You are on page 1of 36

የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ

የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት

የእሴት ሰንሰለት ትንተና

የቴክኖሎጂ ቅጂ እና ሽግግር

የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ሰነዶች

መስከረም 2015

አዲስ አበባ

0|Page
ማውጫ

የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት 2

እሴት ሰንሰለት ትንተና 10

የቴክኖሎጂ ቅጅ እና ሽግግር 19

የአእምሮ ንብረት (INTELLECTUAL PROPERTY) 29

1|Page
የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት
የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት ጽንሰ ሀሳብ
ምርጥ ተሞክሮ ምንድን ነው?

ቶሪስ የተባለ ጸሐፊ ምርጥ ተሞክሮን ሲገልጽ ዕቅድን በማዘጋጀትና በመተግበር ረገድ በተወሰኑ አካባቢዎች
ስኬታማነታቸው ከተረጋገጡ ተግባራት ውስጥ የትኞቹ ሊተገበሩ እንደሚችሉና እንደማይችሉ፤ እንዲሁም
በተለያዩ ሁኔታዎች እና አውዶች ውስጥ እንዴት? ለምን? እንደሚሰሩ ዕውቀት ለማካበትና በሥራ ላይ ለማዋል
የሚያስችል ልምድ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

እንደ Thiyagarajan Word press ድረ-ገጽ ምርጥ ተሞክሮ ለአንድ ድርጅት አፈጻጸም መሻሻል አስተዋፅኦ
ያበረከቱ፣ ለየት ባለ ዘዴ ፈጠራ የታከለበትን ተግባር የሚያሳይ፤ በተመሳሳይ ድርጅቶች እውቅና የተቸረውና
ብልጫ ያለው ልምድ መሆኑን ይገልጻል፡፡ የምርጥ ተሞክሮ ጽንሰ ሃሳብ ከጥሩ ምሳሌዎች፣ ከመልካም
ልምዶች፣ ከስኬታማ ምንጭ እና ከግንባር ቀደም ተጠቃሽ ተግባራት ጋር የመመሳሰል ትርጉም አለው፡፡ ምርጥ
ፍጹምነትን ወይም የጥራት ደረጃን ሙሉ ለሙሉ የሚወክል ሳይሆን ስኬትን ለማምጣትና ችግሮችን የሚያስችል
ቴክኒካዊ የአሰራር ቅደም ተከተልን የሚያመላክት ነው፡፡

ምርጥ ተሞክሮ በአካባቢ እና በጊዜ አግባብነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አንፃራዊ ነው እንጂ ፍፁም ነው
ማለት አይደለም፤ እንዲሆንም አይጠበቅም፡፡ ምክንያቱም በየትኛዉም ቦታና ጊዜ ፍፁም የሆነ ምርጥ ተሞክሮ
የለም፡፡ ነገር ግን እንደ ምርጥ ተሞክሮ የተወሰደው በአግባቡ በሌላ አካባቢ ሲተገበር በወቅቱ ላሉት ችግሮች
መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል በብዙ አካባቢ በተግባር ተረጋግጧል፡፡ የምርጥ ተሞክሮን ምንነት በተለያየ መልኩ
ቢገለፅም ሁሉም የሚያመላክቱት በተቋማት አሰራር ረገድ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ወይም የላቀና ውጤታማ
የሆነ ሥራ መሥራት ያስቻሉ ተግባራት የውድድር መንፈስ የሚያጭርና የተቋማትን አፈጻጸም ለማሻሻል
የሚያነሳሳ መሆኑን ነው፡፡

በአጠቃላይ የምርጥ ተሞክሮ ለውጤትና ስኬት ያበቁ የተግባራት ዝርዝር ሆነው እነዚህም ሂደትን መሠረት
ያደረጉ፣ በቀላሉ ወደ ሌሎች ሊስፋፉ የሚችሉ በጥልቀት የተለዩ የተግባራት ስብስብ ናቸው፡፡

2|Page
መርሆዎች
 ለምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት ሥራ የሚመረጡ ተግባራት ተግባራዊነቱ ተፈትሾ ስኬታማ መሆኑ
የተረጋገጠ ሊሆን ይገባል፡፡
 ለማስፋት ሥራ ከሞዴሉ የሚወሰደው ልምድና ተሞክሮ በትክክል የተለየ መሆን ይኖርበታል፡፡
 በምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት ሥራ የሚሳተፉ ድጋፍ ሰጪ አካላት ከጅምሩ አንስቶ የሚሳተፉበት
ሁኔታ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡
 የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋቱ ሥራ በወቅቱ ባለው የኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃና
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባል፡፡
 ከማስፋት ሥራ በፊት ያሉት ቅድመ ተግባራት በውል የተዘጋጁ መሆን ይገባቸዋል፡፡
የምርጥ ተሞክሮ ባህርያት
 

የምርጥ ተሞክሮ መገለጫ ባህሪያት በበርካታ ምሁራንና ባለሙያዎች በተለያየ መንገድ የተገለጸ ሲሆን
የጋራ እና ስምምነት የተደረሰባቸው ዋና ዋና ባህሪያት የሚከተሉት ናቸው፡-
ሀ) የለውጡ አድማስ ሠፊ መሆን
ለ) ከፍተኛ የውጤታማነት ደረጃ ያለው
ሐ) በቀላሉ የመስፋፋት ዕድል ያለውና አወንታዊ ልዩነት የሚፈጥር
መ) ፈጠራ የታከለበት አሰራር ያለው
ሠ) በአቅማችን ልንተገብረውና ደጋግመን ለመጠቀም ተጨማሪ ወጪ የማያስወጣ
ረ) ከጊዜ አኳያ ወቅታዊ መሆን
ሰ) ፈጣንና ስር-ነቀል ለውጥ የሚያመጣ
ሸ) የግብ ስኬቱ ሊቀለበስ የማይችል
ምርጥ ተሞክሮ ማስፋት ምንድን ነው?
 የማስፋፋት ስትራቴጂ ማለት በአንድ አካባቢ ተሞክረው ስኬታማነታቸው የተረጋገጠ አሰራሮችን የተለየ
ሁኔታ ባላቸው ሌሎች አካባቢዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ዘላቂነት ያለዉ ተመሳሳይ
አዎንታዊ ለውጥ የመጣበትን ምርጥ ልምዶችን ማዳረስ ማለት ነው፡፡
 ማስፋፋት ስንል በሕብረተሰቡ ዘንድ አዎንታዊ ተጽእኖ የሚኖራቸውን የመንግሥት ፖሊሲዎችንና
ስተራቴጂዎችን በመተግበር በኩል ከውጤታማና ስኬታማ ተቋማት የተገኙ ምርጥ ልምዶችን በሁሉም
አካባቢ ተፈጻሚነት እንዲኖራቸው እቅድና፤ ፕሮግራም በመንደፍ ሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ ነው፡፡
 ማስፋት ተቋምን ለመቀየር ከፍተኛ ተቀባይነት ባለው ተግባር ዙሪያ ለማሰባሰብ የሚደረግ፤ በአንድ
አካባቢ ያሉ ተቋማት ውጤታማ የሆኑበትን እንቅስቃሴ ወደ ሌሎች ተቋማት በማዳረስና ሌሎችም
እንዲያውቁትና እንዲተገብሩት ማድረግ ነው፡፡ በሌላም በኩል የማስፋት ሥራ አላማ ከፍተኛ ቁጥር

3|Page
ያለው የሕብረተሰብ ክፍልን የመድረስ፤ የማነሳሳትና የማንቀሳቀስ ተግባር ነው፡፡
 የማስፋት ሥራ አንዱ መልክ በመጠን መጨመር፤ ቀደም ሲል ከነበረው ደረጃ ሰፋ ወዳለ ደረጃ
ማሸጋገር፤ በተግባሩ የሚሳተፉ ተዋናዮችን ቁጥር ማብዛት ወይም ወደ ከፍተኛ ደረጃ የማሳደግ
ተግባራትን ያካትታል፡፡
 በዘርፉ ልማት በምርጥ ተሞክሮ የተገኙ ስኬታማ ተግባራት ማስፋት በርካታ ኢንተርፕራይዞች፣
የማሰልጠኛ ተቋማት እና የፈጠራ ባለሙያዎች መጠናቸውን በመጨመር ጥራታቸው እንዲጨመርና
ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲረጋገጥ የማነሳሳት ተግባር ሲሆን የሞዴል ኢንትርፕራይዞች፣
የማሰልጠኛ ተቋማት እና የፈጠራ ባለሙያዎች ውጤታማ የሆኑበትን ዝርዝር ተግባራት፣ ውጤቱ
የተገኘባቸውን ስልቶች ዘላቂነት ባለው መልኩ ወደ ሌሎች ተቋማትና ተጠቃሚዎች ወስዶ በመተግበር
በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ አዎንታዊ ለውጥ የሚመጣበትን ተሞክሮ በማዳረስና ሌሎች
አውቀው እንዲተገብሩት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
የምርጥ ተሞክሮ ማስፋት ፋይዳ
 ከማህበራዊ ጠቀሜታ አኳያ በምርጥ ተሞክሮነት የተገኙ ልምዶች እና አዳዲስ አሠራሮችን
ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ የሥራ ፈጣሪነት አመለካካት እንዲጎለብት በማድረግ፣ ለዜጎች በቂ የሥራ
ዕድል በየአካባቢያቸው በመፍጠር፣ ከድህነት ወለል በታች ያለውን የዜጎች አኗኗር በቀጣይነት እየቀነሱ
በመሄድ በማህበራዊ ዘርፎች ውስጥ የሚታዩ ሰፊ ጉድለቶችን ለመሙላት ያስችላል፡፡
 የዘርፉን ልማት ምርጥ ተሞክሮዎች በተጠቃሚው የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ማስፋት በተሞክሮ
ሰጭ እና ተቀባይ መካካል ያለውን የልማታዊ አሰተሳሰብ ልዩነት በማጥበብ በከተሞች የሚታየውን
የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ በመናድ በሂደት በልማታዊ መንገድ ለመጓዝ የሚደረገውን
ጥረት ለማፋጠን ከምንም በላይ ፋይዳው የጎላ ያደርገዋል፡፡
ክፍል ሁለት
ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየትና መቀመር
ምርጥ ተሞክሮ የሚቀመርላቸው አካላትን በመመዘኛ መስፈርቶች መለየት

 ለዘርፉ ስኬት አስፈላጊ ድጋፎችንና አገልግሎቶችን ሲያገኙም ሆነ ሲሰጡ ቆይተው ለሞዴልነት የበቁ
አካላት መሆናቸውን ለማረጋገጥ በተቀመጡ መመዘኛ መስፈርቶች መሰረት ይገመገማሉ፡፡
 በዚህም በእጩ ሞዴልነት ተይዘው በመመዘኛ መስፈርቱ ከተገመገሙት የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞችን መስፈርቱን አሟልተው የተገኙት ለማስፋት ተግባራት በሞዴልነት ይመረጣሉ፡፡

ሀ) የሞዴል ማሰልጠኛ ተቋማት መመዘኛ መስፈርቶች

4|Page
ለ) የሞዴል ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መመዘኛ መስፈርቶች

ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር የሚያስችል ቼክሊስት ማዘጋጀት


የምርጥ ተሞክሮ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉት ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ከምርጥ ተሞክሮ ምንጮች የሚሰበሰበው
መረጃ እንደ ተሞክሮው ሁኔታ በሚዘጋጁ ቼክሊስቶች መሰረት ይሆናል፡፡
 

በዚህ ሁኔታ የሚሰበሰበው መረጃ በቼክሊስቱ መሰረት ሊካተቱ የሚገባቸው ዋና ዋና ይዘቶች የሚከተሉት
ይሆናሉ፡-

ሀ) የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የቼክ ሊስት ይዘቶች፤

ለ) የሞዴል ማሰልጠኛ ተቋማት መመዘኛ መስፈርቶች፤


በቼክሊስት መሰረት መረጃ መሰብሰብ

በየደረጃው በሚገኙ የዘርፉ መዋቅር የተዘጋጁ ቼክሊስቶች እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለየት ሥራ ላይ

የሚውሉ የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ከምርጥ ተሞክሮ መረጃ ማሰባሰቢያ

ዘዴዎች መካከል፡፡

ሀ) የመስክ ጉብኝት እና ምልከታ


ለ) ሰነዶችን በመፈተሽ
ሐ) ቃለ-መጠይቅ
መ) የቡድን ውይይት
ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመር
 ሆኖም ግን ምርጥ ተሞክሮውን የሚቀምሩ አካላት የተሞክሮ ውጤቱ የመጣበትን ዝርዝር ሂደት
ባለማስቀመጥ የተገኘውን ውጤት ብቻ በሪፖርት መልክ መቀመራቸው በመሰረታዊነት የሚያጋጥም
ችግር ነው፡፡
 ይህን የተሞክሮ አቀማመር ዘዴን መከተል ምርጥ ተሞክሮው በሚሰፋበት ጊዜ ውጤቱን ብቻ በማየት
ሌሎች ወደዚህ ውጤት እንዲደርሱ የሚያስችለውን መንገድ ማሳየት አያስችልም፡፡
 ምክንያቱም በቅመራ ሂደት የተገኘው ውጤት እንዴት እንደመጣ በተግባራት አፈፃፀም ቅደም ተከተል
በዝርዝር መቅረቡ ምርጥ ተሞክሮው የመጣበትን መንገድ በግልፅ ለማሳየት ከማስቻሉ በላይ መልካም
ልምዱን በመውሰድ ለሚተገብር አካል አማራጭ መንገዶችን በማየት እንዲጠቀም ያደርጋል፡፡
 በሌላ መልኩ የተቀመረው ምርጥ ተሞክሮ በተገቢው ጊዜና ሁኔታ በተግባር ተተርጉሞ ካልታየ በአጭር
ጊዜ ውስጥ ከጥቅም ውጭ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ የሰፋ ነው፡፡ ምክንያቱም የምርጥ ተሞክሮ

