You are on page 1of 7

በአብክመቴክኒክ፤ሙያናኢንተርፕራይዞችልማትመምሪያ

የሰሜን ጎንደር ዞን የገበያልማትናግብይት ቡድን

የ 2014 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ

ሰኔ/2013 ዓ/ም

ደባርቅ

መግቢያ
ልማትን በማፋጠንድህነትን ለመቀነስ ኢንተር ፐራይዞችን በመመስረታና የሚያመርቱት
ምርት በገበያ ላይ በመጠን በዋጋና በጥራትተወዳዳሪ እንዲሆን እና የገበያ ትስስር በመፍጠር
ልማታዊ ባለሃብት ለመፍጠር ተግባሩን የ 2013 በጀት አመት እቅድ ከዝግጅት ምእራፍ እስከ
ትግበራ ባደረግነው ጥረት የበጀት አመቱን የታቀዱ የቁልፍና የአበይት ተግባራት አፈፃፀም
ግምገማ በመነሳት የ 2014 በጀት አመት እቅድ እንደሚከተለው ታቅዷል
የ 2013 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ
2. ቁልፍ ተግባራት
2.1 የአቅም ግንባታ ስራዎች

የለውጥ ሰራዊት ግንባታ

በለውጥ ሰራዊት ግንባታ የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ በስራ ሂደቱ
የሚገኙ ባለሙያዎች አደረጃጀቶች በግንባር ቀደሞች እንዲመሩና ሰራዊት ሁነው ተግባራትን በውጤታማነት
መፈጸም እንዲችሉ በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በግብአት፣ በአደረጃጀትና በአሰራር ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን
በማጥበብ ተቀራራቢ አስተሳሰብና ዕውቀት ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በመልካም አስተዳደር
የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም በጥንካሬና በእጥረት ተለይተው እንደሚከተለው ቀርቧል፡

 በአመለካከት
 ግንዛቤ ፈጠራ

የ 2013 በጀት ዓመት የታቀዱ ተግባራትን በተሳካ ሁኔታ መከናወናቸውን፤ በክንዋኔ ወቅት የነበሩ ጠንካራ
ጎኖችን፤ እጥረቶችን፤ የወደፊት አቅጣጫዎችንና በመለየት የ 2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ለ 8 የወረዳና ከተማ
የገበያ ልማትና ግብይት ቡድን 31 ወንድ 15 ሴት በድምሩ 46 አስተባባሪዎች የተሻለ የስራ አፈፃጸም
ማስመዝገብ የሚያስችል ግንዛቤ እንዲይዙ ኦሪንቴሸን በመስጠቱ በየደረጃው ያለው መዋቅር ዕቅዱን
በዕምነት ይዞ በመንቀሳቀስ የበጀት ዓመቱን የቁልፍና የአበይት ተግባራት ዕቅድ በተሻለ መፈጸም
ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ በትኩረት ዘርፎች ለተሰማሩ ለ 1632 ኢንተርፕራይዞች (3599 አንቀሳቃሾች) ስለምርት
ጥራትና ደረጃ፤ ደንበኛ አያያዝ፤ በመንግስት በኩል ስለሚደረጉ የገበያ ድጋፎች እና ኢንተርፕራይዞች የተሸለ
የገበያ ትስስር ለመፍጠር ማሟላት ስለአለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ
ከክልል ተዘጋጅቶ የተላከላቸውን የግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነዶችን ከባቢያዊ በማድረግ ለ 1284 ኢንተርፕራይዞች
(ወንድ 1810 ሴት 2424 በድምሩ ለ 4234 አንቀሳቃሾች) በየስራ ቦታቸው እና አደረጃጀትን መሰረት ባደረገ
መልኩ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተሰርቷል፡፡
የዕቅድ አፈጻጸም ከበጀት ዓመቱ በኢንተርፕራይዞች 82% እና በአንቀሳቃሽ 117% መፈጸም ተችሏል፡፡
ለኢንተርፕራይዝ (አንቀሳቃሾች) በተሰጠ ግንዛቤ ፈጠራ እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ ያለበትን የግንዛቤ
ውስንነት ለይቶ ከመስጠት አንጻርና በተደራሽነቱ ውስንነት ቢኖረውም ግንዛቤ የተፈጠረላቸው በርካታ
አንቀሳቃሾች ደንበኛ ተኮር ምርት በማምረት፤ ፤ በደንበኛ አያያዝ፤ በአገር ውስጥ አገር ያሉ
የገበያዕደሎችንአፈንፍኖከመጠቀምአንፃር፤ በየደረጃው በሚዘጋጁ የንግድ ትርዕይትና ኤግዝቢሽን ለመሳተፍ ያላቸው
ፍላጎትና እያመጡትያለዉለውጥአናሳ መሆኑን በተደረገ ግምገማ መገንዘብ ተችሏል፡፡
ስለዚህየነበሩንንየግንዛቤፈጠራአፈፃጸምገምግመንያገኘናቸውንድክመቶች
ቀርፈንመልካምተሞክሮዎቻችንንአጠናክረንበቀጣይበጀትዓመት
እያንዳንዱኢንተርፕራይዝያለበትንየግንዛቤውስንነትናፍላጎት በመለየት የግንዛቤ መፍጠርያ ሰነደ
በማዘጋጀትበህዝብክንፍየልማትቡድንአደረጃጀትንተከትለን
ግንዛቤፈጠራውለሁሉምአንቀሳቃሾችተደራሽበሆነመልኩአጠናክሮለመስራትጥረትለማድረግ ተሞክሯል፡፡

