You are on page 1of 23

የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ

አሰጣጥ እና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 06/2014

ሰኔ /2014 ዓ/ም

አሶሳ

1
መግቢያ

የመንግስት ሰራተኛው በጎ በሆነ ማህበራዊ ህይወት ላይ የተመሰረተ አመርቂ የስራ ውጤት እንዲያስመዘግብ
ለማብቃት እና የስራ ብቃትን ለማጎልበት የስራ ቦታን ለሰራተኞች ጤንነትና ደህንነት በሚስማማ መልኩ
ማዘጋጀት፣ማደራጀት፣ማሻሻልና መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡አንድ ሠራተኛ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት
እንደሥራው ፀባይ ሙሉ በሙሉ ይሁን በከፊል ጤንነቱን እና ደህንነቱን ከተለያዩ የሥራ ቦታ የጤና ጠንቆችና
ጉዳቶች ለመከላከል የሚረዱ የአደጋ መከላከያና የሥራ መሳሪያዎች ወይም ልብሶች መጠቀሙ አስፈላጊ ሆኗል፡፡

ሠራተኛው ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት የሚያጋጥመውን የጤና ጠንቅና ለአደጋዎች በመጋለጥ ሊደርሱ
የሚችሉትን ጉዳቶች በማስቀረት ወይም አደጋ ቢከሰት የሚደርሰውን አስከፊ ጉዳት መጠን ሊቀንሱ የሚችሉ
መከላከያ መሳሪያዎችን መጠቀም አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መከላከሉ ወይም የጉዳቱን
መጠን መቀነሱ የሚወሰነው ሥራው የሚጠይቀውን የመከላከያ መሳሪያዎች አይነት በመለየት እና በአግባቡ
ጥቅም ላይ መዋል እንዲቻል ዕሳቤ መኖሩ እና የወቅቱን የዋጋ ንረት ምክንያት ተቋማት ለሠራተኞቻቸው ግዥ
መፈፀም ባለመቻላቸው እንዲሁም በክልሉ ባሉ መ/ቤቶች በሚፈጠሩ ቋሚም ሆነ ጊዜያዊ ሰራተኞች የደንብ
ልብስ ጥያቄ የሚያስነሱ የስራ መደብ ሲኖር ፈጣን በሆነ አሰራር በየመ/ቤታቸው ምላሸ እንዲያገኙ ለማድረግ
በማሰብ ነው::

በዚሁ መሠረት ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽኑም ይህንን የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ አሰጣጥ እና
አጠቃቀም መመሪያ በመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 150/2010 አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ 4 ድንጋጌ መሰረት
እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

1
ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌዎች

1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት የመንግሥት ሠራተኞች የአደጋ መከላኪያ


መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ አሰጣጥ እና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 06/2014 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2 ትርጓሜ

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፣

1. “የመንግሥት ሠራተኛ” ማለት በክልሉ በየደረጃዉ ባሉ መንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ
የሚሰራ ሰው ነው::

2. “ጊዜያዊ ሠራተኛ” ማለት በክልሉ በየደረጃዉ ባሉ የመሥሪያ ቤት ውስጥ የዘላቂነት ባሕርይ በሌለው
ወይም ሁኔታዎች ሲያስገድዱ በቋሚ የሥራ መደብ ላይ በጊዜያዊነት ተቀጥሮ የሚሠራ ሰው ነው፤

3. “የሥራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት” ማለት የሠራተኞችን አካላዊ፡አዕምሯዊ እና ማህበራዊ ደህንነታቸውን


መንከባከብና ማሳደግ፤በሥራቸው ምክንያት ጤንነታቸው እንዳይጓደል መጠበቅና መከላከል፤ሠራተኞችን
ከተፈጥሯዊ አካላቸው እና አዕምሯቸው ጋር በተጣጣመ መልኩ መድቦ ማሰራትና መከታተል ነው፡፡

4. “የሥራ ላይ የጤና ጠንቆች”ማለት በሥራ ላይ የሚገኙ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሠራተኛውን በሥራ


ምክንያት ለሚመጣ በሽታ ወይም ጉዳት የሚዳርጉ በንክኪ፣በትንፋሽ ወይም በሌሎች አጋላጭ መንገዶች
ሳቢያ የህመም ወይም የአካል ጉዳት የሚያደርሱ ወይም የስራ አካባቢን የሚበክሉ ንጥረ
ነገሮች፣ቁሶች፣መሳሪያዎች ወይም ስነ - ህይወታዊ ተውሳኮች ናቸው፡፡

5. “በስራ ላይ የሚደርስ ጉዳት››ማለት በሥራ ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ
ነው፡፡

6. “የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች“የሚባሉት ሠራተኛው ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ከጤና ጠንቆችና


አደጋዎች ራሱን ለመከላከል የሚለበሱ፣የሚደረጉ፣የሚታሰሩ፣የሚጠለቁ ወይም በጆሮዎች ውስጥ
የሚሸጎጡ የሥራ መሳሪያች ወይም የሥራ ልብስ ናቸው፡፡

7. “የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ“ማለት ሠራተኛው ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት በአፍና አፍንጫ ከሚገቡ
አቧራ፣ብናኝ፣ኬሚካል፣በመተንፈሻ አካል ከሚገቡ ጀርሞች እና ሌሎች የጤና ጠንቆች ለመከላከል የሚረዳ

2
ከጨርቅ፣ከጥጥ መሰል ወይም ከፕላስቲክ የተሰራ መሸፈኛ ነው፡፡

8. “ጎግል (የአይን መከላከያ መነፅር)”ማለት አይንን ከአቧራ፣ከብናኝ፣ከኬሚካላዊ ፍንጣሪ፣ከብየዳ ፍንጣሪ


እና ከጨረር ለመከላከል የሚረዳ ከፕላስቲክ የተሰራ የአደጋ መከላከያ መሳሪያ ነው፡፡

9. “ሶላር መነፀር”ማለት አይንን ከማሽኖች ከሚወጣ ነፀብራቅ ወይም ጨረር የሚከላከል የጉዳት መከላከያ
መሣሪያ ነው፡፡

10. “ሙሉ የሥራ ቱታ”ማለት ከፖሊስተር ካኪ (6000) ጨርቅ የሚዘጋጅ ሆኖ ሰራተኞች ስራቸውን
በሚያከናውኑበት ወቅት ከጤና ጠንቅ፣ከአቧራ እና ከብናኝ እንዲሁም የልብስን መቆሸሽ የሚከላከል
በልብስ ላይ ተደርቦ የሚለበስ ቀለሙና አይነቱ ተመሳሳይ የሆነ የስራ ልብስ ነው፡፡

11. “ካፖርት”ማለት ከሱፍ፣ከጥጥ ወይም ከጥጥ ሴንቴቲክ የተሰራ ሙቀት እንዲሰጥ ገበር ያለው በተለይ
ለለሊት ብርድ መከላከያ የሚያገለግል ቀለሙና አይነቱ ተመሣሣይ የሆነ ልብስ ነው፡፡

