You are on page 1of 49

ክፍል II

የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ


የዳሰሳ ጥናት
OVERVIEW
 
የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ
 የስልጠናው አጠቃላይ ዓላማ
ሰልጣኞች ደረጃውን የጠበቀ የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ በተሟላ መልኩ
እንዲያዘጋጅ ማስቻል ነው፡፡
 የስልጠናው ዝርዝር ዓላማ

ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኋላ የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ ደረጃን መሰረት


በማድረግ ፡-
 የዳሰሳ ጥናት በተሟላ ሁኔታ ያከናውናሉ፣

 የአዋጭነት / ቅኝት ጥናት በትክክል ያካሄዳሉ፣

 የዝርዝር ምርመራ እቅድ ያዘጋጃሉ፡፡


የዳሰሳ ጥናት ዝርዝር ዓላማ

ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኋላ የክዋኔ ኦዲት እቅድ ደረጃን መሰረት


በማድረግ ፡-

 የዳሰሳን ዓላማ በትክክል ይገልጻሉ፣


 የዳሰሳ ኦዲት ዘዴዎች (Methodlogy) በመለየት በሙሉ
ይተገብራሉ፣
 ከፍተኛ ስጋት ያለባቸውን የኦዲት አካባቢዎችን ይለያሉ፣
 የዳሰሳ ሪፖርት ያዘጋጃሉ፣
 ከኦዲት ተደራጊው እና ከማኔጅመንት ጋር የሚደረግን ግንኙነት
የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ

የክዋኔ ኦዲት ውስብስብ፣ ሰፊ፣ ጊዜ እና ጉልበት የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡

በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ለመለየት፣ ለመመርመር እና ሪፖርት

ለማድረግ የክዋኔ ኦዲቱን በተቀናጀ ዘዴ ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል፡፡


ከክዋኔ ኦዲት ተግባራት ውስጥ ዋናውን ድርሻ የሚወስደው የዕቅድ ዝግጅት ክፍል

ነው፡፡
የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ ዝግጅት የኦዲቱን ሥራ ከኢኮኖሚ፣ ብቃት እና ውጤታማነት

አንፃር አፈፃፀሙን ለመገምገም እንዲያስችል ዝግጅቱ በቂ መረጃ የሚሰጥ፣ ተለይቶ


የተገለፀ እና ለውሳኔ አሰጣጥ አጥጋቢ ሊሆን ይገባዋል፡፡
የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ የቀጠለ

የክዋኔ ኦዲት ዕቅድ የሚከተሉትን ክፍሎች ይይዛል፡-

 የዳሰሳ ጥናት (Overview)፣

 ዳሰሳን ወቅታዊ የማድረግ ሥራ (Marking)፣

 ዓመታዊ እና ስትራቴጂክ ዕቅድ ማዘጋጀት፣

 የአዋጭነት ጥናት (Fesibility) እና

 የዝርዝር ኦዲት ዕቅድ ናቸው፡፡


የዳሰሳ ጥናት / Overview

የዳሰሳ ጥናት (Overview)፡-


 ከክዋኔ ኦዲት የዕቅድ ዝግጅት ሂደት ከሆኑት ቁልፍ ተግባራት
መካከል አንዱ ነው ፡፡
 የክዋኔ ኦዲት የመጀመሪያ ደረጃ ነው፡፡

 ክዋኔ ኦዲት ስለሚካሄድበት መ/ቤት፣ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክት


ወይም ተግባር መነሻ የሚሆን መረጃ ለማግኘት የሚረዳ
ነው፡፡
የዳሰሳ ጥናት ዓላማ

 የክዋኔ ኦዲት የአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅድ


ለማዘጋጀት፣
 ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው የኦዲት አካባቢዎችን
ለመለየት፣
 በክዋኔ ኦዲቱ የሚሰሩ የኦዲት ጭብጦችን ለመለየት
የዳሰሳ ጥናት ግብ
 ስለኦዲት ተደራጊው መስሪያ ቤት ዓላማ፣ አሰራር፣ የሀብት አጠቃቀም
እና ፖሊሲ መረዳት፣
 ከገንዘብ ጠቀሜታ ለማግኘት ስጋት የሚሆኑ የኦዲት አካባቢዎችን
መለየት፣
 በዝርዝር ምርመራ ኦዲት የሚታዩ የኦዲት አካባቢዎችን መወሰን፣
 በቀጣይ የኦዲት ትኩረት የሚሰጥባቸውን አካባቢዎች መጠቆም፣
የዳሰሳ ጥናት ወሰን

