You are on page 1of 31

 

በቂርቆስ ክፈለ ከተማ የወረዳ አምስት የሰው ኃይል አስተዳደር


ደጋፊ የስራ ሂደት በዲሲፕሊን አፈፃፀም እና በቅሬታ አፈታት ስነስርዓት
ላይ የተዘጋጀ የስልጠና ማኑዋል፡፡

አዘጋጅ ፡- ዓለምሰገድ ሲሳይ (በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሰው ኃይል


ደጋፊ የስራ ሂደት አስተባባሪ)
መግቢያ

• የዲሲፕሊን ፣ ቅሬታ አቀራረብ የአፈፃፀም ደንቦች መመሪያዎችንና


አዋጆችን ለሚመለከታቸው አስፈፃሚ አካላት ግልፅ ለማድረግ እና
ለማብራራት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የሰው ሃይል ደጋፊ የስራ
ሂደት የዲሲፕሊን የቅሬታና የአቤቱታ አቀራረብ የስልጠና ማኑዋል
ተዘጋጅቷል፡፡
ዓላማ

• የስልጠናው አላማ የዲሲፕሊን ኮሚቴዎችን፣ የስራ መሪዎችን የሰው


ኃብት አስተዳደር ባለሙያዎችን፣የወረዳው የዲሲፕሊን እና ቅሬታ ሰሚ
ኮሚቴዎችን በዲሲፕሊንና ቅሬታ አፈፃፀም ረገድ ከፌደራል፣ከክልሎች
እና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የመንግስት ሰራተኞች አዋጆች እና
ደንቦች አንጻር ለስራ አፈፃፀም ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡
የስልጠናው ግብዓቶች

• የፌደራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99


• የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር
6/2000
• የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/97
• የፌደራል የመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊንና የቅሬታ አቀራረብ ደንብ
ቁጥር 77/1994 ዓ.ም
• የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊንና
የቅሬታ አቀራረብ አፈፃፀም ደንብ ቁጥር 24/2002
• የፍታብሄር ስነስርዓት ህግ፣የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣የወንጀለኛ መቅጫ
ስነስርዓት ህግ
• ስለቅሬታና አቤቱታ እንዲሁም ስለዲሲፕሊን አፈፃፀም የፅንስ ሀሳብ
መፅሃፍት እና የመረጃ መረብ
ስልጠናው የሚሰጥበት ሁኔታ

• ከስራ ውጭ (out of the job training) ሆኖ አሰልጣኝ ለሰልጣኞች


የተዘጋጀውን ፅሁፍ እና ማሳያ በማብራራት
• ከሰልጠኞች ጋር በመወያየት እና የልምድ ልውውጥ በማድረግ ይሆናል፡፡
 
ምዕራፍ አንድ
ዲሲፕሊን

• ዲሲፕሊን የሚባለው ቃል የመጣው ከላቲን ቃል ዲሲፑለስ ከሚለው ሲሆን ትርጉሙም


ተከታዮች፣ጀማሪዎች፣ተማሪዎች ማለት ነው፡፡

• አብዛኛዎቹ የዲሲፕሊን ትርጉሞች ከግለሰቦች የባህሪ ጥናት ጋር ይህንኑም ለማስተካከል ከመመሪያዎች ጋር


የተያያዙ ናቸው፡፡

• የቀደሙ የዲሲፕሊን ትርጉሞች ከቅጣት ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በ13ኛው ክፈለ ዘመን ኃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች
ላይ ግለሰቦችን ለመቅጣትም እንደ ተጀመረ ይነገራል፡፡ (WWW.Merriam- webster.com dictionary )

• የዲሲፕሊን ጥፋት ውሳኔ ስነ ስርዓትን በተከተለ ሁኔታ በስራ መሪዎች ወይም በአስተዳደር ኃላፊዎች ወይም
በስራ መሪዎች ውሳኔ ወይም በዲሲፕሊን ኮሚቴዎች የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በመስርያቤቶች የበላይ ኃላፊዎች
የሚፈፅም አስተዳደራዊ ውሳኔ ነው፡፡

