You are on page 1of 13

የቡድን አገልግሎት

የመሪዎች ስልጠና የመጀመሪያ ሳምንት


የቡድን አገልግሎት ለመገንባት
1. የቡድን አገልግሎት ለመገንባት ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር አንድ መሆን ይጠይቃል

2. የቡድን አገልግሎት እርስ በርስ ተደጋግፎ መስራትን ይፈልጋል

3. አገልግሎት ውስጥ በቡድን እርስ በርሳችን የክርስቶስ ባህሪን መለማምድ


ይጠበቅብናል
ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር አንድ መሆን
• በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት
ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥
አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ (ፊሊ. 2:1-2)
ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር አንድ ለመሆን
• ከክርስቶስ ጋር ያለን አንድነት እርስ በርስ ካለን አንድነት ጋር ሚዛናዊ ይሆን ዘንድ
ይገባዋል።
• ከክርስቶስ ጋር ካለን ግንኙነት የሚመነጭ ምንም አይነት አገልግሎት ቢኖር እርስ በርስ
ያለንን ግንኙነት ወደ አንድ ሃሳብ የሚያመጣ ሊሆን ይገባዋል።
አንድ ሃሳብ
አንድ ሃሳብ እንዴት ነው የምንሆነው?
• 1) አንድ ፍቅር ሲኖረን
• 2) አንድ ልብ ሲኖረን
በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥
ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ
ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ (ፊሊ. 2:1-2)
1) አንድ ፍቅር

• አንድ አይነት ሊኖረን የሚችለው ፍቅር agape የሚባለው ፍቅር ሲኖረን ብቻ ነው።
በፊል 2፥1 ላይም የተገለፅው የግሪክ ቃል ይህ agape የተባለው ነው።
• የወዳጅነት ፍቅር አንዳንዴ ስህተት ሊኖረው ይችላል ነገር ግን አጋፔ ስህትትና እንከን
የሌለበት መለኮታው ፍቅር ስልሆነ የእርስ በርስ ግንኙነታችን በዚህ የእግዚአብሔር
ፍቅር ዙሪያ መገንባት አለበት።
1) አንድ ፍቅር
• ግንኙነታችን በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር ዙሪያ ሲገነባ በማንስማማባቸው ነገሮች እንኳ
አንድነታችን ሳይናጋ ይቀጥላል። አስቸጋሪ ከሚባሉ ሰዎች ጋር ሳይቀር አብረን
መስራትና ማገልገል እንችላለን።
• ይህ አንድ ፍቅር 1) እግዚአብሔርን በመውደድ 2) ቅዱሳንን በመውደድ ይገለፃል
• አንድ ፍቅር ስራ ተኮር ሳይሆን ልብ ተኮር እንድንሆን ያደርገናል
• ዮሐ 13፥34
2) አንድ ልብ

• አንድ ልብ መሆን በሃሳብ ከመስማማት ያለፈ ነው። አንድ ልብነት መሰረቱ


ከማናቸውም ነገሮች በላይ ከፍ ያለ በእግዚአብሔር መለኮታዊ አላማ ላይ የተመሰረተ
ነው።
• አንድ ልብ ሲኮን እግዚአብሔር ዋጋ የሰጣቸውን ነገሮች ማወቅና ራስን አስተካክሎ
መጓዝን ይጠይቃል እርሱ ዋጋ የሰጣቸውን ነገሮች አለማወቅና አሳንሶ መመላለስ ወደ
ራሳችን አጀንዳና የቤተክርስቲያን ፖለቲክስ ይወስደናል።
የመሪዎች ስራ

1. ቡድኑን ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ገፅ ላይ እንዲሆን ማድረግ


2. ቡድኑ የእግዚአብሔርን ሃሳብ እንዲስማማ ማድረግ
3. የእግዚአብሔርን ፊትና ሃሳብ በፀሎት መፈለግ
4. የእግዚአብሔርን መንገድ ማወቅና በመንገዱ መራመድ
2) የቡድን አገልግሎት እርስ በርስ ተደጋግፎ
መስራትን ይፈልጋል
• ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥
ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና
ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ
እንጂ። (ፊሊ . 2:3-4)
እርስ በርስ ተደጋግፎ መስራትን
• የግል ሃሳብንና አጀንዳን በቡድን ውስጥ ለመፈፀም መሞከር የቡድንን ስራ ውጤታማ
እንዳይሆን ያደርገዋል።
• ስለ ቡድኑ ውጤታማነትና ስኬት ስንል የግል ሃሳባችንን ወደ ጎን ማድረግ አለብን
• interdependence, not independence.
• ከንቱ ውዳሴ
• ለወገኔ ይጠቅማል
• ለሌላው የሚጠቅመውን ለይቶ ማወቅ
• ባልንጀራችንን ከኛ እንደሚሻል መረዳት
3) አገልግሎት ውስጥ በቡድን እርስ በርሳችን
የክርስቶስ ባህሪን መለማምድ ይጠበቅብናል
• በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።
እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት
እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ
ራሱን ባዶ አደረገ፥ (ፊሊ. 2:5-7)
የክርስቶስ ባህሪን መለማምድ
• በእርሱ የነበረ ትህትናና የአገልግሎት መንፈስ እርስ በርስ ስኬታማ አገልግሎትን ከማገልገል
ባሻገር ባልተስማማንባቸው ጉይዳዮች ላይ እንኳ ሳይቀር በሌሎች ላይ ተፅእኖ እንድናመጣ
ያግዘናል።
• መቀማት እንደሚገባ
• ትህትና
• የባሪያን መልክ
• የሰው ምሳሌ
• ራስን ባዶ ማድረግ

You might also like