Professional Documents
Culture Documents
መስከረም, 2013
Table of Contents
መግቢያ....................................................................................................................................................3
አንቀፅ 2 ትርጓሜ...................................................................................................................................3
አንቀጽ 3 አላማ.....................................................................................................................................5
1
አንቀጽ 5 ቅጥር.....................................................................................................................................6
አንቀጽ 24 ዝውውር............................................................................................................................18
አንቀጽ 27 ጠቅላላ...............................................................................................................................24
2
አንቀጽ 32 የመጓጓዣ ሰርቪስ አገልግሎት.................................................................................................27
አንቀጽ 42 ጠቅላላ...............................................................................................................................33
አንቀጽ 43 ልዩ ፈቃድ...........................................................................................................................34
አንቀፅ 50 ጠቅላላ................................................................................................................................36
3
አንቀፅ 55 የሰራተኛ የአገልግሎት የእድሜ ጣሪያ.......................................................................................52
ቅፃቅፆች................................................................................................................................................54
4
መግቢያ
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ የኢፌዴሪ አሠሪና ሠራተኛ ህግ አዋጁን በአገናዘበ ሁኔታ
ይህንን የሰው ሃብት አስተዳደር መመሪያ አዘጋጅቷል። የዚህ መመሪያ ዋና ዓላማ ቢዝነስ እንተርፕራይዙ
በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ላይ የሚያጋጥሙ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት ያለው ውሳኔ
ለመወሰን ማገዝና ሠራተኛው ጥቅሙን፣ መብቱንና ግዴታውን እንዲያውቅ ማስቻል ነው።ይህ መመሪያ
በሠራተኛ አስተዳደር፣በሥራ ቀናት፣ በሥነ ሥርዓት አከባበር፣ በንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣ በደመወዝና
ጥቅማጥቅም፣ በመረጃ አያያዝና አጠቃቀም፣ በልዩ ልዩ አበል አከፋፈልና ሌሎች ጉዳዮች ላይ
የኢንተርፕራይዙን ደንቦች እንዲይዝ ተደርጓል።
አንቀፅ 2 ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ
1. “አዋጅ” ማለት የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ማለት ነው።
2. “ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ” ማለት ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቢዝነሰ ኢንተርፕራይዝ ማለት ነው።
3. “ሠራተኛ” ማለት በአዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀፅ 2/3 መሰረት ከኢንተርፕራይዙ ጋር በቅጥር ላይ
የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ ነው።
4. “የስራ ሁኔታ” ማለት በአሰሪ እና ሰራተኛ መካከል ያለ ጠቅላላ ግንኙነት ሲሆን ይህም የስራ
ስዓትን፣ ደመወዝን፣ ፈቃዶችን፣ ሰራተኛ ከስራ በሚሰናበቱበት ጊዜ የሚገባቸውን ክፍያዎች፣
ጤንነትና ደህንነት፣ በስራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች የሚከፈል ካሳ፣ ሰራተኖች
ከስራ የሚቀነሱበትን ሁኔታ፣ የቅሬታ አቀራረብ ስርዓቶችንና የመሳሰሉትን ያጠቃላል።
5. “የሰራተኛ ቅነሳ” ማለት የአሰሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/11 በአንቀፅ 29 መሰረት
የተሰጠ ትርጉም ነው።
6. “ፈቃድ” ማለት በአዋጅ ቁጥር 1156/11 እና በዚህ መመሪያ መሰረት ሠራተኛው በመደበኛ የስራ
ጊዜ ደመወዝ እየተከፈለው ወይም ሳይከፈለው ከመደበኛ ስራው ለመቅረት የሚሰጥ ፈቃድ ነው።
7. “ላልተወሰነ ጊዜ የሚደረግ የስራ ውል” ማለት በአዋጁ አንቀፅ 9 መሰረት በቋሚ የስራ መደብ ላይ
የሚደረግ የስራ ውል ማለት ነው።
8. “ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ የሚደረግ የስራ ውል” ማለት በአዋጁ አንቀፅ 10
መሰረት የሚፈፀም የስራ ውል ነው።
9. “ደመወዝ” ማለት በአዋጁ አንቀፅ 53 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አንድ የኢንተርፕራይዙ
ሠራተኛ በስራ ውል መሰረት ለሚያከናውነው ስራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው።
ሆኖም ደመወዝ በአዋጁ አንቀፅ 53 ንዑስ አንቀፅ 2 ከ ሀ-ረ የተጠቀሱትንና የቢዝነሰ
ኢንተርፕራየዙን ጡረታ መዋጮ ድርሻ አይጨምርም።
10. “የሙከራ ጊዜ” ማለት አንድ ሠራተኛ የቢዝነሰ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ በስራ ውሉ
መሠረት ሊቀጠርበት ለታቀደው ቦታ ተስማሚ መሆኑን ለመመዘን ሚሰጥ ጊዜ ነው።
5
11. “የስራ ስንብት ካሳ” ማለት በአዋጁ 1156/11 አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የሙከራ
ጊዜውን የጨረሰና የስራ ውሉ የተቋረጠበት ሰራተኛ ከቢዝነሰ ኢንተርፕራየዙ የሚከፈለው
የስራ ስንብት ክፍያ ነው።
12. “መደበኛ የስራ ሰዓት” ማለት በአዋጁ አንቀጽ 61 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ሰራተኛው
ስራውን የያከናውንበት ወይም ለስራ የሚገኝበት ጊዜ ነው።
13. “ትርፍ የስራ ሰዓት” ማለት በአዋጁ አንቀጽ 66 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ በተጠቀሰውና በዚህ
ደንብ መሰረት ከተወሰነው የቀኑ መደበኛ የስራ ሰዓት በላይ የሚሰራ የስራ ሰዓት ማለት
ነው።
14. “የወሊድ ፈቃድ” ማለት ነፍሰ ጡር የሆነች የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ ከእርግዝናዋ
ጋር በተያያዘ ለምርመራ ከወሊድ በፊትና በኋላ በአዋጁ አንቀፅ 88 መሰረት ቢዝነሰ
ኢንተርፕራይዙ የሚሰጣት ፈቃድ ሆኖ ሰራተኛዋ ከምርመራ በኋላ የሀኪም ማስረጃ
የምታቀርብበት ነው።
15. “በስራ ላይ የሚደርስ ጉዳት” ማለት ስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም በስራ ምክንያት
የሚመጣ በሽታ ማለት ነው።
16. “በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ” ማለትበአዋጁ በአንቀፅ 98 በተቀመጠው መሰረት
ሰራተኛው ከሚሰራው የስራ አይነት ወይም ከሚያከናውናቸው የስራ አካባቢ የተነሳ
ሰራተኛው ላይ የሚደርስ የጤና መታወክ ማለት ነው።
17. “የአካል ጉዳት” ማለት በኣዋጁ አንቀፅ 99 በተቀመጠው መሰረት የመስራት ችሎታ መቀነስ
ወይም ማጣትን የሚያስከትል ሁኔታ በስራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው፡
18. “የደንብ ልብስ” ማለት አንድ ሰራተኛ በተመደበበት የስራ ፀባይ ምክንያትና በቢዝነስ
ኢንተርፕራይዙ አሰራር መመሪያ መሰረት በስራ ጊዜ ሁሉ የሚለበስ ልብስ ማለት ነው።
19. “የሙያ ደህንነት” ማለት በአዋጁ አንቀፅ 92 መሰረት የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙን ሰራተኞች
ደህንነትና ጤንነት በሚገባ ለመጠበቅ የጤና መታወከና የአካል ጉዳት እንዳይደርስባቸው
መከላከል የሚያስችል እርምጃዎችን መውሰድ ነው።
20. “ዝውውር” ማለት አንድ የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ በቅጥር ከተመደበበት የስራ
መደብ ወይም አካባቢ ወደሌላ የስራ መደብ ወይም አካባቢ የሚፈፀም የሰራተኛ ዝውውር
ነው።