• አስተዳደራዊ ውሳኔ“አስተዳደራዊ ውሣኔ” ማለት በዚህ አዋጅ በክፍል 1ዐ ለተመለከቱት ጉዳዮች ሲባል የመሥሪያ
ቤቱ የበላይ ኃላፊ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም በዲሲኘሊን ኮሚቴ ተጣርተው በቀረቡ ጉዳዮች ላይ ወይም
በዲሲኘሊን ኮሚቴ መታየት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ሥነ-ሥርዓቱን ሳይጠብቅ ወይም በቀጥታ በሕግ በተሰጡት
ሌሎች ጉዳዮች ላይ በጽሑፍ ወይም በቃል የሚሰጠው ውሣኔ ነው፡፡( የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አዋጅ
ቁጥር 6/2000)
 
ዲሲፕሊን ማለት፡ ዲሲፕሊን ማለት አንድ ቋሚ የመንግስት ሰራተኛ በአዋጁ አንቀፅ
62 እና 63 የተመለከቱትን የሰራተኛውን ግዴታዎችና ስነምግባር የሚያከብር
መልካም የሙያና የስራ ስነምግባር ነው፡፡

ከአዋጅ ቁጥር 6/2000 አንቀፅ 62 እና 63 ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች


መተላለፍ ደግሞ የዲሲፕሊን ጥፋቶችን ያስከትላል፡፡
የዲሲፕሊን ጥፋት አይነቶች
በአዲደ አበባ ከተማ መስተዳድር እና
በፌደራል መንግስት የመንግሰት
ሰራተኞች አዋጆች መሰረት የዲሲፕሊን
ጥፋት ዓይነቶች በሁለት ይከፈላሉ
• ቀላል የዲሲፕሊን ጥፋት ዓይነቶች
• ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት አይነቶች
ተብለው በሁለት ተከፍለዋል፡፡
ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት አይነቶች
• ትዕዛዝ ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በመለገም ወይም ሆን ብሎ የአሠራር ሥነ-ሥርዓት
ወይም የመንግሥትን ፖሊሲ ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፣
• ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም ባለጉዳዮችን ማጉላላት ፣
• ሥራ እንዳይሰራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፣
• በቀላል የዲሲኘሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ
ከሥራ መቅረብ ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፣
• በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነት መደባደብ፣
• በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፣
• ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ ፣
• በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃብኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ፣
• የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈፀም ፣
• የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈፀም ፣
• በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረግ ፣
• በስልጣን አለአግባብ መጠቀም ፣
• በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ጥቃት መፈፀም ፣
• ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲኘሊን ጉድለት መፈፀም፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር እና በፌደራል መንግስት
የመንግሰት ሰራተኞች አዋጆች ቀላል የዲሲፕሊን ጥፋቶች ማለት

• ቀላል የዲሲፕሊን ቅጣቶች እስከ አንድ ወር የሚደርስ የደመወዝ


መቀጮ ሊያስከትሉ የሚችሉ የዲሲፕሊን ጥፋቶች ናቸው፡፡
የዲሲፕሊን ቅጣት አላማ

• የዲሲፕሊን ቅጣት አላማ የመንግስት


ሰራተኛው በፈፀመው የዲሲፕሊን ጉድለት
ተፀፅቶ እንዲታረምና ብቁ ሰራተኛ እንዲሆን
ለማስቻል ወይም የማይታረም ሆኖ ሲገኝ
ለማሰናበት ነው፡፡
የዲሲፕሊን ስነስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የመንግስት ሰራተኞች ደንብ እና
አዋጅ

