Professional Documents
Culture Documents
1.1. መግቢያ
በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ 2013 በጀት ዓመት የህዳር ወር ሪፖርት የኮርፖሬሽኑን እቅድ መነሻ ተደርጎ ከተዘጋጀው
ዓመታዊ እቅድ ተነጻጽሮ የቀረበ ነው፡፡
የሪፖርቱ ዓላማ የእቅድ አፈጻጸምን ለመገምገም ሲሆን በውስጥ የተካሄዱ የክትትልና እና ሳምንታዊ ግምገማ መሰረት
የአፈጻጸም ደረጃ ያለበትን ማወቅ፣ ችግሮችን ለይ ለቀጣይ ዓመት እንዳይደገም መፍትሄ ለመስጠት፣ ግልጽነትና
ተጠያቂነትን ለማምጣት ነው፡፡
ሪፖርቱ ሲዘጋጅ የመረጃ ምንጭ ያደረጋቸው በየሳንምቱ የተካሄደውን የሚኒ ማኔጅመንት ግምገማና አቅጣጫዎች፣
የለውጥ ስራዎች አፈጻጸም መረጃዎችን ፣ ሪፖርቶችን ከየቡድኖች የቀረቡ የአፈጻጸም ሪፖርቶች እና የመደበኛና
ድንገተኛ ሱፐርቪዥን ውጤቶችን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን 280 ቤቶችን ውል በማደስ፣ በውስጥ አቅም 41
ቤቶችን እና በደንበኞች 46 ቤቶችን በመጠገን እና 2,397,000. ብር ሰብስበናል፡፡
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ስራ ላይ ላሉት ሰራተኞች ግንዛቤ የማስጨበጥ፣
አገልግሎት ሲሰጥ የአንድ ሜትር ርቀት ለማስጠበቅ ተችሏል፣ ተገልጋይ ለአገልሎት ሲገቡ ማስክ እንዲጠቀሙ
እየጠየቅን ነው፣ ስራተኞቻችን በሙሉ በራሳቸው ወጭ ማስክ እዲጠቀሙ እየተደረገ ሲሆን መግቢያ ላይ የእጅ
ማስታጠብ ስራ እና የሙቀት መለካት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የሪፖርቱ አቀራረብና የመረጃ ትንተና በተመለከተ የኢላማ አፈጻጸም ከእቅድ ጋር በማነጻጸር ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም
መሰረት ሪፖርቱ ስምንት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፤ በክፍል አንድ መግቢያ፣ በክፍል ሁለት የ 2013 በጀት ዓመት የህዳር ወር
ኦፕሬሽናል ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም፤ በክፍል ሦስት ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራት ከነምክንያታቸው፣
ክፍል አራት ሳይታቀዱ የተከናወኑ ተግባራት፣ ክፍል አምስት በአፈጻጸም ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ
እርምጃዎች፣ ክፍል ስድስት የክትትልና ግምገማ ተግባራት፣ ክፍል ሰባት መደምደሚያ፣ ፈታኝ ሁኔታዎችና ወደፊት
ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች፤ ክፍል ስምንት ደካማና ጠንካራ ጎኖችን እና በመጨረሻም ማጠቃለያ አካትቶ የያዘ
ነው፡፡
የ ህዳር ወር Page 1
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
2.1. ተልዕኮ
2.2. እሴቶች
የ ህዳር ወር Page 1
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
የአፈጻጸም አቅጣጫዎች
የደንበኞችን ቅሬታ በወቅቱ ለመፍታት የሚያስችል የቅሬታ አፈታት ሥርዓት ዘርግቶ መንቀሳቀስ፣
3. ለቤቶች ተገቢውን ጥበቃ በማድረግና ይዞታዎቻችን በህግ አግባቡ የተጠበቁ እንዲሆን ማድረግ፣
4. የጥገና ሥራዎችን በውስጥና በውጭ እንዲሁም በተከራዮች ተሳትፎ ለማከናወን የሚያስችል ጠንካራና
ነቅቶ መዋጋት፤
8. የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ሥርዓታችንን በማዘመንና የተቋሙን ሥራዎች ሊደግፍ የሚችል ዘመናዊ
እንዲኖር ማድረግ፡
የ ህዳር ወር Page 2
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
