You are on page 1of 51

የአፈፃፀም አመራር ማፈጸሚያ ፕሮሲጀር

 
 
 

ባህር ዳር
ኤፕሪል
2021
መግቢያ

የድርጅቱን የስራ አፈፃፀም ዉጤታማ ከማድረግ አንፃር


ዕቅድ አቅዶ ለመንቀሳቀስ፤ ለመከታተል፤ ለመተግበርና
ለመመዘን ይቻል ዘንድ ኩባንያዉ የአፈጻጸም አመራር
ማስፈጸሚያ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
ትርጓሜ
የቃሉ አግ ባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካል ሆ ነ በስተቀር በዚህ የአፈፃፀም አመ ራር ፕሮሲጀር ውስጥ ፤

2.1. “ኩ ባን ያ” ማለት ገንዳ ውሃ የጥ ጥ መ ዳመ ጫ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ ል ማኅበር ማለት ነው


2.2. “ሠ ራ ተ ኛ ” ማለት በገንዳ ውኃ የጥ ጥ መ ዳመ ጫ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ ል ማኅበር ውስጥ በቋሚነት
ተቀጥ ሮ የሚሰራ ሰው ነው፡፡
2.3. “አፈ ፃፀም ” ማለት በመ ጨ ረሻ የሚጠበቀው ውጤ ት የሚገለጽበት ክንውን ነው፡ ፡
2.4. “የአፈ ፃፀም አመ ራ ር ” ማለት አፈፃፀምን በማቀድ፣ በመ ከታ ተል ፣ በመ መ ዘን፣ ፈፃሚውን
በማብቃት፣ በመ ገምገምና በማበረታ ታ ት ቀጣይ ነት ያለው የአፈፃፀም መ ሻሻል ን ማረጋ ገጥ
የሚያስችል የተቀናጀ የአመ ራር ሂ ደት ነው፡ ፡
2.5. “እይ ታ ዎ ች ” ማለት የተቋምን አፈጻጸም ከፍ ይ ናንስ፣ ከደንበኛ፣ ከውስጥ አሰራር ፣ መ ማማርና
እድገት አቅጣጫዎ ች አንፃር ለማየት የሚያስችሉ ሚዛናዊ ሌንሶች ናቸው፡፡
2.6. “ስት ራ ቴ ጅያዊ ግ ብ/S trate gic Obje ctive s /” ማለት የተቋሙ ን ስትራቴጅ በአራቱ እይ ታ ዎ ች ወደ
ስትራቴጅያዊ ተግ ባር የሚቀየር ባቸው ጥ ቅል አላማዎ ች ናቸው፡፡
2.7. “ቁ ል ፍ የአፈ ፃፀም አመ ል ካች /Ke y Pe rformance Indicator/” ማለት የተቋም ስትራቴጅያዊ
ግ ቦችን ለማሳካትና ለመ ለካት የሚተገበሩ ዋና ዋና ቁል ፍ ተግ ባራት ናቸው፡፡
1. “የአፈፃፀም እቅድ ስምምነት/Performance Planning Agreement” ማለት ቁልፍ የአፈፃፀም
አመልካቾችን ለመተግበር በፈፃሚውና በቅርብ ኃላፊው መካከል የሚደረግ የውል ስምምነት ነው፡፡
2. “የድርጊት መርሃ ግብር” ማለት የፈፃሚው የዓመት፤ የግማሽ ዓመት፣ የሩብ ዓመት፣ የወር እና
የሳምንት የሥራ እቅድ የሚከናወንበት የጊዜ ሰሌዳ ነው፡፡
3. “የአፈፃፀም ምዘና” ማለት በጊዜ፣ በጥራት፣ በመጠን እና በሌላም መለኪያ የተገኘ ስትራቴጅያዊ
ግቦች ወይም የቁልፍ አመልካቶችን የአፈፃፀም ውጤትን መለካትና መመዘን ማለት ነው፤
4. “የአፈፃፀም ደረጃ” ማለት ከእያንዳንዱ ቁልፍ አመልካቾች ፈፃሚው የሚያገኘው ውጤት እና
አጠቃላይ ተደምሮ የሚገኘውን የመጨረሻ ውጤት የሚያመላክት ደረጃ ነው፤
5. “የሥራ ሂደት ስምምነት/Service Level Agreement/” ማለት በኩባንያው የሥራ እንቅስቃሴ
ውስጥ ውጤት ለማምጣት አንዱ የስራ ክፍል ከሌላው የስራ ክፍል ከመነሻው እስከ መድረሻው
ከላይ ወደ ታች /Vertical/ ወይም ወደ ጎን/Horizontal/ የሚጠበቀው አገልግሎት/ስራ ለማከናወን
የሚደረግ የሁለትዮሽ ስምምነት ነው፡፡
6. ማንኛውንም በወንድ ፆታ የተገለፀው ሴትንም ይጨምራል፡፡
ዓላማ
የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች ይኖሩታል፡-
 ለተቋማት ራዕይና ተልዕኮ መሳካት ከፈፃሚዎች የሚጠበቁ ውጤቶችን በማሳወቅ
ተቋማዊ ስትራቴጅውን ከዕየለት ሥራቸው ጋር በማስተሳሰር ውጤታማነትን
ለማሳደግ

 የፈፃሚውን አፈፃፀም በማሻሻል ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ መማማርን እውን


ለማድረግ፤

 የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ሰራተኞች የማትጊያና የሽልማት ሥርዓት ለመዘርጋት፣


እንዲሁም ደካማ አፈፃፀም ያላቸውን ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ሥራዎችን
ለማከናወን፤
የአፈፃፀም የምዘና ሥርዓት መርሆዎች፡-

1. የአፈፃፀም እቅድ የሚዘጋጀው ከተቋሙ ስትራቴጅ አራቱን እይታዎች መሰረት


በማድረግ ከስትራጅያዊ ግቦችና ከቁልፍ አመልካቾች/KPI/ ጋር በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ በሚመጋገብበት አግባብ ይሆናል፡፡

2. ፈፃሚዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ ክትትል፤ ድጋፍና ግብረ-መልስ(ongonig


Coaching and mentoring) እንዲያገኙ ይደረጋል፤

3. የሥራ አፈፃፀም እቅድ በፈፃሚው ንቁ ተሳትፎ በቅርብ የሥራ ኃላፊው


እንዲዘጋጅ ይደረጋል፤

4. የሥራ አፈፃፀም እቅድ የነባራዊ ሁኔታዎችን ግምገማ መሰረት ያደረገ ለውጥ


ሊደረግበት ይችላል፤
5. በሥራ አፈፃፀም ምዘና የሚሰጡ ውሳኔዎች በጽሑፍ በተደራጁ
መረጃዎች(Data Collection and Performance Review)
መሰረት ይሆናል፤

6. የፈፃሚው ክንውን ግልጽ፣ ውስንና ተጨባጭ በሆኑ ቁልፍ


የአፈፃፀም አመልካቾች (ጊዜ፣ ጥራት፣ መጠን ወይም ሌላ መለኪያ)
አማካኝነት የሚመዘን ይሆናል፡፡

7. የአፈፃፀም ምዘና በዓመት ሁለት ጊዜ ይከናወናል፤

8. አፈፃፀምን መሰረት ያደረገ የማትጊያና የማበረታቻ ስርዓት


ተጨባጭ በሆነ የአፈፃፀም ምዘና ውጤት ላይ የሚመሰረት ይሆናል፡፡
የአፈፃፀም እቅድ ዝግጅት ሂደት (Performance Planning Process)

