Professional Documents
Culture Documents
ማውጫ
ተ.ቁ ርዕስ ገጽ
1. ክፍል አንድ
1.1. መግቢያ--------------------------------------------------------------------------------------2
1.2. የተለዩ ሰልጣኞች ድልድልና አገባብ ሁኔታ-------------------------------------------3
1.3. በልዩ ስልጠናና በሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት የተከናወኑ ተግባራት------5
2. ክፍል ሁለት
አደረጃጀቶች የነበራቸውን እንቅስቃሴ በተመለከተ
3. ክፍል ሶስት
ክፍል አንድ
1.1. መግቢያ
ሀገራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ድህነትን ተረት በማድረግ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ
የአመራሩንና የፈፃሚ አካሉን/ባለሙያውን/ በአመለካከት፣ በክህሎትና በእውቀት መገንባት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን
በማመን መንግስት በየደረጃው ያለውን አመራርና ባለሙያዎችን አቅም በስልጠናና በተለያዩ የተሞክሮ ልውውጥ
የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚም በየደረጃው ያሉ አመራርና ባለሙያዎችን በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች
እንዲሁም የልማት አቅጣጫዎች ላይ የምንከተለውን ልማታዊ አስተሳሰብ የማስተማር፣ የማስረጽና
የማሳወቅ በሂደቱም በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር ሚናውን የመጫወት
ተልዕኮ የተሰጠው የመንግስት ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ተቋሙ የተሰጠውን ይህን ትልቅ ሃገራዊ
ተልዕኮ ለማሳካት የተቋሙ የውስጥ አቅም መብቃትና ማጎልበት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም የአካዳሚው
አመራርና ባለሙያ በዋና ዋና ሀገራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ዙሪያ የጠራ ግንዛቤና የጋራ አመለካከት
እንድይዙ ከዚህ በፊት ስልጠና ያልወሰዱትን ድፖሎማና ከዚያ በታች ያላቸውን የአካዳሚው ሰራተኞችን
በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እንዲሁም አካዳሚው ሀገራችን በተያያዘችው የህዳሴ ጉዞ ላይ ባለው ጉልህ ሚና ላይ
በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ በታቀደው እቅድ መሰረት ሰልጣኞችን በአካዳሚው ውስጥ ካሉ 10 ዳይሬክቶሬቶች በማከፋፈል
መረጃዎቹ ተደራጅተው እንዲመጡ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ስልጠናውን የማደራጀት ስራ ተከናውኗል፡፡ ይህ