21. “የደረጃ እድገት” ማለት ከአንድ የስራ መደብና ደመወዝ ወደ ከፍተኛ የስራ መደብና
ደመወዝ የሚደረግ የደረጃ ለውጥ ማለት ነው።
22. “የዲሲፒሊን እርምጃ” ማለት የበቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ የተጣለበትን ግዴታና
ሃላፊነት ባለመወጣቱ ወይም ደንቡንና መመሪያዎችን ባለማክበሩ በሚፈፅማቸው ጥፋቶች
ምክንያት በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ በስነስርአት እርምጃ አወሳሰድ ሰንጠረዥ መሰረት የፍርድ
ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ በመመሪያው መሰረት በተቀመጠው የቅጣት ሰንጠረዥ ሰራተኛውን
ከጥፋቱ ለመመለስና ለማስተካከል የሚወስዳቸው የዲሲፒሊን እርምጃዎች ማለት ነው።
23. “የጉዳት ካሳ” ማለት በአዋጅ አንቀፅ 109 መሰረት በስራ ላይ በሰራተኛው ጥፋት
ምክንያት ላልተከሰተ ጉዳት ለሰራተኛው የሚከፈል ካሳ ማለት ነው።
24. “በስራ ላይ የደረሰ አደጋ” ማለት ማንኛውም የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሠራተኛ ስራውን
በማከናወን ላይ ሳለ ወይም ከስራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ አደጋ ከደረሰበት ሠራተኛ
ውጭ በሆነ ምክንያት ወይም ሰራተኛው ስራውን ለማከናወን ባደረገው ጥረት ምክንያት
በሰራተኛው አካል ወይም በአካሉ በማንኛውም ክፍል ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት
የደረሰበት ጉዳት ማለት ነው።
25. “ኮሚቴ” በዚህ ደንብ መሰረት የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ የስራ መሪዎች የሚወክሏቸው
አካላት የሚገኙበት ኮሚቴ ማለት ነው።
6
26. “የአስተዳደር ስራ መመሪያ” ማለት አዋጁንና በመንግስት የሚወጡትን የአሰሪ እና
ሠራተኛ ጉዳይ የሚመለከት ደንቦችና መመሪያዎችን ሳይቃረን ቢዝነሰ ኢንተርፕራየዙ
ሚያወወጣው የስራ ደንብ ነው፡
አንቀጽ 3 አላማ
ይህ መመሪያ የሚከተሉት ዓላማዎች አሉት፡-
1.2 በማንኛውም የስራ ደረጃ የሚወጣ ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ የሚከተሉትን
መረጃዎች ማካተት ይኖርበታል፡-
7
ሠ/ ለሰራ መደቡ የሚያስፈልገው የስራ ልምድ
ረ/ የክፍት ስራ መደቡ ብዛት
ሰ/ የመመዝገቢያ ቦታ፣ ቀንና ስዓት
ሸ/ ፆታ ፣ እድሜ እንደ አስፈላጊነቱ
ቀ/ የቅጥር ሁኔታ /ቋሚ ወይም ኮንትራት/
በ/ የፈተና ቀኑ ወደፊት በውጥ ማስታወቂያ ይገለፃል
ተ/ ተያዥ
ቸ/ የስራ መደቡ ጥቅማ ጥቅም ካለው
ነ/ እንደ አስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ
ኘ/ የስራ መደቡ የሚጠይቀው ልዩ እውቀት፣ ችሎታና ክህሎት ካለ
1.3 የቅጥር ማስታወቂያ በጋዜጣ ወይም ስራ ፈላጊ ያየዋል ተብሎ በሚታሰቡ የማስታወቂያ
ቦታዎች ለ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ተለጥፎ ምዝገባ ይካሄዳል።
1.4 ዲፕሎማ፣ ዲግሪ፣ ማስተርስ ለሚጠይቁ የስራ መደቦች የስራ መደቡ የስራ ልምድ
የማያስፈልግ ከሆነ እንደ አስፈላጊነቱ ፈተና መስጠት ሳያስፈልግ በ G.P.A ውጤት በመለየት
ቅጥር ይፈፀማል። ይህም በሰው ሀብት አስተዳደርና በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ አስተባባሪ
ቀርቦ ሲወሰን ተግባራዊ ይሆናል።
1.5 አንድ ሰራተኛ ሲቀጠር ቢያንስ የሚከተሉትን መረጃዎች ማሟላት ይኖርበታል፡-
ሀ/ የትምህርት ማስረጃ
ለ/ የስራ ልምድ /አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ/
ሐ/ የጤንነት ምርመራ ማረጋገጫ የሀኪም የምስክር ወረቀት
መ/ የሂወት ታሪክ ቅጽ መሙላት
ሠ/ የፖሊስ እጣት አሻራ መርመራ ውጤት
ረ/ ተያዥ ማቅረብ /አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ/
ሰ/ ቃለ ማሀላ መፈፀም፣ ሆኖም ከስራ ላይ ለሚቀጠሩ ሰራተኞች በ ሐ እና ሠ
የተጠቀሱት ግዴታ አይሆኑም።
1.6 የጣት አሻራና የጤንነት ምርመራ ውጤት ለማቅረብ የማይቻልበት ሁኔታ በጊዜያዊነት
ሲያጋጥም የሰው ሀብት አስተዳደርና የገቢ ማመንጫ ዋና አስተባባሪ ውሳኔ ይሰጡበታል።
1.7 ለአንድ ክፍት የስራ ቦታ ቢያንስ ሦስት ተወዳዳሪዎች ያልተገኙ እንደሆነ ለሁለተኛ ጊዜ
ማስታወቂያ በድጋሚ እንዲወጣ ተደርጎ በመጨረሻ የተገኙትን በማወዳደር ቅጥሩ
በኢንተርፕራይዙ ዋና አስተባባሪ ሲፀድቅ ቅጥሩ ይፈፀማል። የስራ መደቡ አስቸኳይነት
በድጋሚ ቢወጣም የመገኘት እድሉ ግምት ውስጥ ገብቶና ቅጥሩ የሚፈፀምለት የስራ ክፍል
8
አስተያየት ተጠይቆ መስፈርቱን አሟልተው ለውድድር የቀረቡ ቁጥራቸው ከሦስት በታች
ቢሆን በሰው ሀብት አስተዳደር ቅጥር እንዲከናወን በመስፈርቱ መሰረት የውሳኔ ሀሳብ
ከቀረበና በኢንተርፕራዙ ዋና አስተባባሪ ፀድቆ የተገኙትን ተወዳዳሪዎች በማወዳደር ቅጥሩ
ይፈፀማል።
1.8 በቢዝነስ ኢንተርፕራዙ ውስጥ በኮንትራት ተቀጥረው በማገልገል ላይ የሚገኙ ሰራተኞች
ለቦታው የተጠቀሰውን መስፈርት አሟልተው ከተገኙ በቋሚ የስራ መደብ ላይ ተመዝግበው
ሊወዳደሩ ይችላሉ።
1.9 በቢዝነስ ኢንተርፕራዙ በዲሲፕሊን የተሰናበተ ሰራተኛ በድጋሚ መቀጠር አይችልም።
1.10 በተመሳሳይ ቀንና ቁጥር ከወጡ የተለያዩ ማስታወቂያዎች መካከል አንድ
አመልካች መመዝገብ የሚችለው በአንድ ክፍት የስራ መደብ ብቻ ይሆናል።
1.11 አዲስ ሰራተኛ ሲቀጠር አመልካቹ ለስራው ተፈላጊ ችሎታ ያለው መሆኑን
ለማረጋገጥ እንደ አስፈላጊነቱ የፅሁፍና የቃል ወይም የተግባር ፈተና ይሰጣል።
1.12 አንድ ሰራተኛ የሙከራ ጊዜውን ፈፅሞ በውሉ መሰረት ሲቀጠር ደብዳቤ
እንዲሰጠው ይደረጋል፣ በልዩ ልዩ ምክኒያት ደብዳቤ ሳይደርሰው ቢቀር በውሉ ጊዜ
እንደተቀጠረ ይቆጠራል።
1.13 በአጠቃላይ ውጤት የነጥብ ብልጫ አግኝቶ/ታ የተመረጠ/ች ተወዳዳሪ የጥሪ
ማስታወቂያ ለ 3 ተከታታይ የስራ ቀናት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲለጠፍ ይደረጋል፣
በ 3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ሪፖርት ካላደረገ አንደኛ ተጠባባቂ በተመሳሳይ
መንገድ እንዲቀጠር ይደረጋል። አንደኛ ተጠባባቂ ካልቀረበ በውጤታቸው መሰረት
በተከታታይ ጥሪ በማድረግ እንዲቀጠሩ ይደረጋል።
የኮሚቴው አባለት
ሀ. የሰው ኃይል አስተዳደር (ፐርሶኔል)……………………………….. ሰብሳቢ
ለ. በስራ አስከያጁ የሚመረጡ 2 የማኔጅመንት አባላት……………… አባል
ሐ. ቅጥር የሚፈፀምለት መምሪያ አስተባባሪ ……………..……..…… ፀሃፊ
መ. 2 የሰራተኞች ተወካዮች ………………..…………………...…… አባል
9
ሠ/ የቅጥርና ደረጃ እድገት የደመወዝና የደረጃ ሁኔታ በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ቦርድ
በሚሰጠው ደረጃና መጠን የሚወሰን ይሆናል።
10
3. 12 ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ወይም ከ 1992 ዓ.ም በኋላ 10 ኛ ክፍል ያጠናቀቀና ከዚያ በታች
የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን ለሚጋብዙ የስራ መደቦች ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት
ያገልግሎት ማስረጃ ከሚወዳደሩበት መደብ ጋር ያለውን ተዛማጅነት በቀጥታና በተዘዋዋሪ
ይዛመዳል ወይም አይዛመድም ብሎ መፈረጅ ሳያስፈልገው እንዲወዳደሩበት ይደረጋል።
ይህም ማለት ፈተናውን ማለፍ እስከቻሉ ድረስ የስራ ልምዳቸው በሁለገብነት
ያገለግላቸዋል።
4. በተለያየ ሙያ ስልጠና ሰርፍትኬት ፣ ዲፕሎማ በሚጠይቁ የስራ መደቦች ላይ 12 ኛ ክፍል
ያጠናቀቁና ከ 1992 ዓ.ም በኋላ 10 ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ከዛ በታች የሆኑ የትምህርት
ዝግጅት ያላቸው አብረው የሚጋበዙበት ሁኔታ ሲኖር የሚያቀርቡት ማስረጃ ለስራ መደቡ
አግባብ ያለው ሊሆን ይገባል። የስራ መደቡ የሚጠይቀውን የሙያ መስፈርት ፣ የትምህርት
ዝግጅት ወይም በልምድ /በሁሉም/ አሟልተው ያልቀረቡ መወዳደር አይችሉም። ይሁን
እንጅ ኢንተርፕራይዙ የተሻለ ብቃት ያለው ሰራተኛ በተለየ ሁኔታ ሊቀጥር ይችላል።
5. ለአንድ ስራ መደብ ለመወዳደር ከሚጠይቁት ተፈላጊ ችሎታዎች በላይ ማስረጃ ይዘው
የሚቀርቡ ቢኖሩ ማስረጃው ተጨማሪ ነጥብ አያስገኝም፣
6. ለአንድ የስራ መደብ በርካታ አመልካቾች በሚቀርቡበት ጊዜ በቅጥርና በደረጃ እድገት
ኮሚቴው አማካኝነት የማጣሪያ ምርጫ በማድረግ ተመራጭ ችሎታና ብቃት ያላቸውን
እጩዎች ብቻ መርጦ ለውድድር ሊያቀርብ ይችላል። በእጩነት የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች
እስካሉ ድረስ ቢያንስ ለአንድ መደብ ከሦስት ያላነሱ ተወዳዳሪዎች ቢሆኑ ይመረጣል፣
ካልሆነ ግን አንድም ተወዳዳሪ ቢሆን ከተቋሙ ጥቅም አንፃር ተመዝኖ ቅጥር ሊፈፀም
ይችላል።
7. ተፈላጊው ሰራተኛ ለመቅጠር ተፈላጊ ችሎታውን የሚያሟላ ካላገኘ የሚከተሉትን
ሁኔታዎች በማሟላት ሰራተኛ በታሳቢ ሊቀጥር ይችላል። ክፍት ለሆኑ ዲግሪና ከዚያ በላይ
ለሚጠይቁ የስራ መደቦች ተወዳዳሪ በዝውውርም ሆነ በደረጃ እድገት በማይገኝበት ጊዜ
የኢንተርፕራይዙ የስራ አመራር ቦርድ በወሰነው ደረጃና ደመወዝ በታሳቢነት ቅጥር
እንዲፈፀምለት ያደርጋል።
11
የሚቅርብ ሳይኖር ሲቀር ወይም በቂ ባለሙያዎች ቀርበውም ዝቅተኛውን
የማለፊያ ነጥብ ሳያሟሉ ሲቀሩ ነው።
12
እየተከፈላቸው በመደበኛ የስራ ስዓት የተወሰነ ስራን ለማከናወን ሊቀስም የሚችለውን
የስራ ችሎታን የሚገልፅ ማስረጃ ሲሆን ማስረጃውም የተሟላ ነው የሚባለው፡-
