You are on page 1of 104

ለኅብረት ሥራ ኦዲተሮች የተዘጋጀ

የኅብረት ሥራ ሂሳብ አያያዝ የስልጠና ሰነድ

ፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ


ታህሳስ 2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ከሥልጠናዉ ምን ይጠበቃል ?
የስልጠናው ተሳታፊዎች በማንዋሉ አዘገጃጀት እና ይዘት ላይ
ግልጽ ሆነው ወደፊት ስልጠና በሚሰጡበት ጊዜ ለሰልጣኞች በቂ
ዕውቀት ለማስጨበጥ የሚያግዛቸውን ግንዛቤ ያገኛሉ፣
የኅብረት ሥራ ማህበራት የሂሳብ አያያዝ
የስልጠና እና ትግበራ ማንዋል

ፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ


ታህሳስ 2011
አዲስ አበባ
ማውጫ

ተ.ቁ ርዕስ ገጽ
መግቢያ 1-2
ክፍል አንድ
1 የሂሳብ አያያዝ ትርጉም፣ዓላማ፣ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ
1.1 ትርጉም 3
1.2 ዓላማ 3
1.3 አስፈላጊነት 3
1.4 ጠቀሜታ 3
1.5 የሂሳብ አያያዝ መረጃ ተጠቃሚዎች 4
1.6 መሰረታዊ መርሆዎች 5-9
ክፍል ሁለት
2 የሂሳብ አመዘጋገብ ዘዴዎች፣መሰረቶችና የሂሳብ መዋቅር 10
2.1 የሂሳብ አመዘጋገብ ዘዴዎች 10
2.2 የሂሳብ አያያዝ መሠረቶች 10
2.3 የሂሳብ መዋቅር (Charte of Accounts) 1

2.3 .1 የሃብት መደብ 11


2.3. 2 የዕዳ መደብ 11
2.3. 3 የካፒታል መደብ 12
2.3. 4 የገቢ መደብ 12
2.3. 5 ለሽያጭ የተገዙ ዕቃዎች ዋና መደብ 12
2.3. 6 የወጪ መደብ 12
2.4 መሠረታዊ የሂሳብ መዛግብቶችና ሠነዶች 16 - 17
ክፍል ሦስት
3 የሂሳብ አያያዝ ዑደት 18

3.1 የሂሳብ አያያዝ ዑደት ምንነት 18


3.1.1 የሂሳብ ልዉዉጥ 18
3.1.2 የሰነድ ዝግጅት 20
3.1.3 በመዝገብ መመዝገብ 20
3.1.4 ወደ ሂሳብ ቋት ማስተላለፍ 21
3.1.5 ያልተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ ማዘጋጀት 21
3.1.6 የሂሳብ ማስተካከያ ምዝገባ እና ወደ ሂሳብ ቋት ማስተላለፍ 22
3.1.7 የተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ ማዘጋጀት 22
3.1.8 የሂሳብ መግለጫ ማዘጋጀት 22
3.1.9 የሂሳብ መዝጊያ ምዝገባ 22
ክፍል አራት
4 የን/ቆጠራ፣የአገ/ተቀናሽ፣ሂሳብ አሰራርና የባንክ ሂሳብ ማስታረቅ 65

4.1 የንብረት ቆጠራ አሰራር 65 - 70


4.2 የቋሚ ንብረት እርጅና ተቀናሽ አሰራር 71 - 78
4.3 የባንክ ሂሳብ ማስታረቅ 78 - 81
ክፍል አምስት
5.1 ዕዝል 82 - 102
የቀጠለ…
ክፍል አንድ
የሂሳብ አያያዝ ትርጉም፣ዓላማ፣ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ
1.1 ትርጉም
የሂሳብ አያያዝ ማለት

መረጃ መሰብሰብ፣ማጠቃለል፣መተንተን፣መመዝገብና የተላ መረጃ


መስጠት የሚያስችል ሪፖርት ማዘጋጀትን ያጠቃልላል፡፡
1.2. ዓላማ
የኅ/ሥ/ማህበሩን የሂሳብ እንቅስቃሴ በመመዝገብ፣በመተንተ

ንና በማደራጀት በአባላቱና በባለድርሻ አካላት ዘንድ ተዓማኒነት እንዲኖር


ለማድረግ፣
የቀጠለ…
• ኅ/ሥ/ማ/ት በቁጠባም ሆነ በሌሎች ስራዎች ለሀገር ኤኮኖሚ
የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ለይቶ ለማወቅ፣
• ለሥራ አመራሩና ለአባላት ለውሳኔ የሚያመች ቀልጣፋና ወቅታዊ መረጃ
መስጠት፣
1.3 አስፈላጊነት
 ለሂ/ምርመራ ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ቀልጣፋና ጥራት ያለው
የኦዲት አገ/ለመስጠት፤
 አባላት በማህበራቸው ያላቸው እምነት እንዲጨምርና የባለቤትነት ስሜት
እንዲጎለብት ለማድረግ፣
የቀጠለ…
 አባላትና ከኅ/ሥ/ማኅበሩ ጋር የሥራ ግንኙነት ያላቸው ድርጅቶችና ተቋማት

በማህበሩ ላይ ጠንካራ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል፣


• ቀልጣፋና ዘመናዊ የቁጠባ ሥርዓት እንዲጠናከር ለማድረግ፤
 ተደራሽ፤አስተማማኝ እና ጥራት ያለው የኅ/ሥ/ማህበራት

የመረጃ ምንጭ ሥርዓት ለመዘርጋት፣


1.4 ጠቀሜታ
 ስለ ኅብረት ሥራ ማህበሩ ለመረዳትም ሆነ ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል

ያደርጋል፣
 የኅብረት ሥራ ማህበሩ አጠቃላይ ደህንነት እንዲጠበቅ ያደርጋል፤
የቀጠለ…
•ለሂሳብ ምርመራ ቅድመ ሁኔታዎች በማመቻቸት ሥራውን ቀልጣፋና ግልጽ
ያደርጋል፣
• ለኅብረት ሥራ ማህበሩ የወደፊት ዕቅድና ተግባራት ዝግጅት በቂ መረጃ
ለመስጠት ያስችላል፣
• የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን በተቀላጠፈ መንገድ ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር
ያስችላል፡፡
 አባላት ገንዘባቸዉን በወቅቱ በኅ/ሥ/ማኅበራቸው እንዲቆጥቡ ያደርጋል፤

 አባላት በማኅበራቸው ላይ ያላቸውን የተሳትፎ መጠን በግልጽ እንዲያውቁት


ያደርጋል፤
የቀጠለ…
• የኅብረት ሥራ ማኅበራት የቁጠባ ባህል እንዲዳብርና በሀገር ያላቸውን
የኢኮኖሚ ድርሻ ለይቶ ያስረዳል/ያሳውቃል
• ለመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለሚያደርጉት
ኢኮኖሚያዊ ሆነ ማኅበራዊ ጥናትና ምርምር እንደ መረጃ ምንጭ ሆኖ
ያገለግላል፣
• አዲስ ተቀጥረው ለሚገቡ ሂሳብ ሰራተኞች ግልጽ ሆነው ወደ ስራ
ፈጥነው እንዲገቡ ያደርጋል
1.5 የሂሳብ አያያዝ መረጃ ተጠቃሚዎች
 የውስጥና የውጪ መረጃ ተጠቃሚዎች በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡
የቀጠለ…
1.5.1 የውስጥ ተጠቃሚዎች፡-
 አባላት፣የኅ/ሥ/ማህበሩ ኃላፊዎች እና ቅ/ሠራተኞች ሲሆኑ፣

 አባላት በኅብረት ሥራ ማኅበራቸው ላይ ያላቸውን እንቅስቃሴ ለመረዳት፣

 የኅ/ሥ/ማህበሩን የሂሳብ መረጃዎች ወይም የሂሳብ መግለጫዎች፣


በኅ/ሥ/ማህበሩ ያሉትን ሀብትና ንብረት ለመቆጣጠር፣
 በባንክና በእጅ ምን ያህል ጥሬ ገንዘብ እንዳለው፣

 ተሰብሳቢ ሂሳብ እና ተከፋይ ዕዳን በመለየት ለመከታተል፣ስልት ለመንደፍ፣


የቀጠለ…
ገቢና ወጪ በማየት አትራፊ ወይስ አክሳሪ መሆኑን ለማወቅና ተገቢ

እርምጃ ለመውሰድ፣

1.5.2 የውጪ ተጠቃሚዎች፡-


 የውጪ ተጠቃሚዎች የምንላቸው በድርጅቱ እንቅስቃሴ በቀጥታም

ይሁን በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸውና ከኅብረት ሥራ ማህበሩ ውጪ ያሉ

አካላት የውጪ ተጠቃሚዎች ይባላሉ፡፡ እነርሱም፡-

1.የመንግስት ፖሊሲ አውጪዎች፣


 በአገሪቱ የኢኮኖሚ ድርሻ ውስጥ የሚኖራቸው ድርሻ በምን
የቀጠለ…

ሁኔታ ላይ እንዳለ የሚጠቁም በመሆኑ ለቀጣይ የፖሊሲ ውሳኔዎች


አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፣

2.የተለያዩ ድርጅቶች፣
እንደ ባንክና ኢንሹራንስ ያሉት ድርጅቶች ኅ/ሥ/ማህበሩ ምን አይነት
ቋሚ ሀብት እንዳለውና የድርጅቱ እንቅስቃሴ አትራፊ ወይስ አክሳሪ
መሆኑን በሚቀርቡት የሂሳብ መግለጫዎች መሠረት ለድርጅቱ ብድር
ለመስጠት ወይም የኢንሹራንስ ዋስትና ለመስጠት ይጠቀሙበታል፡፡