 ስለ ኦዲት ተደራጊው መ/ቤት አጠቃላይ መረጃ /Background


 ዓላማ እና ግብ / Aims & Objectives
 ችግሮች / Constraints
 ጥቅም ላይ የዋለ ሃብት / Resources Used
 የተከናወኑ ተግባራት /Activities undertaken
 የአሰራር ሥርዓት እና መመሪያ / Procedures & controls
 የገንዘብ ጠቀሜታ ስጋት / Risk to VFM
 የውስጥ ኦዲት ስጋት / Risk to the Audit office
 ሌሎች መረጃዎች / Other information
የዳሰሳ ጥናት ውጤት

 ለውስጥ ኦዲት ዳይሬክተር የሚቀርብ ሪፖርት ሲሆን ሪፖርቱም፡-


 ኦዲቱ የተመለከታቸው መረጃዎች ን

 ቅድሚያ የሚሰጣቸው አካባቢዎች ድልድልን

 በመጪው 2-3 ዓመታት በኦዲቱ የሚታዩ ሥራዎች ላይ የተሰጠ


አስተያየትን ያካተተ ይሆናል፡፡
 የዳሰሳ ሪፖርቱ ለውስጥ ጥቅም የሚውል እንጂ ለውጪ
ተጠቃሚ የሚውል አይደለም፡፡
ኦዲት ተደራጊውን አካል ስለመረዳት

ኦዲት ተደራጊውን ለመረዳት እዲቻል ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች፡-


 የመ/ቤቱ ዓላማ /Objective/ ምንድን ነው?
 በዋናነት ምን ምን ተግባራትን /Activities/ ያከናውናል?
 ምን ምን ግብዓቶችን /Inputs/ ይጠቀማል?
 ምን ምን ውጤቶች /Outputs/ ይጠበቃሉ?
 በሥራው ሂደት የመጡ ለውጦች /Impacts/ ምንድን ናቸው?
 አስተዳደራዊ አደረጃጀቱ /Management Structure/ እንዴት ነው?
ኦዲት ተደራጊውን አካል ስለመረዳት
የቀጠለ
ኦዲት ተደራጊውን መረዳት የሚሰጣቸው ጥቅሞች፡-
 ክዋኔ ኦዲት ስለሚካሄድበት ተቋም ግንዛቤ ይሰጣል ፣
 የኦዲት መነሻ ወሰን (Scope) ለመወሰን የሚያስችል መሠረት ይሰጣል፣ 
 በቅድሚያ መሠራት ያለበትን የኦዲት ሥራ ለመወሰን ያስችለናል ወይም
ለውጥ ሊደረግበት ለሚገባው የኦዲት ሥራ መሠረት ይጥላል፡፡
 ለዕቅድ፣ ለቅኝት ጥናት፣ ለዝርዝር ኦዲት እና ለሪፖርት ደረጃዎች ጠንካራ
መሠረት ይፈጥራል፡፡
 የክዋኔ ኦዲቱን ኢኮኖሚያዊ በሆነ እና በተቀላጠፈ መንገድ ለመስራት
ይረዳል፡፡
የዳሰሳ ጥናቱ ዘዴ (Methodology)

የዳሰሳ ጥናት ከላይ ወደታች የመረጃ አሰባሰብና አተናተን ዘዴን (Top-down


approach) ያካትታል፡፡ ይህም፡-
ከስትራቴጂክ እና ከተጠቃለሉ መረጃዎች በመነሳት በእያንዳንዱ የኦዲት አካባቢ
(Potential audit area) ላይ በቂ የሚሆኑ መረጃዎችን ብቻ ማሰባሰብን ይፈልጋል፡፡

የመረጃ መሰብሰቢያ እና መተንተኛ ዘዴዎች በሁለት ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ ፡-


 የመነሻ መረጃ አሰባሰብ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትንተና፣
 ዝርዝር መረጃ አሰባሰብ እና ግምገማ፣
 