• 1- ስለ ቅጣት ዓይነቶች
• በአዋጁ አንቀፅ 68 እና 69 መሰረት ሁለት አይነት የዲሲፕሊን ቅጣቶች
አሉ
(1) ቀላል እና ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት አይነቶች በመባል ተለይተዋል
ቀላል
(ሀ) የቃል ማስጠንቀቂያ
(ለ) የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ
(ሐ) እሰከአንድ ወር ደመወዝ የሚደርስ መቀጮ
ከባድ
(መ) እስከ ሶስት ወር ደመወዝ የሚደርስ መቀጮ
(ሠ) እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ለሚደርስ ጊዜ ከስራና ደረጃና
ደመወዝዝቅ ማድረግ
(ረ) ከስራ ማሰናበት፡፡
….. ስነስርዓት
2. የዲሲፕሊን እርምጃ አወሣሠድ
• 2.1 ስለምርመራ
• በከተማዉ አሰተደደር የዲሲፕሊን እና ቅሬታ አቃራረብ አፈፃፀም
መሠረት የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረትና የዉሣኔ አሣጣጥ ስነ ሰርዓት
በደንብ ቁጥር 24/2002 ምዕራፍ ሁለት ላይ ተቀምጧል፡፡ክስ
ከመመሰርቱ በፊት የዲሲፕሊን ኮሚቴው ወይም ጥፋት የሚያጣራ
አንድ ወይም ከአንድ በላይ የመንግስት ሠራተኞች ተመድበዉ ከሆነ፡
ምርመራ ይካሄደል፡፡
… ስነስርዓት

•የምርመራ አይነቶች
ሀ. የተፋጠነ የዲሲፕሊን
ምርመራ
• ለ. መደበኛ ምርመራ ናቸዉ
ሀ- የተፋጠነ የዲሲፕሊን ምርመራ

• ለቀላል የዲሲፕሊን ጥፋቶች የተፋጠነ


የዲሲፕሊን ምርመራ መጠቀም ነዉ፡፡
• መርማሪዎች ከሚመለከተዉ የሥራ
ሃላፊ ጥፋቱን እንዲያጣራ ሊመድቡ
ይችላሉ፡፡ የስነ ስርዓቱ ቅድም
ተከተልም እንዲሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
1-ጥፋት
እንዲያጣራ
5.የሚመለከተው ለአጣሪው ከስራ
ኃላፊ የቀረበለትን
መሪ ይገለፃል
የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ
ውሳኔ ይሰጣል

2. አጣሪ የክስ
ፅሁፍ አዘጋጅቶ
ይልካል

4.ሰራተኛው ጥፋቱን
ካላመነ አጣሪው አግባብ
ያላቸውን ማስረጀዎች
መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ
ያቀርባል

3. ሰራተኛው የክስ
መልስ
መቃወሚያውን
4.ሰራተኛው ጥፋቱን ያቀርባል
ካመነ አጣሪው
የጥፋተኝነት የውሳኔ
ሀሳብ ያቀርባል
ስለ ስልጣን ውክልና
• የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ቁጥር 24/2002 እና
አዋጅ 6/2000 እንዲሁም ይህንን ደንብ
ለማስፈፀም በወጣው የዲሲፕሊን ቅጣት እና
የቅሬታ አቀራረብ መመሪያ መሰረት
ስለዲሲፕሊን ቅጣት አወሣሠን የሥልጣን
እርከንየስራ ሂደት መሪ/አስተባባሪ፣
የመስርያቤቱ ኃላፊ እስከ አንድ ወር ድርስ
የሚደርስ የደመወዝ ቅጣት የመቅጣት ስልጣን
አለው ፡፡
ለ- መደበኛ ምርመራ

• ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ


በከባድ የዲሲፕሊን ጥፋቶች
የሚያስቀጣ የዲሲፕሊን ጥፋት
የተከሰሰ እንደሆነ ክሱ በሚከተለው
ስነስርዓት ይታያል፡፡ መደበኛ
ምርመራ የሚያካሂደውም
የዲሲፕሊን ኮሚቴ ነው፡፡
ጥፋት

