Professional Documents
Culture Documents
ሰላዚህ በሬጅመንቶች (ሠልጣኞች) ጠንካራ በሽታ የመከላከል ስራዎች ቀጣይና ተከታታይነት እንዲኖረው
በማዕከሉ እስታፍ እና ማሕበረሰብ እንዲሁም የባለጓዝ መኖሪያ ሰፈር ልክ እንደሬጅመንቶች ጠንካራ
በሽታ የመከላከል ስራ ለመስራት የሚታዩ አደናቃፊና ደካማ አስተሳሰብ ለመቅረፍ የተጀመረው የፅዳት
ዘመቻ ተጠናክሮ እና ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል የእስታፍ አመራርና የጤና ባለሙያ ቅንጅት አጠናክረን
መስራት ይጠበቅብናል፡፡
1.6 የእስክሪን ስራ
የሰላም ማስከበር እስክሪን በተመለከተ
ከዚህ በፊት እየሰራነው የመጣን ስራ ቢሆንም ቀላል የማይባሉ ግድፈቶች ሲያጋጥሙ እንደነበር
የቅርብ ትዝታችን ነው፡፡ስለሆነም ግድፈቶቹ የሚከሰቱት ከሞያተኛ እስከ አመራር እና አጠቃላይ
አባሉ የየራሱ ስራ ባለመስራትና የቅድመ ዝግጅት ባለማድረግ እንደ ሬጅመንት በአንድ ላይ ግር ብሎ
በመምጣትን አመራርም የሞያተኛ ስራ ነው ብሎ ችላ በማለት እና ትኩረት አለማድረግ በመጣደፍ
ወይም በሩጫ ሩጫ ሲሰራ ስለነበር የዶክመንት መጥፋትና ውጤት የመዛባት ሁኔታ አጋጥሞናል፡፡
ስለዚህ ሁሉም ሰው የየራሱ ስራ በመስራት ችግሮች እንዳይከሰቱ በታቀደ እና በፕሮግራም ብቻ
በመሄድ ችግሮች
በዚህ መሰረት ወደ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤታችን የሚገቡ የሰራዊት አባላት የሰላም ማስከበር
መምሪያ መሰረት ከክፍላቸው እስክሪን የተደረገላቸው የማረጋገጥ ስራ መስራት
የማረጋገጥ ስራ መስራት
የእስክሪን ስራ አጭር ዕቅድ ማውጣት
የእስክሪን ስራ እና የክትባት ስራ በአግባቡ መስራት
የእስክሪን ስራ በሚኖርበት ጊዜ ጊዜያዊ አደረጃጀት ማበጀት ማን ምን መሰራት
እንዳለበት በግልፅ ማስቀመጥ
ለሰላም ማስከበር ግዳጅ የሚሰማራው ብቁ የሆኑትና ብቁ ያልሆኑ የተሟላ ዳታ መያዝ
ስለ እስክሪን ስራ እና እስክሪን የተሰራላቸው ሰዎች የማረጋገጥ ስራ በመስራት ለጤና
ባለሞያዎች ግልፅ ኦረንቴሽን መስጠት
1.7 በሆስፒታል የሚሰጠው ሰርቪስ በተመለከተ
1.7.1 በተመላላሽ ህክምና በተመለከተ
በተመላላሽ የሚታከሙት ሳይጉላሉ በጊዜ ታክሞ ወደ ስልጠና እንዲመላለሱ ማድረግ
የሚሰጠው አገልግሎት በፍጥነት እንዲያገኙ ማድረግ
መሰረታዊ የስራ ሂደት በተቻለ ሁኔታ ማስቀጠል
የምርመራ ሁኔታ ዝግጁ ማድረግ
ለምርመራ አጋዥ የሆኑ ማቴሪያሎች መጠየቅና ማሟላት
ምሳሌ፡- በላቦራቶሪ
መድሃኒትና የማቴሪል እጥረት እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ
የመፍትሄ አቅጣጫ
የሪፖርት ስርዓት
ለት/ቤቱ ሎጀስቲክሲ በየሳምንቱ ያለው የጤና ሁኔታ በአካል ወይም በስልክ ሪፖርት ይደረጋል
የእለት አስተኝቶ የህክምና ሪፖርት በየቀኑ 3-4 ባለው ሰዓት በመከላከያ ስልጠና ዋና መምሪያ ለጤና
አገልግሎት ሪፖርት ይደረጋል፡፡
ሃሙስ እለት በየሳምንቱ ሪፖርት ለሎጀስቲክሲ ፅ/ቤት ይላካል፡፡
ወርሃዊ ሪፖርት ሎጀስቲክሲ ፅ/ቤት ወር በገባ በ 20 ኛው ቀን ለስልጠና መምሪያ ወር በገባ በ 25 ቀን
ይደረጋል
ወር ሪፖርት ወር በገባ 15-20 ም/አዛዥ ሎጀስቲክስ ፅ/ቤት እና 15-20 በስልጠና ዋና መምሪያ
ለጤና አገልግሎት ሪፖርት ይላካል
የማሰልጠኛ የጤና አገልግሎት በተቀመጠለት ፕሮግራም መሰረት የተለያዩ የጤና ማበልጸግና በሽታ
የመከላከል ስራዎችን በፎርማቱ መሰረት የወር ሪፖርት የሚላክ ይሆናል፡፡
የኮንቲንጀንት ማ/ት/ቤት 2013 በጀት ዓመት የ 1 ኛ ሩብ ዓመት ዝርዝር ስራዎች
የጊዜ ሰሌዳ