Professional Documents
Culture Documents
Poltcal Report of Diplomas
Poltcal Report of Diplomas
ማጠቃለያ ሪፖርት
ነሐሴ/2009 ዓ.ም
ደብረ ዘይት
ማውጫ
ርዕስ ገጽ
1. መግቢያ..................................................................................................................................................................3
2. በስልጠናው አስፈላጊነት ላይ የተደረገው አጠቃላይ ግምገማን በተመለከተ.................................................................................4
3.1.1. 2.1 የ EBC አመራሮችንና ባለሙያወችን አቅም ከመገንባት አንጻር በስልጠናው አስፈላጊነት ላይ የተደረገ አጠቃላይ ግምገማ........4
3.1.2. 2.2 ከኮርፖሬሽኑ ተልኮና ተግባራት አንፃር የስልጠናው አስፈላጊነትና ወቅታዊነት በተመለከተ........................................7
3.1.3. 2.3 የተሃድሶ መስመርና የኢት/ያ ህዳሴ ላይ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ባለሙያ የተሟላ ግልፅነት እንዲፈጥሩ የማድረግ
አስፈላጊነትን በተመለከተ..............................................................................................................13
3.1.4. 2.4. ልማታዊ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለኢት/ያ ህዳሴና የሚድያው/EBC /ሚና ላይ የተሟላ ግንዛቤ
የመፍጠር
አስፈላጊነት……………………………………………………………………………………………………… ..
3.1.5. 2.5. ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሙሽን ዕቅድ ዙሪያ ግንዛቤን የመፍጠር
አስፈላጊነት……………………..
3.1.6. 2.6. በኢት/ያ ፌዴራሊዝም ስርዓት ግንባታ ስኬቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች ዙሪያ ግንዛቤን የመፍጠር
አስፈላጊነትን በተመለከተ..............................................................................................................17
3.1.7. 2.5. የህዳሴ ጉዟችንና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችንን የመገንዘብ አስፈላጊነትን በተመለከተ..........................25
3.1.8. 2.6. በአዎንታዊ አስተሳሰብ ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር አስፈላጊነት በተመለከተ……………………………….…28
3. በየሰነዱ የተቀመጡ የስልጠና ግቦች መሳካትን በተመለከተ......................................................................................................34
3.1.9. 3.1. የተሃድሶ መስመርና የኢት/ያ ህዳሴ ላይ ግልፅነት ተፈጥሯል................................................................34
3.1.10. 3.2. የልማታዊ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለኢት/ያ ህዳሴ ላይ የኮርፖሬሽኑ( EBC)ሚና ምን ሊሆን
እንደሚችል ግልፅነት ተፈጥሯል.................................................................................................35
3.1.11. 3.3. በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ግልፅነት
ተፈጥሯል------------------------------------------
3.1.12. 3.4. የኢት/ያ ፌዴራል ስርዓት ግንባታ ስኬቶች፣ የወደፊት አቅጣጫዎችና በዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት ፅንሰ ሃሳብ ላይ በአመራሩና
በባለሙያው ግልፅነት ተፈጥሯል......................................................................................................35
3.1.13. 3.5. የሃገራችን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ በኮርፖሬሽኑ አመራርና ባለሙያዎች ግልጸኝነት ተፈጥሯል..................36
