You are on page 1of 11

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሠራተኞች መዝናኛ ክበብ መተዳደሪያ ደንብ

መ ግ ቢያ

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ሠራተኛው የመሥሪያ ቤቱን አላማ ለማስፈፀም የተጣለበትን የሥራ ኃላፊነት በአግባቡ
በመነቃቃት ለመወጣት እንዲችል ዋጋውን ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው የክበብ አገልግሎት ለመስጠት፣ በሥራ የዛለ የሠራተኛውን አዕምሮው
በተለያዩ የመዝናኛ አገልግሎቶች ለማደስ እና በሠራተኛው መካከል ያለውን የእርስ በርስ የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ከተቋቋመ
ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በታለመበት መንገድ ሠራተኛው የሚፈልገውን ደረጃውን የጠበቀ የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ሊሰጥ ግን
አልቻለም።
ይህንን ለክበቡ አቅም መውረድ መንስኤዎች ተብለው ከተያዙት ለመጥቀስ ያህል ጥራትን መሠረት በማድረግ በአገልግሎቱ በኩል የሚስተዋሉ በተለይ
በግዥ እና በምግብ ቁጥጥር ሂደት በኩል የሚታዩ ጉድለቶች፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎች፣ በመዝናኛ ክበቡ አካላዊ አደረጃጀት ወጥነት
አለመኖር፣ በመዝናኛ ክበቡ በኩል ለሚሰጠው አገልግሎት በተጠያቂነት መንፈስ ኃላፊነት የሚሰማው አመራር እጦት እና ሌሎች የመሳሰሉት ችግሮች
ሲሆኑ ከዚህ ባለፈ ግን መዝናኛ ክበቡ የሚተዳደርበት የሕግ ሰነድ በአግባቡ አለመዘጋጀቱ አንዱና ዋናው ችግር እንደሆነ የሚታመን ነው።
በነዚህ ምክንያት ከ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የመዝናኛ ክበቡን በተሻለ ሁኔታ ለማስኬድ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም
ውስጥ በዝቅተኛ የደምወዝ ክፍያ ተቀጥረው የሚሰሩትን በጽዳት ሥራ ላይ የተሰማሩ የመሥሪያ ቤቱ ሴት ሠራተኞችን የገቢ ደረጃን ለማሻሻል
እንዲቻል በማሰብ የመሥሪያ ቤቱ የሴት ሠራተኞች ፎረም ይህንን የመዝናኛ ክበብ የማስተዳደር ኃላፊነቱን መውሰዱ ይታወሳል፡፡
ከዚህም በመነሳት መሥሪያ ቤቱ ሠራተኛው በዝቅተኛ ዋጋ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በማሰብ ከአዳራሽ ኪራይ፣ ከውሃና ከኤሌክትሪክ ፍጆታ
ወይም ክፍያ ነጻ በማድረግ እንዲጠቀሙበት ለማበረታታት ጥረት እያደረገ ይገኛል። ሆኖም
 አሁንም መዝናኛ ክበቡ በተሻለ የአሰራር ሥርዓት እንዲዋቀር

 ለሠራተኛው የሚሰጠው አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ የተቀላጠፈና የሠራተኛውን የመግዛት አቅም ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን
ለማስቻል
 መዝናኛ ክበቡ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው አካል እንዲሆን ለማድረግ
 የመዝናኛ ክበቡን የሥራ እንቅስቃሴ በአግባቡ ለመቆጣጠር እና ተገቢውን የእርምት እርምጃ ለመውሰድ

 የመዝናኛ ክበቡን አስተዳዳሪዎችን ተጠያቂነት በሕጉ መሰረት ለማስፈን እንዲቻል በማስፈለጉ አግባብነት ያለው የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀት
እንዳለበት በመታመኑ ይህ መተዳደሪያ ደንብ ሊወጣ ችሏል።

1
አንቀፅ 1
መቋቋም

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ በ ቀን ወር በ ዓ.ም. ተቋቁሟል፡፡

አንቀፅ 2
ስያሜ
በዚህ መተዳደሪያ ደንብ የተቋቋመው መዝናኛ ክበብ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ በሚል
ስም የሚጠራ ሲሆን ከዚህ በኃላ “መዝናኛ ክበብ” ተብሎ ይጠቀሳል፡፡

