You are on page 1of 20

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የሥራ አመራር ሥልጠና መመሪያ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የማሕበራት ማደራጃና ማስፋፊያ


ኤጀንሲ

በኮከብ ብርሀን ኘሮግራም ሥር በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑ ሕፃናት መጠቀሚያ


ሰኔ 2004

1
ማውጫ

1. መግቢያ................................................................................................................................................1

2. ክፍል አንድ: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት አደረጃጀት ............................................................5

3. ክፍል ሁለት : የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ የሥራ አመራር መዋቅራዊ አደረጃጀት.....................................9

4. ክፍል ሶስት: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ የአመራር አካላት ተግባራት፣ ኃላፊነቶችና ተጠያቂነት .............12

5. ክፍል አራት: የቁጠባ አሰባሰብና የብድር አሰጣጥ .....................................................................................15

የኮከብ ብርሀን በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናት ኘሮግራም በፓክት፣ በቻይልድ ፈንድና በኤፍ.ኤች አይ 360
የሚተገበር ኘሮግራም ሲሆን ኘሮግራሙ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት በኩል የጋራ ትብብር ስምምነት
ቁጥር - 663 - A - 11 – 00005 መሠረት ከአሜሪካ ሕዝብ በተደረገ እርዳታ ነው፡፡
ለተጨማረ መረጃ በሚከተለው የፓክት አድራሻ ይጠቀሙ፡፡

ፓክት

ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌ 20፣ የቤት ቁጥር 2129፣ የመ.ሣ.ቁጥር 13180,  አዲስ አበባ ፣
ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር : (251) 11-661-4800,  (251) 11-662-3796/Fax: (251) 11-662-3789/ የኢሜይል አድራሻ
pact@ethionet.et

1
መግቢያ

የብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት ለኑሮ ተጋላጭ የሆኑትን ህብረተቦች የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከሚያስችሉ
ብድር አገለግሎቶት ሰጭዎች አንዱ ነው፡፡በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት ምክንያት በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች፣
ቤተሰቦች፣ ማሕበረሰቡና በአጠቃላይም አገሪቷ ላይ ቀላል የማይባል ችግሮች ተፈጥሮባቸዋል፡፡ በተለይም ከፍተኛ
ቁጥር ባላቸው ወላጆቻውን ባጡና ለችግር በተጋለጡ ሕፃናት እድገት ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ የቅርብ
ክትትልና ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በድህነት ለሚኖሩ ሰዎች የገንዘብ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲጠቀሙ
ማመቻቸት መጀመሩ ይሄም በገቢ ምንጭ ዋስትናና እድገታቸው ላይ የሚኖረው ሚና ጉልህ እንደሆነ በግልጽ
እየታየ መጥቷል፡፡ በማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ገንዘብ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የሚያጠያይቅ
አይደለም፡፡ ነገር ግን በድሕነት ለሚኖሩ ሰዎች ፍላጐት ተስማሚ በሆነ መልኩ ገንዘብ እንዲያገኙ ማመቻቸት
መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ድሀውን እንዲጠቅሙ ተብለው የተቋቋሙት ጥቃቅንና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማትም
ቢሆኑ የገጠሩን ማሕበረሰብ ሁኔታና ፍላጐት ያላገናዘቡ በመሆናቸው ሙሉ በሙሉ ፍላጐታቸውን እያሟሉ
አይደሉም፡፡ ይህን ተጨባጭ ሁኔታ በየጊዜው መገንዘብ የደሀውን ማህበረሰብ ፍላጐት በተሻለ መልኩ የሚያሟላና
ሊጠቅም የሚችል አማራጭ እንዲኖር እንዲታሰብበት አድርጓል፡፡ የብድርና ቁጠባ ማሕበራት ከማናቸውም
ተቋማት በላይ ለሕብረተሰቡ ቀረቤታ ያላቸውና ባለቤትነት የሚተዳደሩ ተቋማት ሲሆኑ በፍጥነትና በቀላሉ
እንዲሁም በአንፃራዊነት አነስተኛ በሆነ የአገልግሎት ዋጋ የገንዘብ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎቶች መስጠት
የሚችሉ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ከዚሁ የሚገኝ የአገልግሎት ዋጋ ለአባላቱ አገልግሎት የሚውሉ መሆኑ ተጨማሪ
ጥቅም ነው፡፡
የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ አሰራር ከማሕበረሰብ የራስ አገዝ የቁጠባ ቡድን፣ ከራስ አገዝ ቡድን እና ባሕላዊ
ከሆነውና በማሕበረሰቡ በራስ ተነሳሽነት ከሚጀመርና እርስ በእርስ በመተማመን ከሚተዳደረው የቁጠባ አሰራር
ማለትም ከእቁብ ጋር ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገሮች አለው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ እቁብ በየአካባቢው የተወሰነን
ችግር ለመቅረፍ ወይም ለማሟላት የሚጀመር ሲሆን በአባላቱ አቅም ላይ በመመስረት መጠኑ በቅድሚያ
በስምምነት በእቁቡ ሰብሳቢ ይወሰናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እቁብ በአንድ ሰብሳቢና ፀሐፊ የሚተዳደር ሲሆን
አሰራሩም ሁሉም አባላት በቅድሚያ የተወሰነውን የገንዘብ መጠን ሰብሳቢው ከወሰደ በኋላ በስምምነት በሚደረግ
ተራ ወይም እጣ ሁሉም አባላት እስከሚወስዱ ድረስ ይቆያል፡፡ እቁብ የቁጠባና የብድር አይነት አሰራር ቢሆንም
አሰራሩ አባላት እንደፈለጉ ከሚቆጥቡት ገንዘብ ላይ ብድር እንዳይወስዱ ውሱንነት ያለበት ሲሆን ሌሎች ከላይ
የተጠቀሱት የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት በቅድሚያ አባላት በሚያደርጉት ስምምነትና መመሪያ
መሠረት ብድር የመውሰድ እድል ይሰጣቸዋል፡፡ ሌላው እቁብንና የማሕበረሰብ የቁጠባ ራስ አገዝ ቡድንን
የሚያመሣስላቸው ነገር በሁለቱም አሰራሮች አባላቶቻቸው በየጊዜው የሚያደርጉት መዋጮ በቅድሚያ ለተወሰነ
ጊዜ ብቻ የሚጠራቀም ሲሆን በራስ አገዝ ቡድንና የብድርና ቁጠባ ማሕበር ግን ተቋማቱ ሙሉ በሙሉ እስኪፈርሱ
ድረስ የአባላት መዋጮ እንደቀጠለ ይቆያል ፡፡

ነገር ግን በሁሉም የብድርና ቁጠባ አሰራሮች አባላት ከተጠራቀመው ተቀማጭ በየጊዜው ለአጭር ጊዜ
ፍላጐታቸው ብድር በመውሰድ የሚጠቀሙበት ሲሆን በገንዘባቸውም ወለድ ያገኙበታልም፡፡ ይሄውም አባላት
በከፍተኛ ወለድ ገንዘብ የሚያበድሩ አበዳሪዎች ጋ መሄድ ሳያስፈልጋቸው በየጊዜው በሚወስዱት ብድር ጥቃቅንና
አነስተኛ ስራዎችን ለመስራት ለሚያስፈልጋቸው ገንዘብ፣ ማሕበራዊ ግዴታዎችን ለመወጣትና
የሚያጋጥማቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች ለማሟላት ይጠቀሙበታል፡፡ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ
ለመቋቋሚያቸው የሚያስፈልጉትን ተፈላጊ መስፈርት ካሟሉ በኋላ ሕጋዊ ሰውነት ማግኘት ይችላሉ፡፡

የብድርና ቁጠባ ማሕበራትን ለመመሥረትና ለማንቀሳቀስ እንዲቻል ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትና


ቢሮዎች ጋር በቅርበት አብሮ መሥራት አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የሥልጠና ማንዋል እንደየክልሎች
ተጨባጭ ሁኔታ ከተዘጋጁት መመሪያዎችና የአሰራር ሁኔታዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
ይህም ለኘሮግራሙ ቀጣይነትና ስኬታማነት የሚረዳ ሲሆን የተቋቋሙትን ማሕበራት ለየክልሉ የማስረከብ ሂደትን

2
የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡ ከሁሉም በላይ የብድርና ቁጠባ ማሕበራት አመሠራረት ሂደት ውስጥ ከመገባቱ በፊት
በቅድሚያ ማሕበራቱ እንዴት እንደሚንቀሳቀሱና ከሌሎች መሰል ተቋማት ማለትም ከማሕበረሰብ ቁጠባ ራስ
አገዝ ቡድንና ከራስ አገዝ ቡድን እንዲሁም ከተግባሪ ድርጅቶች እንዴት እንደሚለዩና ያላቸውን ጥቅም በግልጽ
መረዳት አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

