You are on page 1of 44

ታህሳስ /20067ዓ.


 ክፍል አንድ፡
 መግቢያ፣ ማኑዋሉ አስፈላጊነት፣ የማኑዋሉ ዓላማ፣ የማኑዋሉ
ይዘቶች፣ የተፈጻሚነት ወሰን፣ የማኑዋሉ አጠቃቀምና የሚጠበቁ
ውጤቶች
 ክፍል ሁለት
 የለውጥ ሥራ አመራር መሳሪያዎች ጽንስ ሃሳባዊ ማዕቀፍ
 ክፍል ሶስት
 ስትራቴጂን ወደ ፈፃሚ አካላት የማውረድ ምንነት እና የማውረጃ
ዘዴዎች
 ክፍል አራት
 የሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና ሥርዓት የትግበራ ደረጃዎች /Steps/
እና የአተገባበር ሞዴል /Template/

2
መግቢያ
 በከተማችን በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት ተግባራዊ
ሲደረግ የቆየው የለውጥ ስራ ተስፋ ሰጪ ጅምር ዉጤት
ያስገኘ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ስር-ነቀል ተቋማዊ
ለውጥን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡
 ስለሆነም በከተማችን ልማት እና መልካም አስተዳደርን፣
የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን ለማጎልበት እና አገራዊ
ራዕይ እዉን ለማድረግ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮችን በቅደም
ተከተል በማስቀመጥ እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት
እንዲግባቡበት በማድረግ ስር ነቀል ተቋማዊ ለዉጥ
የማረጋገጥ ጥረት አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡

3
 በተለይም የBSC ስርዓትን በተሟላ መልክ ለመፈጸም ከደረጃ ሰባት እስከ
ዘጠኝ ባሉት የትግበራ ደረጃዎች የአፈፃፀም ችግሮች ተስተውለዋል፡፡
• በደረጃ ሰባት የስኮር ካርዱን ዕቅድና ሪፖርት አውቶሜት አድርጎ ቀጣይነት ባለው
መልኩ ተግባራዊ ያለማድረግ፣
• በደረጃ ስምንት ስኮር ካርዱ ኬዝ ቲም ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ መቅረቱና እስከ
ፈፃሚ ግለሰብ ካስኬድ አለመደረጉ፣
• እንዲሁም በደረጃ ዘጠኝ የምዘና ስርዓቱ በማዕከል ደረጃ እስከ ስራ ሂደት፤ በክፍለ
ከተማና በወረዳ ደረጃ እንደ ጽ/ቤትና በትምህርትና በጤና ተቋማት እንደ ተቋም
ብቻ የሚካሄድና እስከ ግለሰብ ድረስ ያልወረደ መሆኑ እና የዕውቅናና ሽልማት
ስርኣቱም ከምዘናው ውጤት ጋር በማያያዝ በመመሪያ የተደገፈ አልነበረም፡፡
 በመሆኑም ይህንን የማስተግበሪያ ማኑዋል ለማዘጋጀት በሚዛናዊ ስራ አመራር
ስርዓት የተሻለ ተሞክሮ ካላቸዉ ከከተማ ልማት፣ ቤቶች እና ኮንስትራክሽን
ሚኒስቴር እንዲሁም ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ተሞክሮ
ለመዉሰድ ተችሏል፡፡ በዚሁ መሰረትም ከከተማ ልማት፣ ቤቶች እና
ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተገኘዉ ልምድ እንዴት ስኮር ካርዱን እስከ ግለሰብ
ድረስ ማዉረድ እንደሚቻል የተወሰደ ሲሆን ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና
ምዝገባ ጽ/ቤት የግለሰብን የእለት ተዕለት አፈጻጸም እንዴት ኦቶሜት ማድረግ
እንደተቻለ በተሞክሮ ተወስዷል፡፡

4
 የከተማአስተዳደሩ ቀልጣፋና ውጤታማ የአሰራር
ስርዓቶችን በመዘርጋት የተለያዩ የለውጥ
መሳሪያዎችን አቀናጅቶ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
ይህንንም ስራ ውጤታማ በሆነ መልክ ለመምራትና
ለመፈጸም እንዲሁም ግቦችንና ስትራቴጅን ወደ
ፈጻሚ አካላት የማውረዱን ስራ በተገቢው ቅደም
ተከተል ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ
ለማከናወን የሚያሥችል የማስፈጸሚያ ማኑዋል
ባለመኖሩ የማኑዋሉን ዝግጅት አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡

5
 የዚህ ማኑዋል ዋና ዓላማ ከላይ እስከታች
በአስተዳደሩ ስር ያሉ ሴክተሮች በሚዛናዊ ሥራ
አመራርና ምዘና ስርዓት የተጣሉ ግቦችን በየደረጃው
ለሚገኙ ፈጻሚ አካላት በተሟላ ሁኔታ ማውረድ
የሚቻልበትን ስርዓት በመዘርጋት ለአፈጻጸም
ክትትል፤ ግምገማና ምዘና ስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር
ነዉ፡፡

6
ዝርዝር ዓላማዎች
 ስትራቴጂን ወደ ፈጻሚ አካላት ማውረድ( cascading) ምንነት
እና በጽንሰ ሃሳቡ ዙሪያ ግንዛቤ በማዳበር የማንዋሉን አጠቃቀም
ቀላል ለማድረግ፤
 ግቦችንና ስትራቴጂዎችን በየደረጃው ለሚገኙ ፈጻሚ አካላት
የማውረድ እና የምዘና ስራውን ውጤታማ በሆነ መልክ
ለመምራት/ለማካሄድ፤
 የካስኬዲኒግ ስራ በተለያዩ ተቋማት ሊከናወን የሚችል በመሆኑና
እንደ ተቋሙ ግንዛቤ፤ ደረጃና የአጠናን ዘዴ የሚለያይ ስለሚሆን
ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት ለመከተልና የተቀላጠፈ አሰራር
ለመፍጠር፤
 የካስኬዲኒግን የአሰራር ሂደት የአንድ የስራ ሂደት ግቦች በመውሰድ
እንዴት እስከ ግለሰብ ፈጻሚ ሊወርድ እንደሚችል በምሳሌ
በማሳየት በከተማው አስተዳደር ስር በሚገኙ ተቋማት
የሚደራጀው የካስኬዲንግ ቡድን ይህን ተከትሎ ስራውን
እንዲያከናውን ለማስቻል ነው፡፡
7
 የለውጥ ሥራ አመራር መሳሪያዎች (BPR እና BSC ) ላይ ያለው
ግንዛቤ ይዳብራል፤
 ሰራተኞች ስለ ተቋማቸዉ ራዕይ፤ ተልዕኮ፤ እሴቶችና
ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ግንዛቤ ይኖራቸዋል፤
 በአቅም ግንባታ ቢሮ በስራ ሂደት ደረጃ ከተዘጋጀው ካስኬዲንግ
ሞዴል በመነሳት ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ ሴክተር ቢሮዎች፣
ተቋማት፣ ግቦቻቸውንና ተግባሮቻቸውን ለፈጻሚዉ ካስኬድ
የማድረጉን ስራ ያከናዉናሉ፤
 ፈጻሚዎች በተቋማቸዉ እና በግለሰብ ደረጃ የተቀመጡትን
ግቦች በመረዳት ለግቦቹና ለዒላማዎች መሳካት ያላቸው
አስተዋጽኦ ያድጋል፤
 ስትራቴጂ ተኮር ተቋማት (Strategy Focused
Organizations) እና ለውጤት የሚሰሩ ሰራተኞች ይፈጠራሉ፡፡
8
የተፈጻሚነት ወሰን
 በዚህ ስትራቴጂን እስከ ግለሰብ የማውረጃ እና ማስተግበሪያ ማኑዋል
መሰረት የሚዛናዊ ስራ አመራር እና ምዘና ስርዓት አጥንተዉ ወደ ትግበራ
የገቡ በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ተቋማት እና ፈጻሚዎች ይጠቀሙበታል፡፡