ለድፖሎማና ከዛበታች ላላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና ከህዳር 20/2010 እስከ ታህሳስ 06/2010 ዓ.ም
ለመስጠት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ 47 ሰልጣኞችን ለማሰልጠን የታቀደ ቢሆንም ወደ ስልጠና ማዕከሉ (አ/አ ስራ አመራር
ኢንስቲትዩት) ቀርበው የተመዘገቡና ስልጠናቸውን መከታተል የጀመሩት ወንድ 17፣ ሴት 20 በድምሩ 37 (መሰልጠን
ካለባቸው 78.7%) ሰልጣኞች ናቸው፡፡ የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት ከሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር
የሰልጣኞችን ዝርዝር በማሰባሰብ የተለያዩ የስራ ዳይሬክቶሬቶችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ በቡድን የመደልደል ስራ
እንዲከናወን በማድረግ ሰልጣኞች ወደ ስልጠና ቦታ ሲመጡ ለምዝገባ በሚመች መልኩ የማደራጀትና ሰልጣኞችን
የመመዝገብ ስራ ተከናውኗል፡፡
በዚሁ መሰረት የዚህ ስልጠና ከቅድመ ዝግጅት እስከ አቀባበልና አጀማመር የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት
በአቀባበል ሪፖርት የተገለፀ ሲሆን ለስልጠናው የተዘጋጁ ሰነዶች ማለትም የተሃድሶው መስመርና የኢት/ያ
የህዳሴው ጉዟችንና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በሚል የቀረቡት ሰነዶች በተያዘላቸው የስልጠና የጊዜ ሰሌዳ
መሰረት ተጠናቀዋል፡፡ በእነዚህም የስልጠና አጀንዳዎች የተፈጠረውን አቅምና የስልጠና ሂደቱን መገምገም
አስፈላጊ በመሆኑ በስልጠናው ሂደት የተፈጠሩ አደረጃጀቶችን እንቅስቃሴ ከአደረጃጀቶችና ከምልከታ በተገኘ
መረጃ መሰረት የተገኘው ውጤት ለቀጣይ ስልጠና ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል በሚያስችል መልኩ
በስልጠናው ማጠቃለያ የአደረጃጀት ስራዎች በሦስት ምዕራፍ በመክፈል ማለትም ምዕራፍ አንድ መግቢያ፤
መሰልጠን ያለባቸው ድፕሎማና ከዛ በታች የሆኑ ሰልጣኞች ድልድልና በልዩ ስልጠናና በሰው ሃይል ልማት
ዳይሬክቶሬት የተከናወኑ ተግባራን ያካተተ ሲሆን፤ በአደረጃጀት የተከናወኑ ተግባራትን በምዕራፍ ሁለት ፣
አንዲሁም በምልከታ የተገኙ መረጃዎችንና ያጋጠሙ ችግሮች በተመለከተ በምዕራፍ ሶስት ተካተው ሪፖርቱ
ድፕሎማና ከዛ በታች ላላቸው ባለሙያዎች የሚሰጠውን ስልጠና መሰልጠን ያለባቸው ሰልጣኞች በሁሉም
የአካዳሚው የስራ ክፍሎች/ዳይሬክተሮች/ ድልድል የተደረገ ሲሆን በመመልመያ መስፈርቱ መሰረት ሰልጣኞች
ተመልምለው ወደ ሰልጠና እንዲላኩ በማድረግ በምልመላ ሂዴቱ ላይ የክትትል ስራ በዳይሬክቶሬታችን
ተሰርቷል፡፡ የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት የሚቀየሩና በሌላ የተተኩ ሰልጣኞችን በስዓቱ እንዲቀየሩ የማድረጉን
