You are on page 1of 13

በንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ዘርፍ

መሠረታዊ ድርጅት የግዥ ፋይናንስና የውስጥ


ኦዲት ህዋስ ቁጥር 7 የ 2008 በጀት አመት
የድርጅትና የፖለቲካ ስራዎች ዕቅድ

ህዳር/2 ዐዐ 8 ዓ/ም
ማውጫ ገጽ
1. መግቢያ -------------------------------------------------------------------------------- 2

2. ነባራዊ ሁኔታ ------------------------------------------------------------------------ 3

3. ዓላማ ---------------------------------------------------------------------------------- 3

4. የሚጠበቁ ውጤቶች ----------------------------------------------------------------- 3

5. ዋና ዋና ግቦች ----------------------------------------------------------------------- 4

6. ግቦችና ዝርዝር ተግባራት ---------------------------------------------------------- 4-5

7. የዓመቱ የሥራ ዕቅድ የጊዜ ሰሌዳ ------------------------------------------------ 6


1. መ ግ ቢ ያ

በድርጅታችን መሪነት የተጀመረውን ፈጣን ልማት ቀጣይነት በማረጋገጥ የህዝባችንን ተጠቃሚነት

ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሰፋፊ የልማት ግቦችን አስቀምጠን ከፍተኛ ርብርብ እያደረግን እንገኛለን፡፡

በአሁኑ ወቅትም የመጀመሪያውን ዙር የእድገትና ትራንስፎርሜሼን ዕቅድ አፈፃፀም ገምግመን

ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ገብተናል

በመሆኑም ባሳለፍናቸው የትራንስፎርሜሽን ዘመን ያስመዘገብናቸውን ውጤቶች የበለጠ በማስፋት

እና የታዩብንን ጉድለቶች ለቅመን በማስተካከል ማዋ ቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት

በድርጅታችን አቅጣጫ ተቀምጦ በዚያ ልክ እንቅስቃሴ ተጀምሯል በዚሁ መሰረት የታዩብን ጉድለቶች

ማለትም የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ ወደ ልማታዊነት ለማሸጋገር የህዝቡን የመልካም

አስተዳደር ችግሮች የመቅረፍ ጉዳይ የሞት ሽረት ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ የተቋማችን

የድርጅት ክንፍ በዚህ በጀት አመት የተልዕኮ እምብርት ተደርጎ መወሰድ ያለበት የልማት ሰራዊት

በመገንባት በሰራዊቱ አማካኝነት ጠንካራ ትግል በማድረግ ከላይ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የውስጥ

ድርጅት ስራችን ከመቼውም በላይ በተጠናከረ ሁኔታ በዕቅድ መምራትና መፈፀም ይገባናል፡፡ በዚሁም

መሰረት በንግድ ኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ዘርፍ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ የግዥ ፋይናንስና

የውስጥ ኦዲት ህዋስ 7 (ሰባት) የ 2 ዐዐ 8 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ የ 12 ወራት እቅድ ክንውን

በመገምገምና የ 2 ዐዐ 8 ዓ.ም ዓመታዊ እቅድ በማዘጋጀት መከናወን ያለባቸውን ግቦችና ተግባራት

በመለየት እቅዱ በዝርዝር ተዘጋጅቷል፡፡

ከመስከረም 2 ዐዐ 8 እስከ ነሐሴ 3 ዐ/2 ዐዐ 8 .ም ድረስ በሕዋሱ የሚከናወኑ ተግባራት ዝርዝር

የሚፈጽምበት የጊዜ ሰሌዳ በግልጽ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ የሥራ ክንውን ሪፖርት በየወቅቱ

ለመሠረታዊ ድርጅቱ የሚተላለፍበት ሁኔታና እያንዳንዱ የሕዋሱ አመራር የተጣለበትን ኃላፊነት

ስለመወጣቱና ስለተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የሚደረግበት ሁኔታ በእቅዱ እንዲካተት ተደርጓል፡፡


ሕዋሱ በእቅዱ መሠረት መመራት እንዲችል በዓመቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ግቦችና ተግባራትን