የመነሻ መረጃ አሰባሰብ እና የመጀመሪያ ደረጃ
ትንተና፣
የመነሻ መረጃ አሰባሰብና የመጀመሪያ ደረጃ ትንተና ዓላማ ኦዲት
ስለሚደረገው አካል/ ዘርፍ አጠቃላይ እና ዝርዝር ዕይታ ማግኘት ነው፡፡
 የመ/ቤቱ ዓላማ ምን እንደሆነ፣
 መ/ቤቱ ምን ምን ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን፣
 የገንዘቡ ምንጭ ምን እንደሆነ፣
 በዋናነት ወጪው ምንድን ነው
የሚለውን የሚያሳይ መግለጫ ለማዘጋጀት የሚጠቅመን ነው፡፡
የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች

 ቃለ መጠይቅ

 የሰነድ ማስረጃዎችን በመከለስ

 ምልከታ

 ትንተና

 ግምገማ

መረጃ በመሰብሰብ ሂደት ኦዲተሩ ብዛት ያላቸውን ሰነዶችን መዳሰስ ቢኖርበትም ሁሉም

ሰነዶች ጥቅም ላይ የሚውሉ ባለመሆናቸው ሙያዊ ብቃቱን ተጠቅሞ ዋናና ትኩረት

የሚሹ ጉዳደደች ላይ ለመድረስ አቋራጭ /Cross cut/ ዘዴን መጠቀም ይኖርበታል፡፡


ዝርዝር መረጃ አሰባሰብ እና ግምገማ

 የዚህ የዳሰሳ ክፍል ዓላማ በመነሻ መረጃ የተሰበሰበውን እና


በተወሰደው አቋራጭ (Cross Cuts) የተለዩትን ርዕሶች (Topics)
ከቀሪ መስፈርቶች አንፃር ለመመዘን ነው፡፡
 ኦዲተሩ እያንዳዱን ርዕስ ከገንዘብ ተመጣጣኝ ዋጋ ስለመገኘቱ፣
ወደፊት ሊመጣ ስለሚችለው ተጽዕኖ፣ ኦዲት ሊደረግ ስለመቻሉ
ወዘተ እንዲገነዘብ ያስችለዋል፡፡
 ኦዲተሩ የኦዲት የትኩረት አካባቢን ከእያንዳንዱ መመዘኛ አንጻር
በክብደት ደረጃው መሰረት ቅደም ተከተል እንዲውስን ያደረገዋል፡፡
የኦዲት አካባቢዎችን መምረጥ (Selecting Audit Areas)

 በዳሰሳው ሂደት ወቅት ስለ ኦዲት ተደራጊው አካል/ ዘርፍ በጣም ብዙ


መረጃዎች ይሰበሰባሉ፡፡
 ጥናቶቹ ጥሩ ሆነው ስለመሠራታቸው ወይም ስለአለመሰራታቸው
አስተያየት ለመስጠት እንዲሁም በጥናቶቹ መካከል የፍላጐት ቅደም
ተከተላቸውን (Priorities) ደረጃ ለማውጣት እና የተሰበሰቡትን
መረጃዎች ለመገምገም መስፈርት ልንጠቀም ይገባል፡፡
 መስፈርቱም የሥጋት መስፈርት (Risk criteria) ይባላል፡፡
የሥጋት መስፈርት (Risk criteria)

 የሥጋት መስፈርት የጉዳዩን አሳሳቢነት ለመገምገም


ያስችላል፡፡
 ከሌሎች ጋር በማወዳደር ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ
ተግባራትን ለመለየት ያግዛል፡፡
 የተሰበሰቡት መረጃዎች ከእያንዳንዱ የሥጋት መሥፈርት
አንፃር መገምገም ያስችላል፡፡
 ዳሰሳው በብቃት እና በውጤታማነት እንዲካሄድ ያግዛል፡፡
የሥጋት መስፈርት ዓይነቶች

 ጉልህነት (Materiality)
 ከገንዘብ ፋይዳ ስለመገኘቱ ስጋት (Risk to VFM)
 ለሕዝብ ተጠያቂነት (Public accountability)

 ሊከሰት የሚችል ተፅዕኖ/ ውጤት (Possible Impact)