ስራ በጥብቅ ለማከናወን የሞከረ ቢሆንም አንዳንድ ሰልጣኞች ዘግይተው የመግባትና የመንጠባጠብ ሁኔታ
በሰፊው ታይቷል፡፡ በተለይም የሰልጣኝ መንጠባጠብ ችግር እስከ መጨረሻው ሰዓት የቀጠለና ሰፊም ነበር፡፡
ከዚህ በመነሳት ለስራ ክፍሎች/ዳይሬክቶሬቶች/ የተሰጠ የሰልጣኞች ድልድል፣ የገባ ሰልጣኝና የቀረ ሰልጣኝ
በየዳይሬክቶሬቶች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ብዛት
በ% በ%
1 ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት 3 1 2 3 100 - - 2 66.7 1
2 ፋይናንስ አስተዳደር 5 1 2 3 60 2 40 3
ዳይሬክቶሬት
3 ጠቅላላ አገ/ን/አስ/ር 21 10 4 14 66.7 7 33.3 7 50 7
ዳይሬክቶሬት
4 እቅድ ክትትልና ግምገማ 2 - 2 2 100 - - 2
ዳይሬክቶሬት
በአጠቃላይ በዚህ ስልጠና መሰልጠን ካለባቸው 47 ሰልጣኞች መካከል 37 ቱ (78.7%) በስልጠናው የተገኙ
ሲሆን፤ 10 ሰልጣኝ ወይም ከጠቅላላው 21.3% የሚሆኑ ሰልጣኞች ወደ ስልጠናው አልገቡም፡፡ በተጨማሪም
13 ሰልጣኞች (ለስልጠናው ከገቡት ውስጥ 35.1%) ቢሮ ለስራ በመፈለግና በህመም ምክንያት ቀሪ
በማብዛታቸው በስልጠና ኮሚቴው ውሳኔ ስልጠናውን ያቋረጡ ሲሆን ወደ ስልጠናው ከገቡት ውስጥ 24
1.3. በልዩ ስልጠናና በሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬቶች የተከናወኑ ተግባራት በጥንካሬና በጉድለት
የልዩ ስልጠና ዳይሬክቶሬት በዋናነት ከሰው ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር እንድሁም በተዋረድ ጉዳዩ
ከሚመለከታቸው ሌሎች ዳይሬክቶሬቶች ጋር በመተባበር ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የጋራ እቅድ በማቀድ ወደ
ስራ ለመግባት ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህም ስልጠናው የተቀመጠለትን የውስጥ አቅምን የመገንባት ግብ ማሳካት
እንዲቻል የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር፣ አፈፃፀማቸውን የመገምገምና ኦረንቴሽን የመስጠት ስራ
ተሰርቷል፡፡ ከዚህም አንፃር ዳይሬክቶሬቱ እነዚህ ሰነዶች ሲሰጡ ያከናወናቸው ተግባራት ከእቅድ አንፃር
ተግባራትን በመገምገም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
በጥንካሬ፤
መጠቀም መቻሉ፤
የሰልጣኞች፣ የቡድን እንደ አካል፣ የቡድን መሪ እና የረዳት ቡድን መሪዎች የየራሳቸው መመዘኛ
(መገምገሚያ) ነጥቦች ከሰልጣኞች አንፃር መዘጋጀቱ፤
የስልጠናውን የእለታዊ የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት መቻሉ፤
የስልጠናውን ቦታና ቀን መወሰኑ፤
ስልጠናውን የሚያስተባብሩ ንዑስ አደረጃጀቶችን በማዋቀር ወደ ስራ መገባቱ፤
በመስፈርቱ መሰረት አወያዩችን መመልመላቸውና መመደባቸው፤