የማኑዋሉ አጠቃቀም
 ይህ ማኑዋል በሚዛናዊ ሥራ አመራርና ምዘና ስርዓት ጥናት
የተለዩትን ግቦችና ስትራቴጂዎች እንዴት ወደ ፈጻሚ አካላት
ማውረድ እንደሚቻል በምሳሌ (Template) በማስደገፍ እና
የተለያዩ የለውጥ ስራ አመራር መሳሪያዎችን አንድነትና ልዩነት
በማስቀመጥ በተገቢ ማብራሪያዎች በመደገፍ በቅደም ተከተል፤
ግልጽና ለአጠቃቀም ቀላል በሆነ መልኩ የቀረበ በመሆኑ ማንኛውም
የካስኬዲንግ ሥራ እንዲያከናውን የተመደበ ቡድን ተረድቶት
የካስኬዲንጉን ሥራ ማከናወን እንዲያስችለው ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

9
 ይህ ማኑዋል አራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን ፤ ክፍል አንድ መግቢያ፤
ዓላማ፤ የሚጠበቁ ውጤቶች፤ የተፈጻሚነት ወሰንና የማኑዋሉ
አጠቃቀም የሚሉ ይዘቶች ሲኖሩት፤ ክፍል ሁለት የለውጥ ሥራ
አመራር መሳሪያዎች ትርጓሜና አጠር ያለ ጽንሰ ሀሳብ የያዘ
ሲሆን ይህም በስራ አመራር መሳሪያዎቹ ዙሪያ ያለውን ብዥታ
በማጥራት ግልጽነትና የጋራ ግንዛቤ እንዲኖር በማስቻል
የማኑዋሉን ዝግጅት ለመምራት ያስችላል ተብሎ የተካተተ ነው፡፡
ክፍል ሦስት የካስኬዲንግን (ግቦችንና ስትራቴጂዎችን ወደ ፈጻሚ
አካላት ማውረድ) ምንነትና የማውረጃ ዘዴዎች በንድፈ ሃሳብ
ደረጃ የሚተነትን ሲሆን ክፍል አራት ዋናው የማኑዋሉ አካል
በመሆኑ በከተማችን የሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና ሥርዓት
ለመዘርጋት መከተል የሚገባንን የአሰራር ሂደት ቅደም ተከተል
በምሳሌነት አንድ የስራ ሂደት በመውሰድ የሚተነትን ነዉ፡፡

10
ሀ. መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ /BPR/
መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት ስርነቀል የአሰራርና
የአደረጃጀት ስርዓት በመዘርጋት አገልግሎቶችን በተመጣጠነ ወጪ፣
ጥራት፣ መጠንና ፍጥነት በማቅረብ እመረታዊ የአፈጻጸም ለውጥ
ለማምጣት የሚያስችል የሥራ አመራር መሳሪያ ነው፡፡
ለ. የሚዛናዊ ሥራ አመራርና ምዘና ስርዓት /BSC/
የሚዛናዊ ሥራ አመራርና ምዘና ስርዓት ማለት የተቀናጀ
የስትራቴጂያዊ እቅድ ሥራ አመራር፤ የተግባቦትና የአፈጻጸም
መለኪያ ስርዓትን አጣምሮ የያዘ የለውጥ መሳሪያ ነው፡፡ ሚዛናዊ ስራ
አመራር ስርዓት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፣ እነዚህን
ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ለመተግበር የሚያስችሉ ግቦችን ለይቶ
የሚያስቀምጥ፣ ግቦቹ በምክንያትና በውጤት ተሳስረው እንዴት
እሴት እንደሚፈጥሩ የሚያሳይ፣ የተቋምን ስኬት እንዲያረጋግጡ
የተቀረጹ ግቦች እንዴት እንደሚለኩ የሚያሳይና ለግቦች
የተቀመጠላቸውን ዒላማ ለማሳካት የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ
እርምጃዎች የሚቀረጹበትን አግባብ የሚያስቀምጥ የለውጥ
መሳሪያ ነው፡፡
11
 በተለያዩ የሥራ አመራር ምሁራን እንደተገለጸው ለሁሉም ተቋማዊ የአሠራር
ችግሮቻችን ምላሽ የሚሰጥ አንድና የተዋጣለት ብቸኛ የሥራ አመራር
መሳሪያ እንደሌለ ነው፡፡ እያንዳንዱ የሥራ አመራር መሳሪያ የራሱ የሆኑ
መሠረታዊ መነሻ፣ ይዘትና ባህርይ ያለው በመሆኑ በአንድ ተቋም ውስጥ
የሚገኙትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በተሟላ ደረጃ ለማቃለልና ለመፍታት የራሱ
እጥረት/ውስንነት ይኖረዋል፡፡ ከዚህ እውነታ መገንዘብ የሚቻለው ብቸኛ
የሆነ የሥራ አመራር መሳሪያ ይዞ ውጤታማ መሆን እንደማይቻል ነው፡፡
በመሆኑም እንደተቋማዊ የአሠራር ችግሮቻችን ዓይነትና ብዛት እንዲሁም
ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት በማድረግ የተለያዩ የለውጥ ሥራ አመራር
መሳሪያዎችን አቀናጅቶ መጠቀም የበለጠ ውጤታማ ሊያደርግ እንደሚችል
በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡
 በልምድ ልውውጥ ወቅት የተመለከትናቸው ተቋማት የተጠቀሟቸው የሥራ
አመራር መሳሪያዎች እንደሚያመለክቱት መሳሪያዎቹ ዕርስ በዕርሳቸው
እንዲደጋገፉ በማድረግ ወይም በማቀናጀት መጠቀማቸው
ለውጤታማነታቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ለመረዳት ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዋማት ከፍ ብሎ የተገለጹትን የለውጥ
ሥራ አመራር መሳሪያዎች ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በተሟላ
መልኩ አቀናጅቶ መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
12
በሚዛናዊ ስራ አመራር ሥርዓት የግንባታ ደረጃዎች ሥራ ከተጠናቀቀ
በኋላ የተዘጋጁትን ግቦችና ስትራቴጂዎች ተግባራዊ የማድረግ ሥራ ቀጣዩ
አብይ ተግባር ነው፡፡ በተለይ ደረጃ ስምንት/Cascading/ ከፍተኛ ግምት
የሚሰጠው ተግባር ይሆናል፡፡
1. ስትራቴጂን ወደ ፈጻሚ አካላት የማውረድ ምንነት
ስትራቴጂን በየደረጃው ላሉ አካላት ማውረድ ሲባል የተቋሙን
ስትራቴጂ ሁሉም ፈፃሚ አካላት ተገንዝበውት የዕለት ተዕለት ሥራቸው
እንዲያደርጉት ማስቻል ነው፡፡
በየደረጃው የሚገኙ አካላት ለስትራቴጂው ስኬታማነት የበኩላቸውን
ድርሻ ሊያበረክቱ ይችሉ ዘንድ ስለስትራቴጂው ሙሉ ግንዛቤ መፍጠርን፣
ስትራቴጂውን ሲወስዱ ስትራቴጂያዊ ትስስሩን ጠብቀው
ለስኬታማነቱም ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ መሆናቸውን ማረጋገጥ
ያጠቃልላል፡፡
ስትራቴጂ በየደረጃው ላሉ አካላት የሚወርደው በስትራቴጂያዊ ግቦች
አማካይነት ነው፡፡ ስትራቴጂን የሚያወርደው አካል /የካስኬዲንግ ቡድን/
የተቋሙን ስትራቴጂያዊ ግቦች መሠረት በማድረግ ለሚያዘጋጃቸው
ግቦች መለኪያዎችን፣ ዒላማዎችንና እንዳስፈላጊነቱ ስትራቴጂያዊ
እርምጃዎችን ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

