Professional Documents
Culture Documents
መሐረነ አብ ጸሎት
መሐረነ አብ ጸሎት
+ ሃሌ ሉያ ፤
ለእርሷ ሲል ታስሮ መጎተትን የቻለ፤ የበደለውን በደል ሳይኖር ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሰ
አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ
🙏 ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ፤
🙏 ሃሌ ሉያ፤
፥ሃሌ ሉያ፤
+++ ወአድኅነነ፤
አድነንም፤
🙏 አምላክነ፥
አምላካችን
+++ ወመድኃኒነ
መድኃኒታችን
🙏 ደምስስ አበሳነ፤
በደላችንን አጥፋልን፤
🙏 እስመ እምኀቤከ፤
ባንተ ዘንድ ነውና፤
+++ ወተሣሃለነ፤
ይቅርም በለን፤
🙏 ሀብ ሣህለከ መሐሪ ፤
ይቅር ባይ ሆይ! ይቅርታህን ላክ፤
🙏 በምህረትከ፤
በይቅርታህ፤
🙏 ሰማዒ ወትረ፤
ሁልጊዜ ሰሚ ነህ፤
+++ ከሃሊ ዘውስተ አድኅኖ፤
በማዳን ጊዜ ቻይ ነህ፤
🙏 ከሃሊ፤
ቻይ፤
🙏 ይፈኑ ለነ ሣህሎ፤
ይቅርታውን ይልክልን ዘንድ
🙏 ሃሌ ሉያ፤
ሃሌ ሉያ፤(ቅድመ ዓለም የነበረ፥አሁንም ያለ፥ድኅረ ዓለም የሚኖር )፤
+++ ሃሌ ሉያ ፤
ሃሌ ሉያ ፤
🙏 ወይእዜኒ፤
አሁንስ(እንግዲህስ)
+++ መኑ ተስፋየ?
ተስፋየ ማን ነው?
🙏 አኮኑ
አይደለምን፤
+++ እግዚአብሔር፤
እግዚአብሔር
🙏 አመኀጽን ነፍስየ፤
ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤
🙏 አመኀጽን ነፍስየ፤
ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤
🙏 አመኀጽን ነፍስየ፤
ነፍሴን አስጠብቃለሁ፤
🙏 ኀበ አምላከ ምሕረት፤
ወደ ምሕረት አምላክ
🙏 ኀበ ንጉሠ ስብሐት፤
ወደ ምስጋና ንጉሥ፤
🙏 በእግዚእየ ወአምላኪየ፤
በጌታየና በአምላኬ፤
🙏 አመኀጽን ነፍስየ፤
ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤
🙏 አመኀጽን ነፍስየ፤
ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፤
🙏 አመኀጽን ነፍስየ፤
ነፍሴን አስጠብቃለሁ፤
🙏 ሀቡ፤
ኑ
+++ ንስአሎ፤
እንለምነው፤
🙏 ንስአሎ
እንለምነው፤
+++ ናስተምህሮ፤
ራራልን እንበለው (እንማልደው)፤
🙏 ወበከመ ዐቀብከነ እምነግህ እስከ ሠርክ ዕቀበነ እግዚኦ እምሠርክ እስከ ነግህ፤
ከጧት ጀምሮ እስከማታ እንደጠበቅከን ከማታ እሰከ ጧት ጠብቀን፤
✟✟✟(፫ ጊዜ በል በቅብብል)
+++ ተሣሃልከ እግዚኦ ምድረከ፥ሃሌ ሉያ፥ስማዕ ጸሎተነ ወስዕለተነ፥ ወስረይ ኵሎ
ኃጢአተነ፥ስማዕ ጸሎተነ ወስዕለተነ፥ዘሰማዕኮ ጸሎቶ ወስዕለቶ ለዕዝራ፥ተወከፍ
ምህላነ፥ሰላመከ ኀበነ ወእማዕከሌነ ኢትርሐቅ።
አቤቱ ከኛ መዓትህን መልስ፥ሃሌ ሉያ፥ያማረች ርግቤ የአፏ እስትንፋስ እንደ እንኮይ ያማረ
ነው፥ንግግሯም ሀሉ ሰላማዊ ነው፥ርግቤ ሆይ! ወደ እኔ ነይ።
+++ ብፁዐ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ በኀበ እግዚኡ፥ ይንሳእ እሴተ፥ቦአ
ገዳመ ደብረ ሊባኖስ በፍስሐ ወበሰላም።
ብፁዕ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በጌታው ዘንድ ዋጋን ያገኝ ዘንድ ወደ ገዳማት
የገሰገሰ፡፡በደስታና በሰላም ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባ ፡፡
+++ ሣህል ወርትዕ ተራከባ ጽድቅ ወሰላም ተሳዐማ አመ ተሰምዓ ዜናከ በዓለም ዜና
ማርቆስ ክቡር መምህረ ሰላም ዘህላዌከ ገዳም
አባ ሳሙኤል ሆይ! በረከትህን እቀበል ዘንድ ባርከኝ፥ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ስትል
ባርከኝ፥በረከትህንም እቀበላለሁ።
አባ ዘርዓ ብሩክ ሆይ! በረከትህን እቀበል ዘንድ ባርከኝ፥ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
ስትል ባርከኝ፥በረከትህንም እቀበላለሁ።
ለዓለም ሁሉ መስቀል ብርሃን ነው፡፡ የቤተክርስቲያን መሠረት እርሱ ነው፡፡ ሰላምን የሚሰጥ
ዓለምን የተቤዘህ አምላክ ሆይ ሰላምህን ስጠን፡፡
+++ ሰላመ አብ ወሰላመ ወልድ ወሰላመ መንፈስ ቅዱስ የሃሉ ማዕከሌክሙ አኃው
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
ይ.ካ. ሰላመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወፍቅራ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ
አምላክ ሞገሰ መስቀሉ ወሀብተ ረድዔቱ የሃሉ ምስለ ኵልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም።
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