You are on page 1of 53

እንካDን ወደ ክዋኔ ኦዲት

ስልጠና በደህና መጣችሁ!!!


ክፍል I
የክዋኔ ኦዲት
መሠረተ ሃሳብ
አጠቃላይ የስልጠናው ዓላማ
ሰልጣኞች የክዋኔ ኦዲት መሰረተ ሀሳቦችን
እንዲገነዘቡ ማድረግ ነው፡፡
ዝርዝር ዓላማ

ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኋላ ፡-


 የክዋኔ ኦዲት ፅንሰ ሀሳብን በትክክል ይገልጻሉ፣
 የክዋኔ ኦዲት ዓላማ እና ወሰንን ሙሉ ለሙሉ ይለያሉ፣
 የክዋኔ ኦዲት ደረጃዎችን በተሟላ መልኩ ይተገብራሉ፣
 የክዋኔ ኦዲት እና የፋይናንስ ኦዲት አንድነት እና ልዩነት
ያውቃሉ፣
የክዋኔ ኦዲት ታሪካዊ አመጣጥ
 ለክዋኔ ኦዲት መፈጠር ዋነኛ ምክንያት የመንግሥት ወጪዎች መጨመርና
የመንግሥት ተጠያቂነት እና የወጪ አፈጻጸም ውጤታማነት ላይ የሕዝብ
ተጠያቂነት ለማስፈን የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ጥያቄዎቹም፡-
 የመንግስት ወጪ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ፋይዳ እያሳካ
ነውን?
 የመንግስት ወጪ ውጤታማ ነውን? ለታለመለት ዓላማስ በብቃት
እየዋለ ነውን ?
 በመንግስት ኃላፊዎች ላይ ከፍተኛ የተጠያቂነት ደረጃ አለን?
 በልማድ ሲሰሩ የቆዩ ኦዲቶች ይህንን አይነት መረጃ ይሰጣሉን?
የሚሉት ናቸው፡:
የክዋኔ ኦዲት ታሪካዊ አመጣጥ የቀጠለ
በዚሁ መሰረት፡-
 የክዋኔ ኦዲት እ.ኤ.አ ከ1960ዎቹ ጀምሮ ትኩረት እያገኘ መጥቶና
በ1970ዎቹ በጥቂት የምዕራባዊያን አገሮች ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ በአደጉ
እና በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡
 የክዋኔ ኦዲት በሙያ ማሕበር ደረጃ የታወቀው በ1990ዎቹ ነው፡፡
/AFROSAI-E / SADCOSAI regions/
 አገራችን እ.ኤ.አ ከ1992 ጀምሮ በፍደራል ዋናው ኦዲተር መ/ቤት
ተጀምሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥቂት የመንግሥት መ/ቤቶችና ክልሎች
ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል፡፡
The Southern African Development Community Organization of Supreme
Audit Institutions
የመወያያ ጥያቄ

ክዋኔ ኦዲት ምን
ዓይነት/ በምን ላይ
የሚያተኩር ኦዲት ነው?
የክዋኔ ኦዲት ትርሜዎች
Definition of performance auditing

የክዋኔ ኦዲት በተለያዩ ዓለም አቀፍ የኦዲት


ተቋማት ትርጓሜ የተሰጠው ቢሆንም ትርጓሜው
መሰረታዊ የሆኑ ልዩነቶች የሉትም፡፡
የክዋኔ ኦዲት ትርሜዎች የቀጠለ
በINTOSAI /International Organization of Supreme
Audit Institutions/ የተሰጠው ትርጓሜ ፡-
ክዋኔ ኦዲት ማለት የኢኮኖሚ፣ የብቃት እና የውጤታማነት ኦዲት ሲሆን
ኦዲት ተደራጊ አካላት ውስን ሀብታቸውን በመጠቀም ዓላማቸውን
ስለማሳካታቸው ለማረጋገጥ የሚካሄድ ኦዲት ነው ፡፡

“Performance auditing is an audit of the economy,


efficiency and effectiveness with which the audited
body uses its resources to achieve its goals.”
ወይም