3.የመንግስት ገቢ ሰብሳቢ አካላት፣


የመንግስት ገቢ ሰብሳቢ አካላት ኅ.ሥ.ማ.ት ከቅጥር ሰራተኞች
የቀጠለ…
የሚሰበስቡትን የሥራ ግብር ፣የጡረታ ክፍያ፣ለአባላት ከሚደረግ
ትርፍ ክፍፍል የሚቆረጥ ታክስ… በተገቢው መንገድ እየተሰበሰበ
በወቅቱ ገቢ መደረጉን ለማረጋገጥ፣
መሰረታዊ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች
 ማንኛውም ኅብረት ሥራ ማህበር የሂሳብ ሰነዶችንና የሂሳብ
መግለጫዎችን ማዘጋጀት ያለበት አጠቃላይ ተቀባይነት ባላቸው የሂሣብ
አያያዝ መርሆዎች መሰረት መሆን አለበት፡፡እነዚህም
የቀጠለ…
ሀ. የንግድ ድርጅት ህጋዊነት /Business Entity Concept/
• የኅብረት ሥራ ማህበሩ የሥራ እንቅስቃሴ፣አሰራርና አመራር ራሱን ችሎ
ህጋዊ ሰውነት ያለው በመሆኑ ከባለቤቶቹ ማለትም ከአባላት የተለየና
ነጻነትና ተጠያቂነት ኖሮት የሚሰራ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡
• ኅብረት ሥራ ማህበሩ ኪሳራ ቢያጋጥመው ከአባላት የግል ንብረት
/ሀብት/ጋር ምንም ግንኙነት አይኖረውም
የቀጠለ…
ለ. ቀጣይነት /Going Concern/
• የሂሳብ አያያዝ ስርዓት ሲዘረጋ ኅብረት ሥራ ማህበሩ ላልተወሰነ ጊዜ
ይሠራል/ዘላቂነት/ይኖረዋል የሚል ግምት ተወስዶ የሂሣብ አያያዝ ሥርዓት
እንዲዘረጋለት የሚያደርግ ፅንሰ ሐሳብ ነው፡፡
• ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እድሜውን በቅድሚያ በመተንበይ
አይመሰረትም፡፡
• ቀጣይ በመሆኑም ቅድሚያ ኢንሹራንስ ይከፍላል፤የረጅም ጊዜ ብድር
ይበደራል፣ያበድራል፡፡
የቀጠለ…
ሐ. ተጨባጭ ማስረጃ /ደጋፊ ማስረጃዎች /Objective evidence/
 በሂሳብ ልውውጡ ሂደት በመዛግብቶች የሚደረጉ ምዝገባዎች በሙሉ
መከናወን ያለባቸው ተጨባጭና አስተማማኝ ከሆኑ የገቢ እና የወጪ
ማስረጃዎች ነው፡፡ የሂሳብ መግለጫዎች ተዘጋጅተው
ሪፖርት የሚሆኑትም እነዚህን ማስረጃዎች መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡
• በማስረጃ ተደግፎ የሚያዝ ሂሣብም ስህተቶችን ፈጥኖ ለማረም በሚቀርበው
የሂሣብ ሪፖርት ለአባላቱ ሙሉ እምነት የሚያሳድር ሲሆን ለሂሣብ ምርመራም
ምቹ ይሆናል፡፡
የቀጠለ…
መ. እንደ መለኪያ አካልነት /Unit of Measurement/
 የሂሣብ ልውውጥ የሚመዘገበው ሆነ ሂሣቡ የሚያዘው በገንዘብ መልክ ነው፡፡
ያለው አጠቃላይ ሀብት፣ የግዥ እንቅስቃሴ፣ የእርጅና ተቀናሾች በሙሉ
በገንዘብ መለኪያነት ተሰልተው ሂሣቡ በተገቢው
መዛግብት ተመዝግቦ መረጃዎቹ ተጠቃለው እንዲደራጁ ይደረጋል፣
የቀጠለ…

ሠ.የሂሣብ ወቅት /Accounting Period/


 አንድ የስራ ዘመን ሲሆን በጠቅላላ ጉባኤ በሚወሰነው መሰረት በመነሻነት

ከተያዘው ቀን ሂሳብ እስከ ተዘጋበት ዕለት ያለው ጊዜ የሂሳብ ወቅት ይባላል፣


የቀጠለ…
ረ. የገቢና ወጪ መጣጣም ወይም ተገጣጣሚነት /Matching/
 የሂሳብ ሪፖርቱ በቀረበበት የሂሣብ ዘመን ወቅት የታየው የተጣራ ገቢ ሁለት
መልክ ገጽታ ያለው ችግሮች እንዳለበት ታምኖበታል፡፡
1. የዘመኑን ገቢዎች ግንዛቤ ለማግኘት/Recognition of Revenue/
 በአንድ የሂሣብ ዘመን የኅብረት ሥራ ማህበሩ ገቢ ትክክለኛ ለመለካት
ለደንበኞቹ በዱቤ በተሸጠ መጠንና በተሰጠ አገልግሎት በሚገኘው ገቢ
መሠረት ነው፡፡
የቀጠለ…
2 - የዋጋ አመዳደብ /Allocation of Costs/
ኅ/ሥ/ማህበሩ ለዕቃ ወይም ለአገልግሎት ግዥ ቅድሚያ ክፍያ ይከፍላል በዚህ
መርህ መሰረት እንደተከፈለ በወጪነት አይዘ
ውም በወጪነት የሚይዘው ሂሳቡ በሚዘጋበት ጊዜ ነው
ለምሳሌ፡ወለድ ወጪ፣ኢንሹራንስ ወጪ…
ሰ. በቂ መግለጫ /ግልጽነት/ Adequate Disclosure/
• የምናቀርበው የሂሣብ ሪፖርትም ሆነ ሃሣብ አጭርና ግልጽ መሆን ይኖርበታል፡፡
የቀጠለ…
1.የተጠቀመበት የሂሳብ አያያዝ ዘዴ
•ኅ/ሥ/ማ/ት የሚስማማቸውን ዓይነት ዘዴ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

•ነገር ግን ለሂሣብ መግለጫዎቹና ሪፖርቶቹ ማብራሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ይሆናል፡፡


ለምሣሌ፡የቆጠራ ዘዴ፣የአገልግሎት ተቀናሽ ስሌት ዘዴ እና የመሳሰሉት ከሂሣብ
መግለጫ ሪፖርቱ ጋር ለመረጃ ተጠቃሚዎች ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
2. የግምት ለውጥ ሲደረግ
በሂሳብ ሪፖርት ተደርጎ የነበረ ንብረት ዋጋ ጨምሮ ተገምቶ ከሆነ
ምክንያቱ ግልጽ ሆኖ መብራራት አለበት፣

 
የቀጠለ…

3 - ያልታሰበ ድንገተኛ ዕዳ
ያልታሰቡ ዕዳዎች በሂሣብ ዘመኑ ሊከሰቱ ይችላሉ

ለምሳሌ ፡በፍርድ ቤት ተከሶ እንዲከፍል ሲወሰንበት፣ሲሆን

ባጋጠመበት ወቅት ጉዳዩን በዝርዝር ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል

4.በሂሳብ መግለጫ ዝግጅት ወቅት የሚያጋጠሙ ድንገተኛ ሁኔታዎች፣


• በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የሚከሰት አደጋ ማለትም ጎርፍ፣እሳት አደጋ
ምክንያት የሀብት መቀነስ ስለሚከሰት በግልጽ ማብራሪያ መዘጋጀት
አለበት፣
የቀጠለ…
ሸ. ቋሚነት /Consistency/
 ኅብረት ሥራ ማህበሩ የሚፈልገውን ስልት መርጦ መጠቀም ይችላል ነገር
ግን በየጊዜው ተለዋዋጭ መሆን የለበትም ምክንያቱ
የሂሳብ መግለጫዎቹን ውጤት ከፍ ወይም ዝቅ በማድረግ ተጽዕኖ
ያደርጋል፡፡ የተጠቀመበትን ስልት መቀየር ከፈለገ ከሂሣብ መግለጫ
ሪፖርቶች ጋር በማብራሪያ መግለጽ አለበት፡፡
የቀጠለ…
ቀ. ቁሣዊነት /materiality/
 ቁሳዊነት በማለት አንድን የሂሣብ ጉዳይ ለመወሰን እንደ ሂሣብ ባለሙያው
ብስለትና የሙያ ብቃት የሚወሰን ሲሆን የጉዳዩ መጠንና ስኬት ከጉዳዩ ጋር
ሲነጻፀር የሚኖረው ክብደትና ቅለት ከግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡
 ለምሳሌ፡- አነስተኛ ገንዘብ ለቋሚ ንብረት መጠገኛ ቢወጣ ሂሳቡን
በንብረትነት ሳይሆን በወጪነት ሊያዝ ይችላል፡፡ ወይም ከአመት በታች
የሚያገለግል ንብረት በወጪነት ሊመዘገብ ይችላል፣
የቀጠለ…
የሂሳብ አመዘጋገብ ዘዴዎች፣መሰረቶችና የሂሳብ መዋቅር
2.1 የሂሳብ አመዘጋብ ዘዴዎች/Accounting record methods/
የሂ/አመዘጋገብ ዘዴዎች በሁለት ክፍሎች ይመደባሉ፡፡ እነርሱም
2.1.1 ነጠላ ምዝገባ /single entry/ የአንድን ልውውጥ/ክንውን/ በአንድ
ሂሳብ ላይ ብቻ ለውጥ እንደሚያስከትል ሆኖ
የሚመዘገብበት ስልት ነው፡፡
የቀጠለ…
2.1.2 መንትያ ምዝገባ / double entry/
 ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣የንግድ ድረጀቶች፣ፋብሪካዎች እና
የመሳሰሉት የሚጠቀሙበት የሂሳብ አመዘጋገብ ስልት ሲሆን፣ የሂሳብ
ልዉዉጥ ክንወኑ ያሰከተለውን ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ
ልውውጥ /Transactions/ የሚመዘግቡበት እና የክስተቶችም ምክንያት
በሚያስረዳ መልኩ በቀኝና በግራ /በዴቢት እና በክሬዲት/በአንድ ጊዜ
የመመዝገብ ሂደት የመንትያ ምዝገባ ይባላል፡፡
የቀጠለ…

2.2. ሂሳብ አያያዝ መሰረቶች

የሂሳብ አያያዝ መሠረቶች በሁለት ይከፈላሉ፣

 2.2.1. የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴን መሰረት ያደረገ የሂሳብ አያያዝ / Cash


basis/
 የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴን መሰረት ያደረገ የሂሳብ አያያዝ/Cash basis/
የሽያጭ እንቅሰቃሴዎች በዱቤ ከሆኑ የማይመዘገቡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ
ገቢ ከሆኑ በገቢነት የመመዝገብ ሂደት ሲሆን እንዲሁም የግዥ
እንቅስቃሴዎች በጥሬ ገንዘብ ካልተከፈሉ በወጭነት የማይመዘገቡበት
ሂደት ማለት ነው፡፡
የቀጠለ…
2.2.2.ያልተሰበሰበ ገቢና ያልተከፈለ ዕዳን በመመዝገብ ላይ የተመሰረተ
/Accrual basis/
 ገቢ በጥሬ ገንዘብ የተሰበሰበም ይሁን ያልተሰበሰበ እንደ ገቢ
የሚመዘገብበት ሲሆን ወጪ ደግሞ በጥሬ ገንዘብ የተፈጸመም ይሁን
ያልተፈጸመ እንደ ወጭ የሚያዝበት ሂደት ማለት ነው፡፡
2.3. የሂሳብ መዋቅር/Chart of account /
 ኅ.ሥ.ማ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ሚዘጋጅ በሂሳብ እንቅስቃሴው
የሚጠቀምባቸውን የሂሳብ አርዕሥቶችና የሂሳብ መለያ ቁጥር
የሚያመለክት መግለጫ /Chart of accounts/ ይባላል፡፡
የቀጠለ…
• እንደየ ሥራ እንቅስቃሴው መጠን የሚዘጋጅ ይሆናል።
 እያንዳንዱ የሂሳብ አርዕስት በየሂሳብ መደቡ ስር እራሱን የቻለ
የሂሳብ ቁጥር ይኖረዋል፤
 በሂሳብ አያያዝ ስርአት ቅደም ተከተል መሰረት እያንዳንዱ
የሂሳብ ልውውጥ የሚመዘገብበት የሂሳብ መደቦች አሉ፡፡እነርሱም፡-
2.3.1 የሀብት(የንብረት) መደብ /Assets /
 በሁለት ይከፈላሉ፡- ተንቀሳቃሽ እና ቋሚ
የቀጠለ…
 ተንቀሳቃሽንብረት፡-