4. ፈተናውን ያለፉት ተወዳዳሪዎች ዝርዝር የኮሚቴውን የውሳኔ ሀሳብ የያዘ የመረጣ ሂደቱ ቃለ
ጉባኤ ጋር በውጤታቸው ቅደም ተከተል ተደራጅቶ ስራ አስከያጁ ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ
እንዲሰጥበት ይደረጋል። ዳይሬክተሩ በማይገኝበት በተወካይ ውሳኔ እነዲሰጥበት ይደረጋል።
13
አንቀጽ 11 የስራ ውል
በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ መዋቅር እና የረጅም ጊዜ የሰው ኃይል ዕቅድ መሰረት ክፍት የስራ መደብ
በሚኖርበት ጊዜ ኢንተርፕራይዙ ውስጥ ካሉ ሰራተኞች መካከል በዝውውር ወይም በዕድገት
በክፍት ቦታው ላይ ሰራተኛ መመደብ ሳይችል ሲቀር በአዋጁ እና በዚህ መመሪያ መሰረት ሰራተኛ
ቅጥር ይፈጽማል። የሰራተኛ ቅጥር እና የሥራ ውል ይዘት በአዋጁ መሰረት ይሆናል
14
አንቀጽ 17 የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ግዴታዎች
ቢዝነስ ኢንተርፕራየይዙ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል፡-
1. በአዋጁ ወደፊት መንግስት የሚያወጣቸው ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን የማክበር።
2. ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ የተቋቋመበትን ዓላማና ስትራቴጂ፣ ራዕይ፣ ተልዕኮና እንዲሁም
አሰራር ስርዓትና የሥራ ዕቅድ የማሳወቅ።
3. ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ለሥራ መሪዎች እና ለሰራተኞች የአዋጁን ትርጉም፣ መንፈስና
አፈፃፀም በሚገባ እንዲረዱ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ።
4. በአዋጁ አንቀጽ 92 ስለ ሙያ ደህንነት፣ ጤንነት እና የሥራ አካባቢ የተዘረዘሩትን የስራ
ግዴታዎች መወጣት፣ በሥራ ላይ ሊደርሱ ለሚችሉ የአደጋ መከላከያዎችና የሥራ እና የደንብ
ልብስ የማቅረብ እንዲሁም አግባብ ያላቸው መ/ቤቶች የሚሰጡትን መመሪያዎች የመከታተል
እና የመተግበር።
5. ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የስራ ኃላፊነቱንና ገደብ የሚገልጽ የሥራ መዘርዝር የመስጠት፣
6. በስራ ውሉ መሰረት ሰራተኛው ስራውን በሚፈልገው ጊዜና ጥራት እንዲያከናውን እንደ
አስፈላጊነቱ ለሥራ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ ማቴሪያልና መሳሪያ ማቅረብ።
7. የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ለሰራተኛው ያለምንም
ክፍያ የመስጠት ግዴታ ሲኖረው ነገር ግን ሰራተኛው የተሰጠው መታወቂያውን ካጠፋ ላጠፋው
መታወቂያ ወረቀት ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ በሚያወጣው የክፍያ ስርዓት መሰረት ክፍያ
በመፈፀም ተለዋጭ መታወቂያ ይሰጣል።
8. ሰራተኛው በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ የስራ ደንብና በአዋጁ ማግኘት የሚገባውን ጥቅማጥቅም
በወቅቱ እንዲያገኝ ማድረግ።
9. በማንኛውም ሁኔታ የሰራተኛውን መብትና ክብር፣ ህሊና የሚነኩ ተገቢ ያልሆኑ አሰራሮችና
ተግባሮች ከመፈፀም መቆጠብ።
10. በአዋጅ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ለሰራተኛው ደመወዝና ሌሎች ተገቢ
ክፍያዎች የመክፈል።
11. በአዋጅ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 6 የሰራተኛው ጤንነት እነዲመረመር በህግ ወይም አግባብ
ባለው አካል ግዴታ በሚጣልበት ጊዜ ለምርመራው የሚያስፈልገው ወጪ ይሸፍናል።
12. በአዋጅ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 8 በተጠቀሰው መሰረት የስራ ውል በሚቋረጥበት ጊዜ
ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛው የነበረውን የሥራ ዓይነት፣ የአገልግሎት ዘመኑን፣ ሲከፈለው
የነበረውን ደመወዝ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ለሰራተኛው ያለክፍያ ይሰጣል።
13. ከአንድ የስራ ቦታ ወደ ሌላ የስራ ቦታ ለሚዛወር ሰራተኛ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ በቦታው
ሊያገኙ የሚገባውን ጥቅማጥቅሞች ይሰጣል።
15
5. ለሥራው ሲባል የተሰጡትን ማቴሪያሎችና ንብረቶች ወጪ ቆጣቢ በሆነ፣ ወጪን መቀነስ
በሚያስችል አግባብ ረጅም የአገልግሎት ዘመን መስጠት በሚያስችል አግባብ መያዝና
መጠቀም።
6. አደጋ የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በቀጥታ ቢመለከተውም ባይመለከተውም አደጋው
ከመድረሱ በፊት ለሚመለከተው አካል አስቀድሞ ማሳወቅ፣ በሥራ ቦታ ወይም በሰራተኛው
ላይ አደጋ ሲደርስ ግንባር ቀደም ሆኖ መቆም፤መርዳትና መተባበር።
7. ለራሱ እና ለሥራ ጓደኞቹ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ደህንነትና ለ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ
ሥራ ጐጂ የሆኑና አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያመጡ ድርጊቶችን አለመፈፀም፣ ሌሎችም ሲፈዕሙ
ሲመለከት ለሚመለከተው ኋላፊ ማሳወቅ።,
8. ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ በሚያቀርብለት የሰው ኃይል፣ ማቴሪያልና የሥራ መሣሪያ ተጠቅሞ
ውጤታማ ሥራ የመስራት ግዴታ አለበት።
9. በሚመለከተው ባለስልጣን ፈቃድ ካልተሰጠ በስተቀር በሥራ ምክንያት በእጁ የገባውን ሰነድ
እና ሚስጥር፣ ማናቸውም የድርጅቱን ንብረት መሳሪያ ወይም ቁሳቁስ ለግል ጥቅሙ መውሰድ
ወይም ለ 3 ኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ወይም ከድርጅቱ ሥራ ጋር ላልተያያዙ ተግባር
አለማዋል። ሌሎችም እንዳይፈፀሙ የመቆጣጠር ሲያጋጥመውም ለሚመለከተው ኃላፊ
ማሳወቅ።
10. በአዋጁና በዚህ የአስተዳደር መመሪያ የተጠቀሱትን የስነ - ስርዓትና ዲሲፕሊን ደንቦች
ማክበር ሌሎችም እንዲያከብሩ ማድረግ፣ የማያከብሩ ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው ኃላፊ ሪፖርት
ማድረግ።
11. ሰራተኛው ለሕይወቱ ወይም በሥራ ባልደረባው ወይም በሌሎች ሰዎች ወይም በስራ ሁኔታ
አደጋ ከሚያስከትል ከማናቸውም ድርጊት መራቅ።
12. ሰራተኛው በስራ ውሉና በስራ ደንቡ መሰረት በቅርብ ኃላፊ የሚሰጡትን የስራ ትዕዛዝና
መመሪያ መፈፀም።
13. ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ሰዓትና በስራ ላይ የተሰጡትን የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን
መጠቀም፣ የራሱን ንጽህና መጠበቅ እና የተሰተካከለ አልባሳት መልበስ አለበት።
14. ማንኛውም ሰራተኛ በራሱ ፈቃድ ስራ በሚለቅበት ጊዜ ለኢንተርፕራይዙ ከአንድ ወር
በፊት የማሳወቅ ግዴታ አለበት።
15. የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙን አንድነት፣ ሰላም የሚያናጋ የሀሰት ወሬና አልቧልታ ከመንዛት
መቆጠብ፣ የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙን ጥቅም የሚፃረር ስራ በወሬም ይሁን በተግባር
አለመፈፀም፣ ሌሎችም እንዳይፈጽሙ መቆጣጠርና ሲያጋጥመዎ ለሚመለከተው የቢዝነስ
ኢንተርፕራይዙ ኃላፊ ማሳወቅ /ሪፖርት/ ማድረግ።
16. በምርት ላይ የተሰማሩ ሰራተኛ ለምርት ሂደት ፈርሞ የተረከባቸውንና የተሰጡትን ጥሬ
ዕቃዎችና ሌሎች ማቴሪያሎች በአግባቡ በተቀበለበት ስታንዳርድ መሰረት ተጠቅሞ የምርት
ሂደቱን ሪፖርት እና የእጅ ቀሪ ጥሬ ዕቃና ማቴሪያል ከተቀበለው ጋር አገናዝቦ የባከነውን
በሪፖርት መልክ አስቀምጦ በሰነድ የማስረከብ።
17. በተጨማሪም ኃላፊው የሚያዘውን ተጨማሪ ሥራዎች የመስራት ግዴታ አለበት።
16
2. ሰራተኛው ፈፀመ የተባለው ጥፋት እስከሚጣራ ድረስ ሰራተኛውን ከስራ ደህንነት በተያያዘ
ጉዳይ ማገድ አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ወድያው ለተወሰነ ጊዜ ያለ ደመወዝ ከስራው ማገድ ይቻላል።
አንቀጽ 24 ዝውውር
አንድ ሰራተኛ በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ውስጥ ከአንድ የሥራ መደብ ወደ ሌላ ተመሳሳይ የሥራ
መደብ የማዛወር አላማ ስራ እና ሰራተኛውን በማገናኘት የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ የሥራ
እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራ ስራ እንደተጠበቀ ሁኖ:-
17
5. በልዩ ልዩ ምክንያት ጊዜያዊ ክፍት የስራ መስክ ስልጠና የወሰደ ሰራተኛ መመደብ ሲያስፈልግ
በኢንተርፕራይዙ በተመሳሳይ የስራ መስክ ስልጠና ከወሰደ ሰራተኛ መካከል በቋሚነት ወይም
በጊዜያዊነት አዘዋውሮ ሊያሰራ ይችላል።
6. ነፍሰ ጡር ሴት የምትሰራበት የስራ መደብ ለጤናዋ የማይመች መሆኑ በህክምና ቦርድ ሲረጋገጥ
የምታገኘው ጥቅም ሳይነካ የሚመጥናት ክፍት የስራ መደብ ከተገኘ ኢንተርፕራይዙ ለጤንነትዋ
ወደሚያመች ሌላ የስራ መደብ አና ቦታ ያዛውራታል፤
7. አንድ ሰራተኛ የተፈፀመበት ዝውውር አግባብነት የለውም ብሎ ሲያምን አቤቱታውን በቅሬታ
አቀራረብ ስነ-ስርዓት መሰረት የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