13
የተቀረጹትን ስትራቴጂዎች ወደ ፈፃሚ አካላት ማውረድ
ስትራቴጂዎቹን ስኬታማ ለማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ይኸውም፡-
የተቋሙን ራዕይ የጋራ በማድረግ ስትራቴጂውን በየደረጃው
የሚገኙ ፈፃሚዎች የዕለት ተዕለት ተግባር እንዲያደርጉት፣
ስትራቴጂ ተኮር የሆነ የሥራ ባህል ለመገንባትና እያንዳንዱ
ፈፃሚ አካል የመጨረሻውን ተቋማዊ ውጤት እያሰበ
እንዲሰራ ለማድረግ፣
ማበረታቻና ሽልማትን ከስትራቴጂያዊ ውጤት ጋር
ለማያያዝና ሠራተኞች ውጤት ባመጣ ምን አገኛለሁ /
what is in it for me? / በማለት ለሚያነሱት ጥያቄ
ምላሽ ለመስጠት፤
የተቋሙን ስትራቴጂ በመመንዘር በየደረጃው ካሉ ግቦችና
መለኪያዎች ጋር እንዲተሳሰሩ ለማስቻል፡፡
14
በተቋም ደረጃ የተዘጋጀን ስትራቴጂ በየደረጃው ለሚገኙ ፈፃሚ
አካላት ለማውረድ በሚከተሉት ተያያዥነት ባላቸው ሶስት ዘዴዎች
መሰረት ይወርዳል፡፡ እነዚህም ስትራቴጂውን ማስረጽ /Spiritual
Cascading/፣ ግቦችን ለፈፃሚ አካላት ማውረድ /Physical
Cascading/ እና ውጤትን ከሽልማት ጋር ማያያዝ /Reward/
በመባል ይታወቃል፡፡
ሀ. ስትራቴጂውን ማስረጽ ወይም የትምህርትና ተግባቦት ሥራ
በየደረጃው የሚገኙ አካላት በሴክተሩ እና በተቋሙ ደረጃ
የተዘጋጁትን ስትራቴጂዎችንና ስለስትራቴጂዎቹ አዘገጃጀት
አስፈላጊውን መረጃና ትምህርት በመስጠት ጠለቅ ያለ ውይይት
በማካሄድ ስትራቴጂውን በእምነት፣ በዕውቀትና በባለቤትነት ስሜት
ካልተቀበሉት ሥራዎችን ቆጥረው ቢወስዱም እንኳ በተሳካ ሁኔታ
ይፈጽሙታል ለማለት ያስቸግራል፡፡ በመሆኑም የተቋሙን ራዕይና
ስትራቴጂ በሠራተኞች ዘንድ ማስረጽ የለውጥ ሃይሎችን
ለማፍራት እና ለመጠቀም የሚያስችል ስትራቴጅን ወደ ፈጻሚ
አካላት የማዉረጃ ዘዴ ነዉ፡፡
15
 በሚዛናዊ ስራ አመራር ሥርዓት ትምህርትና ተግባቦት ማለት
የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ግንዛቤን ለመፍጠር
የሚረዱ ጭብጦችን በጹሁፍ፣ በስብሰባ እንደዚሁም በተለያዩ
የመገናኛ ዘዴዎች ማስተላለፍ ነው፡፡ የተግባቦት ሥራው ሥርዓቱ
ለምንና እንዴት እንደሚተገበር ማሳወቅን፣ በዕቅዱ የሚፈቱ
ችግሮችን፣ በሥራ አመራር ሂደትና በሠራተኛ አስተዳደር ረገድ
ዕቅድ የሚኖረውን ፋይዳ እና ተቋሙ ሊያመጣ የሚገባውን ለውጥ
ለመላው ፈፃሚ ኃይል ማሳወቅን ያጠቃልላል፡፡ በተጨማሪም
የሚከተሉትን የተግባቦት ሥራዎች በየወቅቱ ማከናወን
ያስፈልጋል፡፡
 ስኬትን ማብሰር
 የአፈፃፀም ውጤት ማሳወቅ

 ስትራቴጂያዊ እርምጃዎችን ማሳወቅ

 የፈፃሚዎችን ልቦናና አዕምሮ መግዛት

ይህንንም ለማድረግ፡-
16
i. መሰረታዊ የስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን መወሰን
 ተቋማት ስትራቴጂያቸውን በተቀናጀና በተጣጣመ መልኩ
ለማሳካት ይችሉ ዘንድ ከፈፃሚዎቻቸው፣ ከተገልጋዮቻቸውና
ከባለድርሻ አካላት ጋር የትምህርትና ተግባቦት ስራ
የስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን ወስነው መስራት ይገባቸዋል፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሚከተሉትን ማከናወን ተገቢ ይሆናል፡፡
 የአመለካከት ክፍተቶችን መለየትና መሙላት፣
 የሠራተኛውን የስራ ተነሳሽነትና ዝግጁነት ማሻሻል፣
 በለውጥ መሳሪያዎች ዙሪያ የፈፃሚዎችንና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ
ማሳደግ ፣
 የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል፣
 የመረጃ አገልግሎት ስርዓት ማሻሻል፣
 የቡድን ስራ ባህል ማሻሻል፣
 የICT አጠቃቀምን ማሳደግ፣
 የፈፃሚውን አቅም ማሳደግ፣