ጥሬገንዘብበዕጅ፣በባንክተሰብሳቢሂሳብ፣የተቆጠረጽ/
መሳሪያ፣ኢንቨስትመንት፣ቅ/ክፍያ፣ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
 ቋሚ ንብረት፡- ሊታዩ እና ሊዳሰሱ የሚችሉ ከአንድ በጀት አመት በላይ
የሚያገለግሉና የአገ/ ተቀናሽ ሊሰራላቸው የሚችሉ ሀብቶችን ይወክላል፡፡
እነርሱም፡- ጽ/ቤት፣መጋዘን፣መኪና፣መገልገያዎች፣የቢሮ ዕቃዎች ወ.ዘ.ተ.
ናቸው፡፡
2.3.2 የዕዳ መደብ /Liabilty/
 ዕዳ፡-የተበደረው፣በዱቤ የገዛው፣ የተሰበሰበ ታክሰ እና የመሳሰሉትን ሲሆን
ለምሳሌ፡-የደሞዝ ግብር፣የትርፍ ክፍፍል ታክስ፣የብድር ተከፋይ እና የአባላት
ቁጠባ
የቀጠለ…
2.3.3 የካፒታል መደብ /Capital/
 ከጠቅላላ ሀብት ተከፋይ ዕዳ ተቀንሶ የሚቀረው
ካፒታል(አንጡራሀብት)ይባላል፡፡
 የካፒታል መደብ ዕጣን/Share/፣ ስጦታን፣ የመጠባበቂያ
ሂሳብን፣ያልተከፋፈለ ትርፍን እና ስጦታን የሚይዝ ነው፡፡
  2.3.4 የገቢ መደብ /Revenue/
 ገቢ በስራ እንቅስቃሴ ከሚፈጸም ልውውጥ የሚገኝ ካፒታል በማሳደግ
(በመጨመር) ለውጥ የሚያስገኝ ከብድርና ከባንክ ወለድ፣ ከመመዝገቢያ
እና የመሳሰሉትን ገቢዎች የሚያጠቃልል የሂሳብ መደብ ነው፡፡
የቀጠለ…
2.3.5 የወጪ መደብ /Expenses/
 አስተዳደራዊ ወጪዎች ሲሆኑ እነርሱም የሰራተኛ ደመወዝ ፣መጓጓዣ
፣ለሠራተኛ ፣ለውሎ አበል፣ለስልክ ለመብራት እና ዉሃ፣ለብድር እና ለቁጠባ
ወለድ፣ የዘመኑ አገ/ተቀናሽ ወጪ ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡
 እነዚህ ከላይ በዝርዝር የተገለጹት የሂሳብ መደቦች እያንዳንዳቸው
በሥራቸው በርካታ የሂሳብ አርዕስቶች ይኖሯቸዋል የሂሳብ መደቦችንና
የሂሳብ አርዕስቶችን በቅደም ተከተል በዝርዝር የያዘ ሠንጠረዥ የሂሳብ
መዋቅር/Chart ofaccount / ይባላል፡፡
የቀጠለ…
 ለሂሳብ መደቦች መለያ መስጠት እንደ ኅብረት ስራ ማህበራቱ ሂሳብ
እንቅስቃሴ ስፋትና ጥበት የሚለያይ ቢሆንም በሂሳብ አያያዝ ስርአት ቅደም
ተከተል መሰረት የሀብት፣ እዳዎች፣ ካፒታል፣ገቢ፣ወጪ በተከታታይ
መቀመጥ አለባቸው፡፡እያንዳንዱ ልውውጥ የሚመዘገብበት የሂሳብ አርዕስት
በሂሳብ መዋቅር ላይ በሚገኝበት መደብ መሰረት በመሆኑ፣የትኛው የሂሳብ
መደብ በዴቢት እና የትኛው በክሬዲት በኩል መደበኛ ሚዛን እንደሚኖረው
እንመለከታለን፣
የሂሳብ መደቦችና የሂሳብ አርዕሰቶች የሂሳብ የሂሳብ መደቦችና የሂሳብ የሂሳብ ቁጥር
ቁጥር አርዕሰቶች
ሀብት/ንብረት 100 ካፒታል 300
ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 101 ዕጣ 301
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በቁጠባ 102 ስጦታ 302
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በተንቀሳቃሽ 103 ያልተከፋፈለ ትርፍ 303
የሚሰበሰብ ሂሳብ 104 ለብድር ዋስትና 304
የሚሰበሰብ ወለድ 105 ገቢ 400
ጽ/ቤት 120 ከባንክ ወለድ ገቢ 401
የጽ/ቤት አገ/ተቀናሽ 120-1 ከብድር ወለድ ገቢ 402
የቢሮ ዕቃ 121 ከመመዝገቢያ ገቢ 403
የቢሮ ዕቃ አገ/ተቀናሽ 121-1 ከቅጣት ገቢ 404
ዕዳ 200 ልዩ ልዩ ገቢ 405
ቁጠባ 201 ወጪ 500
የቁጠባ ወለድ 202 ለደመወዝ ወጪ 501
ብድር ተከፋይ 203 ለውሎ አበልና ትራንስፖርት 502
የብድር ወለድ 204 ለስልክ ውሃና መብራት 503
ሥራ ግብር 205 ለአገ/ተቀናሽ 504
ጡረታ ተከፋይ 206 ልዩ ልዩ ወጪ 505
ተ/ቁ የሂሳብ መደብ ሲጨምር ሲቀንስ መደበኛ
ሚዛን

1 ሀብት/ንብረት/Assets/ ዴቢት ክሬዲት ዴቢት

2 ዕዳ/Liabllity/ ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

3 ካፒታል/Capital/ ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

4 ገቢ/Revenue/ ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

5 ወጪ/Exepenses/ ዴቢት ክሬዲት ዴቢት


የቀጠለ…
2.4.መሰረታዊ የሂሳብ ሰነዶች እና መዛግበት፡-
 የኅበረት ስራ ማህበራት የሚጠቀሙባቸው ልዩ ልዩ ሰነዶችና መዛግብት
ያስፈልጋቸዋል፡፡
2.4 .1 መሠረታዊ ሂሳብ ሰነዶች
2.4.1.1 የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ / Cash Receipt Voucher /
• የዕጣ ገንዘብ፣ መመዝገቢ፣ ከብድር የሚገኝ ገንዘብ፣ ከቁጠባ፣ ከተሰብሳቢ
ሂሳብ የተሰበሰበ እና ከተለያዩ ምንጮች የሚገኝ ገቢ ገቢ የሚደረግበት)
ደረሰኝ ነው፡፡
የቀጠለ…
 የገንዘብመቀበያ ደረሰኝ ሲዘጋጅ በደረሰኙ ላይ ገቢ የሆነው ገንዘብ፣ገቢ
የሆነበት ምክንያት ገቢ የሆነው ገንዘብ መጠን በአሃዝና በፊደል፣ገቢ የሆነበት
ቀን ወርና ዓ/ም በግልጽ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው ከተጻፈ በኋላ ገንዘቡን
የተቀበለው ገንዘብ ያዥ ይፈርምበታል፡፡
 ደረሰኙበሦስት ኮፒ ተዘጋጅቶ የመጀመሪያው ለገንዘብ ከፋዩ፣ሁለተኛው
ለሂሳብ ክፍል ሦስተኛው ከጥራዙ ጋር ይቀራል፡፡
የቀጠለ…
2.4.1.2 የገንዘብ ወጪ ማዘዣ /Payment Voucher/
 በጥሬ ገንዘብ ወይም በቼክ ወጪ በሚያደረግበት ወቅት የሚዘጋጅ ሰነድ
ገንዘብ ከእጅ ወይም ከባንክ ወጭ ሆኖ ክፍያ የሚፈጸምበት ሰነድ ነው፡፡
 ምሳሌ፡-
ለደመወዝ፣ ለአባላት ብድር ፣ለቋሚ ዕቃ ግዥ፣ ለጽ/መሳሪያ፣
ለትራንስፖርት፣ ለወሎ አበል፣ለኪራይ … ወዘተ
 የወጪ ደረሰኝ በሁለት ኮፒ ይዘጋጃል የመጀመሪያው ከወጪ ማስረጃ
(ደጋፊ)ሰነዶች ጋር ተያይዞ በሂሳብ ክፍል ይቀመጣል ሁለተኛው ኮፒ በጥራዙ
ውስጥ ይቀመጣል፡፡
የቀጠለ…
2.4.2. የሂሳብ መዘግብቶች /Journals /
2.4.2.1. አጠቃላይ መዝገብ /General Journal /
ማንኛውም አይነት የልውውጥ ለምሳሌ የማስተካክያ ሂሳቦች፣ጊዚያዊ
ሂሳቦችን ለመዝጋት፣ኅብረት ሥራ ማህበሩ በልዩ መዝገብ ገቢና
ወጪውን ለያይቶ የማይጠቀም ከሆነ የገቢና የወጪ ሂሳቦች
የሚመዘገቡበት መዝገብ ነው፡፡በአጠቃላይ መዝገብ የተመዘገቡ ሂሳቦች
በሙሉ በአጠቃላይ የሂሳብ ቋት እና በግል የሂሳብ ቋቶች ይተላለፋሉ፡፡
2.4.2.2. የጥሬ ገንዘብ ገቢ መዝገብ
ከተለያዩ የገቢ ምንጮች በገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ የተሰበሰቡትን
የምንመዘግብበት ነው፡፡
የቀጠለ…
2.4.2.3 የጥሬ ገንዘብ ወጪ መዝገብ
 በወጪ ማዘዣ ደረሰኝ ተዘጋጅቶ ከቀረቡት ደጋፊ የወጪ የሂሳብ
መረጃዎች ጋር በማገናዘብ በኅብረት ስራ ማህበሩ የኃላፊነት ስልጣን
በተሰጣቸው ግለሰቦች ተፈርሞና ፀድቆ ክፍያ የተፈጸመባቸው የጥሬ ገንዘብ
የወጭ ሂሳቦች የሚመዘገብበት መዝገብ ነው፡፡
2.4.2.4 የገቢና ወጪ መዝገብ/Combination journal/
  . የገቢም የወጪም ሂሳቦች በአንድ ላይ የሚመዘገቡበት ነዉ
 
የቀጠለ…

ገ/መ/ደ/RV/ የሂሳብ
ወጪ/ማ/P V/ መዝገብ
ማስ/ሰነድ/J V/ /Journal/

የሂ/ቋት
/Ledger/
ክፍል ሦስት
3. የሂሳብ አያያዝ ዑደት /The Accounting cycle/
3.1 የሂሳብ አያያዝ ዑደት ምንነት፡-
 የሂሳብ አያያዝ ዑደት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች ያጠቃልላል ፡፡