10. በቤት አስተዳደር ዘርፍ ሚሰጡ አገልግሎቶች ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ ሕፃናትን፣ አዛውንቶችንና
ማድረግ፣
12. ከደንበኞች፣ ከባለድርሻና ከተባባሪ አካላት ጋር የተቀናጀና የደንበኞችን ተሳትፎ የሚያረጋግጥ ሥርዓት
መዘርጋት ፡፡
ክፍል ሶስት፡
ተግባር፡-3 መደበኛ ኪራያቸውን በወቅቱ ያልከፈሉትን ደንበኞች በመለየት በወቅቱ ባልከፈሉት ላይ በመመሪያው መሰረት
እርምጃ በመውሰድ ውዝፍ 208,000 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 68,798.20 በመሰብሰብ
33.076 ፐርሰንት ተከናውኗል፣
ተግባር፡-5 የኮርፖሬሽኑ ደንበኞች ውላቸውን በወቅቱ እንዲያድሱ በማድረግ የውል ዕድሳት አገልግሎት ክፍያ
48,000 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 58,650.00 ብር በመሰብሰብ 122.19 ፐርሰንት ተከናውኗል፡፡
የ ህዳር ወር Page 3
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ኦፕ.ግብ 2.፡- ወጪ ቆጣቢ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ከደንበኞች ጋር የወጪ መጋራት አሰራርን በመዘርጋት የቀነሰ
ወጭ ብር 625,000 ብር ታቅዶ 1.62 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ 260 ፐርሰንት ተከናወኗል፣ (4%)
ተግባር፡-.1 በጽህፈት ቤቱ ወጪ ቆጣቢ የአሰራር ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ በወረቀት አጠቃቀም፣
የግንባታ ተነቃይ እቃዎችን መልሶ የመጠቀም ስራ ተከናውኗል፤
ኦፕ.ግብ 3፡- ተዘጋጅቶ የቀረበ በጀትና የበጀት አጠቃቀም ሪፖርቶችና ወቅታዊ የሂሳብ መግለጫዎች፣ (2%)
ተግባር፡-2 ወቅታዊ የበጀት አጠቃቀም ሪፖርት በየወሩ፣ በየሩብ ዓመቱና የዓመቱን በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል
ሪፖርት መላክ፣
ተግባር፡-3 በየወሩ የበጀት አጠቃቀምን ትክክለኛነት በማረጋገጥና በመገምገም ለሥራ ክፍሎች ግብረ-መልስ ለመስጠት
ታቅዶ ተከናውኗል፤
ተግባር፡-1 ሊሰበሰቡ በማይችሉ ተሰብሳቢዎች መረጃ አደራጅቶ ለዉሳኔ እንዲሰጥ አደራጅቶ አቅርበናል፣
ተግባር፡-2 ለሌች የተሰጡ የኦዲት አስተያቶች ተቀብሎ ለማረም ታቅዶ አስተያየት ስላልቀረበ
አልተከናወነም፡፡
ተግባር፡-1 በአለም አቀፍ የሂሳብ ሪፖርት አዘገጃጃት ላይ ለአማካሪ ድርጅት የሚያሰፈልጉ ሰነዶችን ለማቅረብ
ታቅዶ የተጠየቅናቸውን መረጃዎች አቅርበናል፡፡
ተግባር፡-2 የ 2010 እና የ 2011 በጀት ዓመት የሂሳቦች በዓለም አቀፍ የሂሳብ ሪፖርቶች አዘገጃጀት ደረጃዎች
መሰረት የሂሳብ ሪፖርቶች ለማዘጋጀት መረጃ ለማቅረብ ታቅዶ 2009 እና የ 2010 ተሰብሳ
ከሌጀር በማጥራት ለፋይናንስ ዳይሬክቶሬት አቅርበናል፡፡
የ ህዳር ወር Page 4
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ተግባር፡-1- የ 16 አፓርታማ ነዋሪዎችን ማህበራት ለማጠናከርና ለአንድ ቁጠባ ማህበር የማጠናከር ስራዎች
ታቅዶ በ 16 ቲም ማህበራት ላይ ያሉ ነዋሪዎችን የማወያየት ሰራ ተሰርቷል
ተግባር፡-2- የአንድ የቁጠባ ማህበራትን ማጠናከር 2 የቁጠባ ማህበር የማቋቋም ሰራ ለመሰራት የታቀደ ሰሆን
አንዱን የቁጠባ ማህበር በዚህ ወር ተቋቁሟል
ተግባር፡ 1- የተዘጋጀውን የደንበኞች ማስተናገጃ ማንዋል በብሮሸር ለማሰራጨት ታቅዶ ማኑዋል ስላልጸደቀ
አልተከናወነም ፡፡
ኦፐ.ግብ .8፣ የዜጎች ቻርተር ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ በስተንዳርዱ መሰረት ለመስራት ጥረት ተደርጎ የውል እድሳት፣
የዘርፍ ለውጥ በስታንዳርዱ መሰረት ሲሰራ ጥገና በስታንዳርዱ መሰረት አልተከናወነም (2%).