እንዲይዝ ተደርጐ የተዘጋጀ እቅድ ነው፡፡

2. ነባራዊ ሁኔታ

ነባራዊ ሁኔታን ገምግሞ መነሳት ለቀጣይ ዕቅድ አፈጻጸማችን የሚኖረው ፋይዳ እጅግ የጎላ ነው፡፡ ስለሆነም
መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ነባራዊ ሁኔታውን ከህዋስ አመራር እና ከአባሉ ጋር በማስተሳሰር
ከአመለካከት፣ከተግባር እና ከግብአት አቅርቦት አንጻር በመገምገም በቀጣይ ማስተካከል ጠቃሚ ይሆናል፡፡

2.1 የአመራር ሁኔታ

ከአመለካከት አንፃር የውስጥ ድርጅት ስራችን ማጠናከር ለሁሉም የልማትና የመልካም አስተዳደር
ስራዎቻችን ማጠንጠኛ ማዕከል መሆኑን በመገንዘብ የህዋስ አመራሩ አባላትን ክትትል እና ድጋፍ ከማድረግ
አኳያ የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም መሰረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ከማድረገግ አንጻር ሰፊ ክፍተት
የታየበት እንዲሁም የአባላት የዕለት ተዕለት ግንባታ ስራችን ለማጠናከር የሚካሄዱ መደበኛ ውይይቶችን
በአብዛኛው የተንጠባጠበበት ሁኔታ ተገምግሟል የተደረጉ ውይቶችም ቢሆኑ የብስለት ደረጃቸው ገና ብዙ
የሚቀርባቸው እንዲሆን ተምልክቷል በአጠቃላይ በተቋማችን ጠንካራ ድርጅት በመትከል የጎላ ትግል
ከማድረግ እንዲሁም በከተማ የበላይነቱን ይዞ የሚገኝውን ኪራይ ሰብሳቢነት በማደናቀፍ የልማታዊነት
አስተሳሰብ ተግባር የበላይነቱን እንዲይዝ ከማድረግ አኳያ አሁንም የአመራሩን ጠንካራ ትግል የሚጠይቅ
ጉዳይ እንዲሆን ተገምግሟል፡፡ በመሆኑም የውስጠ ድርጅት ስራችንን የማጠናከር ስራ ከምንም በላይ
የህዋስ አመራሩ እንደ ቁጥር አንድ ተግባር ተደርጎ ሊወሰድና በቀጣይነት በትኩረት መፈጸምና
መምራት ያለበት ሲሆን ይገባዋል፡፡

በሌላ በኩል የኪራይ ሰብሳቢነት ዋሻ የሆኑ የጥገኛ ዝቅጠት እና የሀይማኖት አክራሪነት አደጋዎች
ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ክፉኛ የሚፈታታኑ መሆናቸውን ግልፅ ሆኖ ሲያበቃ ከእነዚህ አደጋዎች
ጋር ተያይዞ የሚመጣውንና የሚታዩትን አመለካከትና ተግባር መልክ ከማስያዝ አንጻር በህዋስ
አመራሩ ዘንድ ክፍተት ተገምግሟል፡፡ በመሆኑም እነዚህን አዝማሚያዎች አመራሩ በአደገኝነታቸው
ልክ ታግሎ በማታገል ምንጫቸው እንዲደርቅ የማድርግ ተግባር በቀጣይ በትኩረት መፈጸጸም
አለበት፡፡