3.1.1 ልውውጥ
3.1.2 የሰነድ ዝግጀት
3.1.3 በመዝገብ መመዝገብ
3.1.4 ወደ ቋት ማሰተላለፍ
3.1.5 ያልተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ
3.1.6 የሂ/ማስተካከያ ምዝገባ እና ወደ ቋት ማሰተላለፍ
3.1.7 የተስተካከለ የሂብ ሚዛን መሞከሪያ
3.1.8 የሂሳብ መግለጫ ዝግጀት
3.1.9 የመዝጊያ ምዝገባ
የቀጠለ…
3.1.1 ልውውጥ
 በገንዘብና በዓይነት ሊገለጽ የሚችል የመለወጥ፣በመግዛት እና በስጦታ
ወይም በብድር የመቀበል ወይም የመስጠት ክንውን መፍጠር ማለት ነው፡፡
 ለምሳሌ፡-ዕቃ/አገልግሎት መግዛት፣መበደር፤ ስጦታ መቀበል እና ልዩ ልዩ
ወጪዎችን መክፈል ሊገለጽ የሚችል የክንውን ክስተት ነው፡፡ልውውጦችን
በመዝገብ ላይ ከማስፈሩ በፊት በመነሻነት የተመደበው ሀብት፣ዕዳ እና
ካፒታል መለየት ይኖርበታል፡፡ በመቀጠልም የተለየው ሀብትና ዕዳ በሀብትና
ዕዳ መግለጫ ብሎም በቋሚ መዝገብ (በአጠቃላይ መዝገብ)ላይ ይሰፍራል ፡፡
የቀጠለ…
3.1.4 ወደ ሂሳብ ቋት ማሰተላለፍ /Posting /የሂሳብ ቋት የራሱ ባህሪ ያለው
የንብረት፣የዕዳ፣የካፒታል፣ የገቢና ወጪ ሂሳብ ዓይነት ለየብቻ በሂሳብ አርዕስቱ
ተለይቶ የሚመዘገብበት ማለትነው፡፡በሂሳብ መዝገብ የተመዘገበው እያንዳንዱ
የገቢና የወጪ ሂሳብ አርዕስት ለየብቻ ወደ ተከፈተለት የሂሳብ ቋት እያለፈ
ይሰበሰባል ፡፡ይህ ከአጠቃላይ ወይም ከልዩ መዝገብ ወደ ቋት የማሰተላልፍ ሂደት
ፖሰቲንግ ወይም የማወራረስ ሂደት ይባላል፡፡ የሂሰብ ቋት እንደ አጠቃላይ ወይም
ልዩ መዝገብ ሁሉ የቀን ዝርዝር፣የማጠቃቀሻ እንቅሰቃሴ ዴቢት ክሬዲት እና
የሚዛን አምዶች ይኖርበታል፡፡
የቀጠለ…
3.1.5 የሂሳብ መተንተኛ ማዘጋጀት/work sheet/
 እያንዳንዱ የሂሳብ ርዕሰ ከሂሳብ ማሰተካክያ በፊት እና በማሰተካክያ ጊዜ
የሚኖረውን ሚዛን እንዲሁም የሂሳብ መግለጫዎችን የሚያሳይ ጊዜአዊ
የስራ መተንተኛ ወረቀት የሂሳብ መተንተኛ ይባላል፡፡
3.1.6 ያልተስተካከለ ሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ
 እያንዳንዱ የሂሳብ አርዕስት በሂሳብ ቋት/Ledger/ላይ የሚኖረው ሚዛን
በዴቢት እና ክሬዲት ተለይቶ ከተመዘገበ በኋላ የሁለቱም ጎን ምዝገባ
ጠ/ድምር እኩል መሆኑን የሚረጋገጥበት ሲሆን ማስተካከያ ሂሳብ ከሚባሉት
ማለትም አገልግሎት ተቀናሽ፣ወለድ የመጨረሻ ቆጠራ የመሳሰሉትን ሂሳቦች
አያካትትም፡፡
የቀጠለ…
3.1.7 የሂሳብ ማስተካክያ ምዝገባ እና ወደ ቋት ማሰተላለፍ
 በበጀት ዘመኑ ማስተካክያ የሚያስፈልጋችው የወጪ ወይም የገቢ ክስተቶች
እንደ አላቂ የጽፈት መሳሪዎች፣ኢንሹራስ፣ ተሰበሰሳቢ ሂሳቦች፣የእርጅና
ተቀናሽ ወጪ፣…ወ.ዘተ በአመቱ መጨረሻም ሂሳብ ውሰጥ ለማካተት የሂሳብ
ማስተካክያ ይሰራላቸዋል
3.1.8 የተስተካከለ ሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ
 የሂሳብ ማስተካክያ ምዝገባን ወደ ቋት የማሰተላለፍ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ
እያንዳንዱ የሂሳብ አርዕስት የሂሳብ ቋት የመጨረሻ ሚዛን እኩል መሆኑን
ለማረጋገጥ የሚሰራ ማመዛዘኛ ነው፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ የሂሳብ
መግለጫዎች ይዘጋጃሉ፡፡
የቀጠለ…
3.1.6 የሂሳብ መግለጫ ማዘጋጀት
 በሂሳብ ዓመቱ መጨረሻ የሂሳብ አቋም ለማወቅ የሚዘጋጅ የትርፍና
ኪሳራ /የገቢና ወጪ መግለጫ/፣የሃብት እና ዕዳ መግለጫ፣የጥሬ ገንዘብ ፍሠት
መግለጫ /ካሽ ፍሎው/… ወዘተ ማለት ነው::
3.1.6 የሂሳብ መዝጊያ ምዝገባ
 በበጀት ዘመኑ መጨረሻ በትርፍና ኪሳራ መግለጫ የሚታዩ ጊዚያዊ የሂሳብ
መደቦች በራሳቸው የማጠናቀቂያ ሂሳብ ምዝገባ ከተዘጉ በኋላ የማይዘጉ
ወይም ቋሚ ሂሳቦች ለሚቀጥለው ዓመት ማዘጋጃ ምዝገባ በማካሄድ
ወደሚቀጥለው ዓመት እንዲተላለፉ ያደርጋል፡፡
9. የሂሳብ
መዝጊያ ምዝገባ
የሂሳብ አያያዝ ማዘጋጀት 1.የሂሳብ
ዑደት
ልዉዉጥ
8.የሂሳብ 2. የሰነድ
መግለጫ
ማዘጋጀት ዝግጅት

7.የተስተካከለ ሂሳብ
3. ወደ
መሞከሪያ ሚዛን
ማዘጋጀት
መዝገብ
ማስተላለፍ
4.ወደ ሂሳብ
6. የማስተካከያ ሂሳብ
መመዝገብ ቀት
5.ያልተስተካከለ የሂሳብ
መሞከለሪያ ሚዛን ማዘጋጀት
ማስተላለፍ
ምሳሌ
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብ/ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማህበር፡-
 በኅብረት ሥራ ማህበሩ በተዘጋጀው የሂሳብ መዋቅር መሠረት የሂሳብ
እንቅስቃሴውን ሲያካሂድ ቆይቶ ሰኔ 30/2007 ዓ/ም ሂሳቡን በመዝጋት
በኦዲት ሪፖርቱ የሂሳብ አቋም መነሻ በማድረግ ሂሳብ ሠራተኛው ለቀጣይ
እንቅስቃሴ ዝግጁ አደረገ፡፡ በዚህም መሠረት የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሂሳብ
መዋቅር በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር የሂሳብ መወቅር/Chart ofaccount/
የሂሳብ መደቦችና የሂሳብ አርዕሰቶች የሂሳብ የሂሳብ መደቦችና የሂሳብ አርዕሰቶች የሂሳብ ቁጥር
ቁጥር
ሀብት/ንብረት/ / 100 ካፒታል/ / 300
ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 101 ዕጣ 301
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በቁጠባ 102 ስጦታ 302
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በተንቀሳቃሽ 103 ያልተከፋፈለ ትርፍ 303
የሚሰበሰብ ሂሳብ 104 ገቢ/ / 400
የሚሰበሰብ ወለድ 105 ከባንክ ወለድ ገቢ 401
ጽ/ቤት 120 ከብድር ወለድ ገቢ 402
የጽ/ቤት አገ/ተቀናሽ 120-1 ከመመዝገቢያ ገቢ 403
የቢሮ ዕቃ 121 ከቅጣት ገቢ 404
የቢሮ ዕቃ አገ/ተቀናሽ 121-1 ልዩ ልዩ ገቢ 405
ዕዳ / / 200 ወጪ/ / 500
ቁጠባ 201 ለደመወዝ ወጪ 501
የቁጠባ ወለድ 202 ለው፤ሎ አበልና ትራንስፖርት 502
ብድር ተከፋይ 203 ለስልክ ውሃና መብራት 503
ተከፋይ ወለድ 204 ለአገ/ተቀናሽ 504
ሥራ ግብር ተከፋይ 205 ልዩ ልዩ ወጪ 505
ጡረታ ተከፋይ 206
የቀጠለ…
በተዘጋጀው የሂሳብ መዋቅር መሰረት ከሰኔ 30/2007 ዓ/ም ኦዲት ሪፖርት
መነሻ አድርጎ ወደ ቀጣይ ዓመት ሥራ ገብቷል፡፡
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድርኃ/የተ/ የኅብረትሥራማህበር
የሂሳብ መክፈቻ (መነሻ ሂሳብ)
1/11/2007 ዓ/ም
የሂሳብ አርዕስት ዴቢት ክሬዲት
ተንቀሳቃሽ ሀብት
ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 1500.00
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በቁጠባ 985300.00
ከብድር ተሰብሳቢ 150000.00
ከወለድ ተሰብሳቢ 5500.00
ቋሚ ሀብት
ጽ/ቤት 80000.00
የጽ/ቤት የተ/አገ/ተቀናሽ 8000.00
የቢሮ ዕቃ 45000.00
የቢሮ ዕቃ አገ/ተቀናሽ 11250.00
ዕዳ
የአባላት ቁጠባ 537000.00
ለቁጠባ ወለድ ተከፋይ 20245.00
ካፒታል
ዕጣ 600000.00
መጠባበቂያ 53415.00
ያልተከፋፈለ ትርፍ 37390.00
አጠቃላይ መዝገብ ገጽ፡- 020
ቀን የሂሳብ አርዕስት ማጠቃቀሻ ቁጥር ዴቢት ክሬዲት
ሐምሌ ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 1500.00
1/2007 ጥሬ ገንዘብ በባንክ በቁጠባ መነሻ ሀብትና ዕዳ
ዓ/ም መግለጫ 985300.00
ከብድር ተሰብሳቢ 150000.00
ከወለድ ተሰብሳቢ 5500.00
ጽ/ቤት 80000.00
የጽ/ቤት አገ/ተቀናሽ 8000.00
የቢሮ ዕቃ 45000.00
የቢሮ ዕቃ አገ/ተቀናሽ 11250.00
ቁጠባ 537000.00
ለቁጠባ ወለድ ተከፋይ 20245.00
ዕጣ 600000.00
መጠባበቂያ 53415.00
ያልተከፋፈለ ትርፍ 37390.00
ሰኔ 30 ቀን 2007 ከተዘጋጀው
መነሻ ሀብትና ዕዳ መግለጫ
የቀጠለ…
 በአጠቃላይ መዝገብ ከሰፈረ በኋላ የተደረጉ ልውውጦች በሚከተለው
መሰረት በመዛግብት ይመዘገባሉ፡፡
• በሀምሌ ወር 2007ዓ/ም ያከናዎናቸው ልውውጦች የሚከተሉት ናቸው
• በተገቢው መሰ/ሰነድ የሰፈሩና የተሰነዱ ናቸው የሚል ታሳቢ ተወስዷ ል፡፡
 በዚህም መሰረት ከተደረጉት ልውውጦች ቀጥሎ በሂሳብ መዛግብት
መዝግቧል፡፡ በሀምሌ ወር 2007 ዓ/ም በተዘጋጁት መሰረታዊ የሂሳብ ሰነዶች
መሰረት የተደረጉት ልውውጦች መረጃ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡
1. በ5/11/07 ለአባላት ብድር ብር 250,000.00 ከባንክ ወጪ ሆኖ ተሰጠ የወጪ ደረሰኝ
ቁጥር 365
2. በ 10/11/07 ለውሎ አበል ብር 500.00 ከዕጅ ወጪ ሆኖ ተከፈለ የወጪ ካ/ቁጥር 366
3. በ12/11/07 ከብድር ብር 85,000.00 ከዋና ብር 3,400.00 ከወለድ ተሰበሰበ የገቢ
ደ/ቁጥር 202
4. በ/30/11/07 ብር 30,000.00 የአባላት ቁጠባ ተሰበሰበ የገቢ ደ/ቁጥር 203
5. 30/11/07 ብር 3,000.00 ለደመወዝ ወጪ ሆነ የወጪ ካ/ቁጥር 367
6. በ30/11/07 ብር 115,442.00 ከዕጅ ወደ ባንክ ገቢ ሆነ የማስተካከያ ሰነድ ቁጥር 050
 ከላይ የተዘረዘረው የልውውጥ መረጃ በገቢና ወጪ መዝገብ እንደሚከተለው
ተመዝግቧል፣
የገቢ እና የወጪ ገጽ 85
የገቢ ጥሬ ገንዘብ በዕጅ ጥሬ ገንዘብ በባንክ ተሰብሳቢ ሂሳብ ተሰብ ለአበል ቁጠባ ለደመ ለጡረ ለሥራ
ዝርዝር ደ/ና ሳቢ ወጪ ወዝ ታ ግብር
ወለድ ተከፋይ
የወ