2.2 ክህሎት
 ዕቅድ ዝግጅት

፤ የ 2013 ዓ.ምበጀት ዓመት ፊዚካል ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም የ 2014 ዓ.ም እቅድ ታቅዷል፤ የልማት
ቡድን ዕቅድ፤ የመልካም አስተዳደር ዕቅድ፤የኪራይ ሰብሳቢነት እና የቡድን ቻርተር በማዘጋጀት ለወረዳዎች
በማውረድ ወደ ተግበራ በመገባቱ በተሻለ መልኩ ስራ መሰራት ተችሏል፡፡
2.3 አደረጃጀት
በየደረጃው ለቡድኑ የተመደበ ባለሙያ ከተፈቀዱ 76 የስራ መደቦች የተመደበ የሰው ኃይል ወንድ 38 ሴት 18
በድምሩ 56 ባለሙያዎች ከዞን እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ የሚገኙ የስራ ሂደቱ ባለሙያዎች
በ 9 የለውጥቡድን ተደራጅተው በአመለካከት፤ በክህሎት፤ በግብዓት፤ በአሰራርና በአደረጃጀት የሚታዩ
ችግሮችን በማስወገድ ተቀራራቢ አስተሳሰብ በመፍጠር የሰራዊት አቋም እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡
በለውጥ ቡድን በሚደረገው የመማማር መድረክ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች በአመለካከት፤ በክህሎት፤
በግብዓት፤ በአሰራርና በአደረጃጀት የሚታዩ ችግሮችን በማስወገድ ተቀራራቢ አስተሳሰብ በመምጣቱ
ለተገልጋይ ማህበረሰብ የተሸለ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን በመምሪያው የገበያ ልማትና ግብይት ቡድን
ከመጡ በርካታ ተገልጋዮች መካከል ከተሰጡ አስተያየቶች በተሰጣቸው አገልግሎት እርካታ እንዳገኙ
አስተያየት ሰጠዋል፡

ስለዚህ በቀጣይ 2014 በጀት ዓመት በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች በአመለካከት፤ በክህሎት እና በአሰራር
ተቀራራቢ አቅም ፈጥረን የተሸለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል የመማማር መድረኩን አጠናክረን
የምንቀጥልበት ይሆናል፡፡