የአፈፃፀም እቅድ ዝግጅት ከፋብሪካዉ ተቋማዊ ስትራቴጅ፣


ከኩባንያው ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች እና ስትራቴጅያዊ ግቦች
ጋር በማስተሳሰር በአራቱም እይታዎች ቁልፍ የአፈፃፀም
አመልካቾች/KPI/ ወደ ፈፃሚዎች እንዲወርድ ተደርጎ
ይዘጋጃል፡፡
የአፈፃፀም እቅድ ዝግጅት ሥርዓት የትግበራ ሂደት በሚከተለው
ቅደም ተከተል መሰረት መፈፀም ይኖርበታል፡፡
የፈፃሚ እቅድ ዝግጅት
1. በኩባንያው ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች፣ ስትራቴጅ፣ ስትራቴጅያዊ ግቦች፣ መለኪያዎችና
ኢላማዎች ላይ ቀጣይነት ባለው የጋራ መግባባት ላይ መድረስ፤

2. የፈፃሚ ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካች(KPI) ዕቅድ ሲዘጋጅም በተቻለ መጠን ቢያንስ


የሚከተሉትን ነጥቦች አሟልቶ የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
 ፈፃሚው ተመድቦ በመስራት ላይ የሚገኝበት የሥራ ክፍል ዕቅድ፣
 የፈፃሚ የሥራ መዘርዘር (Job-description)
 የሥራ አፈፃፀም እቅድ ሲሰጥ የፈፃሚው አጠቃላይ አቅምና የመፈፀም ብቃት ማለትም
የፈፃሚውን የሥራ ልምድ፤ የሥራ መደብ ደረጃ (Junior, Senior Level)፤ እና የሥራ መዘርዝር
ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል፤ (Cascading by assignment)
 የፈፃሚው የሥራ ተነሳሽነትና የሥራ ባሕል፣
 በተቋሙ እየተተገበረ ያለውን ስትራቴጅያዊ እርምጃ (Strategic Intiatives)
 ዋና ዋና ተግልጋዮች ወይም ደንበኞች፤
 እቅዱን ለማሳካት የሚያግዝ ስልጠና (ልዩ ክህሎቶች) የያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡
1. የፈፃሚ ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች ዕቅድ ሲዘጋጅ የሚከተሉትን ነጥቦች አሟልቶ
የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

 ግልፅ መሆኑን ማረጋገጥ(Specific)፡- ግልፅ ተደርገው የተዘረዘሩ እና ከሥራ ሂደት ይልቅ ውጤት
ላይ ያተኮረ መሆን አለበት፣
 ሊለኩ/ሊመዘኑ የሚችሉ(Measurable)፡- የሚፈለገውን የሥራ ውጤት ለመለካት የሚያስችል
 ሊተገበሩ የሚችሉ(Achievable)፡- የሚቀመጡት ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች ተግባራዊ
ሊደረጉ የሚችሉ እና ጥረት የሚጠይቁ (Streched) መሆን ይኖርባችዋል፡፡
 አግባብነት ያላቸ(Relevant/Realistic)፡- ከተቋሙና ከሥራ ክፍሉ ስትራቴጅያዊ ግብ እና
እቅድ ጋር የተያያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡
 ከጊዜ ጋር የተገናዘቡ(Time bounded)፡- በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ሊከናወኑ የሚችሉ
መሆን ይኖርባቸዎል፣
ፈፃሚ እቅድ ሲታቀድ መረጃ ማሰባሰቢያ ስልቶችን ማለትም የሚያስፈልገውን የማቴሪያል አቅርቦት፣ የአመለ
ttitudes)፣ የክህሎት (Skill) እና የአሰራር ማነቆዎች የዳሰሱና የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀድሞ ያስቀመጡ መ
ኖርባቸዋል፤

ፈፃሚ እቅድ በዓመት 2 ጊዜ (በየስድስት ወሩ) በየደረጃው ባለ የቅርብ የሥራ ኃላፊው ታቅዶ የሚሰጥ ሲሆን ይ
ጃንዋሪ 01 እስከ ጁን 30 እና ከጁላይ 01 እስከ ዴሴምበር 31 እ.ኤ.አ ድረስ ይሆናል፡፡

ደረጃው የሚሰጠው የፈፃሚ እቅድ ከተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚው/አመራር / እቅድ ጋር የተሳሰረ መሆን አለበት፤

አንድ እይታ(Perspecive) ስር ቢበዛ 5(አምስት) ስትራቴጅያዊ ግብ መቀመጥ ይኖርበታል፤

ፈፃሚ የቁልፍ አፈፃፀም አመልካች(KPI) እቅድ በተቻለ መጠን ከአንድ ገፅ መብለጥ የለበትም፤

ንዱ የሥራ ክፍል ከሌለው የሥራ ክፍል ከመነሻው እስከ መድረሻው ሥራዎችን ለማከናወን ከላይ ወደ ታች/Vert
ይም ወደ ጎን/Horizontal/ የሚጠበቀው አገልግሎት/ሥራ ለመሥራት ግዴታ በሚሆንበት ጊዜና በቅብብሎሽ(Rol
p) የሚሠሩ ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ በሥራ ክፍሎች መካከል የአፈፃፀም እቅድ ስምምነት(Service L
greement) ሊኖር ይገባል፡፡
7. የአፈፃፀም እቅድ ስምምነቱ(Service Level Agreement) እንደ
ሥራው ስፋት እየታየ ሥራውን በምን ያህል ጊዜ ማለቅ እንዳለበት
ስምምነት በሚያደርጉ የሥራ ክፍሎች መካከል ሆኖ የሚደረገው
ስምምነት፡-

 በውስጥ ማስታወሻ (Office Memo) ከሆነ በ2 ቀን ውስጥ ለቀረበው


ጥያቄ መልስ መስጠት ይኖርበታል

 በኢሜይል የተላከ ከሆነ የተጠየቀው የሥራ ክፍል በ3 ቀን ውስጥ መልስ


መስጠት ይኖርበታል፡፤ ሆኖም ግን በዚህ በተጠቀሰው ጊዜ መልስ ያላገኘ
ፈፃሚ/ሥራ ክፍል/ መረጃውን ለሚቀጥለው የሥራ ኃላፊ በማቅረብ
እርምጃ እንዲወስድ ማድረግ አለበት፡፡
ክብደት (Weight) መወሰንና መስጠት፤
1. የአፈፃፀም እይታዎች የተቋሙን አፈፃፀም ለማየት የሚያስችሉ መነፀሮች በመሆናቸው
ለ4ቱም ከ100% እየተሸነሸነ ክብደት እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
2. ለእይታዎች የሚሰጠው ክብደት እይታው ለኩባንያው ወይም ለሥራ ክፍሉ ስትራቴጅ ያለው
አስተዋፅኦ (Strategic Importance) እየተመዘነ ይሆናል፡፡
3. በኩባንያ ወይም በሥራ ክፍል ደረጃ ለሚዘጋጀው እቅድ ለእያንዳንዱ እይታ የሚሰጠው
የክብደት መጠን ከ15-40% ይሆናል፤ ይህ ማለት ለአንዱ እይታ ቢያንስ 15% ቢበዛ 40%
ክብደት የሚሰጠው ይሆናል፤ ነገር ግን ወደ ሠራተኞች ሲወርድ ለአንድ እይታ የሚሰጠው
የክብደት መጠን ከ5% ማነስ የለበትም ከፍተኛውም ከ40% መብለጥ የለበትም፡፡
4. በእያንዳንዱ እይታ የተሰጠው ክብደት ስትራቴጅያዊ ግቦችን መሰረት አድረጎ ለሚዘጋጁ
ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች(KPIs) እየተሸነሸነ እንደ ቁልፍ አፈፃፀም አመልካቾች
ስትራቴጅክ ጠቀሜታ እየታየ ክብደት ይሰጣቸዋል፡፡
የቁልፍ አፈፃፀም አመልካቾች መለኪያዎች መወሰን
•የቁልፍ አፈፃፀም አመልካች መለኪያዎች እንደ አስፈላጊነቱ፡-