ኦፕ.ግብ 9፣ ከደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና የአገልግሎት ጥያቄዎችን በመመሪያውና በአሠራር ሥርዓቱ በወቅቱ
ምላሽ ያገኘና የተፈጠረ የደንበኞች እርካታ 75 ፐርሰንት ለማድረስ ታቅዶ በ 2012 እንደተለካው 73.05
ደርሷል፤ (4%)
ተግባር 2. የቀረቡ ቅሬታዎችን በመቀበል አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ታቅዶ ከማህደር መፈለግ ጋር
የተያያዘውን ችግር ለመፍታት የመረጃ ማዘመን ስራ ሰርተናል ፣
ተግባር 3. የደንበኞችን እርካታ ከ 72 ወደ 75 ፐርሰንት ለማድረስ ታቅዶ አሁን ያለው የደንበኞች እርካታ ደረጃ
2012 መጨረሻ በተለካው መሰረት 73 ፐርሰንት ላይ ይገኛል፡፡
የ ህዳር ወር Page 5
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
አገልግሎት ለመስጠት ውል ፈጻሚዎችን፣ የመረጃ ባለሙያን፣ የቤቶች አስተዳር ቡድን መሪ እንደ ስራ ፍሰት
እንዲገናኙና የስራ ትእዛዝ መስጠትና መቀበል እንዲሁም ሪፖርት በቀጥታ ማየት ሚያስችል አሰራር
የወረቀት አልባ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ተግር 1፡ በተለያየ ምክንያት በቅርንጫፉ የሚለቀቁ 5 የመኖሪያ ቤቶችን መረጃ ማደራጀትና ለማሳወቅ
ታቅዶ 11 አስለቅቀን 220 ፐርሰንት ተከናውኗል፡፡
ኦፕ.ግብ 12፡- በመመሪያው መሰረት በጨረታ የተከራዩ 10 የንግድ ቤቶች መረጃ ለማከራየት ታቅዶ 10 ቤቶ አሸናፊ
የቀረበባቸው ሲሆን 7 ቤቶች ውል ሞልተዋል 3 ተጠባባቂ ጠርተናል ዉል ለመፈጸም በዝግጁት ላይ እንገኛለን (100%).