3.1.14. 3.6.በአዎንታዊ አስተሳሰብ ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጥሯል..................................................................................37
4. ከአመለካከት አኳያ ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተ...........................................................................................39
5. በሰነዱ መካተትና መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ተብለው የቀረቡ፤...........................................................................................42
3.1.15. 5.1. የተሃድሶ መስመርና የኢት/ያ ህዳሴ ሰነድ ላይ .............................................................................34
3.1.16. 5.2. ልማታዊ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለኢት/ያ ህዳሴ ................................................................35
3.1.17. 5.3. የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
………………………------------------------------------------
3.1.18. 5.3 የኢት/ያ ፌዴራል ስርዓት ግንባታ ስኬቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች.............................................................35
3.1.19. 5.4 የሃገራችን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ..............................................................................................36
3.1.20. 5.5. አዎንታዊ አስተሳሰብ ሰነድ.......................................................................................................37
6. የስልጠናውን አጠቃላይ አመራርና አካሄድ በተመለከተ....................................................................................................45
3.1.21. 6.1. መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚን በተመለከተ.....................................................................................45
3.1.22. 6.2. አሰልጣኝ (ዋና መምህራን) አመራረጥ፣ ገለጻና ማጠቃለያ አቀራረብ..................................................46
ክፍል አንድ
1. መግቢያ
ሀገራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ድህነትን ተረት በማድረግ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ
የአመራሩንና የፈፃሚ አካሉን በአመለካከት፣ በክህሎትና በእውቀት መገንባት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን በማመን መንግስት
በየደረጃው ያለውን አመራርና ባለሙያ አቅም በስልጠናና በተለያዩ የተሞክሮ ልውውጥ መድረኮች የመገንባት ስራ
እየሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የልማታዊ መንግስቱ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሴክተሮች በየፊናቸው የአመራርና
ሙያተኛ አቅም በመገንባት የተነደፉትን ግቦች ለማሳካት ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚም
ይህንን የስልጠና ስራ ለማከናወን ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ተግባር ገብቷል፡፡
ስልጠናውን በሁለት ዙር ለመስጠት የታቀደ ሲሆን የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና ከነሃሴ 08/2009 እስከ ነሃሴ 28/2009
ዓ.ም ድረስ የተሰጠ ሲሆን በዚህም ዙር 204 ሰልጣኞችን በደብረ ዘይት ስራ አመራር ማሰልጠኛ ማዕከል ለማሰልጠን
የታሰበ ቢሆንም ወደ ስልጠና ማዕከሉ ቀርበው የተመዘገቡና ስልጠናቸውን ለመከታተል ከጀመሩት ወንድ 148 ሴት 45
በድምሩ 193 (94.6%) ሰልጣኞች መካከል --------------- ሰልጣኞች በድሲፕሊን ከስልጠናው