"ኦዲት ተደራጊ አካላት ትክክለኛ ስራ በተሻለ መንገድ እየሠሩ


ነውን
የክዋኔ ኦዲት ትርሜዎች የቀጠለ
በፌደራል የውስጥ ኦዲተሮች የክዋኔ ኦዲት' የክዋኔ ኦዲት ደረጃ
እና የአሠራር መመሪያዎች ማንዋል የተሰጠ ትርጓሜ፡-
ክዋኔ ኦዲት መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ መ/ቤቶች
ፕሮግራሞቻቸውን፣ ፕሮጀክቶቻቸውን፣ የሥራ አመራር የአሰራር
ሥርዓቶቻቸውን እና ተግባራቶቻቸውን በጥልቀት በመመርመር
ባሉዋቸው ግብዓቶች ተጠቅመው በኢኮኖሚ፣ በብቃት እና
በውጤታማነት /Economically, Efficiently,
Effectively/ ማከናወናቸው የሚረጋገጥበት ኦዲት ነው፡፡
በአጠቃላይ አገላለጽ የክዋኔ ኦዲት፡-
 ለመንግስት ተቋማት ዓላማ ማስፈጸሚያ የሚመደበው የህዝብ
ሀብት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚገባውን ጠቀሜታ በተገቢ ሁኔታ
ማስገኘቱን ለማረጋገጥ የሚከናወን ኦዲት ነው፡፡
 ገንዘብ ሊያስገኝ የሚገባው ጠቀሜታ ማለት:-
ተቋማት ለሥራ የሚያውሉት ሃብት በኢኮኖሚ፣ በብቃት እና
ውጤታማ በሆነ መልኩ የአካባቢ እንክብካቤ ተጠብቆ በጥቅም ላይ
ማዋል ሲሆን የሚገኘው ጥቅም ለተግባሩ ከሚወጣው ወጪ
የሚበልጥ ነውን ? የሚሉትን በአዋነታዊነት የሚመልስ ነው፡፡
የክዋኔ ኦዲት መመዘኛ ነጥቦች
/ሶስቱ ኢዎች /THE THREE Es

 ቁጣባ /ECONOMY/
 ብቃት / EFFICIENCY/
 ውጤታማነት /EFFECTIVENESS/
የክዋኔ ኦዲት መመዘኛ ነጥቦች የቀጠለ
1. ቁጠባ /ECONOMY
 ተግባሩን ወይም የተመረጠውን እንቅስቃሴ ለማከናወን ጥቅም ላይ
የዋለው ግብዓት በተፈለገው የጥራት ደረጃ ሆኖ በተሻለ ወይም
አነስተኛ ተወዳዳሪ ዋጋ መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣
 ጥራት ግምት ውስጥ ሳይገባ አነስተኛ ዋጋ በራሱ ብቻውን በጣም
የተሻለ አድርጎ መውሰድ አይቻልም፡፡
 አነስተኛ የጨረታ ዋጋ መውሰድ በቂ የማይሆንበት ሁኔታ አለ፡፡
ምክንያቱም ተጫራቾች የሚመሳጠሩበት ሁኔታ በመኖሩ፡፡
የክዋኔ ኦዲት መመዘኛ ነጥቦች የቀጠለ
2. ብቃት / EFFICIENCY
 የግብዓትን እና የውጤትን ትስስር የሚያሳይ ሆኖ በተወሰነ የግብዓት መጠን
ከፍተኛ ውጤት መገኘቱ የሚለካበት ነው፡፡
/Relationship between inputs and outputs /
 በከፍተኛ ሁኔታ ሀብትን አሟጦ መጠቀም ነው፡፡

/Optimum utilization of resources/


 ከሀብት አጠቃቀም የተሻለ ምርታማነት ማስገኘት ነው፡፡
/Obtaining best productivity from resources/
የክዋኔ ኦዲት መመዘኛ ነጥቦች የቀጠለ ብቃት
 ያለን ግብዓት ተጠቅሞ ከፍተኛውን ውጤት ማስገኘትን ነው፡፡
/Maximizing outputs from given inputs / ወይም
 የምንጠቀመውን ግብአት በመቀነስ ጥራቱ ሳይጓደል የሚጠበቀውን
ውጤት ማግኘት ነው፡፡
/Minimizing inputs to obtain given outputs/ without
sacrificing quality
 በአጠቃላይ ተግባራትን በተሻለ አማራጭ ማከናወን ነው፡፡
/Doing things well/
የክዋኔ ኦዲት መመዘኛ ነጥቦች የቀጠለ

