You are on page 1of 107

የምግብ መድሃኒት እና ጤና ክብካቤ አስተዳደር እነ

ቁጥጥር ጽ/ቤት የ2009 በጀት ዓመት መሪ እቅድ


የአቅዱ ይዘት

 መግቢያ
 መነሻ ሁኔታ
 የ2009በጀት ዓመት አቅድ
 የክትትል እና ድጋፍ አግባብ
 በአቅድ ትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችልለ ችግሮችና
መፍትሄ እርምጃ
 ማጠቃለያ
 የድርጊት መርሃ ግብር
 አራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ
አስር ክፍለ ከተሞች መካከል አንዱ እና ነባር የከተመው
ክፍል ሲሆን በሰሜን ጉለሌ ፣ በምእራብ አዲስ ከተማ እና
ልደታ በደቡብ ቂርቆስ እና በምስራቅ የካ ክፍለ ከተማ
ያዋስኗታል ፤ ክፍለ ከተማው ነባር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ
ከማስተር ፕላን ውጪ ጥቅጥቅ ብለው የተሰሩ የመኖሪያ
መንደሮች ውስጥ ከ250000 ሺ በላይ ነዋሪዎች
ይኖሩባታል፡፡
 ክፍለ ከተማው ነባር እና የከተማው እንብርት ከመሆኑ
ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ያለባት ሲሆን
ለአብነት የህል አታክልት ተራ ፣ ጎጃም በረንዳ የሚጠቀሱ
ሲሆን 127 በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ጤና ተቋማት ፣
1556 ምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች 711 ጤና ነክ
ተቋማት እና 63 አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ይግኙባታል ፡፡
ክፍለ ከተማው በዚሁ ልክ ዘርፍ ብዙ ችግሮች ያሉባት
ሲሆን መነሻቸው መኖሪያ ቤቶች ከማስተር ፕላን ውጪ
ጥቅትቅ ብለው የተሰሩ ከመሆኑ
 የተነሳ ነዋሪው ህብረተሰብ እና የንግዱ አካላት እንዲሁም
መሃበራዊ ተቋማት የደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ
ስርዓታቸው ደረጀውን የጠበቀ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ
ለተለያዩ ተላላፊ እና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች
የተጋለጡ ሲሆን መንግስት ከዚህ ጋር በተያያዘ
የህብረተሰቡን ጤና ከአደጋ ለመከላከል የጤና ፖሊሲን
መነሻ በማድረግ ምግብ መድሃኒት እና ጤና ክብካቤ
አስተዳደር እና ቁጥጥር ባስልጣን ምስሪያ ቤት የተቋቋመ
ሲሆን
 እንደ አራዳ ባለፈው ሁለት ዓመት በምግብ እና መጠጥ
ተቋማት እና ኢንዱስትሪዎች ፣ የጤና ነክ ተቋማት እና
ኢንዱስትሪዎች ብቃት እና ቁጥጥር ውጤታማነትን የማሻሻል
፣የሃይጅን፣ አካባቢ ጤና አጠባበቅና ተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር
ማጠናከር እና የጤና አገልግሎትን ጥራት ማሻሻል ስራዎች
ለማሳካት የተሸሉ ስራዎች ለመስራት የተሞከረ ቢሆንም
ተግባራትን ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ውጤትን
መሰረት በማድረግ ለመፈጸም የሪፎርም መሳሪያዎችን እንደዋና
መሳሪያ አለመያዝ ፣ የህዝብ ክንፉን እና ባለድርሻ አካላትን
በተቀናጀ መልኩ አለማሳተፍ እና ተግባራትን በሰራዊት ቁመና
አለማከናወን የነበሩ ደካማ ጎኖች ሲሆኑ በቀጣይ 2009 በጀት
ዓመት እንዚህን እጥረቶች በመቅረፍ የጽ/ቤቱን ተልእኮ
ለማሳካት ይህ እቅድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል ፡፡
የእቅዱ መነሻ ሁኔታ
ውስጣዊ ሁኔታዎች ሲተነተኑ
የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ
እንደመነሻ
 በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በክፍለ
ከተማችን የጤና ቁጥጥር ስራ በማጠናከር ነዋሪው
ህብረተሰብ ደህንነቱ እና ጥራቱ የተጠበቀ ግብዓት እና
አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ግብ የጣለ
በዚህ መሰረት ጽ/ቤታችን በዚህ በጀት ዓመት
የእስትራቴጂው ሁለተኛ ዓመት ግብን እንደ መነሻ ታሳቢ
ያደረገ መሆኑ፡፡
የ2008 በጀት ዓመት አፈጻጸም
እንደመነሻ
ከሰራዊት ግንባታ አፈጻጸም አንጻር
 በበጀት ዓመቱ ቀድሞ ለጤና ቁጥጥር ሰራዊት ግንበታ ምቹ
የነበረውን ሁኔታ በመጠቀም በሁለቱም የልማት ሃይሎች ዘንድ
የተሟላ የጤና ቁጥጥር ሰራዊት ለመገንባት እቅድ የተያዘ
ቢሆነም በዝግጅት ምእራፍ ወቅት ለዚህ መሰረት የሆኑትን
የአንድ ለመአስት ቡድንን መልሶ ማደራጀት እቅድ ዝግጅት እና
ኦረንቴሽን በተሸለ መልኩ የተፈጸመ ሲሆን በመንግስት ክንፍ
በኩል ያለው ፈጻሚ በበጀት ዓመቱ በተከሰተው አተት ወረርሽኝ
በሽታ ለመከላከል ከሌሊቱ አስራ እንድ ሰዓት እየተገኘ ቢሆንም
በተግባር አፈጸጸም ወቅት ነባር ባለሙያዎች ወደ ሌላ ቦታ
የተሸለ ደመወዝ አግኝተው መልቀቅ እንዲሁም በሁሉም ደረጃ
የሚገኘው አመራር ለተግባሩ ትኩረት ባለመስጠት ምክንያት
 እስከ ወረዳ የሚገኙ ሁሉም ፈጻሚዎች የጤና ቁጥጥር
ሰራዊት መፍጠሪያ በሆኑት በአንድ ለአመስት ቡድን
ተደራጅተው እቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባታቸው ፣
አደረጃጀቱን በእምነት ተቀብለው የመልካም አስተዳደር
እጦት እና ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ለልማት እንቅፋት
ነው በማለት አጀንዳ አድርገው ውይይት መጀመራቸው
እንደ ጠንካራ ጎን የሚታይ ሲሆን ዘላቂነት ያለው ችግር
ፈቺ ውይይት አለመደረጉ፣ አሁንም እስከ ወረዳ ድረስ
በተሟላ መልኩ የጤና መስፈረት የማያሟሉ ተቋማትን
ብቃት ማረጋገጫ ከመስጠት እነጻር ክፍተቶች ያለ ሲሆን
ባጠቀላይ ለቀጣበበጀት ዓመቱ ለሰራዊት ግንባታ ፡፡
ከሪፎርም መሳሪያዎች አንጻር ያለው አፈጻጸም

 የሪፎርም መሳሪያዎችን በተመለከተ በሁሉም


ወረዳዎችና የስራ ሂደቶች ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር
ለማስቻል በክፍለ ከተማ ደረጃ የእቅዱ ዝግጅት በአንድ
ማእከል እንዲከናወን የተደረገ ሲሆን በዚህ ሂደት ሁለም
ወረዳዎች እቅዳቸውን በእስኮር ካርድ በማስገባት ወደ
ፈጻሚዎች እንዲወርድ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪ
የሪፎርም ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ከሪፖርት
በተጨማሪ በዓመት ውስጥ
 በወረዳ ሁለት ጊዜ ድጋፋዊ ክትትል የተካሄደ ሲሆን
አብዛኛው ወረዳዎች በተሸለ ደረጃ የሚገኙ ሲሆን
የሪፎርም መሳሪያውን በተሟለ መልኩ ተግባራዊ
በማድረግ በጽ/ቤቱ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ያለበት
አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ከማድረግ አንጻር አሁንም
ከፍተኛ ውስንነት ያለ ሲሆን መሰራተዊ ችግሩ የአመራሩ
ክትትል አናሳ መሆን እና ስራውን የለመዱ ባለሙያዎች
ስራ መልቀቅ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ናቸው ፡፡
ሐ. በጽ/ቤቱ የኪራይ ሰብሳቢነት ትግል ያለበት ደረጃ

 በመጀመሪያ ደረጃ ጽ/ቤቱ ከተልእኮው አንጻር የሚያከናውናቸው


ተግባራት የኢኮኖሚው አካል ከሆነው ንግዱ ማህበረሰብ ጋር ከፍተኛ
ቁርኝት ያለው በመሆኑ ከአመራሩ እስከ ፈጻሚው በኪራይ ስብሳቢነት
አመለካከት እና ተግባር ውስጥ የመግባት እድሉ ሲፊ ሲሆን ህን
አመለካከት ለመስበር በጽ/ቤቱ በሚዘጋጁ ማንኛውም መድረኮች
አጀንዳ እንዲሆን እና የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ያለውን
ጥፋት እንዲገነዘቡ እራሳቸውን ከዚህ አይነት አመለካከት እና ተግባር
እንዲያርቁ የመወያየት ስራ የተሰራ ቢሆንም እስከ ወረዳ ባለው የስራ
አፈጻጸም ባሉ ክፍተቶች ዙሪያ ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር ያለቸውን
ዝምድና ተከታትሎ ማረም ላይ የሚቀር ስራ መሆኑ ፣
መ. መልካም አስተዳደር ያለበት ደረጃ