በመሰናበታቸውና---------- ያክሉት ደግሞ በህመም ምክንያት እንድሁም---------- ሰልጣኞች በአስቸኳይ የተቋሙ ስራ
ምክንያት በድምሩ------------ ሰልጣኞች ስልጠናውን ያቋረጡ ሲሆን በአጠቃላይ------------- ሰልጣኞች ስልጠናውን
ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመተባበር የሰልጣኞችን ዝርዝር በማሰባሰብ የተለያዩ የስራ
ዘርፎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ በቡድን የመደልደል ስራ እንዲከናወን በማድረግ ሰልጣኞች ወደ ስልጠና ቦታ ሲመጡ
ለምዝገባ በሚመች መልኩ የማደራጀትና ሰልጣኞችን የመመዝገብ ስራ ተከናውኗል፡፡
በዚሁ መሰረት የዚህ ዙር ስልጠና ከቅድመ ዝግጅት እስከ አቀባበልና አጀማመር የተከናወኑ ተግባራትን
በሚመለከት በአቀባበል ሪፖርት የተገለፀ ሲሆን ለዙሩ ከተመረጡት ስድስት ሰነዶች ማለትም የመጀመሪያ
የስልጠና ሰነድ ከሆነው የተሃድሶው መስመርና የኢት/ያ ህዳሴ(አጀንዳ /ሰነድ/1) ጀምሮ እስከ መጨረሻው
አዎንታዊ አስተሳሰብ ሰነድ ድረስ የቀረቡት ሰነዶች በተያዘላቸው የስልጠናው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት
ተጠናቀዋል፡፡ በእነዚህም የስልጠና አጀንዳዎች የተፈጠረውን አቅምና የስልጠና ሂደቱን መገምገም አስፈላጊ
በመሆኑ በስልጠናው ሂደት ከተፈጠሩት አደረጃጀቶችና ከምልከታ በተገኘ መረጃ መሰረት የተገኘው ውጤት
ለቀጣይ ሰነድ ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል በሚያስችል መልኩ የሰነዶችን የፖለቲካ ዘርፍ ስራዎች በዝርዝር
የምንገኝበት ዓለም በፈጣን የመረጃ ቴክኖሎጂና ሚዲያ ስርፀት የመጠቀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን
ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የመረጃ ተደራሽነትና ስርፀት ጉዳይ በሃገራችን በሚፈለገው ደረጃ ያልደረፀና
ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ነው፡፡
የሃገራችን ዜጎችም ሆኑ ውጭዎች ስለሃገራችንና አጠቃላይ አለም አቀፍ ሁኔታዎች ማወቅ
ስለሚፈልጓቸው በርካታ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መረጃ ለመስጠት
የተቋቋመው ኢቢሲ በዘመናዊ መልኩ የሚጠበቅበትን ጉልህ ሚና እንዲጫወት የህዳሴውን ጉዞ
ለማሳለጥ የሚያስችል የአመለካከት፣ የዕዉቀትና የክህሎት ደረጃ ተላብሶ በመገኘት በኩል በአግባቡ
ያላሳካቸው ማነቆዎች ነበሩ፡፡
አብዛኛዎቹ ሰልጣኞች የሚሰጠውን ስልጠና የአሰለጣጠን ሂደቱ በሀይል መድረክ ገለጻና በቡድን ፣ በህዋስ እንዲሁም
ኳሊቲ ሰርክልና ፕሮዳክሽን ቲም ውይይቶች በመታገዝ የሚሰጥ የተደራጀ ስልጠና እንደሚሆን ያልገመቱ
መሆኑን፤
የስልጠና ሰአት አጠቃቀሙም በስልጠናው ሂደት ካዩት በተሻለ በቂ እረፍትና የሚዝናኑበትን ጊዜ
የሚሰጣቸው እንደሚሆን ይጠብቁ እንደነበር አንስተዋል፡፡
ስልጠናውን ከመጀመራቸው በፊት መድረኩ ሀሳባቸውን በነጻነት ማንሸራሸር የማይችሉበት፣
በኮርፖሬሽኑ የሚንጸባረቁ የአመለካከት ችግሮችን ባወጣ እፈረጃለሁ ብሎ የመስጋት ሁኔታዎች
እንደነበሩባቸውና የተሳሳተ አመለካከት ቢያንጸባርቁ የሚያስጠይቃቸው እንደሆነ ይገምቱ እንደነበር
አንስተዋል፡፡
ሰልጣኞች ከሚጠበቅባቸው ሚና አንጻር ለስልጠናው በተለዩት አጀንዳዎች ላይ በቂ ግንዛቤ የሌላቸው
መሆኑ፣ የአመለካከት፣ የክህሎትና የግንዛቤ ክፍተት የነበረባቸው መሆኑና የነበራቸው ግንዛቤም በተለያየ
ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደነበር በሰጡት አስተያየተም ሆነ በቡድን ውይይቶች ከሚያነሷቸው የተሳሳቱ ሀሳቦችና
አመለካከቶች መረዳት ተችሏል፡፡ በተለይም፡-
በልማታዊ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን፣ በልማታዊ ደሚክራሲ ፅንሰ ሃሳብና በአወንታዊ አስተሳሰብ
ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ያልነበረበት እንዲሁም ጋዜጠኛው ተልዕኳቸውን ከልማታዊ ደሚክራሲ
አስተሳሰብ አኳያ እንዴት መፈፀም እንዳለባቸው የነበረው ግልጽነት አናሳ ነበር ማለት
ይቻላል፡፡
በቡድንም ሆነ በዶርም የሰልጣኝ አመዳደብን በተመለከተ አመዳደቡ ከተለያየ የስራ ዘርፎች የተውጣጡ
ሰልጣኞችን በማሰባጠር መሆኑ ሠልጣኞች የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው እንዲዳብርና ትስስራቸው
እንዲጎለብት ያደረገ በመሆኑ ስልጠናውን በጥሩ መነቃቃት እንዲከታተሉ ያገዛቸው መሆኑን
ገምግመዋል፡፡
ያልተቋረጠ ትግል የተደረገባት በመሆኗ የአገራችን ታሪክ ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም ታሪክን ማወቅ ከታሪክነቱ ባሻገር ካለዉ ጊዜ ድክመታችንና ጥንካሬአችን ለመማር