 በምን ያህል መጠን(Quantity of work)፤


 በምን ዓይነት ጥራት(Quality of work)፤
 በስንት ጊዜ (timeliness of work)
 በስንት ወጪ (cost)
 በምን ያህል ፍጥነት (Speed of work)
 መጠናቀቅ (Completeness)
 ውጤታማነት (Effectiveness)
 ቅልጥፍና (Efficiency)
 ምጥጥን (Value for Money or Economy)
 እርካታ (Satisfaction)
• ማክበር/ተገዥነት (Compliance and Governance) ሊይዝ ይችላል፡፡
ኢላማ ማስቀመጥ (Target Setting)
1.ኢላማ ከኩባንያው ስትራቴጅ እና ከሥራ ክፍሉ ዓመታዊ እቅድ በመነሳት ይቀመጣል፤
2.ኢላማ ሲቀመጥ በዘፈቀደ ሳይሆን ከልምድና ምርጥ ተሞክሮ፣ ካለፈው አመት
አፈፃፀም(Baseline Data)፣ ሳይንሳዊ የሆኑ ስታንዳርዶች፣ ከተደረጉ ጥናቶች፣ ከግብረ
መልስ እና ሪፖርቶች፣ ከኢንደስትሪ ስታንዳርዶች(Marketing, Profit Marigion,
Machine Capacity, etc); ከውስጥና ከውጭ ደንበኞች/ተገልጋዮች እርካታና እሮሮ
መሰረት ማድረግ በፈፃሚው ጥረት ተደራሽ(achievable but Streched)እንዲሆን
ተደርጎ ይቀመጣል፤
3.ለእያንዳንዱ ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች ኢላማ የሚኖራቸው ሲሆን የፈፃሚው
ኢላማም በዓመት፣ በግማሽ ዓመት፣ በሩብ ዓመት፣ እንዳስፈላጊነቱ በወር እና
በሳምንት በሚከናወንበት የድርጊት መርሃ ግብር የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይሆናል፤
4. የባሕሪ ብቃት መመዘኛዎች
4.1 የፈፃሚው ስነ-ምግባና የሥራ ባሕል፡-

 በሥራ ሰዓት ሙሉ ጊዜውን በሥራ የማሳለፍ ሁኔታ፣


 ሥራ ወዳድነትና ጠንካራ የሥራ ባሕል ያለው፤
 በኋላ ቀር ልምዶች እያሳበበ መደበኛ ሥራውን የማይበድልና ከሥራው
የማይቀር ወይም በሥራ ላይ አዘውትሮ የመገኝት ሁኔታ(Absenteeism)
ከሥራ ባለደረቦቹና ከቅርብ ሃላፊዎቹና ከተገልጋዮች ጋር ተግባብቶ የመስራት
ሁኔታ(Teamsprit)፤
 በተሰማራበት የሥራ መስክ ከመጥፎ ስነ-ምግባር የራቀና በመልካም ስነ-ምግባሩ
የተመሰገነ ወይም በሥነ - ምግባሩ ለሌሎች ሠራተኞች ያለው አርአያነት፣
4.2 ፈፃሚው ለድርጅቱ ያለው የባለቤትነት ስሜት፤

 የድርጅቱን ሃብትና ንብረት ለመንከባከብ የሚያሳየው ጥረት፣


 ለሥራ የተሰጠውን ንብረት በአግባቡና በቁጠባ የመጠቀም
ልምድ/ባህል/፤
 ለድርጅቱ ሃብትና ንብረት መጠበቅ በተለያዩ መድረኮች
የሚያነሳቸው ገንቢ አስተያየቶችና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች፣
 የድርጅቱን ህግና አሰራር ተከትሎ መስራት፣
4.3 ፈፃሚው በቀጣይነትና ባለማቋረጥ አቅሙንና ችሎታውን ለማሻሻል
የሚያሳየው ጥረት

 በውስጥና በውጭ አካላት የሚሰጡ የተለያዩ ስልጠናዎችና ኦሬንቴሽን በሥራ ላይ


የሚያሳየው መሻሻል፣
 በሥራ አፈፃፀም ግምገማና ግብረ-መልስ አስተያየት በወቅቱና በአግባቡ የመስጠትና
የመቀበል ወይም በሥራ አፈፃፀም ወቅት በመረጃ ላይ ተመስርቶ ለራሱና ለሌሎች
ተጨባጭ ሂስ በማቅረብ ያለው ተሳትፎ፤
 በአፈፃፀም ሂደት ከቅርብ ሃላፊዎችና ከሥራ ባልደረባቹ የሚሰጡትን ምክርና የሥራ
ላይ ስልጠና ተግባራዊ የማድረግ ሁኔታ፣
 ያለውን ዕውቀትና የሥራ ችሎታ ለሌሎች ለማካፈልና የሥራ ባልደረቦቹን ለማገዝ
የሚያሳየው ጥረት፣
 አዳዲስ ነገሮችንና የፈጠራ ሃሳቦችን የማፍለቅና ተግባራዊ የማድረግ ብቃቱ፣
4.4 አላግባብ ተጠቃሚነትን ማስወገድ
 በተሰማራበት የሥራ መስክ አላግባብ ተጠቃሚነትን አጥብቆ
የሚጠላና የሚታገል፣
 ሠርቶ በድካሙ ውጤትና ጥቅሙን ለማስከበር የሚታገል፣
 ድርጅቱን ሊጎዱ የሚችሉ አዝማሚያዎችና ድርጊቶች ሲፈፀሙ
ለሚመለከተው አካል በተገቢው መንገድ የሚያጋልጥ፣ የለውጥ
አሰራሮችን ተቀብሎ መተግበር፤ የተቋሙ እሴቶች እና እምነቶችን
ተረድቶ በሥራው ላይ እየተገበራቸው እና በትክክል ተገዥ ሆኖ
እየሠራባቸው መሆኑ… ወዘተ) በመማማርና እድገት እይታ ውስጥ
ተካተው የመደበኛ የእቅዱ አካል እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
የአፈፃፀም ደረጃ ማስቀመጥ (Threshold/Level of
Agreement)

የአፈፃፀም ደረጃ ማለት ከእያንዳንዱ ቁልፍ አመልካቾች ፈፃሚው


የሚያገኘው ውጤት እና አጠቃላይ ተደምሮ የሚገኘውን የመጨረሻ
ውጤት የሚያመላክት ደረጃ ነው፤
• ስለሆነም የፈፃሚው የቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች(KPI) መሰረት
በማድረግ የአፈፃፀም ደረጃ (ከ0 እስከ 5) ነጥብ የሚሰጥ ሆኖ
በአፈፃፀም ደረጃ የሚቀመጠውን የስምምነት ውጤት (Level of
Agreement) መነሻ በማድረግ በሁሉም የሥራ ክፍሎች /ዘርፎች
ወጥ በማድረግ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ስሌቱም በሚከተለው
የንፅፅር ሰንጠረዥ (Correlation Table) መሰረት የሚሰላ ይሆናል፤
የአፈፃፀም ደረጃ (Threshold/Level of Agreement)
 