12. “3/4 ጋዋን” ማለት ከፖሊስተር ካኪ (6000) ጨርቅ የተሰራ በልብስ ላይ ተደርቦ የሚለበስ እና ቆሻሻ
ወይም አቧራ የሚከላከል ቀለሙና አይነቱ ተመሣሣይ የሆነ ልብስነው፡፡

13. “ሽርጥ” ማለት ከፖሊስተር ካኪ (6000) ጨርቅ የተሰራ ሆኖ በስራ ላይ ቆሻሻ ወይም አቧራ ለመከላከል
የሚለበስ ቀለሙና አይነቱ ተመሣሣይ የሆነ ልብስ ነው፡

14. “አጭር ቆዳ ጫማ”ማለት ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ሆኖ ቁመቱ ከቁርጭምጭሚት የማያልፍ
በቀላሉ ተንቀሳቅሶ ስራ ለማከናወን የሚረዳ በአገር ውስጥ ከቆዳ የተሰራ ቀለሙና አይነቱ ተመሣሣይ የሆነ
ጫማ ነው፡፡

15. “ቡትስ ቆዳ ጫማ”ማለት ዚፕ ወይም ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ሆኖ ቁርጭምጭሚት የሚሸፍን እና
ሰራተኞችን ከአደጋ ለመከላከል የሚረዳ በአገር ውስጥ ከቆዳ የተሰራ ቀለሙና አይነቱ ተመሣሣይ የሆነ
ጫማ ማለት ነው፡፡

16. “የዝናብ ልብስ”ማለት ከሲንቴቲክ የተሰራ ዝናብ የማያስገባ ቀለሙና አይነቱ ተመሣሣይ የሆነ የዝናብ ልብስ
ነው፡፡

17. “ቆብ (ፊልድ ኬፕ)”ማለት የራስ ቅልን የሚሸፍን ፀሀይን ለመከላከል የሚረዳ የተዘጋጀ /ሬዲሜድ/ የሆነ
የራስ ቆብ ነው፡፡

18. “የእጅ ጓንት (የፕላስቲክ)”ማለት ከፕላስቲክ የተሰራ ሆኖ በእጅ ላይ የሚጠለቅ

3
ከቅዝቃዜ፣ከአቧራ፣ከስለታም ነገሮች እና ጉዳት ከሚያደርሱ ፍሳሾች ለመከላከል የሚያገለግል የሥራ
መሳሪያ ማለት ነው፡፡

19. “የፀጉር መሸፈኛ ሻሽ”ማለት ላስቲክ ያለው በፅዳት ወቅት የጸጉር ንጽህናን እና ደህንነትን ለመጠበቅ
የሚያስችል ሻሽ ነው፡፡

20. “ዣንጥላ” ማለት ትልቅ ሆኖ በዝናብ ወቅት ዝናብን ለመከላከል የሚያገለግል መሳሪያ ነው፡

21. “የደንብ ልብስ”ማለት የሥራ ልብስ ሆኖ አንድ የመንግስት ሠራተኛ በተመደበበት የሥራ መደብ ላይ
ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ እንደሥራው ፀባይ ለሠራተኛው መለያ እንዲያገለግል እንዲሁም ተገልጋይ
በቀላሉ ለይቶ እንዲያውቀው የሚረዳ ቀለሙና አይነቱ ተመሳሳይ የሆነ ልብስ ነው፡፡

22. “ኮትናሱሪ”ማለት ሱፍነክ ከሆነ ጨርቅ የሚሰፋ ቀለሙና አይነቱ ተመሳሳይ የሆነ ልብስ ነው፡፡

23. “ኮትና ጉርድ ቀሚስ”ማለት ሱፍነክ ከሆነ ጨርቅ የሚሰፋ ቀለሙና አይነቱ ተመሳሳይ የሆነ ልብስ ነው፡፡

24. “ሸሚዝ”ማለት ቀለሙና አይነቱ ተመሳሳይ የሆነ ለሸሚዝ አገልግሎት የተዘጋጀ /ሬዲሜድ/ ልብስ ነው፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን

የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ መጠቀም በሚያስፈልጋቸው የስራ መደቦች ላይ በክልሉ ውስጥ
ባሉ መ/ቤት ተመድበው ለሚሰሩ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

4. የፆታ አገላለፅ

በዚህ መመሪያ በወንዱ ፆታ የተገለፀ ለሴትም ያገልግላል፡፡

ክፍል ሁለት

5. ለአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እና የደንብ ልብስ የሚውሉ የጨርቅ እና የጫማ አይነቶችና መጠናቸው

5.1 የጨርቅ አይነቶች፡-

5.1.1 ለቱታ፣ ለአንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ፣ ለጃኬትና ጉርድ ቀሚስ፣ ለኮትና ሱሪ፣ ለሙሉ ካፖርት፣ ለ3/4
ካፖርት፣ ለጋዋንና ለሽርጥ የሚሰጠው የጨርቅ ዓይነት በሃገር ውስጥ ወይም በውጪ ሀገር የተመረተ
ፖሊስተር ቪስከስ ወይም ተመሣሣይና ተመጣጣኝ የልብስ ጥራትና የዋጋ መጠን ያለው ጨርቅ
ይሆናል፣

4
5.1.2 ለከረባት የሚሰጠው የጨርቅ ዓይነት በሃገር ውስጥ የተመረተ ፖሊስተር ቪስከስ ነው፣

5.1.3 ለካፖርት የሚሰጠው የጨርቅ ዓይነት ሙቀት የሚሰጥና ገበር ያለው ሆኖ የጥጥ ወይም የሴንተቲክ
ወይም ከጥጥና ከሴንተቲክ ጥሬ እቃ የተሰራ ይሆናል፡፡ ይህ የማይገኝ ከሆነ በምትኩ ሙቀት
የሚሰጥና ገበር ያለው ፊልድ ጃኬት ከመንግስት ወይም ከግል ድርጅቶች በማወዳደርና በወቅቱ
ያለውን የካፖርት ዋጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ገዝቶ መስጠት ይቻላል፡፡

5.1.4 የሚሰጠው የዝናብ ልብስ ከጥጥና ከሴንተቲክ የተሰራ የዝናብ ልብስ ነው፡፡የዝናብ ልብሱ የማይገኝ
ከሆነ በምትኩ ዣንጥላ ይሰጣል፡፡

5.1.5 ለካባና ለፈረጅያ የሚሰጠው ጨርቅ ፖሊስተር ቪስከስ ወይም ተመሣሣይና ተመጣጣኝ ዋጋ እና
የጥራት ደረጃ ያለው ጥቁር ጨርቅ ነው፡፡

5.1.6 ሙሉ በሙሉ ከጥጥ ወይም ከጥጥና ከሴንተቲክ ድብልቅ ከሆነ ጥሬ ዕቃ የተሠራ ጨርቅ ለሴቶች
ቀሚስ የሚሰጥ ይሆናል::

