You are on page 1of 3

የዋና ኦዲተር መ/ቤት ለሥራ ኃላፊዎቹና ለሰራተኞቹ በሪከርድ ሥራ አመራር ጽንሰ ሀሳብ እና በትምህርትና ስልጠና

ዙርያ ስልጠና ሰጠ!


የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለመ/ቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሪከርድ ሥራ አመራር
ጽንሰ ሀሳብና በትምህርት እና ስልጠና ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የስልጠናውን መድረክ
ያስጀመሩት የመ/ቤቱ ም/ዋና ኦዲተር አቶ አባይነህ አቹላ መዝገቦች እና መረጃዎች በስነምግባር መመራትና
መተዳደር እንዳለባቸው ጠቅሰው ከመ/ቤቱ ባህሪ አንጻር ማህደሮች በተለየ ትኩረት እና በጥብቅ ዲሲፕሊን
መመራት ስላለበት ሕጎችንና አሰራሮችን በሚገባ ማወቅ አስፈላጊ ከመሆኑ አንጻር የሚሰጥ ስልጠና መሆኑን
በመጥቀስ ነው።
በማህደርና የሪከርድ ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና የሰጡት ክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የሰው
ሀብት መረጃና ስታትስቲክስ የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ አሚን በስልጠና ሰራተኞች በቂ ግንዛቤ
በመጨበጥ አስፈላጊውን የማህደርና ሪከርድ ስርዓት ተረድተው ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በማስገንዘብ፤የአንድ
መሥሪያ ቤት (ድርጅት) ህልውና፣ ጥንካሬ፣ ያለፈውን ታሪኩና የወደፊት ዕድገቱ እንዲሁም የሥራው ጥራትና
እንቅስቃሴ ባለው የሪከርድ ወይም ሰነዶች አያያዝና አመራር ችሎታ ሊለካ የሚችል ስለሆነ የተሟላ መረጃ ያለው
ድርጅት ወይም ግለሰብ የተሟላ ኃይል አለው ማለት እንደሚቻል ጠቅሰው ሪከርዶች በሚገባ ተደራጅተው
በተፈለጉ ጊዜ ካልቀረቡ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱን በማጓተት በሥራ ጥራትና ቅልጥፍና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ
እንደሚኖራቸው ጠቅሰው ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የሪከርድ ሥራ አመራር ሥርዓት መዘርጋት
አስፈላጊነቱ የላቀ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የማህደርና ሪከርድ ጽንሰ ሀሳብ ስልጠና መድረክ ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የመ/ቤቱ ም/ዋና ኦዲተር አቶ አባይነህ
አቹላ የሚሰጡ የስልጠና መረጃዎችን በማንበብ የተቀላቀሉ መረጃች ካሉ ስርዓት ለማስያዝና በመለያየት በየጎራው
በሀርድና በሶፍት ዌር ለማደራጀት በቅድሚያ የስራ ክፍሉ የሰው ሀያልም ሆነ በጀትም በአግባቡ ተገቢ እንደሆነ
አሳስበዋል፡፡
በትምህርት እና ስልጠና ስልጠና የሰጡት ደግሞ በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ የኢንስፔክሽንና የሰው ሀብት ህጎች ማሻሻያ
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይበቃል አሰፋ ሲሆኑ ተቋማት ዓላማቸውን ለማሳካት እንዲያስችላቸው
የሠራተኞቻቸውን አቅም ለማጎልበትና ለማሳደግ እንዲሁም በስትራቴጂያዊ ዕቅዳቸው የተቀመጠውን የሰው
ሀይል ፍላጎት ለማሟላት የሚረዳቸው በዕቅድ የሚመራ ትምህርትና ሥልጠናን አጠቃሎ የያዘ የሰው ሀብት ሥራ
አመራር ሥራ በመሆኑ የሰራተኞችን ዕውቀት፣ክህሎት፣አመለካከትና አሠራር ዘዴ በመለወጥና በማሳደግ ሥራን
በውጤታማነት በማከናወን የግለሰቦችን አቅም ማጎልበትና የተቋምን የዕቅድ አፈጻጸም ማሳካት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሰው ሀብት ልማት የግለሰቦችንም ሆነ የተቋማትን አቅም ለመገንባት ቁልፍ መሣሪያና የግለሰቦች፣ የቡድንና