ከስልጠናው ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሆን የስልተናውን ሂደት በመገምገም እርምጃ እስከመውሰድ የደረሱ
መፍትሄዎች ላይ በጋራ መስራት መቻሉ፤
በድክመት፤
የስልጠና ሰነዶች ኮፒና በእጅ ስቴፕለር የተመቱ በመሆናቸው ለእይታ የማይስቡና ለማንበብ አመች
ያለመሆናቸው፤
በጥንካሬ
በአካዳሚችን ውስጥ ባሉ ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ስር ያሉ ድፕሎማና ከዛ በታች ያላቸውን
ሰራተኞች መረጃ በዝርዝር በመለየት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ መግባት መቻሉ፤
ስልጠናውን በጋራ የሚያሰራን የጋራ እቅድ መታቀዱ፤
በክፍተት
የለም
ክፍል ሁለት
ስልጠናውን ሁሉን አቀፍና አሳታፊ ለማድረግ ያመች ዘንድ ሰልጣኙን በተለያዩ አደረጃጀቶች በማደራጀትና
እንዲታቀፉ በማድረግ የሚማማሩበትን ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡ ስለሆነም ሰልጣኞችን በ 2 ቡድኖችና
እያንዳንዱን ቡድን የሚያስተባብሩ ሁለት ቡድን መሪዎች(ዋናና ረዳት ቡድን መሪ) ያሉ ሲሆን የአቅም
ማጎልበት ስራዎችን በዋና ቡድን መሪዎች እንድሁም የአደረጃጀት ስራዎችን በረዳት የቡድን አወያይዩች
አማካኝነት ክትትልና ድጋፍ እየተደረገና እየተመሩ ወደተግባር ገብተው ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
በጥንካሬ፡-
በክፍተት፡-
አንዳንድ የተመደቡ የቡድን አወያዩች በተለያዩ ምክንያቶች አለመገኘታቸውና ስልጠናው ባልተሟላ
የቡድን አመያዩች መካሄዱ፤
አንዳንድ የቡድን አባላት የስዓት ፊርማ በስዓቱ ያለመፈረም፤
አልፎ አልፎ በኃይል መድረክ ወጣ ገባ የማለትና ከሻይ እበፍት የመንጠባጠብ ሁኔታ፤
አንዳንድ ሰልጣኞች በቡድን ውይይት ወቅት ጥሩ እየተሳተፉ በሃይል መድረክ ግን ንቁ ተሳትፎ ያለማድረጋቸው፤
በጥንካሬ
ፍትሃዊ፣አሳታፊ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ መድረክ መፍጠር መቻላቸው፤
አዳዲስ ሀሳቦች እንዲወጡ ማበረታታቸው፤
ውይይቱ ሁሉንም አሳታፊ እንዲሆን በስም በመጥራት ጭምር ጥረት ማድረጋቸው፤
ትኩረት የሚያስፈልጋቸውና አከራካሪ ጉዳዩችን ለይተው ለቡድኑ በመግለፅና በመስጠት ሰልጣኙ የጋራ
መግባባት ላይ እንዲደርስ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የጠራ አመለካከት ለማስያዝ ጥረት
ማድረጋቸው፤
ከአጀንዳ ሲወጣና ግልፅ ላልሆነ ጥያቄ እና ሀሳብ አቅጣጫ መስጠት መቻላቸው፤
ውይይቶችና ክርክሮች ከግለሰብ ጋር ሳይገናኙ/ሃሳብን ከግለሰብ በመለየት/ ሀሳብ ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ
መምራት መቻላቸው፤
ለራሳቸው ሰፊ ሰዓት በመውሰድ የሌሎች ተሳትፎ እንዲገደብ ከማድረግ በመቆጠብ በጣም አጭር ጊዜ
መውሰድ፤