8. አንድ ስራተኛ የጊዜያዊ ዝውውር ከ 6 ወራት ለበለጠ ጊዜ እንዲቆይ አይደረግም፤
18
1.8 የኢንተርፕራይዙ ስራ አስከያጅ ያላፀደቀው እንደሆነ የደረጃ እድገቱ እንደገና
እንዲታይ ለሰው ሀብት አስተዳደር ይመለሳል፣ የሰው ሀብት አስተዳደርም
አስፈላጊውን ማስተካከያ ይሰራል።
1.9 የደረጃ እድገቱ የሚሰጠው እድገቱ በደብዳቤ ወጭ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ሲሆን
ክፍያውም በዚህ መሰረት ይፈፀማል።
1.10 ለደረጃ እድገት ብቸኛ ተወዳዳሪ ቢቀርብ መስፈርቱን ተፈትኖ ማለፊያ ውጤት
ካገኘ እድገቱን ሊያገኝ ይችላል።
1.11 እድገት ያገኘው ሰራተኛ የሙከራ ጊዜ አይኖረውም።
1.12 ደረጃ እድገት ያገኘ ሰራተኛ ለሌላ እድገት የሚወዳደረው እድገቱን ካገኘ ከ 9 ወር
በኋላ ይሆናል።
1.13 አንድ የደረጃ እድገት ያገኘ ሰራተኛ የደመወዝ መጠን ከስራ መደቡ ጋር እኩል
ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ያንድ እርከን ደመወዝ ይጨመረዋል።
1.14 የደረጃ እድገት ያገኘ ሰራተኛ ደመወዝ ከአዲሱ የስራ መደብ ደረጃ ጣሪያ እኩል
ወይም ከዚያ በላይ ሆኖ ከተገኘ ደመወዙ ያው የድሮው ይሆናል።
2. ለደረጃ እድገት ብቁ ስለመሆን፡-
19
በ/ የኮንትረት ስራ መደብ ሲኖር የኮንትራት ሰራተኞች ተወዳድረው እድገት ሊሰጣቸው
ይችላል፣ በዚህ መመሪያ የተቀመጡ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣
ሀ/ የባችለር ዲግሪና የስራ ልምድ ለሚጠይቅ የስራ መደብ ሰራተኛው ዲግሪውን ከማግኘቱ
በፊት ዲፕሎማውን ይዞ የሰራው አገልግሎት ከስራው ጋር በቀጥታ አግባብነት ያለው
አንድ ዓመት እንደ አንድ ዓመት ይያዝለታል፣
8. 12 ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ወይም ከ 1992 ዓ.ም በኋላ 10 ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ /ከዚህ በታች
የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን በደረጃ እድገት የሚጋበዙ የስራ መደቦች ተወዳዳሪዎች
የሚያቀርቡት የአገልግሎት ማስረጃ በተመለከተ በዚህ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፣
20
9. ለደረጃ እድገት የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ የሚያገለግለው ነጥብ በመስጠት
ለማበላለጥ ሳይሆን በደረጃ እድገት የወጣው ክፍት የስራ መደብ የሚጠይቀውን ተፈላጊ
ችሎታ መስፈርት በማሟላትና ለውድድር ለመመዝገብ ብቻ ይሆናል፣
10. በአንድ ደረጃ እድገት በወጣ ክፍት የስራ መደብ ለመወዳደር ከሚጠይቁ ዝቅተኛ ተፈላጊ
ችሎታዎች በላይ ማስረጃ ይዘው የሚቀርቡ ቢኖሩ ማስረጃው በተለየ ሁኔታ ታይቶ
ተጨማሪ ነጥብ አያስገኝላቸውም፣
11. የሰራተኛው የስራ አፈፃፀም መመዘኛ ቅጽ በየ 6 ወር አንድ ጊዜ ሚሞላ ቢሆንም ለደረጃ
እድገት ውድድር ግን የሚወሰደው ለተወዳዳሪው የሚሞላው 3 ቱ የመጨረሻ አማካኝ
ውጤት ነው። ቢያንስ በ 2 ቱ የስራ አፈፃፀም 50% እና በላይ መሆን አለበት፣
12. አዲስ ሰራተኛ ከሆነ የሁለት ጊዜ የስራ አፈፃፀም ይወሰድለታል፣
13. የደረጃ እድገት ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ የሚሞላ የስራ አፈፃፀም በወቅቱ ለወጣው
ማስታወቂያ አይወሰድም፣
14. የዲስፕሊን ቅጣት ወይም አፈፃፀም በሰራተኛው ማህደር ውስጥ በሪከርድነት ተይዞ
ከሰራተኛው ላይ ሊጠቀስ ወይም የደረጃ እድገት ነጥብ ለማስቀነስ የሚችለው ከዚህ በታች
በመለከተው ሰንጠረዥ መሰረት ይሆናል፡-
21
ለፅሁፍ ፈተና ------------- 30%
ለቃል ፈተና ---------------- 10%
4.2 የፅሁፍና የተግባር ፈተና መስጠት በማያስፈልግበት የስራ መደቦች ላይ የቃል ፈተና
ከ 100% ይወሰዳል፣
22
ክፍል ሶስት ደመወዝና ጥቅማጥቅም
23
አንቀጽ 29 የደመወዝ ጭማሪ
1. ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የገቢ ተቋሙ ከሚያገኘው የተጣራ ትርፍ
የመንግስት ገቢ ግብር፣ የንግድ ፈቃድ ግብር ተከፍሎ ለዩኒቨርሲቲው ፈሰስ በቦርዱ
በሚወሰነው መሰረት ሆኖ ቀሪውን ለኢንተርፕራይዙ ማስፋፊያ እና ለሰራተኛ ማበረታቻ
ክፍያና ደመወዝ ጭማሪ ያደርጋል።
2. በዓመቱ ደመወዝ ጭማሪ የተዘጋጀውን ገንዘብ ለሰራተኞች ለማደላደል ገቢ ማመንጫ
ተቋማቱ በጋራ በሚስማሙበት መሰረት ይፈፀማል።
3. ኢንተርፕራይዙ የደመወዝ ጭማሪ ሲያደርግ ሰራተኛው ጭማሪ የሚያገኘው ፡-
24
3. ጉዞው እንደተከናወነ ተልኮውን የፈፀመ ሰራተኛ የጉዞ ሂሳቡን ከማወራረዱ በፊት ስለ ተልዕኮው
የስራ ክንውን ሪፖርት ተልዕኮውን ለሰጠው ኃላፊ ማቅረብ አለበት።
4. ማንኛውም ሰራተኛ አስቀድሞ የተሰጠውን አበል ከማወራረዱ በፊት ሌላ ተልዕኮ እና አበል
አይሰጠውም።
5. የውሎ አበል ክፍያ ከአንድ ወር በላይ አይፈቀድም ሆኖም አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠር እና የውሎ
አበል ክፍያ የሚፈፀምበት ጉዞ በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይም እሱ
በወከለው አካል ሲፀድቅ ለአንድ ተጨማሪ ወር ብቻ ሊራዘም ይችላል።
6. ለጉዞ ከተፈቀዱት የጉዞ ቀናት በላይ የአበል መጠን ከፍ አድርጐ መስጠት አይፈቀድም።
7. አንድ ሰራተኛ የውሎ አበል የሚከፈለው በቋሚነት ከተመደበበት ከተማ 25 ኪሎ ሜትር እርቀት
ሲንቀሳቀስ ብቻ ነው።
8. የውሎ አበል አከፋፈል በመንግስት የአበል አከፋፈል መጠን መሰረት ተፈፃሚ ይደረጋል።
25
በግል ድርጅቶች ሠራተኛ ጡሮታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 መሠረት ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ የቢዝነስ
ኢንተርፕራይዙ ሠራተኞች ከደመወዛቸው እና ከድርጅቱ እየተቆረጠ የጡረታ ዋስትና ይቀመጥላቸዋል።
ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ለቋሚ ሠራተኞች በሥራ ሰዓት የ 24 ሰዓት የአደጋ ዋስትና ይገባል።
26
ተ.ቁ የስራ መደብ መጠሪያ ምርመራ
የደንብ ልብስ/ የስራ ልብስ ዓይነት
1. የጥበቃ ሰራተኛ በአመት 1 ቴትሮን ኮትና ሱሪ፣1 የተዘጋጀ ሸሚዝ፣ 1 ቆዳ ጫማ፣ 1 ኮፍያ
እንዲሁም በ 2 አመት 1 የዝናብ ልብስ እና በ 3 አመት 1 ካፖርት።
2. ጽዳትና ተላላኪ በአመት 2 ቴትሮን ጋወን፣ 2 ቆዳ ጫማ፣2 ባለ ሸምቆቆ ኮፍያ እንዲሁም
በአመት 1 ጃንጥላ እና ፕላስቲክ ጓንት እንዳለቀ።
3. የትራንስፖርት አገልግሎት አስተባባሪ፣ የህትመት ስራዋች አስተባባሪ፣ በ 1 አመት 1 ቴትሮን ጋዎን።
ለረዳት ንብረት ሰራተኛ፣ ለዋና ገንዘብ ያዥ እና ለረዳት ገንዘብ
ያዥ
4. የእነዳስትሪ ወርክሾፕ አስተባባሪ፣ የኮነስትራክሽን ና ህንጻ ግንባታ በአመት 1 የደህንነት ጫማ 2 ቴትሮን እስከ ደረቱ ኪስ ያለው ቱታ
ዲዛይን መምርያ ስ/አስከያጅ ዲዛይን ክፍል ሃላፊ ፣ ኮንስትራክሽን
ሱፐርቫዘር ክፍል ሃላፊ
5. በያጅ፣ ረዳት በያጅ፣ የእንጨት ስራዋች ባለሞያ ፣ ረዳት የእንጨት በአመት 2 የደህንነት ጫማ፣ 2 ቴትሮን እስከ ደረቱ ኪስ ያለው ቱታ ፣የአይን
ስራዋች ባለሞያ ፣ አውቶመካኒክ ፣ ረዳት አውቶመከኒክ መከላከያ መነፅር (እንዳለቀ) ፣የእጅ ጓንት(እንዳለቀ)
6. የእንስሳት ሃብትና የእርሻ ልማት አስተባባሪ በአመት 1 የፕላስቲክ ጫማ፣ 1 ቴትሮን እስከ ደረቱ ኪስ ያለው ሱሪና
ሸሚዝ
7. የዳልጋ ከብት ተንከባካቢ ሰራተኛ ፣ የበግና ፍየል ተንከባካቢ ሰራተኛ ፣ በአመት 2 የላስቲክ ጫማ፣ 2 ቴትሮን እስከ ደረቱ ኪስ ያለው ሱሪና ሸሚዝ
የደሮ አርቢና መጋቢ ሰራተኛ ፣ እና በ 2 አመት 1 የብርድ መከላከያ ካፖርት፣ የእጅ ፕላስቲክ
ጋንተ(እንዳለቀ)።
8. የእንስሳት ጤና ባለሞያ ፣ የእርሻ ልማት ባለሞያ ፣ የግምት ባለሞያ ፣
የጥረዛ ባለሞያ ፣ የህትመት በለሞያ በአመት 1 ቴትሮን ጋዎን።
9. የደረቅ ጭነት ሽፌር፣ የህዝብ ማመላለሻ ሹፌር ፣ የትነሽ መኪና ሽፌር
፣ ረዳት ሽፌር 2 ካኪ ቱታ በዓመት
10. ስትራክቹራል ኢንጂነር፣ ሳኒተሪ እነጂነር፣ ኤለክትሪካል ኢንጂነር፣
አርክቴክት ኢንጂነር፣ ረዚደንት ኢንጂነር፣ ሳይት ኢንጂነር፣ በአመት 2 የደህንነት ጫማ፣ 1 ቴትሮን ጋወን
መካኒካል ዲዛይን እንጅነር፣ ፣ ሰርቨየር
27
9. ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ በሥራው ባህሪ ምክንያት የሥራ ልብስ ለሚሰጣቸው ሠራተኞች በወር
አንድ ባለ 250 ግራም የልብስ ሳሙና ይሰጣል። ለጋራዥ ለወርክ ሾኘ ለማምረቻ መሳሪያዎች
መካኒኮች ለሥራው ኦሞ ያቀርባል። ለእያንዳንዱ ሠራተኛ አንድ ጥቅል የመፀዳጃ ወረቀት እና
ባለ 145 ግራም አንድ የገላ ሳሙና በወር አንድ ጊዜ ይሠጣል።
28
3. ስለ ትርፍ ሰዓት ክፍያ አንድ ሰራተኛ በሳምንት የእረፍት ቀኑ ከሰራ በአዋጁ አንቀፅ 68 ንዑስ
አንቀፅ 1 ባለው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
4. ማንኛውም የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ በመደበኛ የስራ ቀናት ትርፍ ሰዓት እንዲሰራ
ከተገደደ ለሰራባቸው ትርፍ ሰዓት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ይፈፀምለታል።
29
መሆኑ ሲረጋገጥ እና የአመት እረፍት ፈቃዱ ወደ ሚቀጥለው የበጀት አመት እንዲተላለፍ
የሰው ኃይል አስተዳደር መምሪያ ስራ አስኪያጅ በደብዳቤ ሲያጸድቀው ይሆናል።
4. አንድ የቢዝነስኢንተርፕራይዙሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀፅ 77