እንደሆነ ግንዛቤ ተይዟል፡፡ ኢትዮጵያ አገራችን ከታላቅ ስልጣኔ ለማሽቆልቆል ጉዞ የተዳረገችዉ ባለፉት
ስርዓቶች ብዝሃነትን ማስተናገድ አቅቶን እንደነበር የተሻለ ግንዛቤ ተይዟል፡፡
የሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ፖኬጅ ምንነትና አስፈላጊነት፣ በፓኬጁ ውስጥ በተዘረዘሩ
መሠረታዊ ጉዳዮች እና በአተገባበር ሂደት ሚዲያው ያለው ሚና ላይ መግባባት ተደርሷል፡፡
የአወንታዊ አስተሳሰብ መገንባት በጋዜጠኛው ሚና ላይ ያለው አስተዋፅኦ ምን ሊሆን እንደሚችል
የተሟላ ግልጸኝነት ተፈጥሯል፡፡ በአጠቃላይ ባለሙያው/የኢቢሲ ጋዜጠኛ/ በሀሉም አጀንዳዎች የተሻለ
እና ለተልዕኮ የሚመጥን አቅም ፈጥሮ በአገራችን ልማት፣ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት
ግንባታ ላይ ያገባኛል የሚል የጠራ አስተሳሰብ ፈጥሯል፡፡
በጥንካሬ፡-
የተመረጡት የስልጠና አጀንዳዎች ተገቢ ሲሆኑ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ባለሙያ ተልዕኮውንና ሃገሪቷ
የምትመራበትን ፖሊሲዎች በግልጽ ተረድቶና አውቆ የተሟላ አቅም ፈጥሮ የኢቢሲን ዓላማና ግቦች
ለማሳካትና በሃገራችን ልማት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዲችል የሚያስችለው ስለሆነ ስልጠናዉ
ታስቦ መሰጠቱ ጥሩ ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ በመንግስት የልማታዊ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ፍልስፍና መሰረት ጋዜጠኛው ስራውን
እንዲሰራና ልማትን የሚያፋጥን ስራ ለመስራት የተሻለ ግንዛቤ የፈጠረበት በመሆኑ፣
የስልጠናው ቅደም ተከተልም በአግባቡ የታየና የርዕሶቹን ተከታታይነትና ተመጋጋቢነት የጠበቀ በመሆኑ
ጥሩ ነበር፤
በኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት የብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት መከበር አስፈላጊ የሆነበትን፣
የብዝሃነትና ዴሞክራያዊ ብሄርተኝነትን ወዘተ… የነበረውን የተሳሳተ አመለከካከት ለማስተካከል
የተሟላ ዕውቀት ያስጨበጠ በመሆኑ፣
ሰልጣኞች በስልጠናው የአወንታዊ አመለካከት ጥበብን ለጋዜጠኝነት ሙያ ያለውን ወሳኝነት
የተገነዘቡበት ስለሆነ ለተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚረዳ ክህሎት በመፍጠሩ፣
2.3. የተሃድሶ መስመር መነሻ፣ ቀጣይ አቅጣጫና መድረሻ ላይ ግልፅነትና የጠራ ግንዛቤ የመፍጠር
አስፈላጊነት
ሀገራችን ያለፈችባቸውን የታሪክ ሂደቶች መገንዘብ ለዛሬው ትውልድ ያለውን ፋይዳ፤ ለተሃድሶ
መስመራችን መነሻ በሆነው ጉዳይ፣ በቀጣይ አቅጣጫና መድረሻ በጥቅሉ በሃገራዊ ህዳሴያችን
አቅጣጫና መዳረሻ፣ ለኢቢሲ አመራሮች ባለሙያዎች/ልማታዊ ጋዜጠኞች/ አንዲሁም ለሚያገለግሉት ሰፊው
ህዝብ ሁለንተናዊ እድገት ላይ ባላቸው እንድምታ ዙሪያ ሰልጣኞች ለመገንዘብ ችለዋል፤ ልማታዊና
ዲሞክራሲያዊ መንግስታችን ለመሰረታዊ ለውጥ የበቃው የተሃድሶ መስመር ነድፎ፣ ይህንኑ
በተደራጀ የህዝብ ንቅናቄና ተሳታፊነት ተግባራዊ ማድረግ በመቻሉ መሆኑንም ጭምር ግልፅነት
ተይዟል፡፡
ከዕድገቱ ጋር በተያያዘ አኳኋን የኪራይ ሰብሳቢነት መልሶ መላልሶ እያገረሸ ፈጣኑን የዕድገት
ጉዟችንን እንደሚፈታተን፤ በመሆኑም ሃገራዊ ህዳሴያችንን ለማሳካት የሚያስችል እና ኪራይ
ሰብሳቢነትን ይበልጥ የሚያዳክም ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ስራ መስራት የምንችልበትን ሁኔታ
መፍጠር እንደሚቻል ግልፅነት ተፈጥሯል፡፡
ኒዩ ሊብራሊዝም ትንሽ የህ/ሰብ ክፍልን ይዞ ካፒታሊዝም እንደሚገባና ልማታዊ ደሞክራሲ ግን
አብዛኛውን የህ/ሰብ ክፍል በማበልፀግ ወደ ካፒታሊዝም እንደሚገባና እኛም አብዛኛው ህ/ሰባችን
ድሃ ስለሆነ ከድህነት ለመውጣት ልማታዊ ደሞክራሲ የተሻለ አማራጭ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ
አመራርና ሙያተኞች በልማታዊነትና ዲሞክራሲያዊነት መካከል ያለውን መሰረታዊ ልዩነት፣
በሁለቱ መካከል የሚደረገውን ትግልና የትግል ስልቶችን በሚገባ ተገንዝቦ ከልማታዊና
ዲሞክራሲያዊ አቅጣጫ የመነጩትን በልማታዊ መንግስታችን የተነደፉ ፕሮግራሞችና ግቦች በተሟላ
መንገድ እንዲያሳኩ ግንዛቤያቸውን ማሳደግ ተችሏል፤ኒዩ ልብራሊዝምም አሁን ባለንበት ነባራዊ
ሁኔታ ለኢት/ያም ሆነ ለአፍሪካ አይሰራም በሚል መግባባት ተችሏል፤
በሃገራችን ለመመጀመሪያ ጊዜ የብዝሃ ፓርቲ ስርዓት የተፈጠረው በ 1983 ዓ.ም መሆኑንና
በመጠናከርም ላይ ያለበት ሁኔታ ላይ ነው በሚል መግባባት ተደርሷል፤
አሁን ካለን አቅም አንፃር ቴክኖሎጂ ካላቸው ሃገራት እየኮረጂን ቀስ በቀስም ጎን ለጎን የቴክኖሎጂ