በተግባር እንደታየው የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራን ማቋቋም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ይሄውም
አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ማሕበረሰብ ደረጃውን የጠበቀ የገንዘብ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት መስጠት
መቻል፣ ጠንካራ ድጋፍ የሚሰጥ የፖሊሲ ሁኔታዎች መኖር፣ ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት ብቁ መሆን፣ ተቀባይነት
ያላቸውና ለረጅም ጊዜ በሥራ ላይ የዋሉ አለም አቀፋዊ አሰራሮችና ልምዶች መኖር፣ ወላጆቻዋውን ላጡና
ተጋላጭ ለሆኑ ሕፃናት በሌሎች ጉዳዮች ላይ ድጋፍና እንክብካቤ ለማድረግ እንዲረዳ እንደመነሻ የሚያገለግል
መሆኑ፣ ከመንግሥት ድርጅቶች የሚሰጥ የቴክኒክ ድጋፍና ክትትል ማግኘት፣ የአጋር ድርጅቶች በተረጋጋ ሁኔታና
ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ሥራቸውን መስራት መቻልና የሙያው ላይ የካበተ ልምድ መኖር ናቸው፡፡

ብድርና ቁጠባ ማሕበራትን ለማቋቋም እንደአስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎች ሊታዩ የሚችሉ ነገሮች በተጓዳኝነት ያሉ
ሲሆን እነዚህም መሠረተ ልማት ባልተስፋፋባቸውና የመንግሥት ተቋማት የማይገኙባቸው ቦታዎች ለማቋቋም
መሞከር፣ ሰነዶችን ብቃት ባለው ሁኔታ ለመያዝ የሚችል በቂ የሆነ የተማረ ሰው አለመኖር ፣ከማሕበረሰቡ መካከል
በፈቃደኝነት ላይ በተመረኮዘ መልኩ ድርሻቸውን ማዋጣት የሚችሉ በጣም ተጋላጭና መገለል የደረሰባቸውን
ሰዎች ማካተት አለመቻል እንዲሁም ከዚህ ቀደም ስለብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ አመሠራረት የነበረ የተሳሳተ
አመለካከት ናቸው፡፡

በብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራና በማሕበረሰብ ቁጠባ ራስ አገዝ ቡድን አመሠራረት ላይ እንደታየው ሁለቱም ላይ
ያሉት ዋና ዋና ጉዳዮችና ሂደቶች ተመሣሣይነት አላቸው፡፡ በመሆኑም በማሕበረሰብ ቁጠባ ራስ አገዝ ቡድን ላይ
ያሉት ሶስት መሠረታዊ ደረጃቸውን የጠበቁ አሠራሮች፤ ከመጨረሻ ደረጃ በስተቀር፤ በብድርና ቁጠባ ማህበር
አመሠራረት ሂደትና እድገት ላይ ያሉትን አሠራሮች ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡ አጀማመሩ በሚመለከተው
የመንግሥት አካል ተቀባይነት ካገኘ በሌላው ላይ የሚታየው የአጨራረስ ደረጃ በብድርና ቁጠባ ማሕበራት ላይ
ሊታለፍና በዚሁም ምክንያት የማሕበሩ ራሱን በመቻል ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በመሆኑም በማሕበረሰብ ቁጠባ ራዝ
አገዝ ቡድን ላይ ያሉት ሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ማለትም አጀማመር፣ ማስፋፋትና ዕድገት ደረጃዎች ላይ የጊዜና
የድርጊት ማስተካከያ ተደርጐባቸው ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡

በብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ አመሠራረትና እድገት ላይ በሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች


የሚደረጉ እንደ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዳሰሳ ሥራዎች፣ የመስራች ኮሚቴ አወቃቀርና የመሥራች ኮሚቴዎች
መተዳደሪያ ደንብን ማዘጋጀት፣ ፍላጐት ያላቸውንና ለአባለትነት ብቁ የሆኑትን የመለየት ሥራ፣ ማሕበራቱን
ለማስጀመር የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሌሎች ለጅማሮ የሚጠቅሙ ቅደመ ዝግጅቶችን ጨምሮ በሚተገበሩት
ተጨማሪ ድርጊቶች ምክንያት በማሕበረሰብ ቁጠባ ራስ አገዝ ቡድን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ከሚፈጀው ጊዜ
በላይ ተጨማሪ ሣምንታትን ሊወስድ ይችላል፡፡ የአስፈፃሚ ድርጅት ሙያተኞች የምሥረታው ሂደት ሊወስድ
የሚችለውን ጊዜ ለመቀነስ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዳሰሳዎችን በራሳቸው ለማድረግ ከሚመለከታቸው
የመንግስት ቢሮዎች ሥምምነት ካገኙና ዳሰሳውን ከፈፀሙ በኋላ የዳሰሳ ውጤቱ ፈቃዱን በሰጠው አካል
እንዲረጋገጥ ይሆናል፡፡ ከመጀመሪያው የትውውቅ ስብሰባ በኋላ መስራች ኮሚቴዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ
ለመወያየት ከማሕበረሰቡ አባላት ጋር ውይይት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ላይ በመመርኰዝ
ኮሚቴው ከአንድ ስብሰባ በላይ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በመቀጠልም መስራቹ ኮሚቴ እነማን የብድርና ቁጠባ ማሕበር
ማቋቋም እንደሚችሉ የሚያሳይ ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል፡፡ መስራች ኮሚቴው የመንግስትን
የማሕበራት ማቋቋሚያ ደንብ በመከተልና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ማሕበራትን ለመመስረት
ተጨማሪ ስብሰባ ያደርጋል፡፡ ቀጥሎም ለአምስት ቀናት የሚቆየውን ስለብድርና ቁጠባ ማሕበር የሚገልጽ ስልጠና
አባላት እንዲከታተሉት ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ለማሕበራት ምስረታ የምንከተላቸው መመሪያና ሂደቶች
በተለይም በቅድመ ዝግጅት ወቅት ሊከናወኑ የሚገቡ ሥራዎች ሥልጠናው ከመሰጠቱ በፊት በትክክል

3
መከናወናቸው መጤን የሚኖርባቸው ሲሆን ስልጠናዎች አንድ አይነት እንዳይሆኑ በየጊዜው ማሻሻያዎች
ሊደረግባቸው ይገባል፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ አመሰራረት ልምድ እንደሚያሳየው
እንደማንኛውም የማሕበረሰብ ብድርና ቁጠባ አሰራሮች የሚጀምረው ማሕበራቱ የሚቋቋሙበትን ማሕበረሰብ
ከብድርና ቁጠባ አሰራር ጋር ከማስተዋወቅና ከማወያየት ነው፡፡ በመቀጠልም የምስረታ ሂደቱ ለብድርና ቁጠባ
ማሕበር መመስረት አስፈላጊ የሆኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ባሕላዊ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጥናት ማድረግና
ማረጋገጥ ሲሆን ውጤቱም በሚመለከተው የመንግሥት አካል መጽደቅ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሠረት የማሕበሩ
መቋቋም በሚመለከተው የመንግስት አካል ከጽደቀ በኋላ የመስራች ኮሜቴ እንዲቋቋም ይደረጋል፡፡ የመስራች
ኮሜቴ ኃላፊነትም የሚከተሉት ናቸው፣

i. ከባለሙያ በሚያገኙት የቴክኒክ ድጋፍ መሠረት ለብድርና ቁጠባ ማሕበር ምሥረታ ማንኛውንም
አስፈላጊ ጥረት ያደርጋል፡፡
ii. አቅራቢያ ከሚገኝ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ስለማሕበራት አመሠራረት፣ አሠራርና እድገት
እንዲሁም ስለሚኖራቸው ጥቅሞች ልምድ ይቀስማል፡፡
iii. ከማሕበረሰቡ አባላት ጋር ስለብድርና ቁጠባ ማሕበር ውይይት በማድረግ ስለጠቀሜታው
ያስተዋውቃል፡፡
iv. ሊኖሩ የሚችሉ ችግሮችን በመለየትና ከባለሙያ ጋር ምክክር ያደርጋል፡፡
v. ማሕበሩ የሚገኝበት መሠረታዊ ሁኔታዎች ለመስራች አባላት ሪፖርት በማዘጋጀት ያቀርባል፡፡
vi. ፍላጐቱ ያላቸውን የማሕበረሰብ አባላት በመመዝገብና ስብሰባ በመጥራት ለወደፊቱ የብድርና ቁጠባ
ማሕበር ለመመስረት የሚያስችሉ የአባላት አቅምና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና ለመለየት
ይሰበሰባል፡፡
vii. ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል፡፡
viii. በመጨረሻም መስራች ኮሚቴው የመስራቾች ስብሰባ በመጥራት የመተዳደሪያ ደንቡን ያፀድቃል፣
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ የሚያደርግ የአስመራጭ ኮሚቴ እንዲቋቋም ቅድመ ሁኔታዎችን
ያመቻቻል፣ እንዲሁም ኃላፊነቱንና ሌሎች ሰነዶችን ለተመረጡት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያስረክባል፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ስልጠና ዋና ዋና ዓላማዎች፣

