You are on page 1of 174

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር👏👏👏

//ያችን ቀን በፀፍፀፍ...!//
ልጄ አይተሽው ቢሆን የመስቀል ላይ ሞቴን፣

ጀሮሽ ሰምቶ ቢሆን ተጠማሁ ማለቴን፣

አይንሽ አይቶ ቢሆን ምን እንደደረሰኝ፣

ኮምጣጣ ከሃሞት ጋር ልጠጣው ሲሰጡኝ፣

የሆነውን ሁሉ አይንሽ ቢመለከት፣

ልጄ ሰምተሽ ቢሆን የጅራፉን ጩኸት፣

ከኔ አትርቂም ነበር የኔ ልጅ ላንዳፍታ፣

መስቀል ላይ ብታይኝ ቆሜ ጎለጎታ።

ስለናንተ ብየ ሂወቴን መስጠቴን፣

ልጆቼ እንዳትረሱት የመስቀል ላይ ሞቴን።

#ስቀለውነው እንጅ ፍታው የሚል ጠፋ፣

ያችን ቀን በፀፍፀፍ #ተከዳሁ በይፋ፣

ሞት እንደሚገባኝ አይሁድ ደነገጉ፣

ደም ውሃ እስኪወጣኝ ጎኔን #በጦር ወጉ።

ህዝቡም መኳንንቱም ካህናትም ተጠሩ፣

በደል እንደሌለኝ #ነገስታት አወሩ።

ይሙት የሚለው ህዝብ እጁን አነሳብኝ፣

ያችን ቀን በፀፍፀፍ ሞት ተፈረደብኝ።

እውነት ተዘንግቶ አመፅ ተወደደ፣

ያችን ቀን በፀፍፀፍ ተንጋደደ።

ለመብሌ ሃሞት ሰጡኝ ሆምጣጤ ለጥሜ፣


ልጆቼን ለማዳን ለናንተው ደክሜ።

ከልባችሁ ነበር አባቴ እምትሉኝ፣

እርቃኔን ልጆቼ መስቀል ላይ ብታዩኝ፣

ስለናንተ ብየ ሂወቴን መስጠቴን፣

ልጆቼ እንዳትረሱት የመስቀል ላይ ሞቴን።

👉ፆማችንን በሰላም እንዳስጀመረን በሰላም አስፈፅሞ ለብርሃነ ትንሳኤው እንዲያደርሰን የእመቤታችን የቅድስት
ድንግል ማርያም #ምልጃ የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቃ አይለየን ...አሜን አሜን አሜን..

ለመጸለይ የጸሎት መጽሐፍ ለምን ያስፈልጋል? +++


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከሚለዩባቸው ብዙ ነገሮች አንዱ ከእጃቸው
የማይለዩት የጸሎት መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነዚህን የጸሎት መጻሕፍት የሚመለከት አንዳንድ ሰው ታዲያ ‹‹ያለ
ጸሎት መጽሐፍ መጸለይ አይቻልም ወይ? በጸሎት መጽሐፍ ላይ ያለው ሃሳብ የልቤን ነገር ባይገልጽልኝስ?
የጸሎት መጽሐፍ እያነበብኩ ከምጸልይ የራሴን ሃሳብ ብናገርስ? ሌላ ሰው ለራሱ የጸለየውን ጸሎትና
ያቀረበውን ምስጋና እኔ ደግሜ ለምን እጸልያለሁ? የተጻፈን ደጋግሜ ስጸልይ እንደ ሥራ አይሆንብኝም ወይ?
እንዴትስ ልመሠጥ እችላለሁ?›› የሚል ጥያቄ ሲያነሣ ይታያል፡፡
በመሠረቱ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሰው ጨርሶ የራሱን ሀሳብ መጸለይ አይችልም የሚል ክልከላ
የለም፡፡ ሆኖም በቤተ ክርስቲያኒቱ የጸሎት ሥርዓት ውስጥ ሰፊውን ድርሻ የሚይዘው አስቀድሞ በጽሑፍ
የተዘጋጀውና መጽሐፍ እያዩ በማንበብ ወይም በቃል ይዞ በመድገም ወይም ደግሞ በማዜም የሚቀርበው
ጸሎት ነው፡፡ ስለዚህ ለመጸለይ የጸሎት መጽሐፍ አስፈላጊ ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ ተገቢና ማብራሪያ
የሚፈልግ ጥያቄ ነው፡፡
በመጀመሪያ ማስታወስ የሚገባን ትልቁ ቁምነገር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር የሚጸለየው
ትልቁ የጸሎት መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ነው፡፡ ለመጸለይ የጸሎት መጽሐፍ አስፈላጊ ነው ወይ
የሚለው ጥያቄም ‹መጽሐፍ ቅዱስ ለጸሎት አስፈላጊ ነው ወይ?› የሚልም ጭምር ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ታሪክነቱ ትተርከዋለች ፣ የንጉሥ ቃል እንደመሆኑ ጥላ ዘርግታ ፣
መብራት አብርታ ልጆችዋን በፍርሃት ‹ቁሙና ስሙ› ብላ ታነበዋለች ፣ እንደ ቅዱስ ቃልነቱ ትሳለመዋለች ፣
እንደ ምሥጢርነቱ ትተረጉመዋለች ፣ እንደ መዝሙርነቱ ትዘምረዋለች ፣ እንደ ጸሎትነቱ ደግሞ
ትጸልየዋለች፡፡ በዚህም ምክንያት ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጸሎት መጻሕፍት ውስጥ አብዛኛው ክፍል ቃል
በቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ሲሆን እጅግ ጥቂቶቹ ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ የአነጋገር ለዛንና አገላለጽን
የወሰዱ (Bible inspired) ናቸው፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቁን ሥፍራ የያዘው የጸሎት መጽሐፍ ‹መዝሙረ ዳዊት› ነው፡፡ በልዩ ልዩ ርዕሶች ላይ
ቅዱስ ዳዊትና በሥሩ የነበሩ መዘምራን የጸለዩት ይህንን ታላቅ መጽሐፍ የሚጸልይ ሰው የራሱን ጊዜያዊ
ጭንቀት ፣ ውስጣዊ ምኞት ፣ ልመና እና ሙግት በዚህ ታላቅ መጽሐፍ ውስጥ ያገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ
ክርስቲያን ሊቃውንት ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ የልባቸውን ሲያደርስላቸው ‹ለጌታዬ ማን ነገረው እርሱ
እግዚአብሔር እርሱ ሰማኝ› (መኑ ነገሮ ለእግዚእየ) የሚለውን የዳዊትን አነጋገር ተውሰው ‹‹ለዳዊት የልቤን
ማን ነገረው?›› (መኑ ነገሮ ለዳዊት) እያሉ ያደንቃሉ፡፡
ከዳዊት መዝሙር ቀጥሎ የሚጸለዩት ዐሥራ አምስት ጸሎቶችም ቃል በቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱ
ናቸው፡፡ ሙሴ የጸለያቸው ሦስት ጸሎቶች ፣ የሳሙኤል እናት የሀና ጸሎት ፣ የሕዝቅያስና የምናሴ ጸሎቶች ፣
ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሆኖ የጸለየው ጸሎት ፣ የዳንኤል ፣ የሦስቱ ወጣቶች ፣ የኢሳይያስ ጸሎቶች
ከሐዲስ ኪዳን ደግሞ የድንግል ማርያም ፣ የካህኑ ዘካርያስና የአረጋዊው ስምዖን ጸሎቶች ከመዝሙረ ዳዊት
ቀጥሎ የሚጸለዩ ጸሎቶች ናቸው፡፡ ጌታችን ለሐዋርያቱ ያስተማረው ‹አባታችን ሆይ› የሚለው ጸሎት አካሉ
የሆነች ቤተ ክርስቲያን ‹እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ› ብላ ጸሎትን ማስተማር እንደሚገባት የሚያሳይ ነው፡፡
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በጸሎት መጽሐፎችዋ ውስጥ ከኛ ቀድሞ ተጸለዩ ጸሎቶችን እንድንጸልይ
ያደረገችው ይህንን ልማድ ከራሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ በማየት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዱ የጸለየውን
ጸሎት ሌላው ደግሞ ሲጸልይበት ፣ ያመሰገነውን ምስጋና ወስዶ ደግሞ ሲያመሰግንበት ፣ በተለመነበት ልመና
ድጋሚ ሲለመን በተደጋጋሚ ተጽፎአል፡፡ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ የሚሆነን በመስቀል ላይ ሆኖ የዳዊትን
መዝሙር የጸለየው የሃይማኖታችን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የጥበብ መገኛ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ
የጥበብ ባለቤት ፣ ራሱም ጥበብ ሆኖ እያለ ፣ አዲስ ንግግር መናገር ሳይሳነው ፣ አዲስ ጸሎት መጸለይ ሳያቅተው
በታላቅ ድምጽ ‹‹አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ?›› በማለት ሃያ አንደኛውን የዳዊት መዝሙር መግቢያ ቃል
በቃል ጸልዮአል፡፡ (መዝ. 21፡1) ፈጣሪ ሆኖ ሳለ የፍጡሩን ጸሎት ሳይንቅ ከጸለየ እኛ ፍጡር ሆነን እንዴት
የነቢያትን ጸሎት እንንቃለን?ጌታችን በትሕትና የዳዊትን ጸሎት በመስቀል ላይ እንደጸለየ ሁሉ እዚያው
መስቀል ላይ ሆኖ የጸለያቸውን ‹‹የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው›› እና ‹‹አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ
አደራ እሠጣለሁ›› የሚሉትን ሁለት ጸሎቶቹን ደግሞ የመጀመሪያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
ጸልዮአቸዋል፡፡ ሰማዕቱ በድንጋይ ተወግሮ በሚሞትበት ሰዓት ከጌታው የተማረውን ጸሎት ‹‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ
ነፍሴን ተቀበል›› ‹‹ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› በማለት ሲጸልይ ተገኝቶአል፡፡ (ሉቃ. 23፡
34፣46 ፤ ሐዋ. 7፡59-60) አንዱ የጸለየውን ጸሎት መድገም ማለት ይኼም አይደል?ከሁሉ በሚገርም ዝርዝር
ሁኔታ ሌሎች የጸለዩትን ጸሎት በድጋሚ በመጸለይ ምሳሌ የሚሆነን ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም የጸለየችው ጸሎት ነው፡፡ ‹ጸጋን የተሞላች› ተብላ የተመሰገነችው እመቤታችን ፣ እንግዳ የሆነ አዲስ
ድርሰት የመድረስ ጸጋ ሳያንሳት ፣ ለነአባ ሕርያቆስ ለነቅዱስ ኤፍሬም የተረፈው ጸጋዋን በትሕትና ሸሽጋ ቃል
በቃል የነቢዩ ሳሙኤልን እናት የሃናን ጸሎት ከነቢያት ጸሎት ጋር አጣምራ ደግማ ጸልያለች፡፡ የሳሙኤል እናት
‹‹በማዳንህ ደስ ብሎኛል›› እንዳለች እመቤታችን ‹‹መንፈሴ በመድኃኒቴ ደስ ይላታል›› ብላለች፡፡ ሃና ‹‹እንደ
እግዚአብሔር ቅዱስ የለም›› ስትል ድንግል ማርያም ‹‹ስሙም ቅዱስ ነው›› ብላለች፡፡ ሃና ‹‹የኃያላንን ቀስት
ሰብሮአል ፤ ደካሞችንም ኃይል አስታጥቋቸዋል›› ስትል ድንግሊቱ ደግሞ ‹‹ብርቱዎችን ከዙፋናቸው
አዋረዳቸው የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ አደረጋቸው›› ብላለች፡፡ ሃና በጸሎትዋን መጨረሻ ‹‹እንጀራን ጠግበው
ነበሩ ተራቡ ፤ ተርበውም የነበሩ ጠገቡ›› ስትል እመቤታችንም ‹‹የተራቡትን በቸርነቱ አጠገባቸው ፤
ባለጸጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው›› በማለት ደግማዋለች፡፡ (1 ሳሙ.2፡1-7 ፤ ሉቃ.1፡47-53) የቀሩት
ሌሎቹ ጥቂት ዐረፍተ ነገሮችም ከዕንባቆም ጸሎት እና ከዳዊት መዝሙራት የተውጣጡ ናቸው፡፡ጌታና ቅዱሳኑ
‹ያደረጉት አይቅርብኝ› የምትለው ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማድ ይዛ ‹የጻድቅ ሰው
ጸሎት በሥራዋ ኃይልን ታደርጋለች› የሚለውን በማሰብ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጸለዩና በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፉ
የቅዱሳን ጸሎቶችን ለቅማ አውጥታ ደግመን እንድንጸልያቸው ታደርገናለች፡፡ ጠቃሚ ጸሎት ነው ብላ
እስካመነችበት ድረስ እንኳን የጻድቃን ጸሎት ‹የወንበዴውም ጸሎት› አይቀራትም፡፡ከጌታ ቀኝ የተሰቀለው
ወንበዴ ‹‹ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ›› ብሎ የጸለየውን ጸሎትም ‹ለወንበዴ ልጆቼ
ሳይጠቅማቸው አይቀርም› ብላ ነው መሰል በቅዳሴ መከከል ‹‹ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ በከመ
ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕጸ መስቀል ቅዱስ›› (አቤቱ በመስቀል ላይ ሳለህ በቀኝህ
የተሰቀለውን ወንበዴ እንዳሰብከው እኛንም በመንግሥትህ አስበን) እያልን በዜማ እንድንለምን ታደርገናለች፡፡
(ሉቃ. 23፡42 ፤ ቅዳሴ ሐዋርያት)
ጌታችን ልጁን እንዲፈውስለት አማላጅ ከላከ በኋላ ‹‹ጌታ ሆይ ከቤቴ ጣሪያ በታች ትገባ ዘንድ አይገባኝም ፤
ቃል ብቻ ተናገር ልጄም ይፈወሳል›› ያለውን የመቶ አለቃ ታስታውሱታላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
የዚህ የመቶ አለቃ ንግግርም እንደ ዋዛ አንብባ አልተወችው፡፡ ልጆችዋ ምእመናንና ካህናት የጌታን ሥጋና ደም
ወደ ከመቀበላቸውና ቤት ወደ ተባለ ወደ ሰውነታቸው ከማስገባታቸው በፊት እንደ መቶ አለቃው ሁሉ
በትሕትና ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከረከሰችው ከቤቴ ጣራ በታች ትገባ ዘንድ አይገባኝም ፤
እኔ አሳዝኜሃለሁና በፊትህም ክፋትን አድርጌአለሁና... ሥጋህን ደምህን መቀበሌ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ››
እያሉ እንዲጸልዩ ታደርጋለች፡፡ (ሉቃ.7፡6)
ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጸሎት መጻሕፍት ቃል በቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱት ብቻ አይደሉም፡፡ ቋንቋ
እና የአገላለጽ ጥበብን ከመጽሐፍ ቅዱስ የተዋሱ ብዙ የጸሎት መጻሕፍትም አሉ፡፡ በእነዚህ የጸሎት መጻሕፍት
ላይ ጥያቄ የሚፈጥር አነጋገርና አገላለጽ ቢገኝ እንኳን ሰው ሊመዝናቸው የሚገባው በምንጫቸው በመጽሐፍ
ቅዱስ ሚዛንነት ነው፡፡ለምሳሌ በአንዳንድ የጸሎት መጻሕፍት ላይ ‹‹ጠላቴን እንዲህ አድርገው ፣ መንገዱን
ዝጋው ፣ እግሩን ቁረጠው ፣ ዓይኑን አሳውረው›› የሚል አገላለጽ ሲመለከቱ ግራ የሚጋቡ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ
ዓይነቱ ጸሎት ግን በመዝሙረ ዳዊት ‹‹አቤቱ፥ የሚበድሉኝን በድላቸው፥ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው። ጥሩርና
ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ። ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦
መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት። ነፍሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቈሉም ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይፈሩ ወደ
ኋላቸውም ይበሉ። በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የእግዚአብሔርንም መልአክ ያስጨንቃቸው።
መንገዳቸው ዳጥና ጨለማ ይሁን፥ የእግዚአብሔርም መልአክ ያሳድዳቸው በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ
ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥ ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና። ያላወቁት ወጥመድ ይምጣባቸው፥
የሸሸጉትም ወጥመድ ይያዛቸው በዚህ ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ።›› ከሚለው የዳዊት ጸሎት ጋር ተመሳሳይ
ነው፡፡ (መዝ. 34፡1)ይህ ዓይነቱን ጸሎት ስናገኝ ማሰብ ያለብን ጠላት ዲያቢሎስን ነው፡፡ ለሰው ከአጋንንት
ሠራዊት ሌላ ምን ጠላት አለው? ሰው የሚል ቃል እንኳን ቢገኝ ሰይጣን ሰውን መሣሪያ አድርጎ ወደ እኛ
እንደሚመጣ በማሰብ የአጋንንትን ፈተና ከኔ አርቅልኝ በሚል ሃሳብ ተርጉመን መጸለይ ያስፈልጋል እንጂ ቤተ
ክርስቲያን በሰው ላይ ክፉ አድርግ በሉ የሚል ትምህርት የላትም፡፡ ‹‹ሰይጣንም በሰው አድሮ ካልሆነ
አይመጣምና›› (ኢይመጽእ ሰይጣን ዘእንበለ ምስለ ሰብእ) እንዲል (ስንክ.) በመጨረሻ የምናየው ከመጽሐፍ
ቅዱስ የተወሰደ የጸሎት አካሔድ ‹ለአይኖችህ ፣ ለጆሮዎችሽ ፣ ለእግሮችህ ሰላም እላለሁ ...ወዘተ› እያሉ
የሰውነት አካልን እያመሰገኑ የሚጀምሩ የመልክእ ጸሎቶች ናቸው፡፡ ይህን ጸሎት የሚያዩ አንዳንዶች ሃሳቡን
ወደ ሥጋዊ መንገድ ለመተርጎምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመንቀፍ ምእመናንንም ለማሳቀቅ ይሞክራሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ አስተውሎ የሚያነብ ሰው ግን የሰውነት አካል ተመሰገነ ብሎ ወደ ሌላ ሃሳብ
አይሔድም፡፡በተለይም ለመልክእ ጸሎቶች መነሻ የሆነውን መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን የነበበ ሰው እነዚህ
ጸሎቶች እንግዳ አይሆኑበትም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ሥጋዊ ውበትን ሲደነቅ ስናገኝ መንፈሳዊ ትርጉም
እንደምንሠጠው ሁሉ በቤተ ክርስቲያንም መንፈሳዊ ቋንቋ የሰውነት አካልን እያነሣ ሲያመሰግን በብዙ ቦታ
ስናገኝ በመንፈሳዊ መነጽር መረዳት አለብን፡፡ እስቲ መኃልየ መኃልይን ሳንነካ በሌሎች መጻሕፍት መነጽርነት
ብቻ የመልክእ ጸሎትን እንመልከት፡፡ከራሱ ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ንግግር ብንጀምር ‹‹እናንተ የምታዩትን
ሊያዩ ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ወደዱ አላዩም ፣ ሊሰሙ ወደዱ አልሰሙም›› ካሉ በኋላ ‹‹ዓይኖቻችሁ
ስለሚያዩ ጆሮዎቻችሁ ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው›› ብሎ እርሱን ያዩ ዓይኖቻቸውንና ጆሮዎቻቸውን
አመስግኗል፡፡ ይህ ምስጋና በእኛ ቤት ቋንቋ ‹‹ሰላም ለአእይንቲከ›› ‹‹ሰላም ለአእዛኒከ›› (ለዓይኖችህ ጆሮዎችህ
ሰላም እላለሁ) ማለት ነው፡፡ ዓይን የሚመሰገነው በውበቱ ፣ ጆሮ የሚመሰገነው በቅርጹ ሳይሆን ስለሚያየው
እና ስለሚሰማው መልካም ነገር ነው፡፡ (ማቴ. 13፡16)
‹መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ ‹እግሮቻቸው› እንዴት ያማሩ ናቸው?›› የሚለው ንግግር ደግሞ ቃሉን
ለመስበክ የሚደክሙ ‹እግሮችን› ለማመስገን የቀረበ ምሳሌ ነው፡፡ (ሮሜ. 10፡15) የወንጌል መልክአ ማርያም
ተብሎ የሚጠራው ‹ያጠባሃቸው ጡቶችና የተሸከመችህ ማኅጸን የተመሰገኑ ናቸው› የሚለው ምስጋናም
(ምንም እንኳን ያቀረበችው ሴት በልቧ ውዳሴን በመፈለጓ የተገሠጸች ብትሆንም) ጌታችን ‹አዎን› ብሎ
ያጸናውና ‹ለጡቶችሽ ሰላምታ ይገባል ፤ ለማኅጸንሽ ሰላምታ ይገባል› ለሚለው የእመቤታችን ምስጋና መነሻ
ነው፡፡(ሉቃ.11፡28) የእመቤታችን ጡቶችዋ የሚመሰገኑት ለምን እንደሆነ መልክአ ማርያምን ሔደን
ስንመለከት ደግሞ ‹‹ድንግልናዊ ወተትን በአምላክ አፍ ውስጥ ላፈሰሱ ጡቶችሽ ሰላምታ ይገባል›› ሲል
እናገኘዋለን፡፡ በእርግጥም የሁሉ መጋቢ የሆነውን አምላክ የመገበች ድንግል ምንኛ ምስጋና ይገባት ይሆን?
በዚህም አነጋገር የመልክእ ጸሎቶች ከሥጋዊ ውበት ይልቅ መንፈሳዊ ክብርን ለመግለጽ ያለሙ መሆናቸውን
እንረዳለን፡፡ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና (ከመልክአ ኢየሱስ) አንዱን ለምሳሌ እንጨምር፡፡ ‹ሰላም
ለአእዳዊከ ጽቡረ እለ ገብራ ፤ በምራቀ አፉከ ቅዱስ አዕይንተ ዕውር ይፍጥራ›› ይላል ‹‹በተቀደሰው ምራቅህ
የዕውርን ዓይን ልትፈጥር ስትል ጭቃን ለለወሱት እጆችህ ሰላምታ ይገባል›› ማለት ነው፡፡ ይህም በዮሐንስ
ወንጌል ጌታ የዓይነ ስውሩን ዓይን ለማብራት ሲል በከበሩት እጆቹ ጭቃን መንካቱን በማድነቅ የተነገረ እንጂ
ስለ እጁ ብቻ በመናገር ላይ ያተኮረ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ የመልክእ ጸሎቶች ከአካልም አልፈው ሃሳብን
ያደንቃሉ ‹ሰላም ለኅሊናከ› (ለሃሳብህ/ሽ ሰላም እላለሁ) እያሉ ማለት ነው፡፡ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ንጉሥ
ዳዊት ‹በእጄም በቀል እንዳላደርግ ዛሬ የከለከለኝ አእምሮሽ የተመሰገነ ይሁን፥ አንቺም የተመሰገነሽ ሁኚ።›
ብሎ የናባልን ሚስት አቢግያን እንዳመሰገነው አይነት ምስጋና ነው፡፡ (1 ሳሙ. 25፡33) ዳዊት ግእዝ ቢያውቅ
ኖሮ ‹‹ሰላም ለኅሊናኪ ዘከልአኒ እም ተበቅሎ ፣ ለናባል ምትኪ ሶበ ፈጠንኩ እቅትሎ›› የሚል ይመስለኛል፡፡
(ናባል ባልሽን ልገድለው በፈጠንኩ ጊዜ ከበቀል ለከለከለኝ ሃሳብሽ ሰላም እላለሁ! እንደማለት ነው፡፡)
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ባሕር የሚዋኙ ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚቀኙ ፣ ሌላው ቀርቶ
(ተገቢ ባይሆንም እንኳን) እውቀት ተርፎአቸው በመጽሐፍ ቃል ‹በነገር የሚጎሻሸሙ ፣ የሚጨዋወቱ›
ሊቃውንት ያሉባት የወንጌል መፍሰሻ ናት፡፡ ርዕሳችን ስለ ጸሎት መጻሕፍት ስለሆነ እነዚህን ብቻ ለምሳሌ
አነሣን እንጂ ጊዜ ቢኖረን ኖሮ ‹‹አአትብ ወእትነሣእ ... እመኒ ወደቁ እትነሣእ ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት
እግዚአብሔር ያበርሕ ሊተ ...›› (... ብወድቅ እነሣለሁና በጨለማም ብመላለስ እግዚአብሔር ብርሃን
ይሆንልኛል...) ብሎ በነቢዩ ሚክያስ መዝሙር ስለሚጀምረውና በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሚራቀቀው የሌሊቱ
ጸሎት ስለ ሰዓታት ባነሣን ነበር፡፡ (ሚክ. 7፡8 ፤ መጽሐፈ ሰዓታት መጀመሪያ)ጊዜ አጣን እንጂ ‹... ኢይበል ፈላሲ
ዘገብአ ኀበ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እም ሕዝቡ... › (ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ። በእውነት
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል አይበል...) ብሎ በነቢዩ ኢሳይያስ የትንቢት ቃል ስለሚጀምረውና እስከ
ፍጻሜው ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ማዕበል ስለሚያማታን ቅዳሴያችን ብዙ በተናገርን ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉን
እንዳንተርክ ጊዜ ያጥርብናል፡፡ (ኢሳ. 56፡3 ፤ መጽሐፈ ቅዳሴ መግቢያ) ከራሳችን አመንጭተን የምንጸልየው
የእኛ ጸሎት በተበታተነ ሃሳብ የሚጸለይ ፣ በአብዛኛው ምድራዊ ፍላጎቶቻችን ላይ ብቻ ያተኮረ ፣ እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነ ጸሎት መሆኑን የተረዳችው ቤተ ክርስቲያናችን በተመሥጦ የተጸለየውን ፣
መንግሥቱንና ጽድቁን በመፈለግ ላይ ያተኮረውን ‹የፈቃዱን ምሥጢር በሚያውቁት› እና ‹እንደፈቃዱ
በሚለምኑት› ቅዱሳን የተጸለየውን ጸሎት እንድንጸልይ አስተምራናለች፡፡ (1 ዮሐ. 5፡15 ፤ ኤፌ.1፡9) ሰው
እንደፈለገ የሚናገርበት የጸሎት መድረክ ብዙ መዘባረቅ ፣ ስሜታዊነት ፣ ሥጋዊ ሃሳብ እንደሚሠፍንበት
በመረዳት የጸሎት መጻሕፍትን በብዙ ድካም አዘጋጅታ የሠጠችን የዚህች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን
ልጆች ስላደረገን ስሙ የተመሰገነ ይሁን!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
henoktsehafi@gmail.com
ሰኔ 2007 ዓ.ም.
ኩዌት

ምኑ ነው ስህተቴ ''!!
(ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ)
===========
ተሳሳትሽ አትበለኝ የቱ ነው ስህተቴ፤
ጥበብ ነው ማርከሻ የብዕር ጥይቴ።
አዎ መንጋማ አለ ከጥንት መሰረቱ፤
እየሱስን አስረው በርባንን ሲያስፈቱ።
በኔ ዘመን
የመንጋ ፍርድ ነው ሀገሬን የፈታት፤
አዋቂ ዝም ብሎ መንጋ እየፈተታት።
በድንጋይ በርሚል ውስጥ ሽ ድንጋይ ቢቀቀል፤
ሽ ዘመን ተጥዶ እልፍ አመት አይበስል።
አገር ተረክቦ በሰፈረ የኮራ፤
የመንጋ ፍርድ አይደል ያበቃን ለተራ።
የቱ ጋ ነው የሳትኩ አርመኝ መምህሩ፤
ምላስክን አጥፈኽው ሞክር በብዕሩ።
ዘመን የሰጠው ቅል ድንጋይ ቢሰብር ጣሪያ፤
ማዕዘን ተደርጎ አይሆን ለቤት መስሪያ።
ሰውነት ነው ልኩ የሰው ሚዛን ፍርዱ፣
አዋቂ እንዲበይን መንጋዎች ይውረዱ።
እላለው
በመንጋ ተፈጭቶ በመንጋ ተጋግሮ፤
እልፍ ጾም አዳሪ ወና ነው ጉረሮ።
ቤት መምታት ቤት መድፋት ስንኝ መቋጠሩ
ጥበቡ ቢያቅተው፤
እያፈረሰ ህዝብ እያስደደ
አገሩን አመሰው።
እኔ ይሄንን ሰው፣
ሌላ ምን ልበለው፣
መንጋነትም ሲያንሰው።
በባዶነት ሙሌት በዘር እብሪት ታስሮ፣
ከጥበብ ጓዳ ውስጥ ከሰውነት አጥሮ።
አበውን ሲያሰደድ ሲያርድ ሲያጎሳቁል፣
አንተም መንጋ ካልሆንክ መቼም ሰው ነው አትል።
እና ምኑ ላይ ነው ብዕሬ የሳተች፣
ብሔር የነቀፈች ህዝብን ያዋረደች።
በሞቴ የመንጋው ጠበቃ
አንተም ሰው ሁንና መንጋነትህ ይብቃ"
ባለፈ አመት ክረምት ፣ ዛሬ አይታረስም
ጀግኖች አይጠሩም ፣ በፈሪዎች ስም፡፡
ሼር ይደረግ
ስም ብቻ ምን
1.

ሊጠቅመኝ 
መጠሪያ ብቻ
ከሆነኝ እኔ
-

ክርስቲያን መባሌ፣
በግብሬ ካላሣየሁት-

ካልተዋሐደ ከአካሌ፣
በጨለማ መቅረዝ
ሆኖኝ እግሬን
-

ከእንቅፋት
ካላዳነ፣
 

ስሙ ብቻ ምን
ሊጠቅመኝ ምን-

ሊሠራልኝ ነውለኔ፣
በአርባ ቀኔ ስጠመቅ -

ክርስቲያን ተብዬ
ልጠራ፣
በእምነት ዳብሬ
እንዳድግ መልካም -

ፍሬን እንዳፈራ፣
ሥነ-ምግባሬ መጨነቄን-እንዲያሳይልኝ አጉልቶ፣
ክርስትናዬን እንዲናገር-በደረስኩበት ሁሉ ገብቶ
የተቀበልኩት ልጅነት-በእኔነቴ ዙሪያ አብርቶ፣
ለዚህ ነበር ምክንያቱ-በጥምቀት ክርስቲያን መሆኔ፣
ከኃጢአቴ ነጽቼ-ልጁ የተባልኩት እኔ፡፡
በአነጋገር በሥራዬ-ክርስትናዬን ካላሣየሁ፣
ጌታዬ በሰጠኝ መክሊት-አትርፌበት ካልተገኘሁ፣
እንደተዘናጋሁ ካለቀ-ከተጨረሰዘመኔ፣
ክርስቲያንመባሌ ምን ሊረባኝ-ምን ሊጠቅመኝ ነው ለእኔ፡፡
//
ይድረስ ለፈጣሪ መንበረ ጸባዖት
ከትልቁ ሥፍራ ከሰማዩ መንግሥት
ፍርድ ሳይዛነፍ ከሚፈጸምበት፡፡
 ላኪው በምድር ላይ ግፍ የደረሰብኝ
ጐስቋላ አገልጋይህ ደካማው ባሪያህ ነኝ፡፡
ሳጥናኤል የሚሉት የቀድሞ ጠላቴ
 ቂሙን ሳይዘነጋ እንደ አዳም አባቴ
 ከገነት ሊያስቀረኝ ቀጥቅጦ ጥሎኛል

በአፍና አፍንጫዬ ደግሞም በጆሮቼ


መርዙ ተጠቅጥቆ በየብልቶቼ
አውጣኝ እያልኩህ ነው እባሕር ገብቼ፡፡
ደካማ ነኝና ራሴን አልቻልኩም
ለመታገል ሞከርኩ ከእጁም አልወጣሁም
ፍርድ ሰጭው ዳኛ ችግሬን ቃኝተኸው
 መፍትሔ እንድትሰጠኝ ወዳንተ እጮኻለሁ፡፡
 ግጥማዊ ተውኔት፨

2.አባ ይፍቱኝ
መስቀሉን ያሳልሙኝ
ልጄ የተባረክህ
እማይሰራ ኃጢአት
እግዚአብሔር ይፍታህ
እስኪ ጠጋ በለኝ
ክርህን አሳየኝ።
አንገትህን ልየው
ማተቡን አስረሃል?
እንዴታ አባቴ
ማተብ ምልክቴ
መቼ ትለያለች
በጭራሽ ካንገቴ
ማህተቤ እኮ ናት
እጅግ የማከብራት
ክርስቲያን መሆኔን
በጌታ ማመኔን ምመስክርባት
የውስጥ እምነቴን ለሰው ማሳይባት
መናገሪያ ቃሌ
ይችናት መስቀሌ
በልቤ ያለውን
ውስጤ የሚያምነውን
እንዴት አሳይ ነበር
ማተቤ ከሌለች
እንዴት ልመስክር
አባ ማተቤማ ምስክሬ እኮናት
የመጣው ይምጣ እንጂ ካንገቴ አለያት።
በማለት ሲናገር ለንስሐ አባቱ
አቶ ግብዝነት ሐይማኖት ባንገቱ
አፍ የላትም ብሎ በማተብ ሲደበቅ
ድንገት አፍ አውጥታ "አ" ከማለትዋ
ዝም በይ ብሎ በጁ አፍዋን ሊይዝ ሲል
መናገር ቀጠለች ማተብ የእውነት ቃል

ይቀጥላል....

....የቀጠለ

አባ እኔን ይስሙኝ
ከልብዎ ያድምጡኝ
ሰዎችን ሳይፈራ እግዜርን ሳያፍር
በስንቱ ሰዎች ፊት ሐሰት ሲመሰክር
እኔን እያሳየ ስንቱን ሰው አሞኘ
ብዙ ታግሻለሁ አንገቱ ላይ ሆኜ
በድፍረት ሲያታልል የሐይማኖት አባቱን
ዛሬ ግን አልቻልም ልናገር እውነቱን።
ያለሁበት ሥፍራ ይህ ደንዳና አንገቱ
መካከለኛ ነው ለልብ ላንደበቱ።
ስለዚህ ልቡ ላይ ሲያስብ ሚውለውን
ደግሞም ባንደበቱ የሚናገረውን
እመሰክራለሁ ያየሁትን ሁሉ
በኔ ተሸፍኖ እንዳይጠፋ ዉሉ
ሐይማኖትን ትቶ ቅዱሱን ያምላክ ቃል
ከንቱ ሐሳብ ሲያስብ ራሱን ሲያታልል
አንዱን በሌለበት በሐሰት እያማ
ሌላውን ባፍ ቃል ክፉኛ እያደማ
ሲወረወር ቀስቱን የሾሉ ቃላቱን
በመርዝ አንደበቱ የነደፈው ስንቱን
ውስጡ ክፋት እንጂ ወንጌል ካልተሞላ
ያምላክን ቃል ትቶ የሰውን ከበላ
እንዴት እሆናለሁ የእምነት ምልክቱ
መሸፈኛው እንጂ እንዳይታይ ፊቱ።
ይቀጥላል.....

የቀጠለ...
ማተብ ሚስጢሩ እርስዎ ያስተማሩት
የላይ ምልክት ነው በልብ ላመኑት
ከቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳኢ
እንደ ተማረነው ወግ ከአበው መጻኢ
እውነተኛው እምነት በልባቸው ሆኖ
ለፈጣሪ ሲታይ በልበ ተአምኖ
ማተብ ግን ለሰው ነው ልቡን ለማያይ
የውስጣችን እምነት በተግባር እስኪታይ።
ይህ ነበር እውነቱ የኔ ጥቅም ለሰው
ወንጌሉን እንዲኖር ሁሌ ላስታወሰው።
ዛሬ ግን ብዙዎች ይህን ሳይረዱ
ባንገት እያመኑ በምግባር የካዱ።
ውስጣቸውን ዘግተው ከውጭ እያሰሩኝ
መገለጫ ሳይሆን መሸፈኛ አረጉኝ።
ይህም ሰው አባቴ ከእዚህ አንዱ ነው
በኔ ተሸፍኖ ውስጡ ግን ሌላ ነው
እርሱ እንደ ነገርዎት ብዙም አይወደኝም
ከነመኖሬ እንኳ አያስታውሰኝም
ለባለንጀሮቹ ሲናገር በሐሰት
ምንም አይመስለውም በስሜ ሲገዝት።
እኔን ያየ ሁሉ ክርስቲያን ሽፍኜበት።
ብዙ ሰው አታሎአል አባይ ነው ምላሱ
ውስጡን ያሳልሙልኝ ልቡን ይቀደሱ።
ምግብ ቤት ነው ተብሎ ከውጭ ከተጻፈ
እንጀራ ይገኛል ወደ ውስጥ ላለፈ።
እንዲሁም አንገት ላይ ማተብ መታስሩ
ወደ ታች ወደ ልብ ጣቱን መቀሰሩ።
ውስጥ ያለውን ሊያሳይ መሆኑን ንገሩት
ክርስቶስን ለብሶ እንዲኖር ምክሩት።
ብዙ ሰው አታሎአል አባይ ነው ምላሱ
ውስጡን ያሳልሙልኝ ልቡን ይቀድሱ።

ተፈፀመ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መነባንብ፨

3.የብርሃን እናት
የብርሃን እናት የሁሉ አስታራቂ
እንሆ ምስጋናሽ ከእኛም እንዳትርቂ
ስምሽ ይጣፍጣል ከማር ከወተት
ተብለሻልና የአምላክ እናት።
ማህደር ብርሃን ሃመልማለ ወርቅ
የመወለደሽ ጥበብ እንደምን ይረቅ
በሄዋን ተዘግቶ የነበረው በር
ባንቺ ተከፈተ ምስጋናሽ የከበር።
ጌታ የመረጠሽ ለክብር ለፀጋ
ካንቺ ተወለደ በድንጋሌ ስጋ
ሰማይና ምድርን ያፀና በቃሉ
አምላክ አንቺን መርጦ ከደናግል ሁሉ
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የከተመብሽ
እፁብ ድንቅ እመቤት ድንግል አንቺ ነሽ።
ጡቷን እያጠባች አምላክን ታቅፋ
ምድራዊ ችግርን ስንቱን አሳልፋ
ይኸው ትኖራለች ክብሯን ተጎናፅፋ።
የምህርት አማላጅ እመቤቴ ሆይ
እንመስልሻለን በወርቅ ሙዳይ
አንቺን ያመነ ሰው ይኮነናል ወይ?
አማላጅ ነሽና ለሃጥአን ሁሉ
እኔንም ሰውሪኝ ከመከራ ሁሉ።
ነቢያት በትንቢት የተናገሩልሽ
የሰማይ መላዕክት ስምሽን የሚያገኑሽ
ብፅዕት እያሉ የሚያመሰግኑሽ
እነማን አፈሩ ያመኑ በስምሽ?
ምንም ተስፋ የለኝ አንቺውነሽ እምነቴ
አማልጂን ከልጅሽ ክብርት እመቤቴ
እኛን እንዲያድነን ወገኖችሽ ነንና
ቃሉም አይታበይ ፍርዱም የተቃና
የሰጠሽ ቃልኪዳን አይሻርምና።
ደስ ደስ ይበልሽ ቤዛዊተ ዓለም
አምላክን ስለወለድሽ በቤተልሔም
ክብርን አድሎሻል ለዘለዓለም።
ሰማይና ምድርን የማይችሉትን
ወልደሽ አሳድገሽ መድሃኒዓለምን
አዳምን ለማዳን ቃልኪዳን ገባና
ቅድስተ ቅዱሳን አንቺን መረጠና
ስጋሽን ለበሰ ምድር እንድትፀና።
ዓለምን ለማዳን ከሰማያት ወርዶ
መለኮት ከስጋሽ ፍፁም ተዋሕዶ
ነፃነትን ሰጠን ለኛ ሲል ተዋርዶ።
ወደአንቺ ተማፀንኩ ልመናዬ ፀንቶ
የሰውነቴ ሃጢያት በእኔ ላይ በርክቶ
መሳፍንት እርኩሳን እንዳይቀርቡ ከፊቴ
እንዳይ በረታብኝ በኔ ላይ ጠላቴ
አስታግሽልኝ አንቺ ክብርት እመቤቴ።
ይቀጥላል.....

....የቀጠለ
አምላክን የወለድሽ የሰማዩን ጌታ
ምህረትን አሰጭን ያድለን ይቅርታ።
በስምሽ ሲያጠጣ ሲጓዝ በበርሀ
በላይሰብ ጀኘኘአኸ በአንድ ጥሪኝ ውሃ።
እናትና አባትሽ ልጅ በማጣታቸው
ያለቅሱ እንደነበረ ወደ ፈጣሪያቸው
የወለድን እንደሆን ወንድም ሆነ ሴት
እንሰጣለን አሉ ለእግዚአብሔር ቤት።
ያናገራቸው ይህ ነበር ትንቢቱ
ቀድሶ ሰጣቸው ለዘጠኝ ወር ቤቱ።
እናትና አባትሽ ስመው ሳይጠግቡሽ
ለስለት ወሰዱሽ በሶስት ዓመትሽ
በክብር ስለኖርሽ በቤተመቅደስ
ገብርኤል ሲያበስርሽ የመውለድሽን ዜና
ፍፁም አደነቀው ዓለም ያንቺን ዜና
የመላእክት እህት የሰው ልጅ እናት
በገብርኤል ሰላምታ እናመስግናት
በድንጋሌ ስጋ አምላክን ስትወልድ
ኮከቡን አዩና ከምስራቅ ሲወርድ
ይቀጥላል...
....የቀጠለ
ተነስተው ተጓዙ ሄደው ለመስገድ
ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱን አይተው
ወድቀው ሰገዱለት ከመሬት ተደፍተው
ለኛ በመወለዱ በጣም ተደስተው
ኪሩቤል ሱራፌል የጋረዱልሽ
የብርሃን ደመና ዙርያውን ከቦሽ
መላዕክት ወርደው የሰገዱልሽ
አፁብ ድንቅ እመቤት ማርያም አንቺ ነሽ።
የምንመካብሽ መከታ ጋሻችን
አንቺ ስለሆንሽ ጠላት ድል መንሻችን
እንደ እሳት ይነዳል ባንቺ ላይ ፍቅራችን።
ብዙ መምህራኖች መስክረውልሻል
የአምላክ ካህናት ያገለግሉሻል
እንደ መላዕክትም ይዘምሩልሻል።
ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፈቀደ እግዚአብሔር
አዳምን ከሲኦል እንዲያወጣው ወዶ
እንደኛ ሰው ሆነ ስጋን ተዋህዶ
በፍቅሩ ጎበኘን ልጁ በምህረት
ዘመን አስቆጥሮ ዳግመኛ ልደት
ለዓለም ቤዛ ሆነ ስረ መለከት
ስሟ የከበረ ከሁሉ በላይ
ታቦተ ፅዮን ናት ንግስተ ሰማይ
ያገለግሏታል አእላፍ መላዕክት
መሆኗን ሲያጠይቅ የሰማይ ንግስት
ምን ያጠራጥራል አማላጅነቷ
ማርልኝ ስትለው ቆማ በጉልበቷ
ልጄ ወደጄ ሆይ ስለ እናትነቴ
እማፀንሃለው ባጠባሁህ ጡቴ
የምትል ነች ድንግል ቸር አማላጃችን
ለስጋችንም ቢሆን እንኳን ለነፍሳችን
ከፅኑ መከራ የምታድን ናት
እንግዲህ ለክብሯ እንስገድላት።×2
ተፈፀመ ዝንቱ መነባንብ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

4.እሰይ ተወለደ
፨፨፨፨፨፨፨፨
ለአዳምና ዘሩ ቃልኪዳን ገብቶለት
ይኸው ተወለደ ቃሉን ጠብቆለት
ክብሩን ዝቅ አድርጎ አምላክ ሰው ሆነለት
ሁሉን አዘጋጅቶ አሟልቶ ሲፈጥረው
በለስ እንዳይበላ አዳምን ቢያዘው
ሴጣን በተንኮሉ መጣና አሳተው።
አዳም አዳም እያለ አምላኩ ቢጠራው
አቤት አለ አዳም የአምላኩን ጥሪ ደጋግሞ ቢሰማው
ሁሉን ስላወቀ ከወዴት ነህብሎ ደግሞ በጠይቀው
የሆነውን ሁሉ አንዳችም ሳያስቀር አውጥቶ ነገረው።
አምላኩ ሲቆጣው በጣም ሲያዝንበት
አዳም ተፀፀተ ጥፋቱ ገብቶት
እርሱን ማሳዘኑ በደሉ ተሰምቶት።
እንዲህ አስከፍቶት እንዳይቀር በድሎ
ሱባኤ ሲጀምር ሊታርቀው ብሎ
ከይሲው ሰልጥኖበት በገብርኤል ተመስሎ
በፀሎቱ ተግቶ ሱባኤ ሊጨርስ 5 ቀን ሲቀረው
ዛሬ እንደገና ዲያብሎስ መጣና አዳም አዳም አላው
ይበቃህና ውጣ አምላክህ ሰምቶሃል ብሎም አቋረጠው
ድል በመነሳቱ ዳግምበዲያብሎስ
አምላኬ አምላኬ እያለ ሲያለቅስ
እንዲያ ተንሰቅስቆ ደም እምባ ሲያፈስ
አለሁልህ አለው አዳም ሆይ አታልቅስ
አዳም ሲያቅተው ሰይጣንን ማሸነፍ እርሱ ተመልክቶት
እንኳን ደስ አላችሁ ይኸው ተወለደ ዘመኑን ቆጥሮለት
ለአዳምና ዘሩ ከልጅ ልጅህ ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለት
ሊያስተምረን ወዶ በታላቅ ጥበቡ ሰይጣንን ድል ነስቶት
እሰይ ተወለደ አሁን ደስ ይበለን
በቃሉ መሰረት አምላክ ሰው ሆነልን
ባጉል ምኞት ወድቀን እኛ እሱን ለመሆን
ደስ ይበለን ብሎ እርሱ እኛን ሆነልን
እሰይ እንበል እስቲ እሰይ ተወለደ እኛን ሊታደገን
ወደ ቀድሞ ክብርም ዳግም ሊመልሰን
ይህው ተወለደ አምላክ ሰው ሆነልን።

5.፨ያኔ ጥንት ነበረ፨


በዱር በገደሉ በዓለም ዙርያ ሁሉ
አምላክ ይወለዳል ብለው ተናገሩ
የነቢያት ተስፋ የነበለአም
አምላክ ተወለደ መድሃኒዓለም
ያኔ ጥንት ነበር...
ይወለዳል ሲሉ በመንፈስ ሲመሩ
አምላክ አዶናይን ለማየት ሲጥሩ
እንደው ኩርምት ብለው በተስፋ ሲኖሩ
ድንግል ትፀንሳለች ብለው ሲናገሩ
ቀናትን ሲቆጥሩ ሳምንታት ሲሠምሩ
ሳምንታት በግንድ ላይ ወራትን ሲሠሩ
ወራት ተቀናጅተው ዓመትን ሲሰጡ
ዓመታት ተቆጥረው ዘመናት ሲመጡ
እናያለን ሲሉ ለማየት ሳይበቁ
በመንፈስ ሲሰክሩ እንዲውል ሲሳለቁ
ያኔ ጥንት ነበር....
ያኔ ጥንት ነበር በመንፈስ መሰከሩ
አምላክ ይወለዳል ብሎ መዘከሩ
በርቀት ተሳልሞ ለዓለም ማብሰሩ
ያኔ ጥንት ነበር የመውደቅ ሚስጥሩ
ሃጢአትን መፀነሱ የመውደቅ ሚስጥሩ
ሃጢያትን መፀነሱ ሞትንም መውለዱ
ከገነት ተባሮ እንዲያው መዋረዱ
ፀጋውን ተገፎ በለስ ማገልደሙ
ያኔ ጥንት ነበር...
አዳምን ሊጎበኝ አምላክ መጣራቱ
አዳም አዳም አዳም ብሎ መፈለጉ
አትብሉ ያልኩህን በላህው ማለቱ
አዳምን በመፍጠር እንዲያው መፀፀቱ
አዳምም አዘነ በሔዋን ፈረደ
ሔዋንም አዘነች እባቡ ነው አለች
እባብ ተረገመች አፈራ ባይሆናት
አዳም ተባረረ ሄዋን አለቀሰች
ምድር ተረገመች እሾህ አበቀለች
አቤት ያኔ ነበር ያኔ ጥንት ነበረ
አዳም መበደሉ ሰዎችን ለውድቀት ለሞት መደረጉ
ያኔ ነበር ፅንሱ ሰዎችን ለሽንፈት ለሞት መፈለጉ
ዛሬ ግን ዛሬ ያ የጥንቱ ቀረና
እራሱን አዋርዶ አዳም ከበረና
ሲወለድ በቤተልሔም በነብዩ ተፅፎአልና
አምላክ ተወለደ በከብቶች መና
ታሪኩ ሲተርክ የሰማህ ወንድሜ
ራስክን መርምረው ና ይልሃል ዛሬ
አቤት ያኔ ጥንት ነበር....
ያኔ ጥንት ነበር የአዳም ውድቀቱ
ዛሬ በክርስቶስ ሕይወትን ማግኘቱ
ዛሬስ እኛ ወገን
የያኔ የጥንቱ ትተን ለንስሐ ቀርበን
ስጋውንም በልተን ደሙንም ጠጥተን
በድያለሁ ብለን ከፊቱ ላይ ወድቀን
መመለስ ይሻላል ክርስቶስን ብለን
መመለስ ያሻል ኪዳነ ምህረትን ብለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
ልደቱ ልደታችን ነው
መልካም በዓል

6.እምነቴን አልክድም
ሃይማኖት አንድት ናት የሕይወት ጎዳና፣
ጻድቃን የሄዱባት መንገዷ የቀና፣
ይህቺ ናት እምነቴ የሰጠኝ ክርስቶስ፣
ከአበው የአገኘዋት እምዬ ኦርቶዶክስ።
ቢርበኝ ቢጠምኝ ዘመድ እንኳ በአጣ፣
ክፉውን አልፈራም የመጣው ቢመጣ።
መስቀሉ ሃይሌ ነው አለ በልቤ ላይ፣
እናቴም ማርያም ናት አገሬም በሰማይ።
የአንገቴ ማህተም የአሰርኩት ጥቁር ክር፣
ስለ ተዋሕዶ ይናገራል ምስጢር።
እናም አልበጥስም ማኅተቤን ከአንገቴ፣
ብኩርናዬ እኮ ናት ኦርቶዶክስእነቴ።
የደሙን መሰረት ተዋሕዶን ጥዬ፣
እንደት ፍልስፍናን ልመን እውነት ብዬ።
የመሠረተውን ማንም ሰው ተነሰቶ፣
እንደት ይታመናል ፍልስፍና ከቶ።፡
ሃይማኖቴን ክጄ ገነትን ከማገኝ፣
ኦርቶዶክስ ሆኜ አምላክ ይኮንነኝ።
እምነቴን ከምክድ ለገንዘብ ለእንጀራ ፣

ይቅርብኝ መክበሩ ስሜም አይጠራ፣


ጓዳዬ ሳይሞላ ኑሮየ ሳያምር፣
ከአባ መቃብር ላይ ከዋሻው ልቀበር፣
ነፍስ ያስምራልና የቃል ኪዳኑ አፈር፡፡፡
በክብር ከምለብስ የሳኦልን ካባ፣
ሌጦው ይሻለኛል የአባቶቼ ዳባ።
ከእነርሱ አልላይም ማንም ሰው አይለዬኝ፣
የስባአር አጽማቼው እሾህ ሆኖ ይውጋኝ።
ያአመንኩት እውነት ነው አልጠራጠርም፣
እሞታለሁ እንጂ እምነቴን አልክድም።
ከሰማእታቱ ከጻድቃኑ ሕይወት፣
ይሄን ነው ያማውቀው ስለ ስሙ መሞት።
ኢየሩሳሌም (ተዋሕዶ) ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ። ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤
(መዝ ፻፴፯፥፭)

7.የፈጣሪ ችሎት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አባ ተቀምጠው ከሾላ
ለሊት አድርሰው ምህላ
ሲጠባበቁ ፅድቂቱን
ሲኖሩ ሲኖሩ አንድ ቀን
ያባን ዛፍ ላይ መኖር
ሽፍቶቹ ተረድተው
ጠጋ አሉ ከሥፍራቸው
አባም በጥርጥር
ዓይናቸው ሲማትር
አባ አባታችን
አንድ ገዜ ይስሙን
የቃየል መንፈስ እየተከተለን
አንዳች ሳንበደል
ብዙ ነፋስ አጠፋን
ግብራችንን ትተን
ንስሐ ሰጥተውን
ከራሶት እንድንሆን
ፍቃዶት ይሁነን!
አባም በተራቸው
የፈጣሪ ጥሪ እየገረማቸው
እንደዚህ አሏቸው
እኔ ካለሁበት
መራሩ ምግቤ ነው
የአራዊቱ ዜማ
ጣዕመ ዜማዬ ነው
እንደኔ ለመሆን
ፍፁም ከሻታችሁ
የጠራችሁ አምላክ
ፅናቱን ይስጣችሁ።
8.፨ትንቢተ ዮናስ፨
ክፍል ፩
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በሕዝቡ መካከል አመጽ ስለ ጸና
በጣም ተቆጥቼ አዝኛለሁ እና
ይህንን ለነነዌ ንገራት በአዋጅ
አለና ለዮናስ ለአሚታይ ልጅ
እግዚአብሔር አዘዘው እንዲሄድ በቶሎ
ዮናስ እቢተኛው አሰበ ኮብልሎ
ከአምላኩ ተደብቆ አምልሎ ሊጠፋ
ወደ ተረሲስ ሲጓዝ የሄደ ወደ ያፋ።
ዋጋ ክፍልና ከመርከብ ተሳፍሮ
እያጉረመረመ ባሕሩን ተሻግሮ
ዮናስ ተደብቆ ሲሄድ በግስገሳ
ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ማዕበል ተነሳ
ታላቅ ሞገድ ሆነ ባሕሩ ተቆጣ
መርከበኞች ፈሩ ታላቅ ሽብር መጣ
መርከቡ እንዲቃለል እናድርግ እያሉ
አንስተው ብዙ ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉ
ባህሩም ባሰበት በጣም ተናወጠ
መረከቡ መሰለ የተገለበጠ
ሰው ሁሉ ተነሳ ጸሎት ለማድረስ
ይኽ ሁሉ ሲሆን ተኝቷል ዮናስ
ወደ ዮናስ ሄዶ የመርከቡ አለቃ
ቀሰቀሰው እና ከእንቅልፉ ሲነቃ
እግዜር እንዲያድነን ከዚህ ክፉ ጥፋት
ተነስ ጸልይ አለው ይብቃህ ማንቀላፋት
በመርከቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ተሰብስበው
ተመካከሩ እና ቢናገሩ አስበው
አለው ኃጢአት ሰርቶ ከእኛ ጋር የመጣ
ለይተን ለማወቅ እንጣጣል ዕጣ
አለዚያ አንድንም ስለተባባሉ
ተሰባሰቡና ዕጣ ቢጣጣሉ
እውነትም እንዳሉት አጥፊው ሰው ታወቀ
በእንቢተኛው ነብይ በዮናስ ወደቀ
በዮናስ ተረዳና እጁ እንደ ተያዘ
ያጠፋውን ጥፋት ገልጦ ተናዘዘ
ምነው ባትመጣ ተጣልተክ ከጌታ
እየው መርከባችን እንደሚንገላታ
ቁጣውን እንዲታገስ ለማግኘት ጸጥታ
በል አንተው ፍረደን ምን ይበጃል ቢሉ
ዮናስ መለሰና እዚህ ያለ ሁሉ
ስለምን ይጠፋል በእኔ የተነሳ
ወደ ባሕር ጣሉኝ አለብኝ አበሳ
ተመልከቱ እንሆ ስራውን ዐወቀ
ጥፋቱን ገለጠ ይኽው መች ደበቀ
እሱ ከፈረደ መልሶ በራሱ
ምን እናድርግ ብለው ሊጥሉት ተነሱ
ከደሙ አንጻን ሲሉ ለእግዜር አመልክተው
ወደ ባሕር ጣሉት ዮናስን አውጥተው
በዮናስ ላይ ኖር የመጣው ይህ ጥፋት
ባሕሩ ጸጥ አለ ልክ በዛው ሰዓት
ይቀጥላል.....
ትንቢተ ዮናስ
ክፍል ፪
ዮናስም ተውጦ በእግዚአብሔር ፍቃድ
ሶስት ቀን ሶስት ለሊት ሊያድር በዓሣ ሆድ
ተቀይመህ ኖረህ ከላይ ብትቆጣ
እንዲህ ያለ መአት በራሴ ላይ መጣ
የባሕሩ ሞገድ እኔን አዋከበኝ
ውኃና ጨለማ ሲኦልም ከበበኝ
እያለ በአሳ ሆድ ዮናስ ሲቀመጥ
አምላኩን ለመነው በመለማመጥ
የታዛዥነትም ጠባይ እያሳየ
አዝኖ ተጸጽቶ ከልቡ ጸለየ
ምንጊዜም ቢቆጣ ነውና መሓሪ
ፊቱን መልሶለት ታረቀው ፈጣሪ
ዓሣውም ዮናስን ውጦ ሳያስቀረው
ከባሕር ተፋና መሬት ወረወረው
ይቀጥላል.....
ትንቢተ ዮናስ
ምዕራፍ፫
ይህንን የኔን ቃል ስማና በቶሎ
ሄደህ ለነነዌ እንድትነግራት ብሎ
ደገመና እግዚአብሔር ዮናስን አዘዘ
ነነዌ ሊገባ ዮናስም ተጓዘ
ድምጹን ከፍ አድርጎ ነቢዩ ዮናስም
ከዛሬ ጀምሮ አርባ ቀን ድረስ
ነነዌ ጠፊነች ከስር ተገልብጣ
አለና ለፈፈ የእግዚአብሔርን ቁጣ
ሳያንገራግሩ ሁሉም ቢለምኑ
የነነዌ ሰዎች ተጨንቀው አዘኑ
ከትልቅ ጀምሮ ሕፃኑ ድረስ
ሕይወቱ የቆመች በሥጋ በነፍስ
ሰውም ሆነ እንስሳ ይቀበል ንስሐ
ፍጡር ሁሉ ይጸልይ ይጹም ከእህል ውሃ
ሁሉም ከልብ አዝኖ ማቅ እየለበሰ
ከክፉ ወደ ደግ እየተመለሰ
መቼም ወሰን የለው የእግዚአብሔር ምሕረቱ
ይጸልይ አለና ይለምን በብርቱ
ንጉሡ አሳወጀ ከነ መኳንንቱ
የነነዌ ሰዎች በእውነት ከልቦና
መፀፀታቸውን እግዚአብሔር አየና
ፍጡር ቢለምነው እምባ እያፈሰሰ
ምሕረቱን አውርዶ መአቱን መለሰ።
ይቀጥላል...
ትንቢተ ዮናስ
ምዕራፍ ፬
የተናገረው ቃል ስላልተፈጸመ
ዮናስ ተቆጥቶ እያጉረመረመ
እንደዚህ እያለ ጸለየ ወደ አምላከ
እኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክ
አሰብህ በታዘኝ ይህንኑ አውቄ
ወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄ
ምሕረት የበዛ መሓሪና ታጋሽ
በደል የምትረሳ ከቁጣ ተመላሽ
የቁጣህን ያህል ምሕረትህ የጸና
መሆንክን ጥንቱን እኔ አውቃለሁና
እኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ሐሰት ተናግሬ የማይሆን ነገር
አልፈልግምና ቆሜ ለመኖር
ከከተማ ወጥቶ በምስራቅ በኩል
ከወደ ዳር ሆኖ ነነዌን ሲያሰተውል
ምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስ
ሠርቶ ተቀመጠ አንድ ትንሽ ዳስ
እግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎ
ቅሉም እንደገና ከፍ ከፍ ብሎ
የዮናስ እራስ እንዲያገኝ ጥላ
ለጸሓዩ ንዳድ ሆነለት ከለላ
በዚህ ብቅል ነገር ዮናስ ደስ አለው
እንዲህ ቶሎ ደርሶ ሲያገለግለው
እግዜር በማግስቱ ጧት በማለዳ
ቅል የሚበላ ትል ፈጣሪ አሰናዳ
ትሉ ቅሉን በልቶ በፋጥነት ደረቀ
ፀሐይ ወጣችና ጊዜው በጣም ሞቀ
እግዜር አዘዘና ትኩስ ንፋስ መጣ
የሚከለከልበት መጠጊያ ስላጣ
ቅሉ ደረቀና ንዳድ ቢያቃጥለው
ዮናስ ተበሳጭቶ ለአምላክ እንዲህ አለው
እንደዚህስ ሆኜ ቆሜ ከምኖር
እባክህ ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ደረቀበኝ ብልህ ይህን ቅል ለመጣት
እውን ይገባል ወይ ያንተ አሁን መቆጣት?
ብሎ እግዜር ቢጠይቅ መለሰ ዮናስ
በንዴት ብዛት እስክሞትም ድረስ
አዎን ይገባኛል መናደድ መጨስ
እግዜርም መለሰ ለምን ጠፋ ስትል
ይህ ያልለፋሕለት ያልደምክለት ቅል
አንተ ስትናደድ ፈጥራያት እኔማ
ሳጠፋት ሳፈርሳት ነነዌን ከተማ
መቶ ሃያ ሺህ ነው የህዝቧ ብዛት
ለምን ትቆጣለህ እኔ ባዝንላት
ብሎ በምሳሌ ሲያስተምር ይቅርታ
ለዮናስ ነገረው የምሕረት ጌታ
ለእግዚአብሔር ቸርነት ምስጋና ይደረስ
በዚህ ተፈጸመ ትንቢተ ዮናስ።
\= ተፈፀመ = /
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
* ከክቡር አቶ ከበደ ሚካኤል" የቅኔ አዝመራ" የተወሰደ 1956 ዓ.ም
እንሆ የነነዌ ፆምም ተፈፀመ የነነዌን ሰዎች ልመና ተቀብሎ በምሕረት እንደጎበኛቸው እኛንም በምሕረቱ ይጎበኝን
ለሀገራችንምም ሰላም ለህዝቦቿም ፍቅር አንድነትን ቁጣውን እና መአቱን መልሶ በምሕረቱ ብዛት ይመልከተን ይቅር
ይበለን!!!አሜን 

9.ቃል ብቻ ተናገር...! (ማቴ፡8÷8)


ቃል ብቻ ተናገር ቃልህ ቃልን ያውጣ
ፀጋህ ከአርያም መጎብኘትህ ትምጣ
ልምሾው ቀንቶ ይሂድ ይፈወስ ድውዩ
ቅን ማድረግን ይማር ይመለስ በዳዩ
ማየት ላልሆነለት በለምፅ ለነደደው
በችግር ሸለቆ ቁልቁል ለወረደው
በጦርነት እሳት ለሚለበለበው
ሰላምን ተጠምቶ ፍቅር ለተራበው
ለምስኪኑ ሕዝብህ በግፍ ለተገፋ
ከቃልህ በስተቀር ከየት ይገኛል ተሥፋ?
እንኳን ይሄ ችግር የሰው ልጆች እንከን
ተዐምር አይተናል በቃልህ ሲከወን
ጥንትስ ሕያው ሆነው ዓለማት የቆሙት
ሰማይና ምድር ሕዋው ላይ የፀኑት
ጨለማና ብርሃን የሚመላለሰው
ቀላዩ አፍላጋቱ ሞልቶ የሚፈሰው
ይሄ የሚታየው ትንሹ ትልቁ
ደግሞ የማይታየው ስውሩ ረቂቁ
የትመጣው ቃልህ ነው ሥረ-ምክንያቱ
በቋንቋው ይናገር ይመስክር ፍጥረቱ
መለኮት ነው ቃልህ ከዘላለም ኗሪ
ሥርዓተ ዓለሙን በወጉ ቀማሪ
ወቅት አፈራራቂ ዘመን አመላላሽ
ውብ አርጎ የሚያንፅ ሲለው ደግሞ አፍራሽ
አልፋ ኦሜጋ ነው ፊተኛ ኋለኛ
ለፍጥረታት ሁሉ ምክንያት መገኛ
በቃልነት ከዊን በደም የተፃፈ
የከበረ ስም ነው ሥንቱን ያሳረፈ
ወላፈን ነው ቃልህ ነዲድ የእሳት ቋያ
ወርቅና አፈሩን አንጥሮ መለያ
ብረትን አራቂ ጥሬውን ማብሰያ
የሕይወት እሳት ነው ሕይወትን መሳያ
በቁጣ ሲነገር መዓት ነው ገሞራ
ምድር ትጤሳለች ይቀልጣል ተራራ
ሰማያትን ፈቺ በታላቅ ትኩሳት
ቃል ነው መተግበሪያው ግሩም ነደ እሳት
ቃልህ መዶሻ ነው አለቱን ሰባሪ
የደነደነን ልብ ፈርክሶ አሳማሪ
አስተካክሎ ጠርቦ ውብ አርጎ የሚያንፅ
የባከነን ሕይወት እንደ እርሳስ የሚቀርፅ

ሸለቆ የሆነን በቀቢፀ ተሥፋ


በትዕቢት ያበጠን እንደ አድማስ የሰፋ
ከደልዳላ መሬት የሚያስተካክለው
ቃልህ ባለ ሥልጣን የእውነት ዳኛ ነው
ቃልህ ነበልባል ነው ሁለት ስለት ያለው
የልቦናን ሃሳብ የሚመረምረው
ነፍስና መንፈስን ቅልጥምና ሥጋ
ሲቃጣ ሳይታይ ዘልቆ የሚወጋ
ሸለፈትን ቆራጭ አዚምን ገፋፊ
ሰነፉን ገስፆ ዘባቹን ቀሳፊ
የመንፈስ ሰይፍ ነው ቃልህ የእኛ ጌታ
ለማዳን ለፍትሕ የምትበረታ
ቃልህ ወለላ ነው ማርና ወተት
የእኔ የእኔ እያሉ የሚሻሙበት
የነፍስ ምግብ ነው የሕይወት እንጀራ
አጥንት አለምልሞ ገፅን የሚያበራ
የሕግ መብራት ነው የብርሃን መንገድ
ወደ እውነት ሀገር እየመራ የሚወስድ
ሺውን የሚያፈራ ቃል ነው የዘር ቅንጣት
ቃል ብቻ ተናግረህ ምድሪቱን ለውጣት
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብሎ ለሚጣራ
ለተነወረች ሴት ደም ለምታዘራ
ወዮታ ላበዛው በድን ልጅ ታቅፎ
ታምኖ ለተገኘ ሺህ ምዕራፍን አልፎ
በባርነት ቀንበር አንገቱን ለደፋ
ባህር በረሃውን በስደት ለለፋ
ቁራሽ እንጀራና እፍኝ ጥሬ አጥቶ
ቅስሙን ለሰበረው ራቡ በርትቶ
ከሞት ትንፋግና ከባሩድ ጢስ በቀር
አጥቶ ለጨነቀው ሰላም ንፁህ አየር
ሞራሉ ላሽቆበት ግብረ ገብ ለራቀው
በኃጢአት አዘቅት ውስጥ ቁልቁል ለወደቀው
በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ክፉኛ ተይዞ
በምርኮ ለሚኖር ሕሊናው ደንዝዞ
ለዚህ ሁሉ ምስኪን ለዚህ ችግርተኛ
እንቆቅልሽ ፈቺ ቤዛና መዳኛ
ከቶ የለምና ቃል ሆይ ከአንተ በቀር
ቃልህ ቃልን ያውጣ ቃል ብቻ ተናገር
የየሰዉ ወጥመድ ችግርና ቀንበር
በኃይልህ ይወገድ በቃልህ ይሰበር

ቃል...... ብቻ.........ተናገር..........!