 የሕግ አውጪው ወይም የሕዝብ ፍላጐት (Legislative or
public interest)
የሥጋት መስፈርት ዓይነቶች የቀጠለ

 የውስጥ ኦዲት ሥጋት (Risk to the Internal Audit Interest)


 ኦዲት ተደራጊነት (Auditability)
 የሥራ ክፍሉ ጉዳዮች (Departmental issue)
 ተስማሚነት (Suitability)
 ወቅታዊነት (Timeliness)
 ከዚህ በፊት የተሰሩ የኦዲት ሥራዎች
 ከሌሎች ከፍተኛ የሥራ ዕቅዶች ወይም በሂደት ላይ ካሉ ሥራዎች
 ግምገማ ላይ ተፅዕኖ ሊኖራቸው ከሚችሉ የለውጥ እድገቶች
ጉልህነት (Materiality)

 በክዋኔ ኦዲት አንድ ነገር ጉልህ ነው ሊባል የሚችለው የሚቀርበው


መግለጫ (Disclosure) በሪፖርት ተጠቃሚው ዘንድ ትልቅ
ትኩረት የሚሰጠው አንኳር ጉዳይ ሲሆን ነው፡፡
 ጉልህነት በሶስት ዋና ዋና ሁኔታዎች ይወሰናል፡፡ እነሱም፡-
1. ጉልህነት በዋጋ መጠን (Materiality by Amount)

ጉልህነት በዋጋ መጠን ግንዛቤ ሊያገኝ የሚገባው የገንዘብ ዋጋ


በሪፖርቱ ተጠቃሚዎች ፍላጐት ላይ ተፅዕኖ ያሳደረ ከሆነ
ነው፡፡
ጉልህነት (Materiality) የቀጠለ

2. ጉልህነት በባህሪይ (Materiality by Nature)


ጉልህነት በባህሪይ የሚታሰበው የአንድ ሥራ የተፈጥሮአዊ ባህሪው
ጉልህነት የሪፖርቱ ተጠቃሚዎችን ፍላጐት የሚስብ ወይም
የሚያግባባ ከሆነ ነው፡፡

3. ጉልህነት በወቅቱ ሂደት/ አግባብ (Materiality by Context)


ጉልህነት በአግባቡ የሚዛመደው በራሳቸው ጉልህ ሆነው የማይታዩ
ነገር ግን በያዙት ቁም ነገር ምክንያት ትኩረት እንዲሰጣቸው
ከሚፈልጉ ጉዳዮች ጋር ነው፡፡
ለገንዘብ ፋይዳ ስለመገኘቱ ስጋት (Risk to VFM/3Es)

 የገንዘብ ፋይዳ ስጋት በቁጠባ፣ በብቃት እና በስኬታማነት ካለመፈፀም


የሚመጣ ስጋት ነው፡፡
 ሥጋት አንድ ሁኔታ ወይም ድርጊት መ/ቤቱን የሚጐዳ ሲሆን፣ ይህም
ለፋይናንስ ክስረት መጋለጥ፣ ዝናን ማጣት ወይም
 ፕሮግራምን በቁጠባ፣ በብቃት እና ስኬት ተፈላጊውን ውጤት
ማስገኘት በማያስችል መልኩ መተግበር ወይም
 የአካባቢን እንድምታ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለመቻል
በመሳሰሉት አጋጣሚዎች ሊደርስ የሚችል ክስተት ነው፡፡
ለገንዘብ ፋይዳ ስለመገኘቱ ስጋት የቀጠለ

ለገንዘብ ፋይዳ ስለመገኘቱ ሥጋት በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነሱም፡-

1. ተፈጥሮአዊ ስጋቶች (Inherent Risks)


አንዳንድ ተግባራት የገንዘብ ፋይዳ ለማስገኘት በተፈጥሮአቸው ሥጋት እንዳለባቸው
ይታወቃል፡፡ እነዚህም ከኦዲት ተደራጊው ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ምክንያቶች ሲሆኑ
እነሱም፡-
 አዲስ አገልግሎት ማቋቋም፣