 ፍላጐቱ ያላቸውን የማሕበረሰብ አባላት ስለብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ አሠራርና ጥቅም


እንዲሁም ስለ ሀብት አሰባሰብ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማድረግ፣
 አባላቱ እንዴት በራሳቸው የገንዘብ ምንጭ ዘለቄታነት ያለው አነስተኛና ጥቃቅን ሥራዎች ላይ
መሠማራት እንደሚችሉ ለማዘጋጀትና ለማበረታታት ናቸው፡፡

በስልጠናው ጊዜ በሰነዱ ውስጥ የሚሸፈኑ አራት ዋና ዋና ክፍሎች ፣

ሥልጠናው የሚሸፍነው ክፍሎች

 የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ትርጓሜ፣ ዓላማና ባሕሪያት 1

 የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የሥራ አመራር ድርጅታዊ አወቃቀር 2

 የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የሥራ አመራር ኃላፊዎች

ተግባራት፣ ኃላፊነቶችና ተጠያቂነት፣ 3

4
 የቁጠባ ገንዘብ አሰባሰብና የብድር አሰጣጥ 4

የትምህርቱ ዓላማዎች

ይህ የስልጠና ክፍል በሚጠናቀቅበት ጊዜ ተሳታፊዎች የሚከተለውን ግንዛቤ ይጨብጣሉ፡፡


 ተሳታፊዎች እርስ በርስ ይተዋወቃሉ፣ በሚቀጥለው የስልጠና ጊዜ ላይ ራሳቸን ነፃ በማድረግ ተሳትፎ
ያደርጋሉ፣ የስልጠናውን አላማ፣ የሚወስደውን ጊዜና ዝርዝር መርሀ ግብሩን ይገነዘባሉ፡፡
 የሥልጠናውን ይዘት በመረዳት በስልጠናው ጊዜ ሊኖር ስለሚገባው የውስጥ ደንብ ይቀርፃሉ
ከስልጠናው የሚጠብቁትን ውጤት በግልጽ ያስቀምጣሉ፡፡

የሚፈጀው ጊዜ: 1 ሰዓት

የስልጠናው ዘዴ: አሰልጣኙ ስለልጠናው ይዘት ያቀርባል፣ የተሳታፊዎች ውይይት


ተፈላጊ እቃዎች: ፍሊኘ ቻርት፣ ማርከር (ሃሳብ መግለጫ ካርዶች)

የሰልጣኞች ትውውቅ

የእንኳን ደህና መጣችው መልዕክትና ለሥልጠና የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች– 20 ደቂቃ

ለተሳታፊዎችና ለሌሎችም እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ጊዜያቸውን በመሰዋት
በስልጠና ላይ ስለተገኙ ማመስገን፡፡ የመክፈቻ ስርዐቱን ለመከታተል ከወረዳ ማሕበራት ማደራጃ ቢሮ ወይም ከሌላ
ቦታ የመጡ እንግዶች ካሉ የመጡበትን ዓላማ ለተሳታፊው በመግለጽ ማስተዋወቅ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እንግዶቹ
ስለስልጠናው የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ መጋበዝ፡፡ ለሰልጣኞች ስለስልጠናው ይዘትና ስለሚቆይበት ጊዜ
መግለጽ፡፡ የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ስልጠናው ለአምስት ቀናት ይካሄዳል፡፡ ስልጠናው
ለአምስት ተከታታይ ቀናት ወይም እንደጊዜው አመቺነት በሚቀጥሉት 2 ወይም 3 ወይም ከዚያ በበለጠ ሳምንታት
ውስጥ ሊካሄድ ይችላል፡፡ እያንዳንዱ ተሳታፊ ስልጠናውን መከታተል እንዲችል ለማረጋገጥ የሚመቻቸውን ጊዜና
ሰዓት ለማወቅ መወያየት ተገቢ ነው፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና የሚቻል ከሆነ የስልጠና ጊዜውን ለተሳታፊዎች አመቺ
በሆነ ጊዜ ማስተካከል ተገቢ ነው፡፡

ትውውቅ – 20 ደቂቃ

ተሳታፊዎች ከ 2 እስከ 4 ሆነው በቡድን እንዲከፈፋሉ መጠየቅ፡፡ ሁለት ሰዎች እርስ በርስ በየተራው ስማቸውን፣
ስለቤሰብ ብዛትና ሁኔታ፣ ምን እንደሚሰሩ፣ እንደአስፈላጊነቱ ስለትምህርት ደረጃና ቡድኑ ስለእነሱ እንዲያውቅ

5
የሚፈልጉት መረጃ ካለ እንዲጠያየቁ ማድረግ፡፡ ከ 15 -20 ደቂቃ በመመደብ እርስ በርስ ትውውቅ እንዲያደጉ
ማድረግ፡፡ በመቀጠልም እያንዳንዱ ተሳታፊ ስለባልደረባው ለቡድኑ እንዲያስተዋውቅ በየተራ ጊዜ መስጠት፡፡

የስልጠናው ዓላማና በስልጠናው ጊዜ ሊኖር ስለሚገባ ውስጠ ደንብ – 20 ደቂቃ

የሥልጠናው ዓላማ ተሳታፊዎች በብድርና ቁጠባ ማሕበር እንዲደራጁ በቅድሚያ እነሱን ማዘጋጀት እንደሆነ ገለጻ
ማድረግ፡፡ ይሄም ስኬታማ እንዲሆን እያንዳንዱ ተሳታፊ ቁርጠኛነት እንደሚያስፈልግ መግለጽ ያስፈልጋል፡፡
አሰልጣኙ/አመቻቹ ተሳታፊዎች በሥልጠናው ወቅት የሚጠቀሙበትንና ራሳቸው የሚፈልጉትን የውስጥ ደንብ
እንዲያወጡ እገዛ ማድረግ፡፡ የሚከተሉት ሊኖሩ ከሚገቡ የውስጥ ደንቦች መካከል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

 በሁሉም የሥልጠና ክፍለ ጊዜ መገኘትና በሰዓቱ መገኘት፣

 በንቃት ተሳትፎ ማድረግና ሌሎች የሚሰጡትን ሃሳብ ማክበር፣

 ሌሎች ጉዳዮችን ለማስፈፀም የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን አለመተው፣

 በሚቀጥለው የሥልጠና ቀን/ሳምንት ሊኖር ስለሚችለው የትምህርት ጊዜ በጥሞና ማሰብ፣

 በስልጠናው ወቅት ያቀዱትን ጥቃቅን ስራዎችን መጀመር ወይንም ማስፋፋት፣

 በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ዝግጅት ማድረግ፣

 ተሳታፊዎች በተነሱት ነጥቦች ላይ እንደሚስማሙ መጠየቅና ውይይት ማድረግ ናቸው፡፡

ክፍል አንድ : የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አመሰራረት

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ትርጓሜና የብድርና ቁጠባ ማሕበር ዓላማዎች

የትምህርቱ ዓላማዎች
 ተሳታፊዎች የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ባሕሪያትን እንዲያውቁ ማድረግ፣
 የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አባላት ስለብድርና ቁጠባ ማሕበር እንዲረዱ ማስቻል፣
 አባላት በግልጽ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ገጽታዎችን እንዲረዱ ማድረግ፣

ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ : 2 ሰዓታት

የስልጠናው ዘዴ: ሃሳብ መለዋወጥ፣ ጥያቄዎችን ማንሸራሸር፣ መወያየት

ተግባር 1.1

በፊት የተደረጉ ስብሰባዎችን ወደኋላ መለስ ብሎ ማየት – 20 ደቂቃዎች

6
ከዚህ ቀደም ስለ ብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አመሠራረት ላይ በተደረጉ ውይይቶች የተሳታፊዎች
አጠቃላይ የዕውቀት ደረጃና የማስታወስ ችሎታ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ዳሰሳ ማድረግና ሌሎች ሊያነሱ
የሚፈልጓቸው ነጥቦች ካሉ መወያየት፡፡ እያንዳንዱ ተሳታፊ ራሱን ለመግለጽ እንዲችል እድል መስጠት፡፡ ሃሳቡን
ለመግለጽ የሚፈራ ተሳታፊ ካለ ማበረታታት፡፡ በቀላሉ ለውይይቱ መልስ በተሳታፊዎች የማይሰጥ ከሆነ
የማሕበረሰብ ንቅናቄ ሰራተኛ አብዛኛውን ነጥብ መሸፈን ይኖርበታል፡፡