የኢላማ አፈፃፀም በ % የተሰጠ ደረጃ
9.99% እና በታች 0
10-14.999% 0.25
15-19.999% 0.5
20-24.999% 0.75
25-29.999% 1
30-34.999% 1.25
35-39.999% 1.5
40-44.999% 2
45-49.999% 2.25
50-54.999% 2.5
55-59.999% 2.75
60-64.999% 3
65-69.999% 3.25
70-74.999% 3.5
75-79.999% 3.75
80-84.999% 4
85-89.999% 4.25
90-94.999% 4.5
95-99.999% 4.75
100% እና በላይ 5
ስትራቴጅያዊእርምጃዎች (Strategic Intiatives)
1.ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች በተቋሙ የአፈጻጸም መነሻ (Performance
Baseline) እና በተቀረጹት ዒላማዎች መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት
የሚቀረጹ አስቻይ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡

2.ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች ማለት ስትራቴጂያዊ ግቦችን በማስፈጸም


ስኬታማነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ፣ ከስትራቴጂያዊ ግቦች ጋር ቁርኝት
ያላቸውና ወደ ተግባር የሚቀየሩ፣ እና ትርጉም ያለው ተቋማዊ ለውጥ
ለማምጣት ሰፊ ዕድል የሚፈጥሩ የአጭርና የረጅም ጊዜ ፕሮጄክቶች ናቸው፡፡

3.ስትራቴጅያዊ እርምጃዎች እንደየስራ ባህሪው እየታየ ለሰራተኞች በሚሰጠው


የቁልፍ አፈፃፀም አመልካቾች(KPI) ውስጥ ተካቶ ይሰጣል፡፡
የእቅድ ጥራት ማረጋገጫ (Quality Check)
1.እያንዳንዱ የሥራ ክፍል ከላይ በክፍል ሁለት ከአንቀፅ 6 እስከ 11 የተገለፁትን መሰረታዊ
ስታንዳርዶች በትክክል በማካተት እቅዱን አዘጋጅቶ ጥራቱን ለማረጋገጥ ለሰው ኃብት ክፍል
ከጥር 1-5 እና ከሐምሌ 1-5 በየአመቱ ይላካል፤
2.የሰው ኃብት ክፍል የእቅዱ ይዘት መሰረታዊ የሆኑ ነጥቦችን ማካተቱን እና ጥራቱን በማረጋገጥ
እቅዱ በቀረበ በ3 ቀን ውስጥ መልስ ይሰጣል፤
3.እቅዱን ያቀረበው የስራ ክፍል የተሰጠውን ግብአት በማካተት በ2 ቀን ውስጥ የመጨረሻ እቅድ
ለሰው ኃብት ያቀርባል፤ የመጨረሻ የፈፃሚ እቅድ ተደርጎ ይወሰዳል፤
4.የእቅድ ማረጋገጫ ሲካሄድ ከላይ በክፍል ሁለት ከአንቀፅ 6 እስከ 11 የተገለፁትን መሰረታዊ
ስታንዳርዶች በትክክል ማካተቱ ይረጋገጣል፤
5.ለፈፃሚዎች የሚሰጠው እቅድ ጥራት(Quality) ጥራቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል
እንደየኩባንያው የሰው ኃይል ብዛት እስከ 10 ቀን (ጥር 1-10 እና ከሀምሌ 1-10 ድረስ) ሁሉም
ስራ ተጠናቆ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
የአፈፃፀም እቅድ ስምምነት

የአፈፃፀም እቅድ ስምምነት በተቋማዊ የአደረጃጀት


መዋቅር መሰረት እንደየተጠሪነታቸው የቅርብ
ኃላፊዎች ከፈፃሚዎች ጋር እቅዱን በጋራ ገምግመው
መስማማት ላይ ሲደርሱ በመፈራረም ተግባራዊ
ይደረጋል፡፡
የአፈፃፀም እቅድ መረጃ አያያዝ (Planning
Documentation

1.የአፈፃፀም ዕቅድ በኩባንያው የሰው ሀብት ልማትና


አስተዳደር መምሪያ እና የፕሮጅክቶች በፕሮጀክት
ጽ/ቤት በማስረጃነት ከሠራተኛው ማሕደር ጋር
ይይዛል፡፡
• የአፈፃፀም ዕቅድ በ3 ኮፒ ተዘጋጅቶ ፈፃሚው
ለሚሰራበት ከፍል፣ ለሰው ኃብት እና ለፈፃሚው
እንዲደርስ ይደረጋል፤
የአፈፃፀም ሂደትን መከታተል፣ መደገፍና ግብረ-
መልስ መስጠት

•የአፈፃፀም አመራር (Performance Management) ዋና


አላማው ሠራተኛውን መገምገም ሳይሆን የማብቃት ሥራ
መስራት ነው፡፡ ይህም ፈፃሚውን ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ
እስከ ትግበራ ባለው ሂደት የመከታተል፣ መደገፍና፤፣ ግብረ
መልስ የመስጠትና መረጃዎችን በማደራጀት ለምዘና
የማዘጋጀት ሂደት ነው፡፡
ክትትልና ድጋፍ (Ongoing Coaching, Mentoring and
feedback)
1.ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የቅርብ ኃላፊው የፈፀሚዎችን ያላቸውን አቅም (Potential) እና የጎደለውን
ክፍተቶች (Gaps) በመለየት የአስልጣኝነት (Coach)፣ የአጋዥነት (facilitator) እና የማማከር ሥራ
ተባብሮ በመሥራት የማገዝና የማበረታታት ተግባር በሚገባ ተገንዝቦ መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡
2.የቅርብ ሃላፊዎች የፈፃሚውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመገምገም ግብረ-መልስ መስጠት ይኖርበታል፤
ግብረ መልሶችም ገንቢና ቀጣይ ሥራውን በተፈለገው መንገድ ፈፃሚው በራሱ ጥረት እንዲፈፅም
የሚያግዝ (Positive feed back) ሊሆን ይገባል፤
3. የቅርብ ሃላፊዎች ከሚሰጡ ግብረ መልሶች በተጨማሪም በታዩት Incident፤ በተገልጋዮች/ ደንበኞች/
የሚሰጥበት ግብረ መልስ እንደ ሁኔታው እየታየ በአማራጭ መፈፀም ይኖርበታል፡
4.በተለያዩ አካላት ሚሰጡ ግብረ-መልሶች (feedbacks) የቀጣይ የሥራ አፈፃፀም ማሻሻያ ዕቅድን
(Performance Improvement Plan) ለማዘጋጀት የሚያግዝ ሊሆን ይገባል፤
5.ለፈፀሚው የሚሰጠው ግብረ መልስ የሥራ መነሳሳት፣ የስነ-ምግባር ሁኔታ በቀጣይነት የመማርና
የመሻሻል ሁኔታው በሚገባ በሪከርድ መያዝና ቁጥጥር ማካሄድ ይኖርበታል፤
የአፈፃፀም መረጃ የማደራጀት (Data Collection, and
Perfromance Review)