2.2 የአባሉ ሁኔታ


ከአመለካከት አንጻር የውስጠ ድርጅት ስራችንን ለማጠናከር በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ አባሉ
ለመውጣት የተወሰኑ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ከዚህ አንጻር የሚታዩ የአመለካከት
ክፍተቶች ሰፊ እንደሆኑ ተገምግሟል፡፡ የአመለካከት ዝንፈቱ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖሎቲካል ኢኮኖሚ
ለመናድና ልማታዊነትና ለማረጋገጥ እንደ ዋነኛ መሳሪያ የምንጠቀምበትን የህዋሳት ውይይት መድረክ
በአግባቡ ካለመጠበቅ ይጀምራል፡፡ ውይይት የማንጠባጠብ፣ የሚካሄዱ ውይይቶች ላይ የተሳትፎ
ውስንነት መኖሩ፣ የውይይቶች የብስለት ደረጃ ገና ወደሚፈለግበት ደረጃ ላይ ያለደረሰ መሆኑና
ለመርሀ-ግብር ፍጆታ ማካሄድ፣ የተጋጋለ የትግል ከባቢያዊ ሁኔታ ያለመፍጠር እና መሰል ክፍተቶች
በአባሉ ዘንድ ሰፋ ብለው የሚታዩ የአመለካከት ክፍተቶች ናቸው፡፡ ግቦቻችንን ለማሳካት እንደ
መሳሪያ ለመጠቀም ያስቀመጥናቸውን የለውጥ ስራዎች በአግባቡ ትርጉም ሰጥቶ ተግባራዊ ከማድረግ
አኳያም አባሉ ዘንድ ስፋ ያሉ ክፍተቶች እንዳሉ ተገምግሟል፡፡ ስለዚህ በቀጣይ አባሉ የዕለት ተዕለት
ግንባታ መድረኮችን ትርጉም ሰጥቶ በመጠቀምና የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በተለይም በመልካም
አስተዳደርና በኪራይ አጀንዳዎች ላይ የሰላ ትግል በማድረግ የውስጠ ድርጅት ስራችንን ከማጠናከር
አኳያ አሰላለፉና ቁመናው የተስተካከለ ሊሆን ይገባዋል፡፡

አባሉ የድርጅት ክንፉ ኃይላችን ነው፡፡ የተግባሮቻችን ስኬትና ውጤታማነት በሰፊው የአባላት
እንቅስቃሴ ላይ በእጅጉ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎቻችንን ወደ መሬት
በማውረድ ተጨባጭ ውጤት የማስመዝገብ ጉዳይ በአብዛኛው የአባሉ ተግባር ነው፡፡ ስለዚህ ከተግባር
አንጻር የአባሉን ሁኔታ በመገምገም ለቀጣይ ትምህርት መውሰድ ለግቦቻችን ስኬት የሚኖረው ፋይዳ
እጅግ የጎላ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በተግባራቸው ግንባር ቀደም አባላት እንዳሉ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ
ማየት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የድርጅትና የመንግስት ተግባራት ሳያንጠባጥቡ ቆጥሮ በመፈፀም
ውጤታማነት ከማረጋገጥ አኳያ ሰፊ ክፍተት ያለባቸው አባላት ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም፡፡
በመሆኑም የተግባር ማንጠባጠብ፣ በዕቅድ ያለመመራት፣ የቅልጥፍናና የስራ ጥራት ክፍተት፣
የአገልግሎት አሰጣጥ ውስንነቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ በቀጣይ አባሉ እነዚህን ክፍተቶች ፈጽሞ
ሊሻገራቸው ይገባል፡፡

3. ዓላማ

በህዋሷ ውስጥ ባሉት ተቋማት ላይ ሰራዊት በመገንባት በሰራዊቱ አማካይነት የኪራይ ምንጮች ላይ
የሰላ ትግል በማድረግና ምንጮቹን በማድረቅ ለኪራይ ሰብሳቢነት የማይመች የስራ አካባቢ
እንዲፈጠር ማድረግ፡፡
4. ቁልፍ ግብ
በህዋሷ ውስጥ ባሉት ተቋማት ላይ የተደራጀ የልማት ሰራዊት ተገንብቷል ፡፡
5. ዝርዝር ግቦችና የሚከናወኑ ተግባራት
ግብ 1፡ በህዋሷ የአደረጃጀትና የአሰራር ግልጽነት ተፈጥሯል፡፡
 የህዋሷን አደረጃጀት መፈተሸ፣
 በህዋሷ ውስጥ ያሉ አባላት ቁጥራቸውን ወቅታዊ ማድረግና ኦርኔል ማደራጀት፣
 በህዋሱ ስር የሚገኙ ሁሉም አባላት የድርጅት መታወቂያ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
 የድርጅት የአደረጃጀትና የአስራር መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ፡፡
ግብ 2፡ በሴክተሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተቀርፈዋል፡፡
 በተቋሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መለየት፣
 የመልካም አስተዳደር ችግሮቹንና መንስኤዎች መለየት፣
 የመልካም አስተዳደር ችግሮቹን የዕቅድ አካል ማድረግ፣
 ለመልካም አስተዳደር ችግሮቹ መፍትሔ መስጠትና ችግሮቹን መቅረፍ፣
 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ዕለት ተዕለት የስራ መመሪያ አድርጎ መፈጸም፡፡