17
ii. ስልቶችን መንደፍ
የተግባቦት ስልቶች የሚባሉት ፈፃሚውን
ይበልጥ ግልጽ አድርጎ ለማሳመን የሚያገለግሉ
ውጤታማዎቹ መልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች
ናቸው፡፡ በመሆኑም በዕቅድ ዝግጅት ላይ ብቁ
ስልቶች በመንደፍ በዋነኛነት ፈፃሚውን
በማሳወቅ፣ በማሳመንና ወደ ተግባር ሊያስገባ
የሚያስችል ስልት የመንደፍ ጉዳይ ነው፡፡
 የውይይት መድረክ ዝግጅት
 የጉብኝትና ተሞክሮ ልውውጥ ዝግጅት

 ፖስተሮች

 የድህረ-ገጽ አገልግሎት

 መጽሔት

 የአንድ ለአምስት አደረጃጀት

18
ለ. ግቦችን የማከፋፈል ሥራ (Physical Cascading)
 ግቦችን ለፈጻሚ ማከፋፈል በዋናነት በሁለት ደረጃዎች
የሚከናወን ይሆናል፡፡
 ለሥራ ሂደቶች እና ኬዝ ቲሞች ማውረድ
 ሁለተኛው ለግለሰብ ፈፃሚዎች ማውረድ ነው፡፡
 የተቀረፁ ግቦችን መሰረት በማድረግ እንደተቋሙ
ተጨባጭ ሁኔታ የሚወሰን የካስኬድንግ ቡድኖችን
ማደራጀት ያስፈልጋል፡፡ የካስኬድንግ ቡድኑ ስትራቴጂውን
የእያንዳንዱ ፈፃሚ አካል የዕለት ተዕለት ተግባር ለማድረግ
በሚያስችል መንገድ ሊደራጅና ሊሰራ ይገባል፡፡
 ስትራቴጂውን ወደ ፈፃሚ አካል የማውረድ ኃላፊነት
በዋናነት የእያንዳንዱ የሥራ ሂደት ሲሆን አጠቃላይ
የማውረድ ሥራው ከተቋሙ አመራር ጋር በመሆን
የሚሰራ ነው፡፡
19
i. ለሥራ ሂደቶች እና ኬዝ ቲሞች ማውረድ
 በሴክተር ቢሮ ደረጃ የተዘጋጁት ስትራቴጂያዊ ግቦች ትስስሩን /Alignment/
በጠበቀና ባጣጣመ መልኩ ለስራ ሂደቶች እና ኬዝ ቲሞች መዉረድ አለባቸዉ፡፡
በስራ ሂደት ወይም በኬዝ ቲም ደረጃ የሚቀረጹ ግቦች የተቋሙን ስትራቴጂያዊ
ግቦች የማስፈጸም ወይንም የመደገፍ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ ይህ ስትራቴጂያዊ
ዕቅድም ወደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ዕቅድ የሚመነዘር መሆን ይኖርበታል፡፡
i i. ለግለሰብ ፈፃሚዎች ማውረድ
 ግለሰብ ፈፃሚዎች በኬዝ ቲም ደረጃ የተቀመጡትን ግቦች መነሻ በማድረግ
የራሳቸውን ዕቅድ ያዘጋጃሉ፡፡ በግለሰብ ፈፃሚ የሚዘጋጀው ዕቅድ የሚከተሉትን
ሊያካትት ይገባል፡፡
 ፈፃሚ ግለሰቡ የሚሰራበት ቢሮ /የስራ ሂደት/ የቀረጻቸውን ግቦች ያሳካ
ዘንድ ከግለሰቡ የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ፣
 በቢሮ //የስራ ሂደት/ ወይም በተቋም ደረጃ የተቀመጡ ስትራቴጂያዊ
እርምጃዎች /ልዩ ኘሮጀክቶች እንዲፈጸሙ ለግለሰቡ ሊሰጥ የሚችለውን
ሃላፊነት፣
 የግለሰቡን አቅም ለማሳደግ ግለሰቡ ከራሱ የሚጠበቁ የአቅም ግንባታ
ሥራዎች /Self Development Plan/ ዕቅድ ሊይዝ ይገባል፡፡ ይህም
ግለሰብ ፈፃሚዎችን የማብቃት ዕቅድ በኮምፒውተር አጠቃቀም፣ ዕቅድ
አዘገጃጀት፣ ሪፖርት አፃፃፍ፣ ወዘተ ዙሪያ ሊሆን ይችላል፡፡
20
 የግለሰብ ፈፃሚዎች ዕቅድ ከተቋሙና ከስራ ሂደቱ
ስትራቴጂ ጋር ተናቦ መዘጋጅቱ የሚከተሉት
ጠቀሜታዎች ይኖሩታል፡-
 ስለ ስትራቴጂው በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና
ለተግባራዊነቱ በተነሳሽነትና በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ
ያስችላቸዋል፤
 ግለሰቦች ዕቅዳቸውን ሲያዘጋጁ የተቋሙና የሥራ
ክፍላቸው ውጤት ተኮር ዕቅዶች ያላቸውን ትስስር
አጥርተው እንዲያዩትና እንዲፈጽሙት ይረዳቸዋል፤
 እያንዳንዱ ፈፃሚ/ግለሰብ ከስትራቴጂው አንፃር እሴት