 እንደ ጽ/ቤታችን በመልካም አስተዳደር ችግር የሚነሱ ችግሮች ያሉ


ሲሆን እነርሱም አዲስ ብቃት ማረጋገጫ እና እድሳት የሚሰጠብት
ሂደት ውስጥ ባለሃብቱ ከጤና መስፈርት ባለማሟላት ምክንያት
የሚከሰት ሲሆን ይህን ችግር ከምንጩ በማድረቅ የንግዱ ማህበረሰብ
ላልተገባ ውጪ እንዳይዳረግ እና መልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት
እንዳይሆን ከባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት እና ንግድ ጽ/ቤት ጋር
የስምምነት ሰነድ መፈራረም የተከናወነ ቢሆነም ወጥ የሆነ የጋራ
መግባባት ተፈጥሮ የጤና መስፈረት ግዴታ መሆኑን ከግንዛቤ
በማስገባት መስራት ላይ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት
የተወሰኑ ሙከራዎች ያሉ ሲሆን እንደ ወረዳ አሁንም ውስንነት ያለ
መሆኑ
 ፤ከዚህ በተጨማሪ በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው
የሚሰሩ አብዛኛዎቹ የብቃት መረጋገጫ የማያሟሉ
መሆኑ ከአደራጃቸው አካል በዚህ ዙሪያ የሚደረገው
ድጋፍ አናሳ መሆን በዚህ ምክንያት አብዛኛዎቹ በምግብ
እና መጠጥ ዝግጅት እና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ የምግብ
እና መጠጥ አያያዛቸው ከጤና መስፈረት አንጻር ደካማ
በመሆኑ እርምጃ መውሰድ ላይ የመልካም አስተዳደር
እጦት ምክንት መሆን፤
ሠ. ከመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም አንጻር

 በሴክተሩ የተከናወኑ መደበኛ ስራዎች ስናይ 387 ምግብ እና


መጠጥ ድርጅቶች ፣ 311 ጤና ነክ ተቋማት ፣ 49
ኢንዱስትሪዎች መስፈርቱን በማሟላታቸው አዲስ የብቃት
ማረጋገጫ ተሰጧቸዋል ፡፡ ሌላው ለነባር 1556 ምግብ እና
መጠጥ ድርጅቶች ፣ 689 ጤና ነክ ተቋማት እና 79
ኢንዱስትሪዎች በተሰጣቸው ደረጃ እየሰሩ መሆኑ ተረጋግጦ
የብቃት ማረጋገጫ የታደሰ ሲሆን እንዚህ ተቋማት በተሰጣቸው
መስፈርት መሰረት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ከሁለት
ጊዜ ባለይ በተቋማቱ ላይ አጠቃላይ ቁጥጥር የተካሄደ ሲሆን
 በዚህ ሂደት ከተሰጣቸው የአካካቢ ጤና አጣባበቅ
መሰፈርት በታች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 79 ምግብ እና
መጠጥ ድርቶች ፣ 94 ጤና ነክ ተቋማት እና 05
ኢንዱስትሪዎች አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደባቸው
ሲሆን በአገልግሎት ላይ ቢውሉ ለጤና ችግር ይፈጥራሉ
የተባሉ 8840 ኪ.ግራም ምግብ ፣1367 ኪ.ግራም አሳ
፣360 ሜ.ኩብ አታክልት 2966.5 ሊትር የተለያዩ መጠጥ
አይነቶች እና 2030 ለምግብ ማዘጋጃነት ፣ ማቅረቢያ
የሚሆኑ እነ አልባሳት እንዲወገድ ተደርጓል ፡፡
 ከዚህ በተጨማሪ ህብረተሰቡ የጤናው ቁጥጥር ስራ አካል
እንዲሆን 20809 የህብረተሰብ ክፍል የተለያዩ የቀጠና
መድረኮችን በመጠቀም ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ የተሰራ
ሲሆን 6052 የሚሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ በራሪ ወረቀቶችን
ለማሰራጨት ተችሏል ይህ እንዳለ ሆኖ የንግዱ ማህበረሰብ
ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እንዲያዳብር እና
የቁጥጥር አካል እንዲሆን የተሄደበት ርቀት ከፍተኛ ነው ከዚህ
በተጨማሪ የተወረሱ ምግብ ፣ መጠጥ ቁሳቁስ በወቅቱ
እንዲወገድ አለመደረጉ የታዩ ውስንነቶች ናቸው ፡፡
ሸ. ወቅታዊ ስራዎች አፈጻጸም በተመለከተ (የአተት በሽታ ወረርሽኝ ለማልበስ የተሰራ)

 በከተማችን የተከሰተውን አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት


በሽታ ስርጭትን ለመከላከል ጽ/ቤታችን አቅድ
በማዘጋጀት እስከ ወረዳ ያለውን አመራር እና ፈጻሚ
በማወያየት በመጀመሪያ ዙር በአስራ አራት ቡድን 1074
ምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች ፣ 110 ሉካንዳ ቤቶች እና
300 አታክልትእና ፍራፍሬ መሸጫ ድርጅቶች ላይ
ከአንድ ጊዜ በላይ ቁጥጥር የካሄደ ሲሆን
 የበሽታው ስርጭት መጨመር ተያይዞ የመከላከሉን ስልት
በመቀየር በምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች ፣ስጋ ቤቶች እና
አታክልት እና ፍራፍሬ ቤቶች መጸዳጃ ቤት አጠቃቀም እና
አታክልትንና ፍራፍሬ ለምግብነት ከመዋሉ በፊት ከበሽታ
አምጭ ህዋስ ነጻ ማድረጊያ ዘዴ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ
የተሰራ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ በሁሉም ተቋማት ላይ የጥቆማ
ስርዓት ተዘርግቷል ፤ ከዚህ በተጨማሪ በምግብ እና መጠጥ
ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ምግብ አዘጋጅና አስተናጋጅ ለሆኑ
የምግብ ቤት ሰራተኞች የጤና ትምህረት የተሰጣቸው ሲሆን
የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ ተድረጓል ፡፡
የአመራሩ ሁኔታ

 በጽ/ቤታችን አመራር ሲባል ወረዳ ጽ/ቤት አመራር እና


የክፍለ ከተማ የስራ ሂድት አስተባባሪ ተብሎ የሚለይ
ሲሆን በ2008 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሂድት
ውስጥ ያለቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ለማስቀመጥ
ሁለቱን በየፈርጁ ለይቶ ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው ፣
የወረዳው አመራር

 በወረዳ ያለው አመራር የጽ/ቤቱን ተልእኮ ተረድቶ


በእምነት ጨብጦ ከመንቀሳቀስ አንጻር እቅድ አዘጋጅቶ
ከፈጻሚዎች ጋር የጋራ በማድረግ ወደ ተግባር መግባት
ላይ የተሸለ ሲሆን የተቀመጡ ግቦችን ከማሳካት አንጻር
የሰው ሀይል እና ግብዓት አሟልተው ስራን እና የሰው
ሀይል በማገናኘት እና የተግባራትን አፈጻጸምን ወቅቱን
ጠብቀው እተከታተሉ እየገመገሙ እና ማስተካከያ
እርምጃ እወሰዱ መሄድ ላይ ውስንነቶች ያሉ ሲሆን
 በወረዳ ያለው አመራር የጽ/ቤቱን ተልእኮ ተረድቶ
በእምነት ጨብጦ ከመንቀሳቀስ አንጻር እቅድ አዘጋጅቶ
ከፈጻሚዎች ጋር የጋራ በማድረግ ወደ ተግባር መግባት
ላይ የተሸለ ሲሆን የተቀመጡ ግቦችን ከማሳካት አንጻር
የሰው ሀይል እና ግብዓት አሟልተው ስራን እና የሰው
ሀይል በማገናኘት እና የተግባራትን አፈጻጸምን ወቅቱን
ጠብቀው እተከታተሉ እየገመገሙ እና ማስተካከያ
እርምጃ እወሰዱ መሄድ ላይ ውስንነቶች ያሉ ሲሆን
የክፍለ ከተማ የስራ ሂደት አስተባባሪ ያሉበት ደረጃ
 በጽ/ቤቱ ሁለት የስራ ሂደት መደብ ያለ ሲሆን የሁለቱም
መደቦች አስተባባሪ ከመደበኛ ስራቸው ደርበው እንዲሰሩ
በተወከሉ ባለሙያዎች የሚመራ ሲሆን ይህ ደግሞ
በተወከሉት ባለሙያዎች ላይ ጫና የሚፈጥር ቢሆንም
የጽ/ቤቱን እቅድ መነሻ በማድረግ እቅድ አዘጋጅተው ወደ
ተግባር መግባት ፣ ሪፎርም መሳሪያዎችን በእምነት
ተቀብሎ ተግባረዊ ማድረግ እና በወረዳ የሚገኙ
ፈጻሚዎችን በሂደት ለማብቃት ያላቸው እንቀስቃሴ
የተሸለ ቢሆንም ሰራተኛን እና ስራን አገናኝተው
አፈጻጸሙን እገመገሙ እና ማስተካከያ እያደረጉ መሄድ
ላይ ወስንነት ያለባቸው መሆኑ፡፡
የሴክተሩ ፈጻሚዎች ያሉበት ደረጃ