1.አግባብ ያልሆኑ የአፈፃፀም ምዘና ውጤት አሰጣጥ ስህተቶችን ለማስወገድ የሥራ


አፈፃፀም ምዘና ከመካሄዱ በፊት ለምዘናው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በቅድሚያ በቅርብ
የሥራ ሃላፊው መሰብስብና መተንተን የሚይኖርባቸው ሲሆን በዚህ መሰረት ከምዘና በፊት
በቅርብ ሃላፊው እና በፈፀሚው የሚዘጋጁ ለምዘና ጠቃሚ መረጃዎች ማለትም፡-
 የአፈፃፀም ዕቅድ፣
 የአፈፃፀም ሪፖርቶች፣
 በቅርብ ኃላፊው፣ በስራ ክፍሉ አባላትና በራሱ በፈፃሚው የሚያዙ የአፈፃፀም
ማስታወሻዎች ማለትም የግልና የባህሪ ግድፈት የክስተት መመዝገቢያ (Personal Diary
and Behavioral Incident Recording)፣
 ከፈፃሚው ጋር የሥራ ግንኙነት የነበራቸው ተገልጋዮችና
ባለድርሻዎች አስተያየት (ወቀሳ ወይም ምስጋና)
 በአፈፃፀም ሂደት ወቅት ለፈፃሚው የተሰጡ ድጋፎች ፤ ምክርና
ግብረ መልሶች፤
 ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮችና ምክንያታቸው፣
 ፈፃሚው ከተሰጠው የሥራ አፈፃፀም ዕቅድ ወጪ በተጨማሪ
ያከናወናቸው ተግባራት ካሉ፣
 ፈፃሚው የወሰዳቸው የተለያዩ ፍቃዶችና የስነ-ምግባር ሁኔታ
የሚመለከቱ መረጃዎች፣ ወ.ዘ.ተ በቅድሚያ መሰብስብና
መተንተን ይኖርባቸዋል፣
2. የአፈፃፀም አመራር ሲተገበር የአመት እረፍት ፈቃድ
አሰጣጥ በሰው ኃብት የሥራ ክፍል አማካኝነት ቀድሞ በእቅድ
መያዝ ይኖርበታል፡፡
3. ሠራተኞች በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት፤ ማርፈድ ፤
በተደጋጋሚ የሕምም ፈቃድ መውሰድና ሌሎች ተያያዥ
ጉዳዮች በየደረጃው በሚገኝ ኃላፊ በጥብቅ ዲሲፕሊን
የሚመራ ይሆናል፡፡
የአፈፃፀም ምዘና ውጤት መስጠት (Performance Apprisal
and Rating)

1. በአንቀጽ 16 የተጠቀሱት የመረጃ ምንጮችን መሰረት በማድረግ


የፈፃሚው ውጤት በሚከተለው መንገድ እንዲሞላ ይደረጋል፤
2. የአፈፃፀም ምዘና ውጤት የሚሰጠው የፈፃሚው የቁልፍ
የአፈፃፀም አመልካቾች (KPI) የእቅድ ክንውን ንፅፅር ከሚያርፍበት
የአፈፃፀም ስምምነት ደረጃ (ከ 0 እስከ 5) ከቁልፍ የአፈፃፀም
አመልካቾች (KPI) ክብደት (Weight) ጋር እየተባዛ በሚከተለው
የንፅፅር ሰንጠረዥ (Correlation Table) መሰረት የሚሰላ ይሆናል፤
የአፈፃፀም የተሰጠ የአፈፃፀም
ደረጃ የቁልፍ አፈፃፀም
ውጤት = የአፈፃፀም
የኢላማአፈፃፀም በ% (Threshold አመልካት ክብደት
ደረጃ (2) X የቁልፍ
(1) /Level of (KPI Weight) በ
አፈፃፀም አመልካት
Agreement) % (3)
(2) ክብደት (3)
9.99% እና በታች 0    
10-14.999% 0.25    
15-19.999% 0.5    
20-24.999% 0.75    
25-29.999% 1    
30-34.999% 1.25    
35-39.999% 1.5    
40-44.999% 2    
45-49.999% 2.25    
የቁልፍ
አፈፃፀም
የአፈፃፀም ደረጃ የተሰጠ የአፈፃፀም ውጤት = የአፈፃፀም
አመልካት
የኢላማአፈፃፀም በ% (1) (Threshold /Level of ደረጃ (2) X የቁልፍ አፈፃፀም አመልካት
Agreement) (2) ክብደት (KPI
ክብደት (3)
Weight) በ%
(3)
50-54.999% 2.5    
55-59.999% 2.75    
60-64.999% 3    
65-69.999% 3.25    
70-74.999% 3.5    
75-79.999% 3.75    
80-84.999% 4    
85-89.999% 4.25    
90-94.999% 4.5    
95-99.999% 4.75    
100% እና በላይ 5    
 
ከ5ቱ የተገኘ ውጤት
 
1. የተቀመጠው አፈፃፀም ደረጃዎች (Thresholds) የኢላማውን አፈፃፀም መነሻ (Range) ተደርጎ ይወሰዳል፤
2. ከ5ቱ የተገኘው አጠቃላይ የአፈፃፀም ድምር ባረፈበት አፈፃፀም ደረጃዎች (Thresholds) መሰረት ከኢላማውን
አፈፃፀም መነሻ (Range) ጋር ተነፃፅሮ ከ (100%) የተገኘው ውጤት ተሰልቶ ይቀመጣል፤
3. የባሕሪ ብቃት መመዘኛዎች ከመማማርና እድገት እይታ ውስጥ ተካተው የእቅዱ አካል ስለሚሆኑ በሚታዩ
የክስተት ደረጃዎች (Level of Incedents) አማካኝነት የምዘናው ውጤት የሚሰጠጥ ይሆናል፤
4. የፈፃሚው የምዘና ውጤት ከመሞላቱ በፊት በቅድሚያ ፈፃሚው ራሱን እንዲገመግም ዕድል መስጠቱ ራሱን
እንዲያውቅ የሚያደርግ በመሆኑ ለስኬታማነቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
5. የፈፃሚው የምዘና ውጤት በዓመት 2 ጊዜ (በየስድስት ወሩ) በየደረጃው ባለ የቅርብ የሥራ ኃላፊው የሚሞላ ሲሆን
ይህም ከጁን 30 እስከ ጁላይ 5 እና ከዴሴምበር 31 እስከ ጃንዋሪ 5 እ.ኤ.አ በ5 ቀን ውስጥ ተሞልቶ በየደረጃው
ለሚገኝ የሰው ኃብት ክፍል መላክ ይኖርበታል፡፡