10.ተጠቃሚ ያጡ መድኃኒቶች
1/ ቃለ እግዚአብሔር
 ጠዋት አንድ
ማታ አንድ
2/ ንስሐ
በየሳምንቱ አንድ አንድ
3/ ስጋወ ደሙ
 ቢያንስ በ 40 ቀን አንዴ
4/ ጠበል
 ከምግብ በፊት በየቀኑ አንዴ
5/ እምነት
  ዘወትር በየሰከንዱ ያለማቋረጥ
6/ ፍቅር
 ዘወትር ያለማቋረጥ ለሁሉም
7/ ሰላም
   ለተከታታይ ሰዓታት እስከ ዘላለም
8/ጸሎት

 በቀን ሰባት ግዜ ያለማቋረጥ


9/ ፆም
 ከምግብ በፊት
10/ ምፅዋት
በየቀኑ ከምታገኘው ጥቂቱን
11/ ስግደት
ጠዋት 21
ማታ 20
☞☞ማሳሰቢያ፡- ሁሉም መድኃኒቶች ተስፋ በተባለ ውሃ ማወራረጃነት መዋጥ ይኖርባቸዋል።

11.ኃይሌን መልስልኝ፨
ጧት በማለዳ
ቤትህ ስገሰግስ
ሳልታክት ዘወትር
አንተን ሳገለግል
ስምህን ሳወድስ
ያኔ በኃይል ነበረኝ
ጸጋህም በዝቶልኝ
ስንፍና ርቆልኝ
መሰልቸት የለብኝ
አሁን ግን ጌታዬ ሆይ
ደሊላ ደልላኝ
ጉልበቴ ብርክ ይዞት
ኃይሌን አሳጥታኝ
እንደው ላታዛልቅ
በጥላቻ አፍቅራኝ
በጭንቀቴ ላትደርስ
ለጠላቴ ሰጥታኝ
በምርኮ አለሁና
በኃጢአት ተከብቤ
አንተን እንዳመልክህ
ተመልሶ ልቤ
እንደው ለአንድ አፍታ
ኃይሌን መልስልኝ
የኃጢአቴን ምሰሶ
ነቃቅዬ ጥዬ
የአንተ ሆኜ ልገኝ።

የልቤ ማድጋ፨
ዘወትር ጠዋት ማታ ስለፋ ስተጋ
እሞላለሁ ብዬ የልቤን ማድጋ
ዛሬ በንስሐ ሞላችልኝ ብዬ
በሐሰት ስቦርቅ አይሎ ደስታዬ
ነገ ደግም ባዶ ወና ሆና ሳያት
ኀዘኔ በርትቶ ስሞክር ልሞላት
ጠብም ላይልላት ደግም እየሞላች
ዳግም ስትጎድል ምሬቴ አይሎ
ደክሜ እንዳልዝል
ከዚያ ከምንጩ ዳር አግኝቼ አምላኬን
ዳግም ላይጎድልብኝ ሞልተህ ማድጋዬን
ለስምህ ልዘምር ላብዛ ምስጋናዬን።

12.ተወው ምን በወጣህ ¡
~~> እንዳትበላ!
የቀድሞ ህግ ትዕዛዙ
ፍጡራን ለፈጣሪ እንዲገዙ
ድንበር ገደብ ቢበጅለት
መከልከል መች ሊዋጥለት
"ስለምን ይሆን ቀድሞ መፈጠሩ?
ኋላስ በህግ መታጠሩ?
እንዳልገባበት ነው በሥልጣን በክብሩ?"
እንዳትበላ ቢከብድበት
እጁን ሰዶ ቢያደማት
በባህሪው እኩይ ንዋይ ሸመተበት
ጽነት መርገም ለበሰበት
የእንቢታ ዋጋ ንረት
በሥጋ የመቃብር ግዞት
በነፍስ የሲኦል ርደት
በስብዕናው ላይ አጠላበት
የሞት ሞትን አመጣበት
አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዲያ ከሰረበት
+++
"ፍጠረኝ ሳይለኝ ፈጥሬው
ሺውን ሰጥቼ አንዷን ብነፍገው
አትብላን መጠበቅ አቃተው?"
ተካሽን ልካስህ አሰኘው
"አበስኩ ገበርኩ" ብሎ ቢያለቅስበት
አርአያ ገብርን ነስቶ ሞቶ ሞቱን አጠፋለት
+++
የትላንተ የገበያ ውሎ
ለዛሬው ተስተካክሎ
ከመስኩ እንዳትርቅ እረኛው ቢወድህ
ላንተ በዚህ ዘመን ህጉ እንዳይከብድብህ
በይቡስ ሳር ፈንታ እራሱን ሰዋልህ
"ዳግም ብላና ዳን ይኸው ሕይወት" አለህ
አንተማ እንጂ መች ተረዳህ
የተቃርኖ ድንበር ናፈቀህ
የእንዳትበላ ህግ አሰኘህ
ብላና ዳን መች ሊቀልህ
+++
ምነው ያኔ አንተን በገነት ቢያኖርህ
ሺውን ሰጥቶ አንዷን ቢነፍግህ
+++
ግን ተወው ኧረ ተወው ምን በወጣህ
የብላና ዳን ህግ ከከበደህ ካስጨነቀህ
አትናደድ .... አትበሳጭ ..... አትቆጣ
ገሃነመ - እሳት እንጂ ሌላ ምን ሊመጣ¡

13.የመፃጉዕ ትዝታ
በዕብራይስጥ ቤተ-ሳይዳ ከውኃው ዳር መጠመቂያ
ከድኅነቱ ቀዬ ከደዌ ፍታት መላቀቂያ
ህመም የደቃው አካሌን እየወቀረው ንፋስ ብርዱ
ኩምትር መንፈሴን ያዘለ የልቦናዬ አጸዱ
ከተስፋ ጽንፍ የቆመ ተሰውሮበት መንገዱ
ፈውስ ርቆኝ እንደሰማይ ከአልጋዬ እንደተሳፋሁ
የብጤዎቼን ድውያን የጣር ድምጸት እየሰማሁ
መላኩ ወርዶበት ውኃው ቢናወጥም
እዳር ሆኖ መሻት እንጂ ገብቼበት ከቶ አላውቅም
በለስ ቀንቶት ከውኃው ቀድሞ የገባ
ዳግም እንደወለዱት ሲፈነጥዝ እንደ እምቦሳ
ያን ኩምትር መንፈሴን ከጥጋቱ አነቃለሁ
ተስፋ ቀጥላለው ድኅነት እናፍቃለሁ
ግና ሰው የለኝም መላኩ እንደወረደ ከውኃው የሚዘፍቅ
ልድን እወዳለው ከጠፈረኝ ደዌ ልፋታ ልላቀቅ
ሠላሳ ስምንት ዓመት በአንድ ጎልማሳ እድሜ
ህመሜን ታቅፌ ባልተኛሁት እንቅልፍ ከአልጋ ተጋድሜ
ልድን እወዳለሁ የኔ ቀን መቼ ነው
ለካ ዛሬ ደግሞ ዕለቱ ሰንበት ነው
በአይሁድ ሥርዐት ማረፊያ ብቻ ነው
ልድን እወዳለሁ እንደመቶ አለቃው ልጅ በቃል ከሞት መነሳት
እንደዓይነ ስውሩ በጭቃ ዓይን መብራት
ልድን እወዳለሁ
ደግሞ በዚህ መሀል
ደም ግባቱ ያማረ የተጎናጸፈው ከወተት የነጣ
አንድ ሰው አየሁኝ ወደኔ ሲመጣ
ወደኔ መምጣቱ የውበቱ ማማር እጅጉን ገርሞኛል
ይባሱኑ ደግሞ ልትድን ትወዳለህ? ብሎ ይጠይቀኛል
እንዴ!
ካልተኛሁት እንቅልፍ ከደዌ ቅዠቴ
ፋታ ከነፈገኝ ከራቀኝ እረፍቴ
ተኛ እየተባለ ይኸው ተኝቻለሁ
እስከዛሬም ሰው ባይኖረኝ ከኖርኩበት አለሁ
አዎን ጌታዬ ሆይ ልድን እወዳለሁ
ፀሐይን ባስናቁ ዓይኖቹ እያየኝ ይህን ተናገረኝ
አልጋህን ተሸከም ተነስተህ ሂድ አለኝ
የጓጎለ ደሜ በአካሌ ሲራወጥ ተሰማኝ ሙቀቱ
ድንዝዙ ጅማቴ ከውስጤ ላይ ሲያብብ አነቃኝ ንቃቱ
ዕፀ ሕይወት ፉት እንዳለ ከእፍታው እንደቀመሰ
ከራስ እስከ ጥፍሬ አካሌ ታደሰ
በእጆቼ አዘዘ በእግሮቼም አዘዘ
እንደ በትር ቀሎት እጄ አልጋዬን ያዘ ከእንቦሳ ቀልጥፎ ፀንቶ እግሬ ተጓዘ
የዓመታት ሸክም እኩል ከአንድ ቀን
ከውለታ ሚዛን ቀርቦ ባይመዘን
ጽናቱን ለመቅመስ ጣዕሙ ምን እንዲል
የተሸከመንን መሸከም ደስ ሲል
ግና ሸክሜን ረሳሁ
ውቡ ደም ግባትህ በደም ተሸፍኖ ጽሕምህ ተነጭቶ
መለኮት የሞላው ተነስ ያለኝ ቃልህ በመከራ ቃትቶ
እጅህ ለእጄ እግርህ ለእግሬ ከመስቀል ተሰፍቶ
የመታደሴን ቀን የሰንበት ዕለት ፈውሴን ህመሜን ረስቼ
ልማድ ሻረ ብዬ ክንዴን ባንተ አንስቼ
ከወገኔ ወግኜ ከገፉህ ልገፋህ
ባፀናኸው እጄ በጥፊ ስመታህ
ማሩን ቸርነትህን በእሬት የቀየረ
ውለታ ቢስ እጄ ይኸው ደርቆ ቀረ፡፡
በደም ብቻ ወገን ሲመሽ ለሚረሳ
መዳን እየሸሸ አመጽ ለሚያወሳ
ቃል ብቻ ተናግሮ ከደዌ ሚፈታ
ከዘላለም አባት ከምህረት ጌታ
እንዴት ይመረጣል? ብዬ ጠይቃለሁ
ሕመሜን አልጋዬን ደዌን እመኛለሁ
ወደኔ ስትመጣ የበራው ጸዳልህን ዓይንህን እያየሁ ተነሳም ባላልከኝ በቀረሁ እላለሁ
ፍቃድህ ነውና መነሳት ካልቀረ
ከልቤ መንበር ላይ ፍቅርህ እንዳደረ
ማዳንህ ብቻ እንዲታይ አልጋዬን እንደተሸከምኩ
ሐውልት ሆኜ ቆሜ ዘላለም ባሸለብኩ
ከዕብራይስጥ ቤተ-ሳይዳ ከውኃው ዳር መጠመቂያ
ከድኅነቱ ቀዬ ከደዌ ፍታት መላቀቂያ
ጸጸቱ ሲያደብነኝ የክህደት ጅራፉ
አንተን ሳልከተል ያ ጊዜ ማለፉ
ቁጭ አርጎ ያሰተክዘኛል
አሁን ቦታው ረጭ ብሏል
ውኃውም ደራርቆ ትቢያ ብቻ ቀርቷል
የመላኩን መውረድ በጉጉት ሚጠብቅ
ባለደዌ ሽባ በሽተኛ የለም መዳን የሚናፍቅ
ከአስታማሚ ግርግር ከታማሚ ሲቃ
ከሁካታው ሰክኗል ተኝቷል ላይነቃ
ቦታው ረጭ ብሏል
አሁን ከአካል ደዌ ከሽባነት ይልቅ ሌላ ሕመም ገዝፏል
የተጣመመ ልብ የአእምሮ ስብራት ክፋት ብቻ ነግሷል
እንደኔ እጅ ደርቆ ያልታየ ሰልሎ
ከግራህ የቆመ የቀኝህን መስሎ
ብዙ ከሃዲ እጅ አለ ተከልሎ
ኤዲያ እኔን ብሎ ወቃሽ
ከቀድሞ ቦታዬ ዛሬም ከዛው አለሁ አንተን አስባለሁ
የሰንበት ቀን ደም ግባትህን የአርብ ስቃይ ከከለለው አነፃፅራለሁ
የሰንበት ቀን ራስህን የአርብ እሾህ ከነደለው
አነፃፅራለሁ አንተን አስባለሁ
ሞት ድል መንሳትህን ትንሳኤህን ሰምቻለሁ
ግና
እኔ አልተነሳሁም ከፈኔን አልገለጥኩ
እንደተዘጋብኝ አለሁ እንደነበርኩ
አልጋህን ተሸከም ተነስ ሂድ እንዳልከኝ
መስቀልህን ሰጥተህ ና ወደኔ በለኝ
ካንተ ጋር ልነሳ እሱ ነው ሚበጀኝ
አብሬህ ልነሳ እሱ ነው ሚበጀኝ
14.አበው ይናገሩ
እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡
እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡
ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡
ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡
ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?
ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡
የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡
እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡
ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?
በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡
ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡
ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡
የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡
ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡
እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡
እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡
ምንጭ፡- መለከት 1 ኛ ዓመት ቁጥር 6

ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቶአል እንጂ በዚህ የለም። ሉቃ 24፥5-6
15.ትንሣኤ
የመቃብሩን ድንጋይ ፈንቅሎ
የመግነዝ ጨርቁን አውልቆ ጥሎ
በአይሁድ ወታደሮች ላይ
በኃይል ሰልጥኖ
ክርስቶስ ተነሳ ከፍ ከፍ ብሎ።
ለማያልፍ ርስት ዳግመኛ የወለደን
ሕይወቱን ሰጥቶ ያከበረን
ለአዳም ልጆች ሁሉ ተስፋ የሆነን
ይኸው በኩራት ተነስቶአል ደስ ይበለን።
ከእንግዲህ ቀረልን በሞት መጠቃቱ
ሲፈርስ አይተነዋል የዲያብሎስ ግዛቱ
ክርስቶስ ሲነሳ በግርማ መለኮቱ።
እኛን በገዛ ደሙ ገዝቶ
በፍቅሩ ወድዶ ስቦ
ወደሚደነቅ ብርሃን ጠርቶ
ኃጢአታችንን ሽሮ አጥፍቶ
ዛሬ አየነው በክብር ተነስቶ
የእሱ የሆነውን በዲያብሎስ ላይ ሹሞ
ረግጠን እንድንገዛው ማህተሙን አትሞ
ትንሣኤ ሆነልን በጸጋው ሸልሞ
አማኑኤል የተባለው
አልፋና ኦሜጋ የሆነው
መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው
እርሱ እኮ ራሱ ትንሳኤ ነው።
አሕዛብን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛ
ከበረዶ ይልቅ እጅግ የነጣ
ነጭ ልብስ ለብሶ ሲነሳ
ሞት ሆይ መውጊያህ ታዲያ የቱ ነው?
አዳምን ከክብሩ አውርዶ የለየው
ወደ መሬት ቁልቁል የጣለው
እኛስ ይኸው ዕልል ብለናል
ዳግማዊው አዳም ሲነሣ አይተናል
ዲያብሎስ እንደማይችለው አውቀናል።

16.ዛፏ አስተማረችን
አለም ለስጋው ያንተን ፍቅር ትቶ
ለክብሩ ቢጨነቅ ዋጋውን እረስቶ
ለስጋው ሲያደላ ነብሱን እየረሳ
ከትቢያ ከደይኑ ያወጣውን ከአበሳ
ለዲያቢሎስ ተገዝቶ
ፀጋውን ተቀምቶ
ተስፋው ጨላልሞ
በጨለማ ቆሞ
የከፈለውን ዋጋ ለአፍታ እንኳን ቢረሳ
ጠላት እያደባ ሲያጓራ እንደ አንበሳ
ምንም እንኳን ቢረሳ የአምላክ ቸርነቱ
ፈጥሮ አሳልፎ ማይሰጥ ለጠላቱ
እየበደልነው የሚያነሳ
ሚያስታውስ ብንረሳ
ብንወድቅ የሚያነሳን
ተርበን ያጠጣ ያበላንን
እንደ ወዳጅህ ይሁዳ ስንበድል አንተን
ንስሃ እንድንገባ ዛፏ አስተማረችን
ለብዙ ምክንያትም ወንጌል እያወጀች
መዳን አሁን ነው ብላ እየሰበከች
አንታዘዝ ብለን አድልተን ለስጋ
የሞታችን ጦማር ከፊት ቢዘረጋ
በሃጥያት ተጨማልቀን ቢገፈፍ ፀጋችን
በባርነት ግዞት ዲያቢሎስ ሲገዛን
በእጃችን ላይ ያለው አርነት ባርነት
ነብሳችን ከወዴት ከሲኦል ወይስ ገነት
ንስሃ ገብተን እንዲምረን በእውነት
አምላክ ይጠብቀን በፍፁም ቸርነት

17.መነባንብ
፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል ፩
አለሁ አለሁ ለእናቴ
ለብርታት ጉልበት ፅናቴ
አለሁ!አለሁ ለርስቴ
ሀገሬ ከላይ ነው አባቴ እግዚአብሔር ነው
ዘራፋ! በቀራኒዮ የተሠቀለው
የምስጢር ደሙ እጄን ቢነካው
ከመኝታዬ ከእንቅልፌ ነቃሁ
ዘራፋ!2 አትደፈርም ፅኑ ሃይማኖቴ
አትሠደብም ድንግል እናቴ
ይቀዳ ደሜ ይርገፍ አጥንቴ
መቃብር ልግባ ይቀላ አንገቴ
ልሠደድ ልውጣ ይቅርብኝ ቤቴ
ይቅርብኝ እምቢ ሀብት ንብረቴ
አትደፈርም ፅኑ ሃይማኖቴ።
ዘራፍ!2 አይበጠስም ቃል ማህተቤ
አይበረዝም የእምነት ክታቤ
አትናወጥም ታንኳ መርከቤ
አትለወጥም እውቀት ጥበቤ
አትታደስም ታሪክ እንቅቤ
ከምትቃጠል እኔ ጠግቤ
ሁሉም ይቅርብኝ ልሙት ተርቤ።
ዘራፍ!2 የጀግኖቹ ዘር ጀግና የተባለች
የጳውሎስ ወኔ በፅኑ የጠራኝ
የዲዮስቆሮስ የፀጋው ልጅ ነኝ
ማንም አይነካሽ ፊትሽ አይቆዝም አትዘኚብኝ።
ክፍል፪

ዘራፍ!2 ታሪክ እምነቴን አልሸጥም ከቶ


የተዋህዶ ስም አይቀርም ጠፍቶ
ፅላት ብራናው አይሔድም ወጥቶ
አይቀርም በእንቶ ፈንቶ
ነገም ይኖራል ልጆች አፍርቶ
ሰው ይማርካል በደማቅ በርቶ
ከቶም አይሞትም ይቆያል ፈክቶ
በብርቱ አለት ዘላለም ፀንቶ
እማ አትዘኚ ልጆች አለንሽ
ይተላለፋል ገድል ታሪክሽ
አይኮበልሉም ውድ ቅርሶችሽ።
ክፍል፫
ዘራፍ!2 በቀራንዩ የተሠቀለው
የምስጢር ደሙ እጄን ቢነካው
ከመኝታዬ ከእንቅልፌ ነቃሁ
ዘራፍ!2 ሞቶም ተቀብሮም የሚፈሩት
ገድለውት እንኳ የሚሠጉት
መቃብሩ ሳይቀር የሚጠበቅ
ገዳያችንን የሚጠረቅ
ሞትን በሞቱ እየገደለ
የጥንቱን ጠላት ከጥልቅ የጣለ
የሞትን መዝጊያ የሰባበረ
ቀበሪያችንን የቀበረ
መስቀል ላይ ሆኖም የሚያሸንፍ
የጥልን ሠነድ ክስን የሚያጠፋ
ጅራፋ እያየ የማይፈራ
ሁሉን በፍቅር የሚጠራ
የአለም መድሃኒት የይሁዳ አንበሳ
በሶስተኛው ቀን ፈጥኖ የተነሳ
የንጉስ ልጅ ነኝ ስሙም ተፈሪ
ነፃ የሚያወጣ ወጥመድ ሰባሪ
ከቶ አልሠጋ አልሆንም ፈሪ
ዋጋ ከፋዩ ሆኖኛል መሪ።
ይቀጥላል.....

መነባንብ
፨፨፨፨፨፨
ክፍል፬
ዘራፍ!2 ፍቅርን ታጥቄ ፍቅርን ለብሼ
በንስሐ እንባ ውስጤን አድሼ
የጌታን ስጋ ደሙን ጠጥቼ
በቤትሽ ኖሬ ደጅሽ ፀንቼ
አሁንም ልኑር ጡትሽን ጠብቼ
ዘራፍ!2 ማነው የሚነካሽ የታለወንዱ
ቢፈራገጥም አምላኩ ሆዱ
መሠረትሽን ከቶ አይንዱ
ዘራፍ!2 የቄርሎስ ምላሽ ጥንተ ሃይማኖት
የአባ ጊዮርጊስ ፀሎት ደረሰቱ
የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ስብከት
የአግናጢዎስ የአንበሳ ራቱ
የአባ እንጦስ ብርታት ፅናቱ
የቅዱስ መቃርስ ምናኔ ቤቱ
የቅዱስ ያሬድ ዜማ ስርዓቱ
የአትናቴዎስ ብርታት ስደቱ
የአረጋዊ ወዳጅ እናቱ።
ዛሬም ይስማል ስዓታት ቅኔሽ ዚቅ ማህሌቱ
ይከበራል ነገም ገና ከፍ ይላል መስቀል ፅላቱ
እማ ተዋህዶ መቼም አትጠፋም ይሰማ ፍጥረቱ 2
አትጠፋም... አትጠፋም
አትጠፋም.... እማ ተዋህዶ❕
*/ተፈፀመ ዝንቱ መነባንብ

18.፨አዘክሪ ድንግል፨
በኃጢአት በሽታ በበደል ቁስል
በክፋት በተንኮል በቂም በበቀል
በጭካኔ ጅራፍ በዘር ክፍፍል
ተመተናልና አማልጅን ድንግል።
ለተፈጠርንበት እንድንቆም ለዓላማ
ሕገ እግዚአብሔርን ጆሮአችን ሲሰማ
በወንጌሉ አንድምታ በቅኔው ከተማ
ይፃፍ በውስጣችን አግዥን እማማ።
በማስተዋል ጥበብ ይሰራ ውስጣችን
ለጾም ጸሎት ስግደት ይነሳ ልባችን
ፍቅር ቸርነት ቅንነት ይክበበን
የአማኑኤል እናት ኪዳንሽ ያበርታን።
ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ
ክብርሽ የገነነ እናቱ የአዶናይ
ምሕረትን አሰጭን ይመልከተን ከላይ
አሳዝነነዋል እየሆንን ኮብላይ።
የመከራው ዱላ እስከ አጥንት ደርሶ
ፊታችን ጠቋቁሯል በዕንባ በለቅሶ
በከንቱ እንዳንጠፋ ይማረን መላልሶ
አዘክሪ ድንግል ያቁመን አድሶ።
በተሰጠን መንገድ ዘመን በማይሽረው
በአንዲቷ ጥምቀት በደም በታተመው
በሕያው መዝገብ ላይ በቃል በተፃፈው
ለቅዱሳን ሁሉ አንዴ በተሰጠው
እንድንፀና አድርገን ጠብቀን ከከፋው
አምላከ አማልእክት ስልጣኑ ያንተ ነው።
ድንግል ሆይ አሳስቢ

19.፨የሚያስገርመኝ የለም፨
ያዓለም ከንቱ ካባ አይለብስ ትከሻዬ
ሁሉን ምረታበት እምነት ነዉ ጋሻዬ
ዉዳሴም አይጠቅመኝ አድናቆት አልሻ
ፅድቅነዉ ምኞቴ እስከመጨረሻ
ቢሉኝ ዉበት ለብሰዉ ገፄን ያደንቀዋል
ወይም ጎስቆል ብለዉ ሰዉን ይንቀዋል
እንዳትሳሳቱ አልደክምም ለመልሱ
ጥያቄ ትታችሁ ባንድ ለማመስገን ሁላቹ ተነሱ
ሁሉን የሚቀበል በክብር ዙፋኑ አለ በመቅደሱ
የዘዉትር ድካሜ የሌተ ቀን ህልሜ
እግዚያብሔር ነዉ ሁል ጊዜም ሠላሜ
እሱን ነዉ ማደንቀዉ አንድዬን ነዉ ማዉቀዉ
ማንም ጠቢብ የለም እኔ የምናፍቀዉ
ታዲያ ዉብ ነኝ ብልህ እንዳታስጨንቀኝ
ሰዉ ትጠያለሽ አትበል በቅድሚያ ሳታዉቀኝ፣
ላንቺም ነዉ እህቴ የምልሽን ስሚኝ
አመለካከቴም አይደለም ጨለማ
እስኪ አርቂና እንይ እሱ ነዉ መሪያችንማ
ተደምስሶልናል በሞቱ ሞታችን
እንግዲያዉ ለዚህ ነዉ ዓለምን ማላየዉ
ህያዉ ያደረገኝ ፅድቄን የምለየዉ
ፀባዬን ተረዱኝ ሚስጥሩ የገባችሁ
ሚያስገርመኝ የለም ተዉኝ እባካችሁ

20.ተዋህዶአትፈርስም
ድርጅት አይደለም በሰዉ የታነጰ
ፖለቲካም አይደል ዘርን ያጣቀሰ
ሚስጥሩ ፍቅር ነዉ ቃላቶች ማይበቃዉ
እኛን ስለመዉደድ በፍቅር ተስቦ
መስቀል ላይ የወጣዉ
በደም ታንጰናል በማይጠፋ ቀለም
ለኛ ብሎ እርሱ ቢሰቀልም
መሰረቱ እየሱስ ነዉ
ግርግዳዉ ቅዱሳን
ግንቦቹ እኛ ነን የእርሱ ምእመናን
ልንወድቅ አንችልም በእርሱ ፍቅር ጰንተናል
እግዚአብሔርን ይዘን ማንስ ይንደናል
ማሃመዳዊም ሁን ወይም ጆቫዊትነስ
ፕሮቴስታንትም ሁን ወይ ደሞ ካቶሊክ
አለቱን ላታፈርስ የሰዉ ደም አታፍስስ
ምንጩንም ላታደርቅ ከመቅደሱ እራቅ
ካህኑ ቢታረድ መቅደሱ ቢቃጠል
እንበዛለን እንጂ የለም የሚጎድል
ስንሞት እንበዛለን
መከራዉ ሲበዛ በፍቅር እንጰናለን
በእሳት ስንቃጠል እንለመልማለን
ከማይደክም አባት ተፈጥረናልና
አርዮስ አትልፋ እንላለን ቀና
ሰልፉ የእኛ ነዉ ድልም የኛ ብቻ
እንደ አሸዋ የበዛን እስካለም ዳርቻ
ካህኑን ግደሉ መቅደሱን አቃጥሉ
ቅጥሩንም አፍርሱ ልጆቹን በትኑ
እናንተ ስትጠፉ እነሱ ቀና ብለዉ
ባባታቸዉ እቤት ይሰበሰባሉ
ይህ ነዉ ክርስትና የማይጠፋ ቀለም
በፍጱም ማይጨልም ሁሌ ሚሰጥ ብርሃን
እናማ አርዮስ ቁርጥህን እወቀዉ
ድል ላታደርግ እንደዉ ነብስህን አታስጨንቀዉ
ሃሰት እዉነትን እስኪ የቱጋር ነዉ አሸንፎየሚያቀዉ
ባንድነት ተነሱ የእምነትን ሰይፍ ያዙ
በፍቅር ማርኩና የዲያቢሎስን
በእምነታችሁ ናዱ
በእምነት እንሞላ በጱናት እንቁም
በተስፋ እንዉጣ
ጠላት አፍሮ እንዲቀር መድረሻ እንዲያጣ
የጦር እቃችሁን ልበሱ እንደ ካባ
ዘመቻዉን አጵኑት ቅድስት ምድር
አርዮስ ሳይገባ
የጦርሰልፍ አንሻም ቀስት አንወረዉርም
ደም እያፈሰስን እርሱ የፈጠረዉን እኛ አንገድልም
ቀስትና ጦር ይዘን አንወጣም ዘመቻ
ጠጠርም አንለቅምም አሳዳጁን መምቻ

21.ጾምና ኩነኔ
ልቤ በቂም በቀል በተንኮል ተሞልቶ፣
እጄ ሲተባበር መልካም መሥራት ትቶ፣
ጆሮየ ለመስማት ከመረጠች ክፋት፣
የእግሬ ጉዞ ከሆነ ወደ ሃፂያት ፣
አይኔ ሲቅበዘበዝ ክፉውን በማየት ፣
ምላሴም ሳትፀዳ ተዘፍቃ በሀሜት ፣
ከጮማው ቆርጬ፤መጠጡን ጠጥቼ ፣
ቅበላ ነው ብየ አእምሮየን ስቼ ፣
ቅድመ ዝግጅቴ ሆድ ለመሙላት ሆኖ ፣
ማየት ከተሳነኝ ነገር አመዛዝኖ ፣
በንስሀ ሳልነፃ ከነቆሻሻዬ ፣
ፆሙን ለማስገባት ሽር ጉድ ብዬ ፣
ሠዎችን በድዬ ይቅርታ ካልጠየኩ ፣
ተበድየም ቢሆን ምህረትን ካልፈፀምኩ ፣
ተፈቶ ሲፈሰክ መዳን ካላገኘው፣
ጥፋቱ የኔው ነው ፣
መፆሜም ከንቱ ነው ፣
የበደሉኝን ይቅር ሳልል እኔ ፣
አንተ ይቅር በለኝ ብየ ማላዘኔ ፣
አብረውም አይሄዱ ፆምና ኩነኔ ።

22.፨እንካ ሰላምትያ፨
እንካ ሰላምታ?
በምንትያ
በመሰንቆ
ምን አለ በመሰንቆ?
ለሰው ይበጀዋል መኖር በቤቱ ፈጣሪውን አውቆ።
እንካ ሰላምትያ
በምንትያ?
በደውል
ምን አለ በደውል?
መሆን ያስፈልጋል የዋህ እንደ ርግብ ብልህ እንደ እባብ።
እንካ ሰላምትያ
በምንትያ
በከበሮ
ምን አለ በከበሮ?
ዘመንም ህይወትም አብሮ ይቀየራል ከአምና ዘንድሮ።
እንኪ ሰላምትያ
በምንትያ
በጽላት
ምን አለ በጽላት?
ለተዋህዶ እናት ለቅድስቷ ቤት ጠበቃ ሁንላት።
እንካ ሰላምትያ
በምንትያ
በሰረገላ
ምን አለ በሰረገላ?
ፊተኞች ስንባል እንዳንሆን ኋለኛ መትጋት ያስፈልጋል ከእንግዲህ በኃላ።
እንካ ሰላምትያ
በምንትያ
በጧፍ
ምን አለ በጧፍ?
አይዞህ በርታ ተነስ አምላክ ይመራሃል የህይወትህን ሰልፍ።
እንካ ሰላምትያ
በምንትያ
በጉልላት
ምን አለ በጉልላት?
የቅዱሳን ፀሎት ምልጃ በረከት ትልቅ ዋጋ አላት።
‍ እንካ ሰላምትያ
በምንትያ
በሻማ
ምን አለ በሻማ?
ምልጃ በረከቷ ሁሌም አይለየን የሰማእቷ አርሴማ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር

ዘመን እንደዋዛ
ሰከንድ ደቂቃውን ደቂቃ ሰዓቱን
እያደገ ሲሄድ ሰይገታ ጉዞውን
በዚህ ሳያበቃ ሰዓት ቀንን ወልዶ
ቀኑም ሳምንት ሲሆን ተሻግሮ ተራምዶ
ሳምንትም በተራው ወራትን ሲተካ
የተቦካው ሲያልቅ ተፈጭቶ ሲቦካ
ወራት ወደ አመታት በአንዴ ሲቀየሩ
እረፋት የለሽ ሰዓት ሲዞር መዝወሩን
እድሜዬ አብሮ ሮጠ አለፈ ዘመኔ
ጆሮዬ እየሰማ እያየኹት በዓይኔ።
ብልጭ ድርግም ስትል ያቺ ፈጣን ሰኮንድ
በእጄ ላይ አስርያት ተቀምጣ በእኔ ክንድ
እኔ ስስቅባት ፍጥነቷን እያየሁ
ምንድን አስቸኮለሽ አጣደፈሽ እያልሁ
ለካስ ምስጢር አላት ዘመን ትቆጥራለች
በእድሜ መቀለዴን ነጋሪ ኖራለች።
እኔ መች ተረዳሁ ምስጢሩ መች ገባኝ
እብድነች እላለሁ ለካስ እብዱ እኔ ነኝ።
ዛሬ ባስታውሰው ያለፈ ዘመኔን
የሰኮንድ ደቂቃ የሰዓት ምስጢሩን
የሳምንት የወራት የዓመታት ድምሩን
ለካ ሄዶብኛል
ዘመን አልቆብኛል
በራሴ ላይ ሆኖ ሞት ይስቅብኛል።
ልጠይቅ እራሴን ምን ሰራሁ በእድሜዬ❔
በኖርኩበት ዘመን በዚህ ቆይታዬ
አንድ ነገር ቀረቶኛል
ጭንቀት ይሰማኛል
ኑሮ እንዴት እንደሆነ ማሰብ ተስኖኛል
የእኔነቴ መሰረት አምላክ ከእኔ ርቋል።
አዎ❕

አሁን ገባኝ ሁሉ የእድሜ አቆጣጠሩ


የሳምንት የወራት የዓመታት ምስጢሩ
ያለ ቅጽበት ዕረፍት በፍጥነት መብረሩ
ሰዓት በእርሷ ስስቅ ለካ ትስቃለች
እግሬን ወደ ጉድጓድ ይዛ ትሮጣለች።
እኔማ መች ገባኝ ቁም ነገር መሥራቷ
በሕይወቴ ዙርያ በእድሜ መጫወቷ።
ከአምላክ መለየቴ መች ተገለጸልኝ
እርቃኔን መቆሜን ማን አይቶ አለበሰኝ።
ውሃና ሳሙና ተቀምጦ በፊቴ
አድፌን ሳላስወግድ ድረስ ሰዓቴ
አይ ዘመን❕
አምላክ ለእኔ አስቦ ተጨንቆ ተጠበበ
ለንስሐ ብሎ ጊዜዬን ቆጥቦ
ምህረት ቢለግስኝ ወደ እረሱ እንድመለስ
እኔ ግን ዘነጋሁት መስቀሉን ማስታወስ።
እስኪ አንተም ንገረኝ
በይ አንቺም ንገረኝ
ዘመንህ እንዴት ነው❔
ዘመንሽ እንዴት ነው❔
የአጠቃቀም ስልቱ ዘዴው እንደምን ነው❔
በሃሜት በወሬ ወይስ በለቅሶ ነው❔
በወሬም ይቆጥራል
በሃሜት ይበራል
በፀሎትም ያልቃል
ከእንባ ጋር ይወርዳል
ጊዜማ መብረሩን መች አቁም ያውቃል።
ግን ቁጥሩ አንድ ቢሆንም ጥቅሙ ይለያያል።
እናም የእናቴ ልጅ ዘመንህን ተመልከት
ሃሜቱን ተውና ንስሐ ግባበት
ሃሜቱን ተይና ንስሐ ግቢበት
ኮንትራትህ ሲያልቅ ቁም ነገር ሥራበት
በላይ በሰማያት ስንቅን አስቀምጭበት።
በሉ አሁን ተነሱ ያለፈው ይብቃና
እኔም አንተም አንቺም ንስሐ እንግባና
ከአምላክ እንታረቅ
መንገዱን እንወቅ
ቀሪ ዘመናችን ከእርሱ ጋር ትዝለቅ።
፧፧፧ስብሐት ለእግዚአብሔር፧፧፧
ገጣሚ መምህር አለምቀረ ሙሉ

23.እንኳን አደረሰሽ እትዮጵያዬ !! ..................


እኔው ባይሞላልኝ: ባይሰላ ጎጆየ፣
እንደ ውሃ ፈሶ: ቢያልቅብኝ ጊዜየ፤
በሰባራ መንገድ: ተጉዘሽ በሾክ ላይ፣
እዚህ ስለደረሽ: በምድር በሰማይ፤
አበባየን ይዠ: በር ላይ ቆሜያለሁ፣
እንኳን አደረሰሽ: ልልሽ እወዳለሁ።
በተስፋ ገመድ ላይ: እላይ ታች እያለ፣
ዓመታትን ያየ: እንዳንች ማን አለ ??
ይሁና... ሃገሬ: ይህን ማን አየብሽ፣
ዘመንን ባንች ቤት: ቀምሮ አኑሮብሽ፣
የእድሜያችን ልኬት: አንችው ስለሆንሽ፣
እጅ ነስቻለሁ: እንኳን አደረሰሽ።
ዓመታትን ሰፊ: አንች ግን ቀዳዳ፣
አመድ አፋሽ ቢሆን: እጅሽ ሰርቶ ባዳ፤
የገረጣው ፊትሽ: ቢያስከፋንም ቅሉ፣
በእንቁ-ጣጣሽ ቅጠል: ሸፍነን ላመሉ፣
እስኪ ደስስስ ብሎሽ: ይከበር በዓሉ፣
እንኳን አደረሰሽ: ኢትዮጵያችን ሙሉ።
በየ ደነጊያው ገብቶ: እንጀራ ፍለጋ፣
ሲባዝን ቢከርምም: ክረምት እስከ በጋ፣
ክፉና ደግ አልፎ: ሌሊቱ ሲነጋ፤
የምሕረት ጥላ: ባንች ላይ አርፎብሽ፣
ዘመንን በዘመን: ቀይሮ ሲያድስሽ፣
በተሰጠሽ ፀጋ: አንችን ደስ ሲልሽ፣
ማን የማይል አለ: እንኳን አደረሰሽ።
ቀሚስሽን ለብሰን: ከስር ብንቆርጠው፣
ከጉያሽ ተጣብቀን: ጡትሽን ብንግጠው፣
ያቀፈን እጅሽን: ዙረን ብንረግጠው፤
መልኳ ቢወይብም: ቢሰባበር ፀጉሯ፣
የናት እናትነት: ደም ነውና ፍቅሯ፣
ስሟን ሳትሸርፉ: ደሞ እንዳፈሯ፣
እንኳን አደረሰሽ: በሏት ከነ ክብሯ።
የፈጣሪ ኪዳን: ፅድቅ ያለብሽ ሃገር፣
ስምሽ መድኃኒት ነው: ማተብ የሚታሰር።
እናት ዘበአማን: ግብረ ገብ እመቤት፣
እንኳን አደረሰሽ: አንችም ለዚህ ዓመት።
የለመድነው ጣፋጭ: ወዝሽ ሲናፍቀን፣
እዚህ ካንች ጋራ: ባህር ማዶም ሆነን፣
ያውዳመትሽ ወጉ: ጎልቶ ሲመጣብን፣
ሃሴት በነፍሳችን: ሞልቶ ሲያናውጠን፣
አንች እያለሽ እኛ: መች እንከፋለን፣
እንኳን አደረሰሽ: ኢትዮጵያ እናታችን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አዲሱ አመት የሰላም የፍቅር የንሰኃ የምስጋና ዘመን ይሁንልን አሜን

24.ፅዩን ማርያም
ፅዮን ማርያም አማላጅዋ
ግሩም ድንቅ ነው ከለላዋ
ተነግሮ አያልቅ ጥበቃዋ።
ስሟን ስጠራ ተጨንቄ
ፅዮን ማርያም ስላት አጥብቄ
ሰለምናት ለመንገዴ እንድትሆነኝ ስንቄ ፣
ተናግሬ ሳልጨርስ
ከተፍ አለች እኔኑ ልታድስ።
ልትመራኝ ደግፋ ልትሆነኝ ተስፋ
ልትታደገኝ በይፋ።
ምኞትህ መልካም ነው ልጄ፣
አትጥፋ እንግዲ ከደጄ
ብፅዕት ነሽ በለኝ አሁንም ወዳጄ
አስታርቅሃለሁ አማልጄ፤
እያለች ስታፅናናኝ
ፅዮን ማርያም እመቤቴ
መታወቂያ የእኔነቴ
መንገድ መሪዬ መስታወቴ
የኑሮዬ ትርጉም የልማቴ
የድካም ሁሉ ብርታቴ
ምቹ ማረፊያ የስደቴ።
ርቄ ብሄድ ባህር ማዶ
መቼ ሆነ ቤቴ ማዶ
እንባዬ ታብሶልኝ
ፀሎቴ ተሰምቶልኝ
መውደዴ ተቆጥሮልኝ
ፅዮን ማርያም አብራኝ መጣች
ጣፋጭ ቃሏን እያሰማች
ብፅዕት ነሽ በለኝ እያለች።
* * */ /* * *
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር።

25.ከዘማዊቷ አንደበት
________________
በሰው እጅ ወድቄ በደካማው ጎኔ
ይገባታል ስባል ሞትና ኩነኔ
በፊትህ ለመቆም ሳይገባኝ ለኔ
ባንተ ፊት አቁመው አይሁድ እንዲህ ሲሉህ
መምህር ስለዚች ሴት አንተ ምን ትላለህ
ስትዘሙት አግኝተን ይዘናት መጥተናል
ሙሴ በኦሪቱ በደንጋይ ተወግራ እንድትሞት አዞናል
ብለው ሲጠይቁህ አይሁድ ሊፈትኑህ
አትወገር ብትል ህጋችን አፍርሷል
ትወገርም ብትል እንዴት ይጨክናል
ለሰው ሞት አያዝንም? የእግዜር ልጅ ነኝ ይላል
ለማለት አስበው ወዳንተ ሲመጡ
በዚህ ከባድ ሐሳብ አንተን መልስ ሊአሳጡ
ከናንተ መካከል ኀጢአት የሌለበት
መጀመሪያ አንስቶ ደንጋይ ይጣልባት
ብለህ ስትናገር ስትፈርድ ስለእውነት
ከአይሁድ መካከል ማን ነበር ካንተ ፊት
ቁሞ የተገኘ ኀጢአትን ያልሠራት
ባንቺ የሚፈርዱት ሰዎች ወዴት አሉ
ብለህ ስጠይቀኝ አወቅሁ እንደሌሉ
አይሁድ ሲዘጋጁ በኔ ላይ ሊፈርዱ
ዘማ ናት እያሉ እኔን ሊያዋርዱ
ቃላቸውን ሰምተህ መጻፍ ስትጀምር ያንዱን ኀጢአት ባንዱ
ትንሹም ትልቁም እየወጡ ሄዱ
አቤቱ ጌታየ እኔ ግን ከንቱ ነኝ
ኀጢአቴን ሰውረህ ከሞት አድነኸኝ
ኢየሱስ የት አለ? ብለው ሲጠይቁኝ
በጣቴ ጠቁሜ ለአይሁድ ያሳየሁኝ
መልካም ውለታህን መመለስ ያልቻልኩኝ
ወርቀ ደምህ ዋጅቶኝ በደምህ ስትገዛኝ
ስለመልካም ሥራህ ክፉ የመለስኩኝ
ከንቱ ነኝ ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱ ነኝ
የአንተን ውለታ መመለስ ያልቻልኩኝ።
ዮሐ ፰ ፥ ፫

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

26.ማለዳ ይጨልማል
ባስመሳዩ አለም ሳልሰራ ገና
ፍቅር ነበር ያኔ የዛሬ አያርገውና
ለጥቅማ ጥቅም ስል ቀርቤ ነበር ሰው
ያሻኝን አግንቼ አጣጥሜ እስክጥለው
ነበር ትናንት ዛሬ በርቅርቅታው አለም
በአለም ተሸሽጌ የኖርኩት ያለ ሰላም
የአለምን ሃሳብ ስኖረው ሳስበው
ፍቅር የለም ለካ ከጊዜ ወደ ጊዜው
ትናንትና ዛሬ ሰዎችን ስቀርባቸው
ትህትና ነበር ሲያዩ በአይናቸው
አሁን ወዴት አለ ያ የቀድሞ ፍቅር
አለምን አሸንፎ የኖረ በክብር
ወዴት ተሸሸገ የቱ በለጠበት
አለም እንዲህ እኮ ነወ ፍቅር የሌለበት
አሁንስ ታድያ ወዴት እንታደስ
ከከፋው ተምሳሌት ወይስ ቅዱስ መንፈስ
አይበቃም በአለም ሁሉን ነገር አየው
ክፉውንና በጎውን ሁሉን መርምሬያለው
ፍቅር ዋጋ እንዳለው ስላየው ተከቦ
ማለዳው ጨለመ ለሊቱ ተውቦ
የፍቅር ከፍታው ማሰርያው መንግስቱ
መነገዱ ይቅርብኝ በፍቅር መዋሸቱ
እና ፍቅር ማለት ለሚወደኝ ሳይሆን
ለሚጠላኝ ሁሉ መስጠቴ ነው ነብሴን
ስለዚህ ከጥንቱን ፍቅር ለመመለስ
ያለፈውን ረስቼ መመለስ ወደ መቅደስ
እና ከአለም ዳር ቆሜ አይኖቼ እንዳይፈዙ
በአለም ሃጥያት እንዳይመረዙ
ከልብ ከመነጨ ከሃጥያት ተነስቼ
ከማይጠቅመው አለም ካስመሳይ ወጥቼ
ምዕራባዊውን አለም ሁሉንም ረስቼ
ገስግሼ ወደ ቤቱ እጆቼን ዘርግቼ
በአዲሱ መንፈስ ልብሴንም አጥቤ
መቃኘት ነው ዛሬ ፍቅርን ገና አንግቤ
አሁን እንደ አለፈው አይደለሁምና
ያስመሳይ ማንነት ተወግዷልና
አትዩኝ ሰዎች እንደ በቀደሙ
አትሞኛልና በህያው ቅዱስ ስሙ
አትሞኛልና በህያው ቅዱስ ደሙ.አሁን ግን የሱ ነኝ......
ከአምላኬ ርቄ ለስጋ ያደላው
በእራሴ ዛፕያ ጉዞዬን ያቀናው
ፆም ፀሎት ረስቼ አርብ ሮብ ገድፌ
ነብሴን እየጎዳው ለስጋ አጭልፌ
በብልጭልጭ ነገር ስጋ እንዲደለድል
እራሱን በሰጠኝ አንድም ሳያጎድል
እስከ መስቀል ታዞ ገሎ ሞትን በሞት
ልቡን እስከ መቃብር የሰጠኝ ሳይሰስት
እና አሁንስ እኔ ግን የማነኝ
ባጠፋሁት ጥፋት ወጥቼ ከገነት
ሁለት ሞትን ሞቼ መኖሬ በሃጥያት
ፍጠረኝ ሳይለኝ ፈጥሬያለሁ ብሎ
የፍቅር መገለጫ እፀበለስ ተክሎ
በኋለኛውስ ዘመን በመስቀል ተሰቅሎ
ህይወት የተሰጠኝ ስለኔ ተብሎ
ፍቅርን በተግባር ገልጦ ቢያሳየኝ
እኔስ ለመታገስ በእውኑ የተሳነኝ
በእርግጥ እኔ ግን ማነኝ
ራሱን ጥሎ ከከፍታ ወርዶ
ሊያድነኝ ከሰማይ ከድንግል ተወልዶ
ፍቅር መታገስን ቅንነት ተስፋን
በመከራው መስቀል በመስቀሉ ታሞ
በአደባባይ ለኔ ቀራንዮ ላይ ቆሞ
ስጋውና ደሙን ሰቶ ለህይወቴ
ከሲኦል እሳት ያወጣኝ አባቴ
በኔ ፈንታ ስድብ ምራቅ ለተረጨበት
አንዷን እንኳን መክፈል ያልተቻለኝ በእውነት
እረ ንገሩኝ እኔ ከወዴት ነኝ
ልጁ ለኔ ደስታ ጧት ማታ እየተጋ
እሱ ለኔ ስኬት  ለከፈለው ዋጋ
ህግና ስርአቱን ሳልፈፅም ቢመጣ
እና ስበድለው ንስሃም ሳልገባ
ይሆናል እንዴ ወደ ቤቴ ግባ
በፍፁም ካልታጠበ አይችልም ሊገባ
ዳግም ላትሸልመኝ ከንቱነትን ምድር
ልመለስ ወሰንኩኝ ከክርስቶስ ፍቅር

27.፨ምነው እመብርሃን፨
አዬ ምነው እመብርሀን
ኢትዮጵያን ጨከንሽባት
ምነው ቀኝሽን እረሳሻት
እስከመቼ ድረስ እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት
ልቦናሽን ታዞሪባት
ፈተናዋን ሰቀቀኗን ጣሯን ይበቃል ሳትያት
አላንቺ እኮ ማንም የላት
አውሮፓ እደሁ ትናጋዋን በፋሺስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ ተምሳ በስብሳ
ምድራዊ እባጭ ጫንቃዋን እንደ ኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት ስልጡን ብኩን መፃጉዕ ናት
እና ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ውጋጋን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ በርታ በይኝ እመብርሀን
ቃልኪዳኔን እንዳልረሳት እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይክዳት ሰጋሁ
አዋጅ የምስራች ብዬ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማህፀን አልፌ በኢትዮጵያ ማህፀን አርፌ
ካፈሯ አጥንቴን ቀፍፌ ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟወዟን ቀፍፌ
በህፃን እግሬ ድኬባት በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ
በጋው የረኛ አደባባይ ክረምት እንደ ወዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ በገደል የሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅና ከሚዳቋ ከጅግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር እሩጫ ስገጥም ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከራዳ ጫፍ ሳር ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎቼ እራት ለማታቸው ጥቂት ድርቆሽ
ለግልገሌ ከአውሬ ከለል እማሳው ስር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሳር ሲለመልም ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከምበል ሲል ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመብርሀን ምነው እረሳሻት
ያቺን የልጅነት ምስራች የህፃንነት ብስራት
የሳቅ የፍንደቃ ዘመን የምኞት የተስፋ ብፅዓት
ያቺን የልጅነት እናት
አዛኝቱ እንዴት ብለሽ ጥርሶችሽን ትነክሺባት
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት ቅኔ ቤት ከድጓ ቤት መጻህፍት
ካንቺ ተቆራኝታ እድሌ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀ ሰላም ከቤተልሄም ቅዳሴ
አኮ... ቀዶ.. ቀፍፎ .... ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ .....ግስ ገሶ
መቅደስ አጥኖ ማሕሌት ቆሞ
በልብሰ ተክሕኖ አጊጦ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመብርሀን ያንቺ ፅላት ነፍሴ ላይ በሳት ታትሞ
የመናኒው የአባ ተድላ ርድ ሆኜ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ፀንሶ
ስጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ሆነሽኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ በወንበሩ አኖርሽኝ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያን ዛሬ ኢትየጵያ ስትወድቅ ከምትሰጪኝ ለፍርሃት ጦስ
ምነው በእረኝነት እድሜ አይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥምብ አንሳ ከንፎ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
እባክሽ እመብርሀን ይብቃሽ እባክሽ ስለ ፍቅሩ ወልዳ
ፅናት ስጪኝ እንድካፈል የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ከነደደችበት እቶን
የእሷን ሞት እኔ እንድሞታት ገላዋ ገላዬ እንዲሆን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
ህፃን ሆኜ የርግብ ጫጩት
አንዳንዴ ራብ ሲያዳክማት
ችጋር ከጎጆዋ ገፍቶ እዛፉ ግርጌ ሲጥላት
እናቷ በርራ ደርሳላት
በአክናፏ ሙቀት ታቅፋት
እፍ እያለች ግንባሯ ላይ ሕይወት ስተነፍስባት
ወዲያው ነፍስ ትዘራለች
ችር.... ብር.... ትር.... እያለች
እባክሽ

28.ወደ ማምሻው
አጭር ግጥማዊ ጭውውት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተራኪ .......እገሌ...          አንድ ቀን ጠላቴ እንዲ ሲል መጣና
                                       በጓደኞቼ ልብ ከንቱነት ዘራና
                                       አንድቀን በማታ ጓዴዎች ጠሩኝና
                                       እንዲ ሲሉ ነገሩኝ በውስጣቸው አደባና
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይ........እገሌ...  ለምን አንሰራም የግል ስራችን
                                  ራቅ ያለ ስፍራ እኛ ወጣ ብለን
                                  ለምን የቢዝነሱን ስራ አንሰራም
                                  አንተ ከቤተሰብ ተማከር በሰላም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተራኪ......እገሌ...ብለው ተለያየን እኔም ቤት ገባሁና
                            ቤተሰብ ባለበት ሃሳቤን ዘራሁና
                            የድርሻዬን ስጡኝ አልኩ ኮራ አልኩና
                             አባቴ በሃሳቤ እጅግ አዘነና
በትረካው  መኋል አባት ድምፁን ዘግቶ ይመክረዋል
                            ቢለኝ ቢገስፀኝ አልሰማ አልኩኝና
                             ንብረት ተካፈልኩኝ ወርቄን ሰበርኩና
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተራኪ.....እገሌ...ጓደኞቼም መተው በጠዋት በማለዳ
                          እንገስግስ አሉኝ ወደ ሃጥያቱ ጓዳ
በመኋል ጓደኞቹ እያቻኮሉ ይወስዱታል
                          እኔም ተከትዬ ብዙ በራኩ ጊዜ
                          ብሬ ከእጄ አለቀ ወደኩኝ በትካዜ
                          ጓደኞቼም ሸሽተው ከዳር ተበትነው
                          እኔ ሜዳ ቀረው እንደ መናኝ ሰው
                          ቀን በቀን ሲጨምር ርሃብና ጥሜ
                          አይዞህ ሚለኝ ጠፍቶ የሚቆም ለህመሜ
                          ባጣ ቢቸግረኝ ለስራ ዘምቼ
                         ሰርቼ አልሆን ሲለኝ ሳድር ተደፍቼ
                         ወደ አጨዳ ማሳ ዋናውን ለመቃረም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይበመኋል ማጭድ ይዞ ሲያጭድ ባለቤቱ ያባሯል በዝግታ ድምፅ
                         ስሰራ ሳበላሽ ስገፋ ከአለም
                         ወደ አንድም ስፍራ አመራና እግሬ
                         ልጠራርግ ገባው የአሳማ ፍርፋሬ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይ ሰውየውም እየተሳደበ እየመታው ያባሯል
                         የቤቱም አለቃ እያጉረጠረጠ
                         ገፍቶ አባረረኝ  እየረጋገጠ
                         አሁንስ ሲከብደኝ ኑሮ ሲዛባብኝ
                        የሰበርኩት ወርቅ ከልቤ ተሰማ
በመኀል ልጄ ተመለስ የሚል ድምፅ ይሰማል
                      ያኔ ባባቴ ቤት እጅግ ተትረፍርፎ
                       እበላ እኖር ነበር ሁሉ ነገር ተርፎ
                       አሁን ወደ አባቴ እንደ ገና አቅንቼ
                       እንደ ልጅህ ሳይሆን ከጉያህ ተደፍቼ
                       ከባርያዎችህ አንዱ አድርገኝ ብዬው
                       ከእግሩ ተደፍቼ እለምነዋለሁ
                       ብዬ ገሰገስኩኝ ከቀድሞዋ ሃገሬ
                      ግን እሺ ይለኝ ይሆን እያልኩ ከመንደሬ
                       አባቴም አይቶኝ ከሩቅ ሳለው ገና
                       እንባው ከአይኖቹ ዱብዱብ አለና
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይ ሲናገር
                      ወዮ ልጄ እያለ እያቀና
                       የቀደው ልጄ ጠፍቶ የነበረው
                        ከኔ ተለይቶ ሞቶ የነበረው
ተራኪ........እገሌ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እያለ አባቴ በደስታ እያነባ
ከእቅፉ ወሰደኝ ከፍቅሩ እያስገባ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናዩ አባት ሲናገር
አባቴም አለ ልጄ አሁን መቷል
የጠፋው የሞተው በዳግም ተነስቷል
ንፁሁን በግ አምጡ ፍሪዳው እረዱ
መንገደኛው ሁሉ ጥሩ ከመንገዱ
አባት ሲል ሲናገር ወንድም ከች ሲል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይ ወንድምየው ሲናገር
ይሁሉ ምንድነው ብሎ ሂሳብ ሲስል
ከባርያዎቹ አንዱ ወንድምህ መቶ ነው
አንተም ከደስታው ተቀላቀል ቢለው
ወንድም ልቡ ጠቁሮ ፊቱ እየሳቀ
በንዴት ተጠምዶ አንዴ እየተደነ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይ ወንድሙ ሲናገር
ከደስታው ማብቂያ ወንድሙን ጠራና
ለምን ተመልሰህ መጣህ እንደገና
ቢለው ቢጠይቀው መረር አለውና
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይ የጠፋው ልጅ ሲናገር
ወንድም መለሰ ቀስ ብሎ እያፅናና
አለምን እንዳያት እግዚአብሔር ላከኝ
ሁሉንም አየሁት ጉዳት ብቻ ታየኝ
ከጎጂው በስተቀር ጥቅሙ ስላልታየኝ
ዳግም እንድመለስ እግዚአብሔር ጠራኝ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዋናይ ወንድሙ ሲናገር
ወንድሙ ተደንቆ ልቡ ፊቱ ስቆ
ይቅርታ ጠየቀው ከእግሩ ስር ወድቆ።
--ተፈፀመ--
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

29.ንግስና እንዴት ነበር?


