You are on page 1of 11

መሐረነ አብ (የምህላ ጸሎት)

+++ መሐረነ አብ ሃሌ ሉያ
አባት ሆይ ማረን ሃሌ ሉያ

+++ ተሣሃለነ ወልድ ሃሌ ሉያ


ወልድ ሆይ ማረን ሃሌ ሉያ

+++ መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ


መሐሪ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በይቅርታህ አስበን
(3 ጊዜ)

+++ ለከ ንፌኑ ስብሐተ ወለከ ነዓርግ አኮቴተ


ላንተ ምሥጋናን እንልካለን ላንተም ምሥጋናን እናሳርጋለን

+++ መሐረነ መሐሪ ኃጢአተነ አስተሥሪ


ይቅር ባይ ይቅር በለን ኃጢአታችንንም አስተስርይልን

+++ ወአድኅነነ
አድነንም

+++ ወተማህፀን ነፍሰነ ወሥጋነ


ነፍሳችንንና ሥጋችንን ጠብቅ
+++ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር
የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ሆይ

+++ አምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሣሃለነ


አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅር በለን

+++ በብዝኃ ምህረትከ


በምህረትህ ብዛት

+++ ደምስስ አበሳነ


በደላችንን አጥፋልን

+++ ወፈኑ ሣህለከ ዲቤነ


ይቅርታህንም ወደኛ ላክልን

+++ እስመ እምኀቤከ


ባንተ ዘንድ ነውና

+++ ውእቱ ሣህል


ይቅርታ

+++ ሃሌ ሉያ መሐረነ አብ መሐሪ


ሃሌ ሉያ ይቅር ባይ አባት ሆይ ማረን

+++ ወተሣሃለነ
ይቅርም በለን

+++ ሀብ ሣህለከ መሐሪ


ይቅር ባይ ሆይ ይቅርታህን ላክ

+++ ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት


ያለፈው በደላችንን አስበህ አታጥፋን

+++ በምህረትከ
በይቅርታህ

+++ እስመ መሐሪ አንተ


አንተ ይቅር ባይ ነህና

+++ ወብዙህ ሣህልከ ለኩሎሙ እለ ይጼውዑከ


ለሚጠሩህ ሁሉ ይቅርታህ ብዙ ነው

+++ ይጼውዑከ በጽድቅ


በእውነት ለሚጠሩህ
+++ ሰማዒ ወትረ
ሁልጊዜ ሰሚ ነህ

+++ ከሃሊ ዘውስተ አድኅኖ


በማዳን ጊዜ ቻይ ነህ

+++ ከሃሊ
ቻይ

+++ ዘውስተ አድህኖ


በማዳን ጊዜ

+++ ለአምላክነ እስመ ጽድቅ ቃሉ


ለአምላካችን ቃሉ እውነት ነው፡፡

+++ ንስአሎ ለአብ ይፈኑ ለነ ሣህሎ


አብን እንለምነው ምሕረቱን ይላክልን

+++ እስመ አብ የአክል ለዘሰአሎ


አብ ለለመነው ሁሉ ይበቃልና

+++ ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሉያ
+++ ስብሐት ሎቱ ይደሉ
ለርሱ ምስጋና ይገባል

+++ ሃሌ ሉያ አኮቴት ሎቱ ይደሉ


ሃሌ ሉያ ለርሱ ምስጋና ይገባል

+++ ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሉያ

+++ ለክርስቶስ ለእግዚአ ኩሉ


ለሁሉ ጌታ ለክርስቶስ

+++ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ

+++ ወይእዜኒ
አሁንስ

+++ መኑ ተስፋየ
ተስፋየ ማን ነው

+++ አኮኑ እግዚአብሔር


እግዚአብሔር አይደለምን

+++ ውስተ እዴከ እግዚኦ አመኀጽን ነፍስየ


አቤቱ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ

+++ ኀበ አምላከ ምህረት


ወደ ምህረት አምላክ

+++ አመኀፅን ነፍስየ


ነፍስየን አደራ እሰጣለሁ

+++ ኀበ ንጉሠ ስብሐት


ወደ ምስጋና ንጉሥ

+++ አመኀጽን ነፍስየ


ነፍስየን አደራ እሰጣለሁ

+++ በእግዚእየ ወአምላኪየ


በጌታየና በአምላኬ

+++ አመኀጽን ነፍስየ


ነፍስየን አስጠብቃለሁ
+++ እምኩሉ ምግባረ እኩይ አድኅና ለኀፍስየ
ነፍሴን ከክፉ ሥራ ሁሉ አድናት

+++ ሀቡ
ስጡ

+++ ንስአሎ
እንለምነው

+++ ናስተምህሮ
ራራልን እንበለው

+++ ለአምላክነ ጻድቅ እስመ ጽድቅ ቃሉ


እውነተኛ የሆነው አምላካችን ቃሉ እውነት ነውና

+++ ዘይክል ኩሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ


ሁሉን የሚችል የሚሳነው ነገር የሌለ

+++ አምላከ ነዳያን ረዳኤ ምንዱባን


የድሆች አምላክ የተቸገሩትን የምትረዳ

+++ ነህነ ኀቤከ ተማኅፀነ


እኛ ባንተ ተማጽነናል
+++ ዘይክል ኩሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ
ሁሉን የሚችል የሚሳነው ነገር የሌለ