6. በሥራ አፈፃፀም ወቅት ፈፃሚዎችን ከመተቸት ይልቅ በቅድሚያ አድናቆትና ምስጋና በማስቀደም ክፍተቶች ላይ
በማተኮር በቀጣይነት እንዲሻሻል ማድረግ(Kiss- Kick-Kiss/ Sandwich Approach) ይሆናል፤
የውጤት ማረጋገጫ መስጠት (Quality Check and Calibration)
1. የውጤት ማረጋገጫ የሚያስፈልገው ፈፃሚው የላቀ አፈፃፀም 95% እና በላይ
ወይም ዝቅተኛ አፈፃፀም ከ50% በታች አፈፃፀም ሲያስመዘግብ ብቻ ይሆናል፡፡
2. የውጤት ማረጋገጫው ሲካሄድ የምዘና ውጤቱ ከቁልፍ አፈፃፀም አመልካቾች ጋር
እና በድጋፍና ክትትሉ ወቅት ከተመዘገቡ መረጃዎች ጋር ያለው ትስስርና ተዛምዶ
መሰረት ያደርጋል፤
3. ለፈፃሚዎች የተሰጠው ውጤት የላቀ ወይም ዝቅተኛ አፈፃፀም ሲሆን በፋብሪካዉ
የሰው ኃብት ክፍል አማካኝነት በፋብሪካዉ ማኔጅመንት እየቀረበ እና በጋራ
እየተገመገመ ውጤቱ ውሳኔ የሚያገኝ ይሆናል፤
4. የፋብሪካዉ ደግሞ በፋብሪካዉ ማኔጅመነት የተሰጠው የውጤት ውሳኔ የመጨረሻ
ተደረጎ ይወሰዳል፡፡
ዋና ዋና የምዘና ውጤት አሰጣጥ ስህተቶች (Common Errors/Pitfalls)
በምዘና ወቅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩተን ስህተቶች ማስወገድ (Avoiding Pitfalls);
1. በአንድ የተግባር ምዘና ብቻ የታየን መልካም ወይም የተሻለ አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ የሌሎች
ተግባራትን አፈፃፀም በተመሳሳይ መንገድ የመፈረጅ ወይም የመመዘን ስህተት
(Haloerror)
2. በአንድ የተግባር ምዘና ብቻ የታየን መጥፎ ወይም ዝቅተኛ አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የሌሎች
ተግባራት አፈፃፀምን በተመሳሳይ መንገድ የመፈረጅ ወይም የመመዘን ስህተት
(Hornserror)
3. ምዘናው ከመፈፀሙ በፊት ፈፃሚውን በአወንታዊ ወይም አሉታዊ መንገድ በመገንዘብ የቀጣይ
ጊዜ የሥራ አፈፃፀም ምዘናን በአውንታዊ ወይም በአሉታዊ መንገድ የመመዘን ስህተት (First
impression error)
4. በፈፃሚው የመጨረሻ የሥራ አፈፃፀም የምዘና ጊዜ ብቻ መነሻ በማድረግ አጠቃላይ የሥራ
አፈፃፀም የምዘና ጊዜ በመልካምነት ወይም በመጥፎነት መንገድ የመመዘን ስህተት
(Regencyerror)
5. የፈፃሚው የሥራ አፈፃፀም ምዘና በሚሞላበት ጊዜ ማግኘት ከሚገባው በላይ
ውጤት የመስጠትና የውጤት ግሽበት የመፈጠር ስህተት (Leniencyerror).
6. የፈፃሚው የሥራ አፈፃፀም ምዘና በሚሞላበት ጊዜ ማግኘት ከሚገባው በታች
ውጤት የመስጠት ስህተት (Severity error)
7. የሁሉንም ፈፃሚዎች አፈፃፀም አማካኝ ውጤት የመስጠትና የመመዘን ስህተት
(Central tendency error)
8. የምዘና ውጤት በሚሞላበት ጊዜ ከሥራ አፈፃፀም መዛኙ (የቅርብ ኃላፊው) ጋር
የግል ግንኙነትና ቀረቤታ ለሚኖራቸው ፈፃሚዎች የተሻለ ውጤት የመስጠት ስህተት
(Clone error)
9. የበፊት ሥራ አፈፃፀም ጉድለትን መነሻ በማድረግ የሥራአፈፃፀምምዘና ውጤት
በሚሞላበት ጊዜ በተመሳሳይ ወይም ከዚህ በፊት በነበረው አፈፃፀም በመቀጠል ዝቅ
በማድረግ የመሙላት ስህተት (Spill over error)
የአፈፃፀም ምዘና ደረጃ አሰጣጥ፤
ጥረት ከተቋቋመበት አላማ አንፃር ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል (World Class Employee)
ለመፍጠር አለማቀፍ የምዘና ስታንዳርድ (Differentation Strategy) በመጠቀም 10፤ 70፤ 20 መርህን
ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

1. 10% ማለት በተቋሙ ውስጥ ካሉት ፈፃሚዎች ውስጥ 10 ከመቶ የላቀ አፈፃፀም ያላቸው ፈፀሚዎች
(Super Star- Performers) ናቸው፡፡ ይህ ማለት አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀማቸው ከ95% እና በላይ
የፈፀሙ ወይም ከ 4.75 በላይ ቢሆን) የአፈፃፀም ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው፡፡

2. 70% ማለት በተቋሙ ውስጥ ካሉት ፈፃሚዎች ውስጥ 70 ከመቶ አፈፃፀም ያላቸው ፈፀሚዎች
(Core Performers) ናቸው፡፡ ይህ ማለት አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀማቸው ከ50% እስከ 94.99%
የፈፀሙ ወይም ወይም ከ2.5 እስከ 4.5 ቢሆን የአፈፃፀም ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው፡፡

3. 20% ማለት በተቋሙ ውስጥ ካሉት ፈፃሚዎች ውስጥ 20 ከመቶ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው
ፈፀሚዎች (Under Performers) ናቸው፡፡ይህ ማለት አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀማቸው ከ50% እና
በላይ የፈፀሙ ወይም ከ2.5 በታች ቢሆን)) የአፈፃፀም ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው፡፡
የአፈፃፀም ምዘና ውጤት መረጃ ስለመያዝ(Result Documentation)

1.የአፈፃፀም ምዘና ውጤት በኩባንያው የሰው ሀብት


ልማትና አስተዳደር መምሪያ በማስረጃነት
ከሠራተኛው ማህደር ጋር ይይዛል፡፡
2.የአፈፃፀም ምዘና ውጤት በ3 ኮፒ ተዘጋጅቶ
ፈፃሚው ለሚሰራበት ከፍል፤ ለሰው ኃብት እና
ለፈፃሚው እንዲደርስ ይደረጋል፡፡
የአፈፃፀም ማሻሻያ እርምጃ አወሳሰድ (Performance Improvement Plan):
የአፈፃፀም ምዘና ውጤት የመስጠት ሥራ ከተከናወነ በኋላ የአፈፃፀም ክፍተት (Performance Gaps) ለታየባቸው ፈፃሚዎች
የቀጣይ የሥራ አፈፃፀም ማሻሻያ ዕቅድ (Performance Improvement Plan) በማዘጋጀት በሚከተለው መንገድ የማስተካከያ
እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል፡፡
1. የአፈፃፀም ውጤትን መሰረት በማድረግ ያልተፈፀሙ የቁልፍ አፈፃፀም አመልካቾችን እና ኢላማዎችን መለየት (Detail the
Specific Target area and Performance Concerns where Performance Standards have not been met)

2. በቀጣይ ከፈፃሚው የሚጠበቁ ውጤቶችና የማሻሻያ እርምጃዎች በመለየት ተግባራዊ እንዲሆኑ መስማማት (Detail the
Specific Expected Standard of Performance and Agreed Improvement Actions need to be taken to meet
expected standard of Performance);

3. የአፈፃፀም ውጤትን መሰረት በማድረግ የአመለካከት፣ የእውቀት፣ የክህሎትና የአቅርቦት እጥረቶችን በመለየትና በመፍታት
የመፈፀም አቅምን ማሻሻል (Detail the Specific Supports required to achieve expected standard of
Performance);

4. በየስራ ሥራ ክፍሉየተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ፈፃሚዎች በመለየትዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን ፈፃሚዎች በብቃት
የሚደግፉበትን ስልት መቀየስ፣

5. ፈፃሚዎች የተደረገላቸውን ድጋፍ፤ ክትትልና ምክር አገልግሎት (ongoing Coaching) ሥራዎች በሚገባ የአፈፃፀም
ማሻሻያው አካልማድረግ፤