5.1.7 ሙሉ በሙሉ ከጥጥ ወይም ከሌላ ተስማሚ ጥሬ ዕቃ የተሠራ ጨርቅ ለሴቶች የውስጥ ልብስ የሚሰጥ
ይሆናል::

5.2 የጫማ አይነቶች፡-

5.2.1. ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ቁመቱ ከቁርጭም ጭሚት የማያልፍ ከቆዳ የተሰራ አጭር ጫማ ነው፡፡

5.2.2.. ዚፕ ወይም ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ሆኖ ቁርጭምጭሚት የሚሸፍን ከቆዳ የተሰራ ቡትስ ጫማ
ነው፡፡

5.2.3.ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ቁርጭም ጭሚትን የሚሸፍን ከፕላስቲክ የተሰራ ቡትስ ጫማ ነው፡፡

5.2.4 ከአንቀጽ 5.1.1 እስከ 5.1.7 ያለው እና ከ 5.2.1 እስከ 5.2.3 ድረስ ያሉት ሀሳቦች በተመለከተ በየወቅቱ
ያለውን የገበያ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በጥራታቸው፣ በዋጋቸውና በደረጃቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የአገር
ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚመረቱ ጫማዎችን ከመንግስት ወይም ከግል ድርጅቶች በማወዳደር
ገዝቶ መስጠት አለበት፡፡

5
ክፍል ሶስት

6. የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ አሰጣጥ እና አጠቃቀም ሁኔታ

6.1. የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ ለማግኘት በተፈቀደለት የሥራ መደብ ላይ ማንኛውም ሰራተኛ
በቋሚነት ሆነ በጊዜያዊነት ሲመደብ ይሰጠዋል፤

6.2. የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እና የደንብ ልብስ ከታሰበላቸው አላማ አኳያ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ
ለማስቻል ብትን ጨርቅ ተገዝቶ በመ/ቤቱ በኩል ተሰፍቶ እንዲሰጥ ይደረጋል፤

6.3. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 6.2 ላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ አመት ውስጥ ሁለት የደንብ
ልብስ የሚያገኝ ሰራተኛ አንድ በበጀት አመቱ መጀመሪያ የተቀረው በዓመቱ አጋማሽ ላይ ተሰፍቶ
ይሰጠዋል፤

6.4. ከሁለት ወራት በላይ በትምህርት ምክንያት በሥራ መደቡ ላይ የሌለ ሠራተኛ የአደጋ መከላከያ፣የደንብ
ልብስ በበጀት ዓመቱ አይሰጠውም፡፡

6.5 የአደጋ መከላከያ፣የደንብ ልብስ በበጀት ዓመቱ ዕቅድ መሠረት ተገዝቶ ለተጠቃሚው መሰጠት
አለበት፡፡ሆኖም ግን በበጀት እጥረት፤በአሰራር ስህተት ወይም በመ/ቤቱ በማንኛውም ችግሮች በበጀት
ዓመቱ ውስጥ ያልተሰጠ የስራ ልብስ እና መሳሪያ ለሚቀጥለው የበጀት አመት ይተላለፋል:፡ነገር ግን
የደንብ ልብሱ ሳይሰጥ የቀረው በአሰራር ስህተት ከሆነ ስህተቱን የፈፀመው አካል በዲስፕሊን ክስ
ቀርበው እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡

6.6- የአደጋ መከላከያ፣የደንብ ልብስ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወሰደ ከሥራ ቢለቅ እና በሥራ መደቡ አዲስ
ቢቀጠር ወይም ቢወከል በበጀት ዓመቱ ለሥራ መደቡ 2 የተፈቀደ ከሆነ የቀጣዩን ቀሪ 6ወር አንድ
ያገኛል፡፡ነገር ግን በበጀት ዓመቱ ለሥራ መደቡ አንድ የተፈቀደ ከሆነ አያገኝም፡፡

6.7 የአደጋ መከላከያ፣የደንብ ልብስ የሚጠቀሙ ሰራተኞች የሚሰጧቸው አልባሳት ቀለም እና የጥራት ደረጃ
አንድ አይነትና ተመሳሳይ ይሆናል፤

6.8. በበጀት አመቱ መጀመሪያ ተሰፍተው የሚሰጡት የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣የደንብ ልብስ ለሁሉም
ተጠቃሚዎች ተመሣሣይ ቀለም ይኖራቸዋል፡፡በዓመቱ አጋማሽ ላይ የሚሰጡት የአደጋ መከላከያ
መሣሪያዎች፣የደንብ ልብስ በተጠቃሚ ሰራተኞች ተወካዮች በሚቀርበው የተጠቃሚ ሰራተኞች ምርጫ
አንድ ተመሣሣይ ቀለም ይኖረዋል፡፡

6.9. የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ ለሚጠቀሙ ሠራተኞች በሙሉ በ6 ወር አንድ የልብስ

6
ሳሙና፣አንድ የገላ ሳሙና፣አንድ ሶፍት የሚሰጥ ሲሆን እና የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ
ለማይጠቀሙ ሌሎች ሠራተኞች በሙሉ በየ6 ወር ሶስት ሶፍት እና በየክፍሉ ሶስት ኤርፍሬሽ እንዲሁም
ፀረ-ተባይ ሶስት ይሰጣል፡፡ነገር ግን የጽዳት ሰራተኛው ለሚሰራው ሥራ የሚያስፈልገው የጽዳት
መጠቀሚያ መሳሪያ ቀደም ሲል ሲጠቀም በነበረበት አግባብ ተገዝቶ ተግባራዊ ማድረግ አለበት፡፡

ክፍል አራት

7. በክልሉ ውስጥ ባሉመ/ቤቶች ወይም ፑል መ/ቤቶች የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ወይም ቡዲን መሪ የሥራ
ክፍሎች ስልጣንና ኃላፊነት

7.1 የዕቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ኃላፊነት

7.1.1. በበጀት አመቱ ውስጥ ወቅቱ ተጠብቆ የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ ለመግዛት
የሚያስችል በቂ የሆነ በጀት እንዲመደብ ያደርጋል፡፡

7.1.2. ዕቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የተመደበው በጀት ስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፡፡

7.2 የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ሀላፊነት

7.2.1. በመመሪያው መሰረት የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ለደንብ ልብስ የተመደበውን በጀት በወቅቱ
የግዥ ወጪ እንዲፈፀም ማቅረብ አለበት

7.3 የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ኃላፊነት

7.3.1 ከሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት በሚቀርብ ሪፖርት መሰረት የአደጋ መከላከያ
መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ የሚያስፈልጋቸው ሠራተኞች ዝርዝር ተቀብሎ የግዥ ጥያቄ ያቀርባል፡፡