3. ውጤታማነት /EFFECTIVENESS
መ/ቤት፣ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክት ወይም ዓላማዎች ግብ መምታታቸውን
እንዲሁም በመ/ቤቱ በተገኘ ፋይዳ እና ሊገኝ በታሰበ ፋይዳ መካከል

ያለው ግንኙነት ነው፡፡

 የታለመው ግብ ስለመምታቱ የሚዳሰስበት ነው::

/Achieving pre determined objectives/


የክዋኔ ኦዲት መመዘኛ ነጥቦች የቀጠለ ውጤታማነት
ውጤታማነትን የምናይባቸው የተለያዩ እይታዎች ፡-
 ተቋማዊ ውጤታማነት /Organizational
effectiveness
 የፕሮግራም ውጤታማነት /Program
effectiveness
 የዋና ዋና ተግባራት ውጤታማነት /Operational
effectiveness
የክዋኔ ኦዲት መመዘኛ ነጥቦች የቀጠለ ውጤታማነት

ውጤታማነትን መለካት አስቸጋሪ የሚያደርጉ ጉዳዮች፡-


 ግቦች በአግባቡ ለመለካት በሚያስችል መልኩ ተለይተው
ካልተቀመጡ፡፡ /Objectives may not be well defined
 አንዳንዴ በየትኛው ደረጃ /በውጤት ወይስ በፋይዳ /አፈጻጸሙ
መለካት እንዳለበት ግልጽ የማይሆንበት ሁኔታ መኖሩ ፡፡
 ፋይዳን ለመገምገም ረዘም ያለን ጊዜ ስለሚጠይቅ ፡፡
ጥያቄ?
በቁጠባ፣ በብቃት እና
በስኬት መካከል ምን ዓይነት
ትስስር አለ?
በቁጠባ፣ በብቃት እና በስኬት መካከል ያለ
ትስስር

 ቁጠባ አንድን ውጤት ለማምጣት/ ለማሳካት ጥቅም ላይ


የሚውል ግብዓት ነው፡፡
 ብቃት ደግሞ ግብዓትን ተጠቅሞ የሚከናወን ተግባር/
አፈጻጸም ነው፡፡
 ስኬት በቁጠባ እና በብቃት ትስስር የሚገኝ/ የሚመጣ
ለውጥ/ ፋይዳ ነው፡፡
THE 3 E’S

Economy Efficiency Effectiveness

Maximising Achieving
Minimising
OUTPUT/ intended
INPUT
INPUT effects at
costs
relatios low cost
THE FULL INPUT-OUTPUT
MODEL

Goals

Activities at
Input Output Effects
the auditee

Effectiv
Economy Efficiency
eness
በቁጠባ፣ በብቃት እና በስኬት መካከል ያለ ትስስር
ግብዓት/ Inputs

ብቃት/ Efficiency

ስኬት/ Outcomes

ፋይዳ/ Impact
በቁጠባ፣ በብቃት እና በስኬት መካከል ያለ ትስስር የቀጠለ

1. ግብአት /INPUTS
ውጤትን /Outputs/ ለማምጣት የምንጠቀመው ሃብት
/Resources ሲሆን

ይህም ገንዘብ ፣ ቁሳቁስ /Materials፣ የሰው ሀብት /Human


resources፣ መረጃ /Information/ data እና የመሳሰሉትን
ያካትታል፡፡
ኦዲተሮች ኢኮኖሚን /‘economy’ ሲመረምሩ ግብአቶች የተገኙት በጣም
ባነሰ ወጪ ነውን የሚለውን መልስ ለመስጠት ነው፡፡
were inputs obtained at the most economical cost?
በቁጠባ፣ በብቃት እና በስኬት መካከል ያለ ትስስር
የቀጠለ

2. ውጤት/OUTPUTS
ግብአትን በመጠቀም ያመረትናቸው /ያገኘናቸው ዕቃዎች ወይም
አገልግሎቶች / Goods and services produced by utilizing the
inputs / ሲሆኑ ይህም ት/ቤቶች / የተገነቡ የመማሪያ ክፍሎች፣
የተዘረጉ መንገዶች፣ የተሰጠ የስልክ አገልግሎት እና የተሰጠ የኦዲት
አገልግሎት እና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
ኦዲተሮች የብቃት ምርመራ ሲያከናውኑ / ‘efficiency’/ ውጤት
ለማስገኘት በስራ ላይ የዋለው ግብአት አጠቃቀም ከፍተኛ
ምርታማነት ስለመስጠቱ ለማረጋገጥ ነው፡፡
were inputs used most productively to produce the outputs?
በቁጠባ፣ በብቃት እና በስኬት መካከል ያለ ትስስር
የቀጠለ

