You are on page 1of 6

የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የቤ/ጉ/ክ/መ/ቴ/ሙ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አገልግሎትና የንግድ የምግብና ምግብ የስራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክቶሬት
ነክ ኢንተርፕራይዞች ክትትል
ባለሙያ III

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ


የከተማ የስራ ዕድል ፈጠራና XIII
ኢንተርፕራይዞች ልማት ቡድን መሪ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
አሶሳ
II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት፤
2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-

 ለአገልግሎትና ንግድ ዘርፍ የሚረዱ ማንዋል መመሪያ ማዘጋጀት፣ ጥናት ማካሄድ፣ ከኢ-መደበኛ ንግድና አገልግሎት ወደ
መደበኛ ማሸጋገር፣ ስልጠና መስጠት፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት
ለማፈጠን ነው፡፡
2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡- የአገልግሎትና ንግድ ማንዋል መመሪያ ማዘጋጀት፣ ጥናት ማካሄድ
 በአገግሎት በንግድና ዘርፍ ያልተካተቱ አሰራሮች በመለየት በፖሊሲና ስትራቴጂ ማዕቀፍ እንዲካተቱ የመነሻ
ጽሁፍ ያዘጋጃል፣
 በአገልግሎትና ንግድ ዘርፍ ለሚደራጁ ኢንተርፕራይዞች የአደረጃጀት ደንብና መመሪያ ያዘጋጃል፣
 ለንግድና አገልግሎት ዘርፍ የሚሆኑ ማንዋሎችን ያዘጋጃል፣
 የንግድና አገልግሎት ዘርፍ ስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሠነድ ያዘጋጃል፣ ለዘርፉ አዋጭነት የሚያገለግሉ
ፅንሰ-ሀሳብ ያመነጫል፣
 የሥራ ዕድል መፍጠርያ መስኮችን በመለየት ጥናት ያደርጋል፣
 የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ባለው መልኩ መሰጠት እንዲችሉ ስታንዳርዶች ያዘጋጃል፣
 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሚሰማሩ ንግድና አገልግሎት ሥራዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በጥናት
በመለየት የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፣
 የከተሞቹን የእድገት ደረጃ መሠረት በማድረግ የሥራ እድል እንዲፈጠር የሚያስችል ጥናት ያደርጋል፣
 በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ተወዳዳሪነት ላይ እንቅፋት የሆኑ
ጉዳዮችን በጥናት ይለያል፣ መፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፣

1
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ

 በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የኢንተርፕራይዞችን የክህሎት ክፍተት ዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፣ የተገኘውን የዳሰሳ ጥናት
ውጤት ለቴክኒክና ሙያ ተቋም ያቀርባል፣

 በዘርፉ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ የገቡ የህግና የድጋፍ ማዕቀፎች ያመጡትን ፋይዳ በጥናት
ይለያል፣
 ከአገልግሎት ዘርፍ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች ለመሸጋገር ያሉ ማነቆዎችን በመለየት ጥናት ያካሄዳል፣
 የተለያዩ ጥናቶችን ለማካሄድ የሚረዳ የማስፈጸሚያና በንግድና አገልግሎት ዘርፍ ሞዴል የቢዝነስ እቅዶችን
ያዘጋጅል፣

ውጤት 2፡- ከኢ-መደበኛ ንግድና አገልግሎት ወደ መደበኛ ማሸጋገርና ስልጠና መስጠት፣


 በንግድና በአገልግሎት ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን ኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃን መሰረት በማድረግ ከአገልግሎት ዘርፍ
ወደ አምራች ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፣
 በአዳዲስ የንግድና አገልግሎት አሰራሮች ፣ ደንብና መመሪያዎች ላይ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣
 ከቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ጋር በመተባበር የንግድ ሥራ አመራርና የክህሎት ክፍተት ሥልጠና እንዲያገኙ
ያደርጋል፣
 በትኩረት ዘርፎች የተካተቱ ኢ-መደበኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች በመለየት የዘርፉ ልማት መንግስታዊ ድጋፍ
ተጠቃሚ ለማድረግ ወደ መደበኛ ያዛውራል፣
 ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር በኢ-መደበኛ ንግድ ላይ የተሰማሩትን ወደ መደበኛ ንግድ ስርዓት እንዲሸጋገሩ
ማድረግ፣
 በኢ-መደበኛ የንግድ ስራ ለተሰማሩት ወደ መደበኛ ንግድ ስርዓት እንዲገቡ የግንዛቤ ያስጨብጣል፣
ውጤት 3፡- ክትትል ድጋፍ ማድረግ ፣

