You are on page 1of 2

ስለ ቼክ

ደንበኞቻችን ሥለ ቼክ ምን ያህል ያውቃሉ?


በቼክ ገንዘብ ሊሰጣችሁ ወይም ቼክ ልትፈርሙ ስለምትችሉ ቀጣዮቹን ቼክን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች እናንሳ።
ቼክ ማለት ገንዘብን ተክቶ የሚያገለግል ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ነው፡፡ ቼክ ሊፈርም የሚችለው በአንድ ባንክ ውስጥ
ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ያለው ሰው ነው፡፡ድርጅት ከሆነ ደግሞ ፈራሚው በድርጅቱ ቼክ ላይ የመፈረም ስልጣን
የተሰጠው መሆን አለበት፡፡ -ቼክ ከመቀበላችሁ በፊት በቼኩ ላይ -የሚከፈለው የገንዘብ መጠን በአሀዝና በፊደል
መፃፉን - የሚከፈለው ሰው ስም እና የባንኩ ቅርንጫፍ መፃፉን -ቼኩን የሰጠው ሰው ፊርማ መኖሩን -ቼኩ
የተፃፈበት ቀን እና ቦታ መኖሩ ማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ መሆኑን የንግድ ህግ አንቀፅ 827 ይደነግጋል። -ቼኩ ለማን
እንደሚከፈል ስም ካልተጠቀሰበት ማንኛውም ቼኩን ይዞ የቀረበ ሰው ይከፈለዋል። ቼኩ በስሙ የተፃፈለት ሰው
ወይም በትዕዛዝ የሚል ካለበት ደግሞ በቀላሉ ከጀርባው በመፈረም ለሌላ ሰው ሊያስተላልፈው ይችላል ።ያም
ሰው በጀርባው ፈርሞ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላል፡፡ -የገንዘብ መጠኑ ያልተጠቀሰበትን ቼክ ፈርሞ መስጠት
አደገኛ ነው ፡፡ ቼኩ የተፃፈለት ወይም የተላለፈለት ሰው የፈለገውን ገንዘብ ሊሞላበት ይችላል፡፡ -ቼኩ የሚከፈለው
ለባንኩ ለክፍያ በቀረበ ቀን ነው። - ሆኖም ቼኩ በን/ሕ/ቁ 857 መሠረት የወጣበት ቀን ከግምት ሳይስገባ ቼኩ ላይ
ከተፃፈው ቀን ጀምሮ በ 6 ወር ውስጥ ለባንኩ ለክፍያ መቅረብ አለበት፡፡ -ቼኩን የሚፈርመው ሰው የክፍያውን ቀን
ቼኩን ከፃፈበት ወይም ቼኩን ካወጣበት ቀን ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ሊያደርገው ይችላል። ለምሳሌ ዛሬ ቼኩን
ሲፅፍ የተፃፈበት ቀን ወደኃላ 7 ወር አድርጎ ቀኑን ቢፅፈው ለክፍያ መቅረብ ያለበት 6 ወር ጊዜ ስላለፈ ባንኩ
መክፈልም ሆነ ያልከፈለበትን ምክንያት ለመግለፅ ሳይገደድ ቼኩ ለክፍያ መቅረብ ባለበት ጊዜ ባለመቅረቡ
ብቻይመልሰዋል፡፡ ዛሬ የሚሰጥህን ቼክ ወደፊት የዛሬ 4 ወር አድርጎ ቀኑ ከተፃፈበት ለክፍያ መቅረብ የሚችለው
ከአራት ወራት በኃላ ካለው ቀን ጀምሮ ባለው 6 ወራት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ቼክ ተቀባዬች የሚሰጣቸውን ቼክ
ገንዘቡን መቀበል ከሚችሉበት ቀን አንፃር በጥንቃቄ የተፃፈበት ቀን ማየት አለባቸው -ቼክ የሰጠው ሰው ቼኩ
ለባንኩ ለክፍያ ከመቅረቡ በፊት ባንኩን እንዳትከፍል ብሎ መከልከል ይችላል። ባንኩም የክፍያ መከልከያ ትእዛዝ
ከደረሰው መክፈል የለበትም። -የተረጋገጠ ቼክ (cpo) የተጠቀሰው ገንዘብ መኖሩ በባንኩ ተረጋግጦ የተቀመጠ
በመሆኑ ከተራ ቼክ የበለጠ አስተማማኝ ነው። -ቼኩን ለባንክ አቅርበህ በቼኩ ላይ የተጠቀሰውን ያህል በቂ ገንዘብ
ከሌለ በሂሳቡ ውስጥ ያለውን ያህል መቀበል ይቻላል። -ለቀረው ገንዘብ ደግሞ ባንኩ ‘‘በቂ ስንቅ ለውም’’ የሚል
የፅሁፍ ማስረጃ ቼኩን ይዞ ለቀረበው ሰው ይሰጠዋል። -በተለምዶ ‘‘ደረቅ ቼክ’’ የሚባለው ለክፍያ ሲቀርብ በሂሳቡ
ውስጥ በቂ ገንዘብ ከሌለው ሲሆን ባንኩ በሚሰጠው ማስረጃ መሰረት ቼክ ሰጪውን ወይም አውጭውን በወንጀል
ያስጠይቃል። ሆን ተብሎ ከተፈፀመ ቼክ አውጪው በወንጀል ህግ አቀፅ 693 መሰረት በቀላል እስራት ወይም ነገሩ
ከባድ ከሆነ ደግሞ ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስርና በመቀጮ ይቀጣል። -ደረቅ ቼኩ የተሰጠው በቸልተኝነት
ከሆነ ደግሞ ሰጭው በመቀጮ ወይም ከንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስር ይቀጣል ፡፡ -ሳይከፈል የቀረውን የቼኩን
ገንዘብ ና ወጭውን ቼኩ የተፃፈለት ወይም ተፈርሞ የተላለፈለት ሰው በፍትሀ ብሔር ከሶ ገንዘቡን ማስመለስ
ይችላል፡፡ -በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ደረቅ ቼክ የሚሰጡ ሰዎች በጥፋታቸው በጥቁር መዝገብ ውስጥ
የሚገቡ ሲሆን ከገንዘብ መቀጮ አንስቶ በቼክ ሂሳብ የማንቀሳቀስ መብታቸውን እስከማሳጣት ቅጣት
ይጣልባቸዋል፡፡ እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው ህጎች ቼክን የገንዘብ ያህል አስተማማኝ ለማድረግ የተደነገጉ ናቸው።
ለግብይት ቅልጥፍና እንዲሁም ለገንዘብ እንቅስቃሴ አመቺነት በቼክ መጠቀሙ ከጥሬ ገንዘብ የተሻለ ዘመናዊ
አሰራር በመሆኑ ቼክ አስፈላጊና ልንጠቀምበት የሚገባ የገንዘብ ሰነድ ነው። ለማንኛውም ቼክ ስንሰጥም ሆነ
ስንቀበል ከላይ የተነሱትን ነጥቦች ልብ እንበል፡፡የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ

You might also like