5|Page
ሥራ በባህርዩ በፈጣን ሁኔታ በየጊዜው የሚቀያየርና ዛሬ ምርጥ ተሞክሮ የተባለውን ነገ የሚበልጠው
ሊመጣ የሚችልበት ሁኔታ ስለሚኖር ነው፡፡
 በዘርፉ ልማት ምርጥ ተሞክሮዎች የሚዘጋጁበት በርካታ መንገዶች ሲኖሩ ተሞክሮው የተገኘበትን
ዝርዝር ውጤት በቅደም ተከተል በማስፈር ሌሎች ልምዱን ወስደው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ግልጽ
በሆነ ቋንቋ በተዘጋጀ የጽሑፍ ሰነድ፣ በፎቶግራፍ እና በቪዲዮ አስደግፎ ማቅረቡ የበለጠ ለመረዳት
አመቺ ስለሆነ ሁሉንም አዋህዶ መጠቀሙ የተሻለ ይሆናል፡፡
የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ የዋና ዋና ተግባራት ቅደም ተከተል

ሀ) በቼክ ሊስቱ መሠረት የተሰበሰቡ የምርጥ ተሞክሮ መረጃዎች ከመስፈርቶቹ አንፃር


ማደራጀት፡፡
ለ) መረጃዎቹን በመተንተን ማዘጋጀት (በጽሑፍ በተዘጋጀ ሰነድ፣ በፎቶግራፍ እና በቪዲዮ) አስደግፎ
ማቅረብ፡፡
ሐ) በከተማ/ በወረዳ/ በቀበሌ ደረጃ የተቀመሩትን ሰነዶች በማደራጀት ከሚመለከታቸው ፈፃሚ አካላት
ጋር በመሆን ማጽደቅ፤ ማስፋት፡፡
መ) በዘርፉ መዋቅር የጸደቁ/ የሰፉ የተሞክሮ ሰነዶች በየደረጃው ለሚገኘው የዘርፍ መዋቅር በሪፖርት
ማስተላለፍ፡፡
የምርጥ ተሞክሮ ሰነድ አዘገጃጃት

 በዘርፉ ልማት ከሞዴል ኢንተርፕራይዞች፣ ከድጋፍ ሰጪ ተቋማትና ከከተሞች የምግብ ዋስትና


ፕሮግራም ተጠቃሚዎች የምርጥ ተሞክሮ መረጃ ማሰባሰብ፣ ማደራጀትና መተንተን ሥራዎች
ከተከናወኑ በኋላ መረጃው በየፈርጁ ለመፃፍ በሚመች መልኩ የምርጥ ተሞክሮ ሰነድ ማዘጋጀት ቀጣዩ
ሥራ ይሆናል፡፡
በዚሁ መሠረት የምርጥ ተሞክሮ ሰነድ የሚከተሉትን ዋና ዋና ርዕሶች አካቶ መያዝ ይኖርበታል፡፡
ክፍል ሦስት

የሞዴሎችን ምርጥ ተሞክሮ ስለማስፋት

 የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምርጥ ተሞክሮ ማስፋት ከቁጥርና ከቦታ ስፋት ባሻገር በስኬታማነት
የትግበራ ሂደት ውስጥ የታዩ ውጤታማ ተግባራትን ወደ ሌሎች ተቋማት ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር
በማስማማት ለማድረስ ከጅምሩ አንስቶ አስከ ፍጻሜው በተደራጀ መንገድ የሚከናወንበትን ሁኔታ
መፍጠር ተገቢ ነው፡፡
 እንደ ክልሎች/ ከተሞች/ ነባራዊ ሁኔታ የማሰልጠኛ ተቋማት የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን

6|Page
አጣጥሞ ለማስፋት መሰረታዊ የሆኑ የሥራ ቅደም ተከተሎችን ያለማቆራረጥ ተግባራዊ ሊያደርጓቸው
ይገባል፡፡
የምርጥ ተሞክሮ ማስፋትሥራ ቅደም ተከተሎች

ሀ) የጠራ ራእይ መያዝ


ለ) ሁኔታዎችን ማወቅ
መ) ዕቅድ ማዘጋጀት
ሠ) የጋራ አመለካከት መፍጠር
ረ) ደጋፊ የህግና የድጋፍ ማዕቀፎችን ማወቅ
ሰ) ፈፃሚ እና ባላድርሻ አካላትን መለየትና በአግባቡ ማሰማራት
ሸ) አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ
ቀ) ውጤታማ የግምገማና የክትትል ስርዓት መዘርጋት
ምርጥ ተሞክሮ ከማስፋት በፊት ጥንቃቄ እና ትኩረት የሚደረግባቸው ቁልፍ ጉዳዮች

 የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ የሚኖረው ወሳኝ ጉዳይ ምርጥ ተሞክሮውን
ወቅታዊነቱን በመጠበቅ የማስፋት ሥራ መስራት ነው፡፡ ምርጥ ተሞክሮ በሚሰፋበት ወቅት ልምዱን
በሚወስደው አካል ላይ ተጨባጭና አወንታዊ ለውጥ የማይመጣ ከሆነ ምርጥ ተሞክሮውን
ለመለየትና ለመቀመር የተደረገው ጥረትና ድካም ውጤት አልባ ሆኖ ይቀራል፡፡
 በመሆኑም ምርጥ ተሞክሮዎችን ከማስፋታችን በፊት የተቀመሩ ተሞክሮዎችን ሁሉንም ማስፋት
የሚጠበቅ ባይሆንም ስለሚሰፋው ምርጥ ተሞክሮ አስቀድሞ ማወቅ ተገቢ እና ትኩረት ሊሰጠው
የሚገባ ጉዳይ ይሆናል፡፡
በዚህ መሰረት ምርጥ ተሞክሮ ከማስፋት በፊት ብርቱ ጥንቃቄ እና ትኩረት የሚደረግባቸው ቁልፍ ጉዳዮች
መካከል በዋነኛነት የሚከተሉት ናቸው፡-
ሀ) ምርጥ ተሞክሮ የሚሰፋባቸው ተጠቃሚዎችን በትክክል መለየት፡፡
ለ) ተጠቃሚዎች ምርጥ ተሞክሮውን ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ለመተግበር ያላቸው
ፈቃደኝነትና ዝንባሌ ማረጋገጥና ስምምነት ላይ መድረስ፡፡
ሐ) በተቋሙ የሚገኙ የሥራ ባለቤቶች ሥራው ምርጥ መሆኑን ያመኑበት መሆን አለበት፡፡
መ) በምርጥ ተሞክሮው ብዙ ተጠቃሚዎች እና ባለድርሻ አካላት የረኩበት ማረጋገጫ
የተሰጠበት መሆን አለበት ፡፡
ሠ) ምርጥ ተሞክሮው በሚሰፋበት ወቅት የህብረተሰቡን እሴት፣ ባህልና እምነት የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
ረ) በተሞክሮው ውስጥ የመጣው ለውጥ ሲመዘን ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር በመፍጠር በግንባር

7|Page
ቀደምትነት የሚጠቀስ መሆን አለበት፡፡
ሰ) የሚወሰደው ተሞክሮ ከተመሳሳይ ተቋማት ጋር ሲነጻፀር በተጨባጭ ብልጫ ያሳየና የተመሰከረለት
መሆን አለበት፡፡
ሸ) ለስራው ጥራትና ምርታማነት በአለው ቴክኖሎጂ ተጣጥሞ መጠቀም የሚቻል መሆኑ፡፡
ምርጥ ተሞክሮዎችን የማስፋት ዘዴዎች
ሀ) ፈጣን ኢንኩቤሽን ሞዴል
ለ) በተለያዩ ንዑሳን ዘርፎች የተሰማሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
የልምድ ልውውጥ ቡድንመፍጠር
ሐ) በተመሳሳይ ንዑስ ዘርፍ የተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ቡድን
በማቋቋም
መ) መገናኛ ብዙሐን
ሠ) የሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር በማዘጋጀት
ክፍል አራት
የፈጻሚ እና ባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት
ክፍል አምስት
የክትትል፣ ግምገማ፣ ግብረ-መልስ እና የማበረታቻ ሥርዓት
5.1 የክትትልና የግምገማ ሥርዓት ዝርዝር አፈጻጸም
5.2 የውጤታማ አፈጻጸም አመልካቾች
5.3 አባሪዎች

8|Page
እሴት ሰንሰለት ትንተና
የእሴት ሰንሰለት ፅንሰ-ሃሳብ

ፅንሰ-ሃሳብ

የእሴት ሰንሰለት ትንተና በተለያ ጊዜያት በተለያዩ ጸሀፍት በብዙ መልኩ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህልም፡፡

ማይክል ፖርተር (1985)

ማይክል ፖርተር እ.ኤ.አ 1986 በፃፈው መፅሃፉ የእሴት ሰንሰለት ትንተና ማከናወን ለተወዳዳሪነት ያለውን
ጥቅም የሚያትት ሲሆን ለዚህም አንድ ድርጅት ወይም ኢንተርፕራይዝ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቆየት በውስጡ
የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመፈተሸ የተሻሻሉ አሰራሮችን ወደ ተግባር ማምጣት ይኖርበታል የሚል ነው፡፡

ጌሪ ጌሬፊ በ1990

ይህ ጸሀፊ እ.ኤ.አ በ1990 በጻፈው ጽሁፍ ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚጸድቁ የንግድና የገበያ ስርአቶች
በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ የሚያመጡትን ውጤት በእሴት ሰንሰለት ትንተና ማየት ይቻላል የሚል ነው፡፡

አፕሮች ፊለር ApprocheFilière

ይህ ጸሀፊ ደግሞ የሚያብራራው የመንግስት ፖሊሲዎች፣ ኢንቨስትመንቶች እና ተቋማት በየአካባቢው


የሚመረቱ የግብርና ምርቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በእሴት ሰንሰለት ትንተና ለማየት ይቻላል የሚል ነው፡፡

ሆፕኪንስ እና ዋለርስታይን 1986

በዚህ ጸሀፊ የተዳሰሰው ደግሞ ሂደትና የሰው ሃይል በምርት ላይ ያለውን ተጽዕኖ በእሴት ሰንሰለት ለማሳየት
ችሏል፡፡

ከላይ ማየት እንደሚቻለው የእሴት ሰንሰለት ትንተና በተለዩ ጸሃፍት በብዙ መልኩ ሲገለጽ ቢቆይም የሁሉም
ጽንሰ-ሃሳቦች የሚያተኩሩት አንድ አምራች ወይም አገልግሎት ሰጪ ምርት ወይም አገልግሎት ተወዳዳሪ ሆኖ
ለመቆየት በእሴት ሰንሰለት ትንተና የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመፈተሸና ክፍተቶችን በመለየት የተሻለ
የሚለውን አሰራር መተግበር ምርታማነት፣ ተወዳዳሪነትን፣ ፈጠራንና ማሻሻል ላይ ያተኮረ ዘላቂ ተነሳሽነት
እንዲኖር ማድረግ እና ጥቃቅንና አነስተኛ እቀሳቃሾችን ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅዎ አለው፡፡

9|Page
የእሴት ሰንሰለት ትንተና በሀገራችን

ሀገራችን የተያያዘችውን የህዳሴ ጉዞ ጫፍ ለማድረስና ሌሎች ያደጉ ሀገራት የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ
የሀገራት ተሞክሮና ልምድ ለመቅሠምና የተሻለ የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት በአለፉት ዘመናት እንደየመስሪያ
ቤቶች ሁኔታ በተለያየ መልኩ የእሴት ሰንሰለት ትንተና ሥራዎች በተበጣጠሰ መልኩ ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡
ለአብነት ያህልም በግብርና ሚኒስቴር።፣ በኢንዱስትሪ ሚንስቴር፣ በተለያዩ የምርምር ተቋማት እና
በዩኒቨርስቲዎች በየወቅቱ በተበታተነ ሁኔታ የእሴት ሰንሰለት ትንተና በማከናወን አዳዲስ አሠራሮችን፤
አደረጃጀቶችን፤ አጠቃላይ የዘርፉን ችግሮች በመዳሰስ ለችግሮቻቸው በመፍትሄ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡
በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትኩረት ከተሠጣቸው ተግባራት አንዱና ዋነኛው የዘርፎችን ውጤታማነትና
ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ በምርትና በአገልግሎት ላይ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት እና አጠቃላይ የአሠራር፤
አደረጃጀትና የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን በማስቀመጥ ተወዳዳሪነትን በሚያረጋግጥ መልኩ መፍታት ነው፡፡

ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ ተወዳዳሪነትን የሚያረጋግጥ አዋጭ ቴክኖሎጂ
ለኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር ነው፡፡ በመሆኑም የምርት ወይም የአገልግሎት የአመራት/የአሰጣጥ ሂደት
በመተንተን ክፍተቶችን በመለየት እና ለክፍተቶቹም የቴክኖሎጂዎችን መፍትሄ ለማስቀመጥ የእሴት ሰንሰለት
ትንተና ማከናወን አስፈላጊ ነው፡፡