 የሕግ መለወጥ፣

 ሊፈጠሩ የሚችሉ ከፍተኛ ድንገተኛ ሁኔታዎች፣

 አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ ፖሊሲዎችን ማስተዋወቅ፣


ለገንዘብ ፋይዳ ስለመገኘቱ ስጋት የቀጠለ

 ከድርጅቱ መደበኛ አሰራር ውጭ የሆኑ ያልተለመዱ ክስተቶች፣

 ያልተለመዱ የገንዘብ ስምምነቶች፣

 በገንዘብ እንቅስቃሴ እና በመዋዕለ ነዋይ ተግባራት ላይ የሚታዩ


ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ሁኔታዎች፣
 ለወለድ እና ለዋጋ ግሽበት ተጋላጭነት፣

 የተወሳሰቡ ፕሮግራሞች፣

 አዲስ ቴክኖሎጂና፣

 በባህሪያቸው ተመሳሳይነት የሌላቸው ዓላማዎች ውጤቶች፡፡


ለገንዘብ ፋይዳ ስለመገኘቱ ስጋት የቀጠለ

2. በታወቁ ድክመቶች ወይም በቁጥጥር ድክመቶች


የሚከሰቱ ስጋቶች (Identfied/ Control Risks) ናቸው፡፡
ተለይተው የታወቁ የቁጥጥር ሥጋቶች የተለዩ ሁኔታዎች፣
ድርጊቶች ወይም የተወሰነ ማስረጃዎች አንድ ሥራ ጥሩ
የገንዘብ ፋይዳ የማያስገኝ ወይም ሊያስገኝ የማይችል
መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡
ለሕዝብ ተጠያቂነት (Public Acountability)

የሕዝብ ተጠያቂነት በኦዲተሩ የኦዲት መስክ ምርመራ እና የኦዲት


አመራረጥ ላይ በሁለት መንገዶች ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ እነሱም፡-
 የሕግ አውጭው ከፍተኛ የመንግሥት ወጭ የተመዘገበባቸውን
መ/ቤቶች ሂሣብ ለማየት ያለው ፍላጎት፣
 የውስጥ ኦዲቱ ዓላማ የኦዲት ሪፖርቶችን ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር
ሚኒስቴር እና ለመ/ቤቱ ኃላፊዎች በወቅቱ በማቅረብ የሕዝብ
ተጠያቂነትን እንዲሻሻል የማድረግን ኃላፊነት ፡፡
ሊከሰት የሚችል ዘለቄታዊ ተፅዕኖ /ውጤት
(Possible Impact)

 የክዋኔ ኦዲት ዓላማ ጥቅም ያለው በጐ ተፅዕኖ


በማምጣት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
 ኦዲተሩ የክዋኔ ኦዲቱን ሲጀምር የሚካሄደው ኦዲት
ምን ተፅዕኖ እንደሚያመጣ እና የሚሻሻል አሰራር
ስለመኖሩ ራሱን መጠየቅ አለበት፡፡
የሕግ አውጪው ወይም የሕዝብ ፍላጐት
(Legislative or public interest)

 የክዋኔ ኦዲት በራሱ የመጨረሻ አይደለም፡፡ የመንግሥት መ/ቤቶች


ከፍተኛ ወጭ አውጥተውበት የዋና ዋና ደንበኞቻቸውን ፍላጐት
ለማርካት የሚገለገሉበት ሲሆን ይህም ለሕግ አውጭውና በሕግ
አውጭው በኩል ለሕዝቡ እና ለመገናኛ ዘዴዎች የሚገለፅ ነው፡፡
 ኦዲተሩ ለኦዲት ሥራ ቅድሚያ ሰጥቶ ስለለያቸው ሀሳቦች፣ ነጥቦች
በሕግ አውጭው ወይንም በሕዝቡ ፍላጐት ላይ የተመሠረተ ወይንም
የውስጥ ኦዲተሩ በቂና አሳማኝ መረጃዎችን ካቀረበ ፍላጐቱን ያሟላ
መሆን አለበት፡፡
የውስጥ ኦዲት ሥጋት
Risk to the Internal Audit Interest

 ማንኛውም የኦዲት ሥራ ሲከናወን በኦዲት ሊደረስባቸው የማይችሉ


ግድፈቶች ይኖራሉ የሚል የኦዲት ስጋት በኦዲተሩ ላይ ያስከትላል፡፡
 በክዋኔ ኦዲት የሚታይ ስጋት በቁጠባ፣ በብቃት እና በስኬታማነት
ያልተካሄደ የክዋኔ ኦዲት ነው፡፡
 የተዋጣለት የኦዲት ተግባር እነዚህን ሥጋቶች የለየ እና የሥጋቱን
መጠን ዝቅተኛ የሚያደርግ ነው፡፡
ከኦዲት ተደራጊነት (Auditability)