ተግባር፡- 1 የተለቀቁ የንግድ ቤቶችን መረጃ በተሟላ ሁኔታ አደራጅቶ ለመያዝ ታቅዶ 3 ቤቶቸ መረጃ
አደራጅተን ይዘናል፡፡
ኦፕ.ግብ 13፡-በቤቶች አስተዳደር መመሪያ መሠረት ደንበኞች እየተገለገሉ መሆኑን በመስክ ክትትል በማረጋገጥ ለ 242
ቤቶች ውል ለማደስ ታቅዶ ለ 280 ቤቶች ውል በማደስ 115.70 ፐርሰንት ተከናውኗል፣ (115%)
አፈጻጸም ከፍ ያለ ምክንያት ከፍተኛ ቅሰቀሳ ሰለተደረገ ነው፡፡
ተግባር፡-1 የመስክ ክትትል ሥራ በመስራት በ 242 ቤቶች በቤቱ የሚገለገሉ ተከራዮች ህጋዊነትና በውሉ መሰረት ቤቱን
እየተጠቀሙ መሆኑን ለማጣራት ታቅዶ 280 ቤቶች ላይ ማጣራት አፈጻጸም ከፍ ያለ ምክንያት ከፍተኛ
ቅሰቀሳ ሰለተደረገ ነው፡፡
ተግባር፡-2 በመስክና በማህደር የተከራይን ህጋዊነት በማረጋገጥ የኪራይ ለ 242 ቤቶች ውል ዕድሳት
ለመፈጸም ታቅዶ ለ 280 ቤቶች ውል በማደስ 115.70 ፐርሰንት ተከናውኗል፡፡
ተግባር፡-3 ከቤቶች አስተዳደር መመሪያ ውጭ በቤት ውስጥ እየተገለገሉ የሚገኙ ደንበኞች ላይ ተገቢውን
የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ፡፡
ተግባር 4 አበል የሚከፈላቸው የቀድሞ ባለቤቶችን መረጃ ማደራጀትና ወቅታዊ በማድረግ ለክፍያ ለማስተላለፍ
ታቅዶ 100 ፐርሰንት ተከናውኗል፣
ኦፕ.ግብ 14፡- የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ያልወጣላቸው ቤቶች ካርታ ለማሰራት ታቅዶ ክትትል የተደረገ
ቢሆን በክለ ከተማው ካርታ አልተዘጋጀም፡፡(2%)
ተግባር፡-1 ካርታ ያልወጣላቸውን 17 ቤቶች መረጃ አደራጅቶ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ተላልፏል፡፡
የ ህዳር ወር Page 6
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ተግባር፡-3 ካርታ ኮፒ ከማህደር ማያያዝ ታቅዶ በዚህ ወር ምንም የካርታ ኮፒ ሰላልመጣልን ኮፒ አድርገን
በየማህደሩ ያለሰርን ቢሆንም በመሰከረም ወር 26 ቤቶች ካርታ ከማህደር ተያይዟል፡፡
ተግባር፡-4 ካርታ የወጣላቸው ቤቶችን የይዞታ ምዝገባ በተጀመረበት አካባቢ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት
እንዲሰጣቸው ለማድረግ 5 ታቅዶ ምዝባ በከተማ አስተዳደሩ ስላልተጀመረ አልተከናነወም፣
ተግባር፡-1 ጥያቄ ተቀብሎ መረጃ ለማረጋገጥ ታቅዶ የአንድ ጥያቄ ቀርቦ ገንዘብ እንድያሲዙ ተደርጓል፡፡
ተግባር፡-1 በተለያየ ምክንያት የፈረሱ ቤቶችን መረጃ ማጥራትና ወቅታዊ ለማድረግ ታቅዶ ተከናውኗል፣
ተግባር፡-2 ካሣ ያልተከፈለባቸውን 7 ታቅዶ 13 ቤቶች በመረጃው መሰረት ክፍያው እንዲፈጸም የቅርብ ክትትል
ለማድረግ ታቅዶ ክትትል የተደረገ ነው፡፡
ኦፕሬሽናል ግብ 17፡- በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ያሉ ጉዳዮችን ክትትል ለማድረግ ታቅዶ 5 ቤቶች በፍርድ ቤት ክርክር ላይ
ይኛሉ፣ (1%)
ተግባር 1፡- ክርክር እየተደረገባቸው ያሉ 5 ጉዳዮችን መረጃ አደራጅቶ ለሚመለከተው አካል ለመላክ ታቅዶ
መረጃውን በወቅቱ ልከናል፡፡
ተግባር 2፡- የፍርድ ውሳኔ ለማስፈጸም ታቅዶ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት 1 ቤቶችን ተረክበናል፡፡
