You are on page 1of 4

በኮንትራት/ በጊዜያዊነት በፌዴራሌ የመንግስት መሥሪያ

ቤቶች ተቀጥረው የሚገኙ ሠራተኞችን ቋሚ ሇማድረግ

የወጣ የአፈጻጸም መመሪያ

የፌዴራሌ የመንግሥት ሠራተኞች ስሇሚቀጠሩበት እና ስሇሚተዳደሩበት አጠቃሊይ


አሰራር በአዋጁ ቁጥር 515/99 በዝርዝር መደንገጉ ይታወቃሌ፡፡ በዚሁ አዋጅ
አንቀጽ 1 የመንግስት ሠራተኛ ማሇት በፌዴራሌ የመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ
በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው መሆኑን በግሌጽ ተመሌክቷሌ፡፡ በላሊም በኩሌ
በአዋጁ አንቀጽ 2 እና አንቀጽ 22 ሊይ ጊዜያዊ ሠራተኛ ማሇት በመንግስት መ/ቤት
ውስጥ የዘሊቂነት ባህርይ በላሇው ሥራ ወይም ሁኔታዎች ሲያስገድዱ ሇአጭር ጊዜ
የሚቀጠር እና ሥራው ሲጠናቀቅ የሚሰናበት መሆኑ ግሌጽ ቢሆንም በፌዴራሌ
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ከሚታዩ ያሌተስተካከለ የቅጥር አፈጻጸም
አሠራሮች ውስጥ የኮንትራት/ ጊዜያዊ ቅጥር ዋነኛው ሆኖ ተገኝቷሌ፡፡

ይህ አሠራር በመንግሥት የበጀት አጠቃቀምና በዕቅድ አፈጻጸም ሊይ ከፍተኛ ችግር


እያስከተሇ ከመሆኑም ባሻገር ሰራተኞቹ ዘሊቂነት ባሊቸው የተቋሙ ሥራ መደቦች
ሊይ በመቀጠራቸው ይኸው የኮንትራት ውሌ ሇረዥም ዓመታት እየተንከባሇሇ
መቆጣጠር እማይቻሌበት ደረጃ ከመድረሱም ባሻገር አሁን ያሇው በእቅድ
ያሇመመራት የሰው ኃይሌ ቅጥር ችግር የሚቀጥሌ ከሆነ በመንግስትና በዜጐች ሊይ
ከፍተኛ ኪሳራ ሉያስከትሌ እንደሚችሌ እንዲሁም በየተቋሙ በኮንትራት የተቀጠሩ
ሠራተኞች የሚቆዩት ቋሚ ሥራ እስኪያገኙ ድረስ ብቻ በመሆኑ ቀጣይነት ባሇው
መሌኩ የሰው ኃይሌ ሌማት ማረጋገጥ ስሇማያስችሌ ሇአንዴና ሇመጨረሻ ጊዜ ችግሩ
መፍትሄ ማግኘት እንዳሇበት በመንግስት ታምኖበታሌ፡፡
በመሆኑም የጠቅሊይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ህዳር 18 ቀን 2ዏዏ5 ዓ.ም በቁጥር መ8ዏ-
839/1 በተጻፈ ደብዳቤ ዘሊቂነት ባሇውና በተመደበ የሥራ መደብ ሊይ
በኮንትራት/በጊዜያዊነት/ በፌዴራሌ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ተቀጥረው
ያሌተቋረጠ አገሌግልት ሲሰጡ የቆዩ ሠራተኞች በክፍት የቋሚ የሥራ መደቦች ሊይ
በቋሚነት እንዲመደቡ ትዕዛዝ ሰጥቷሌ፡፡ በዚህም መሠረት ማንኛውም የፌዴራሌ
መንግስት መሥሪያ ቤት ይህ መመሪያ እስከተሊሇፈበት ቀን ድረስ ዘሊቂነት ባሇውና
በሲቪሌ ሰርቪስ ሚኒስቴር በተመደበ የሥራ ደረጃ ሊይ በኮንትራት/በጊዜያዊነት
ቀጥሮ ሲያሰራቸው የነበሩ ሠራተኞችን በመሇየት፣

ሀ/ ቋሚ ምደባ ከመከናወኑ በፊት በስሩ የሚገኙና ይህ መመሪያ


የሚመሇከታቸውን የኮንትራት/ጊዜያዊ ሠራተኞችን ዝርዝር እና ላልች
ሁኔታዎች ከዚህ መመሪያ ጋር ተያይዞ በተሊከው ቅጽ ሊይ በመሙሊት
ሇሲቪሌ ሰርቪስ ሚኒስቴር እንዲሊክ፣

ሇ/ የጊዜያዊ/የኮንትራት ሠራተኞቹ ቋሚ የመንግስት ሠራተኛነት በተቋሙ ውስጥ


ሇመቀጠሌ ፍሊጐት ያሊቸው መሆኑ ተረጋግጦ የቅጥር ማስታወቂያ ማውጣት
ሳያስፈሌግ ሠራተኞቹ በፌዴራሌ የመንግስት ሠራተኞች የተፈሊጊ ችልታዎች
መመሪያ መሠረት በኮንትራት/በጊዜያዊነት ተቀጥረው ሲያገሇግለ ሇነበረበት
የሥራ ደረጃ ዝቅተኛውን የተፈሊጊ ችልታ ማሟሊታቸውን እየተረጋገጠ በዚሁ
የሥራ መደብ ሊይ መመሪያው ከተሊሇፈበት ቀን ጀምሮ ቋሚ እንዲሆኑ፣

