት መከላከል መቻሏ የሚወደስ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የጎረቤት አገራት ስደተኞችን ተቀብላ ማስተናገዷ የመንግሥታቱ ድርጅቱ በአዎንታ

እንደሚያየው ነው የተናገሩት።

በተያዘው ዓመት በኦሮሚያ፣ በደቡብና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም መንግሥት እያደረገ ካለው

ጥረት ባሻገር የዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ልማትን ማምጣት

የሚያስችሉ የልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፉም ነው ዋና ጸሃፊው የጠቆሙት።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው መንግሥት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በሰውና

በእንሥሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አገሪቷ ባለፈው ዓመት የተከሰተውን ደርቅ ለመቋቋም ከፍተኛ በጀት መድባ ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ከድርቅ አደጋ

መታደግ እንደቻለች አስታውሰዋል።

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የተናገሩት ምክትል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ይህን ለመቋቋም የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚን ለመገንባት እየሰራች መሆኑን ነው

ያብራሩት።

በአሁን ወቅት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም መንግሥት 47 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር

መድቦ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን ድርቁን ለመከላከል ግን 948 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግም

አብራርተዋል።

59
ሀገሪቱ ድርቅን ጨምሮ ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ

እንደሚያስፈልጋትም አስታውቀዋል።

በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ስቴቨን ኦሪን የተመራ ቡድን በሶማሌ ክልል የሦስት ቀናት ጉብኝት በማድረግ

ድርቁ ያስከተለውን ጉዳት በቅርበት ለመታዘብ ችሏል።

በአካባቢው መንግሥትና ሰብዓዊ ድርጅቶች ለድርቅ ተጎጂዎች ውኃ፣ ምግብና መድኃኒት እንዲሁም ለእንሥሳት መኖ

እየቀረበ መሆኑን ቡድኑ አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ህዘብና መንግሥት ድርቁን ለመቋቋም በቁርጠኝነት እየሰሩ ቢሆንም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከ 5 ነጥብ 6

ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከአደጋው ለመታደግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ሊያደርህ እንደሚገባ ስቴቨን ኦሪን

ተናግረዋል።

መንግሥት በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች የከፋ ጉዳት እንዳይደርስባቸው የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ

ከወዲሁ እያደረገ መሆኑን ብሄራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

3. Actuality: በዚህ የሬዲዮ ዜና ፎርማት ዜና የሚያነበው አንባቢና የመረጃ


ምንጭ ድምፅ የሚካተትበት ፎርማት ነው፡፡ የዕለቱ የዜና አንባቢ በዋናነት
ዜናውን እየመራ የመረጃ ምንጩን በየመሃሉ ያስተናግዳል፡፡

ኬንያ ፣
ጥር 22/ 2009
ቢቢሲ
ኬንያውያኑ ጥንዶች ጋብቻቸውን ለመፈፀም ለሚካሄደው የሰርግ ስነስርዓት አንድ የአሜሪካ ዶላርን ብቻ

መመደባቸው በርካቶችን አነጋግሯል።

ዊልሰን እና አን ሙቱራ በፈረንጆች 2016 ሊጋቡ ቀን ቆርጠው ሁለት ጊዜ አራዝመውታል፤ ምክንያቱም እስከ

300 ዶላር የሚጠይቅ ክፍያን መሸፈን ባለመቻላቸው ነበር።

በመሆኑም ዊልሰን እና አን ሙቱራ የሰርጋቸውን እለት በዚህኛው ዓመት ቀለል ባለ መልኩ ለማድረግ

ወስነዋል።

ሙሽሪት አን በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ አስመልክታ ገንዘብና ጋብቻ መተሳሰር የለባቸውም ብላለች፡፡

60
የአና ድምፅ (10 ሴኮ.)
"ጋብቻን በገንዘብ ሳይሆን በእርስ በእርስ መዋደድ እና መተሳሰብ መመስረት ልዩ ፀጋ ነው" ፡፡
ይህን ያደረጉት ጥንዶቹ በአንድ ዶላር የተከናወነው የሰርግ ስነስርዓት በሚል በማህበራዊ ድረገጾች የሰርክ

ልብሳቸውን ለብሰው በለቀቁት የሰርግ ፎቶግራፍ በርካቶችን አነጋግረዋል፡፡

የጋብቻ ውላቸውም በመንግስታዊ ተቋም ሳይመዘገብ በቤተክርስቲያን ብቻ ተፈጽሟል፤ ምክንያቱም የጋብቻ

ውሉን ለሚመለከተው የመንግስት ተቋም ለማሳወቅ ክፍያን ስለሚጠይቅ፥ እነሱም ወጪውን መሸፈን

ስለማይችሉ ነው፡፡

እንዲህ ያለው የ27 ዓመቱ የዊልሰን እና የ24 ዓመቷ የአን የፍቅር ታሪክ የበርካታ ማህበራዊ የትስስር ገጽ

ተጠቃሚዎችን ቀልብ ስቧል፡፡

ከሶስት ዓመት የፍቅር ግንኙነት በኋላ በገንዘብ ምክንያት ሰርጋቸውን በወጉ ያላደረጉት ሁለቱ ጥንዶች፥

የፈጣሪን ህግ ቅዱሱን ጋብቻን አክብረው ለመኖር ቃል ተገባብተዋል፡፡

ሰርጋቸውም ድግስ ሳይደገስ፣ ኬክ ሳይቆረስ፣ ያለምንም የሰርግ ጌጣጌጥ እና አበባ፣ በናይሮቢ ተደርጓል፡፡

አለባበሳቸውም የተለመደ ጂንስ ሱሪ፣ ቲሸርት እና መደበኛ ጫማ ሲሆን፥ ሰርግ የሚያስመስለው ነገር ቢኖር

ከብረት የተሰሩት ሁለት ክብ ቀለበቶች ብቻ ናቸው፡፡

በቤተክርስቲያን ውስጥ ሰርጉ ሊፈጸም በነበረበት ወቅትም ዊልሰን ሁለቱን በአነስተኛ ዋጋ የሚሸጡ የብረት

ቀለበቶች ለመግዛት ሮጦ ሲወጣ በስነስርዓቱ ላይ የነበሩትን ሁሉ አስደምሟል፡፡

በማህበራዊ ድረገጽ የተለቀቀውን የሁለቱን ጥንዶች ነገረ ጋብቻ የተመለከቱ እና ፀጋው ያላቸው ሁሉ

ስጦታቸውን እየላኩላቸው ሲሆን፥ አንድ የጉዞ ድርጅትም የአምስት ቀን የጫጉላ ሽርሽር እንዲያደርጉ ሙሉ

ወጪያቸውን ለመሸፈን ቃል ገብቷል፡፡

4. Voice Wrape: ይህ የሬዲዮ ዜና ፎርማት ዓይነት ደግሞ የዕለቱ ተራኛ


ዜና አንባቢ እና የሪፖርተሩ ዝርዝር ከመረጃ ምንጩ ጋር ተዋህዶ
ይቀርባል፡፡ ስለዚህ በዜናው ውስጥ ሶስትና ከዚያ በላይ ድምፆች
ይካተቱበታል፡፡

61
ኬንያ ፣
ጥር 22/ 2009
ቢቢሲ
ኬንያውያኑ ጥንዶች ጋብቻቸውን ለመፈፀም ለሚካሄደው የሰርግ ስነስርዓት አንድ የአሜሪካ ዶላርን ብቻ

መመደባቸው በርካቶችን አነጋግሯል።

አስቴር ተሾመ የቢቢሲን ዘገባ ዝርዝሩን አዘጋጅታዋለች

ኬንያ ፣
ጥር 22/ 2009
አስቴር ተሾመ (ቢቢሲ)
ዊልሰን እና አን ሙቱራ በፈረንጆች 2016 ሊጋቡ ቀን ቆርጠው ሁለት ጊዜ አራዝመውታል፤ ምክንያቱም እስከ

300 ዶላር የሚጠይቅ ክፍያን መሸፈን ባለመቻላቸው ነበር።

በመሆኑም ዊልሰን እና አን ሙቱራ የሰርጋቸውን እለት በዚህኛው ዓመት ቀለል ባለ መልኩ ለማድረግ

ወስነዋል።

ሙሽሪት አን በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ አስመልክታ ገንዘብና ጋብቻ መተሳሰር የለባቸውም ብላለች፡፡

የአና ድምፅ (10 ሴኮ.)