በእሴትሰንሰለት ትንተና የአንድን ምርት/አገልግሎት ከግብዓት/አምራች እስከ ደንበኛው/ ተጠቃሚው


እስከሚደርስ ያለውን አጠቃላይ ሂደት የምናይበት ቁልፍ፣ የተሻለ እና ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ በቴክኒክና ሙያ
ሥልጠና እስካሁን በርካታ የእሴት ሰንሰለት ትንተናዎች የተዘጋጁ ቢሆንም የተሰሩት ትንተናዎች በሚፈለገው
ደረጃ አዋጭ ቴክኖሎጂዎች ለይቶ ወደ ኢንተርፕራይዞች አልተሸጋገሩም፡፡ በመሆኑም የኢንተርፕራይዝ
የአሰራር ሂደት በመተንተን ከአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮ ጋር በማነፃፀር የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን/ ተግዳሮቶችን
መለየት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ስለዚህ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና በነባሩና በተለየው የተሻለ አሠራር መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ ልዩነት
በማውጣት ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪ ሊያደርግ የሚችል አማራጭ ቀርቧል፡፡ ይህም እሴት ሰንሰለት ትንተና
አሠራር ሲሆን የቴክኖሎጂ ክፍተትን ከመለየት በተጨማሪ ለፕሮጀክት ተኮር ስልጠና እና ለመቶ ፐርሰንት
ቴክኖሎጂ ቅጅን በግብአትነት ያገለግላል፡፡

መርሆዎች

እሴት ሰንሰለት የሚከተሉትን መሠረታዊ መርሆች አሉት

 በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ቅድሚያ ለተሰጣቸው ዘርፎች ትኩረት ይሠጣል፤

10 | P a g e
 የእሴት ሰንሰለት ትንተና ከዘርፎች፤ ከንዑስ-ዘርፎች እና ከየሙያ ዘርፉ በተውጣጡ ባለሙያዎች
ይዘጋጃል፤
 የእሴት ሠንሠለት ትንተና ዝግጅት በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት፤ በመንግስታዊና መንግስታዊ
ያልሆኑ ድርጅቶችና ሌሎች በባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የሚያስተባብሩትና የሚደገፉት
ይሆናል፤
 እሴት ሰንሰለት ትንተናው የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾችን ተወዳዳሪነትን በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ
ይሆናል፤
 የእሴት ሰንሰለት ትንተና የአሠራር ሂደት ከነባሩ አሠራር በመነሳት በአለም አቀፍ ደረጃ ምርጡ
የአሠራር ሂደት ጋር በማነፃፀር ይከናወናል፤
 የእሴት ሠንሰለት ትንተናው ወቅቱ በሚፈልገው የቴክኖሎጂ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ይሆናል፤
 የተዘጋጁ የእሴት ሠንሰለቶች ትንተና ሠነዶች በየደረጃው መረጋገጥ፤ ሪፖርት መደረግ እና ተደራጅቶ
መቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
የእሴት ሰንሰለት ትንተና

የእሴት ሰንሰለት ትንተና አንድን ምርት ከግብአት እስከ ፍጆታ እና ተረፈ ምርቶቹን ለመልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን
ጨምሮ ያለውን የሂደት ዑደት የሚያሳይ ነው፡፡ ድርጅቶች የሚሠጡትን የምርት/ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ
አገልግሎቱን በተወዳዳሪነት በመስጠት ለመቆየት የተሻለ ጥራትና ዋጋ ያላቸው ምርቶች ወይም አገልግሎቶች
ከማቅረብ በተጨማሪ የደንበኞችን እርካታ ለመጠበቅ የደንበኞችን ፍላጎት ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ተወዳዳሪነትን
ለማምጣት የተለያዩ በርካታ አማራጮች ቢኖሩም አንዱና ዋነኛው መሳሪያ ግን የእሴት ሠንሠለት ትንትና
ማከናወን ነው፡፡ ምክንያቱም የእሴት ሠንሠለት ትንተና የአንድን ምርት/ዕቃ/ አገልግሎት ከጫፍ እስከ ጫፍ
ያሉ እያንዳንዱን ተግባራት ከግብዓት እስከ ምርት ያለውን ሂደት በመዘርዘር የሚሠራ በመሆኑ ነው፡፡

በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የእሴት ሰንሰለት ትንተና አካሄድ በየዘርፉ ጥራት ያለው ምርት/አገልግሎት ለመስጠት
እንዲቻል ያለውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመለየት ከተለየው የምርጡ አሠራር ሂደት የነባሩን አሠራር በማነፃፀር
የሚከናወን ይሆናል፡፡ የተለየውን ቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት የተለየውን ቴክኖሎጂ በመቅዳትና ለጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እና ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች በማሸጋገር
ኢንተርፕራይዞች ጥራት ያለው ምርት እና አገልግሎት እንዲሠጡ አቅም በመፍጠር ተወዳዳሪነታቸውን
ማረጋገጥ ነው፡፡

የተዋጣለትና ጥራቱን የጠበቀ የእሴት ሰንሰለት ትንተና ሥራ ለመስራት በቅድሚያ ለተዋንያን እና ባለድርሻ
አካላት የሚያስፈልጉ መለኪያዎች ምርት፤ የምርት ሂደት እና የሎጀስቲክ ሙያዊ ብቃት ብሎም ዝርዝር
ተግባራትን በመዘርዘርና አቅጣጫ በማስያዝ የተዋናዮችን ሚና በሚገባ በመተንተን ግንዛቤ ማስጨበጥ

11 | P a g e
አስፈላጊ ነው፡፡ የምርት/አገልግሎት የእሴት ሰንሰለት ትንተና የሚያከናወኑ ተዋንያን በዘርፍና ንዑስ ዘርፍ
ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ታችኛው የእርከን ደረጃ በሚገኙ እና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዝ ተወዳዳሪነት
በሚሠሩ የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡ በዚህ ሰንሰለት ውስጥ ቁልፍ ተዋናዮች እና በእሴት ሰንሰለት ዝግጅቱ ወቅት
ኃላፊነቱን ወስደው የሚያከውኑት አካላት የቴክኖሎጂ ክፍተቶችንና አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን በመለየት
ሚናቸውን የሚወጡ ይሆናል፡፡

የእሴት ሰንሰለት ትንተና ዘዴዎች

የእሴት ሰንሰለት ትንተን በሁለት ዜዴዎች ማከናወን ይቻላል፡፡ እነሱም፤

በተራዘመ ትንተና (ይህ አይነት የእሴት ሰንሰለት ትንተና በዘርፍ ወይም በንዑስ-ዘርፍ ደረጃ የሚዘጋጅ ሲሆን)
ወይም በቀላል ትንተና (በምርት/አገልግሎት ) መልኩ ሊዘጋጅ ይችላል፡፡

በዚህ ማንዋል የእሴት ሰንሰለት ትንተና በሁለቱም ዘዴዎች ማከናወን እንደሚቻል ይገልጻል፡፡ በንዑስ-ዘርፍ ደረጃ
(በኢኮኖሚ ውስጥ ብዙ ተግባራት የሚከናወንበት ይህም የተለያዩ ምርት /አገልግሎት ለማምረትና ለመስጠት
ያስችላል ለምሳሌ ብረታ-ብረት፤ ጨርቃ-ጨርቅ) ወይም በምርት/በአገልግሎት ደረጃ (ቲማቲም እሴት
ሰንሰለት፤ የአልጋ ዝግጅት እሴትሰንሰለት) ማዘጋጀት ይቻላል ፡፡

የተራዘመ ትንተና

ይህ የትንተና ዘዴ ከቀላል ትንተና በበለጠ የተለያዩ ዘርፎች የሚሳተፉበት ከመሆኑ በተጨማሪ የተለያዩ ትስስር
ፈጥረው ምርት/አገልግሎት የምንተነትንበት የትንተና አይነት ሲሆን ሠንሰለቱ የበዛ እንደመሆኑ የተለያዩ ዘርፎች
እና ንዑስ-ዘርፎች እንዲካተቱ ሆኖ ይዘጋጃል፡፡

የተራዘመ እሴት ሰንሰለት ትንተና የሚከተሉት ባህሪያት አሉት

 ከዘርፍ እና ከንዑስ-ዘርፍ መስሪያ ቤቶች ደረጃ በተውጣጡ የቴክኒክ ባለሙያዎች ተሳትፎ የሚዘጋጅ
መሆኑ፤
 የአንድ የንዑስ ዘርፍ ወይም ከዚያም ባለፈ ያሉትን ሁሉንም የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን የሚያሳይ መሆኑ፤
 በፌዴራል እና በክልል ደረጃ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ አስተባባሪነትና መሪነት መዘጋጀት አለበት፤
ቀላል ትንተና

ይህ የትንተና አይነት ደግሞ በዋናነት በንዑስ-ዘርፍ ውስጥ ከሚገኝ አንድ ምርት/ አገልግሎት ላይ ያተኮረ
የእሴት ሰንሰለት ትንተና ዘዴ ነው፡፡

12 | P a g e
የዚህ አይነት የእሴት ሰንሰለት ትንተና የሚከተሉት ባህሪያት አሉት

 የአንድ ምርት/አገልግሎት ከግብዓት እስከ ምርት ድረስ ያሉትን ሁሉንም ተግባራት ይዘረዝራል፤
 በአንድ ንዑስ-ዘርፍ ደረጃ ማንኛውም በዘርፉ ባለሙያዎች ሊዘጋጅ ይችላል፤
 ከየአካባቢው የልማት ኮሊደር በመነሳት በየትኛውም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት
አስተባባሪነትና መሪነት ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
የእሴት ሰንሰለት ትንተና መምረጥ

 የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ


 በዘርፍ ውስጥ ያለው ድርሻ
 የሥራ እድል
 የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ
 የገበያ ድርሻ
 የወጪ ምርት ድርሻ
 የማደግ አቅም
 የገበያ አቅም
 ሌሎች(የሰው ኃይል፣ ቁስ፣ እውቀት፣ የገንዘብ አቅም፣ መሰረተ ልማት)
 የምርት ማስፋት/ጭማሪ (Product Diversfication)
 በጥቃቅንና አነስተኛ፣ በወጣቶችና ወዘተ የሚያመጣው ለውጥ
 የአካባቢ ጥበቃና ደህንነት
 የሴቶችንና አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት
መረጃ መሰብሰብ

 መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ማዘጋጀት (Gathering tool development)


 ቅድመ-ዝግጅት
የሠንሰለት ማስቀመጥ (Mapping Value chain Activities)

እሴት ትንተና

እሴት ትንተና ማለት የእያንዳንዱን ተግባር በምንና እንዴት ይከናወናል ብሎ መተንተን ሲሆን ይህም የሚሆነዉ ነባራዊ
አሠራሩን (AS IS) ከምርጡ አሠራር (Benchmark) ጋር በማነፃፀር የእሴት ትንተና የጥራትና የመጠን የያዙ
የተግባራት የዳራ መረጃዎችን (Backgrounding information) ይሠጣል።
ለእሴት ትንተና የሚረዱ የመረጃ ምንጮች፡- የታተሙ ወይም ያልታተሙ ጽሁፎች፤ የዳሰሳ ጥናቶች፤ የቡድን
13 | P a g e
ውይይቶች፤ የምርምር ዉጤቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ለእያንዳንዱ ተግባራት የእሴት ትንተና ማከናወን ያለብን ሲሆን ይህም ለውጥ የሚያስፈልጋቸውን ተግባራት
በመለየት የደንበኞች ወይም ተጠቃሚዎች ፍላጎት ማርካት ያስችላል፡፡
ማነፃፀሪያ ዘዴዎች
በአጠቃላይ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማቀናጀት የእሴት ትንተና ንፅፅር ከዚህ በታች በቀረቡት ዘዴዎች
ማከናወን ይቻላል፡፡
ሀ. አራቱ መለኪያዎች (የምርት መጠን፣ ጥራት፣ ወጪ እና ጊዜ)
ለ. የመስመር ስዕላዊ መግለጫ (Line Graph)
ሐ. በወጪና ገቢ ትንተና
ክፍተት መለየት

ክፍተት ማለት፦ የተሟላ ወይም ፍጹም የአሰራር ዘዴ እንዳይኖር የገታዉ ወይም እንከን ያለዉ የአሰራር ዘዴ
ማለት ሲሆን በዚህ ማንዋል አገላለጽ ግን በነባሩ አሠራር (AS IS) እና በምርጡ አሠራር (Benchmark)
መካከል ያለው ልዩነት ማለት ነው፡፡ ይህም በቀጥታ ከቴክኖሎጂ ክፍተት ጋር የተያያዘ ሆኖ ቴኪኖሎጂ ስንል
አንድን ግብዓት ገበያ ወደሚፈልገው ምርት/አገልግሎት የመለወጥ ሂደት ነዉ፡፡

የእሴት ሰንሰለት ትንተና ክፍተቶችን ለመለየት የተቀመጡ ክፍተት መለያዎችና ትርጓሚያቸዉ፡፡

 የአብይ-ሰንሰለት ክፍተት (Main Chain Gap)፡- ቀይ ቀስት ሳጥን በመጠቀም የምንገልጸዉ


የሰንሰለት ክፍተት ነዉ፡፡
 ንዑስ-ሰንሰለት ክፍተት (Sub-Chain Gap)፡-ይህ ክፍተት በቢጫ ሳጥን በመጠቀም የምንገልጸዉ
ሰንሰለት ነዉ፡፡
 የተበላሹ አሠራሮች ክፍተት ( Critically miss-Managed Approach)፡- ይህ ክፍተት ደግሞ
በአረንጓዴ ሳጥን የሚገለፅ ሲሆን በነባሩ አሠራር (AS IS) እና በምርጡ አሠራር (benchmark)
ዉስጥ ያሉ የተበላሹ የአሰራር ክፍተት ነው፡፡
ቴክኖሎጂ መለየትና መመደብ /Technology Identification and Catagorization
ቴክኖሎጂ መለየት
ቴክኖሎጂ መለየት ማለት ምርጡ አሰራር (benchmark) የሚጠቀምበትን ቴክኖሎጂዎች የምንለይበት
ሂደት ነው። ነገር ግን በምርጡ አሰራር (benchmark ውስጥ የተገኘው ቴክኖሎጂ ውስብስብና አሻሚ
ከሆነ ሌሎች የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም መለየት ይቻላል፡፡
ቴክኖሎጂን መመደብ/ technology categorization/
ቴክኖሎጂ መመደብ ማለት ቴክኖሎጂን በአራት ክፍሎች የማስቀመጥ ሂደት ነዉ፡፡ እነርሱም ቁሳዊ፣