የሚጨምሩ ተግባራት ላይ እንዲያተኩር ያደርገዋል፡፡

21
ሐ. ውጤትን ከእውቅናና ሽልማት ጋር ማያያዝ (Recognition and
Reward)
 ማበረታቻን /እውቅናና ሽልማት/ ከውጤት ጋር ማያያዝ
የተቋሙ ስትራቴጂ በሠራተኞች ዘንድ ትኩረት
እንዲያገኝና ተግባራዊ እንዲሆን ያስችላል፡፡
 የሚዛናዊ ስራ አመራር ስርዓት የአሠራር ባህልን የመቀየር
ዓላማ ያለው እንደመሆኑ መጠን ማበረታቻዎቹ ከግቦች
መሳካት ጋር መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የማበረታቻ ስርዓት
ሲዘረጋ በቢሮ፣ በተቋም፣ በስራ ሂደትና ግለሰብ ፈፃሚ
ደረጃ ሥርዓቱ በትክክል መዘርጋቱን ማረጋገጥና
ፍትሃዊነቱን ማየት ይጠይቃል፡፡
 ለዚህም የዙሪያ መለስ ምዘናንና የሚዛናዊ ስራ አመራርና
ምዘና ሥርዓትን በጥምረት በመተግበር ሠራተኞች
ከሚሰጣቸው ግብረ መልስ በመነሳት ራሳቸውን፣ የሥራ
ባልደረቦቻቸውንና ተቋማቸውን እንዲያውቁና እንዲረዱ
ብሎም የባህሪ ለውጥን እንዲያመጡ ማገዝ ይገባል፡፡
22
 በባላንስድ ስኮር ካርድ ጥናት የትግበራ ምዕራፍ
/Implementation Phase/ ሶስት ደረጃዎች
ማለትም የአውቶሜሽን ሥራ /ደረጃ ሰባት/፣
ስትራቴጂያዊ ግቦችን በየደረጃው ላሉ ፈፃሚ
አካላት /እስከ ግለሰብ ድረስ/ የማውረድ ሥራ /ደረጃ
ስምንት/ እና የአፈፃፀም የክትትል ግምገማና ምዘና
ሥራዎች /ደረጃ ዘጠኝ/ አንዳሉ ይታወቃል፡፡
 የአውቶሜሽን ደረጃን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ኢኮቴል ኤጀንሲ አማካይነት ተሰርቶ የሚጠናቀቅ
ይሆናል
23
 ስትራቴጂን ከተቋም እስከ ግለሰብ ፈፃሚዎች በየደረጃው
ማውረድን፣ ራስን የማብቃት እቅድን ማዘጋጀትና
የትግበራ ደረጃዎችን ያጠቃለለ ሲሆን በትግበራው
የለውጥ ሥራ አመራር መሳሪያዎች ተሳስረውና
ተመጋግበው በሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ በምሳሌ
በማስደገፍ ለማመልከት ተሞክሯል፡፡

 በዚህም መሠረት የተዘጋጁትን ስትራቴጂያዊ ግቦች


እንዴት ከተቋም እስከ ፈፃሚ ግለሰብ ድረስ መውረድ
እንዳለባቸው በቢሮ፤ በስራ ሂደትና ኬዝ ቲም እንዲሁም
በግለሰብ ደረጃ ስትራቴጂንና ተግባርን ማውረድ
እንደሚቻል በምሳሌ በማስደገፍ ለአተገባበር ቀላል በሆነ
ሁኔታ በደረጃዎች በመለየት ቀርቧል፡፡
24
 የከተማአስተዳደሩ ባላንስድ ስኮር ካርድ ጥናት እስከ
ደረጃ ዘጠኝ የተጠናቀቀ በመሆኑ ቀጣዩ ወደ ተግባር
የመለወጥ ስራ ነው፡፡ ለዚህም የተዘጋጀውን ስትራቴጂ
ለመተግበር ሁሉም ፈፃሚ አካላት ማለትም በከተማ
አስተዳደሩ ስር ያሉ ቢሮዎች/ተቋማት
የየድርሻቸውን ሊወሰዱና ባላንስድ ስኮር ካርድ
ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡

25
 የሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና ሥርዓት /BSC/
ስትራቴጂያዊ ግቦችን ከስትራቴጂያዊ ዕቅድ
ኘሮግራሞችና ኘሮጀክቶች ጋር የማናበብ ሥራ ከላይ
እንደተገለጸው በስትራቴጂያዊ እርምጃዎች ደረጃ ላይ
የተከናወነ ቢሆንም በግብ ደረጃ የማናበቡ ሥራ ግን በዚህ
ደረጃ የሚሰራ ይሆናል ማለት ነው፡፡

 ሁለቱን ስትራቴጂያዊ ሰነዶች በግብ፣ በተቋምና በስራ


ሂደት ደረጃ ተመጋጋቢና ተናባቢ ለማድረግ ቀጥሎ
የተዘረዘሩትን ጉዳዮች ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

26
1. ለየቢሮው በተለዩት ሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና ሥርዓት
ትራቴጂያዊ ግቦች ሥር ሊወድቁ የሚችሉትን የቢሮውን ስትራቴጂያዊ
ዕቅድ /SPM/ ግቦች ስትራቴጂዊ እርምጃዎች ደረጃ ላይ ከተሰራው
ጋር በተናበበ ሁኔታ መለየትና በሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና ሥርዓት
ስትራቴጂያዊ ግቦች ስር ማስቀመጥ ሲሆን ይህም በስትራቴጂያዊ ዕቅድ
ሰነድ ቀደም ብሎ ለግቦች የተቀመጠውን ዒላማ /Target/ እንዳለ
በመጠበቅ የሚፈጸም ይሆናል፤
2. በመቀጠልም በተቋም ደረጃ ከሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና
ሥርዓት /BSC/ ግቦች ጋር የተጣጣሙት /የተናበቡት ተቋማዊ
ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ግቦች በስራቸው ላሉ የሥራ ሂደቶችና ኬዝ
ቲሞች የማከፋፈል ሥራ ይከናወናል ፡፡

3. ለድጋፍ ሰጪ የሥራ ክፍሎች ልክ እንደ ዓላማ አስፈፃሚ ወይም ዋና


የስራ ሂደቶች ከተቋሙ ውጤት ተኮር ሥርዓት የሚመለከታቸውን
ግቦች በቀጥታ በማውረድ ከተልዕኮአቸው አንፃርና የዓላማ አስፈፃሚ
ተቋማትና የስራ ሂደትን ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት
ከሚቀርጿቸው ግቦች ጋር አጣጥሞ የራሳቸውን ሚዛናዊ ስራ አመራር
ሥርዓት ሰነድ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፤

27
4. በሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና ሥርዓት /BSC/ ግቦች
ስር የሚወድቁት የየኘሮግራሙ የስትራቴጂዊ ዕቅድ ግቦች
የBSC የግብ አጣጣልን ሥርዓት የተከተሉ እንዲሆኑ
ማድረግ ይገባል፤ ይህም ማለት ቀጣይ ሂደትን የሚያሳዩና
ድርጊት ተኮር መሆን ይኖርባቸዋል፤

5. በዚህ መሠረት የሚዛናዊ ስራ አመራርና ምዘና


ሥርዓት /BSC/ እና የስትራቴጂክ ዕቅድ ሰነዶች በዚህ
መልክ ተናበውና ተመጋግበው የተቋሙን አላማዎች
ለማሳካት በሥራ ላይ እየዋሉ የሚቆዩ ይሆናል፡፡