 የሴክተሩ ፈጻሚዎች የተሰጣቸውን ተግባር ተቀብለው


ከመፈጸም አንጻር የተሸሉ እና የሰራዊት መገቢያ
አደረጃጀቶችን አንድ ለአምስት ውይይት እቅድ
አዘጋጅተው ኪራይ ሰብሳቢነት እና መልካም አስተዳደር
ችግር አጀንዳ አድረገው ውይይት መጀመራቸው
በጠንካራ ጎን የሚታይ ሲሆን አሁንም የሴክተሩን ተልእኮ
እና ግብ በመረዳት በራስ ተነሳሽነት ስራዎችን መፈጸም
ላይ የሚቀር መሆኑ ፡፡
የህዝብ አደረጃጀት ያሉበት ደረጃ እንደመነሻ

 በጽ/ቤታችን የህዝብ አደረጃጀት ተብለው የተለዩት


ወጣት ሊግ ፣ወጣት ፎረም ፣ወጣት መሀባር ፣ ሴት
ፎረም ፣ሴት መሀባር ፣ሴት ሊግ እና ነዋሪ ፎረም ሲሆኑ
በአስፈጻሚው እና ፈጻሚው አካል ላይ ከተቋቋሙበት
አላማ አንጻር መብታቸውን ለማስከበር የሚያደርጉት
እንቅስቃሴ እንዲሁም የጤና የቁጥጥሩ ተግባር ላይ
ሚናቸውን ከመወጣት አንጻር ውስንነት ያለ መሆኑ፡፡
የግብዓት አጠቃቀም በተመለከተ

 የጽ/ቤቱ የተቀመጡትን ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት


የሰው ሃይል የቢሮ ቋሚ እና አላቂ ግብዓቶች ማሟላት ወሳኝ
ሲሆን በ2008 በጀት ዓመት ከዚህ አንጻር የተሟላ ግብዓት ይዞ
ወደ ተግባር የtገባ ቢሆንም በትግባራ ምእራፍ እና ማጠቃለያ
ምእራፍ ላይ አርባ በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ ባለሙያ
በዝውውርና በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማ እና ፌደራል
ተቋማት የሄዱ ሲሆን በጽ/ቤቱ የተጀመሩ በተለይ ሰራዊት
የሚፈጠርባቸው አደረጃጀቶች እና የሪፎርም ስራዎች
አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊሳርፍ የቻለ ሲሆን
 ሌላው በበጀት ዓመቱ ተመደበውን ጽ/ቤት በጀት አሟጦ
መጠቀም ላይ የተሸለ አፈጻጸም ያለ ቢሆንም ከፍተኛ
የበጀት ዝውውር መከናወኑ እና የበጀት ዓመቱ
ማጠቃለያ ላይ በጀትን ለመጠቀም መሯሯጥ የነበረ
ሲሆን ይህን እንደ እጥረት መወሰድ እና መስተካከል
ያለበት ነው ከዚህ በተጨማሪ በጽ/ቤቱ የሚገኘውን ቋሚ
የቢሮ መገልገያ እቃዎች በመመዝገብ ስርዓት ማስያዝ
ላይ ችግሮች ያሉ መሆኑ፤
የአካባቢ ውጫዊ ሁኔታ ግምገማ
የመንግስት ፖሊሲ እና እስትራቴጂ
 መንግስት የህብረተሰቡ ጤና ለማሻሻል መከላክልን መሰረት
ያደረገ የጤና ፖሊሲ ቀርጾ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን ይህን
መነሻ በማድረግ በፌደራል አዋጅ ቁጥር 661/2002 እና
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 30/2004
የምግብ እና መድሃኒት እና ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና
ቁጥጥር ባለስልጣን እነዲቋቋም ያደረገ ሲሆን እንደ አራዳ
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የጤና ቁጥጥር ስርዓቱን እስከ
ወረዳ ድረስ ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን ጤና
ለመታደግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአስሩም ወረዳ
ጽ/ቤት ተቋቁሞ ስረዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡
የኢንፎርሜሽንእና ቴክኖሎጂ

 ዘመኑ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሊጂ ሲሆን ጽ/ቤታችን


ስራን ለማሳለጥ እና የተገልጋዩን ህብተተሰብ እርካታ
ከማምጣት አንጻር ቴክኖሎጂውን ከመጠቀም አንጻር
አሁንም እጥረቶች ያሉ መሆኑ ፣
ባለድርሻ አካላት ሁኔታ አንደ መነሻ

 የጽ/ቤቱ ባለድርሻ አካላት ብዙ ቢሆኑም ከዚህ በታች


የተዘረዘሩት ባለፈው በጀት ዓመት ለህብረተሰቡ
በሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ ያጋራ እና ተመጋጋቢ ሚና
ባላቸው ላይ ይሆናል በዚህ መሰረት ጤና ጽ/ቤት ፣ ደንብ
ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት ፣ ባህልና ቱሪ,ዝም ጽቤት
፣ንግድ ጽ/ቤት፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይ
ጽ/ቤት
 ፣ፖሊስ መምሪያ ከጽ/ቤታችን ጋር ጥብቅ የስረ ግንኙነት
የነበራቸው ሲሆን በእቅዳችን ያስቀመጥነውን ግቦች
ከማሳካት አንጸር ያላቸውን ሚና ለይቶ በደረጃ
ለማስቀመጥ የስምምነት ሰንድ መፈራረም የተካሄደ
ቢሆንም ቅንጅታዊ አሰራሩ የተመራበት አግባብ ክፍተት
ያለበት ሲሆን ከዚህ አንጻር ጽ/ቤቶቹ ያሉበት ደረጃ
እደሚከተለው ይሆናል ፣
ሀ. ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

 ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ለሆቴል ፣ሬስቶራንት፣ ገስት


ሀውስ ወዘተ የሙያ ብቃት ማረጋጫ የሚሰጥ ሲሆን
በበጀት ዓመቱ ከጽ/ቤታችን ጋር በተደረገው የትስስር
ሰነድ መፈራረም እና የሁለትዮሽ ውይይት በኋለ እንደ
ክፍለ ከተማ ጽ/ቤቱ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ከመስጠቱ
በፊት የጤና መስፈረት ማሟላታቸውን ማረጋገጥ
መጀመራቸው በጥሩ የሚወሰድ ሲሆን ይህ አሰራር
ወረዳ ድረስ አለመፈጸሙ እንደ አሁንም ያለ ችግር
መሆኑ፣
ለ. ጤና ጽ/ቤት

 ከጤና ጽ/ቤት ጋር ህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በጋራ


ሚናዎች ላይ የትስስር ሰነድ መፈራረም የተከናወነ
ሲሆን በዚያው ልክ በቅንጀት የተሰሩት ስራዎች በጣም
ዝቅተኛ ናቸው ምክንያቱ ጤና ጣቢያዎች በአዲሱ አገር
አቀፍ የጤና መስፈረት መሰረት ፈቃድ እንዲያዎጡ እና
ቁጥጥር የሚደረገባቸው አካሄድ ላይ ክፍተት የነበረ
ሲሆን የኋላ ኋላ ከሁለት ጤና ጣቢያዎች የሙያ ፈቃድ
ያወጡ መሆናቸው እንደ በጎ ጎን የሚቆጠር መሆኑ፣
ሐ. ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት

 ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት የስምምነት ሰነድ


በተፈራረመበት ልክ ከጽ/ቤታችን ጋር ስራዎች
የተከናወኑ ሲሆን ለአብንት ያህል በስጋ ቤቶች ፣
በአታክልት ተራ የተካሄደው የቁጥጥር ስራ የሚጠቀስ
ሲሆን የተከናወኑ ስራዎችን በስምምነት ሰነዱ ላይ
በተቀመጠው የግንኙነት ወቅት ጠብቆ አለመወያየት
እንደ እንደ እጥረት የሚወሰድ ነው ፡፡
መ. ንግድ ጽ/ቤት