6. አፈፃፀምን በቀጣይነት የሚሻሻልበትንና ሌሎች እርምጃዎችን በጥናት እየለዩ ተግባራዊ ማድረግ፣


የአፈፃፀም ማሻሻያ መወሰኛ የጊዜ ገደብ

1.አንድ ፈፃሚ በአንድ የምዘና ጊዜ (6ወር) ዝቅተኛ (ከ50% በታች) የአፈፃፀም ውጤት ካመጣ
የአፈፃፀም ማሻሻያ ድጋፍ፤ ክትትል፤ እንደአስፈላጊነቱ ስልጠና ይሰጠዋል፡፡
2.በተሰጠው ስልጠና ድጋፍ ማሻሻል ካልቻለ እና በቀጣይ የ6 ወር የምዘና ጊዜ በድጋሜ ዝቅተኛ
(ከ50% በታች) ካመጣ ወይም ማሻሻል ካልቻለ የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፤
3. ፈፃሚው በአንድ አመት ውስጥ ማሻሻል ካልቻለ እና በቀጣይ 6 ወር ውስጥ ዝቅተኛ (ከ50%
በታች) የአፈፃፀም ውጤት ካመጣ ውሉ እንዲቋረጥ ይደረጋል፤
4.በአንቀፅ 23 ተ.ቁ 2 የተጠቀሰው ቢኖርም በአንዳንድ የስራ መደቦች እና የስራ ባህሪ፤ የስራ
ልምድ፤ የትምህርተ ዝግጅት፤ የፈፃሚው እውቀትና የክህሎት ከስራው ጋር አለመገናኘት
ምክንያት (Skill and Job mismatch) የመጣ ዝቅተኛ አፈፃፀም ከሆነና የቅርብ ኃላፊው
ይህንን ክፍተት የቅርብ ድጋፍና ክትትል ሲያደርግለት በግልፅ ከተለየ ፈፃሚውን ወደ ሌላ ቦታ
በማዛወር ማሰራት ይቻላል፡፡
የማትጊያና እና ማበረታቻ ሥርዓት (Motivation and
Rewarding Schem)፤
•  

የማትጊያና የማበረታቻ ስርዓት ፈፃሚዎች ለተቋሙ ስትራቴጅ መሳካት


ያላቸውን ሚና የበለጠ ለማሳደግ የሚያግዝ ስርዓት ሲሆን የፈፃሚዎች የ2
ጊዜ አፈፃፀም አመካኝ ተወስዶ በአፈፃፀማቸው ደረጃ የማትጊያና
የማበረታቻ ስርዓቱ በሚከተለው መንገድ በማዕከሉና በኩባንያዎች ተፈፃሚ
ይሆናል፡፡
• 
የኩባያው የማትጊያና የማበረታቻ ስርዓት

የላቀ/መካከለኛ አፈፃፀም ላላቸው ፈፃሚዎች በኩባንያዎች


መተዳደሪያ ደንብ፤ የህብረት ስምምነት፤ የኩባንያዎች
ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ እና የመክፈል አቅምን ከግምት
ውስጥ በማስገባት በኩባንያው ማኔጅመንት እየተገመገመና
አቅጣጫ እየተሰጠበት እንደሁኔታው እየታየ ከዚህ ቀጥሎ
በተገለፀው አግባብ ተግባራዊ ይሆናል፤
1. የላቀ አፈ ፃፀም /100 እና በላይ / አፈ ፃፀም ያላቸ ው (S upe r pe rforme rs )
 S uce s s ion P rogra m ውስጥ እንዲገቡ ይ ደረጋ ል በተደጋ ጋ ሚ የላቀ ውጤ ት ሲያስመ ዘገቡ
በኃላፊነት ቦታ ቢሰሩ ውጤ ታ ማ ይ ሆ ናሉ ተብሎ በኩ ባንያው ማኔ ጅመ ንት ከታ መ ነበት የኃላፊነት
ቦታ ው ይ ሰጣቸዋል ፤
 የተሻለና የሚያበረታ ታ የቦነስ ክፍ ያ ያገኛሉ (መ ጠኑ በኩ ባንያው ማኔ ጅመ ንት የሚወሰን ይ ሆ ናል )
 በሰራተኛ በዓል ቀን እውቅና /Re cogniton/ ይ ሰጣቸዋል ፤
 በመ ደበኛ የደረጃ እድ ገት ለመ ወዳደር ይ ችላሉ፤

2.መ ካከለኛ አፈ ጻ ጸም / Core Pe rforme rs /


1.1. መ ካከለኛ አፈፃፀም ካስመ ዘገቡ ፈፃሚዎ ች መ ካከል ከ65--69% የአፈፃፀም ውጤ ት ያስመ ዘገቡ
ፈፃሚዎ ች ከዚህ ቀጥ ሎ የተገለፀውን የማት ጊያና ማበረታ ቻ ተጠቃሚ ይ ሆ ናሉ፤
 ቦነስ ክፍ ያ ይ ሰጣቸዋል ( መ ጠኑ በኩ ባንያው ማኔ ጅመ ንት የሚወሰን ሲሆ ን የላቀ አፈፃፀም
ካላቸው ያነሰ የቦነስ ክፍ ያ ይ ሆ ናል )
 የእዉ ቅና ሰር ፍ ት ት ኬ ት ይ ሰጠዋል
 በመ ደበኛ የደረጃ እድገት ለመ ወዳደር ይ ችላሉ
1.2. ከ50 እና ከዚያ በላይ % የአፈፃፀም ውጤ ት ያስመ ዘገቡ ፈፃሚዎ ች በመ ደበኛ የደረጃ እድ ገት