ፈጠራን ማሳደግ ትኩረት እንደሚሰጠው መግባባት ተችሏል፡፡
ልማታዊ ደሞክራሲያዊ መስመር አማራጭነቱን ህዝቡ ተገንዝቦ ይህን የሚያስከትል ፓርቲ
እንዲፈጠር በማድረግ የህ/ሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እምዲቻል እንጅ ህ/ሰቡ ሌላ አስተሳሰብ
የሚከተል ፓርቲ ከመረጠም የሚችል መሁኑንና በዚህም መድበለ ፓርቲ ስርዓቱን የማገድ
አስተሳሰብ እንዳልሆነ ግንዛቤ ተይዞበታል፤
2.4. የልማታዊ ጋዜጠኝነት ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ፍልስፍና በሚሉት መሰረተ ሃሳቦችና
መነሻዎች የኢቢሲ አመራርና ባለሙያዎችን ዕውቀትና ክህሎት የመገንባት አስፈላጊነት፣
በልማታዊ ሚድያና ኮሚኒኬሽንና በኒዩ ሊብራሊዝም ጋዜጠኝነት ፍልስፍና መካከል ያለው ልዩነት ግልፅነት
ያልተያዘበትና የኒዩ ሊብራል ጋዜጠኝነት አቀንቃኝነት ስሜት የተንፀባረቀበት ሁኔታ መኖሩ በቡድን ውይይት
ወቅት ተንፀባርቋል፤
ኢቢስ ባለቤትነቱ የማን እንደሁነ ማለትም የህዝብ ወይስ የመንግስት እንደሆነ በሰልጣኞች በውል
ያልታወቀበት ሁኔታ መኖሩ፤
መንግስት ለኮርፖሬሽኑ/ኢቢሲ/ በቂ ድጋፍ እያደረገ እንዳልሆነና በአሰራር ላይም ጣልቃ እየገባ መሆኑን
አድርገው ማየትና ይህ ባሆነበት ሁኔታ ኮርፖሬሽኑ የተጣለበትን አላማ ከግብ ለማድረስና ተልእኮውን
በአግባቡ መወጣት አይችልም የሚል የጨለምተኝነት አስተሳሰብና በኮርፖሬሽኑ የሚታዩ የአፈጻጸም
ችግሮችን በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ማረም የሚያስችል አቅም ያልነበረውና ታግሎ ማስተካከልም አይቻልም
የሚል የስጋት አመለካከት የነበረ መሆኑ፣
2.5. ለሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬት የአመራሩን አቅም የማጎልበትና ዝግጁነቱን የማረጋገጥ
አስፈላጊነት
በጥልቀት በመታደስ ግምገማ እንደተረጋገጠው አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 25 ዓመታት በተለይም ደግሞ ባለፉት 15
አመታት በሁሉም የልማት መስኮች ስኬታማ የሆኑ ለውጦች ተመዝግቧል፡፡ በሃገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በገጠርና
በከተሞች በተደረገው እንቅስቃሴ የመጀመሪያ ደረጃ ካፒታል ክምችት የፈጠረች ሃገር መገንባት ተችሏል፡፡ ይህ በጐ ጎኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ የማስፈፀም አቅም ችግራችን በሚፈለገው ደረጃ ባለመቀረፉና ይህ ችግር ከለውጥ ሥራችን መዳከም
ጋር ተዳምረው ሃገራችንንም ሆነ መንግስታችንን ለአደጋ የማጋለጥ ሁኔታ እየተፈጠረ መጥቷል፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት
የፖለቲካ ኢኮኖሚ በሚፈለገው ፍጥነትና መጠን አልከሰመም፡፡ የትምክህት ፣ የጠባብነትና የሃይማኖት አክራሪነት
እንዲሁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ከመዳከም ይልቅ እየተጠናከሩ የመጡበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
በአመራሩና በባለሙያው ውስጥ የሚታየው የአድርባይነት፣ የጎራ መደበላለቅ፣ የኪራይ ሰብሳቢነትና ስራን በትጋት፣
በተነሳሽነትና ውጤታማነት የመፈፀም ችግርም በአግባቡ አልተቀረፈም፡፡ ፀረ-ዴሞክራሲያዊነት፣ ውሳኔን በወቅቱ
ያለመወሰን፣ የህዝብን ችግሮች አዳምጦ ያለመፍታት፣ የህዝብ የተደራጀ ተሳትፎን ያለማጠናከር፣ በኔት ወርክ
መጠቀምም....ወዘተ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጎልተው
በመታየታቸው ህዝቡ ምሬት ውስጥ ከመግባት አልፎ የፀረ-ሰላም ሃይሎች መጠቀሚያ ጭምር እየሆነ መምጣቱን
በጥልቀት የመታደስ ግምገማው ተረጋግጧል፡፡ እነዚህን ችግሮች በፍጥነት በመፍታት የሁለተኛው የዕድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችንን የቀጣይ ተከታታይ ሶስት ዓመት ግቦች ማሳካት እንደሚገባ ግልፅ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የኪራይ ሰብሳቢነት የፖለቲካል ኢኮኖሚ የበላይነትን በልማታዊ
የፖለቲካል ኢኮኖሚ በመቀየር መሰረታዊ ለውጥ የማረጋገጥ ጉዳይ የሞትሽረት ስራ ተደርጐ ተወስዷል፡፡ ይህንኑ
ለማረጋገጥም በአንድ በኩል ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ልማታዊነትን የሚያጎለብቱ ድጋፎችንና ስራዎችን በመስራት በሌላ
በኩል የኪራይ ሰብሳቢነት ዋነኛ ምንጮች ሆነው የተለዩ ጉዳዮችን በማምከን ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በቁጥጥር ስር
በማዋል ልማታዊነት የበለጠ እንዲጎመራና የበላይነት እንዲይዝ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባው አፅንኦት