ውይይቱ አሰልቺ እንዳይሆን በመሀል ዘና የሚያደርጉ ቀልዶችን መጠቀማቸው፤
ከቡድን የተነሱ ጥያቄዎች አደራጅተው ሲጨርሱ መጀመሪያ ለቡድኑ አባላት በማቅረብ የተረሳ ካለ ለማካተት
መሞከሩና የተመረጡ ጥያቄዎችን አባላቱ ጋር ተስማምተው ለኃይል መድረክ እንዲቀርቡ ማድረጋቸው፤
የቀሩ/ያረፈዱ/ ሰልጣኞችን መለየትና ለአስተባባሪ ኮሚቴው መጠቆም መቻላቸው፤
በድክመት
ረዳት የቡድን አወያይ ባለመኖሩ ምክንያት የስራ ጫና በመኖሩ ለሃይል መድረክ የሚሄዱ ጥያቄዎችን በስዓቱ
ለማስተላለፍ መቸገር፤
በአንዳንድ ተሳታፊዎች ሃሳብ ሲደጋገም ያለማስቆም፤
በሰልጣኞች መካከል ተመጣጣኝ እውቀት እንዲኖር ጥረት የተደረገ ቢሆንም የተወሰነ ድክመት ያለ
መሆኑ፤
ሰንጠረዥ 2፤ ቡድን እንደ አካል ሲገመገምና የቡድን መሪዎች ደረጃ ፍረጃ
ጠ/ድምር 2 2 1
የሰንጠረዡ ማብራሪያ፤
የቡድን ደረጃ ምደባ እንደአካል ሲታይ ከተገመገሙት 15 ቡድኖች መካከል ሁሉም ቡድን
በ A ደረጃ ተፈርጀዋል፡፡
በ 2 ቡድኖች ከተመደቡት 3 ዋናና ረዳት አወያዮች ውስጥ ሁሉም ቡድኖች ለዋና አወያዩቻቸው(ቡድን
መሪዎቻቸው) እና ለረዳት አወያዩቻቸው ማለትም ለሁለቱም አወያዩቻቸው A ደረጃ የሰጡ መሆኑን
መረጃው ያሳያል፡፡
በጥንካሬ
በሃይል መድረክም ሆነ በቡድን ውይይት በተነሱ ጥያቄዎችም ሆነ ያልበሰሉ ሀሳቦች መካከል ግልፅ
ባልሆኑ ጉዳዩች ላይ ሰፊ ጊዜ ሰጥተው መወያየታቸውና ወደ ቡድን ቀርቦ ውይይት ሊደረግባቸው
የሚገቡትን በመለየት ረገድ ጥሩ ጥረት መደረጉ፤
የህዋስ ውይይቶችንና የሂስ ግለሂስ ሪፖርቶችን በአግባቡ አዘጋጅተው ማቅረባቸው፤
አባላት የስልጠና ሰነዱን እንዲያነቡና ለስልጠናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ መደገፋቸው፤
ሰልጣኙ ጥሩ ዲሲፕሊን እንዲኖረውና ወደ ተመጣጣኝ አቅም እንድመጣ የተሞከረ ጥረት መኖሩ፤
በክፍተት የታዩ፡-
በስዓት እጥረትና በሰርቪስ ስዓት መድረስ ምክንያት በየለቱ በመገናኘት የውሎ ግምገማ
አለማድረጋቸው፤
ህዋስ አባላትን በተሟላ መልኩ ወደ ተመጣጣኝ አቅም ማምጣት ላይ ውስንነት መኖሩ፤
የአባላትን ተሳትፎ፣ አመለካከትና ብስለት በመከታተል ጉድለትን ሊያሻሽል የሚችል ተከታታይ
ግንባታና ድጋፍ ማድረግ ላይ ክፍተት መኖሩ፤
በመካከላቸው ያለውን ተነፃፃሪ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት 1 ለ 1 እንድደጋገፉ ማድረግ ላይ
ውስንነት መኖሩ፤
በውይይት ወቅት ሰፊ ጊዜ ወስደው የማብሰልና ክርክር በማድረግ በኩል ውስንነት መኖሩ፤
ስልጠኙ ለሀይል መድረክ ከሚሰጠው ማብራሪያ፣ ከሰነድና በግሉ ከነበረው ግንዛቤ ተነስቶ ሃሳቦችንና
አመለካከቶችን በነፃነት በማንሸራሸር ግንዛቤውን እንዲያዳብር ይረዳ ዘንድ የስልጠናው ስነ ዘዴ ሰልጣኝ ተኮር
ሆኖ እንዲመራ ተደርጓል፡፡ በዚህም በቡድኖችና በህዋስ ውይይት አባሉ በንቃት እንዲሳትፍ ተደርጓል፡፡ ከዚህ
አንፃር የነበረው እንቅስቃሴ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
በጥንካሬ፡-