ኦፕ.ግብ 18፡- በአፓርታማ ነዋሪዎች እንዲሸፈኑ ተሳትፎና ተጠቃሚነትና በተሰጡ አገልግሎቶች የተሻሻለ የአፓርታማ
አስተዳደር፣ (1%)
ተግባር፡-2 በአፓርታማ ነዋሪዎች ወጭ መጋራት የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የያዘ ሰነድ ማዘጋጀትና
ለመተግበር ታቅዶ 18 ሰነድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል፣
ተግባር፡-.1 በጥናት ሰነዱ መሰረት በውስጥ ሀይል የሚጠገኑ ቤቶችን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለማዘጋጀት ታቅዶ ስራ
ላይ አውለናል፣
ተግባር፡-2 በውጪ ሥራ ተቋራጭና በደንበኞች የሚጠገኑ ቤቶችን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለማዘጋጀት ታቅዶ
ተከናውኗል፣
ኦፕ.ግብ 4.20፡- በውስጥ ዐቅም የተካሄደ 25 ቤቶች ለመጠገን ታቅዶ 41 ቤቶች ተጠግነዋል እንዲሁም በደንበኞችን
የተካሄዱ የ 30 ቤቶች ጥገናና ለማከናወን ታቅዶ 46 ቤቶች በድምሩ 87 ቤቶች ተጠግነዋል
1,911,792.31 ብር (2%)
የ ህዳር ወር Page 7
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ተግባር፡-1 በውስጥ አቅም ጥገና የሚደረግላቸውን ቤቶችን ዝርዝር በመለየት ለማዘጋጀት ታቅዶ ተከናውኗል፤
ተግባር፡-2 በውስጥ አቅም ጥገና የሚደረግላቸውን የጥገና ፕሮግራም ለማዘጋጀት ታቅዶ ተከናውኗል፤
ተግባር፡-4 የአፓርታማዎችን የውጭ ቀለም እድሳት መስራት 1 ታቅዶ 4 ተሰረቷል 400 ፐርሰንት ተከናውኗል፡፡
ተግባር 5፡- የተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ እድሳት ማጠናቀቅ ግምት ዝግጅት ተጠናቅቋል፣ ፕሮግራምና እቃ
አቅርቦት ቅድመ ዝግጅ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ተግባር 8፡ ለ 30 ደንበኞች የሚቀርቡ የጥገና ጥያቄዎች በራሳቸው ወጭ እንዲጠግኑ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ 46
ደንበኞች ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ተግባር 9፡ በተሰጠው የጥገና ፈቃድ መሰረት ጥገናና እድሳት መከናወኑን በመስክ ተገኝቶ 20 ፐርሰንቱን
ለማረጋገጥ ታቅዶ 89 ፐርሰንት በሱፐርቪዥን ታይቷል፡፡
ኦፕ.ግብ 21፡ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ለማስፈን መመሪያዎችን ለመተግበር ታቅዶ መመሪያና አሰራር
መሰረት ተደርጎ ተከናውኗል (2%)
ተግባር፡-1 የለውጥ መሳሪያዎችን (ካይዘን፣ የለውጥ ቡድንና ቢኤስሲን) ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ ስራ ላይ
አውለናል፡፡
ተግባር፡-2 የአፈፃፀም ክፍተት በታየባቸው የለውጥ መሳሪያዎች ላይ ተገቢውን ማስተካከያ ለማድረግ ግብዓት
ለመስጠት ታቅዶ አስተያየት ተሰጥቷል ተከናውኗል፡፡
የ ህዳር ወር Page 8
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ተግባር፡-1 በኦዲት ግኝቶች ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ታቅዶ በዚህ ህዳር ወር የተሰጠ እርምት ስለሌለ