"ጋብቻን በገንዘብ ሳይሆን በእርስ በእርስ መዋደድ እና መተሳሰብ መመስረት ልዩ ፀጋ ነው"፡፡
ይህን ያደረጉት ጥንዶቹ በአንድ ዶላር የተከናወነው የሰርግ ስነስርዓት በሚል በማህበራዊ ድረገጾች የሰርክ

ልብሳቸውን ለብሰው በለቀቁት የሰርግ ፎቶግራፍ በርካቶችን አነጋግረዋል፡፡

የጋብቻ ውላቸውም በመንግስታዊ ተቋም ሳይመዘገብ በቤተክርስቲያን ብቻ ተፈጽሟል፤ ምክንያቱም የጋብቻ

ውሉን ለሚመለከተው የመንግስት ተቋም ለማሳወቅ ክፍያን ስለሚጠይቅ፥ እነሱም ወጪውን መሸፈን

ስለማይችሉ ነው፡፡

እንዲህ ያለው የ27 ዓመቱ የዊልሰን እና የ24 ዓመቷ የአን የፍቅር ታሪክ የበርካታ ማህበራዊ የትስስር ገጽ

ተጠቃሚዎችን ቀልብ ስቧል፡፡

62
ከሶስት ዓመት የፍቅር ግንኙነት በኋላ በገንዘብ ምክንያት ሰርጋቸውን በወጉ ያላደረጉት ሁለቱ ጥንዶች፥

የፈጣሪን ህግ ቅዱሱን ጋብቻን አክብረው ለመኖር ቃል ተገባብተዋል፡፡

ሰርጋቸውም ድግስ ሳይደገስ፣ ኬክ ሳይቆረስ፣ ያለምንም የሰርግ ጌጣጌጥ እና አበባ፣ በናይሮቢ ተደርጓል፡፡

አለባበሳቸውም የተለመደ ጂንስ ሱሪ፣ ቲሸርት እና መደበኛ ጫማ ሲሆን፥ ሰርግ የሚያስመስለው ነገር ቢኖር

ከብረት የተሰሩት ሁለት ክብ ቀለበቶች ብቻ ናቸው፡፡

በቤተክርስቲያን ውስጥ ሰርጉ ሊፈጸም በነበረበት ወቅትም ዊልሰን ሁለቱን በአነስተኛ ዋጋ የሚሸጡ የብረት

ቀለበቶች ለመግዛት ሮጦ ሲወጣ በስነስርዓቱ ላይ የነበሩትን ሁሉ አስደምሟል፡፡

በማህበራዊ ድረገጽ የተለቀቀውን የሁለቱን ጥንዶች ነገረ ጋብቻ የተመለከቱ እና ፀጋው ያላቸው ሁሉ

ስጦታቸውን እየላኩላቸው ሲሆን፥ አንድ የጉዞ ድርጅትም የአምስት ቀን የጫጉላ ሽርሽር እንዲያደርጉ ሙሉ

ወጪያቸውን ለመሸፈን ቃል ገብቷል፡፡

--------------------0----------

5. Live: የሬዲዮ ዜና ከስፍራው በስልክ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል፡፡


በዚህ ጊዜ መስክ ላይ ያለው ሪፖርተር ስቱዲዮ ጋር ካለው የዕለቱ የዜና
አስተናጋጅ ጋር ይገናኛሉ፡፡ የቀጥታ ሥርጭት ብዙውን ጊዜ ስክርፕት
አይጻፍለትም፡፡ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ የሚያደርጉት ነገር በሚያቀርቡት
ጉዳይ ላይ ዝግጅት በማድረግ ማስታወሻ መያዝ ነው፡፡

2.3.5 የሬዲዮ ዜና አፃጻፍ ደንቦች

የሬዲዮ ዜና በሚጻፍበት ጊዜ ልንከተላቸው የሚገቡ ደንቦች

 በዜናው ራስጌ ዜናው የያዘውን ጉዳይ፣ የተሰራበትን ቀንና የሰራውን ሰው


ስም ማስቀመጥ (copy Slug)
 ሁሌም በወረቀቱ የአንድ ገጽ ብቻ መፃፍ
 በሚፃፍበት ጊዜ ከላይ፣ ከቀኝና ከታች አንድ ኢንች በግራ በኩል ደግሞ
አንድ ነጥብ አምስት ኢንች ህዳግ መተው

63
 የተወሳሰቡ ቁጥሮችን በአሃዝና በማጠጋጋት ግልጽ ማድረግ
 በአንድ ገፅ የማያልቁ ዜናዎችን ምልክት ማስቀመጥ
 ዜናው ማለቁን የሚገልጽ ምልክት ማስቀመጥ
 በመስመሮች መካከል ያለውን ቦታ ለዓይን ምቹ እንዲሆን 2 ማድረግ
 ዜናዎችን በተገቢው ቅደም ተከተል ማስቀመጥ

ማጠቃለያ

ዜና በሬዲዮ ከሚሰሩ የጋዜጠኝነት ዘውጎች አንዱ ሲሆን በዋናነት አንድ ክስተት


በተከሰተበት ፍጥነት በመረጃዎች ተሟልቶ የሚቀርብ ሲሆን በዋናነት ደግሞ
የጋዜጠኝነትን መሰረታዊ የሙያ ብቃቶች የሚለካ ሥራ ነው፡፡ ዜናን በምናዘጋጅበት ጊዜ
መረጃዎችን በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በጥናትና ምርምር እናገኛለን፡፡ዜና በቋንቋ
አጠቃቀሙም ሆነ በአወቃቀሩ የተለየ ነው፡፡ ዜናዎች በተለያየ ፎርማት ይዘጋጃሉ፡፡
እነዚህን ፎርማቶች ለመምረጥም የጉዳዩ ክብደትና ቅለት እንዲሁም የዜናው ዝግጅት
ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ በየትኛውም ፎርማት ቢጻፍም ለአድማጭ ምቹ እንዲሆኑ
እንደሚፈለገው ሁሉ ለአንባቢውም እንዲመቹ የራሱ የሆነ የአጻፃፍ ደንብ ሊኖረው
ይገባል፡፡

64
3. የሬዲዮ ፕሮግራም

3.1 የሬዲዮ ፕሮግራም ማለት ምን ማለት ነው?

