You are on page 1of 6

በመንግስት የልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን


የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ

የፕሮጀክት መከታተያ ስትራቴጂ

1
ማውጪያ
1. መግቢያ 3
2. የክትትልና ግምገማ ዓላማ 3
3.ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች 5
3.1 የገንዘብ አቅርቦትን ለማሻሻል የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣ 5

3.2 የወጪ አስተዳደር ላይ በቂ ትኩረት ሰጥቶ መደገፍ 5

3.3 መሣርያዎችን ወደ መጠናቀቅ ላይ ካሉ ፕሮጀክቶች ወደ ሌሎች ፕሮጅክቶች ማንቀሳቀስ 6

3.4 ፕሮጀክቶችንና ዲስትሪክቶችን ከመደገፍ አንፃር6

2
1. መግቢያ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ዘርፉ አሁንም ወደፊትም ለሚያከናውናቸው
ተግባራት ስኬታማነት የክትትልና ግምገማ ስርዓት መገንባት ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ የክትትልና ግምገማ ዘዴዎች ወቅቱን የጠበቀ
የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብ፣ ውጤትን በመገምገም፣ የግምገማ መድረኮች /ስብሰባዎች/ በማካሄድ፣ የአካል ምልከታ ማድረግን
ያካትታሉ፡፡ በመሆኑም ማንኛውንም የስራ እንቅስቃሴ በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት በተፈለገው አግባብ፣ወጪ እና ጊዜ
እየተተገበረ እና መተግበራቸውን የሚጠቁም ቀጣይነት ያለው የክትትል እና ግምገማ ስትራቴጅ ለመዘርጋት ታስቦ የተዘጋጀ
ነው፡፡

2. የክትትልና ግምገማ ዓላማ

ክትትልና ግምገማ ከማኔጅመንት ወይንም አስተዳደር መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ለትክክለኛ ፕሮጀክት አስተዳደር
ክትትልና ግምገማ በምንም አይነት መልኩ ሊተኩ ወይንም ሊቀየሩ አይችሉም፡፡

የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሥርዓት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዓላማዎች ይኖሩታል፡፡

 የተቀመጡ ግቦች በስትራቴጂያዊና ዓመታዊ ዕቅድ ዝግጅት ሂደት የተለዩ ክፍተቶችን እየሞሉና
ችግሮችን እየፈቱ መሆኑን ለማረጋገጥ፣

 የታቀዱ ሥራዎች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሠረት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ለመገምገምና ቀጣይ
አቅጣጫ ለማስቀመጥ፣

 በዕቅድ ተይዘው የሚከናወኑ ሥራዎች የተቋሙን ተልዕኮና ራዕይ ከማሳካት አንጻር ያሉበትን ደረጃ
ለመገምገም፣

 በትግበራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ትክክለኛና ወቅታዊ ድጋፍ ለመስጠት ናቸው፡፡

 አግባብነት ያለው የግብዓት አጠቃቀም፣ ግብዓት ወደ ምርት መቀየራቸውን ማረጋገጥ፣ የዕቅድ ትግበራ ጊዜንና እና
በጀት አጠቃቀም ላይ ማስተካከያ ለማድረግ፣ የስራ ክፍሎችን/ፕሮጀክቶችን አቅም እና ያሉበትን ሁኔታ
በማገናዘብ የዕቅድ አፈፃፀማቸውን መፈተሽ እንዲሁም የተከናወኑ ስራዎችን መከለስ እና ተፅዕኖዎችን
መገምገም የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የሚከተለው ቻርት የክትትልና ግምገማ አላማዎችን ያሳያል፡-

3
የፕሮጀክቶችን
እንቅስቃሴ ይዳስሳል

ትግበራው በተያዘለት
የፕሮጀክቶችን ጊዜ መከናወኑን
አላማና ግብ ማረጋገጥ
ይዳስሳል
ምርትን እና
ውጤትን ይዳስሳል

የገባኛል ባዮችንና
ባለድሻዎችን
የመሳብና በቡድን
የመስራት ልምድን
ያዳብራል የክትትልና የታዩ ለውጦችንና
ግምገማ መሻሻሎችን
አላማዎች ይዳስሳል