ተሰጥቶታል፡፡ ይህንኑ እውን ለማድረግ የኢቢሲ አመራሩንና ባለሙያውን ለተልዕኮው በብቃት ማዘጋጀት ይገባናል፡፡
የሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ በመገንባትና በኢኮኖሚው መታየት
የጀመሩትን የሚዛን ክፍተቶች በማስተካከል ኢኮኖሚውን 11 በመቶ ማሳደግና ለሃገራዊ ራዕይ መሳካት አስተዋጽኦ
ማድረግ፣ አገራዊ የኢንጂነሪንግና ፋብሪኬሽን አቅማችንን በማሳደግ የአምራች ዘርፎች ምርታማነት፣ ጥራትንና
ተወዳዳሪነትን በማጎልበት የኢኮኖሚ መወቅራዊ ለውጥን ማረጋገጥ፣ የህዝብን የተደራጀ አቅም በቀጣይነት መገንባትና
የልማቱ ባለቤትና ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል፣ እና ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መንግስትን በማጠናከር ልማታዊ
የፖለቲካ ኢኮኖሚን መገንባት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጦለታል፡፡ የኢቢሲ አመራርና ባለሙያዎች ከአንደኛው
የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ሊወስዱ በሚገቡ ጠቃሚ ልምዶችና የሁለተኛው የዕቅድና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረታዊ መነሻዎች፣ አቅጣጫዎች ላይ ተነሳሽነትና የመፈፀም ቁርጠኝነት ተላብሶ በተደራጀ
የህዝብ ንቅናቄ በልማታዊ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራዎች የማስፈጸም አቅሙን መገንባት ይጠይቃል፡፡
ከዚህም በመነሳት ሃገሪቱ በ 2008 በጀት ዓመት የሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ በጀመረችበት
ወቅት በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች በኢሊኖ ምክንያት በተከሰተው የድርቅ አደጋ በዜጐችና በእንስሳት ሃብታችን ላይ
ያጋጠመውን ችግር በራሳችን አቅም ለመቋቋም በተደረገው ጥረት ችግሩን መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም የችግሩ
መፈጠር መንግስት በዕቅድ ዘመኑ የያዛቸውን ሰፋፊ የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እንዳይከናወኑ የራሱ
አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በተጨማሪም በመንግስታችን ውስጥ በተፈጠረው የአስተሳሰብና የአፈፃፀም ብልሽትና
ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም በፀረ-ልማትና ፀረ-ሰላም ሃይሎች አማካይነት የተቀሰቀሱት አለመረጋጋቶች በልማትና
የሃገር ግንባታ ስራዎቻችን ላይ የበኩላቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድረው አልፈዋል፡፡ በመሆኑም የሁለተኛውን የዕድገትና
የትራንስፎርሜሽን ትግበራ የባከነውን ጊዜ በሚያካክስና የላቀ ውጤት በሚያመጣ አኳኋን በውጤታማነት እንዲፈፀም
የኢቢሲ አመራሩና ባለሙያው ለዚህ ትልቅ ሃገራዊና ከባቢያዊ ተልዕኮ መገንባት ልዩ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ሆኖ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ለሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬት የኢቢሲ አመራርና ባለሙያውን ለማዘጋጀትና
ለማብቃት ስልጠናው መሰጠቱ በጣም ያስፈልጋል፡፡
2.6. የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት ባህሪያት የዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባታ ሂደት ስኬቶችና የወደፊት
አቅጣጫዎችን የመገንዘብ አስፈላጊነት
በኢትዮጵያ ሃገራዊ ለውጥ ለማምጣትና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንድንጀምር የግድ ያሉን ሁለት
መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የትላንቷ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ
የህዝቡና የልማታዊ መንግስታችን የልማትና የለውጥ ፍላጐት ነው፡፡ አምባገነኑ የደርግ መንግስት በኢህአዴግ
መሪነት በተካሄደው ህዝባዊ ትግል ከተወገደ ማግስት ጀምሮ ከላይ የተቀመጠውን መሰረታዊ እውነታ
መሰረት በማድረግ በኢትዮጵያ መሰረታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የውጭ ግንኙነት
ተግባራትን በማካሄድ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ ይህም በመሆኑ በሃገሪቱ ባሉ ሁሉም አካባቢዎች