መሰረት ላገለገለበት የመጀመሪያ አንድ ዓመት 16 የስራ ቀናት የአመት ፈቃድ ይሰጠዋል።
ከአንድ አመት በላይ የተበረከተ አገልግሎት ለእያንዳንዱ ሁለት የአገልግሎት አመታት አንድ
የስራ ቀን እየተጨመረ ይሰጣል።
5. አንድ ሰራተኛ የአመት ፈቃዱን በሚወስድበት ጊዜ በስራ ላይ ቢሆን ኖሮ ሊከፈለው ከሚገባው
ጋር እኩል የሆነ በእረፍት ላይ ለሚቆይበት ጊዜ ደመወዝ በቅድሚያ መውሰድ ይችላል።
6. በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ጠያቂነት ሰራተኛው የአመት እረፍት እንዲወጣ ከተደረገ እረፍቱን
የሚወስድበት ጊዜ ከ 15 ቀናት በፊት ይነገረዋል። ሆኖም ይህ አባባል ውሉ የሚቋረጥበትን
ሰራተኛ አይመለከትም።
7. የአመት እረፍት ፈቃድን በገንዘብ ለውጦ ክፍያ ማድረግ አይፈቀድም። ሆኖም የአመት እረፍት
ተጠናቆ ከመውሰዱ በፊት የስራ ውሉ የተቋረጠ ሰራተኛ ፈቃድ ወደ ገንዘብ ተለውጦ
ይሰጠዋል።
30
አንቀጽ 43 ልዩ ፈቃድ
1. ለቤተሰብ ጉዳይ የሚሰጥ ፈቃድ ሆኖ ሰራተኛው
ሀ/ ለአንድ ጊዜ ህጋዊ ጋብቻ ሲፈፅም ወይም
ለ/ የትዳር ጓደኛው፣ ወላጅ፣ ተወላጅ ወይም እስከ ሁለተኛ ዘር ግንድ ድረስ የሚቆጠር
የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመድ ሲሞትበት ከክፍያ ጋር ለሦስት የስራ ቀናት ፈቃድ
ይሰጠዋል።
2. አንድ የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ቋሚ ሰራተኛ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ የሰው ኃይል አስተዳደር
መምሪያ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ቢዝነስ ኢንተርፕራየዙን ወክለው የሚሄዱ ሰራተኞች
በቀብር ስርዓት ላይ እንዲገኙ ይደረጋል።
2. በአዋጅ አንቀፅ 83/2 መሰረት አንድ ሰራተኛ የሲቪል መብቱን ሊያስጠብቅ ወይም የሲቪል
ግዴታውን ሲፈፅም ለዚሁ አላማ ላጠፋው ጊዜ ብቻ ከክፈያ ጋር ፈቃድ ይሰጠዋል።
3. አንድ የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ በፍርድ ቤት ወይም ፖሊስ ለተለያዩ ጥያቄዎች ሲፈለግ
እና ጥያቄውም በፖሊስ ወይም በፍርድ ቤት ሲረጋገጥ በፍርድ ቤት ወይም በፖሊስ የተፈለገበትን
ጉዳይ በመደበኛ የስራ ሰአት ከሆነ ለጥያቄው ለተፈገበት ወቅት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
ይሰጠዋል።
31
3. ማንኛውም ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛ የህመም ፈቃድ የሚያገኘው በመንግስት ከታወቀ
የህክምና ድርጅት ወይም ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ውል ከወሰደበት የህክምና ተቋም የህክምና ምስክር
ወረቀት እና ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ ይሆናል።
4. የህመም ፈቃድ ከማለቁ በፊት የስራ ውሉ ዘመን ካለቀ የህመም ፈቃድ አብሮ ይቋረጣል።
32
ስም እና የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ምልክት
የፋይል ቁጥር
የተከፈተበት ቀን
በውስጡ የያዘው ፋይል ብዛት
7. ደብዳቤዎች ከቢሮ ውስጥ በውስጥ ማስታወሻ ደብዳቤ የቢሮ ውስጥ ማስታወሻ ተብሎ በራስጌው
ተፅፎ ሊፃፃፉ ይችላሉ።
33
አንቀጽ 53 የስነ - ስርዓት ጉድለቶች ማረሚያ እርምጃዎች የተፃፈ ደብዳቤ ስለመቀበል
1. ጥፋት የፈፀመ ማንኛውም ሰራተኛ የስነ-ስርዓት ጉድለት ማረሚያ ፎርም ወይም ደብዳቤ
አልቀበልም ማለት አይችልም። ሆኖም ቅሬታ ካለው ፎርሙን ወይም ደብዳቤውን ተቀብሎ
በቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት መሰረት ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
2. በቃል ማስጠንቀቂያ ፎርም ላይ አልፈርምም ማለት እና ደብዳቤ አልቀበልም ማለት እንደ የስነ-
ስርዓት ጉድለቶች ተቆጥሮ በስነ-ስርዓት ጉድለቶች ማረሚያ እርምጃ ሰንጠረዥ መሰረት
ያስቀጣል።
3. የስነ ስርአት ጉድለቶች ማረሚያ እርምጃ ሰንጠረዥ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የተከለከሉ ድርጊቶች
መፈጸም ወይም የታዘዘውንና እንዲፈጽም ግዴታው የሆኑትን አለመፈጸም ለዲሲፕሊን
ግድፈቶች በቂ ምክንያቶች እንደሆኑ በመቁጠር በአጥፊው ላይ የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰዳል
የጥፋቶቹ አይነቶችና ደረጃ በደረጃ የሚወሰዱት የዲስፒሊን እርምጃዎች እንደሚከተለው
ተዘርዝረዋል
34
የጥፋት ዓይነት ለ 1 ኛ ጊዜ ለ 2 ኛ ጊዜ ለ 3 ኛ ጊዜ ለ 4 ኛ ጊዜ ለ 5 ኛ ጊዜ
ያለ በቂ ምክንያት ማርፈድ መዘግየት የጽሁፍ የመጨረሻ
ወይም ቀደም ብሎ መውጣት ወይም ማንቀጠንቀቂያና የ 5 የጽሁፍ
መቅረት የቃል ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቀን ደመወዝ ቅጣት ማስጠንቀቂያና ስንብት
ሀ/ እስከ ግማሽ ሰዓት መዘግየት ወይም የ 15 ቀናት
ቀደም ብሎ መውጣት ደመወዝ ቅጣት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ለ/ግማሽ ቀን መቅረት ያልሰራበት የጽሁፍ ማንቀጠንቀቂያና የ 7
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ የ 15 ስንብት
ደመወዝ ተቆርጦ ቀን ደመወዝ ቅጣት
ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ሐ/ አንድ ቀን መቅረት ያልሰራበት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የ 7 የመጨረሻ የጽሁፍ
ደመወዝ ተቆርጦ ቀናት ደመወዝ ቅጣት ማስጠንቀቂያ የ 15 ስንብት
ቀናት ደመወዝ ቅጣት
መ/ ከአንድ ቀን በላይ መደዳውን እስከ 3 የመጨረሻ የጽሁፍ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ቀን የቀረ ያልሰራበት ደመወዝ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
የ 5 ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ተቆርጦ ደመወዝ ቅጣት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ሠ/ መደዳውን አራት ቀን የቀረ የቀረበት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የ 10
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ቀን ደመወዝ ተቆርጦ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ደመወዝ ቅጣት
ረ/ መደዳውነ አምስት ቀን የቀረ ስንብት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ሰ/ አልፎ አልፎ በአንድ ወር ውስጥ 1 ዐ
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ቀን የቀረ
ደመወዝ ቅጣት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ሸ/ ለሚቀጥለው ተረኛ ሳያስረክብ የሄደ
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ሰራተኛ
ደመወዝ ቅጣት
የመጨረሻ
29.4.5.2 መዘዋወር/መታጣት
የ 10 ቀን ደመወዝ የጽሁፍ
ሀ/ ከምድብ ስራው መታጣት በሥራ ጊዜ የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና 2 ኛ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቅጣትና 2 ኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያና ስንብት
ስራውን ትቶ ያለፍቃድ ሲዘዋወር ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የ 15 ቀናት
የተገኘ
ደመወዝ ቅጣት
ለ/ በሥራ ሰዓት ከድርጅቱ ቅጥር ግቢ የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የ 7 ቀን ደመወዝ ቅጣትና 2 ኛ የመጨረሻ የጽሁፍ ስንብት
ያለፈቃድ የወጣ ያልሰራበት 2 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያና የ 15
35
ደመወዝ ተቆርጦ ማስጠንቀቂያ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ሐ/ ስራ መስራት ባለበት ሰዓት
ከተፈቀደው ጊዜ ቀድሞ ወይም የመጨረሻ
ከተፈቀደው ጊዜ በላይ ካፍቴሪ ተቀምጦ የጽሁፍ
የ 7 ቀናት ደመወዝ
የተገኘ ሰራተኛ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የ 2 ቀናት ደመወዝ ቅጣት ማስጠንቀቂያና ስንብት
ቅጣት
የ 15 ቀናት
ደመወዝ ቅጣት
ለ/ የተመደበበትን ስራ በቸልተኝነት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ወይም በግድየሌሽነት ሳያከናውን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 7
ማስጠንቀቂያ የ 15 ቀናት ስንብት
መቅረቱ በማስረጃ ከተረጋገጠ ቀን ደመወዝ ቅጣት
ደመወዝ ቅጣት
ለሚደርሰው ጥፋት ተጠያቂ ሆኖ
ሐ/ እንዲጠበቅ በተሰጠው ሥፍራ
ተገቢውን ጥበቃ ሳያደርግ ቀርቶ
ስንብት
ንብረት እንዲጠፋ ያደረገ
ለሚደርሰው ጉድለት ተጠያቂ ሆኖ
መ/ በኃላፊነት በተመደበበት የሥራ ክፍል
ተገቢውን ቁጥጥር ባለማድረጉ
ሁለተኛ ደረጃ የጽሁፍ
በሚመራቸው ሰራተኞችም ሆነ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 5 ከደመወዝና ከሥራ
ማስጠንቀቂያና የ 1 ዐ ቀናት ስንብት
በሌላ ወገን ወይም በድርጅቱ ላይ ቀናት ደመወዝ ቅጣት ደረጃ ዝቅ ማድረግ
ደመወዝ ቅጣት