አልተከናወነም፡፡
ተግባር፡-2 የተቀናጀ የሙስና መከላከያ ስትራቴጂ ስራ ላይ ለማዋል ታቅዶ አሰራርና መመሪያን መሰረት ያደረገ
ስራ ተሰርቷል እንዲሁም ሰራተኞች ሃብትን አስመዝገቧል፣
ኦፕ.ግብ 25፡- በመልካም አስተዳደር መስፈን ተጠቃሚ የሆኑ የውጪና የውስጥ ደንበኞች (2%)
ተግባር 1፡- በጽህፈት ቤት ደረጃ ከመልካም አስተዳደር መርሆዎች አኳያ ያለውን ችግር የውስጥና የውጭ
ችግሮች ለመለየት ታቅዶ ችግሮችን ለይናል፡፡
ተግባር 2፡- በጽህፈት ቤት ደረጃ ከመልካም አስተዳደር መርሆዎች አኳያ ዕቅድ ለማዘጋጀት ታቅዶ እቅድ
አዘጋጅተናል፤
ተግባር 3፡- በጥናት የተለዩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ የሥራ ክፍል
በፍጥነት መፍታት እንዲቻል የመረጃ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ስራ
ተሰርቷል፣
ተግባር 4፡- የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታትና ሪፖርት ማቅረብ፤ ከዋና ተከራዮች ጋር እየኖ ለነበሩ
ችግረኛ የድጋፍ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡
ኦፕ.ግብ 26፡- የተዘጋጀ የፊዚካል ሥራዎች እቅድ፣አፈፃጸም ሪፖርቶችና፣ የተደረጉ የግምገማና የሱፐርቪዥን
ሥራዎች፣ (3%)
ተግባር 1፡- ወቅታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በየወሩ ማዘጋጀት በየደረጃው በጋራ በመገምገም ለሚመለከተው
ሪፖርት ተልኳል፣
ተግባር 2፡- በወሩ የተሰሩ ሥራዎችን ትክክለኛነት በሱፐርቪዥን በማረጋገጥ ግብረ-መልስ ተሰጥቷል፡፡
ኦፕ.ግብ 27፡- የግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋትና ተግባራዊ በማድረግ የ 1.5 ሚሊዮን ብር ግዥ
ተፈጽሟል (1%)
ተግባር፡-1 የበጀት ዓመቱን የግዥ ዝርዝር ዕቅድና ፕሮግራም በማዘጋጀት ለማፀደቅ ታቅዶ የግዥ አቅድ አስጸድቀን
ወደ ስራ ገብተናል፡፡
ተግባር 2፡- በአቅርቦት ዕቅዱ መሰረት የተለያዩ የግዥ ዘዴዎችን በመጠቀም 1,573,140.37 ሚሊዪን ብር ግምት ያለው እቃ
ተገዝቷል
የ ህዳር ወር Page 9
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ተግባር 3፡- የግዥ ጥያቄ አደራጅቶ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለማቅረብ ታቅዶ አቅርበናል፡፡
ተግባር 4፡- ግዢዎች በስፔስፍኬሽን መሰረት መሆናቸውን በማረጋገጥ ለመረከብ ፕሮፎርማ ሲሰበሰብና እቃ ሲገባ
የሚያረጋግጡ ባለሙያዎች መድበን እየተሰራ ይገኛል፡፡
ተግባር 1:- ቋሚና አላቂ ንብረቶችን መመዝገብና በየጊዜው ወቅታዊ ለማድረግ ታቅዶ የቋሚ ንበረት
ምዝገባ ተካነውኗል፡፡
ተግባር 2:- አገልግሎት ሰጥተው የተበላሹና ሊጠገኑ የማይችሉ ንብረቶችን በባለሙያ አረጋግጦ ወደ ዕቃ ግ/ቤት
ተመላሽ ማድረግና እንዲወገዱ ለማድረግ መረጃ ለይተን ለግዥ ዳይክቶሬት አቅርበናል፡፡
ተግባር 3፡- በግዥና በዕቃ ግ/ቤት ያሉ ንብረቶችን ለየስራ ክፍሎች ስርጭት ለማድረግ፤ ታቅዶ 1,025,569.18
ብር ግምት ያለው ንብረት ተሰራጭቷል፡፡
ኦፕ.ግብ 29 ፡- የተሻሻለ የማህደር አደረጃጀትና የመረጃ አያያዝ (1%).