ሐ. ቋሚ የመንግስት ሠራተኛ ሆነው መቀጠሌ የማይፈሌጉ ጊዜያዊ/ኮንትራት


ሠራተኞች ይህ መመሪያ በተሊሇፈበት አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሊቸው ተቋርጦ
እንዲሰናበቱ ፡፡

መ. ከጊዜያዊ/ከኮንትራት ወደ ቋሚ የመንግስት ሠራተኝነት ሇመቀጠር የተስማሙ


ሠራተኞች በተቋሙ የሚመደቡበት /የሚደሇደለት እንደሚከተሇው ይሆናሌ፡፡

1. ተቋሙ የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ሇውጥ ጥናት አከናውኖ አዲስ


ድርጅታዊ መዋቅር አጥንቶ አጠቃሊይ የሠራተኛ ድሌድሌ
የሚያካሂድበት ደረጃ ሊይ ካሇ ከአጠቃሊይ ሠራተኞች ጋር
ተወዳድረው በሚያሟለበት የሥራ ደረጃ ይመደባለ፡፡
2. ከሊይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ቢኖርም ቋሚ ሰራተኛና
ጊዚያዊ/ኮንትራት ሰራተኛ ተወዳድረው እኩሌ ነጥብ ካገኙ ቋሚ
ሰራተኛው ቅድሚያ ይደሇደሊሌ፡፡

3. መሥሪያ ቤቱ በአዲስ መዋቅር ሠራተኞችን ደሌድል ያጠናቀቀ


ሆኖ ባለት ክፍት የሥራ መደቦች ሊይ ተመድበው የሚያገሇግለት
በጊዜያዊነት/በኮንትራት የተቀጠሩ ሠራተኞች ከሆኑ አጠቃሊይ
የሠራተኞች እንደገና ድሌድሌ ማድረግ ሳያስፈሌግ
ጊዜያዊ/ኮንትራት ሠራተኞቹ ሇሥራ መደቡ የሚያስፈሌገው
ዝቅተኛ ተፈሊጊ ችልታ ማሟሊታቸውን በማረጋገጥ ይመደባለ፡፡

4. ከፍ ሲሌ በፊደሌ ‘ሀ’ የተጠቀሰው ቢኖርም በተመሳሳይ የሥራ


መደቦች ሊይ ያለ የኮንትራት ሠራተኞችን ቋሚ በማድረጉ ሂደት
የሠራተኞች ቁጥር ከሥራ መደቦች ቁጥር የበሇጠ ከሆነ
ሠራተኞችን በማወዳደር ብሌጫ ያገኙት በስራ መደቡ ሊይ
በቋሚነት እንዲቀጠሩ ይደረጋሌ፣

5. በኮንትራት ቅጥራቸው ምክንያት ከፍ ያሇ ወይም ዝቅ የሇ


ደመወዝ የሚከፈሊቸው ሠራተኞች ካለ በሲቪሌ ሰርቪስ ሚኒስቴር
ሇሥራ ደረጃው የተፈቀደው ደመወዝ በቋሚነት ከተመደቡበት ጊዜ
ጀምሮ ይከፈሊቸዋሌ፡፡

6. በቋሚነት እንዲቀጠሩ የተደረጉ የኮንትራት/ጊዜያዊ ሠራተኞች


አገሌግልታቸው ሇጡረታ የሚታሰብሊቸው ቋሚ የመንግስት
ሠራተኛ እንዲሆኑ ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሆን፣
7. ሠራተኞቹ ቀደም ሲሌ በላልች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በቋሚነት
ተቀጥረው ሲያገሇግለ የነበሩ ከሆነ አገሌግልታቸው ከዚህ በኋሊ
ከሚሰጡት አገሌግልት ጋር እየተደመረ እንዲያዝሊቸው፣

ሠ/ በሲቪሌ ሰርቪስ ሚኒስቴር ባሌተመደበና ዘሊቂነት በላሇው የሥራ መደብ ሊይ


በኮንትራት/በጊዜያዊነት ተቀጥረው የነበሩ ሠራተኞች ቅጥር እንዲቋረጥ ሆኖ
በአስቸኳይ እንዲሰናበቱ፣

ረ/ በኘሮጀክት የሚፈፀም የኮንትራት/ጊዜያዊ ቅጥር ቀደም ሲሌ በነበረው አሠራር


እንዲቀጥሌ፣

እንዲደረግና አፈጻጸሙ በአስቸኳይ እንዲገሇጽሌን እያሳሰብን፣ ይህ መመሪያ ሇአንድ ጊዜ


አፈፃፀም ብቻ የሚያገሇግሌ ሲሆን ከየካቲት 30/2005 ዓ.ም በኋሊ ተግባራዊ ማድረግ
አይቻሌም፡፡

ከዚህ በኋሊ በማንኛውም የፌዴራሌ መንግስት መሥ/ቤት እጅግ አስፈሊጊ ሇሆነና ሇአጭር
ጊዜ ብቻ የኮንትራት/ጊዜያዊ ቅጥር መፈፀም አስገዳጅ ሁኔታ ከተፈጠረ ጥያቄው በቅድሚያ
ሇመሥሪያ ቤታችን እየቀረበ ተቀባይነት ማግኘቱ መረጋገጥ ያሇበት መሆኑን እየገሇጽን፣
ከዚህ ውጭ በማንኛውም መሌኩ የኮንትራት/ጊዜያዊ ቅጥር ፈጽሞ የተገኘ የሥራ ኃሊፊ
በሕጉ መሠረት ተጠያቂ እንደሚደረግ እናስታውቃሇን፡፡

You might also like