በተነፃፃሪ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እየጎለበተ መጥቷል፡፡ አስተማማኝ ሰላምም ሰፍኗል፡፡ ለልማትና ዲሞክራሲ
ስርዓት ግንባታም መሰረት ተጥሏል፡፡ በዚህም ምክንያት አዲሲቷ ኢትዮጵያ የትላንቱን አሮጌ ባህሪ ትታ
አዲሱን ባህሪ ለመላበስ በሚያስችል የሽግግር ምዕራፍ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ከትላንቱ የድህነት አዙሪት ወጥታ
የነገን ባህሪ ሙሉ በሙሉ የተላበሰች ሃገር ለመሆን የሚያስችላትን የህዳሴ ጉዞ ጀምራለች፡፡ ይህንን በጎ
ጅምር አጐልብቶ መቀጠል ይገባል፡፡
የጀመርነው የልማትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና የዚሁ ማስፈፀሚያ የሆኑት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን
ዕቅዶችና ሀገራችን የተያያዘችው የህዳሴ ጉዞ በወሳኝነት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉት በውስጣዊ አቅማችን
የተጠናከረ ልማታዊ መንግስት በመፍጠር ነው፡፡ ስለሆነም ውስጣዊ ፈፃሚ ሃይሎቻችንን በብቃት ማዘጋጀትን
ስናስብ የኢቢሲ አመራርና ባለሙያዎቻችንን የብቃትና የሙያዊ ስብእና አቅም ማሳደግን ያካትታል፡፡ ይሁንና
ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስታችን የሚሰራበት ከባቢያዊና አለምአቀፋዊ ሁኔታዎች መልካም
ዕድሎችንና ፈተናዎችን ይዘው የሚመጡ በመሆናቸው በተሃድሶ ጉዟችን ላይ የማፋጠን ወይም የሟጓተት
ተፅዕኖ ሊያሳርፉ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ ልማታዊ መንግስታችን ልማታችንን የሚያፋጥኑ
መልካም ዕድሎችን በማስፋትና በመጠቀም፣ ለልማታችን እንቅፋት የሚሆኑ ፈተናዎችንና አሉታዊ
ተፅዕኖዎችን ደግሞ በመቀነስ የህዳሴ ጉዟችንን ይበልጥ ሊያራምድ የሚችለው ይህንኑ ውጫዊ ሁኔታ የተገነዘበ
እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ውጫዊ ሁኔታን አስመልክቶ ልማታዊ መንግስቱ ያለውን ግምገማ፣ የትኩረት
አቅጣጫ፣ መልካም ዕድሎችን አሟጦ ለመጠቀም እንዲሁም ለማስፋትና ተግዳሮቶቹን ለመቀነስ
የሚከተላቸውን አቅጣጫዎችና ስትራቴጅዎች የኢቢሲ አመራሮቻችንና ባለሙያዎች እንዲገነዘቡ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ልማታችንን የሚያፋጥኑ መልካም ዕድሎችን በማስፋትና በመጠቀም በልማታችን
ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፉትን ለመቀነስ የሚያስችላቸውን የማስፈጸም አቅማቸውን መገንባት ይገባል፡፡
በመሆኑም የህዳሴ ጉዟችንና ውጫዊው ሁኔታን የመገንዘብ ጉዳይ ለኢቢሲ አመራሮችና ጋዜጠኞች
ስልጠናው መሰጠት ይኖርበታል፡፡
4.2.2. የኢት/ያ ፌዴራል ስርዓት ግንባታ ስኬቶች፣ የወደፊት አቅጣጫዎችና በዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት ፅንሰ ሃሳብ ላይ
በአመራሩና በባለሙያው ግልፅነት ተፈጥሯል
4.2.3. የሃገራችን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ በኮርፖሬሽኑ አመራርና ባለሙያዎች ግልጸኝነት ተፈጥሯል
ሰልጣኙ በሁሉም ሰነዶች ከሚያነሳቸዉ ሀሳቦችና በጥያቄ መልክ ወደ አካዳሚዎች ከሚቀርቡ ሪፖርቶች ከተደረገው
ግምገማ አንጻር ሲታይ መሰረታዊ የአመለካከት ችግሮች እንደነበሩ የሚያመላክት ቢሆንም በዉይይት ወቅት ከተካሄዱት
መተጋገሎችና በዋና አሰልጠኞች በኩል በተሰጠዉ መልስ መግባባት ላይ የተደረሰባቸው እንደሆነ ተገምግሟል፡፡
ይሁን እንጂ ደጋግመዉ ሲነሱ የነበሩና ሰፊ ክርክር ተካሄዶባቸዉ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች ቢሆኑም ቀጣይ
ክትትል የሚያስፈልጋቸዉ እንደሆነ ተገምግሞ ከሁሉም ሰነዶች በተደጋጋሚ ይንጸባረቁ የነበሩና ዋና ዋና የአመለካከት
ችግሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
አካዳሚው ስልጠናው የሚመራበት እቅድ አስቀድሞ በመላክ ማእከላቱ በዝግጅት ምእራፍ በመነሻነት
ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በውቅቱ እቅድ እንዲያዘጋጁ ያገዘ መሆኑ፤
ለ/ በድክመት
የሚላኩ የሪፖርት ፎርማቶች በወቅቱ የመላክ ውስንነቶች፣ ለሚላኩ ሪፖርቶች በተለይም በሁለተኛ መጽሃፍ
ግምገማ ላይ ግብረ መልስ የመስጠት ውስንነቶች መኖራቸው፣ በመጨረሻው መጽሃፍ ላይ በየአካዳሚው አንደኛ
የወጡ የእቅድ አቅራቢ ሰልጣኞች በቀጥታ በፕላዝማ እንደሚያቀርቡ ሲገባ አሰልጣኟ እንድታቀርበው መደረጉ
በዚህም ለአሰልጣኟና ለማዕከላት ቀድሞ የማሳወቅ ውስንነቶች ነበሩ፡፡
የስልጠና ርዕሶች መብዛትና ለስልጠናዉ የተሰጠዉ ጊዜ ማጠር መታረም አለበት