ቅፅ 001

28
 የግቦችን አፈፃፀም ለመከታተልና ለመመዘን ከላይ
እንደተገለጸው በአራቱ መለኪያዎች ማለትም በመጠን፣
በጊዜ፣ በበጀት/ወጪና በጥራት ዒላማ መቀመጡን ማረጋገጥ
ይገባል፡፡ ይህን ለመስራት በቅድሚያ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮችን
ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

1. ግቦችን ከስትራቴጂያዊ ጠቀሜታቸው አንፃርና የተቋምን፤


የስራ ሂደትንና የኬዝ ቲምን ስትራቴጂያዊ አላማ ከማሳካት
ረገድ ባላቸው ድርሻ በቅደም ተከተል ለይቶ የመቶኛ
ክብደት /Weight/ መስጠት
2. በጠቀሜታቸው ደረጃ ለተለዩትና በቅደም ተከተል
ለተቀመጡ ግቦች በክብደታቸው መሠረት በጀትን ማከፋፈል
ነው፡፡
29
ለግቦች የመቶኛ ክብደት ለመስጠት የሚከተሉትን መነሻ
መስፈርቶች ማጤን ያስፈልጋል፡፡
ሀ.የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ሰነድን መነሻ በማድረግ የግቡን የሥራ
ስፋት እና የሚወስደውን ጊዜ በመለየት፣
ለ. በስራ ሂደቱና ኬዝ ቲሙ ስር ለተጣሉት ግቦች ስትራቴጂያዊ ማኘ
በማዘጋጀት ተመጋጋቢነታቸውንና የምክንያት ውጤት ትስስራቸውን
በመለየት የትኛው ግብ ወሳኝ ሚና እንዳለው በመለየት፣
ሐ. የትኛው ግብ የቢሮና የተቋም አላማ ለማሳካት የበለጠ ሚና
እንደሚጫወት ሙያዊ ትንታኔ በመስጠት፣
መ. ከላይ በተጠቀሱት የስራ ሂደቶችና ኬዝ ቲሞች በየራሳቸው ተጨባጭ
የሥራ ሁኔታ ግቦችን በስትራቴጂያዊ ጠቀሜታቸው ለመለየት
በሚያስቀምጡት ተጨማሪ መስፈርቶች መሠረት በቅደም ተከተል
ለተለዩ ግቦች የመቶኛ ድርሻ ይሰጣሉ፡፡
ሠ. ከዚህም በተጨማሪ አንድ የስራ ሂደት፤ኬዝ ቲም ከሌላ ጋር በጋራ
የሚፈጸሙ ግቦች ካሉት ከላይ በቀረቡት መስፈርቶች መሠረት ለጋራ
ግብ የመቶኛ ድርሻ በመስጠት ግቡን በውጤት ተኮር ተግባራት
በመከፋፈል ከግቡ ጠቅላላ ክብደት የየራሳቸውን የመቶኛ ድርሻ
ለይተው ይወስዳሉ፡፡
30
ሀ.የስትራቴጂያዊ ግቡን ወጪ ለመገመት የሚከናወኑ ዝርዝር
ተግባራትን ለይቶ ወጪያቸውን ማስላት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ
ከዝርዝር ተግባራት የወጪ ግመታ የግቡን የወጪ ግምት ከታች
ወደ ላይ እያሰሉ በመሄድ የግቡን ወጪ ማስቀመጥ፣
ለ.ግቡን ለማስፈጸም ለተቀመጡ ኢላማዎች የሚያስፈልጉ
ግብአቶች አይነትና መጠን በመለየት፣
ሐ.ከቢሮ፣ ሥራ ሂደቱ ወይም ኬዝ ቲም ተልዕኮ አንፃር ግቦች
ያላቸው ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታና የተሰጣቸው የመቶኛ ድርሻ
ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣
መ.የጋራ ወጪዎች /ለምሳሌ የስቴሽነሪ ወጪ ስልክ ወዘተ/
ለአንድ ግብ ተብሎ የግቡ በጀት ስሌት ውስጥ ሳይገባ ነገር ግን
የተለየ የህትመት ወጪ ሆኖ ለአንድ ግብ ተለይቶ የሚታወቅ
ከሆነና የበጀትን ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ ከሆነ በግቡ ወጪ ስሌት
ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ግብዓት አይነትና መጠን ላይ ተመስርቶ
የሚሰራ ይሆናል፡፡
31
ለአራቱ መለኪያዎች፡- ለመጠን፤ ለጊዜ፣ ለበጀት/ወጪና ጥራት የሚሰጥ
የመቶኛ ድርሻ
የቢሮ፣ የስራ ሂደቱንና ኬዝ ቲሙን አፈጻጸም ለመከታተልና
ለመመዘን 4ቱን መለኪያዎች ማለትም መጠን፤ ጊዜ፣
በጀት/ወጪና ጥራትን መጠቀም ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት በእነዚህ
መለኪያዎች አፈጻጸምን ለመመዘን እያንዳንዳቸው የተለያየ
ክብደት ሊኖራቸው ይገባል፡:
ምክንያቱም በመጠን የተቀመጠ ኢላማና አፈጻጸም ከጊዜ
ወይም ከወጪ ወይም ከጥራት መለኪያዎች ጋር በእኩል ክብደት
ሊለካ ስለማይገባ ነው፡፡ ይህን ከግንዛቤ በመውሰድ 4ቱ
መለኪያዎች የተለያየ የመቶኛ ድርሻ/ክብደት/ እንዲኖራቸው
ተደርጓል፡፡
ቅፅ 003

32
 ይህ ደረጃ ለስራ ሂደትና ኬዝ ቲም የወረዱ ስትራቴጂያዊ ግቦች
በውጤት ተኮር ተግባራት ተመንዝረው ወደ ፈጻሚ ግለሰብ ደረጃ
እንዴት መድረስ እንዳለባቸው የምናይበት እና የግለሰብ ፈጻሚዎችን
ድርሻ በመለየት የተግባሮቹን አፈጻጸም በሚቀመጡት መለኪያዎች
መሰረት በመከታተልና በመለካት ግለሰብ ፈጻሚው ከ50 በመቶ
የሚመዘንበት ነው፡፡ ይህን ለማስፈጸም የሚከተሉትን ንዑስ
ደረጃዎች ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