14 | P a g e
እውቀታዊ፣ ሰነዳዊ እና የአደረጃጀት ቴክኖሎጂ በሚል ይከፈላሉ፡፡

ቴክኖሎጂ ዝርዝር

ቁሳዊ-ቴክኖሎ (Techno-Ware) ይህም የሥራ መሳሪያዎችን የሚያጠቃልል ሲሆን ማሽኖችን ተሸከርካሪዎችን


መገልገያ መሳሪያዎችን ያካተቱ ቁሳዊ ቴክኖሎጂን ያጠቃልላል

እውቀታዊ-ቴክኖሎጂ (Human የሰዉን ዕዉቀት፣ ችሎታ፣ ልምድ እንዲሁም የአንድ ሰዉ ቴክኖሎጂን በስራ ላይ
ware) የማዋል፣ የመስራት፣ የመጠቀም ችሎታዎችን የሚያካትት ነዉ፡፡

ሰነዳዊ-ቴክኖሎጅ የተደራጁ መረጃዎች፣ የሰራ ሂደቶች፣ ስልት፣ ንድፎችናበተጨማሪነትም ሌሎችን እንደ


ምን፣ ለምን፣ አንዴት የሚለውን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ የቴክኖሎጂዉን
(Info ware)
መረጃ የሚይዙ ክፍሎች ናቸው (ለምሳሌ መለኪያ፣ ምስል፣ ቀመር፣ ንድፍና መመሪያ)
ያካትታል፡፡
የአደረጃጀታዊ-ቴክኖሎጂ የድርጅቱ መዋቅር (አደረጃጀት) ስራ የሚሰሩበት መንገድ እና በተጨማሪነትም የስራ
ፍሰቶች እና ክፍሎች ለምሳሌ እንደ አፈር መመርመሪያ ቤተ-ሙከራ፣ የምግብ
(Orga-ware)
ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ያካትታል፡፡

የዘርፎች ትስስር

ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ችግር ፈች የእሴት ሰንሰለት ትንተና ለማከናወን የዘርፎች ባለቤትነትና ተሳትፎ
እጅግ ወሳኝ በመሆኑና ይህም ውጤት ሊገኝ የሚችለው በዘርፎች የላቀ የእርስ በእርስ ትስስርና ግንኙነት ነው፡፡

ማረጋገጥ

ማንኛዉም የእሴት ሰንሰለት ትንተና ሰነድ ከተጠናቀቀ በኋላ ዘርፉን በሚመራዉ አካል መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ይህ
የሚከናወነው ዘርፉ ውስጥ በሚገኙ አካላት ማለትም ቴክኒካል ቡድን ሲሆን የሚያረጋግጠውም ሰነዱ ሙሉ መረጃ
መያዙን፤ በምርት/አገልግሎት ያሉ ችግሮችን/ ክፍተቶችን የያዘ መሆኑን፤ ለችግሮች የተለዩት ቴክኖሎጂዎች አግባብነት
እንዲሁም የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በመገምገም የማረጋገጥና የማፅደቅ ሥራ እንደ ዘርፍ የሚሠራ ይሆናል፡፡

ክትትልና ግምገማ

የእሴት ሠንሰለት ትንተና ለምርት/አገልግሎት ተሰርቶ ወደ ትግበራ ከተገባ በኃላ ያመጣው ለውጥ በክትትልና ግምገማ
ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ሲፈታተኑ የነበሩ ክፍተቶች በተለየውና በተሸጋገረዉ ቴኪኖሎጂ የመጣው
አወንታዊ/አሉታዊ ለውጥ በተሰራዉ የእሴት ሰንሰለት ትንተና ላይ ክትትልእና ግምገማ ይደረጋል፡፡ ከምርጡ አሠራር
(Benchmark) ላይ የተለየውን ቴክኖሎጂ በመቅዳትና በማሸጋገር የመጣውን ለውጥ መለካት ስለሚያስፈልግ በከፍተኛ
ትኩረትና ጥንቃቄ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ክትትልና ግምገማዉ ሥራው የሚሰራዉ መቶ ፐርሰንት የቴክኖሎጂ ቅጅ ሽግግር

15 | P a g e
ማንዋል መሰረት ነው፡፡

የፈፃሚዎቹና የባለ ድርሻ አካላት ሚና

ፈፃሚዎች

በቀጥታ የእሴት ሰንሰለቱን ሥራ ላይ የሚሳተፉ አካላት ናቸዉ፡፡

ባለድርሻ አካላት

እሴት ሰንሰለቱን ለመስራት አጋዥ አካላት ናቸዉ፡፡

የዘርፍፎች እና ንዑስ-ዘርፎች

የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች

ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት

 ፌደራል ደረጃ
 በክልል ደረጃ
የዞን/ወረዳ/ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች

የቴ/ሙ/ስ/ተቋማት

 ዲን/የኢንዱስትሪ ኤክቴንሽን ምክትል ዲን


 አሰልጣኝ
ኢንዱስትሪዎች (ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ)

የባለ ድርሻ አካላት ሚና

16 | P a g e
የቴክኖሎጂ ቅጅ እና ሽግግር

ቴክኖሎጂ ምንድን ነው?

ቴክኖሎጂ፡- ማለት በቀላሉ አሠራር ገበያ ላይ አንድን ግብአት ወይም ሊውል ወደ ሚችል ምርት/አገልግሎት የመለወጥ
ሂደት ነው፡፡

የተለያዩ መዝገበ ቃላት ቴክኖሎጂን በተለያዩ አስተሳሰቦች የተረጎሙት ቢሆንም በቴ/ሙ/ስ ስትራቴጂ መሠረት
ቴክኖሎጂ ማለት አንድ አዲስ እሴት በመፍጠሩ ወይም በመጨመሩ ምክንያት ተጠቃሚዎች ወይም ደንበኞች ከሌሎች
አብልጠው በፍላጎት ሊገዙት የሚችሉት ቁስ፣ ማምረቻ መሳሪያ፣ አሰራር ወይም አገልግሎት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡

ቴክኖሎጂን በይበልጥ ለመረዳት አንዱ መንገድ አምራች ድርጅቶች የሚፈልጉትን ቴክኖሎጂዎች በሁለት ዋና ዋና
ክፍሎች ማየት ያስፈልጋል፡፡

ሁለቱ የቴክኖሎጂ አይነቶች

የምርት/አገልግሎት ቴክኖሎጂ የምርት ቴክኖሎጂ የሚባለው ሰዎች በነፍስ ወከፍ የሚጠቀሙበት (consume)
የሚያደርጉት እንደ ምግብ፤ ሸቀጣ ሸቀጦች፤ ኬሚካል ፕሮሰሰኒንግና የመሳሰሉት።

የማምረቻ/አሰራር ቴክኖሎጂ የምርት ቴክኖሎጂዎችን ለማምረት የሚውሉ መሳሪያዎች ወይም ማሽኖች ናቸው፡፡

ቴክኖሎጂዎች በየሙያ ዘርፎቹ ሲተረጎሙ የምርት ቴክኖሎጂ የአገልግሎት ቴክኖሎጂ ሊሆኑ የሚችል ሲሆን
የማምረቻ ቴክኖሎጂ ደግሞ በአሰራር ቴክኖሎጂ ሊተካ ይችላል፡፡

ቴክኖሎጂን በይበልጥ ለመረዳት አንዱ መንገድ አምራች ድርጅቶች የሚፈልጓቸውን ቴክኖሎጂዎች በአራት ዋና
ዋና ክፍሎች በማየት ነው፡-

1. ቁሳዊ ቴክኖሎጅ Technoware ቁስን ያካተቱ መሳሪያዎች፡- የተለያዩ መሳሪያዎች፡፡

2. ዕውቀታዊ ቴክኖሎጅ Humanware ሰውን ያካተቱ ችሎታዎች፡- ሙያ፤ ዕውቀት፤ ችሎታ፡፡

3. ሠነዳዊ ቴክኖሎጅ Inforware መዝገብን ያካተተ ሰነዳዊ ማስረጃዎች፡- ደረጃዎች፤ የንድፍ


ዝርዝሮች፤ ያሰራርና የጥገና ማንዋሎች፡፡

4. ድርጊታዊ ቴክኖሎጂ Orgaware ተቋምን ያካተተ የአደረጃጀት ማዕቀፎች፡- ዘዴዎች፤ ቴክኒኮች፤


ግንኙነቶችና ልምዶች፡፡

የቴክኖሎጂ አቅም ምን ማለት ነው?

የቴክኖሎጂ አቅም ማለት ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ተስማምቶ መሄድ የሚያስችል የተቀናጀ ችሎታ ሲሆን ይህ
17 | P a g e
አቅም የሚገኘው በቴክኖሎጂአዊ የመቀበል ችሎታ ነው፡፡

የመቀበል አቅም የነባራዊ እውቀት እና የተጠናከረ ጥረት ተብሎ በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ይወሰናል፡፡

ነባራዊዉ እውቀት

አዲስ ቴክኖሎጂ (እውቀትን፣ አሰራርን፣ አደረጃጀት) ለማዋሃድና ለመጠቀም የተሻለ የመቀበል አቅም
የሚፈጥር ነው፡፡

የተጠናከረ ጥረት

የተጠናከረ ጥረት ችግሮችን ለመፍታት በጋራ የሚደረግ የተጠናከረ ኃይል ማለት ሲሆን የመቀበል አቅምን
ለመፍጠር ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

የቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት መቅዳት ምንነት

ቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት መቅዳት ማለት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነት ያላቸውን የምርት/አገልግሎት
ወይም የማምረቻ/አሰራር ቴክኖሎጂዎችን በማፈላለግ አዋጭነታቸው የተረጋገጡትን ንድፉን/አሰራሩን
በማግኘት ወይም ቴክኖሎጂውን በማግኘት አንድ በአንድ አካሎቻቸውን በመፈታታትና በመለካት
(rengineering) እና እንዲሁም በአገልግሎትና አሰራር ዘርፍ ያሉትን በመፈተሽ አስመስሎ በመቅዳት ለአገር
ውስጥ ገበያ ማቅረብ ማለት ነው፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ሊቀዱ የማይችሉ የቴክኖሎጂው አካላት ስለሚኖሩ እነኚህን ስታንዳርድ የሆኑ እቃዎች
በቀጥታ ከገበያ ላይ ገዝቶ መጠቀም የሚቻል ሲሆን በዚህ መልኩ የተቀዳ ቴክኖሎጂ ከኦርጂናል ቴክኖሎጂው
በጥራት፣ “በቀለም”፣ በአሰራርና በውጤታማነቱ /functionality/ እስካልተለየ ድረስ መቶ ፐርሰንት ተቀድቷል

18 | P a g e
ማለት ይቻላል፡፡

ቴክኖሎጂን መቶ ፐርሰንት የመቅዳት ዝርዝር አላማ

የልማት ፕሮግራሞችን ፍላጎት በማገናዘብ ሌሎች ያፈለቁትን ቴክኖሎጂዎች ፈጥኖ በመኮረጅ ሀብት አፍርቶ
አቅም ለመገንባት፡፡

በተገነባ አቅምና በፈራ ሀብት የተኮረጀውን ቴክኖሎጂ በማላመድ በሂደት በማሻሻል ተጨማሪ ሀብት
ለመፍጠር፡፡

ደረጃ በደረጃ በዩኒቨርስቲ፣ በግል ኩባንያዎችና በመንግስት የምርምር ተቋማት አቅምን በመፍጠር፣ በምርምር
ሀብት ለመፍጠር፡፡

አሰልጣኞችም ሆነ ሰልጣኞች በስፋት በቴክኖሎጂ የመቅዳት ሂደት ውሰጥ በማካፈል አቅምን በመፍጠር
ፕሮጀክትን መሰረት ባደረገ ስልጠናን እንዲያጎለብቱ ማድረግ፡፡

በሂደት በርካታ ተመራማሪዎችና ቴክኖሎጂስቶችን በማፍራት የግል ኩባንያዎች ለሚያቋቁሟቸው የምርምር


ተቋማት የሚሆን የሰው ኃይል በጥራትና በቁጥር ለማፍራት፡፡

ቴክኖሎጂን መቶ ፐርሰንት መቅዳትና ማሸጋገር የቅደም ተከተል የአሠራር ሂደት

የተመረጡ አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን በተሳካ ሁኔታ ለማሸጋገር ከታች በተቀመጠው የሽግግር ስርዓት (high
Level map) መሰረት ከዘርፍ እሴት ሰንሰለት ትንተና የተለዩትን ቴክኖሎጂዎች አዋጭነታቸውን በማረጋገጥ፣
ናሙና አምርቶና ፈትሾ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ አሰራሮችን ፈትሾ እስከ ሽግግር ድረስ የቴክኖሎጂ
ሽግግር ሂደቶች የሚያሳይ ነው፡፡

ይህንን ሂደት በትክክል መተግበር ከተቻለ የዘርፉን (ጥ/አ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የአ/መ ኢንተርፕራይዞች)
ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጡ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት ማቅረብ/ማሸጋገር ይቻላል፡፡

19 | P a g e
25 | P a g e
ቴክኖሎጂ መቶ ፐርሰንት የመቅዳትና ማሸጋገር ሂደቶች

ከዘርፍ ጋር በመሆን በተዘጋጀ እሴት ሰንሰለት የተለየ መሆኑንና በቴክኖሎጂ ዓይነቶች (humanware,
technoware, infoware and orgaware) ተለይቶ የተቀመጠ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡

የተለየውን ቴክኖሎጂ በጥልቀት በመረዳትና በመተንተን የአዋጭነት ትንተና ማከናወን፡፡

ኢኮኖሚክ አዋጭነት

ቴክኒካል አዋጪነት

አካባቢ ደህንነት አዋጭነት

ቴክኖሎጂን ማቀብ (ማከማቸት)

በኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ ያለ የትኩረት ኢንዱስትሪን የዕሴት ሰንሰለት ትንተና ያገናዘበ ምርጥ ቴክኖሎጂን
ለማሸጋገር ሌሎች ደረጃውን ጠብቀው እንዲሰሩት ለማድረግ ቴክኖሎጂውን ማቀብ (ማከማቸት) ያስፈልጋል፡፡
ቴክኖሎጂ በማቀብ ሂደት ውስጥ የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ንድፍ (አሰራር ሂደት) ማዘጋጀትና ናሙና አምርቶ
ተከታታይ ፍተሻ ማካሄድ ዋና ዋና ሥራዎቹ ናቸው፡፡ የቴክኖሎጂ ተቋማት ቴክኖሎጂ ማቀብ ዋና ስራቸው
በመሆኑ በሳይንሳዊ ትንተናና መረጃ ተመስርተው የቴክኖሎጂ ንድፍ ማዘጋጀት ይጠበቃል፡፡ በተዘጋጀው ንድፍ
መሠረት ብቃት ያለው ናሙና ማዘጋጀት፣ የተዘጋጀውን ናሙና በተገቢው ቦታና የሥራ ምህዳር ደረጃውን ጠብቆ
ለመመረቱ በተከታታይና ለበቂ ጊዜ የፍተሻ ሥራ ማካሄድ እና በፍተሻ በተገኙ መረጃዎች ላይ በመመርኮዝ
ማስተካከያ/ማሻሻያ አድርጎ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የተፈላጊ ቴክኖሎጂ መረጃ ምንጮች

የመቶ ፐርሰንት ቅጂውን የተሳካ ለማድረግ ከላይ የጠቀስናቸውን ስለሚቀዳው ቴክኖሎጂ የሚገልጹ ሰነዶች
በእጃችን ሊገቡ ይገባል፡፡ እነዚህ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ካሟላን መሰረታዊ የሆነውንና የመጀመሪያውን የቅጂ
ምእራፍ ስራን እንዳሳካን ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ እነዚህ መረጃዎችን ከየት እንደምናገኛቸው ማወቅ አብይ
ጎዳያችን ይሆናል፡፡

ከታች ቀጥለው የተገለጹት ምንጮች ስለሚቀዳው ቴክኖሎጂ መረጃ ልናገኝ የምንችልባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

 ከኤሌክተሮኒክስ የመረጃ ምንጭ (google.com/patents, uspat.gov)


 ከዩንቨርሲቲዎች እና ከጥናትና ምርምር ተቋማት
 ከአእምሯዊ ንብረት ጠባቂ/ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት
 በአካባቢያችን ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ወይም በእጅ ካለ ቁሳዊ/አሰራር ቴክኖሎጂ
26 | P a g e
 ከእጅ ባለ ሰነዳዊ ቴክኖሎጂ
የቴክኖሎጂ ምንጮች

ለተመረጠው ቴክኖሎጂ ንድፍ (የአሰራር ሂደት) ማዘጋጀት

የተመረጠውን ቴክኖሎጂ አብዢዎች እንዲያመርቱት/አገልግሎት እንዲሰጡና እንዲያሰፉት የሚያስችል ወጥ


የሆነ ሁሉም ሰው በሚረዳው መልክ የአሠራር ንድፍ ድሮዊንግ/ማኑዋል እንደ ሙያ ዘርፉ የተዘጋጀ ሰነድ
ሊኖረው ይገባል። በዚህም መሠረት የድሮዊንግ ንድፍ ስራ እና የአሠራር ማንዋል ንድፍ እንደ ሙያ አይነቱና እነደ
አስፈላጊነቱ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ይገባል፡፡ የንድፍ አዘገጃጀት ይዘቱም ከዚህ በታች በተገለፀው አግባብ
የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

የድሮዊንግ ንድፍ ሥራ ሲባል አንድን ቴክኖሎጂ በወጥነት ደረጃውን ጠብቆ እንዲባዛ ለማገዝ የቴክኖሎጂ
ልኬትና ምስል (Detail Drawing, sub-assembly, full Assembly Drawing exploded view in
Isometric view)፤ የአመራረትና አገጣጠም ሂደት (manufacturing Method Description)፤
የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ዝርዝር ከነመገለጫቸው (specification) የያዘ ሠነድ ሆኖ የሚዘጋጅ ሲሆን
የአሠራር ንድፍ ማንዋል ደግሞ በእሴት ሠንሠለት የተለየውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ሊሞላ የሚችል
በአሠራር/አገልግሎት ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር የሚያስችል ከመነሻው እስከ ምርት ሥራው/ አገልገሎት
አሠጣጥ ድረስ የሚያስፈልገውን የሥራ/ውህድ ቅደም ተከተል፤ አስፈላጊ የጥሬ እቃ ዝርዝር ከነመገለጫቸው
(Specification)፤ ቁሳቁስና መሳሪያዎችን ያከተተ ሠነድ ሆኖ ይዘጋጃል፡፡

27 | P a g e
የወጪ ተመን ማዘጋጀት

 የጉልበት ወጪ (Labour Cost)


 የጥሬ እቃ ወጪ (Raw Material Cost)
 የተለያዩ ወጪዎች (Other expences)
በተዘጋጀው ንድፍ መሰረት የቴክኖሎጂውን ናሙና ማምረት

የተቀዳውን ቴክኖሎጂ ናሙና ፍተሻ ማከናወን

በፍተሻ የተረጋገጠውን ቴክኖሎጂ ማሸጋገር

 የአብዢዎችን አቅም ክፍተት መለየት


 አብዢዎችን ማብቃት
 የፋይዳ ዳሰሳ (Impact Assessment)

28 | P a g e
የአእምሮአዊ ንብረት (INTELLECTUAL PROPERTY)
ህገ-መንግስታዊ መሰረቱ

የአእምሮአዊ ንብረት ከድሮ ጀምሮ ሮማውያን የግለሰብ መብት (personal right) እና ግዙፍ መብት (real
right) በሚል ከሚመድቧቸው የንብረት መብቶች በተጨማሪ ለየት ያለ መብት ሲሆን ስያሜውን በተመለከተ
የተለያዩ ፀሓፍት የተለያየ አጠራር ሲጠቀሙ ይስተዋላል፡፡

ለዚህም አንዳንዶቹ ግዙፍነት የሌለው መብት (incorporeal right) ሌሎቹ ደግሞ የአእምሮ ንብረት
(inteiiectual property) በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህ ግን ምንነቱን የሚቀይር ባለመሆኑ በይዘት አንድ
(semantic) ነው፡፡ የአእምሮ ንብረት መብት ግዙፍነት የሌለው የንብረት መብት ሲሆን  አገሮች ይህን የንብረት
መብት ከሚከተሉት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲ በመነሳት በህገ-መንግስታቸውና ከዚያ በታች ባሉ
ህጐቻቸው ጥበቃ በመሰጠት በልማት መሳሪያነት ሲገለገሉበት የሚገኝ የንብረት መብት ነው፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.
ህገ መንግስት ለአእምሮ ንብረት  የተሰጠው የህግ ማእቀፍ ስንመለከት በአንቀፅ 51(19) ላይ "የፈጠራና
የድርሰት መብቶችን ይፈቅዳል፣ ይጠብቃል" ሲል መንግስት ለአእምሮ ንብረት መብት መከበር የሚኖረውን
ኃላፊነት መሰረት በማድረግ ሲደነግግ በአንቀፅ 77(5) ላይ ደግሞ "የፈጠራና የኪነጥበብ መብቶችን
ያስጠብቃል" በማለት ይደነግጋል፡፡ ከነዚህ ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው በአገራችን ኪነ
ጥበብ፤ ድርሰትና የቴክኖሎጂ እድገት ከፍ እንዲል በማድረግ ዜጐች በአገሪቱ ማሕበረ ኢኮኖሚ ለውጥና
እድገት ላይ ያላቸውን ሚና ከወትሮው በተሻለ መንገድ እንዲጫወቱ በማስቻል በሰፊው የልማት ተሳታፊና
ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ከፍ ብሎ ከተጠቀሱት የህገ-መንግስት ድንጋጌዎች ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ የአእምሮ ንብረት


መብት በፈጠራ (patent) እና በኪነ-ጥበብ ስራ ወይም ድርሰት (copy right) ብቻ የታጠረ የንብረት መብት
ነውን? የሚል ሲሆን የአእምሮ ንብረት መብት ከፈጠራ መብት (patent) እና የድርሰትና ወይም የኪነ ጥበብ
ንብረት መብት (copy right) በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ንድፍ (Industrial design)፣ የንግድ ምልክትና
(Trade marks)፣ የእፅዋት አዳቃዮች መብት (plant breeders right)  የሚያካትት በመሆኑ የህገ-
መንግስቱ ህጋዊ ሽፋን ጠበብ ያለ ነው ብሎ መረዳት የሚቻል ቢሆንም የነዚህ መብቶች ጥበቃ ከህገ-
መንግስቱ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች በመነጩ ሌሎች ህጐች የህግ ሽፋንና የአእምሮ
ንብረት ባለቤትነት መብቶች ጥበቃ የተደረገላቸው በመሆኑ የዜጐች መብቶች ለአደጋ የተጋለጡበት ሁኔታ
በአገሪቱ የፍትህ ስርዓት የለም ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡

የአእምሮአዊ ንብረት መብት ጥበቃ ከሌሎች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህግ-መንግስት ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይም ነፃ

29 | P a g e
ሃሳብ የመያዝና የመግለፅ ዲሞክራሲያዊ መብት አንፃር በአንቀፅ  29(2) ‘’ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ
ገብነት ሃሳቡን የመግለፅ ነፃነት አለው። ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት
በቃልም ሆነ በፅሑፍ ወይም በህትመት፣ በስነ-ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ
ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሃሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጫት ነፃነቶችን ያካትታል፡፡’’ በማለት
ስለሚደነግግ ዜጎች ይህን መብታቸውን ተጠቅመው ለሚሰሩትና ለሚያወጡት የአእምሮ ንብረት መብት ህጋዊ
ጥበቃ አግኝተው የልማቱ ተዋናይ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ነው። መንግስትም በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 89(1)
መሰረት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሃገሪቱ የተጠራቀመ ዕውቀትና ሀብት ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት መንገድ
የመቀየስ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ ይህን ህገ መንግስታዊ ኢኮኖሚያዊ መርህ ተግባራዊ ለማድረግ
የሚያስችሉ በርካታ አዋጆችን አውጥቶ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ የአእምሮ ንብረት መብትን የሚያስጠብቅ
አሰራርና አደረጃጀት ዘርግቶ ለዘላቂ ልማት ስትራተጂ ስኬት በዚህ መስክ ሊገኝ የሚችለውን ውጤት
ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡

በመሆኑም የአእምሮ ንብረት መብት መረጋገጥና አለመረጋገጥ በአንድ አገር የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንዲሁም
ዲሞክራሲ ስርአት እድገት ያለው ፋይዳን መሰረት በማድረግ የህግ ሽፋን የሚሰጠው የንብረት መብት
እንደመሆኑ መጠን በፍትህ አካላት ዘንድም በየጊዜው የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች በአግባቡ በማስተናገድ በህገ
-መንግስቱ አንቀፅ 13 (1) የተጣለባቸውን የማክበር እና የማስከበር ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያስችላቸው
ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

የአእምሮአዊ ንብረት ዓይነቶች

የፈጠራ ሥራ (patent)

የፈጠራ ሥራ ማለት ምን ማለት ነው? የአእምሮ ንብረት ለማስጠበቅና በስርዓቱ እንዲመራ ለማድረግ የወጣው
አዋጅ ቁጥር 123/1987 በአንቀፅ 2 (5) ላይ "ፓተንት ማለት የፈጠራ ሥራን ለማስጠበቅ የሚሰጥ መብት
ሲሆን የፈጠራ ስራውን ከአንድ ምርት ወይም የምርት ሂደት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡" በማለት ሲተረጉመው
በአንቀፅ 2 (3) ላይ ደግሞ "ፈጠራ ማለት በቴክኖሎጂ መስክ ለአንድ የተወሰነ ችግር ተግባራዊ መፍትሄ
ለመስጠት የሚያስችል የፈጠራ ሠራተኛ ሃሳብ ነው" በማለት የፈጠራን ምንነት ይገልፃል፡፡

Wikipedia, the free encyclopedia በድረ ገፁ ላይ የፈጠራ ሥራን (patent) እምብዛም በአዋጁ
ከተሰጠው ትርጉም ባልተለየ መልኩ እንዲህ ሲል ተረጉሞት እናገኘዋለን፡፡