ለመ ወዳደር ይ ችላሉ፡፡
የኩባንያው የማትጊያና ማበረታቻ ስርዓት አፈፃፀም

ከላይ የተቀመጠው የማትጊያና የማበረታቻ ስርዓት አፈፃፀም ወደፊት የኩባንያውን


ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ እና የመክፈል አቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት በኩባንያው
ማኔጅመንት እየተገመገመና አቅጣጫ እየተሰጠበት እንደ ሁኔታው እየታየ ተግባራዊ
የሚደረግ ይሆናል፡፡
ስለ ቅሬታ አቀራ ረብና የአፈታ ት ስርዓት ፡
በአፈፃፀም እቅድ ስምምነት፤ በአፈፃፀም ምዘና እና በማትጊያና ማበረታቻ ስርዓት ላይ የሚነሱ
ቅሬታዎ ች እንደየ ተቋሙ በኩባንያው ባለው አደረጃጀት መሰረት እንደሚከተለው ይሆናል፤
1. በፈፃሚው እና በቅርብ ኃላፊው በእቅድና ምዘና ውጤት ስምምነት ላይ መድረስ ካል ተቻለ
ቀጥሎ ያለው ኃላፊ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨ ረሻ ይሆናል
2. በማትጊያና ማበረታቻ አፈፃፀም ላይ በኩባንያው ማኔጅመንት ቀድሞ በተቀመጠው ውሳኔ
መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል ፡፡
3. የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓቱ በድርጅቱ ማኔጅመንት አባላት ይወሰናል ፡፡
ከአፈ ፃፀም አመ ራ ር ጋ ር ተ ያያዥ ነት ያላቸ ው ጉ ዳዮች ፤
1. በእር ግ ዝና እና ወሊድ ምክንያት በአፈፃፀም ዕቅድ ስምምነት ጊዜ ውስጥ በሥ ራ ላይ ያል ተገኝ ሴት
ሰራተኛ በበጀት ዓመ ቱ ውስጥ በሥ ራ ላይ በቆየችበት ጊዜ ያላት የ6 ወር ወይ ም የ1 አመ ት የሥ ራ
አፈፃፀም ተመ ዝኖ አፈፃፀሟ ከ50% እና በላይ ከሆ ነ ለተለያዩ ጥ ቅማጥ ቅሞች ይ ያዝላታ ል ፤
2. እንደየተቋሟቱ የሥ ራ ባህር ይ ይ ህን የአፈፃፀም አመ ራር ፕ ሮሲጀር አሻሽለው መ ጠቀም የሚፈል ጉ
ኩ ባንያዎ ች/ፕ ሮጀክቶች/ካሉ መ ሰረታ ዊ መ ር ሆ ችን ሳይ ሸራር ፉ የውስጥ አሰራራቸውን(Ope ra tiona l
Exce lle nce ) ሊያግ ዝ በሚችል መ ል ኩ አሻሽለው በኩ ባንያዎ ች ማኔ ጅመ ንት በማፀደቅ መ ጠቀም
ይ ችላሉ፤
3. አንድ ሳምንት እና በላይ በተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎ ች ተመ ድ በው የሚሰሩ ፈፃሚዎ ች
የኮሚቴ ስራው በመ ደበኛ ዕቅዳቸው ላይ ተካት ቶ የአፈፃፀም ምዘና ውጤ ት አካል ሆ ኖ የሚወሰድ
ይ ሆ ናል ፤
4. በውክል ና አንድ ወር ና ከዚያ በላይ የሚሰራ ሥራ የአፈፃፀም እቅድ ስምምነቱ አካል ተደር ጎ
ይ ወሰዳል ፣ አንድ ሠ ራተኛ በሚወከል በት ጊዜ ለሁ ለት ሰው ተጠሪ ከሆ ነ ለእያንዳንዱ
የአፈፃፀም እቅድ በማዘጋ ጀት ከሁ ለቱም ጋ ር ይ ፈራረማል ፡ ፡
5. የአፈፃፀም ዕቅድ በውጫዊ ተፅዕኖ ምክንያት /የሦስተኛ ወገን ሚና /ወይ ም ከፈፃሚው የመ ወሰን
ስል ጣን በላይ የሆ ኑ ተግ ባራት ና ኃላፊነቶች በሚኖሩ በት ጊዜ ከራሱ ከፈፃሚው የሚጠበቁና መ ፈፀም
የሚገባቸው ተግ ባራት ታ ይ ተውና ተገምግ መ ው በቀረቡ ተጨ ባጭ ማስረጃዎ ች መ ሰረት የአፈፃፀም
ምዘና ውጤ ት ይ ሰጠዋል ፡ ፡
ፕሮሲጀሩን አለመፈፀም ስለሚያስከትለው ተጠያቂነት፤
ይህን የአፈፃፀም ፕሮሲጀር በኩባንያው ማኔጅመንት ፀድቆ ተግባረዊ እንዲሆን
ከተወሰነበት ጀምሮ በማወቅ ወይም በቸልተኝነት ያልፈፀመ ወይም እንዳይፈፀም ያደረገ
ማንኛውም አካል በተቀመጠው የአሠራር ደንብና መመሪያዎች ወይም አግባብ ባለው ሕግ
መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ፕሮሲጀሩ ስለሚፀናበት ጊዜ
ይህ የአፈፃፀም አመራር ፕሮሲጀር በኩባንያው ማኔጅመንት ፀድቆ ከጥር 01/2020 እ.ኤ.አ
ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ል ዩ ል ዩ የሥ ራ ቅ ፃቅ ፆ ች (Work S he e ts )
ቅ ጽ -1. የቁ ል ፍ አፈ ፃፀም አመ ል ካች የዕቅ ድ ስ ም ም ነ ት ቅ ጽ
(Ke y Pe rfromane Indicators - KP I)፤

የ ፈፃሚው ስም፡ የስራ ክፍ ል ፡ የስራ መ ደብ መ ጠ ሪያ፡

የ አፈፃፀም ስምምነት ጊዜ፡ ከ እስከ

በቅ ጹ ላይ የ2019 እ.ኤ .አ መ ነ ሻ (ba s e line ) ይ ጨ መ ር በት


ቁል ፍ የቁ ል ፍ
የእይ ታ ስት ራ ቴ
የ 201 9
ዒ ላማ (Targe t) ስ ት ራ ቴ ጅ ያዊ
አፈ ፃፀ ም አፈ ፃፀ ም
ተ/ ዎ ች ጅያ ዊ እር ም ጃዎ ች
እይ ታ ዎ ች አመ ል ካቾ አመ ል ካቾ ች እ.ኤ .አ
ቁ ክብ ደት ግ ቦች አመ ታ 1ኛ 6 2ኛ 6 (S tra te g ic
ች (KP I)ክብ ደ መ ነሻ
ከ10 0% ዊ ወር ወር Intative s )
(KP I) ት በ%
ግብ
1 KPI 1
1 ፋይ ና ንስ XX
ወዘተ ወዘተ…

ግብ 1
ደንበኞች KPI 1
2 XX ወዘተ
/ተገል ጋ ይ ወዘተ…

ግብ 1
የ ውስጥ KPI 1
3 XX ወዘተ
አሰራር ወዘተ…

ግብ
መ ማማር ና 1 KPI 1
4 XX
እድ ገት ወዘተ ወዘተ…

የፈ ፃሚ ሙ ሉ ስ ም ………………… የቅ ር ብ ኃ ላፊ ሙ ሉ ስ ም
……………………..

ፊ ር ማ -------------------- ፊ ር ማ -----
--------------------------

ቀ ን --------------------- ቀ ን ------
--------------------
ቅ ጽ -2. የአፈ ፃጸ ም ም ዘና ቅ ጽ (Ke y P e rfromane Indic ators - KPI)፤

የ ፈፃሚው ስም፡ ------------------------------ የሥ ራ ክፍ ል ፡ -------------------------------የ ሥ ራ መ ደብ


መ ጠሪያ፡ --------------------------

የ አፈፃፀም ስምምነት ጊዜ፡ ከ-----------------------------እስከ---------------------------

የእይ ታ
የቁ ል ፍ አጠ ቃ ላይ
ስት ራ ቴ ጅ ቁል ፍ አፈ ፃፀም የተ ሰ ጠ
ዎ ች የተ ገኘ ውጤት
ተ/ ያዊ አፈ ፃፀም አመ ል ካቾ ች ዒላ ከን የ አፈ ፃፀ ም ደረ ጃ
እይ ታ ዎ ች ክብ ደት
ግ ቦች አመ ል ካቾ ች ( (KPI)
(KP I) ክብ ደት
ቁ ከ100 ማ ውን ው ጤ ት ከ (0-
KP I) ክብደት x አፈ ፃፀ ም
% 5)
በ% ደረ ጃ)
ግብ 1
KP I 1
1 ፋይ ና ንስ XX ወዘተ
ወዘተ …

ግብ 1
ደንበኞች KP I 1
2 XX ወዘተ
/ተ ገል ጋ ይ ወዘተ …

ግብ 1
የ ውስጥ KP I 1
3 XX ወዘተ
አሰራር ወዘተ …

ግብ 1
መ ማማር ና KP I 1
4 XX ወዘተ
እድ ገት ወዘተ …

ከ5ቱ የተ ገኘ ው ጤ ት
ከ100% የተ ገኘ ው ጤ ት

የፈ ፃሚ ሙ ሉ ስ ም ………………… የቅ ር ብ ኃ ላፊ ሙ ሉ ስ ም
……………………..

ፊ ር ማ -------------------- ፊ ር ማ -----
--------------------------

ቀ ን --------------------- ቀ ን ------
--------------------
አመሰግናለሁ

You might also like