3. ስኬት/ ፋይዳ /OUTCOMES/ IMPACTS


የተመረቱ የዕቃዎች እና አገልግሎቶች ትክክለኛ በሆነ ውጤት ነው፡፡ Actual
results of the goods and services produced (outputs) ይህም
የሚገለጽበት በ% ነው፡: /አዳዲስ ክህሎት የጨበጡ ሰዎች፣ ስራ ያገኙ ሰዎች፣
ቤተሰቦቻቸውን መርዳት የቻሉ ሰዎች፣ የአየር ብክለት መጠን ፣ በአየር ውስጥ
የ CO መጠን ፣ የመተንፈሻ አካል ችግር /ህመም/ ያጋጠማቸው ሰዎች ፣
የማጭበርበር ድርጊት ጉዳዮች እና የተጭበረበረ የገንዘብ መጠን
ኦዲተሮች ውጤታማነትን ሲመረምሩ /effectiveness:/ የተቋሙ ግቦች ከላይ
በምሳሌነት በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ መሳካታቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡
were organizational objectives in the above areas being met?
የክዋኔ ኦዲት ዓላማ
Objectives of Performance Audit

 ለህዝብ ተጠያቂነትን ማሳደግ እና ጠብቆ ማቆየት ፣


 የለውጥ ኃይል በመሆን ጠቃሚ የሆኑ ለውጦች በሀብት
አስተዳደር ላይ እንዲመጣ እና ገንዘብ ሊያስገኝ የሚገባውን
ጠቀሜታ እንዲያስገኝ ማስቻል፣
 በመንግስት ተቋማት የማሻሻያ ሥራዎች አስፈላጊ
መሆናቸውን እና ወጪ ቆጣቢ ሊሆኑ እንደሚገባ ማሳወቅ ፣
የክዋኔ ኦዲት ዓላማ የቀጠለ

 ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው ተቋማት ለሌሎች በአርአያነት ሊያገለግሉ


እንዲችሉ እድል መፍጠር /ጥሩ ተሞክሮዎችን ማስፋት/ ፣
 በዋና ዋና አካባቢዎች /የሀብት አስተዳደሮች ላይ/ ስለ ሶስቱ ኢዎች
ነጻ የሆነ የማረጋገጥ እና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 ኦዲት ተደራጊ አካላት ማሻሻል የሚገባቸው የአሰራር ሥርአቶች ላይ
የማሻሻያ እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታታት እና መምከር ነው፡፡
የክዋኔ ኦዲት ዓላማ የቀጠለ

ተጠያቂነት / ACCOUNTIBILITY
 ተጠያቂነት ለተሰጠ ኃላፊነት ተገቢ ምላሽ መስጠት
ሲሆን ይህም በጥቂቱ ሁለት አካላትን ያሳትፋል::
ኃላፊነት የሚሰጥ እና ሀብትን
የሚመድብ አካል

ይህንን ኃላፊነት ተቀብሎ የሚፈጽም እና


ስለተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት የማቅረብ
ግዴታ ያለበት አካል
የክዋኔ ኦዲት ዓላማ የቀጠለ
 የተጠያቂነት ግንኙነት ACCOUNTABILITY RELATIONSHIPS

የተወካዮች
ምክር ቤት

ዋና ኦዲተር የሚኒስትሮች
መ/ቤት ምክር ቤት

የውስጥ
ገ/ኢ/ት/ሚ
ኦዲት
የክዋኔ ኦዲት ዓላማ የቀጠለ
የመንግስት ወጪ እና ተጠያቂነት
መንግስት የህዝብን ሃብት በምን አይነት መንገድ እያስተዳደረ መሆኑን እና
የመንግስት ወጪ ሥርዓት የሚመራበትን ሁኔታ ማወቅ ለዜጎች በጣም ወሳኝ
ጉዳይ ነው፡፡
 የተወካዮች ም /ቤት የመንግስትን ወጪ እና ፕሮግራም ያጸድቃል፡፡
 መንግሥት የጸደቀውን በጀት ተግባር ላይ የማዋል እና የጸደቀው በጀት በምን ሥራ
ላይ እንደዋለ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ፡፡
በመሆኑም የተወካዮች ም/ቤት ላጸደቀው በጀት በመንግሥት በኩል ሥራ ላይ ውሎ
ስለአፈጻጸሙ የሚቀርብለት መረጃ ተአማኒ እና የተሟላ መሆኑን በክዋኔ ኦዲት
እንዲረጋገጥ ያደርጋል፡፡
አፈጻጸምን በኦዲት የማረጋገጥ ኃላፊነት