አንቀፅ 3
ዓላማ
የመዝናኛ ክበቡ አላማዎች የሚከተሉት ናቸው፤

1. ትርፍን ባልተከተለ አሰራር መሠረት በማድረግ የምግብ፣ የለስላሳ እና የትኩስ መጠጦች እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመሥሪያ ቤታችን
ሠራተኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ
2. ለመሥሪያ ቤቱ ሠራተኛ ከሥራ ጫና ለመነቃቃት የሚችልበት የመዝናኛ አገልግሎት ድባብ መፍጠር
3. በዝቅተኛ የደምወዝ ክፍያ የሚተዳደሩትን ሴት ሠራተኞችን ከመደበኛ የሥራ ሰዓታቸው ውጪ ገቢያቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን
የሥራ ዕድል መፍጠር
4. ንጽህናው በአግባቡ የተጠበቀ የአገልግሎት እና የመስተንግዶ አሰራር በተለይ ደግሞ የሠራተኛውን ጤንነት ሙሉ በሙሉ ባማያጓድል
ደረጃ የተስተካከለ የመዝናኛ አካባቢ መፍጠር

2
5. የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ለሚኖራቸው እንደ ሠርግ አይነት ልዩ ፕሮግራሞች የመሥሪያ ቤቱን አዳራሽ በነጻ መስጠትን
እንዲሁም ለሚቀርቡ የተለያዩ ስብሰባዎች፣ ስልጠናዎች እና ሌሎች ዝግጅቶች የመስተንግዶ አገልግሎት በክፍያ ማቅረብ
6. በገንዘብ አቅም ማነስ ምክንያት የትምህርት ደረጃቸውን ማሻሻል ላልቻሉት የመሥሪያ ቤታችን ሠራተኞች ልዩ ድጋፍ ማድረግ
7. በመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች መካከል ጥሩ የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር በዓመት አንድ ጊዜ የመዝናኛ የጉዞ ሽርሸር እና የጉብኝት ፕሮግራሞችን
ማዘጋጀት
አንቀፅ 4
የበጀት አመት

የመዝናኛ ክበቡ የበጀት አመት ከሐምሌ 1 እስከ ሰኔ 30 ይሆናል፡፡

አንቀፅ 5
ትርጉም

1. “መዝናኛ ክበብ” ማለት በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የተቋቋመ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የሰራተኞች መዝናኛ
ክበብ ነው፡፡
2. “ማኔጅመንት' ማለት የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ያቀፈ የመዝናኛ ክበቡ የበላይ አካል ሲሆን የመዝናኛ
ክበቡ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል።
3. ‘ሠራተኛ' ማለት በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ነው።
አንቀጽ 6
የፆታ አገላለጽ
በዚህ ደንብ ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል።

አንቀፅ 7
የመሥሪያ ቤቱ መዝናኛ ክበብ አስተዳደር
በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የመዝናኛ ክበቡ አስተዳደር ሲሆን የሚመረጠውም በማኔጅመንቱ ነው፡፡
አንቀጽ 8
የሠራተኞች መብት
1. በመዝናኛ ክበቡ የሚሰጡትን ማንኛውም የምግብ፣ የለስላሳ እና የትኩስ መጠጥ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አለው፡፡
2. በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያለውን ቅሬታ ለመዝናኛ ክበቡ አስተዳደር ማቅረብ እና ሀሳብ የመስጠት መብት አለው።

አንቀፅ 9

የሠራተኞች ግዴታ

1. የክበቡን ንብረት በሚገባ የመጠበቅ፣ ጉዳት ሳያደርስ ተገቢ በሆነ መንገድ የመጠቀምና በሚያደርሰው ጉዳትም በኃላፊነት የመጠየቅ ግዴታ አለበት

