You are on page 1of 2

የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተጠሪነቱ ለዋና ዳሬክተር ሆኖ ሥልጣንና
ተግባሩ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
      
 የኤጀንሲውን የፋይናንስ፣ የግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራዎች ዕቅድ ያዘጋጃል፤ይመራል፤ ያስተባብራል፡፡

1. ለኤጀንሲው የተፈቀደውን በጀት ሥራ ላይ እንዲውል ለሥራ ክፍሎች ይደለድላል፤  ያስተዳድራል፡፡

2.  የኤጀንሲውን የፋይናንስ፣ የንብረት አያያዝ፣ አጠቃቀም እና የግዥ አፈጻጸም በመንግስት ደንብና


መመሪያ መሰረት ሥራ ላይ እንዲውል ደርጋል፡፡

3.  ከተገልጋዮች የሚሰበሰብ ገቢ በወቅቱ እንዲሰበሰብና ለሚመለከተው አካል ፈሰስ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

4. የሂሳብና የንብረት መዛግብት ወቅታዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

5. የገንዘብና የንብረት ቆጠራ ከመዝገብ ጋር ባላንስ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

6. የገቢና የወጪ ሂሳብ መግለጫዎች እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡

7. የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት (cash flow)  በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው እንዲደርስ ያደረጋል፡፡

8. በመ/ቤቱ በላይ ኃላፊ በሚሰጠው ውክልና መሰረት በተሰጠው የገንዘብ መጠን ገደብ በታች የሆኑትን
ግዥዎች ያጸድቃል፡፡

9.  በአዋጅ ከተፈቀደላቸው መሰረት ማንኛውም የመንግስት ግዥ በኤጀንሲው ከተመዘገቡ እና የባንክ


ሂሳብ ካላቸው አቅራቢዎች የተፈጸመ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

10. የመጫረቻ ሰነዶችን በቡድን በመሆን ይገመግማል ወይም እንዲገመገም ያደርጋል፤ የግዢው መጠን
በመመሪያ መሰፈረት ስለመሆኑ ያረጋግጣል፡፡

11.  በግዢ አጽዳቂ ኮሚቴ የሚጸድቁ ግዢዎችን በሚመለከት ከኮሚቴው ለሚቀርቡ የማብራሪያ
ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣል ወይም ማብራሪያ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

12. በሶስተኛ ወገን የሚከናወኑ ግዢዎችን ይከታተላል፤ ያስተባብራል፡፡

13. ለተገልጋዮች እርካታ በሚሰጥ መልኩ አቅርቦት እንዲሟላ ያደርጋል፡፡

14. የተገዙ እቃዎች በአግባቡ ለሚፈለገው አገልግሎት እንዲሰራጭ ያደርጋል፡፡


15.   ከጥቅም ውጭ የሆኑ ንብረቶች እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡

16.   ዓመታዊ የቋሚ ንብረት ቆጠራ እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡

17.   ለቋሚ ንብረቶች ወቅቱን ጠብቆ የእርጅና ቅናሽ በመስራት ከሌሎች የሂሳብ መዛግብት
እንዲመሳከር ያደርጋል፡፡

18.   የሂሳብ ምርመራ እንዲካድ ያደርጋል፡፡

1.    የስራ ሂደቱን ሠራተኞች የውጤት ተኮር እቅድ እንዲዘጋጅና የአፈጻጸም ግምገማ እንዲካሄድ
ያደርጋል፡፡

You might also like