ንግስና እንዲህ ነበር ተኝቶ በራዕይ
እዛሬ ላይ ሁኖ የነገው ንግስና በህልም የሚታይ
በወንድም ተሽጦ በባርነት ኑሮ
ባላደረገው ላይ ፍርድ ሸንጎ ውሎ
የታየው ራዕይ እውን እንደሚሆን ልቡ ስላመነ
መጣል መገፋቱን አምኖ ይሁን አለ
መመረጥስ እንዲህ መሾምስ እንዲህ ነው
ዮሴፍ የነገሰው ምድረ ግብፅ ላይ ነው
ሙሴ እንዴት ነገሰ?
ሙሴ የተሾመው ከማህጸን ነበር
ፈርኦን ነግሶ ህዝቦችን ሲያሸብር
እስራኤልን ገዝቶ በባርነት ቀንበር
እናም
እናም በዛ ጊዜ
ወልዶ መቅበር እንጅ ማቀፍ እኮ የለም
የራሔል እንባ ግን መሬት ፈሶ አልቀረም
እግዜሩም ጠራና ሙሴን እንዲህ አለ
ህዝቦቸን እንዲለቅ መልዕክት ንገር አለ
ቅንና የዋሁ ሙሴም እንዲህ አለ
እንዴት ነጻ ላውጣ ህዝብህን አድኜ
እኔ አፌ ኮልታፋ በምን አንደበቴ ንጉሥ አሳምኜ
ለእስራኤላውያን የነጻነት ቀን ሲመጣ
ሙሴም በእምነት ህዝቡን ይዞ ወጣ
ከጠራው አምላክ ጋር እየተማከረ
ህዝቡን ለማሻገር ባህርን ከፈለ
በምድረ በዳ ላይ መናን ተቀብሎ ዘመን ተሻገረ
ዳዊት እንዴት መጣ?
ከበረት ተወልዶ እረኛ የሆነው የላይኛው ጌታ
ከእረኝነት ጓዳ ዳዊትን መረጠው ጎልያድ እንዲረታ
ሳኦል የነገሰው ህዝቡ ጠይቆ ነው
የሳኦል ንግሰቱ መንገድ መጥረጊያ ነው
የዳዊት ንግስና ከአምላክ ንግስና ጋር ምሳሌው አንድ ነው
እረኛ ነበረ ዳዊት ሳይጠራ
የነገሰ ጊዜ እንደ ልቤ ተብሎ በአምላኩ ተጠራ
የአሁኑስ እንዴት ነው?
ንጉሱ ባሉበት ግብር ይበላሉ?
መሪና ተመሪ ይተዋወቃሉ?
ንግስናው ከየት ነው?
ምንጩስ ከወዴት ነው?
ንጉስ የሆነውስ ለየቱ ወገን ነው?
ለዛኛው ወገንስ ንጉሥ የትኛው ነው?
መሪማ ሙሴ ነው
ህዝቤ ከሚጠፋ እኔ ልጥፋ ያለው
ልጥፋ ያለው ደግሞ ከሕይወት መዝገብ ነው
የአሁኑ ንጉሥስ
ምን ብሎልን ይሆን ምንስ ሲል ተሰማ
ምንም አይበልልን ምንም ሲል አንስማ
ይልቅ ይ ል ቅ
አምላካችን ታርቆን ታሪክ በታደሰ
ሙሴያችን በመጣ ዳዊት በነገሰ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
በሳምራዊት አይቸው (ወለተ መድኅን)
ቅዳሜ ፳፰/፪/፳፻፲፫

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።


መነባንብ
አይዞሽ እናት አለም አትዘኝባቸው
አይክፋሽ አያሳዝንሽ
ዛሬ እኛ ብንክድሽ
እኛ ብናቋሽሽ ብንጠላሽ
ቃልሽን ሰምተን ብንጥለው
ጥበብ ምስጢርሽን ብናጎድፈው
እውነተኛ የወንጌል ምንጭሽን ብናደርቀው
በውስጥሽ ተሰግስገን ብናጎሳቅልሽ
ለጠላት አሳልፈን ብንሰጥሽ
ሰምተን እንዳልሰማን ሆነን ብናለፍሽ
አታልቅሽብንም እናታለም አታዛኝብን
እኛ ------ብንሸሽ
እኛን ሳትጠሪ ባንሰማሽ
መጡ እንባሽን ሊያብሱ ልጆችሽ
በእውነት የወለድሻቸው ከአብራክሽ
ቃልሽን ሰምተው በእውነት የቆሙልሽ
በእውነት ምግባር የመሰከሩልሽ
መጡ ዳግም ሊናገሩ ታሪክሽን
መጡ ሊያስተውሱን ሊነግሩን
የጥንት የጥዋቱን ሊያስታውሱን
የኛ መክዳት አሳዝኞን ሊያጽናኑን
የኛ ባድነት ሲነግሩን እውነቱን ሊያሳዩን
ሳንሞት ሞተን ለቀረነው
በለያችን የሀጢያት መቃብር ለተገነባው
አትዘኚ እናት አለም
አታልቅሽብን
ይበቃል የፈሰሰው እንባሽን ጥረጊ
የለበሰሽውን ማቅ አውልቂ
የፍትሽን አመድ ጥረጊ
ምንም ታጥቦ ጭቃ ቢሆንም ስራችን
አለንልሽ በማለት አይደፍርም ቃላችን
እውነት ከደቶናል ከለያችን
እናት አለም
እናት አለም ዳግም ማቅ እንዳናለብስሽ
ቃልሽን ለትውልድ እንድናደርስልሽ
ከቤትሽ እንዳንጠፋ ልጆችሽ
በእውነት እንዳንመላለስ
ያለፈውን ይቅር ባይ
ለአሁኑ ጠብቂን /2/
እመኝን እናት አለመ
ዳግመኛ አናስከፋሽም
አናሳዝንሽም
ሰማን እስጢፋኖስ ሊቃ ሰማእታት
ሳትጠራ የመጣህባት እናትህ በእውነት
ቆመህ መስከርክላት እንደ ጥንት
አስታወስክላት ለከዳት
ለኔደ ከቤቷ ጥሏት
ነገርኮላት አሳሰብክላት
ዳግም እንዳናስከፋት እናትህን
ይጠብቀን አጽም ጸሎትህ
ይርዳን እስከዘላለም
ቃልህን እንድናሳውን ለትውልድ
እንዳንጠፋ እናትህ እንዳንክድህ
ሰማን አትናቲምስ እናትህን ብናስቀይም
ቃልህን ሰምተን ትዛዝህን ባንፈጽም
አትዘንብን በኛ በልጆችህ
ሀጢአት ላደከመን የጽድቅ መንገድ ለጠፋን
በእናትህ ላይ ማቅ አመድ መጨመርን
ይቅር በለን ተማጽነናል በቃልህ
ዳግም አናስከፋም ልጆችህ እናትህ
ዲዮለቆሮስም አትዘንብን
የሀይማኖት ፍሬ ይህ ነው ብለን ሰጠኸን
እኛ ግን ለወጥነው በጥቅም ላይ ነን
አትዘንብን ዲዮቆሮስም ብናስከፋህ እናትህ
ዳግመኛ ከረፋክባት ብንቀሰቅስህም
ተመጽነንሀል በረገፍው ጥርስህ
ዳግም እንዳንቀሰቅስህ
አትዘኝብን እናታለም
ተማጽነንብሻል በልጆችሽ
በዲዮስቆሮስ በአትናቲኖስ
በእስጢፋኖስ
አትዘኝ እናት አለም
አታልቅሽ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

፨ማን ነው አትበሉኝ፨

ማን ነው አትበሉኝ የደማ ላንተ


ማን ነው አትበሉኝ አደኖህ የሞተ
በአብ በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ
በምድር የመጣ የሰማይ ንጉስ
ከከብቶቹ ጋጥ ውስጥ የተወለደለኝ ከድንግል እናቴ
እኔ ሞቼበት ነው ሊያድን ከሃጥያቴ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
በወርቅ አክሊል ምትክ እሾህ የለበሰ
እንባዬን ሊያብሰው ደሙን ያፈሰሰ
እኔኑ ሊያድነኝ ሲገርፍ የዋለ እኔ ግን የካድኩት
ለማተብ መኖርን ያስተማረኝ እምነት
ብርክክ የምልለት የንጉሶች ንጉስ
እልል ይባልለት ለኔ ጌታ እየሱስ
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ አድኖህ የሞተ
እንደ ጴጥሮስ ሆኜ ብክደውም ቅሉ
ዶሮ ሳይጮህ ሶስቴ ሳይል አኩሉሉ
እሱ ግን እሱ ነው የይቅርታ ንጉስ
ምህረትን ለመስጠት ዘውትር የማይሰለች
እየሱስ ነው ጌታ ፊቱ የሚያበራ
ግርማው የሚያስፈራ
እናም..
ማን ነው አትበሉኝ ደም የደማ ላንተ
ማን ነው አትበሉኝ ሊያድንህ የሞተ።

"ድንግል ማርያም መርህ ለመንግሥተ ሰማይ ለምን ተባለች?"


~ቡዙ ጊዜ ተሃድሶዎች መናፍቃን በመጻሕፍት ሆነ በተለያዩ የሚሰርዎቸው ቪዲዮዎች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ለመቃወም ሰለ እመቤታችን የተጻፉ መጻሕፍት ሲነቅፉ እንሰማለን፡፡ ከለማወቃቸው ከሚነቅፉዎቸው መጻሕፍት አንዱ
ተአምረ ማርያም ነው፡፡ መናፍቃኑ "ታአምረ ማርያም ከክርስቶስ ለይቶን የኖረ ነው፡፡ ለምሳሌ ማርያም ቢሂል መርህ
ለመንግስተ ሰማይ ይላል ይህ ደግሞ ክርስቶስ የሚያሳጣ መልእክት ነው ፈጽማ መንግሥተ ሰማይ ልታሰገባ አትችልም"
ይላሉ፡፡
~ይህን ብለው ከሚናገሩ ግን ምን ማለት ነው ብለው ቢጠይቁ ይሻላቸዋል ነበር የማያውቁት ከሚፈተፈቱ ይልቅ፡፡
በመሰረቱ ታአምረ ማርያም ምን እንደሚል ለምን እንደተጻፈ ለማወቅ ሆኖም አፍህ ሞልተህ ለመናገር መጀመሪያ
ሰለታአምረ ማርያም በቂ የሆነ እውቀት ሊኖርህ ፡፡
ይገባልሰለ እመቤታችን መርህ ለመንግሥተ ሰማያት መሆንዋን ለማወቅ መጀመርያ የመንግሥተ ሰማያት ባለቤት ማን ነው?
የሚለው ጥያቄ ማወቅ ያሰፈልጋል፡፡
~ታአምረ ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን አምለካች ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያሳጣ ሳይሆን ሰለአምላካችን እንድናውቅ የበለጠ
ወደ እርሱ እንድንቀርብ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በትክክልም መርህ ለመንግሥተ
ሰማያት ናት ታአምሩም ትክክል ነው፡፡ በመሰረቱ የመንግሥተ ሰማያት ባለ ቤት እግዚአብሔር ነው፡፡ ለዚህ ነው በሉቃ-23፡42
ላይ ወንበደው ባለ መንግሥት መሆኑ አውቆ" ጌታየ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ" ብሎ የለመነው፡፡ ይህች
መንግስተ ሰማያት ደግሞ አዳም ባደረገው በደል በኃጢያት ምክንያት ተዘግታ ነበረ ፡፡
~ወደዚህ መንግሥት ለመግባት ደግሞ የተዘጋው መከፈት አለበት የሚከፈተው ደግሞ የሰው ልጅ ከኃጢያቱ ድኖ ከተፈረደበት
ፍዳ ባርነት ነጻ ሲወጣና ያጣውን የልጅነት ሀብት ሰመለስለት ነው፡፡ ምክንያቱ ወደዚህ መንግሥት ለመግባት የግድ ልጅነት
ማግኘት አለበት፡፡ የሚያገኘው ደግሞ ድኅነት ከተፈጸመለትና ካሳው ከተከፈለለት በኃላ በጥምቀት ልጅነቱ ያገኛልና፡፡ ድኅነት
ከለተፈጸመ እግዚአብሔር ካላዳነን ጥምቀት አይኖርም የሰው ልጅም ልጅ አይባልም ካልተባለ ደግሞ ልጅነት ከሌለው ወደ
መንግሥቱ መግባት ሆነ ወራሽ ሊባል አይችልም፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ " ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት
የእግዚአብሔር ወራሾች ነን" ሮሜ- 8 : 17 ያለው፡፡
~ጥምቀት ለመፈጸም ሰው ከፍዳው የግድ መዳን አለበት ምክኒያቱ የሚወርሰው ካለተከፈተ ወዴት ይገባል፡፡ የሰው ልጅ
ከተፈረደበት ፍዳ መዳን አለበት፡፡ ይህ ድህነት የሚፈጸመው ደግሞ በክርስቶስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ሰው ከሲኦል
ለማውጣት በደሉ ለመደምሰስ ሰው መሆን አለበት ምክያቱ የበደለ ሰው ሰለሆነ ሰው ሲሆን ነው የሚከፈል እና፡፡
ዕዳው
~በዚህ ጊዜ ነበር የድንግል ማርያም ወሳኝ የድህነት ሚና የተወጣቹው፡፡ ማስተዋል ያለብን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል
ልያበስራት ሲመጣ እስዎ ሙሉ ነጻነት ያለት ናትና ከእኔ አይወለድም ብትል የዓለም ድህነት የመንግሥተ ሰማያት መከፈት
ምን ይሆን ነበር? አስገድዶ ከእርስዎ ይወለዳል እንዳይባል እርሱ የነጻነት አምላክ ነውና ለባሕሪው
እግዚአብሔርየማይስማማው አደረገ ሊባል ነው ይህ ደግሞ ህጸጽ አለበት እግዚአብሔር ደግሞ ህጸጽ ያለበት አምላክ
አይደለም፡፡ ሰዓቱ ጊዘው ለሰከንዶች እንኳ ቢሆን ከዘገየ ደግሞ የሚያፈርስ ቃሉን የማይጠብቅ አምላክ ይባላል ይህም
ለባሕሪው ቃልኪዳኑአይስማማውም፡፡
~አይ ከሌላ ሴት ይወለዳል እንዳይባል ፡-
1.በምድር ላይ እንደ ድንግል ማርያም ያለች ንጻሐ ነፍስ ንጽሐ ሥጋ አሰተባብራ ድንግል በሥጋ ድንግል በሕልና የለም ፡፡ ለዚህ
ነው"በአማን ነጸረ እግዚአብሔር አብ እምሰማይ ምሥራቀ ወምዕራበ ወደቡበ ወውስተ ኵሉ አጽናፍ አስተንፈሰ ወአጼነወ
ወኢረከበ ዘከማኪ ወሠምረ ሰሜነመዓዛ ዚአኪ ወአፈቀረ ሥነኪ ወፈነወ ኀቤኪ ወልዶ ዘያፈቅር፡- እግዚአብሔር አብ በሰማይ
ሆኖ ምስራቅንና ምዕራብን ሰሜንንና ደቡብን ዳርቻዎችንም ሁሉ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰ አሸተተም እንደ አንቺ ያለ
አላገኘም የአንቺን መዓዛ ወደደ ደም ግባትሽንም ወደደ የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ" ያለው ቅዳሴ ማርያም፡፡
ሰለሞንም " ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም" መኃ- 4 : 7 ያለው፡፡
2.የተነገረው ትንቢት የተቆጠረው ስባኤ ማርያም ነበረ፡፡ ሰለዚህ ከድንግል ማርያም ነው ይህን ባያደርግ ቃሉ ለድንግልየሐሰት
ነው ይባላል፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ የሐሰት አምላክ አይደለም ይህ ለባሕሪው አይስማማም ፡፡
~አይ እርሷ ፈቃደኛ ካልሆነች ድኀነቱ ይቅር እንዳይባል ፡-
1. የእግዚአብሔር መንግስት አትከፍትም የሰው ልጅም አይድንም
2.እግዚአብሔር አድንኃለሁ ያለው ቃልኪዳኑ አይፈጸምም ሰለዚህ እግዚአብሔር የተናገረው የማይፈጽም ነው ይባላል፡፡ ይህ
ደግሞ ለባሕሪው አይስማሙም ፡፡
~ሌላ አዲስ ሰው ፈጥሮ ሰጋው ይለብሳል እንዳይባል ያጠፋ አደም ነውና የሚያድነው ሌላ ሳይሆን ከራሱ አዳም ዘር የተወለደ
መሆን አለበት የተነገረው ትንቢትም ከዳዊት ዘር እንደሚወለድ ነው ሰለዚህ ይህም ለባሕሪው አይስማማውም፡፡ አሁን ምን
ይደረግ?
~ሰለዚህ የድንግል ማርያም መኖር እጅግ ወሳኝ ነው፡፡የእስዋን "ይኩነኒ" ማለት ለድኅነት መርህ ለመንግሥተ ሰማያት መከፈት
ቁልፍ መርህ ሰለሆነም ነው መልአኩ ገብርኤል ይህን ቃል እስኪሰማ የጠየቀችው እየመለሰ የማይችለው ለእግዚአብሔር
የሚሳነው ነገር የለም እያለ በትዕግስት የጠበቃት፡፡ ይኩነኒ ስትል መልአኩ ሄደዋል፡፡ ይኩነኒ እስክትል ድረስ ግን መላአኩ ንቅንቅ
አላለም፡፡
~ይህ ቃል የሚያስረዳን ድንግል ማርያም ለድኅነታች ወሳኝ መሆንዋን ነው፡፡ አንዳንድ መናፍቃን ሆኑ ተሃድሶዎች እመቤታች
ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም ሰንላት ይነቅፋሉ፡፡ ለመሆን ቤዛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ክርቶስ ቤዘወነ ስል ምን ማለት ነው?
ይህ ቃል የግዕዝ ቃል ነው፡፡ ሰለ እኛ እራሱን ሰጥቶ ነቢይ ኢሳይያስ " በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም
ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።" ኢሳ-53 : 4 እንዳለው
ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ አዳነን ማለት ነው፡፡ ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም ብለን ከምንጠራባቸው ከቡዙ ምክንያተቀች
አንዱ "ይኩነኒ"ብላ ለዓለም እራስዋ መስጠትዋ ነው፡፡ ምክንያቱ የሰው ልጅ እንዲድን እራስዋ ለድኅነት ይኩነኒ ብላ ሰጥታ
የድኅነት መጀመሪያም መፈጸምያም የሆነችው፡፡
~መጀመሪያ ሰንል ድያብሎስ በዘር በሩካቤ ቅቤ በድንጋይ ሲፈስ እንደሚወሃሃድ እየተወሃሃደ የአዳም ዘር በሙሉ የሲኦል
ባርያዎች ያደርገው የነበረው እንዲቆረጥ በድንግል ማኅጸን ተጸንሶ ቆርጦታል የመጨረሻም ስንል ክርስቶስ በቀራንዮ ሲሰቀል
ሰይጣን ስቀጠቅጦው የተቆረሰው ሰጋ የፈሰሰው ደም ከድንግል ማርያም የተወሰደ ነውና፡፡ ሰለዚህ ድንግል ማርያም ቤዛዊተ
ዓለም ስንል ቤዛዊተ ዓለም ሰለሆነች እንጂ ስላልሆነች ሆኖ አይደለም፡፡
~ሊቁ ቅዱስ ሄሬኒዎስ" ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ሰውን የማዳን መለኮታዊ አሠራር ጋር ተባብረች" ያለው ለዚህ
ነው፡፡ ለዚህ ነው መቅድመ ታአምረ ማርያምም ማርያም ቢሂል መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ያላት፡፡ ወደ ባለመንግሥቱ ወደ
ልጅዎ መርታ የምታደርስ ናትና፡፡ መርታ ወደ ድኅነት ሰላደረሰችን ነው ድኅነት የፈጸመው ክርስቶስ ከእርስዎ የተወለደው፡፡
ክርስቶስ በመወለዱ መላእክት ከእረኛች አብረው ዘምረዋል፡፡ ክርስቶስ ተሰቅሎ ዓለም አድነዋል ፡፡የተቆረሰው ሥጋ የፈሰሰው
ደም ዓለም የዳነበት ከእርሷ በነሣው ሥጋ ነው፡፡ ታዲያ እመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም መርህ ለመንግሥተ ሰማያት
ብትባል ምኑ ላይ ነው ስህተቱ?
~አደለም እመቤታችን ቅዱሳንን እንኳ መርህ ናቸው፡፡ " ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም
ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። እውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና
ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል" ማቴ- 10 :14-15 ብሎ የተናገረው ከእነርሱ የተለየ ዋጋ እንደሌለው ሲገልጽና መንግሥቱ
እንደማይወርስ ሰያስረዳን ነው፡፡ሰለዚህ ቅዱሳንም ወደ መንግሥተ ሰማያት መረተው ያሰገባሉ ነው፡፡
~በሌላ ቦታም
" በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን
ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ
ብርሌ የጠራ ነበረ፤
ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፥ አሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ፥ የአሥራ ሁለቱም
የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር። በምሥራቅ ሦስት ደጆች፥ በሰሜንም ሦስት ደጆች፥ በደቡብም
ሦስት ደጆች፥ በምዕራብም ሦስት ደጆች ነበሩ።
ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው
ነበር" ራዕ-21 ፡10-14 ተብሎ የተጻፈው ሐዋርያት መርህ መሆናቸው ከእነርሱ የተለየ መግባት እንደማይች እነሱ መንግሥተ
ሰማያት ለመግባት መሰረት መሆናቸው ነው፡፡
~ ሰለዚህ ቅዱሳን ይህን ያህል ከተባሉ የክርስቶስ እናቱማ እንዴት መርህ አትሆንም ይባላል፡፡ ሰለዚህ ማርያም ማለት
መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታገባ ማለት ነው የሚለው ትክክል ነው ከክርስቶስ የሚለይ አይደለም ይሉቁንም የሚያቀርበን
ነው፡፡
የእመቤታችን ምልጃና በረከት አይለየን፡፡ አሜን!!!!!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡


“ማንም ኃጢያትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ”1 ኛ ዮሐ. 2፡1
ቢብራራልን?
++በመልዕክቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች++
"ማንም ሐጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" 1 ኛ ዮሐ 2:1
መልዕክቱን ከላይ 1 ኛ ዮሐ 1:5 ጀምረን ስንመለከት ስለ ኃጢአትና ስለ ንስሐነበርና ነው፡፡ ግኖስቲኮች ይህን ይቃወሙ ይህን
በማፍረስ አስተምራል፡፡
ግኖስቲኮች "መዳን በዕውቀት" ነው በማለት ንስሐን በመቃወም ያስተምራሉ፡፡
1 ኛ. ግኖስቲኮች ከእግዚአብሔር ጋር የሚፈጠር ህብረት ከሐጢአት መለየት ነው፡፡ ስለዚህ የፈለግነውን ብናደርግ ሐጢአት
በእኛ ዘንድ ሊኖር አይችልም ብለዋል፡፡ በመልዕክቱም "ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማ ግን ብንመላለስ እንዋሻለን"
እያለ መልስ ሰጥቷል።
2 ኛ.ሐጢአት የለብንም ምክንያቱም አንድ ጊዜ ጌታን ተቀብለናልና ለምንሰራው ስራ በደለኞች አይደለንምየለብንም
ሐጢአትን አንድ ጊዜ አጥፍቶልናል ይሉ ነበር፡፡ ሐዋርያውም "ሐጢአት ብንል ራሳችንን እናስታለን፡፡" እያለ መልስ
ሰጥቷቸዋል፡፡
3 ኛ.ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ያለው ሐጢአትን አይሰራም በማለት ያስተምሩ ነበርና "ሐጢአት አላደረግንም ብንል
ሐሰተኛ እናደርገዋለን መንፈሱም በእኛ ውስጥ የለም" እያለ እኚህን የመሰሉ ንስሐን የሚቃወሙ ትምህርቶች ነበሯቸውና
መልስ ሰጥቷል፡፡በዚህ መልኩ ከመለሰ በኋላ የንስሐ ፍፃሜው ሐጢአትን በማስተሰረይ በእግዚአብሔር ፊት እንድንቆም
የሚያስችለን የልጁ ስጋና ደም በመቀበል ነው ለማለት የተናገረው ነው፡፡ሐጢአትን ብንሰራ በምን ሐጢአታችን
ያስተሰርይልናል ብላችሁ አትጨነቁ፡፡ "ማንም ሐጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው እርሱም የሐጢአታችንመሆኑን ማስተሰርያ ነው በማለት "ጠበቃ" ተብሎ የተገለፀው ስንቀበለው
ሐጢአታችንን የሚያስተሰርይ ስጋና ደሙ አስቀምጧል፡፡ ዝቅ ብሎም ክርስቶስ ደሙ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡ የኢየሱስ
ክርስቶስ ደም ከሐጢአትየኢየሱስ ሁሉ ያነፃል የተባለውም ንስሐ ገብተን የምንቀበለው ስጋና ደሙ ከሐጢአታችን የሚያነፃ
መሆኑን የንስሐ መፈፀሚያ ፍፁም የሐጢአት ስርየት ማግኛ መሆኑን በመናገሩ ነው፡፡ (ሁለቱ ኪዳናት)

"ጠበቃ" የሚለውን ቃል ወስዶ "ስለ እኛ ይከራከራል ያማልዳል" ማለት ስህተት ነው፡፡ አምላክን ሊከራከረው የሚችል ማን
አለ?? ይህ ንግግር አምላክነት ካለመረዳት የመነጨ የዘመኑ የግኖስቲክ እርሾ ነው፡፡
ዘወትር ስለሐጢአት እኛን የሚከስ ጠላት ዲያብሎስ የሚያሳፍር ነውና "ጠበቃ" ብሎታል፡፡ እንጂ ስለ እኛ ይከራከራል ማለትስ
አይደለም፡፡ በራዕ 12፡10-11 ላይም "ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ዲያብሎስ
ተጥሎአልና ከበጉም ደም የተነሳ ከምስክራቸውም ቃል የተነሳ ድል ነሱት" በዚህም ክፍል ላይ "ዲያብሎስን ከበጉ ደም የተነሳ
ድል ነሱት" ይላል። የክርስቶስ ስጋ እና ደምን በመቀበል ሃጢአታችን ይነፃል። ዲያብሎስንም ድል
እንነሳለን። ይህን ከማስረዳት ውጪ አማናዊውን ትርጉም ባለመረዳት ኢየሱስ ክርስቶሰን "አማላጅ" ማለት ፍፁም ስህተት
ነው፡፡
በመቀጠልም ጠበቃና አማላጅ ያላቸውን ልዩነት እንመልከት
- ማለት ለተከሳሽ የሚከራከር ተከሳሽን ነፃ በማውጣት ከሳሽን የሚያሳፍር ነው፡፡
፡- ማለት በአንድ በከበረ ሰው ፊት አሊያም በእግዚአብሔር ፊት አንድን ሰው ወክሎ ይቅርታ የሚጠይቅ ወይም የሚለምን
ሲሆን በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ከመሆኑም በተጨማሪ የበዳዩን በደል ማለትም የአጥፊውን ጥፋት በመግለጽ በድሏል
እና ይቅር በለው ብሎ የሚለምን(የሚማጸን) ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ አማላጅ ኃጢያትን ገልፆ ይቅርታን የሚለምን ነው፡፡
በዚህ መሰረት የቃሉን ሀሳብ ስንመለከት ቅዱስ ዮሐንስ በመልዕክቱ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹን ኃጢያት እንዳያደርጉ
እንዲህ ሲል ይጽፍላቸዋል ቁጥር 1 ላይ ልጆቼ ሆይ ኃጢያትን እንዳታደርጉ ይህንን እጽፍላችኋለሁ ይልና ቁጥር 2 ላይ
ከስጋቸው ድካም የተነሳ ሳያውቁ በስህተት እያወቁ በድፍረት ኃጢያትን ቢያደርጉ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን በማለት የአብ
የባህሪ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃችን ነው ይላቸዋል፡፡
ምክንያቱም ሰው ኃጢያትን በሰራ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት የሚከስ ከሳሽ አለ እርሱም ሰይጣን ዲያቢሎስ ሰዎችን
በእግዚአብሔር ፊት እንደሚከስ ትን.ዘካ.3፡1-5 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡- ታላቁም ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ
ፊት ቆሞ አሳየኝ ሰይጣን ይከሰው ዘንድ በስተቀኙ ቆሞ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ሰይጣንን ሰይጣን ሆይ ኢየሩሳሌምን የመረጠ
እግዚአብሔር ይገስጽህ በውኑ ይህ ከእሳት ትንታግ አይደለም አለው፡፡ ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ
ነበር እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው እርሱንም እነሆ አበሳህን ከአንተ
አርቄያለሁ ጥሩ ልብስን አለብስሀለሁ አለው ደግሞ ንጹህ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉ አለ እነርሱም በራሱ ላይ ንጹህ
ጥምጥም አደረጉ ልብስንም አለበሱት የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር፡፡
በዚህ ታሪክ ላይ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ለኢያሱ አማላጅ ሆነለት ወይስ ጠበቃ ሆነለት ብለን ብንጠይቅ? አማላጅ
አልሆነለትም ምክንያቱም ኃጢያቱን በመግለጽ ሲለምን አልታየምና ነገር ግን  ሆኖለታል፡፡ ምክንያቱም ከሳሹን(ሰይጣንን)
አሳፍሮለታልና ነው፡፡ እንዲሁም ዳኛ(ፈራጅ) ሆኖለታል ማለት ነው እንጂ አማልዶታል ማለት አይደለም ምክንያቱም
የሀጥያትን ስርየት እራሱ ሰጥቶናልና።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።።

 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ጥያቄ፡ በሕጻንነት ዕድሜ ለምን እንጠመቃለን?
መልስ፡
አዳምና ሔዋን ሕግ አፍርሰው ከተከለከሉት ዛፍ ፍሬ ከበሉባት ሰዓት ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔርን ተገፈው
እርቃናቸውን ቀርተዋል፡፡ በወቅቱም የተሰማቸውን እንግዳ የሐፍረት ስሜት መቆጣጠር ስለተሳናቸው
ዕርቃናቸውን የሚሸፍኑበትን ቅጠል በገነት ካሉት ዛፎች ቆርጠው በሰውነታቸው ላይ አገለደሙ፡፡ እግዚአብሔርም
ከገነት ባስወጣቸው ጊዜ ያገለደሙት የቅጠል ስፌት የዚህን ዓለም ብርድ እንደማይቋቋምላቸው ስላወቀ ከእንስሳት
ለምድ የተዘጋጀ የሚሞቅ የቁርበትን ልብስ አለበሳቸው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የሰው ልጅ ሁሉ ልብስ ያስፈልገው
ጀመር፡፡ የዕድሜ ክልል ገደብ ሳይኖረው አረጋዊውም ፣ዛሬ የተወለደውም ሕጻን በጨርቅ የሚጠቀለል ሆነ፡፡
ማንኛውም ሕፃናት ልጆች ያሉት ጤናማ ወላጅ ልጆቹ የልብስን ጠቀሜታ ስላልተረዱ ‹አድገው እስኪረዱት ድረስ
እርቃናቸውን ይቆዩ› በማለት እንደማይተዋቸው የታወቀ ነው፡፡ ምንም ክፉና ደጉን ባይለዩ፣ ራቁት የመሆን
የሐፍረት ስሜት ባያሸንፋቸውም ፤ ከጤናቸው አንጻር በብርድ እንዳይታመሙበት ሲል ለልጆቹ በማሰብ ልብስ
ያለብሷቸዋል፡፡የሰው ልጅ ሥጋዊ ወይም ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ፍጥረት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ለግዙፍ
ሥጋው መጎናጸፊያ ልብስ እንደሚያስፈልገው ፤ ለረቂቅ ነፍሱም ልብስ ያስፈልጋታል፡፡ በልብስ ያልተሸፈነ ሰውነት
ለብርድና ለተለያዩ በሽታ አምጪ ሕዋሳት እንደሚጋለጥ ፣እንዲሁ በልብስ ያልተሸፈነች ነፍስም በኃጢአት
ከሚመርዟት አጋንንት ማምለጥ አትችልም፡፡ ታዲያ ይህ የነፍሳችን ልብስ ምንድር ነው? እንዴትስ ነው
የምትለብሰው?ድንኳን ሰፊ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነፍሳችን ስለምትለብሰው ረቂቅ በፍታና
ስለምትለብስበትም መንገድ ምንነት ለገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ ‹የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን
ለብሳችኋል› ሲል ይናገራል (ገላ 3፡27)፡፡ ከዚህም የሐዋርያው ትምህርት በመነሣት የነፍስ ልብስ የተባለው
‹ክርስቶስ› ሲሆን ፤ እርሱን የምንለብስበት መንገድ ደግሞ ‹ጥምቀት› መሆኑን እንረዳለን፡፡በዛሬ ጽሑፋችን
ምሥጢራትን በመመገብ የእናትነት ድርሻዋን የምትወጣው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለምን በሕፃንነት
ዕድሜያችን እንድንጠመቅ እንደምታደርገን በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ሲነሣ በተቃራኒ
የትምህርት ጎራ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን ከሚያቀርቧቸው የተቃውሞ አሳቦች መካከል ዋናዎቹ የሚከተሉት
ናቸው፡፡አንደኛው ‹ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ› የሚለውን
የቅዱስ ጴጥሮስን የስብከት ቃል ይዘው ‹እነዚህ የምታጠምቋቸው ሕጻናት ምን ኃጢአት አለባቸው?› ሲሉ
የሚጠይቁት ሲሆን ፣
✌ ️ ሁለተኛው ደግሞ ‹ገና ሕጻናት
ሲሆኑ ምን አውቀው ነው ያለ ፈቃዳቸው የምታጠምቋቸው?› የሚል ከማወቅ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ነው (ሐዋ 2፡
38)፡፡
 የመጀመሪያው ጥያቄ የጥምቀትን ጥቅሞች ካለመረዳት የመጣ ጥያቄ ይመስላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ጥምቀት
ከሚፈጸምባቸው ምክንያቶች አንዱ ለኃጢአት ስርየት እንደሆነ ቢናገርም ‹ለኃጢአት ሥርየት ብቻ› ግን አይልም፡፡
ከሁሉም በላይ በጥምቀት የምናገኘው ትልቁ ጸጋ ‹ልጅነት›ን ነው፡፡ ስለዚህም ታላቅ ጸጋ መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ለአይሁድ አለቃ ለኒቆዲሞስ ‹ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ… › በማለት በጥምቀት ስለሚገኘው
የእግዚአብሔር ልጅነት አስተምሮታል (ዮሐ 3፡5)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንደሚናገረው ቤተ ክርስቲያን
ሕጻናትን የምታጠምቀው ኃጢአት ፣በደል አለባቸው ብላ ሳይሆን ፤ ከለጋነት ዕድሜያቸው ጀምረው ፍቅሩን
እያጣጣሙ እንዲያድጉ የሚያስችላቸውን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን ጸጋ ልትሰጣቸው ነው፡፡
ወደ ሁለተኛው ጥያቄ ስንመጣ በራሱ በጥያቄው መነሻ አሳብ ላይ የምንመለከተው እንደ ገደል የሰፋ ክፍተት
አለ፡፡ ይህም ክፍተት ጥያቄውን የሚጠይቁ ሰዎች የተነሡበት ‹ሕጻናት አያውቁም› የሚለው ጭፍን መንደርደሪያ
ነው፡፡ እነርሱ ‹ሕጻናት እንደማያውቁ በምን አወቁ? አንድ ሕጻን ስላልተናገረና አሳቡን በቃላት ስላልገለጸ ብቻ
አያውቅም ሊባል ይችላል? ፡፡ እንዲህ ካሉ ደግሞ የጌታ እናት እመቤታችን ወደ እርሱ እንደቀረበች አውቆ በስግደት
የደስታውን ስሜት ስለገለጸው የስድስት ወር ፅንስ ምን ይላሉ? ሳያውቅ ነው የዘለለው ሊሉን ይሆን? ቢቀበሉ
ደግሞ ይህን የመሳሰሉ ድንቅ ማስረጃዎችን ከቅዱሳን አበው ገድላት እናቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እንኳን
የአዋልዱን ይቅርና የአሥራው መጻሕፍቱንም ምስክር ለማመን ስለሚቸገሩ ማስረጃ አናባክንም፡፡ታዲያ እነዚህን
ጥያቄዎች ስንጠይቅ እኛ ደግሞ በተቃራኒው ሕጻናት ያውቃሉ ወደሚል ሌላ ጽንፍ እያመራን አይደለም፡፡ ቤተ
ክርስቲያን ሕጻናትን የምታጠምቀው ያውቃሉ ወይም አያውቁም ብላ አይደለም፡፡ የቤተሰቦቻቸውን እምነት
ምስክር በማድረግ ነው እንጂ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በልጅነታቸው ጥምቀተ ክርስትና የተፈጸመላቸው እንዳሉ
የሚያሳዩ ልዩ ልዩ የንባብ ክፍሎች አሉ፡፡ ለአብነትም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በተመሳሳይ ምዕራፍ ላይ
የምናገኛቸውን ሐር ሸጯ ልድያንና የወኅኒ ቤተ ጠባቂውን ማቅረብ እንችላለን፡፡ መጽሐፉ ሁለቱም ሰዎች
ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደተጠመቁ ይናገራል (ሐዋ 16፡15 ፣34)፡፡ ታዲያ ከቤተሰቦቻቸው መካከል ሕጻናት ሊኖሩ
አይችሉምን?ሌላው በበዓለ ሃምሳ ከተሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ውስጥም ስለ ሕጻናት ጥምቀት የሚናገር
ግልጽ ማብራሪያ እናገኛለን፡፡ ይኸውም ‹ኃጢአታችሁ ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
ተጠመቁ… የተስፋው ቃል (ተጠምቆ መንፈስ ቅዱስን መቀበል) ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም
ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ነውና› የሚለው ሲሆን በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ‹ለልጆቻችሁ› የሚለው ቃል ያለ
ማብራሪያ ጥምቀት ለሕጻናት እንደሚፈጸም የሚያሳይ ነው (ሐዋ 2፡38-39)፡፡ ጌታችንም በወንጌል ‹ሕፃናትን
ተዉአቸው ፤ ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው› ሲል የተናገረውን ቃል እንዴት እንረዳዋለን? ሕፃናት ወደ
እግዚአብሔር እንዴት ይቀርባሉ? ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችሉት በምሥጢራት (Sacraments)
ነው፡፡ ታዲያ ከምሥጢረ ጥምቀት የበለጠ ሕፃናት እና አምላክን በአባትና ልጅነት የሚያቀራርብ ምን አለ? ሕጻናት
እንዳይጠመቁ ከመከልከል የበለጠስ እነርሱን ከፈጣሪ የማራቅ ሥራ ምን አለ? (ማቴ 19፡14)፡፡እነ ቅዱስ ጎርጎርዮስ
ነባቤ መለኮትም ቅዱስ ጳውሎስ ለጥምቀት ምሳሌ አድርጎ ያነሣውን የግዝረት ሥርዓት ለሕጻናት ጥምቀት ማስረጃ
አድርገው አስተምረውበታል፡፡ በአብርሃም ዘመን ግዝረት የእግዚአብሔር ሕዝብ ወይም ወገን ለመሆን ምልክት
ነበር፡፡ ስለዚህም በአብርሃም ቤት የሚወለዱ ሕፃናት ስምንት ቀን ሲሆናቸው እንዲገረዙ ሕግ ወጥቷል (ዘፍ 17፡10-
14)፡፡ ሕፃኑም በዚያ የቀናት ዕድሜ ላይ እያለ ይገረዛል እንጂ ቆይ ይደግና ጠይቀነው አይባልም፡፡ ልክ እንደ ግዝረቱ
በሐዲስ ኪዳንም ጥምቀት ከእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ጋር በሕዋስነት የምንቆጠርበት ምሥጢር ነው፡፡ ግዝረት
በሕጻንነት ይፈጸም እንደነበር ፤ ጥምቀትም በሕፃንነት ይፈጸማል፡፡ እንደ ቅዱስ ጎርጎርዮስም አባባል ‹የጣቶቻቸው
ጥፍር ሳይጸና› በጨቅላነት ዕድሜያቸው ይጠመቃሉ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!


ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 14 : 14
ወደማን ነው የምንጸልየው?
ጌታችን ስሜ የሚለው (ክርስቶስ) የሚለውን የሥጋዌ ስሙን ነው፡፡ ይህ ስም ሰውነቱንና አምላክነቱን፣ ምድራዊነቱንና
ሰማያዊነቱን፣ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን የሚገልጥ ስም ነው፡፡ቅዱስ ጳውሎስ "ከመላዕክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ
ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል፡፡ " ብሎ የተናገረው ክርስቶስ የሚለውን ስም ነው፡፡ ቅዱስ
ጴጥሮስም ብፁዕ የተባለው የተመሰገነው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ በማለቱ ነው፡፡ ማቴ 15:15-17
እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ሆይ ስማኝ ብሎ የሚጸልይ ሁሉ ጸሎቱ ይሰማለታል፡፡ ቅዱስ
ጴጥሮስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ አንካሳ የነበረውን ሰው "በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳ ተመላለስ፡፡" ሐዋ 3:6
ፈውሶታል፡፡ የሕያው የኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደፈወሰውም ሲመሰክር "በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና
የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፡፡" ብሏል፡፡ ሐዋ 3:16፣ ሐዋ 5:28 ቅዱስ ጳውሎስም የሟርተኝነት መንፈስ የነበረባትን
ሴት ባገኘ ጊዜ "ከእርሷ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ" ሐዋ 16:16-18 ብሎ ርኩሱን መንፈስ
አስወጥቶታልና፡፡ እኚህም ጥቅሶች "በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ" የሚለው ቃል እንደተፈፀመ ያስረዳል፡፡በዮሐ
16:23 ላይም "አብ በስሜ የምትለምኑትን አብ ይሰጣችኅል፡፡" በማለት በፈቃድ በስልጣን ከአብ ጋር አንድ መሆኑን
ያመለክታል፡፡ የአንድምታ ትርጓሜም እንደሚገልጠው በተሰቀለው በተቸነከረው ልጅህ ብላችሁ ብትለምኑ አብ
የለመናችሁትን ሁሉ ይሰጣችኀል በማለት ይገልጠዋል፡፡ በስሜ ማለት ሕማሜን መከራዬን እያሰባችሁ ብትለምኑ ልመናችሁ
ምላሽ ያገኛል ማለት ነው፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅም "መንፈስ ቅዱስ ከወረደላችሁ በኋላ በአካል የምታዩትና የሚያያችሁ
አስታራቂ አያስፈልጋችሁም ስሜ ይበቃችኀል ማለቱ ነው" ይላል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ
ቅዱስ በማለት ጸሎቷን ጉባኤዋን ጀምራ የምትፈፅመው ይህን ቃል አብነት አድርጋ ነው፡፡ ከዚህ በተለየ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን
አማላጅ ለማለት የሚዥጎደጎዱ ክፉ ሰራተኞች እንደሚሉት አይደለም፡፡ ለዚህም ነው በዮሐ 16:26 ላይ "እኔም ስለ እናንተ
አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለም፡፡" በማለት ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ሁሉን በስልጣኑ የሚያደርግ እንጂ የሚለምን እንዳልሆነ
በግልጥ አስቀምጦት እናገኛለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ጥያቄ፡ ወላዲተ አምላክን ሳይቀበሉ መዳን ይቻላል?
መልስ፡
ፈታሔ በጽድቅ የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር ስለስሙ ብለው ደማቸውን ለሚያፈሱ እና መራራ ሞትን ለሚታገሱ
ቅዱሳን ‹የማያልፈውን የክብርን አክሊል› ያቀዳጃቸዋል(1 ኛ ጴጥ 5.4)፡፡የባሪያዎቹን ጉልበት በዝብዞ ዋጋቸውን እንደሚነፍግ
እንደ ክፉ ጌታ ስለ ቤተ ክርስቲያን ብለው የተቀበሉትን ተገፍዖ ‹ስለ ስሙም ያሳዩትን ፍቅር› አይቶ ይረሳ እና ያስቀር ዘንድ
ፈጣሪያችን እንደ ሰው አመጸኛ አይደለም(ዕብ 6.0)፡፡በሃይማኖት ጸንተው ባርንም አደራጅተው ለተገኙ ሁሉ የሚሰጣቸው
እሴት የሚያገኙት አክሊለ ክብር አለ፡፡ስለዚም ነገር መጻሕፍት ተባብረውበታል፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ‹ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል
ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል› በማለት ስለሚጠብቀው መንፈሳዊ ሽልማት
ሲናገር ቅዱስ ያዕቆብም በመልዕክቱ ‹በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ
የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።› በማለት እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ የወጣ ምዕመን የሕይወት አክሊልን
ከአምላኩ እንደሚያገኝ አስተምሯል(2 ኛ ጢሞ 4.8፣ያዕ 1.02)፡፡
ታዲያ ለሮጡ ሳይሆን በሩጫው ጸንተው እና በርትተው ድልን ላገኙ ብቻ የምትሰጠው ሽልማት፣ ምዕመናን በሃይማኖት
ጸንተው በምግባር ጎልምሰው ሲገኙ የሚያገኟት ይህቺ አክሊል ማን ናት? በንጽሕና እና በአሚነ ሥላሴ ለኖሩ ሁሉ የምትሰጥ
ይህቺ የቅዱሳን የክብር ቀጸላ ማን ናት? ያለምንም ጥርጥር ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና የሆነች እመ አምላክ
ድንግል ማርያም አይደለችምን!፡፡እርሷ የቅዱሳን ሁሉ የክብር አክሊላቸው ሽልማታቸው ናት፡፡ለዚህም ነው አበው ‹አክሊል
ንጹሕ ለቅዱሳን› ‹የቅዱሳን ንጹሕ አክሊል› በማለት የሚጠሯት፡፡በማክሰኞ የውዳሴ ማርያም ጸሎታችንም ላይ ‹አክሊለ
ምክህነ ወቀዳሚተ መድኃኒትነ ወመሠረተ ንጽሕነ› ‹የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችን መሠረት›
በማለት አፈ በረከት የተባለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም አንደበት አድርገን ምስክርነትን እንሰጣለን፡፡የእመቤታችን የድንግል ማርያም
አክሊል መባል እንግዳ እና ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጣ ሃሳብ አይደለም፡፡እንኳን እመ አምላክ እመቤታችን ትቅርና ቅዱስ ጳውሎስ
የተሰሎንቄን ሰዎች ‹ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት
በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን› በማለት አክሊሌ ብሎ ጠርቷቸዋል(1 ኛ ተሰ 2.09)፡፡ታዲያ እመቤታችንን ‹አክሊለ
ቅዱሳን› ማለት ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ? ‹ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ› የሆነች እርሷ ከተሰሎንቄ ሰዎች አትበልጥምን?
የእግዚአብሔርን አካላዊ ቃል በማኅጸኗ የተሸከመች እመቤታችን የቃሉን የምስራች ከሚማሩ የተሰሎንቄ ምዕመናን ይልቅ
ለድኅነታችን ተስፋ ለጎሰቆለው ባሕርያችን መመኪያ አልሆነችምን ? ፡፡ስለዚህ ቅዱሳን ያገኟት እና ያጠለቋት የቅድስና
አክሊል ድንግል ማርያም ናት፡፡በብዙ የቅዱሳን ገድልም ተጽፎ እንደምናገኘው የመጨረሻ የቅዱሳን ልመናቸው እመቤታችንን
በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ማየት ሲሆን ከሞቱም በኋላ ቁርጥ ምኞታቸው የራሳቸው አክሊል ቀጸላ ሽልማት ሆና እንድትሰጣቸው
ነው፡፡በምድር ወልዳ ያጠባችውን በእቅፏ የያዘችውን በስደቱ የተንከራተተች እና በመከራው ጊዜ እናቱ በመሆኗ የልጅነት
ፍቅሩን ፈጣሪዋም ስለሆነ በአምላካዊ ንጽሕናውን እያሰበች እንደ ሰይፍ የሚቆርጥ እንደ ጠገራ የሚሰነጥቅ የልብ ሀዘን
ተሸክማ በምድር ያልተለየችው እናቱ በሰማይስ እንዴት ሆና ይሆን? ብንል በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በእምነት መነጽር
ድንግል ማርያምን በንጉሱ እልፍኝ በቀኙ ቆማ በሰማዩም ደስታ ሳትለየው በክብር እናያታለን፡፡እርሷን የማይወዱ መናፍቃን
ወደ ልጇ ቤት እንዴት ይገቡ ይሆን? ድንግል የሌለችበት የእንግዶች መሰንበቻ የሆነች መንግስተ ሰማያት እኮ የለችም!፡፡
በየትኛውም መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ሳያከብር ወላዲተ አምላክ ብሎ ሳይቀበል ክርስቶስን በማመኑ ብቻ የጸደቀ ሰው
የለም፡፡የአምላክ ሰው መሆን ምንጩ እርሷ ናትና፡፡ይህንም ያለ ምክንያት አላልንም፡፡‹ክርስቶስ ብቻ› ብለው የሚያስተምሩ
መናፍቃን የእመቤታችንን የአምላክ እናትነት ካልተቀበሉ የክርስቶስን አምላክነት እና ሰው መሆን መካድ ይሆንባቸዋል፡፡ታዲያ
‹በጎ ሥጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ› ከእርሱ የሚገኝ አምላክ የከበረች እናቱን ሕያው አክሊል አድርጎ ለወዳጆቹ ቅዱሳን
ቢያቀዳጃቸው ‹እንዴት ቢታደሉ ይሆን?!› የሚል አግራሞትን የሚፈጥር እንጂ ደርሶ የሚያከራክር ሆኖ ነውን? አይደለም!፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም እንደተናገረው ጻድቅ ቢመካ እና መመካት እንኳ ቢገባው የመመኪያ አክሊል ሆና በተሰጠችው በእመቤታችን
ነው፡፡አባ ጽጌ ድንግልም በጥዑም የማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ ‹ብፁዓን ኃጥአን እለ ተአምረኪ ተወከሉ እምጻድቅ እስጢፋ
ዘይትሜካህ በጻማህ ገድሉ› ‹ጻድቅ ነኝ ብሎ በገድሉ ከሚመካ እስጢፋ ይልቅ ታአምርሽን ተስፋ አድርገው ያመኑ ኃጥአን
የተመሰገኑ ናቸው› በማለት በገድሉ ብዛት ከሚመካ ጻድቅ ይልቅ በእመቤታችን አማላጅነት በእግዚአብሔር ቸርነት ያመነ
ኃጥእ የተመሰገነ እንደሆነ አጠይቆት አድርጎልናል፡፡‹በሩ እኔ ነኝ፣በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል ይገባልም ይወጣልም፤መሰማሪያም
ያገኛል› በማለት ብቸኛው እና እውነተኛው በር እርሱ እንደሆነ ነግሮናል(ዮሐ 0.9)፡፡ምንም በሩ አንድ ቢሆንም በበሩ ከገባን
በኋላ ግን ብዙ መሰማሪያ ስላለ በአንዱ እና በእውነተኛው በር በክርስቶስ አምነን በእርሱ በርነት ስንገባ የምናገኛቸውን
የቤቱን ባለሟሎች ቅዱሳንን ልንቀበል ያስፈልጋል፡፡በሩ አንድ ሲሆን መሰማሪያው ግን ብዙ ስለሆነ፡፡አንድ ‹ጻድቅ› እርሷን
ወላዲተ አምላክ፣እመ አምላክ ሰዓሊተ ምሕረት ሳይል ሰማዕትነትን እንኳ ቢቀበል ለማን ብዬ ተቀበልኩ፤በማን ስም ተቀበልኩ
ብሎ ይናገራል? እርሷን በሚገባ ሳያውቁ የበቁ የሚመስላቸው የዋሐን ልፋታቸው ከንቱ መሆኑን ቀጥሎ በምንጠቅሰው
የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት እንረዳለን፡፡‹ድሆችን ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ
ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም› በማለት ሰው ፍቅር ሳይኖረው እነዚህን ሁሉ መንፈሳዊ ምግባራት ቢፈጽም መዳን
እንደማይችል እና ሥራው ምንም ረብ እንደሌለው ነገረን (1 ኛ ቆሮ 03.1)፡፡ምን አገናኘውና ተጠቀሰ የሚል ይኖራል?
በእርግጥ ያለ ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስን ማባከን ትልቅ ጥፋት ቢሆንም ይህ ግን ምክንያታዊ እንደሆነ ለመገንዘብ
እስቲ የሚቀጥሉትን ሃሳቦች በየዋሕ ልቡና በትሑት ስብዕና ሆነህ ተመልከተው! ከላይ በርዕሳችንም ያነሳነው ኃይለ ቃል ከዚህ
ጥቅስ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ አልተሰማህምን? አንተ አስተውል እንጂ ከሳቴ ምሥጢር (ምሥጢር ገላጭ) የሆነ መንፈስ
ቅዱስ ሁሉን ያሳይሃል፡፡የሰው ልጅ ወላጅ ራሱ ሰው እንደሆነ ፤የወለደችው ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ከሆነ፤እናቱ ድንግል
ማርያምም የፍቅር እናት እርሷ ራሷስ ፍቅር አይደለችምን? ታዲያ ይህን ካወቅህ ማኅደረ ፍቅር የተባለች እመቤታችንን
ሸሽቶ ረድኤቷን አቃልሎ ጽድቅን ፍለጋ ቁልቁል ቢሰቀል፣በራሱም ቢተከል ነፍሱን ማዳን የሚችል ማን አለ ብለህ ታምናለህ?
ማንም! እንደሚሆን መልስህ አልጠራጠርም፡፡ይህ ካልሆነ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ከሰበከልን ወንጌል የተለየ ‹ሌላ ወንጌል›
ስለምትሰብክ አይሆንም እንጂ ንጽሕናህ ‹እንደ ሰማይ መልአክ› ቢሆን እንኳ አንቀበልህም!በሕግ መጽሐፍ 'አባቱን ወይም
እናቱን የሚያቃልል› የሞት ፍርድ እንደሚገባው ተጽፎልናል(ዘዳ 7፡6)፡፡ታዲያ የፍጡር ሳይሆን የፈጣሪ እናት የሆነች
እመቤታችንን መስደብ በእርሷም ላይ ክፉ ቃልን መናገር ምንኛ ያስቀጣ ይሆን? ወንዝ የማያሻግር ምግባር ይዘው የጻድቃንን
ተራዳኢነት ክደው ቅዱሳንን ንቀው ራሳቸውን አክብረው በራሳችን ሥራ ብቻ እንጽደቅ የሚሉ በምሕረት ፈንታ
መርገምን፣በእግዚአብሔር ፈንታ ዲያብሎስን፣በመንግስተ ሰማያት ፈንታ ገሃነምን ርስት እንደሚያደርጉ አንጠራጠርም!!!
ይቆየን

በስመ አብ:ወወልድ:ወመንፈስ ቅዱስ:አሜን!!!

ጥያቄ፡
ስለቅዱሳት ሥዕላት ክብርና በሥዕላቱ ፊት ስለመጸለይ ከቅዱሳኑ ሕይወት ተሞክሮ አንጻር ብታሥረዱን?
መልስ፡
ቅዱሳን አባቶቻችን በቅዱሳን ሥዕላት ዙሪያ በስፋት አስተምረዋል። በተለይም በሥምንተኛው መ/ክ/ዘ/ አካባቢ ከጸረ ሥዕለ
ቅዱሳት የተጋደሉት ተጋድሎ የማይረሳና ዛሬ ላለነው ትውልድ ለትምህርት የምንጠቅሰው መጽሐፋችን ነው። አሁን ላይ
በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለአምልኮ ሥርዓት የምንጠቀምባቸው የቅዱሳን ሥዕላት የእነርሱ የተጋድሎ ውጤቶች ናቸውና፡፡
በተለያዩ የአባቶቻችን ድርሳናት ውስጥ ተመዝግበው እንደሚገኘው ቀደምት አበውና እማት በቅዱሳን ሥዕል ፊት ሻማ
በማብራት በጎ በጎ መዓዛ የሚሸት ሽቶን በመቀባት የተለየ ስፍራ:(ቦታ) በማስቀመጥ መጋረጃ በመጋረድ በፊታቸው ጸሎትና
ስግደትን በማቅረብ ለሥዕላቱ ክብር እንደሚሰጡ እናገኛለን። ከነዚህም መሐከል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው። ቡሩክ የሚሆ
ን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሐዋርያውን የቅዱስ ጳውሎስን መልእክታት ከመጠን በላይ ይወድ ነበር። የሐዋርያውን ሥዕልም
በሚገባ ቦታ አስቀምጦት ነበርና መልእክታቱን በሚያነብበት ወቅት ሥዕሉን በፊቱ አድርጎና ሐዋርያው አጠገቡ በአካል
እንደተገኘ በማድረግ ይናገር እርሱንም ያመሰግነውና ሐሳቡንም በሙሉ ወደ እርሱ ያደርግ ነበር።ከመምህራችን ከቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ አድራጎት እንደተረዳነው የስእሉ ባለቤት ቅዱስ ጳውሎስ በአካል አጠገቡ እንዳለ ሆኖ ያነጋግረውና በፊቱም
የጸሎት ሐሳቡን ይናገር ነበር። እኛም ለቅዱሳኑ ሥዕላት የሚገባውን ክብር ከመስጠት ጋር በዚሁ መንገድ በፊታቸው
ጸሎታችንን ልናቀርብ ይገባል። በመቀጠልም ማር ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ሥዕላቱም ክብር ሲገልጽ "የቤተመንግስቱን ልብስ
ብትንቅ ንጉሱን መናቅህ አይደለምን?የንጉሱን ሥዕል መናቅ ንጉሡን መናቅ መሆኑን አትመለከትምን??አንድ ሰው ከእንጨት
ለተሰራ ሥዕል ወይም ከብረት ለተቀረጸው የንጉሡ ሐውልት ንቀት ቢያሳይ ሰውየው የሚዳኘው ሕይወት ለሌለው ቁስ ንቀት
እንደአሳየ ሳይሆን ለንጉሡ ንቀት እንዳሳየ መሆኑን አታውቁምን?? ለንጉሡ ሥዕል የሚቀርብ ማንኛውም ንቀትና ማዋረድ
ለንጉሡ የሚቀርብ ንቀትና ማዋረድ ነው።"" በማለት ለቅዱሳኑ ሥዕላት ክብር መስጠት እንደሚገባ በምድራዊ የንጉሥ ሥዕል
ክብር ምሳሌ በማድረግ አስረድቷል። እኛስ የምድራዊው ንጉሥ ሥዕል ይህንን ያህል ክብርና መፈራት ከተደረገለት ለቅዱሳኑ
አምላክና ለቅዱሳኑ ሥዕል ያለን አክብሮት ምን ያህል ይሆን??ደግመኛም በ 8 ኛው መ.ክ.ዘ. በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት
ብዙ ክርስቲያኖች የቅዱሳት ሥዕላትን ክብር ለማስጠበቅ መስዋዕትነት የከፈሉ ሲሆን ይህንን የቅዱስ ዮሐንስን ምስክርነት
በደንብ የሚያንጸባርቅ ታሪክ ተከስቷል። ይኸውም:-ከዕለታት በአንድ ቀን በኒቆሜዲያ የሚኖር አንድ ቀናኢ መነኩሴ ቅዱሳት
ሥዕላትን አስመልክቶ ከንጉሡ ፊት ተጠርቶ በቀረበ ጊዜ የሰጠውን አስገራሚ ምላሽ ነው። ይኸውም:- ንጉሡ መነኩሴውን
በቁጣ ቃል ""አንተ ሰነፍ መነኩሴ!!እነሆ ማንኛውም ሰው በክርስቶስ ሥዕል ላይ መረማመድ እንደሚችልና በዚህም ክርስቶስን
ከማክበር እንደማይወጣ አትመለከትምን??አለው። መነኩሴውም ወዲያውኑ የንጉሡ ምሥል ያለበትን ሳንቲም በቤተ
መንግስቱ ወለል ላይ ወርውውሮ ""በዚህ አይነት እኔም አንተን ከማክበር ሳልወጣ በአንተ የፊት ምሥል ላይ መመላለስ
ይፈቀድልኛል ማለት ነዋ!!"" ሲል መለሰለት። በዚያን ጊዜ የንጉሡ ባለሟሎች ፈጥነው መነኩሴውን ከድርጊቱ ከለከሉትና
የንጉሡን ሥዕል በድፍረት ሥላቃለለ በሞት እንዲቀጣ አድርገውታል። ይህ ታሪክ የሚስተምረን የንጉሡ ድርጊት የአስመሳይ
ክርስቲያኖች ምሣሌነትን ይዞ ነው። ብዙ ጊዜ እንደንጉሡ በአንደበታችን ክርስ ቶስን እንደምናከብረው እንናገርና ምግባራችን
ግን ሌላ ይሆናል። ንጉሡ ለክርስቶስ ሥዕል ክብር ከመስጠት ይልቅ ለራሱ ሥዕል ክብር ተጨንቆ ትክክለኛውንና ቀናኢውን
መነኩሴ በሞት አስቀጣው። ስንቶቻችን እንሆን ለራሳችን ጥቅም ብለን ወንድሞቻችንን ጉዳት ላይ የምንጥል?? በአንጻሩም
ደግሞ እንደ መነኩሴው የንጉሥን አሥፈሪ ግርማ ሳያስደነግጠን እውነትን በመመስከር የሃይማኖታችንን ጽናት የምናሳይ
ስንቶቻችን እንሆ?? አንግዲህ የምንፍቅናው ግርማ ሳያስፈራን በጽናት ስለ ቅዱሳት ሥዕላት የአባቶቻችንን አሥተምህሮ
ሳናፋልስ መመስከር ከኛ ከዘመኑ ትውልድ ይጠበቃል። ቅዱሳን አበውም አክብረው እንዳቆዩልን እኛም በሥላቱ ፊት ቆመን
ልንጸልይና ልንሰግድ ያስፈልጋል። በዚህም ከሥዕሉ ባለቤት በረከትና ረድኤት እናገኛለን። ይህንን በማድረጋቸው ብዙሀኑ
ተጠቅመዋልና። በቅዱስ መርቆሪዎስ ገድል እንደ ተገለጸው:- ዓላዊው ንጉሥ ኡልያኖስ ወንድማማቾቹን ባስሌዎስንና
ጎርጎርዮስን ሊገላቸው በሚያሳድዳቸው ወቅት የመርቆሪዮስ አምላክ ከንጉሡ ቁጣ እንዲሰውራቸው በሥዕለ መርቆሪዎስ
ፊት ተደፍተው ቢማጸኑ ሥዕሉ በተአምራት መንገድ ሄዶ ኡልያኖስን ገደለው።" ኡልያኖስን ገደልኩት"" ሲል በሥዕሉ ላይ
የደም ምልክት አሳያቸው። "ገደልከውን??" ሲሉትም ሥዕሉ ከአንገቱ ዘንበል ብሎ "አዎን" እንደማለት አመልክቷቸዋል።
በእውነት:በቅዱሳኑ:ሥዕል:ፊት:ሆነን:በፍጹም:እምነትና:በቅንነት:ብንማጸናቸው:በአጸደ:ሥጋና በአጸ
ደ:ነፍስ:መሀከል:ያለውን:ጥብቅ:ግንኙነትና:አገልግሎት:በግልጽ:የ,ምናይበት:ሌላኛው:ማስረጃ:ነው።ይህም:ከላ:ያየነው:ታሪክ:ከ
ዚህ:ውጭ:ሌላ:ምን:የሚነግረን:ነገር:አለና??
======================በተጨማሪም:በዚሁ:በሀገራችንና:በዘመናችን:የሰማዕቱ:የቅዱስ:መርቆሪዎስ:ሥዕል:ዓመታ
ዊ:ክብረ:በዓሉ:በሚከበርበት:እለት(በህዳር:-25 እና ሐምሌ 25)
ካህናቱ:ሲያሸበሽቡ:አብሮ:ይንቀሳቀሳል።ይህንን:ተአምር:ለማመን:የሚከብደው:ሰው:ካለ:ደግሞ:ቦታው:ድረስ:በመሄድ:ማረጋገ
ጥ:ይችላል።(ቦተው:በሰሜን:ሸዋ:ደብረ:ሲና:ወረዳ:ጋሹ:አንባ:ቅዱስ መርቆሪ ዮስ:ከሚባል:ቤተ ክርስቲያን:ከቅኔ ማህሌት:ፊት
ለፊት:የሚገኝ:ሥዕል ነው።)) ሲጠቃለል:-የቅዱሳንን:ሥ ዕል:ማክበርና በፊታቸው:ቆሞ:መ
ጸለይንና:ከባለ:ሥዕሉ:በረከት:ረድኤትን:ማግኘት:የተማርነው:ከቅዱሳን:አባቶቻችን:እንደሆነ:እንረዳል።==============
==========ወስብሐት:ለእግዚአብሔር=====ወለወላዲቱ:ድንግል========ወለመስቀሉ:ክቡር:አሜን!!!