The term patent usually refers to a right granted to any one who invents or discovers
process, machine, article of manufacture, or composition of matters, or any new and
useful improvement there of.
30 | P a g e
ከነዚህ የተቀራረቡ ትርጓሜዎች መገንዘብ የሚቻለው የፈጠራ መብት (patent right) የሚመነጨው አንድ
ሰው በአእምሮው ከሚፈጥረው አዲስና ጠቃሚ ምርት ወይም ግኝትና አዲስ ባይሆንም በሌላ ሰው ፈጠራ
ተሰርቶ በስራ ላይ የቆየን ነገር በማሻሻል የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችለው ተጨማሪ የፈጠራ ስራ
በማከልና በማሻሻል እንደሆነ ነው፡፡  በመርህ ደረጃ የፈጠራ መብት አዲስ በመፍጠር ወይም ያለውን
በማሻሻል ሊገኝ የሚችል የአእምሮ ንብረት መብት እንደሆነ መገንዘብ ቢቻልም የአገራችንን ህግ ያየን እንደሆነ
ግን  የዚህ ዓይነት መብት የሚሰጠው በአዋጁ አንቀፅ 40(1) መሰረት ለአገልግሎት ሞዴል (ለአነስተኛ
የፈጠራ ስራ) ካልሆነ በስተቀር በፓተንት መብትነት አንድን ቀደም ሲል የነበረን የፈጠራ ስራ አሻሽሎ በመስራት
 የአእምሮ ንብረት መብት ማግኘት እንደሚቻል የሚደነግግ አይደለም፡፡ የዚህ ዓይነት ልዩነት በብዙ አገሮች
ህግም ያለ ነው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ የፓተንት ህግ አንድን ሰው ፈጠራ አሻሽሎ መስራት እንደ መብት ጥሰት
ተወስዶ የፍ/ብሄር ተጠያቂነትን የሚስከትል ሲሆን በአውስትራልያ ህግ ተጨማሪ የፈጠራ ሥራ መስራት
ማለትም አሻሽሎ ማውጣት የተፈቀደ ነው፡፡

በአገራችን የፈጠራ ሥራን ለማስጠበቅ የወጣው አዋጅ ቁጥር 123/1987 አላማዎችን ስንመለከት የፈጠራ
ሥራ አእምሯዊ ንብረት መብት የአንድን ሰው በፈጠራው ስራ መገልገልን (Use or practice) መብት
የሚጐናፀፍ በመሆኑ በዋና አላማነት ይዞት የሚነሳው ሌሎችን ያለ ባለመብቱ ፈቃድ እንዳይገለገሉበት
መከልከል (excluding others) ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፡-

ለአገር ውስጥ ፈጣሪዎች (local inventors) ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የአገሪቱን የቴክኖሎጂ እድገት
በማፋጠን የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲንና ስትራተጂን ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ስራን የመስራት አላማ
ያለው ነው።

ከአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች በተጨማሪ ከውጪው ዓለም የቴክሎጂ ሽግግር እንዲኖር የሚያስችል
ምቹ ሁኔታን በመፍጠር አገሪቱ ከዚህ ተጠቃሚ እንድትሆን በማድረግ ዘርፉ ለሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ልማትና
መልካም አስተዳደር ስኬት የበኩሉን ሚና እንዲጫወት የማስቻል አላማን በመያዝ የወጣ ህግ ለመሆኑ
ከአዋጁ መግቢያና ከዝርዝር ህጐቹ መረዳት እንችላለን፡፡ በመሆኑም የአገር ውስጥ ፈጠራን በዋና የልማት
መሳሪያነት በመጠቀም ከውጪው ዓለም መውሰድ ያለብንን ተሞክሮ መበውሰድ ጠንካራ፣ ዘላቂና ተወዳዳሪ
ኢኮኖሚን መገንባት መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ እድገት ማምጣት እንደ ግብ የያዘም ነው፡፡

የፓተንት መብት መጠበቅ አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ አንስተን ስናይ
አገሮች የፓተንት መብት  እንዲጠበቅ የሚያደርጉባቸው ምክንያቶች በርካታ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹን ወሰደን ያየን
እንደሆነ:-

ለኢኮኖሚ እድገት ያለው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ ከዚህ ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ፤

31 | P a g e
መብቱ በመጠበቁ ሰዎች ፈጠራቸውን እንዲያወጡና ህዝቡ ከዚህ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል፤

ጥበቃ የሚሰጣቸውና የማይሰጣቸው የፈጠራ ሥራዎች

በመቀጠል የፈጠራ ሥራ መብት (patent right) የሚሰጠው እንዴት ላለ ፈጠራ ነው? የሚለውን ስናይ ይህ
መብት ለሁሉም እንደማይሰጥ አዋጁ በአንቀፅ 3 ላይ በዝርዝርና ለይቶ የሚያሳይ መልኩ የደነገገውን ወስደን
ማየት ጠቃሚ ነው፡፡

አንድ የፈጠራ ሥራ የህግ ጥበቃ እንዲያገኝ ከተፈለገ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት
ይጠበቅበታል፡-

አዲስነት- አንድ የፈጠራ ሥራ አዲስ ነው የሚባለው በቀደምት ጥበብ ያልተሸፈነ ሲሆን ነው፡፡ ቀደምት ጥበብ
ማለት የፈጠራ ስራውን በተመለከተ ማመልከቻ ከገባበት ወይም እንደአግባቡ ከቀዳሚው ቀን በፊት
በየትኛውም የአለም ክፍል በተጨባጭ በሚታይ ህትመት ወይም በቃል ወይም ጥቅም ላይ በማዋል ወይም
በሌላ ማናቸውም መንገድ የተገለፀ ነገርን ያጠቃልላል (አንቀፅ 3(2))

ፈጠራዊ ብቃት- አንድ የፈጠራ ስራ ፈጠራዊ ብቃት አለው የሚባለው ከሚመለከታቸው ጋር አግባብነት ካለው
ቀደምት ጥበብ አንፃር ሲታይ በመስኩ ተራ እውቀት ላለው ሰው ግልፅ ያልሆነ እንደሆነ ነው፡፡ (አንቀፅ 3(4))

ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት- አንድ የፈጠራ ስራ ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት አለው የሚባለው በዕዳ ጥበብ፣
በግብርና፣ በማህበራዊ አገልግሎቶችና ሌላ ማናቸውም መስክ ሊሰራ ወይም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል
ሲሆን ነው (አንቀፅ 3(5))

በመሆኑም አንድ የፈጠራ ሥራ የህግ ጥበቃ አግኝቶ ፈጣሪ ነኝ የሚለው ሰውም በመብቱ ተጠቃሚ ለመሆን
ሥራው እነዚህን ከፍ ብሎ የተዘረዘሩትን ህጋዊ መስፈርቶች (legal requirements) ማሟላት የግድ ይላል፡፡

የፈጠራ ሥራ ጥበቃ የማይደርግላቸው ስራዎች በአዋጁ አንቀፅ 4 ላይ ተዘርዝረው ያሉት ሲሆኑ እነሱም፡-

የህዝቡን ሰላም ወይም ስነ-ምግባር የሚፃረሩ ፈጠራዎች፤

የእፅዋት ወይም የእንስሳት ዓይነቶች ወይም የእፅዋት ወይም የእንስሳት ውጤቶችን ለማስገኘት በስነ-ህይወት
ዘርፍ የሚከናወኑ ሥራዎች፤

ጨዋታዎችን ለማካሄድ ወይም የንግድና የኢንዱስትሪ ሥራዎችን ለማከናወን የተዘጋጁ ስልቶች፣ ደንቦች፣
ዜዴዎች እንዲሁም የኮምፒዩተር ፕሮግራም፤

ግኝቶች፣ ሳይንሳዊ ቲዎሪዎች (theories) እና የቅመራ ዘዴዎች፤ (mathematical methods)

32 | P a g e
ሰውን ወይም እንስሳትን በቀዶ ጥገና ወይም በቴራፒ ህክምና ዘዴዎች ለማከም እንዲሁም የሰዎችን ወይም
እንስሳትን በሽታ ለመመርመር የሚረዱ ዘዴዎች የፈጠራ መብት ጥበቃ የማይሰጣቸው ክንዋኔዎች ተደርገው
ነው የሚወሰዱት፡፡ ይህ ማለት ግን የሰዎችን ወይም የእስሳትን በሽታ ለመመርመር የሚረዱ ዘዴዎችን በጥቅም
ላይ ለማዋል የሚያገለግሉ ውጤቶች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ (አንቀፅ 4(2)

ስለዚህ ህጉ ለፈጠራ ስራ የህግ ጥበቃ ለመስጠትም ላለመስጠትም በምክያነት የሚገለገለው የፈጠራ ስራው
የህዝብን ጥቅም ያስጠብቃል ወይስ አያስጠብቅም? በግል የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት ሊያዝ የሚችል ነው
ወይስ አይደለም? የሚሉትን መስፈርቶች  የሚጠቀም ነው፡፡

የፈጠራ ሥራ መብትና ይዘት

የፓተንቱ ይዘት ባለቤቱ በፈጠራው ላይ ያለውን ብቸኛ መብት የሚያረጋግጥና ሌሎች በደንብ ቁጥር 12/89
አንቀፅ 14 እና ቀጥሎ ባሉ ድንጋጌዎች መሰረት ዝርዝር ነጥቦችን የያዘ መሆን አለበት፡፡ (የአዋጁ አንቀፅ
15) አንድን የፈጠራ ስራ የስራ የፓተንት ባለ መብት የተሰጠውን ፈጠራ ለመፈብረክ ወይም በሱ ለመገልገል
ወይም በሌላ ማናቸውም መንገድ ለመጠቀም መብት ይኖረዋል፡፡ ሶስተኛ ወገኖችን የባለ ፓተንቱ ፈቃድ ሳያገኙ
ፓተንት በተሰጠው ፈጠራ ለመፈብረክ አይችሉም፡፡ ሶስተኛ ወገኖች ተጠያቂ ሊሆኑ የማይችሉት የፓተንት
መብት (patent right) ለፈጣሪው የተሰጠው ከሆነ ብቻ ነው፡፡ (አንቀፅ 22 (1) እና 23) ይህ ሰው ያለእርሱ
ፈቃድ ፓተንቱን የሚፃረር ወይም መብቱን ሊነካ የሚችል ድርጊትን በሚፈፅም ማናቸውም ሰው ላይ በፍ/ቤት
ክስ የመመስረት መብት አለው፡፡ መብቱ ያልተረጋገጠለት ሰው የኔ ፈጠራ ሥራ ነው በሚል ብቻ ግን በሦስተኛ
ወገኖች ላይ  ክስ ማቅረብ አይችልም፡፡ የፈጠራው ባለቤት የፓተንት መብት የማግኘትና በሦስተኛ ወገኖች
ሊመጣ ከሚችል መጣስ ህጋዊ ጥበቃ እንደሚደረግለት ሁሉ ግዴታም ያለበት ነው፡፡ ይሄውም ባለፓተንቱ
በኢትዮጵያ ውስጥ ፈጠራውን ስራ ላይ የማዋል ወይም በርሱ ፈቃድ ሌሎች ሰዎች ፈጠራውን ስራ ላይ
እንዲያውሉ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ (አንቀፅ 27)

የፓተንት መብት የሚሰጠው እንዴት ነው? የሚለውን አንስተን ስናይ በመርህ ደረጃ መብቱ የሚሰጠው ለፈጠራ
ሰራተኛው ሲሆን የፈጠራ ስራው በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች በጋራ ሆነው አንድን የፈጠራ ስራ ካከናወኑ
የጋራ የፓተንት መብት ይኖራቸዋል፡፡ ሁለት የተለያዩ ሰዎች ተመሳሳይ የፈጠራ ሥራ ሰርተናል በማለት
በሚቀርቡበት ጊዜ የፈጠራው ባለቤት የሚሆነው አስቀድሞ ማመልከቻ ያስገባው ነው። (አንቀፅ 11 (1))
ይሄውም ህጉ first to file rule and right of priority በመርህ ደረጃ የሚከተል ነው፡፡ ፓተንት
የሚሰጠውም በአዋጁ አንቀፅ 14 መሰረት ኮሚሽኑ ፓተንት ስለመስጠቱ በኦፊሴል ጋዜጣ በማሳወቅ፤
የፓተንቱን ሰርትፍኬትና የፓተንቱን ቅጂ ለአመልካቹ በመስጠት፤ በመመዝገብና ክፍያ ለሚያስፈፅም አካል
የፓተንቱን ቅጂ በመስጠት ነው፡፡ የፓተንቱ ይዘትም ባለፓተንቱ በፈጠራው ላይ ያለውን ብቸኛ መብት

33 | P a g e
የሚያረጋግጥና በደንቡ መሰረት ሌሎች ነገሮችን ያካተተ ይሆናል። (አንቀፅ 15)  በኢትዮጵያ የፓተንት መብት
የሚሰጠው ለተፈጥሮና የህግ ሰው ሲሆን በአሜሪካ አገር የዚህ ዓይነት መብት የሚሰጠው ለተፈጥሮ ሰው
ብቻ  ነው፡፡  