ሬዲዮ ፕሮግራም ሲባል አንድ ዓየር ላይ የሚውል ዝግጅት ሙሉ ግብዓት ጥንክር


ማለት ነው፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራም በዋናነት ሁሉንም አስፈላጊ የሚባሉትን የድምፅ
ግብዓቶች መያዝ ይኖርበታል፡፡ ሬዲዮ ፕሮግራሞች አንድ ጋዜጠኛ ሊሰራው ባሰበው
አርዕስት ላይ በቂ ምርምርና ዝግጅት ካደረገ በኋላ ማህበረሰቡን ያሳውቃል፣ ያስተምራል
ወይም ያዝናናል ብሎ በሚያስበው መልኩ የሚያዘጋጀው የድምፅ ሙሉ ፓኬጅ ነው፡፡
በዚህ ፓኬጅ ውስጥ ስክርፕቱና አስፈላጊ የሆኑ የድምፅ ግብዓቶች ሁሉ ይሟላሉ፡፡

3.2 የሬዲዮ ፕሮግራም ዓይነቶች

የብዙኀን መገናኛ ፕሮግራሞች በአጠቃላይ እንዲሁም የሬዲዮ ፕሮግራም በተለይ


ሲዘጋጁ የተለያዩ ሆነው ነው፡፡ በዋናነት ከዓላማቸውና ከጥቅማቸው አንፃር ሬዲዮ
ፕሮግራም በሶስት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-

1. የማሳወቂያ ፕሮግራም
2. የማስተማሪያ ፕሮግራም እና
3. የመዝናኛ ፕሮግራም ናቸው፡፡

አንድ ፕሮግራም በዋናነት የማሳወቂያ፣ የማስተማርያ ወይም የመዝናኛ ፕሮግራም


ተብሎ ሊሰራ ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ የፕሮግራም ክፍፍል አንድን ፕሮግራ ከታሰበለት
ውጭ ተጨማሪ ጥቅም ሊኖረው ስለሚችል አንድን ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ ይህ ብቻ
ነው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ አንድ የሬዲዮ ድራማ ሲዘጋጅ በዋናነት ዓላማው
ማዝናናት ነው ተብሎ ቢቀመጥም ከድራማው በርካታ ቁምነገሮችን የሚማሩበትና
የሚታወቁበት ፕሮግራም ጭምር ስለሚሆን ነው፡፡

3.2.1 የማስተማርያ ፕሮግራም (Educational Programmes)

ትምህርታዊ ፕረግራሞች በሬዲዮ ድራማ ውስጥ መደበኛ ወይም መደበኛ ባልሆነ


መልኩ ይዘጋጃሉ፡፡ አንድን የሬዲዮ ፕሮግራም ትምህርታዊ ፕሮግራም ነው የሚያሰኙት
የሚከተሉት እልባቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ከተሰራ ነው፡፡ የሬዲዮን ፕሮግራም
ትምህርታዊ ነው የሚያሰኙት፡-
65
 አድማጮች ላይ ግንዛቤ ሲፈጥር፣
 የዕውቀት ሽግግር ሲያመጣ፣
 በአድማጮች ላይ የባህርይ ለውጥ ሲያመጣ ወይም እንዲያመጡ ምቹ
ሁኔታዎችን ሲፈጥር፣
 ክህሎትን ሲያዳብር፣
 አድማጮችን በማሳተፍ አንድ ነገር እንዲያደርጉ ሲያበረታታ፣
 በአድማጮች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ በመፍጠር አንድ ነገር
እንዲያደርጉ ሲያሳምን፣
 ለአድማጮች አቅጣጫ ሲሰጥ/ ሲያሳይ፣
 የማሰብና የመፍጠር አቅምን ሲቀሰቅስና እንዲያደርግ ሲረዳና የመሳሰሉት
ናቸው፡፡

3.2.2 የማሳወቂያ ፕሮግራም (Informational Programmes)

በዓለማችን ላይ በየቀኑ የሚከናወኑ ክስተቶችን በተከሰቱበት ወቅት ለአድማጮች


የሚያደርስ የሬዲዮ ፕሮግራም የማሳወቂያ ፕሮግራም ይባላል፡፡ ይህ ፕሮግራም አዳዲስ
መረጃዎችን ለአድማጭ የሚያደርስ የሬዲዮ ፕሮግራም ዓይነት ሲሆን በዋናነት
አድማጭን፡-

 ከዛሬ ቀን ውጭ ሰምተውት የማያውቁትን መረጃ ያቀርባል፣


 የማያውቋቸውን ሰዎች ያስተዋውቃል፣
 ለህይወት ጠቃሚ የሆነውንና የማይጠቅመውን እንዲሁም ስጋት የሆኑትን
ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ግንዛቤ እንዲኖር ያደርል፣
 አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ያነሳሳል፣
 እርምጃ ወይም ግብረ መልስ ለመውሰድ ከውሳኔ የሚያደርስ ከሆነ የማሳወቂያ
የመረጃ ፕሮግራሞች ጥቅሞች ናቸው፡፡

3.2.3 የመዝናኛ ፕሮግራም (Entertainment Programmes)

ምንም እንኳ አንድ የማስተማርያና የማሳወቂያ ፕሮግራም ውስጥ መዝናናት ቢኖርም


እንዳንድ ፕሮግራሞች ግን በተለያ መዝናኛነትን ታሳቢ በማድረግ የሚዘጋጁ አሉ፡፡
የመዝናኛ የሬዲዮ ፕሮግራሞች በአድማጮች አዕምሮ ውስጥ እረፍትንና ፈታ ማለትን

66
የሚፈጥሩ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ሲሆኑ በዋናነት አድማጮች ጊዜያቸውን ለፕሮግራሙ
ለመስጠት መዝናናትን በመፍጠር ዘና እያሉ የማህበረሰባዊ ጉደዮችን የሚያከናውኑበትን
ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚችል የሬዲዮ ተወዳጅ ፕሮግራም ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም
ለአድማጮች የሚከተሉት ገጸ በረከቶች ያበረክታል፡፡

 ደስታን ይሰጣል፣
 ከጭንቀትና ከድካም ይገላግላል፣
 ተሳትፎን ያበረታታል፣
 ልምድን ያሰፋል፣
 የባህል ተግዳሮቶችን ያጠፋል/ከተግዳሮቶች ባሻገር ያለውን እንዲታሰብ
ያደርጋል፣
 የውይይት አጀንዳዎችን እንዲቀረፁ ያስችላል፣
 የማህበረሰብ አገልግሎትን የሚያሳድጉ የጋራ ተሞክሮን ያቀርባል፣
 የተግባቦትና የጠያቂነት ክህሎትን ያዳብራል፣
 ሌላ ወጭ የሚበዛባቸውን የመዝናኛ መንገዶች በማስቀየር አማራጭ ይሆናል፣
 የሌሎችን ባህል ያስተምራል፡፡

የውይይት ጥያቄዎች

 አንድ የምታውቁትን የሬዲዮ ፕሮግራም በመለየት የትኛው የሬዲዮ


ፕሮግራም ሥር እንደሚመደብ ተወያዩ?
 አድማጮች በአብዛኛው የሚፈልጉት የሬዲዮ ፕሮግራም ዓይነት የትኛውን
ነው?
 የሬዲዮ ፕሮግራም መስራት የምትፈልጉት በየትኛው ዓይነት ነው?

3.3 የሬዲዮ ፕሮግራም ባህርያት

አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮግራም ሊያሰኙት የሚችሉ የራሱ የሆኑ ባህርያት አሉት፡፡
እነዚህም ባህርያት፡-

 ቋሚ የፕሮግራም መጠሪያ ርዕስ


 ቋሚና ተመሳሳይ የስርጭት ቀንና ሰዓት
 ተመሳሳይ የአየር ላይ ቆይታ

67
 የተለየ የፕሮግራም መክፈቻ ወይም መለያ ሙዚቃ (signature tune/ Jingle)
 የታወቀና ሙሉ ሃላፊነት የሚወስድ አዘጋጅ እና
 ለየት ያለ የራሱ የይዘት አቀራረብ ያለው

እነዚህ ባህርያትን ይዞ አየር ላይ የሚውል የሬዲዮ ፕሮግራም ጥሩ ወይም መጥፎ


ሊሆነ ይችላል፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራሙ መጥፎ ከሆነ አድማጭ ስለሚያጣ በተቻለ መጠን
የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጁ በተቻለው መጠን ጥሩ ፕሮግራም መቅረፅና መስራት
ይኖርበታል፡፡ አንድን የሬዲዮ ፕሮግራም ጥሩ ነው የሚያስብለው ደግሞ በአድማጮች
ህይወት ላይ ተፅዕኖ መፍጠር ሲችል፣ የሃሳብ ሙግት በሰዎች ዘንድ መፍጠር ሲችል፣
አስደሳች አቀራረብና አቅራቢ ሲኖረው፣ ለአድማጮች ግልፅ ከሆነ፣ በአድማጮች አዕምሮ
ውስጥ ምስል ሲፈጥር፣ የተለያዩ የድምጽ ግብዓቶችን አካቶ ከያዘ እና አድማጮች
የሚሳተፉበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