2.4 ከአሰራር አንፃር


የአካባቢ የገበያ አማራጮችን በመለየትና አቅዶ ከመስራት አንፃር፤- ኢንተርፕራይዞች በጥራትና በዋጋ
ተወዳዳሪ የሆነ ምርት እንዲያመርቱ በመደገፍ፤ ለግብይት ማሳለጫ የተለያዩ ሰነዶችን በግብዓትነት በማዋል፤
በየደረጃው በሚዘጋጁ የተለያዩ የምርት ማስተዋወቅያ ስልቶች በማዘጋጀትና ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ
እና በየደረጃው የሚገኙ የገበያ አማራጮችን በመለየት ወደ ገበያ እንዲገቡ በተደረገ ጥረት በሀገር ዉስጥ የገበያ
ትስስር መፈጠሩ አበራታች ነው፡፡

በቀጣይ 2014 በጀት ዓመትም ይህን አጠናክሮ በማስቀጠል በዋናነት በተመሳሳይ ስራ መስክ የተሰማሩ
ኢንተርፕራይዞችን ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች እና ከተቋማት ጋር እንዲሁም በጎንዮሽ እርስ
በእርሳቸው በምርትና በግብዓት ዘላቂነት ባለው አሰራር በማስተሳሰር ዉጤታማ የገበያ ትስስር የመፍጠር ስራ
መስራት ይጠበቅብናል።
2.5 የግብዓት አጠቃቀም
ለስራዉ የሚመደበዉን የመንግስት ንብረት በአግባቡ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ በመጠቀም የሂደቱን
ተግባራት በማከናዎን ላይ የምንገኝ ሲሆን ከሚመለከታቸዉ ጋር ሚደረጉ የስልክ ግንኙነቶች ስራወችን በአንድ
በማቀናጀት መገናኘት መቻሉ ወጭ መቆጠብ ተችሏል፡፡
የ 2014 በጀት አመት እቅድ አላማዎች፣ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት
. 1. ቁልፍ ተግባራት
 የማስፈፀም አቅም ግንባታ
አላማ፡- የስራ የቡድኑአደረጃጀቶች በልማት ሠራዊት አደረጃጀት ሰራዊት ሆነው የሚንቀሳቀሱትን ከመምሪያው
እስከ አንድ ማዕከል የለውጥ ቡድኖች፣አደረጃጀቶች 100% በማድረስ የመፈፀም አቅማቸውን
በማሳደግ በ 2014 በጀት አመት እቅድ የተጣሉ ግቦችን በማሳካት የዞኑን ህዝብ የኑሮ ደረጃ
ማሻሻል ፡፡

ግብ-1፡-ከላይ እስከ ታች ያለውን ባለሙያ የመፈፀም አቅሙን ማሳደግ፡፡


ዋና ዋና ተግባራት፣
አመለካከት
በየደረጃዉ ለሚገኙ ለ 9 የለውጥ ቡድንና አደረጃጀት ተልኮአቸውን እንዲወጡ ለባለሙያዎች
በስትራቴጅዎችና መመሪያዎች የድጋፍ ማእቀፎች ዙሪያ አዲስ ለሚቀጠሩ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት
የአመለካከት አንድነት መፍጠር

በቡድኑ አመታዊ እቅድ አፈፃፀም በነበሩ መልካም አፈፃፀሞች፣ የአመለካትና ተግባራዊ ችግሮች መግባባት መድረስ
በ 2014 በጀት አመት እቅድ ግቦችና የአፈፃፀም አቅጣጫዎች ላይ በወረዳና ከተማ አስተዳደሮ ከሚገኙ የስራ
ሂደቶች ጋር መግባባት መፍጠር
በየደረጃዉ ላሉ ባለሙያዎችሪፖርታቸውን መነሻ በማደረግ በየወሩ የስልክ በየሩብ ዓመቱ የጹሁፍ ግብረ-መልስ
በመስጠት በነበሩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች የታዩ የአመለካከትና የተግባር መዛነፎች እንዲታረሙ ይደረጋል
በእቅድ ዝግጅት ወቅት ትንሽ አቅዶ እሷን በመፈፀም የተሻለ ሆኖ መገኘት፤ የእቅድ የጥራት ችግር በተለይም
የአካባቢን ፀጋዎች ቆጥሮ ያለመያዝና ህዝቡን ተጠቃሚነት በረጅሙ ያለማሰብ የአመለካከት ችግር በትግል
በየደረጃዉ መፍታት፤
ክህሎት
በ 2013 አመት አመት አፈፃፀም ግምገማና በ 2014 በጀት አመት እቅድ ላይ 6 ወረዳዎችና ለ 2 የከተማ
አስተዳደሮችየቡድኑ አስተባባሪዎችን በማሳተፍ አቅማቸዉ መገንባት
የበላይ አካልን እቅድንና የአካባቢ ፀጋን መነሻ ያደረገ እቅድ በየደረጃዉ ማዘጋጀት
በየደረጃዉ ቢያንስ አንድ እርከን ዝቅ በማለት የወጣዉን እቅድ አፈፃጸም በማየት ድጋፍ መስጠት
በየሩብ አመቱ የዕቅድ አፈፃጸም ግብረ-መልስና የቀጣይ አቅጣጫ በመስጠት የባለሙያዎችን ክህሎት ማሳደግ፡፡

በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች ማስፈፀሚያ ደንብና የአሰራር መመርያዎችን በማውረድ ቀልጣፋ


አሰራር እንዲከተሉ ማድረግ፡፡
አደረጃጀትና አሰራር
ከዞን እስከ አንድ ማዕከል የተደራጀውን 9 የለውጥቡድን አደረጃጀት የታቀፉትን 56 ሠራተኞችን የማጠናከር
(የጎደለ ሙያተኛን የማሟላት) ስራ መስራት
100% የለውጥ ቡድኖች አደረጃጀቶች በግንባር ቀደሞች እንዲመሩ ማድረግ
የልማት ቡድኖች በየሳምንቱ እየተገናኙ እርስ በእርስ የሚረዳዱበትና በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ
ተወያይተው የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያስቀምጡ ማድረግ

በቢ.ኤስ.ሲ የባለሙያዎች እቅድ እንዲታቀድ፣ በየወሩ እና በየ 6 ወሩ የፈፃሚዎችን የውጤት ተኮር ዕቅድ


አቅዶ ውል መያዝና ውጤት መሙላት ግብረመልስ መስጠት፣

ከየቡድኑ በየወሩ ዕቅድ አፈፃጸማቸው ላቅ ያለ ባለሙያ በመለየት እውቅና መስጠት

በአፈፃፀማቸው ወደ ኋላ የቀሩትን ወረዳና ፣ ከተሞች፣ እንዲሁም የአንድ ማዕከል አገልግሎት


ጣቢያዎችንና ፈፃሚዎችን ተከታታይ ድጋፍ በመስጠት ማብቃት

ግብዓት አቅርቦት
መመሪያዎች ፤ደንቦችና ሰትራቴጅዎች በየአካባቢዉ የሌሉት ተለይቶ እንዲቀርብ ማድረግ

የዞኑንየቡድኑን እቅድ ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሸንሽኖ በመነሻነት እንዲያገለግል መስጠት


II. አበይት ተግባራት
አላማ፡-ምርትና አገልግሎትን በገበያ በማስተሳሰር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
በማድረግ ልማታዊ ባለሀብት በመፍጠር የዘርፉን ልማት ማስፋፋት፣
ግብ-1 በየደረጃው ለሚገኙጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችንልማት ዘርፍ የትኩረት መስኮች ላይ በቂ
ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለ 1600 ኢንተር ፕራይዞች ለ 4800 አንቀሳቃሾች ግንዛቤ ይፈጠራል ፡፡
ግብ-2፡-
በሀገርውስጥገበያበእድገትተኮርዘርፍየተሰማሩትንየኢንተርፕራይዞችንምርትናአገልግሎትመንግስታዊናመንግስታዊካልሆ
ኑከተቋማትናእርስበርስበጎንዮሽበማስተሳሰርከሽያጭየሚገኘውንገንዘብብር 123,072,000 በማድረስለ 1721 ኢንተር
ፕራይዞችን(5162 አንቀሳቃሽን)
ማለትምአሁንበስራላይያሉኢንተርፕራይዞችንናአንቀሳቃሾችንእንዲሁምበ 2014 ዓ/ምይፈጠራሉከተባሉትኢንተርፕራ
ይዞችመካከልበከተማእናበገጠርበድምሩ
1721 ኢንተርፕራይዞችንተጠቃሚበማድረግየገበያተወዳዳሪነትንናትርፋማነትንማሳደግ።
ዋና ዋና ተግባራት
የአካባቢ የገበያ አማራጮችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በመለየት ያለዉን የገበያ ዕድል አሟጦ በመጠቀም
ኢንተርፕራይዞቻችንን በሀገር ዉስጥ ገበያ ተጠቃሚ ለማድረግ በስፋት መስራት
በጨርቃጨርቅና አልባሳት፤ የቆዳ እና የዕደ ጥበብ ውጤቶች የተለያዩ ምርት ናሙናዎችን በማሰባሰብና
ለገዥ ድርጅቶች በማሳየት የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ድጋፍ ማድረግ
የዕድገት ተኮር ዘርፎች በጥናት ላይ ተመስርቶ በመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑከተቋማትና በርስ በርስ
በግብይት ስርዓቶች መሰረት የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት
ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚነት ማሳደግ