ጉዳት የሚያደርስ ጥፋት ቢፈጽም
ለደረሰው ጉዳት ኃላፊ ሆኖ
36
ሊተባበር ሲገባው ለመተባበር
ፈቃደኛ ሆኖ ያለመገኘቱ ሲረጋገጥ
29.4.5.4. ካርድ መምታት/መፈረም
የመጨረሻ የጽሁፍ
ሀ/የሌላውን ሰራተኛ ካርድ የመታ ወይም
ማስጠንቀቂያ የ 15 ቀናት ስንብት
አስመስሎ የፈረመ
ደመወዝ ቅጣት
ለ/ ያለበቂ ምክንያት የሰዓት የመጨረሻ
መቆጣጠሪያ ካርድ ሲወጣና ሲገባ የጽሁፍ የጽሁፍ
ያልመታ ወይም የቃል ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ማንቀጠንቀቂያና የ 5 ማስጠንቀቂያና ስንብት
ያልፈረመ/ያልፈረመበት ደመወዝ ቀን ደመወዝ ቅጣት የ 15 ቀናት
ተቆርጦ ደመወዝ ቅጣት
ሐ/ በሰዓት መቆጣጠሪያ መዝገብ ላይ
የመጨረሻ የጽሁፍ
ፈረሞ ወይም ካርድ መትቶ ከስራው
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ያልተገኘ በስራ ላይ ያለነበረበት ጊዜ
ደመወዝ ቅጣት
ከደመወዙ ተቀናሽ ተደርጎ
የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የ 15 ቀናት ደመወዝ ቅጣትና
36.8.5.5 መተኛት
2 ኛ ደረጃ የጽሁፍ የመጨረሻ የጽሁፍ ስንብት
ሀ/ በስራ ጊዜ ተኝቶ የተገኘ ሰራተኛ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
የመጨረሻ የጽሁፍ
ለ/ በስራ ጊዜው ተኝቶ የተገኘ የጥበቃ
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ሰራተኛ
ደመወዝ ቅጣት
የመጨረሻ
29.845.6 በስራ ሰዓት መላፋት
የ 5 ቀን ደመወዝ የጽሁፍ
ሀ/ በሥራ ሰዓትና በስራ ላይ ሆኖ ሲላፋ የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና 2 ኛ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቅጣትና 3 ኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያና ስንብት
የተገኘ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የ 15 ቀናት
ደመወዝ ቅጣት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ለ/ በኢንተርፕራይዙ ቅጥር ግቢ ውስጥ
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም
ደመወዝ ቅጣት
29.845.7 በሥራ ሰዓት ፣ የሥራ፣የደንብ
ልብስና የአደጋ መከላከያ አለመጠቀም
37
የመጨረሻ
ሀ/ ለሥራ የተሰጠውን ልብስ፣ጫማ፣ የ 2 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የ 7 ቀን ደመወዝ የጽሁፍ
የአደጋ መከላከያና የመሳሰሉትን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 21 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ቅጣትና 3 ኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያና ስንብት
አለመጠቀም እና በንፅህና አለመያዝ ማስጠንቀቂያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የ 15 ቀናት
ደመወዝ ቅጣት
ለ/ የተሰጠውን የስራ ልብስ፣ጫማ የአደጋ የ 4 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
መከላከያ ባለመጠቀም አደጋ 1 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ቢደርስበት ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
ሐ/ ቀበቶ ያላቸውን ተሽከርካሪ የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና 3 ኛ
ለሚያሽከረክሩ ሾፌር የአደጋ 2 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
መከላከያ ቀበቶ አለማሰር ማስጠንቀቂያ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
29.4.5.8 በንብረት ላይ ወይም በስራ ቦታ
ሆን ብሎ አደጋ ስለማድረስ የመጨረሻ የጽሁፍ
የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የ 7 ቀን ደመወዝ ቅጣትና 3 ኛ
ሀ/ የሚሰራባቸውን መሳሪያዎች የጣለ፣ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
መሳሪያውን ተክቶ ወይም ዋጋውን ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ከፍሎ
ለ/ ለሥራ አስፈላጊ ሳይሆን መርዛማ
በህግ ተጠያቂ ሆኖ ስንብት
ኬሚካል ይዞ የተገኘ
የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ሐ/ጉዳት ሊያደርስ የሚችል
3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ያልተመደበበትን ሥራ ሲሰራ የተገኘ
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
መ/ ያተመደበበትን ስራ /በተለየ ሁኔታ
የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ሳይታዘዝ/ በመስራት ጉዳት ያደረሰ
3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ላደረሰው ጉዳት/ጉድለት/ተጠያቂ
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
ሆኖ
ሠ/ የድርጅቱ ንብረት በሆኑና
በሚሰራባቸው መሳሪያዎች ሆን ብሎ
ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ስንብት
ማድረሱ በማስረጃ ሲረጋገጥ
የንብረቱን ዋና ክፍሎ
29.4.5.9 ሳይፈቀድለት ስንብት
ኢንተርፕራይዙን ንብረት ወይም
38
ገንዘብ ለግል ጥቅም ያዋለየንብረቱን
ዋጋ ከፍሎ እና በሕግ ተጠያቂ ሆኖ
29.4.5.10 ንብረት አሳልፎ መስጠት
ሀ/ በኃላፊነት የተረከበውን ንብረት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ያለትዕዛዝ አሳልፎ የሰጠ ወይም
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ያከራየ የንብረቱን ዋጋና ኪራይ
ደመወዝ ቅጣት
በወቅቱ የገበያ ዋጋ ተገምቶ
እንዲከፍል ተደርጎ
29.4.5.11 የኢንተርፕራይዙን ተሽከርካሪ
የመጨረሻ የጽሁፍ
ማሽከርከር
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ሀ/ ከሚመለከተው ክፍል ሳይፈቀድለት
ደመወዝ ቅጣት
የኢንተርፕራይዙን ተሽከርካሪ ያሽከረከረ
ለ/ ማንኛውም የኢንተርፕራይዙን
ተሽከርካሪ ያለ ኢንተርፕራይዙ
ፈቃድ ወይም ያለ ደረጃ ያሽከረከረና ስንብት
ጉዳት ያደረሰ ለደረሰው ጉዳት
ተጠያቂ ሆኖ
ሐ/ ጥንቃቄ ባለማድረግ
የ 10 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
በሚያሽከረክረው ተሽከርካሪ ላይ
3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ጉዳት ያደረሰ ለደረሰው ጉዳት
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
ተጠያቂ ሆኖ
መ/ የግል ጥቅም ሊያስገኝ በሚችል
የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
አኳኋን ዕቃም ሆነ ሰው የጫነ፣
3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ለጫነው እቃ ወይም ሰው በወቅቱ
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
የገበያ ዋጋ ሂሳብ መሰረት ክፍሎ
ሠ/ በመደበኛ የስራ ስዓት
የመጨረሻ የጽሁፍ
የኢንተርፕራይዙንሰራተኛ አላግባብ የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና 2 ኛ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
አላሳፍርም ያለ ወይም ትቶ የሄደ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ቀናት ደመወዝ ቅጣት
አሽከርካሪ
ረ/ ኢንተርፕራይዙ ቋሚ የመኪና የመጨረሻ የጽሁፍ ስንብት
መሳደሪያ ቦታ ባዘጋጀለት ቦታ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት
ማሳደር ሲገባው ያለፈቃድ ደመወዝ ቅጣት
39
መኪናውን ከኢንተርፕራይዙ ወይም
ከቅርንጫፉ ውጭ ያሳደረ ሾፌር
ሰ/ የሰርቪስ አገልግሎት ከሰጠ በኋላ
የ 7 ቀናት ደመወዝ ቅጣት የመጨረሻ የጽሁፍ
ከሚመለከተው ኃላፊ የተለየ ፈቃድ
የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ሳይሰጠው መኪና ይዞ ወደ ግቢ
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
በሰዓቱ ያልተመለሰ ሾፌር
ሸ/ ከሚመለከተው አካል ለመኪና ለስራ የመጨረሻ የጽሁፍ
የበር መውጫ ፈቃድ ሳይኖረው ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
መኪና ከግቢ ይዞ የወጣ ሾፌር ደመወዝ ቅጣት
29.4.5.12 ብክነት
የመጨረሻ የጽሁፍ
ሀ/ ለሥራ የተሰጡትን ዕቃዎች፣ የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና 2 ኛ
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
መሳሪያዎችና ሰነዶች ያለአግባብ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ያባከነ ወይም ያበላሸ
ለ/ በኢንተርፕራይዙ ስልክ በሥራ የ 10 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ሳይሆን ለግል ጉዳይ አገር ውስጥ 2 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