ማ/ ዴቢት
ሐምሌ

ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት ክሬዲ ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት ክሬዲ
ቀን

ቁ ት ት

05 የተሰጠ 365 250000 250000


ብድር

10 ለአበል 366 500 500


ወጪ

12 ብድር 202 88400 85000 3400


የተሰበ
ሰበ
30 ከአባላ 203 30000 30000

ቁጠባ
30 ለደመ 367 2458 3000 210 332
ወዝ
ወጪ
30 ከዕጅ 055 115442 115442
ወደ
ባንክ
30 ድምር 118400 118400 115442 250000 250000 85000 3400 500 30000 3000 210 332
ወደ ሂሳብ ቋት( ሌጀር) ማስተላለፍ
 ለያንዳንዱ የሂሳብ አርዕስት አብይ ሌጀር ተዘጋጅቶለት ይተላለፋል፡፡
 በተሰብሳቢ እና በተከፋይ ሂሳብ በአብይ ሌጀር ያለው በእያንዳንዱ አበዳሪና ተበዳሪ የግል
ሂሳብ ቋት ይኖረዋል የግል ሂሳብ ቋት ድምር ከተሰብሳቢና ከተከፋይ አብይ ሂሳብ ቋት ጋር
እኩል መሆን አለበት፡፡
ሂሳብ አርዕስት ፡- ጥሬ ገንዘብ በዕጅ የሂሳብ ቁጥር፡-

ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን

ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲ



ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 1500

ሐም.30 07 የወሩገቢ እና ወጪ ገ/ እና 118400 118400 1500


ወ/መ/ገ/85
የሂሳብ አርዕስት ፡- ጥሬ ገንዘብ በባንክ በቁጠባ የሂሳብ ቁጥር፡- 102
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
መነሻ አጠ/መ/ገ/020 985300 00
ሐም.1 07
የወሩገቢ እና ወጪ ገ/ና ወ/መ/ገ/85 115442 00 250000 00 850742 00
ሐም.30 07

ከባንክ ወለድ ገቢ
የሂሳብ07አርዕስት ፡- ተሰብሳቢአጠ/መ/ገ/021
 ሐም30 ሂሳብ 12759 00 863501
የሂሳብ 00
ቁጥር፡- 104
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
መነሻ አጠ/መ/ገ/020 150000 00
ሐም.1 07
የተሰበሰበና የተሰጠ ገ/ወ/መ/ገ/85 250000 00 85000 00 315000 00
ሐም.30 07
 የሂሳብ አርዕስት ፡- ተሰብሳቢ ወለድ የሂሳብ ቁጥር፡- 105
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 5500 00

ሐም.30 07 የተሰበሰበ ወለድ ገ/ወ/መ/ገ/85 3400 00 2100 00

ሐም.30 07 ተሰብሳቢ ወለድ አጠ/መ/ገ/21 1284 25 3384 00


የሂሳብ አርዕስት ፡- ጽ/ቤት የሂሳብ ቁጥር፡- 120
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

ሐምሌ1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 80000 00

የሂሳብ አርዕስት ፡- የጽ/ቤት የተ/አገ/ተቀናሽ የሂሳብ ቁጥር፡- 120-1


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት

ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 8000 00

ሐ.30 07 የወሩ አጠ/መ/ገ/21 667 00 8667 00

አገ/ተቀናሽ
የሂሳብ አርዕስት ፡- የቢሮ ዕቃ የሂሳብ ቁጥር፡- 121

ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን


ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 45000 00
የሂሳብ አርዕስት ፡- የቢሮ ዕቃ የተ/አገ/ተቀናሽ የሂሳብ ቁጥር፡- 121-1
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐምሌ1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 11250 00

ሐም.30 07 የወሩ አገ/ተቀናሽ አጠ/መ/ገ/21 937 00 12187 00

የሂሳብ አርዕስት ፡- ቁጠባ የሂሳብ ቁጥር፡- 201


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 537000 00

ሐም.30 07 የቁጠባ ገቢ ገ/ወ/መ/ገ/85 30000 00 567000 00

የሂሳብ አርዕስት ፡- ለቁጠባ ወለድ ተከፋይ የሂሳብ ቁጥር፡- 202


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 20245 00

ሐም.30 07 ለወለድ ወጪ አጠ/መ/ገ/021 1471 20 21716 20


የሂሳብ አርዕስት ፡- ለሥራ ግብር ተከፋይ የሂሳብ ቁጥር፡- 205
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐምሌ1 07 ለሥራ ግብር ተከፋይ ገ/ወ/መ/ገ/85 332 00 332 00

የሂሳብ አርዕስት ፡- ለጡረታ ተከፋይ የሂሳብ ቁጥር፡- 206


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 ለጡረታ የተከፈለ ገ/ወ/መ/ገ/85 210 00 210 00

ሐም.30 07 የመዝጊያ ምዝገባ አጠ/መ/ገ/22 210 00 -- --

የሂሳብ አርዕስት ፡- ዕጣ የሂሳብ ቁጥር፡- 301


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/20 600000 00 600000 00

ሐም.30 07 ካልተ/ ትርፍ የዞረ አጠ/መ/ገ/21 37390 00 637390 00


የሂሳብ አርዕስት ፡- መጠባበቂያ የሂሳብ ቁጥር፡- 302
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐምሌ1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 53415 00 53415 00

የሂሳብ አርዕስት ፡- ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ቁጥር፡- 303


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 መነሻ አጠ/መ/ገ/020 37390 00 37390 00

ሐም.30 07 ወደ ዕጣ የዞረ አጠ/መ/ገ/21 37390 00 - -

የሂሳብ አርዕስት ፡- የገቢና የወጪ ማጠቃለያ የሂሳብ ቁጥር፡- 304


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.30 07 የመዝጊያ ምዝገባ አጠ/መ/ገ/22 14043 25 5104 00 14043 25 5104 00
የሂሳብ አርዕስት ፡- ወለድ ገቢ የሂሳብ ቁጥር፡- 401
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.30 07 ከወለድ ገቢ ገ/ወ/መ/ገ/85 14043 25 14043 25

ሐም.30 07 የመዝጊያ ምዝገባ አ/ጠ/መ/ገ/22 14043 25 -- --

የሂሳብ አርዕስት ፡- ለደመወዝ ወጪ የሂሳብ ቁጥር፡- 501


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.30 07 ለደመወዝ የተከፈለ ገ/ወ/መ/ገ/85 3000 00 3000 00

ሐም.30 07 የመዝጊያ ምዝገባ አ/ጠ/መ/ገ/22 3000 00 -- --

የሂሳብ አርዕስት ፡- ለአበል ወጪ የሂሳብ ቁጥር፡- 502


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.30 07 ለአበል የተከፈለ ገ/ወ/መ/ገ/85 500 00 500 00

ሐም.30 07 የመዝጊያ ምዝገባ አ/ጠ/መ/ገ/22 500 00 -- --


የሂሳብ አርዕስት ፡- የአገ/ተቀ/ወጪ የሂሳብ ቁጥር፡- 503
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.30 07 የወሩ አገ/ተቀናሽ አጠ/መ/ገ/21 1604 00 1604 00

ሐም.30 07 የመዝጊያ ምዝገባ አጠ/መ/ገ/22 1604 00 -- --

የሂሳብ አርዕስት ፡- ወለድ ወጪ የሂሳብ ቁጥር፡- 504


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐም.1 07 የወለድ ወጪ አጠ/መ/ገ/21 1471 20 1471 20

ሐም.30 07 የመዝጊያ ምዝገባ አጠ/መ/ገ/22 1471 20 -- --

የተሰብሳቢ ሂሳብ የግል ሂሳብ ቋት


የተበዳሪ ስም ፡- አቶ ለማ ተሰማ የሂሳብ ቁጥር፡- 103-1
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ግን 2 2 የተሰጠ ብድር የገ/ናወ/መ/ገ82 150000 00 150000 00

ሐም30 30 የተመለሰ ብድር ገ/ወ/መ/ገ/85 85000 00 65000 00 -- --


የተበዳሪ ስም ፡- ወ/ሮ አገር ይልማ የሂሳብ ቁጥር፡- 103-2
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐምሌ 30 07 የተሰጠ ብድር የገ/ወ/መ/ገ/85 130000 00 130000 00

የተበዳሪ ስም ፡- አቶ ልዩ ሆነልኝ የሂሳብ ቁጥር፡- 103-3


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ሐምሌ 30 07 የተሰጠ ብድር የገ/ወ/መ/ገ/85 120000 00 120000 00

የተከፋይ ሂሳብ የግል ሂሳብ ቋት


የተበዳሪ ስም ፡- ወ/ሮ ነኢማ ኑሩ የሂሳብ ቁጥር፡- 201-1
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ጥር30 07 ቁጠባ የገ/ናወ/መ/ገ66 90000 00 90000 00

የካ.30 07 የተቆተበ ገንዘብ የገ/ናወ/መ/ገ67 50000 00 140000 00


የተበዳሪ ስም ፡- አቶ ልዩ ሆነልኝ አገር የሂሳብ ቁጥር፡- 201-2
ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ጥር30 07 ቁጠባ የገ/ናወ/መ/ገ66 80000 00 80000 00

የካ.30 07 የተቆተበ ገንዘብ የገ/ናወ/መ/ገ67 50000 00 130000 00

የተበዳሪ ስም ፡- ወ/ሮ አገር ይልማ የሂሳብ ቁጥር፡- 201-3


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ጥር30 07 ቁጠባ የገ/ናወ/መ/ገ66 100000 00 100000 00