የውይይት ጥያቄዎች

 አንድ የምታውቁትን የሬዲዮ ፕሮግራም በመለየት ከሬዲዮ ፕሮግራም


ባህርያት አንጻር ገምግሙ፡፡

3.4 የሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት

አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ለመድረስ በሂደት ውስጥ


ማለፍ ይኖርበታል፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራም ሃሳብን ከማመንጨት እስከ ስርጭትና የግብረ
መልስ ስብሰባ ዳሰሳ ጥናት ድረስ ያሉትን የዝግጅት ሂደቶች ሶስት ምዕራፎች አሉት፡፡
እነሱም፡-

1. ቅድመ ዝግጅት (pre-production)


2. ዝግጅት (production)
3. ድህረ ዝግጅት (post-production

68
3.4.1 የቅድመ-ዝግጅት ምዕራፍ

ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ለተሳካ የሬዲዮ ፕሮግራም የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡


ይህ ምዕራፍ ዋናው የዝግጅት ሥራዎች ከመሰራታቸው በፊት ያለው ጊዜ ውስጥ
የሚያከናውኑትን ሥራዎች የሚያጠቃልል ሲሆን የስራውን አጠቃላይ ውጤታማነት
የሚወስን የማሰቢያና የማቀጃ ጊዜ ነው፡፡አዳምስና መሳይ የተባሉ ምሁራን እንዳሉት
“የተሻለ ሥራ የተሻለ ነፀብራቅ ነው”፡፡ በዚህ ምዕራፍ የተሻለ ሥራ የሰራ ሰው ስኬታማ
ፕሮግራም ማዘጋጀት ይችላል፡፡ በዚህ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ የሚከተሉት ዝርዝር
ተግባራትና ንዑስ ተግባራት መከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. ዓላማውን መለየት

በመጀመሪያ የሚሰራው የሬዲዮ ፕሮግራም ለምን ዓላማ እንደሚሰራ መለየት የቅድመ


ዝግጅት ምዕራፍ ዋነኛ ሥራ ነው፡፡ ቢያንስ በፕሮግራሙ ማሳካት የተፈለገው ግብ ምን
እንደሆነ መገለፅ ይኖርበታል፡፡ በአብዛኛው የሬዲዮ ፕሮግራም የማሳወቂያ፣
የማስተማርያና የመዝናኛ ዓላማ ስላለው የሬዲዮ ፕሮግራሙን ማህበራዊ ፋይዳዎች
መለየት የመልዕክቱን ዓይነት፣ የአቀራረብ ሁኔታ፣ የአድማጮች ምላሽና አቀባበል
ግምት ለማስቀመጥ ይረዳል፡፡ በአጠቃላይ የፕሮግራሙ ዓላማ ከአድማጮች ፋላጎትና
ከተቋሙ አቅም አንጻር የተቃኘ ያደርገዋል፡፡

2. የአድማጭ ፋላጎት የዳሰሳ ጥናት

አንድን የሬዲዮ ፕሮግራም ከመቅረፃችን በፊት አድማጮችን መለየትና ፋላጎታቸውን


ማወቅ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ የአድማጮችን ባህርይ ከፆታ፣ ዕድሜ፣
የትምህርት ደረጃ፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ሐይማኖት፣ ባህል፣ የኢኮኖሚ ሁኔታና የአካባቢውን
ወቅታዊ ሁኔታ መለየት ወዘተ የመሳሰሉት በዳሰሳ ጥናት የሚገኝ ሲሆን ከፕሮግራሙ
ሥራ በፊት ይህን የዳሰሳ ጥናት ማከናወን የሚያገለግለው፡-

 ፕሮግራሙን ጠቃሚና አግባብነት ያለው ለማድረግ


 ፕሮግራሙን በትክክለኛ ጊዜ ለማቅረብ
 የፕሮግራሙን የመደመጥ ዕድል ለመጨመር
 የፕሮግራሙን ይዘትና አቀራረብ ለመወሰን

69
በአጠቃላይ የአድማጮችን ባህርይና ፍላጎት የበለጠ በታወቀ ቁጥር የሬዲዮ ፕሮግራሙ
ለአድማጮች የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ነው፡፡

3. ማቀድና መበጀት

ዕቅድ የማኔጅመንት ሥራ አንድ ተግባር ሲሆን የአንድን የሬዲዮ ፕሮግራም ወደፊት


አጠቃላይ ሂደት፣ ግብዓትና ተግባራትን ለመለየት የታለመለትን ግብ እንዲመታ
ማስቻል ነው፡፡ ስለሆነም ወደተግባር ከመገባቱ በፊት ዕቅድ መታቀድ ይኖርበታል፡፡
ዕቅድ በሂደት ውስጥ ምንና እንዴት እንደሚሰራ የሚወሰንበት ምዕራፍ ነው፡፡ ዕቅድ
ሲታቀድ፡-

 ወደፊት ምንና እንዴት እንደሚሰራ ማሳየት ይኖርበታል


 ከግብ ለከመድረስ የሚደረግ የውሳኔ ሥርዓት ይኖረዋል
 ዓላማዎች መሳካት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይኖርበታል፡፡

የተለያዩ ልሂቃን እንደሚሉት “ማቀድ አለመቻል አለመቻልን ማቀድ ነው” እንደሚባለው


አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ዕቅድ በሚገባ ከተሰራ ውጤታማ ይሆናል፤ ዕቅዱ ላይ ችግር
ካለበት ደግሞ ስኬታማ ፕሮግራም ማዘጋጀት አይቻልም፡፡ በዕቅድ ውስጥ የሚከተሉት
ተግባራት ይከናወናሉ፡፡

1. ፕሮግራሙን መለየት፡- የፕሮግራሙን ይዘትና አድማስ መለየት፣ ፕሮግራሙ


የሚፈይደውን መለየት፣ እና ፕሮግራሙ ለማን እንደተዘጋጀ መለየት
2. አድማጭን መለየት፡- ተቀዳሚና ቋሚ አድማጮችን መለየት፣ የሚመቻቸውን
ፎርማት መለየት
3. ግለጽ ዓላማዎችን ማስቀመጥ
4. የሥራዎችን ቅደመ ተከተል ማስቀመጥ
5. የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን መለየትና የሚገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት
6. ለተሳታፊ አካላትና ግለሰቦች ስለፕሮግራሙ ያሉትን መረጃዎች ማጋራትና
በጉዳዩ ዙሪያ ግልጽ ውይይት ማድረግ

70
በሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት ላይ የዕቅድ ሥራ ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸው ግብዓቶች
የሚሆኑት መረጃ፣ ሰዎች፣ መሳሪያዎች፣ ጊዜና በጀት ናቸው፡፡ በጀት ስንል
ለፕሮግራሙ የሚያስፈልግ አጠቃላይ የማቴሪያልና የገንዘብ መጠንን ያጠቃልላል፡፡

4. ፎርማትን መምረጥ

ሬዲዮ በርካታ ግብዓቶችን የሚፈልግ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያለው የመረጃ ማስተላለፊያ