 ንግድ ጽ/ቤት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የበለጠ


ከጽ/ቤታችን ጋር የስራ ግንኙነት ያለው ሲሆን በ2008
በጀት ዓመት ስራዎችን እየተናበቡ እና እያረሙ ከመሄድ
አንጻር የተሸለ ሲሆን አሁንም በወረዳ ደረጃ ንግድ
ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ
በንግድ ጽ/ቤት ምንም እርምጃ ሳወሰድባቸው ብቃት
እንዲረጋገጥላቸው ወደ ጽ/ቤት የሚላኩ ሲሆን የጤና
መስፈረት ማሟላት የማችሉት ዘንድ እንደ መልካም
አስተዳደር እጦት መነሻ መሆኑ፣
ሠ. ፖሊስ መምሪያ

 ከመምሪያው ጋር የስምምነት ሰነድ የመፈራረም ሂደት


ባይኖርም እስከ ወረዳ ባለው ጽ/ቤታችን ጋር
በሚያድርጉት የቁጥጥር ስራዎች ላይ ጸጥታ ችግር
እንዳያጋጥመናቸው ድጋፍ ከማድረግ አንጻር በጥንካሬ
የሚወሰድ መሆኑ፣
ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት

 ቀድሞ በጥቃቅን አነስተኛ በተለያየ ዘርፍ ተደራጁ


አካላት እዛኛዎቹ የጤና መስፈረት ዝቅተኛውን ደረጃ
የማያሟሉ መሆኑ ይህን ከጽ/ቤታችን ጋር በጋራ
እንዲስተካከል ከማድረግ ይልቅ በጥቃቅን እና አነስተኛ
የሚደራጁ ፈጽሞ የጤና ብቃት ማረጋገጫ የማያሟሉ
እና የኢኮኖሚው መሰረት ስለሆኑ መስፈርቱ
ኮምፕሮማይዝ እንዲሆን ግፊት ማድረግ ፣
የንግዱ ማህበረሰብ እንደመነሻ

 የንግዱ ማህበረሰብ ተብለው እንደ ጽ/ቤታችን


የምንያቸው ምግብ እና መጠጥ አገልግሎት ሰጪ
ድርጅት ፣የምግብ እና መጠጥ ማዘጋጃ እና ማቀነባበሪያ
ድርጅት ፣የምግብ እና መጠጥ ግብዓት ማከፋፈያ እና
ችርቻሮ መሸጫ ድርጅት፣ ጤና ነክ ተቋማት እና
ኢንዱስትሪዎች ጤና ተቋማት እና የመድሃኒት ችርቻሮ
ንግድ ድርጅት ባለቤቶች ሲሆኑ
 ቀደም ብሎ ጽ/ቤቱ እንደተቋቋመ አብዛኛው የንግዱ
ማህበረሰብ የጤና ቁጥጥር ስራዎች ተቋማቸውን
የሚያፈርሱ ለስራቸው እንቅፋት አድርጎ ማሰብ የነበረ
ሲሆን የህ አመለካከት በተለያየ ጊዜ በተደረጉ ውይይቶች
በተሟላ መልኩ ባይሆንም እየተቀየረ የመጣ ሲሆን
አሁንም የንግዱ ማህበረሰብ የሚያጋጥማቸውን ችግር
ተቋመዊ በሆነ መልኩ እንዲፈታ ከመፈለግ ይልቅ
ከባለሙያዎች ጋር በመደራደር /በመነጋገር ለመፍታት
መሞከር
የጽ/ቤቱ የ2009 በጀት ዓመት እቅድ
የጽ/ቤቱ ራእይ

 በ2012 አዲስ አበባ በአፍሪካ ከሚገኙ አቻ ከተሞች የላቀ


የጤናና ጤና ነክ የሃጅን እና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ
የቁጥጥር ስርዓት ተፈጥሮ ማየት፡፡
የጽ/ቤቱ ተልእኮ

 የጤና ባለሙያዎችን ሙያዊና ሰነ ምግባራዊ ብቃት


በማረጋገጥ በመስጠት፤ የጤና፤ ጤና ነክ፤ የምግብና
የመድሃኒት ተቋማት ብቃት በማረጋገጥ ፈቃድ
በመስጠትና የኃይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ
እንዲሁም የአገልግሎትቸንና ግብአቶች ጥራት
ደረጃቸውን ለማስጠበቅ እንስፔክሽን በማካሄድ እና
ወቅታዊ የጤና ቁጥጥር መረጃ ለህብረተሰቡ በማቅረብ
የህብረተሰቡን ጤናን ማበልጸግና መጠበቅ ነው፡፡
የጽ/ቤቱ እሴቶች

 ተጠያቂነት፣
 ግልጽነት፣
 የላቀ አገልግሎት መስጠት፣
 ለለውጥ ዝግጁነት፣
 በእዉቀትና በእምነት መምራት/መስራት፣
 ለሙያ ስነምግባር ተገዢነት፣
 ጥራት ተቀዳሚ ተግባራችን ነው፣
የማስፈጸሚያ ስልቶች

 ዝርዝር አቅድና ፈጻሚዎችን ማዘጋጀት


 ስራዎችን በጤና ቁጥጥር ሰራዊት አቅም መፈጸም
 ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ
 የማስፋት ስትራቴጂ ተግባረዊ ማድረግ
 የክትትልና ድጋፍ አግባብን ማጠናክር
 የኪራይ ሰብሳበቢነት ምንጮችን ከዝህብ አደረጃጀቶች ጋር
በመሆን መለየት እና የማክሰሚያ አቅድ አዘጋቶ ወደ ተግባር
መግባት እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ተግባሩን እየገመገሙ
መሄድ ፣
 የሪፎርም ስራዎችን በሁሉም ወረዳዎች እና የስራ ሂደቶች
በተሟላ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ
 በቀጠና ደረጃ የሚገኙ የሴት እና ወጣት ልማት ቡድን አቅም
አድርጎ መጠቀም
 ውስን የሆነውን ሀብት በቁጠባ መጠቀም
የጽ/ቤቱ ቁልፍ ተግባር

 የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተደራጀ የቁጥጥር


ሰራዊት ቁመና በላቀ ደረጃ መፈጸም ነው በዚሁ ሂደት
ከሴክተራችን ባህሪ አንጻር ለልማታችን አዳጋ የሆነውን
የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባር በሰራዊት
አቅም በመታገል በምትኩ ልማታዊ አስተሳሰብ እንዲኖር
ማስቻል ፣
የቁልፍ ተግባሩ ዓላማ

 በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የቁጥጥር


ሰራዊት በመገንባት የመልካም አስተዳደር
ተግባሮችን ውጤታማ በሆነ መልኩ መፈጸም፣
 በክፈለ ከተማችን የሴክተራቸን አገልግሎት
ተደራሽነት ፣ ፍትሃዊነት ፣ እና ጥራትን በማረጋጥ
የምእተ ዓመቱን ግብ ማሳካት፣
 የመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥና የሪፎርም
ስራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ በመምራት እና የህዝብ ክንፍ
የሆነውን አደረጃጃት በማነቃነቅ ሴክተራችንን አገልግሎት
አሰጣጥ ጥራት እና ቅልጥፍና ላይ መሰረታዊ ለውጥ
ማምጣት
 የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባር ላይ በሰራዊት
አቅም በመጠቀም የተደራጀና ቀጣይነት ያለው ትግል
በማካሄድ ልማተዊ አመለካከት ማስፋትና እና የኪራይ
ሰብሳቢነት አደጋ መቀነስ
የቁልፍ ተግባሩ ግብች እና ግቦችን ለማሳካት መካወን
ያለባቸው ተግበሮች
ግብ 1. ከክፍለ ከተማ አስከ ወረዳ ያለውን የሴክተሩን
አመራር ፣ ፈጻሚ እና አገልግሎት ፈላጊ ውስጥ
ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ በመፍጠር
የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባርን ማዳከም

የሚከናወኑ ተግባራት

 4000 የሴት እና ወጣት ልማት ቡድን በጤና ቁጥጥር


ስራዎች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ
 ለ2261 የንግዱ ማህበረሰብ በመልካም አስተዳደር እና
ኪራይ ሰብሳቢነት መከላከል ዙሪያ ማወያየት
 ለ100 የጸጥታ አባላት በህገ ወጥ ተግባራትን መከላከል
ዙሪያ ማወያየት
ግብ 2. የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር
የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ
እንዲሆኑ ማድረግ
 በሁሉል ደረጃ እቅድ በእስኮር ካርድ እንዲዘጋጅ ማድረግ
 በእስታንዳርድ በሚሰጡ አግልግሎቶች ዙሪያ በየደረጃው ካለ
አመራር እና ፈጻሚ ጋር መግባባት ላይ መድረስ
 ለተገልጋዩ ህብረተሰብ አስተያየቱን የሚሰጥበት እና
ቅሬታውን የሚያቀርብበት ስርዓት መዘርጋት
 በበጀት ዓመቱ ውስጥ በሪፎርም መሳሪያዎችን ለማጠናከር
ሁለት ጊዜ ድጋፋዊ ክትትልማድረግ
 12 አመራርና 48 ፈጻሚዎች በአገልግሎት አሰጣጥ
ዙሪያግንዛቤ ማስጨበጥ
ግብ 3. በሴክተራችን ለሰራዊት መገንቢያ
የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የጤና ቁጥጥር
ሰራዊት በመገንባት የመልካም አስተዳደር
ስራዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ
የሚከናወኑ ተግባራት
 የአንድ ለአምስት እና የለውጥ ሀይል ቡድን እንደገና ማደራጀት
 አደረጃጀቶች እቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባት
 በአምት ሁለት ጊዜሞዴል ምዘና ማካሄድ
 2 ሞዴል የስራ ሂደት ፣ ሁለት ሞዴል የለውጥ ሀይል ቡድን ፣ ሶስት
ሞዴል አንድ ለአመስት እና 9 ሞዴል ፈጻሚ መለየት
 የህዝብ አደረጃጀቶችን በጤና ቁጥጥር ስራ ዙሪያ እቅድ እንዲያዘጋጁ
ድጋፍ ማድረግ
 አረጃጀቶች በእቅዱ መሰረት አፈጻጸማቸውን በሩብ ዓመት አንድ
ጊዜ መገምግም
 ሶስት ሞዴል የህዝብ ክንፍ መፍጠር
አቤይት ተግባር ስራዎች
የበጀት ዓመቱ የጽ/ቤቱ ዓቤይት ተግባር