የደወለ ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
29.4.5.13 እምቢተኝነት
የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና
ሀ/ በስሙ የተፃፈ ደብዳቤ አልቀበልም ከደመወዝ ማገድና እስከ 5 ቀን
3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ
ያለ የተሞላለትን የሰራ አፈፃፀም ላይ ካልተቀበለ ስንብት
ማስጠንቀቂያ
አልፈርምም ያለ
የመጨረሻ የጽሁፍ
ለ/ ለአደጋ መከላከል እንዲተባበር
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ሲጠየቅ ያልተባበረ
ደመወዝ ቅጣት
40
ሐ/በአዋጁ ከተቀመጠው ውጭ ሥራ አንዳይሰራ የመጨረሻ የጽሁፍ
ሠራተኛውን የገፋፋ ወይም ያነሳሳ ወይም ተፃራሪ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
ቅስቀሳ ያደረገ ወይም ያሳደመ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
መ/ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 3.2.4 የመጨረሻ የጽሁፍ
የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና
መሰረት ሥራውን እንዲሰራ በበላይ ኃላፊው ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ሲታዘዝ አልሰራም ያለ ደመወዝ ቅጣት
29.4.5.14 ጠበኛነት
የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ሀ/ በሥራ ላይ የበላይን ወይም የበታችን ወይም
3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ማንኛውንም የሥራ ባልደረባ መሳደብ
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
በማስረጃ ሲረጋገጥ
የ 7 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ለ/ በሥራ ጊዜ ጠብ መጫርን ማስፈራራት ወይም
የመጀመሪያ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
ሥራ ማወክ በማስረጃ ሲረጋገጥ
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
ሐ/ በኢንተርፕራይዙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰው
የመጨረሻ የጽሁፍ
የደበደበ፣ የደበደበውን ሰው የህክምና ወጪ
ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
ሸፍኖ በድብደባው ወቅት በንብረት ላይ ጉዳት
ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ከደረሰ የንብረቱን ዋጋ ከፍሎ
መ/ በኢንተርፕራይዙ ውስጥም ሆነ ውጭ በሥራ
በህግ መጠየቁ
ላይ ተሰማርቶ በሚገኘው ሰራተኛ ላይ ሆነ
እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
ብሎና አውቆ አስቦ አደጋ ያደረሰ
ሠ/ ደንበኞችና ወኪሎችን ማጉላላት፣ የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የ 7 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ለደንበኞችና ለወኪሎች ተገቢውን አገልግሎት 1 ኛ ደረጃ የጽሁፍ 3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
አለመስጠት ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ረ/ የኢንተርፕራይዙን ደንበኞች የዘለፈ በማስረጃ የመጨረሻ የጽሁፍ
ሲረጋገጥ የ 10 ቀን ደመወዝ ቅጣትና
ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ደመወዝ ቅጣት
29.4.5.15 እምነት ማጉደል
ሀ/ ስርቆት፣ በኢንተርፕራይዙ ውስጥ በህግ መጠየቁ
የኢንተርፕራይዙ ሆነ የሌላ ሰራተኛ ንብረት እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
ወይም ገንዘብ መውሰዱ በማስረጃ ሲረጋገጥ
ለ/ ለመውሰድ ወይም ለመስረቅ የሞከረ በማስረጃ የመጨረሻ የጽሁፍ ስንብት
41
ሲረጋገጥ ማስጠንቀቂያና የ 15
ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ሐ/ በግዢ አሰራር ላይ የኢንተርፕራይዙን ጥቅም
ሳይጠብቅ ለግል ጥቅም ለማግኘት ጥረት
ያደረገ ወይም በግዥ ሥራ ወቅት
በህግ መጠየቁ
የኢንተርፕራይዙን ጥቅም ያላስከበረ
እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
በኢንተርፕራይዙ ላይ የደረሰውን ኪሳራና
ኢንተርፕራይዙ ሊያገኝ የነበረውን በገንዘብ
ከፍሎ
መ/ ለማጭበርበር የሃሰት ሰነዶችንም ሆነ
ማስረጃዎችን ያቀረበ በኢንተርፕራይዙ
በህግ መጠየቁ
ማህተም ወይም አርማ በያዙ እትሞች
እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
በመጠቀም ያጭበረበረ ወይም አስመስሎ
የፈረመ
ሠ/ የግዥ ዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዶችን
በህግ መጠየቁ
ሚስጥራዊነት ያልጠበቀ ወይም የአንዱን ዋጋ
እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
ተመን ለሌላ ሰው /ወገን/ ያሳየ
ረ/ ከደንበኞች ገንዘብ፣ ወይም ሌላ ነገር በህግ መጠየቁ
ያጭበረበረ መሆኑ ሲረጋገጥ እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ሰ/ የኢንተርፕራይዙ ማስታወቂያ ያለፈቃድ
2 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ቀናት ስንብት
የቀደደ፣ ያበላሸ ወይም ያነሳ
ማስጠንቀቂያ ደመወዝ ቅጣት
ሸ/ የኢንተርፕራይዙን ዕድገት፣ ህልውናና ጥቅም
የመጎዳ ምስጢር ለሌላ ሰው አሳልፎ የሰጠ፣ በህግ መጠየቁ
ያሳወቀ በኢንተርፕራይዙ ላይ ለሚደርሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
ጉዳት ተጠየቂ ሆኖ
ቀ/ ከኢንተርፕራይዙ ገንዘብ/ንብረት ተረክቦ እስከ 5 ቀን ገቢ ካላደረገ እስከ 10 ቀን ገቢ ካላደረገ
ያለበቂ ምክንያት ገቢ ያላደረገ ለንብረቱና የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የ 15 ቀን ደመወዝ ቅጣትና እስከ 15 ቀን ገቢ
ለገንዘቡ ተጠያቂ ሆኖ 2 ኛ ደረጃ የጽሁፍ የመጨረሻ የጽሁፍ ካላደረገ ስንብት
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
42
በ/ ራሱን ወይም ሌላውን ለመጥቀም ሲል የሃሳት
ሰነዶችን በማስረጃነት ያቀረበ ወይም በህግ መጠየቁ
የኢንተርፕራይዙን የሚጎዳ የሃሰት የምስክር እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
ወረቀት የሰጠ በማስረጃ ሲረጋገጥ
ተ/ የራሱን ወይም የሌላውን ሰው ብልጽግና
በመሻት ማንኛውንም የኢንተርፕራይዙን
ንብረት ወይም ሰነድ ወይም ገንዘብ ለግል በህግ መጠየቁ
ጥቅሙ ያዋለ ወይም ያለፈቃድ የወሰደ እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
ወይም ለ 3 ኛ ወገን አሳልፎ የሰጠ መሆኑ
በማስረጃ ሲረጋገጥ
29.4.5.16 በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር የ 5 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና
377/96 እና በዚህ መመሪያ መሠረት የትርፍ 3 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
2 ኛ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ሰዓት ሥራ ትዕዛዝ አለመቀበል ማስጠንቀቂያ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
29.4.5.17 ማጥፋት
ሀ/ በኃላፊነት የተረከበውን መሣሪያ፣ ንብረትና
የ 7 ቀን ደመወዝ ቅጣትና የመጨረሻ የጽሁፍ
ገንዘብ ካለመጠንቀቅ የተነሳ በሦስተኛ ወገን የ 3 ቀን ደመወዝ ቅጣትና
2 ኛ ደረጃ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
ያስወሰደ ወይም ያሰረቀ በሦስተኛ ወገን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
ማስጠንቀቂያ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
ስለመወሰዱ ሲረጋገጥ ለጠፋው ንብረት
ተጠያቂ ሆኖ
ለ/ በኃላፊነት የተረከበውን መሣሪያ የጣለ፣ ወይም
ለሦስተኛ ወገን ያስወሰደ ወይም ያሰረቀ በህግ ስንብት
ተጠያቂ ሆኖ
29.4.5.18 አሳልፎ መስጠት
በኃላፊነት የተረከበውን መሣሪያ /መኪና/ የመጨረሻ የጽሁፍ
ላልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው ማስጠንቀቂያና የ 15 ስንብት
እንዲጠቀምበት ወይም እንዲነዳ አሳልፎ የሰጠ ቀናት ደመወዝ ቅጣት
በማስረጃ ሲረጋገጥ
29.4.5.18 ማጭበርበር
በማስመሰል በባለስልጣን ፊርማ የተጠቀመ
በህግ መጠየቁ
ወይም የኢንተርፕራይዙ ማኀተም ለግሉ
እንደተጠበቀ ሆኖ ስንብት
ወይም ለሌላ ወገን ጥቅም ላይ ያዋለ
43
29.4.5.19 አንድ ሠራተኛ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ጥፋት አጥፍቶ ከተቀጣ በኋላ ቅጣቱ ከሚነሳበት ጊዜ በፊት ሌላ ጥፋት ቢያጠፋ የሚቀጣው ለመጨረሻ ጊዜ
ላጠፋው ጥፋት/ጥፋቶች ለከፍተኛው በስነ ስርዓት እርምጃ አወሳሰድ ሠንጠረዥ ሊቀጣ የሚገባውን በሁለተኛ ደረጃ ያለውን ቅጣት ይሆናል።
29.4.5.20 በዚህ የቅጣት ሠንጠረዥ ውስጥ ያልተሸፈኑ የሥነ ሥርዓት ጉድለቶች ባጋጠሙ ጊዜ ኢንተርፕራይዙ ከተመሳሳይ የስነ ስርዓት ጉድለቶች ጋር
በማዛመድ የቅጣት እርምጃ ይወስዳል።
a.