የካ.30 07 የተቆተበ ገንዘብ የገ/ናወ/መ/ገ67 50000 00 150000 00

የተበዳሪ ስም ፡- ወ/ሮ አለም አያና የሂሳብ ቁጥር፡- 201-4


ቀን መግለጫ ማጠቃቀሻ እንቅስቃሴ ሚዛን
ዴቢት ክሬዲት ዴቢት ክሬዲት
ጥር30 07 ቁጠባ የገ/ናወ/መ/ገ66 100000 00 100000 00

የካ.30 07 የተቆተበ ገንዘብ የገ/ናወ/መ/ገ67 80000 00 180000 00


 በወሩ ውስጥ የተከናወነውና በሂሳብ መዝገብ የተመዘገበው
ልውውጥ ወደ ሌጀር ከተላለፈ በኋላ ወደ ሌጀር የተላለፈው መረጃ
በሙሉ አመዘጋገቡ ጤናማ ለመሆኑ ያልተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን
መሞከሪያ ሚዛን በማዘጋጀት መረጋገጥ አለበት፡፡
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃላፊነቱ የተ/ የኀብረት ሥራ ማህበር
ያልተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ
ሐምሌ 30/2007 ዓ/ም
የሳብ አርዕስት የሂሳብ ቁጥር ዴቢት ክሬዲት
ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 1500 00
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በተንቀሳቃሽ 850742 00
ከብድር ተሰብሳቢ 315000 00
ከወለድ ተሰብሳቢ 2100 00
ጽ/ቤት 80000 00
የጽ/ቤት አገ/ተቀናሽ 8000
የቢሮ ዕቃዎች 45000 00
የቢሮ ዕቃዎች አገ/ተቀናሽ 11250
የአባላት ቁጠባ 567000
ለወለድ ተከፋይ 20245
ሥራ ግብር ተከፋይ 332
ለጡረታ ተከፋይ 210
ዕጣ 600000
መጠባበቂያ 53415
ያልተከፋፈለ ትርፍ 37390
ለደመወዝ ወጪ 3000 00
ለዉሎ አበል 500 00
ድምር፡- 1297842 00 1297842
 ያልተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ ትክክለኛነት ከተረጋገጠ በኋላ
የሂሳብ ማስተካከያ የሚሰራላቸው የአገ/ተቀናሽ፣ ተሰብሳቢና ተከፋይ
ወለድ፣ ማስተካከያ ተሰርቶ በጠቅላላ መዝገብ ይመዘገባሉ፡፡
 የየማስተካከያ ሰነድ ተዘጋጅቶላቸው በአጠቃላይ መዝገብ ተመዝግበዋል፣
1.የቢሮ አገ/ቀናሽ ብር 667.00፣ የቢሮ ዕቃዎች ብር 937 በድምሩ ብር
1604.00 የማተካከያ ሰነድ ቁጥር 058
2.የብድር ወለድ ብር 1284.25፣ከባንክ የተገኘ ወለድ ብር 12759.00
የማተካከያ ሰነድ ቁጥር 059
3.የቁጠባ ወለድ ብር 1471.20 የማተካከያ ሰነድ ቁጥር 060
4. የተደረገ የትርፍ ክፍፍል ብር 37390.00 አባላት ወደ ዕጣ ይዙርልን ብለው
በወሰኑት መሰረት ወደ ዕጣ ሂሳብ የዞረ የማስተካከያ ሰነድ ቁጥር 061
አጠቃላይ መዝገብ ገጽ፡- 021
ቀን የሂሳብ አርዕስት ማጠቃቀሻ ዴቢት ክሬዲት
ቁጥር
ሐምሌ የአገ/ተቀናሽ ወጪ 1604 00
30/2007 058
ዓ/ም የጽ/ቤት አገ/ተቀናሽ 667 00

የቢሮ ዕቃ አገ/ተቀናሽ 937 00


ጥሬ ገንዘብ በባንክ 12 759 00
በቁጠባ 059
ተሰብሳቢ ወለድ 1284 25
ወለድ ገቢ 14043 25
ወለድ ወጪ 060 1471 20
ተከፋይ የቁጠባ ወለድ 1471 20
ያልተከፋፈለ ትርፍ 061 37390 00
ዕጣ 37390 00
በ30/11/07 ከተዘጋጀ
ማስተካከያ ሰነድ
 የተመዘገቡትማስተካከያዎች በሙሉ ከላይ በተዘጋጁት አብይ ሌጀሮች
ይተላለፋሉ የእያንዳንዱ ሌጀር ሚዛን ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ
የተስተካከለ የሒሳብ ሚዛን መሞከሪያ በማዘጋጀት መረጋገጥ
ይኖርበታል፡፡ በዚህ መሰረት የኅ/ሥ/ማህበሩ በሐምሌ 30/2007 ዓ/ም
የተዘጋጀውን የተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ በቀጣይ እናያለን፡፡

የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃ/የተ/ የኀ/ሥ/ማህበር


የተስተካከለ የሂሳብ ሚዛን መሞከሪያ
ሐምሌ 30/2007 ዓ/ም
የሂሳብ አርዕስት የሂሳብ ቁጥር ዴቢት ክሬዲት
ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 1500.00
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በተንቀሳቃሽ 863501.00

ከብድር ተሰብሳቢ 315000.00


ከወለድ ተሰብሳቢ 3384.25
ጽ/ቤት 80000.00
የጽ/ቤት አገ/ተቀናሽ 8667.00
የቢሮ ዕቃዎች 45000.00
የቢሮ ዕቃዎች አገ/ተቀናሽ 12187.00
የአባላት ቁጠባ 567000.00
ለወለድ ተከፋይ 21716.20
ሥራ ግብር ተከፋይ 332.00
ለጡረታ ተከፋይ 210.00
ዕጣ 637390.00
መጠባበቂያ 53415.00
ያልተከፋፈለ ትርፍ ---

ወለድ ገቢ 14043.25
ለደመወዝ ወጪ 3000.00
ለዉሎ አበል 500.00
አገ/ተቀናሽ ወጪ 1604.00
ወለድ ወጪ 1471.20
ድምር፡- 1314960.45 1314960.45
 ሂሳብ አመዘጋገባችን በሙሉ የተስተካከለ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ የሂሳብ
መግለጫዎ ሀብትና ዕዳ መግለጫ፣ገቢና ወጪ (ትርፍና ኪሳራ መግለጫ
የጥሬ ገንዘብ ፍሰት መግለጫ ( cash flow) ይዘጋጃሉ ፡፡ የኅብረት ሥራ
ማህበሩ የሂሳብ መግለጫዎች በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅተዋል፡፡

የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃ/የተ/ የኀ/ሥ/ማህበር


የገቢና ወጪ/የትርፍና ኪሳራ/መግለጫ
ሐምሌ 30/2007 ዓ/ም
ገቢ
ወለድ ገቢ 14043.25
የገቢ ድምር 14043.25
ወጪ
ወለድ ወጪ 1471.20
ለደመወዝ ወጪ 3000.00
ለውሎ አበል ወጪ 500.00
የአገ/ተቀናሽ ወጪ 1604.00
የወጪዎች ድምር 6575.20
የተጣራ ትርፍ 7468.05
የትርፍ አደላደል
ለመጠባበቂያ ብር፡- 30% ብር 2240.00
ያልተከፋፈለ ትርፍ፡- 70% ብር 5228.05
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃ/የተ/ የኀ/ሥ/ማህበር
ሃብት እና ዕዳ መግለጫ
ሐምሌ 30/2007 ዓ/ም
ሀብት
ተንቀሳቃሽ
ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 1500.00
ጥሬ ገንዘብ በባንክ በቁጠባ 863501.00
ተሰብሳቢ ከብድር 315000.00
ተሰብሳቢ ወለድ 3384.25
የተንቀሳቃሽ ሀብት ድምር 1183385.25
ጽ/ቤት 80000.00
የተ/አገ/ተቀናሽ (8667.00) 71333.00
የቢሮ ዕቃዎች 45000.00
የቢሮ ዕቃዎች አገ/ተቀናሽ (12187.00) 32813.00
የቋሚ ሀብት ድምር 104146.00
የጠቅላላ ሀብት ድምር 1287531.25
ዕዳ
የአባላት ቁጠባ 567000.00
ለወለድ ተከፋይ 21716.20
ተከፋይ የደመወዝ ግብር 332.00
ለጡረታ ተከፋይ 210.00
የዕዳ ደምር 589258.20
ካፒታል
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃ/የተ/ የኀ/ሥ/ማህበር
የጥሬ ገንዘብ ፍሰት መግለጫ
ሐምሌ 30/2007
ከስራ እንቅስቃሴ

በዘመኑ የተገኘ ትርፍ 7468.05


የእርጅና ተቀናሽ ወጪ 1604.00
ተሰብሳቢ ሂሳብ መጨመር (162884.25)
ተከፋይ ገንዘብ መጨመር 32013.20
የተጣራ ገንዘብ ፍሰት ከስራ እንቅስቃሴ (121799.00)
ከፋይናንስ እንቅስቃሴ
የተከፋፈለ ትርፍ ወጪ (37390.00)
ከዕጣ ገቢ 37390.00
የተጣራ የገንዘብ ለውጥ (121799.00)
በ30/10/2007 ዓ/ም ጥሬ ገንዘብ በዕጅና 986800.00
በባንክ
በ30/11/07 ዓ/ም ጥሬ ገንዘብ በዕጅና በባንክ 865001.00
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃ/የተ/ የኀ/ሥ/ማህበር
ካፒታል (Capital) መግለጫ
ሐምሌ 30/2007 ዓ/ም