በእኛ አገር የአሰጣጥ ስነ-ስርአቱ ምን ይመስላል? የሚለውን ስንመለከት ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር አንድ
ሰው ተቀጥሮ በሚሰራበት ጊዜ ለሚገኘው የፈጠራ ስራ የፓተንት መብቱ የሚሰጠው ለቀጣሪው ነው። የቅጥሩ
ሁኔታ ከፈጠራ ስራው ግንኙነት የሌላው ወይም ከቅጥር ወይም የአገልግሎት ውል ጋር ግንኙነት በሌለው
መንገድና የቀጣሪው ወይም የአሰሪውን ሃብት፣ መረጃ፣ ማምረቻ ወይም የአገልግሎት መስጫ ማቴሪያል
ወይም መሳርያ ሳይጠቀም የፈጠራ ስራውን ያከናወነው ከሆነ ግን የፓተንት መብቱ የሚሰጠው ለፈጣሪው
ወይም ለተቀጣሪው ወይም ለአገልግሎት ሰጪው ነው፡፡ ከፍ ብሎ የተጠቀሱት እንዳሉ ሆነው የቀጣሪውን
መሳሪያ በመጠቀምና የተቀጣሪው የግል አስተዋፅኦ ታክሎበት ለሚገኝ የፈጠራ ስራ ተቃራኒ ስምምነት
ከሌለው በስተቀር እኩል ድርሻን መሰረት በማድረግ የሁለቱ ማለትም የቀጣሪውና የተቀጣሪው የጋራ ንብረት
ይሆንና የፓተንት መብቱ በጋራ ይሰጣል፡፡ (አንቀፅ 7) ስለዚህ የፈጠራ ስራ ባለቤትነት ይዘቱ የፈጠራውን ብቸኛ
ባለመብትነት የሚያረጋግጥ ሰነድ ሲሆን የዚህም ውጤት በሶስተኛ ወገኖች ላይ ተፈፃሚነት እንዲኖረው
በማድረግ የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት ጥበቃ እንዲያገኝ ማስቻል ነው፡፡ የፈጠራ ስራ ባለቤትነት መብት
(patent) የሚሰጠው አንድም ለፈጣሪው ለራሱ ወይም ይህን ስራ እንዲያከናውን የተቀጠረ ወይም
አገልግሎት የሚሰጥ በሆነበት ጊዜ ፓተንቱ የሚሰጠው ለቀጣሪው መሆኑንና ተቃራኒ ስምምነት ከሌለና
ለፈጠራ ስራው የሁለቱም አስተዋፅኦ ካለበት ደግሞ ፓተንቱ የሚሰጠው ለሁለቱም በጋራ ባለቤትነት
እንዲያገግል በሚያስችል አገባብ ይሆናል፡፡

የባለፓተንት መብት ገደቦች

የፓተንት መብት የአእምሮ ንብረት መብት እንደመሆኑ መጠን የፈጠራ ስራው ባለቤት በዚህ መብቱ ብቸኛ
ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ወገኖች ያለሱ ፈቃድ በዚህ የፈጠራ ሥራ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የመከልከል ውጤት
ያለው መብት (negative right) ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህ መብት በህግ ገደብ (limitation) የማይደረግበት
የንብረት መብት (monopoly right) ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ በመሆኑም በአዋጁ አንቀፅ 25 ላይ የተወሰኑ
ገደቦች ተጥሎበታል፡፡ እነዚህም፡-

ሀ. ንግድ ነክ ባልሆኑ ተግባሮች ያለፈጣሪው ፈቃድ ቢገለገሉበት በህግ አያስጠይቅም፡፡

ለ. ፓተንት የተሰጠበት ፈጠራ ለሳይንሳዊ ምርምርና ሙከራዎች ዓላማ አገልግሎት ብቻ እንዲውል


ማድረግ የተፈቀደ ነው፡፡

ሐ. በባለፓተንቱ ወይም በሱ ፈቃድ ኢትዮጵያ ውስጥ በገበያ ላይ ከዋሉ ፓተንት የተሰጣቸው ሸቀጦች
34 | P a g e
ጋር በተያያዘ መልክ የሚከናወኑ ድርጊቶች፡፡

እንዲሁም በአንቀፅ 25 (2) ላይ የህዝብን ጥቅም በተለይም የብሄራዊ ደህንነት፣ የምግብና የጤና ወይም
የሌሎች ብሄራዊ የኢኮኖሚ ዋና ዘርፎች የልማት ፍላጐት ለመጠቀም ኮሚሽኑ ያለባለፓተንቱ ፈቃድ የመንግስት
ድርጅት ወይም ኮሚሽኑ የሚሰይመው ሶስተኛ ወገን ለባለፓተንቱ ተገቢውን ክፍያ በመፈፀም ፈጠራውን
እንዲጠቀም ሊወሰን ይችላል፡፡ የካሳ ክፍያውን በሚመለከት ኮሚሽኑ በሰጠው ውሳኔ ላይ ወደ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሊባልበት ይችላል፤ ሲል ይደነግጋል፡፡

የነዚህ ድንጋጌዎች አላማ በህገ-መንግስቱ እውቅና የተሰጠውን የፈጠራ ጥበቃ በመርህ ደረጃ የባለቤትነት
መብቱ የፈጣሪው ሰው የራሱ ወይም ከአንድ በላይ በሚሆኑበት ጊዜ የጋራ እንደሆነ በመቀበል ለህዝብ
ጥቅምና አገር ደህንነት ሲባል ግን በዚህ የአእምሮ ንብረት መብት ላይ ገደብ (Limitation) ሊጣልበት
እንደሚችልና ይህም በሚሆንበት ጊዜ ባለፓተንቱ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ ነው፡፡

የፓተንት መቋረጥ፣ መተው እና መሰረዝ

የፓተንት መብት ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጥበቃ ለማግኘት የቀረበው ማመልከቻ ከተመዘገበበት ቀን አንስቶ
ለአስራ አምስት ዓመታት ቢሆንም በተለያየ ምክንያት የመብቱ መቋረጥ፣ መተው፣ መሰረዝ ሊከሰት ይችላል፡፡
የፓተንት መብት ሊቋረጥ የሚችለው ባለመብቱ ፓተንቱን የተወ መሆኑን ለኮሚሽኑ በፅሑፍ ሲያሳውቅና የመብት
ማቆያ ክፍያ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልተፈፀመ ሲሆን ነው፡፡ ይሄውም የመብቱ መቋረጥ ሊከሰት
የሚችለው በፍላጐትና ግዴታን በአግባቡ ባለመፈፀም ምክንያት እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ የፓተንት መብት
መተው ሊከሰት የሚችለው ደግሞ በፍላጐት ላይ ተመስርቶ የሚመጣ ሲሆን የክንውኑ ስነ-ስርዓትም ባለፓተንቱ
መብቱን መተውን ለኮሚሽኑ ሲያሳውቅና ኮሚሽኑ ይህን የመተው ሁኔታ በመመዝገብ አትሞ ሲያወጣው ነው፡፡
ባላፓተንቱ መብቱን ትቻለሁ በሚልበት ጊዜ መብቱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን በውል ከተሰጠ በኃላ ከሆነ የሚኖረው
ስነ-ስርዓት የመተው ጥያቄው ተቀባይነት የሚያገኘው ሌላው ተዋዋይ ወገን ስምምነቱን ሲሰጥ ብቻ ነው።
ይህም የሆነበት ምክንያት መብቱ በውል የተላለፈለት ሰው ጥቅም (third party interest) ለመጠበቅ
እንደሆነ መገመት ቢቻልም ስምምነቱን በማይሰጥበት ጊዜ ስለሚኖረው ስነ-ስርዓት ህጉ በግልፅ የሚለው ነገር
የለም፡፡

ከአጠቃላይ የድንጋጌው ይዘት ለመረዳት እንደሚቻለው ግን ይህ መብት ፀንቶ ለሚቆይበት ጊዜ በውል የፓተንት
መብት የተላለፈለት ሰው በፓተንቱ እየተገለገለበት ሊቆይ እንደሚችል ነው፡፡ የፓተንት መብትን መሰረዝ
የሚመለከትም ቀጥለው የምናያቸው መስፈርቶች በሙሉ ወይም በከፊል ከተሟሉ ፍ/ቤት ፓተንቱን ሊሰርዘው
ይችላል፡፡ (አንቀፅ 34፣35 እና 36) ይሄውም

ሀ. ፓተንት የተጠየቀበት ነገር በአዋጁ ቁጥር 123/89 አንቀፅ 3 እና 4 መሰረት ፓተንት ሊሰጥበት

35 | P a g e
የማይችል ሆኖ ሲገኝ፡፡

ለ. ፈጣሪው በሚበቃ መጠን ግልፅና ሙሉ በሆነ መልክ ባለመገለፁ በመስኩ ለሰለጠነ ሰው በተግባር
ለመተርጐም የማያስችል ሲሆን ነው፡፡

ፓተንቱ ሲሰረዝ የዚህ የፓተንት መብት መሰረዝ ህጋዊ ውጤትም ወደ ኃላ ተመልሶ በሚሰራ ውጤት
(retroactive effect) ይኖረዋል፡፡ ለዚህም ነው አንቀፅ 37(2) "በከፊል ወይም በሙሉ የተሰረዘ ፓተንት ዋጋ
ቢስ ሆኖ የሚቆጠረው ፓተንቱ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ይሆናል’’ ሲል የሚደነግገው፡፡

ስለዚህ አጠር ባለ መልኩ ሲታይ የፓተንት መብት ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ፈጠራ ስራ ባለቤቶች
የሚሰጥ የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት ሆኖ ህገ-መንግስታዊና ከዚያ በታች ባሉ አዋጆችና ደንበች ጥበቃ
የተደረገለትና ወደ ሶስተኛ ወገን ሊተላለፍ የሚችል ግዙፍነት የሌለው የንብረት መብት ነው፡፡ የፓተንት መብት
ጥበቃ የሚያገኘው ለ15 ዓመት ሆኖ የዚህ መብት ዋናው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታም ሶስተኛ ወገኖች
ያለባለፓተንቱ ፈቃድ እንዳይገለገልበት መከልከል ነው፡፡ ፓተንት ግዙፍነት የሌለው የንብረት መብት ቢሆንም
በአንድ ወቅት ተፈጥሮ ለ15 ዓመት ህጋዊ ውጤት ኖሮት ማንነቱን ሊያጣ ወይም ቀሪ ሊሆን የሚችል ወይም
በመሃል እክል ገጥሞት ሊሰረዝ ወይም ሊቋረጥ ወይም በነፃ ፈቃድ ሊተው የሚችል የአእምሮ ንብረት መብት
ነው፡፡

የአስገቢ ፓተንት (patent of introduction)

የአስገቢ ፓተንት የሚሰጠው ለማን ነው? የአስገቢ ፓተንት የሚሰጠው በውጭ አገር የፓተንት ፈቃድ
ለተሰጠውና የጥብቃ ጊዜው ላላለፈበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ፓተንት ላልተሰጠው የፈጠራ ስራ መግለጫ
ለሰጠና ሙሉ ሓላፊነት ለሚወስድ ማንኛውም የአስገቢ ፓተንት ሊሰጠው ይችላል፡፡ (አንቀፅ 18) የአስገቢ
ፓተንት መመዘኛዎችም ለፈጠራ ፓተንት ከሚጠይቁት መመዘኛዎች ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም የአስገቢ ፓተንት
መሰረቱ የውጭ ፓተንት እንደመሆኑ መጠን የአስገቢ ፓተንት ፈቃድ እንዲሰጠው የሚያመለክት ሰው
የውጭውን ፓተንት ቁጥር፣ ቀንና ምንጭ ወይም ዝርዝር መረጃውን የማያውቅ ከሆነ የሚገኝበትን ምንጭ
መጠቆም ይኖርበታል፡፡ (አንቀፅ 19(1) (2)

የአዋጁ አንቀፅ 11(2) የእንካ ለእንካ መርህ (principle of reprocity) እንደተጠበቀ ሆኖ የአስገቢ ፓተንት
አመልካች በአንቀፅ 11(2) የተጠቀሰው አንድ ዓመት ጊዜ ከማለቁ በፊት የውጭው ፓተንት ባለቤት ማመልከቻ
ካላቀረበ ወይም የአስገቢ ፓተንት ባለቤቱ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 21 ማለትም የአስገቢው ፓተንት መብት ፀንቶ
የሚቆይበት ጊዜ መሰረት ፈጠራው ስራ ላይ መዋሉን ማረጋገጥ ካልቻለ ወይም ዓመታዊውን ክፍያ መፈፀም
ካልቻለ  የአስገቢ ፓተንቱ ዋጋ ቢስ ወይም ህጋዊ ውጤት የሌለው እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ (አንቀፅ 20(1)) ይሄም
በሚመለከተው አካል ጠያቂነት የአስገቢ ፓተንት መብቱ በአዋጁ አንቀፅ 36 መሰረት በፍ/ቤት የሚሰረዝ

36 | P a g e
ይሆናል፡፡

የአስገቢ ፓተንት መብት ፀንቶ የሚቆየው የአስገቢ ፓተንት ከተሰጠ ከሶስት ዓመት በኃላ በየዓመቱ በስራ ላይ
የዋለ መሆኑ የማረጋገጥ ግዴታና ዓመታዊ ክፍያ የመክፈል ግዴታው እንደተጠበቀ ሆኖ የአስገቢ ፓተንቱ ፀንቶ
የሚቆየው እስከ አስር ዓመት ሊደርስ ይችላል፡፡ (አንቀፅ 21) የዚህ ዓይነት የፓተንት መብት መፍቀድ አላማው
የውጭ ፓተንት የተሰጠን ፈጠራ ስራ በኢትዮጵያ እንዲገባ በመፍቀድ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖርና ከዚህ
ዘርፍ ልናገኝ የምንችለውን ጥቅም አሟጦ በመጠቀም ለልማት በማዋል በዘርፉ የአሰራር፣ አደረጃጀትና የሰው
ሃይል ብቃት እንዲጨምር ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ወሳኙ የአገር ውስጥ እድገት ቢሆንም ለውጭውም
ቢሆን ተገቢ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አሁን ዓለማችን ከደረሰችበት የግሎባላይዘሽን ዘመን አኳያ ሲታይ በእጅጉ
አስፈላጊና ተገቢም ነው፡፡

የአገልግሎት ሞዴል (Utility model)

በአዋጅ ቁጥር 123/87 እና ደንብ ቁጥር 12/89 ለአነስተኛ የፈጠራ ሰዎች የሚሰጣቸው ጥበቃ የአገልግሎት
ሞዴል ሰርትፍኬት እንደሆነ ከአዋጁ አንቀፅ 38 እና ከደንቡ አንቀፅ 39 መረዳት የሚቻል ሲሆን እንደ ፓተንት
መብት ሁሉ የአገልግሎት ሞዴል በህግ ጥበቃ የሚደረግላቸውና የማይደረግላቸው የፈጠራ ስራዎችን ያካተተ
ነው፡፡