 የምግብ ደህንነት ፣ጥራት ፣የመድሃኒቶች ደህንነት


፣ፈዋሽነት ፣ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀም የህክምና
ባለሙያዎች ብቃት እና አሰራር ፣የሃይጅን ፣የአካባቢ ጤና
እና የጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግበት አነስተኛ
ኢንዱስትሪዎች የቁጥጥር ደረጃዎችን ማሟላታቸውን
የማረጋገጥ ስራ ይሰራል ፡፡
የአቤይት ተግባር ዓለማዎች

 የመንግስት፤ ጤና ተቋማት ካለዉ የከተማዋ እድገት ጋር


የሚመጣጠን፣ ስታንዳርዱንና ደረጃዉን የጠበቀ እንዲሆን
በስታንዳርዱ መሰረት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 ለግል፣ ለመንግስታዊ ባልሆኑ ጤና ተቋማትና፤ የመድኃኒት
ችርቻሮ ንግድ ድርጅቶችና የባህል መድሃኒት ቤቶች
በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት የሙያ ሥራ ፈቃድ
በመሰጠት እና ወቅታዊ እድሳት በማድረግ ከከተማዋ
እድገት ጋር ተመጣጣኝና ደረጃዉን የጠበቀ ጤና ተቋም
እንዲኖር ማድረግ፣
 ለግል፣ ለመንግስታዊ ባልሆኑ ጤና ተቋማትና፤ የመድኃኒት
ችርቻሮ ንግድ ድርጅቶችና በተቀመጠው ስታንዳርድ
መሰረት የሙያ ሥራ ፈቃድ በመሰጠት እና ወቅታዊ
እድሳት በማድረግ ከከተማዋ እድገት ጋር ተመጣጣኝና
ደረጃዉን የጠበቀ ጤና ተቋም እንዲኖር ማድረግ፣
 በሙያ ስነ-ምግባርና ክህሎት የተላበሰ ባለሙያና ጥራት
ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት የጤና ባለሙያው
ቁጥጥር ስርዐት ይጠናከራል፡፡
 በተቀመጠዉ ስታንዳርድ (የአካባቢ ጤና አጠባበቅ)
መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የምግብና መጠጥ
ድርጅቶች የጤና-ነክ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች አዲስ
ለሚያወጡም ሆነ እድሳት ለሚያደርጉ ንግድ ተቋማት
የብቃት ማረጋገጫ በመስጠት ደረጃዉን የጠበቀ ጤና-ነክ
ተቋምና ደህንነቱና ጥራቱ የተረጋገጠ ምግብና መጠጥ
እንዲኖር የማረጋገጥ ስርዓቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
 በምግብና መጠጥ፣ ጤና-ነክ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች
የሚሰጠውን አገልግሎት፣ የምግብ ደህንነትና ጥራት
በተረጋገጠና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እዲከናወን
የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት እንዲጠናከር ይደረጋል
 ዘርፈ-ብዙ (ኤች-አይ-ቪ/ኤድስ፣ ሴቶች፣ ህፃናት እና
ወጣቶችን ያካተቱ …) ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን ትኩረት
ሰጥቶ መስራት፣
የአቤይት ተግባር ግቦች እና ግቦችን ለማሳካት
የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት
ግብ 1. የህዝብ ተሳትፎና የልማት ባለቤትንነትማሳደግ

 ተግባር 1. በእቅድ ዝግጅት አንድ ፣ በእቅድ አፈጻጸም አራት


እና ምዘና ላይ ሁለት ጊዜ የህዝብ አደረጃጀቶችን ማሳተፍ
 ተግባር 2. በምግብ ፣መድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር
እና ቁጥጥር ዙሪያ 176 ወጣት እና 565 የሴቶች ልማት
ቡድን ማሳተፍ ፣
 ተግባር 3. በምግብ መድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር እና
ቁጥጥር ዙሪያ 2261 ባለሃብቶች ግንዛቤ ማስጨበጥ
 ተግባር 4. የጤና ቁጥጥር ስራዎች ላማሳደግ የሚረዱ
የጥቆማ ስርዓት 565 የሴቶች እና 176 የወጣት ልማት ቡድን
በመጠቀም በማሳደግ ለሁሉም ጥቆማዎች ምላሽ መስጠት
ግብ 2. የመረጃ ተደራሽነት እና ጥራትን ማሳደግ

 ተግባር 1. የጤና ቁጥጥር ስርዓት የሚያሻሽል 9 ዓይነት


መረጃዎችን በበራሪ ወረቀት እንዲዘጋጅ ማድረግ
 ተግባር 2. የጤና ቁጥጥር ስራዎችን ለማሻሻል
መረጃዎችን በበራሪ ወረቀት እና በኤፎር በማዘጋጀት
ተደራሽ ማድረግ
ግብ 3. ህብረተሰቡ በጤና ተቋማት በግል አገልግሎት ሰጪ እና ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶች ላይ ያለውን የጤና ቁጥጥር ስራዎች እርካታ ማሳደግ ፣

 ተግባር 1. በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ የሚፈጥሩ አሰራሮችን


በመለየት ማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ እርካታውን 75 በመቶ
ማድረስ
 ተግባር 2. በጽ/ቤቱ ተገልጋዮች በሚሰጡ አግልግሎቶች
እርካታውን በሚለካ ችግር በሚፈታ መልኩ ተጤቂነትን
በሚያሰፍን መልኩ ስርዓት መፍጠር
 ተግባር 3. ህብረተሰቡ በጤና ቁጥጥር እርካታ ዳሰሳ ጥናት ሁለት
ጊዜ ማካሄድ
 ተግባር 4. የህብረተሰብ የጤና እርካታ ዳሰሳ ጥናት ውጤት መሰረት
የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ
ግብ 5. ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም ማሳደግ

 ተግባር 1. የጽ/ቤቱን በጀት ውጤታማ በሆነ መልኩ


ለመጠቀም የበጀት አጠቃቀም እቅድ ማዘጋጀት
 ተግባር 2. የበጀት አጠቃቀምን በሶስት ወር ውስጥ
እየገመገሙ መሄድ
 ተግባር 3. በጽ/ቤቱ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ
ንብረቶች ምዝገባ እንዲደረግ ማዳረግ
ግብ 6. የመልካም አስተዳደር ለመፍታት የኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከት እና ተግባር መቀነስ

 ተግባር 1. ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓት


መዘርጋት
 ተግባር 2. ተገላጋዩ ህብረተሰብ አግልገሎት አግኝቶ ሲጨርስ
በተሰጠው አገልግሎት አስተያየት እና ሀሳብ አንዲያቀርብ ማድረግ
 ተግባር 3. ተግላጋዩ ህብረተሰብ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ
የሰጠውን አስተያየት በመለየት (በተለይ በመልካም አስተዳደር
ችግር እና ኪራይ ስብሳቢነት ዝንባሌ ዙሪያ )
 ተግባር 4. አገልግሎት ፈላጊው ህብረተሰብ በሰጠው አስተያየት
ዙሪያ በዓመት አራት ጊዜ መድረክ ማዘጋጀት ፣
 ተግባር 5. ህብረተሰቡ በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት በሰጠው
አስተያያት መሰረት በአሰራሮች ላይ ማስተካከያ ማድረግ
ግብ 7. የምግብና መጠጥ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ብቃትና ቁጥጥር
ውጤታማነትን ማሻሻል