3
2. ማንኛውም ሠራተኛ የመዝናኛ ክበቡን አላማና የገባቸውን ግዴታዎች ማክበር ግዴታ አለበት።

አንቀጽ 10
የመ ዝና ኛ ክበቡ አደረጃጀት

1. ለመዝናኛ ክበቡ የሚከተሉት አመራር አካላት ይኖሩታል፡፡


ሀ. የ መ ሥ ሪ ያ ቤ ቱ ማ ኔ ጅ መ ን ት ፕ ሮ ሰ ስ ካ ው ን ስ ል ( ከ ዚ ህ በ ኋ ላ
ማኔጅመንት' ተብሎ ይጠራል)
ለ. ኦዲተር
ሐ. ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና

መ. ሌሎች ኮሚቴዎች ይኖሩታል፡፡

2. የመዝናኛ ክበቡ በሚከተለው መልኩ የተዋቀረ ነው፡ደ

የማኔጅመንት ፕሮሰስ ካውንስል

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኦዲተር

3. የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነ ማናቸውም ሰው በተጨማሪ ኦዲተር ወይም ሊ ቀ መ ን በ ር ሆኖ ሊሰራ አይችልም፡፡

አንቀፅ 11
የማኔጅመንት ስልጣንና ተግባር

ማኔጅመንቱ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ ላይ የተጠቀሱትን አባላትን የሚያካትት ሆኖ በህግና በመዝናኛ ክበቡ
መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ደ
ሀ. ማኔጅመንቱ የመዝናኛ ክበቡ የበላይ አካል ነው፣
ለ. የክበቡን መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፣ያሻሽላል፣
ሐ. በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት የክበቡን ኦዲተር ይመርጣል፣
መ. መ ዝ ና ኛ ክ በ ቡ ን በ ተ መ ለ ከ ተ የ ማኔጅመንቱን ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሳቢና ፀሀፊ ይሾማል፤ ይሽራል፤
ሠ የመዝናኛ ክበቡ አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት፣ የሂሳብ መግለጫ፣ የኦዲት ሪፖርት በሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴ በኩል ሲቀርብለት ገምግሞ ያፀድቃል፣
4
ረ. የክበቡ ሂሳብ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ያደርጋል

አንቀፅ 12
የማኔጅመንቱን አመራር አካላት ስልጣንና ተግባራት

የማኔጅመንቱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሃፊ የሚኖረው ሲሆን ስልጣንና ተግባራቸውም የሚከተለው ነው፣
1. የማኔጅመንቱ ሰብሳቢ፣
ሀ. የማኔጅመንቱን ስብሰባዎች ይጠራል፤ ከፀሃፊው ጋር በመሆን አጀንዳዎችን ያዘጋጃል
ለ. የማኔጅመንቱን ስብሰባ በሊቀመንበርነት ይመራል
ሐ. ማኔጅመነቱ ክበቡን በተመለከተ የሚያወጣቸውን ደንቦች የሚሰጣቸውን ውሳኔዎች በትክክል ስራ ላይ
መዋላቸውን ይከታተላል
መ. በማ ኔ ጅ መ ን ቱ የ ሥ ራ አ ስ ፈ ጻ ሚ ኮ ሚ ቴ ው አ ቅ ር ቦ ያ ጸ ደ ቀ ው ን አመታዊ የስራ ክንውን፤ የስራና የኦዲት
ሪፖርቶችና የሂሳብ መግለጫ በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል
ሠ.. ለጉባኤው የሚቀርቡ ጉዳዮችን ቅደም ተከተል በማውጣት ለውይይት እንዲቀርቡ ለፀሃፊው

በአጀንዳነት ያስይዛል፣

2. ምክትል ሰብሳቢ
ሀ. ሰብሳቢው/ዋ በማይኖርበት/ በማትኖርበት ጊዜ ተክቶ/ታ ይሰራል
ለ. በሰብሳቢው ወይም በማኔጅመንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ስራዎች ያከናውናል
3. ፀሃፊ
ሀ. ከሰብሳቢው ጋር በመሆን በማኔጅመንቱ አጀንዳዎችን ያዘጋጃል
ለ. የማኔጅመንቱን ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ይይዛል