ተግባር 1.2

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበርን መተርጐም – 30 ደቂቃ

ደረጃ 1: የሃሳብ ልውውጥና ውይይት

ተሳታፊዎች ስለብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ምን እንደሚረዱ በመጠየቅ መጀመር ያስፈልጋል፡፡


ተሳታፊዎች ቀደም ሲል ስለብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የሚያውቁት ካለ ስለማሕበሩ በተሻለ ሁኔታ
ግንዛቤ እንዲኖርና ትርጉሙ ግልጽ እንዲሆን ውይይቱ ተጨባጭ ምሳሌዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ማድረግ
ተገቢ ነው፡፡በመቀጠልም የሚከተሉትን የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ትርጉም ማብራራት፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ትርጉም፣ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ አዋጅ ቁጥር
147/1998 ላይ እንደተገለፀው የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ማለት በጋራ በመሆን ማሕበራዊ ወይም
ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለማቃለልና ይህንኑ ማሕበር በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመምራት በግለሰቦች በፈቃደኝነት
የተቋቋመ ማሕበር ማለት ነው፡፡ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ በአዋጁ ውስጥ ከተካተቱት ከሌሎች የሕብረት
ሥራ ማሕበራት መካከል እንደ አንድ የሚጠቀስ ነው፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አንደኛው ዓይነት የገንዘብ ተቋም ሲሆን አመሠራረቱ ሕጋዊ በመሆነ
መልኩ የተመሠረተ ሲሆን በአባላቱ ይዞታና ቁጥጥር ስር ሆኖ ራሳቸው የሚገለገሉበትና በዲሞክራሲያዊ መንገድ
የሚያስተዳድሩት ተቋም ነው፡፡ ዋና ዓላማውም አባላቱ የቁጠባ ባሕልን እንዲያዳብሩ ለማበረታታትና
ለማመቻቸት እንዲሁም አባላት ከተጠራቀመው ገንዘብ ላይ ምክንያታዊ የሆነ ወለድ በመክፈል መበደር
እንዲችሉና ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸውን ለማሻሻል እንዲችሉ ሌሎች መሰል የገንዘብ ተቋማት
የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ በማሕበራቱ ውስጥ ተሳታፊ ለሆኑ
የማሕበረሰብ ክፍል ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳያቸው ላይ ለመወሰን እንዲችሉ በማመቻቸት ረገድ ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበርን አንድ ለየት የሚያደርገው ባሕርይ ማሕበሩ ለበጐ አድራጐትም ሆነ
ለትርፍ የቆመ አለመሆኑ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት ዋና ዓላማው አባላቱን ለማገልገል በመሆኑ ላይ ነው፡፡
እንደሌሎች የበጐ አድራጐትም ሆነ ለትርፍ ያልቆሙ ድርጅቶች፣ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር በልገሣ
በሚገኝ ገንዘብ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የገንዘብ ተቋሙን ሕልውናና ቀጣይነት በማስቻል አባላቱን ለማገልገል
እንዲችል መጠነኛ ትርፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ማሕበረሰቡ ኢኮኖሚያቸውን ለማሻሻል እንዲረዳቸው አመቺ የሆነ
የገንዘብ ምንጭ ለማግኘት ሲሉ በፍላጐትና በራስ ተነሳሽነት ላይ በመመስረት የሚያቋቁሙት ማሕበር ሲሆን
የዚህ አይነት አመቺ አገልግሎት በመደበኛ የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ በመገንዘብ ጭምር ነው፡፡
የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር እንደ አንድ የኢኮኖሚ ተቋምና እንደራስ አገዝ ድርጅት የአካባቢውን
ማሕበረሰብና የአባላቱን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ሁኔታዎችን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

7
እንደማንኛውም የሕብረት ሥራ ማሕበር፣ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር መሠረታዊ ሕግን በመከተል
የሚመሰረትና የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ በብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አሠራር ውስጥ አባላት የተቋሙ
ባለቤት ሲሆኑ ከአባላቱ ውጪ የባለቤትነት መብት ያላቸው ሌሎች ሰዎች የሌሉ፣ ፖሊሲ አውጪ የአመራር
አካላት የሚሰየሙት ከአባላት ውስጥ ሲሆን የአመራር አካላቱ ምንም የተለየ ክፍያ አይኖራቸውም፡፡

ደረጃ 2: ክለሳና የስልጠናው ማጠቃለያ

በዚህ ደረጃ ላይ አሰልጣኙ/አመቻቹ ተሳታፊዎች የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ምን ማለት


እንደሆነ በትክክል የመረዳታቸውን አስፈላጊነትና ተሳታፊዎች በአግባቡ መረዳታቸው ላይ ትኩረት
በማድረግ ከዚሁ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ማንኛውንም ጥያቄ እንዲያነሱ ማበረታታት፡፡
በመቀጠልም የትርጉሙን ዋና ዋና ነጥብ በማንሳት ማጠቃለያ መስጠት፡፡

ተግባር 1.3

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ዓላማዎች – 25 ደቂቃ

ደረጃ 1: የውይይት አርዕስት:

ዓላማ ማለት ምን ማለት ነው?

አሰልጣኙ/አመቻቹ ዓላማ ማለት ምን እንደሆነ ለማብራራት እንዲችል ከተለያየ አቅጣጫ ዝግጅት ማድረግና ከብድርና ቁጠባ
የሕብረት ሥራ ማሕበር ዓላማ ባሻገር ስለዓላማ የሃሳብ ልውውጥ እንዲደረግና ግልጽ እንዲሆን ለማስቻል ጥንቃቄ ማድረግ
ይኖርበታል፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ዓላማዎች

በአዋጁ ላይ እንደተቀመጠው የሕብረት ሥራ ማሕበር ዓላማዎች የሚከተሉትን ይይዛል፡፡


o አባላት በተናጠል ሊያቃልሉት የማይችሉትን ችግር በጋራ በመሆን ለመፍታት፣
o እውቀታቸውን፣ ሀብታቸውንና ጉልበታቸውን በማቀናጀት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ፣
o በአባላት መካከል እርስ በርስ መደጋገፍን ለማበረታታት፣
o ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ ለመቋቋም፣ ለመከላከልና ለማቃለል፣
o የምርትና የአገልግሎት ዋጋን በመቀነስ አባላትን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል፣
o ቴክኒካዊ እውቀቶች በተግባር ላይ የሚውሉበትን አሠራር ለማስፋት፣
o የብድርና ቁጠባ አገልሎቶችን ማስፋፋትና ማስተዋወቅ፣
o የአስጊ ነገሮችና የማይታወቁ የወደፊት ስጋቶች የሚኖራቸው ተጽዕኖዎችን ለመቀነስና አነስተኛ
እንዲሆኑ ለማድረግ፣
o በትምህርትና ሥልጠና መሠረት የአባላትን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረቶችን ለማሳደግ
ናቸው፡፡

ደረጃ 2: ከተሳታፊዎች የተሰጡትን ሀሳቦችን ነጥብ በነጥብ በመከለስ ማጠቃለያ ማድረግና ከውይይቱ
ምክንያታዊ የሆነ ግንዛቤ መጨበጣቸውን ማረጋገጥ፡፡

ተግባር 1.4: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ገጽታዎች

የሥልጠና ጊዜ : 25 ደቂቃ

8
ደረጃ 1
ከታች በተመለከተው ቅደም ተከተል መሠረት አሠልጣኙ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ገጽታዎችን
በእርጋታ ውይይት እንዲደረግ ያደርጋል፡፡

በአለማችን ላይ ባሉ ሁሉም የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት መካከል ከዓላማቸው፣ ከሚከተሉት


ስትራቴጂ፣ ከአሠራር እና ከፍልስፍናቸው አኳያ ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገሮችና ልዩነቶች አሉ፡፡ ሆኖም ግን ወሳኝ
የሆኑ የሚያመሳስላቸው ነጥቦች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

 ደንበኛ ተኰር መሆን: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት የሚቋቋሙት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ
ያላቸውን የማሕበረሰብ አካል ለመጥቀም የሚቋቋሙ መሆናቸው፡፡

 አገልግሎት: ቁጠባና በአጭር ጊዜ በተከታታይነት የሚመለስ የብድር አገልግሎት መስጠት የብድርና የቁጠባ
የሕብረት ሥራ ማሕበር ገንዘብ ነክ አገልግሎት አንዱ መገለጫ መሆን፡፡ በጣም ውሱን የሆኑ የሕብረት ሥራ
ማሕበራት ሌሎች አገልግሎቶችን ማለትም የጡረታ ዋስትና፣ የሕክምና ተቀማጭና የቡድን ግዥ
አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፡፡