 ተግባር 1. የግል ባለሃብቱ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው


ምግብ እና መጠጥ ግብዓቶች በመለየት ለጽ/ቤታችን
እንዲያሳውቁ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት
 ተግባር 2. መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ ሁሉም ምግብ
እና መጠጥ ድርጅቶች አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት
 ተግባር 3. ለ1556 ምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች
የዘመመኑን የብቃት ማረጋገጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 4. መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ ሁሉም ምግብ
እና መጠት ኢንዱስትሪዎች አዲስ የብቃት ማርጋገጫ
መስጠት
 ተግባር 5. ለነባር 116 ምግብ እና መጠጥ ኢንዱስቱሪዎች የብቃት
ማረጋገጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 6. በነባር 735 ምግብ እና መጠጥ አገልግሎት መስጫ እና
594 ማከፋፋያ እና መሸጫ ድርጅቶች በዓመት ሁለት ጊዜ ክትትል
እና ቁጥጥር ማካሄድ
 ተግባር 7. በ116 ምግብ እና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላያ በዓመት
ሁለት ጊዜ ክትትል እና ቁጥጥር ማካሄድ
 ተግባር 8. ምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች በድርጅታቸው
የሚያዘጋጁትም ምግብ ጥራት የሚያረጋግጡበት ስርዓት
መዘርጋት
 ተግባር 9. በቁጥጥር እና ክትትል ወቅት ጉድለት
የተገኘባቸው ምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች እና
ኢንዱስትሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ
 ተግባር 10. በምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች በሚደረግ
ቁጥጥር እና ክትትል ለብክለት የተጋለጠ ነው ተብሎ
የሚጠረጠር ምግብ እና መጠጥ ላቦራቶሪ ምርመራ መላክ
 ተግባር 11. በምግብ እና መጠጥ ድርጅቶች ላይ በሚደረግ
ቁጥጥር ወቅት የተለዩ ለጥቅም የማይውሉ ምግብ ፣መጠጥ
እና ቁሳቁሶች እንዲወገዱ ማድረግ
ግብ 8. የጤና ነክ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ብቃትና
ቁጥጥር ውጤታማነትን ማሻሻል
 ተግባር 1. መስፈርት አሟልተው ለተገኙ ሁሉም ጤና ነክ
ተቋማት አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት
 ተግባር 2. ለ721 ነባር ጤና ነክ ተቋማት የብቃት
ማረጋገጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 3. መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ ሁሉም ጤና
ነክ ኢንዱስትሪዎች አዲስ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት
 ተግባር 4. ለነባር ጤና ነክ ተቋማት ኢንዱስትሪዎች
ብቃት ማረጋጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 1. መስፈርት አሟልተው ለተገኙ ሁሉም ጤና ነክ
ተቋማት አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት
 ተግባር 2. ለ721 ነባር ጤና ነክ ተቋማት የብቃት
ማረጋገጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 3. መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ ሁሉም ጤና
ነክ ኢንዱስትሪዎች አዲስ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት
 ተግባር 4. ለነባር ጤና ነክ ተቋማት ኢንዱስትሪዎች
ብቃት ማረጋጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 5. በ548 ነባር ጤና ነክ ተቋማት ሁለት ጊዜ ክትትል እና
ቁጥጥር ማድረግ
 ተግባር 6. በ2 ጤና ነክ ኢንዱስትሪዎች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር
ማካሄድ
 ተግባር 7. በቁጥጥር እና ክትትል በታየባቸው ጉድለት
ያላስተካከሉ ጤና ነክ ኢንዱስትሪዎች ላይ አርምጃ መውሰድ
 ተግባር 8. በቁጥጥር እና ከትትል ወቅት በጤና ነክ ኢንስትሪዎች
ህብረተሰቡ ቢጠቀሙበት ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል
የኢንዱስትሪ ፍሳስ ናሙና ለላቦራቶሪ ምርመራ መላክ
 ተግባር 9. በክፍለ ከተማችን ህዝብ የሚሰበሰብበት
1255 ተቋማት ላይ የትንባሆ ማጨስ ክልከላ እንዲኖር
ማረጋገጥ
 ተግባር 10. በክፍለ ከተማችን አደንዛዥ አጽ ወሰድበታል
ተብሎ የተጠረጠረ 6 ተቋማት ላይ ቁጥጥር እና ክትትል
ማድረግ
ግብ 9. የሃይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ማጠናከር

 ተግባር 1. በክፍለ ከተማችን በአካባቢ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ


ህብረተሰቡ ጥቆማ የሚደረግበት ስርዓት መዘርጋት
 ተግባር 2. ከህብረተሰቡ በአካባቢ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ
ለቀረቡ ሁሉም ጥቆማዎች ምለሽ መስጠት
 ተግባር 3. በአመቱ ውስጥ በወረዳ ደረጃ 60 ጊዜ የአካባቢ
ብክለት ቁጥጥር ማካሄድ
 ተግባር 4. በክፍለከተማችን በወረዳ ደረጃ የድምጽ ብክለት
እያደረሱ የሚገኙ 30 ተቋማት ክትትል እና ቁጥጥር ማካሄድ
ግብ 10. የጤና አገልግሎት ጥራት ማረጋገጥ

 ተግባር 1. መስፈርት አሟልተው የተገኙ የግል እና የመንግስት


ጤና ተቋማት አዲስ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት
 ተገባር 2. ለ92 ነባር የግል እና መንግስት ጤና ተቋማት ሙያ
ብቃት ማረጋገጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 3. መስፈርቱን ላሟሉ 29 ነባር የመድሃኒት ችርቻሮ
ንግድ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ እድሳት ማድረግ
 ተግባር 4. መስፈርቱን ላሟሉ ሶስት የመድሃኒትና ችርቻሮ
ንግድ ድርጅቶች አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት
 ተግባር 5. በሁሉም ጤና ተቋማት ትንባሆ እንዳይጨስ ክልከላ
እንዲኖር ማድረግ መከታተል
 ተግባር 6. በቁጥጥር እና ክትትል ጉድለት በተገኘባቸው ጤና
ተቋማት እና መድሃኒት እና ችርቻሮ ንግድ
 ተግባር 7. 12 የግል አና መንስግት ጤና ተቋማት እና መድሃኒት እና
ችርቻሮ ንግድ ድርጅቶች የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ ስርዓት
እንዲዘረጉ ማድረግ
 ተግባር 8. አግባበዊ የመድሃኒት አጠቃቀም በስራ ላየ የሚያውሉ
እና የማያውሉ ጤና ተቋማትን በመለየት ችግር ባለባቸው ላይ
የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ
ግብ 11. የጤና ባለሙያዎችን ሙያዊ ብቃትና ስነ ምግባር ማረጋገጥ

 ተግባር 1. በበጀት አመቱ ውስጥ በክፍለ ከተማችን


በሚገኙ 910 የግል እና መንግስት ጤና ባለሙያዎች ላይ
ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ ፣
 ተግባር 2. በክፍለ ከተማችን ለሚገኙ 910 የግል እና
መንግስት ጤና ተቋማት ባለሙያዎች በስነ ምግባር ዙሪያ
የአንድ ጊዜ ስልጠና መስጠት
 ተግባር 3. በግል ጤና ተቋም ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች
መልቀቂያ እና ድጋፍ ደብዳቤ መጻፍ
ግብ 12. አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታምነት ማሻሻል

 ተግባር 1. እስታንዳርድ ያላቸውን 42 አገልግሎቶች ላይ


በየደረጃው ካለው አመራር እና ፈጻሚ ጋር መግባባት ላይ መድረስ
 ተግባር 2. የሚሰጡ አገልግሎቶች በጊዜ በጥራት እና እርካታ
(ነባራዊ ሁኔታው በሚፈቅደው መሰረት ) እንዲለኩ ማድረግ
 ተግባር 3. ለህብረተሰቡ በface book በመታገዝ መረጃን
ተደረሽ እንዲሆን ማድረግ
ግብ 13. የትስስርና ባለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አሰራር ስርዓት ማሳደግ

 ተግባር 1. ባለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ስር በማከተት


የሚታቀዱ ስራዎችን በመለየት ከአስሩ ወረዳ እና ሁለት
ክፍለ ከተማ የስራ ሂደት በእቅድ እንዲካተት ማድረግ
 ተግባር 2. በእቅዱ መሰረት ባለ ብዙ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች
ስኬታማ እንዲሆኑ ድጋፍ ማድረግ
 ተግባር 3. ሰባት የውጭ የትስስር ሰነድ መፈራረም (ጤና
፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ደንብ ፣ ንግድ ፣ባህልና ቲሪዝም
፣ጥቃቅን ፣ሴቶች እና ህጻነት )
 ተግባር 4. በስምምነቱ መሰረት የጋራ ውይይት አራት
ጊዜ ከባለድርሻ አካለት ጋር ማድረግ
 ተግባር 5. ሁለት የውስጥ የትስስር ሰነድ መፈራረም
 ተግባር 6. በክፍለ ከተማችን በስራ ሂደትና አንድ
ለአምስት የሚመሩ ሴቶችን 53 በመቶ ማድረስ
ግብ 14. ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት
አሰራርን ማሳደግ
 ተግባር 1. በ2008 በጀት ዓመት የተሸለ አፈጻጸም
ያላቸውን ሁለት ክፍለ ከተማ የልምድ ልውውጥ ማካሄድ
 ተግባር 2. በልምድ ልውውጥ ወቅት የተገኘ ተሞክሮ
መቀመርና ማስፋት
ግብ 15. የአፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ ግምገማና ግብረ መልስ ስርዓትን ማሻሻል