አንቀፅ 13
የማኔጅመንት ስብሰባ

1. የማኔጅመንቱ መደበኛ ስብሰባ ቢያንስ በአመት ሁ ለ ት ጊዜ በማኔጅመንቱ ሰብሳቢ ጠሪነት የሚካሄድ ሆኖ የበጀት

አመቱ አጋማሽ እና የበጀት ዓመቱ ከተዘጋ በኋላ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

2. በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት የማኔጅመንቱ ሰብሳቢ በ 15 ቀናት ውስጥ ስብሰባ ያለጠራ እንደሆን ፣ በአንድ
ወይም ከዚህ በላይ በሆኑ በማኔጅመንቱ አባላት ጠያቂነት ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡

3. የመዝናኛ ክበቡ አስቸኳይ ስብሰባ በማናቸውም ጊዜ በ ማ ኔ ጅ መ ን ቱ ሰብሳቢ ወይም የማኔጅመንቱ አባላት


በሚጠይቁበት ጊዜ ሊካሄድ ይችላል፡፡
4. ለማኔጅመንቱ መደበኛ ስብሰባ አስራ አምስት የስራ ቀናት በፊት እንዲሁም አስቸኳይ ስብሰባ ሲሆን ከአምስት የስራ
ቀናት ባልበለጠ ጊዜ በፊት አባላት የስብሰባው አጀንዳ፣ ቦታውን፣ ቀኑን እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
5. በማ ኔ ጅ መ ን ቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ጉዳዮች እንደየሁኔታው በአጀንዳነት ተይዘው ለውይይት ይቀርባሉ፣
ማንኛውም ጉዳይ በአጀንዳ እንዲያዝለት የሚፈልግ የ ማ ኔ ጅ መ ን ት አባል ከስብሰባው ቢያንስ ከአንድ ሳምንት
5
በፊት ለ ሥራ አስ ፈጻ ሚ ኮ ሚ ቴው ሊቀ መንበር ወይም ለማኔጅመንቱ ሰብሳቢ በፅሁፍ ይህንኑ ማስታወቅ
ይኖርበታል፡፡

አንቀፅ 14
የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የምርጫና የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት

1. ክበቡ የሚመራው በመዝናኛ ክበቡ የማኔጅመንት አባላት በሙሉ ተሳትፎ በተመረጡ ሰዎች
ይሆናል፣
2. ማ ኔ ጅ መ ን ቱ ምርጫ ሲያደርግ ምልአተ ጉባኤው እንደተሟላ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ተመርጠው
ምርጫው እንዲካሄድ ያደርጋሉ፣
3. አስመራጭ ኮሚቴው ከሁሉ አስቀድሞ የምርጫ መመዘኛዎች በማኔጅመንቱ እንዲወስኑ አድርጎ ምርጫውን
ያስፈፅማል፣
4. ማ ኔ ጅ መ ን ቱ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁ ወይም የተሻሩ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች የተጓደሉ የስራ
አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለመተካት እንደአስፈላጊነቱ የአስመራጭ ኮሚቴ ያቋቁማል፣
5. የምርጫ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ ተመራጮች በድጋሚ እንዲያገለግሉ ከተፈለገ በጥቆማ ለውድድር ቀርበው በድምፅ

ብልጫ መመረጥ ይኖርባቸዋል፣ ሆኖም ለ 3 ኛ ጊዜ ለመመረጥ ቢያንስ ለአንድ የምርጫ ዘመን (2 ዓመት) ማረፍ
ይኖርባቸዋል፡፡
6. የማኔጅመንቱ ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ እ ን ዲ ያ ል ፍ ይ ደ ረ ጋ ል ፣ ድምጽ እኩል ሲሆን

የማኔጅመንቱ ሰብሳቢ ወይም የኮሚቴው ሊቀመንበሩ ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል፣

7. የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት እራሳቸውን ለኮሚቴ ምርጫ በእጩነት ማቅረብ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን ማኔጅመንቱ
ካመነበት ከአስመራጭ ኮሚቴነት በማንሳት ለእጩነት ሊያቀርባቸው ይችላል፣

8. አስመራጭ ኮሚቴው አዲሶቹ ተመራጮች 30 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ስራቸውን ተረክበው እንዲሰሩ