ጾመ ፍልሰታ

"ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር"


በመምህር ንዋይ ካሳሁን
ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጉም ስናነሣ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ /የተገኘ/ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ ከምድር ከመቃብር
መለየት፣ ማረግ፤ ወደ ላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ያመለክታል፡፡ በዚህ መሰረት ጾመ ፍልሰታ በአጠቃላይ የእመቤታችን
ድንግል ማርያም የሥጋዋን ከመቃብር መለየትና ወደ ገነት ማረጉን የሚያመለክት ሲሆን
ቅድስት ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንዲጾሙት ከምታዘው አጽዋም አንዱና ለዓመቱ ደግሞ የመጨረሻው ጾም ነው፡፡
ይህ ጾመ ፍልሰታ በሌላ አጠራሩ ጾመ ማርያምም በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ወቅት በብዛት የሚወሳው /የሚነገረው/
ቃለ እግዚአብሔር በአብዛኛው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የተያያዘ በመሆኑና የእርስዋ የሥጋዋ ፍልሰት
መታሰቢያ በመሆኑ ጾመ ማርያም ተባለ፡፡ ነገር ከስሩ ውኃ ከጥሩ እንዲሉ አበው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ይህንን
የእመቤታችንን ጾም ለምን እንደምታከብር ለመዘርዘር እንወዳለን፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች የሰው ልጆች
መኖሪያ በሆነችዋ ምድር ከእናትና ከአባቷ ማህፀንና አብራክ ተከፍላ ከተወለደችበት ግዜ አንስቶ እስከ መጨረሻዋ
የዕረፍት ዘመን በምድር ላይ ስልሳ አራት ዓመታትን ማለትም ከእናት ከአባቷ ቤት ሦስት ዓመት ከሰባት ወር፣ በቤተመቅደስ
12 ዓመት፣ በቤተ ዮሴፍ 34 ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታ እርገት በኋላ ከወንጌላዊው ዮሐንስ ጋር 14 ዓመት ኖራለች፡፡ ከዚህ
በኋላ እርሷም የአዳም ዘር ናትና ጥር 21 ቀን ዐርፋለች፡፡ አበው"ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ"እንዳሉት የእመቤታችን
እረፍት እንባ መራጨት፣ ጠጉር መንጨት፣ ደረት መድቃት እንዳለበት የሰው ሞት
አልነበረም፡፡ ይልቁንም አንደ ሠርግ ቤት መላዕክት በውዳሴ፤በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና ወደ ሰማይ ሸኟት፡፡ እንጂ ቅዱስ
ያሬድም"ተለዐለት እምድር ወበህየ ነበረት ዘምስለ ወልዳ በየማነ አብ ወመንፈስ ቅዱስ"እመቤታችን ድንግል
ማርያም ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለች፡፡ በዚያም ከልጇ ጋር በአብና በመንፈስ ቅዱስ ቀኝ ተቀመጠች በማለትም
ዘምሯል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋ ከጌቴሴማኔ ወደ ገነት መፍለሱን አስቀድሞ አባቷ ቅዱስ ዳዊት በትንቢት ሲናገር
"ተንስእ እግዚኦ ውስተ እረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ"አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት በማለት
ተንብዮዋል፡፡ መዝ. 131፡8 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት ጥር 21 ሲሆን
እረፍቷና ዕርገቷ ብዙ መንፈሳዊ ተአምራትና አስደናቂ ምስጢር የተገለጠበት በመሆኑ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር
የተባለበትም ምክንያት ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ የእመቤታችን እረፍት በሆነበት እለት አይሁድ በአስከሬኗ ጥፋት ለማድረስ ብዙ
ጥረዋል፡፡ እነ ታውፋንያም እጁን በመቆረጥ ተአምር ተደርጎበታል፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙ ንውጽውጽታ ስለነበር
ሐዋርያትም በሀዘን ከጌቴሰማኔ ተመለሱ፡፡ በዚህ ሀዘንም እያሉ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ
ሲመጣ እመቤታችንን መላዕክት ሲያሳርጓት አየ፡፡ ሰገደላት፣አመሰገናትም እርሷም ባርካው ተለያዩ፡፡ ለሐዋርያው ቶማስም
የእመቤታችንን መቀበር ደቀ መዛሙርት አስረዱት፡፡ ቶማስም ሥጋዋን አስከማይ አላምንም አላቸው፡፡ ሥጋዋን ያሣዩት ዘንድ
ወደ መቃብርዋ በአደረሱት ጊዜ በመቃብር ውስጥ ሥጋዋን አላገኙም ደንግጠውም አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ
ሰማይ ስታርግ እመቤታችንን እንዳገኛት ቶማስ ነገራቸው፡፡ በዚህም ሥጋዋ ሲያርግ ባለማየታቸው አንድ ቀን
እንደሚያሳያቸው ጌታችን ተገልጦ ቃል ገባላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ከሚያስተምርበት ሀገረ እስያ ወደ
ሰማይ ተነጥቆ የእመቤታችን ሥጋ ያለበትን ስፍራ አየ፡፡ ሐዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ
ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ፡፡ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆይተው ነሐሴ በባተ በመጀመሪያው ቀን በጾም
በጸሎት ሱባዔ ያዙ፡፡ ነሐሴ 14 ቀን ሁለት ሱባዔ ሲጨርሱ ሥጋዋን አምጥቶ ሰጣቸው በጥር ወር የእረፍት ጊዜ ተወስኖ
በነበረው ቦታ በጌቴሰማኔ ቀበሯት፡፡ነሐሴ 16 ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ
ሰማይ አወጣቸው፡፡ በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋህዳ ተነሥታ እመቤታችንን አዩዋት፡፡
እጆችዋንም ዘርግታ ሐዋርያትንም ባረከቻቸው በእልልታ በደስታ ወደ ሰማይ አረገች፡፡ ሐዋርያትም በልባቸው ደስ አላቸው፡፡
እንግዲህ ከላይ ለማስነበብ እንደሞከርነው ጾመ ፍልሰታ እንደወንዝ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ የሆነ ታሪክ ሳይሆን ልብን
የሚነካ መንፈሳዊ ታሪክ ነው፡፡ ለዚህም ነው ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት "አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት"ያለው፡፡
አንተ ያለው ጌታችንን ሲሆን የመቅደስህ ታቦት ያለው ጌታ ለዘለዓለም አድሮባት የኖረባትን እናቱ ድንግል ማርያምን ነው፡፡
ጌታ በገዛ ፈቃዱ ሞትን ድል አድርጎ በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ እርሷም በልጅዋ ቸርነት ከሦስት ቀን በኋላ ከሞት ተነሳች፡፡
ስለዚህም ነው ምዕመናን ነሐሴ አንድ ቀን የምትገባዋን ጾመ ማርያም ሱባዔ ለመያዝ ህጻናቱ ተማሪው የክረምት
እረፍትበመሆኑ፣ ሰራተኛው የዓመት ፈቃዱን ወስዶ ሌሊት በሰዓታት፣ቀን በትርጓሜና በቅዳሴ የሚያሳልፈው፡፡
እግዚአብሔርአብርሃምን "የሚባርኩህን እባርካለሁ፣ የሚረግሙህን እረግማለሁ"እንዳለው፡፡ ዘፍ.12፡3 የአብርሃም ዘር የሆነች
ድንግል ማርያምን የሚያመሰግን ትውልድ ይባረካል፡፡ ለዚህም ነው እመቤታችንም "ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል" በማለት
የተናገረችው፡፡ ይህ የሱባዔ ወቅትም እመቤታችንን እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደስ ይበልሽ ብለን አመስግነን፣እንደ
ቅዱሳን አባቶች ሰአሊነነ ቅድስት በማለት ለምነን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የምናገኝበት ልዩ ወቅት ነው፡፡ በብዙዎቻችን
ዘንድ የዚህ ሱባዔ ወቅት የማይረሳ ልዩ ትዝታም አለው፡፡ ስለሆነም በተለይ በአሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያን የሚታየውን ፈተና
ለመቋቋም በርትተን "ጸልዮ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን"እንዲል ስለቤተክርስቲያን ሰላም መፀለይ ይገባናል፡፡ ክፉ የተባሉ
ቀናት አይቻልም የሚባሉ ችግሮች በጸሎት ኃይል እንደሚሸነፉ የመጽሐፍ ቅዱሳን ምስክርነት ማየት ይበቃል፡፡ሐዋ. 12፡5፡፡
የጾመ ፍልሰታ ልዩ ገጽታ☘
ቅድስት ቤተክርስቲያን ሰባት ያህል አጽዋማትን በአዋጅ
ታጾማለች፡፡ ነገር ግን የጾመ ፍልሰታ ልዩ ገጽታን ለማየት
ያህል፤
1. ከዚህ በፊት በተለየ መልኩ ሙሉ ጊዜ /ቀንም ሆነ
ሌሊት/ያልተቋረጠ የቤተክርስቲያን አገልግሎት
ማለትም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የሰዓታት ድርሰት፣
የቅዱስ ያሬድ ዜማ፣ የቅዱስ ኤፍሬም የውዳሴ
ማርያም ትርጓሜ፣ የአባ ህርያቆስ ቅዳሴ ማርያም
በስፋትና በጥልቀት የሚሰማበት መሆኑ ከፍተኛ
የመንፈስ እርካታን ይሰጣል፡፡
2. በትምህርት ጊዜ ሲባዝኑ የነበሩ ህጻናትና ተማሪዎች፣
ወጣት፣ አረጋውያኑ ለመቁረብ ነጠላ ለብሰው በጊዜ ቤተክርስቲያን ገብተው ሲያስቀድሱ ማየት የህብረት
የተሰጥኦ ዜማቸውን መስማት አንዱ ልዩ ገጽታ ነው፤
3. ጊዜው ሁለት ሱባዔ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በፍቅር የምትጾም መሆኗም ከሌሎቹ የአጽዋማት ጊዜ ልዩ የጾመ ማርያም
ገጽታ ነው፡፡ እንግዲህ ምዕመናን በሩቅም በቅርብም ከሀገር ውጭም በውስጥም ያለን ስለአንድነታችን፣ ስለሰላማችን ስለ
ሀገራችን እየጸለይን ልዩ መንፈሳዊ በረከት ከእመቤታችን እንድናገኝ
ልንተጋ ይገባል፡፡
✿ወስብሐት ለእግዚአብሔር✿

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።


ግብረ አውናን' በእግሊዘኛው 'Masturbation' አንድ ሰው በዝሙት ዝንባሌ ተይዞ ከእንቅልፍ ውጪ ዘርን እያወቁ ወደ ውጪ
ማፍሰስ ማለት ነው፡፡ 'ግብረ አውናን' የተባለበት ምክንያት አውናን የተባለው የይሁዳ ልጅ ከሚስቱ ጋር ተኝቶ ሳለ ዘሩን
ከሚስቱ ማህጸን ውጪ ያፈሰው ስለ ነበር ነው፡፡ ዝሙትን ወዶ ክቡር ዘርን የትም ማፍሰስና የአውናን ዘሩን ከማህጸን ውጪ
ማፍሰስ አንድ ናቸውና፡፡ ዘፍ. 38:9
አንድ ገበሬ ለዘር የሚያስቀረው ዘር ራሱ ከሚመገበው እንኳ የተሻለውን ምርጥ ዘር ነው፡፡ ስለሆነው ከዘር በፊት ተጠንቅቆ
በሪቅ (በጎተራ) ያስቀምጠዋል፡፡ በዘር ወቅት ደግሞ አውጥቶ በመልካም ማሳ ላይ ይዘራዋል እንጂ ያለቦታው አይበትነውም፡፡
እንዲሁም የሰው ዘር ከእህል ዘር ይከብራልና በመልካም ጎተራ ማለትም በሰውነት ተጠብቆ መቆየት አለበት፡፡ ከጋብቻ በኋላ
ባልና ሚስት ሩካቤ ሲፈፅሙ ደግሞ በመልካሟ ማሳ በሚስት ማህፀን መዝራት እንጂ በልዩ ልዩ ምክንያት ሆን ብሎ ዘርን እንደ
ጉድፍ ከማህጸን በአፍአ (በውጪ) ማፍሰስ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡
አውናን የተባለው ሰው ዘሩን ከማህጸን ውጪ በማፍሰሱ ምክንያት የደረሰበትን መቅሰፍት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ
ይተርከዋል፡፡ "አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ፡፡ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይሰጥ
ዘሩንጠበምድር ያፈሰው ነበር፡፡ ይህመ ስራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት እርሱንም ደግሞ ቀሰፈው፡፡" ዘፍ 38:9-10::
ይህ ታሪክ በማንኛውም ምክንያት ዘር አፍሳሽ መሆን ሊያስቀስፍ የሚችል ክፉ ስራ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ፡፡ እነዚህም ዝሙት ርኩሰት ፍትወት ክፉ
ምኞትም ጣዖትን ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው፡፡" ቆላ 3:5 እዚህ ላይ "ብልቶቻችሁን ግደሉ" ሲል ቆርጣችሁ ጣሏቸው
ማለቱ ሳይሆን አትቀስቅሱ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ዘርን ለማፍሰስ ብልትን መነካካት ተገቢ አይደለም፡፡
ዳግመኛም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ፡፡" 1 ኛ ቆሮ
7:9 ብሏልና በዝሙት ለሚቃጠሉ መፍትሔው ማግባት እንጂ መሰንጋት (ሴጋ መፈጸም) አይደለም፡፡ ሐዋርያውም ይህን
እንደ መፍትሔ አልመከረምና፡፡ (ሕይወተ ወራዙት፡ ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ)
ወስብሐት ለ እግዚአብሔር!

፨፨፨፨፨ ሳይፀልዩ ማደር ፨፨፨፨፨


"ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዮ"
የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋ ፀለየች....
"አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ
ነብሩም ተርቦ
ወደ አምላኩ ቀርቦ
ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ
የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም - ሰማቸው ፈጣሪ አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት "እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታው
ጠላት"
.ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት፣
ምግህ አድርገህም ብላት"።
ሚዳቆዋ ስትሮጥ፣
ከነብር ለማምለጥ፣
ነብሩም ሲከተላት፣
ሆዱን ሊሞላባት፣
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ፣
ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ፣
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር፣
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር።
አውጣኝ ያለው ወቶ - አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ።
☞ገጣሚ በረከት በላይነህ ☜

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ከምግብ በፊት እና በኋላ ምን ብለን እንጸልይ?


"""""""""""""""""""""""""""""""""""""
(በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ )
ከመመገባች በፊት ይህንን አባቶቻችን ከመዝሙረ ዳዊት አውጣጥተው የደረሱትን ጸሎት እናድርስ!
«እግዚአብሔ አምላክነ ዘትሁብ ሠናያቲከ ለኩሉ ፍጥረት እኩት አንተ ወስቡሕ ስምከ ወንህነኒ ነአኩተከ ወንሴብሐከ በእንተ
ፍጹም ጸጋከ ዓይነ ኩሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ እስመ አንተ ትሁብ ሲሳየ ለኩሎ በጊዜሁ ትሰፍህ የማነከ ወታጸግብ ኩሎ ወይእዜኒ
ስፋሕ የማነከ ቅድስተ ወባርክ ዘንተ መብልዓ ወመስቴ ዘአስተዳለውከነ ከመ ይኩነነ ኃይለ ወጽንዓ ለ ጋነ ወነፍስነ እስመ አንተ
ኄር ወምእመን መጋቤ ለዓለመ ዓለም አሜን! አቡነ ዘበሰማያት»«ለፍጥረ ሁሉ መልካምህን የምትሠጥ አምላካችን
እግዚአብሔር አንተ ምስጉን ነህ ስምህም የተመሰገነ ነው። እኛም ስለ ፍጹም ሥጦታህ ፈጽመን እናመሰግንሃለን። የፍጥረት
ሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል። አንተ ለሁሉ በጊዜው ምግቡን ትሠጠዋለህና ቀኝህን ትዘረጋለህ ሁሉንም ታጠግባለህ።
አሁንም ልዩ የሆነች ቀኝህን ዘርጋ ይህንን የሠጠኸንን ምግብና መጠጥም ባርክ ለሥጋችንና ለነፍሳችን ኃይልና ብርታት ይሆነን
ዘንድ አንተ ቸር ታማኝ መጋቢ ነህና ለዘለዓለሙ አሜን! አባታችን ሆይ!»ከዚያም እንደየመዓርጉ መዓዱን የባረከው ሰው
ለሌሎች ቆርሶ «በእንተ ማርያም በእንተ ኢየሱስ» እያለ ይሠጣል። ቀሳውስት ደግሞ «በረከተ አብ ወወልድ ወመንፈስ
ቅዱስ» እያሉ ሲሰጡ ሰዉ «ይምጻእ ኀቤየ መንፈስ ቅዱስ» እያለ ይቀበላል። ይህም ጌታችን በኤማሁስ አብረውት ሊበሉ
ለተቀመጡት አርድእት እንደሰጣቸው በማየት የተሠራ ሥርዓት ነው።የመዓድ ጸሎት ትልቁ ጠቀሜታ ሰው ምንም ለጸሎት
ጊዜ የለኝም ቢል እንኩዋን ለምግብ ጊዜ አጣሁ ሊል ስለማይችል በበላ ቁጥር እንዲጸልይ ያደርገዋል። በቀን ሦስት ጊዜ
የሚበላ ሰው ቢያንስ በቀን ሦስቴ ይጸልያል። አቅሙ ቢችልና ለሥጋውም ሆነ ለነፍሱ ጤና ካልሰጋ በስተቀር አንድ ሰው በቀን
ሰባት ጊዜ ቢበላ ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠነቀቀ ማለት ነው። ጥቅሙን ለማስረዳ ይህንን አመጣነው እንጂ ይህ እንኩዋን
ለመብላት መጸለይ ሳይሆን ለመጸለይ መብላት ይሆናል።ከበላን በኋላ ስብሐት እንላለን። በምንም ምክንያት ለመብላት ጊዜ
እስካለን ድረስ ስብሐት ለማለትም ጊዜ መሥጠት አለብን። የበላነውን የጤና እንዲያደርግልንና እንዲስማማን ፣ እንዳያሳጧን
ላጡትም እንዲያድላቸው ማመስገን ይገባል። አንዳንድ ሰዎች «ምግቡ ከተረፈ ስብሐት አንልም ምክንያቱም ስብሐት
ብለንበት ለውሻ ሊሠጥ ይችላል ፤ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ይላል።» ይላሉ። ይህ ሃሳብ ግን ብዙ የማያስኬድና
አንዳንዴም ለስንፍና ምክንያት ይሆናል።አንደኛ ስብሐት ከማለታችን በፊት ገና መብላት ስንጀምር ምግቡን በመባረካችን
ምግቡ ከመነሻው የተባረከ ነው። ሌላው ስብሐት የምንለው በመብላታችን ፈጣሪን ለማመስገን ነው እንጂ ባለማስተረፋችን
አይደለም። የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ የሚለውም ቃል ውሾችን ስላለመመገብ የተነገረ አይደለም። በደመ ነፍስ
የሚኖሩት ምንም የማያውቁት እንስሳትስ ካለ እኛ ማን አላቸው? ውሾች እኛ ያስተረፍነውን ሊበሉ አይገባም ማለት
ከወንጌሉም ሃሳብ ጋር «ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ» ይላልና
{ማቴ. 15፡27}እንዲያውም ከቅዱሳኑ የተማርነው ለውሾች ያስተረፍነውን መከልከል ሳይሆን ያልቀመስነውንም ከላዩ አንስተ
መሥጠት እንዳለብን ነው። ርኅርኅተ ኅሊና እመቤታችን ለውሻ የሰጠችው እስዋ እንኳን ሳትቀምሰው አጉድላ አልነበር?
ጻድቅ ለእንስሳው ነፍስ ይራራል ይልስ የለ?
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የሕይወት ዋጋው ...?


ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን
“የህይወት ዋጋው ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡
አባትም መልስ በመስጠት ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ “እንካ ይህንን የድንጋይ ቁራጭ...ወደ ገበያ ውሰደው "
"ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር” አለው፡፡ ልጁም ድንጋዩን
ወሰደ፡፡ ወጥቶም በገበያ መሃል ቆመ፡፡ አንዲት ሴትም መጣች፡፡
“ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው? ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ምንም
ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳያት፡፡
እሷም አለች
“ሁለት ብር? እወስደዋለሁ!!”
ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በገበያ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም አለው
“አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ ሙዚየም ሂድ ዋጋውን ሲጠይቁህም ሁለት ጣቶችህን አሳይ”
ልጁም ወደ ሙዚየም ወጣ፡፡ ገዢም መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “ሁለት መቶ ብር?
እወስደዋለሁ!” አለው፡፡ ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ ማዕድናት መሸጫ ሂድ ለባለቤቱም አሳየው” አለው፡፡
ልጁም ሄደ ለሱቁም ባለቤት አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም
“ይህ እኮ አለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡ “ከየት አገኘኸው? ስንትስ ትሸጠዋለህ?” ሲል
ጠየቀው፡፡ ልጁም ምንም ሳይናገር
ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡ የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን ድንጋይ በሁለት መቶ
ሺህ ብር እወስደዋለሁ፡፡”
ልጁም በመገረም እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያጋጠመውን ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡
አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣ ሃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣ የተወለድክበት ቦታ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ ዋናው ራስህን
የምታስቀምጥበት ቦታ፣ ራስህን የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም በምትመርጥበት
መንገድ ነው፡፡ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡ ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ ሁለት
ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ ድንጋይ በውስጡ ይዟል።
ወስብሐት ለእግዜብሔር።

በዓለ መስቀል

የመስቀል በዓል የሚከበረው መስከረም ፲፯ (17) ነው። ይህም በዓል በክርስትያኑዓለም ሁሉ ይከበራል። 
ታሪኩም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎሙቶ ከተነሳ በኋላ
ህሙማን መስቀሉን እየዳሰሱ በመስቀሉ እየታሹ ይፈወሱ ነበር። በዚህም ተአምራት እየተሳቡ ብዙዎች ክርስትያን ሆኑ። ይህ
ን ያዩም አይሁድ መስቀሉን ባንድ ቆሻሻ መድፊያ ቦታ ጣሉት። ከጊዜ ብዛትም ያ ቦታ እንደ ጉብታ ሆኖ ምስቀሉ ውስጥ ተደበ
ቀ። በጊዜው ምንም እንኳን ክርስትያኖች መስቀሉን ማውጣት ባይችሉም ቦታውን ለይተው ያውቁት ነበር። በኋላ ግን በጥጦ
ስ ወረራ ክርስትያኖች ኢየሩሳሌምን ጨርሰው ለቀው ስለወጡና የከተማዋም መልክ ፈፅሞ ስለተለወጠ መስቀሉ የተደፈነበት 
ቦታ ወዴት እንድሆነ ለማወቅ አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ከ 300 አመታት በላይ ተዳፍኖ ቆይቷል። 

በአራተኛው ክፍለ ዘመን በ፫፻፳፯ (327) ዓም የንጉስ ቆስጠንጢኖሥ እናት ንግስት ዕሌኒ በስእለቷ መሰረት ወደ ኢየሩሳሌም


ወረደች ። ስዕለቷም ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስትና ከተመለሰ ኢየሩሳሌም ወርዳ የፈራረሱትን ቤተክርስቲያን ማነጽና
የክርስቶስን መስቀል መፈለግ ነበር ። ልጇም ቆስጠንጢኖስ መክስምያኖስ ከሚባል ንጉሥ ጋር ሊዋጋ ሲል በሰማይ ላይ "በዚህ
የመስቀል ምልክት ጠላትህን ተሸንፋለህ " የሚል ጽሁፍ አየ ። ወዲያውኑ የመስቀሉን ምልክት በወታደሮቹ ልብስና በፈረሶቹ
ላይ የመስቀል ምልክትን አደረገ ። ከመክስምያኖስም ጋር በተዋጋ ጊዜ ድሉ የቆስጠንጢኖስ ሆነ ። ይህም ክርስትናን
እንዲቀበል አስገድዶታል ። ዕሌኒም ስእለቷ ደርሶላት ወደ ኢየሩሳሌም ወረደች ።
እዚያም ደርሳ ጉብታ የሆነውን ሁሉ ብታስቆፍር መስቀሉ ያለበትን አላገኘችውም፤ሰውም ብትጠይቅ የሚያውቅላት አላገኘ
ችም። በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃዱ ነበርና አንድ አረጋዊ ስሙ ኪርያኮስ የሚባል የአይሁድ
መምህር ተገኘ ። በትውፊትም እንደሚነገረው እሌኒም ጨው የበዛበት ምግብ ሰጥታው ውሃ በመከልከል ቦታውን
እንዲነግራት አደረገች ። ኪራኮስም " ቦታውን በውል ባላውቀውም ከእነዚህ ተራሮች አንዱ ነው "ብሎ ጠቆማት ።
ቦታው ቆሻሻ የበዛበትና ትክክለኛው የመስቀሉ ቦታ የማይታወቅ በመሆኑ ዕሌኒ ሀሳብ ውስጥ ገባች ። ቅዱስ ሚካኤልም
በራዕይተገልጦ"እንጨት ሰብሥበሽ ከምረሽ እጣን አፍሺበት፤ በእሳትም ኣያይዢው፤ የእጣኑ ጢስ ወደላይ ወጥቶ ወደታች ሲ
መለስ አቅታጫውን አይተሽ አስቆፍሪው፤ በዚህም ምልክት ታገኝዋለሽ ።" አላት
እሷም ያላትን ሁሉ አደረገች። ጢሡ ወደላይ ደርሶ ወድታች ሲመለስ መስቀሉ ያለበትን ያለበትን ቦታ በጣት ጠቅሶ እንደማሳ
የት ያክል አሳየ፤ ያን ምልክትም አይታ መስቀሉ አውጥታዋለች።
በኢትዮጵያም በዓሉ ከመስከረም (ከጥቢ) ጋር መያያዙ በተለየ ድምቀት እንዲከበር አድርጎታል። በዋዜማው ማለትም መስከረ
ም 16 ካህናት ችቦ ተሰብስቦ በተደመረ ደመራ ፊት ለፊት ፀሎት አድረሰው ቀጥሎም ህዝቡ "ኢሆሃ አበባየ መስከረም ጠባዬ" 
እያሉ ይዘምራሉ ። ይህ በአል በኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ ንዑስ በዓላት አንዱ በዓል ነው።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ምጽዋት በኦርቶዶክሳውያን አበው
የወንጌል ትርጓሜ የሆኑ በህይወታቸው ክርስትናን የሰበኩ ቅዱሳን አባቶቻችን ምጽዋትን እስከ ጥጉ ድረስ ፈጽመውታል፡፡
ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን አባ አንጢላርዮስ ነው፡፡ እርሱም በቀደመ ህይወቱ ንፉግ ባለጸጋ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት
ህይወቱ ተለውጦ ሀብት ንብረቱን ሽጦ ለድሆች መጸወተ፡፡ በዚህም አልበቃም በመንገዱም መስጠቱን የሰሙ ነዳያን ወደርሱ
በመጡ ጊዜ ርቧቸው ጠምቷቸው ነበርና አዘነላቸው፡፡ "ገንዘብ የለኝም ነገር ግን ሽጡኝና በምታገኙት ገንዘብ ተጠቀሙ
አላቸው" ችግር ጸንቶባቸው ነበርና እርሱን ሽጠውት ገንዘቡን ተከፋፍለውታል፡፡ በረከቱ ይደርብን! እኛ እስከዚህ የመስጠት
ከፍታ ባንደርስ በትንሹ እንኳ ካለን ቀንሰን መመጽወት ይገባናል፡፡ ያኔ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ፈፃሚ የቅዱሳኑ ልጆች
እንሆናለን፡፡
 "የሚጣፍጥ ቃልም ይህ ነው፡፡ ችግረኞች በበዘበዙህ ባስቸገሩህ ጊዜ እንዳትቆጣ እንዳትሰድባቸው ተጠንቀቅ፡፡ ካለህ ስጥ፤
ከሌለህ ግን የለኝም፤ ጌታየ ይስጥህ (ካለው ያድርስህ) በለው፡፡ የምታገኘውን ውሃ ግን አጠጣው፤ እሳት አሙቀው፤ ከቤትም
አታባርረው (አታስወጣው) ይህም ይቻልሃል፡፡ በኋላ ልብህ እንዳያዝን ተቀበለውም፡፡ ማንኛውንም የጽድቅ ተግባራትን
በምታከናውንበት ጊዜ ዕልፍ አድርጎ የሚከፍልህ በአጠገብህ እንዳለ እወቅ፡፡ በሰፊው ስጥ ፤እቸገራለሁም አትበል፤
በምትሰጥበት ጊዜ ይበዛልሃልና፡፡ ስጡ ይሰጣችኀል እንዲል፡፡"
 በቁስጥንጥንያ የነበረ በመመጽወቱ ልዩ የሆነ አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱ በከተማው ጎዳና ሲዘዋወር ለድሆች ከመጸወተ በኋላ
እንዳያውቁትና ምስጋናቸውንም ላለመስማት ፈጥኖ ከነርሱ ይሄድ ነበር፡፡ አንድ ወዳጁ እንዴት እንዲህ ለጋስ ሊሆን እንደቻለ
በጠየቀው ጊዜ አንድ ቀን በቤተ ክርስቲያን ካህኑ 'ለድሆች የሚመጸውት ለክርስቶስ ነው የሚሰጠው' ብለው ሲያስተምሩ
ሰማሁ "ይህማ እንዴት ይሆናል? ክርስቶስ በሰማያት ያለ አይደለምን?" በማለት ለማመን ተቸገርኩ፡፡ ከዕለታት ባንዱም ቀን
ወደ ቤቴ እየሄድኩ ሳለ አንዱ ነዳይ ሲለምን ከራሱ ላይም የክርስቶስ ፊት ሲያበራ አየሁ፡፡ አንድ መንገደኛም ጥቂት እንጀራን
በሰጠው ጊዜ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንጀራውን ተቀብሎ የሰጠውንም ሰው ሲባርከው ተመለከትኩ፡፡ ከዚያች ጊዜ ጀምሮ በነዳያን
ራስ ላይ የክርስቶስ ፊት ሲያበራ እመለከታለሁ፡፡ ስለዚህም በታላቅ ፍርሀት የሚቻለኝን ልግስና አደርጋለሁ፡፡" በማለት
ተናግሯል፡፡
(ከምስራቃውያን አባቶች አንዱ) ✝
የድሆች ጠበቃ የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የምጽዋትን ታላቅነት ተአምራትን ከማድረግ ጋር አነጻጽሮ ሲናገር እንዲህ
ብሏል፦... በማለት ይገልጸዋል፡፡
"ከንፉግነት ወደ መመጽወት ከተለወጥክ የሰለለውን እጅ ዘረጋህ፡፡ ቲያትርን ትተህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትሄድ ሽባውን እግር
ፈወስህ፡፡ አይንህን ከዝሙት ብታነሳ ከዕውርነት ወደ ብርሃን አመጣሀቸው፡፡ እኚህ ናቸው ታላቅ ተአምራቶች፡፡ " ብሏል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አባ ሰራፕዮን የተባለ መነኮስም ያለውን የወንጌል መጽሐፍ ሽጦ ለተራበው ነዳይ መጽውቷል፡፡ "ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ
ብሎ ያዘዘኝን ወንጌል ሽጬ ለድሆች ሰጠሁ" በማለት ተናግሯል፡፡"አንተ ያስቀመጥኸው እንጀራ ለተራበው እንጀራ ነው፡፡
በቁም ሳጥንህ ያስቀመጥኸው ልብስህ ለታረዘው ልብሱ ነው፡፡ የማትጫማው ጫማህ በባዶ እግር ላለው ጫማ ነው፡፡ ቋጥረህ
ያስቀመጠኸው ገንዘብህ የድኃው ገንዘብ ነው፡፡ በምጽዋት በልግስና የማትሰጠውም አንተ የምትፈጽመው በደል ነው፡፡"
ቅዱስ ባስልዮስ

ማንም "እኔ ድሀ ነኝ መመጽወት አይቻለኝም አይበል፡፡" ባለጸጎች ለቤተ መቅደስ እንደሚሰጡት ልታደርግ ባትችል ድሀዋ
መበለት እንደሰጠችው ሁለት ናስ ብትሆን እንኳ ስጥ፡፡ ሁለቱ ናስ እንኳ ባይኖርህ ለታመመው በማዘን በህመሙ ጊዜም እርሱን
በማገልገል ምፅዋት አድርግ፡፡ ይህንንም ማድረግ ባይቻልህ የወደቀው ወንድምህን አጽናናው፡፡ "መልካም ቃል ከስጥታዎች ሁሉ
ይበልጣልና፡፡"
 አባ ዶሮቴዎስ
ቅዱስ ጳውሎስም "በጎ ፈቃድ ቢኖር እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም፡፡" 2 ኛ ቆሮ.
8:12 እንዳለ ለመመጽወት ባለጸጋ መሆንን ሳንጠብቅ ያለችንን ከዕለት ምግባችን፣ ከሻይ ሳንቲም ቀንሰን ለድሆች ብንሰጥ
በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ይሆንልናል!

✞ በመጨረሻም...አንድ ባህታዊ ወደ አባ ቴዎዶር ዘንድ ሄዶ "የመኖርን አላማ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሰውን
የሚያዘውን እርሱን ለማገልገል ምርጡን መንገድም አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ጌታዬን ለማገልገል ማድረግ የሚገባኝን ለማድረግ
እየተቻለኝ አይደለም በማለት ይነግራቸዋል፡፡
አባ ቴዎዶርም በዝምታ ከቆዩ በኋላ "ከባህሩ ማዶ ከተማ እንዳለ ታውቃለህ፡፡ ነገር ግን መርከብ የለህም እቃዎችህን
አልጫንክም፣ ባህሩንም አልተሻገርክም፡፡ ከተማው ምን እንደሚመስል በከተማዎቹ ጎዳና ስለ መዘዋወር ማውራቱ ምን
ይረባል?" በማለት መለሰለት፡፡✝
እኛም_ስለ_ምጽዋት_በቃልም_በጽሁፍም_ብንሰማ_እግዚአብሔርን_ደስ_የሚያሰኘውን_ነገር_ብናውቅ_በስራ_ካልገለጥ_
ግን_በዜሮ_ማባዛት_ይሆንብናል፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!
በወንድም ተክለ ማርያም.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ጥያቂ፡ በጥቅምት 25 ቅዱስ መርቆሬዎስ ዚቅ ላይ በግእዝ


"ሰማይን በከዋክብት የሸፈንክ ፣ ምድርንም በአበቦች ያስጌጥክ መርቆሬዎስ ሆይ ለስምህ እገዛለሁ: በኃይልህም
አመሰግንሀለው : ወደ አንተ የሚመጣውን የስጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎት ስማ ይቅርታህንም አታዘግይብን ብርሃንህንና እውነትህን
ላክ እነርሱም ይምሩኝ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ መቅደስህ ይምሩኝም ይውሰዱኝም>> በማለት ተጽፏል። ይህ
ለእግዚአብሔር የተሰጠውን ለቅዱሳን መስጠት አይሆንብንም?
መልስ፡
 ወደ ጥያቄው ምላሽ ከመግባታችን በፊት አስቀድመን መሠረታዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶችን በአጭሩ እንመልከት።
የዚቅ አደራረስ

የዚቅ ድርሰት የሚወጣው ለአንድ ቅዱስ ከተደረሰው መልክእ ነው። ከመልክኡም ከወቅቱ የሚስማማውና አመቺ የሆነው
ይመረጣል። በመቀጠልም ከመልክኡ ጋር የሚሄድ ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይ ከሌላ ሊቃውንት መጽሐፍ ተፈልጎ ዚቁ
ይደረሳል፡፡ በዚህ መሠረት ከላይ ያለ የዚቅ ድርሰት የወጣው በቅዱስ መርቆሬዎስ መልክእ ለዝክረ ስምከ ከሚለው ላይ ነው።
ንባቡም እንዲህ ይላል። "የኢየሱስ አገልጋይ ማለት ለሆነው ስም አጠራርህና ጥቁር ጸጉርህ ሰላም እላለሁ። ኃይልና ተአምር
የምትሰራ ሰማዕት መርቆሬዎስ ለዮሐንስ በምድረ በዳ የድኅነትን ጎዳና እንደመራኸው እኔም ልጅህን የእውነትና የይቅርታ
ጎዳና ምራኝ።" ቀጥሎም ከመልክኡ "ምራኝ" የሚለውን ይዞ ከመዝሙረ ዳዊት "ይምሩኝ ይውሰዱኝ" የሚለውን
ቀጠለ።(መዝ 43፥3) ሌሎቹም ከዚሁ ከዳዊት መዝሙር ተያይዘው የመጡ ናቸው። (ዘፍ 1÷9 : 19) ( መዝ 64÷1-2)
ተአምር አይደለም ሰማይንና ምድርን አስጊጦ መፍጠር ይቅርና ማንኛውም በጎ ተአምራት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፡፡ ነገር
ግን አንዳንዱ ቀጥታ በአምላካችን ሲገለጽ ሌሎቹ ደግሞ በቅዱሳኑ ይገልጣል። ለምሳሌ፡ ሙሴ ባህረ ኤርትራን በበትሩ ለሁለት
ከፈለ ሲባል ይህን ያደረገው እግዚአብሔር መሆኑ ይታወቃል ግን ይህን ተአምር በሊቀ ነቢያት ሙሴ እንዲነገር አድርጓል።
ምክንያቱ ደግሞ እግዚአብሔር ወዳጆቹ ቅዱሳን እንዲመሰገኑ ክብር እንዲያገኙ ስለሚፈልግ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ
እግዚአብሔር ለምን በሙሴ አደረገው? ካልን ምላሹ ሙሴ በቅድስና የሚኖር መሪ ስለነበረ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ያዕቆብ
በፍኖተ ሎዛ በሌሊት ካልባረከኝ አለቅህም ብሎ ከእግዚአብሔር እንደታገለ ቢገለጽም ነቢዩ ሆሴዕ ግን "ያዕቆብ በጎልማሳነቱ
ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ ጋር ታግሎ አሸነፈ" (ሆሴ 2፡4) ብሏል። የእግዚአብሔር ለመልአኩ የሰጠው መላእክት ሁልጊዜ
ከአምላካችን እንደማይለዩ ለመግለጽ ስለተፈለገ ነው።
 ፈቃዱንና ነገሮችን ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚያስገዛ ለራሱ ሕያው አይደለም። ራሱን ክዷልና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በእርሱ
የሚኖረው እግዚአብሔር ነው። ቅዱስ ጳውሎስም "ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም
ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል" (ገላ 2:20) ያለውን ይህን ሲያመለክት ነው። አውግስጢኖስ በቀደመ ሕይወቱ የምታውቀው ዘማ
ሴት ወደ በአቱ በመምጣት በሩን ታንኳኳለች። እርሱም "አውግስጢኖስ ሞቷል!" ብሎ መለሰላት። ሴቲቱም "ይህ
የአውግስጢኖስ ድምጽ ነው እኮ" ብትለው "አውግስጢኖስ ሞቷል አሁን የሚያናግርሽ ክርስቶስ ነው" ብሏታል። ይህንንም
ያለበት ምክንያት እርሱ የበቃ ስለነበረና እርሱ ለዚህ ዓለም ሞቶ በእርሱ ክርስቶስ ይኖር ስለነበር ነው።ከዚህ የምንረዳው
ቅዱሳን የክርስቶስ መገለጫ መሆናቸውን ነው፡፡ ስለዚህ መገለጫው የሆኑትን ቅዱሳንን ማመስገን እግዚአብሔርን ማመስገን
ነው። ልበ አምላክ ዳዊትም ይህን በመረዳት በመዝሙሩ "አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ--- እግዚአብሔር
በጻድቁ እንደ ተገለጠ (ተመሰገነ) እወቁ" (መዝ 4:3፤) ያለው፡፡ስለዚህ ወደ መነሻ ጥያቄው ስንመለስ በድርሰቱ ላይ ያሉት
ምስጋና ቅዱስ መርቆሬዎስ ያደረጋቸው ሳይሆን በእርሱ በኩል እግዚአብሔርን ለማመስገን የታሰበ ነው። ምክንያቱ ደግም
ቅዱስ ዳዊት እንደገለጸልን እግዚአብሔር በወዳጆቹ በቅዱሳን በኩል እንዲመሰገን ፈቃዱ ነውና። በመቀጠልም ወቅቱ የአበባ
ጊዜ በመሆኑ ምድርን በአበባ ያስጌጥክ የሚለውን ምስጋና ደራሲው መርጦታል።
በአጠቃላይ ስንመለከተው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያሉት የምሥጋናም ሆኖ ሌሎች ሥርዓቶች የእግዚአብሔርን
ክብር የሚሻሙ ሳይሆን እግዚአብሔርን በልዩ ልዩ መልክ ማመስገኛ ዘዴዎች መሆናቸውን ተገንዝበን እኛም ከምስጋናው
ተሳታፊዎች ልንሆን ይገባል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!

የማርያም መንገድ
ከሥራ እንደተመለስኩኝ ... የሰፈራችንን ሜዳ አቋርጬ በቀጥታ ወደቤት ነበር የምሄደው ውሎዬን ሳወጣና ሳወርድ ስለነበር
በሀሳብ ተውጫለሁ ድንገት ሳላስበው ከሚጫወቱት ልጆች አንዱ ገጨኝና ሚዛኔን አሳተኝ ልቆጣው ይሁን ለምን እንደሆነ
ባላውቅም ተከተልኩት ጥቂት ሮጦ መሬት ላይ በተከበበ መስመር ውስጥ ገባና “እቤቴ . . . እቤቴ . . .” አለ። ቀጥሎም ትንሽ
እንደ ማሰብ አለና “’የማርያም መንገድ’ . . . ‘የማርያም መንገድ’ . . . ስጡኝ” አለ። ጥቂት መንገድ ከፈቱለት በዚያች መንገድ
አምልጦ ወጣ… በማርያም መንገድ አምልጦ ታስረው የነበሩ የቡድን አጋሮቹን አስፈታ በልጁ ቅልጥፍና ይሁን በጨዋታው
ተስቤ ንዴቴን ረሳሁት ትንሽ አለፍ ብለው ሦስት ህፃናት ሴቶች መሬት ላይ አስምረው የሰኞ፣ የማክሰኞ ቤት ብለው
በሰየሟቸው ቤቶች ላይ በእነርሱ አጠራር ከምች እየወረወረሩ ይጫወታሉ።
በጨዋታው ሕግ የተገዛ ወይም የተወረሰ ቤትን መደገፍ መርገጥም አይቻልም አንድ ነገር ካልተባለ በቀር . . . . ‘ማርያም
ብታነሳኝ’. . . ቤት የተገዛባት ወይም የተወረሰባት ልጅ ቀድማ ‘ማርያም ብታነሳኝ’ አለች።
ተፈቀደላት ተደግፋ ከምቿን አነሳች ቀድማ ቤት ቢገዛባትም ብዙ በመግዛት ወይም በመውረስ ጨዋታውን አሸነፈች፡፡ህፃን
ሁኜ ተጫውቼ ያሳለፍኩት ዛሬ ግን እንደ አዲስ የተረዳሁት ጨዋታ ልቤን ነካኝ ወደ ልጅነት ዘመኔ ተመልሼ የቻልኩትን ያህል
ስለ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ማስታወስ ሞከርኩ፡፡ ከነፍሳት በተለየ መልኩ ‘የማርያም ፈረስ’፣ ቀስተ
ደመናው-‘የማርያም መቀነት’፣ በሰውነት ላይ የታየች ጥቁር ነጥብ- ‘ማርያም የሳመችኝ’፣ማንም ሰው ሳይጠራን ስማችን
የተጠራ በሚመስለን ጊዜ ‘የማርያም ብቅልእየፈጨሁ ነው’፣ እኛ ስንወለድ ‘ማርያም’፣ ‘ማርያም’ እየተባለልን ነበር . . .
አባቶቻችን ግን ምን ያህል ጥበበኛ ናቸው? የእመቤታችንን ፍቅር በልባችን፣ ጣዕሟን በአንደበታችን የቀረፁበት መንገድ
ይገርማል:: በህፃንነት ዘመናችን በምንወጣበትና በምንገባበት ሁሉ ከለላ ጠባቂ የነበረው አጋንንትን ድል እየነሳ ዛሬ እዚህ
ለደረስንበት ዕድሜ ፣ ረድኤትና በረከት የሆነን፤ ለዚህ ያበቃን ‘ማርያም’፣ ‘ማርያም’ የሚለው ስም ነው::
በተአምረ ማርያም ላይ ያለው ህፃን ትዝ ይላችኋል . . . በወላጆቹ ስህተት ለአጋንንት የተሰጠውን ህፃን ከአጋንንት ቀንበር
ለማውጣት በቤተ መቅደስ የሚያሳድጉት ካህን ህፃኑን አጋንንት እንዳይነጥቃቸው ዘወትር ከእጃቸው አይለዩትም ነበር።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ለቅዳሴ ሲቻኮሉ ህፃኑን ረስተው ወደ ቤተመቅደስ ይገሰግሳሉ፤ ይህን መልካም አጋጣሚ ያገኘው
አጋንንት ህፃኑንይዞት ወደ መቀመቃት ይወርዳል፡፡ በዚህ ሰዓት ያ ህፃን ያጠናው ምን መሰላችሁ በኮልታፋ አንደበቱ ‘ማርያም’፣
‘ማርያም’ የሚለውን ቃል እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዓይን ጥቅሻ ደርሳ ያንን አጋንንት ድል ነስታ ህፃኑን በቤተ
መቅደስ አቆመችው፡፡ ለእኛም ውለታዋ እንደዚህ ነው፡፡ ደግሞም ጨዋታውን ሁሉ ካስተዋላችሁት በሕይወት ዘመናችን
የሚጠቅም ቁም ነገር ነው፡፡ እንደ በላኤሰብ በኃጢአት በወደቅን ጊዜ በጽድቅ እንድንነሳ ለንስሐ እንድንበቃ ቃል ኪዳኗን
ምርኩዝ አድርገን ማርያም ብታነሳኝ እንላለን፤የዓለም ድሪቶ ተብትቦን መንገድ በጠፋብን ጊዜ የማርያም መንገድ ብለን
በቀናች በጸናች በተዋሕዶ መንገድ ተጉዘን ሀገረ ሕይወት መንግሥተ ሰማያት እንደርሳለን መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት
ናትና፤ጠላት ዲያቢሎስ ባስጨነቀን ጊዜ የማርያምን ብቅል እየፈጨን በዝክሯ በጸበሏ ድል እንነሳዋለን፡
በዮሐንስ ራዕይ ዘንዶ ሆኖ የተነሳው ዲያቢሎስ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ላይ ካለው መሪር ጥላቻ የተነሳ
በሄሮድስ ላይ አድሮ በግብጽ በረሃ ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ አሳደዳት፡
ዛሬም እንደሄሮድስ እንደ አሽን በፈሉ መናፍቃን ላይ አድሮ ምርኩዛችንን ሊያስጥለን ከላይ ከታች ይላል እኔስ እንደ ቅዱስ
ባስልዮስ እንዲህ እላለሁ. . . “ቅድስት ድንግል ማርያም ማንስ ነው ከቅዱሳን ሁሉ በላይ እንደሆነች ያላስተዋለ?
እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ሰው ሁሉ ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቻው ያረፈበት ተአምር
ከተፈጸመለት፣ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ከዳነ፣ የቅዱስ ጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ እራፊ መናፍስትን ካወጣ፣ለእናቱማ ምን
ዓይነት ሥልጣንና ኃይል ሰጥቷትይሆን?
ለቅዱሳኑ ይህንን ያህል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሳደገችው እናቱማ ምን ያህል ይሰጣት ይሆን?
በምን ዓይነት ስጦታ አስጊጧት ይሆን? ቅዱስ ጴጥሮስ “ክርስቶስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ስላለው ብፁዕ
ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው እርሷ ከሁሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች /ብፅዕት/ አትሆን?
ቅዱስ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ
የሆነ መናውን ሳይሆን የሕይወትን ሰማያዊ እንጀራ ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃው ትሆን?
”እኔስ እላለሁ አብዝቼ እንደ ልጅነቴ ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሐን ድንግል ማርያም . . . ማርያም . . . ማርያም…”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

"ሂድና ውደዳት!"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
በአንድ ወቅት አንድ ሰው ሚስቱ እንድትወደው ብዙ ነገር አድርጎ ስላልተሳካለት ሚስቱም ስላልወደደችው ተበሳጭቶ
ወደሰባኪው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይሄዳል፡፡
"ሚስቴ እንድትወደኝ ብዙ ለፋሁ ፤ ያላደረኩት ነገር የለም ፤ምንም ልትወደኝ አልቻለችም፡፡ እንድትወደኝ ማድረግ
የምችለው በምን መንገድ ነው?" ሲል በሀዘን ተሰብሮ ይጠይቀውና የሚነገረውን ጥበባዊ መንገድ በጥንቃቄ ለመረዳት
እዝነልቦናውን አዘጋጅቶ የአባቱን ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ የአንደበቱን ጥኡም ቃል ይጠባበቃል፡፡
ቅ/ዮሐንስ ግን የነገሩት በአጭሩ በሁለት ቃል ብቻ የተዋቀረ ነበር፡፡ "ሂድና ውደዳት!"

ሰውየው 'ያልኩትን አልተረዳኝ ይሆን እንዴ?' እያለ እያሰበ ጥያቄውን ደግሞ አቀረበ። "ሚስቴ አልወደኝ አለች ምንም ባደርግ
ልትወደኝ አልቻለችም ነው ያልኩት" አለ በድጋሜ፡፡
"ሂድና ውደዳት" አለው ሰባኪው በድጋሜ፡፡
አሁንም ለሶስተኛጊዜ ሰውየው "ልትወደኝ የሚገባት ሚስቴ አልወደደችኝም ነው ያልኩዎትኮ!" አለ፡፡
ሰባኪውም መልሶ "ሂድና ውደዳት!" አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው እርሱ እንደሚወዳት ለመናገር 'እኔማ...' ብሎ ጀምሮ ራሱን መፈተሽ ጀመረ፡፡ እሱ ውስጥ ያለው፣ እርሱ
የሚወደው፣ የእርሱ ፍላጎት የእርሱን የራሱን በእርሷ መወደድ እንጅ እርሷን መውደድ አልነበረም፡፡ ጊዜውን ለመወደድ
በመጣር ብቻ አሳልፎታል፤ ጥረቱ ሁሉ እንድትወደው እንጅ እንዲወዳት አልነበረም፡፡ አዘነ፡፡ እርሷን መውደድ ሲገባው ራሱን
በርሷ ለማስወደድ ሲጥር ኖሯል፤ አልተሳካለትም፡፡
ፍቅር የሚመጣው በራሱ በፍቅር እንጅ በሌላው ሁሉ ጥረት አይደለም፡፡ በሌላ ጥረት የሚመጣ ሰው ሰራሽ "ፍቅር" ካለ ግን
ፍቅሩ ሀሰተኛ ነው፡፡
ራስን ከመውደድ አልፈን ራስን ወደማስወደድ ከመሄድ ይልቅ ሌላውን በመውደድ መወደድን አናጣውም፤ ፍቅር ሌላውን
የሚወድ ከሆነ ፍቅርንማ እንደምን አይወድ!
እርሷን ስትወዳት ፍቅሯን ታገኛለህ እንጅ ፍቅሯን ያለፍቅርህ አትሞክረው! አንዳንዶቻችን እኔ ላደረኩት ነገር ለምን
አልተደነቅሁም ለምንስ አልተወደድኩም እንላለን። እንደዚህ ካልን ያደረግነውን ላደረግንለት ሳይሆን ለራሳችን ነው ማለት
ነው ያደረግነው፤ ይህ ደግሞ የፍቅር ባህሪ አይደለም፡፡ እኛ ለሌሎች የሌለንን ፍቅርም ሌሎች ጋ ወደኛ መጠበቅ የለብንም፡፡
ለባለቤቴ ባደረኩላት ነገር ከእርሷ ምስጋናን የምሻ ከሆነና ካልተመሰገንኩ ከከፋኝ እኔ ከፍቅር የነፃሁ ምስኪን ነኝ፡፡ በርቅጥ
ሚስቴ ደስ ስትሰኝ ማየት ሊያስደስተኝ ይገባል፤ ይህ ማለት ግን እንደዋጋ አድርጌ ልወስደው ሳይሆን መደሰቷን
ስለምመርጥላት ስለእርሷ ደስታ ስል ነው፡፡ ስለእኔ በደስታዋ መደሰት ያይደለ፡፡
"ሂድና ውደዳት !" የሁልጊዜም መርሃችን ልትሆን ይገባል፡፡ እንድትወደን ሳይሆን እንድወዳት ስወዳት የምር ትወደናለች፡፡
ስንወድ ከተወዳጁ በምንጠብቀው ነገር መመስረት የለብንም የፍቅራችን መሰረት መመስት ያለበት ፍቅራችን ላይ እንጅ
በሚጠበቅ በሌላ ፍቅርም ሆነ ሌላመሰረት ላይ መሆን የለበትም፡፡
አምላክ እኛን ስለወደድነው አይደለም የወደደን ፤ በራሱ ፍቅር ተመስርቶ ወደደን እንጅ፡፡ እኛም በራሳችን ፍቅር ተመስርተን
ልንወደው ወይም ስለማይናድ በራሱ ፍቅር ተመስርተን ልንወደው ይገባል፡፡
ሰው ላይ ግን መመስረቻው የሰው ፍቅር አይደለም ፤ አያስተማምንም፡፡ በራስ ፍቅር መሠረት ላይ የተተከለች ፍቅር በራስ
ይዞታ ላይ እንደተሰራች ቤት ናት፡፡ ማንም መጥቶ አያፈርሳትም፡፡ ወዳኝ ከምንዋደድ ወድጃት ብንዋደድ ይሻለኛል፡፡ መሰረቱን
ራሴ ላይ ራሴ ብይዘው!
ብጹእነታቸው ከጻፋቸው አንዱ ከሆነው መንፈሳዊ ውጊያዎች ከሚለው መጽሐፍ የተገኝ ተከታታይ ጽሁፍ

ክፍል ፩
ውስጣዊ ውጊያዎች

መንፈሳዊ ውጊያዎች ወደ ሰው የሚመጡት ከውስጥ ፤ ከዲያብሎስ፤ ከዓለምና ፤ ከክፋ ሰዎች ነው ፡፡


☞ እነዚህ ውጊያዎች ከልብ ምኞት፤ ከአእምሮ ሀሳብና ፤ከሰውነት እንቅስቃሴ ይመጣሉ ።
ውስጣዊ ውጊያ ከውጫዊ ካለው ውግያ ጉዳቱ የላቀ ነው ፡፡ ምክንያቱም በውስጣዊ ውግያ ሰው የገዛ ራሱ ጠላት ስለሚሆን
ነው ፡፡ ሰውየው ስለሚመኝውና ሊቋቋመው ስለማይፈልግ ይህ ውጊያ ከባድ ነው ፡፡
ከቅዱሳን አንዱ "ንጹሕ ልብ የማይደፈር ምሽግ ነው " ብሎ እንደተናገረ በሰው ሕይወት ውስጥ የልብ ንጽሕና ከምንም በላይ
ይቆጠራል ። ልብ በዓለት ላይ የተመሰረተ ቤትን ይመስላል ፡፡ ከውጭ የተፈለገውን ያህል ነፋስ ቢነፍስም ምንም ዓይነት ጉዳት
ሊያደርስበት አይችልም ፡፡ ማቴ 7*24-25
ምናልባት ውስጣዊ ውጊያ የሚመጣው የአንድ ሰው ተፈጥሮ በኃጢአት ሲጠመድ ሊሆን ይችላል ። እዚህ ላይ ውጊያ
የሚመጣበት በልቦና በአሳቡ ውስጥ በተተከሉ የቀደሙ ጉዳዮች ነው ።
ከዚህም በተጨማሪ ለኃጢአት በሚንበረከክ ደካማና ዝልፍልፍ ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል ። ከዚህ ሌላ ውስጣዊ ውጊያ
መንፈሳዊውን አካሄድ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመጣ ዝንጉነት በሰው ላይ ሊከፈት ይችላል ፡፡ እንዲህ ያለው ዝለት ልብን
ከማድከሙም በላይ ሕሊና ያለ ምንም ቁጥጥር ልቅ ሆኖ እንዲማስን ያደርገዋል ።
ውስጣዊ ውጊያዎች ከሚባሉት መካከል የአሳብ ውጊያ አንዱ ነው ፡፡

የአሳብ ውጊያ ....... ይቆየን ለቀጣይ !

ክፍል ፪
.......የአሳብ ውጊያ
አሳቦች በውንም ይሁን በእንቅልፍ ሊመጡ ይችላሉ ፡፡ አሳቦች አሳብ ወለዶች ቀን የተደረጉ ነገሮች ውጤት ወይም በምኞትና
በአሳብ ምክንያት ሕሊና ውስጥ የሰፈሩ ጉዳዮች ወይም በሰውየው የተደመጡ ወሬዎችና ወጎች ሆነው በሕሊናው ውስጥ
የተተከሉ ሊሆን ይችላል ።
እነዚህ ሁሉ በሕልም ፤ በሕሊና ፤ ብክነት ወይም ሰው ልቡ እስከ ተቀበላቸው ድረስ በቁሙ ቅዠቱ ውስጥ የሚያመላልሳቸው
ሆነው ሊገለጡ ይችላሉ ፡፡ ልብ ካልተቀበላቸው ግን ሊቆሙ ስለሚችሉ ሰውየው ወደ ማንነቱ መመለስ ይችላል ።
አሳቦች ወደ ህሊና እንዲገብ የሚፈቅደው ሁነኛ ተቆጣጣሪ የሰው ፈቃድ እንዲቆይ ወይም እንዲወጣ ማዘዝ ይችላል ።
ዲያብሎስ ያለ ሰው ፈቃድ በሕሊና ውስጥ አንድ አሳብ ሊያስተዋውቅ ይችላል ። ይሁን እንጂ አሳብ ወደ ሕሊናህ እንዲገባ
ኃላፍነቱን ባትወስድም ልትቀበለው ኃላፊነቱን የምትወስደው ግን አንተ ነህ ።
ከፈለግህ እንዲህ ያለውን አሳብ ልታጠፋው ወይም ላትሞገተው ወይም እንኳን ደህና መጣህ ብለህ ላትቀበለውም ትችላለህ
። ይህን የኃጢአት አሳብ ከተቀበልህ ግን በአንተ ውስጥ ያደረውን መንፈስ ቅዱስንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ትክዳለህ ፡፡ በዚህ
ምክንያት የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና የልብህን ቅድስና መጠበቅ ያልቻልህ ሰው ሆነህ ትቆጠራለህ ማለት ነው ።
አሳቦች እንዳይቆጣጠሩህ በፈቃድህና በአንተ ውስጥ ባለው ጸጋ ልታሸንፋቸው ትችላለህ ። አንተ ካልታዘዝካቸው በስተቀር
የኃጢአት ሀሳብ ንጽሕናህን ሊያሳጡህ አይችሉም ፡፡
ስለሆነም የሀሳብህ ተገዢ አትሁን ፨ አሳብ እንዴት እንደሚጀምር ፤ እንደሚዳብር ፤ በሕሊና ውስጥ እንደሚመላለስ
እያንዳንዱ ሰው ሊያውቅ ይገባዋል ። አሳብ በገርነትና በዝግታ ከጀመረ በኀላ መጨረሻው በኃጢአት እንደሚጠቃለል ሁሉም
ሰው ይወቅ ። አሳብ የበለጠ እንዳይበረታታ ዕድሉን እንዳይሰጠው እያንዳንዱ ሰው የራሱ ዘብ ይሁን ።
☞ አሳብ አጥብቆ ቢይዝህና ያለማቋረጥ ቢወተውትህ ተስፋ አትቁረጥ መቋቋም ምንም ጥቅም የለውም ብለህም አትረታ ።
ተስፍ መቁረጥ ሰውን ቸልተኛ ስለሚያደርገው የውስጥ መዝጊያዎችን ወለል አድርጎ እንዲከፍት ያደርገዋል ። በመጨረሻም
ደግሞ ይወድቃል ፡፡ የምንመክራችሁ ግን አሳብን ተዋግታችሁ ድል እንድትነሱት ነው ፡፡ ግን እንዴት ???
 አሳብን ድል የምንነሣው እንዴት ነው ??
ለቀጣይ ይቆየን ........