 ኦዲተሩ ብቃት ባለው ኦዲት ተግባራት ላይ ብቻ አስተያየት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡


 ኦዲት ተደራጊነትን ሊወስኑ የሚችሉ ጉዳዮች/፡-

 በጉዳዩ ባህርይ፣

 ባስፈላጊው የኦዲት የአሠራር ዘዴ /የውስጥ ኦዲቱ ብቃት፣ የባለሙያ


ክህሎት../ መሟላት፣
 በማስረጃዎች መኖር፣

 ለኦዲት አስፈላጊ ክህሎት፣

 በአጠቃላይ የሚያስፈልግ ሀብት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡


ወቅታዊነት (Timeliness)

 ኦዲተሩ የክዋኔ ኦዲቱን ለማከናወን የሚከተሉትን ማመዛዘን አለበት፡-


 የኦዲት አካባቢውን ለመመርመር ለውስጥ ኦዲቱ ትክክለኛው ጊዜ
መሆኑን፣
 ኦዲት ተደራጊው ከውስጥ እና ከውጭ ግምገማ የተገኙ
አስተያየቶችን እና አዲስ ሕግ በመውጣቱ ምክንያት የተከሰቱ
ለውጦችን የመሳሰሉ ሥራዎችን ለመተግበር ብዙ ጊዜ የሚፈልግ
መሆኑን፡፡
የሥራ ክፍሉ ጉዳዮች (Departmental issue)

 ኦዲት የሚደረገው መ/ቤት/ ክፍል የሚመረመረውን


ተግባር አፈፃፀም ላይ በሁለት መንገድ ተፅዕኖ
ያሳድራል፡፡
ጥናቱን ራሳቸው በመፈፀም

የተለየ ጥናት ማካሄድን በመቃወም


ተስማሚነት (Suitability)

ኦዲተሩ አስተያየት መስጠት ያለበት ለሚመለከተው ተጠቃሚ አካል ተስማሚ ለሆኑ


ተግባራት ብቻ ሲሆን በሁለት ጉዳዮች ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ እነርሱም፡-
 አንደኛው ጉዳይ ርዕሱ ፖለቲካዊ አወዛጋቢነት ያለው ከሆነ በውስጥ ኦዲት ሪፖርት
መሠረት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ አከራካሪ ይሆናል፡፡ የውስጥ ኦዲተሮች
የመንግሥትን የፖለቲካ ዓላማዎችን ሊያስተቹ ከሚችሉ ወይንም በውጭ
ተጠቃሚዎች ለዚሁ የፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ የሚሆኑ የኦዲት ተግባራትን
ማከናወን አይኖርባቸውም፡፡
 ርዕሱ በተፈጥሮ ቴክኒካል በመሆኑ የውስጥ ኦዲት የአድማጩን ፍላጎት የሚያሟላ
ሪፖርት ማቅረብ የማይችል ከሆነ ኦዲቱን ማከናወን አይኖርበትም፡፡
ከዚህ በፊት የተሰሩ የኦዲት ሥራዎች

 ቀደም ሲል ከተከናወኑ የፋይናንስ እና የክዋኔ ኦዲት


የሚገኝ ልምድ እና ዕውቀት መከናወን ያለበትን
የክዋኔ ኦዲት ለመምረጥ ጠቃሚ መረጃዎች ናቸው፡፡
ከሌሎች ከፍተኛ የሥራ ዕቅዶች ወይም
በሂደት ላይ ካሉ ሥራዎች