 ቁጠባ: ቁጠባና ብድር ያላቸው ቁርኝት በተገቢ መንገድ በመመሥረቱ አባላት ብድር ለመውሰድ ብቁ ለመሆን
በቅድሚያ ቁጠባ እንዲያደርጉ ይበረታታሉ፡፡ ብድር ለመውሰድ አባላት ማስቀመጥ የሚኖርባቸው የቁጠባ
መጠን ድርሻ በጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰን ሲሆን ይሄውም በሕጉ ላይ በግልጽ ይሠፍራል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ
ምክንያታዊ የሆነና በልምድ እንደሚታየውም የብድር ለቁጠባ ድርሻ 3:1 ሲሆን ይሄም የሚወሰነው በሚኖረው
የተቀማጭ ገንዘብ ላይ በመመሥረት ነው፡፡

 ብድር: ብድር የሚወሰደው ተለይቶ ለታወቀ ፍላጐት ወይም/እና ዓላማ ላይ በማትኮር አይደለም፡፡ ብድር
የሚሰጠው ለቤተሰብና ሥራ የማስፋፋት እቅድ ፍላጐትን ለማሟላት ነው፡፡ አባላት ብድር እንዳይወስዱ
የሚያግዱ በቅድሚያ ተለይተው የታወቁ የብድር ዝርዝሮች የሉም፡፡ የማሕበሩንና የአባላቱ ሕልውና ለመጠበቅ
እንዲረዳ ቀደም ብለው በተቀረጹት መመሪያዎች ብድር የሚሰጥ ሲሆን አባላት ከመውሰዳቸው በፊት በደንብ
እንዲያስቡበትና የብድሩ አላማና በተጓዳኝ ያሉ ስጋቶች ምን እንደሆኑ ለማጤን እንዲችሉ በተቀመጡ
ሂደቶች ውስጥ እንዲያልፉ መበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡

 ተቋማዊ አደረጃጀት: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ባለቤትነት የሚመራው በአባላት ሲሆን
የሚንቀሳቀሰውና ተጠቃሚዎችም እነዚሁ አባላት ናቸው፡፡ አባላት እያንዳንዱን ውሳኔ የሚያስተላልፉት
ራሳቸው ሲሆኑ ከአባላቱ ውጪ ብድር ከተቋሙ የሚወስዱ ሰዎች የለም፡፡

 ገንዘብ ነክ አሰራሮች: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የሚንቀሳቀሰው ከውስጥ ምንጭ በተገኘ ገንዘብ
ሲሆን እንደዋነኛ የካፒታል ምንጭ የሚታየው ከቁጠባ የሚገኘው ገንዘብ እንጂ ከውጭ በሚገኝ ልገሳ/ምንጭ
አይደለም፡፡

9
ምንም እንኳን የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ዓላማ የብድርና ቁጠባ ፍላጐት ያላቸውን የተወሰነውን
ዝቅተኛ/መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የማሕበረሰብ አካል ለማገልገል ቢሆንም በተግባር እንደታየው ግን ዋና ዋና
ችግሮችና ድክመቶች እንዳሉ ተስተውለዋል፡፡ እነዚህም ችግሮች/ድክመቶች እንደሚከተለው ተጠቃለው
ቀርበዋል፡፡

 የብድር ሕብረቶች አነስተኛ በመሆናቸው አገልግሎታቸውን ብዛት ወዳላቸው ጥቃቅን የሥራ ዘርፎች
የማስፋፋትና የማዳረስ ችግር አለባቸው፡፡ አባላት ለብድር ያላቸው ፍላጐት ማሕበሩ ካለው ተቀማጭ የቁጠባ
ገንዘብ መጠን ስለሚበልጥ ለብድር የሚሆን ጥሬ ገንዘብ የማጣት ችግር ከመኖሩ በላይ ለአባላት የሚሰጠውን
የብድር መጠን ውሱን ማድረጉ፡፡
 ውስጣዊ ፖሊሲዎችና የአሠራር መመሪያዎች ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ እንዲችሉ የሥራ አመራር ሂደቱ፣
የአሠራር ስርዐቱና የሂሳብ አያያዙ ዘመናዊ በሆነ መልኩ ተሻሽለው መቅረብ መፈለጋቸው ፡፡

ከብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አሰራር ልምድ እንደታየው አገልሎቶችን ለማሻሻል በየጊዜው የሚሰጡ
አገልግሎቶች እንደማስተማሪያ መሳሪያ እንደሚያገለግሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በየቦታው የሚደረግ
የቁጠባ ሥራ የረጅም ጊዜ ልማት ለማካሄድ እንደሚያስችልና ጥቅም እንዳለው ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

ሌሎች ከብድርና ቁጠባ የሕብረት ስራ ማሕበር የተገኙ ትምህርቶች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 በለጋሾች ከሚተዳደሩ ተቋማት በተሻለ ሁኔታ በብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ውስጥ የበለጠ
ኃላፊነት መኖሩ፣

 የሚገኙ ጥቅሞች ከመጠናቸው አንፃር መሆኑ፣ ከመጠናቸው አነስተኛነት የተነሳ የአባላቱን የብድር ፍላጐት
ለማርካት በቂ የሆነ የገንዘብ መጠን ማጣት፣

 የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የተለያዩ የደንበኞች መሠረት ያለውና ከተለያዩ በየተራ ከሚመጡ
ፍላጐቶች ጋር አብሮ የሚሄዱ መሆኑ ከሌሎች መሰል አነስተኛ ተቋማት የተለየ ያደርገዋል፡፡

ደረጃ 2

ማጠቃለቃለያ: 20 ደቂቃ
ተሳታፊዎች ጥያቄ ካላቸው መጠየቅ፡፡ በዋናው ስልጠና ጊዜ የተስተዋለና ገለፃ የሚፈልግ ነጥብ ካለ በደንብ መዘርዘር፡፡ በድጋሚ
ተሳታፊዎች መጠየቅ የሚፈልጉት ጥያቄ ካለ መጠየቅ፡፡ ለተሳትፎአቸው በማመስገን ውይይቱን ማጠቃለል፡፡

ክፍል 2: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ የሥራ አመራር መዋቅራዊ አደረጃጀት

10
የትምህርቱ ዓላማዎች:
 ተሳታፊዎች የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራን ድርጅታዊ አወቃቀር እንዲረዱ ማስቻል፣
 የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ አባል ለመሆን ምን መሟላት እንደሚገባ ተሳታፊዎች እንዲያውቁት ማድረግ፣

የሥልጠና ጊዜ : 2 ሰዓት
የስልጠናው ዘዴ: የሃሳብ ልውውጥ፣ ውይይት ፣ምሳሌዎችን ማቅረብ
ተፈላጊ እቃዎች: ፍሊኘ ቻርት፣ ማርከርና ተሳታፊዎች የሚጠቀሙበት ወረቀት

ተግባር 2.1 ድርጅታዊ አወቃቀር

የሚወስደው ጊዜ : 45 ደቂቃ

ከታች በቀረበው ማስታወሻ መሠረት አሠልጣኙ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ድርጅታዊ አወቃቀር ላይ
ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ ተሳታፊዎች በትክክል መረዳት እንዲችሉ በማሕበረሰቡ ውስጥ ያሉ ማሕበራዊ ተቋማት
ማለትም የእድር፣ የእቁብና ወዘተ አደረጃጀትን በማንሳት ተግባራዊ ምሳሌዎችን ይሰጣል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 147/98 በተደነገገውና በየክልሉ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ቢሮዎች በወጣው
መመሪያ መሠረት የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አደረጃጀት ሊዋቀር ይችላል፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ስራ ሶስት ዋና ዋና የሥራ አመራር አካላትና ሌሎች ንዑስ ኮሚቴዎች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡
ጠቅላላ ጉባኤው፣ የሥራ አመራር ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚቴዎች የማሕበሩ ውሳኔ ሰጪ አካላት ናቸው፡፡
በተጨማሪም ማሕበሩ የብድርና የቁጠባ ማስፋፊያ ኮሚቴ፣ የትምህርትና የስልጠና ንዑስ ኮሚቴዎች ሊኖሩት
ይችላል፡፡ የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ የማሕበሩን የእለት ከእለት ሥራ የሚያከናውን ሰራተኛ ሊቀጥር
ይችላል፡፡ የአንድ ማሕበር ድርጅታዊ አወቃቀር ከታች የቀረበው አይነት ሊሆን ይችላል፡፡