ክፍል ፫

.......... ካለፈው የቀጠለ

☞ አሳብን ድል የምንነሳው እንዴት ነው ?

፩ . አሳቦችን አትፍራ በእነሱ እሸነፋለሁ ብለህ አታስብ ። ይልቁንም "ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ "በል {
ፊል 4*13}
አሳቦችን በመዋጋት ጽኑ ሆነህ እነዚህን ድንቅ ቃላት አስታውስ ፦ "የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ
የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን .. { 2 ቆሮ 10*5}
፪ . አሳቦችህን ለመምራት ራስህን አለማምድ እንጂ አሳቦችህ አይምሩህ ።
፫ . ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ ፦ ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ
እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም ፡፡ ዘወትር በስራ ራስህን ባተሌ አድርግ ፡፡ ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ
የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርግ ፡፡
፬ . ባልጠበኸው ሰዓት የኃጢአት አሳብ እንዳይጥልህ የልብህን ንጽሕና በመጠበቅ ሁልጊዜ ንቁ ሁን ፡፡
አሳቦች ደካማ አንተ ደግሞ ብርቱ በሆናችሁበት ጊዜ አሳቦችን ከጅምሩ አጥፍቸው ። አሳቦችን ለጥቂት ግዜ በሕሊና ውስጥ
ካቆየሀቸው ወዲያውኑ ሰፍረው ይቆጣጠሩሃል ። በአንተ ውስጥ ተደራጅተው ሲሰፍሩ ስለምትደክምና ልትቋቋማቸው
ስለማትችል ትወድቃለህ ። ስለዚህ አሳቦችን ካንተ ለማራቅ ንቁና ቀልጣፍ ሁን ።
፭ . የአሳብ መንፈሳዊ ባሕርይና የአሳብ ይሉኝታ ።
ሕሊናህ በጸሎት በተመስጦ ፤ በፍቅር ቃላት ፤ በውዳሴና ፤ በመዝሙር ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ይሆናል ። በዚህ ግዜ ሕሊና
በሌሎች የኃጢአት አሳቦች ላለመጠመድ ይሉኝታ ይይዘዋል ። በመሆኑም እነዚህን አሳቦች ያስወግዳል ።
፮ . በሌላ መልኩ ጥቃቶችን ሊያመጡብህ ከሚችሉ የኃጢአት አሳቦች መራቅ አለብህ ።
ከማንኛውም ክፍ ስብሰባ ፤ ከማንኛውም ክፍ ባልጀርነት ወይም ከማንኛውም ግንኙነት ራቅ ። መጥፎ አሳብ ሊያስከትሉብህ
የሚችሉና ከመንፈሳዊ አሳቦችህ ሊያስወጡህ የሚችሉ አሳቦች ያላቸው ጹሁፎችን ከአንተ ዘንድ አስወግድ ። በአጠቃላይ ክፋ
አሳብ ሊያመጡብህ የሚችሉ ነገሮችን ከአጠገብህ አስወግድ ፡፡
፯. ስሜቶችህ የሕሊናህ መግቢያዎች ስለሆኑ ንጹሕ አሳቦችን ይሰጡህ ዘንድ ንጹሕ አድርገህ ጠብቃቸው ።
በስሜቶችህ ቸልተኛ ከሆንህ ራስህን ተዋጋው ። ራስህን ጠብቅ ። ስሜቶችህ ያገልግሉህ እንጅ አይቃወሙህ ። ከዚህ በኀላ
በቅዱሳን ሥዕላት ላይ ተመስጦ አድርግ ስለ እነርሱ አድምጥ ፤ ማህሌቱን ቅዳሴውን አድምጥ ። እነዚህ ሁሉ ለልብህ
መንፈሳዊ አሳቦችን ያቀርባሉ ።
፰ . መልካም ወይም መጥፎ ያልሆኑ የጥርጥር አሳቦችን ተጠንቀቅ ።
እነዚህ አሳቦች በአብዛኛው ወደ ኃጢአት አሳቦች የሚመሩ ናቸው ። ሕሊናውን ሊቆጣጠር የማይችለውን ሰው ሕሊናውን
እንደ ወደደው እንዲባዝን ስለሚተወውና በኃጢአት የተሞላ ጉዳይ እንዲያገኝ ስለሚረዳው በእርሱ የተጠመደ ይሆናል ።
ሕሊናህን በጎ በሆነው በእግዚአብሔር ፍቅር ወይም በሌሎች ጠቃሚ ጉዳዮች ሙላው ።
፱ .በአሳብ ታውከህ ልታሸንፈው ካልቻልክ ከሌሎች ጋር በማውራት ከእርሱ ሸሽተህ ሂድ ፡፡
ሕሊናህ በተመሳሳይ ሰዓት በአሳብና በንግግር ሊጠመድ ስለማይችል በግንኙነትህ ውስጥ ያለውን ንግግር የኃጢአት አሳብህን
ያጠፋል ።
፲ .አሳብን ለማጥፋት የጸሎት እርዳታ ፈልግ ፡
ወደ እግዚአብሔር አንተን የማያስደስት ማንኛውንም ዓይነት አሳብ ከእኛ አርቅልን ብለን እንጸልያለን ፡፡

፲፩ . አሳቦችን ከመዋጋት ይልቅ አሳብን መሸሽ ይሻላል ።


ምንም እንኳን አዕምሮህን ወጥሮ የያዘውን ክፍ አሳብ ልታሸንፈው ብትችልም እግረ መንገዱን ሊያረክስህ ይችላል ።
በታላቅ መሻት ውስጥ ሆነህ "አሳብ እንዴት እንደሚጀምርና እንዴት እንደሚጠናቀቅ አውቃለሁ !" በማለት ራስህን አታታል

በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ሕሊናህ ብርታት በሚሰጡ በጎና ንጹህ አሳቦች ጥመድ ። ሕሊናህን አንተን ሊጠቅሙ በሚችሉ
አሳቦች እንጂ ሊጠቅሙ በማይችሉ ተቃዋሚ አሳቦች አትሙላው ።
፲፪ . አሳቦች እያደጉ ሲሄዱ ወደ ሌላ አሳብ ወይም ወደ ምኞት ይመራሉ ። እነዚህ ላይ አሳቦች የበለጠ አደገኛ ይሆናሉ ።
ምክንያቱም ከሕሊና ወደ ልብ ከአሳብ ወደ ድርጊት ስለሚሸጋገሩ ነው ። በዚህ ላይ ወደ ሌላ ነጥብ እንሸጋገራለን ።

 የምኞት ውጊያ ፦ ለቀጣይ ይቆየን !

ክፍል ፬
....... ካለፈው የቀጠለ
+ የምኞት ውጊያ
ብዛት ያላቸው የምኞት ዓይነቶች አሉ ። ከእነርሱ መካከል ፦ የሥጋ ምኞት ፤ የስልጣንና የደረጃ ፤ የብቀላ ፤ የበላይነት ፤
የሀብት ፤ የባለቤትነት ፤የክብርና ፤የዝና ምኞት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።
እዚህ ላይ ልብ ንብረትነቷ ከእግዚአብሔር ይልቅ ወደ ሌላ ስለሚሸጋገር "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ...( ምሳ 23*26) ለሚለው
የእግዚአብሔር ቃል የምትሰጠው ምላሽ አይኖርህም ።
1, በአንድ ምኞት ከተጠቃህ በእርሱ አትግፋ
ባገኛችሁት ምኞት ሳይሆን ባሸነፋችሁት ምኞት ደስ ይበላችሁ ፡፡ ሰውን ይበልጥ ደስ የሚያሰኝው ራሱን ማሸነፍ ሲችል ነው

2, ምኞት ቢያሰለችህም ተስፋ አትቁረጥ ! ምንም ጥቅም የለውም ብለህም አታስብ አንተ ልትመለከተው የሚገባህ መድህን
አለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ የሚያደርግልህን ነገር እንጅ አንተ ለራስህ ልታደርገው ያቃተህን ነገር አይደለም ጌታ
ሳምራዊቷን ሴት ወደ ወንጌል መስካሪነት መቅደላዊት ማርያምን ወደ ቅድስትነት የለወጠ አምላክ ነው ። እግዚአብሔር
ከሌሎቹ ጋር በጸጋ እንደሰራ ሁሉ ከአንተም ጋር ይሰራል ፡፡ ስለዚህ ብቻህን እንደምትዋጋ አድርገህ አታስብ ።
3, ድል ከተቀዳጁ በሗላ በፊትህ የቀደሙ ውድቀቶችህንና ደካማ ተፈጥሮህን ያላጎሉብህን ቅዱሳንን አስብ ።
እግዚአብሔር ድል የነሡትን እንደወዳቸው አንተንም ይወድሃል ። ከሌሎች ጋር ሆኖ እንደሚሰራውም ከአንተም ጋር የሠራል
። ጥቃት ሲጨምር የእግዚአብሔር ጸጋ ይበልጥ ይጨምራል ፡፡ ስለዚህ ወደ የእግዚአብሔር በመጠጋት የእርሱን እርዳታ ፈልግ

4, በምኞትህ ውስጥ ስትሆን እግዚአብሔር በምሕረቱ እስኪጎበኝህ ድረስ ከእርሱ ጋር በጽናት ታገል ።
በጠለቀ ኃጢአት ውስጥ ስትሆን ለመጸለይ አትፈር ። አባታችን አዳም ኃጢአት ከሠራ በሗላ ከእግዚአብሔር ፊት በመሸሽ
ራሱን ከዛፍ በስተ ጀርባ እንደደበቀ አንተም ራስህን አትደብቅ ። በወደቅህ ቁጥር እግዚአብሔር እንዲያነሳህ ወደ ንስሓ
እንዲመራህና እንዲያነጻህ በእርሱ ላይ ተጣበቅ ። "አቤቱ ጌታዬ ሆይ !አንተ በእኔ ላይ አድረህ ተዋጋ ። የእኔንና የአንተን
ጠላቶች ድል ንሳቸው !አንተ አትተወኝ በለው! " ፡፡
እንዲህ በለው "አቤቱ ጌታዬ ሆይ በኃጢአት ብወድቅም የአንተ የሆንሁና ከአንተ ጋር የተዛመድኩ ልጅህ ነኝ ! ከጋጣህ
ብጠፋም የመንጋህ በግ ነኝ !ከገንዘብ ቦርሳህ ውስጥ ብጠፋም የአንተ ድሪም ነኝ !ጠላት ከአንተ ጋር ሊለየኝ ቢሞክርም እኔ
አንተን ፈጽሞ አልረሳም አንተም እንዲሁ ! ።
5, ኃጢአት ከእግዚአብሔር ፍቅር እንዲለይህ አይሁን ። ይልቁንም ልብህን ለእርሱ ከፍተህ "አቤቱ አምላኬ ሆይ ! ይህን
ኃጢአት የፈጸምኩት ከድካሜ የተነሣ ነው እንጅ ከጥላቻ ወይም ከክህደት የተነሣ አይደለም ! "በለው ።
6, እግዚአብሔር ድካምህን እንደሚያውቅና እስካሁን ድረስም እንደሚወድህ እርግጠኛ ሁን ! በኃጢአት ውስጥ ብትሆንም
እግዚአብሔር ሊያድንህ ወደ እርሱ ሊያቀርብህና ወደ ቀደመ ደረጃህ ሊመልስህ እንደሚሰራ እመን ። አዳም የዳነው ንሥሐ
ለመግባት ባደረገው ሙከራ ሳይሆን አዳምን በተመለከተው የእግዚአብሔር ቸርነት ነው ።
7, የኃጢአት ምኞትህን የሚዛን ልክ በልብህ ውስጥ ያመጣጥን ዘንድ ማንኛውንም ዓይነት መንፈሳዊ ሥራ በመሥራት
የክፋታቸውንና የአደጋቸውን መጠን ቀንስ ። የምኞት ኃጢአት እስክታስወግደው ድረስ መልካም ፈቃድ በልብህ ውስጥ ቀስ
በቀስ እንደሚያብብ እርግጠኛ ሁን ። መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ እንደሚሰራ ሲታወቅህ ችላ አትበለው ! ከእርሱ ጋር ሥራ
እንጂ በምኞትህ ልትቀጥል አትሞክር ።
8, ድካምህን ስታውቅ በሌላ ጊዜ ራስህን ለውጊያ አታጋልጥ ።
❖ ውጪያዊ ውጊያዎች ፦ ለቀጣይ ይቆየን
ከብጹዕነታቸው መንፈሳዊ ውጊያ ከተሰኝው መጽሐፋቸው የተገኝበስመ አ
ክፍል ፭ ......ከለፈው የቀጠለ

ውጪያዊ ውጊያዎች

እነዚህ ውግያዎች የሚመጡት በሚገባ ከሚታወቁ ምንጮች ነው ። የሚመጡት ከዲያብሎስና ጠላት ከሆኑ ሰዎች ወይም
የቅርብ ወዳጆች ከሆኑ ሰዎች ነው ። እነዚህ ውጊያዎች ከዓለም ከቁሳዊ ነገሮች ፤ ወይም በውስጡ ጥቃት ከያዘ ከአካባቢ
ሊመጡ ይችላሉ ።
❖ የዲያብሎስ ውጊያዎች
የዲያብሎስ ውጊያዎች ዝግ ብለው የተራዘሙ ወይም ድንገተኛና ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ።
ዲያብሎስ ሰለባዎቹን የሚስበው በተራዘመ ለዘብተኛ አቀራረብ ስለሆነ ተጠቂዎቹ ምን ሊመጣባቸው እንደሚችል
አያውቅም ። ስለሆነም እነዚህን ዝግ ያሉ ውጊያዎቹን አንገነዘባቸውም ።
ዲያብሎስ ሕይወታቸውን እስኪለወጥ ድረስ መንፈሳዊ ፍቅራቸውን በዝግታ እያሳጣ ወደ ሰፊው የውጊያ ዓውድ ቀስ በቀስ
ይጎትታቸዋል ። የሚባንኑት እድላቸው ካለፈ በሗላ ስለሚሆን ዲያብሎስ ባልተዘጋጁበት ሰዓት ድንገት ይመታቸዋል ።
ምናልባት ጠቢቡ ሰለሞን የተወጋው ቅንጦት ፤ ድሎት ፤ብዙ ሴቶችና ይሉኝታ ባሉበት በዚህ መንገድ ነው ።በመሆኑም ወደቀ
። 1 ኛ ነገ 11*1-8 የወደቀው በእድሜው የመጨረሻ ዘመን ላይ ነው ።
ከባድ ከሚባሉትና ድንገት ከሚደርሱት ውጊያዎች መካከል በጻዲቁ እዮብ ላይ የወረደው አንዱ ነው ። ይህ ውጊያ
በእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኢዮብ ሊሸከመው በሚችለው መጠን የተወሰነና በመልካምና በተባረከ መንገድ የተጠናቀቀ
ውጊያ ነው ።
ከዚህ የተለዩ ዲያብሎስ የሚቀሰቅሳቸው ሌሎች ውጊያዎች አሉ ። እነዚህም ዲያብሎስ በአሳብ ውስጥ ወደ ሕሊና
የሚያስወነጭፋቸው ወይም በልብ ውስጥ የሚያሳድራቸው ውጊያዎች ናቸው ። እነዚህ ውጊያዎች ሲጀምሩ በአብዛህኛው
ደካማ ከመሆናቸው በላይ ለሰውየው እንግዳ ስለ ሆኑ ነው ። ሰውየው ወደ ልቡና ወደ ፍላጎቶቹ ዘልቀው እንዲገቡ
መዝጊያውን እስኪከፍትላቸው ድረስ በዚያው ይቆያሉ ። ከከፈተላቸው እዚህ ላይ ከፍተኛውን ስህተት ይፈጽማል ።
በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለሚያጠፋ ጠላት መዝጊያዎችህን መክፈት መንፈሳዊ ክህደት ነው ። ይህ
ክህደት ወደ ቤትህ ገብቶ ሊቀመጥ በወደደው በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ክህደት ነው ። እርሱ ለአንተ ቅዱሳት
ምሥጥራትን ከመግለጡም በላይ ልብህን የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ አድርጎልሃል ። አንተ ግን ለዲያብሎስ በመታዘዝ ልብህን
ከፍተህ የእርሱን ተቃዋሚ አሳቦችመቀበልህ ታላቅ ክህደት ነው ። በዚህ ክህደት ምክንያት በአንተ ውስጥ ያለውን
የእግዚአብሔርን የጸጋ ስራ ስለምትቃወም ዲያብሎስ በአንተ ላይ ኃይል ይቀዳጃል ።
ውጫዊ ውጊያዎች ከባድ ናቸው በማለት ምንም ዓይነት ምክንያት አታቅርብ ። ይህን የምታደርግ ከሆነ ለእነርሱ እጅህን ስለ
ሰጠህ ኃይል የምታጎናፅፋቸው አንተ ትሆናለህ ። የምትቃወማቸው ከሆንህ ግን ሐዋርያው እንደተናገረው ዲያብሎስ በአንተ
ፊት ደካማ ይሆናል "ዲያብሎስን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል "{ያዕ 4*7}
አንተ በውስጥህ ያለው ልብህ ብርቱ እስከሆነ ድረስ በዲያብሎስ ውጊያዎች ፊት በጭራሽ ደካማ አትሆንም ።
የርኩሳን መናፍስት አለቃ የሆነው ዲያብሎስ ከረዳቱ አንዱን ወደ አንድ ክርስቲያን እንዲዋጋው ሲልከው ርኩስ መንፈሱ
እየተንቀጠቀጠ ። ከዚህ የመንፈስ ቅዱስ ማደርያና የእግዚአብሔር መላእክት ዙርያውን የከበብት ይህን ብርቱ ሰው እንዴት
እዋጋለሁ እንዴትስ እቀርባለሁ ይላል ። በመስቀልስ ቅርፅ እጆቹን ለጸሎት ቢያነሳብኝ ወዴት አመልጣለሁ "ሂድ አንተ ሰይጣን
ቢለኝ" ወዴት እገባለሁ በማለት ይጠይቃል ።
ለዲያብሎስ ውጊያዎች ዓይነተኛ ምሳሌ ከሚሆኑን መካከል እግዚአብሔርን አለማመንና ተስፋ መቁረጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው
። ይሁን እንጂ እነዚህ የአንተ እጅ የሌለባቸውና የአንተ ያልሆኑ ውጪያዊ አሳቦችና ጥቃቶች ስለሆኑ አትፍራቸው ።
☞ ዲያብሎስ ወደ ሕሊናህ የሚያስወነጭፋቸው ፍላፃዎች የእግዚአብሔርን ሕልውና ፣ ፍቅሩንና ፣ጥበቃውን እንድንጠራጠር
የሚያደርጉ ናቸው ። የጸሎትህን ውጤታማነትና የቅዱሳንን አማላጅነት የሚያጠራጥሩ አሳቦችም በሕሊናህ ውስጥ
ይጨምራል ። ይሁን እንጅ አንተ በዚህ አልተደሰተሁም ብለህ አሳቦቹን በመቃወም እግዚአብሔር ከአንተ ያርቅልህ ዘንድ ወደ
እርሱ ስትጸልይ ዲያብሎስ "እነዚህ ሁሉ አሳቦች በአንተ ውስጥ እያሉ እንዴት ልትድን ትችላለህ ?" ይልሃል ። ይህ የአሳብ
ውጊያ ነው እንጂ በአሳብ የሚመጣ ውድቀት አይደለም ። ለጥቂት ደቂቃዎች ብትወድቅም እንኳ ከድካም የተነሣ እንጂ
በእግዚአብሔር ባለመታመን አይደለም ። ስለዚህ እርሱም ይቅር ይልሃል ።
አሳቦች ወደ ሕሊናህ የሚያመጣ ጽሑፍ እንዳታነብ እመክርሃለሁ ።እነዚህ አሳቦች የሚያቀብሉህን ክፋ ግንኙነቶች አስወግድ
። ዲያብሎስ አሳቦች አንተን ለመዋጋት ሊጠቀምባቸው ስለሚችል ቀድመኸው ብልህ ሁን ።
✞ ክፉ ባልጀርነት
ለቀጣይ ይቆየን
ክፍል ፮
.........ካለፈው የቀጠለ
 ክፋ ባልጀርነት
እንዲህ ያለ ባልጀርነት ለመንፈሳዊነትህ ፣ ለእምነትህና ለሕሊናህ ጎጂ ነው ። አልፎ ተርፎም ሕሊናህንና ስሜቶችህን
ሊያጠፋ ይችላል ።
የእናታችን የሔዋን የመጀመርያ ውድቀት የተከተለው ከእባብ ጋር በመሠረተችው ክፍ ባልጀርነት ምክንያት ነው ። ንጉሥ
አካአብ የወደቀው በክፋ ሚስቱ በኤልዛቤል ከንቱ ምክር ነው ።
ስለዚህ የአሳቦቻቸውን ተጽዕኖዎች በእናንተ ላይ በቀላሉ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ባልጀሮቻችሁን በሚገባ እንድትመርጡ
ትመከራላችሁ ። የትዳር ጓደኛ ደሚሆናችሁንም በጥንቃቄ እንድትመርጡ ትመከራላችሁ ። ምክንያቱም እነሱ
መንፈሳዊነታችሁን ሊክብም ሆነ ሊንድ የሚያስችል የአሳብ ተጽዕኖ በእናንተ ውስጥ ማሳደር ስለሚችሉ ነው ።
የቅርብ አጋሮች ከጓደኞች ወይም ከወዳጆች ወይም ከባልጀሮች የበለጠ ጥልቀትና አደገኛ ውጤት ሊያስከትሉ ይችላሉ ።
ከባልጀሮች ጋር የምትገናኙት አልፎ አልፎ ሲሆን ከቅርብ አጋሮች ጋር የምትኖሩት ግን እስከ መጨረሻው ድረስ ነው ። ስለዚህ
ከምንም ነገር አንጻር የእግዚአብሔር ሰው የሆነ አጋር መምረጥ የግድ ነው ። ልትደሰቱ የሚገባችሁ በውጭያዊው ገጽታ
ሳይሆን በውስጣቸው ባለው ጥልቀት ነው ። ይህን አስመልክቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው ቃል እንዲህ ይላል ፦
"አትሳቱ ክፋ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋዋልና "።{1 ኛ ቆሮ 15*33} ። ..ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል
።{ማቴ 10*36}ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑን ልጆቻቸው እንዳይጾሙ እግዚአብሔርን እንዳያመልኩ በጉባኤ ላይ እንዳይሳተፍና
በቤተ ክርስቲያን እንዳያገለግሉ የሚከለክሉ ወላጆች ናቸው ። አልፎ ተርፎም እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ራሳቸውን
እንዲያስጌጡና በተለያዩ ዓለማዊ መዝናኛዎች እንዲሞላቀቁ የሚመክሩ ናቸው ። በመሆኑም ይህን የሚመስለው ቤተሰብ
ራሱን እንደ አንድ መንፈሳዊ ቤተሰብ የሚመራ ቤተሰብ አይደለም ።አንድ ሰው ራሱን ከቤተሰቦቹ ወይም ከባልጀሮቹ መለየት
ሊያዳግተው ይችል ይሆናል ። ይሁን እንጂ እነርሱን ከመውደድ ይልቅ እግዚአብሔርን ሊወድ ለእነርሱ ከመታዘዝም
ለእግዚአብሔር ሊታዘዝ ይገባዋል ። እምነቱንና መንፈሳዊነቱን ስለ ወዳጆቹ ሲል መሥውአት አድርጎ ማቅረብ የለበትም ።
አንድ ሰው ምን ግዜም ቢሆን "ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባልናል ።{ሐዋ 5*29} የሚለውን የሐዋርያውን ቃል
ሊያስታውስ ይገባዋል ። ከእግዚአብሔር የሚሻል ወይም ከእርሱ ይበልጥ የሚወደድ ማንም ሊኖር አይገባውም ።
ከዘላለማዊነትህ የሚበልጥ ምንም ዓይነት ጠቃሚ ነገር አይኖርም ።ይሁን እንጅ ልትርቃቸው የሚገብ አንዳንድ ዘመዶች
ይኖሩሃል ። ይህም መራቅ በአካል መራቅ ሳይሆን በሥራቸው ፤ በንግግራቸውና በማናቸውም የተሳሳቱ ድርጊቶቻቸው ውስጥ
ተባባሪ ባለመሆን ሊሆን ይገባዋል ። ይህ በዚህ እንዳለ ክፋ አድራጊ ዘመዶቻቸውንም ሆነ ባልጀሮቻቸውን ስለ ይሉኝታቸው
ብለው የማይርቁ ሰዎች ብዙዎች ናቸው ። በመሆኑም ስለ ይሉኝታቸው የክፋ ስራቸው ተባባሪ ይሆናሉ ።መንፈሳዊ ሰው ግን
ይሉኝታ ወሰን እንዳለው ያውቃል ። ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ጥቃቶችና ምክንያቶቻቸው ለመራቅ ጠበቅ ያለ አቋምና
ብርቱ ሰብእና ሊኖር ያስፈልጋል ።ስለ መንገዱ ከመጠየቅህ በፊት ስለ ጓደኛህ ጠይቅ የሚባል አባባል ትክክለኛ ነው ።
ምክንያቱም አንዳንዶቹ ወዳጆችህ ነፍስህን ሊያጠፋ የሚችል መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ነው ። እነዚህ ሰዎች
ለልብህና ለአዕምሮህ እንግዳ የሆኑ መመሪያዎችንና አሳቦችን በማስተዋወቅ ሕይወትህን ከትክክለኛው መንገድ ያስወጧቸዋል
።የአንተ እውነተኛ ጓደኛ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብህ መሆኑን እወቅ ። እውነተኛ ጓደኛህ መልካም ዝናህን የሚጠብቅና
ስለ ድኀነትህ የሚያስብ ጻድቅና ልባም ሊሆን ይገባል ።

በመቀጠል ሌላኛውን መንፈሳዊ ውጊያ እንመልከታለን ፡፡


☞ ከብጹዕነታቸው {መንፈሳዊ ውጊያዎች ከተሰኝው መጽሐፍ ቁ. ፪ }

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣


‹‹ኢየሱስም ስለ ምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም››(ማርቆስ 1 ዐ÷28)
ይህን ጥቅስ በመጥቀስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእግዚአብሔርነቱ በማስወጣት እርሱ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር የተለየ
ነው የሚሉ ከኃድያን አሉ፡
፡ ዳሩ ግን የዚህ አባባል ምሥጢሩ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
በመሠረቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ባሕርይ፣ አንድ መለኮት ከሆኑት ከሦስቱ አካላት አንዱ መሆኑንና እግዚአብሔር
ተብሎ የሚጠራም
ተገልጿል፡፡ ለግንዛቤ ያህል ዮሐ. 1÷1-14 ተመልከት፡፡ ቃል እግዚአብሔር መሆኑንና ይኸው አካላዊ ቃልም ሥጋን ተዋሕዶ
በሰዎች መካከል
መገኘቱን፤ ጌታ ራሱ ሲናገር ያለው ሁሉ የእኔ ነው$ (ዮሐ. 16÷15)በማለት ለአብ የሚነገር ሁሉ ለእሱም እንደሚነገር፣ አብ
ቸር እንደሆነ ሁሉ
እሱም ቸር መሆኑን ገልጿል፡፡ እንዲሁም ግልጽና ጥርት ባለ አነጋገር ቸር አባት መሆኑን ሲገልጽ ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ ብሏል
(ዮሐ. 1 ዐ÷11)፡፡
እንግዲህ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ከሌለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በባሕርየ በመለኮት
አንድ ካልሆነ እንዴት ብሎ  ጠባቂ እኔ ነኝ$ ሊል ቻለ? እንግዲህ ክርስቶስ እግዚአብሔር በመሆኑ ለዚያ ሳይሠራ በአፈጮሌነት
ብቻ ምሥጋናን ከጌታ ዘንድ ለማግኘት ለመጣው ሰው ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር የለም በማለት የእሱን ቸር መሆን
ሲገልጽ ሰው ግን ቸር ሊባል እንደማይገባው ከእግዚአብሔር በቀር ሰው ቸር ሊባል አይገባውም ብሎ መለሰለት፡፡ በዚህም
በልቡ አስቦ የመጣውን እንዳወቀበት ገልጾለታል ሰውየው ቸር ብለው ቸር ይለኛል በማለት ነበርና አመጣጡ፡፡ ጌታ ደግሞ
የሰው ልቡና ያሰበውን ጠልቆ የሚያውቅ አምላክ መሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ የሠፈረ ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ ሳይጠራህ ከበለስ
በታች ሆነህ አየሁህ$ (ዮሐ.1÷49)፤ እንዲሁም የሰማር ያይቱ ሴት ባል የለኝም ባለች ጊዜ አምስት ባሎች የነበሩአት መሆኑን
ገልጾላታል (ዮሐ. 4÷18)፡፡
በሉቃስ ወንጌል 11-27 አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ የተሸከመችህ ማኀፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው
ባለችው ጊዜ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመልስላት የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁ ናቸው$ የሚል መልስ
መልሶላታል፡፡ እንግዲህ በዚህ መልሱ እናቱን ብፅዕት አይደለችም ሊል ፈልጐ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ይህንን እንዳንል ብፅዕት
ናት$ ተብሎ በሉቃስ 1÷45 ላይ ተጠቅሷል፡፡ ዳሩ ግነ
የጌታ መልሱ ያቺ ሴት በተንኮል መጥላቻና በተንኮል መምጣትዋን ዐውቆባት ማለትም ብፁዕ ብለው ብፅዕት ይለኛል የሚል
አስተሳሰብ አድሮባት ነበርና ጌታም አንቺ ብፅዕት አይደለሽም ብፁዓን ሊባሉ የሚችሉ ወንጌልን ሰምተው የሚጠብቁ
ናቸው፡፡ እመቤታችን ደግሞ የፀሐየ ጽድቅ የእውነተኛው ወንጌል የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እንደመሆንዋ መጠን በጸጋው
የተመላች መሆንዋ የታወቀ ነው፡፡
ስለዚህ አመላለሱ እመቤታችንን የነቀፈ የሚመስላቸው ቢኖሩም እርሱ ግን ሊናገር የፈለገው ያቺን ሴት ነው፡፡ በማርቆስ
1 ዐ÷28 ላይ ያለው አባባልም
ከዚሁ ጋር አንድ ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ጥያቄ፡
አንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ከሌላ የእምነት ድርጅት ተከታይ ጋር የፍቅር ግንኙነት ቢጀመር ወይም ቢጋባ ችግሩ
ምንድንነው?
መልስ፡
 ምስጢር ያፋልሳል።
አምላካችን ቅዱሱን ጋብቻ ሲሰጠን በውስጡ ምስጢር አለበት። ይህም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው ጋብቻ የኢየሱስ
ክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ ባል ሚስቱን የሚወዳትን ያህል ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ይወዳታል። ሚስት
ለባልዋ የምትታዘዘውን ያህል ቤተ ክርስቲያንም ለክርስቶስ ትታዘዛለች። (ኤፌ 5፥23) ጋብቻ በሚያምኑና በማያምኑ ሰዎች
መካከል ከተፈጸመ ምሥጢሩ ከክርስቶስና ከቤተ ክርስቲያን ተዋሕዶ ጋር አይስማማም፡፡ ከዚህም አልፎ ባልና ሚስት በጋራ
መፈጸም ያለባቸውን ምስጢራት (ምስጢረ ተክሊል፡ ምስጢረ ቍርባን...) የማይፈጽሙ ይሆናሉ።
 የጌታችንና የአባቶቻችን ትዕዛዝን ይጣረሳል።
"እግዚአብሔር እስራኤልን ከሰባቱ አሕዛብ ጋር አትጋባ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ
አትውሰድ" (ዘዳ 7፥3) ስለዚህ የጌታችንን ትዕዛዝ ከመተላለፍ ባለፈ አምላካችንን የካደን ሰው ስናገባ ለአምላካችን ያለን
ፍቅርን ጥያቄ ውስጥ ይከታል።
ቅዱስ ጳውሎስም በተደጋጋሚ ከሌላ የእምነት ድርጅት ተከታዮች ጋር ያለንን ከልክ ያለፈ ግንኙነት ያወግዛል። "ከማያምኑ
ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመድ ጽድቅ ከአመጽ ጋር ምን ተካፋይነት አለው? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
ወይስ ከሚያምኑ ከማያምን ጋር ክፍል አለው?" (2 ኛ ቆሮ 6÷14) "ከእነርሱ ጋራ እንዳትተባበሩ፣
እንደነዚህ ካሉት ጋር መብል እንኳ እንዳትበሉ እጽፍላችኋለሀ" (1 ቆሮ 5÷11-12)
 መልካም አመልን ያጠፋል።
አባቶቻችን ሲያስተምሩ ሰው ውሎውን ጓደኛውን ይመስላል "ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፣ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ
ትገኛለህ፣ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ" (መዝ 17÷26) "አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት
መልካሙን አመል ያጠፋል።"(1 ኛ ቆሮ 15÷33) በመሆኑም ከአሕዛብ የተጋባ መጨረሻው አሕዛብ መሆን ነው። ለዚህም
ትልቁ ማሳያ በምድራችን ከእርሱ በላይ ጠቢብ ያልነበረ አባታችን ሰሎሞን ነው። ሰሎሞን ፍቅር አዘንብሎት የአሕዛብን
ሴቶች አገባ በመጨረሻም አምላኩን ረስቶ ለጣዖቶቻቸው ሰግዷል። (1 ኛ ነገ 11፥4-8) ስለዚህ "እሷም በሃይማኖቷ እኔም
በሃይማኖቴ" የሚለውን አባባል ከተለያዩ ማኅበረ ሰብእ ለመኖር እንጂ ለትዳር እንደማይሆን አውቀን ቢቻል እምነታችንን
ሊያዳብርልን ከሚችል ሰው ጋር ነው መጋባት ያለብን።
 ክፉ ፍሬ ይወጣበታል፡፡
የተለያየ እምነት ያላቸው ሰዎች የሚወልዱት ልጅ ሃይማኖት ለመምረጥ ይቸገራል። ብዙ ጊዜ እምነት የለሽ ወይም
የአሕዛቡን እምነት ተከታይ ይሆናል። "እግዚአብሔር እስራኤልን ከሰባቱ አሕዛብ ጋር አትጋባ... እኔን እንዳያመልክ ሌሎችንም
አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና" (ዘዳ 7፥3)
በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ዘንድ ቁጣ እና መቅሰፍት ያስከትላል።
"እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ እናንተም ወደ
እነርሱ እነርሱም ወደ እናንተ ብትደራረሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህችም ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፋ
ድረስ መውደቂያና ወጥመድ በጎናችሁ መግረፊያ በአይናችሁ እሾህ ይሆንባችኋል…." (ኢያ 23÷12-13)
 በእርግጥ ከአሕዛብ ወይም ከመናፍቃን ወገን የትዳር አጋር የመረጥን ካለን ትምህርተ ሃይማኖትን እንዲማሩና የክርስትና
ጥምቀትን እንዲጠመቁ በማድረግ ቀድሰን ማግባት እንችላለን። "ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት
በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።" (1 ኛ ቆሮ 7:14፤) (ፍት. አን. ፳፬፣
ቍ. ፱፻፲፪-፱፻፲፭)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ጥያቄ
ሰው ከሞተ በኋላ ለምን ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳል? ፍትሐት ለምን ይፈታል? ስለ ተዝካር መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መልስ

 በቅዳሴያችን ገና ከጅምሩ "እምነ በሐ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፡ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደምን አለሽ" ብለን
እየተሳለምን ቤተ ክርስቲያን እናታችን መሆኗን እንመሰክራለን። ይህም በስጋዊ ልደት ያይደለ በጥምቀት የወለደችን ናት፡፡
ስለዚህ ሁሉም በሕይወታችን የሚከናወኑ ነገሮች በእሷ በኩል ማለፍ አለበት። ይህም ጥምቀታችን፡ ሠርጋችን፡ ሞታችን
ሁሉንም ለማስተናገድ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት አዘጋጅታ እጆቿን ዘርግታ ትጠብቀናለች።
ከእነዚህ ውስጥ በሞት ጊዜ ጸሎተ ፍትሐትና ተዝካር የመሳሰሉት ታከናውናለች። ፍትሐት ማለት ፈትሐ ከሚለው የግእዝ
ግስ የወጣ ሲሆን መፍታት፡ ማስለቀቅ ማለት ነው። ተዝካር ደግሞ ተዘከረ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ማስታወሻ
ማለት ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በሕይወተ ስጋ ሲሞቱባት በድለው ከሆነ ብላ የፍትሐት ጸሎት ታደርጋለች
እንዲሁም ከክርስቲያኖች ኅበረት እንዳልተለዩ ስትገልጽ በቅዳሴ ጊዜ ስም እየጠራች፡ በእነሱ ስም ምጽዋት እየሰጠች
ያረፉትን ታስታውሳቸዋለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለምን ሰው ከሞተ በኋላ ጸሎተ ፍትሐት ወይም ተዝካር ይደረግለታል ቢሉ?
1) እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለሆነ የሞተው ሰው በደለኛ ቢሆንም ከእርስ በርስ ፍቅር አንጻር በአሁኑ ፍርድ ሆነ በዳግም
ምጽአት እንዲምረው ለመለመን ነው።
ለምሳሌ፡ ሙሴ ከእሱ 100 ዓመት በፊት ለሞተው ለያዕቆብ ልጅ ሮቤል ከአምላክ ዘንድ ምሕረት እንዲያገኝ ለምኗል። ይህም
ሮቤል በሕይወተ ስጋ እያለ ከአባቱ ሚስት ጋር ዝሙት በመፈጸሙ እስራኤላውያን ከግብጽ ሲወጡ ከ 12 ቱ ልጆች አጽም
የእሱ ተለይቶ በመጥቆሩ ነበር። (ዘዳ 33፥6)
እንዲሁም ቅዱስ ጳውሎስ ብዙ አገልግሎት በኋላም በሞት ለተለየው ለሄኔሲፎሩ በዳግም ምጽአት ጊዜ ምሕረት እንዲያገኝ
ለምኗል። (1 ጢሞ 1፥16)
2፡ የቤተ ክርስቲያን ባህርይዋ የሚገጽበት ስለሆነ
ቤተ ክርስቲያን ሲባል ብዙ ትርጉም ቢኖሩትም ከእነሱ ውስጥ የክርስቲያኖች አንድነት ይግኝበታል። ይህም አንድነት ልዩ ነው
ምክንያቱም በውስጡ በዘመን፡ በቦታ፡ በእድሜ እና በመሳሰሉት የሚለያዩ ሰዎች ስብስብ ስለሆነ ነው። ለዚህም አንድነት ራስ
የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ብልቶቹ ደግሞ እኛ ነን። "አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር
ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤" (1 ኛ ቆሮ 12:12፤) እንዲል
ቅዱስ ጳውሎስ። በመሆኑም አንድ ሰው በሕይወተ ስጋ ስለሞተ ብቻ ከዚህ አንድነት አይለይም ይልቁንም በመንፈሳዊው
ዓለም ውስጥ ካሉት ጋር ተርታ ተሰልፎ አንድነቱን ያጠነክራል። በመሆኑም ጸሎተ ፍትሐት ይህን አንድነት ከሚሰብኩ
ጸሎቶች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱም ላረፉ ወገኖቻችች ስንጸልይ ምሕረትን ለመለመን ብቻ ሳይሆን የራሳችን አካል ናቸውና
እነሱን ማሰብ፡ መዘከር ተአጥሮአዊ ስለሆነም ጭምር ነውና።
3፡ ከሞት በኋላ ሊሰረይ የሚችል ኃጢአት ስላለ ነው።
በወንጌል "በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን
ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።" (ማቴ 12:32፤) ተብሎ እንደተጻፈ በዛኛው ዓለም ይቅር የሚባል ኃጢአት እንዳለ
እናውቃለን። ይህም ከሞት በኋላ ንስሐ አለ ማለት ሳይሆን በሕይወተ ስጋ ያሉትና በቅዱሳኑ ምልጃ ምክንያት የሚመጣ
ስርየት ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕይወት ዘመኑን በሙሉ በኃጢአት ኖሮ በጸሎተ ፍትሐት ምሕረትን አገኛለሁ የሚል ፈጽሞ ተሳስቷል።
ምክንያቱም ይህ ጸሎት ተግባራዊ የሚሆነው በንስሐ ሕይወት ለሚመላለሱና በኑሮዋቸው እንደየአቅማቸው ተጋድሎ
ለሚያደርጉ ነው።
በመጨረሻም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ "በዚህ በሚደረግለት ጸሎትና ቁርባን እንዲሁም ምጽዋት ያረፈው ሰው ጥቅም
እንደሚያገኝ አትጠራጠር" ሲል ይመክረናል።
ምንጭ፡ መድሎተ ጽድቅ (ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::


ስለ "ቶ" መስቀል ወይም ፊደል የተሰጠ ማብራሪያ፡፡
ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት "ቶ"
የመላእክታን ልሳን፣ ሰማያዊ ቋንቋ፣ የሰው ልጆችም ቢሆን የመጀመሪያ መግባቢያ ቋንቋ (የቋንቋዎች እናት) የነበረው አሁን
በምድር ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ያውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ የሚገኘው ታላቁ ሀብት
የግእዝ ቋንቋ ነው:: ግእዝ ማለት መጀመሪያ ማለት ነው::
ለነገሩ እንደ ህጻናት እንደገና
ሀ-ግእዝ
ሁ-ካብዕ
ሂ-ሣልስ
ሃ-ራብዕ
ሄ-ኅምስ
ህ-ሳድስ
ሆ-ሳብዕ
ብንል እንደ ልጆቹ " አ ቡ ጊ ዳ ሄ ው ዞ" ብለን ፊደል ብንቆጥር፣ ምሥጢሩን ብንመረምር፣ ኅልዎተ እግዚአብሔርን፣ የስነ
ፍጥረት ምስጢርን፣ የአዳም የቃል ኪዳን ተስፋን፣ ተዝቆ የማያልቅ ወንጌልን፣ ተነግሮ የማይጨረስ የክርስቶስ ነገረ ድኅነትን፣
የእመ አዶናይ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትን የእያንዳንዱ ፊደል ቅርጽና ይዘት እንዲሁም ቀመር፣ ቅደም ተከተልና
አቀማመጣቸው አስረጂ ምልክቶችና ትምህርቶች ናቸው እንጂ እንዲሁ በዘፈቀደ የተደረደሩና የተሳሉ አይደሉም::
እስኪ የተወሰኑ ፊደሎችና ትርጉማቸውን እንደ ምሳሌ እንመልከት :-
"ሀ"- ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እም ቅድመ ዓለም፡፡
"ሀ"- ማለት የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው፡፡
"ለ"- ብሂል- ለብሰ ሥጋ እምድንግል፡፡
"ለ"- ማለት- ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ሥጋን ለበሰ፡፡
"ሐ"- ብሂል ሐመ ወሞተ ወተቀብረ፡፡

"ሐ"- ማለት ክርስቶስ ታመመ፣ ሞተ፣ ተቀበረ፡፡


"መ"- ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር፡፡
"መ"- ማለት የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው
"ሠ"- ብሂል ሠረቀ በሥጋ፡፡
"ሠ"- ማለት ጌታ በሥጋ ተወለደ (ተገለጠ)፡፡
"ረ"- ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ፡፡
"ረ"- ማለት ምድር በቃሉ ረጋች (ጸናች)
"ሰ"- ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ፡፡
"ሰ"- ማለት ጌታችን ሰው ሆነ፡፡
"ቀ"- ብሂል ቀዳሚሁ ቃል፡፡
"ቀ"- ማለት በመጀመሪያ ቃል ነበር፡፡
"በ"- ብሂል በትኅትናሁ ወረደ እግዚእነ፡፡
"በ"- ማለት ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ (ተወለደ)፡፡
"ተ"- ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ፡፡
"ተ"- ማለት ጌታችን ሰው ሆነ፡፡
ዛሬ እግዚአብሔር በፈቀደልን መጠን በግእዝ ቋንቋ ውስጥ ካሉት ሆህያት መካከል ባለ ብዙ ምሥጢር ሆሄ የሆነውን "ቶ"
ፊደልን እንመለከታለን::

የድንግል ማርያም ልጅ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተዋልና ጥበቡን ያድለን::
ከላይ በቀረበው ምሳሌ መሠረት የ"ተ" ቤተሰብ የሆኑት:-
ተቱቲታቴትቶ
ሲሆኑ "ተ" ማለት ከላይ በምሳሌ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በሰጠው የተስፋ ቃልኪዳን መሠርት
ጊዜው ደረሰና የሚወደውን አንድያ ልጁን ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል የሆነውን ጌታችንና
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ የሆነ በፍጹም ተዋህዶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም
ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነበትን ምሥጢር ወይም ምሥጢረ ሥጋዌን ያመሣጥል
ፊደል "ተ":: "ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ " (ዮሐ 1:14) "የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም
(ከድንግል ማርያም) ተወለደ" (ገላ 4:4) በዚህም መሠረት "ተ" ፊደል የሚወክለው ወይም የሚያመሣጥረው "ተሰብአ
ወትሰገወ፣ አምላክ ሰው ሆነ" የሚለውን ነው::

ታድያ አምላክ ሰው መሆንን እና "ተ" ፊደልን ምን አገናኛቸው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል:: ይህንን ጥያቄ ለመመልስ የ"ተ"
ፊደል ቅርጽን ልብ ብለን ማስተዋል ይገባናል:: የ"ተ" ፊደል ቅርጽ ሁለት ነገሮች የተመሳቀሉ የሚመስሉ ማለትም የላይኛው
ክፍል አጠር ያለ፣ የታችኛው ደግሞ ርዘም ያለ፣ እንዲሁም በግራና በቀኝ የተቀመጡት አግድም ክፍሎች እኩል የሆኑ ሲሆን
ለዚህም ነው ሁለት እጁን የዘረጋ የሰው ልጅ ምስልን ወይም ቅርጽን ይወክላል ወይም ይመስላል የተባለው"ተ" ፊደል::
በዚህም መሠረት "ተ" ፊደልን አባቶች "ተሰብአ ወተሰግወ፣ አምላክ ሰው ሆነ" ብለው ያመሠጥራሉ::

"ተ" ፊደል ይህን ያህል ከዳሰስን የ"ተ" ቤተሰብ የሆነውን "ቶ" ፊደልን እንደሚከተለው እንመለከታለን::
በቅድሚያ የ"ቶ" ፊደል ቅርጽን ልብ ብለን ልናስትውል ይገባል:: እንደምንመለከው "ቶ" ከ"ተ" ፊደል አናት ላይ ክብ (o)
ተቀጥሎበት "ቶ" ቅርጽን ይሰጣል:: በዚህም መሠረት በመጀመሪያ "ተ" የነበረው ፊደል በመጨረሻም ወደ "ቶ" ፊደል
ይቀየራል:: "ቶ" ፊደል የሚመስለውም የሰው ቅርጽን ይዞ ከላይ ያለው ክቡ ነገር የሰው ልጅ የራስ ክፍል ወይም የራስ ቅልን
የሚመስል ሲሆን ሌላው የፊደሉ አካል ግን ከ"ተ" ጋር አንድ ዓይነት ነው:: ስለዚህ "ቶ" ፊደል ሁለት እጆቹ በመስቀል ቅርጽ
የተዘረጉ እንዲሁም በራሱ ላይ ደግሞ ክብ ነገርን ወይም አክሊልን የደፋ የሰው ልጅ ምስልን (ቅርጽን) ይዟል:: በዚህም
መሠረት "ቶ" ፊደል ክርስ"ቶ"ስን የሚወክል ሲሆን ምንም በደል የሌለበት ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምንና
ልጆቹን ከወደቁበት የኃጢአት መርገም ለማዳን ሲል በመስቀል ላይ የፈጸመውን ዋጋ ያመሣጥርልናል፣ ያሳየናል፣
ያስተምረናልም "ቶ"::

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ጥያቄ፡
ለምንድነው ስንጸልይ ወደ ምሥራቅ ማየት ያለብን?

መልስ፡
 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ቤተክርስቲያን የምትታነጸው ምስራቁን አቅጣጫ ጠብቃ ነው እንዲሁም
ከቤተክርስቲያኑ ጋር አብሮ የሚሰራው ቤተልሔም በስተምስራቅ በኩል ይደረጋል፡ በጸሎት ሰዓትም ወደ ምስራቅ ዞረን ነው
የምንጸልየው፡ በሥርዓተ ቀብር ላይም የሞተ ሰው ሲቀበር ራሱ ወደ ምዕራብ እግሩ ወደ ምስራቅ ሆኖ ይቀበራል ፡፡
ሌላው ዲይቆኑ በሥርዓተ ቅዳሴው ላይ ወደ” ነጽሩ ውስተ ጽባሕ ምስራቅ ተመልከቱ” ይላል። ምክንያቱ ደግሞ፡

1• ፦የአዳም አባታችን ጥንተ ርስት ገነት በምስራቅ ናት። ዘፍ 2፥8

ይህች ርስታችን በአዳም በደል ምክንያት በኪሩቤል ሰይፍ ተዘግታ ስትኖር ሞትን ድል አድርጎ በበደልን ክሶ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ከፈተልን። (ሉቃ. 23፥4)

ወደ ምስራቅ በተመለከትን ቁጥር ወደ ገነት ለመግባት የተሰጠን ተስፋ ትዝ ይለናል የተከፈተችውም ቤታችን ገነት በእምነት
ወለል ብላ ትታየናለች በክርስቶስ ያገኘነውን ጸጋ እናስባለን ምድራውያን አለመሆናችንም ይታወሰነል።
                               
   2• ጌታ የተወለደው በምስራቅ ነው።
ሰብአ ሰገል ኮከቡን ያዩት በምስራቅ ሲሆን ያ ኮከብ የምሕረተ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው። እነርሱን ወደ እግዚአብሔር
እንዳደረሳቸው ሁሉ እኛንም ወደ ለመለመው መስክ ይመራናል። ማቴ 2፥2 መዝ 22፥14

ወደ ምስራቅ በተመለከትን ቁጥር የጌታ መወለድ እና ያደረገልን ውለታ ይታወሰናል የምሕረቱ ኮከብ እየመራን መሆኑ ትዝ
ይለናል።                                                 
   3• ፦ ምስራቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው።

ከምስራቅ ጨለማውን የሚገፈው ፀሐይ እንደሚወጣ ሁሉ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያምም የዓለምን የኃጢአት ጨለማ
የሚገፍ ፀሐዬ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷል፡፡ "ለእናንተ ስሜን ለምትፈሩ የፅድቅ ፀሐይ ትወጣላችሁለች" ሚል 4፥1
ሕዝ 44፥1፦4 ነብዩ ሕዝቅኤልም እመቤታችንን ያያት በምስራቅ ነው ስለዚህ ወደ ምስራቅ በተመለከተ ቁጥር እመቤታችን
ትዝ ትለናለች የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ስለተወለደልን በጨለማ አለመሆናችን ትዝ እያለን ከኃጢአት እንርቃለን።

  4• ፦የዓለም ድኅነት የተገኘው በምስራቅ ነው ።

ጌታ የተሰቀለው እና ዓለምን ያዳነው በምስራቅ ነው ኢየሩሳሌም ምስራቃዊት ከተማ ናት እና በመሆኑን ወደ ምስራቅ በዞርን
ቁጥር የተሰቀለውን ክርስቶስን እና የተከፈለልንን ዋጋ እናስባለን።
                           
5• ፦ክርስትናና ቤተክርስቲያን የተመሰረቱት በምስራቅ ነው።

የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን የተመሰረተው ኢየሩሳሌም ሲሆን ወንጌል የተሰበከውም ከዚሁ በመነሳት ነው ።ስለዚህ
ወደምስራቅ ስንዞር የቤተክርስቲያን ጉዞ የወንጌል መስፍፍት እና የሕዝበ ዓለም መዳን ትዝ ይለናል።

   6.ምስራቅ የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው ።

ኢሳ 28:13 እግዚአብሔርን በምስራቅ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ ት.ሕዝ 43፦2
የእስራኤል አምላክ ክብር ከምስራቅ መንገድ መጣ።

  7• ፦የጌታ ዳግም ምጽአትም ከምስራቅ ነው።

ዘካ 14፥14 በዚያን ቀን እግሮቹ ኢየሩሳሌም ትይዩ በምስራቅ በኩል ይቆማሉ ሐዋ 1፦11 ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው
ኢየሱስ ወደሰማይ ሲርግ እዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል ።
                                 
8• ፦ቅዱሳን አበው ሲጸልዩ ወደ ምስራቅ ይዞሩ ነበር።

ዳን 6፥ወደ ኢየሩሳሌም ያለውን መስኮት ከፍቶ ይጸልይ ነበረ ነብዩ ዳንኤል እግዚአብሔር ምሉዕ በኩልሄ (የሌለበት ቦታ የሌለ)
መሆኑን ያውቃል።

9• ፦ታቦቱ በምስራቅ በኩል ባለው ቤተ መቅደስ አስቀምጠን ስጋወ ደሙ የሚፈተተው ጌታ በምስራቅ ሀገር ጎለጎታ ለኛ
ስጋውን መቁረሱ ደሙን ማፍሰሱበማሰብ ነው
10• ፦በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ ወደ ምስራቅ ተመልከቱ በምስራቅ የተደረገልንን ውለታ የተከፈለልንን ዋጋ ከድንግል
ማርያም ከሆነችው እመቤታችን የተገኘውን ፀሐየ ፅድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን አስቡ ማለቱ ነው ።

11• ፦ በቀብር ሥነ-ሥርዓት የአስከሬኑን ፊት ወደ ምስራቅ የሚዞርበት ምክንያት በዳግም ምጽአት በሚነሳበት ጊዜ ፊቱን
ወደ ጌታ እንዲያዞር እና እንዲመለከት በማስብ ነው ።
እንግዲህ ወደምስራቅ መዞር የክርስቶስን የማዳን ስራ የቅዱሳንን ሕይወት የሰማዕታትን ገድል የክርስቲያንን ተስፈ
የሚያሳስበን ነው እና ወደ ምስራቅ እንዞራለን ይህንን ሥርዓት ያስተማሩን ቅዱሳን አበው በረከታቸው ይደርብን።

ምንጭ፡ ሐመረ ኖኅ ድረ ገጽ
ወስብሐት ከእግዚአብሔር!

፨ኧረ አልሆንልኝም አለ፨


/የንስሐ መነባንብ/
ኧር አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ???
መንጸፈዴን ወደቅኩኝ ነፍሴ በኃጢያት ሸፈተ
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ
ኧር አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ
ጨርሶ አለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ
ነጭ ነጠላ አጣፍቼ ከቤተ መቅደስ ስወጣ
መጽሐፍ ቅዱስ ዘርግቼ ለስብከት መድረክ ስወጣ
ልብስ ተክህኖ ለብሼ ነፍቅ ገባሬ ሰናይ ስሆን
ጥቅስ በቃሌ ስደረድር ለዜማ ቅኔ ስቀኝ
አካሌ እዚህ ሆኖ መንፈሴ እየሸፈተ
ነፍሴን በኃጢአት ገንዞ ስጋዬ ነፍሴን ጎተተ
*
*
*
ኧር አንድ በይኝ እመብርሃን ወለላይቱ ተማለጂኝ
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ
ማለዳ ኪዳን አድርሼ ቅዳሴ ጸሎት ጨርሼ
ከቤተክርስቲያን ወጥቼ ወደ ስጋ ገቢያ ተመልሼ
በኃጢአት ባህር ስዋኝ የግፍ ዳንኪራ ስረግጥ እውላለሁ
የልጅነት ፀጋዬን አውጥቼ ብኩርናዬን እሸጣለሁ
እዚህ መላዕክ መስዬ ላዬ በቅድስና በርቶ
ውጪ ከክፋት ከፍቼ ኃጢአት በጽድቄ ተተክቶ
በሀሜት የሰው ስጋ ስበላ በወንድሜ ሸር ስሸርብ
ስዋሽ ስቀጥፍ ውዬ ስሰርቅ ሳሽሟጥጥ ስሳደብ
ነጠላ ስለብስ ግን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ስገባ
ሰዓሊለነ ቅድስት ስል ያለ ንስሐ እንባ
የመውደቂያዬ ጉድጓድ ጥልቀቱ ወሰን ዳርቻ የለውም
እዝነ ህሊናዬ ለዓለም እንጂ ለጽድቅ ቦታ የለውም
መሃረነ ክርስቶስ እንዳልል ተዘከረነ ፈጣሪዬ
ኃጢአት በደሌ አፈነኝ በሀፍረት ነደደ ህሊናዬ
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን ተዘከረነ ብዬ
ስለእኔ መገረፉን የመስቀሉን ፍቅር አቃልዬ
እንዴት ማረኝ ልበለው ስለ ስጋ ጣዕም ተቃጥዬ
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን?
ዓይኔን ወደ ፀፍፀፈ ሰማይ ወደ ሥላሴ መንበር
አንስቼ ማየት አቃተኝ መረኝ ብዬ ለመናገር
ለሰው ጻድቅ መስዬ የኃጢአት ጎተራ ሆኛለሁ
እንዴት አባቴ ቀና ብዬ መንበረ ጸባኦትን አያለሁ
እባክሽን እናቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ
እንደቃና ዘገሊላ ባዶ ማድጋዬን ሙዪልኝ
ከፊቱ እንዳላፍር ከአማኑኤል ጋር አስታርቂኝ
ለተጠማ ውሻ እንዳዘንሽ ለመጻተኛው እዘኚልኝ
አንቺ የትሁታን ትሁት ርህሪይተ ልብ እናቴ
ከልጅሽ ከኢየሱስ አማልጂኝ እዘኚ ለእኔም እመቤቴ
አንቺ ውዳሴሽ የነፍስ ስንቅ ስምሽ ከማር የጣፈጠ
በላኤ ሰብ በእፍኝ ውሃ በምልጃሽ ከሞት ያመለጠ
አንቺ መላእክት የሚጎበኙሽ የካህናት አለቆች ምስጋናቸው
በመወሰን የማይወሰን እሳተ መለኮትን የቻልሽው
አንቺ በገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋ የሆንሺው
ዛሬም ለእኔ ሁኚኝ ስለ ነፍሴ ተዋሺው
እንጂ እኔማ አልቻልኩም የልቤ ንጽህና ጠፍቷል
ለጸሎት እንኳን ስቆም ልቤ ለሁለት ተከፍሏል
*
*
*
ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ
የልቤን መወላወል የነፍሴን ድካም አበርቺ
በአማላጅነትሽ ስር ነኝ እና ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺ
ለሰው አይን ባይገለጥም ሰውሬ የሰራሁት ኃጢአት
አምላክን አሳዝኖታል የምኖርበት ሕይወት
ይኸው የምናገረው አይሰምር የወረወረኩት አይመታ
ስጋዬ አልተቀደሰ ገበታዬ በረከት የለውም
ዕውቀት ምርምር አይዘልቀኝም ህሊናዬ ፍሬ አይቋጥር
ዝርው ሆኖብኝ ቀርቶ የነፍስ የስጋዬ ምስጢር
ይኸው የማወራው ለሰው አይጥም ፍቅር ከእኔ ቤት ርቋል
መቆም መቀመጤ አያምርም ሰው በስራዬ ይማረራል
የኃጢአት ምንዳዬ ይኸው የኃጢአት ደሞዜ ይኸው
ስቃዬ ውስጤን በልቶታል
ለአንድነት የተናገርኩት ዛሬም ጉባኤ ይበትናል
እና አዛኝቱ ታረቂኝ ከልጅሽ ከአማኑኤል አማልጂኝ
ከሰው የሸሸኩትን ኃጢአት ጨርሶ ብልቶ ሳይውጠኝ
የበላዪ ሰብ እመቤት እባክሽን ተማለጂኝ
አንቺ ሕይወቴን ዳብሺው ነፍሴን ዕርፍት እንድታገኝ
*
*
*
ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ???
*//*

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡርበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ጥያቄ (6-2)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ ብሉ የሰጠበት ምክንያት ምንድን ነው?
መልስ፡
 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ 33 ዓመት ከ 3 ወር ከተመላለሰ በኋላ በምሴተ ኀሙስ ለሐዋርያት
የዘለዓለምን ሕይወት እንዲያገኙ በሕጽበተ እግር ካጠመቃቸው በኋላ ስጋውንና ደሙን ሰቷቸዋል።
ይህም ቍርባን የሚያስገኘው ጥቅም
(1) የሕይወትን ምግብ እና ዘለዓለማዊ ሕይወትን ያስገኛል።
"ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ
አይጠማም። ... "54፤ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥"
(ዮሐ 6:35-54)
(2) ሥርየተ ኃጢአትን
"ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።" (ማቴ 26:28፤)
(3) ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆንን
"ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።" (ዮሐ 6:56፤)
(4) እርስ በርስ በፍቅር መተሳሰርን
"የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር
ኅብረት ያለው አይደለምን?
አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።" (1 ኛ ቆሮ
10፥16-17)
ይህ በእንዲህ እንዳለ ታዲያ ለምን በምግብ መልክ መስጠት አስፈለገ ቢሉ?
(1) በምግብ የመጣውን በደል በምግብ ለማጥፋት አዳምና ሔዋን አትብሉ የተባሉትን ዕፀ በለስ በልተው እንደወደቁ ሁሉ እኛ
ደግሞ የክርስቶስ ስጋና ደም እየተመገብን ከወደቅንበት እንነሳለን።
(2) ምግብ ከሰውነት ይዋሃዳል። እኛም ስጋና ደሙን ስንቀበል ከላይ እንደገለጽነው ከክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን።
(3) መብል መጠጥ ያፋቅራል፡፡ እንደዚሁም የክርስቶስ ስጋና ደምም በፍቅር የተሞላን አድርጎን እርስ በርስ ያፋቅረናል።
ምንጭ፡ ትምህርተ ሃይማኖት ጥራዝ /ዘኆኅተ ብርሃን/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምለክ አሜን

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!