ነው፡፡ አድማጮች የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን ብዝሃነታቸውን ከግምት ውስጥ
ያስገባ ፎርማት መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ ፎርማት ማለት አንድን ፕሮግራም ለአድማጮች
የሚቀርብበትን የአቀራረብ ቴክኒክ የመምረጥ ሂደት ነው፡፡ ሬዲዮ የተለያዩ ፎርማቶች
ያሉት ሲሆን እንደሚቀርበው ርዕስ ፎርማቶችን እያሰባጠሩ ማቅረብ ይመከራል፡፡
የተለያዩ ፎርማቶችን መጠቀም ማለት የተለያየ ፍላጎት ያላቸውን አድማጮችን ፍላጎት
ማርካት ስለሆነ የተለያዪ የድምጽ ግብዓቶችን በመጠቀም መስራት አስፈላጊ ነው፡፡
የሰዎችን ድምፅ፣ ሙዚቃንና የድምፅ ኢፌክቶችን በመጠቀም የሚሰራ ሬዲዮ ፕሮግራም
ደግሞ ተመራጭ ነው፡፡

5. ስክርፕት መጻፍ

የሬዲዮ ፕሮግራም ስክርፕት ፅሁፍ በምርምርና የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎችን በመጠቀም


የተገኙ መረጃዎችን ለአድማጭ የምናደርስበት ፅሁፍ ሲሆን መልዕክቱን መለየት ተገቢ
ነው፡፡ የስክርፕቱ መልዕክት ወቅታዊ፣ አስደሳችና ጠቃሚ መሆን ይገባዋል፡፡ የመረጃ
ምንጮችን በአግባቡ መጥቀስና መረጃዎችን ያለማዛነፍ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡ የሬዲዮ
ስክርፕት በሚጻፍበት ጊዜ እንደንግግር ይጻፋል፡፡ ይህም ማለት የንግግር ቋንቋን
በመጠቀም ይፃፋል፡፡ የሬዲዮ ስክርፕት በሚጻፍበት ጊዜ የስክርፕቱ ዓላማ አወቃቀሩን
ይወስናል፡፡ የስክርፕቱን አወራረድ ግልፅ መደረግ አለበት፡፡ ሁልጊዜም በጽሁፍ ወቅት
ለጓደኛ እንደምንናገር እንጽፋለን፡፡ በመጀመሪያ ላይ ልብ አንጠልጣይ በሆነ ዓረፍተ ነገር
ተጀምሮ አድማጭን ይዞ ይጀምርና በመጨረሻም አድማጮችን አርክቶ መጨረስ
ይኖርበታል፡፡

ስክርፕት በሚጻፍበት ጊዜ፡-

71
 የምንጠቀምባቸው ዓረፍተ ነገሮች አጭር መሆን ይኖርባቸዋል፤ ተከታታይ
አጭር ግን አይሆኑም ምክንያቱም ግጥም ነው የሚመስሉት፤
 የምንጠቀምባቸው ዓረፍተ ነገሮች ቀላል መሆን አለባቸው፣
 የምንጠቀምባቸው ዓረፍተ ነገሮች ግልጽና ቀጥተኛ ሊሆኑ ይገባል፤
 የተወሳሰቡ ለአነባብ አስቸጋሪና ለአድማጭ ግልጽ ያልሆኑ ቁጥሮችን
ማጠጋጋትና በአሃዝ መፃፍ፣
 በአዕምሮ ውስጥ ምስል መሳል፤
 ፅሁፍን ለአንድ ሰው እንደማውራት መፃፍ
6. ተሰጥዖና ድምፅ መረጣ

ተሰጥዖ ያላቸውን አንባቢዎች መምረጥ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ አንዱ ተግባር ሲሆን
በዋናነት የሚከተሉት ብቃትና ተሰጥዖ ያሏቸውን አንባቢዎች ማግኘት ደግሞ
የፕሮግራሙን አቀራረብ ውጤታማ ያደርገዋል፡፡

 ጥሩ የኮሚዩኒኬሽን ክህሎት
 ስሜትን የመግለፅ ብቃት
 በራስ መተማመን
 የጊዜ አጠቃቀም
 የፅሁፍን ውስጠት የመረዳትና በተረዱት መጠን የማቅረብ ብቃት
 ልምድ

ድምፅ ስንመርጥ የፕሮግራማችን ይዘትን ያማከሉ ሊሆን ይገባል፡፡ ሙዚቃ ለሬዲዮ


ፕሮግራም ፅሁፍን በማሳመርና ለይዘቱ ድጋፍ በመስጠት እንደቅመም ሆኖ ያገለግላል፡፡
የሙዚቃው ዓይነት መለያ ሙዚቃ፣ የመግቢያ መዚቃ፣ የመሸጋገሪያ ሙዚቃ፣
የማጀቢያ ሙዚቃ ወይም የሙዚቃ ግብዣ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ከፕሮግራሙ ይዘት
ጋር ተዛማጅነት ያለው ወይም ይዘቱን የሚያጠናክር ሙዚቃ በመምረጥ እንደግብዓት
መጠቀም ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የአንዳንድ ኩነቶችንና አካባቢውን ድምፅ በመቅረፅ
ለፕሮግራሙ ውበት ይሆን ዘንድና ተፈጥሮዓዊ መቼቱን ለማሳየት ይጠቅማል፡፡
ስለሆነም ተሰጥዖ ያላቸውን አንባቢዎች ከመምረጥ በተጨማሪ በፕሮግራሙ ውስጥ
የሚካተቱትን የሙዚቃና ድምፅ ኢፌክቶችን መምረጥ ያስፈልጋል፡፡

72
3.4.2 የዝግጅት ምዕራፍ

ይህ ምዕራፍ በቅድመና በድህረ ዝግጅት ወቅት ያለውን ጊዜ የሚያጠቃልል ሲሆን ዋናው


የስቱዲዮ ቀረፃ የሚከናወንበት ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ የስክርፕት ንባብ ልምምድ፣ የስቱዲዮ
የዳይሬክቲንግ ሥራ እና የስክርፕት ወደ ድምፅ ለመቀየር የድምፅ ቀረጻ የሚከናወንበት ወቅት
ነው፡፡

የስክርፕት ንባብ በሚከናወንበት ጊዜ፡

 የራስን ድምፅ ማወቅና መጠቀም፤ የሌሎችን አለማስመሰል ወይም ለማስመሰል


አለመሞከር፣
 የድምጽን ከፍታና ዝቅታ መለዋወጥ፣
 ስክርፕቱን ደጋግሞ በማንበብ መገንዘብ፤
 በስክርፕቱ ውስጥ ያሉትን ረዣዥም ዓረፍተ ነገሮች አጭር ማድረግ፣
 ስክርፕቱ የሚፈልገውን የድምፅ ዓይነት መለየት፣
 ስክርፕቱን መለየትና ማስተካከል፣
 የድምፅ አወጣጥና የሥርዓተ-ነጥብ አጠቃቀምን መለየት፣
 የአነባብ ፍጥነትን መለየት፣
 ከማይክራፎን ጋር ያለውን አቅጣጫና ርቀት ማስተካከል፣
 ስክርፕቱን ያለስህተት ማንበብ፤ ከተሳሳቱም ይቅርታ ጠይቆ በድጋሜ አስተካክሎ
ማንበብ፣

ከእነዚህ የስክርፕት ንባብ ላይ ከምናተኩርባቸው ዓበይት ጉዳዮች በተጨማሪ ሮበርት ማክሊሽ


(1999) ስክርፕት በሚነበብበት ጊዜ የሚታዩ ጉዳዮችን “7 ps” በማለት ይጠራቸዋል፡፡ እነሱም፡-

1. Posture (ዜና በሚነበብበት ጊዜ የሚኖረን አቀማመጥና ወረቀት አያያዝ)


2. Pitch (ድምፅ ከፍታና ዝቅታ)
3. Pronunciation (ቃላትን በትክክል የማንበብና የመጥራት)
4. Projection (የድምጽ ሃይል አጠቃቀም)
5. Pace (አነባብ ፍጥነት ልኬት)
6. Pause (የሥርዓተ-ነጥብ አጠቃቀምና የአተነፋፈስ ስልት)
7. Personality (የማይክ አጠቃቀም፣ ሥህተትን በፍጥነት የማረምና የፈጠራ ክህሎት)