ግብ 3፡ የህዋሷ አመራሩ መደብኛ ግንኙነት በዓመት 24 ጊዜ ተካሄዷል፡፡


 የአመራሩን ወቅታዊ የግንኙነት አጀንዳ መቅረጽ፣
 በአጀንዳው መሰረት መደበኛ ውይይት ማካሄድ፣
 የህዋሷንና የአባላትን የፖለቲካ አዝማሚያ በተመለከተ መገምገምና መረጃ
መለዋወጥ፣
 አቅጣጫዎችን ማስቀመጥና ተግባራዊነታቸውን መከታተል፡፡
ግብ 4፡ የህዋሷን ለመሰረታዊ ድርጅት ኮንፍረንስ ዝግጁ ተደርጓል
 የኮንፈረንስ ፕሮግራም መቀበልና ለህዋስ አባላት ጥሪ ማስተላለፍ፣
 በኮንፍረንሱ ሁሉም አመራር እና አባል መገኝቱን ክትትል ማድረግ፣

ግብ 5፡ ህዋሷ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ብስለትና ጥልቀት ያለውን ውይይት

በየሳምንቱ በተሟላሁኔታ እንዲያካሄዱ ተደርጓል፡፡

 የውይይት አጀንዳ በወቅቱ ለአባላት ማስተላለፍ፣


 እያንዳንዱ አባል በጊዜ ሰሌዳው መሠረት ውይይት ማካሄዱን መከታተል፣
 በውይይት ወደ ኋላ የሚቀሩ አባላት ደግፎ ማጠናከር፣
ግብ 6፡ በውይይቱ መነሻ ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ ሪፖርት ለመሰረታዊ

ድርጅቱ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

 በፎርማቱ መሠረት ሪፖርት ማቅረብ፣


 የቀረበውን ሪፖርት ቀሪ አደራጅቶ መያዝ፣
 የተላከውን ግብረ መልስ ለአመራሩና አባላት ማሳወቅ፣
 የሪፖርት ግብረ መልስ ተቀብሎ ማስተካከያ ማድረግ፡፡

ግብ 7፡ በተቋሙ በአመለካከታቸው ግንባር ቀደም የሆኑትን ምልመላ በማድረግ

የአባላት ቁጥር 30 በመቶ እንዲያድግ ተደርጓል፡፡

 በተግባራቸው ግንባር ቀደም የሆኑትን አባላት በእጩነት መመልመል፣


 በድርጅቱ መርህ መሠረት የአመለካከት ግንባታ ስራመስራት፣
 የዕጩ አባልነት መታወቂያ እንዲሰጣቸው ማድረግ ፣
 የእጩነት ጊዜ ገደብ ሲያጠናቅቁ ወደ ሙሉ አባልነት ማሸጋገር፡፡

ግብ 8፡ ከአባላት መዋጮ ገቢ ብር 11308 ተሰብስቦ ለድርጅት ማዕከል ገቢ

ተደርጓል፡፡

 የአባላት መዋጮ በየወሩ መሰብሰቡን ማረጋገጥ፣


 የተሰበሰበው መዋጮ ለደኢህዴን ማዕከል ገቢ መደረጉን ማረጋገጥ፣
 ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ ሰነዶች በተገቢው ሁኔታ መደራጀታቸውን ማረጋገጥ፣