የማድረግ ሃላፊነት አለበት፣

9. የቀድሞ ተመራጮች በምርጫ ከተሰናበቱ እለት ጀምሮ ከማኔጅመንት ውሳኔ ውጪ ከርክክብ በስተቀር
ስራውን ማንቀሳቀስ አይችሉም፣

10., የመዝናኛ ክበቡን በተመለከተ በማኔጅመንቱ አጀንዳ ላይ ቀርበው ያልፀደቁና ያልሰፈሩ ጉዳዮችን በተመለከተ የተሰጡ
ውሳኔዎች ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፣

አንቀፅ 15

የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስለማቋቋም

የመዝናኛ ክበቡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚዋቀረው ከ ሲሆን ተጠሪነቱ ለመሥሪያ ቤቱ ማኔጅመንት ወይም ለበላይ አመራር
ሆኖ የክበቡን የዕለት ተዕለት ሥራ ያከናውናል።
አንቀፅ 16
የሥራ አስፈፃሚ ኮ ሚቴው ስልጣ ንና ተግባራት
6
የ ሥ ራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

1. የመዝናኛ ክበቡን አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት ለማኔጅመንት አቅርቦ እንዲፀድቅ ያደርጋል፣
2 . የመዝናኛ ክበቡን አመታዊ የስራ መርሃ ግብርና የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ አዘጋጅቶ
ለማኔጅመንቱው አቅርቦ እንዲፀድቅ ያደርጋል፣
3. የመዝናኛ ክበቡን አላማዎች ለማስፈፀም ጥረት ያደርጋል፤ ይህንንም ለማሳካት የገቢ ምንጮችን የገንዘብ፣ የጉልበት
ወይም የማቴሪያል ድጋፍ የሚገኝበትን ዘዴ ያፈላልጋል፣
4. የራሱን የአሰራር ስነስርአት ለ መዘ ር ጋ ት የ ው ስ ጥ አ ሰ ራ ር ደ ን ብ ያወጣል፡፡
5. በክበቡ የፋይናንስ አቅም መሠረት ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚተዳደሩበትን ደንብ ያወጣል፣፡
6. በማኔጅመንቱ የሚተላለፉ ውሳኔዎች በተግባር ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡
7. ለመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች የሚያስፈልጋቸውን የክበቡ አገልግሎት አቅም በሚፈቅደው መሠረት በንጽሕናና በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲቀርብ
ያደርጋል፡፡
8. በማኔጅመንቱ የተሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል፡፡
9 . የመዝናኛ ክበቡን ጉዳዮች በተመለከተ የሴቶች ፎረሙን መደበኛ እና አስቸኳይ ስብሰባዎች ይጠራል፡፡
10. በየጊዜው በመዝናኛ ክበቡ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖች ላይ ከ ጋር በመሆን በስብሰባ ይመክራል፤ ያጋጠሙ
ችግሮችን በመለየት እንዳስፈላጊነቱ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር ይተገብራል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
11. ከመዝናኛ ክበቡ ኮሚቴ ሊቀመንበር በሚቀርበው የግዥ ጥያቄ መሠረት ከመደበኛና ከዕለታዊ መስተንግዶ ወጣ ያሉ የቋሚና የአላቂ ዕቃዎችን
ግዥ አፈጻጸም አግባብነት መርምሮ ኃሳብ ያቀርባል፤ በዕቅድ የሚመራበትን ሥርዓት ያመቻቻል፡፡
12. በመዝናኛ ክበቡ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ድክመቶችን በመለየት ወቅታዊ የዕርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ ማሳሰቢያ ይሰጣል ለውጥ
ካልታየ በበቂ ሁኔታ መረጃ አስደግፎ የውሳኔ ሃሳብ ለማኔጅመንቱ ያቀርባል
13. የመዝናኛ ክበቡ ሠራተኞች ሥነ ምግባር ጠብቀው መስራታቸውን ይከታተላል፤ የሥራ ዲሲፕሊን እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡
14. የመዝናኛ ክበቡ ንብረቶችና ገንዘብ በአግባቡ መያዛቸውንና በተገቢው ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል
15. የመዝናኛ ክበቡን የዕለት ገቢዎችን እና አጠቃላይ ሂሳብ አያያዝ ግልጽና ከብኩንነት የጸዳ የሚሆንበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ አፈጻጸሙን
ይከታተላል፡፡
16. ለተለያዩ ስብሰባዎች የመስተንግዶ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የመዝናኛ ክበቡን ጥቅም መሠረት በማድረግ ዝርዝር የወጪ እና የገቢ ስሌቶችን በማካሄድ
ይወስናል፡፡
17. የመዝናኛ ክበቡ የምግብ፣ የለስላሳ እና የትኩስ መጠጦች የዋጋ ሁኔታ ተመጣጣኝ እንዲሆን በየጊዜው እያጠና ከሚመለከታቸው ጋር ተመካክሮ
ይወስናል፡፡