73
3.4.1 የድህረ ዝግጅት ምዕራፍ

ዋናው የሥቱዲዮ የቀረጻ ፕሮግራም ከተጠናቀቀ በኋላ ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል፡፡ በዚህ ምዕራፍ
ውስጥ የኤዲቲንግና የሥርጭት ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡ ኤዲቲንግ ማለት አንድ የተቀረጸን
ድምፅ ውስጥ አስፈላጊ ያልሆኑትን የማስወገድ፣ አስፈላጊ ድምጾችን ደግሞ የማስገባትና
ቦታቸውን የማስተካከል ሂደት ነው፡፡ ኤዲቲንግ ሲሰራ የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፡፡
 የተቀረፀው ድምፅ በትክክል ለማስቀመጥ/ ለማስተካከል፤
 የሚያስፈልጉ ወይም የቴክኒክ ብልሽት ያለባቸውን ድምፆች ለማጋድ፣
 የፕሮግራሙን ግብዓቶች ከፕሮግራሙ ሰዓት ጋር ለማጣጣም፣
 ሙዚቃና የድምፅ ኢፌክቶችን ለመጨመር

ኤዲቲንግ ማንዋል፣ ኤሌክትሮኒክ ወይም ኮምፒውተራይዝድ ሊሆን ይችላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት


ግን የኮምፒውተር ሶፍት ዌር በመጠቀም የሚከናወነው ኤዲቲንግ በሁሉም ሬዲዮ ስቱዲዮዎች
ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ነው፡፡ ይህ የኮምፒውተር ፕሮግራም Adobe Audition ይባላል፡፡

ማጠቃለያ

አንድን የሬዲዮ ፕሮግራም ከቅድመ ዝግጅት (ፕሮፖዛል ቀረፃ) እስከ ድህረ ዝግጅት የሚከናወኑ
ተግባራትን መለየት ለአንድ የፕሮግራም አዘጋጅ ወሳኝ ሆኑ ፋይዳዎች አሉት፡፡ ምክንያቱም
የሬዲዮ ፕሮግራም በሚዘጋጅበት ጊዜ ስኬታማነቱ የሚወሰነው በየምዕራፉ በምናከናውናቸው
ተግባራት ነው፡፡ ስለሆነም በየአንዳንዱ ምዕራፍ የምንሰራቸው ሥራዎች ጥራታቸውን የጠበቁና
ሙያውን ያማከሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

74
ዋቢ መፅሐፍት







































75

አባሪ፡- የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮፖዛል አዘገጃጀት


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል

“የምሁራን ጨዋታ”
(የሬዲዮ ፕሮግራም ትልም)

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ


ኤም 97.7 የሚቀርብ
ዋና አዘጋጅ፡- ደሳለው ጌትነት

ተባባሪ አዘጋጅ፡- ሐይማኖት ጌታቸው

ታህሳስ 2009 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ

76
ማውጫ
ይዘት ገፅ

1. .............................................................................................................................................. መግቢያ
..................................................................................................................................... 78
2. ............................................................................................................. የፕሮግራሙ አጠቃላይ መግለጫ
..................................................................................................................................... 79
2.1 ስያሜ ....................................................................................................................................... 79
2.2 ዓላማ ...................................................................................................................................... 79
2.3 አድማስ .................................................................................................................................... 79
2.4 አዘጋጆች................................................................................................................................... 80
5 የሚቀርብበት ቋንቋ ....................................................................................................................... 80
2.6 ርዝመት (ቆይታ) ......................................................................................................................... 80
2.7 መቼት ..................................................................................................................................... 80
2.8 ይዘት ....................................................................................................................................... 80
2.8.1 የምሁራን ትንታኔ .................................................................................................................. 80
2.8.2 የሙዚቃ ግብዣ .................................................................................................................. 81
2.8.3 የአድማጮች ጥያቄ................................................................................................................ 81
2.8.4 ጥያቄና መልስ .......................................................................................................................... 81
3. አቀራረብ ....................................................................................................................... 81
4. የፕሮግራሙ ጊዜያዊ የጨዋታ አጀንዳዎች .................................................................................. 83
5. ........................................................................................................................... የሚያስፈልጉ ግብዓቶች
..................................................................................................................................... 84
5.1 የሰው ሃይል ................................................................................................................................ 84
5.2 ቁሳቁስ ..................................................................................................................................... 84
5.3 ገንዘብ ...................................................................................................................................... 85
6......................................................................................................................... የገንዘብ ማግኛ መንገዶች
..................................................................................................................................... 85
7. ......................................................................................................... የፕሮግራሙ ማስተዋወቂያ መንገዶች
..................................................................................................................................... 85

77
መግቢያ

የብዙሃን መገናኛ እንደወግ ይከተሏቸው የነበሩ ንድፈ ሃሳቦች በአብዛኛው የብዙሃን መገናኛ
ከመንግስት ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ መሠረት ያደረጉ ነበሩ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተቀየረ መጥቶ ህዝብን መሠረት ያደረጉ፤ የመረጃ ፍሰታቸውን ከህዝብ ወደ ህዝብ በማድረግ
ትኩረታቸውን ህዝብ ላይ ያደረጉ ንድፈ ሃሳቦች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ንድፈ ሃሳቦች
አንዱ የሆነው የልማታዊ ጋዜጠኝነት ንድፈ ሃሳብ ደግሞ በሶስተኛው ዓለም ላለው የሚድያ
ተቋም ምርጥ ፍልስፍና በመሆን ድምፅ አልባ ለነበሩት ዜጎች ድምፅ በመሆን አማራጭ የመረጃ
ማግኛና ማስተላለፊያ መንገዶችን በማቅረብ ሚናውን እየተጫወተ ነው፡፡ በዚህ ፍልስፍና ውስጥ
ሚዲያ የህዝብ ወገን በመሆን የልማቱ ተጠቃሚ የሆነውን ሰፊ ህዝብ የማገልገል ሚና
ይጫወታል፡፡ ህዝቡ በራሱ አንደበት ለራሱ መናገር የሚችልበት ሁኔታ እያመቻቸ የሚሄድ
የብዙሃን መገናኛ ንድፈ ሃሳብ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ነው፡፡ ልማታዊ ጋዜጠኝነት በታዳጊ አገራት
ህዝቦችን ንቃተ ህሌናቸውን በማሳደግ ለልማት እና ለዲሞክራሲያዊ ግንባታ የሚያበረክተው
አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

የልማታዊ ጋዜጠኝነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲጫወት እንደመሳሪያ የሚያገለገለው


ዘልማዳዊው የሚዲያ ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ በህዝብ ተመስርተው በህዝብ የሚንቀሳቀሱት
የማህበረሰብ የሚዲያ ተቋማት ጭምር መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የማህበረሰብ ሚዲያ
አድማሳቸው ሠፊ በሆኑ ሚዲያዎች ላይ ትኩረት ያላገኙትን ወይም የተረሱትን የማህበረሰብ
አባላት ድምፃቸውን እንዲያሰሙ የሚያስችሉ ተቋማት ናቸው፡፡ እነዚህ የማህበረሰብ የሚዲያ
ተቋማት ባለቤትነታቸው ለራሱ ለማህበረሰቡ ሲሆን የማህበረሰቡን የልብ ትርታ በማዳመጥ
ማህበረሰቡን የማሳወቅ፣ የማዝናናት፣ የማስተማር እና የእነዚህ በማደባለቅና በማሰባጠር
የሚሰሩ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የብዙሃን መገናኛ ዓይነቶች የመንግስት፣ የንግድና የማህበረሰብ በመባል በሶስት


