Professional Documents
Culture Documents
አዘጋጅ
ገድሻ ካቶላ(MS.C) ኢትዮጵ
ያ
አርባ
ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ማህበራት ምቹና ቀልጣፋ
የገበያ ትስስር ለመፍጠር የተዘጋጄ ስልጠና
ለመኖር እና ለመኖር.
እኛም የለውጥ ሂደቱን መጀመር አለብን።
አንዳንድ ጊዜ ደስ የማይል አሮጌ ትውስታዎችን, አሉታዊ ልማዶችን እና ቋሚ
አስተሳሰባችንን ማስወገድ አለብን፡፡
1. ለውይይት የሚቀርብ
ችግር
2. የድርጊት መርሐ-ግብር ያወጣሉ
ከዚያም ለበላይ አካል ያስፀድቃሉ
ማስታወቂያ
ለደንበኞችዎ መረጃዎች በመስጠት የእርስዎን ምርት ወይም
አገልግሎት ለመግዛት ይበልጥ ፍላጎት እንዲያድርባቸው መቀስቀሻ
ዘዴ ነው፡፡
ብዙ ገንዘብ ሳያወጡ ምርትዎን ሊያስተዋውቁ የሚችሉባቸውን
ጥቂት ዘዴዎች እንመለከታልን፡፡
መሰረታዊ የማስታወቂያ ዘዴዎች፤
-ሰሌዳዎች፣ ፖስተሮች፣ ብሮሸሮች፣ በራሪና የሚታደሉ ፅሁፍች፤-
በእነዚህ ተጠቅሞ ለደንበኞች ልዩ ቅናሾችን፣ አዳዲስ ምርቶችን፣
ወዘተ. ማስተዋወቅ ይቻላል፡፡
የዋጋ ዝርዝር፤-የሚሸጡትን ምርቶች ዝርዝር በሙሉ ከነዋጋቸው ለደንበኞች
ያሳውቃል፡፡
የፎቶ አልበም፤-የሚሰሯቸውና በክምችት ላይ የሌሉ እቃዎችን ለደንበኞች
ለማሳየት፣
ቢዝነስ ካርድ፤ ስለንግድዎ፣ የት ቦታ እንደሚገኝና የሚሸጧቸውን ምርቶች
ለደንበኞች ያሳውቃል፤
ብዙ ነጋዴዎች በእነዚህ መሰረታዊ ዘዴዎች በመጠቀም ምርታቸውን
የሚያስተዋውቁ ሲሆን ዋናው ነገር ግን በደንበኞች አእምሮ ጥሩ ነገር በቀላሉ
እንዲያዝ/ኢንዲሰርፅ ማድረግ ነው፡፡
ስለዚህ የሚያዘጋጇቸው የፅሁፍ ማስታወቂያዎች በተቻለ መጠን ንፁህና
መልእክታቸውም ቀላልና ቅልብጭ ያለ መሆኑን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
አዘገጃጀታቸውም ከንግዱ ስም፣ ሎጎ፣ ቀለሞች፣ ደዛይን፣ አቅድ(ስታይል)፣
ወዘተ. ጋር ወጥ መሆን አለበት፡፡
ደንበኞች የተሻለ ማስታወስ የሚችሉት አንድ ነገር ደጋግመው ሲመለከቱ
ነውና፡፡
በግራ በኩል ያለው ማስታወቂያ በጣም ብዙ መረጃ ስለያዘ
በደንበኞች የመታወስ እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ሰዎች ላያነቡት
ይችላሉ/አያነቡትም፡፡ በቀኝ በኩል ያለው ግን ንፁህ፣ ቀላልና
ቅልብጭ ያለ መረጃ ይዟል፡፡ ስለሆነም ሰዎችን መሳብ ይችላል፡፡ በግራ
በኩል ከሚታየው ጋር ሲነፃፀር የመነበብና የመታወስ እድሉም የበለጠ
የንግድ ማስታወቂያ ፅሁፎች ለማሳተም ብዙ ወጪ የሚጠይቅ
እንደመሆኑ መጠን በጥንቃቄ መጠቀም ይጠይቃል፡፡
ፓስተሮችዎን የት ቦታ እንደሚለጥፉ፣ ለእነማን በራሪ ፅሁፎች
እንደሚያድሉ፣ ወዘተ. በደንብ አስበው ካደረጉ ማስታወቂያዎ
ውጤት ይኖረዋል፡፡
በየጎዳናው ላይ በራሪ ፅሁፎች ማደል ጎዳና ከማቆሸሽ በስተቀር
ንግድዎን የረባ አያስተዋውቅም፡፡
ብዙ ሰዎች ወዲያውኑ መልሰው ስለሚጥሉት እንዲውም ንግድዎ
በጎዳና ማቆሸሽ መጠየቅ አለበት የሚል ስሜት ይፈጥራል፡፡
ባለብራንድ የማስታወቂያ ቁሳቁሶች፤
የንግዱ የገበያ መለዮ/መታወቂያ (ብራንድ) የተደረገባቸው
እንደኩባያ፣ ኮፊያና ካናቴራ የመሳሰሉ የማስፋፊያ እቃዎች ሲሆኑ
ብዙውን ጊዜ የሚጠቅሙት ሽያጭ ለማነቃቃትና (ለማነሳሳት)
ንግድዎን ለማስተዋወቅ ነው፡፡
ባለብራንድ የማስታዋወቂያ እቃዎች ለመጠቀም የሚከተሉትን
ከግምት ውስጥ ያስገቡ፤
ደንበኞችዎ የሚወዷቸውን እቃዎች ይምረጡ፡፡ ኢላማ ያደረጓቸው
ደንበኞች ምናልባት ህፃናት ከሆኑ አሻንጉሊት ወይም ባሉን ጥሩ
ይሆናል፤ አስራዎቹ እድሜ ውስጥ ያሉና ጎልማሶች ከሆኑ ደግሞ ኮፊያ
ወይም ከናቴራ ይመርጣሉ፡፡
- በብልህነት ያስተዋውቁ፡፡ ለምሳሌ፣ ከናቴራው የሚያምር ከሆነ
ይለብሱታል፡፡ በተቀራኒው አስቀያሚ ከሆነ ምናልባት ሊጥሉት
ይችላሉ፡፡
ባለብራንድ የማስታወቂያ ቁሳቁሶች፤
ከምርትዎ ጋር የሚተጋገዝ ወይም አብሮ መጠቀም የሚያስችል እቃ
ይምረጡ፡፡ ለምሳሌ፣ አረንጓዴዎች አረንጓዴ የአኗኗር አቅድን ስለሚደግፉ
የእነሱ ሎጎ ያለበትን የጨርቅ ቦርሳ ያድላሉ እንጂ ፌስታል አያሰጡም፡፡
ማስታወቂያ ሁልጊዜ ውድ ላይሆን ይችላል፡፡ የራስዎን ፈጠራ
ይጠቀሙ! ወጪያቸው ያልበዛ በጣም ብዙ የማስታወቂያ ዘዴዎች
አሉ፡፡ በበለጠ ፈጠራ ችሎታ ማስተወቂያ ቢሰራ የበለጠ የታላሚዎችን
ትኩረት ይስባል፡፡
የሽያጭ ማስፋፊያ ዘዴዎች