ከትንሣኤ በፊት ያለው ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ይኸውም በነቢዩ ኢሳይያስ ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማምነ፣ በእውነት
ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንም ተሸከመ፤ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡ /ኢሳ. 5፤34-36/ ተብሎ በመንፈስ ቅዱስ
ትንቢት የተነገረው ቃል ተፈጸመ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሳምንት ውስጥ ለድኅነተ ዓለም ሲል
በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ የተቀበለውን ጸዋትወ መከራ ለማስታወስ የወጣ ስያሜ ነው፡፡
በሰሙነ ሕማማት መስቀል መሳለምና እርስ በእርስ መሳሳም የለም፡፡ ይህም ይሁዳ ጌታን በመሳም አሳልፎ እንደሰጠው
ለማሰብ ነው፡፡
በዚህ ሣምንት ውስጥ ያሉት ዕለታት ስያሜያቸውና በየአንዳንዳቸው ዕለታት የተፈጸሙትን ድርጊቶች እንደሚከተለው
እንመለከታለን፡፡
#ሰኞ ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር ያድራል በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ /ማር. 11፣11-14/
ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፣ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም
ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ ዕለት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፡፡
በለስ የተባለች
ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች፣ ሃይማኖትና ምግባር ናት፡፡ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፡፡
እስራኤልን ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ
ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡
በለስ ኦሪት ናት
ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን
ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና
እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡
በለስ ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል
ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ደስ ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ
ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ
እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደ፤ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምሥያጥ /የንግድ ቤት/
ሆኖ ቢያገኘው፤ «ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች... እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት» ማቴ.21፣13 ብሎ የሚሸጡበትን
ሁሉ ገለበጠባቸዉ፣ ገርፎም አስወጣቸዉ፣ ይህም የሚያሳየዉ ማደሪያው ቤቱ የነበርን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን
ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት
ሰኞም ይባላል፡፡
#ማክሰኞየጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡
ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ
ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፡፡
ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ
መፍታት በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበር ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት
ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም? ይለናል፡፡ ከሰው
ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው
ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም
አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፡፡
ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡
በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣
ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው፡፡
እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ጻማ ወድካም
አመ ከመ ዮም
ያብጽሐነ ያብጽሐክሙ
እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም
ለብርሀነ ትንሣኤሁ ቅድስት አሜን

የፊደል ገበታ

ሀ ብሎ ጀምሮ የፊደል ገበታ


ለመማር አስቦ ከጥዋት እስከማታ
የሰው ሀገር ሂዶ ተጠርቶ ከጌታ
ያለ ምግብ ዋለ የትንሳኤ ለታ::
የናቱን ቤት ትቶ:በልጅነት ወጥቶ
ልመና ሲለምን የሚዘከር አጥቶ
በረሃብ ይሰቃያል ውሻውንም ፈርቶ
ቢለምንም እንኳን በርትቶ ተፅናንቶ
ትንሽ ነው የሚያገኝ ብዙ ሰአት ለፍቶ
ውሻውን ራቡን ሁለቱን ታግሶ
ይማራል ትምህርቱን ድሪቶውን ለብሶ፡፡
የውሻውን ነገር፡እረ እንዴት ልናገር
ይናገርው እንጂ የተማሪው እግር
በውሻ እግሮቹን ተነግሶ ተነግሶ
ለምጡ ምስክር ነው ሁለመናው ቆስሎ
ከውሻ ጋር ታግሎ፡የሚበለው ቆሎ
ሰውነቱም ከስቶ በውሻ ቆሳስሎ
ሌት ተቀን ቀፅሎ :ተምሬ መምህር እሆናው ብሎ:ከናት ካባቱ ቤት
የላመ የጣመ ሁሉ እያለለት
ይሄን ሁሉ ትቶ ወጣ ትምህርት ቤት::
እራቡ ጥማቱ:እንቅልፍ ማጣቱ
የዘመድ ናፍቆቱ:የትምህርት ብዛቱ
ብርዱ መሰልቸቱ፡ተሎ አይመሽ መአልቱ
አይነጋ ሌሊቱ፡
የቆሎ ተማሪ ስቃዩ መብዛቱ፡፡
ይህን ሁሉ ችሎ
ዳዊቱን ተምሮ ዜማውን ቀፅሎ
ቅኔ ቤት አመራ ጓዙን ጠቀላሎ
ቅኔውን ለመማር ከቅኔ ቤት ገብቶ
ቅፀላ ጀመረ ከሁሉ ተስማምቶ
የሚያውቀው ሰው የለም፡አይተዋወቅም
ከዛ ያለው ሁሉም
ሀገር ወዴት ነው ተብሎ አይጠያየቅም
መቀፀል ብቻ ነው የቅኔውን ቀለም
የሚለምንበት መንደር ተደልድሎ
መንደሩ እንዲደርስ በቁጥር ተከፍሎ
ለእንግደው ተማሪ መንደሩ ተሰጠው
ለምኖ እንዲማር ትምርት እንዲገባው
ልመና ሲለምን ትንሹ ተማሪ
ውሻው ቢመጣበት እረዳው ፈጣሪ
አኩፋዳ ሞልቶ የያዘው ኮቸሮ
ሲታገል ተደፋ ነጋ ጦሙን አድሮ፡፡
ግሱን እያጠና ቅኔውንም ቆጥሮ
ቅኔ እንደተቀኘ አቋቋም ለመማር
አቋቋም ቤት ሄደ ወጣ ሌላ ሀገር
እንዲህ ሁኖ ሳለ ትምህርት የሚማረው
አንዳንዱ ይቀራል ሞት እየነጠቀው
ተረቱም ይባላል በተለያየ ቃል
ተማሪ በሞተ በሰባት ዓመቱ
ተምሮ ይመጣል ትላለች እናቱ፡፡
የተማሪ ነገር ይሄ ነው እውነቱ
አንዱ ውሃ ወስዶት አንዱ ውሻ በልቶት
አንዱ ወባ ገድሎት አንዱ ትምህርት ከብዶት፡ሀገሩ ሳይመለስ እንደወጣ ቀረ
በትምህርት እንዳለ ስንቱ ተቀበረ
መከራውን አልፎ የሚቀረው ከሞት
እከኩ እርሃቡ መልኩን እጅጉን ቀይሮት
እናቱ ስታየው ሌላ ሰው መሰላት
ሙሉ ሰውነቱን እከኩ አቁስሎት፡፡
ልምና የወጣ ስላጣ አይደለም
በስሟ ሲለምን ብሎ በእንተ ማርያም
ቃል ኪዳኗን ይዞ ሊማር ነው ዘላለም
በግብፅ በረሃ ድንግል ስትለምን
ያነን በማሰብ ነው ተማሪ ሚለምን
የማርያም ወዳጂ የቆሎ ተማሪ
ምግቡ ማርያም ናት ሁሌም ስሟን ጠሪ
ሲጠራት ውሎ ሲጠራት አዳሪ፡፡
ትምህርት ቤት ሲሄድ የተጓዘ ይዟት
አንድ አኮፈዳ ቁራሽ የመለመኚያ
አንድ ዳዊት ጸሎት መፀለያ
ሁለት ዘንጎች ውሻ መከልከያ
አንዲት ቅምጫና ፡አንዲት ደበሎ ናት
የተማሪ ሀብቱ እነዚሁ ናቸው
ከናት ካባቱ ቤት ይዞ የወጣቸው፡፡
የቆሎ ተማሪው እንደዚህ ተምሮ
ቅኔውን ድጓውን መጻፉን ተምሮ
አቋቋም ቅዳሴ ዝማሬን ጨምሮ
አቡሻህር ሳይቀር አራቆ አስመስክሮ
የቤተ ክርስቲያን የሀገር አለኚታ
ተብሎ እየተጠራ የኔታ የኔታ
መምህር መርጌታ ቀኝ ጌታ
መከራውን አይቶ ተምሮ ሲመጣ
ስራ አላገኘም የሚበላው አጣ
ያልተማረው በዘር ከላይ ተቀምጦ
በጉቦ በጎሳ ስልጣን ተቆናጦ
የተማረው ቀረ ጥበቃ ተቀጥሮ፡፡
ይግባኝ ለፈጣሪ እንዲህ ነው ዘንድሮ
የተማረው ከላይ ሲሰቃይ እያየ
ከስር ከስር ያለው ለመማር ዘገየ
የኔታ ተምረው ከወዴት ደረሱ
እያለ ያወራል ሁሉም እርስ በርሱ
አልማርም እኔ ለመሆን እንደሱ፡፡
ጉባኤ ቤት ገብቶ የሚማር ሳይጠፋ
የአብነት ትምህርቱ በሁሉ እንዲስፋፋ
ቅድሚያ ለተማረው፡ቦታ እንዲኖረው
የቤተክርስቲያን ልጆች ድምፃችን ይሰማ
የጉባኤ ቤቶች ሳይሆኑ ባድማ፡፡
የተማረው ታዛዥ
ያልተማረው አዛዥ
ያልተማረው ከላይ
ባማረ ወንበር ላይ
ባበባ ምንጣፍ ላይ
የተማረው ከታች ከሚዳው አፈር ላይ፡፡
ይግባኝ ለአምላኬ ስለ ምሁራኑ፡፡
*አማላጅ አብጁ*
እመቤቴ ማርያም
ሰርግ ቤት ተጠርታ
የደጋሹን ጭንቀት
ዕፍረቱን ተረድታ
ውኃ ወይን አረገች
ለልጇ አመልክታ
ዩሐ 2:1
አይሁድ በባቢሎን
ሰባ ዓመት ሲገዙ
ስቃይ በዝቶባቸው
ጩኸትን ቢያበዙ
ወደ ኢየሩሳሌም
ዳግም ሲመለሱ
መልአኩ ለምኗል
ቆሞ ስለነርሱ፡፡
ዘካ 1:12
መልካሙ ንግግር
ባይወጣ ካፋቸው
በተናገሩት ቃል አምላክ ቢቆጣቸው
የኢዩብን ጓደኞች
ወደ ኢዮብ ላካቸው
መስዋዕት ሰውቶ
እንዲያስታርቃቸው፡፡
ኢዮ 42:8
ንጉስ አቤሜሌክ
ሳራን ተመኝቶ
ሊወስዳት ሲፈልግ
በራእዩ ተጠርቶ
ነበይ ነውና፡፡
እርሱ እሚያማልድው
ልዑለ እግዚአብሔር
ወደአብርሃም ላከው
ከመርጥኳቸው ጋር
ይፀናል ኪዳኔ
መከራውም ያጥራል
ስለ ቅዱሳኔ
ብሎ በሰጠው ቃል
ሊሻር በማይችለው
ቅዱሳንን አምነን
ማረን እንበለው
ያምናው ጥፋታችን
በንስሐ ታጥቦ
ያሰረው ተፈቶ ዲያብሎስ ተተብትቦ
ጌታን አመስግነን ስለቸርነቱ
ሰለጨመርልን ዕድሜን በያመቱ
ለወዲያኛው ደግሞ
ኑሮአችን እንዲያምር
ከትለየን ድንግል ከኛ ጋር ትኑር
ስለዚህ አዋቂ ጎልማሳም ልጆችም
ለነፍሳቹ በርቱ አማላጅ አብጁ፡፡
ከሐመር መጽሔት
አህያዋ
ከእንስሳት ተለይታ
ልትቆም በሰው ተርታ
ሊቀመጥባት ጌታዋ
ሊታወቅላት ዋጋዋ
ላይጠፋባት አደራዋ
ሰው የማገልገል ስራዋ
ሲመጣላት ፈጣሪዋ
ደስ አላት አህያዋ
ሲቀመጥባት በጀርባዋ።
ውርንጭላነቷ ቀርቶ
የታሰረችበት ገመድ ተፈቶ
መናቅ መሰደቧ ጠፍቶ
የዋሁ የጺዮን ልጅ ትህትናን ተመልቶ
አስገባት ከተማ በህዝቡ ፊት መርቶ።
አፋቸው ተለጉሞ
ሃሳባቸው ከፍቶ ጠሞ
አዋቂ ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
ዝም ቢሉ ለምስጋና
ለመራቸው በደመና
ለመገባቸው ከሰማይ መና
መመስገኑ መቼ ቀረና
እየተባለ ሆሳእና።
በሴቶች በወንዶቹ
በአዛውንት በልጆቹ
በህጻናት ጡት ጠቢዎቹ።
የዘኪዮስ ምኞት
መቼ ተረሳ በእጥረቱ
ዛፍ ላይ ብቻ በመታየቱ
አለቀረም ፍላጎቱ
ለመዘመር መጓጓቱ
ገብቶለታል ወደ ቤቱ
የጺዮን ልጅ ያትሁቱ
ሊበላ አብሮት ከፍትፍቱ።
መቅደስ ገብቶ ዞሮ ሲቃኝ
ሲመለከት ጊዜ አባካኝ
ጽሎት ትቶ ሲቸረችር
ከሌባ ጋር ሲደራደር
አልቻለም ስለ ቤቱ
ሲያቃጥለው ቅንአቱ
ጅራፍ ሰራ ለትምህርቱ
ቤቱን ሊያጠራ ከጠላቱ።

እንጠይቅ ታምሯን

፦ዮሐ ፦2 ፥1-11
፦ሉቃ ፦1 ፥ --
እንጠይቅ ስለሷ እውነታው ያልገባችሁ
ከምትናገሩ እንደመጣላችሁ
አበዉን እንጠይቅ ይንገሩን ባካችሁ ።
ብዙ አባቶች አሉ የለበሱ ፍቅሯን እነሱን እንጠይቅ የንገሩን ታምሯን ።
ታምራቱዋን ያየው የተደረገለት
ዶኪማስ ይመስክር ይናገር ስለ እውነት ፦
በዛ በሰረጉ ቤት ቃና ዘገሊላ
ሰርገኛዉ ታድሞ ሲጠጣ ሲበላ ፦
ድንገት በመሀከል ወይኑ በመጥፋቱ
ዶኪማስ ተጨንቆ ሲርድ ሰዉነቱ
የነበረው ደስታ ሁሉም ሲሆን ከንቱ
መቋቋም አቅቶት ሲዝል ጉልበቱ
ተዋረድኩኝ ብሎ ሲታየዉ ሽንፈቱ
እማምላክ አንብባ ጭንቀቱን ከፊቱ ።
እሩህሩህ ናትና እናቴ አዛኚቱ
የዶኪማስ ጭንቀት ሀዘኑ እንዲፈታ
ድንግል ልታማልድ ሄደች ወደ ጌታ
ተዓምር የሚያደርግ ስላላት ቃልኪዳን
"ወይንኪ ዓልቦሙ "አለችው ልጇን ።
ልጇም ሰማና የናቱን ልመና
ውሃውን ቀየረዉ ወደ ወይን ቃና ።
ትናገር ኤልሳቤጥ ትመስክር ታምሯን
የሰላምታዋን ቃል ስትሰማዉ ድምጿን
በምንፈስ ተሞልታ ለክብሯ መስገዷን
በማሕፀኗ ያለዉን ፅንስ ማዘለሏን ።
ልቧ ሀሴት አርጎ መጮኋን በደስታ
ፅንሱም እደዘለለ በድንግል ሰላምታ ።
ምድራዉያንን እኛን ወክላ
ለክብሯ ሰገደች "ሰላም ለኪ "ብላ
ሰማያዉያንን ሁሉ ወክሎ
ገብረኤል አበሰራት" ሰላም ለኪ "ብሎ
ታደያ በኛም ዘመን አሁን ባለንበት
የድንግል ተዓምር በሚገለጥበት
ዓለም በምልጃዋ ድህነት ባገኝበት
ታድያ ለምን ካዱ ጠፋባቸው እውነት ።
አይናቸው እያየ ገድል ታምራቷን
ጆሮአቸውም ሰምቶ ሙታን ማስነሳቱዋን
ታድያ ለምን ይሆን ሰው ናት ማልታቸዉ
ስላልተፃፈ እንጂ ፍቅሯ በልባቸው ።
ከዚህ ሓጥያት ለመዉጣት ለመቅመስ ፍቅሯን
እንጠይቅ ስለሷ ይንገሩን ታምሯን ።
እውነትን ተማሩ ግቡ ወደ በረቱ
የእውነት አማላጅ ናት ድንግል አዛኚቱ ።

እውነት አለቀሰች

ልብ ያለህ አስተውል ጆሮ ያለህ ስማ


እግርህ እንዳይገባ ከክህደት ከተማ።
የያዝከውን አጽና ልብህ አይጨነቅ
ለጥያቄህ መልስም ሊቃውንትን ጠይቅ።
ለእውነት የቆመ ሃይማኖቱን የሚያውቅ
ንባብ ትርጓሜን ጠንቅቆ የሚዘልቅ
ተናገር ዩሐንስ አንተ ልሳነ ወርቅ።
ቄርሎስን ጠይቀው የተዋህዶን ምስጢር
የክርስቶስ ነገር እንዴት እንደነበር
ከብሉይ ከሐዲስ በማቀነባበር
እንዳመሰጠረው በብዙ ምስክር።
ነቢዩ ኢሳያስ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ
መዝሙረኛው ዳዊት ሐዋርያው ሉቃስ
አባ ዝክረ ማርያም ወአባ ጴጥሮስ
የስነ ዘፍጥረት ሊቅ ኤጲፋኒዮስ
ዝም አትበል ተናገር ቅዱስ ሳዊሮስ
በሥጋው ማክበሩን አምላክ ክርስቶስ።
ጊዮርጊስ ተናገር አንተ የጥዋት ጮራ
ክርስቶስ መሲሕም ተብሎ እንደሚጠራ።
ወልድ ቅብዕ በማለት ክህደት አስተማሩ
የሥግው ቃል ነገር መች ገባቸው ዳሩ
የተዋሕዶ ምስጢር ሳይገባቸው ቅሉ
ሃይማኖት ከምስጢር ይደባልቃሉ።
ክርስቶስ በሥጋ እንደሞተ ሲያውቁ
በሥጋስ መክበሩን እንዴት አላወቁ
ሊቃውንት እያሉ ለምን አይጠይቁ
በተዋሕዶ ከበረ ብለው ሲናገሩ
ለዚህ ብሂላቸው የታል ምስክሩ።
ግብርን በማፋለስ አንድ ገጽ ካለው ከሰባልዮስ
አንድነትን ትቶ ሁለት አካል ካለው ከእርጉም ንስጥሮስ
መንፈስ ቅዱስ ሕጸፅ ካለው ከመቅዶንዮስ
ወልድ ፍጡር ካለው ከእርጉም ከአርዮስ
የዚህ ክህደቱ በምንም አያንስ።
ፈላጊዋ ጠፍቶ እውነት አለቀሰች
ግብራቸው ተቃርኖ ሀሰት ጥላት ሄደች።
ዳሩ ግን ወገኔ ይህ ክህደት ነውና
ቀኑ ሳይመሽብህ መንገድህን አቅና
እውነትን ከፈለክ ታገኛለህና
እረፍት ስላላት የህይወት ጎዳና
የያዝከውን ይዘህ በሃይማኖት ጽና።
___________________________

እኔ እመረቃለሁ

ሀሁ ABCD ፊደላት ቆጥሬ


ጥበብን ለመማር መፃሕፍት ደርድሬ
ሀገሬን ወገኔን እናቴን ለመርዳት
ድንቁርናን ጥዬ ከችግር ለመውጣት
ጋራውን ስወጣ ቁልቁለት ወርጄ
ከአንድ ወደ ሌላ ማለፍ ተላምጄ
ነገን ለማሸነፍ እቅድ እነድፋአለሁ
ተስፋ ስንቅ ሆኖልኝ እሩቅ አልማለሁ፡፡
ደግሞ
መቼነው የማያት ያቺን የብርሃን ቀን?
ነፃ ምወጣባት ከቴንሽን ሰቀቀን
መች ትሆን እያልኩኝ አማትሬ ሳያት
ያቺን የቀናት ቀን እንዲሁ ስናፍቃት
ቀናት ተሰብስበው ወራት አቀናጁ
ወራትም አብረው አመታት አበጁ
የዘመን ባለቤት ጊዜያት አቀዳጅቶ
ጉዞና መንገዴን ጥርጊያዬን አቅንቶ
በጊዜው ውብ አርጎ ሁሉን አስተካክሎ
የምርቃቴን ቀን ለገሰኝ በቶሎ፡፡
የእናት የአባቴ ህልም የተስፋ ቀናቸው
የብርሃን ቀን መጣች ሀሴት ልትሞላቸው
የምመረቅባት....የልፋት ካባዬን የምደርብባት
ራዕይ ዓላማዬ ግብ የሚመታባት፡፡
ነገ!
ሀገሬን ወገኔን የምጠቅም ዜጋ
ለእውነት ለቅንነት ጦር ይዜ ምዋጋ
የማይነቃነቅ ብርቱ ትውልድ ሆኜ
ለጥፋት የማልቆም የማልቀር ባክኜ
አንድነት ሰላምን ፍቅርን ተነቅሼ
የዳዊትን ትምክህት የምጓዝ ለብሼ
እንድሆን ብሩህ ትውልድ ሥላሴ ድረሱ
መላ ማንነቴን ህይወቴን ቀድሱ፡፡
የአብርሃምን ቤት እንደባረካችሁ
ትውልዱንም ታላቅ እንዳደረጋችሁ
ብርቱ መጠለያ ዋስ ድጋፍ ሁኑልኝ
ዓጋዕዝተ ዓለም ቀኔን መርቁልኝ፡፡
እንደ ያዕቆብ ሌሊት ይባረክ ህይወቴ
ሙሉ ሀሴት ይሁን የምርቃት ለቴ፡፡
ባላቅን ልካችሁ
ሰዓታት ዕለታት ቀኔን መርቁልኝ
በጴጥሮስ መክፈቻ
የገዛ ሀጥያቴን አጥባችሁ አጥሩልኝ፡፡
መልአከ ምክራችሁን ወደኔ ላኩልኝ
ዲግሪዬን በትንፋሹ እንዲቀድስልኝ
አብሳሪውን መልአክ ጠርታችሁ ላኩልኝ
የምስራች ነግሮ ደስታ እንዲበዛልኝ፡፡
ጆሮዬ ይሰማው የድንግል ሰላምታ
ይታጠፍ ጉልበቴ ይስገድ ለአንተ ጌታ
ጉዞዬን በሙሉ ባንተ ላይ ስጥለው
መቻል እስቂያቅተኝ ያኔ እመረቃለሁ፡፡አንድ እለት አንድ ወጣት
አንድን የበቁ አባት
በማለት ጠየቀ በጣም ፈልጋለሁ አምላኬን ለማየት
ከልብህ ከፈለክ አምላክን ለማግኘት
ልምራህ ወዳለበት ተነስ ተከተለኝ
ታዲያ ግን አደራ ልመለስ አትበለኝ
አምላክን ለማየት ከልብህ ከፈለግክ
እርሱ ወዳለበት ስንሄድ ታየዋለክ
ካሉት በኋላማ ተነሱ በአንድነት ወደ አምላክ ሊሄዱ
ከጠበቀው በላይ ሩቅ ሲሆንበት ወጣቱ መንገዱ
እስኬት ነዉ ምንሄደው አምላክ የት ነው ያለው
እርሱ አምላክ ሳለ በዚህ በበረሃ ለምን ነው ሚኖረው
እኔ ግን አባቴ ልሞት ነው ደክሞኛል
ከምነግሮት በላይ ጉሮሮዬ ደርቋል
አባቴ ይንገሩኝ አምላክ የት ይገኛል
እኔስ ሄድኩ እንበል እርሱ ግን ያውቀኛል
አሁን ተቃርበናል ልንደርስ ነው አምላክ ጋ
እዚሁ ጠብቀኝ እኔ ግን ልሄድ ነው ሚጠጣ ፍለጋ
አሉትና እኚያ አባት ፈጥነው ተራመዱ
ወጣቱም በድካም ተንጋሎ አያቸው በፍጥነት ሲሄዱ
እራሱን ጠየቀ እጅጉን ተገርሞ
እኚህ አባት ጥንካሬያቸውን ኬት አመጡት ደግሞ
እኚያ አባት ሄደው ትንሽ እንደቆዩ
ወጣቱ ዞረበት ምድርና ሰማዩ
አምላኬን ሳላየው ልሞት ይሆን እንዴ
ምነው ግን ቢያቆየኝ እስካገኘው አንዴ
ብሎ ሳይጨርሰው እዚያው ራሱን ሳተ ተንጋሎ ሜዳ ላይ
ልክ እንደ ነቃ ዙሪያ ገባውን ሲያይ
እኚያ አባት ተቀምጠው ይፀልዩ ነበር
እሱም ቀና ብሎ የሚፀልዩትን ይሰማቸው ጀመር
ይስሙኝማ አባቴ
አምላኬን አየሁት ለዚያውም ሁለቴ
ወዴት አገኘኸው እንዴትስ ለየኸው
ባገኘኸው ጊዜስ ምንድን ነበር ያልከው
እኔ ወጣት ሆኜ በድካም ስሰቃይ
እርሶ ግን ሸምግለው ጥንካሬዎትን ሳይ
ያን ጊዜ አየሁት አምላኬን በእርሶ ላይ
ውሃ ጠምቶኝ ደክሞኝ ህሊናዬን ስቼ
ስነቃ ለየሁት ፀሎቶን ሰምቼ
በል አድምጠኝ ልጄ ታዲያ አሁንስ ገባህ
አምላክ ሁሌም አለ በዙሪያ በደጅህ
ይገለፅልህ ዘንድ
የትም ሳትሰደድ
በተስፋ ጠብቀው ልቦናህን ከፍተህ
ይህንን ስትፈፅም ያኔ ታየዋለህ
ጾመኛ ነኝ
ከምግብ እርቄ
ሰዓቷን ጠንቅቄ
ሥርዓት አከብራለሁ
ከሥጋ ከወተት ንክች አላደርግም በደንብ እጾማለሁ
በእርግጥ ወዳፍ ሚገባ ነውና የማያረክስው
ጾምን ባልበላበት ሰዶቤበታለሁ
እጄ ሥጋም ባይዝ ሰውን ይጠቁማል
ሰው ይወነጅላል
እግሬ አመድ ሆኖበቅቤ ባዮወዛም
ወደ ጥፋት መንገድ መሮጡ አልቀረም
የውስጡ አካሌ ያ ድብቁ ነገር
ያ የልቤ ወዳጄ ቅቤና ቅባቱ
አልፎ ባይነካካው እዚያ ተደብቆ
ሰዎች ላይ ለማሴር
ክፋት ለማውጠንጠን
እንደምን ይሳነው!
አዎን ይሄ ሳይቆጠር
በርግጥ እጾማለሁ
ነጠላ አድርጌ
ቅዳሴ አስቀድሼ
በአንድ እግሬ ቆሜ
ጸሎት አደርሳለሁ
አዎን ጾመኛ ነኝ
በደንብ አከፍላለሁ
ሩጫዬን ያለግብ እደመድማለሁ።

እንጠይቅ ተዓምሯን

፦ዮሐ ፦2 ፥1-11
፦ሉቃ ፦1 ፥ --
እንጠይቅ ስለሷ እውነታው ያልገባችሁ
ከምትናገሩ እንደመጣላችሁ
አበዉን እንጠይቅ ይንገሩን ባካችሁ ።
ብዙ አባቶች አሉ የለበሱ ፍቅሯን እነሱን እንጠይቅ የንገሩን ታምሯን ።
ታምራቱዋን ያየው የተደረገለት
ዶኪማስ ይመስክር ይናገር ስለ እውነት ፦
በዛ በሰረጉ ቤት ቃና ዘገሊላ
ሰርገኛዉ ታድሞ ሲጠጣ ሲበላ ፦
ድንገት በመሀከል ወይኑ በመጥፋቱ
ዶኪማስ ተጨንቆ ሲርድ ሰዉነቱ
የነበረው ደስታ ሁሉም ሲሆን ከንቱ
መቋቋም አቅቶት ሲዝል ጉልበቱ
ተዋረድኩኝ ብሎ ሲታየዉ ሽንፈቱ
እማምላክ አንብባ ጭንቀቱን ከፊቱ ።
እሩህሩህ ናትና እናቴ አዛኚቱ
የዶኪማስ ጭንቀት ሀዘኑ እንዲፈታ
ድንግል ልታማልድ ሄደች ወደ ጌታ
ተዓምር የሚያደርግ ስላላት ቃልኪዳን
"ወይንኪ ዓልቦሙ "አለችው ልጇን ።
ልጇም ሰማና የናቱን ልመና
ውሃውን ቀየረዉ ወደ ወይን ቃና ።
ትናገር ኤልሳቤጥ ትመስክር ታምሯን
የሰላምታዋን ቃል ስትሰማዉ ድምጿን
በምንፈስ ተሞልታ ለክብሯ መስገዷን
በማሕፀኗ ያለዉን ፅንስ ማዘለሏን ።
ልቧ ሀሴት አርጎ መጮኋን በደስታ
ፅንሱም እደዘለለ በድንግል ሰላምታ ።
ምድራዉያንን እኛን ወክላ
ለክብሯ ሰገደች "ሰላም ለኪ "ብላ
ሰማያዉያንን ሁሉ ወክሎ
ገብረኤል አበሰራት" ሰላም ለኪ "ብሎ
ታደያ በኛም ዘመን አሁን ባለንበት
የድንግል ተዓምር በሚገለጥበት
ዓለም በምልጃዋ ድህነት ባገኝበት
ታድያ ለምን ካዱ ጠፋባቸው እውነት ።
አይናቸው እያየ ገድል ታምራቷን
ጆሮአቸውም ሰምቶ ሙታን ማስነሳቱዋን
ታድያ ለምን ይሆን ሰው ናት ማልታቸዉ
ስላልተፃፈ እንጂ ፍቅሯ በልባቸው ።
ከዚህ ሓጥያት ለመዉጣት ለመቅመስ ፍቅሯን
እንጠይቅ ስለሷ ይንገሩን ታምሯን ።
እውነትን ተማሩ ግቡ ወደ በረቱ
የእውነት አማላጅ ናት ድንግል አዛኚቱ ።

አቃጥሏት ግድ የለም

ቤተ ክርስቲያክርስቲያን ቅድስት እመ ኵሉ፣


የወንጌል ማኅደር የጸናብሽ ቃሉ፣
ስብከትሽ ሰላም ነው ለዓለም በሙሉ፤
አፅራረ ሰላም ግን አንቺን ይጠላሉ፤
ተልእኮሽ ፈውስ ነው ለታመሙ ኹሉ፤
መዳን የማይወዱ ከአንቺ ይሸሻሉ፤
ጭራሽ ሊያሳድዱሽ ይመካከራሉ፤
አጥፍቶ ጠፊዎች ሊያጠፉሽ ይሻሉ።
የጥፋት ልዑካን ለጽድቅ ያልታደሉ፣
ሕንፃሽን በእሳት አቃጠሉት አሉ፤
ጣሪያ ግድግዳዉን አፈረሱት አሉ፤
ባያውቁት ነው እንጂ ቢጠፋቸው ውሉ፣
በአንቺ እሳትነት አብረው ይጨሳሉ፤
በማገዱት እንጨት ኋላ ይነዳሉ፤
ዛሬ እንዳፈረሱሽ ነገ ይፈርሳሉ፤
በሠፈሩት መጠን ዋጋን ያገኛሉ።
አህዛብ ግብዞች ሆይ የሰይጣን ፈረሱ፣
ደስ ካሰኛችሁ እሳት መለኮሱ፣
አቃጥሏት ግዴለም ጣሪያዋን አፍርሱ፤
ግድግዳ ወለሉን ብሎኬቱን አንሡ፤
ለጊዜውም ቢኾን ቅፅሮቿን ደምስሱ፤
ልጆቿን በሙሉ ደም ዕንባ አስለቅሱ።
ነገር ግን ጌታዋ ሲቆጣ ንጉሡ፣
መቃጠላችሁን ፈጽሞ እንዳትረሱ፤
ጽዋ ተርታችሁን ዘወትር አስታውሱ፡፡
ጌታ ችሎ ችሎ መዓቱን ሲያመጣ፣
ቅፅሩን ለማስከበር ሲፈርድ በቁጣ፣
በተራ መንደድ ነው የኹላችሁ ዕጣ፡፡
እስከዚያው ድረስ ግን እስኪመጣ ጌታ፣
የዓለምን መድኀኒት የሕዝብን አለኝታ፣
ቤተ ክርስቲያንን አፍርሷት በአንድ አፍታ፤
አቃጥሏት ግዴለም አንድዷት በተርታ፡፡
እርሷ በትረ ወንጌል የሾለ ብረቱ፣
ብትቆሙ ደፍራችሁ በኃያል ስለቱ፣
ደዌው ለእናንተ ነው ሕመሙ ጉዳቱ።
ጣሪያና ግድግዳው አካሏ ቢደማ፣
ብትነድ ብትቃጠል በክፉዎች ፊርማ፣
መቅደስ ማኅሌቱ ቢመስልም ባድማ፣
አትፈርስም በፍጹም በግብዞች ዐድማ፤
እሳት የሚያነዳት አይደለችም እማ፤
በክርስቶስ ፍቅር ተቃጥላለች ቀድማ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ይቺ ምድራዊቷ፣
መለኮት እሳት ነው ጥንትም መሠረቷ፣
የክርስቶስ ደም ነው እስትንፋስ ሕይወቷ፣
አቃጥሏታልና ክርስቶስ እሳቷ፣
አጽንቷታልና አምላክ ባለቤቷ፣
በፍጹም አትፈርስም ጽኑ ነው ዐለቷ፤
በጠላት ዘመቻ አይኾንም ኅልፈቷ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

የታወረ ትውልድ

ከእናቱ አፈንግጦ እምነት ወዲያ ብሎ በአለም የታለለ


በዚህ በእኔ ዘመን ልበ ስውር ወጣት እጂግ ብዙ አለ
ዶግማና ቀኖና መፈፀም ሲያቅተው በስጋው ሲታለል
ይችን ቅድስት እምነት መፍትሄ ነው ብሎ ትታደስ ይላታል
የመለውጥ ትርጉም ጠንቅቆ ያልገባው ልበ ስውር ጓዴ
በኃጢያት ያደፈ እሱነቱን ይዞ ትታደስ ይለኛል ያላረጀ ነገር ይታደሳል እንዴ?
እነዲዎስቆሮስ ፂም የተነጩላት የፀናች ሀይማኖት
ቆዳቸው እንደ ድንች በአህዛብ ጭካኔ ያኔ የተላጡላት
በሚያስፈራ እሳት ነጎድጓድ በላበት
ለኛ ያቆዩልን ህይወትን ሰውተው
ተዋህዶ እምነቴ ምኗ ነው ያረጀው
በሀጥያት አረንቋ የተቆሳቆለ እርሱ ተቀምጦ
ፍርሀት እንኳን አያውቅ ትታደስ ይለኛል ካፉ ቃል አውጥቶ
መላ በሉት'ማ ምከሩት ይህን ስው
የመታደስ ትርጉም ምን አልባት ቢገባው!!!የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይበረከካሉ
ያከበሩሽም የከበሩ ናቸው
ማሪያምን የጠላ የለውም ከለላ

ፍቅር ማለት

ያን ሁሉ መስዋእት ያን ሁሉ ግርፋት
ልጅን ከአባት ጋር አባትን ከልጅ ጋር
           አስታርቆ ለማየት ፤
እኔ ያያ ሰው ነኝ የከበረ ዋጋ የተከፈለበት
እኔ ያ. ሰው ነኝ በደሙ ታጥቤ ነፃ የሆንኩበት ፤
ታድያ ለዚህ ከንቱ አለም ላልወደደው
         በትንሽነቱ ሰው ሁሉ ለናቀው ፤
እንዴትስ ተገብቶት ጌታ ሊሞትለት
እንዴትስ ተደርጎ ክብሩን ሊተውለት ፤
ይህ ፍጡር ማን ቢሆን ነው ከቶ
የሰማዩ ንጉሥ ግዛቱን አስትቶ
በሀጥያቷ ክርፋት ወደ ገማች ምድር
ጠርቶና ጎትቶ ፤ሞትን ያቀመሰው የትኛው ፍቅር ነው

የቱ  ቅድስና የቱ ማንነቴ የቱ ንፅህና ፤
ንፁህ የሆነውን  ፅድቅ የለበሰውን
ስጋ ያለበሰው ሀጥያት ያደረገው
የቱ እኔነቴ እሱነቱን ትቶ እንዲያ
ሚያዋርደው ? ፤
ያንን ፍቅራማ ቃላት ተቆፍረው
ያንን መውደድማ ፊደላት ተጣምረው ፤
ከቶ አይገልፁትም ፍፁም አይደርሱትም
ብርሀን አያደምቀው ጨለማ አይጋርደው
የቀናት መገስገስ የአመታት መንጎድ
        ዘመን የማይሽረው ፤

ፍ ቅ ር ማለት ያ ያ ነው
ፍቅር ውልደቱ ነው ፍቅር መከራው ነው
ፍቅር መሞቱ ነውፍቅር ትንሳኤው ነው ፤
በዘመን ጅማሬ በዘመን ፍፃሜም
የፍቅር  ስንኙ   የፍቅር ሀረጉ
         እ  የ  ሱ  ስ ብቻ ነው !
______________________

የአምላክ መገኛ

አንድ እለት አንድ ወጣት


አንድን የበቁ አባት
በማለት ጠየቀ በጣም ፈልጋለሁ አምላኬን ለማየት
ከልብህ ከፈለክ አምላክን ለማግኘት
ልምራህ ወዳለበት ተነስ ተከተለኝ
ታዲያ ግን አደራ ልመለስ አትበለኝ
አምላክን ለማየት ከልብህ ከፈለግክ
እርሱ ወዳለበት ስንሄድ ታየዋለክ
ካሉት በኋላማ ተነሱ በአንድነት ወደ አምላክ ሊሄዱ
ከጠበቀው በላይ ሩቅ ሲሆንበት ወጣቱ መንገዱ
እስኬት ነዉ ምንሄደው አምላክ የት ነው ያለው
እርሱ አምላክ ሳለ በዚህ በበረሃ ለምን ነው ሚኖረው
እኔ ግን አባቴ ልሞት ነው ደክሞኛል
ከምነግሮት በላይ ጉሮሮዬ ደርቋል
አባቴ ይንገሩኝ አምላክ የት ይገኛል
እኔስ ሄድኩ እንበል እርሱ ግን ያውቀኛል
አሁን ተቃርበናል ልንደርስ ነው አምላክ ጋ
እዚሁ ጠብቀኝ እኔ ግን ልሄድ ነው ሚጠጣ ፍለጋ
አሉትና እኚያ አባት ፈጥነው ተራመዱ
ወጣቱም በድካም ተንጋሎ አያቸው በፍጥነት ሲሄዱ
እራሱን ጠየቀ እጅጉን ተገርሞ
እኚህ አባት ጥንካሬያቸውን ኬት አመጡት ደግሞ
እኚያ አባት ሄደው ትንሽ እንደቆዩ
ወጣቱ ዞረበት ምድርና ሰማዩ
አምላኬን ሳላየው ልሞት ይሆን እንዴ
ምነው ግን ቢያቆየኝ እስካገኘው አንዴ
ብሎ ሳይጨርሰው እዚያው ራሱን ሳተ ተንጋሎ ሜዳ ላይ
ልክ እንደ ነቃ ዙሪያ ገባውን ሲያይ
እኚያ አባት ተቀምጠው ይፀልዩ ነበር
እሱም ቀና ብሎ የሚፀልዩትን ይሰማቸው ጀመር
ይስሙኝማ አባቴ
አምላኬን አየሁት ለዚያውም ሁለቴ
ወዴት አገኘኸው እንዴትስ ለየኸው
ባገኘኸው ጊዜስ ምንድን ነበር ያልከው
እኔ ወጣት ሆኜ በድካም ስሰቃይ
እርሶ ግን ሸምግለው ጥንካሬዎትን ሳይ
ያን ጊዜ አየሁት አምላኬን በእርሶ ላይ
ውሃ ጠምቶኝ ደክሞኝ ህሊናዬን ስቼ
ስነቃ ለየሁት ፀሎቶን ሰምቼ
በል አድምጠኝ ልጄ ታዲያ አሁንስ ገባህ
አምላክ ሁሌም አለ በዙሪያ በደጅህ
ይገለፅልህ ዘንድ
የትም ሳትሰደድ
በተስፋ ጠብቀው ልቦናህን ከፍተህ
ይህንን ስትፈፅም ያኔ ታየዋለህ

ተዋህዶ አትፈርስም

ድርጅት አይደለም በሰዉ የታነፀ፣


ፖለቲካም አይደል ዘርን ያጣቀሰ፣
ሚስጥሩ ፍቅር ነዉ ቃላት የማይበቃዉ፣
እኛን ስለመዉደድ በፍቅር ተስቦ መስቀል ላይ የወጣዉ።
በደም ታንፀናል በማይጠፋ ቀለም፣
ለእኛ ብሎ እርሱ ጌታ ቢሰቀልም፣
መሠረቱ ኢየሱስ ግድግዳዉ ቅዱሳን፣
ግንቦቹ እኛ ነን የእርሱ ምዕመናን።
ልንወድቅ አንችልም በእርሱ ፍቅር ፀንተን፣
እግዚአብሔርን ይዘን ማን ይሆን የሚከሰን?
መሃመዳዊያን ወይም ጅሆቫ ዊትነስ፣
ፕሮቴስታንትም ሁን ወይ ደግሞ ካቶሊክ
አለቱን ላታፈርስ የሰዉ ደም አታፍስስ፣
ምንጩንም ላታደርቅ ከመቅደሱ እራቅ።
ካህኑ ቢታረድ መቅደሱ ቢቃጠል፣
እንበዛለን እንጂ የለም የሚጎድል።
ስንሞት እንበዛለን መከራዉ ሲበዛ በፍቅር እንፀናለን፣
በእሳት ስንቃጠል እንለመልማለን።
ከማይደክም አባት ተፈጥረናልና፣
አርዮስ አትልፋ እንላለን ቀና።
ሰልፉ የእኛ ነዉ ድልም የእኛ ብቻ፣
እንደ አሸዋ የበዛን እስከዓለም ዳርቻ።
ካህኑን ግደሉ መቅደሱን አቃጥሉ፣
ቅጥሩንም አፍርሱ ልጆቹን በትኑ፣
እናንተ ስትጠፉ በገሀነም እሳት፣

ሰማዕታት በአባታቸዉ እቤት


ይሰበሰባሉ መንግስተ ሰማያት።
ይህ ነዉ ክርስትና የማይጠፋ ቀለም፣
በፍፁም ማይጨልም ሁሌ ሚሰጥ ብርሃን።
እናማ አርዮስ ቁርጥህን እወቀ፣
ድል ላታደርግ እንደዉ ራስህን አታስጨንቀዉ፣
ሃሰት እዉነትን መቼ ነዉ አሸንፎ የሚያቀዉ?
ባንድነት ተነሱ የእምነትን ሰይፍ ያዙ፣
በፍቅር ማርኩና የዲያቢሎስን ሴራ በእምነታችሁ ናዱ።
በእምነት እንሞላ በፅናት እንቁም በተስፋ እንዉጣ፣
ጠላት አፍሮ እንዲቀር መድረሻም እንዲያጣ።
የጦር ዕቃችሁን ልበሱ እንደ ካባ፣
ዘመቻዉን አፅኑት ቅድስቲቷ ምድር አርዮስ እንዳይገባ።
የጦር ሠልፍ አንሻም ቀስት አንወረዉርም፣
ደም እያፈሰስን እርሱ የፈጠረዉን እኛ አንገድልም።
ቀስትና ጦር ይዘን አንወጣም ዘመቻ፣
ጠጠርም አንለቅምም አሳዳጁን መምቻ።
መምቻው ክርስቶስ ነው የእሳት መዶሻ፣
ምሽጋችን ቅድስት የኃጥአን መሸሻ።

ይህችን ዓመት ተወኝ

ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ


በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ
አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ
አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ
ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ
ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም
ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም
የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ
የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ!
አውቃለሁ ታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር
ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር
‹ዘንድሮስ…!› እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ
ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ
ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ
እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ
የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ -
ዘመን ተቆጠረ
ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ
ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ
በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ
ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ
ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ
ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም
ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም!
እባክህ አልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ
ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ
የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ
ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ!
አታውጣኝ ከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ!
ቦታስ የሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው
ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው!
ከሊባኖስ ዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው!
እኔ አይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት
ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት
ይሀችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!..
ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት
ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት!
ይሄ ዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ
እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ

መስከረም ሲታጠን
ከብሶት አድማስ ሥር - ከጽልመቱ ማዶ - የብርሃን ጎህ ሲቀድ፣
በሃይማኖት ፍቅር - ሀገር ልቡ ነዶ - ፍርሐት ሲቀረደድ፣
የእማትን ልቅሶ - የአበውን እንባ - የውርዛዌን ወኔ፣
የአንድነትን እርሾ - የአትንኩንን ካባ - የፍትሕን ጠኔ፣
ከእግዚኦታው ማዕድ - ከካህናቱ ዕድ - ይህን ኹሉ ይዞ፣
ዕጣኑ ዐረገ - ወጣ ወደ ሰማይ - ሺ ጸሎት አርግዞ።
በታደለች ሰንበት - ዣን ተከል ሥር ያለው - ወዲህም ከጦሳ፣
በሃይማኖት እሳት - ልቡ የተቃጠለው - የመንፈሱን እንጂ - የምድሩን ቢረሳ፣
ይግባኙን ወደ ላይ - በእግዚኦታ ሊያደርስ - በአንድነት ሲነሣ፣
ምድር ሰማይ ሆነች - ሰውም መልአክ ሆነ - ግዙፋን ረቀቁ፣
ሰላማዊ ብለው - በሰማያዊ ሰልፍ - ከሰማይ ታረቁ።
በዚህችስ ሰንበት - ግዙፍ አይደለች ምድር - አፈርም የለባት፣
ከኢዮር ከኤረር - ከራማ የተለየ - ምንስ ተሠራባት?
በዚህችስ ሰንበት.....
የመላእክት ሀገር - ኢዮር ኤረርና - ራማ ብቻ አይደሉ፣
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ - መሐረነ ክርስቶስ - እግዚኦ እያሉ፣
ማዕጠንቱን ይዘው - ጎንደርና ወሎም - ለሦስቱ ሰማያት - ራብዓይ ሆነው ዋሉ።
እኛስ የምናውቀው - በዕለተ መልአኩ - በ 12 ኛው ቀን - ኅዳር ሲታጠን ነው፣
ሀገር መልአክ ኾኖ - በ 12 ኛ ዓመት (2012) - ወሎና ጎንደር ላይ -መስክዬን አጠነው።
መስከረም ሲታጠን...
ከልቡና ደጃፍ - ብሔር ሚሉት ዕድፍ፣
በማዕጠንት ምድጃ - ተጠርጎ ሲራገፍ፣
ጎጥ ሚሉት ቆሻሻ - ዘር የሚሉት ትቢያ፣
ነዶ ሲቀጣጠል - በፍቅር ማራገቢያ፤
መስከረም ሲታጠን - ከኦርቶዶክስ አድማስ ሥር፣
የምድሩ ያየሩ - የሲዖሉ ጋኔን - በጢሱ ሲታወር፣
ወዶ የታወረው - የጋኔኑ ቢጤም - ተባሉ ተጣሉን - በትግኃት ሲዘክር፣
ይህን ለመመስከር - አላየሁ አልሰማሁ - ብሎ ሲግደረደር፣
ያደለው ዐይናማ - የመላእክቱን ዐይን - ዐይኑ ያደረገ
ከሰልፈኞቹ ጋር - ያየውን መስክሮ - በክብር ዐረገ።
መስከረም ሲታጠን....
የተስፋ ብርሃን - በአቅሌስያ ደጃፍ - ጭል ጭል እያለ፣
የበሯ ላይ ጽልመት - በአንድነቱ ክንድ - የሚናድ መሰለ።
መስከረም ሲታጠን - የዕጣኑ መዓዛ - ደቡብ ላይም ሔደ፣
ሰሜንና ምሥራቅ - ምዕራብ ላይም ሔደ፣
ለሃይማኖት የመሞት - ሰማዕት የመሆን - ጥብዓት እያወደ።
መስከረም ሲታጠን....
ጥቅምትና ኅዳር - ታኅሣሥና ጥር - መጋቢት ሚያዝያም - ፈክተው ይውላሉ፣
ቤተ ክርስቲያን ሆይ - ክረምትሽ አለፈ - በጋ ነው እያሉ።
ብዙ ልጆች አሉት

ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር


በዙሪያዉ ያሉት አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃዉ የኔ ግን ይለያል
መልኩ ሚካኤል ስለዉ ደስ ይለኛል
አዝ
ከመላእክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላክ የተሾመ ዘንዶዉንም ጥሎ
አሳዳጊየ ነዉ ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ
አዝ
ከሚታየዉ ሁሉ ልቤ ከሚፈራዉ
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረዉ
ያድነኛል ፈጥኖ ከመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
አዝ
በባህራን ታሪክ በነ ጠናፊኖስ
በአፎሚያ መትረፍ በነዱረታዎስ
በነብዪ ዳንኤል የጭፍን ሰምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
አዝ
በጉዞ የረዳችሁ በባህር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ እንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ በዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
አዝ
ክብር ለሚገባዉ ክብርን እንሰጣለን
ንጉስ ለወደደዉ እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምት

ለካስ ዛሬም አለ

ትዕቢት ያጀገነው
ራሱን መውደዱ ልቡን ያሳበጠው
አምላኩን ለመግደል ሰይፍ የመዠረጠው
እንደ ነዳጅ ረግጦ ሰይጣን 'ሚሾፍረው
የጋኔን መኪና ሄሮድስ የተባለ
144 ሺህ ጠርቶ የገደለ
ለካስ ዛሬም አለ።
ጳውሎስ ቃል ሲያወጣ ጴጥሮስም ሲፈውስ
'ግደል' የሚል ጋኔን ከአንጀቱ ተጣብቆ ክፋቱ 'ሚላወስ
ከነገሥታት መኻል ኔሮን የተባለ ነበረ አንድ ቀውስ።
የስንቱን ከተማ መኖሪያ አቃጠለ
አንዱን በሰይፍ ጣለ
በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ አንዱንም ሰቀለ።
ለካስ ንጉሥ ኔሮን ዛሬም ሰይፉን ስሏል
ዘቅዝቆ የመስቀሉ ሥራውም ቀጥሏል
መቅደሱን አቃጥሎ እሳቱንም ሞቋል
እንደ በቆሎ እሸት የሰው አካል ጠብሷል
ለካስ ዛሬም ኖሯል!
በቅድስቲቱ አገር ባገሬ በ'ማማ
ከጥንት ግፍ መኻል ምን አለ ያልተሰማ?
መንኮራኩር ሠርቶ አካል የሚፈጨው
የሰው አካል ገፎ የሚነሰንስ ጨው
ከአንበሳ 'ሚያታግል
በዕብን ወግሮ 'ሚገ'ል
በቁም አሥሮ 'ሚያነድድ
ቆዳ 'ሚቀረድድ
እንደ ጥንቱ ኔሮ
እልፍ ነው ዘንድሮ።
ግራኝ ግብሩ አልሞተም ሕያው ነች ዮዲትም
መቅደስ ሚያነድና ካህንን የሚሰድ አይታጣም የትም።
የነ ሜንዴዝ እሾኽ መቼ ተነቀለ?
ይኸው አመርቅዞ ስንት አማኝ ገደለ።
በአየር ላይ በሮ መርዙን የረጨብን ጥልያን መች ጠፋ
መርዝ የሚያዘንብ ኪይ ቦርድ በዘመኑ አየር ቀጥሏል ቀጠፋ።
እነ ሄሮድስ አሉ
እነ ኔሮን አሉ
እነ ግራኝ አሉ
እነ ዮዲት አሉ
ድምጥያኖስ አለ ዲዮቅልጥያኖስ
የጋኔን ቀኝ እጅ የዲያቢሎስ በርኖስ::
መክስምያኖስ አለ አማኝ እየቀጣ
ቆስጠንጢኖስ 'ሚባል ንጉሥ እስኪመጣ

በስመ ሥላሴ
በክርስቶስ ፍቅር በስመ ስላሴ፤
ከእግሬ በርከክ ብዬ ዝቅ ብዬ ከራሴ።c
በወልድ ሀብተ ወልድ በድንግል ተዋህዶ፤
በክርስቶስ ክርስትያን ያ’ረጋችሁ ፈቅዶ።
በሰማታት አማንያን የተሰኛችሁ፤
ወልደና ወለተ ይህ ድምፅ ሚሰማችሁ፤
እንደምን ከረማችሁ? እንደምን ሰነበታችሁ?
እንደምንስ እስከዚች ሰአት ደረሳችሁ?
አሜን አልፋና ኦሜጋ የሰራዊት ጌታ፣
ይመስገን በፍጥረት ከጥኋት እስከ ማታ።
አምላክ ሲመሰገን ሁሌም በባህሪ፣
ለአዳም ዘር በሙሉ የሆነች ተጠሪ፣
ሁል ጊዜም ከቀኙ አትለይም እና፣
ከፍጥረት ይድረሳት የፀጋ ምስጋና።
መላእክት ሰማታት ፃድቃናት በሙሉ፤
ስላዳም ዘር ድነት በመማፀን ያሉ፤
መርጦ ለኛ ድነት ፀጋ ያደላቸው፤
ሁሌም ይመስገኑ እንደዬ ክብራቸው።
ቃል ነበረ
ጨረቃ ክዋክብት ፀሀይ እና ምድር፤
መላእክት ሰማእታት ስነ-ፍጥረት ሳይኖር፤
አልፋ እና ኦሜጋ የማይመረመር፤
የሁሉ መሰረት ያን ጊዜ ቃል ነበር።
ምድርና ሰማይን በአንድ ቀን ፈጠረ፤
ደግሞም ለአምስት ቀናት ሌሎችን ጨመረ፤
እንደየ አይነቱ ሁሉን አሳመረ፤

በሰባተኛው ቀን መፍጠር በጀመረ፣


እግዚአብሔር እንዲ አለ፦
“ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር፤
አዋፍትንም ይግዛ ይሰልጥን በምድር።”
ከሰባት ባህርያት በጆቹ አበጃጀው፤
የመጀመሪያም ሲል አዳም ብሎ ጠራው፤
ሁሉ ወደአለበት ገነትም ወወሰደው፤
የሞት ሞት እንዳይሞት አንዷን ከለከለው፤
አልፋ እና ኦሜጋ የማይመረመር፤
የሁሉ መሰረት ያን ጊዜም ቃል ነበር።
በሰባተኛው ቀን ከሰባት ባህርያት የተበጀው አዳም፤
የገነት ኑሮውን ከሰባት አመታት ማሳለፍ አልቻለም።
አምላኩን ሰረቀ፤
ሁሉንም አወቀ፤
አውቆም ተደበቀ፤
አልፋና ኦሜጋ ማይመረመረው፤
አዳምን እንዲ አለው፦
ወደምድር ሂድ ጥረህ ግረህ ብላ፤
እሷም ታብቅልብህ እሾህ አሜከላ።
ለአምስት ቀን ከግማሽ ይበዛል መከራህ፤
ስወለድ ነው ምትድን እኔ ከልጅ ልጅህ።
አዳም ተፀፅቶ እጅግ ብዙ ለፋ፤
ነገር ግን አልቻለም ሀፂያቱን ሊያጠፋ።
ከመጠበቅ በቀር ያንን ቃል በተስፋ።
ሁሉንም ከማድረግ አንዳች ማይሳነው፤
መፍረድ እና ማዳን ባህሪው የሆነው፤
የሚገለጥበት የው ደረሰ ጊዜው።
መኖር ሳይጀመር ይኖር የነበረ፤
አልፋና ኦሜጋ ጥንትም ቃል ነበረ።
በሰማይ በምድር ታላቅ ደስታ ሆነ፤
በከብቶቹ በረት ዛሬ ቃል ሰው ሆነ።
በኮከብ ተመርተው ሰባ ሰገል መጡ፤
ለንጉስነቱ ወርቁን አስቀመጡ ፤
ለሞቱ የሚሆን ከርቤውን አወጡ፤
ለአምላክነቱ እጣን ሰግደው ሰጡ።
በደስታ እልል እንበል ልዩ ቀን ነው ለኛ፤
ከድንግል ተወልዷል እውነተኛው ዳኛ፤
አዳምን ለማዳን ከሰይጣን ቁራኛ።
አሲናበል አሲና ገናዬ፤
ተወለደ ጌታችሁ ጌታዬ።
በነብያት የተነገረለት፤
አማኑኤል ነው የተኛው በበረት።
እመብርሃን አብሳሪተ ፀጋ፤
አትለየን ሁሌም ከልጇጋ።
ስናከብር በዐለ እልደቱን፤
ያስቀየምነ ይቅርታ ጠይቀን፤
የተቀየምን ከልብ ይቅር ብለን፤
እንዋደድ እርስበርስ ሁላችን።
እንዲህ ደምቀን እንደተሰባሰብን፤
የበዓሉ ባለቤት በረከት ያድለን።
በማልት በሰርክ ፀሎት ስታደርጉ፤
ለገብረ ሚካኤል ማለትን አዘንጉ።
ያስቀየምኋችሁ በምላስ ወለምታ፤
በእግዚያብሄር ስም ይቅርታ(3)።

ተፃፈ በመስፍን ምትኬ ፪፻፲፪/፬/፪፭ ዓ.ም

*:ጊዜ ምን በደለ;*
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እውነትን ደብቀን ሀሰትን አንግሰን
አባቶች እያሉ ልጆች እያስተማርን
አርብ እሮቡን ሳናውቅ ሁልጊዜ አየበላን
ቤቱ መመላለስ ጭራሹን አቁመን
*
*
የእግዛብሔርን መቅደስ በሀጢያት ስንሞላ
እንደሰዶም ሆነን ህግን ስንጠላ
አህዛቦች ሲቀድሙን እኛ ቁመን ሇላ
ፀጋችን እያለ እሱን ሳናውቅበት ስንፈልግ ሌላ
*
*
የምንጓዝበት መንገዱ ረዝሞብን ቤቱ መሄድ ሲቀር
ሀይማኖት በገንዘብ እንደስም ሲቀየር
መፅሀፍትን ሳናነብ አባቶች እግር ስር ቁጭ ብለን ሳንማር
ቅዱስ ሁኑ ተብለን ምርጫችን ሲቀየር
*
*
ውበት ከአምላክ በላይ እኛ ስንሰራ
ቀለም እያማረጥን አለምን ስንመርጥ አምላክን ሳንፈራ
ማህሌት አዳር ትተን ስንመርጥ ጭፈራ
ሀብታችን ሀጢያት ገዝቶ ሲያስመስል ተራራ
*
*
ልብሳችንን ጥለን እርቃንን ስንመርጥ
በማናውቀው አለም ከላይ ሁነን ሳለ ወደ ታች ሰንዘቅጥ
አማርጠን ስንበላ ከደረቅ እስከ ቁርጥ
በደካማው ስጋ ለነፍሳችን ስንቅ ጭራሽ ሳናስቀምጥ
*
*
አወቀን ብለን ሳናውቅ በትቢት እየተጓዝን
ምርጫችን ከኛ በልጦ እኛኑ ሲመክረን
አልመለስ ስንል አምላክ እላይ ሁኖ በትዝብት ሲያዩን
ፍርጃ እላይ ቆመን ጌታ ሊመዝነን
እኛ ከሱ በልጠን ጭራሽ ፈራጅ ሁነን
*
*
ክፋትን አንግሰን ጠፋቶብን በጎነት
የውጩን አድንቀን ስንጓዝ በስህተት
ምርጫችን ተምታትቶ ስናማርጥ ውሸት
ሚስጥሩን ሳናውቀው ለመፋረድ ስንዋትት
*
*
በል በትርርህን አፅና የሚባል ሲጠፋ
መገንዘብ ሲያቅተን ምንድነን እንደሆነ የወደፊት ተስፋ
በማይጠቅም ህይወት ስንማስን ስንለፋ
ማወቁ ሲጠፋን ሁሉም ሟች መሆኑን ጠብቆ ወረፋ
*
መቶ ለማይሞላው ለዚህ አጭር እድሜችን
ምን ለማይጠቅመው እንጨነቃለን ለአፈሩ ስጋችን
አድሜአችን ሲቀንስ ከግባራችን ሲለቅ ፀጉራችን
መመለስ ሲያቅተን ዛሬ ነገ እያልን ሲመርሽ ቀናችን
*
አባቶችን ሰምተን ታሪክ ካልጠበቅን
ዘመናዊነት ሚስጥሩ ካልገባን
በአምና ተምረን ዘንድሮ ካልነቃን
ጊዜ ምን በደለ በሱ የፈረድን
*
ጊዜማ ሂደት ነው ድሮም የነበረ
እራሱን ሳይለውጥ ይሆን ሁሉ ዘመን በክብር የኖረ
ታዲያ ምን አጠፋ በሰው ተደፈረ
ንገረኝ ወንድሜ(ቴ) ጊዜ ምን በደለ":;"""''!?