የመንግሥት ተቋማት አፈጻጸም ን የማረጋገጥ ኃላፊነት


በዋናነት፡-
 የዋናው ኦዲተር መ/ቤት እና
 በመንግስት ተቋማት ውስጥ የተደራጁ የውስጥ ኦዲት
የሥራ ክፍሎች ነው፡፡
እነኚህ አካላት የፋይናንስ፣ የሕጋዊነት እና የክዋኔ የኦዲት
አይነቶችን በማከናወን ያረጋግጣሉ፡፡
የፋይናንስ ኦዲት / Financial Audit
 መንግሥት ተገቢ የሆነ የሂሳብ መዝገቦች አሉትን? በአግባቡ
ምዝገባ ያከናውናልን? የፋይናንስ መረጃዎች በትክክል
ይቀርባሉን ?
 ኦዲተሮች የሂሳብ መግለጫዎችን /Financial
statements/ በመመርመር የሂሳብ መግለጫዎቹ
በትክክል የመ/ቤቱን የፋይናንስ አቋም የሚያሳዩ
ወይም የማያሳዩ መሆናቸውን በማረጋገጥ የኦዲት
አስተያየታቸውን የሚሰጡበት የኦዲት ዓይነት ነው፡፡
የአሠራር ሕጋዊነት ኦዲት/ Compliance Audit

 መንግስት የሚሰበስባቸውን ገቢዎችም ሆነ የሚያወጣቸውን


ወጪዎች የሚያስተዳድረው በሥራ ላይ በዋሉ ሕጎች እና
የአሠራር ሥርዓቶች መሰረት ነውን ?
 ኦዲተሮች ኦዲት ተደራጊ አካላት ተግባራቶቻቸውን
ሲያከናውኑ ፓሊሲዎችን፣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን
እና የአሠራር ሥርዓቶችን ተከትለው ስለመፈጸማቸው
የሚያረጋገጡበት የኦዲት አይነት ነው፡፡
የፋይናንስ እና ኮምፒሊያንስ ኦዲት ትኩረቶች

 በሂሳብ መግለጫዎች ላይ አስተያየት መሰጠትን ፣


 የህጎች፣ ደንቦች እና ሥርዓቶች መከበርን ማረጋገረጥ፣
 የማጭበርበር ድርጊት ጉዳዮችን መለየትን፣
 የፋይናንስ እንቅስቃሴ /Financial Transactions/ በተመለከተ
የቀረቡ የቁጥጥር /Control/ ሪፖርቶችን እና
 የገቢ አሰባሰብ እና አጠባበቅ በተመለከተ የሚቀርቡ ሪፖርቶችን
ማረጋገጥ ላይ ነው፡፡
የፋይናንስ እና ኮምፒሊያንስ ውስንነቶች

የፋይናንስ እና የሕጋዊነት ኦዲት ተግባራት ፡-


 የተጠበቀው ውጤት መገኘቱን½
 የሀብት ብክነት መኖሩን እና
 የሀብት አጠቃቀሙ በብቃት መሆኑን መረጃዎችን መስጠት
አለመቻላቸው ነው፡፡
ይህም የክዋኔ ኦዲት ሃሳብ እንዲፈልቅ ምክንያት ሆኗል፡፡
የክዋኔ ኦዲት /Performance Auditing/

 የክዋኔ ኦዲት ለየት ያለ ዓላማ ኖሮት የሚከናወን ኦዲት ነው፡፡

 የክዋኔ ኦዲት የተለያዩ ችግሮችን ለመድረስ የሚያስችል ኦዲት

ነው፡፡

 በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደየአገራቱ ሁኔታ የክዋኔ ኦዲት ሂደት ላይ

የተወሰኑ ልዩነቶች ቢኖሩም በዋና መሰረተ ሃሳቡ ላይ ልዩነት

የለም፡፡
የክዋኔ ኦዲት የተለያዩ ስያሜዎች

 የክዋኔ ኦዲት /Performance audit


 ገንዘብ ሊያስገኝ የሚገባው ጠቀሜታ /Value-for-money audit
 የተጠቃለለ ኦዲት /Comprehensive audit
 የሥራ አመራር ኦዲት /Management audit
 አራቱ ኢዎች /4Es audit
 የኦፕሬሽን ኦዲት /Operations audit በሚል ስያሜ በተለያዩ አገራት
ይጠራል፡፡