በ30/10/2007 ዓ/ም የነበረ ካፒታል 690805.00


ለአባላት የተከፋፈለ ትርፍ (37390.00)
ከዕጣ ሽያጭ ገቢ የሆነ 37390.00

ከ8በዘመኑ የተገኘ ትርፍ 7468.05


በ30/10/2007 ዓ/ም የካፒታል መጠን 698273.05
የሂሳብ መዝጊያ ምዝገባ
 በበጀትዘመኑ መጨረሻ የትርፍና ኪሳራ መግለጫ ተሰርቶ የትርፍ
ወይም ኪሳራው መጠን ሲታወቅ በጊዚያዊ የሂሳብ መደቦች ላይ
የሚታየው ሚዛን በገቢና ወጪ ማጠቃለያ ተዘግቶ ወደ ካፒታል ርዕስ
እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡እነዚህም ጊዚያዊ የሂሳብ መደቦች ከተዘጉ በኋላ
የማይዘጉ ወይም ቋሚ ሂሳቦች ለሚቀጥለው ዓመት ማዘጋጃ ምዝገባ
በማካሄድ ወደ ሚቀጥለው ዓመት እንዲተላለፉ ያደርጋል፡፡የመዝጊያ
ምዝገባዎች የማስተካከያ ሰነዱን መሰረት በማድረግ በጠቅላላ መዝገብ
በሚከተለው መንገድ ተመዝግበዋል፡፡
አጠቃላይ መዝገብ ገጽ፡- 022
ቀን የሂሳብ አርዕስት ማጠቃቀሻ ዴቢት ክሬዲት
ቁጥር
ሐምሌ30/200 ወለድ ገቢ 14043.25
7 ዓ/ም የገቢ ማጠቃለያ ማ/ሰ/ቁ/62
14043.25
የወጪ ማጠቃለያ
ሐምሌ30/200 ማ/ሰ/ቁ/63 6575.20
7 ዓ/ም ወለድ ወጪ 1471.20
ደመወዝ ወጪ 3000.00
አበል ወጪ
500.00
አገ/ተቀ/ወጪ 1604.00
ሐምሌ 30 ቀን07 ከተዘጋጀ
ማስተካከያ ሰነድ
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ብድር ኃ/የተ/ኅ/ሥ/ማህበር
መነሻ ሀብትና ዕዳ መግለጫ
ነሀሴ 1/2007 ዓ/ም
ቀን መግለጫ ማመቃቀሻ ዴቢት ክሬዲት
ነሐሴ 1 ጥሬ ገንዘብ በዕጅ 1500.00
2007ዓ/ም ጥሬ ገንዘብ በባንክ በቁጠባ 863501.00
ተሰብሳቢ ሂሳብ 315000.00
ተሰብሳቢ ሂሳብ 3384.25
ጽ/ቤት 80000.00
የጽ/ቤት አገ/ተቀናሽ 8667.00
የቢሮ ዕቃ 45000.00
የቢሮ ዕቃ አገ/ተቀናሽ 12187.00
የአባላት ቁጠባ 567000.00
ተከፋይ ወለድ 21716.00
ተከፋይ ደመወዝ ግብር 332.00
ለጡረታ ተከፋይ 210.00
ዕጣ 637390.00
መጠባበቂያ 55655.00
ያልተከፋፈለ ትርፍ 5228.06
ሐምሌ 30/2007 ከተዘጋጀ
ሀብትና ዕዳ መግለጫ
ክፍል አራት
የቋሚ ንብረቶች እርጅና ተቀናሽ /Depreciation/
 እርጅናቅናሽ /Depreciation/ ማለት ቋሚ ሀብቶች ወይም ንብረቶች
የሚሰጡት የኢኮኖሚ አገልግሎት ወይም ጠቀሜታ መቀነስ ማለት እንጂ
የዕቃዎች የገበያ ዋጋ ማነስ ማለት አይደለም
 እርጅና/እልቀት/ በሁለት ክፍሎች ሊከፈል ይችላል፡፡
1. አካላዊ እርጅና/Physical deprecial/
2. የአገልግሎት እርጅና /Functional depreciation/
አካላዊ እርጅና/Physical depreciation/
 ቋሚ ሀብቶች ወይም ንብረቶች በሚደርሰው አካላዊ መሰበር ወይም
መቀደድ ወይም መበላሸት ምክንያት መስጠት ከሚገባቸው አገ/ ሊቀንሱ
ይችላሉ ተብሎ ለመቀነሳቸው የሚሰጠው ስያሜነው፡፡
የአገልግሎትእርጅና /Functional depreciation/
 በማርጀትናጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ምክንያት የተነሳ ያሉት መሳሪያዎች
የሚያመርቷቸው የፋብሪካ ውጤቶች ለሌላ መሳሪያ ከተመረቱ ተመሳሳይ
የፋብሪካ ውጤቶች ጋር በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪ ሳይሆኑ ሲቀሩ
መሳሪያዎች ስለማርጀታቸው የሚሰጠው ስያሜ ነው፡፡
 ስለዚህቋሚ ሀብቶች/ንብረቶች/ ከላይ በተጠቀሰው በአንድ ወይም
በጣምራ ምክንያቶች አገልግሎት ለመስጠት ብቁ አይደሉም ተብለው
ሊወገዱ ይችላሉ፡፡
የቀጠለ…
1.እያንዳንዱ ቋሚ ሀብት ከተገዛበት ጊዜ ጀምሮ በተወሰኑ ዓመታት ውስጥ
የወጣውን ወጪ መሸፈኛ የሚሆን ገንዘብ እየተቀነሰ እንዲቀር ይደረጋል፡፡
የእርጅና ቅናሽ የሚታሰብላቸው ሶስት ነገሮችን አሟልተው መገኘት
አለባቸው፡፡ እነርሱም የእቃው መነሻ ዋጋ /Historical Cost/ የእቃው
አገልግሎት ዘመን /Economy Life/ እና የእቃው የመዝገብ ዋጋ ወይም
በየዓመቱ ይቀነሳል ተብሎ የሚታሰበው ምጣኔ /Percentage Rate/
ናቸው፡፡
2. አንድ ቋሚ እቃ የእርጅና ቅናሹ እንዲታሰብለት ቢያንስ አንድ ወር የሞላው
መሆን ይኖርበታል፣
የቀጠለ…
3. የቋሚ ሀብት /ንብረት ወይም መሳሪዎች ዋጋ የሚያጠቃለለው እቃውን
በሚገዛበት ወቅት ኅብረት ሥራ ማበሩ ያወጣቸው፡-
 ዕቃው የተገዛበት ዋጋ

 የትራንስፖርት ክፍያ

 የኢንሹራንስ ክፍያ /ንብረቱ ከተገዛበት አስከ ስራው ከሚሰራበት ቦታ


ድረስ ለማድረስ የተከፈለው ብቻ
 እቃውን ለመትከል ወይም ስራ ለማስጀመር ያወጣ ወጪዎች

 የሽያጭ ታክስ/ሻጩ እቃውን በሚሸጥበት ወቅት/

 የባንክ ወለድ /ኅብረት ሥራ ማኅበሩ የመጀመሪያ የማምረት ሥራ

እስኪጀምር ድረስ ባለው ብቻ/


የቀጠለ…
4. የቋሚ ዕቃዎች ዋጋ ላይ የማይካተቱ ወጪዎች
 የዋጋ ቅናሽ/Purchase Discount/
 በሠራተኞች አያያዝ ጉድለት ወይም በአድማ ለተሰበረ ዕቃ ጥገና የጥገና
ወጪዎች፤
 የእርጅና ቅናሽ የሚደረግለትን ንብረት ሀብት ለማግኘት፣ለማሻሻል፤
ለማደስና መልሶ ለመገንባት የተደረገ ወጪ
 የባንክ ወለድ/ንብረቱ ሥራውን ከጀመረ በኋላ የወጣ ከሆነ/
 መሳሪዎቹ ከተተከሉ በኋላ ላለው ዋስትና የተከፈለ የኢንሹራንስ ክፍያ
የቀጠለ…

 የኅብረት ሥራ ማኅበራት የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ በ1996


ባወጣውየሂሳብ አያያዝ መመሪያ መሰረት ቀጥተኛ የእርጅና
አቀናነስ ዘዴ/Straighet Line Depreciation Method/
መጠቀም እንዳለበት የተቀመጠ ሲሆን ማንኛውም የኅብረትሥራ
ማኅበር የቋሚ ንብረት መዝገብ መያዝ ይኖርበታል፡፡
ለእያንዳንዱ የኅብረት ሥራ ቋሚ ንብረት የአገልግሎት ተቀናሽ
በየዘመኑ ተሰልቶ ለዚሁ በተከፈተ ሂሳብ ተለይቶ መቀመጥ
ይኖርበታል፡፡የአገልግሎት ተቀናሽ ወጪ ለየቋሚ ንብረት ዓይነት
ቀጥሎ በተዘረዘረው መሰረት መሆን ይኖርበታል/ፌዴራልኅብረት
ሥራኤጀንሲ በ1996 እንዳወጣው መመሪያ መሰረት/
ተ/ቁ የቋሚ ንብረት ዓይነት የአገልግሎት ተቀናሽ በ ምርመራ
%
1 ህንጻዎች 5
2 ለትራንስፖርት መኪናዎች 20
3 ለመጋዘንና ጽ/ቤት ቋሚ ዕቃዎች 10
4 ኮምፒተሮችና ሦፍትዌሮች 25
5 ለእርሻ መሳሪያዎች 16 ለመጀመሪያ ዓመት

6 ለእርሻ መሳሪያዎች 12 ለሚቀጥሉት


አመታት
7 ለእርሻ መኪና ትራክተር 20
8 ለቡልዶዘር ግሬደር 20
9 ለአፈር/ድንጋይ መዛቂያ 20
10 ለእርሻ መሳሪያ 33
11 ለእህል ጎተራ 20
12 ለሎሚ፣ብርቱካንና ማንጎ ተክሎች 3
13 ለመንደሪን ተክል 4
14 ለፓፓያ ተክል 25
15 ለሙዝ ተክል 16
16 ለወይን ተክል 4
17 ለቃጫ ተክል 13
ክፍል አምስት
የባንክ ሂሳብ ማስታረቅ
 በየወሩ መጨረሻ የኅብረት ሥራ ማህበሩ የባንክ ሂሳብ መግለጫ ሪፖርት
ሲመጣ በባንኩ እና በኅ/ሥ/ማህበሩ ባላንስ መካከል ያለዉን ልዩነት
ምክንያት ለማወቅና ያለውን ልዩነት ለማስታረቅ የሂሳብ ባለቤቱን መዝገብ
እና የባንክ ሂሳብ መግለጫውን ማስተያየት ያስፈልጋል ይህንንም ልዩነት
የምናስታርቅበት የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ይባላል፡፡ የባንክ ሂሳብ
ማስታረቂያ በሁለት ክፍሎች ይከፈላል
1. ከሂሳብ ባለቤቱ መዝገብ ላይ ተነስቶ የተስተካከለ ባላንስ ይደርሳል
2. ከባንክ ሂሳብ መግለጫ ጀምሮ በተስተካከለ ባላንስ ይጨርሳል
የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ይዘት
1. የባንክሂሳብ ባላንስ በማህበሩ መዝገብ መሰረት ብር xx
ሲደመር -- ባንኩ የመዘገበውና ለማህበሩ ዘግይቶ የደረሰ ገቢ xx
 -- የማህበሩ የአመዘጋገብ ስህተትxx ብር xx
ሲቀነስ --በባንክ በኩል ተቀንሶ በማህበሩ ያልተቀነሰ ክፍያxx
 -- የማህበሩ የምዝገባ ስህተት xx ብር xx
 -- የተስተካከለ የባንክ ሂሳብ ባላንስ ብር xxx
2. የባንክ ሂሳብ ባላንስ በባንክ ሂሳብ መግለጫው መሰረት ብር xx
ሲደመር -- ማህበሩ የመዘገበውና በሂ/መግለጫው ላይ ያልታየ ገቢxx
 -- የባንክ የአመዘጋገብ ስህተት xx ብር xx
ሲቀነስ -- በማህበሩ ተመዝግበው ባንክ ያልደረሱ ቼኮች
ቼክቁጥርየገ/መጠን
xx xx
xx xx ብር xx
--የተስተካከለ የባንክ ሂሳብ ባላንስ ብር xxx
የሂሳብ ሰራተኛ ስም፡------ የገ/ያዥስም፡---------
ፊርማ፡----------- ፊርማ፡------------
ምሳሌ
የነገ ተስፋ የገ/ቁ/ኅ/ስራ ማህበር ፡-በ30/10/07 በተላከው የባንክ ሂሳብ
መግለጫ ላይ የሚታይ ባላንስ፡- ብር 8350.10 ሲሆን በማህበሩ መዝገብ መሰረት
ደግሞ የባንክ ሂሳብ ባላንስ፡- ብር 7100.50
የማህበሩ ሂሳብ ሰራተኛ መረጃዎችን አጣርቶ የሚከተሉትን ልዩነቶች
አገኘ28/10/07 የተላከ ገቢ ባንክ ያልመዘገበው ብር 200.00 በማህበሩ
ተመዝግበው ባንክ ያልደረሱ ቼኮች
ቼክ ቁጥርየገ/መጠን
 AB1568 ብር 150.00
 AB1569 ብር 100.00
 AB1560 ብር 500.00 750.00
3. ከአቶ አስራት ከዕዳ በባንክ በኩል የተሰበሰበ ማህበሩ ያልመዘገበው ብር
850.00
4. በቼክ ቁጥር AB1567 የተከፈለ ብር 500.10 ሲሆን ማህበሩ ብር 500.00
ብሎ የመዘገበው
5. ባንክ መግለጫ ላይ የታየ ማህበሩ ያልመዘገበው የባንክአገ/ክፍያ ብር 150.30
የነገ ተስፋ/የኅ/ስራማህበር የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ
30/10/2007 ዓ/ም
የባንክ ሂሳብ ባላንስ በማህበሩ መዝገብ መሰረት ብር 7100.50
ሲደመር -- ባንኩ የመዘገበውና ለማህበሩ ዘግይቶ የደረሰ ገቢ ብር 850.00
ሲቀነስ -- በባንክ በኩልተቀንሶ በማህበሩ ያልተቀነሰ ክፍያ ብር 150.30
 -- የማህበሩ የምዝገባ ስህተት ብር 0.10 ብር 150.40
የ30/11/07 የተስተካከለ የባንክ ሂሳብ ባላንስ ብር 7800.10
የባንክ ሂሳብ ባላንስ በባንክ ሂሳብ መግለጫው መሰረት ብር 8350.10
ሲደመር -- ማህበሩ የመዘገበውና በሂ/መግለጫው ላይያልታ የገቢ ብር 200.00
ሲቀነስ -- በማህበሩ ተመዝግበው ባንክ ያለልደረሱ ቼኮች
ቼክ ቁጥር የገ/መጠን
 AB 1568 150.00
 AB 1569 100.00
 AB 1570 500.00 ብር750.00
የ30/10/06 የተስተካከለ የባንክ ሂሳብ ባላንስ ብር 7800.10