ዜና ሕማሙ የመድኃኔዓለም

አይሁድ አርብ ሌሊት ዘመድ መሰሉና


ወደ ጌታ መጡ እያበሩ ፋና
በመንፈቀ ሌሊት ልይዙት ሲመጡ
ግርማ መለኮቱን አይተው ደነገጡ
ማንን ትሻላችሁ ብሎ ጠየቃቸው
ኢየሱስ ናዝራዊ አሉት በቃላቸው
ኢየሱስ ናዝራዊ እኔ ነኝ ስላቸው
ኃይለ መለኮቱ የኋሎሽ ጣላቸው
ዳግመኛ አስነሳና አበረታታቸው
በሰውነቱም ላይ አሰለጠናቸው
ከእነርሱ ጋር ነበር ይሁዳ መሪያቸው
 ጫማውን ሳመና አመለከታቸው
ተረባረቡበት እንዳያመልጣቸው
የአምላክነት ስራው ትዝም አላላቸው
ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ሄደ ከላያቸው
ሴይጣን በጨለማ ስላሳወራቸው
የሃይማኖት ብርሃን ጠፋ ከልባቸው

ገመሱና ራሱን መቱት በብረት ዘንግ


ይጎትቱት ጀመር እንደ ሚታረድ በግ
የሚጎትቱበት ገመዱ ሁለት
አንደኛው ከአንገቱ ያጠለቁበት
አንደኛው የፈጥኝ የታሰረበት
አንዱ ወደ ኋላ አንዱ ወደፐፊት
አየተጓተቱ አመናተሉበት
ዓይኖቹን ሸፍነው እንደዚህ አሉት

በጥፊ ማን መታህ

በዱላ ማን ገጨህ

በል ተንቢይ ትንቢት
ኢየሱስ ናዝራዊን አሉት በትንቢት

የይህዳ ዘመዶች ምቀኞች አይሁድ


     አስረው አንገላቱት በቃጫ ገመድ
ከዮሃንስ በቀር የለውም ዘመድ
ከድንግል ማርያም ጋር እንባቸው ሲወርድ
ግሩማን መላእክት የሚሰግዱለት
እንስገድ እያሉ  አሽሟጠጡበት

ደረቱን በብረት ጦር አምጥተው  ወጉት


        በ አምስት እንጄራና በሁለት አሳ
       አጥግቦ ሲመግብ ለሐምሳ ሺ ጎሳ
መለኮቱን ቢገልጥ በደብረ ታቦር ላይ
ፊቱ ተለውጦ ባበራ እንደ ፀሃይ

ሸሽተው ተደበቁ እናዳያዩ ስቃይ

ሙሴ በመቃብር ኤልያስ በሰማይ


ፊቱን በእጅ መታው የሐና አገልጋይ
መከራውን ሁሉ ችሎ በትእግስት
ሰሪ የሉም ብሎ ማለደ ስርየት
ሳያውቁ ነውና የሚበድሉት

እሱም እንደ አንድ ሰው ስጋ ተዋሃደና


አስረው አስገረፉት ቀያፋና ሃና

 እንደ በደለኛ ልብሱ ተገፈፈ


        እንደ ወንጀለኛ ጀርባው ተገረፈ
     ደሙም እንደ ዝናብ ከመሬት ጎረፈ
የእናቱ ልቦና ምንም አላረፈ
የእርሱን ደም እያየ እንባዋ ረገፈ

የሚሰቅሉበትን መስቀል አሸክመው


እንደ ደካማ ሰው ጉልበቶቹ ደክመው
የግርፋት ቁስል ክንዱን ስለመታው
እጹን ተሸክሞ መራመድ አቃተው
በስጋው ስቀበል የአለምን መከራ
አምላክ ተሰቀለ ከወንበዴ ጋራ

ጌታዬ !
ቤተክርስቲያን እኔ ፥ በመቅደስህ ሳለው
ራሴን ስመረምር ፥ ዙርያዬን ስቃኘው
የመቅደስህ ታዛ ፥ እጅግ አሸብርቋል
በቀለም ተውቧል ፥ እዩኝ እዩኝ ይላል
የህንፃ ቤተክርስቲያንህ ፥ የአሰራር ጥበብ
ፈፅሞ ቢደንቀኝ ፥ አልኩኝ መንክር ዕፁብ።
የቤተክርስቲያንህ አፀድ ፥ ልምላሜን ታጥቆ
ንፁሕና ፅዱ ሆኖ ፥ በደንብ ተጠብቆ
መዓዛው ያውዳል ፥ ሜትሮችን ርቆ።
በውስጥ የሚገኙ ፥ ችግኞች በሙሉ
የሚተጉላቸው ፥ ወንድሞች ስላሉ
መጠውለግ መጠንዘል ፥ ምንም ሳይኖራቸው
ባለ ደምግባቶች ተወዳጆች ናቸው።
ይህንን ተመልክቼ
በዚህ ተደስቼ
በአድናቆት እንዳለሁ..
ወደ ራሴ ሳይ ግን ፥ እኔ ያንተ መቅደስ
ለመውደቅ ተዛምሜ ፥ ተንጋድጀ ልፈርስ
ለመንፈሳዊ ዓይን ፥ ደምግባቴ ጠፍቶ
በረቂቅ ለሚያሸትተኝ ፥ ሽታዬ ከርፍቶ
ራሴን አየሁት
ደግሞም የሚገርመው
ለታቦትህ ማደርያ ፥ ቅፅር የሚተጉ
ሲቆሽሽ የሚያፀዱ ፥ የሚያደገድጉ
የቅጥርህን ችግኞች ፥ ውሃ የሚያጠጡ
የጠወለጉ ቅርንጫፎችን ፥ በጊዜው የሚቆርጡ
ብዙ ሰራተኞች ፥ እንዳሉ አይቼ
ይህንን ፥ ተመልክቾ ...
እኔ ምስኪን ልጅህ ግን ፥ ይህ ዕድል ተነፍጎኝ
ለነፍሴ ጠባቂ ስለመገናኘት ፥ ድካሙ በዝቶብኝ
ከቀናትም ወራት ፥ እንዲህ ይነጉዳሉ
ሚዛን በማይደፋ ምክንያት ፥ ይሸኛሉ
የዛሬን ጨምሮ ፥ ብዙ ቀናቶችን
ስለ ነፍሴ ውበት ፥ ለማግኜት አባቴን
ደጅ መጥናትን ባዘወትር ፥ አብዝቼ ብፈልግ
አልሆንልህ አለኝ ፥ እኔስ ግራ ገባኝ ፥ እንግዲህ ምን ላድርግ?
ይገርማል !
ህንፃ ቤተክርስቲያን ለመስራት ፥ እንዲሁም ለማደስ ብዙዎች ሲተጉ ፥ ብዙ ጉልበትና ብዙ ፥ ንዋይ ሲፈስስ
ነገር ግን ፦
ሕንፃ ሰብ ሲጎሳቆል ፥ ዕለት ዕለት ሲፈርስ
በፍትወት ሲቃጠል ፥ ከሰውነት ሲያንስ
ቅጠልነቱ ጠውልጎ ፥ ልምላሜ ሲለየው
ዘወር ብሎ የሚያይ ፥ አይዞህ ባይ ጥቂት ነው።
ዮሴፍ ጌትነት

++ ሰማዕትነት ማለት +++


ዓላዊ ነገስታት ፥ በሰለጠኑበት
የዓለማዊነት እሳቤ ፥ በሚዎደስበት
እግዚአብሔርን መፍራት ፥ ፍፁም በሌለበት
አምልኮ ውዳሴ ፥ ለክብሩ መቀኘት
የመቀደስ ሃሳብ ፥ በጠወለገበት
አሁን በዚህ ሰዓት ...
በጎልያዶች ዛቻ ፥ በፈርዖናዊያን ምክር
በመስቀሉ ዕንቅብ ተደፍቶ ፥ ጣዖት በአዋጅ ሲከበር
ክርስቶስን ያሉ ፥ ሲገፉ ፥ ሲገረፉ
አንገታቸው ሲቀላ ፥ ደምን ከሰውነታቸው ሲያጎርፉ
ታቦት ባህር ሲጣል
ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል
አሁን በዚህ ሰዓት...
ሰማዕትነት ማለት
ምስክርነት ነው ፥ በኑሮ የሚገልጡት
አንድም
በዓላዊያኑ በነገስታቱ ፊት...
እኔ ክርስቲያን ነኝ
ከክርስቶስ ፍቅር ፥ የለም የሚለየኝ
ብሎ መመስከርና ለክብሩ መቀኘት
አንገቴ ይበጠስ ከማዕተቤ በፊት
ስለ ስሙ ልኑር ስለ ስሙ ልሙት
አንድም
ዓላዊ ነገስታት ፥ የስሜት ሕዋሳት
በፍትዎት ማዕበል ፥ ነፍስን ሲያስጨንቋት
ለአይን አምሮትና ፥ ለልብ ክፉ ምኞት ፥ አልገዛም ማለት
በንጹሕ አኗኗር ፥ መመስከር በሕይዎት
አንድም
ጎልያድ በበዛበት በዚህ ክፉ ዘመን
ለወገን ስለ መድረስ ህዝብን ስለማዳን
ተግዳሮትን ስለማራቅ ፥ ለቤቱ ስለመቅናት
መጀገን መታጠቅ ፥ የራስን ወንጭፍ ማንሳት ፥ መሆን እንደ ዳዊት
አንድም
ሀሰት በበዛና ፥ ፍርድ በተገመደለበት
ደካማና ምስኪን አንገት በደፋበት ፥ አሁን በዚህ ሰዓት
ከተገፉትና ከእውነት ጎን መቆም
ሀሰትን መገሰፅ ፥ ሀሰትን መቃወም
ስለ እውነት ዋጋ መክፈል
ስለ እውነት መመስከር
አንድም
መስቀል ቀባሪነት ፥
ጣዖት አክባሪነት
እንዲህ በበዛበት
እውነት እንዲገለጥ ፥ ዓለም እንዲያከብረው
ሰማዕትነት ማለት ፥ እሌኒን መሆን ነው
ሰማዕትነት ማለት
ቆስጠንጢኖስነት
ዮሴፍ ጌትነት
መስከረም 2013 ዓ.ም
ጌታዬ ንገረኝ ?!
ስላንተ መወለድ ፥ በውስጧ ስለመኖር
ቤተልሔም ሰማይ ፥ ጨለማዋ በርቷል
ጨለማ ለጸናብን ለእኛ ፥ ለሆነብን ድቅድቅ
እጅግም ተማርረን ፥ ብርሃን ለምንናፍቅ
አሁን በዚህ ሰዓት
በሕይዎታችን ሌሊት
ከልደትህ ብርሃን ሱታፌ እንድናገኝ
ምን እናድርግ ጌታ በየትስ እንገኝ ?
እረኞችን መስለን
በጎችን እየጠበቅን
እሳትን እየሞቅን
ብንጠብቅህ አንተን
እኛን የሚጠብቅ ፥ እረኛ መልአክ
ወዳንተ እንዲያደርሰን ፥ ይሆን የምትልክ ?
ወይስ ፥
ምድራዊ ክብርና ፥ ንግሥናችን ንቀን
አንተን ስለ ማዬት ፥ ራሳችን ክደን
እንደ ጥበብ ሰዎች ፥ ብንፈልግህ አንተን
ወደ አንተ ማደርያ ፥ ብንገሰግስ ይሆን?
ወይስ ፥
ለተቸገሩ ፥ ለአንተ ባለሟሎች
ለዮሴፍ ፥ ለማርያም ፥ ማደርያ እንደሆነች
ባንተ ዘንድ መወደድ ፥ ሞገስን እንዳገኘች
የቅዱሳን ማኅበር ፥ እንደከተሙባት
የብርሃን ጎርፍ ፥ እንደፈሰሰባት
የቤተልሄም ዋሻ ፥ የቤተልሄም በረት
ለተቸገሩት ሁሉ ፥ ልቦናዬን ብከፍት
ደግሞም ለወዳጆችህ ፥ ለባለሟሎችህ
ለዮሴፍ ለሰሎሜ ፥ እንዲሁም ለእናትህ
ለቅዱሳኖችህ ፥ ማደርያ እንዲሆን
በእኔ ዘንድ ያለች ፥ ቤት ልቦናዬን
ክፍት አድርጌ ብኖር ፥ አንተን አገኝ ይሆን?
ጌታዬ ንገረኝ !
ብርሃንን የምሻ ፥ እኔ ጉስቁል ልጅህ
በምን አይነት መንገድ ፥ አንተን እንዳገኝህ
ግልጥልኝና እርሱን ላድርግ አሁን
ሱታፌን እንዳገኝ ከልደትህ ብርሃን !
27/04/2013 ዓ.ም
ዮሴፍ ጌትነት

እኛ ለእኛ ሳንኖር !
ጌታ ሆይ !
ከመናገር ማዳመጥ
እንዲሻል ስትገልጥ
ሁለት ጆሮን እና አንድ ምላስን ብትሰጥ ፤ ...
ከመናገር ይልቅ ፥ ቢቀልልም ማዳመጥ
የአሁን ዘመን ትውልድ ፥ እኛ የሰው ልጆች
ተቃርኖን የምንወድ ፥ ግሩማን ፍጥርቶች
ማዳመጥን አንቅረን
መደመጥን የሙጥኝ ብለን..
አንድም
ራሳችን ማዳመጥን ፥ ቸል ብለን
የህሊናችን ደጅ ፥ ጥርቅም አድርገን ዘግተን
ግልፅ ዓላማ ፣ ግልፅ ርዕይ ፣ እኔነት ሳይኖረን
የማንነት ጥያቄያችንን ሳንመልስ በውዝግብ ቆመን
ግራ መጋባት ሸብቦን ፥ ባለማወቅ አሮንቋ ተዘግተን
የሌሎችን እኔነት ለመኖር መወራጨት
አሳጥቶን ማንነት ፥ አድርጎን ባዶ ወጭት..

ሆነን ሳለ ፥ የተለሰንን መቃብር


ስለ እኔነታችን ፥ ስናቅራራ ስንፎክር..
ጉስቁልናችንን ለማዳመጥ
ኢምንት ጊዜ እንኳ ሳንሰጥ...
የሰወችን ድካም ግን ፥ ለመንቀፍ ለመተቸት
ስንባዝን ስንታትር ፥ ስንደክም ፥ ቀን ከሌት
ትላንትናችን ቀስፈን
ዘሬያችንን አወስልተን
ይሄው እንዳለን አለን !
አንድም
ሌሎችን ላናዳምጥ ፥ እኔን ስሙኝ ብለን ፥ እኛ ብቻ ልንናገር
ራሳችን እንደ ብልህ/ የልብ አውቃ ፥ እንደ ጠቢብ ስንቆጥር ...
ጥበብና እውቀትን ከመቅዳት ፥ ዘግይተን ያለንን ስንመነዝር ...
መናገርን እንደ ስራ ቆጥረን
ስሩ እንጅ እንስራን ትተን ...
መከራና ስቃይን ፥ የመግለጫ ቃላትን ስናስስ
በቃላት ጨዋታ ስንራቀቅ ፥ ፅህፈትን ስንደርስ
መፍትሔው ያይደል ፥ መደመጣችን ገድዶን
ምስኪን መደገፋችን ያይደል ፥ መደነቅን ሽተን
የሌሎች መከራ ፤ ችግርና ስቃይ
የመናገርያ ዕድል፥ መልካም መስሎ ፥ ለእኛ ሲታይ..
ለእውነት ቋሚ ፣ ተናገሪ መባላችን
ለህዝብና ለእውነት ያይደል ፥ ለክብራችን
ሌሎችን ማድመጣችንም ሳይቀር
ለመደመጥ ሲመነዘር
ማንበባችንም እንኳ ፥ ለመለወጥ ያይደለ
ለመናገር ለመደመጥ ፥ አንባቢ ለመባል እየዋለ
ኑሩ ለማለት ስንታትር
ለመኖር ቀን ስንቀጥር
ኖርን ብለን ፥ ቀን ስንቆጥር
በመወለዳችን ስንፅናና ፥ ልደታችንን ስናከብር
ዕድሜያችንን ጨረስነው ፥ አድርገን የቀን ድምር
እኛ ለእኛ ሳንሆን ፥ እኛ እኛን ሳንሆን ፥ እኛ ለእኛ ሳንኖር።
08/05/2013 ዓ.ም

ለመሞት መኖር
በእኛ ዘንድ እንዲኖር ፥ ትንሣኤ ና ሕይወት
ሞትን ለማሸነፍ ፥ በእኛ ሕያውነት
ሙተንም እንዳንሞት
ለመኖር ከመስራት
አንድም
ብል የማያገኘው
ሌባ የማይሰርቀው
በመጽሐፍ የሚያስፅፍ ፥ መልካምን ከመስራ
የማይጠፋ መዝገብ ፥ ለእኛ እንዲኖረን አጥብቀን ከመትጋት
ለሚጠፋውና ፥ ለሚያጠፋን መስራት ፥ ምን አይነት ሞኝነት?
አንድም ፥
ከሞትንም በኋላ ፥ ሕያው የሚያደርገን
በሰወች ልቦና ፥ አትሞ የሚያስኖረን
ከመቃብር በላይ ፥ እኛን የሚያስጠራን
ይህንን እየሰራን ፥ ትውልድ ከማሻገር
ለዚህ ከመቅናትና ፥ ለዚህ ከመታተር
ለመስራት ከመትጋት ፥ ለመስራት ከመኖር
ከዚህ ሁሉ ይልቅ፦
ለመስራት ከመትጋት ፥ ለመስራት ከመኖር
የመረጥነው ጉዞ ፥ የዘመናችን ስሌት የኑሮአችን ቀመር
ስንሞት መቀበርያ ፥ ስናንፅ መቃብር
ቀባሪ እንዳናጣ ፥ ስንገባ እድር
ሌሎች እንዲኖሩ ፥ ከምንተጋው በላይ
ሲሞቱ ለመቅበር ፥ ስንል ከታች ከላይ
ቀባሪ አታሳጣኝ ፥ ብለን ስንፀልይ
ለመኖር ከመስራት
ስንሰራ ስንተጋ ፥ "ስንኖር - ለመሞት"
እንዲህ መጎሳቆል ፥ ራሳችን ማጣት
ከእውነት መደህየት ፥ ከክብር መታጣት
አቤት የእኛ ነገር ፥ ቅኔ ኑሮ ቅኔ ሕይወት
በሰም ኑረን ፥ በወርቁ ተዘርፈን ፥ በፍፃሜው መሞት !
ዮሴፍ ጌትነት
08/05/2013 ዓ.ም

 ስማኝማ ዳዊት ? ! +++


መዝ 64፥11
በቸርነትህ ፥ ዓመትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውን ፥ ስብን ታጠግባለህ
የምድረ በዳ ተራሮችን ፥ አንተ ታረካለህ
ኮረብቶችህንም በልምላሜ ደስታ ፥ የምታስታጥቅ ነህ
ሸለቆችም ከቶ ፥ በእህል ተሸፈኑ
ማሰማሪያዎችህ ፥ በመንጎች ተሞሉ
ሁሉም በአንድነት ፥ በደስታ ይጨሃሉ
የምስጋና ቃልን ፥ የዝማሬ ድምፅን ላንተ ያቀርባሉ
የምትል ዳዊት ሆይ ፥ እስኪ ልጠይቅህ
ከቶ ይህንን ምስጢር ፥ ስለ ማን ተናገርህ ?
ተራራው ኮረብታው ምድረ በዳው ማነው ?
ማሰማሪያ ያልከው ፥ የሸለቆው ምስጢር
በደስታ የሚጮሁት ...፥ የመንጋውና የእህሉ ነገር
እውን ለግዑዛኑ ፍጥረታት ፥ ለደመ ነፍሳዊያን
ምስክር መሆንህ መናገርህ ይሆን ?
ወይስ ተራራና ኮረብታ ያልካቸው
ከምድር ከፍ ያሉ ቅዱሳንህ ናቸው
ሸለቆ ፥ ምድረ በዳን የማንሳትህ ጉዳይ
ራሳቸውን በፈቃዳቸው ላደሩጉት ነዳይ
ያለበስካቸውን ጸጋ ፥ የመንፈስ ርካታ ፥
ያስታጠቅሃቸውን ልምላሜ ፥ የደስታ ገበታ ፤
መናገርህ ይሆን ?
መዝሙረኛው ዳዊት ፥ ጻድቁ አባቴ
ይህን የመናገርህ ነገር ፥ ለእኔ ለሕይዎቴ
ትርጉሙ ይህ ይሁን ፥ ብዬ እለምናለሁ
በፍፁም ተማፅኖ ፥ ፊትህ እቆማለሁ...
እንዲህ እንደነርሱ ፥ ዓመትን በመቀዳጀት ፥ ኅብረትን ካገኘሁ
በዕድሜ ከባረከኝ ፥ ዘመንን አልፌ ፥ ለዘመን ከበቃሁ
ምድረ በዳው ፥ “ልቤ” ፥ በኃጢአት በረሃ ዋዕይ የሚነደው ፤
ምድረበዳ እኔነት ፥ ልምላሜ ምግባር ፍፁም የተለዬው
ተራራው ... ፥ ኮረብታውም "እኔ" ፥ ዕቡይ እኔነቴ በስጋ መክበሩ ፍፁም የሚገደው
ሸለቆውም እኔ ፥ በዓለም ማዕበል ፥ ጎርፍና ውሽንፍር
ልቤ ተሸርሽሮ ፥ ተስፋን የቆረጥኩኝ በመዳኔ ነገር ...
የነፍሴ ጥም ሊቆረጥ በነፍሴ ልፈወስ ፥
በደስታ ልዘምር ልቤ ሊረሰርስ
የጊዜውን መቅረብ የጊዜውን መድረስ
ላንተ ሳበስርህ ነው ብለህ አስደስተኝ ፥ ብልዬቴን አድስ...
አወ ትርጉሙ ይህ ይሁን፤ ስለ ፀሎትህ ኃይል ፥ ስል እማፀናለሁ
የምድረ በዳ እኔነቴን መርካት ፥ በደስታ መታጠቅ ፥ በምናብ እያየሁ
የዕቡይ ልቡናዬን ፥ በአንተ ፊት መንበርከክ
የሸለቆ እኔነቴን ፥ በፍሬ መባረክ
ፍፁም ስለ መሻት
ይህን እልሃለሁ
ቅዱሱ አባቴ ፥ ስማኝማ ዳዊት
አሁን ይህን ሰዓት
አብዝቸ ስቃትት ፥ ...
የዝማሬህ ምስጢር ፥ የትንቢትህ ነገር
ለእኔ ይሁንና በደስታ ልታጠቅ ፥ በደስታ ልዘምር
4/1/2013

ምን ይሆን ምስጢሩ ?
መርከብ ልቦናችን ፥ በባህር ዓለም ውስጥ
ማዕበል ሲያማታው ፥ በሞገድ ሲናወጥ
የኑፋቄና የክህደት ፥ ጎርፍና ውሽንፍር
የዓለማዊነት ትኩሶት ፥ የዘረኝነት ሀሩር
በላያችን ሲወርድ ፥ ልባችን ሲሸበር
እንዲህ ስንቸገር ...
በጥፋት ውሃ ፊት ፥ ከሞት ጋር ተፋጥጠን
የፈርዖን ግልምጫ ፥ ፊታችን ሲገርፈን
የዲዮቅልጥያኖስ ጡጫ ፥ ሲያደማን ሲገፋን
እንዲህ ባሁን ዘመን ...
እናርፍበት ወደብ ፥ እንከለልበት ጥሩር
እንመክትበት ጋሻ ፥ እንሸሽበት አውጋር
መጠጊያ ፍለጋ ፥ ነፍሳችን ተርባ
በዓይናችን ሲያቀርር ፥ ፅኑ ትኩስ እንባ
ድረስልን አምላክ ፥ ራራልን ጌታ
የሚል ተማፅኖና ፥ የምዕመናን ዋይታ
መቅደሱን ሲሞላው ...
በጸሎቱ የሚደግፍ
በቃሉ የሚያሳርፍ
ለሕይወታችን ጨው ፥ ለጨለማችን ብርሀን
የሕይወት መንገድን ፥ ገልጦ የሚያሳየን
የምንድንበትን መርከብ ፥ የአሰራር ብልሀት
ጥበብን የሚነግረን ፥ የምስጢር ባለቤት
ኖኅን የምንሻ ፥ ሳለን የእናንተ ልጆች
ኖኅን የምትመስሉ ፥ ብፁዓን አባቶች
በአሳቻ ሰዓት ፥ ከእኛ መለየት
ምስጢሩ ምን ይሆን ፥ አልገባኝም በእውነት?
ከፊታችን ሆኖ ፥ በእረኝነት በትር
የኤርትራን ባህር ፥ ከፍሎ የሚያሻግር
መዓትና መቅሰፍት ፥ በእኛ ላይ እንዳይወርድ
ራሱን አስይዞ ፥ ስለ እኛ የሚማልድ ፥ ስለ እኛ የሚጋረድ
የክርስቶስን መንጋ ፥ ከጥፋት የሚያድን
ከነዓን ሊያስገባን ፥ የተሰጠው ኪዳን
ሙሴን የምናሻ ፥ ልጆቻችሁ ሳለን
የደጋግ አባቶች ፥ ከእኛ ዘንድ መለየት
ምስጢሩ ምንድን ነው ፥ አልገባኝም በእውነት !
ስለ ሀገርና ስለ ሃይማኖት ክብር
በጥብዓት የሚቆም፥ አዋጅ የሚያስነግር
ሰማዕትነትን ባርኮ ፥ ለእኛ የሚሰጠን
የእምነት አርበኛ ፥ ስንሻ ጴጥሮስን
አሁን በዚህ ሰዓት ፥ የእናንተ መለየት
ምስጢሩ ምን ይሆን ፥ አልገባኝም በእውነት !
ይህንን ስለ ማሰብ ፥ ይህንን ስለ ማየት
ሀዘናችን በረታ ፥ አቃተን መጽናናት
እንኪያስ እኛም ፥ ከእናንተ ፥ አባቶቻችን አንበልጥም
በረከታችሁ ደርሶን ፥ የምናርፍበት ፥ ተራው የኛ ይሁን !
27/03/2013 ዓ.ም

ምን ተሰምቶህ ይሆን ?!
ሀገር የምትኖረው ፥ ሀገር የምትድነው
ለሀገር ፅኑ ደዌ ፥ ፈውስ የሚገኜው
አንተ የሀገር ልጅ ፥ ጠቢብ ስትሆን ነው !
ርሃብ ቸነፈር ፥ ከሀገር የሚጠፋው
ደስታና ሀሴት ፥ ፍስሐ የሚሆነው
መሰደድ ተሰድዶ ፥ ባይንህ የምታየው
በሀሳብ ልዑል ስትሆን ፥ ልጄ ስትማር ነው !
ያለማወቅ ፅልመት ፥ ከሀገር ተወግዶ
ህዝብ ሰላም ሆኖ ፥ ርስ በርስ ተዋድዶ
በሀገር የሚኖረው
ልጄ ስትማር ነው !

የመሻገርና ፥ የማሻገር ተስፋ ፥ እውን የሚሆነው


ሀገርን የመምራት ፥ ለወገን የመድረስ ፥ ቁልፉ ጉዳይ ያለው
በማወቅህ ብዛት ፥ በብልህነት ጥግ ፥ በመማርህ ላይ ነው
እናም እልሀለሁ ....!
አፈ ሙዝን ማንሳት
ኃይልና ጉልበት
መፍትሔ የነበረው
በድሮው ዘመን ነው ።
ኢላማና ተኩስ ፥ ያረጀ ያፈጀ ፥ ድሮ የቀረ ነው
ያሁን ዘመን ፍልሚያ ፥ የሀሳብ ብቻ ነ..ው ።
በአሁን ዘመን ኖሮ ፥ ትልቁ ትጥቅ ያለው፤
ስልጣን የሚያዘው ፥ ሀገር የሚመራው
በሀሳብህ ልዑልነት ፥ በሰላም ትግል ነው
በመማር ማኅፀን ፥ በመማር ወገብ ነው ።
ሀገርህን ብትወድ ፥ ህዝብህን ብታፈቅር
በመማርህ ትጋት ፥ በተግባር አስመስክር
ብለህ የመከርከኝ ፤ የቀድሞው መምህሬ
ስለዚህ ንግግርህ ፥ ምን ተሰማህ ዛሬ?
ማሰብና መወቅ
አዲስ ሀሳብ ማፍለቅ
በእውነት ጥዩፍ ሆኖ
አለማወቅና አለማመን ገንኖ
ሀሳብ አለን ያሉ
ለወይኒ ሲጣሉ
በሰይፍ ሲቀሉ
በጥይት ሲቆሉ
መምህሬ ፥ አባቴ ፥ ይህንንስ እያዬህ
አሁንም ተማሩ ፥ አሁንም አስቡ ፥ ብለህ ትመክራለህ?
ደግሞስ
ለህዝብ ለወገን
ለራስህም ቢሆን
ማሰብ ከእኛ በላይ ፥ እንዲያው ለአሳር ነው
ማሰብህ ጥፋት ነው ፥ ማሰብህ ቅዠት ነው
እናም ለአንተ አኗኗር ፥ በርግጥ የሚበጀው
ራስህን ቆርጠህ ፥ ሃሳብህን ጥለህ
በእኛ ራስነት ፥ መኖርህ ብቻ ነው !
ሰላም ነህ ከተባልህ
የታለ ሰላሙ ፥ ስለ ምን ትላለህ?
አድገሀል ከተባልክ ፥ በርግጥም አድገሀል
ሌላ ማስረጃና ፥ ተጠየቁ ሁሉ ፥ ምን ያደርግልሀል?
እኛ ያንተ አለቆች ፥ እኛ ያንተ ገዦች ፥ በልተሀል እያልንህ
የታል የጠገብኩት ፥ ብለህ መሞገትን ፥ ከቶ እንደምን ደፈርህ
ምንስ አይነት ሰይጣን በልብህ ገባብህ ?
ጭራሽ ይባስ ብሎ ፥ የአንተን አሳቢነት ፥ ለእኔ ልታሳዬኝ
የሰላም ሰልፍ ብለህ ፥ ልትወጣ ሲያምርህ ሳይ ፥ እጅጉን ገረመኝ
መማርና ማወቅ ፥ ጥበብ የሚጠቅመው
ሀሳብን ለሚያከብር ፥ ህዝብና ንጉስ ነው
እናም ይህን እውነት ፥ ንገረን ከአልከን
እኛ ያንተ ገዦች ፥ አንወድም ማሰብክን
ደግሞም የማንወደው ፥ እጅግ የምንፈራው
ማሰብህን ብቻ ያይደል ፥ ማሰባችንም ነው!
በሚል መሪና ፥ ገዢ ፊት ስንቆም
የእኛ መማርና ፥ የእኛ ማወቃችን
ለጥበብ መሰደር ፥ ቀለም መቁጠራችን
መንስኤ ሲሆነን ፥ ለመገደላችን ለመወገራችን
ይህንን ስለማዬት ...
ስለ ቀደመ ምክርህ ፥ ምን ተሰማህ በእውነት ?
ዶ/ር ዮሴፍ
21/02/2013 ዓ.ም

ሥራችን ፥ ምንድን ነው ?
እንዲህ ባገራችን
ባሁን ዘመን ሚዛን
አዋቂነት ቀልሎ
ግልብነት አይሎ
"እኛ" ነት ተገድፎ
ለእኔ ማለት ገዝፎ
ብፁዕ ተሰይፎ
ዕቡይ ተደግፎ
አማኝነት ተከስሶ
ህዝብነት ኮስሶ
አለማመን ገንኖ
ፍቅር ተመናምኖ
አውሬነት ጀግኖ
ጥበብ ስትገፋ
ስንፍና ሲሰፋ
የሚያስታርቅ ጠፍቶ
የሚያጣላው በዝቶ
ጥላቻና ሴራ
በሀገር ሲዘራ...
እያዬን ፥ በዓይናችን
ይሄው እንዳለን አለን...
ከመሆን ተራቁተን
መኖርን ረግጠን
በመምሰል ተፅናንተን
አለመሆናችን እሽሩሩ ብለን
ከአለመኖራችን ፥ ተዋደን ተላምደን
መምሰልን ፥ ለዛሬ ብለን
በታይታ ተሸምነን
መኖርን ለነገ ቀጥረን
በመምሰል ተቃኝተን
መኖርን ተዘርፈን...
መታወቅን ደጅ ጠንተን
ማወቅን አወስልተን
እያዬን ባይናችን
ይሄው ፥ እንዳለን አለን !
ትላንትን አማግጠን
ዛሬ ላይ ተኝተን
ዛሬን አዘሙተን
ነገን አገልሙተን
ዛሬ ሳንሰራ ፥ ለነገ ሳናቅድ
በትላንት ትውልድ ፥ መርገም ስናወርድ
እያዬን በዓይናችን
ይሄው እንዳለን አለን!
ዛሬን ላለመኖር ፥ ትላንትን ስንጠቅስ
ታሪክን አጣርሰን ፥ ትውልድን ስንከስ
የመዋደድን ፥ ታሪክ ዘንግተን
የጥላቻን ድርሳን ፥ አንግበን
ጥርስ መንከስ በቀልን ፥ በልባችን ከትበን
ታሪክን መስራትና ፥ ዛሬን መኖር ታክቶን
ትላንትን ማወደስ ፥ ትላንትን ማነወር ፥ ስራ የሆነብን
ብዙ ብኩን ሰዎች ፥ ብዙ ጉስቁል ሰዎች ፥ ይሄው ዛሬም አለን ?
ከዚህ ሁሉ ነገር ፥ በዕድሜያችን -ዛሬ ፥ እኛ ከሰራነው
ለነገ የሚሆን ፥ ትውልድ የሚወርሰው ፥ ስራችን ምንድን ነው?
ዶ/ር ዮሴፍ
19/2/2013 ዓ.ም

+++ ዝምታ ፥ ቅኔ ነው ! +++


ዝምታ ወርቅ ነው ፥ ብዬ እንዳልናገር
ጣዕሟን መች ቀመስኩ ፥ የዝምታን ነገር
እንዲህም አልልም ...
ዝም ካለ አፍ ፥ ዝንብ አይገባበትም
ብዬ አልናገርም ፥ ብዬ አልመሰክርም
ዝም ካላለ አፍ ፥ ዝንብ ሲገባበት
በራሴ ባዬውም ፥ በእኔ ብመለከት
ዝም ካለ አፍ ውስጥ ፥ እንደማይገባ ዝንብ
መቼ አጣጥሜው ፥ ለምስክርነት ይህንን ላስነብብ?
ደግሞም እሽሽሽ ... ፥ ብሎ የሚናገር
ዝንብን የሚገስፅ ፥ ዝንብን የሚያባርር
በሌለበት ገላ ፣ በሌለበት ሀገር ፣ በሌለበት ምድር
የዝንቦች መፈንጫ ፣ ስለመሆናችን የሚያሻማም አይደል
በዚች በሀገሬ ፥ በኢትዮጵያ ምድር
ንፁህን የሚጠዬፍ ፥ ግፍን የሚያከብር
ለህዝብ ጤና ጠንቅ ፥ ዝንቦች የበዙብን
በብሔር ፣ በሰፈር ፥ በቤታችን ገብተው የሚያንዣብቡብን
የተቀደሰውን ሊያረክሱ
በግፍ የሚከሱ ...
የእነዚህ ዝንቦች ቁጥር ፥ እንዲህ መበራከት
በእነርሱ ጥረት ፣ በእነርሱ ኃይልና በእነርሱው ብርታት
ብቻ እንዳልሆነ ፥ እንዳይደለ አውቃለሁ ፥ ይህንን አምናለሁ
ዝም ስለ ማለት ፥ ስለ ቸልታችን የተፈጠረ ነው ።
መናገር ያለበት ፥ የእውነት አፍ ተዘግቶ፤
ሀሰት ሲያቅራራብን ፥ አደባባይ ወጥቶ
እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ፥
በሚል የአበው ብሂል ፥ ስንፍናን ስንደልል
ለእኛ ስንፍና ፥ በሚመች ትርጓሜ ፥ ጥቅስን ስናባብል
ይሄው ለዚህ በቃን
የሽቶ ማሰሯችን ፥ ዝንቦች አገሙብን !
እናም ይሄን እያዬሁ
ዝምታ ወርቅ ነው ፥ ብዬ እንዴት እላለሁ?!
የአንዳንዱ ዝምታ ከወርቅም በላይ ነው
ያለቦታው ደግሞ ዝምታ ገዳይ ነው
እናም ዝምታ ወርቅ አይደለም ፤ ደግሞም ዝምታ ወርቅ ነው
ተርጓሚ የሚሻ ፥ በሕይዎት የሚኖር ፤ ዝምታ ቅኔ ነው

12/02/2013 ዓ.ም
ዶ/ር ዮሴፍ ጌትነት

እንደ አባቴ አብርሀም፡ እንዳገኝ በረከት


ስላሴ ሆይ ግቡ፡ በኔ በባሪያህ ቤት
(ባይገባኝ እንኳ እንደ ቸርነትህ)

አስወግደህ ከኔ፡ የይሁዳን ስስት


ጌታ ሆይ አድለኝ: ከአብረሀም በረከት

ከሰሎሞን ጥበብ፡ ጨልፍልኝ ጥቂት


ደግሞም አትንፈገኝ፡ ከዳንኤል ዕምነት

እንዳመሰግንህ፡ በመዝሙር በቅኔ


ከያሬድ አድለኝ :ጥቂት ዕውቀት ለኔ

እንደ ዳዊት ሙላው፡ ልቤን በምስጋና


እንዳመሰግንህ: በክብር በበገና
~
ስላሴ ሆይ ቸርነትህ አያልቅ
~
ደግሞም ጨምርልኝ ከኢዮብ ትዕግስት
አሁንም አድርገኝ ፡እንደ ሙሴ ትሁት

እንዳገለግልህ፡ በጸሎት በትጋት


በረከት አድለኝ ፡ከአባ ተክለ ሃይማኖት
~
(ስላሴ ሆይ ሁሉ ካንተ ዘንድ አይደል።)

ሁሉን ብትሰጠኝ፡ ጸሎት ከጸለይኩት


ሀብትና በረከት ፡ ጥበብና ዕውቀት፡
በከንቱ ደከምኩኝ፡ ካልሰጠኸኝ ፍቅር
ሰውን ሀሉ እንድወድ: ባንተ ጉያ እንድኖር
ጸጋህ ይሟላልኝ አድለኝ ካንተ ፍቅር።

ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ።

ጉዞ ወደ ቅዱስ ቁርባን
ክፍል አንድ
፨፨፨
ከሁለት አመት በፊት ነው ጊዜው አብይ ፆም ነበር። ፆም ለነፍስ ደስታን ስትሰጥ ለስጋ ደግሞ ምቾት ትነሳለች።
ለመንፈሳዊነት ብርታትን ከእግዚአብሔር እንደሚያስገኝ ስላመንኩና የቤተክርስቲያናችን ቀኖና ስለሆነ እየጾምኩ ነበር።
ወጣት ነኝ
መንፈሳዊ መፅሀፍትን በቻልኩት መጠን ለማንበብ እተጋለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስና ልዩ ልዩ አዋልድ መጽሐፍትን አነባለሁ።
ስለ አምስቱ አዕማደ ምሥጢር ለአንድ ክርስቲያን በቂ የሚባል ዕውቀት ያለኝ ይመስለኛል
ስለ ቅዱስ ቁርባንም አንዱ pillar እንደመሆኑ እግዚአብሔር ባሳወቀኝ ያህል አውቃለሁ።
ስለ ቅዱስ ቁርባን ልዩ ልዩ መርሐ ግብር ተካፍያለሁ።
ስጋውን ካልበላን ደሙን ካልጠጣን ንሰሀ ብንገባም የዘላለም ህይወት እንደማይኖር በተለያዩ ትምህርቶች አውቃለሁ።
ነገር ግን እንኳን ወደ ቅዱስ ቁርባን መቅረብ ስለ ቅዱስ ቁርባን ሲወራ ራሱ እጅግ እፈራ ነበር።
መቅረብ ብፈልግም ምክንያት እየደረደርኩ አልቻልኩም ነበር።

እግዚአብሔር ግን እርሱን ከመፍራት ወደ እርሱ እንድቀርብ አደረገኝ።


ነገሩ እንዲህ ነው።

ከንሰሀ አባቴ ጋር እቀራረባለሁ


አንዴ የመከሩኝ ምክር ከልቤ ገብታ ህይወቴን ቀየረችው

እንዲህም አሉኝ "ቆይ አንተ ክርስቲያን ነህ አደል። አስርቱ ትዕዛዛት ታውቃለህ ታዲያ ከነዚህ ውስጥ ላለመፈፀም ያቀድከው
ዕቅድ አለህ?"
"እኔም የለም አልኩት" "ታዲያ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ እንደሆነ ካመንክ ስጋውንና
ደሙን ለሀጢዓት ስርየት ለዘላለም ህይወት እንደሰጠን ካመንክ እግዚአብሔር ሌላ ምን ይፈልጋል።" እምነትህንና አሥርቱን
ትዕዛዛትን መፈጸምንና እምነትህን ብቻ እንጅ
አሥርቱ ትዕዛዛትን ደግሞ እንኳን የተማረ ክርስቲያን የማያምኑ አህዛብ እንኳን በህሊናቸው በተጻፈ ህግ ካለማመን ውጭ
ትዕዛዙን አይሽሩም ።
ቆይ እግዚአብሔርን ትወደዋለህ?' አለኝ
ዝም አልኩ "ዝም ብትልም መቸም በልብህ እወደዋለሁ ትለኝ ይሆናል።ከወደድከው ትዕዛዙን ጠብቅ በወንጌሉ ይህንን
ብሏልና። "

" አንድ ንጉስ ሰዎችን ቢጠራና ኑ እናንተ ይሄን ምግብ ልትበሉ ይገባል በማለት ሄዳችሁ ነገር ግን ባትበሉ ንጉሱ ምን ሊል
ይችላል?
ምሳሌውም;
ንጉሱ፡ ክርስቶስ
መጠራታችን፦ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መሆናችንና ቤተክርስቲያን መሄዳችን
ምግብ፦ ስጋና ደሙ
የእግዚአብሔር ቃሉ እንደማይለወጥና እውነት እንደሆነ ታውቃለህ አደል?
መቸም የእምነት ችግር ያለብህ አይመስለኝም ያለ መስራት እንጅ።
ስለዚህ ይህን ብሏል
ስጋየን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘላለም ህይወት የለውም።'"
"ጫካ ገብተህ ባህታዊ ሁን አልተባልክ
ገዳም ሄደህ መንኩስ አልተባልክ
እዚሁ በቃ ክርስቲያናዊ ሰዉ ሁን ነው የተባልክ..."

ይሄን ካሉኝ በኋላ ልቤ ተነካ መቅረብ እንዳለብኝ ማንሰላሰል ጀመርኩ።

ጽሑፉ ረዝሞ እንዳትሰላቹ የሚቀጥለውን


በክፍል ሁለት ጠብቁ
ክፍል ሁለት ላለመቅረብ የፈራሁበት ምክንያትና እንዴት እንዳተወገደለኝ፣

፨ክፍል ሁለት፨፨
ወደ ስጋውና ደሙ መቅረብ እንዳለብኝ ባምንም ልቤ ፈራ
የፈራሁትም ምክንያትም
1 ወጣት ነኝ እኔ እንደፈለግኩ የማላዛቸው አካላት ወይም ሁለተኛ ስሜት አለኝ። ብበድልስ?
2 ሰው ምን ይለኝ ይሆን ሽማግሌው እንኳን በማይቀርብበት ዘመን እኔ ቀርቤ...
አይገባኝ ይሆን?
3) ሥርዓቱንም ስለማላውቅ ምን እነደሚደረግ ባነብም በጣም ከበደኝ።
4) ከጓደኞቸ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ይለወጣል እናም በብቸኝነት ልፈተን እችላለሁ።
5) ብዙ ለመተው የሚያስቸግሩ ሃጢዓቶች ወይም የኃጢአትና ሀጢዓት ጥንስሶች ብየ ያሰብኳቸው
ለምሳሌ ምኞት፣ የልማድ ውሸቶች፣ ስድብ፣ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ አልኮል መጠጣት፣ መጥፎ ትውስታዎች፣ የተለያዩ ፊልሞች
የምቀለደው ቀልድ አይነት ይለወጣል
በጊዜው ብዙ የሚያስጨንቁኝ ነገሮች ነበሩ አሁን ባላስታውስም
አነዚህንና የመሳሰሉትን በማሸነፍ ወደ ቅዱስ ቁርባን የሚያደርሰኝን መንገድ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ መጥረግ
ጀመርኩ
በመጀመሪያ ችግርን ወይም ደካማ ጎንን መለየት ለአንድ ነገር መፍትሄ የመጀመሪያው ስቴፕ ነውና።
ችግሮቸን በማስታወሻ መዘገብኩ።
1 ላመንኩበት ነገር ወደ ስራ ቶሎ ያለመግባት
2 አርአያየ የምለውን ሰው አለመከተል
3 ፈራሁ ብየ ያስቀመጥኳቸው ነገሮች

ለመንፈሳዊ ህይወቴ ፈተና ሊሆኑ የምችላቸውን ዘረዘርኩ


1) የማየው ፊልም
2) ሶሻል ሚዲያ ላይ ያሉ ነገሮች
3) በምኖርበት አካባቢ ያሉ ችግሮች
4) ጊዜ አባካኝ የበዛ ጨዋታዎች መዳራት
5) መንፈሳዊ ያልሆኑ ጓደኞች
.
.
.ምሳሌዎች ናቸው።
ምንም እንኳን ታሪክን ለዋጭ እግዚአብሔር ቢሆንም እንኳን መንፈሳዊው ስንት የዲያቢሎስ ፈተና ያለበት ስጋዊው ስራ
እንኳን ብዙ ልፋት ይጠይቃል። እግዚአብሔር ከጎናችን ካለ ግን ሁሉም ቀላል ነው።
ሰው እንዴት ቀስ በቀስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መለወጥ እንደሚችል ከተለያዩ ምንጮች አነበብኩ

ክፍል ሦስት
፨፨፨

በክፍል ሁለት እንዴት ቀስ በቀስ መንፈሳዊነትን ብሎም ወደ ቅዱስ ቁርባን እንዴት እግዚአብሔር መቅረብ እንዳስቻለኝ
እንደምገልጽ ቃል ገብቸ ነበር።
ቀስ በቀስ እንዴት መንፈሳዊ ልሁን ወደ ቅዱስ ቀርባን እንዴት ልቅረብ

1) መንጸሳዊ ጥበብን ማንበብ መማር ና መጠየቅ

ካለወቁ አያምኑ ካለመኑ አይጸድቁ የሚለው Universal Truth ነው ስለዚህ ይህን ማድረግ አስፈላጊ ነው
ይህን ያላደረገ እግዚአብሔር በተዓምሩ የመረጠው/ የጠራው ካልሆነ በስተቀር ሊለወጥ ወደ በጎው መንገድ ሊጓዝ አይችልም
ይመስለኛል። ምክንያቱም ለምን እና እንዴት ለውጥ ማምጣት እንዳለበት አያውቅምና።

2) እኔ ማን ነኝ አሁን ምን እያደረግኩ ነው? በእውኑ ብሞት መግቢያ የት ነው? ገነት? ሲዖል?


ሁሌም በተዓምር (እንደነ አባ እንጦንስ በአንዲት ቃል እንደተለወጡት) ካልሆነ በስተቀር በነገሮች ራስን ለመለወጥና ትክክለኛ
ለውጥ ለማምጣት ጊዜ ያስፈልጋል ነገሮች ሁሌም ቀስ በቀስ ነው መለወጥ የሚቻለው።
ለመለወጥ ቁርጠኛ ከሆንክ ነገ ማለት አያስፈልግም የዛሬዋን ቀን "ቀን አንድ" ብለን መቁጠር ያስፈልገናል።
ብዙዎቻችን እንዲሁ እንኖራለን እንጅ ስለራሳችን ቆም ብለን አናስብም በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቻችን የ 10 ሜትር
ጉዞ እንኳን ለመጓዝ ሰው ጠብቀን ነው የምንጓዘው። ቤተክርስቲያን ስንጸልይ እንኳ እርሱ(አብሮን ቤ/ክ የሄደው ሰው) ጨረሰ
አልጨረሰ ዞር እያልን እያየን ወይም እያሰብን ሊሆን ይችላል የምንጸልየው።

ቆም ብለን የምናስብበት ጊዜ ከቤተሰብ ጋር ከሆንንም ራቅ ያለ ቦታ ብቻህን ሆነህ ስለራስህ ማሰብ ያስፈልጋል።


እኔ ማን ነኝ? ጥሩ አሳቢ ነኝ ወይስ መጥፎ? ብሞት ሰዎች በምን ያስታውሱኛል። ጨካኝ፣ሌባ... ወይስ በጎ ፣ጨዋ ...

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ለራሳችን መጥፎ አይደለነም መጥፎ እንኳን እንደሆን ህሊናችን ጎሰም ሲያደርገን ራሳችን መጥፎ
የሆንበት ምክንያት እያቀረብን ክፉ አለመሆናችን ለራሳችን ለማሳመን እንሞክራለን።
ጥፋት አጥፍተን ምንም እንዳላጠፋን አያደረግን ተላምደነው እንኖራለን።
አንተ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ መሆንህን ማሰብ
ትልቁ ኃጢአትን እንድንጸየፍ የሚደርገን ነው
1 ኛ ቆሮ 3፥16 " የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ
ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ። "
እግዚአብሔርን እወደዋለሁን?
ዮሐ 14፥ 16 የምትወዱኝ ትዛዜን ጠብቁ
ብሎናልና የመውደዳችን ጥግ በትዕዛዙን በማክበር ይወሰናል
"በውኑ ለውጥ ያስፈልገኛልን?"
አሁን የምሰራው ምንድን ነው? የማስበውስ
ስለ እግዚአብሔር ስለ ቸርነቱ ብዛት ስለ መስቀሉ ነገር ወይስ ስለ ዝሙት መዳራት ና በወንድሜ ላይ ስለ መበደል?
የሚለውን ጥያቄ መመለስና ለውጥ እንደሚያስፈልግ ማመን
3) ጥፋታችን ካመንን ትልቁ ነገር ቀለለ ማለት ነው ይኸውም ለማስተካከል ለመስራት አቅደሃል ማለት ነው።
አሁን ፍላጎትህ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው
አሁን ፍላጎትህ ከቅዱሳን በረከት መሳተፍ ነው
አሁን ፍላጎትህ መስቀሉ ነው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።

ይኸን ለማስፈፀም ዋና መድኃኒቱ ጸሎት ነው።


ማመን መፈለግም በእግዚአብሔር ነው። እንግዲህ ፍላጎት እንኳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ የሚገኝ ከሆነ ሌላ ነገር
በራሳችን እንዴት መስራት እንችላለንን አንችልም።
የሞቀ ጸሎትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው!
ስለዚህ እግዚአብሔር እምነትን ፍቅርን በረከትን ጸጋን ያድለን ዘንድ መለመን ያስፈልጋል።

በዚህ ውስጥ የራስን ጸሎት ከሞላ ጎደል መጸለይ ያስፈልጋል ለምሳሌ እኔ

አዘውትሬ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር የምጸልያት ጸሎት አለች። ባስታወስኩት መጠን በቅደም ተከተል እጸልያለሁ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንጸስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ።


አቤቱ አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ምስጋና ይገባሀል።
አቤቱ ምን ያላደረክልኝ አለ ከሆነዉ ሁሉ ባንተ ነውና ዘወትር ምስጋና ይገባሃል።
አቤቱ አንተ ቸርና ይቅር ባይ አምላክ ነህ። እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደኔ ኑ ሸክማችሁን አቀላለሁ። ብለሃልና አሁንም
እነሆ ባሪያህ ልባል የማይገባኝ እነሆ ሸክሜን ታቀልልኝ ዘንድ እግርህ በሚያርፉባት መቅደስህ በፊትህ ወደቅኩ።

አቤቱ ጥበብና ዕውቀትን ልብና ልቦናን ስጠኝ።


ትዕግስትን ፍቅርንና ዕምነትን አድለኝ ሁሉ ካንተ ነውና።

አባታችን ዳዊት እንዲህ ሲል ለመነህ አንዲት ነገርን ለመንኩህ በቤትህ ለዘላለም እኖር ዘንድ በቤተመቅደስህ አገለግል ዘንድ
።አቤቱ እነሆ እኔም እንዲሁ ይኸውን እማጸንሃለሁ በቤትህ ለዘላለም እኖር ዘንድ።
ከመሞቴ በፊት ወደ ንሰሀ ጎዳና ምራኝ
ከበረከትህ አድለኝ
ለስጋወ ደሙ እንደ ቸርነትህ አብቃኝ
ህዝበ ክርስቲያኑን ሀገራችን ኢትዮጵያን በቸርነትህ ጠብቃት
ስብሐት ለእግዚአብሔር
አቡነ ዘበሰማያት..

ክፍል አራት
፨፨፨
በክፍል ሦስት እንዴት ቀስበቀስ መለወጥ እንደምንችል 3 ነጥቦችን አንስተን
1) መንፈሳዊ ጥበብን ማንበብ መማር ና መጠየቅ
2) እኔ ማን ነኝ በማለት መመርመር
3) ጥፋትን አምኖ መቀበልና መጸለይ
ከሶስተኛው ነጥብ ስለ ጸሎት እያነሳሁ እንደሚቀጥል ጽፌ ነበር

አሁን በስመ እግዚአብሔር ክፍል አራትን እቀጥላለሁ


ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኛ ድልድይ ነው
ማቴ 7÷7-8 ላይ የምናውቀው የ ወንጌል ቃል አለ።
"ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።"

በእውነት ቃሉ የታመነ ነው፤ አሁንም እናንኳኳ ይከፈትልናል።


አሁንስ ምንድን ነው ፍላጎታችን? ከጠየቅነው እርሱ በጎውን ያደርግልናልና
በሃሳባችን ባስታወሰነው መጠን የራሳችንን ጸሎት በሚመች መልኩ መጸለይ መልካም ስለሚመስለኝ

ይህንም እጸልያለሁ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ።

አቤቱ የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ


ለዘለዓለም የተመሰገንክ ነህ።
ሰማይን ያፀናህ ምድርን የዘረጋህ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠርክ አምላክ ሆይ ዘወትር ምስጋና ይገባሀል።
አቤቱ ቸር እረኛችን ሆይ ፍፁም ስግደት ይገባሀል።

እንደልቤ የምትለው አባታችን እንዲህ አለህ "እጠበኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።" አሁንም እኔ ባሪያህ ልባል የማይገባኝ
እንዲሁ እለምንሀለሁ።

አቤቱ የልቦናየን ድክመት አንተ ታውቃለህ በኔ ሀሳብ ያይደል ዘወትር በአንተ ሀሳብ እኖር ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ሆይ
እለምንሀለሁ።
አቤቱ የአብርሃም የያዕቆብ የይስሃቅ የቅዱሳን አምላክ ሆይ እንደቸርነትህ እንጂ እንደበደሌ አታድርግብኝ
አቤቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት
በቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ጸሎት
በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣በሁሉ ቅዱሳን ምልጃና ጸሎት እለምንሀለሁ እማጸንሀለሁ።
ስብሀት ለእግዚአብሔር
አቡነ ዘበሰማያት...
የመጨረሻ ክፍል ፨፨፨
7) መጽሐፍትንና ለመንፈሳዊ ልምምዱ ሊረዱ የሚችሉ ነገሮችን መሰብሰብ ምሳሌ ተግባራዊ ክርስትና በዲያቆን ሄኖክ
ኃይሌ እንዲሁም የ አቡነ ሽኖዳ The spritual man ወይም ትርጉሙን መንፈሳዊው ሰው በአያሌው ዘኢየሱስ

9) እያንዳንዱን ቀን በጸሎት በመጀመር መንፈሳዊ ልምምድን መቀጠል


10) እራስን በየቀኑ መገምገም
11) ክፍተት ካለ መመርመርና ማረም።
12) ወደ ኋላ አለማየት ወይም አለ መመልከት
(ወደ ቀድሞ ክፉ ስራ አለመመለስ)
" ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኋላ እንዲህ አለው። ራስህን አድን፤ ወደ ኋላህ አትይ፥ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም
እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ" ዘፍ 19:17

13) ሰው ሴትም ሆነች ወንድ ሁሌም ማለት ይቻላል ስለ ትዳር ያስባል ስለዚህ በዚህ ዙሪያ አንድ አቋም ልትይዝ ይገባል
ትዳር ካለህ እግዚአብሔር ትዳርክን እንዲባርከው እየፀለያችሁ በፍቅር መኖር
ትዳር ካልያዝክ ድንግል ከሆንክ እድለኛ በተክሊል ለማግባት ቁርጠኛ አቋም ይዘህ ከእግዚአብሔር ጋር ፈተናዎችን እያራቁ
በተክሊል ለማግባት ወስነህ ጠይቅ ይሰጥሀል ብሏልና መጸለይ።
ድንግል ባትሆንም የስጋን መመለስ ባይቻልም በነፍስ ይቻላልና በቤ/ክ ስርዓት ለማግባት ወስነህ ራስክን ከፈተናዎች እያራቅክ
እግዚአብሔርን የምትፈራ የትዳር አጋር እንዲሰጥህ እየለመንክ በቤ/ክ ስርዓት መኖር ።

ይሄን ልምምድ ከቀጠልን


ታዲያ ቅዱስ ቁርባን የመጨራሻውና ዋናው Target ነው።
ስለዚህ ምን ላድርግ
ስለ ቅዱስ ቁርባን ማወቅ ና
የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማስወገድ
ለምሳሌ ወጣት ቅዱስ ቁርባን መቀበል የለበትም ምክንያቱም ስለሚሳሳቱ የሚል አመለካከት በምዕመናን አለ ይህ ሰውን
ከበረከቱና ከመንግሥቱ ለማራቅ የመጣ የሰይጣን ሴራ ነውና እንወቅበት።

እስኪ ስለ ቅዱስ ቁርባን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል

ዮሐ 6÷53-56 "ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም
ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።

ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።


ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።"

" እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤"
(1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:7)
የዘላለም ህይወት ማን ማይፈልግ አለ።

ስለዚህ ለዚህ ለመቅረብ ብዙ ምክንያት መደርደር አያስፈልግም እውነት የዘላለም ሕይወት ምንፈልግ ከሆነ
ብዙዎች እኔ ራሴ የራሴን ማንነት አስተካክየ ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄዳለሁ ከዛ ቅዱስ ቁርባን እቀበላለሁ ይላሉ። ነገር ግን
አይችሉም ስራውን ለእግዚአብሔር አልሰጡምና ።
እግዚአብሔር ግን ወደ ቤቴ ና እና እኔ አስተካክልሀለሁ ይላል። ልባችን እግዚአብሔር እንዲነግስበት ከፈቀድንለት በጸሎት
ከጠየቅን ሁሉን ያደርግልናልና።
እግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን የክብሩ ወራሽ የስሙ ቀዳሽ ያድርገን። አሜን
ስብሐት ለእግዚአብሔር

"በእኔ የምትኖር"
ማቴ 6 ፥ 9
አባታችን ሆይ
የምትኖር በሰማይ
ብዬ እንድፀልይ
ለኔ ስታስተምር
ለኔ ስትናገር ...
ደግሞም ፥ ስጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ ፥ በእኔ ይኖራል
ብለህ መናገርህ በቅዱስ መጽሐፍ ፥ በዮሐንስ ወንጌል
(ዮሐ 6)
ቀጠል አድርገህም ...
የምትወደኝ ብትሆን ፥ ትዕዛዜን ብትጠብቅ ፥ በቃሌ ብትኖር (ዮሐ 14)
ከአባቴ ጋር ወደ አንተ እንመጣለን ፥ በአንተ ውስጥ ለመኖር (ዮሐ 14)
ብለህ መናገርህ ምን ይሆን ምስጢሩ ?
በእኔ እንደምታደር ባንተ መነገሩ
ስል እጠይቃለሁ ፥...
በሰማይ የምትኖር ፥ ተብለህ መመስገንን
የዘወትር ጸሎት ፥ አድርገህ ስትሰጠን
እውን በሁሉ የመላህ አንተ ፥ በምድር አትኖርም ?
ዓለማተ ዓለም ስላሴ ፥ በዓለም የለህም?
ስል እጠይቅና ፥ ይህንን አምናለሁ ፥
በረድኤት መኖርህ ፥ ክብርህን መግለጥህ
ነውና የሚደነቅ ፥ ከምድራዊ ሀሳብ ከፍ ባሉ ልጆችህ !
ደግሞም ...
መልስ ቢሆን ስል ሀሳብ አወጣለሁ ፥
ሀሳብ አወርዳለሁ...
አንተ ፥ በእኔ እንደምታደር ፥ ቃልን ከሰጠኸኝ
"በሰማይ የምትኖር" ፥ ብለህ ፀልይ ያልከኝ
መሆኑ ነው ይሆን ፥ ሰማይ ልታደርገኝ?...
ልዑል ሀሳብ ልዑል ምክር ለእኔ ልትሰጠኝ
ከምድራዊነት ዕንቅብ ልትለየኝ ፥ እኔን ልታወጣኝ ፥ ከፍ ልታደርገኝ ፤
በዕርገተ ህሊና ፥ በዕርገተ ልቡና ፥ እኔን ልትሾመኝ እኔን ልታከብረኝ ፤
የፀሐይና ጨረቃ የከዋክብት ውበት
የሚገለጥብኝ በእኔ ሰማይነት
ፍጥረትን የማሞቅ ፥ ብርሃንን የምሰጥ ፤
የፀሀይ ህላዌ በእኔ የሚገለጥ ???