ተግባር 1፡- የቤቶች ማህደር ፣ ካርታ ና ሌሎች መረጃዎች በአግባቡ ለማደራጀት ታቅዶ 3990 ማህደሮችን
የውጭ ሽፋን ቀይረን፣ ስካን አድርገን እና መረጃውን በኤሌክትሮኒክ (eDMS)
መቀባበል የሚያስችል ስራ ተሰርቶ ወረቀት አልባ አሰራር እየተተገበረ ይገኛል፣
ተግባር 2፡- ወርሃዊ ወጭና ገቢ ደብዳቤዎችና መረከብ፣ ማሰራጨትና ሪፖርት ለማቅርብ ታቅዶ ተከናውናል፣
ተግባር 1፡- 1,670 ችግኞችን በጣና፣ በመስከረም አፓርትመንቶችና ገርጂ ነጫጭ ቤቶች እና ደረጃ መዳቢ ቁጠባ
ቤቶች አካባቢ እንክካቤ አደርገናል፡፡
ኦፕ.ግብ 31- ጽህፈት ቤቱ ከባለድርሻ አካላት በተለይም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከፍትህ አካላት፣የመሠረተ
ልማት አቅራቢዎች፣ ከሥልጠና ተቋማት ወዘተ. ጋር የሚያገናኙ ሥራዎችንና በግንኙነቱ የታዩ
ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት፤ የተፈጠረ ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ከቦሌ ና ቂርቆስ ክፍለ
ከተሞች ይዞታ አስተዳደርና ይዞታ ምዝገባ ጋር መግባቢያ ሰነድ በተፈራረምነው መሰረት
እየተተገበረ ይገኛል፡፡ (2%)
ተግባር 1፡ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካላት፣ ከፍትህ አካላት፣ ከመሰረተ ልማት አቅራቢዎች፣ ከሥልጠና ተቋማት፣
ከግንባታ አስፈጻሚ ተቋማት. ወዘተ... ጋር በቅንጅት ስራዎችን ለማከናወን ከቦሌ ና ቂርቆስ ክፍለ
ከተሞች ይዞታ አስተዳደርና ይዞታ ምዝገባ ጋር መግባቢያ ሰነድ በተፈራረምነው መሰረት እየተተገበረ
ይገኛል፡፡
የ ህዳር ወር Page 10
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ኦፕ.ግብ 32፡- በዋናው መ/ቤት የሚገኙ የሥራ ክፍሎች ከቅርንጫፎችና ከአቻ የሥራ በረ በቅንጅት የመስራት ባህል
ከቤቶች አስተዳደር፣ ከጥገና ዳይሬክተሮችና ከቅርንጫፎች ጋር መግባቢያ ሰነድ በተፈራረምነው
መሰረት እየተተገበረ ይገኛል፡፡(3%)
ተግባር 1፡- የሥራ ክፍሎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እና የትስስር ስምምንት ሰነድ ተግባራዊ ለማድረግ መግባቢያ
ሰነድ መሰረት በጋራ በሚያገናኙን ስራዎች ላይ በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን፡፡
ኦፐ.ግብ 33፣ በመዋቅሩ መሰረት የተሟላ 5 የሰው ሀይል ለማማላት ታቅዶ በዚ ወር ምንም ዓይነት ቅጥር የለም (3%)
ተግባር፡-2፡- የተለያዩ የሙሌት ዘዴዎችን በመጠቀም ክፍት የሥራ መደቦችን በሰው ኃይል ለማሟላት 5 ታቅዶ
በዚ ወር ምንም ዓይነት ቅጥር የለም ፣
ተግባር 1፡- የተለያዩ የሰው ሃብት አስተዳደር ስራዎችን መስራት 36 ህክምና አገልግሎት ፣18 ህክምና ወጪ፣ 9 ዋስትና
2 ጡረታ ማስከበር አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡
ተግባር፡-2፡- የሰራተኞች የሞያ ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅ የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ አድርገናል፡፡
ኦፕ.ግብ 35 - ለቅርንጫፉ አመራሮችና ሰራተኞች የአመለካከትና ክህሎት ማሻሻያ ስልጠና ፍላጎት ለይን አቅርበናል፡፡
(3%)
ተግባር 1፡- የስልጠና ፍላጎት በመለየት በበጀት ዓመቱ ልጠና የሚያሰፈልጋቸዉ 5 አመራሮች እና 50 ሠራተኞች በዕቅድ
ተይዟል ፡፡
ተግባር 2፡- በተዘጋጀው ስልጠና ሰራተኛውና አመራሩ አስቀድሞ እንዲያገኝ በማድረግ 10 ሠራተኞች ስልጠና
አግኝተዋል፡፡
ኦፕ.ግብ 36-. የተሸሻለ ተግባራዊ የተደረገ የማበራተቻ ስርአት ለሰራተኞችና አመራሮች የሁለት ወር ቦነስና እርከና
ጭማሪ ተተግብሯል፡፡ (3%)
ተግባር 1፡- የሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና በሁለተኛዉ ሩብ ዓመት የሚከናወን ነዉ፣