በአገልግሎት ሞዴል ሰርተፍኬት ጥበቃ የሚደረግላቸው የአዲስነትና የኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነትን


መስፈርቶች የሚያሟሉ አነስተኛ ፈጠራዎች በአገልግሎት ሞዴል ሰርተፍኬት ጥበቃ ይደረግላቸዋል
መመዘኛዎቹም፦

አዲስነት - አንድ አነስተኛ የፈጠራ ስራ አዲስ ነው የሚባለው ማመልከቻው በተመዘገበበት ቀን ኢትዮጵያ ውስጥ
በታተሙ ፅሑፎች ላይ ቀደም ሲል ያልተገለፀ ወይም ለህዝብ ያልቀረበ ወይም በይፋ ጥቅም ላይ ያልዋለ ከሆነ
ነው፡፡ ይሁን እንጂ የፈጠራ ስራው ማመልከቻ ከመመዝገቡ ከ6 ወራት በፊት መገለፁና ጥቅም ላይ መዋሉ
አዲስነቱ አያስቀረውም (አንቀፅ 39(1) (2))

ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት - አንድ የፈጠራ ስራ ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት አለው የሚባለው በዕደ ጥበብ፣
በግብርናና በማህበራዊ አገልግሎቶችና ሌላ በማናቸውም መስክ ሊሰራ ወይም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል
ሲሆን ነው፡፡ (አንቀፀ 3(5))

የአገልግሎት መዴል ጥበቃ የሚሰጠው ለ5 ዓመት ሲሆን አነስተኛ የፈጠራ ስራው በኢትዮጵያ ውስጥ ስራ ላይ
የዋለ ከሆነ ለተጨማሪ 5 ዓመት ይታደሳል፡፡ (አንቀፅ 44 (1)) አነስተኛ የፈጠራ ስራን መብት የሚያስጠብቀው
የአገልግሎት ሞዴል ከፓተንት ጋር ሲነፃፀር ቀላል፣ ውድ ያልሆነና ፈጣን የፈጠራ ስራ ማስጠበቂያ መንገድ

37 | P a g e
በመሆኑ ብዙዎች ሊገለገሉበት የሚችል የፈጠራ ስራ ማስጠበቀያ ነው፡፡

ቀደም ሲል እንደተገለፀው በአገልግሎት ሞዴል ጥበቃ የሚደረግላቸው የአነስተኛ የፈጠራ ስራዎች


የመኖራቸው ያህል ጥበቃ የማይደረግላቸውም አሉ፡፡ እነዚህም፡-

ፓተንት የተሰጠበት ወይም የህዝብ ንብረት የሆነን ነገር የቀድሞ ይዘት፣ ጠባይ ወይም ተግባር ቀይሮ
በአጠቃቀሙ ወይም በታለመለት ተግባር መሻሻልን የሚያስከትል ካልሆነ በቀር በቅርፅ፣ በመጠን ወይም
በማቴሪያል መልክ የሚደረግ ለውጥ የአገልግሎት ሞዴል ጥበቃ አይደረግለትም፡፡ (አንቀፅ 40(1))

የታወቁ ንጥረ ነገሮችን ጥንቅር ተመሳሳይ ተግባር ባላቸው ሌሎች የታወቁ ንጥረ ነገሮች የመተካትና ይህም
በሚገኘው ጥቅም ወይም አሰራር ላይ ምንም ዓይነት መሻሻል የማያስገኝ ሲሆን፡፡ (አንቀፅ 40(2))

ለህዝብ ሰላምና ስነ-ምግባር ተፃራሪ የሆኑ አነስተኛ ፈጠራዎች ከሆኑ የአነስተኛ የፈጠራ ስራ መብት
ማስጠበቂያ የሆነው የአገልግሎት ሞዴል ሰርተፍኬት አይስጥም፤ የሚደረግላቸው ጥበቃም አይኖርም፡፡
(አንቀፅ 40 (3))

ስለዚህ የአገልግሎት ሞዴል ሰርተፊኬት ለአነስተኛ የፈጠራ ስራዎች መብት ማስጠቂያ ተብሎ የሚሰጥ
የፈጠራ መብት ሲሆን ጥበቃ የሚሰጣቸውና የማይሰጣቸው የአነስተኛ ፈጠራ ስራዎች በህግ ተለይተዋል።

ይህ መብት ፀንቶ የሚቆየው ለአምስት ዓመት ሲሆን የፈጠራ ስራው በአገር ውስጥ በስራ ላይ የዋለ መሆኑ
ሲረጋገጥ ለተጨማሪ አምስት ዓመት ሊታደስ ይችላል:: የጥሰት መፍትሔን (remedies) በሚመለከት
በአሜሪካን አገር የፍ/ብሄር ተጠያቂነትን ብቻ የሚያስከትል ሲሆን በፈረሳይና አውስትራሊያ የወንጀል
ተጠያቂነትን የሚያስከትል ነው።

በእኛ አገር ህግም የፍታብሄር ተጠያቂነት ከውል ውጭ ባለ ሃላፊነት በአንቀፅ 2027ና ቀጥለው ባሉ
ድንጋጌዎች በወንጀል ደግሞ በወ/ህ/ቁ 721 የሚያስጠይቅ ነው።

ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ (Industrial Designs)

የኢንዱስትሪ ንድፍ ማለት ምን ማለት ነው? የኢንዱስትሪ ንድፍ ማለት የመስመሮች ወይም የቀለሞች ቅንጅት
ወይም ከመስመሮችና ከቀለሞች ጋር የተያያዘ ወይም ያልተያያዘ ባለሶስት ገፅታ ቅርፅ ሲሆን ቅንጅቱ ወይም
ቅርፁ ለኢንዱስትሪ ወይም ለዕደ ጥበብ ውጤቶች ልዩ መልክ የሚሰጥና በኢንዱስትሪ ወይም ዕደ-ጥበብ
ለሚመረት ምርት እንደ ንድፍ የሚያገለግል ነው፡፡ ሲል በአንቀፅ 2(2)

Wikipedia free encyclopedia በህጋችን ከተሰጠው ትርጉም እምብዛም ባልተለየ መልኩ

38 | P a g e
Industrial design rights are Intellectual property rights that protect the visual design of
objects that are not purely utilitarian. An Industrial design consists of creation of shapes,
configurations or composition of patterns or color or combination of patterns and color
in three-dimensional form containing aesthetic value. የሚል ትርጉም ሰጥቶታል፡፡

ጥበቃ የሚደረግላቸውና የማይደረግላቸው ንድፎች

በኢንዱስትሪ ንድፍ የንብረት ባለቤትነት መብት እንደሌሎች የአእምሮ ንብረቶች የህግ ጥበቃ የሚደረግላቸውና
የማይደረግላቸው የኢንዱስትሪ ንድፎች ያሉ ሲሆን ጥበቃ የሚደረግላቸውን የተመለከትን እንደሆነ የሚከተሉትን
መመዘኛዎች ያሟሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

እውቅና ስለማይኖረው ጥበቃ ሊደረግለት አይችልም፡፡ (አንቀፅ 46(3))

ቴክኒካዊ ውጤቶችን ለማግኘት ብቻ ለሚውሉ ማናቸውም ነገሮች በዚህ አዋጅ ለኢንዱስትሪያዊ ንድፎች
የሚሰጠው ጥበቃ አይሰጣቸውም፡፡ (አንቀፅ 46(4))

የኢንዱስትሪ ንድፍ መብት እንዴት ይረጋገጣል?

የኢንዱስትሪ ንድፍ መብት የሚረጋገጠው በምዝገባ ሲሆን የምዝገባው ውጤትም የኢንዱስትሪ ንድፍ

አዲስነት - አንድ የኢንዱስትሪ ንድፍ አዲስ ነው የሚባለው የንድፉ ዋና ዋና ባህርያት በኢትዮጵያ ወይም በውጪ
ከታወቁ ተመሳሳይ ንድፎች የተለየና ከምዝገባ ቀን ወይም እንደ አግባቡ ከቀዳሚው ቀን በፊት ባለው አንድ
ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልተገለፁ ሲሆን ነው፡፡ በንድፎቹ መካከል ያሉ የተለዩ ገፅታዎች ልዩነት በጥቃቅን ዝርዝሮች
ከሆነ ተመሳሳይ ናቸው ተብለው ይወሰዳሉ፡፡ (አንቀፅ 46(2) (ሀ))

ተግባራዊ ተፈፃሚነት- አንድ የኢንዱስትሪ ንድፍ ተግባራዊ ተፈፃሚነት አለው የሚባለው ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ
ምርቶችን በተደጋጋሚ ለማውጣት በሞዴልነት ለማገልገል የሚችል ሲሆን ነው፡፡ (አንቀፅ 46(2) (ለ))

የኢንዱስትሪ ንድፍ ህጋዊ ጥበቃ የማይደረግላቸው ንድፎችን ስንመለከት ደግሞ

ለህዝብ ሰላም ወይም ስነ-ምግባር ተፃራሪ የሆነ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ከሆነ አይመዘገብም፡፡ ካልተመዘገበ
ደግሞ ህጋዊ ሰርተፍኬት ባለቤት በንድፉ ለመሰራት ወይም ለመልገል ወይም በሌላ ማናቸውም አኳኃን
ለመጠቀም ብቸኛ መብት እንዲኖረው ማስቻል ነው፡፡ (አንቀፅ 49) ይህን መብት ለማግኘት የሚቀርብ
ማመልከቻ የኢንዱስትሪ ንድፉን ያቀፈ ምርት ናሙና ወይም የንድፉን ስእላዊ አምሳያና ንድፉ ሊያገለግል
የታቀደውን የምርት ዓይነት መያዝ ይኖርበታል፡፡ ከማመልከቻው ጋር የተመደበውን ክፍያ ይከፍላል፡፡ ከዚህ በኋላ
የቀረበው ንድፍ ተመርምሮ ተቀባይነት ካገኘ የኢዱስትሪ ንድፍ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ይሰጠዋል ይሄውም

39 | P a g e
የንድፍ ስራው የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ መሆኑን የኢንዱስትሪ ንድፉን ቀዳሚነት የኢንዱስትሪያዊ ንድፉን ሰራተኛ
ማንነትና ባለቤቱ በኢንዱስትሪው ንድፉ ያለውን ብቸኛ መብት ይይዛል፡፡

በመብቱ ተጠቃሚ ለመሆን ምዝገባ ወሳኝ ነው፡፡ ኮሚሽኑ የቀረበለት ማመልከቻን በማስመልከት በሚሰጠው
ውሳኔ አመልካቹ ካልተስማማው የውሳኔው ቅጂ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በ60 ቀን ውስጥ ይግባኙን ወደ ፍ/ቤት
ማቅረብ ይችላል፡፡ ስለዚህ በአገራችን ሆነ በሌሎች አገሮች የኢንዱስትሪ ንድፍ ህግ ለፈጠራ ስራ ጥበቃ
የሚሰጥ ቢሆንም ለሁሉም የኢንዱስትሪ ንድፎች ልዩነት በሌለው መንገድ (indiscrimnatlly) ጥበቃ የሚሰጥ
ህግ ግን አይደለም፡፡

መብቱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

የአንዱስትሪ ንድፍ የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት እንደሌሎቹ የአእምሮ ንብረት መብቶች ፀንቶ የሚቆይበት
ጊዜ ያለው ነው፡፡ አገሮች እንደየ ፍትሕ ስርዓታቸው የተለያየ መብቱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ አላቸው:: ለምሳሌ
በካናዳ  10 ዓመት፤ በጃፓን 15 ዓመት፤ በአሜሪካ 14 ዓመት በእንግሊዝ የተመዘገበና ያልተመዘገበ የሚል
አሰራር ስለሚከተሉ የተመዘገበ ከሆነ 25 ዓመት ያልተመዘገበ ከሆነ ደግሞ ለ15 ዓመት ፀንቶ ይቆያል።
በኢትዮጵያም የምዝገባ ማመልከቻው ከተመዘገበበት ቀን አንስቶ ለ5 ዓመት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን ይህ
የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ስራ ላይ እየዋለ መሆኑ ሲረጋገጥ ደግሞ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ
መብት ለተጨማሪ ሁለት አምስት ዓመታት ሊራዘም ይችላል፡፡ (አንቀፅ 50(1)) ይህም የይራዘምልኝ ማመልከቻ
የማብቂያ ጊዜው ከመድረሱ በፊት ዘጠና ቀን አስቀድሞ በማመልከት ሊከናወን ይገባል ካልሆነ አይታደስም፡፡
(አንቀፅ 50(2))

ስለዚህ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ የባለቤት መብት የሚሰጠው ለንድፍ ፈጣሪ ሲሆን ጥበቃ የሚሰጣቸው ንድፎች
ለአገር ልማት ከሚያበረክቱት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳ አንፃር እየታዩ ሲሆን በይዘታቸውና
አላማቸው የህዝቡን ሁለንተናዊ እድገት ወደ ኋላ የሚጐትቱ የኢንዱስትሪ ንድፎች የማይመዘገቡና ከሶስተኛ
ወገኖች ጥሰት ለመከላከል ማንኛውም ዓይነት የህግ ጥበቃ የማይደረግላቸው መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር
123/1987 ድንጋጌዎችና ደንብ ቁጥር 12/89 አንቀፅ 40 እና ቀጥለው ያሉ ድንጋጌዎች ልንረዳው የምንችል
እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም የኢንዱስትሪ ንድፍ ህግ እንደሌሎች የአእምሮ ንብረቶች ስርዓት ባለው መንገድ
እየተመራ ለአገር ልማት እንዲውል የማድረግ ህዝባዊ አላማን መሰረት ያደረገ ነው፡፡

40 | P a g e

You might also like