+++ አምላከ ነዳያን ናዛዜ ኅዙናን


የድሆች አምላክ ያዘኑትን የምታጽናና ሆይ

+++ ንህነ ኀቤከ ተማኅፀነ


እኛ በአንተ ተማጽነናል

+++ ዘይክል ኩሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ


ሁሉን የሚችል የሚሳነው ነገር የሌለ

+++ አምላከ ነዳያን ወተስፋ ቅቡፃን


የድሆች እና ተሥፋ ለቆረጡ አምላካቸው

+++ ንህነ ኀቤከ ተማኅፀነ


እኛ ባንተ ተማጽነናል

+++ ወበከመ ዐቀብከነ እምነግህ እስከ ሠርክ ዕቀበነ እግዚኦ እምሠርክ እስከ ነግህ

ከጧት ጀምሮ እስከማታ እንደጠበቅከን ከማታ እሰከ ጧት ጠብቀን


(3 ጊዜ የሚባል)
+++ተሣሃልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ስማዕ ጸሎተነ ወስዕለተነ ወስረይ ኩሎ ኃጢአተነ
ስማዕ ጸሎተነ ወስዕለተነ ዘሰማዕኮ ጸሎቶ ወስዕለቶ ለዕዝራ ተወከፍ ምህላነ ሰላመከ ኀበነ
ወእማዕከሌነ ኢትርሐቅ

አቤቱ ርስትህን ይቅር በል ሃሌ ሉያ ጸሎታችንን እና አስተብቁኦታችንን ስማ ኃጢአታችንንም


ሁሉ አስተስርይልን የዕዝራ ፀሎትና ልመና የሰማህ ሆይ ምህላችንን ተቀበል ሰላምህን ስጠን
ከመካከላችንም አትራቅ

+++ ወሚጥ መዓተከ እምኔነ ሃሌ ሉያ፤ ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ መዓዛ አፉሃ ከመ
ኮል ወኩሉ ነገራ በሰላም
አቤቱ ከኛ መዓትህን መልስ ሃሌ ሉያ ያማርሽ ርግብየ እንደ እንኮይ የአፏ ሽታያማረ ንግግሯም
ሀሉ ሰላም የሆነ ርግቤየ ሆይ ወደ እኔ ነይ

+++ አርእየነ እግዚኦ ሣህለከ ሃሌ ሉያ፤ ማህደረ ሰላምነ ቅድስት ደብተራ እሞሙ ለሰማዕት
ወእኅቶሙ ለመላእክት ንዑ ንስግድ ኩልነ ኀበ ማርያም እምነ

አቤቱ ይቅርታህን አሳየን ሃሌ ሉያ፣ የሰላማችን ማደርያ ደብተራ ኦሪት የሰማዕታት እናታቸው
የመላእክት እህታቸው ኑ ሁላችንም ወደ ድንግል ማርያም እንስገድ

+++ መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል፣ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ
መንበሩ ለንጉሥ አቢይ
የሰላማችን መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ስለኛ ለምን፡፡ ጸሎታችንንም
ከታላቁ ንጉሥ መንበር ፊት አሳርግልን፡፡

+++ ገብርኤል አብሠራ ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ ወይነግሥ ለቤተ ያዕቆብ ለዓለም
ወአልቦ ማኅለቅት ለሰላሙ
ቅዱስ ገብርኤል ድንግል ማርያምን አበሠራት እንዲህ አላት ልጅን ትወልጃለሽ ለዘለዓለሙ
ለያዕቆብ ቤት ይነግሣል ለመንግቱም ፍጻሜ የለውም

+++ ሰዓል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሀረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ


ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብዓ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንስአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ
በሰላም አደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ ወደ እግዚአብሔር ለምንልን


ስለኛ ለምን፡፡ አረዱት ቆራረጡት ስጋውን ፈጭተው እንደ ትቢያ በተኑት፡፡ ወደ ሰባ ነገሥታት
ወሰዱት ምድርን ተረገጠ ሙታንን አስነሣ፡፡ አባታችን ጊዮርጊስ በሰላም ከሞት ወደሕይወት
ተሻገረ ርስት መንግሥተ ሰማያትንም ወረሰ፡፡

+++ ብፁዐ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ በኀበ እግዚኡ ይንሳእ እሴተ ቦአ ገዳመ
ደብረ ሊባኖስ በፍስሐ ወበሰላም
ብፁዕ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በጌታው ዘንድ ዋጋን ያገኝ ዘንድ ወደ ገዳማት የገሠገሠ፡፡
ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባ በታላቅ ደስታና በሰላም ገባ፡፡

+++ ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሳሙኤል አባ ባርከኒ
እንሣእ በረከተከ
አባ ሳሙኤል ሆይ በረከትህን እቀበል ዘንድ ባርከኝ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ስትል
ባርከኝ በረከትህንም እቀበላለሁ

+++ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም ሃሌ ሉያ


ለዓለምና ለዘለዓለም ሃሌሉያ

+++ ሰላመ አብ ወሰላመ ወልድ ወሰላመ መንፈስ ቅዱስ የሃሉ ማዕከሌክሙ አኀው
የአብ ሰላም የወልድ ሰላም የመንፈስ ቅዱስ ሰላም በናንተ በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን
መካከል ይኑር

+++ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ


አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን

You might also like