የተቋማት የሙያ ዕድገት ትስስር የሚረጋገጥበት ሂደትም መሆኑንም በማብራራት ትምህርትና ሥልጠና በግለሰብ
ባህሪይ፣ አመለካከትና አሰራር ላይ የዕውቀት ደረጃ ለውጥ በማምጣትና ክህሎትን በማሳደግ ሥራን በቅልጥፍናና
በውጤታማነት ማከናወን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከተደነገገው ህግ አንጻር በመተንተን ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሰ/ሀ/ሥ/አመ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወይንሸት ኪታንቦ ከሰራተኞች ለተነሱ
ጥያቄዎች ከመስርያ ቤቱ ባህሪ እና ከሰው ሀብት አሰራር ስርዓቱ አንጻር ምላሽና ማባራርያ ሰጥተዋል፡፡
በስልጠና መድረኩ ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የመ/ቤቱ አስ/ፋ/ዘ/ምክትል/ኃላፊ አቶ አስራት አደሮ የሰው ሀብት
ልማት በአግባቡ ካልተመራ ኪሳራ መሆኑን ገልጸው ለሰራተኞች የትምህርትና ስልጠና ዕድል ሲሰጥ በውል መታሰር
እና በሚሰማራበት ሙያ በአግባቡ ማገልገል እንደሚገባው በመግለጽ መድረኩን አጠናቀዋል፡፡
ዘገባው የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።
#

ለግንዛቤዎ! የቀጠለ…
ክፍል -5- በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሚከናወኑ የኦዲት ዓይነቶች
ባለፈው የግንዛቤ ማስጨበጫ ክፍል 4 ጽሁፍ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲሁም በህግ
የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት ለማሳወቅ ተሞክሯል፡፡ በዚህ በክፍል- 5 ጽሁፍ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት
የሚያከናውናቸው የኦዲት ዓይነቶች በአጭሩ ተጠቅሰዋል፡፡
የፋይናንሻል/እና የህጋዊነት ኦዲት (Financial /and Legal Audit)
የፋይናንሻል ኦዲት መንግስት የፌዴራል ተቋማት የተቋቋሙበትን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲያሳኩ የሚመድበውን
ዓመታዊ መደበኛ በጀት እና ለክልል መስተዳድሮች የሚደለደሉ የድጎማ በጀቶች እንዲሁም ከለጋሽና አበዳሪ
የተለያዩ ተቋማት የሚገኝ ገንዘብ በትክክል በገቢና በወጪ መዝገብ የተመዘገቡና የሚቀርቡ የሂሳብ መግለጫዎችም
የመንግስት የሂሳብ አያያዝ ስርዓትን የተከተሉ መሆናቸውን እንዲሁም ከሚያስፈልጉ ሌሎች መረጃዎችና
ማስረጃዎች ጋር የተገናዘቡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚካሄድ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡ ከዚሁ የፋይናንሻል ኦዲት ጋር
የአሠራር ትስስር ያለው የህጋዊነት ኦዲትም ከላይ የተጠቀሱ የመንግስትና የህዝብ ሀብቶች በየተቋማቱ በስራ ላይ
ሲውሉ አግባብነት ያላቸውን ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የተከተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚካሄድ ነው፡፡
የክዋኔ ኦዲት (Performance Audit)
የክዋኔ ኦዲት መ/ቤቱ ኦዲት የሚያደርጋቸው ተቋማት የስራ አካሄድ እና ሌሎች ሀገራዊ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
የተልዕኮ አፈጻጸም ውጤታማ፣ ኢኮኖሚያዊ አሠራርን የተከተለና የታለመለትን ግብና ውጤት ያስገኘ እንዲሁም
በተነደፈው ዕቅድ፣ የሰው ኃይል፣ ንብረትና የገንዘብ አቅም መከናወኑን ለማረጋገጥ የሚካሄድ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡
የአካባቢ ሁኔታ ኦዲት (Environmental Audit)
የአካባቢ ኦዲት አንዳንዴ ከክዋኔ ኦዲት ጋር በጥምረት የሚከናወን ሲሆን ዓላማውም ለአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ
ተግባራት አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት አንድ አካባቢ በዓለም አቀፍ መስፈርቶች የተወሰነውን የልቀትና
የአካባቢ ብክነት ስታንዳርድና ደረጃ የጠበቀ ስለመሆኑ የሚካሄድ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡
የመረጃ ስርዓት ኦዲት(Information Technology Audit)
የመረጃ ስርዓት( IT) ኦዲት ከፍተኛ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎትን የሚጠይቅ ሲሆን ተቋማት
በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የዘረጉት የመረጃ ስርዓት ተገቢውንና ትክክለኛውን መረጃ የሚያመነጭ ወይም የሚሰጥ
መሆኑን እንዲሁም ለመረጃ ስርዓቱ በቂ የጥበቃ ስርዓት የተዘረጋና መረጃዎቹም ከአደጋ የተጠበቁ ስለመሆናቸው
ለማረጋገጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የኦዲት ባለሙያዎች የሚካሄድ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡
ልዩ ኦዲት (Special Audit) ልዩ ኦዲት መንግስት የአንድን የመንግስት ተቋም የተለየ የፋይናንሻልና ሌሎች
አሰራሮች፣ የሀብትና ንብረት አጠባበቅ ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች የሀገራዊ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም
በልዩ ሁኔታ ለመረዳትና ለማወቅ በሚፈልግበት ወቅት በመ/ቤቱ አማካይነት ከመደበኛ የኦዲት መርሀ ግብር በተለየ
መልኩ የሚከናወን ሲሆን በአብዛኛው በትላልቅ ተቋማዊና ሀገራዊ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ
ተመስርቶ የሚካሄድ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡
ክፍል-6 ይቀጥላል…

ለክልል ሴክተር መ/ቤቶች የውስጥ ኦዲት ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች በፋይናንሻል ኦዲት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው
ስልጠና ተጠናቀቀ!
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለክልል ተቋማት የውስጥ ኦዲተሮች በፋይናንሻል ኦዲት ምንነት
፣ዓይነቶች፤ የስራ ቅደም ተከተል፣የኦዲት ዕቅድ፤የጥሬ ገንዘብ፣የባንክ ሂሳብ፣የቋሚ ንብረት፣የደሞዝ ፣የማጭበርበር
ምርመራ ኦዲቶች እና የሪፖርት አጻጻፍና አቀራራ ዙሪያ ለሁለት ቀናት በሀላባ ከተማ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና
አጠናቀቀ፡፡
ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩት በዋና ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ተመስገን
ክንፉ በስልጠናው ወቅት የውስጥ ኦዲተሮችም ሆኑ የውጭ ኦዲተሮች ሁላችንም አንድ ዓይነት ሙያ ላይ የተሰማሩ
መሆናቸውን ገልጸው ፤የሀገርን ሀብት ከብክነት የመጠበቅ ግዴታ ስላለብን ተባበረን ከሰራን የበለጠ ውጤታማ
መሆን እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡
በየተቋማቱ ያለአግባብ የሚባክነውን የመንግስት ንብረት ለተፈለገው ዓላማ ብቻ እንዲውል ማድረግ እንደሚጠበቅ
የገለጹት አሰልጣኝ የማጭበርበር ተግባር የስራ አመራሩን በዋነኛነት የሚያሳስብ ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ የውስጥ
ኦዲተሮችም ይህንን ተግባር በመከላከልና በመመርመር አንዲሁም በማጋለጥ ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነታቸውን
መወጣት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
የማጭበርበር ተግባርን ለመከላከል የመ/ቤቱ ኃላፊ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የመጀመሪያውን ድርሻ
የሚወስድ ቢሆንም ኦዲተሮችም የራሳቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡በአብዛኛው
በመደበኛ የኦዲት ስርዐት የማጭበርበር ተግባራትን ማወቅ ስለማይቻል ኦዲተሩ በተለያየ ዘዴ ችግሮች ያሉበትን
ቦታ ለይተው ከመመርመር በተጨማሪ የውስጥ ኦዲት ቁጥጥር ስርዐትን በማጠናከርና በመገምገም እንዲሁም
በማጭበርበር ተግባር ላይ የተገኙት ግለሰቦችን በመቅጣት የኦዲት ስርዐቱን የተሸለና ውጤታማ ማድረግ ለማስቻል
ማንበብና እራስን ማብቃት ዋናው ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል፡፡
ከየተቋማቱ በስልጠና የተሳተፉ ባለሙያዎች ጥያቄና አስተያየት ያነሱ ሲሆን በዚህም የውስጥ ኦዲተርን አጠናክሮ
የውስጥ ቁጥጥር ከመዘርጋት አንጻር ተጠሪነቱ ለተቋሙ ኃላፊ በመሆኑ ተጽዕኖዎች እንዳሉ፤ለውስጥ ኦዲት ብቁ
የሰው ኃይል ከመመደብና ለመደቡ ካለው አመለካከትና ግምት ዝቅተኛነት፤የዋና ኦዲተር መ/ቤት ሪፖርት ለውስጥ
ኦዲት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የሚታዩ ክፍተቶችን እንዲሁም የውስጥ ኦዲት መዋቅር ማሻሻልን በተመለከተ
አስተያየታቸው ሰንዝረዋል፡፡
በተጨማሪም በአብዛኛው የኦዲት አሰራር ተግባራዊ የሚደረገው በድህረ-ኦዲት ላይ ሲሆን የአሰራርና የህግ ጥሰት
ከመከሰቱ በፊት መከላከል እንዲቻል ቅድመ ኦዲት ላይ ትኩረት ቢደረግ የሚሉ አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡
ሰልጣኞቹ ላነሱት ጥያቄ እና አስተያየት ምላሽና ማብራርያ ከሰጡት የዋና ኦዲተር መ/ቤት ኃላፊዎች የኦዲት
ጥራት ቁጥጥርና ስርጸት ዳይሬክተር አቶ አበራ ጫኬቦ ሲሆኑ የየተቋማቱ ማናጅመንት የዋና ኦዲተር መ/ቤት
ኦዲተሮች በሚያደርጉት የመግቢያና የመውጫ ስብሰባ ላይ የውስጥ ኦዲቱን ማሳተፍ ተቋማቱ ላይ ያለውን
የኦዲት ግኝቶች ከማስተካከል አንጻር ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው፤የውስጥ ኦዲት ማንኛውንም የተቋሙን
መረጃ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡የፋይናንሻል ስህተቶችን ክትትል በማድረግ ከስር ከስር እያረመ
የሚያስተካክለው ውስጥ ኦዲተር ከመሆኑ አንጻር ወቅታዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ማግኘት እንዲችሉ
ተቋማቸውን ማሳሰብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ከዚህም ባለፈ ሰልጣኞቹ የሰጡት አስተያየት ጥሩ ግብዓት መሆኑን
ገልጸዋል፡፡
የስልጠናው ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ ፈዲላ አደም ከሰልጣኞች
ለተነሱት ጥያቄዎች አስተያየትና ምላሽ የሰጡ ሲሆን እስከ አሁን ባለው ልማድ የውስጥ ኦዲተሮችና የውጭ
ኦዲተሮች የሚታይባቸው የተናጠል አሰራር በመስበር ተባብሮ መስራት እንደሚገባ አስረድረዋል፡፡ለተመሳሳይ አላማ
የተሰማራ ባለሙያ ተመሳሳይ እውቀት ሊኖረው እንደሚገባ የገለጹት ዋና ኦዲተር የውስጥ ኦዲተሮችን አቅም
መገንባት የመንግስትን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከቱ በየጊዜው የሚወጡ
አዳዲስ አሰራሮችን ለማስተዋወቅ ተገቢ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ከዚህ ስልጠና የተገኙን ተጨማሪ ግንዛቤዎች በማከል የየተቋማቸውን ውስጥ ቁጥጥር ስርዓት
ከነበርንበት አሰራር አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ነው ብለ

You might also like