አብዛኛው ሰልጣኝ በውይይትም ሆነ በኃይል መድረክ ከተጠበቀው በላይ ንቁ ተሳትፎና በሳል ሃሳቦችን
ማንሸራሸር መቻላቸው፤
በገለፃ ወቅት ማስታወሻ የመያዝ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ፤
አብዛኛው ሰልጣኝ በ 1 ለ 5 /ህዋስ/ አደረጃጀት ላይ በአግባቡ መሳተፋቸው፤
ሰልጣኞች በአፈፃፀም የታዘቡዋቸውን ችግሮች ከመልካም ልምዶች ጋር በማስተሳሰር በያገባኛል
መንፈስ ጥሩ ውይይት ማድረግ መቻሉ፣
ሰልጣኙ በስልጠና አዳራሽና በውይይት ክፍሎች ጥሩ ግንኙነትና ውህደት የነበረው መሆኑ፤
ከሁሉም ዳይሬክተሮቶች ተውጣጥተው በቡድን ተደልድለው መወያየታቸው ለልምድ ልውውጥ
እና መደጋገፉ ትልቅ እገዛ ማድረጉ፤
አጀንዳዎች አገር አቀፍ ሁኔታንና የአካዳሚያችንን ሚና ለመገንዘብ ማስቻላቸው፤
የሴቶች ተሳትፎ ከስልጠናው አጋማሽ በኃላ እየተጠናከረ መምጣቱ፤
ያን ያክል የጎላ የስነምግባር ችግር ያለባቸው ሰልጣኞች አለመኖራቸውና ስልጠናውን በጥሩ
ድሲፕሊን መከታተል መቻላቸው፤
በድክመት፡-
የስልጠናው ቦታ ለቢሮ ቅርብ በመሆኑ ምክንያት ሰልጣኞች በስልጠና ወቅት ለስራ በሃላፊዎቻቸው
በመጠራታቸው የመሄድና የመቅረት እንድሁም የማርፈድ ሁኔታ በመኖሩ የስልጠናውን ሰዓት በአግባቡ
መጠቀም ላይ እንቅፋት መፍጠሩ፤
ሰልጣኖች ማስታወሻ የመያዝ ውስንነት መኖሩ፤
የተሰጣቸውን ሰነዶች በአግባቡ አለማንበባቸው፤
አንዳንድ ሰልጣኞች እስከ ስልጠናው መጨረሻ ድረስ ንቁ፣ መሳጭና የተጠናከረ ተሳትፎ ያለማድረጋቸው፤
አስተማሪና አዝናኝ ቀልዶችን ማቅረብ ላይ ውስንነት መኖሩ፤
የሴቶች ተሳትፎ ወደ ስልጠናው መጨረሻ ላይ መሻሻል ቢያሳይም በሚፈለገው መልኩ ያለመሆኑ፤
በአካዳሚው የስልጠና ሂደት መሰረት እያንዳንዱ ሰነድ ሲጠናቀቅ ሰልጣኞች በእያንዳንዱ የስልጠና አጀንዳዎች
ያመጡትን ለውጥ ለማየት ያስችል ዘንድ የሰልጣኞችና የቡድን እንድሁም የህዋሶች የደረጃ ፍረጃ ግምገማ የሚደረግ
ቢሆንም ይህ ስልጠና በአብዛኛው ድፕሎማና ከዛ በታች ያላቸው የአካዳሚያችን ሰራተኞች የተሳተፉበት በመሆኑና
ከስልጠና ጊዜ መጣበብ ጋር ተዳምሮ ሂስ ግለሂሱን በእያንዳንዱ የስልጠና ሰነድ ከማድረግ ይልቅ በስልጠናው ማጠናቀቂያ
ላይ ብቻ ማየቱ የሚበቃ መሆኑ ስለታመነበት የቡድኖች ደረጃ ፍረጃና የአወያዩችና የሰልጣኞች ሂስ ግለሂስ በስልጠናው
መጨረሻ ላይ ብቻ ተካሂዶ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በ%
የስራ ዘርፍ ድምር
ፋይናንስ እቅድ አመ/ር አቅም የሰው
ቡድን ደረጃ ጠቅላላ ት/ርትና የውስ የስልጠና ምርምር
ፕሬዚዳን አስተዳደ ክትትልና ሃብት
አገ/ን/አስ/ ስልጠና ጥ አመራር ማጎልበት ና ልማት
ት ጽ/ቤት ር ግምገማ ልማት
ር ዳ/ሬት ዘርፍ ኦድት ዳ/ሬት ዳ/ሬት
ዳ/ቶሬት ዳ/ሬት ዳ/ሬት ዳ/ሬት
A ወ 1 1 2
ሴ 1 1
ድ 1 1 1 3 27.3
ወ 1 1 2 4
1 B ሴ 1 1 1 1 4
ድ 1 2 1 1 3 8 72.7
ወ -
C ሴ -
ድ -
ጠ/ድምር 1 3 2 1 4 11 100