ግብ 9፡ ከልሳናት ገቢ ብር 580 ተሰብስቦ ለድርጅት ማዕከል ገቢ ተደርጓል፡፡

 ዓመታዊ የልሳናት ፍላጎት ማዘጋጀትና ለደኢህዴን ማዕከል ማሳወቅ፣


 የልሳናት መዋጮ ከአባላት እንዲሰበሰብና ለደኢህዴን ማዕከል ገቢ እንዲደረግ
ማድረግ፣
 እያንዳንዱ አባል ባቀረበው ፍላጎትና ገቢ ባደረገው ገንዘብ ልክ ልሳናቱን
ማግኘቱን ማረጋገጥ፣

6. የክትትልና ድጋፍ ስርዓት


የተቀናጀና የተደራጀ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት ከመዘርጋት አንፃር የህዋሱ አመራር አባላትን በመከፋፈል
ስምሪት ወስዶ እንዲከታተልና እንዲደግፍ ይደረጋል፡፡ በዚህም መሠረት እያንዳንዱ የህዋስ አመራር
የሚደግፉት አባል የምትገኝበት ቁመና በየወቅቱ በመፈተሽ ለህዋሱና ለመሠረታዊ ድርጅት አመራሩም ጭምር
ግብረ መልስ የመስጠት ስራ ተግባራዊ ይደርጋል፡፡ እንዲሁም ሪፖርት ለመሠረታዊ ድርጅት መስጠት
ከመሰረታዊ ድርጅት ግብረ መልስ የመቀበል እና አባላትን የመደገፍ ስራ ጠንካራ የክትትል እና የድጋፍ
ስርዓታችን ሆኖ ይቀጥላል፡፡ በሌላ በኩል አባሉን በየወቅቱ በመገምገም ግብረ መልስ የመስጠት ስራ ይሰራል፡፡
በዚህም የአባላት ቁመና ማዕከል ያደረገ የደረጃ አሰጣጥ ስራ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ በአጠቃላይ የህዋስ አመራር
በተደራጀ አኳኃን ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በየወቅቱ በሚካሄደው አጠቃላይ የአመራር ግንኙነት
መድረክ ላይ መረጃ በመለዋወጥና በመናበብ አቅጣጫ እያስቀመጥን ተፈፃሚ የምናደርግ ይሆናል፡፡
የአመቱ ዕቅድ
የ 2 ዐዐ 8 በጀት ዓመት ዕቅድ

ተቁ ዋናና ዝርዝር ተግባራት

መለኪያ
ምርመራ

1 ኛ ሩብ ዓመት 2 ኛሩብ ዓመት 3 ኛ ሩብ ዓመት 4 ኛ ሩብ ዓመት

መስ ጥቅ ሕ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ ሐም ነሐሴ

1 በህዋሷ የአደረጃጀት እና የአሰራር ግልፅነት ተፈጥሯል % 100 50 50

1.1 በህዋሷ ስር ያሉትን የአባለት አደረጃጀት መገምገም

1.2 አደረጃጀታቸው ሊስተካከል የሚገቡ ጉዳዮችን መለየት


እና መልሶ በማደራጀት ማጠናከር

1.3 የህዋሷ የአባል ቁጥር ወቅታዊ ማድረግና ኦርኔል ማደራጀት

1.4 በህዋሷ የሚገኙ ሁሉም አባላት የድርጅት መታወቂያ


እንዲያገኙ ማድረግ

2 በሴክተሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተቀርፈዋል % 80 20 20 20 20

2.1 በተቋሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መለየት

2.2 የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መንስኤዎችን መለየት

2.3 የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የዕቅድ አካል ማድረግ

2.4 ለመልካም አስተዳደር ችግሮቹ መፍትሄ መስጠትና


ችግሮቹን መቅረፍ

3 የህዋስ አመራሩ መደብኛ ግንኙነት በአመት 24 ጊዜ ቁጥር 24 2 2 2 2 2 2 2 2 2 2 2 2


ተካሄዷል

3.1 የአመራሩን ወቅታዊ የግንኙነት አጀንዳ መቅረፅ

3.2 በአጀንዳው መሰረትመደብኛ ውይይት ማካሄድ

3.3 የአባላትን አዝማሚያ በተመለከት መረጃ መለዋወጥ

3.4 አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ እና ተግብራዊነታቸውን


መከታተል
4 በአመት ጊዜ በመሰረታዊ ድርጅት ኮንፍረንስ መገኝት ቁጥር 4 1 1 1 1

4.1 ከመሰረታዊ ድርጅት የኮንፍረንሱን ፕሮግራም መቀበልና


ለህዋሱ አመራርና አባል ጥሪ ማስተላለፍ

4.2 አመራሩና አባሉ በኮንፍረንሱ ላይ መገኝታቸውን ክትትል


ማድረግ

5 ህዋሷ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ብስለትና ጥለቀት ያለውን ዙር 48 4 4 4 4 4 4 4 4 4 4 4 4