አንቀፅ 17
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት

1. የስራ አ ስ ፈ ፃ ሚ ኮ ሚ ቴ ው ከ 5-7 አባላት ይኖሩታል፤ ቢሆን የኮሚቴው ቁጥር ለውሣኔ አሰጣጥ


እንዲያመች ጎዶሎ መሆን ይኖርበታልል
2. ለዚህም ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል።
ሀ. ሊቀ መንበር

7
ለ. ምክትል ሊቀ መንበር
ሐ . ፀሐፊ
መ. ሂሳብ ሹም
ሠ. ገንዘብ ያዥ፤
ረ. ዕቃ ግዢ
ሰ. የ ንብረት ክፍል ሃላፊ
3 ሊቀ መንበር

በሴቶች ፎረም አቅራቢነት በማኔጅመንቱ የሚመረጥ ሲሆን የሚከተሉት ስራዎችን ያከናውናል፡፡

ሀ. ማኔጅመንቱ የሚያቋቁማቸው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን በሊቀመንበርነት ይመራል፡፡

ለ. ክበቡን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወክላል፡፡

ሐ. በመዝናኛ ክበቡ ስም የተከፈለው የባንክ ሂሳብ ቼኮችንና የወጪ ሰነዶችን ከሂሳብ ሹሙ ጋር በመሆን
በጣምራ ይፈርማል፡፡

መ. ለመዝናኛ ክበቡ ስራ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን ይፈቅዳል፡፡

ሠ. የ 3 ወር፣ የ 6 ወርና አመታዊ የስራ፣ የፋይናንስ ሪፖርቶችን እያዘጋጀ ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው
ያቀርባል፡፡

ረ. በክበቡ ስም ደብዳቤዎችን ይፈርማል፡፡

ሰ. ሂሳብ ሹምና ገንዘብ ያዡን ጨምሮ በስሩ የሚገኙትን ሰራተኞች እያስተባበረ እየተከታተለና እየተቆጣጠረ

የክበቡን የአለት ተእለት ስራ እንቅስቃሴ ይመራል፡፡

ሸ. የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን በማስፈቀድ በመዝናኛ ክበቡ ስም ንብረት ለመግዛትና ለመሸጥ

የሚያስችሉ ውሎችን ይዋዋላል፡፡

ቀ. በማኔጅመንቱ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን በተግባር ላይ ያውላሉ፡፡

በ. ሌሎች ለስራ አስፈፃሚው የሚሰጠውን ስራ ያከናውናል፡፡

4. ምክትል ሊቀ መንበር
ሀ. ሊቀመንበሩ በማይኖሩበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፣

ለ. በሊቀመንበሩ ወይም በማኔጅመንቱ የሚሰጠውን ተጨማሪ ስራ ያከናውናል፡፡

5. ፀሐፊ፣
ሀ. የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፀኃፊ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ለ. ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት የመዝናኛ ክበቡን የመጻጻፍ ግንኙነት