A ወ 0
ሴ 0
ድ - - - - - - - - - - 0
ወ 2 2
2 B ሴ 1 1 1 1 1 5
ድ 3 1 1 1 1 7 70
ወ -
C ሴ 1 2 3
ድ - - - - 1 - - - - 2 3 30
ጠ/ድምር - - 3 1 1 1 1 1 2 10 100
ጠቅላላ A 0 1 1 - - - 1 - - - 3 14.3
ጠቅላላ B 1 2 4 2 - 1 5 - - - 15 71.4
ጠቅላላ C 1 2 3 14.3
ጠቅላላ ድምር 1 3 5 2 1 1 6 2 21 100
ማሳሰቢያ፤
ከቡድን 1 ሶስት ሰልጣኞች ፈተናውን ተፈትነው ከስዓት በመቅረታቸው ምክንያት የደረጃ ፍረጃ
አልተደረገላቸውም፡፡
በአጠቃላይ የሰልጣኞች ዝርዝር ሁኔታ ሲታይ የደረጃ ምደባ ግምገማ ካደረጉት 21 ሰልጣኞች መካከል
አብዛኞቹ ሰልጣኞች ማለትም ከጠቅላላው 15 ሰልጣኞች (71.4%) በመካከለኛ B ደረጃ ላይ ሲሆን በከፍተኛ
ደረጃ A የተፈረጁት 3 ሰልጣኞች(ከጠቀላላው 14.3%) ናቸው፡፡ የተቀሩት 3 ሰልጣኞች (ከጠቅላላው 14.3%)
ደግሞ በዝቅተኛ ደረጃ C ተፈርጀዋል፡፡ ይህም አብዛኞቹ ሰልጣኞች በመካከለኞ ደረጃ ላይ ያረፉና ተቀራራቢ
የሆነ የእውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ደረጃ እንዳላቸው ያሳያል፡፡
የሴቶችን ተሳትፎና የደረጃምደባ በየቡድኑ ምን እንደሚመስል ለማየት ከላይ የሰልጣኞች ደረጃ ምደባ ሰንጠረዡን
መረጃ መሰረት በማድረግ እንደሚከተለው ማየት ይቻላል፡፡
የደረጃ ምደባ ግምገማ ካደረጉት 13 ሴት ሰልጣኞች መካከል አብዛኞቹ ማለትም 9 (69.2%) በ መካከለኛ B ደገጃ
ሲፈረጁ አንድ ሴት ሰልጣኝ ብቻ በ A ደረጃና ቀሪ 3 (23.1%) ሴቶች በእቅተኛ ደረጃ C የተፈረጁ ናቸው፡፡
በመረጃው መሰረት የሴቶች ተሳትፎ በአንፃራዊ መልኩ ሲታይ፡-
ቡድን 1 በጣም ጥሩ የሴቶች ተሳትፎ ያለበት ቡድን ሲሆን በዚህ ቡድን ካሉት ሴቶች ውስጥ አንድ ሴት
ሰልጣኝ በ A ደረጃ የተፈረጀችና ሌሎች ሁሎችም በመካከለኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡
በአንፃሩ ሲታይ ቡድን 2 በጣም ዝቅተኛ የሴቶች ተሳትፎ ማለትም በቡድኑ ካሉት ሴቶች ውስጥ
0% በከፍተኛ ደረጃና 3 ሰልጣኞች በ C ደረጃ(37.5%) ላይ የተፈረጁ ሲሆን ይህ ቡድን ዝቅተኛ
የሴቶች ተሳትፎ ታይቶበታል፡፡
ከዚህ መረዳት የሚቻለው እንደ አጠቃላይ በዚህ ስልጠና ላይ የሴቶች ተሳትፎ በመካከለኛ ደረጃ B
(ከጠቅላላ ሴቶች 9 ኙ ወይም 69.2%) እንደሆነ ነው፡፡
ክፍል ሶስት
በጥንክሬ፡-
የሰልጣኞች ቁጥር አናሳ ስለሆነ ሃይል መድረኩን ለመቆጣጠርና ለመከታተል አመች መሆኑ፤
አብዛኛው ሰልጣኝ ለሃይል መድረኩ በጊዜ ቀድመው መገኘታቸው፤
ሰልጣኞች በዋና አሰልጣኙ ገለፃ ሲሰጥ ማስታወሻ መያዛቸው ሁኔታ መሻሻሎች ማሳየታቸው፤
ሰነዶቹ ከሌሎች ሰነዶችና ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎች ጋር እየተዛመደ መቅረብ መቻላቸው፤
በዋና አሰልጣኞች የተሰጠው ገለፃ በምሳሌዎች የተደገፈና ለሰልጣኞች ግልፅ በሆነ መልኩ መቅረቡ፤