መነሻ ሃሳብ
የመውሰድ ልምድ
ያዳብራል

ጥራትን ቀድመው ለሚታዩ


ለማረጋገጥ ችግሮች ማስጠንቀቂያ
አቅምን ለመስጠት
ለመተንበይ

በአጠቃላይ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ የክትትልና ግምገማ ሥራዎች የዘርፉን ዕቅድ ውጤታማነት ለማረጋገጥ
እንዲቻል ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደሚከተለው ተለይተው ቀርበዋል፡፡

3.ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

4
3.1 የገንዘብ አቅርቦትን ለማሻሻል የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣

 በዘርፉ ሥር ያሉ ፕሮጀክቶችን የአፈፃፀም ሁኔታ መሠረት በማድረግ ሠፊ ሥራ፣የተሻለ አፈፃፀምና ገቢ ያላቸው


ፕሮጀክቶች(ከራዝ ካናል፣አርጆ ዴዴሳ) የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና ዲስትሪክቶች ላይ ትኩረት ሠጥተን እንሰራለን፤
 በኢመባ በኩል ይሁንታ ያገኘውን የ’’retention’’ገንዘብ የማሥለቀቅ ሥራ እንሰራለን እንዲሁም ከባለሥልጣን መሥርያ
ቤቱ የተገኙ ፕሮጀክቶችን የቅድሚያ ክፍያ(advance payment) በቅርቡ እንዲለቀቅ እየተከታተልን እንገኛለን፤
 ለተሰሩ ሥራዎች IPC ከማስፀደቅ እስከ መሰብሰብ ያሉ ሥራዎች ላይ በድጋፍ ሰጭ የስራ ክፍላችን የበለጠ ትኩረት
ሠጥተን እንሰራለን፡፡

3.2 የወጪ አስተዳደር ላይ በቂ ትኩረት ሰጥቶ መደገፍ


የዘርፉ ሀብትን በአግባቡ አሟጦ ለመጠቀምና የሀብት ብክነትን ለመከላከል እንዲቻል በዘርፉና በስሩ በሚገኙ
ዲስትሪክቶችና ፕሮጀክቶች ከሥራ እቅዳቸው ጋር የተመጣጠነ የሀብት አጠቃቀም እንዲኖር በማድረግ የስራ
ክፍሎች/መምሪያዎች እንዲሁም ፕሮጀክቶች ለስራቸው ማስፈፀሚያ ያቀዱትን በጀት በአግባቡ
መጠቀማቸውን በመገምገምና በመከታተል ስርዓቱን የጠበቀ የበጀት አጠቃቀም እንዲኖር ማስቻል፡፡
የተወሰኑፕሮጀክቶችና ዲስትሪክቶች ካላቸው መጠነኛ የሥራ ሁኔታ፣ የፀጥታና ሌሎች ተያያዥ ሁነታዎች
አንፃር ሌሎች ዉጫዊ ጉዳዮችን እንዲሁም ከአንፀራዊ የነጠላ ዋጋ ሁኔታ በመነሳት በደብረ-ማርቆስ፣
በድሬዳዋና በነቀምት ፕሮጀክቶች እንዲሁም በዱለቻ-አዋሽ፣በጉባ-በጉንዲና በአዋሽ ድልድይ ፕሮጀክቶች ላይ
ጥብቅ ክትትል ይደረጋል፡፡ እንዲሁም አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ በሆኑ ዲስትሪክቶችና ፕሮጀክቶች ላይ ልዩ
ትኩረት ሰጥቶ መደገፍና መከታተል የሚገባ ሲሆን
በዲስትሪክቶች አላስፈላጊ የካምፕ ይዞታዎችን እንዲሁም በዕድሜ መግፋትና በጤና ችግር ምክንያት
ሥራቸውን በአግባቡ መወጣት የማይችሉ በየዲስትሪክቱ የሚገኙ ሰራተኞችን በመለየት ህጋዊ መንገድን
ተከትሎ የ”retrenchement” ፕሮግራም በመጠቀም በመንግስት በኩል ተገቢው ውሣኔ እንዲሰጥ እንሰራለን፡፡

የቀጥተኛ ወጪዎችን ቁጥጥር “cost accounting”ን መሠረት በማድረግ የምንገመግም ሲሆን ቀጥተኛ
ያልሆኑትን ወጪዎች(Indirect costs)ደግሞ አስቀድሞ በታቀደላቸው በጀት እና እስትራቴጅክ ግቦችን
መሠረት በማድረግ እየተገመገሙ ግብረ-መልስ በመስጠትና በቀጣይ ያሉ ለውጦችን የመከታተል ሥራ
ይሰራል፡፡
በተለይ የፕሮጀክቶች ዋና ዋና ወጪዎች ማለትም እንደ ነዳጅ ፣የኪራይ መሣርያ፣የትርፍ ሰዓትና ሌሎች
ክፍያዎችንና የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች አጠቃቀም ጥብቅ ክትትል በማድረግ በተቀመጠው የአሰራር
ስርዓትና ስታንዳርድ መሠረት እንደፈጸም እናደርጋለን፡፡