በጨ/ጨርቅና ልብስ ስፌት ኢ/ዞችን ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር በተለዩ በምርትና ግብአት
ዓይነቶች ማስተሳሰር

ግብ 3 ከማዕከል እስከ ዞን 4 ንግድ ትርዒትና ኤግዚቢሽን በማካሄድ ከምርትና አገልግሎት ሽያጭ


ብር 600,000 በማስገኘት 176 ኢንተርፕራይዞችን (528 አንቀሳቃሾችን) ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ
የሚጎበኝ ህዝብ 800 ማስጎብኘት ፡፡
ዋና ዋና ተግባራት
 ከአንድ ማዕከል እስከ ዞንለሚካሄደዉ ንግድ ትርዒትና ኤግዚቢሽን በተዋረድ ሰፊ ድጋፍ በመስጠት
ዉጤታማ እንዲሆን ይደረጋል
 ለኢንተርፕራየዞቻችን ሰፊ ግንዛቤ በመፍጠር ከጠባቂነት አመለካከት ተላቀዉ ተሳትፎአቸዉን ለማሳደግ
መስራት
 የግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነዶችን በማዘጋጀት እና ግንዛቤ በመፍጠር በዕደገት ተኮር ዘርፍ የተሰማሩ
ኢንትርፕራየዞች በስፋት እንዲሳተፉ የማድረግ ስራዎችን መስራት
 የአካባቢዉ ህብረተሰብ በገበያዉ ሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ሰፊ የቅስቀሳ ስራዎችን በመስራት
የኢንተርፕራየዞችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
በአገር አቀፍ ደረጃናከዞኑ ዉጭ በሚያዘጋጁ ንግድ ትርዕይትና ኤግዝቢሽን 2 ኢንተርፕራይዞችን
በማሳተፍብር 558096 የገበያ ትስስር እንዲፈጠር በማመቻቸት 176 አንቀሳቃሾችን ተጠቃሚ ማድረግና
2140 ጎብኝ ማስገ 0 ብኘት፡፡
የአጋር አካላትን ማለትም የዘርፍ ምክርቤትን፤ የቀበሌ አስተዳደርን፤ንግድ ጽ/ቤትን በኮምቴ ደረጃ
በማካተት ውጤታማ ስራ መሰራት

ግብ -4 ነባር 2 ሰንበት ገበያዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የመሸጫ ቦታ ችግር ያለባቸውን የኢንተርፕራይዞችን


ለ 20 ኢንተርፕራይዞቸንበማሳተፍ ችግር በመፍታት በሚፈጠረው የገበያ ትስስር ብር 20,000 ተጠቃሚ
ማድረግ፤

በክልሉ ዌብ ሳይት ምርቶቻቸዉን በማስተዋወቅ ሰፊ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር መስራት