ለስልጠናው የተመደቡ ሁሉም ዋና አሠልጣኞች የየራሳቸው የአቀራረብ ልዩነት ቢኖርም ስልጠናውን ውጤታማ
ለማድረግ በአመለካከትና በክህሎት የተሻሉ በመሆናቸው ለቀጣይ ሊጠናከሩና ሊበረታቱ ይገባል፡፡ በመሆኑም በየአሰልጣኙ
የቀረቡ ጥንካሬዎችና መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች እንደሚከተለው ተጠቃልለው ቀርበዋል፡፡
ሀ)በጥንካሬ፦
የገለጻ አሠጣጡ ከሞላ ጎደል ዕውቀትን ሊያስጨብጥ በሚችል መልኩ መሰጠቱ፣
የሚሠጡት ገለጻዎች በሚያዝናና መልኩ መስጠታቸው፣
በሠልጣኙ መካከል ብዥታ የፈጠሩ አስተሳቦችን ከተጨባጭ መረጃ ጋር በማስረዳት መቅረፍ
መቻሉ፣
የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ፣የመለስን ለጋሲ በማጣቀስ ግልጽ በሆነ መንገድ ዘርዝሮ ማስረዳት
መቻሉ፣
ለተነሱ ጥያቄዎች በአብዛኛው በበቂ ማብራሪያ ላይ ተመርኩዞ መሰጠቱ፣
በፕሮግራሙ ላይ በተቀመጠው ሰአት አለማክበሩና ጠዋት አርፍዶ የመጀመር ሁኔታ ቢስተካከልና በማእከሉ
የስልጠና ሰአት በቀጣይ ቢከበር
በገለፃ ወቅት 2፡00 ሰዓት መጀመር ሲገባ 2፡30 መጀመሩ እንዲሁም ከሰዓት 8፡00 መጀመር ሲገባ
8፡30 መጀመሩ በሰልጣኙ የሰዓት አጠቃቀም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ በቀጣይ ሊሻሻል
ይገባል፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ አሰልጣኙ ካለው ልምድ አኳያ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ከአዲስ አበባ ስለሚያገኘው ልዩ ጥቅምየድርጅት አቋምን ከማንፀባረቅ ይልቅ የግልን አስተሳሰብ
ማንፀባረቁ ተገቢ ባለመሆኑ ለወደፊቱ ቢስተካከል የተሻለ ነው፡፡
ጥያቀዌዎች ከተነበቡ በኃላ ለተጠየቁ ጥያቄዎችን አደራጅቶ በሚገባ ያለመመለስ፣
7.1.5. የከተማና የገጠር የወጣቶች የልማትና የእድገት ፖኬጅና ስትራቴጂ ያሰለጠኑትን አሰልጣኝ አቶ ርስቱ
ይርዳን በተመለከተ
ሀ/ ጠንካራ ጎኖች
በስልጠናው ጭብጥ ላይ በቂ ዕዉቀት ያለዉ፣ በቂ ዝግጅት ያደረገና በብቃት ያቀረበ መሆኑ
የመጀመሪያዉ ገለጻ ድግግሞሽ የነበረበት መሆኑ፣ እንዲሁም እንደሃገር በሚሰጥ ስልጠና ላይ አርብ
ዕለት ለሙስሊም ሰልጣኞች ጁማ በመሆኑ በሚል መልዕክት ማስተላለፉ ከአካዳሚዎች የስልጠና
ደንብና አሰራር አኳያ የሚጋጭ መሆኑ፣
- አሰልጣኙ በመጀመሪያ ገለፃው በስልጠና ፕሮግራሙ መሰረት ወጣቶች ፓኬጅን ማቅረበገለፃ
አቀራረባቸው ግልፅና ምቹ መኖሩ
ብ ሲገባው ስትራቴጅውን ማቅረቡ በሰልጣኙ ላይ መደናገር የፈጠረ መሆኑ፣
ሀ/ በጠንካራ ጎኖች
ሀ)ጠንካራ ጎኖች
በጥንካሬ
በክፍተት
በጥንካሬ
ፍትሃዊ፣አሳታፊ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ መድረክ መፍጠር መቻላቸው፤
አዳዲስሀሳቦች እንዲወጡ ማበረታታቸው፤
ውይይቱ አሳታፊ እንዲሆን ሀሳቦች በደቂቃ እንዲገደቡ ማድረግ፤
ትኩረት የሚያስፈልጋቸውና አከራካሪ ጉዳዩችን ለይተው ለቡድኑ በመስጠት ሰልጣኙ የጋራ መግባባት
ላይ እንዲደርስ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የጠራ አመለካከት ለማስያዝ ጥረት ማድረጋቸው፤
ከአጀንዳ ሲወጣና ግልፅ ላልሆነ ጥያቄ እና ሀሳብ አቅጣጫ መስጠት መቻላቸው፤
በድክመት
መጀመሪያ አካባቢ ጥያቄ ለመጠየቅና ሃሳብ ለመስጠት ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ተወያዮችን ሃሳባቸውን
እንዲያሳጥሩ ባለማድረግ የሌሎችን ተሳታፊዎች ጊዜ መሻማቱ፤
ከስልጠናው አጀንዳ ውጪ የሆኑ ጥያቄዎችና የውይይት ሀሳቦች ሲነሱ የውይይቱን አቅጣጫ ባለማስያዛቸው
ምክንያት ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች እንዲኖሩ ምክንያት መሆን፤ የቡድን ውይይቶችን አቅጣጫ የማስያዝ
ውስንነት መኖሩ፤
በሰልጣኞች መካከል ተመጣጣኝ እውቀት እንዲኖር ጥረት የተደረገ ቢሆንም የተወሰነ ድክመት ያለ
መሆኑ፤
በጥንካሬ
በሃይል መድረክም ሆነ በቡድን ውይይት በተነሱ ጥያቄዎችም ሆነ ያልበሰሉ ሀሳቦች መካከል ግልፅ
ባልሆኑ ጉዳዩች ላይ ሰፊ ጊዜ ሰጥተው መወያየታቸውና ወደ ቡድን ቀርቦ ውይይት ሊደረግባቸው
የሚገቡትን በመለየት ረገድ ጥሩ ጥረት መደረጉ፤
በየለቱ በመገናኘት የውሎ ግምገማ ማድረግ መቻላቸው፤
በክፍተት የታዩ፡-
ስልጠኙ ለሀይል መድረክ ከሚሰጠው ማብራሪያ፣ ከሰነድና በግሉ ከነበረው ግንዛቤ ተነስቶ ሃሳቦችን፣
ልምዶችንና አመለካከቶችን በነፃነት በማንሸራሸር ግንዛቤውን እንዲያዳብር ይረዳ ዘንድ የስልጠናው ስነ ዘዴ
ሰልጣኝ ተኮር ሆኖ እንዲመራ ይፈለጋል፡፡ በዚህም በቡድኖችና በህዋስ ውይይት አባሉ በንቃት እንዲሳትፍ
ይጠበቃል፡፡ ከዚህ አንፃር የነበረው እንቅስቃሴ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
በጥንካሬ፡-
በድክመት፡-
9. ማጠቃለያ፤