ይከፈላሉ፡፡ የማህበረሰብ ሬዲዮ በቅርብ ጊዜ የመጣ የብዙሃን መገናኛ እይታ ቢሆንም በአሁኑ
ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ከኢትዮጵያ ብሮድካስት
ባለስልጣን ፍቃድ በማግኘት ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ ከእነዚህም የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች
አንዱ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 97.7 ነው፡፡ ኤፍ
ኤም 97.7 የደብረ ማርቆስና የአካባቢው ማህበረሰብ ሬዲዮ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲውና
በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ ዓበይት የሚባሉትን ጉደዮች በመዳሰስ የማሳወቅ፣ የማስተማርና
የማዝናናት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

78
ይህ የማህበረሰብ ሬዲዮ የማህበረሰቡ ድምፅ እንደመሆኑ መጠን ማህበረሰቡን ያሳተፉ
ፕሮግራሞችን በራሳቸው የማህበረሰቡ አባላት በመጠቀም ማከናወን ወሳኝ ሚና እንዳለው
ይታመናል፡፡ ስለሆነም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው
የማህበረሰብ ሬዲዮ የአየር ሰዓት ወስደው ፕሮግራም መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ስለታመነበት
ይህ “የምሁራን ጨዋታ” የተሰኘ የሬዲዮ ፕሮግራም ትልም ቀርቧል፡፡

በዚህ ትልመ ሃሳብ ውስጥ ስለፕሮግራሙ አጠቃላይ መግለጫ ማለትም ስያሜ፣ ዓላማ፣
አድማስ፣ አዘጋጅ፣ ቋንቋ፣ ርዝመት (ቆይታ)፣ መቼት፣ ይዘት እና አቀራረብ እንዲሁም
ለፕሮግራሙ አስፈላጊ የሆኑ ዋና ዋና የቁሳቁስና የገንዘብ ግብዓቶች ቀርበዋል፡፡

የፕሮግራሙ አጠቃላይ መግለጫ

2.1 ስያሜ

የዚህ ፕሮግራም ስያሜ “የምሁራን ጨዋታ” ይሰኛል፡፡ የምሁራን ጨዋታ ከሌላው ዜጋ ጨዋታ
የተለየ ሲሆን በዋናነት የንድፈ ሃሳብና የተሞክሮ ተኮር ጨዋታዎች ይገኙበታል፡፡ የዚህ ስያሜ
የተሰጠው ፕሮግራሙ በውስጡ ከሚሰራቸው የጨዋታ አርዕስቶች ወይም የጨዋታ አጀንዳና
የተጫዋቾች የጨዋታ ሥርዓት አንፃር የሚዘጋጅ ስለሆነ ነው፡፡

2.2 ዓላማ

ይህ ፕሮግራም ዓቢይና ንዑስ ዓላማዎች አሉት፡፡ የፕሮግራሙ ዓበይት ዓላማ ለደብረ ማርቆስ
ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማህበረሰብ መረጃ የመስጠት፣ ማስተማርና ማሳወቅ ነው፡፡ ይህም
ሲተነተን የሚከተሉትን ንዑስ ዓላማዎችን የያዘ ይሆናል፡፡

ለማህበረሰቡ በቂና ጠቃሚ ወቅታዊ መረጃዎችን ከባለሙየዎች አንደበት ማስተላለፍ፣

ሙያዊ ማብራርያ የሚሹ ጉዳዮችን ከባለሙያዎች አንደበት መተንተን፤

የማህበረሰቡን የውይይትና የመረጃ ልውውጥ ባህል እንዲዳብር የማድረግ፤

የማህበረሰቡን የጠቅላላ እውቀት ማጎልበት፤

2.3 አድማስ

ይህ ፕሮግራም አድማሱ የሚወሰነው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር፣ ጥናትና


ምርምር ዙሪያ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ መምህራን፣ ተማሪዎችን እና አጠቃላይ
የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች ደብረ ማርቆስ ከተማናና በዙሪያው የሚገኙ የማህበረሰብ

79
አካላት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ዓለም ዓቀፍ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወቅታዊ
ጉዳዮችም በምሁራን ጨዋታ ፕሮግራም አድማስ ውስጥ ይዳሰሳሉ፡፡

2.4 አዘጋጆች

ፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅና ተባባሪ አዘጋጆች ይኖሩታል፡፡

ሀ) ዋና አዘጋጅ፡-

ደሳለው ጌትነት (የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን መምህር)

ለ) ተባባሪ አዘጋጆች፡-

ሐይማኖት ጌታቸው (የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን መምህር፣ የኤፍ ኤም 97.7 ሬዲዮ ጣቢያ


ዳይሬክተር)

5 የሚቀርብበት ቋንቋ

ይህ ፕሮግራም የሚዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ሲሆን በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰሩ ሙዚቃዎችን


ለፕሮግራሙ ማጀቢያነት ይጠቀማል፡፡

2.6 ርዝመት (ቆይታ)

የምሁራን ጨዋታ ፕሮግራም በሳምንት አንድ ቀን ለአንድ ሰዓት የሚቆይ ፕሮግራም ነው፡፡
ስለዚህ የፕሮግራሙ አጠቃላይ 1 (አንድ) ሰዓት የአየር ላይ ቆይታ ይኖረዋል፡፡ የዚህ ፕሮግራም
በየንዑስ ፕሮግራሞች ተከፋፍሎ በአቀራረብ ላይ ቀርቧል፡፡

2.7 መቼት

ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 11፡00 ጀምሮ እስከ 12፡00 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው
ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 97.7 የሚተላለፍ ፕሮግራም ነው፡፡

2.8 ይዘት

በምሁራን ጨዋታ ፕሮግራም ውስጥ ያሉት ንዑስ ፕሮግራሞች የሚከተሉት ናቸው፡

2.8.1 የምሁራን ትንታኔ

በዓለማችን ውስጥ በሳምንቱ የተከናወኑ ዓበይት ኩነቶች የሚስተናገዱበት ንዑስ ፕሮግራም


ሲሆን ተቀዳሚ ዓላማው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አባላት በዩኒቨርሲቲያችን፣ በክልላችን፣

80
በአገራችን፣ በአህጉራችንና በመላው ዓለም የተከናወኑትና የብዙሃን መገናኛዎችን ቀልብ መሳብ
የቻሉ ጉዳዮች ከምሁራን ሙያዊ ትንታኔ በመስጠት መጨዋወት፡፡

2.8.2 የሙዚቃ ግብዣ

ባለሙያዎች የሚፈልጉትን ሙዚቃ በየመሃሉ ይጋብዙበታል፤ የጨዋታው ማድመቂያም


የፕሮግራሙ መሸጋገሪያም ይሆናል፡፡

2.8.3 የአድማጮች ጥያቄ

አድማጮች ምሁራን በጨዋታቸው በሚያነሷቸው ፕሮግራሞች ላይ ጥያቄዎችንና


አስተያየቶችንማቅረብ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለሌላ ጊዜ ምሁራን ስለምን ጉዳይ ይጫወቱ
ወይም በምሁራን ጨዋታ ላይ የትኛው ጉዳይ ላይ ትንታኔ ይሰጥበት በሚለው ላይ ሃሳብ
መስጠት የሚችሉበት የምሁራን ጨዋታ ንዑስ ፕሮግራም ነው፡፡

2.8.4 ጥያቄና መልስ

በዚህ ንዑስ ፕሮግራም የተለያዩ የጠቅላላ ዕውቀት ጥያቄዎች እየቀረቡ ቀድመው ለሚመልሱ
አድማጮች በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶች የሚያበረክት ሲሆን የዩኒቨርሲቲውና የአካባቢው
ማህበረሰብ ጠቅላላ ዕውቀት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