ተግባር 2፡- የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራርና ሰራተኞች ማበረታቻ የዚህ ወር እቅድ አይደለም፡፡
የ ህዳር ወር Page 11
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ተግባር 1፡- በስራ ክፍሎች መካከል የመረጃ ልውውጥን የሜይል ሲስተም ተጠቃሚ እንዲሆን
ለማድረግ ታቅዶ ቡድኖችና ጽህፈት ቤቱ ተጠቃሚ ናቸው፤
ኦፕ.ግብ 38 ፡ በኢኮቴ አጠቃቀም አቅሙ ያደገ የቅርንጫፍ አመራርና ፈጻሚ (2%)
ክፍል አራት
ክፍል አምስት
5. ሳይታቀዱየተከናወኑተግባራት
የለም
በቤቶቻችን ላይ የሚታየውን ህገ ወጥነትን ለመከላከል በህግ ለመከታተል ጥረት እየተደረገ ቢሆንም በወቅቱ ሁኔታ
በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ከተባባሪ አካላት መፍትሄ አልተገኘም፤ ድጋፍ ያስፈልገናል፡፡
የሚፈለገውን ያህል ድጋፍ ማግኘት ያለመቻልና ጣልቃ
የ ህዳር ወር Page 12
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
ቡድኖች የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን አመታዊ እቅድ መሰረት አድርገው ሪፖርት እስከ ፈጻሚ ድረስ
አዘጋጅተናል፡፡
ሪፖርት ተገምግሞና ግብረ መልስ በመስጠት ቡድኖች ለቅርንጫፍ ጽ/ቤትና ቅርንጫፍ
ጽ/ቤታችን ለቤቶች አስተዳደር ዘርፍና ለስ/ፕላኒንግ እና ቢዝነስ ዴቭሎፕመንት ዳይሬክቶሬት
አቅርበናል፡፡
7.1.2. ሱፐርቪዥን
የ ህዳር ወር Page 13
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
8.1. መደምደሚያ
የ 2013 በጀት ዓመት እቅድ ተዘጋጅቶ እስከ ፈጻሚ ድረስ ካስኬድ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት
በፋይናንስና ገቢ አሰባሰብ 2,397,305.41 ብር በመሰብሰብ እና 87 ቤቶችን በመጠገን ውጤታማ ሥራዎችን
አከናውነናል፡፡
8.2. ፈታኝ ሁኔታዎች
የ ህዳር ወር Page 14
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
9.2. ውስንነቶች
ህገወጥ ድርጊት በመከላከል በኩል የተሰሩ ስራዎች ቢኖሩም ከህገወጥ ግንባታ፣ ከሶስተኛ ወገን ተከራይ ጋር
በተያያዘ አሁንም ያልተሻገርናቸው ችግሮች መኖራቸው፡፡
ጠንካራ የውስጥ አሰራር ስርዓት መዘርጋት ላይ ጅምር ስራዎች ቢኖሩም በአሰራር ላይ ክፍተቶች
መታየታቸው፡፡
የለውጥ ስራ ውጤታማ ለማድረግ ጥረቶች ቢኖሩም በአመለካከት አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ተግዳሮት መኖርና
ለውጡ የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ አለመሆኑ፡፡
ከሙስና መከላከል ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ስራዎች እንደተጠበቁ ሆነው በሁሉም ሰራተኛ እኩል ግንዛቤ ይዞ
መንቀሰቀስ ያለመቻል፡፤
የጥገና ጥራት ጉድለትና መዘግየቶች ማጋጠማቸው፡፡
ማጠቃለያ፡
በዚህም መሰረት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በህዳር ወር ያከናወንናቸውን የግቦች አፈጻጸም ከእቅድ በማነጻጸር ሪፖርት
የተሰራ ሲሆን 280 ቤቶች ውል ለማደስ ተችሏል፡፡ እንዲሁም በነዋሪ ወጭ መጋራት 46 ቤቶች ተጠግነዋል፤ በጽ/ቤቱ
የ ህዳር ወር Page 15
የቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት የ 2013 በጀት ዓመት የ ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
በአጠቃላይ የስራዎች አፈጻጸም የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ግብረ መልሶችን በመስጠት ዓመታዊ
እቅድን ለማሳካት በተደረገው ጥረት አጠቃላይ ጥሩ አፈጻፀም ላይ ደርሷል፡፡
የ ህዳር ወር Page 16