ውይይት በየሳምንቱ በተሟላ ሁኔታ እንዲካሄድ ተደርጓል

5.1 የውይይት አጀንዳ በወቅቱ ለአባላት ማስተላለፍ

5.2 እያንዳንዱ አመራርና አባል በጊዜ ሰሌዳው መሰረት


ውይይት ማካሄዱን መከታተል

5.3 በውይይት ወደ ኃላ የሚቀሩ አባላትን ደግፎ ማጠናከር

6 በውይይቱ መነሻ ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ ሪፖርት ዙር 48 4 4 4 4 4 4 4 4 4 4 4 4


ለመሰረታዊ ድርጅት እንዲቀርብ ተደርጓል

6.1 በየሳምንቱ ሰኞ በፎርማቱ መሰረት የህዋሷን የውይይት


ሪፖርት ለመሰረታዊ ድርጅት ማቅረብ

6.2 የሪፖርቱን ቀሪ አደራጅቶ መያዝ

6.3 ግብረ መልስ ከመሰረታዊ ድርጅት መቀበልና ማስተካከያ


በማድረግ ምላሽ መስጠት

7 በተቋማችን በተግባራቸውና በአመለካከታቸው ግንባር በቁጥር 4 2 2


ቀደም የሆኑትን ምልመላ በማድረግ የአባላትን ቁጥር 40
በመቶ እንዲያድግ ተደርጓል

7.1 በተግባራቸው ግንባር ቀደም የሆኑትን አባላት በእጩነት


መመልመል

7.2 በድርጅቱ መርህ መሰረት የአመለካከት ግንባታ ስራ


መስራት

7.3 የእጩ አባልነት መታወቂያ መስጠት

7.4 የእጩነት ጊዜ ገደብ ሲያጠናቅቁ ወደ ሙሉ አባልነት


ማሸጋገር
794.67

794.67
8 ከአባላት መዋጮ ገቢ ብር 11308 ተሰብስቦ ለድርጅት ገቢ ብር

7674

580

580

580

580

699

699

699

699

699

699
ተደርጓል

8.1 የአባላት መዋጮ በየወሩ መሰብሰቡን ማረጋገጥ

8.2 የተሰበሰበው መዋጮ ለደኢህዴን ማዕከልገቢ መደረጉን


ማረጋገጥ

8.3 ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ ሰነዶች በተገቢው


መደራጀታቸውን ማረጋገጥ

8.4 አባላት ገቢ ለከፈሉበት ወርሀዊ መዋጮ ደረሰኝ አዘጋጅቶ


መስጠት

9 ከልሳናት ገቢ ብር አምስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ተሰብስቦ ብር 588 588


ለድርጅት ማዕከልገቢ ተደርጓል

9.1 አመታዊ ልሳናት ማዘጋጀት እና ለመሰረታዊ


ድርጅት/ለደኢህዴን ማሳወቅ

9.2 የልሳናት መዋጮ ከአባላት መሰብሰብ እና ለደኢህዴን


ማዕከል ገቢ ማድረግ

9.3 እያንዳንዱ አባል ባቀረበው ፍላጎትና ገቢ ባደረገው ገንዘብ


ልክ ደረሰኝ መስጠትና ልሳናቱን ማግኙቱን ማረጋገጥ

ማሳሰቢያ፡ - የአባላት መዋጮና የልሣናት ዕቅድ ከዚህ ቀደም ዕቅዱ የተላለፈ ስለሆነ በዚህ ዕቅድ አልተካተተም፡፡

You might also like