ሀ. የግቦች ዋናዋና ዉጤት ተኮር ተግባራት መለየት


 የግቦችን ዋናዋና ዉጤት ተኮር ተግባራትን ለመለየት መሰረታዊ መነሻ
የሚሆነዉ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ሰነድ ሲሆን በተጨማሪም
የአመታዊ እቅድ ሰነድን እንዲሁም በቢሮ ደረጃ ለየፕሮግራሞች
የተዘጋጀውን የልማት ፕሮግራም ሰነድን መፈተሽ ይገባል፡፡
33
ለ) ለዋናዋና ዉጤት ተኮር ተግባራት የመቶኛ ክብደት መስጠት
 ለዉጤት ተኮር ተግባራት የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ሰነድ
ላይ በሚቀመጡ የጊዜ፣ የመጠንና ጥራት ስታንዳርዶች መሰረት
ተገቢ መለኪያና ኢላማ በማስቀመጥ አፈጻጸምን ለመከታተል
ይረዳል፡፡
የእያንዳንዱ ዉጤት ተኮር ተግባር የመቶኛ ድርሻ ለማስላት
የሚከተሉትን ጉዳዮች መነሻ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
1.ለየግቦቹ የተቀመጡ ዉጤት ተኮር ተግባራትን ለማከናወን
የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ሰነድን መሰረት በማድረግ
ለእያንዳንዱ ዉጤት ተኮር ተግባር የተቀመጠ የስራ ፍሰትን
የሚያሳዩ ዝርዝር ተግባራትን መለየት፣
2.በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ሰነድ ላይ ለተለዩት ዝርዝር
ተግባራት የተሰጣቸዉ የጊዜ መጠን በመደመር ዉጤት ተኮር
ተግባሩን ለማከናወን የሚያስፈልገዉን ጊዜ መለየት፣
34
3.የእያንዳንዱን ዉጤት ተኮር ተግባር የጊዜ መጠን በግቡ ስር ካሉ ሁሉም
ዉጤት ተኮር ተግባራት የጊዜ መጠን ድምር በማነጻጸር የእያንዳንዱን
ዉጤት ተኮር ተግባር የመቶኛ ድርሻ መለየት፣
4.ለእያንዳንዱ ዉጤት ተኮር ተግባር የተለየዉ የመቶኛ ድርሻ ግቡን
ለማስፈጸም ያለዉን የመቶኛ ድርሻ ያመለክታል፡፡ በግቡ ስር የመቶኛ
ድርሻ የተሰጣቸዉ ዉጤት ተኮር ተግባራት የመቶኛ ድርሻ ድምር 100
መሆኑን ማረጋገጥ፤
5.በሌላ በኩል በግቦች አፈጻጸም ምዘና ላይ እንደተገለጸዉ ከሌላ የስራ
ሂደት ኬዝ ቲም ተቆርሶ የመጣ የግብ ክፋይ በሚኖርበት ጊዜ ለግብ ክፋይ
ማስፈጸሚያ የተቀመጡት ዉጤት ተኮር ተግባራት መቶኛ ድርሻ
(ክብደት) ድምር 100% ሲሆን በሌላ በኩል የስራ ሂደት እና ኬዝ ቲም
ከቀሪዉ የግብ ክፋይ ዉጤት ተኮር ተግባራት የመቶኛ ድርሻጋር ሲደመር
በመሆኑ ለተቆረሰዉ የግብ ክፋይ ማስፈጸሚያ የተለዩት ዉጤት ተኮር
ተግባራት የሚሰጠዉ የመቶኛ ድርሻ ወደ ስራ ሂደት ኬዝ ቲም የመጡትን
ዉጤት ተኮር ተግባራት ክብደት በመደመር ድርሻቸዉን በስራ ሂደትና
ኬዝ ቲም ካላቸዉ የድርሻ ድምር በማነጻጸር ነዉ፡፡
ቅፅ 004
35
ሐ. ውጤት ተኮር ተግባራትን በመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ሰነድ
መሰረት ለግለሰብ ፈጻሚዎች ማከፋፈል

ይህን ለማከናወን የሚከተሉትን ጉዳዮች መነሻ ማድረግ


ያስፈልጋል፡-

1. የሥራ መዘርዝርን በመጠቀም የእያንዳንዱን ሰራተኛ ከስራ


መደብ አኳያ የሚኖረውን የስራ ድርሻ መለየት፤
2. የሥራ ሂደት ለውጥ ሰነድን መሰረት በማድረግ ለእያንዳንዱ
ውጤት ተኮር ተግባር የተመለከተውን ፈጻሚ በስራ መደብና
በሙያ መለየት፤
3. ከላይ በሥራ መዘርዝር የተለየውን የስራ ድርሻና የመሰረታዊ
የሥራ ሂደት ለውጥ ሰነድ የሚያመላክተውን በማናበብ ማን
የትኛውን ውጤት ተኮር ተግባር መፈጸም እንዳለበት መለየት፤
36
4.ዋና ዋና ውጤት ተኮር ተግባራቱ ከመቶ የተቀመጠ ድርሻ (ክብደት) ያላቸው
በመሆኑ ለግለሰብ ፈጻሚዎች ሲከፋፈሉ በሁለት መንገድ ማየት ያስፈልጋል፡፡
 ውጤት ተኮር ተግባር ላይ ከአንድ ሰው በላይ የሚካፈል ከሆነ የውጤት ተኮር
ተግባሩ የመቶኛ ድርሻ ለፈጻሚዎቹ እንደ የስራ መደባቸው፤ እንደስራው
ሁኔታ፤ ሌሎች ውጤት ተኮር ተግባራት ላይ እንደሚኖራቸው ድርሻና በሌሎች
መስፈርቶች የውጤት ተኮር ተግባሩ የመቶኛ ድርሻ ለግለሰብ ፈጻሚዎቹ
ተከፋፍሎ ይቀመጣል፡፡
 አንድን ውጤት ተኮር ተግባር አንድ ግለሰብ ብቻውን የሚፈጽመው ከሆነ
ለውጤት ተኮር ተግባሩ የተቀመጠው የመቶኛ ድርሻ ግለሰቡም ከውጤት ተኮር
ተግባሩ የሚወስደው ድርሻ ይሆናል ማለት ነው፡፡
5. እያንዳንዱ ፈጻሚ ከእያንዳንዱ ውጤት ተኮር ተግባር የሚኖረው የመቶኛ
ድርሻን በመለየት በሥራ ሂደቱ ወይም ኬዝ ቲሙ ስር ካሉ ግቦች የሚኖረው
አጠቃላይ ድርሻ ከተለየ በኃላ አፈጻጸሙ ተቆጥሮ ከተሰጠው ከውጤት ተኮር
ተግባሮቹ የመቶኛ ድምር ይነጻጸራል፡፡

37
6.በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ ከአንድ ግብ ውጤት ተኮር ተግባራት 60 % ድርሻ
ቢኖረውና ከሌላ ግብ 50 % ድርሻ ቢኖረው በድምሩ 110 % ክብደት ያላቸው ውጤት
ተኮር ተግባራት ላይ ስለሚሳተፍ አፈጻጸሙ ከ110 ይመዘንና ወደ 50 በመቶ
ይለወጣል ማለት ነው፡፡
ቅፅ 005