7.3.2 በመመሪያው መሰረት የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ የተመደበውን በጀት በወቅቱ ግዥ
እንዲፈፀም ለማናጅመንቱ እንዲያዉቀዉ ማቅረብ አለበት፡፡ ለሰራተኞች አንዱን በበጀት ዓመቱ
መጀመሪያና የቀረውን ደግሞ በዓመቱ አጋማሽ ላይ የማቅረብ ሀላፊነት አለበት፡፡

7.3.3 በአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ አሰጣጥ እና አጠቃቀም እንዲሁም በክልሉ ወይም
መ/ቤቶችሁ ባሉበት አከባቢ የግዢ ሂደት ላይ እንዲሳተፉ ከሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
በተጨማሪ ከጥበቃ፣ከፅዳት እና ከተላላኪ የተውጣጡ ሶስት ተወካዮችን ያስመርጣል፡፡

7.3.4 የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ከሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሪክቶሬት በሚሰጠዉ
አቅጣጫ መሠረት ወቅቱን ጠብቆ ለተጠቃሚዎች የማሰራጨት ሀላፊነት አለበት፡፡

7
7.4 የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሥልጣንና ሃላፊነት

7.4.1 ከሥራ ክፍሎች የሚቀርበውን የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ፍላጎት ተቀብሎ እና
አረጋግጦ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር
ዳይሬክቶሬት ከተመረጡ ሶስት ተወካዮች ጋር በመሆን በአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ
ግዥና ናሙና መረጣዉ ላይ ይሳተፋል፡፡

7.4.2 ለአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ምንነትና አጠቃቀም አስመልክቶ ሰራተኞችን በማወያየት
ግንዛቤ ያስጨብጣል፣

7.4.3 የመመሪያው ተጠቃሚ የሆኑ ሰራተኞች የተሰጣቸውን የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ
ለብሰው ስራ ላይ መገኘታቸውን ይከታተላል፣ጥቅም ላይ የማያውሉ ሰራተኞችን ከሥራ ክፍሎቹ
በሚቀርብ ሪፖርት መሰረት የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡

7.5 የእያንዳንዱ ሥራ ክፍል ተግባርና ኃላፊነት

7.5.1 በክፍሉ ውስጥ የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ የሚያስፈልጓቸውን ሰራተኞች ዝርዝር
በወቅቱ ለሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ሪፖርት ያቀርባል፡፡

7.5.2 የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ በወቅቱ ተሞልቶ መቅረባቸውን ከግዥና ንብረት አስተዳደር
ዳይሬክቶሬት ያረጋግጣል፡፡

7.5.3 ሰራተኞች የተሰጧቸውን የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ በአግባቡ እየተጠቀሙ መሆኑን
ክትትል ያደርጋል፡፡ በአግባቡ ጥቅም ላይ የማያወሉ ሠራተኞችን በመለየት ለሰው ሀብት ሥራ አመራር
ዳይሬክቶሬት ያቀርባል፡፡

7.6.1 የተጠቃሚ ሰራተኞች ተወካይ ሀላፊነት

7.6.1.1 የተጠቃሚ ሰራተኞች ተወካይ ለናሙና የተመረጡትን በማየትና በመገምገም የአደጋ መከላከያ
መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ በዚህ መመሪያ ድንጋጌ መሰረት ጥራቱን መለየት፣መከታተልና
የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፡፡

7.6.1.2 በበጀት ዓመቱ መጀመሪያና አጋማሽ ላይ ለሚሰጡት የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣የደንብ ልብስ
የተጠቃሚ ሰራተኞችን የቀለም አይነት ፍላጎት አረጋግጦ ለግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት
ያሳውቃል፡፡

8
7.6.1.3 የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ ከሻጭ በሚደረገው ርክክብ ላይ እና ወደ ንብረት ክፍል
በሚደረገው ገቢ የማድረግ ሂደት ላይ የተጠቃሚ ሰራተኞች ተወካይ በታዛቢነት ተገኝቶ ሪፖርትም
ለሚመለከተው ኃላፊ ያቀርባል፡፡

ክፍል አምስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

8.1 የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ የሚሰጠው ቋሚ ሰራተኛ ሆኖ በተፈቀደለት የሥራ መደብ ላይ
ይሆናል፡፡

8.2 ለስራ የተሰጠውን የአደጋ መከላከያ መሳሪያ ባለመጠቀም ለሚደርስበት ጉዳት በክልል መንግስት ሰራተኞች
አዋጅ 150/2010 አንቀፅ 55 ቁጥር 4 መሰረት መስሪያ ቤቱን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም፡፡

8.3 የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ በጊዜያዊነት ተቀጥሮ የሚሠሩ ሰራተኞች በሥራ መደቡ ላይ
ስድስት ወር ከአገለገሉ በኃላ በክልሉ ባሉመሥሪያቤት ውስጥ የዘላቂነት ባሕርይ በሌለው ወይም ሁኔታዎች
ሲያስገድዱ እና በቋሚ የሥራ መደብ ላይ ተመድቦ ሲሰሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

8.4 አዲስ የሥራ መደብ ሲፈጠር እና የቀድሞ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ
ልብስ ጥያቄ ሲኖር ጄኢጂ ተግባርና ሀላፊነት መሠረት በማድረግ እያንዳንዱ መስሪያቤት በተቋማቸው
ማናጅመንት በማስወሰን ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሸን አሳውቆ በማስፈቀድ በግዥ መመሪያ መሰረት መፈፀም
አለበት::

8.5 የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ በዚህ መመሪያ የተገለጹት በሙሉ በየወቅቱ የዋጋ ተመን ልዩነት
ሲፈጠር በየተቋሙ የገብያ ጥናት ከሚቴ በማቋቋም ኮሚቴውም ጥናቱን ለማናጅመንቱ በማቅረብ በግዥ
መመሪያ መሠረት ዋጋው ሳይጋነነን ጥራቱ ሳይጓደል ግዥ መፈፀም አለበት::

8.7 በህመም ምክንያት ከስድስት ወር በላይ ሥራውን ያላከናወነ ከሆነ ለመደቡ የተፈቀደውን የአደጋ መከላከያ
መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ አይሰጠውም፡፡ነገር ግን ሰራተኛው ሳይሰጠው በሞት ምክንያት አገልግሎቱን
ቢያቋረጥ ለህጋዊ ወራሸችሁ በገንዘብ ተለውጦ ይሰጠዋል፡፡

8.8 የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስ በጀት ዓመት ወስዶ ሥራ የለቀቀ ሠራተኛ እንዲመልስ
አይጠየቅም፡፡

8.9 በሞቃታማና በውርጭ አካባቢዎች የተመደቡና የሥራ ልብስና መሣሪያ በተፈቀደባቸው የሥራ መደቦች ላይ
ተመድበው በመሥራት ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች በመመሪያው ላይ ለተፈቀዱት የጨርቅና የጫማ ዓይነቶች