ስራዎች ያከናውናል፡፡

8
ሐ. የስራ አስፈጻሚውን አጀንዳ ያዘጋጃል ቃለጉባኤ ይይዛል፡፡

መ. የመዝናኛ ክበቡን ማህተም፣ ሰነድና መዛግብት ይይዛል።

6. ሂሳብ ሹም

ሀ. የመዝናኛ ክበቡን ገቢና ወጪ ሂሳብ በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡

ለ. የመዝናኛ ክበቡ ሂሳብ የሚንቀሳቀሰው በታወቀ የሂሳብ አሰራር ደንብ መሰረት መሆኑን
ያረጋግጣል፡፡
ሐ. በመዝናኛ ክበቡ ስም የተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቼክና የወጪ ሰነዶች ላይ ከሊቀ መንበሩ እና ከምክትል

ሊቀመንበሩ ጋር በጣምራ ይፈርማል፡፡

መ. የክበቡ የሂሳብ መዛግብት በጥንቃቄ እንዲያዙ ያደርጋል፡፡

ሠ. የሂሳብ መዝገብ፣ገቢና ወጭ፣ ሃብትና እዳን ያካተተ ሰነድ ያዘጋጃል፡፡

ረ. ክበቡ ተጨማሪ ገቢ በሚያስገኙ ሥራዎች ላይ በሚሰማራበት ጊዜ ለዚሁ ስራ የሚውሉ የተለያዩ የሂሳብ


መዛግብት እንዲያዙ ያደርጋል፡፡

7. ገንዘብ ያዥ
ሀ. የመዝናኛ ክበቡን ገቢዎች በህጋዊ ደረሰኝ ይሰበስባል፣

ለ. የተሰበሰበውን ገንዘብ በ ኢ ት ዮ ጽ ያ ን ግ ድ ባንክ ገቢ ያደርጋል፤ ገቢ ያደረገበትን ደረሰኝ

በጥንቃቄ ያስቀምጣል፣

ሐ. ለስራ ማስኬጃ ወጪዎች የሚሆን ከብር 2000 (ሁለት ሺህ ) ያልበለጠ መጠባበቂያ ገንዘብ ይይዛል፣

መ. ከሂሳብ ሹሙ ጋር የገቢና የወጪ ሂሳብ በየወሩ ያመሳክራል፡

ሠ. የመዝናኛ ክበቡን ቼክ ይይዛል፣

አንቀፅ 18
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስብሰባ፣ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ-ሥርአትና
የ አ ባ ላ ት አ ገ ል ግ ሎ ት ዘ መን

1. የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ በአመት 4 ጊዜ የሚከናወን ሆኖ አስቸኳይ ስብሰባ የሚያስፈልግበት ምክንያት ሲኖር
ልዩ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል፣
2. አስቸኳይ ስብሰባ በሊቀመንበሩ ወይም በምክትል ሊ ቀ መ ን በ ሩ ሊጠራ ይችላል፣
3. ከኮሚቴው ውስጥ ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤው እንደተሟላ ይቆጠራል፣ ምልአተ ጉባኤ ከተሟላ
ድጋሚ ለስብሰባ ጥሪ ይደረጋል፡፡ በድጋሚ በተደረገው ጥሪ ምልአተ ጉባኤ ካልተሟላ በተገኙ አባላት ስብሰባ
ሊካሄድ ይችላል፣

4. ውሳኔዎች በድምፅ ብልጫ ይተላለፋሉ፤ ድምፅ እኩል የሚከፈልበት ጊዜ ሊቀመንበሩ የደገፈው ሃሳብ ይፀናል፣

9
5. የኮሚቴ አባላት የአገልግሎት ዘመን ለ 2 አመት ይሆናል፡፡ ሆኖም አንድ የኮሚቴ አባል ከሁለት ጊዜ በላይ
ሊመረጥ አይችልም፣

6. የኮሚቴ አባላት ያለደመወዝ ያገለግላሉ፤ ሆኖም ለክበቡ ስራ ለሚያወጡት ወጪዎች ማካካሻ ይከፈላል፡፡

አንቀፅ 19

የኦዲተር ኃላፊነትና ተግባር

1. የመዝናኛ ክበቡ ኦዲተር የክበቡ ሊቀ መንበር ወይም የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሊሆን አይችልም፡፡
2. ኦዲተሩ ተጠሪነቱ ለማኔጅመንት ሆኖ፤የሚከተሉት ስልጣንና ተ ግባሮች ይኖሩታል፡፡
ሀ. የመዝናኛ ክበቡን የገንዘብና የንብረት አስተዳደር ትክክለኛነት ይቆጣጠራል