3.3 መሣርያዎችን ወደ መጠናቀቅ ላይ ካሉ ፕሮጀክቶች ወደ ሌሎች ፕሮጅክቶች ማንቀሳቀስ


በመጠናቀቅ ላይ ላሉ ፕሮጀክቶች ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በአፋጣኝ በማጠናቀቅ መሣርያዎችን ወደ ሌሎች
ሞቢላይዝ በማድረግ የመደገፍ ሥራ ይሰራል፡፡

5
3.4 ፕሮጀክቶችንና ዲስትሪክቶችን ከመደገፍ አንፃር

የት/መ/ል/ኮ ዘርፍ የቁልፍ ጉዳዮች፣የፊዚካል እና የፋይናንሻል ዕቅድ-ክንውን የሚያጠቃልል ሳምንታዊ (Weekly) እና


ወርሃዊ (Monthly) ሪፖርቶችን ከሁሉም ፕሮጀክቶች እና ዲስትሪክቶች ሰብስቦ የሚያጠናቅርና የትንተና ሥራዎችን
የሚሰራ ሲሆን ይህም ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ወቅታዊ ደረጃ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ
ይረዳል፡፡ በበጀት ዓመቱ ለየሥራ ክፍሎቹ የተሰጡ ዕቅዶችን መሠረት በማድረግ አፈጻጸም የመገምገም ሥራ ይሰራል፤

 በማኔጅመንት ደረጃ በየወሩ የአፈጻጸም ግምገማ ይደረጋል፣ ያጋጠሙ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን
ይለያሉ የመፍትሔ እርምጃዎችም ይወሰዳሉ፣

 በማኔጅመንት፣ በመምሪያ፣ በቡድን እንዲሁም በዩኒት (በፕሮጀክቶች በ crew level) ደረጃ ባሉ


አደረጃጀቶች የዕቅድ አወጣጥና የአፈጻጸም ግምገማ ይካሄዳል፣

 በማኔጅመንት ደረጃ በየወሩ፣ በመምሪያ ደረጃ በየ 15 ቀን፣ በቡድን ደረጃ በየሳምንትና በዩኒት/በክሩ
ደረጃ በየቀኑ ሥራን የማቀድ አፈጻጸምን የመገምገም ሥራ ይሰራል፤

 በየሩብ አመቱ ሪፖርት ለሰራተኛው እየቀረበ ግብረ-መልስ ይወሰዳል፡፡ ለምሳሌም የበጀት አመቱ
የስድስት ወር ሪፖርት ለሰራተኛው ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ ጠቃሚ ግብዓቶችም ተገኝተዋል፣
የአፈፃፀም ደረጃቸው በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ለምሳሌ፡- ጅንካ፣ጉባ እና ዱለቻ በየወሩ
ከዕቅድ እስከ አፈፃፀም ድረስ በመምሪያ፣ በዋና መምሪያ እና በዘርፍ ደረጃ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ
በተጨማሪ በየጊዜው የመስክ ግምገማ በማድረግ በአፋጣኝ አፈፃፀማቸው የሚሻሻልበትን መንገድ የመፍትሄ ሃሳብ
በማስቀመጥ ተግባራዊነቱም ክትትል ይደረጋል፡፡

በአጠቃላይ የፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም በኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ ብቃት ላይ በተለያየ አቅጣጫ ያስገኘውን ውጤት መገምገም ዘርፉ
በኮርፖሬሽኑ እንዲሁም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማወቅ ይረዳል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በክትትልና ግምገማው በዘርፉ የታዩ ድክመቶችን እና ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች በመጠቆም በቀጣይ
ዓመታዊ ዕቅድ ላይ እንደ ግብዓት ለመውሰድ አስተዋጽዖ ሊያበረክት ይችላል፡፡ ይህንንም በማድረግ የኮርፖሬሽኑን ዕቅድ አፈፃፀም
በማሻሻል ዘርፉ የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ያግዘዋል፡፡

You might also like