እነኚህ የተለያዩ ስያሜዎች ቢኖሩቱም ኦዲተሮች የሚመረምሩት


ክንውንን /Performance/ ነው፡፡
የክዋኔ ኦዲት እና የፋይናንስ ኦዲት አንድነት
/SIMILARITIES/
ሁለቱም የኦዲት ተግባራት፡-
 የፋይናንስ መረጃዎችን ይጠቀማሉ፣
 የኦዲት አሠራር ሂደትን እና የኦዲትን ዕቅድን ይከተላሉ፣
 የኦዲት ደረጃዎችን /Auditing standards/ ጠብቀው ይከናወናሉ፣
 የነጻነትን እና የብቃት መርህን ይከተላሉ፣
 መረጃን መሰረት ያደርጋሉ፣
 ተጠያቂነትን ማስፈን ላይ ትኩርት ይሰጣሉ፡፡
የክዋኔ ኦዲት እና የፋይናንስ ኦዲት ልዩነት
የፋይናንስ ኦዲት የክዋኔ ኦዲት
 የፋይናንስ እንቅስቃሴ ተኮር ነው፡፡  ግብ ተኮር ነው፡፡ /Objectives
/Transactions oriented oriented
 የሂሳብ መግለጫዎችን /Financial  ማናቸውንም የኦዲት ተደራጊ አካላት
statement/ መመርመርን እና ህጉን ተግባራት ከኢኮኖሚ፣ ከብቃት፣
ተከትሎ ስለመከናወኑ ያረጋግጣል፡፡ ከውጤታማነት እና ከአካባቢ ጥበቃ
 ተቋሙ ያለበትን የፋይናንስ አቋም አከያ ያላቸውን ክንውን ከህጎች መከበር
በተመለከተ አስተያየት ይሰጣል፡፡ በዘለለ ሁኔታ ይመረምራል፡፡
/Opinion on financial position  አፈጻጸምን ለመለካት አመላካቾችን
 አመላካቾችን /Indicators/፣ /Indicators/፣ መስፈርትን
መስፈርትን /Standards/ እና /Standards/ እና ሊደረስበት የሚገባ
ሊደረስበት የሚገባ ግብን /Targets ግብ / Targets / ይጠቀማል፡፡
አይጠቀምም፡፡  በአብዛኛው የተገኘው ጥቅም እና
 በአብዛኛው ጊዜ የተገኘው ጥቅም እና ያስከተለው ወጪ ትንተና /Cost-
ያስከተለው ወጪ ትንተና /Cost- benefit analysis/ ላይ ትኩረት
benefit analysis/ ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡
አያደርግም፡፡
የክዋኔ ኦዲት እና የፋይናንስ ኦዲት ልዩነት
የፋይናንስ ኦዲት የክዋኔ ኦዲት
 የተለዩ ተጠቃሚ ቡድኖችን /Target  የተለዩ ተጠቃሚ ቡድኖቸን /Target
groups/ በተመለከተ አስተያየት groups/ በተመለከተ የእያንዳንዱ
አይሰጥም ፡፡ ቡድን ተጠቃሚነት ጭምር በመለየት
ይገመግማል፡፡
 የማሻሻያ ሥራዎችን በተመለከተ  የማሻሻያ ሥራዎችን በተመለከተ
የመፍትሄ ሃሳብ አይሰጥም፡፡ የመፍትሄ ሃሳብ ያስቀምጣል፡፡
/Improvements/
 በአብዛኛው በመጠን /Quantitative  በአብዛኛው በጥራት ደረጃ
የሚገለጽ ነው፡፡ /Qualitative/ የሚገለጽ ነው፡፡
 የፋይናንስ ዳታዎችን ይጠቀማል ፡፡  የፋይናንስ ነክ እና የፋይናንስ ነክ
ያልሆኑ ዳታዎችን ይጠቀማል፡፡
 ያለፉ፣ አሁን በመደረግ ላይ ያሉ እና
 በአብዛኛው ያለፉ ዳታዎችን
ወደፊት ሊደረጉ የታቀዱ
ይጠቀማል፡፡
አፈጻጸሞች ላይ ያተኩራል፡፡
የክዋኔ እና የፋይናንስ ኦዲት ይዘቶች
የክዋኔ ኦዲት የፋይናንሺያ ኦዲት
ዓላማው የኦዲት ተደራጊ አካላት ክንውን ሶስቱን የሂሳብ መግለጫዎች እውነተኛ እና ሚዛናዊ
ኢዎች ስለሟሟላቱ ለማረጋገጥ ነው፡፡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ /Fair and
True/
መነሻው ሊኖሩ ይችላሉ የሚባሉ ችግሮችን መነሻ በየዓመቱ በመደበኛነት የሚከናወን ነው፡፡
ያደርጋል፡፡
ትኩረቱ ተቋም፣ ፕሮግራም እና ተግባራት ላይ የፋይናንስና የማኔጅመንት አሰራር
ነው፡፡ ስርአቶች ላይ ነው፡፡
የሚጠይቀው የተለያዩ የሙያ መስኮች /ኢኮኖሚክስ፣ አካውንቲንግ
የትምህርት ፖለቲካል ሳይንስ፣ ሶሾሎጂ …..ወዘተ)
ዘርፍ
የሚከናወንበ ከፕሮጀክት ፕሮጀክት ይለያያል፡፡ ወጥ በሆነ መስፈርት ይከናወናል፡፡