 የኦዲ ቱ ዓላማ የመጀ መሪያ መረጃ እና ግም ገማ ለማ በርከት


መሆ ን ይኖርበታ ል፡፡
 ኦዲ ት ተ ደራ ጊ መ/ቤቶ ች ኦዲ ት የሚ ደረገው ን አካባቢ
በመገም ገም ሂደት ላይ ካሉ ወ ይንም በቅ ርብ ጊዜያት ው ስጥ
ዕቅ ድ ይዘው ከሆ ነ ለገንዘብ ፋይዳ መኖ ሩን ለማ ሻሻል እና
የሕ ዝብ ተ ጠያቂ ነት ን ለማ ጐ ልበት እንዲ ቻ ል የው ስጥ ኦዲ ቱ
በክፍሉ በኩል ም ን ማ ከናወ ን እንዳለበት መጠየቅ ይኖ ርበታ ል፡፡
ግምገማ ላይ ተፅዕኖ ሊኖራቸው ከሚችሉ የለውጥ
ዕድገቶች

 የውስጥ ኦዲት አጠቃላይ ዓላማው ከገንዘብ ፋይዳ መገኘትን


ማሻሻል ወይንም የሕዝብ ተጠያቂነትን ማጐልበት ነው፡፡ ይህም
በኦዲት ተደራጊው መ/ቤት በኩል ስጋት ባለበት የሥራ አካባቢ ላይ
ለወደፊቱ ምን መሠራት እንደታሰበ በማወቅ ላይ ይመሠረታል፡፡
 ከፍተኛ የፖሊሲ ወይም የሕግ ዝግጅት በዕቅድ የተያዘ መሆኑ
ከታወቀ የውስጥ ኦዲቱ ጥናት ምን አስተዋጽኦ ማድረግ
እንደሚገባው መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
የስጋት ግመገማ ማካሄድ

 በክዋኔ ኦዲት እንዲሰሩ የተለዩትን የኦዲት አካባቢዎች ከእያንዳንዱ


መስፈርት አንፃር በመመዘን ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ደረጃን
መስጠት፣
 ቅድሚያ የሚሰጠውን የኦዲት አካባቢ በቅደም ተከተል መለየት፣
 ሊጠና ከታሰበው አካባቢ በአጠቃላይ ቅድሚያ ሊሰጠው በሚገባው
አካባቢ ላይ አስተያየት ማቅረብ፣
 ኦዲቱ መካሄድ ያለበትን ጊዜ አስተያየት ማቅረብ
የዳሰሳ ሪፖርት
 የዳሰሳ ሪፖርት ለውስጥ ኦዲቱ ኃላፊ የሚቀርብ የዳሰሳው
ሥራ የመጨረሻ ውጤት ነው፡፡
 ለኦዲት ተደራጊው አካል ወይም ለሌላ ለውጭ አካል
የሚቀርብ መደበኛ የኦዲት ሪፖርት አይኖርም፡፡
 በዚህ ሪፖርት መሠረት የውስጥ ኦዲቱ ኃላፊ ሀሳብ
በተሰጠበት በእያንዳንዱ የኦዲት አካባቢ ላይ ቀጣዩን አካሄድ
ምን መሆን እንዳለበት ያፀድቃል፡፡
የዳሰሳ ሪፖርት ክፍሎች

የዳሰሳ ሪፖርት ሁለት ክፍሎችን ይይዛል እነሱም፡-


 ዋናው የዳሰሳ ሪፖርት ክፍል እና
 አባሪዎች (Appendices) ናቸው፡፡
ዋናው የዳሰሳ ሪፖርት ክፍል

 ክለሳ የተደረገባቸው የኦዲት አካባቢዎች አጭር መግለጫ፣


 በእያንዳንዱ የኦዲት አካባቢ የገቢ እና የወጪ ዝርዝርና ምንጭ፣
 የኦዲት አካባቢው ልዩ ልዩ መሰረታዊ ነገሮች ለኦዲቱ ተስማሚነታቸው እና
ቀደምትነታቸው ላይ የተደረገ ክለሳ፣
 በቅርብ ጊዜ ለሚደረግ ኦዲት በኦዲተሩ የተሰጠ አስተያየት እና በዚህ አካባቢ
ላይ ወደፊት ለሚደረግ የክዋኔ ኦዲት የተሰጠ ማንኛውም አስተያየት፣
 ለኦዲቱ የሚያስፈልገው የወጪ እና የጊዜ ግምት፣
 ማጠቃለያ
አባሪዎች (Appendices)

 ለእያንዳንዱ የኦዲት አካባቢ የስጋት ትንተና ቅጽ


 የስጋት ትንተና ማጠቃለያ
መረጃ አያያዝ (Documentation)