ክስ እንዲመሰረት ትዛዝ ከስራ መሪ ወይም ከበላይ ሃላፊ ለሰው ሃይል ደጋፊ የሰራ
ሂደት ይቀርባል፡፡

የሰው ሃይል ደ/የስራ ሂደት የዲሲፕሊን ክስ ያዘጋጃል

የዲሲፕሊንና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የክስ ፅሁፍንና


የማስረጃዎቹን ቀሪ አያይዞ የክስ ማስታወቂያ ይልክለታል

ተከሳሽ ቀርቦ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ ከፈለገ


በደንቡ አንቀፅ 14 መሰረት ያቀርባል

• አልተቀበለውም
የዲሲፕለንና
ተከሳሽ ተከሳሽ የቅሬታ
መልስ መልስ ኮሚቴው
በፅሁፍ እንዲሰጥ መቃወሚያው ክሱ ይዘጋል
አዎ
ያቀርባል ያዘዋል ን
ተቀብሎታል?
የዲሲፕሊንና ቅሬታ
ሰሚ ኮሚቴው
አዎ የከሳሽና ተከሳሽ የዲሲፕሊን
ክዷል? ምስክሮች ኮሚቴው የከሳሽን
የተከሳሽ ምስክሮች
በመስማትና በፅሁፍ እና ተከሳሽን
ተራ በተራ ይሰማሉ
ማስረጃዎቹን ምስክሮችን
በመመርመር ክሱን ይጠራል
ውሳኔው
በሰው/ሃ/ደ/የስ ያጣራል አንቀፅ
የውሳኔ 16(2)
ሀሳብ ቀላል የተከሳሽ የመንግስት የመስሪያ
ራ ሂደት መሪ
የዲሲፕሊን ጥፋት እስከ የመጨረሻ ቤቱ ተወካይ ቀርቦ
ፊርማና
የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ከሆነ ሀሳብ ካለ መስቀለኛ ጥያቄ
ማህተም
ለስራ ሂደት መሪው ከባድ ከሆነ ይሰማል ይጠይቃል
ተደርጎበት
ለመስርያ ቤቱ የበላይ ሀላፊ
ለሰራተኛው
ይቀርባል፡፡
የውሳኔ አሰጣጥ ምልከታ
• በዚሁም ደንብ መሰረት የዲሲፕሊን
ስነስርዓቱ ከአዲስ አበባ ከተማ
መስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች
የዲሲፕሊን ስነስርዓት ጋር በአብዛኛው
ተመሳሳይ ነው፡፡
የዲሲፕሊን ስነስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ
ውስጥ በሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅት
ሰራተኞች
• የመንግት የልማት ድርጅቶች በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት
የስራ ግንኙነታቸው ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ የዲሲፕሊን ስነስርዓትን በተመለከተ
በደንብ ወይም አዋጅ የተገለፀ ባይኖርም አብዛኛዎቹም የመንግስት የልማት
ድርጅቶች የዲሲፕሊን ጉዳዮቻቸው በህብረት ስምምነቶች ውስጥ ይካተታል፡፡
• የህብረት ስምምነትም በአሰሪው መስሪያ ቤትና ስራ አመራር እና በሰራተኞች
ማህበር ይመሰረታል፡፡
• የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ ከሰራተኞች ማህበር እና ከመስሪያ ቤቱ የአመራር
አባላት በተውጣጣ ኮሚቴ ይተላለፋሉ፣ ይወስናሉ፣ የውሳኔው ሀሳብም ስልጣን
ለተሰጠው የስራ ሀላፊ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
• የስልጣን ውክልና ማኑዋል ያዘጋጁ መስርያ ቤቶች አሰራራቸው በዚህ ረገድ
የተቀላጠፈ እና ግልፅ የሆነ ይሆናል፡፡
በህብረት ስምምነት ስለሚሻሻሉ
ጉዳዮች
•ለሰራተኛው ይበልጥ
የሚጠቅም እስከ ሆነ ድረስ
በአዋጁ ላይ የተቀመጡ
ድንጋጌዎች በህብረት
ስምምነት ሊሻሻሉ ይችላሉ፡፡ (
አንቀፅ ፣ አዋጅ377/96)
ምዕራፍ ሁለት
ቅሬታ እና ይግባኝ
• ቅሬታ” ማለት የመንግሥት ሠራተኛ ከቅርብ አለቃው ወይም
ከሚመለከተው የሥራ ኃላፊ ጋር በሚያደርገው ውይይት ሊፈታ
ያልቻለና በመደበኛ የማጣራት ሂደት ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው
አቤቱታ ነው። ( የተሻሻለው የመንግሥት ሠራተኞች
የዲስፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ስርዓት መወሰኛ
ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር -75/2003 ዓ.ም)
• ቅሬታ ማለት የመንግስት ሰራተኛ ከቅርብ አለቃው ወይም
ከሚመለከተው የስራ ኃላፊ ጋር በሚያደርገው ውይይት ሊፈታ
ያልቻለ እና በመደበኛ የማጣራት ሂደት ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው
አቤቱታ ነው ( የፌደራል የመንግስ ሰራተኞች የዲሲፕሊን እና
የቅሬታ አቀራረብ ደንብ ቁጥ 77/94)
• 
የመንግስት ሰራተኞች የቅሬታ
ማስተናገጃ ስርዓት ዓላማ
• ለቅሬታዎች አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት፣
• ለቅሬታዎች መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉ
ስህተቶችንና ድክመቶችን በማረም እና
• ሁሉንም ሰራተኞች በእኩልነት ለማስተናገድ
የሚያስችልና ፈትሃዊ የሆነ አሰራር ለማስፈን
የሰመረ ግንኙነት እንዲዳብር ማድረግ ይሆናል፡፡
ቅሬታ የሚቀርብባቸው ሁኔታዎች
1. እንደ ፌደራል እና የአዲስ
አበባከተማ መስተዳድር የመንግስት
ሰራተኞች አዋጆች
ቅር የተሰኘ የመንግስት ሰራተኛ ቅሬታውን በሚከተለው
አግባብ ያቀረባል፡፡
(ሀ) ከህግችና መመሪያዎች አተረጓጎሞች ወይም
አፈፃፀም
(ለ) ከመብቶችና ጥቅሞች አጠባበቅ
(ሐ) ከስራው አካባቢ ጤንነትና ድህንነት ሁኔታዎች
(መ) ከስራ ምደባና ደረጃ አሰጣጥ
(ሠ) ከስራ አፈፃፀም ምዘና
….ቅሬታ የሚቀርብባቸው
ሁኔታዎች
• (ረ) በስራ መደቡ የስራ ዝርዝር ላይ ሸፈኑ
እንዲፈፀሙ ከሚሰጡ ተግባራት
(ሰ) በአለቆች ከሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ
(ሸ) ከዲሲፕሊን እርምጃ አወሳሰድ ወይም
(ቀ) የአገልግሎት ሁኔታዎችን ከሚመለከቱ
ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በሰል ደረሰብን
የሚል የመንግስት ሰጣተኛ ቅሬታውን
ለያቀርብ ይችላል፡፡
ቅሬታ የሚቀርብባቸው ጉዳዮች
እንደ አሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር
377/96
• ከስራ ማስወጣትን ጨምሮ በህብረት
ስምምነት ውስጥ የተካከተቱ ሌሎች
የዲሲፕሊን እርምጃዎች
ቅሬታ ሰሚ
• በየመስሪያ ቤቱ የሚቁዋቁዋሙ የቅሬታ
ሰሚ ኮሚቴ አባላት ከሰራተኞች
የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ይሰማሉ፡፡
ስለ ይግባኝ
• በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር እና የፌደራል የመንግስት
ሰራተኞች በመስሪያቤቱ የበላይ ኃላፊ ውሳኔ የተሰጠባቸውን
ጉዳዮች ተንተርሶ ከላይ ከሀ እስከ ቀ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ
ለአስተዳደር ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

• ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ለክልሉ የአስተዳደር ፍርድ ቤት


• ለፌደራል የመንግስት መስሪያቤት ሰራተኞች በፌደራል ሲቪል
ሰርቪስ የአስተዳደር ፍርድ ቤት
• ለመንግስታዊ የልማት ድርጅቶች እና በሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት
ለሚታየ ጉዳዮች የክልል የስራ ክርክር ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ማለት
ይቻላል፡፡
ተፈጸመ
• አዘጋጅ ዓለምሰገድ ሲሳይ
ወልደማርያም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ
የስራ ሂደት አስተባባሪ፡፡

• ( 2009 ዓ.ም)

You might also like