9
ምትክ ለአካባቢው የአየር ጠባይ ተስማሚ የስራ ልብስ መስጠት ይቻላል፡፡

8.10 የተሰጡት የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን፣የደንብ ልብስ በአግባቡ ለብሶ በስራ ገበታው ላይ መገኘት
አለበት፡፡፤

8.11 የተሰጡት የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣የደንብ ልብስን ማንኛውም ሠራተኛ በአግባቡ ለብሶ በስራ ገበታው
እንዲገኝ በማያደረግ ዳይሬክቶሬት ሆነ የቅርብ ሀላፊ በዲስፕሊን ይጠይቃል፡፡

9. መመሪያውን ማሻሻል

ኮሚሸኑ አስፈላጊ የሆኑ አሰራር ችግሮች ሲገጥሙት የሰው ሀብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት አጥንቶ
ለመ/ቤቱ የበላይ አመራር አቅርቦ በማስወሰን መመሪያው እንዲያሻሽል ሊያደረግ ይችላል፡፡

10. ስለተሻሩ መመሪያዎች

ይህ መመሪያ ከመፅደቁ በፊት በሥራ ላይ የነበረው የሥራ ልብስና መሣሪያዎች አጠቃቀም መመሪያ በዚህ
መመሪያ ተሽረዋል፡፡

11.መመሪያው ተፈፃሚ የሚሆንበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በኮሚሽነሩ ተፈርሞ ከወጣበት -----------ቀን ጀምሮ ሥራ ላይ ይውላል፡፡

አቶ መሀመድ አብዱልአዚዝ አኑር

የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲ/ሰ/ኮሚሸን ኮሚሸነር

10
አባሪ አንድ
የተፈቀደ የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያ ዓይነትና መጠን የሚያሳይ ሠንጠረዥ
ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ የሚሰጠው የሥራ ልብስ ዓይነት ብዛት
1 ዘበኛ ወንድ የቀንና የሌሊት ወይም የሌሊት ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ብቻ ወይም በሽፍት የሚሠራ ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ቆብ / መለዮ / በአመት ሁለት
ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በየ3 ዓመቱ አንድ
2 ዘበኛ ሴት የቀንና የሌሊት ወይም የሌሊት ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
ብቻ ወይም በሽፍት የምትሰራ አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
የቆዳ ጫማ አጭር በዓመት ሁለት ጥንድ
ቆብ / መለዮ / በአመት ሁለት
ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ3 ዓመት አንድ
3 ዘበኛ ወንድ የቀን ብቻ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ቆብ / መለዮ / በአመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
4 ዘበኛ ሴት የቀን ብቻ ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
ቆብ / መለዮ / በአመት ሁለት
አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
5 የደን ዘበኛ ቱታ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
ቆብ / መለዮ / በአመት ሁለት
ረዥም የቆዳ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ካፖርት በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ3 ዓመት አንድ
የዝናብ ልብስ በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ3 ዓመት አንድ
6 የዘብ ኃላፊ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ቆብ / መለዮ / በአመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
7 የዘብ ኃላፊ ሴት ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
ቆብ / መለዮ / በአመት ሁለት
አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ

8 አትክልተኛ ወንድ ቱታ በዓመት ሁለት


ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
9 አትክልተኛ ሴት ቀሚስ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት

11
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
10 የጽዳት ኃላፊ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
11 የጽዳት ኃላፊ ሴት ቀሚስ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
12 የጽዳት ሠራተኛ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
13 የጽዳት ሠራተኛ ሴት ቀሚስ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
በዓመት ሁለት
14 የበረት ጽዳት ሠራተኛ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
15 የበረት ጽዳት ሠራተኛ ሴት ቀሚስ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
ሽርጥ በዓመት አንድ
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
16 ተላላኪ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት አንድ
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
17 ተላላኪ ሴት ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት አንድ
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
18 መጥሪያ አዳይ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት
ጃንጥላ በዓመት አንድ
19 መጥሪያ አዳይ ሴት ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ጃንጥላ በዓመት አንድ
20 እግረኛ ፖስተኛ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
ጃንጥላ በዓመት አንድ
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ

12
21 እግረኛ ፖስተኛ ሴት ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ጃንጥላ በዓመት አንድ
22 በሞተርሳይክል የሚሠራ ፖስተኛ ቆዳ መሰል የላስቲክ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ወይም ጃኬትና ሱሪ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
የዝናብ ልብስ በመጀመሪያ አንድ ተሰጥቶ በ3 ዓመት አንድ
የብረት ቆብ/ሔልሜት/ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በ3 ዓመት አንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
23 የመለስተኛ መኪና ሾፌር ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
24 የከባድ መኪና ሾፌር ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
25 የሾፌር ረዳት ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
26 ትራክተር ኦፕሬተር ቱታ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
27 ረዳት የትራክተር ኦፕሬተር ቱታ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
28 በመጸዳጃቤት መምጠጫ መኪና ላይ ቱታ በዓመት ሁለት
የሚሠራ አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የላስቲክ ሽርጥ/አፕሮን/ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
29 የቅባት፣ነዳጅና ዘይት አዳይ /የተሸከረካሪ/ ቱታ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለተ ጥንድ
30 ጐሚስታ ቱታ በዓመት ሁለት

አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ

31 የጋራዥ ሠራተኛ፣መካኒክ፣ረዳት ቱታ በዓመት ሁለት


መካኒክ፣ቀጥቃጭ፣የአውቶ ኤሌክትሪሽያን አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
የጥገና ሠራተኛና መካኒክ፣ በያጅ፣ብረታብረት የእጅ ጓንት እንደ ስራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
ሠራተኛ፣ ቦይለርቴክኒሽያን፣የማቀዝቀዣ መጋዘን
መካኒክ፣ማሽን ሾፕ ሠራተኛ፣ በያጅና ረዳት
መካኒክ
32 መኪና አጣቢ፣ግሪስ የሚያደርግናዘይት ቱታ በዓመት ሁለት

13
የሚቀይር፣ሁለገብ የጉልበት ወይም አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የጥገና ሠራተኛ የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
33 ባትሪ ሠራተኛ ቱታ በዓመት ሁለት
አጭር ቡት የቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የላስቲከ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የላስቲክ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
የላስቲክ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
34 የተሽከርካሪ ጥገና ኃላፊ፣የሾፌር አሰልጣኝ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
35 ንብረት ኦፊሰር ወይም ንብረት ሠራተኛ ፣ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
36 መዝገብ ቤት/ሪከርድ ሠራተኛ/ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
የተማሪዎች ሪከርድ ሠራተኛ
37 ማባዣና ፎቶኮፒ ሠራተኛ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
38 የቢሮ መሣሪያዎች ጠጋኝ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
39 የጥረዛ ክፍል ሠራተኛ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
40 የቤተመፃህፍት ሠራተኛ ወይም ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
ላይብራሪያን
41 ቮይስ ሪኮግኒሽን መሳሪያ ኦፕሬተር ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
42 ፋይል ከፋች ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
43 ልዩ ልዩ የእደጥበብ ሙያ አሰልጣኝ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
44 የብሉ ፕሪንት ማሽን ባለሙያ(ለከተሞች የወተት ክፍያ በወር 100 ብር
ፕላን ኢንስቲትዩት መስሪያቤት ብቻ)
45 የብረታብረት መምህር፣የእንጨት ሥራ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
መምህር፣የምግብ ሥራ መምህር፣
አጠቃላይ የሙያ መምህር፣ አውቶሞቲቭ
መምህር
46 የስፖርት መምህር ወይም አሰልጣኝ ቱታና ቲሸርት በዓመት አንድ
በሙያው የሰለጠነና በሥራው የተመደበ ቶርሸን ስኒከር ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
47 የስፖርት ሜዳ ተንከባካቢ ፖሊስተር ካኪ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት አንድ
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የላቲክ ቡትስ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የመስክ ቆብ /ፊልድ ኬፕ/ በዓመት ሁለት
ባሬስታ ወንድ ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
48 ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ

ባሬስታ ሴት ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ


49 ሸሚዝ በዓመት አንድ
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
አስተናጋጅ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
50
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ከረባት በዓመት አንድ

51 አስተናጋጅ ሴት ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ


ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ከረባት በዓመት አንድ
ንብረት ክፍልና ልብስ አጣቢ ወንድ(ለርዕሰ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
52 መሠተዳድርና ለክልል ምክር ቤት) ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዐመት አንድ ጥንድ

14
የላስቲክ ቡት ጫማ በዐመት አንድ ጥንድ
የፕላስቲክ ሽርጥ/አፕሮን/ እንደ ሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ንብረት ክፍልና ልብስ አጣቢ ሴት(ለርዕሰ ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ
መስተዳድርና ለክልል ምክር ቤት) ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
53
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ

የላስቲክ ሽርጥ/አፕሮን እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ

የፕሮቶኮል ባለሙያ( በህጋዊ መንገድ ባለገበር ሱፍ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ


54 የፕሮቶኮል ባለሙያ ለተመደበላቸው የስራ ሸሚዝ በዓመት አንድ
ሀላፊዎች ብቻ) ቆዳጫማ አጭር በዓመት አንድ
ከረባት በዓመት አንድ
የጂኦሎጂ፣አፈርና ግንባታ ጥራት ናሙና ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
ምርመራ አናሊስት ረጅም ቡትስ ቆዳ ጫና በዓመት አንድ
55
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
56 የአፈር ምርምር ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
የእጅ ፖምፕ አቴንዳንት፣ ቧንቧ ሠራተኛ ቱታ በዓመት ሁለት
57 አጭር ቡት ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
58 የሙዚየም ባለሙያ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
የእጅ ጓንት/ቆዳ/ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ነርስ፣አሰልጣኝና ተመራማሪ ፣ የምግብ ቤት ¾ ካፖርት በዓመት ሁለት
ኃላፊ፣ የጤናመኮንን፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ፋርማሲስት፣ ግንባር ቀደም የጤና
ሱፐርቫይዘር፣ የጤና ኤክስቴንሽንባለሙያ፣
የወባ ቴክኒሽያን፣ የጤና ባለሙያ
ሠልጣኞች፣ ጤና ረዳት፣ላቦራቶሪ
ቴክኒሽያን፣ራዲዮትራፒስት የህክምና
ቴከኒሽያን፣ የጤና አጠባበቅ ተቆጣጣሪዎች
59 /በሆስፒታል ብቻ የሚሰሩ/ ላቦራቶሪ
ተቆጣጣሪ፣የላቦራቶሪ ረዳት፣ ላቦራቶሪ
ውስጥ ለሚሰሩ አንቲሞሎሀዳስትና
ፖቲዮሎጂስት፣ የተባይ መከላከያ ላቦራቶሪ
ሠራተኛ፣ የመድሃኒት መጋዝን ሠራተኛ
፣የመድሃኒት አስተዳደር ኤክስፐርት፣
ፕሮተር/ራነር/፣ እንግዳ ተቀባይ፣ምግብ
ተቆጣጣሪ /የምግብ ጉዳይ ኃላፊ/

የቆዳና ሌጦ ባለሙያ ቱታ በዓመት አንድ


60 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ
የፕላስቲክ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት አንድ
የእንስሳት ሀኪም፣ የእንስሳት ጤና ኳራንቲ፣ ካፖርት በሁለት ዓመት አንድ
የዱር እንስሳት ሀኪም፣ ረዳት የእንስሳት አጭር ቡት ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
61 ሀኪም፣ ረዳት የዱር እንስሳት ሀኪም የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት አንድ
62 የእንስሳት ሀኪም፣ የእንስሳት ጤና ኳራንቲ፣ ቱታ በዓመት አንድ
የዱር እንስሳት ሀኪም፣ ረዳት የእንስሳት ረጅም ቡትስ ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ሀኪም፣ ረዳት የዱር እንስሳት ሀኪም/
ለፊልድ ሠራተኛ ብቻ/ የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ፊልድ ኬፕ በዓመት 2

15
የዝናብ ልብስ ወይም ጃንጥላ በሁለት ዓመት አንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት አንድ

63 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ


የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት አንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት አንድ
64 የጀልባ ካፕቴን ቱታ በዓመት አንድ
ነጭሸሚዝና ሱሪ በዓመት ሁለት
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ
ቆብ በዓመት አንድ
65 የአሣ ማስገሪያ መሣሪያዎች ቴክኒሽያን፣ ቱታ በዓመት አንድ
የመረብ ሥራ ቴክኒሽያን፣ የማስገሪያ የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
መሣሪያዎች ረዳት ቴክኒሽያን
የመስክ ነፍሳትና የጐተራ ተባይ ጥናት ቱታ በዓመት አንድ
መከላከል ባለሙያ፣የእጽዋት በሽታና አረም
ጥናት መከላከል ባለሙያ፣የአይጥና ወፍ የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ኬሚካል መርጫ መሣሪያ ጥናትና
66 መከላከል ባለሙያ፣የኬሚካል መርጫ
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
አያየዝና አጠቃቀም ባለሙያ፣የአረም
ጥናትና መከላከል ባሙያ

67 የሥነ ተዋልዶና ጤና ባለሙያ፣የርባታ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ


ባለሙያ፣የአባለዘርና ፈሳሽ ናይትሮጅን፣ ቱታ በዓመት አንድ
ላቦራቶሪ ቴክኒሽያንና ማሽን ኦፕሬተር ሸሚዝ በዓመት አንድ
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
68 ዳኛ፣ አቃቢህግ፣ ተከላካይ ጠበቃና ካባ በ3 ዓመት አንድ
ነገረፈጅ፤ ለአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኛ
የደሮ ማስፈልፈያ ባለሙያ(ወንድ) ቱታ በዓመት አንድ

69 ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ


¾ ካፖርት በዓመት አንድ
የጨርቅ ቆብ በዓመት አንድ
70 የደሮ ማስፈልፈያ ባለሙያ /ሴት/ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ

የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ


ሙሉ ሽርጥ በዓመት አንድ
የጨርቅ ቆብ በዓመት አንድ

71 የእንጨት ሥራ ቱል ኪፐር፣ የብረታብረት ሥራ ¾ ካፖርት በዓመት ሁለት


ቱል ኪፐር
ኤሌክትሪሽያን፣ ረዳት ኤሌክትሪሽያን፣ የብረታ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
72 ብረት ቴክኖሎጅስት፣ የምርት ጥራትና ቁጥጥር አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሠራተኛ
73 ከፍተኛ ማሽኒስት፣ ማሽኒስት፣ ብረታብረት ቱታ በዓመት ሁለት
ሠራተኛ፣ የእንጨት ሥራ ቴክኒሽያን፣ የእንጨት አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሠራተኛ፣ የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ቀለም ቀቢ ቱታ በዓመት አንድ
74
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
ቆብ በዓመት አንድ
እንጨት ፈላጭና ጉልበት ሠራተኛ፣ ልብስ ሰፊ፣ ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
75 ልብስ ዘምዛሚ፣ ልብስ ተኳሽ አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሸሚዝ በዓመት አንድ

16
ወተት አላቢ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
76 የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዐመት አንድ ጥንድ
ቆብ/ከጨርቅ የተሰራ በዓመት አንድ
ሽርጥ በዓመት አንድ
ችግኝ ጣቢያ ሠራተኛ ቱታ በዓመት ሁለት
77 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
እንጀራ ጋጋሪ ቀሚስ በዓመት ሁለት
የውስጥ ልብስ በዓመት ሁለት
78
ቨሚዝ በዓመት ሁለት
ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሙሉ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ከጨርቅ የተሠራ ቆብ በዓመት አንድ
እንስሳት ተንከባካቢ ቱታ በዓመት ሁለት
79 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
የዝናብ ልብስ በሦስት ዓመት አንድ
ከብት ጠባቂ ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
80 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የዝናብ ልብስ በሦስት ዓመት አንድ
የእጽዋት ጥራት ክሊኒክ ረዳት አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
81
ቱታ በዓመት አንድ
82 ታፒ ሰሪ /ፎቴሰሪ/ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
አጭር ቆዳ ጫማ በአመት ሁለት ጥንድ
የእስካውት ኃላፊ፣ እስካውት፣ የመስክ ሥራ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
83 ተቆጣጣሪ ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ካፖርት በሦስት ዓመት አንድ
ቆብ በዓመት ሁለት
84 የመድሃኒት መጋዘን ሠራተኛ ፣ህትመት ቱታ በዓመት አንድ
ሠራተኛ፣የቅርስ እንክብካቤና ጥገና አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
ኦፊሰር፣የአፈርና እጽዋት ናሙና አዘጋጅ፣የመስክ
ጥራት ኢንስፔክተር ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን
፣የእጽዋት ጥራት ክሊኒክ ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን
85 አናፂና ግንበኛ ቱታ በዓመት አንድ
አጭርቆዳ ጫማ በዓመት አንድ

86 ፎረንሲክ ባለሙያ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ


87 የትራንስፖርት ስምሪት ጋራዥ ክፍል ኃላፊ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ

88 ሰዓሊ ¾ ካፖርት በዓመት አንድ


89 የተሽከርካሪዎች መርማሪ የማንኛውም ¾ ካፖርት በዓመት አንድ
ተሽከርካሪ ፈታኝ
90 የንብ ምርምር ተመራማሪ ፣የንብ ምርምር ከቆዳ የተሰራ የእጅ ጓንት በዓመት አንድ ጥንድ
ቴከኒክ ረዳት አይን ርግብ በዓመት አንድ
ባለዚፕ ቱታ በዓመት አንድ
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ

17
ግሪን ሀውስ ሠራተኛ ቱታ በዓመት ሁለት
91
ፕላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት ሁለት
92 የህክምና መሣሪያዎች ጥገና ክፍል ሠራተኛ፣ ቱታ በዓመት ሁለት
የሬዲዮ ጥገና ሠራተኛ አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት
93 አበነፍስ ጥቁር ፈረጅያ በሁለት ዓመት አንድ
ኮትና ሱሪ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት አንድ
ቱታ በዓመት አንድ
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
ክብ ቆብ በዓመት አንድ
የላውንደሪ ሠራተኛ /ኃላፊ/ ወንድ ቱታ በዓመት አንድ
94 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ላስቲክ ቦት ጫማ በዓመት ሁለት
የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
ፕላስቲክ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
የላውንደሪ ሠራተኛ /ኃላፊ/ሴት ቀሚስ በዓመት አንድ
የውስጥ ልብስ በዓመት አንድ
95
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
ላስቲክ ቦት ጫማ በዓመት ሁለት
የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
ፕላስቲክ ሽርጥ እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
96 የቀበሌ ስነ ስርዓት አስከባሪ /ወንድ/ ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
የዝናብ ልብስ በሶስት ዓመት አንድ
ፊሽካ አንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ
ዱላ አንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ
የቀበሌ ስነ ስርዓት አስከባሪ /ሴት/ ጉርድ ቀሚስ በዓመት ሁለት
የውስጥ ልብስ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት አንድ
97 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
የዝናብ ልብስ በ 3 ዓመት አንድ
ፊሽካ አንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ
ዱላ አንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ
የችግኝ ጣቢያ ሀላፊ ቱታ በዓመት ሁለት
98 አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
የላቲክ ቦት ጫማ በዓመት አንድ
ወጥ ቤት /ወንድ/ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
99 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሙሉ ሽርጥ በዓመት አንድ
ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
ወጥ ቤት /ሴት/ ቀሚስ በዓመት ሁለት
የውስጥ ልብስ በዓመት ሁለት
100 አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሙሉ ሽርጥ በዓመት አንድ
ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
እህል አበጣሪ /ሴት/ ቀሚስ በዓመት ሁለት
የውስጥ ልብስ በዓመት ሁለት
101
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሽርጥ በዓመት አንድ
ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
102 እንጨት ፈላጭ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት

18
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሞግዚት /ወንድ/ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
103
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
ሞግዚት /ሴት/ ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት ሁለት
104 ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
105 የተሸከርካሪ ስምሪት ኃላፊ /ሠራተኛ/ 3/4 ካፖርት በዓመት አንድ ጥንድ

ሴት ፈታሽ ጃኬትና ጉርድ ቀሚስ በዓመት አንድ


106 አንድ ወጥ ሸሚዝና ሱሪ በዓመት አንድ
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
ቆብ ፊልድ ኬፕ ከሆነ በዓመት ሁለት
የመንገድ ጥርጊያ/ጽዳት/ ሠራተኛ /ወንድ/ ቱታ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
ፕላስቲክ ቦት ጫማ በዓመት አንድ
ዝናብ ልብስ በ2 ዓመት 1
107 የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ጨርቅ በዓመት አንድ
የእጅ ጓንት እንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ
አንፀባራቂ ልብስ ሙሉ ገበር ያለው