44
አንቀጽ 54 የተወሰደ የስነ-ስርዓት ጉድለቶች ማረሚያ እርምጃ ስለመሻር
1. አንድ ሰራተኛ ከመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና የደመወዝ ቅጣት በታች የሚያስቀጣ ጥፋት አጥፍቶ
እርምጃ ከተወሰደበት በኋላ የተቀጣበትን ቅጣት ወይም ሌላ ጥፋት በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ ካልፈፀመ
እና ከጥፋቱ የታረመ መሆኑ በኢንተርፕራይዙ ሲረጋገጥ የጥፋት መሻሪያ ደብዳቤ ይጻፍለታል።
2. አንድ ሰራተኛ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና የደመወዝ ቅጣት የሚያስቀጣ ጥፋት አጥፍቶ እርምጃ
ከተወሰደበት በኋላ የተጣለበትን ቅጣት ወይም ሌላ ጥፋት በሚቀጥለው አንድ አመት ውስጥ ካልፈፀመ እና
ጥፋቱ የታረመ መሆኑ በኢንተርፕራይዙ ሲረጋገጥ የጥፋት መሻሪያ ደብዳቤ ይፃፍለታል።
3. ሰራተኛው በግል ማህደር ውስጥ ስለሚያዙ መረጃዎች ለማወቅ በሚፈልግበት ጊዜ የሚመለከተውን ኃላፊ
ጥይቆ ማህደሩን ሊያይ ይችላል።
45
አንቀጽ 60 የሥራ ምስክር ወረቀት ስለመስጠት
ሰራተኛው በስራ ላይ እያለ የምስክር ወረቀት በሚጠይቅበት ጊዜ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሰራተኛው
የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ካመለከተበት ቀን ጀምሮ በ 3 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ በቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ
ሰራተኛው የጠየቀውን የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል።
ቅፃቅፆች
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ የርክክብ
ማስረጃ ቅጽ /ክሊራንስ/
46
ተ.ቁ የስራ ዘርፍ አስተያየት/ዕዳ ካለ ይጠቀስ ፊርማ ቀን
1 የሚሰሩበት ክፍል
2
3
4
5
6
7
8
9
3. ፊርማ ____________
ማሳሰቢያ፡ ሠራተኛው ከለቀቀ ወይም ከተዛወረ በኋላ ዘግይቶ የሚገኝ የኢንተርፕራይዙ ንብረት /ገንዘብ/
በግለሰቡ ላይ ከተገኘ ይህ ቅጽ ከመጠየቅ አያድንም።
አንቀጽ 1 ውሉ የሚፀናበት ጊዜ
47
ይህ ውል ፀንቶ የሚቆየው በአሁኑ ስዓት የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ እያከናወነ ባለው
የ-------------------------- ተቋም ምክንያት የተፈጠረ የስራ ጫና እስከ ሚቃለል ይህ ውል ከተፈረመበበት
ከ---------------- ቀን -------------------- ዓ.ም ጀምሮ አስከ --------------------
ቀን ---------------------- ዓ.ም ነው። ሆኖም የሙከራ ጊዜ ከማለቁ በፊት ማናቸውም ወገን ውሉን
መሰረዝ ይችላል።
ሰራተኛው የተቀጠረበት የስራ መደብ ወይም አይነት ----------------- ሆኖ ከዚህ ጋር የተዛመዱትንና ከዚሁ
ተግባር የሚመነጩትን ስራዎች የማከናወን ግዴታን ያጠቃልላል።
አንቀጽ 3 የስራ ቦታ
አንቀጽ 4 ደመወዝ
አዋጅ ቁጥር 1156/11 ፣ የህብረት ስምምነትና ሌሎች ድንጋጌዎች በሰራተኛውና በኢንተርፕራይዙ መካከል
በተፈፀመው በዚህ ውል ላይ በተመሰረተው የስራ ግንኙነት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።
6.1 በውሉ ጊዜ ውስጥ ሰራተኛው የገባበትን ግዴታ መወጣት ያልቻለ እንደሆነ ወይም የዲሲፕሊን ጉድለት
የፈፀመ እንደሆነ ወይም ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ የቢዝነስ ኢንተርፕራይዙ ሲያጋጥመው ወይም
የተወሰነው ስራ /ጊዜ/ ሲያልቅ ኢንተርፕራይዙ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው የስራ
ውሉን መሰረዝ ይችላል።
48
6.2 በውል አንቀጽ 6.1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በውል አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ሲያልቅ
ይህ ውል ቀሪ ይሆናል። ሆኖም ሁለቱ ወገኖች ውሉ እንዲራዘም ስምምነት ላይ ከደረሱ በደረሱበት
ስምምነት መጠን አሰሪው ውሉ የተራዘመ መሆኑን ጠቅሶ ለሰራተኛው በፅሁፍ ሲያሳውቅ ውሉ እንደ
ታደሰ ይቆጠራል።
አንቀጽ 7 ውሉ ስለሚፀናበት ጊዜ
አንቀጽ 8 ውሉ የተፈረመበት ቀን
--------------------------- -------------------------------
ምስክሮች፡ ስም ፊርማ
1. ---------------------------------- -------------
2. ---------------------------------- -------------
3. --------------------------------- -------------
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ የሠራተኞች
የህይወት ታሪክ ቅጽ
1. የግል ሁኔታ መግለጫ
ሀ/ የሰራተኛው/ዋ ስም ---------------------------------- የአባት ስም --------------------------------------
ሐ/ ዜግነት ---------------------------------
መ/ ፆታ ---------------
2. የቤተሰብ ሁኔታ፡
ሀ/ የጋብቻ ሁኔታ ያገባ ያላገባ በፍች የተለየ
49
ለ/ የሚስት /የባል ሙሉ ስም ----------------------------------- ስልክ ቁጥር ---------------------------
3. የትምህርት ደረጃ፡
50
ተ.ቁ ስም ከነ ክልል ከተማ ክ.ከተማ ቀበሌ የቤት የስልክ
አያት ቁጥር ቁጥር
8. ማረጋገጫ
ከአሁን ቀድም የሞላሁት የሒወት ታሪክ ቅጽ ተመሳሳይና ያልተለየ መሆኑን እያረጋገጥኩ የተለየ ቢሆን ለምሳሌ፡
እንደ ልደት ዘመን የመሳሰሉት የተለያዩ ቢሆን /ከሚመለከተው ክፍል ጥያቄ ቢነሳ ዋስ ሆኘ አመልሳለሁ።
51
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ተቋማት የሠራተኞች
የስዓት መቆጣጠሪያ
የስራ ክፍል ------------------------------------
ከ-------------------------------------------- ቀን እስከ -------------------------------------- ቀን 201------------------------------ ዓ.ም
ዓፈ = የዓመት ፈቃድ
ሕፈ = የህመም ፈቃድ
ወፈ = የወሊድ ፈቃድ
መስ = መስክ ስራ
ሐ = የሐዘን ፈቃድ
እፍ = የእክል ፈቃድ
ቀ = ቀሪ
ዘ = የዘገየ
52
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ
የደመወዝ ውክልና መስጫ ቅጽ
4. ምስክሮች፡-
ስም ፊርማ
1 ኛ. -------------------------------------------------------- ----------------------
2 ኛ. ------------------------------------------------------- ----------------------
3 ኛ.-------------------------------------------------------- ----------------------
53
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ
የፈቃድ መጠየቂያ ቅጽ
ቀን---------------------------
የሠራተኛው ስም ---------------------------------------- መለያ ቁጥር --------------------
54