በክፍተት፡-
አንዳንድ ሰልጣኞች ለሽንትና በሌላ ሰበቦች በሃይል መድረክና በቡድን ውይይት ወቅት መውጣት
መግባት መኖሩ፤
በአንዳንድ ሰልጣኞች ስዓት ያለማክበርና መንጠባጠብ መኖሩ፤
አብዛኞቹ ሰልጣኞች በሃይል መድረክ ገለፃ ወቅት ማስታወሻ ያለመያዛቸው፤
በጥንካሬ
ሰልጣኞች በሃይል መድረክ ገለፃም ሆነ በውይይት ወቅት ማስታወሻ የመያዛቸው ሁኔታ ወደ መጨረሻ
ላይ ጥሩ መሻሻሎችን ማሳየቱ፤
ውይይቱ ፍፁም ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና አሳታፊ ውይይት መሆኑ፤
የቡድን አባላት በኃይል መድረክ ላይ ሀሳብ በመስጠትና በመከራከር የሚሳተፉ መሆናቸው፤
በየአደረጃጀቶቹ ያሉ አባላት በስልጠናው ሂደት ላይ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ክርክርና ውይይት ማድረግ
መቻላቸው፤
በድክመት፤
የአደረጃጀት ዘርፍ ኮሚቴ (በዚህ ስልጠና የቡድን ዋናና ረዳት አወያዮች የተካተቱበት ሲሆን) በሚመለከት፡-
በጥንካሬ
አቴንዳንስ በአግባቡ መያዙና በተደጋጋሚ የቀሩ ሰልጣኞች ላይ ከስልጠና እስከ ማባረር ድረስ ርምጃ
መውሰድ መቻሉ፤
በስራ ጫና ምክንያት በየዕለቱ ማድረግ ባይቻልም በየሳምንቱ መጨረሻ በመገናኘት ስራዎችን
መገምገም መቻሉ፤
የሴቶች አደረጃጀት ባይኖርም የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር ልዩ ትኩረት በማድረግ ሴቶችን
የማጠናከሩን ስራ በአወያዩቹ መሰራቱ፤
አደረጃጀቶች (ቡድኖች፣ ህዋሶች) ለስልጠናው የሚጠበቅባቸውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ
እየተወጡ መሆናቸው፤
በክፍተት
በጥንካሬ
በክፍተት
የሚከተሉት በስልጠናው ወቅት ጎልተው የታዩና ስልጠናው ላይ ተፅዕኖ ያደረጉ ችግሮች ነበሩ፡፡
እነሱም፡-
የስልጠናው ቦታ ለቢሮ ቅርብ በመሆኑ ምክንያት ሰልጣኞች በስልጠና ወቅት ለስራ በሃላፊዎቻቸው
በመጠራታቸው የመሄድና የመቅረት እንድሁም የማርፈድ ሁኔታ በመኖሩ የስልጠናውን ሰዓት በአግባቡ
መጠቀም ላይ ችግር መፍጠሩና ብዙ ሰልጣኞችም እንዲያቋርጡ ምክንያት መሆኑ፤
የተመደቡ የቡድን አወያዩች በተለያዩ ምክንያቶች ባለመገኘታቸው ምክንያት የነበሩትን
በማቀያየር/በመበተን/ እና ባልተሟሉ የቡድን አወያዩች ለመስራት መገደድና በዚህም የተነሳ የቡድን
ሪፖርቶች በወቅቱና በፎርማቱ መሰረት ማዘጋጀትና መላክ ላይ ውስንነት መኖሩ፤
አንዳንድ አሰልጣኞች በማደማደሚያ ወቅት ያለመገኘታቸውና ውይይቶችን ከማደማደም አንፃር
ውስንነት መኖሩ/በተለይ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ስልጠና ሰነድ አሰለልጣኑ ባለመምጣቱ ከቡድኖች
የተነሱ ጥያቄዎችን በቡድን አወያዩችና በአስተባባሪዎች ብቻ ለማደማደም መገደድ/፤
ስልጠናውን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ኬዝ ስተዲዎችና ፓናል ውይይቶች አለመኖራቸው፤