 በተለያዩ የሥራ መስክ ለተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዘርፍ ማህበራት እንዲደራጁ በማድረግ
ፍትሐዊ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍንና ገበያንበማረጋጋት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
 በኢ-መደበኛ የንግድ ስራ ለተሰማሩት ወደ መደበኛ ንግድ ስርዓት እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
 በንግድና አገልግሎት የሚሰማሩና የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ምንጭ እንዲሆን
ያደርጋል ፣
 ከኢ - መደበኛ ወደ መደበኛ የንግድ አሰራር ስርዓት እንዲመጡ ለማድረግ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
 በንግድና አገልግሎት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍ የሚያገኙበትን ስልት በመለየት የቴክኖሎጂና
ካፒታል አቅም አጎልብተው ወደ አምራች ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣
 ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች የሚቀርቡበትን አግባብ ያመቻቻል፣
 በመደበኛ ሁኔታ የተሟላ ድጋፍ በመስጠት በአገልግሎት ዘርፍ ነባሮችን በማጠናከር አዲስ ሥራ ፈላጊ ዜጎች የሥራ

2
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ

ዕድል እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል ፣


 ከንግድና አገልግሎት ዘርፎች ወደ ማኑፋክቸሪንግ ከተሸጋገሩት ኢንተርፕራይዞች መካከል የተሻሉ ተሞክሮዎች
ይቀምራል፣
 በአገልግሎትና በንግድ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች በአመለካከት ፣ በምርታማነት፣ በምርት ጥራትና በካፒታል እድገት የተሻለ
ተሞክሮዎችን ይቀምራል፣ ያስፋፋል ፣
 ከቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ጋር በመተባበር የንግድ ሥራ አመራርና የክህሎት ክፍተት ሥልጠና ማግኘታቸውን ይከታተላል ፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች


3.1 የሥራውስብስብነት
 ስራው በተቀመጠው አሰራር መሰረት ተግባራዊ እንድሆን በንግድና በአገግሎት ዘርፍ ያልተካተቱ አሰራሮች በመለየት
በፖሊሲና ስትራቴጂ ማዕቀፍ እንዲካተቱ የመነሻ ጽሁፍ ማዘጋጀት ፣ለንግድና አገልግሎት ዘርፍ የሚሆኑ
ማንዋሎችን ያዘጋጃል ፣የንግድና አገልግሎት ዘርፍ ስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሠነድ ማዘጋጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ
ጥራት ባለው መልኩ መሰጠት እንዲችሉ ስታንዳርዶች ማዘጋጀት፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሚሰማሩ ንግድና
አገልግሎት ሥራዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ፣የከተሞቹን የእድገት ደረጃ መሠረት
በማድረግ የሥራ እድል እንዲፈጠር የሚያስችል ጥናት ማድረግ ፣ከአገልግሎት ዘርፍ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ
ዘርፎች ለመሸጋገር ያሉ ማነቆዎች ማካሄድ፣በንግድና በአገልግሎት ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን ኢንተርፕራይዞች
የዕድገት ደረጃን መሰረት በማድረግ ከአገልግሎት ዘርፍ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ማሸጋጋር፣ ከንግድና አገልግሎት
ዘርፎች ወደ ማኑፋክቸሪንግ ከተሸጋገሩት ኢንተርፕራይዞች መካከል በአመለካከት፣ በምርታማነት፣ በምርት ጥራትና
በካፒታል እድገት የተሻለ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋፋት ነው፡፡
 uY^ ¡”¨<” ¨pƒ ¾T>ÁÒØS< ‹Óa‹ የመረጃ እጥረት፣ ባለድርሻ አካለት ለዘርፉ ትኩረት አለመስጠት፣ ሥራ ፈላጊ
ዜጎች ለዘርፉ ያላቸው ግንዛቤ ውስን መሆን፣ የአንቀሳቃሾች የጠባቅነት ችግር ሲሆን መረጃዎችን እንዲደራጁ
ማድረግና ኢንተርፕራይዞች የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ተካታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን
መስራት ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋፋት ከኢ - መደበኛ ወደ መደመበኛ የተሻገሩ ኢንተርፕራይዞች ያገኙትን
ጥቅም ማስረዳት፣ ካባለ ደርሻ አካላት ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይት ማድረግ፣ ወጣቶችንና ሴቶችን መድረኮችን
በማዘጋጀት ለዘርፉ ያላቸው አመለካከትእንዲየር ተከታታይ ስራዎችን መስራት ነው ፡፡