11
ጠቅላላ ጉባኤ

የሥራ አመራር ኮሚቴ የቁጥጥር ኮሚቴ

የማሕበራት ማስፋፊያ፣
የብድር ኮሚቴ የትምህርትና ሥልጠና ሥራ አስኪያጅ
ኮሚቴ

ሠራተኞች

ተግባር 2.2 አባልነት

የሚወስደው ጊዜ : 1 ሰዓት

ዘርፈ ብዙ ዓላማ ካላቸው የሕብረት ሥራ ማሕበራት በተለየ መልኩ የብድርና ቁጠባ ማሕበራት የተለየ የአባልነት
መስፈርቶች አሉት፡፡ ይህ የሆነበትም ምክንያት የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ከሌሎች የሃብት
አይነቶች ይልቅ ጥሬ ገንዘብ በማሰባሰብና ጥሬ ገንዘብን በመጠቀም ሥራዎችን የሚሰራ በመሆኑ ነው፡፡
በተጨማሪም የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ሥራውን በአመቱ ውስጥ ባሉት ወራት በማንኛውም ጊዜ
የሚያከናውን ሲሆን ዘርፈ ብዙ ዓላማ ያላቸው የሕብረት ሥራ ማሕበራት ግን ቢበዛ በዓመት ውስጥ ሥራቸውን
የሚያከናውኑት ከሶስት እስከ ስድስት ወራት ውስጥ ቢሆን ነው፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ሥራቸውን የሚያከናውኑት በገንዘብ ዙሪያ ብቻ በመሆኑ


የሚተዳደሩትና የሚገዙት ባንኮች በሚተዳደሩበት ደንብና አሠራር ነው፡፡ አቅማቸው በፈቀደላቸውና እስከቻሉ
ድረስ ሊኖር የሚችለውን ስጋት ለመቀነስና ትርፋማነታቸውን ለመጨመር መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደካማ
የሕብረት ሥራ ማሕበሩ አባላት ለማሕበሩ የሚያመጡት ድክመትን ሲሆን ይሄም ተቋሙ ዓላማውን ከግብ
እንዳያደርስ መሰናክል ይሆንበታል፡፡ አመልካቾች የሕብረቱ አባል ለመሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት
ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሀ. ገንዘብ ነክ መስፈርት

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አባላት በጠቅላላ ጉባኤው የሚወሰነውን አነስተኛ መዋጮ የግድ
ለማዋጣት ፍላጐትና ችሎታው ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አንድ አባል ገቢ ሊኖረው ለማይችላቸው ወራት አስቀድሞ
የሚፈለግበትን መዋጮ ማዋጣት ይኖርበታል፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አንድ አባል በማሕበሩ ውስጥ ካለው አጠቃላይ የባለቤትነት ድርሻ ውስጥ
የሚያስፈልገው አነስተኛውን የተቀማጭ መጠን ድርሻ ለማዋጣት ፈቃደኛ ሊሆን ይገባል፡፡

12
በተጨማሪም አባላት የመመዝገቢያ ክፍያ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆንና አቅሙም ሊኖርው ሲገባ በተመሣሣይ
መልኩ በጠቅላላ ጉባኤ በሚወሰነው ውሳኔ መሠረት ሌሎች በማሕበሩ የሚፈለጉበትን መዋጮዎች ለመክፈል
አቅሙና ፈቃደኝነቱ ሊኖረው ይገባል፡፡ ሕብረቱ እንደተቋቋመ መጀመሪያ አካባቢ ከአባልነት መዋጮ የሚሸፈን
የሥራ ማስፈፀሚያ ወጪ ይኖራል፡፡ የሕብረት ሥራ ማሕበሩ ካደገ በኋላ ሁሉም ወጪዎች ከብድርና ከሌሎች
ተዛማጅ ስራዎች ከሚገኝ ወለድ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ሆኖም የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራው በተቋቋመ
የመጀመሪያና ሁለተኛ አመት ላይ የሚከፈል ወርሃዊ የአገልሎት ክፍያ አነስተኛ መሆን የተለመደ አሠራር ነው፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበሩ አባላት የማሕበሩ አባላት ከመሆናቸው በፊት ከማንኛውም እዳ ነፃ መሆን
ያለባቸው ሲሆን ይህም ማሕበሩን ለአደጋ ላለማጋለጥ ነው፡፡

ለ. መልካም ሥም

የሕብረት ሥራ ማሕበሩ አባላት በሚኖሩበት ማሕበረሰብ ውስጥ መልካም የሆነ ስም ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የአንድ
ማሕበር ስምና ዝና የሚወሰነው በአባላቱ ስምና ዝና ላይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ጠንካራና ጥሩ ስብዕና ያለው
የሕብረት ሥራ ማሕበር በቀላሉ ከሌሎች የገንዘብ ተቋማት ጋር ጥሩ የሆነ የሥራ ግንኙነት ሊያዳብሩ ይችላሉ፡፡

ሐ. የተለያዩ ሥራዎች ላይ መሠማራት

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ስጋት ባለ ሥራ ውስጥ የሚንቀሳቀስ የስራ መስክ ነው፡፡ ሁሉም የማሕበሩ
አባላት ተመሳሳይነት ባላቸው ሥራዎች ውስጥ የሚሰማሩ ከሆነ ይሄ ስጋት ይጨምራል፡፡ በተግባር የተስተዋለ
የአባላት በተለያየ ስራ ላይ የመሰማራት ፍላጐት ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡ በተጨማሪም መሰፈርቱ በፆታ
ስብጥርና ተዋጽኦ ላይ ትኩረት ማድረጉ ሊጤን ይገባል፡፡

መ. የአባላት የእድሜ ወሰን

በአዋጅ ቁጥር 147/98 በተደነገገው መሠረት የአንድ የሕብረት ሥራ ማሕበር አባል ለመሆን ቢያንስ ቢያንስ አንድ
አባል እድሜው/ዋ 14 ዓመት መሆን ይኖርበታል፡፡

ሠ. የአካባቢ መስፈርት

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር አባላት በሚገባ ትውውቅ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በመሆኑም የማሕበሩ
አባላት በአንድ አካባቢ የሚኖሩ መሆን ሲኖርባቸው ቢያንስ ቢያንስ የሕብረት ሥራው ባለበት አካባቢ መደበኛ
ሥራቸውን የሚሰሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ገንዘባቸን በየጊዜው እንዲቆጥቡና ብድራቸውን በወቅቱ መክፈል
እንዲችሉ የአባላት ግፊትና እርስ በርስ ቁጥጥር ለማድረግም ይረዳል፡፡

ተግባር 2.3 ማጠቃለያ 15 ደቂቃ

አባል ለመሆን በሚያስፈልግ መሥፈርት ላይ ግልጽ ያልሆነና የሚያሻማ ነገር ካለ ትኩረት በማድረግ ግልጽ
ማድረግና ውይይቱን ማጠቃለል፡፡

ክፍል 3: የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የሥራ አመራር ኃላፊዎች ተግባራት፣ ኃላፊነቶችና ተጠያቂነት፣

13
የትምህርቱ ዓላማዎች :

 ተሳታፊች የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር የተለያዩ የአመራር አካላት ያላቸውን ተግባራትና ኃላፊነቶችን እንዲገነዘቡ
ማድረግ፣
 ስኬታማ የሆነ የማሕበር አመራር እንዲሰፍን በማሕበሩ የተለያዩ የአመራር አካላትና በአባላት መካከል ስኬታማ ግንኙነት
እንዴት መሆን እንዳለበ ለማረጋገጥ፣

የሥልጠና ጊዜ : 2 ሰዓት
የስልጠናው ዘዴ: የሃሳብ ልውውጥ፣ ውይይት ፣ምሳሌዎችን ማቅረብ
ተፈላጊ እቃዎች: ፍሊኘ ቻርት፣ ማርከርና ተሳታፊዎች የሚጠቀሙበት ወረቀት

ተግባር 3.1 ጠቅላላ ጉባኤ

የሚወስደው ጊዜ : 30 ደቂቃ

ጠቅላላ ጉባኤው የሕብረት ሥራ ማሕበሩ ከፍተኛ ሥልጣን ያለው አካል ሲሆን የሚከተሉት ተግባራትና
ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
 የማሕበሩን ጠቅላላ የሥራ እንቅስቃሴ ከገመገመ በኋላ ውሳኔ ያስተላልፋል፣

 የማሕበሩን የመተዳደሪያ ሕጐችና የውስጥ ደንቦችን ያሻሽላል እንዲሁም ያፀድቃል፣

 የሥራ አመራር ኮሚቴ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሌሎች ንዑስ ኮሚቴ አባላትን