ግብ-5፡-የውጭ አገር የገበያ ትስስር በመፍጠር 17,858USD በማግኘት አዲስእና ኢንተርፕራይዞችን 2 (8 አንቀሳቃሾችን
ተጠቃሚ በማድረግናበአለም አቀፍ ገበያ በምርት ጥራትና መጠን ተወዳዳሪነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን
ማሳደግ
ዋና ዋና ተግባራት
በማኒፋክቸሪንግ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራየዞች ምርት በጥራት እንዲያመርቱ በማድረግ
የዉጭ ሀገር ገበያ ዉስጥ እንዲገቡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተጠናከረ የኢንዱስትሪ ኤክስትኔንሽን
አገልግሎት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ ስራዎችን መስራት
ከደንበኞች ጋር የሚኖራቸዉን ቁርኝት ማለትም ከካፓኒዎች፡ ከግል ደንበኞችና ከወኪሎቻቸዉ ጋር
ያላቸዉን ግንኙነት አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ወጥ በሆነ መልኩ ድጋፍ ማድረግ
በምርት ጥራት እና ስታንዳርድ የተጠናከረ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት እንዲያገኙ
በማድርግ በቅርጽ;በጥራትና በከለር ተፈላጊዉን ምርት እንዲያመርቱ የተጠናከረ ድጋፍ የደረጋል
ለኢንትረፕራይዞችስለ አለም አቀፍ ገበያ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የተወዳዳሪነት
አቅማቸዉ እንዲጎለብት ጥረት ይደረጋል
ምርትና አገልግሎታቸዉን በፌደራልና በክልል ድህረ ገጾች የማስተዋወቅ ስራዎች በስፋት ይሰራል
ቀደም ሲል ወደ ዉጭ ገበያ የገቡ ኢንትረፕራይዞችን ልምድ በመቀመር በአዲስ ለሚገቡ
ኢንተርፕራይዞች ትምህርት እንዲሆን በስፋት ይሰራል፡፡
ግብ-6፡- የእድገትደረጃ ክፍተት መሰረት ባደረገ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንድጋፍ እንዲደረግላቸው በማድረግ
ለ 2100 ኢን/ዞች እና 6300 አንቀሳቃሾችን የ ኦዲት ና ለ 3150 ኢንተረፕራይ 3450 አንቀሳቃሾችንየቅድመ ኦዲት
አገልግሎት መስጠት
ገብ-7፡- ለጥ/አ/ኢን/ዞች የፋይናንስ ቸግር ለመፍታት የብድር አቅርቦትን 108,128,518 ብር በማድረስ ለ 1200 ኢን/ዝ
እና ለ 3600 አንቀሳቃሾች ተጠማቂ በማድረግ የሚቀርበውን ብድርር ከቁጠባ ለመሸፈንከኢንተር ፕራይዝ 19,898,452
የግዴታ ቁጠባ 68604363 በተማሪ 3305167 ከማህበረሰብ 4320536 ከተቋማት 120,000,000 ጠቅላላ ቁጠባ
108,128,5187 ብርማስቆጠብ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን የብድር ማስመለስ ምጣኔን 100% በማስጠበቅ የኢን/ዞችን
ተጠቃሚነት ማሳደግ ነው፡፡

10 ግብ-5.ዘርፈብዙጉዳዮች
የሴቶችን ተጠቃሚነት 35% የወጣቶችን ተጠቃሚነት 80% እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት
100% ለማድረስ ጥረት ማድረግ
ዋና ዋና ተግባራት
ለሴቶችና ወጣቶች የገበያ አገልግሎት እንድመቻችላቸዉ ጥረት ማድረግ
በሴቶች ላይ ያለው የተዛባ አመለካከት እንዲለወጥ በተለያዩ ጊዜያት የውይይት መድረክ ማዘጋጀት
የሴቶችንና ወታቶችን ተሳትፎ ሊያሳድጉ የሚችሉ የድጋፍ አሰጣጥ ተግባራትን ማከናወን፣
የአካል ጉዳተኞች በሚፈጠሩ የገበያ እድሎች ልዩነት ሳይደረግባቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ
ልዩ ፍላጎት ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቀዳሚ እድል ለመስጠት ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
100% በማስጠበቅ የኢን/ዞችን ተጠቃሚነት ማሳደግ ነው፡፡

You might also like