3.2 ራስንችሎመስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 የስራ ማኑዋሎች' ስታንዳርዶች' የሥራ ቅደም ተከተሎች ' ደንቦችና መመሪያዎች በአጠቃላይ ዕቅዶች መሰረት
በማድረግ የሚከናወን ነው፡፡
3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ

3
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ

 ተገቢውን የጥራት ደረጃ ጠብቆ በተሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሰረት ስለመከናወኑ በመጨረሻ ክትትልና ድጋፍ
ይደረግለታል፡፡
3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነትለሥራውጤት /Responsibility for Impact/፣
 ስራው የአሰራር እስታንዳርዶች ደረጃቸውን የጠበቁ አንዲሆን ለማድረግ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሚሰማሩ
ንግድና አገልግሎት ሥራዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት ጥናት ያካሄዳል፣ በአዳዲስ የንግድና አገልግሎት አሰራሮች፣
ደንብና መመሪያዎች ላይ ስልጠናዎችን መስጠት፣ የሥራ ዕድል መፍጠርያ መስኮችን በመለየት ጥናት ማድረግ፣ በንግድ ዘርፍ ሞዴል
የቢዝነስ ዕቅዶች ማዘጋጀት፣ በንግድና በአገልግሎት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ ማድረግ፣
በመደበኛ ሁኔታ የተሟላ ድጋፍ በመስጠት በአገልግሎት ዘርፍ ነባሮችን በማጠናከር አዲስ ሥራ ፈላጊ ዜጎች የሥራ ዕድል እድል
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ በአገልግሎትና በንግድ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች በአመለካከት፣ በምርታማነት፣
በምርት ጥራትና በካፒታል እድገት የተሻለ ተሞክሮዎች መቀመርና ማስፋፋት ነው፡፡ ስራው በሚጠበቀው ደረጃና ጥራት እንዲሁም
በአግባቡ ባይከናወን በተቋሙ ዕቀድ አፈጻጸም ላይ እና በስራ እድል ፈጠራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡

3.4 ፈጠራ
 በንግድና አገልግሎት አሰራር እና አተገባበር ዙሪያ ጥናትና ምርምር ማድረግ፣ የፖሊሲና ስትራቴጂ ሀሳብ ማመንጨት፣ የሥራ
ዕድል መፍጠርያ መስኮችን በመለየት ጥናት ማድረግ፣ የስልጠና የግንዛቤ ማስጨበጪያ ስልቶችን መቀየስ፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው ከውስጥ ከቅርብ ኃላፊው፣ ከክፍሉ ሰራተኞች፣ ከተለያዩ ስራ ክፍሎች ሰራተኞችና ዳይሬክተሬቶችና ከውጭ ከባለድርሻ
አካላት፣ ከማህበራትና ተገልጋዮች ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ
 ሥራው ሪፖርት ለማድረግ፣ መመሪያ ለመቀበል፣ መረጃ ለመለዋወጥና የስራ ግብአቶችን ለማሟላት፣ ለማማከር፣
ለመወያየት፣ የፕሮጀክቶች ዝርዝር እና ቅድመ ዝርዝር ጥናት ላይ ግምገማ ለማካሄድ፣ ሥልጠናዎችን ለመስጠት፣
ተሞክሮዎችን ለመቀመር፣ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግና የስራ አፈጻጸሙን ለማሻሻል ነው፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ሥራው መጠነኛ የሥራ ግንኙነት ማድረግን የሚጠይቅ ሲሆን ከሥራ ጊዜው 35 በመቶ ይሆናል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለም
3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ
 የለም
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ

4
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ

 የለም
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራው ኮምፒዩተር ፣ ጠረጴዛ ፣ ወንበር ፣ ሼልፍ ፣ ላፕቶፕ ፣ ፕርንተርና ለሥራ ስለሚያስፈልገን በአግባቡ የመያዝና
የመጠቀም ኃላፊነት አለበት ግምቱም 70,000 ይደርሳል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ስራው በተቀመጠው አሰራር መሰረት ተግባራዊ እንድሆን በንግድና በአገግሎት ዘርፍ ያልተካተቱ አሰራሮች በመለየት
በፖሊሲና ስትራቴጂ ማዕቀፍ እንዲካተቱ የመነሻ ጽሁፍ ማዘጋጀት ፣ለንግድና አገልግሎት ዘርፍ የሚሆኑ
ማንዋሎችን ያዘጋጃል ፣የንግድና አገልግሎት ዘርፍ ስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሠነድ ማዘጋጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ
ጥራት ባለው መልኩ መሰጠት እንዲችሉ ስታንዳርዶች ማዘጋጀት፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሚሰማሩ ንግድና
አገልግሎት ሥራዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ፣የከተሞቹን የእድገት ደረጃ መሠረት
በማድረግ የሥራ እድል እንዲፈጠር የሚያስችል ጥናት ማድረግ ፣ከአገልግሎት ዘርፍ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ
ዘርፎች ለመሸጋገር ያሉ ማነቆዎች ማካሄድ፣በንግድና በአገልግሎት ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን ኢንተርፕራይዞች
የዕድገት ደረጃን መሰረት በማድረግ ከአገልግሎት ዘርፍ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ማሸጋጋር፣ ከንግድና አገልግሎት
ዘርፎች ወደ ማኑፋክቸሪንግ ከተሸጋገሩት ኢንተርፕራይዞች መካከል በአመለካከት፣ በምርታማነት፣ በምርት ጥራትና
በካፒታል እድገት የተሻለ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋፋት የሚጠይቅ ሲሆን ከሥራ ጊዜው 65 በመቶ ይሆናል፡፡

3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት
 ሥራው በክትትልና ድጋፍ ወቅት ከኢ-መደበኛ ወደ መደበኛ ላለመሸጋገር ከኢንተርፕራይዞች ጋር የሚፈጠሩ
አለመግባባቶች፣ ጭቅጭቆች፣ ክርክሮች እንዲሁም በአንዳንድ ሰነዶችና ፕሮፖዛሎችና ጥናቶች ዙሪያ የሚነሱ
ትችቶችን ተቋቁሞ መስራትን ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 ሥራው የተለያዩ ጥናታዊ ፁሁፎች፣ መጽሀፍትና ሪፖርቶች ማንበብን፣ በኮምፒውተር መጻፍን ይጠይቃል፡፡ የስራ
ሰአቱም 35% ይሆናል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
 ስራው በመቀመጥ 70%፣ በእግር በመጓዝ 10%፣ ፣በመቆም 20% ይከናወናል፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 የለም
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
 ሥራው አልፎ አልፎ በመስክ ስራ ለወባና ለውሀ ወለድ በሽታ ሊጋለጥ ይችላል ፡፡
3.9. እውቀትና ክህሎት፣
3.9.1. ትምህርት

5
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ

የትምህርት ደረጃ የትምህርት ዓይነት


የመጀመሪያ ዲግሪ ቢዝነስ ማኔጅመንት፣ማርኬቲንግና ተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ
3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ፤
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
6 / ስድስት / ዓመት በኢንተርፕራይዝ ልማት ፣ በንግድ ዘርፍ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like