ይመርጣል ብሎም ያሰናብታል፣


 የማሕበሩን አንድ ድርሻ ሊኖረው የሚገባውን መጠን ይወስናል፣

 የማሕበሩ አመታዊ የተጣራ ትርፍ እንዴት መከፋፈል እንዳለበት ይወስናል፣

 በኦዲት ሪፖርት ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

 የሥራ ሪፖርቶችን ያዳምጣል ብሎም ተገቢውን ውሳኔ ይሰጣል፣

 በአዋጁ መሠረት ማሕበሩ ከሌላ ማሕበር ጋር እንዲወሀድ ወይም እንዲከፈል ውሳኔ ያስተላልፋል፣

 ብድሮችንና ሌሎች የስራ መመሪያዎችን ያፀድቃል፣

 አመታዊ የሥራ እቅድና በጀት ያፀድቃል፣

ተግባር 3.2 የሥራ አመራር ኮሚቴ

የሚወስደው ጊዜ : 30 ደቂቃ

ሀ. ተግባራትና ኃላፊነቶች

የሥራ አመራር ኮሚቴ በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ ሲሆን ዋና ተግባሩም የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር
የዕለት ከዕለት የሥራ እንቅስቃሴ እንዲመራ ነው፡፡ የአመራር አባላቱ የሕብረቱን ዓላማ ለማሳካት በአዋጁ መሠረት
ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በአንድ ጊዜ የተመረጠ የሥራ አመራር ኮሚቴ ለሶስት አመታት በሥራ ላይ የሚቆይ ሲሆን
የአመራሩ አባላት ከሁለት ተከታታይ የምርጫ ጊዜ በላይ ሊመረጡ አይችሉም፡፡ የሥራ አመራር ኮሚቴ ሥልጣንና
ኃላፊነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

14
o የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን በጽሑፍ ማስቀመጥ፣
o የማሕበሩን የሂሳብ መዝገብና ሌሎች ሰነዶችን በጥንቅቄ እንዲያዙ ማድረግ፣
o የማሕበሩን አመታዊ የስራ እቅድና በጅት ማዘጋጀት፣
o በመተዳደሪያ ሕግ መሠረት የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ መጥራት፣
o ስለ ማሕበሩ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ መስጠት፣
o በጠቅላላ ጉባኤው የሚጠሰውን ሌሎች ስራዎችን ማከናወን ናቸው፡፡

ለ. ሪፖርት ስለማድረግ

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሪፖርት የሚያደርገው ለጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወርሃዊ
የሂሳብ ሚዛን ሰነድ፣ የሂሳብ መግለጫ ሰነድና የሃብት መግለጫ እንዲሁም በሕጉ መሠረት ወይም ጠቅላላ ጉባኤው
በሚያዘው መሠረት ሪፖርት ያዘጋጃል፡፡

ሐ. ስለ ሰራተኛ ቅጥር

የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴው የዕለት ከዕለት የሥራው ክብደት ወይም ብዛት የተነሳ ሥራውን ብቻውን ለማከናወን
የሚቸገር ከሆነና ይሄው በጠቅላላ ጉባኤ ከተወሰነ ወይም በማሕበሩ መተዳደሪያ ሕጉ ላይ ከተፈቀደ ኮሚቴው
የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበሩን ሥራ ለማከናወን ከአባላት መካከል ወይም አባል ያልሆነ ሰራተኛ ሊቀጥር
ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ የሥራ አመራሩን ሥራ እንዲሰሩ የሚቀጠሩት ሰራተኞ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ
የመቆጣጠር ኃላፊነት የኮሚቴው ይሆናል፡፡

መ. የኮሜቴ አባል ብዛት : ሁልጊዜ በኮሚቴው የሚተላለፉ ውሳኔዎች በአብላጫ ድምጽ አሰጣጥ በቀላሉ
እንዲወሰኑ የኮሚቴ አባላት ብዛት 3 ወይም አምስት ቢሆኑ ይመከራል፡፡

ተግባር 3.3 የብድር ኮሚቴ

የሚወስደው ጊዜ: 30 ደቂቃ

በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጠው የብድር ኮሚቴ ሊቀመንበር/ሰብሳቢ፣ ፀሐፊ እና አንድ አባል የያዘ ቢያንስ ቢያንስ 3
አባላት ይኖረዋል፡፡ የብድር ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ኮሚቴ ሲሆን የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነቶች
ይኖሩታል፡፡

 ከአባላት የሚመጡ የብድር ጥያቄዎችን በመመርመር በሰዓቱ ውሳኔ መስጠት፣


 ብድር ጠያቂዎች ሁሉንም ተፈላጊ ሰነዶችን አሟልተው ማቅረባቸውን ማረጋገጥ፣
 ለአባላት ብድር መስጠት፣
 የብድር ጥያቄዎችን፣ ክፍያዎችን፣ ተሰብሳቢዎችንና ሌሎች ጉዳዮችን በማቀድ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ ማድረግ፣
 ብድር ከመፈቀዱ በፊት ማሕበሩ በቂ ገንዘብ እንዳለው ማረጋገጥና ብድር ከተሰጠ በኋላ በወቅቱ ተመልሶ
እንዲከፈል ክትትል ማድረግ፣
 የኮሚቴውን የሥራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሪፖርት ለሥራ አመራር ኮሚቴ ማቅረብ፣
 በሥራ አመራር ኮሚቴ የሚሰጠውን ማንኛውንም ተግባር ማከናወን ናቸው፡፡

15
ተግባር 3.4 የቁጥጥር ኮሚቴ
የሚወስደው ጊዜ: 30 ደቂቃ

የቁጥጥር ኮሚቴ ለሶስት አመት ጊዜ ማሕበሩን እንዲያገለግል በጠቅላላ ጉባኤ ይመረጣል፡፡ ማንም የቁጥጥር ኮሚቴ
አባል ከሁለት ተከታታይ የአገልግሎት ጊዜ በላይ እንዲመረጥ አይደረግም፡፡ ኮሚቴው የሚከተሉትን ሥልጣንና
ተግባራት ይኖሩታል፡፡
 የሥራ አመራር ኮሚቴውና ሌሎች ንዑስ ኮሚቴዎች በማሕበሩ ደንብና መመሪያ መሠረት ተግባራቸውን

ማከናወናቸውን ይቆጣጠራል፣
 የማሕበሩ መተዳደሪያ ሕግ፣ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በትክክል ሥራ ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፣

 ማንኛውም ማሕበሩ የሚያከናውናቸው ሥራዎች በማሕበሩ መተዳደሪያ ሕግና ፖሊሲ መሆንኑን ቁጥጥር

ያደርጋል፣
 የሂሳብ እንቅስቃሴዎች፣ የሂሳብ ሰነዶችና ሌሎች የማሕበሩን ንብረቶች ይቆጣጠራል፣

 ስለሥራ እንቅስቃሴው ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል፣

 አፋጣኝ መፍትሔ የሚሹ ችግሮች ሲያጋጥሙ በአስቸኳይ ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል በሥራ አመራር

ኮሚቴ ወይም በሌላ አካል በኩል ስብሰባዎች እንዲደረጉ ያደርጋል፣


 በጠቅላላ ጉባኤው በኩል የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል፡፡

3.5 የትምህርትና ስልጠና ኮሚቴ

የትምህርትና ሥልጠና ኮሚቴ በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ ሲሆን ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ኮሚቴ ይሆናል፡፡
ኮሚቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡፡

 ለአባላትና አባላት ላልሆኑ ሰዎች ስልጠናና ትምህርት ይሰጣል፣


 ስለሕብረት ሥራ ማሕበር ጥቅሞች፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ ለአባላቱ
ለማስተማር ማንኛውንም እድል ይጠቀማል፣
 ለአባላት ስለቁጠባ፣ ብድርና በወቅቱ አመላለስ ላይ ትምህርትና ምክር ይሰጣል፣
 ለአባላት ትምህርትና ሥልጠና ለመሰጠት እቅድ ያወጣል፣ ሲፀድቅም በተግባር ላይ ያውላል፣
 ስለማሕበራት ዓላማዎችና አሠራሮች ለአካባቢው ማሕበረሰብ፣ የመንግስት አካላት፣ የገንዘብ ተቋማትና
ለሌሎችም ያስተዋውቃል፣
 ስለኮሚቴው የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርባል፣
 ሌሎች በሥራ አመራር ኮሚቴ የሚሰጠውን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

ክፍል 4: የቁጠባ አሰባሳብና የብድር አሰጣጥ

16
የስልጠናው ዓላማዎች :
 ተሳታፊዎች በብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ውስጥ ያሉትን የቁጠባ አሠራሮችና እድሎችን እንዲገነዘቡ ማድረግ፣
 ተሳታፊዎች ከብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ብድር ለመውሰድ የሚሄዱትን ሂደት እንዲረዱ ማድረግ፣

የሥልጠና ጊዜ : 2 ሰዓት
የስልጠናው ዘዴ: የሃሳብ ልውውጥ፣ ውይይት ፣ምሳሌዎችን ማቅረብ
ተፈላጊ እቃዎች: ፍሊኘ ቻርት፣ ማርከርና ተሳታፊዎች የሚጠቀሙበት ወረቀት