በቅፅ 005 በቀረበው ምሳሌ መሰረት በኬዝ ቲሙ ያሉ 3 ሰራተኞች 2ቱን ግቦች


ለመፈጸም የመቶኛ ክብደት ከተሰጣቸው ውጤት ተኮር ተግባራት ድርሻቸው
ተለይቷል፡፡ ይህም፡-
 አቶ X ከግብ 2 ውስጥ ካሉ ውጤት ተኮር ተግባራት 36 በመቶ ክብደት ባላቸው 6
ተግባራት፤ ከግብ 5 ውስጥ 57 በመቶ ክብደት ባላቸው 3 ውጤት ተኮር ተግባራት
በጥቅሉ 93 በመቶ ክብደት ድርሻ ቢወሰዱ 9 ውጤት ተኮር ተግባራት ላይ ይሳተፋል፡፡
 አቶ Y ከግብ 2 ውስጥ 31 በመቶ ድርሻ ባላቸው 6 ውጤት ተኮር ተግባራት፤ በግብ 5
ውስጥ 43 በመቶ ክብደት ባላቸው 3 ውጤት ተኮር ተግባራት በጥቅሉ 74 በመቶ
ክብደት ድርሻ በወሰዱ 9 ውጤት ተኮር ተግባራት ላይ ይሳተፋል፡፡
 ወ/ሮ Z በስራ ሂደት ዉስጥ እና በስራ መዘርዝር መሰረት በግብ 2 ውስጥ ባሉ 33
በመቶ ድርሻ በሚይዙ 6 ውጤት ተኮር ተግባራት የሚሳተፉ ሲሆን በግብ 5 ላይ ድርሻ
የለው ም፡፡
38
መ.ግለሰብ ፈጻሚዎች ተለይተው ለተቀመጡ ውጤት ተኮር ተግባራት
መለኪያና ዒላማ ማዘጋጀት
 ለፈጻሚው ግለሰብ የመቶኛ ድርሻቸው ተለይቶ የተቀመጠላቸው
እያንዳንዱ ውጤት ተኮር ተግባራት ከመጠን፣ ከጊዜና ከጥራት አንጻር
ዒላማ ይቀመጥላቸዋል፡፡ የመለኪያ ዒላማዎችን በመሠረታዊ የሥራ ሂደት
ለውጥ ሰነድና በአመታዊ ዕቅድ ተግባራትን ለማስፈጸም የተቀመጡ
የመጠን፣ የጊዜና የጥራት ስታንዳርዶችና ዒላማዎችን በመፈተሸ
ማስቀመጥ ይገባል፡፡
ሠ.ለውጤት ተኮር ተግባራት መለኪያና ዒላማ በማስቀመጥ የግለሰብ
ፈጻሚዎችን የስራ ድርሻ መለየት
 ቀጣዩ ስራ በ3ቱ መለኪያዎች ለግለሰብ ፈጻሚዎች ለተለዩ ውጤት ተኮር
ተግባራት ኢላማ ማስቀመጥ ነው፡፡
 በዚህ ደረጃ ላይ እንደተገለጸው የመለኪያዎችን ኢላማዎች ከመሰረታዊ
የስራ ሂደት ለውጥ ሰነድና ከዓመታዊ እቅድ ሰነድ ማግኘት ስለሚቻል
ቀጥታ መለኪያና ኢላማ ለግለሰብ ፈጻሚዎች እንዴት ማስቀመጥ
እንደሚቻል ወደሚያሳየን ቅጽ 006 እንሂድ፡፡ ቅጽ 006

39
ምሳሌ፡- የጥራት አለካክን በተመለከተ ለአብነት አንድ ተግባር ወስደን
ስንመለከት
ግብ 2 ተግባር 2፡ የተቀመጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዶች ከባላንስድ
ስኮር ካርድ ኢላማዎችና መለኪያዎች ጋር እንዲቃኙ ማድረግና ከላይ
እስከታች የተሳሰሩና ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ
ተግባርማድረግ፣ የጥራት አመላካች የጥራት ደረጃ

የተቀመጡ የአገልግሎት ፈፃሚዎች የየዕለት ሥራዎቻቸውን 90 እና ከ90 በላይ በጣም ከፍተኛ

አሰጣጥ ስታንዳርዶች እየመዘገቡና ከስታንዳርድ ጋር


ከባላንስድ ስኮር ካርድ እያነፃጸሩ እንዲሄዱ ማስቻሉ፣ ከ75-89 ከፍተኛ

ኢላማዎችና መለኪያዎች የሚከታተላቸው ተቋማት ከ60- 74 መካከለኛ


ጋር እንዲቃኙ ማድረግና የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ከ50-59 ዝቅተኛ
ከላይ እስከታች የተሳሰሩና በስታንዳርድ መሰረት እንዲሰጡ ከ50 በታች በጣም ዝቅተኛ
ተግባራዊ እየተደረጉ ማድረጉ፣
መሆኑን ክትትልና ድጋፍ የለውጥ መሳሪያዎች አቀናጅተው
ማድረግ፣ እንዲተገበሩ ማድረግ፣

40
 ለግለሰብ ፈጻሚዎች የተሰጡ ውጤት ተኮር ተግባራት
በሩብ ዓመት፤ በግማሽ ዓመት፤ በዘጠኝ ወር እና በበጀት
ዓመቱ መጨረሻ አፈጻጸማቸው ሊመዘን ይገባል፡፡ በዚህ
የሥራ አፈጻጸም ምዘና አንድ ግለሰብ ፈጻሚ ከተለያዩ
ውጤት ተኮር ተግባራት በ3ቱ መለኪያዎች የሚያገኛቸው
ውጤቶች ተጨምቀው ከ50 በመቶ ነጥብ እንዲሰጥ
ይደረጋል፡፡

41
 የዙሪያ መለስ የምዘና ስርዓትን ለመተግበር
የፈፃሚውን ባህሪይ የሰራተኛው የቅርብ አለቃ፣
የሰራተኛው የቅርብ የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም
ሰራተኛው ራሱን በፊት ለፊት ግምገማ (Face to
face evaluation/appraisal) ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡

42
 ራስን የማብቃት ዕቅድ ሰራተኞች በሥራ አፈጻጸም የራስን
ድክመትና ጥንካሬ በመለየት እንዲሁም በተቀናጀ ውጤት
ተኮር ምዘና በሚገኘው ግብረ መልስ መሠረት የተለዩ
ክፍተቶችና ድክመቶች ለማሻሻል የሚረዱ እርምጃዎችን
የማቀድና በዕቅዱ መሰረት ለመተግበር የራሳቸውን ጥረት
የሚያደርጉበት ተግባር ነው፡፡
 ራስን ከማብቃት ዕቅድና አፈጻጸም ከሚገኘው ከተሻሻለ
የአፈጻጸም ደረጃ ባሻገር በራሱ ራስን የማብቃት ዕቅድ
ማዘጋጀት፣ ተግባራዊ ማድረግና ለውጥን ገምግሞ ሪፖርት
ማድረግ ሠራተኛው የሚመዘንበት መስፈርት ይሆናል፡፡
ቅፅ 007

43
44

You might also like