 ተግባር 1. በበጀት ዓመቱ ውስጥ በወረዳ እና ስራ


ሂደቶች ሁለት ጊዜ ድጋፍ እና ክትትል ማካሄድ
 ተግባር 2. በተደረገው ድጋፈዊ ክትትል ተደርጎ ግብረ
መልስ በተሰጠው መሰረት ያሻሸሉ እና ያላሻሻሉ መለየት
 ተግባር 3. በሁሉም ወረዳዎች እና የስራ ሂደት ድጋፈዊ
ክትትል መስተጋብር እንዲዘረጉ ድጋፍ ማድረግ
ግብ 16. የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ማሳደግ

 ተግባር 1. በበጀት ዓመቱ ውስጥ በወረዳ እና ስራ ሂደቶች


ሁለት ጊዜ ድጋፍ እና ክትትል ማካሄድ
 ተግባር 2. ለ12 አመራር እና 48 ፈጻሚዎች በአገልግሎት
አሰጣጥ ዙሪያ ለሁለት ቀናት ስልጠና መስጠት
 ተግባር 3. ለ12 አመራር እና 48 ፈጻሚዎች በአመት ሁለት
ጊዜ ግምጋማዊ ስልጠና ማካሄድ
 ተግባር 4. በአመቱ ውስጥ እስከ ወረዳ 20 ፈጻሚዎች ፣3
የህዝብ ክንፍ ፣3 የስራ ሂደት ፣2 የለውጥ ሀይል ቡድን እና
ሰባት የአንድ ለአምስት ሞዴል ፈጻሚ ማድረግ
ግብ 17. የኢንፎርሜሽን ካፒታል ማሳደግ

 ተግባር 1. ለ12 አመራር እና 48 ፈጻሚዎች የሪፖርት


ስርዓትን አውቶሜትድ ማድረግ ላይ ለአንድ ቀን ስልጠና
መስጠት
 ተግባር 2. ሰባት ወረዳ እና ሁለት ክፍለ ከተማ ሁለት
የስራ ሂድት የሪፖርት ስርዓቱን አውቶሜት ማድረግ
ግብ 18. የሰው ሀብት ልማትና እተዳደር ስርዓት ማሳደግ

 ተግባር 1. የ2008 በጀት ዓመት የተሸለ አፈጻጸም


ያላቸውን ሶስት ወረዳዎች ፣አንድ የስራ ሂድት ፣ሶስት
ፈጻሚዎች አውቅና መስጠት
 ተግባር 2. በ2009 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት
ወራትለሶስት ወረዳዎች ፣አንድ የስራ ሂደት እና ሶስት
ፈጻሚዎች እውቅና መስጠት
 ተግባር 3. ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ ክፍት
መደቦች የሰው ሀይል እንዲማላ ማድረግ
የድጋፍና ክትትል አግባብ
 በሩብ ዓመት ፣ስድስት ወር ፣ ዘጠና ወር እና ዓመታዊ አፈጻጸም
ከአመራሩ ፣ፈጻሚዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም
ተልእኮ መውሰድ እንዲሁም አቅጣጫ ማስቀመጥ ፣
 የስራ ክንውን ክትትል ማድረግ (performance monitoring )

 ጥናት ማካሄድ (Evaluation/operational research)

 የተቀናጀ ድጋፈዊ ክትትል ማድረግ (integrated supporting

supervision )
 በዓመት ሁለት ጊዜ ምዘና ማካሄድ

 የህዝብ አስተያየት እና ጥቆማ መቀበል እና መፍትሄ መስጠት


 የመረጃ ውስንነት ጥራትን ለማሻሻል ከሁሉም ወረዳ
የቁጥጥር ተቋማት የሚሰበስቡትን ሪፖርቶች ታአማኒነት
በመገምገም የቁጥጥር ስርዓቱን መከታተል ፣
 የቁጥጥር ተቋማትን መረጃ በአግባቡ ለመመዝገብ
፣ለማጠናቀር ፣ለመተንተን ፣ለመጠቀምና ወቅታዊ ዘገባ
ለማቅረብ የሚያስችሉ የሰው ሀይል ፣መገልጋያ መሳሪያዎች
እንዲሟሉና የሚያስፈልገው ሀብት እንዲመደብ እንዲሁም
ሪፖርቶች ጊዜውን ጠብቆ እንዲቀርብ ማድረግ (እንደ ክፍለ
ከተማ አንድ ባለሙያ አለ )
 በክትትል እና ግምገማው በተገኙ ውጤቶች ላይ አስፈላጊውን ግብረ
መልስ መስጠት
 የቁጥጥር ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በሚሰጡ የህዝብ አስተያየት
ወይም በየጊዜው ያለውን አሰራር ሁኔታ በተቀመጠው ስታንዳርድ
መሰረት ባለው የውጤት ምዘናና ማሻሻል ሂደት አማካይነት
የአገልግሎት ጥራት የአፈጻጸም ክትትል ማካሄድ
 ወቅታዊ የሆኑ ጥናታዊ ግምገማዎች በማካሄድ የተወሰኑ መረጃዎችን
በማሰባስብና በማመሳከር ፕሮግራሞችን የግብ ስኬት (outcome )
፣የለውጥ ስኬት (impact ) ትክክለኝነት ለማሻሻል ከአገልግሎት ፈላጊ
እና ከአገልግሎት ሰጪው ወገን አኳያ በየጊዜው ጥናቶች እንዲካሄዱ
ይደረጋል ፣
 ድጋፈዊ ጉብኘት የክትትል ስርዓት (ISS) የቁጥጥር ተቋማት
የስራ አፈጻጸማቸውን በማሻሻል ከፍተኛ ጥራት ያለው
አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የቁጥጥር ሰራተኞች
የመምራት ፣የማገዝ ፣ የማሰልጠን እና ማበረታታትን
ለመተግባር በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ሰራተኞችን አቅም
በማሳደግ የተቋማቱን የማስፈጻም አቅምን ማሻሻልና
አስፈላጊውን የስራ ጥራት ለማስገኘት መገምገሚያ ቅጽ
ተዘጋጅቶ በቅንጅት የሚተገበር እና ምርጥ ተሞክሮዎች
የሚስፋፉበት እንዲሁም ግብረ መልስ የሚሰጥበት ይሆናል ፡፡
 ወቅቱን የጠበቀ የእቀድ ክንውን መገምገሚያ መድረኮች
በየሶስት ወሩ የእቅድ ክንውን ግምገማ በማካሄድ
ያጋጠሙ ችግሮችን መለየትና የመፍትሄ አቅጣጫ
በማቀመጥ የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎች በማፋት
ለግብ ስኬቶች የምንጠቀምበት መድረክ ይሆናል ፡፡
 
በእቅድ ትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ
ችግሮች እና የመፍትሄ እርምጃዎች
ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች

 የበጀት እጥረት
 ስራውን ልምድ ያገኙ ባለሙያዎች መልቀቅ
 በወረዳ የጽ/ቤት ሃላፊ አለሟላት (ወረዳ 08 )
የታሰቡ መፍትሄ እርምጃዎች

 ተጨማሪ በጀት መጠየቅ


 ቅጥር እንዲፈጸም /ከሌላ ቦታ በዝውውር እንዲመጣ
ማድረግ
 የጽ/ቤት ሃላፊ እንዲሟላ ከወረዳ አስታደደር ጋር
መወያየት
ማጠቃለያ

 ጽ/ቤታችን በ2009 በጀት ዓመት ህብረተሰቡን ጤና


ከአዳጋ ለመከላከል የሰራዊት ግንባታ እና የሪፎርም
ስራዎችን ማጠናከር ቁልፍ ተግባር አድረጎ የሚንቀሳቀስ
ሲሆን በየደረጃው ያለ አመራር እና ፈጻሚ ይህን ከግንዛቤ
በማስገባት ሁለንተናዊ ርብርብ ማድረግ ይኖርበታል ፡፡
የድርጊት መርሃ ግብር
ዝግጅት ምእርፈ የሚከናወኑ
ተ.ቁ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተግባራት የሚከናወኑበት ጊዜ በጀት ፈጻሚ አካላት
በብር

አንደኛው ሩብ ዓመት

በእስኮር ካርድ ዙሪያ መግባባት ለይ መድረስ ነሀሴ 4ኛ ሳምንት 10000.00

እቅድ ዝግጅት እስከ ግለሰብ ማጠናቀቅ እስከ መስከረም 1ኛ ሳምንት -----

አመራር እና ፈጻሚ ኦረንቴሽን በእቅድ ፣በመልካም አስተዳደር እና የህዝብ ክንፍ መስከረም 2ኛ ሳምንት 13200.00

እቅዶች እንዲሁም የኪራይ ሰብሳቢነት መታገያ ስልቶች ላይ ማካሄድ

የህዝብ ክንፍ እና ባለድርሻ አካላትን የእቅድ ኦረንቴሽን እና አቅድ እንዲያዘጋጁ መስከረም 2ኛ ሳምንት 9000.00

ማድረግና የቁጥጥሩ ስርዓት አካል እንዲሆኑ መግባባት ላይ መድረስ

ግምገማዊ ስልጠና ማካሄድ መስከረም 2ኛ ሳምንት 20400.00

ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመልካም አስተዳደር እና ኪራይ ሰብሳቢነት ዙሪያ መዋያየት መስከረም 2ኛ ሳምንት 30000.00(የውሃ )