ለ. የመዝናኛ ክበቡን የስራ እንቅስቃሴ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መካሄዱን ያረጋግጣል፣

ሐ. በኢትዮጵያ ተቀባይነት ባገኙ መመዘኛዎች መሰረት አመታዊ የኦዲት ሪፖርት አዘጋጅቶ ለማኔጅመንቱ
ያቀርባል

አንቀጽ 20
ስለ ሠራተኛ አቀጣጠር፣ አመዳደብና ጠቅላላ መብትና ግዴታ

1. ለክበቡ አገልግሎት ብቁ የሆኑ ሠራተኞች የመቅጠርና የማሰናበት ሥልጣን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ይሆናል፡፡

2. የክበቡ ሠራተኞች በሙሉ በክበቡ የገንዘብ አቅም መሠረት ይቀጠራሉ፤ ያስተዳደራሉ፡፡

3. የክበቡን ሠራተኞች አስተዳደር የሚመለከት የውስጥ ደንብ በማውጣት ሥራ አስፈጻሚው ይመራል፡፡

አንቀፅ 21
የመዝናኛ ክበቡ የገቢ ምንጭ

የመዝናኛ ክበቡ የገቢ ምንጮች የሚከተሉትን ናቸው


1. ክበቡ የሚያቀርባቸው የምግብ፣ የትኩስ እና የቀዝቃዘ መጠጦች አገልግሎት ገቢ
2. ለተለያዩ የስልጠና እና የስብሰባ ፕሮግራሞች ከሚዘጋጁ የቁርስ እና የምሳ ብፌዎች ከሚገኝ ገቢ
3. የተለያዩ የፍጆታ እቃዎችን ለሠራተኛው በማቅረብ ከሚገኝ ገቢ

አንቀፅ 22
የመዝናኛ ክበቡን መተዳደሪያ ደንብ ስለማሻሻል

10
1. የዚህ መተዳደሪያ ደንብ የማሻሻያ ሃሳብ ከማኔጅመንት አባላት 1/4ኛ ባላነሱ አባላት ጠያቂነት በስብሰባ
አጀንዳነት ይያዛል፡፡

2. የዚህ መተዳደሪያ ደንብ የማሻሻያ ሃሳብ በማኔጅመንት መደበኛ ስብሰባ የሚወሰን ሆኖ የማሻሻያ ጥያቄው ለማኔጅመንት
ሰብሳቢ፤ ጸሃፊ ወይም ከሥራ አስፈጻሚ ኮ ሚ ቴ ሊ ቀ መ ን በ ር ለስብሰባ ጥሪ ከመሰራጨቱ በፊት መቅረብ
ይኖርበታል፡፡

3. የመተዳደሪያ ደንቡ የሚሻሻለው የማሻሻያ ሃሳብ ከግማሽ በላይ የማኔጅመንቱ አባላት በተገኙበት የማኔጅመንት ስብሰባ
3/4 ኛ ድምጽ ሲያገኝ ነው፡፡

አንቀፅ 23
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን ስለማፍረስ
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚመረጠው ቢሆንም በአግባቡ ሥራውን ካልተወጣ ክበቡን የማስተዳደሩን ኃላፊነት ሙሉ
ለሙሉ በማኔጅመንቱ ውሳኔ ሊነጠቅ ይችላል።
አንቀጽ 24
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
የሚመረጠው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተጠናክሮ የመዝናኛ ክበቡን አስተዳደር እስከሚረከብ ድረስ የመሥሪያ ቤቱ ሴት ሠራተኞች ፎረም
መዝናኛ ክበቡን የገቡት የውል ጊዜ እስኪያበቃ እያስተዳደሩ ይቆያሉ፡፡

አንቀፅ 25
የመተዳደሪያ ደንብ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ የመተዳደሪያ ደንብ በ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

11

You might also like