ዘዴ
የሚከናወንበ ለእያንዳንዱ ኦዲት የተለየ መስፈርት ከሁሉም ፋይናንስ ኦዲት ጋር የተጣጣመ
ት መስፈርት ይዘጋጃል፡፡ ወጥ የሆነ መስፈርት ይጠቀማል፡፡
ሪፖርት የተለያያ አይነት አደረጃጀት አለው፡፡ ወጥ የሆነ አደረጃጀት ይከተላል፡፡
ሪፖርቱ የሚወጣበት ጊዜ ወጥነት የሚወጣው በመደበኛነት ወቅቱን ጠብቆ
የለውም፡፡ ነው፡፡
የክዋኔ ኦዲት ክፍሎች
የክዋኔ ኦዲት በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
 በተመረጡ አካባቢዎች ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ምርመራ
(Selective investigation)፣
 ሰፋ ባለ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ምርመራ (Major
broad-based investigation)፣
 የአስተዳደር ሥራ ደረጃዎችን በመፈተሽ የሚደረግ ዋና ምርመራ፣
 አነስተኛ የሆነና ያልታቀደ ምርመራ (Small scale, adhoc
investigation)
የክዋኔ ኦዲት ጥቅሞች
የክዋኔ ኦዲት ዋና ዋና ጥቅሞች፡-
 የፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶች፣ ዓላማዎች እና ግቦች ግልፅነትን፣
 በሁሉም ደረጃ የሚዘጋጁ የዕቅድ አወጣጥ ጥራትን፣
 የፀደቁትን ዕቅዶች ለማስፈጸም የመ/ቤቱ ሥልጣን እና ግልፅነትን፣
 ከፀደቀው ዕቅድ አንፃር ፕሮግራሞችን በጥራት እና በብቃት
ማስፈጸምን፣
 የውስጥ አስተዳደር እና የአፈፃፀም ሪፖርት አቀራረብ ጥራትን እና
 ከተቀመጠለት ዋጋ እና ከሌሎች ዓላማዎች ጋር ሲነፃፀር የተገኘው
የውጤት ጥራት ማስገኘት ናቸው፡፡
በአፈጻጸም የሚገጥሙ ችግሮች