ለህብረተሰቡ በface book በመታገዝ መረጃን ተደረሽ እንዲሆን ማድረግ ከመስከረም ----

ሰባት የውጭ የትስስር ሰነድ መፈራረም መስከረም 3 ሳምንት ----


ተ.ቁ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተግባራት የሚከናወኑበት በጀት ፈጻሚ አካላት
ጊዜ በብር

አንደኛው ሩብ ዓመት

በወረዳ ላይ ድጋፈዊ ክትትል ማካሄድ መስከረም 3ኛ ሳምንት -----

ክፍት መደቦች በሰው ሀይል ማሟላት መስከረም ------

የብቃት ማረጋገጫ እድሳት መስጠት መስከረም -----

አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት መስከረም -------

ቁጥጥር እና ክትትል ማካሄድ መስከረም ------

ፈጻሚዎች በስነ ምግባር ዙሪያ ሰልጠና እንዲያገኑ ማድረግ መስከረም 4ኛ ሳምንት 10500.00

ወደ ተግባር ምእራፍ ለመሸጋገር የዝግጅት ምእርፍ አፈጻጸም በጋራ መስከረም 4ኛ ሳምንት 50000.00

መገምገም እና የ2008 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ምዘና እውቅና መስጠት

ተገልጋዩ ህብረተሰብ አስተያያት እርካታ ማደራጀት መተንተን ለውሳኔ መስከረም 4ኛ ሳምንት -----
ማቅረብ
ትግበራ ምእራፍ
ተ.ቁ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተግባራት የሚከናወኑበት ጊዜ በጀት ፈጻሚ አካላት
በብር
አንደኛው ሩብ ዓመት

የሪፖርት ስርዓትን አውቶሜትድ ማድረግ ጥቅምት ወር ጀምሮ -----

ለሴትና ወጣት ልማት ቡድን በጤና ቁጥጥር ስራዎች ላይ ማሳተፍ ጥቅምት -ታህሳስ 41496.00

የጤና ቁጥጥር ስራዎች መረጃ ማደራጀት ጥቅምት - ታህሳስ 37500.00

ተገልጋዩ ህብረተሰብ አስተያያት እርካታ ማደራጀት መተንተን ለውሳኔ ታህሳስ 4ኛ ሳምንት -----
ማቅረብ

ከሴክተሩ ፈጻሚዎች ጋር ውይይት ማካሄድ ጥቅምት ፣ህዳር እና ታህሳስ ------

በአካባቢ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የጥቆማ ስርዓት መዘርጋት ህዳር 5000.00

የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ማካሄድ ጥቅምት-ታህሳስ -----

የድምጽ ብክለት ቁጥጥር ማካሄድ ታህሳስ 20000.00

የልምድ ለውውጥ ማካሄድ ጥቅምት 2ኛ ሳምንት -----

የተቀመሩ ምርጥ አሰራር ወደ ወረዳ /ስረ ሂደት ማስፋት ህዳር 10000.00

ክፍት መደቦችን በሰው ሀይል ማሟላት ጥቀምት -ታህሳስ ----

ለህብረተሰቡ በface book በመታገዝ መረጃን ተደረሽ እንዲሆን ማድረግ ጥቅምት- ታህሳስ -----
ትግበራ ምእራፍ
ተ.ቁ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተግባራት የሚከናወኑበት በጀት ፈጻሚ አካላት
ጊዜ በብር
ሁለተኛ ሩብ ዓመት

ለአመራሩ እና ፈጻሚዎች በአውቶሜሽን ላይ ስልጠና መስጠት ጥቅምት 4ኛ ሳምንት 31000.00

የብቃት ማረጋገጫ እድሳት መስጠት ህዳር -ጥር ----

አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት ህዳር -ጥር ----

ቁጥጥር እና ክትትል ማካሄድ ህዳር -ጥር -----

የመጀመሪያውን ስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ከአመራሩ ፣ፈጻሚዎች ፣ ባለድርሻ ታህሳስ 4ኛ ሳምንት 22200.00

አካላት እና የህዝብ አደረጃጀቶች ጋር መገምገም


ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅታዊ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ታህሳስ 4ኛ ሳምንት ----
ትግበራ ምእራፍ
ተ.ቁ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተግባራት የሚከናወኑበት ጊዜ በጀት ፈጻሚ አካላት
በብር
ሶስተኛ ሩብ ዓመት

መጀመሪያው ስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ምዘና ማካሄድ ጥር 1ኛ እና 2ኛ ሳምንት 4000.00

ሞዴል ህዝብ ክንፍ ፣ ፈጻሚ ፣ስራ ሂደት፣ የለውጥ ሀይል ቡድን እና አንድ ጥር 3ኛ ሳምንት -----
ለአምስት መመዘን
ከሴክተሩ ፈጻሚዎች ጋር ውይይት ማካሄድ ጥር ፣የካቲት እና መጋቢት ------

ድጋፈዊ ከትትል ማካሄድ ጥር 3ኛ ሳምንት ------

የመጀመሪያው ስድስት ወር አፈጻጸም መገምገም እና የስድስት ወር ጥር 4ኛ ሳምንት 20000.00

አፈጻጸም ምዘና እውቅና መስጠት


ተገልጋዩ ህብረተሰብ አስተያያት እርካታ ማደራጀት መተንተን ለውሳኔ ጥር 4ኛ ሳምንት ----
ማቅረብ
በወረዳዎች ላይ ድጋፋዊ ክትትል ማድረግ የካቲት 1ኛ ሳምንት ----

ለሴትና ወጣት ልማት ቡድን በጤና ቁጥጥር ስራዎች ላይ ማሳተፍ የካቲት 2ኛ ሳምነት 37500.00

የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ማካሄድ ጥር -መጋቢት ----

ክፍት መደቦችን በሰው ሀይል ማሟላት ጥር-ማጋቢት ----


ትግበራ ምእራፍ

ተ.ቁ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተግባራት የሚከናወኑበት ጊዜ በጀት ፈጻሚ አካላት


በብር
ሶስተኛ ሩብ ዓመት

ለህብረተሰቡ በface book በመታገዝ መረጃን ጥር -መጋቢት ---


ተደረሽ እንዲሆን ማድረግ
አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት የካቲት -መጋቢት ---

ቁጥጥር እና ክትትል ማካሄድ የካቲት -መጋቢት ----

በጤና ቁጥጥር ዙሪያ የህብረተሰቡን እርካታ ዳሰሳ መጋቢት 2ኛ እና 3ኛ ሳምንት 30000.00

ጥናት ማካሄድ
ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ መጋቢት 3ኛ ሳምንት ---
ውይይት ማካሄድ
የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም መገምገም መጋቢት 4ኛ ሳምንት 10500.00
ማጠቃለያ ምእራፍ
ተ.ቁ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ተግባራት የሚከናወኑበት ጊዜ በጀት ፈጻሚ አካላት
በብር
ሶስተኛ ሩብ ዓመት

ተገልጋዩ ህብረተሰብ አስተያያት እርካታ ማደራጀት መተንተን ለውሳኔ ሚያዚያ 1ኛ ሳምንት ----
ማቅረብ
ከሴክተሩ ፈጻሚዎች ጋር ውይይት ማካሄድ ሚያዚያ ፣ግንቦት እና ሰኔ ----

ለሴትና ወጣት ልማት ቡድን በጤና ቁጥጥር ስራዎች ላይ ማሳተፍ ሚያዚያ 37500.00

ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ሚያዚያ 2ኛ ሳምንት ------

ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ ክፍት መደቦች የሰው ሀይል እንዲማላ ሚያዚያ - ሰኔ -----
ማድረግ
የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ማካሄድ ሚያዚያ - ሰኔ ----

ሞዴል ህዝብ ክንፍ ፣ ፈጻሚ ፣ስራ ሂደት፣ የለውጥ ሀይል ቡድን እና አንድ ሰኔ 1ኛ ሳምንት -----
ለአምስት መመዘን
ለህብረተሰቡ በface book በመታገዝ መረጃን ተደረሽ እንዲሆን ሚያዚያ - ሰኔ -----
ማድረግ
አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት ሚያዚያ -ሰኔ -----

ቁጥጥር እና ክትትል ማካሄድ ሚያዚያ-ሴ ---

አመታዊ እቅድ አፈጻጸም መገምገም ሰኔ 3ኛ ሳምንት 10500.00


እናመሰግናለን!!!

You might also like