በዓመት ሁለት
የመንገድ ጥርጊያ/ጽዳት/ ሠራተኛ /ሴት/ ቀሚስ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
የውስጥ ልብስ በዓመት ሁለት
ፕላስቲክ ቦት ጫማ በዓመት ዓንድ
የዝናብ ልብስ በ2 ዓመት 1
ቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
105
የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ጨርቅ በዓመት አንድ
እንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ
የእጅ ጓንት
አንፀባራቂ ልብስ ሙሉ ገበር ያለው በዓመት ሁለት

ሪከርድና ማህደር ሠራተኛ /ለሲቪል ሰርቪስ 3/4 ካፓርት በዓመት ሁለት


106
ኮሚሸን ከክልል እስከ ወረዳ ላሉ ሠራተኞች/ የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ጨርቅ በዓመት ሁለት
አስከሬን ቤት ሠራተኛ /ለወንድ/ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
ቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
107
ከጨርቅ የተሰራ ቆብ በ ዓመት አንድ
የፕላስቲክ ሽርጥ እንደ ሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
የእጅ ጓንት እንደ ሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ጨርቅ በዓመት ሁለት
አስከሬን ቤት ሠራተኛ /ለሴት/ ቀሚስ የውስጥ ልብስ በዓመት ሁለት
የውስጥ ልብስ በዓመት ሁለት
የቆዳ ጫማ አጭር በዓመት ሁለት ጥንድ
108
የጨርቅ የተሰራ ቆብ በዓመት አንድ
የፕላስቲክ ሽርጥ እንደ ሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
የእጅ ጓንት እንደ ሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ጨርቅ በዓመት ሁለት

19
ላስቲክ ቦት ጫማ በዓመት ሁለት
ሥጋ መርማሪ / ረዳት ሥጋ መርማሪ ቱታ በዓመት ሁለት
3/4 ካፓርት በዓመት ሁለት
ላስቲክ ሽርጥ በዓመት ሁለት
109 ነጭ ኮፍያ በዓመት ሁለት
ወፍራም የገላ ሹራብ በዓመት ሁለት
/በአገር ውስጥ የተሰራ/ የዝናብ በሶስት ዓመት አንድ ሆኖ እንዳለቀ የሚተካ
ልብስ

የእንሰሳ ዘር ማሻሻያ ቴክኒሽያን/ አዳቃይ የቆዳ ጃኬት በሶስት ዓመት አንድ


ቴክኒሻን የዝናብ ልብስ የመጀመሪያ አነድ ተሰጥቶ ከሶሰት ዓመት በኋላ እንዳለቀ የሚተካ
110 በመጀመሪያ ሁለት ተሰጥቶ በሁለት ዓመት እንዳለቀ የሚተካ
የላሰቲክ ቦት ጫማ እንደ ስራ መሳሪያ የሚሰጥ
የእጅ ጓንት/የፕላስቲክ
ሁለገብ የጉልበት ሠራተኛ ቱታ በዓመት አንድ
ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
111
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት አንድ
ቀያሽ /ሰርቬየር/ ቱታ በዓመት አንድ
አጭር ቡትስ የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
112
የላቲክ ቡትስ ጫማ በመጀመሪያ አንድ ጥንድ ተሰጥቶ በሶስት ዓመት ከአንድ
ሳይበልጥ እንዳለቀ የሚተካ
ቀሚስ በዓመት ሁለት
የሆስፒታል ጽዳት ሠራተኛ /ሴት/ የውስጥ ልብስ በአመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት ሁለት
የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
113
ቱታ በዓመት ሁለት
ሙሉ ሽርጥ
የእጅ ጓንት በዓመት ሁለት

እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት

የሆስፒታል ጽዳት ሠራተኛ /ወንድ/ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት


ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
114 የላስቲክ ቡት ጫማ በዓመት ሁለት
የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
ቱታ በዓመት ሁለት
ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት ተሰጥቶ እንዳለቀ የሚተካ
115 ቱታ በዓመት ሁለት
የቀበሌ ልማት ጣቢያ ሠራተኛ
የላስቲክ ቦት ጫማ በዓመት አንድ
/ሰብል፤ተፈጥሮ፤መስኖ ሰብል፤መስኖ
የሰሌን ባርኔጣ በዓመት ሁለት
ቴክኒሻን፤የገጠ/መሬት አስተ/አጠቃቀም፤
ጃንጥላ በዓመት አንድ
ሁለገብ የጥገና ሰራተኛ /በቢሮ/ ቱታ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
116 ዝናብ ልብስ በሦስት ዓመት አንድ
አጭር ቡትስ የቆዳ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
የላቲክ ቡትስ ጫማ በዓመት አንድ ጥንድ
117 የላቦራቶሪ ጽዳት ሠራተኛ ወንድ ኮትና ሱሪ በዓመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ

20
ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ በዓመት ሁለት
የላቦራቶሪ ጽዳት ሠራተኛ ሴት ቀሚስ በዓመት ሁለት
የውስጥ ልብስ በአመት ሁለት
ሸሚዝ በዓመት ሁለት
አጭር የቆዳ ጫማ በዓመት ሁለት ጥንድ
118
ሙሉ ሽርጥ በዓመት ሁለት
የጨርቅ ቆብ በዓመት ሁለት
የእጅ ጓንት እንደሥራ መሣሪያ የሚሰጥ
119 ኬሚካል ኢንጅነር 3/4 ካፓርት በዓመት ሁለት
120 የኢነርጂ ምንጭ ባለሙያ 3/4 ካፓርት በዓመት ሁለት
ቱታ በዓመት ሁለት
121 ኤሌክትሮ ሜካኒካል ሳንቴሽን ባለሙያ አጭር ቆዳ ጫማ
በዓመት አንድ
ቱታ በዓመት አንድ
ሸሚዝ በዓመት አንድ
የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ጨርቅ በ ዓመት 12
የእጅ ጓንት በዓመት ሁለት
አንፀባራቂ ልብስ ሙሉ ገበር ያለው በዓመት ስድስት
በዓመት ሁለት
122 የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሸከርካሪ ሹፌር በዓመት ሁለት

በዓመት ሁለት

አባሪ.2
ተ/ቁ በሥራ መሣሪያነት የሚታወቁት የሥራ ልብሶች
1 ቱታ
2 ሙሉ የሥራ ካፓረት
3 3/4 ካፖርት
4 የጨርቅ ቆብ
5 ማስክ
6 ሙሉ ሽርጥ
7 ጉርድ ሽርጥ
8 የእጅ ጓንት
9 የስሌን ባርኔጣ
10 ካባ
11 የላስቲክ ቡትስ ጫማ
12 ኬፕ/መለዮ/
13 የዝናብ ልብስ
14 የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ
15 ቆዳ መሰል ጃኬት
16 ሔልሜት /የብረት ቆብ/

21
1

You might also like