3. አቀራረብ

ይህ ፕሮግራም ከ11፡00-12፡00 ሰዓት እንደሚከተለው ይቀርባል

ሰዓት የፕሮግራሙ ይዘት የፕሮግራሙ አቀራረብ

11፡00-11፡02 የሙዚቃ ግብዣ አድማጮችን ለፕሮግራሙ ጆሮ እንዲሰጡ የሚያስችል


የፕሮግራሙ መታወቂያ ሙዚቃ (Signature tune)
መጋበዝ

11፡02-11፡05 አጠቃላዩንና ለአድማጭ የምሁራን ጨዋታ ፕሮግራም መጀመሩን


ቀዳሚውን ፕሮግራም እና በዕለቱ ሊዳስሳቸው የተዘጋጁትን ርዕሰ ጉዳዮችንና
ማስተዋወቅ የንዑስ ፕሮግራም ይዘቶችን ማስተዋወቅ፤

የፕሮግራሙ የጨዋታ እንግዶችን ማስተዋወቅና ወደ


ቀዳሚ ፕሮግራሙ በመሸጋገሪያ ሙዚቃ መግባት

81
11፡05-11፡08 የጨዋታ አጀንዳ የዕለቱን የጨዋታ አጀንዳ ከዓለም አቀፍ እስከ አካባቢ
ያለበትን ሁኔታ በመግለጽ የጨዋታውን ፈር ማስያዝ፣
በአካሄዱ ላይ መነጋገር

11፡08-11፡12 የሙዚቃ ግብዣ የመወያያ አጀንዳውን ከተናገሩ በኋላ ለአድማጮች


የማሰቢያ ጊዜ በመስጠት አዝናኝ ሙዚቃ በመጋበዝ
አድማጮች ዘና እንዲሉ ማስቻል

11፡12-11፡27 የመጀመሪያው በጉዳዩ ላይ ከዓለም አቀፋዊ ንድፈ ሃሳቦችና


ምዕራፍ ጨዋታ ተሞክሮዎችን በማቅረብ የመነሻ የጨዋታ መክፈቻ
ማቅረብ

11፡27-11፡31 ሙዚቃ መጋበዝ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ ከመሻገራችን በፊት


አድማጮችም ተጫዋች ምሁራንም ፋታ እንዲያገኙ
ማድረግ

11፡31-11፡45 የሁለተኛው ምዕራፍ የጨዋታውን አጀንዳ ወደ ሃገራዊና አካባቢያዊ ነባራዊ


ጨዋታ ሁኔታ በማምጣት ትንታኔ መስጠት

11፡45-11፡47 ሙዚቃ ግብዣ አዝናኝ ሙዚቃ ይጋበዝበታል

11፡47-11፡57 የጨዋታው ምዕራፍ ጨዋታውን ዕልባት የማስያዝ ጨዋታዎች ይከናወናሉ


መዝጊያ

11፡55-11፡57 የአድማጮች ጥያቄና የጨዋታው ተከታታዮች የጠየቁትን ጥያቄና መልስ


አስተያየት ጣቢያው ኢዲቶሪያል ፖሊሲ የሚፈቅድላቸው ብቻ
ተለይተው ይቀርቡበታል፤ይስተናገድበታል፡፡

11፡57-11፡59 ጥያቄና መልስ ጨዋታውን በመነሳት ለሳምንት እንዲመለሱ የተጠየቁ


ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበትና አዲስ ጥያቄዎች
የሚጠየቁበት ጊዜ ነው፡፡

11፡59-12፡00 ሙዚቃ የፕሮግራሙ መታወቂያ ሙዚቃ (Signature tune)


መጋበዝ

82
4. የፕሮግራሙ ጊዜያዊ የጨዋታ አጀንዳዎች

በዚህ የጨዋታ አጀንዳዎች ውስጥ ለሶስት ወር የሚሆኑት ለናሙናነት የቀረቡ ሲሆን፤


እንደጨዋታው እርዝመትና ሁኔታ ከአንድ ሳምንት በላይ ሊቀጥል ይችላል፡፡

የጨዋታ የጨዋታ አጀንዳ


ሳምንት

1 ቋንቋና አካዳሚካዊ ስኬት

2 የትምህርት ጥራት

3 የአጠናን ዘዴና አካዳሚካዊ ስኬት

4 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እሴቶች

5 ባህልና ወግ

6 የማህበረሰብ ጤና

7 የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን

8 የግብርና ዘመናዊነት

9 የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች

10 የልጅ አስተዳደግ ሥነ-ልቦና

11 የመሰረተ ልማት ግንባታዎች

12 የከተሞች ዘመናዊነት

83
የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

5.1 የሰው ሃይል

ተ.ቁ የሙያው ዓይነት ብዛት ሃላፊነት


1 ዋና አዘጋጅ 1 ጠቅላላ የፕሮግራሙን ሂደት የአሠራር ሂደት ላይ
ይወያያል፣ ያስፈፅማል፣ ይከታተላል
ፕሮግራሙን በተመለከተ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል፤
ተባባሪ አዘጋጁን ያማክራል፣ የሥራ እገዛ እያደረገ በጋራ
ይሰራል፤
የተሰራውን ፕሮግራም ለአየር ያውላል፤
2 ተባባሪ አዘጋጅ 3 የመረጃ ምንጮችን ይሰበስባል/ የጨዋታውን ተካፋዮች
ይመርጣል፤
የመረጃ ምንጮችን ያነጋግራል/ለጨዋታው ቀጠሮ ይይዛል፣
የጨዋታውን ተካፋዮች ለዋና አዘጋጁ ያቀርባል፤
የተሰራውን ፕሮግራም ለአየር ያውላል፤
3 ቴክኒሽያን 1 በፕሮግራሙ አዘጋጆች የተዘጋጀውን ፕሮግራም አየር ላይ
በጥራት እንዲተላለፍ ያደርጋል፤
5.2 ቁሳቁስ

ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት ብዛት የዕቃው አገልግሎት

1 ዲጂታል ሪከርደር 1 ድምፅ ለመቅረፅ

2 ዲስክቶፕ ኮምፒውተር 1 የተቀረፀን ድምፅ ኤዲት ለማድረግ፣


ለማስቀመጥና ለመጠቀም ያገለግላል

3 ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ 1 በርካታ የፕሮግራሙ ግብዓት የሆኑ


ፋይሎችን (ሙዚቃ፣ ትረካ፣ የድምፅ
ኢፌክቶችንና የመሳሰሉትን) ለመያዝ

4 ፕሪንተር 1 የሚበበቡ ፅሁፎችን ፕሪንት ለማድረግ፤

84
5.3 ገንዘብ

ተ.ቁ የወጭው ዓይነት/የአንድ ሳምንት የአንዱ የተፈለገው ጠቅላላ ወጪ/ብር


ወጪ/ብር ብዛት
የአንድ የአንድ
ሳምንት ወር

1 ለአዘጋጆች የሚሆን ትራንስፖርት 100 2 ሰዎች 200 800


(በወር ለአራት ቀን)

3 ለተሳታፊ አድማጮች የሚደረግ 25 4 ሰዎች 100 400


የማበረታቻ ሽልማት

4 ለአዘጋጆች ተጨማሪ የዝግጅት 500 2 ሰዎች 1000 4000


ወጪዎች

ጠቅላላ 1400 5200

የገንዘብ ማግኛ መንገዶች

ለዚህ ፕሮግራም ወጪ ሊሸፍን የሚችል ገንዘብ በተለያየ መንገድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን
የሚከተሉትን አማራጮች የፕሮግራሙ አዘጋጆች ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ፡፡

 ከሬዲዮ ጣቢያው
 በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ካሉ የሥራ ሂደቶች ስፖንሰር በመጠየቅ፣
 ከውጭ አካላት ስፖንሰር በመጠየቅ፣

የፕሮግራሙ ማስተዋወቂያ መንገዶች

ይህ ፕሮግራም በተለያዩ የማስተዋወቂያ መንገዶች የሚተዋወቅ ሲሆን የሚከተሉት


ይገኙበታል፡፡

 በማህበረሰብ ሬዲዮ
 በውስጥ ማስታወቂያ
 በበራሪ ፅሁፎች አማካኝነት ለአድማጮች የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራል፡፡

85

You might also like