ተግባር 4.1 የቁጠባ አሰባሰብ

የሚወስደው ጊዜ: 30 ደቂቃ

በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ አጠልጣኞች በክልል መስተዳድሩ በተዘጋጀው መመሪያውና ደንብ ላይ የቀረቡትን ዝርዝር
አሰራር በመጠቀም ስልጠና መስጠት ይኖርበታል፡፡ የአንድ ክልል የሕብረት ሥራ ማሕበር መመሪያና ቅደም ተከተል
የተለያዩ አይነት የቁጠባ አሳባሰብ አማራጮችን ስለሚያስቀምጥ ተሳታፊዎች በቀላሉ እነዚህን የማወቅ እድል
ያገኛሉ፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበር ቁጠባ መር የብድር አሰጣጥ አሰራርን ይከተላል፡፡ የሕብረት ሥራ አሰራር
ከሁለት የገንዘብ ምንጭ ማለትም በፈቃደኘነት ከሚገኝ ቁጠባና ከግዴታ ከሚገኝ ቁጠባ ገንዘብ ያሰባስባል፡፡
በግልጽ ለማስቀመጥ ቁጠባ የሚገኘው በመደበኛነት ወይም ከተወሰነ ተቀማጭ ወይም ከአስገዳጅ ተቀማጭ፣
ክፍት ወይም በፈቃደኝነት ከሚደረግ ቁጠባና በተወሰነ ጊዜ ከሚደረግ ቁጠባ ነው፡፡ የቁጠባ ዝርዝር አሰራር
በሕብረት ሥራ ማሕበሩ መተዳደሪያ ሕግ ውስጥ ይቀመጣል፡፡

ድርጊት 4.2 የብድር አሰጣጥ

የሚወሰደው ጊዜ : 30 ደቂቃ

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ለአባላቱ የብድር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ብድር የሚሰጥበት ዋናው አላማ
ከወለድ ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን በአባላት የብድር መክፈል አቅም ላይ በመመርኮዝ ምክንያታዊ በሆነ የወለድ
መጠን ብድር እንዲያገኙ ማስቻልና የአኗኗር ሁኔታቸውን እንዲያሻሽሉ መርዳት ነው፡፡

የብድርና ቁጠባ የሕብረት ሥራ አሠራር የሚመራው በቁጠባ መር ብድር አሰጣጥ አሠራር ነው፡፡ እያንዳንዱ
የሕብረት ሥራ ማሕበር ከታች በተዘረዘሩት ነጥቦች ብቻ ሳይወሰን የብድር አሠጣጥ መመሪያን በማውጣት
ሊጠቀምበት ይገባል፡፡
 የሥራ እቅድ

 ከፍተኛው የብድር መጠን

 የወለድ መጠን

 ብድር የመክፈያ ጊዜ (የጊዜ ገደብ)

17
 ብድር ለመውሰድ ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶችና የማሕበሩ አባላት የሚስማሙበት ሌሎች ጉዳዮች
መካተት አለባቸው፡፡

ተግባር 4.3 የብድር አሰጣጥ ሂደት


የብድር ማመልከቻ

 አባላት ብድር ለመውሰድ በቅድሚያ የማሕበሩን የብድር መውሰጃ ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡


 አመልካቹ የብድር ማመልከቻውን ለብድር ኮሚቴ ይሰጣል፣
 ሌሎች ደጋፊ ሰነዶች ከብድር ማመልከቻው ጋር ተያይዞ በተገቢው መንገድ ሊቀመጥ ይገባል፡፡ እነዚህ
ደጋፊ ሰነዶች በሚከተሉት ብቻ ሳይገደብ ከታች የተዘረዘሩትን ያካትታል፡፡
o ብድር ጠያቂው በግድ መቆጠብ ያለበት የቁጠባ መጠን፣
o የብድር አመልካቹ በማሕበሩ ውስጥ ያለው የባለቤትነት ድርሻ፣
o ተያዡ ያጠራቀመው የቁጠባ መጠንና የባለቤትነት ድርሻ፣
o የሥራ እቅድና ሌሎች ተጓዳኝ ነገሮች፣
o እንደአስፈላጊነቱ የብድር ኮሚቴው ለብድር አመልካቹ ቃለመጠይቅ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
የቃለመጠይቁ ወይም የውይይቱ ይዘት የተጠየቀው የብድር መጠንና ሊውልበት የታሰበበት አላማ
መጣጣሙን፣ ስለ ብድር አጠቃቀም ሁኔታና ብድሩን ለመውሰድ የጠየቀው አመልካች ራሱ
መሆኑን ለማረጋገጥ ሊሆን ይችላል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የማሕበሩ የብድር ኮሚቴ ወይም
የሥራ አመራር ኮሚቴ ቃለመጠይቁን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ብድር ስለማጽደቅ

የብድር ኮሚቴ የሚከተሉትን ነጥቦች ግምት ውስጥ በማስገባት የብድር ጥያቄዎችን ሊያፀድቅ ይችላል፡፡
 የአመልካቹን ግላዊ ባሕሪይ እና የብድር አጠቃቀም እንዲሁም ተበዳሪው ያቀረበው ዋስ ብቁ መሆን፣

 አመልካቹ ከዚህ ቀደም ግዴታዎችን ለመወጣት ያለው ታሪክ፣

 የሕብረት ሥራ ማሕበሩ ያለው የገንዘብ መጠን፣

 ብድሩን ለመፍቀድ በውሳኔ አሰጣጡ ላይ ከ 50 እጅ በላይ የብድር ኮሚቴ አባላት መኖር፣

 ውሳኔ የተሰጠበት ቃለጉባኤ በጥንቃቄ መቀመጥ ይኖርበታል፣

 የአመልካቹን የብድር ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ በግልጽ የታወቀ ምክንያት ሊኖር ይገባል፣

 የብድር መመለሻና ቁጠባ ከብድር ጋር ያለው ተመጣጣኝነት ጨምሮ ብድሩን ለማግኘት የሚያስፈልጉ

መስፈርቶች በትክክል መታወቅ፣


 በቃለጉባኤው ላይ ፊርማ መኖር ናቸው፡፡

ኮሚቴው ከላይ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች በመመልከት የብድር ጥያቄዎችን ማጽደቅም ሆነ መሰረዝ
ይችላል፡፡ የብድር ጥያቄዎች በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያት ሊሰረዙ ይችላል፡፡
 ብድር የሚውልበት ዓላማና የሥራ እቅድ አለመኖር፣

 ያለበቂ ምክንያት የተወሰደ ብድርን መክፈል ማቆም፣

 በአመልካቹ ቀደም ሲል የተወሰደ ብድር ካለ፣

18
 እምነት የማይጣልበት የማሕበር አባል ከሆነ፣
 መደበኛውን ቁጠባ መቆጠብ ያልቻለ አባል ከሆነ፣
 ብድሩን መልሶ የመክፈል አቅም ከሌለው፣
 ሌሎች ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፡፡

ብድር ለተበዳሪ ስለመልቀቅ/ክፍያ ስለመፈፀም

ማሕበሩ የፀደቀውን የብድር መጠን በጥሬ ገንዘብ ወይም በቼክ ክፍያ ሊፈጽም ይችላል፡፡ በወር ጊዜ ውስጥ
የተበዳሪዎችን ስም ዝርዝር የያዘና በተጓዳኙ የተደረጉትን ክፍያዎች የያዘ የተጠቃለለ ሪፖርት ይቀርባል፡፡

የብድር ዓላማ

ብድር የሚወሰድበት ዓላማ በግልጽ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

የብድር ጊዜ

የብድር ጊዜ የማሕበሩ አባላት በተስማሙበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው፡፡

የብድር መጠን :

የሚወሰደው አነስተኛና ከፍተኛው የብድር መጠን የማሕበሩ አባላት በተስማሙበት መጠን ሲሆን ይሄው
በመተዳደሪያ ደንብ ውስጥ መጠቀስ ይኖርበታል፡፡ የሚሰጠው የብድር መጠን የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ
ሊሆን ይገባል፡፡

የብድር ስምምነት

እያንዳንዱ ተበዳሪ ብድሩን ከመውሰዱ በፊት የብድር ስምምነት ከማሕበሩ ጋር መፈራረም ይኖርበታል፡፡ የብድር
ስምምነት ናሙና አባሪ ላይ ተቀምጧል፡፡ በስምምነቱ ላይ አመልካቹ፣ ዋሱና እማኞች መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
የብድር ኮሚቴው በብድር ጥያቄው ላይ ውሳኔ በመስጠት ለክፍያ ለሥራ አመራር ኮሚቴ ያስተላልፋል፡፡

የወለድ መጠን

የሕብረት ሥራ ማሕበሩ አባላት በብድር ላይ ሊከፈል የሚገባውን የወለድ መጠን ይወስናሉ፡፡ ወለድ የሚከፈለው
ዋናውና ወለዱን ጭምር በአንድነት መሆን ሲኖርበት የወለድ መጠኑ ከንግድ ወለድ መብለጥ የለበትም፡፡

19

You might also like