 የክዋኔ ኦዲት መሠረተ ሀሳብ ትርጉም ላይ የግንዛቤ ችግር መኖሩ


እና ተጠያቂነትን ለመለየት ያለው ችግር፣
 መረጃን የማግኘት እና በሕግ የተደገፈ ስልጣን ስለመኖሩ ያለማወቅ፣
 ወጥነት ያለው የተዘጋጀ መስፈርት አለመኖር ይኸውም የክዋኔ
ኦዲት የሚያተኩርባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች፣ ፕሮግራሞች እና
ተግባራት በመሆናቸው ኦዲተሩ እንደ ሥራው ባህሪ መስፈርት
ለማዘጋጀት የሚያስችል ክህሎት ሊኖረው ይገባል፡፡
የክዋኔ ኦዲት ውስንነቶች
 የውስጥ ኦዲቱ በመንግሥት በወጡ ሕጐች መሠረት መ/ቤቱ ምን
ያህል ዓላማውን እንዳሳካ የማየት መብት የተሰጠው ቢሆንም
ማንኛውንም የመንግሥት ሁኔታ/ አሠራር ለመመርመር አለመቻሉ፡፡
 መንግሥት ምን ማድረግ እንዳለበት የሚወሰነው በሕዝብ በተመረጡ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡ /በውስጥ ኦዲት አይደለም/
 ስለዚህም የውስጥ ኦዲቱ የፖሊሲ ዓላማዎችን ጥቅም ጥያቄ ውስጥ
ሊያስገባ አይችልም፡፡
የክዋኔ ኦዲት ውስንነቶች የቀጠለ
ይሁን እንጂ፡-
 የፖሊሲ ዓላማዎችን አስመልክቶ ወደ ውሳኔ የሚወስዱ ክስተቶችን፣
ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን፣
 ዓላማዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጡ ዘዴዎችን፣
 ዓላማዎቹ ምን ያህል እንደተሳኩ፣
 ያልታሰቡ ወይም ተቃራኒ ውጤቶችን ጨምሮ ሌሎች የፖሊሲ
ውጤቶችን ከመመርመር የሚያግደው አይሆንም፡፡
የኦዲት ደረጃዎች (Audit Standards)

የውስጥ ኦዲት
ደረጃዎች ምንድን
ናቸው?
የኦዲት ደረጃዎች (Audit Standards) የቀጠለ

 የኦዲት መለያ የሆኑ ባህሪያትን የሚገልጹ እና የአልግሎቱ


አፈጻጸም የሚለካባቸ ው የጥራት መስፈርቶች ናቸው።
በዚህ የስልጠና ክፍል ስለ አጠቃላይ ደረጃዎች፣ ስለ መስክ ሥራ
ደረጃዎች እና ስለ ሪፖርት ደረጃዎች በአጭሩ
እንመለከታለን፡፡
አጠቃላይ ደረጃዎች /General Standards/

አጠቃላይ ደረጃዎች ኦዲተሩ ኦዲቱን ሲያከናውን በብቃት፣ በቅልጥፍና


እና በስኬታማነት ለማከናወን እንዲችል የሚፈለግ ሙያዊ ስነ ምግባር
ነው፡፡
 የሙያ ነፃነት /Independence and Objectivity/
 የሙያ ብቃት /Proficiency/
 ተገቢ ጥንቃቄ ስለማድረግ /Due Professional Care/
 የጥራት ቁጥጥርን ማረጋገጥ /Quality Control Assurance/
ይይዛል
የመስክ ሥራ ደረጃ /Field work Standard/

የመስክ ሥራ ደረጃዎች ዓላማ ኦዲተሩ ሊከተላቸው የሚገባ ምክንያታዊ፣


ሥርዓታዊ እና ሚዛናዊ ደረጃዎች ወይም ድርጊቶች መስፈርት ወይም
አጠቃላይ ማዕቀፍ ለመመሥረት ነው፡፡
የመስክ ሥራ ደረጃ በሥሩ ፡-
 ሥራን ማቀድን፣
 መ/ቤቱን መረዳትን፣
 የኦዲት አቀራረብ እና ዘዴን፣
 የኦዲት መስፈርትን ይይዛል፡፡
የሪፖርት ደረጃዎች
የሪፖርት ደረጃዎች ኦዲተሩ የኦዲት ውጤቱን ሪፖርት
የሚያቀርብበት አሠራር ሲሆን የኦዲት ሪፖርቱን ቅርፅና ይዘት ምን
መሆን እንዳለበት የሚገልፅ ነው፡፡
የኦዲት ሪፖርት አራት የኦዲት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም፡-
 የሪፖርት የቅርፅ ደረጃ፣
 የሪፖርት ይዘት ደረጃ፣
 የሪፖርት ጥራት ደረጃ እና
 የሪፖርት ስርጭት ደረጃ ናቸው፡፡
አመሰግናለሁ!!!

You might also like