የሂሳብሰራተኛስም፡-------------- የገ/ያዥስም፡-----------------
ፊርማ፡--------------- ፊርማ፡----------------
ክፍል ስድስት
የወለድ ስሌት፣ የትርፍ አደላደልና ዕጣንና ቁጠባን ማጣጣም
6.1 የወለድ ስሌት ዘዴዎች/Interest Methods/
. እንደየ ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አባላት ላስቀመጡት
የቁጠባ ገንዘብ ---- ፐርሰንት ወለድ እንደሚከፈል ይወሰናል፤ ይህ
ከሀገራችን የቁጠባና የብድር አከፋፈል ፖሊሲ ጋር በማጣጣም
የሚወሰን መሆን አለበት፡፡
. በአብዛኛዉ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሁለት ዓይነት የወለድ
ስሌቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል እነርሱም ፡-
1. የአንድ ገዜ ወለድ/ Simple Interest/ ሲሆን ይህ የስሌት ዘዴ
ዋናዉ ገንዘብ በአንድ የሂሳብ ዘመን/ወር/ የወለደዉንና ዋናዉን
በመለየት የቀጣይ ዓመት የሂሳብ ዘመን/ወር/ ወለድ የማስላት ዘዴ
ነዉ ፡፡ ኅ/ሥ/ማኅበራት ለአባሎቻቸዉ ሲያበድሩ አለያም አባለት
በማኅበሩ ላይ ለሚቆጥቡት ገንዘብ ይህን የወለድ ዘዴ ይጠቀማሉ፡፡
2. የወለድ ወለድ/Compound Interest/ በመባል
ይታወቃሉ ይህ ዘዴ ዋናዉ ገንዘብ በመጀመሪያዉ የሂሳብ
ዘመን/ወር/ የወለደዉን ወለድ በዋናዉ ላይ በመደመር እንደ
ዋና ገንዘብ በመያዝ የቀጣዩን ዓመት /ወር/ ወለድ የማስላት
ዘዴ ነዉ ፡፡ ይህ ዘዴ በአብዛኛዉ በባንኮችና በሌሎች አበዳሪ
ድርጅቶች ለብድርም ለቁጠባም የሚተገበር ሲሆን ኅብረት
ሥራ ማኅበራት ለብድር በዚህ ዘዴ አይጠቀሙም ፡፡
6.2 የቁጠባ ወለድ ማባዥያ ቀመር/Formula/
1. በየወሩ የሚሰላ ከሆነ
ወለድ = ዋና ገንዘብ/ሚዛን/ x በወለድ ፐርሰንት
12
የቀጠለ…
2. በየስድስት ወሩ የሚሰላ ከሆነ
ወለድ = (ዋና ገንዘብ x በወለድ ፐርሰንት) x 6
12
3. በየዓመቱ የሚሰላ ከሆነ
ወለድ = (ዋና ገንዘብ x በወለድ ፐርሰንት) x 12
12
6.3 የብድር ወለድ ማባዥያ ቀመር/Formula/
. የብድር ወለድ አሰላል በሁለት ዓይነት ዘዴ መክፈል ይቻላል
1. አማካይ ወርሃዊ ክፍያ ዘዴ በመጠቀም
. አማካይ ወርሃዊ ክፍያን ለማስላት የምንጠቀመዉ ቀመር
. የብድር ክፍያ ማባዥያ ምጣኔ = የብድር ወለድ ፐርሰንት
ለብድሩ ቆይታ ጊዜ
አማካይ ወርሃዊ ክፍያ = የብድር መጠን x የብድር ክፍያ ማባዥያ ምጣኔ
. ምሳሌ - የብድር መጠን ----- 600
- በዓመት የወለድ መጠን ---- 10.5%
- የብድሩ ቆይታ ጊዜ ------- 12 ወራት ቢሆን ስሌቱ
የሚሆነዉ
የብድር ክፍያ ማባዥያ ምጣኔ = 10.5% = 0.875 ይሆናል
12 ወር
ስለዚህ ተበዳሪዉ አማካይ ወርሃዊ ክፍያ ከዋናና ከወለድ
የሚከፈለዉ
600(0.875) = 52.89 በየወሩ ለ12 ወራት ይከፍላል
2 . እየቀነሰ የሚሄድ ወርሃዊ ክፍያ ዘዴን በመጠቀም
ምሳሌ፡- አንድ አባል 600 ብር ለ12 ወራት በ10.5 % ወለድ
በዓመት ከማኅበሩ ብድር ቢወስድ አከፋፈሉ የሚሆነዉ
ቀን የብድር መጠን ወርሃዊ ከዋና ብድር አጠቃላይ ቀሪ ዕዳ በወሩ
በወሩ የወለድ ክፍያ ተመላሽ ወርሃዊ ክፍያ መጨረሻ
መጀመሪያ
1/1/2007 600 5.25 50 55.25 550
1.2/2007 550 4.81 50 54.81 500

6.4 የትርፍ ክፍፍል አደላደል


. በአዋጁ መሰረት በዘመኑ ከተገኘዉ ትርፍ ላይ 30 %
ለመባበቂያ ተቀንሶ ቀሪዉ 70 % በአባላት ዉሳኔ መተዳደሪያ
ደንቡን መሰረት በማድረግ ለተሳትፎና ለዕጣ ቆይታና ድርሻ
ተሰልቶ ይከፋፈላል፡፡
1.ለተሳትፎ ለማከፋፈል የምንጠቀምበት ቀመር
የአንድ ብር ድርሻ = ለተሳትፎ ክፍፍል የተመደበ ገንዘብ
ለጠቅላላ ለብድር የወጣ ገንዘብ
2. ለዕጣ ድርሻና ቆይታ ጊዜ ለማከፋፈል የምንጠቀምበት
ቀመር
የአንድ ዕጣ ድርሻ = ለዕጣ ድርሻና ቆይታ የተመደበ ገንዘብ
ለጠቅላላ ዕጣ ድርሻና በጊዜ ቆይታ
6.5 ዕጣንና ቁጠባን ማጣጣም/ Leverage Ratio/
. እንደየ ኅብረት ሥራ ማኅበሩ የዕጣ መጠንና የቁጠባ መጠን
የተለያየ ቢሆንም በየወሩ የዕጣዉና የቁጠባዉ መጠን
መጣጣም ይኖርበታል በመሆኑም አንድ አባል በማኅበሩ ላይ
በየወሩ ሲቆጥብ በተመሳሳይ የዕጣ ክፍያም መፈጸም
ይኖርበታል ማለት ነዉ፡፡
ልዩ ልዩ ዕዝሎች
 የኅብረት ሥራ ማኅበሩ ዓርማ
 ክልል ቁጥር
 ዞን ቀን--
 ወረዳ
የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ
 የከፋይ ሥም
 የገንዘቡ ልክ በአኃዝ
 የገንዘቡ ልክ በፊደል
 የከፈለበት ምክንያት

የሂሳብ የሂሳብ አርስት ዴቢት ክሬዲት


ቁጥር
ጥሬ ገንዘብ
ከዕጣ
ለመመዝገቢያ
ቁጠባ
ከዋና ብድር
ከወለድ
ድምር
 የኅብረት ሥራ ማኅበሩ ዓርማ
 ክልል ቁጥር ---

 ዞን ቀን ---
 ወረዳ
የወጪ ማዘዥያ ደረሰኝ
 የተቀባይ ሥም
 የገንዘቡ ልክ በአኃዝ
 የገንዘቡ ልክ በፊደል -------------------------
 የተከፈለበት ምክንያት
 ክፍየዉ የተፈጸመዉ በጥሬ ገንዘብ -------- በቼክ ------- የቸክ ቁጥር ----------------
የሂሳብ የሂሳብ አርዕስት ዴቢት ክሬዲት
ቁጥር

ያዘጋጀዉ ያጸደቀዉ የገንዘብ ተቀባይ


 ስም ----------------- ስም --------------------- ስም --------------------------
 ፊርማ ------- ፊርማ ------------- ፊርማ ----------------
የ---------
ገንዘብ ቁጠባ ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር
የገንዘብ መሰብሰቢያ ቅጽ /collectoin sheet/
ቀን ______________________ ገጽ _________
ቁጥር የደንበኛ መለያ ጥሬ ዕጣ መደበኛ የፈቃደ ከብድር ከብድርተ የመመዝ ቅጣት ሌሎች የሂሳብ አስተያየ
ው ሥም ቁጥር ገንዘብ ቁጠባ ኝነት ተመላሽ መላሽ ገቢያ ቁጥር ት
ቁጠባ ከዋና ከዋና
ዴቢት ክሬዲት ክሬዲት ክሬዲት ክሬዲት ክሬዲት ክሬዲት ክሬዲት ክሬዲት

የገንዘብያዥ ፊርማ ____ ሂሳብ ሰራተኛ የብድር ኦፊሰር


የአባላት የቁጠባ ሂሳብ ደብተር
ቀን ቁጠባ የተቀባይ ፊርማ
ገቢ ወጪ ወለድ ቀሪ

ቀን ብድር የተቀባይ ፊርማ


የብድር መጠን ከዋና ከወለድ የ ቀሪ ዕዳ
የተመለሰ ተመለሰ

ቀን ዕጣ የተቀባይ ፊርማ
ገቢ ወጪ ቀሪ
!!!
ለ ሁ
ግ ና
መ ሰ

You might also like