በዳሰሳው መጨረሻ ኦዲተሩ የሚከተሉትን የያዙ የሥራ ወረቀቶች


ማጠቃለያ ማህደር ማዘጋጀት አለበት፡፡
 አጭር የዳሰሳ ሪፖርት
 ለሁሉም የኦዲት አካባቢ የስጋት መገምገሚያ ቅጾች
 የተሰበሰቡ ማስረጃዎች
 በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ሊሸፈኑ የታሰቡ የኦዲት አካባቢዎች የጊዜ
ሰሌዳ፣
 አግባብነት ያላቸውን እና አስፈላጊ የሆኑ ደጋፊ ማስረጃዎችን በሙሉ የያዘ
የሥራ ወረቀት ማህደር፣
ከኦዲት ተደራጊው ጋር ያለ ግንኙነት

 በክዋኔ ኦዲት ተግባር ላይ ዋናው ቁልፍ ነገር ከኦዲት ተደራጊው ጋር የሚኖረን ጥሩ የሥራ
ግንኙነት ለሥራችን ውጤታማነት አዎንታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል መረዳት
አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም የተሳካ የዳሰሳ ሥራ ለማከናወን ከኦዲት ተደራጊው ጋር ጥሩ
ግንኙነት መኖር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
 ኦዲት ተደራጊው በቀጣይ ስለሚሰራው የዳሰሳ ሥራ በቂ መረጃ ሊኖረው ይገባል፡፡
ይኸውም፡-
 የክዋኔ ኦዲት ዓላማ፣

 ዳሰሳ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና የዳሰሳ አስፈላጊነት፣

 የምንከተላቸው ዘዴዎች፣

 የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች
ከኦዲት ተደራጊው ጋር ያለ ግንኙነት የቀጠለ

 የኦዲት ቡድኑ ስለሚያከናውናቸው ሥራዎች፣


 የኦዲት ቡድኑ ሊያነጋግራቸው የሚፈልገውን ባለሙያዎች፣
 የኦዲት ቡድኑ የሰው ኃይልና የኦዲቱን ጊዜ፣
 ከኦዲት ተደራጊው ጋር የሚደረግ ግንኙነት የሚያመቻች
ባለሙያ / Liaison/፣
 የዳሰሳው ውጤት ለምን ሥራ እንደሚውል
የኦዲት ሥራ አመራር

 የዳሰሳን ሥራ ማቀድና መቆጣጠር አስቸጋሪ ተግባር ነው፡፡ ይህም


የመጀመሪያ ዙር መረጃ ስብሰባና ግምገማ ውጤት በመሆኑ እና
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኦዲት ውሳኔ ሃሣቦች ስለሚካተቱበት የሥራ
አመራር ክትትልና ውሳኔ ከሌለበት በቀጣይነት የሚከናወነውን የክዋኔ
ኦዲቱን ሥራዎች ይጐዳል፡፡
 የሥራ አመራሩ እድገቱን ለመከታተል፣ ችግሮችን ለመቀነስ እና
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቁልፍ በሆኑ የውሳኔ ነጥቦች ላይ ጣልቃ እንዲገባ
መደረግ ይኖርበታል፡፡
የሥራ አመራሩ ዋና ዋና ሥራዎች

 የመነሻ ሥራ ዝርዝሮችን ማዘጋጀት፣


 ከኦዲት ተደራጊው የሥራ ክፍል ኃላፊ በቅድሚያ ግንኙነት
ማድረግ፣
 የመነሻ መረጃ መሰብሰብና ብዙዎቹን ሊመለከት የሚችሉትን
መረጃዎች መለየት፣
 ዝርዝር መረጃ መሰብሰብ እና የሥጋት ግምገማ ማካሄድ፣
 የሪፖርት ዝግጅት ናቸው፡፡
በቂ ቁጥጥር

 የኦዲቱን ሂደት መከታተል እና ውጤቱን መከለስ ፣


 በእያንዳንዱ ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ሥራዎች ላይ ውሳኔ
መስጠት፣
 በኦዲት ቡድኑ አባላት መካከል እና ከኦዲት ስራ አመራር ጋር
በቂ ግንኙነትማድረግ
አመሰግናለሁ !

You might also like