ይህን ስለማሰብ እኔ ምድር ልጅህ ፥


ወደድኩ እንዲህ ልልህ
ምንም ከበጎ ምግባር ፥
ብታጣ ብጎድል ፥
አንተን ደስ ባላሰኝ በንፁህ አኗኗር
መፀፀት ፣ መመለስ ፣ መቀደስ ቢያቅተኝ
በዚህ አኗኗሬ አንተ ብቻ ያይደለህ ፥ እኔም ሰላም የለኝ
ስጋዌ ፈቃዴ ፥ አልገራ ብሎ ፤ ከኃጢአት ደጅ ቢያደርሰኝ
በስጋዊ ምኞት ሕግህን እንደረሳሁ ፥ አንተን እንደማላውቅ ፥መስዬ ብታዬኝ
ነገር ግን ጌታዬ ፥ ሁሌ እንደምወድህ ይህንን አስብልኝ
"ጌታ ሆይ ፥ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ "
(ዮሐ 20)
የሚል የጴጥሮስን ፥ ምስክርነትን ይሄው ላቁምልህ፥
ጳውሎስ አባቴ ሆይ ፥ የሃይማኖት መዶሻ ፥ አንተ ምርጥግብር
በሮሜ 7 ምዕራፍ 19 ልቤን የተኮስክ ፥ የእኔ የልብ አውቃ
እኔም እንዳልከው ነኝ ፥
መልካሙን ማድረግ ስወድ ፥ ማድረግ የተሳነኝ
ምንኛ ደካማ ፥ ምንኛ ጉስቁል ነኝ !
ምድር መሆንና የምድራዊነት ግብር
የስጋን ፍሬ መዝራት ፣ ማጨድና ማዝመር
ጨልጦ ገርኝቶኝ ፥ ለሥጋ የምኖር
ደግሞስ ... እኔ ምድር ልጅህ ፥ በሰማይ የምትኖር እያልኩ ስለምንህ ፤
በአባትነት ፍቅርህ ፥ ከቶ እንዴት አስቻለህ ?
ሰልችቶኛል ጌታ ...
በምድር የምትኖር መባልን ካልወደድክ ፥
በትቢያ ልጅህ በእኔ ፥ለመገለጥንና መደነቅ ካልፈቀድክ
በምድር ልጅህ ላይ ፥ ክብርህ ባይገለጥ በረድኤት ባትታይ
እኔ ጉስቁል ልጅህ እንዴት እሆናለሁ ፥ የማደርያህ ሰማይ
እናም እልሃለሁ...
ሰማይን እሆን ዘንድ ፈፅሜ እሻለሁ
"አባታችን ሆይ" ብዬ ፥ "በእኔ የምትኖር" ልልህ እወዳለሁ
፠ ' አይጣል ነው አይድረስ " ፠፠
አይጣል ነው፡ አይድረስ
ሰማይ አይታረስ ፡ንጉስ አይከሰስ
የሞት ነገር መቸም ፡ አይሆንልን ዛሬም
ስሙ ሲነሳብን ፡ይቀፈናል ሁሌም፡፡
በዚህ እስካለ፡ ህይወት
ሞትም ፡ከጎኑ ናት፡፡
(ምንም ማድረግ አይቻልም)
"አሁን ብትሞትስ!"ስልህ፡ ምሳሌ ስሰጥህ
ትሰድበኝ ይሆናል፡ "አንት ሟርተኛ"ብለህ
በርግጥም ያስፈራል ፡ወዳላዩት መሄድ
መቸም ቁርጥ ካልሆነ ፡እኔም እንዲዚያ አልወድ፡፡
ምን እናድርግ ?
በተፈጥሮ ህግ!
አይጣል ነው አይድረስ...
ነፍስህ ፡ባንተ አይደለች
በፈጣሪ እጅ ነው፡የተያዘች ያለች
በቤት ውስጥም ሳለህ ፡በመንገድ ጎዳና
በእግርም እየሄድክ፡በአየር መኪና
ልትሞት ትችላለህ ፡አለም ላይ ናትና፡፡
ድንገተኛ አደጋ ፡ምንኛ ሀያል ነው
እዚሁ ከጎናችን ፡በሰፈር ነው ያለው ፡፡
ሀገር ሰላም ብሎ፡ ሰው ከቤቱ ወጦ፣
ከጓደኞቹ ጋ ፡በስርዓት ተቀምጦ፣
የቆመ ግንድ ወድቆ፣
ተባራሪ ጥይት፡ ሌላን ሁሉ ትቶ፣
ሊገድልህ ይችላል ፡አንተኑ ለይቶ፡፡
ምን ይመጣል ብለህ፡ቤትም ብትቀመጥ
ልትሞት ትችላለህ፡በመሬት መንቀጥቀጥ፡፡
(ምን ይታወቃል እያየን ነው)
አይጣል ነው አይድረስ...
ይሄ ሞት የሚሉት ፡ምንም ምርጫ አያውቅም፣
ህፃን ሽማግሌ ፡ሴት ወንድ አይለይም፣
ቀጭኑ ወፍራሙንም፡ ረዥሙ አጭሩን
አያውቅም መሰለኝ፡ በያይነት መኖሩን፡፡
(አይመርጤ አሉ)
ብዙዎች ነጎዱ፡ ሳያውቁ ሳይነቁ
እምነት ምን እንደሆን፡ ቅኔ ሰሙ ወርቁ
ቢደርስም ባይደርስም፡ ሁሌ ተዘጋጁ
ሊመጣ ይችላል፡ ሊወስድ ነፍሱን በጁ፣
ይሄኔ ነቃ በል፡ ነጋሪት ሳይጎሰም ሳይነገር አዋጁ፡፡
እና በል ወዳጄ ፡እችን ያዝ እንግዲህ፣
አንድ ቀን ብለይህ፣
ምንም እንዳይመስልህ፣
አይመርጤ አይመርጥልህ!
እውነቴን ስነግርህ!
በል በል አንተ ወዳጄ፣ ጊዜ አትውሰድብኝ
አንዳንድ ስራ ልስራ፣ ሳይወሰንብኝ
መቸም አይቆጨኝም፣ ዝግጁ ከሆንኩኝ፡፡
አይጣል ነው አይድረስ
ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ።
ቸሩ መድህንዓለም ክርስቶስ ለንስሀ ሞት ያብቃን!!! አሜን
ስብሀት ለእግዚአብሔር፡፡

"አትናቅ"
፠፠፠
በዘር በወገንህ: ከመመካት ራቅ
የፈለገ ቢወድቅ: የፈለገ ቢደቅ
ሰው ሆነህ ተፈጥረህ፡ ሰዎችን አትናቅ!
ያደርገዋልና የተዋረዱን: ከፍ የከበሩትን ዝቅ::

ቢኖርህ አትመካ ፡ሙሉ አካል ከጤና


ምን ትሆን ወደፊት ፡ከቶ አታውቅምና፡፡

አለኝ ብለህ አትናቅ: ወርቅ ብር ገንዘብ


ሀላፊ ነው እና: ጌታ እንዳይታዘብ::

የሚመካ ቢኖር፡ ኑ ከዚህ አለ ሀይል


(ትምክህትህ በሌላ አይሁን)
በእግዚአብሔር ማዳን ነው፡ በመከራው መስቀል::

አላዛርም ነዌም ፡ደሀውም ሀብታሙም


ክፉው ዘረኛውም፡ ከቶም ያልፋል ሁሉም
በጎ ስራ ግና፡ ይኖራል ዘላለም፡፡

(በእርሱ ፊት)
ዘርህ አንተ ምነው፡ ቅማንት ወይ አማራ?
ይህን አትጠየቅ! ስምክን አትጠራ!

( ምነው ታዲያ )
ዘሬን እየጠራህ፡ ማለትህ አህያ¡
ምርጥ ነን ማለትህ: ሰውስ ከኛ ወዲያ!
አህያን ብታውቃት፡ ጌታ ሰጧታል ክብር
የከበረ አምላኳ ፡ተቀምጦባት ነበር፡፡

በአንድ አምላክ ተበጅተን፡ከአንድ አዳም ተፈጥረን፡


ከሰዎች ልዩ ነን፡ ማለትህ ምን ይሆን?
(እርሱ ይወቅልህ)

በዘር በወገንህ: ከመመካት ራቅ፣


የፈለገ ቢወድቅ: የፈለገ ቢደቅ፣
ሰው ሆነህ ተፈጥረህ፡ ሰዎችን አትናቅ!
ያደርገዋልና የተዋረዱን: ከፍ የከበሩትን ዝቅ::
ሉቃ 1÷51-53
ማር 11÷7
ገላ 6÷14

"
፠ ያንችስ ወዳሴሽ ፠፠"
ያንችስ ወዳሴሽ፡ አያልቅም ቢነገር
ትንሽ ጨለፉ እንጂ ፡ከምስጋናሽ ባህር
ከ ምድር ኤልሳቤጥ፡ ከሰማይ ገብርኤል
ሉቃስ እንደፃፈ አመስግነውሻል ፡እናታችን ድንግል
በማህፀን ሳለ ፡ቅዱስ ዮሐንስ
ከአባ ኤፍሬም፡ እስከ አባ ጊዮርጊስ
ከቅዱስ ያሬድ ፡እስከ ህርያቆስ
የተነሱት ሁሉ ፡በየዘመናቱ
ፅፈው አስቀመጡ፡ እንደየፀጋቸው እንደበረከቱ
ዜማችን ሆነሻል ፡እናታችን ማርያም
አምላክን መውለድሽ፡ታአምር ሆኖብናል ዛሬም ለዘላለም፡፡
ከመቅደሱ አገቡሽ፡ ሲደርስ አመትሽ ሶስት
መላዕኩ ፋኑኤል፡ ሲመግብ ያኖራት
ድንግል እመቤቴ ፡ዕፁብ ድንቅ ሰው ናት፡
ፀጋን የተመላሽ፡ በአካላትሽ ሁሉ
ዛሬም አናግንሽ፡ ከቅዱሳን ሁሉ

ለውሻ የምትራሪ ፡ርህርተ ህሊና


ለኔም ራሪልኝ፡ ፀሎቴን ስሚና
ለነፍሴ የላትም፡ አንዲት በጎ ስራ
ህይወቴን ታደጊያት፡ ከክፉ መከራ
ድንግል ሆይ አማልጅን፡ ከልጅሽ አደራ፡፡
ሉቃ 1÷28-45
እንኳን ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት አመታዊ በዓል በዓታ-ለማርያም በሰላም
አደረሳችሁ፡፡
እናታችን በዓታ ማርያም በጸሎቷ ከክፉው ሁሉ ትጠብቀን አሜን!!!

"የህይወት መድሀኒት"
እንካ እየተባለክ፡የህይወት መድሀኒት:
ምነው መቀለድህ: ጌታህ አዘጋጅቶት
ተቀበለው እንጅ:ምነው ማቅማማት
የዘላለም ህይወት፡ አትፈልግም እንዴ?
ሁሌም ዝግጁ ነው፡ ተቀበል ዘመዴ
ና ቅረብ ወንድሜ: መራቅ ምን ያደርጋል?
ከሰዎች ለይቶ: ህይወትን ያመራል
አስብ!
እስኪ ልጠይቅህ?
መድሀኒት ያለው፡ ቢኖር አንድ ዶክተር
ክትባት ልስጥ ቢል ፡በደስታ ዘላለም የሚያኖር
እርሱን ስለማግኘት: አትታገልምን?
በስንት ወርቅ በስንት ብር ፡ትለውጠው ይሆን?
አሀቲ ቃል ተበቅዑ ፡ይሄውልህ ውዴ
ራስክን አረጋግተህ፡ ይችን ስማኝ አንዴ
(የአንድ ደቂቃ ጥሞና)
በነፃ ሰጥቶሀል፡ አርብ ላይ ተሰቅሎ
ለአለም ቤዛ ሆኗል፡ ብሉኝ ጠጡኝ ብሎ
ራስክን አንፃና፡ ነገ ዛሬ ሳትል
የህይወት መድሀኒትን፡ በክብር ተቀበል፡፡
እናማ ወንድሜ ፡ራስክን አዘጋጅተክ
ከአለም ሰው ሁሉ፡ መርጦህ ከተቀበልክ
መንፈስ ቅዱስ ቀርቦህ
ፀጋው ሁሉ ከቦህ
ዲያቢሎስ ተጨንቆ
ከዙሪያህ ርቆ
ፀሎትህ ደርሶልህ፡ ያልከውን አግኝተህ
በድል ትኖራለህ፡ አክሊል ተቀዳጅተህ፡፡
*:ጊዜ ምን በደለ;*
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እውነትን ደብቀን ሀሰትን አንግሰን
አባቶች እያሉ ልጆች እያስተማርን
አርብ እሮቡን ሳናውቅ ሁልጊዜ አየበላን
ቤቱ መመላለስ ጭራሹን አቁመን
*
*
የእግዛብሔርን መቅደስ በሀጢያት ስንሞላ
እንደሰዶም ሆነን ህግን ስንጠላ
አህዛቦች ሲቀድሙን እኛ ቁመን ሇላ
ፀጋችን እያለ እሱን ሳናውቅበት ስንፈልግ ሌላ
*
*
የምንጓዝበት መንገዱ ረዝሞብን ቤቱ መሄድ ሲቀር
ሀይማኖት በገንዘብ እንደስም ሲቀየር
መፅሀፍትን ሳናነብ አባቶች እግር ስር ቁጭ ብለን ሳንማር
ቅዱስ ሁኑ ተብለን ምርጫችን ሲቀየር
*
*
ውበት ከአምላክ በላይ እኛ ስንሰራ
ቀለም እያማረጥን አለምን ስንመርጥ አምላክን ሳንፈራ
ማህሌት አዳር ትተን ስንመርጥ ጭፈራ
ሀብታችን ሀጢያት ገዝቶ ሲያስመስል ተራራ
*
*
ልብሳችንን ጥለን እርቃንን ስንመርጥ
በማናውቀው አለም ከላይ ሁነን ሳለ ወደ ታች ሰንዘቅጥ
አማርጠን ስንበላ ከደረቅ እስከ ቁርጥ
በደካማው ስጋ ለነፍሳችን ስንቅ ጭራሽ ሳናስቀምጥ
*
*
አወቀን ብለን ሳናውቅ በትቢት እየተጓዝን
ምርጫችን ከኛ በልጦ እኛኑ ሲመክረን
አልመለስ ስንል አምላክ እላይ ሁኖ በትዝብት ሲያዩን
ፍርጃ እላይ ቆመን ጌታ ሊመዝነን
እኛ ከሱ በልጠን ጭራሽ ፈራጅ ሁነን
*
*
ክፋትን አንግሰን ጠፋቶብን በጎነት
የውጩን አድንቀን ስንጓዝ በስህተት
ምርጫችን ተምታትቶ ስናማርጥ ውሸት
ሚስጥሩን ሳናውቀው ለመፋረድ ስንዋትት
*
*
በል በትርርህን አፅና የሚባል ሲጠፋ
መገንዘብ ሲያቅተን ምንድነን እንደሆነ የወደፊት ተስፋ
በማይጠቅም ህይወት ስንማስን ስንለፋ
ማወቁ ሲጠፋን ሁሉም ሟች መሆኑን ጠብቆ ወረፋ
*
መቶ ለማይሞላው ለዚህ አጭር እድሜችን
ምን ለማይጠቅመው እንጨነቃለን ለአፈሩ ስጋችን
አድሜአችን ሲቀንስ ከግባራችን ሲለቅ ፀጉራችን
መመለስ ሲያቅተን ዛሬ ነገ እያልን ሲመርሽ ቀናችን
*
አባቶችን ሰምተን ታሪክ ካልጠበቅን
ዘመናዊነት ሚስጥሩ ካልገባን
በአምና ተምረን ዘንድሮ ካልነቃን
ጊዜ ምን በደለ በሱ የፈረድን
*
ጊዜማ ሂደት ነው ድሮም የነበረ
እራሱን ሳይለውጥ ይሆን ሁሉ ዘመን በክብር የኖረ
ታዲያ ምን አጠፋ በሰው ተደፈረ
ንገረኝ ወንድሜ(ቴ) ጊዜ ምን በደለ":;"""'

፨ግጥማዊ ተውኔት፨

አባ ይፍቱኝ
መስቀሉን ያሳልሙኝ
ልጄ የተባረክህ
እማይሰራ ኃጢአት
እግዚአብሔር ይፍታህ
እስኪ ጠጋ በለኝ
ክርህን አሳየኝ።
አንገትህን ልየው
ማተቡን አስረሃል?
እንዴታ አባቴ
ማተብ ምልክቴ
መቼ ትለያለች
በጭራሽ ካንገቴ
ማህተቤ እኮ ናት
እጅግ የማከብራት
ክርስቲያን መሆኔን
በጌታ ማመኔን ምመስክርባት
የውስጥ እምነቴን ለሰው ማሳይባት
መናገሪያ ቃሌ
ይችናት መስቀሌ
በልቤ ያለውን
ውስጤ የሚያምነውን
እንዴት አሳይ ነበር
ማተቤ ከሌለች
እንዴት ልመስክር
አባ ማተቤማ ምስክሬ እኮናት
የመጣው ይምጣ እንጂ ካንገቴ አለያት።
በማለት ሲናገር ለንስሐ አባቱ
አቶ ግብዝነት ሐይማኖት ባንገቱ
አፍ የላትም ብሎ በማተብ ሲደበቅ
ድንገት አፍ አውጥታ "አ" ከማለትዋ
ዝም በይ ብሎ በጁ አፍዋን ሊይዝ ሲል
መናገር ቀጠለች ማተብ የእውነት ቃል

ይቀጥላል....

...የቀጠለ

አባ እኔን ይስሙኝ
ከልብዎ ያድምጡኝ
ሰዎችን ሳይፈራ እግዜርን ሳያፍር
በስንቱ ሰዎች ፊት ሐሰት ሲመሰክር
እኔን እያሳየ ስንቱን ሰው አሞኘ
ብዙ ታግሻለሁ አንገቱ ላይ ሆኜ
በድፍረት ሲያታልል የሐይማኖት አባቱን
ዛሬ ግን አልቻልም ልናገር እውነቱን።
ያለሁበት ሥፍራ ይህ ደንዳና አንገቱ
መካከለኛ ነው ለልብ ላንደበቱ።
ስለዚህ ልቡ ላይ ሲያስብ ሚውለውን
ደግሞም ባንደበቱ የሚናገረውን
እመሰክራለሁ ያየሁትን ሁሉ
በኔ ተሸፍኖ እንዳይጠፋ ዉሉ
ሐይማኖትን ትቶ ቅዱሱን ያምላክ ቃል
ከንቱ ሐሳብ ሲያስብ ራሱን ሲያታልል
አንዱን በሌለበት በሐሰት እያማ
ሌላውን ባፍ ቃል ክፉኛ እያደማ
ሲወረወር ቀስቱን የሾሉ ቃላቱን
በመርዝ አንደበቱ የነደፈው ስንቱን
ውስጡ ክፋት እንጂ ወንጌል ካልተሞላ
ያምላክን ቃል ትቶ የሰውን ከበላ
እንዴት እሆናለሁ የእምነት ምልክቱ
መሸፈኛው እንጂ እንዳይታይ ፊቱ።
ይቀጥላል.....

የቀጠለ...
ማተብ ሚስጢሩ እርስዎ ያስተማሩት
የላይ ምልክት ነው በልብ ላመኑት
ከቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳኢ
እንደ ተማረነው ወግ ከአበው መጻኢ
እውነተኛው እምነት በልባቸው ሆኖ
ለፈጣሪ ሲታይ በልበ ተአምኖ
ማተብ ግን ለሰው ነው ልቡን ለማያይ
የውስጣችን እምነት በተግባር እስኪታይ።
ይህ ነበር እውነቱ የኔ ጥቅም ለሰው
ወንጌሉን እንዲኖር ሁሌ ላስታወሰው።
ዛሬ ግን ብዙዎች ይህን ሳይረዱ
ባንገት እያመኑ በምግባር የካዱ።
ውስጣቸውን ዘግተው ከውጭ እያሰሩኝ
መገለጫ ሳይሆን መሸፈኛ አረጉኝ።
ይህም ሰው አባቴ ከእዚህ አንዱ ነው
በኔ ተሸፍኖ ውስጡ ግን ሌላ ነው
እርሱ እንደ ነገርዎት ብዙም አይወደኝም
ከነመኖሬ እንኳ አያስታውሰኝም
ለባለንጀሮቹ ሲናገር በሐሰት
ምንም አይመስለውም በስሜ ሲገዝት።
እኔን ያየ ሁሉ ክርስቲያን ሽፍኜበት።
ብዙ ሰው አታሎአል አባይ ነው ምላሱ
ውስጡን ያሳልሙልኝ ልቡን ይቀደሱ።
ምግብ ቤት ነው ተብሎ ከውጭ ከተጻፈ
እንጀራ ይገኛል ወደ ውስጥ ላለፈ።
እንዲሁም አንገት ላይ ማተብ መታስሩ
ወደ ታች ወደ ልብ ጣቱን መቀሰሩ።
ውስጥ ያለውን ሊያሳይ መሆኑን ንገሩት
ክርስቶስን ለብሶ እንዲኖር ምክሩት።
ብዙ ሰው አታሎአል አባይ ነው ምላሱ
ውስጡን ያሳልሙልኝ ልቡን ይቀድሱ።
ተፈፀመ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

፨መነባንብ፨
የብርሃን እናት
የብርሃን እናት የሁሉ አስታራቂ
እንሆ ምስጋናሽ ከእኛም እንዳትርቂ
ስምሽ ይጣፍጣል ከማር ከወተት
ተብለሻልና የአምላክ እናት።
ማህደር ብርሃን ሃመልማለ ወርቅ
የመወለደሽ ጥበብ እንደምን ይረቅ
በሄዋን ተዘግቶ የነበረው በር
ባንቺ ተከፈተ ምስጋናሽ የከበር።
ጌታ የመረጠሽ ለክብር ለፀጋ
ካንቺ ተወለደ በድንጋሌ ስጋ
ሰማይና ምድርን ያፀና በቃሉ
አምላክ አንቺን መርጦ ከደናግል ሁሉ
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የከተመብሽ
እፁብ ድንቅ እመቤት ድንግል አንቺ ነሽ።
ጡቷን እያጠባች አምላክን ታቅፋ
ምድራዊ ችግርን ስንቱን አሳልፋ
ይኸው ትኖራለች ክብሯን ተጎናፅፋ።
የምህርት አማላጅ እመቤቴ ሆይ
እንመስልሻለን በወርቅ ሙዳይ
አንቺን ያመነ ሰው ይኮነናል ወይ?
አማላጅ ነሽና ለሃጥአን ሁሉ
እኔንም ሰውሪኝ ከመከራ ሁሉ።
ነቢያት በትንቢት የተናገሩልሽ
የሰማይ መላዕክት ስምሽን የሚያገኑሽ
ብፅዕት እያሉ የሚያመሰግኑሽ
እነማን አፈሩ ያመኑ በስምሽ?
ምንም ተስፋ የለኝ አንቺውነሽ እምነቴ
አማልጂን ከልጅሽ ክብርት እመቤቴ
እኛን እንዲያድነን ወገኖችሽ ነንና
ቃሉም አይታበይ ፍርዱም የተቃና
የሰጠሽ ቃልኪዳን አይሻርምና።
ደስ ደስ ይበልሽ ቤዛዊተ ዓለም
አምላክን ስለወለድሽ በቤተልሔም
ክብርን አድሎሻል ለዘለዓለም።
ሰማይና ምድርን የማይችሉትን
ወልደሽ አሳድገሽ መድሃኒዓለምን
አዳምን ለማዳን ቃልኪዳን ገባና
ቅድስተ ቅዱሳን አንቺን መረጠና
ስጋሽን ለበሰ ምድር እንድትፀና።
ዓለምን ለማዳን ከሰማያት ወርዶ
መለኮት ከስጋሽ ፍፁም ተዋሕዶ
ነፃነትን ሰጠን ለኛ ሲል ተዋርዶ።
ወደአንቺ ተማፀንኩ ልመናዬ ፀንቶ
የሰውነቴ ሃጢያት በእኔ ላይ በርክቶ
መሳፍንት እርኩሳን እንዳይቀርቡ ከፊቴ
እንዳይ በረታብኝ በኔ ላይ ጠላቴ
አስታግሽልኝ አንቺ ክብርት እመቤቴ።
ይቀጥላል.....

....የቀጠለ
አምላክን የወለድሽ የሰማዩን ጌታ
ምህረትን አሰጭን ያድለን ይቅርታ።
በስምሽ ሲያጠጣ ሲጓዝ በበርሀ
በላይሰብ ጀኘኘአኸ በአንድ ጥሪኝ ውሃ።
እናትና አባትሽ ልጅ በማጣታቸው
ያለቅሱ እንደነበረ ወደ ፈጣሪያቸው
የወለድን እንደሆን ወንድም ሆነ ሴት
እንሰጣለን አሉ ለእግዚአብሔር ቤት።
ያናገራቸው ይህ ነበር ትንቢቱ
ቀድሶ ሰጣቸው ለዘጠኝ ወር ቤቱ።
እናትና አባትሽ ስመው ሳይጠግቡሽ
ለስለት ወሰዱሽ በሶስት ዓመትሽ
በክብር ስለኖርሽ በቤተመቅደስ
ገብርኤል ሲያበስርሽ የመውለድሽን ዜና
ፍፁም አደነቀው ዓለም ያንቺን ዜና
የመላእክት እህት የሰው ልጅ እናት
በገብርኤል ሰላምታ እናመስግናት
በድንጋሌ ስጋ አምላክን ስትወልድ
ኮከቡን አዩና ከምስራቅ ሲወርድ
ይቀጥላል...

....የቀጠለ
ተነስተው ተጓዙ ሄደው ለመስገድ
ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱን አይተው
ወድቀው ሰገዱለት ከመሬት ተደፍተው
ለኛ በመወለዱ በጣም ተደስተው
ኪሩቤል ሱራፌል የጋረዱልሽ
የብርሃን ደመና ዙርያውን ከቦሽ
መላዕክት ወርደው የሰገዱልሽ
አፁብ ድንቅ እመቤት ማርያም አንቺ ነሽ።
የምንመካብሽ መከታ ጋሻችን
አንቺ ስለሆንሽ ጠላት ድል መንሻችን
እንደ እሳት ይነዳል ባንቺ ላይ ፍቅራችን።
ብዙ መምህራኖች መስክረውልሻል
የአምላክ ካህናት ያገለግሉሻል
እንደ መላዕክትም ይዘምሩልሻል።
ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፈቀደ እግዚአብሔር
አዳምን ከሲኦል እንዲያወጣው ወዶ
እንደኛ ሰው ሆነ ስጋን ተዋህዶ
በፍቅሩ ጎበኘን ልጁ በምህረት
ዘመን አስቆጥሮ ዳግመኛ ልደት
ለዓለም ቤዛ ሆነ ስረ መለከት
ስሟ የከበረ ከሁሉ በላይ
ታቦተ ፅዮን ናት ንግስተ ሰማይ
ያገለግሏታል አእላፍ መላዕክት
መሆኗን ሲያጠይቅ የሰማይ ንግስት
ምን ያጠራጥራል አማላጅነቷ
ማርልኝ ስትለው ቆማ በጉልበቷ
ልጄ ወደጄ ሆይ ስለ እናትነቴ
እማፀንሃለው ባጠባሁህ ጡቴ
የምትል ነች ድንግል ቸር አማላጃችን
ለስጋችንም ቢሆን እንኳን ለነፍሳችን
ከፅኑ መከራ የምታድን ናት
እንግዲህ ለክብሯ እንስገድላት።×2
ተፈፀመ ዝንቱ መነባንብ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ስደቷ ፍቅር ነው

ከአረጋዊው ዮሴፍ ጋር _ ኤልሻዳይን አዝላ


ሰሎሜም ሳትቀር_ወጡ ከገሊላ
የአስራአምስት ዓመቷ_ድንግል ማርያም
በግብፁ በረሀ_ ገጠማት ድካም።
ዐፈሩ ረመጥ ነው_ እጅግ የሚያቃጥል
አሸዋ ድንጋዩ_ እንደ ብረት የሚግል
አየር እንፋሎቱ_ ልብን የሚሰውር
የነበረው ስቃይ_እንደምን ይዘርዘር?
ያስጨንቃል በጣም_የመከራሽ ነገር።
በትንቢተ ሆሴዕ _የተጻፈውን
ምስጢራዊ ትንቢት_ ሄደ ሊከውን
የድንግል ማርያም ልጅ_ ኢየሱስ መድኽን
እፁብ ድንቅ ያሰኛል_ የእግዚአብሔር ማዳን።
በፈጣን ደመና _ ወደ ግብጽ በረረ
በማለት ኢሳይያስ_ እውነት ተናገረ
ፈጣኗ ደመና _ ወለተ ኢያቄም
ማኅደረ መለኮት_ ነጻነቱ የአዳም።
ከሦስቱ አካል አንዱ_ ኢየሱስ ክርስቶስ
ተወልዷል በበረት_ ሞትን ሊደመስስ
በገባው ቃል ኪዳን_ በቀጠሮ መጣ
ከሲዖል ቁራኛ_ ነፍሳትን ሊያወጣ።
በከብቶቹ በረት_ ቢታይ በትሕትና
የሕይወት እንጀራ _ የሰማዩ መና
የዳዊት የሙሴ_የነቢያቱ ዜና
ተፈፅሞ ስናይ_ ዘመርን በበገና።
እረኞች በቦታው _ ከመላእክት ጋራ
ሥብሐት ለሥላሴ_ብለዋል በጋራ
ንጉሥ ተወለደ_ በዳዊት ከተማ
አስይ የምሥራች_ በዓለም ይሰማ
ነበር የዚያን ጊዜ_የደስታቸው ዓርማ።
መወለዱን የሰማው_ ሄሮድስ በውሸት ተነስቶ
ብዙ ሕጻናትን _ ቦታው አስጠርቶ
እርዳታ ልሰጥ ነው_ በሚለው ትዕዛዙ
የዋሓን እናቶች_ የሆዳቸውን ፍሬ ወደ እሱ አጋዙ።
ገስግሰው ሲደርሱ_ የሆነው ሌላ ነው
ለጨካኝ ሰራዊቱ_ ደም ለጠማቸው
የሕጻናቱን አንገት_ ቆራርጡት አላቸው
ለወንበር ለሥልጣን_ ስለ ተማረከ
የሥላሴን ፍጥፈት_ በሰይፉ አወከ።
የሰባ ሰገሎቹ_ ጥበብ ስላልገባው
የተወለዱትን _ በሙሉ አስጠራቸው
የተባለው ትንቢት_እንቅልፍ ስለ ነሳው
የነገሥታት ንጉሥን_አስቦ ሊያገኘው
ከዚህ ድንቁርና _ ሰውረን ማለት ነው።
የነፍሳቱ ደም_ ወረደ እንደ ጎርፍ
በዚያች ከተማ _ ቤተልሔም ደጃፍ
በከንቱ ሰዋቸው_ በመሰለው ነገር
ሕፃኑ ግን ሸሽቷል_ ወደ ሌላ ሀገር
የሥላሴ ጥበብ _ ከቶ አይመረመር።
ዛሬም በዚህ ዘመን_ አሉ ብዙ ሞኞች
በአለማዊ ጥበብ_ በባዶ ተሟጋች
ማመን አለማመን_የነሱ ድርሻቸው
እውነትን መመስከር_የልጅ ግዴታ ነው
ሂዱና አሰተምሩ_ መልሱ ነው የሚለው።
ስለኛ ተሰዳ _ተስፋን ለሰጠችን
በልጇ ቸርነት_ ስለተጎበኘን
እንደ ቅዱሳኑ_ ነይ ነይ እንላለን።
በአፀድ በቅጽሯ_ ጽዮንን ከበናል
የአባ ጽጌ ድንግል_ በረከት ደርሶናል
በሰማያዊው ስልት_ማኅሌት ቆመናል
አቤት ያለው ደስታ_ዓለምን ያስረሳል።
ዶግማ የማይሻር_ ከቶ የማይታደስ
ሕጉ አምላካዊ_በፍፁም የማይፈርስ
ቀኖና ፍትሐዊ_ጭንቀት የሚበጥስ
ትውፊት ታሪካዊ_ ለልጅ ልጅ የሚደርስ
የእውነት ቅብብሎሽ_አንዱም አይፋለስ
ከዚህ ውጪ የሆነ_ ልቡ እንዲመለስ
በዋሻ ገደሉ _ጤዛውን በመላስ
ተግተው ይቆማሉ_ እንዳለው ጳውሎስ።
በምድራችን ሰላም_እንዲሆን ደስታ
ትውልዱ እንዲጠግብ_ በአጋፔው ገበታ
በንሰሐ ታጥቦ_ ልቡ እንዲበረታ
ድንግል ሆይ አሳስቢ_ ለታቀፍሽው ጌታ ።
የቤሌሖር ልጁ_ ወድቆ እንዲሰበር
ዳጎናዊው መንገድ_በእውነት እንዲታጠር
የዲያቢሎስ ውጊያ_በቃልህ እንዲሞት
አስነሳልን አምላክ_ የበረታ አባት
ለመንጋው እራርቶ_የሚያፀና በእምነት።
ነኽምያን ላከው_ ያንጽ ቤተመቅደስ
የአምልኮ ሥፍራ_ለሁሉ እንዲዳረስ
ሳሙኤልን ስጠን_ ወንጌልን ሰባኪ
በፀጋው በጥበብ_ራዕይን አሳኪ።
አባታችን ሙሴ_ የማርያም ወንድም
ስማን አሳስብልን_ ለመድኃኒአለም
በኑፋቄ ባሕር_ ገብተን እንዳንሰጥም
ክፈልና አሻግረን_ ተጨንቀናል በጣም
በተሰጠን ፍቅ_ ለመኖር አልቻልንም።
ከውብ ዜማው ጋራ_ ቅዱስ ያሬድ ይምጣ
ምስጢር በማፋለስ_ ከሕግ እንዳንወጣ
እናንብብ እንጠይቅ_ እንማር ከአበው
ከእውነተኛው መምህር_ለኛ ከሚገደው
አምላክ ይሰውረን_ አሁን ከምንሰመው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እንኳን ለወረሃ ጽጌ ፍጻሜ በሰላም አደረሳቹ!
አላፍርም
የብርሃን ጅረት ከእጆችሽ ይፈልቃል
ጨረቃ ከእግርሽ ከጫማሽ ሥር ወድቋል
ከዋክብት በዙሪያሽ ይመላለሳሉ
የጌታችን እናት አንቺ ነሽ እያሉ
ፈጣን ደመና ነሽ ገስግሰሽ ስትደርሺ
ስምሽን በሚጠራው በህዝብሽ ንገሺ
ንገሽ እመቤቴ ግነኚ በዓለም
ከፍጡራን መሐል የሚመስልሽ የለም
ማነው ልበ ንፁህ የሃሳብ ድንግልና
አጣምሮ የያዘ ከሥጋ ንፅህና
እናትም ድንግልም ለመሆን የቻለ
ቅድስት ሆይ አንቺ እንጂ ሌላ ወዴት አለ?
ብርሃን አፍልቃ ወልዳ ፀሐየ ጽድቅ
ማናት የተሰኘች አማናዊት ምሥራቅ?
እመቤቴ አንቺ ነሽ ድንቅ ምልክቷ
በኪዳናት መሐል ምሥክር ሐውልቷ
ጽዮን ቅድስቲቷ ማርያም ንግስቲቷ
ርኅርይተ ኅሊና ድንግል አዛኝቷ
አምሳለ ኪሩብ ነሽ መንበረ መንግስት
የእሳት መቅረዝ ይዘሽ ወለድሽ መለኮት
ለማይነገረው ለክብርሽ ብዛት
እጅ እነሳለሁኝ የጌታዬ እናት
የባለፀጋ እናት ፀጋሽ በእኔ በዝቶ
ባዶ ማድጋዬ በረከት ተሞልቶ
ሃፍረቴ ይከደን ይቅር ነውር እርሜ
ቀና ብዬ ልሂድ ተጠግኖ ቅስሜ
በልጅሽ ፀጋ ውስጥ በክብርሽ ተውጬ
የመንግሥቱ ዜጋ ልሆን ተለውጬ
ፊትሽ በሚፈሰው ብርሃን ተጥለቅልቄ
ቃላት በማይገልጠው ግርማሽ ተደንቄ
ለመኖር እሻለሁ ናፍቄያለሁ በጣም
ዕድል ፈንታዬ ነሽ እመቤቴ ማርያም
ምልጃ ቃልኪዳንሽን አንቺን ተመርኩዤ
የልጅሽን መስቀል ቸርነቱን ይዤ
አምናለሁ እናቴ አልጠራጠርም
ተሥፋዬ ጽኑ ነው እኔ በአንቺ አላፍርም!
_ ማርያማዊት ገብረመ

ደረሰ ሰዓቱ

ደረሰ ሰዓቱ እንገስግስ መቅደሱ


ሊዘረጋልን ነው_ቅኔ መወድሱ
የአባ ጽጌ ድንግል_የምስጋናው ሻማ
ሊበራ ሊነድ ነው_ለነፍስ የሚስማማ።
የተመረጠቱ _ እንደየ ፀጋቸው
መቋሚያ ጽናጽል_ ከበሮውን ይዘው
የድንግልን ስደት_ በዜማ እያዋዙ
በአንደምታው ምስጢር_ በረከትን ገዙ።
ተጠርተው በፍቅሩ_ የሄዱት ምዕመናን
መስቀልያ አጣፍተው_ተውብው በብርሃን
ሐሴት ተጎናፅፈው_በቅድስቷ ድንኳን
ሲታይ በረከቱ_ መዓዛ ወ ዕጣን
ይወስዳል በሀሳብ_ ወደ ሰማይ ዙፋን።
የአምላክን ምሕረት_ፈቅዶ መሰደዱን
ከከበረው ዙፋን_ ስለኛ መውረዱን
የላከው ወደ ግብጽ_ ሙሴን ያናገረው
እሱ ነው ጌታችን_ በማርያም ያደረው።

የቅዱሳን አበው _ የነ ኢሳይያስ


የአማልእክት አምላክ_ የሁሉም ንጉስ
አዶናይ መሆኑን_የጽድቃችን ልብስ
የማኅሌት ሲሳይ_ ለኛ ሲዳረስ
ዕጹብ ድንቅ ያሰኛል_ ፍቅሩ የኢየሱስ።
የቅዱሱን መጽሐፍ_ ተርጉመው ሊቃውንት
አልቀው አርቅቀው_ ፈጽመው ሰማዕታት
ግራ እንዳይገባን_ ቀምረው ስርዓት
በደም አጥንታቸው_ለኛ አስቀመጡት
ምስጋና ይግባቸው_ በቀን በሌሊት።
የኪዳን የሳዓታት_ የቅዳሴን ትርጉም
ያስተማረን ጌታ_ ቸሩ መድኃኒአለም
ከመምህሩ ሰምተው_ ከተቡት በእምነት
በክፉዎች ሴራ_ እንዳይፋቅ እውነት።
ዛሬ የምናየው _ ኹከት ልብሱ የሆነው
በሐሰት ኑፋቄ_ ትውልድ የሚያውከው
የበግ ለምድ ለብሶ_ የዋሕ የሚያስተው
ቀድሞ ይታወቃል_ አሁን ወቅቱ እኮ ነው።
ይልቅ ይሄ ሲያይል_ ክኽደት ሲበረታ
ፈርቶ ተደናግጦ_ በመጨነቅ ፈንታ
የጸኑት ያሉትን_ የጻፉትን እንይ
ቃሉን ከሸቀጡት_ በፍጥነት እንለይ
ወርደን እንዳንጣል_ በትጋት እንጸልይ።
የተዘጋች ደጃፍ_ሕዝቅኤል የሚላት
የእሰይ ልጅ ዳዊት_ የሚያመሰግናት
ሰሎሞንም ብሏል _ የታተመች ገነት
ነቢዩ ኢሳይያስ_ የመሰከረላት
ልዑል ለማደሪያው _ አንዴ የቀደሳት
ከተሰጣት ክብር_ ማን ነው የሚያወርዳት?
ይልቅ የታደለው_ስሟን እየጠራት
በፍቅሯ ይኖራል_ ብጽዕይት እያላት።
ጊዜ የማይሽረው_ በዐለት የተጻፈ
ከሰማይ ከምድር_ እጅግ የገዘፈ
ቃሉ የማይሻር_ በዘመን እርዝማኔ
መርጧታል ኢየሱስ_ ምስክር ነኝ እኔ።
የስደቷን ነገር_ መከራዋን አይቶ
ከአለማመን መንፈስ_ ፈቅዶ ተለይቶ
የክርስቶስ ፍቅር_ እውነቱ ሲገባው
ጣቶቹን አንስቶ_ ማሕሌቷን ጻፈው
አባ ጽጌ ድንግል_ የእውነት አበባ ነው።
በብዙ ምሳሌ _ እያመሳጠረ
ለትውልደ ትውልድ_ ቅኔን አስተማረ
ኋላ የተጠራው_ ቀድሞ ተከበረ
ወድቆ መነሳቱን_ ቆሞ መሰከረ
እናት ተዋሕዶ_ምስጢርሽ ደመረ።
ድንግል ሆይ
በስደትሽ ስደታችንን _ባርኪልን
ከልጅሽ ቸርነት _ ለምኚልን
ፍቅር አንድነትን_ ደራርቢልን
ከክፉ መናፍስት_ በኪዳንሽ ጠብቂን
መስሏቸው ከበረቱ_ ክደው የወጡትን
በአማላጅነትሽ_ መልሽልን
አሜን አሜን አሜን

ሰላም ለኪ
ሰላም ለኪ ልበል
ስምሽን ለመጥራት ከቶ ባይገባኝም
ከአፌ መልካም ነገር ከቶ ባይገኝም
በኃጢያቴ ብዛት አንደበቴ ቢያድፍም
ሰላም ለኪ ብየ ማመስገጌ አይቀርም
ሰላም ለኪ ካላልኩ ሕይወቴም አይሰምርም ።
ሰላም ለኪ ብየ ቀኔን ልጀምር
ከጠዋት ጀምሮ ዉሎየ እንዲያምር
የዕለት ፍላጎቴ ለለት እንዲሰምር
የሚያምረዉ ስምሽ ነዉ ኑሮን የሚያሳምር ።
ሰላም ለኪ ብየ ስምሽን ልሰንቅ
ለጉዞ ስነሳ መንገዴ ነዉ ሩቅ
ጥላሽ እንዲያርፍብኝ እንዲከልለኝ
ከክፉ ነገሮች እንዲጠብቀኝ ።
ጥናቴን ስጀምር ሰላም ለኪ ምለዉ
ፈተናም ስሰራ ሰላም ለኪ ምለው
ስራየን በሙሉ እንድትባርኪዉ ነዉ ።
በቃ በአጠቃላይ ስምሽ ስንቄ ነው
በርሃቤ ጊዜ የምመገበዉ
በጥማቴ ጊዜ የምጎነጨዉ ።
ስለዚህ ድንግል ሆይ ሰላም ለኪ ማለት
ሁሉ ነገሬ ነዉ የተቸገርኩ እለት ።
ሰላም ለኪ ልበል አንደበት ባይኖረኝ
ስምሽን ለመጥራት ፍፁም ባይገባኝ
ስምሽን ላመስግን ሰላም ለኪ እያልኩኝ
ድንግል ሆይ ከልጅሽ እንድታስታርቂኝ ።
ድንግል ሆይ የአንቺ ስም ዕፁብ ድንቅ ነዉ
የአዳም ዘር በሙሉ ይህንን ቢያዉቀዉ
ከራሱ ሰላምታ ቀድሞ ሳያወጣ
ሰላም ለኪ ይላል በመልዐኩ ሰላምታ
ከገብርኤል ሰላምታ ትዉልድ የሚዋሰው
የራሱ አንደበት ስለሚያንስሽ ነው
በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም ለኪ
ድንግል ሆይ ይጠብቀኝ ዘንድ ኪዳንኪ ።
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ አብሳሪዉ መልዐክ
ድንግልን ለማብሰር ከላይ ስትላክ
እንደምን ደስ አለህ ስለተመረጥክ መጠን ነበረዉ ወይ ለደስታህ ልክ?
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ አንደበት አዉሰኝ
ስሟን እንዳልጠራ እኔማ ርካሽ ነኝ ።
ቢሆንም በሆነዉ ባልሆነዉ ሰላም ለኪ እላለሁ
ለሆነዉ ላልሆነዉ ስሟ መልስ ስላለዉ ።
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እንደምን ታደልክ
ከማዜምህ በፊት ሰላም ለኪ ብለህ ምስጋና ጀመርክ ።
ስለዚህ ድንግል ሆይ
ሰላም ለኪ ማለት እኔ አላቆምም
ስለ እናትሽ ሀና ስለእ
ኢያቄም
ታድያለሽ እና የእዉነት ሰላም ።
ድንግል ሆይ
በሕይወቴ ላለዉ የቁልፍ ዘመቻ
ሰላም ለኪ ሆኗል የሁሉም መክፈቻ ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

መነባንብ
፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል ፩
አለሁ አለሁ ለእናቴ
ለብርታት ጉልበት ፅናቴ
አለሁ!አለሁ ለርስቴ
ሀገሬ ከላይ ነው አባቴ እግዚአብሔር ነው
ዘራፋ! በቀራኒዮ የተሠቀለው
የምስጢር ደሙ እጄን ቢነካው
ከመኝታዬ ከእንቅልፌ ነቃሁ
ዘራፋ!2 አትደፈርም ፅኑ ሃይማኖቴ
አትሠደብም ድንግል እናቴ
ይቀዳ ደሜ ይርገፍ አጥንቴ
መቃብር ልግባ ይቀላ አንገቴ
ልሠደድ ልውጣ ይቅርብኝ ቤቴ
ይቅርብኝ እምቢ ሀብት ንብረቴ
አትደፈርም ፅኑ ሃይማኖቴ።
ዘራፍ!2 አይበጠስም ቃል ማህተቤ
አይበረዝም የእምነት ክታቤ
አትናወጥም ታንኳ መርከቤ
አትለወጥም እውቀት ጥበቤ
አትታደስም ታሪክ እንቅቤ
ከምትቃጠል እኔ ጠግቤ
ሁሉም ይቅርብኝ ልሙት ተርቤ።
ዘራፍ!2 የጀግኖቹ ዘር ጀግና የተባለች
የጳውሎስ ወኔ በፅኑ የጠራኝ
የዲዮስቆሮስ የፀጋው ልጅ ነኝ
ማንም አይነካሽ ፊትሽ አይቆዝም አትዘኚብኝ።

ይቀጥላል....

ክፍል፪
ዘራፍ!2 ታሪክ እምነቴን አልሸጥም ከቶ
የተዋህዶ ስም አይቀርም ጠፍቶ
ፅላት ብራናው አይሔድም ወጥቶ
አይቀርም በእንቶ ፈንቶ
ነገም ይኖራል ልጆች አፍርቶ
ሰው ይማርካል በደማቅ በርቶ
ከቶም አይሞትም ይቆያል ፈክቶ
በብርቱ አለት ዘላለም ፀንቶ
እማ አትዘኚ ልጆች አለንሽ
ይተላለፋል ገድል ታሪክሽ
አይኮበልሉም ውድ ቅርሶችሽ።
ይቀጥላል.

ክፍል፫
ዘራፍ!2 በቀራንዩ የተሠቀለው
የምስጢር ደሙ እጄን ቢነካው
ከመኝታዬ ከእንቅልፌ ነቃሁ
ዘራፍ!2 ሞቶም ተቀብሮም የሚፈሩት
ገድለውት እንኳ የሚሠጉት
መቃብሩ ሳይቀር የሚጠበቅ
ገዳያችንን የሚጠረቅ
ሞትን በሞቱ እየገደለ
የጥንቱን ጠላት ከጥልቅ የጣለ
የሞትን መዝጊያ የሰባበረ
ቀበሪያችንን የቀበረ
መስቀል ላይ ሆኖም የሚያሸንፍ
የጥልን ሠነድ ክስን የሚያጠፋ
ጅራፋ እያየ የማይፈራ
ሁሉን በፍቅር የሚጠራ
የአለም መድሃኒት የይሁዳ አንበሳ
በሶስተኛው ቀን ፈጥኖ የተነሳ
የንጉስ ልጅ ነኝ ስሙም ተፈሪ
ነፃ የሚያወጣ ወጥመድ ሰባሪ
ከቶ አልሠጋ አልሆንም ፈሪ
ዋጋ ከፋዩ ሆኖኛል መሪ።
ይቀጥላል.....

ክፍል፬
ዘራፍ!2 ፍቅርን ታጥቄ ፍቅርን ለብሼ
በንስሐ እንባ ውስጤን አድሼ
የጌታን ስጋ ደሙን ጠጥቼ
በቤትሽ ኖሬ ደጅሽ ፀንቼ
አሁንም ልኑር ጡትሽን ጠብቼ
ዘራፍ!2 ማነው የሚነካሽ የታለወንዱ
ቢፈራገጥም አምላኩ ሆዱ
መሠረትሽን ከቶ አይንዱ
ዘራፍ!2 የቄርሎስ ምላሽ ጥንተ ሃይማኖት
የአባ ጊዮርጊስ ፀሎት ደረሰቱ
የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ስብከት
የአግናጢዎስ የአንበሳ ራቱ
የአባ እንጦስ ብርታት ፅናቱ
የቅዱስ መቃርስ ምናኔ ቤቱ
የቅዱስ ያሬድ ዜማ ስርዓቱ
የአትናቴዎስ ብርታት ስደቱ
የአረጋዊ ወዳጅ እናቱ።
ዛሬም ይስማል ስዓታት ቅኔሽ ዚቅ ማህሌቱ
ይከበራል ነገም ገና ከፍ ይላል መስቀል ፅላቱ
እማ ተዋህዶ መቼም አትጠፋም ይሰማ ፍጥረቱ 2
አትጠፋም... አትጠፋም
አትጠፋም.... እማ ተዋህዶ❕
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
*/ተፈፀመ ዝንቱ መነባንብ\*

የማጀት ሥር ወንጌል
ሙያተኛ ሀገሬ ከማጥገብ ጎደለ በረከት እራቀው የገበታሽ ለዛ፣
ተሻምቶ ለመጉረስ ከበላነው ይልቅ የደፋነው በዛ፡፡
ሙያሽ ባያስደፍር አጀብ ቢሰኙበት፣
ማዕዱ ቢሙላላ ዓይነቱ ቢያምርበት፣
አበዛዙ አይደለም አበላሉ ላይ ነው የገበታሽ ውበት፡፡
እየተማመንን! የፉክክር ቅሚያ በርሃብ እየናጥን፣
ከደፋነው ጠግቦ ውሻችን በለጠን፡፡
ከምርት አላነስን፣
ጎተራችን ሙሉ ጀግና አራሽ መች አጥተን፣
ማሰብ የጎደለው አያያዛችን ነው ገደል የከተተን፡፡
ይልቅ ግዴለሽም! ከምግባር ምጣድ ላይ ሳንበስል አንጋግተሸ ከማዕድ አትምሪን፣
ገበታሽ እንዲያምር ከእግዜር የሚያስታርቅ ፍቅር አስተምሪን፡፡
ገበታ ዕድሜ ነው ባለ ማሰብ መክነን፣
ሳንፀነስ ጃጀን፣
ሳንጣድ አረርን፣
ከዘመን ገበታ ከፊደል አቅድመን ዘር እየቆጠርን፡፡
ገበታ ሀቅ ነው በክፋት ሊጥ ጋግረው ያሻገቱት እውነት፣
በሆዳም እስክስታ ረግጠው ያፈኑት የምስኪናን ጩኸት፡፡
እስከ ልጠይቅሽ በጥም ደዌ ደቆ የረሃብ ጠኔ ደፍቶት እልፍ ትውልድ ያልፋል፣
ቢራ ለመጥመቂያ ሚበተን ገብስ ግን ከሀገር መች ይጠፋል፡፡
ከሆድ በማይሻገር የማጀት ቤት ዕውቀት አጥብበሽ አትለኪን፣
እስቲ መኖር ይግባን ከማስተዋል መቅደስ ሰው መሆን ስበኪን፡፡
ዘመን ካልገበረው ከችጋር ተራራ ከሲኦል ዳር ኑሮ፣
እንዴት ነው መሻገር ከመርፌ ቀዳዳ በጠበበ አይምሮ፡፡
ከምስኪን ዘመን ላይ የማይኖሩበትን ዕድሜ መበዳደር፣
ለአንዲት ማምሻ ደስታ በአያት እስትንፋስ ላይ ቁማር መደራደር፣
ያሳፍራል አይደል?
እያደጉ ማነስ እያነሱ መዝቀጥ፣
አጎንብሶ ያፀናን የድሃ እናት ጉልበት በጭካኔ መርገጥ፣
ያሳምማል አይደል?
መንገስ ከሚያባላስ መጥገብ ከሚያቃቅር ማግኘት ከሚያጎለን፣
ማጣት ውሎ ይግባ ባርነት ይሰንብት ድህነት ይግደለን፡፡
ከረፈደ ፀፀት ደረት እየደቁ ከእግዜር ቢዋቀሱ፣
ትርጉሙ ምንድነው ሲኖር ተቃቅሮ ሲሞት መላቀሱ፡፡
በእናታችን አድባር በፍቅሯ ይሁንብን፣
መድመቅ ካጋደለን ቆሽሸን ይመርብን፡፡
በመጠማት ሲቃ እስትንፋስ እስኪያንቃት ነፍሳችን ትርበትበት፣
ብቻህን ከመጥገብ አብሮ መራብህ ነው ሰው የመሆን ውበት፡፡
በድፍን ግልብ እሚያጋድል ህዝብ የመሆን መንጋ አይንዳን፣
በማሰብ ስር እንፈወስ በሰውነት ፀበል እንዳን፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን ከመንጋነት ሚያግድ እረኛ አያሻህም ከህሊናህ በላይ፣
ስታስብ መሪ ነህ በብስለት ከፍታ በማስተዋል ሰማይ፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን የጎጥ አረም ነቅለህ በአንድነት መስክ ላይ ፍቅር ትዘራለህ፣
በወረወሩብህ የጥላቻ ድንጋይ ትውልድ የሚያፋቅር ድልድይ ታበጃለህ፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን ዝምታህ ኃያል ነው ጀግና የሚያንበረክክ፣
ከፈሪ ቀረርቶ ከባዶ ሰው ጩኀት፣
ሀገር ላምስ ከሚል በመንደር አጀንዳ በአሽኮለሌ ተረት፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን ነጻ ነህ እያሉህ መታሰር ያምርሃል፣
መቀመቅ መበስበስ፡፡
የኖርክለት እውነት ሀገር እስኪፈታ፣
በሀቁ እስኪመዘን ስለ በርባን ክብር የቆሸሸው ፍቅር የታሰረው ጌታ፣
ከድል ታሪክ ሰማይ ከሥልጣኔ ዳር ከጥበብ ከፍታ፣
እንሻገራለን ህዝብነትን ትተን ሰው የሆንን ለታ፡፡
በትረ ጥበበ ቢካን ዓለም ሊያንቀጠቅጥ ድል ሥልጣን ቢሰጠው፣
ጀግና መሪ አይደለም ብርቱ ተመሪ ነው ሀገር ሚለውጠው፡፡
አስተውል ወዳጄ ጠልተን ላንጣላ ችለን ላንጋደል ነደን ላንፋጀው፣
የኛው ትርምስ ነው በልቶ ለሚያባላ ጠላት ሚበጀው፡፡
ስጋና ደም እንጂ የአንድነታችን ውል የፍቅራችን ቀለም፣
ያሰመርነው ክልል የታጠርንበት ዘር ቋንቋችን አይደለም፡፡
ከመዋሃድ መቅደስ ትውልድ እናስተምር፣
ዘመን ይመርቀን ፍቅራችን ምን ጎድሎት ደማችን ያስታርቀን፡፡
በልጆቿ አጥንት በደም ኪዳን ምለን የገባንላት ቃል፣
ከጩኀት ያለፈ ዘመን የሚሻገር ተግባር ይጠይቃል፡፡
በአንድ ሃሳብ ተጋምደን በድል ድር እናብር ውድቀታችን ያንቃን፣
ሠርተን እናሳምን ሆነን ድል እንንሳ የአፍ ጀግንነት ይብቃን፡፡
ምስኪኒቷ እናቴ! በሞላ ጎዳና ባልጠበበ ድንበር በዘር ገመድ ታግዳ፣
ነጻ ነኝ ትላለች መንጋነት ያሰረው ባሪያ ትውልድ ወልዳ፡፡
የጀግንነት እብሪት ልባችንን ደፍኖት ማሰብ እየከዳን፣
እንዴት ነው ነጻነት እንዳበደ ፈረስ ስሜት እየነዳን፡፡
ገድሎ የመንገስ ጥማት ጩኀት ላገነነ አመጽ ላጀገነው፣
ለዚህ ምስኪን ትውልድ በጅምላ እየነዱት፣
በመንጋ እያሰበ ነጻነት እንዴት ነው?
ነጻነት ምርጫ ነው አምሮ ቢደላደል ጥፋት ያመነነው የመንጋዎች መንገድ፣
እንቅፋቱን ወዶ ለኖሩለት እውነት ለብቻ መራመድ፡፡
ነጻነት ማመን ነው ቀን ወዶ ቢያጀግን ቀን ጠልቶ ቢከዳም፣
ቢቆሽሹም ቢደምቁም እራስን መቀበል ራስን መምሰል ነው የነጻነት ገዳም፡፡
ነጻነት ማሰብ ነው በአንድነት መለምለም የኔነትን አረም ከህሊና ማጥፋት፣
ዘር ሆኖ ከማነስ ሀገር ሆኖ ማበብ ዓለም ሆኖ መስፋት፡፡
ንገሯት ለሀገሬ በጀግኖቿ ትግል ድንበር ባታስደፍር ከእጀ ገዥ ብትወጣ፣
ነጻ ነኝ እንዳትል በገዛ ልጆቿ በእጅ አዙር ተሸጣ ፡፡
ስሩን ካልሸመነው በመዋሃድ ጥለት በማስተዋል ሸማ፣
ታሪክ አናደምቅም በጭብጨባ ድግስ በሆይ ሆይታ ዜማ፡፡
ምን ብናቀነቅን በየሰልፉ ሜዳ ወኔ ብንደግስም፣
በፈረሰ አይምሮ በደቀቀ አንድነት ሀገር አናድስም፡፡
በጭፍን ከመሮጥ አስቦ ማዝገም ነው የመራመድ ውሉ፣
ሁሉም እንቅፋቶች እስኪጥሉን ድረስ ምርኩዝ ይመስላሉ፡፡
በድፍን ግልብ እሚያጋድል ህዝብ የመሆን መንጋ አይንዳን፣
በማሰብ ስር እንፈወስ በሰውነት ፀበል እንዳን፡፡
ከእግዜር ልንወዳጅ ለምህረቱ ጥላ እምባ ብንደግስም፣
ልብን ሳይመልሱ ለንስሃ መሮጥ ከጽድቅ አያደርስም፡፡
ውብ ነገን እናውርስ ትላንትን አክመን በይቅርታ ፀበል፣
ትውልድ ይጨርሳል ያረገዝነው እምባ የቋጠርነው በቀል፣
ከመስጠት አንጉደል ከቀማኞች ገደል ተረግጠን ብንጣል፣
ካሸከሙን በቀል ምናወርሰው ፍቅር ሀገር ይለውጣል፡፡
ከዕድሏ ጣሪያ ላይ ዘር የቀዳደው ሽንቁሯ ቢበዛም፣
ያ ከንቱ ፎካሪ ባፈጀ ቀረርቶ ሺህ ጉራ ቢነዛም፣
ሚሊዮን ዘር ቢሸጥ አንድ ሀገር አይገዛም፡፡
ኢዮጵያዊነት ነው የትርታችን ልክ የነፍሳችን ግጥም፣
መልስ ቤት በራቀው በከረመ ፀሎት ሰርክ ብታንጋጥም
አጎንብሳ ድሃ ባፀናችው ጉልበት ብትረጋገጥም
ነፍሷን አደህይታ ባሻረችው ቁስል ብትገሸለጥም፣
ሀገር ሆና ገዝፋ በየ ጎጣጎጡ አትርመጠመጥም፡፡
የዘመን እውነት ነን ከደግነት ሰማይ በጥበብ የኖርን፣
ትዕግስትም ልክ አለው ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን፡፡
ማተብ አስሮን እንጂ ተጣልተን እንዳንቀር በክፍፍል ገደል፣
ከሀገር ክብር በልጦ ሞት ብርቃችን አይደል፡፡
ንገሩት ለዛ ሰው ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ ኃይል እንደ ተራራ ገዝፎ ቢከመርም፣
ክንዱን አፈርጥሞ እልፍ የሰገደለት ጀግና ቢሰድርም፣
ዓለም የሞተበት የጠላት ማርከሻ ጦር ቢደረድርም፣
በአንድ ዓይናችን ሰላም በኢትዮጵያችን ክብር አንደራደርም!!!

ተዋህዶአትፈርስም
ድርጅት አይደለም በሰዉ የታነጰ
ፖለቲካም አይደል ዘርን ያጣቀሰ
ሚስጥሩ ፍቅር ነዉ ቃላቶች ማይበቃዉ
እኛን ስለመዉደድ በፍቅር ተስቦ
መስቀል ላይ የወጣዉ
በደም ታንጰናል በማይጠፋ ቀለም
ለኛ ብሎ እርሱ ቢሰቀልም
መሰረቱ እየሱስ ነዉ
ግርግዳዉ ቅዱሳን
ግንቦቹ እኛ ነን የእርሱ ምእመናን
ልንወድቅ አንችልም በእርሱ ፍቅር ጰንተናል
እግዚአብሔርን ይዘን ማንስ ይንደናል
ማሃመዳዊም ሁን ወይም ጆቫዊትነስ
ፕሮቴስታንትም ሁን ወይ ደሞ ካቶሊክ
አለቱን ላታፈርስ የሰዉ ደም አታፍስስ
ምንጩንም ላታደርቅ ከመቅደሱ እራቅ
ካህኑ ቢታረድ መቅደሱ ቢቃጠል
እንበዛለን እንጂ የለም የሚጎድል
ስንሞት እንበዛለን
መከራዉ ሲበዛ በፍቅር እንጰናለን
በእሳት ስንቃጠል እንለመልማለን
ከማይደክም አባት ተፈጥረናልና
አርዮስ አትልፋ እንላለን ቀና
ሰልፉ የእኛ ነዉ ድልም የኛ ብቻ
እንደ አሸዋ የበዛን እስካለም ዳርቻ
ካህኑን ግደሉ መቅደሱን አቃጥሉ
ቅጥሩንም አፍርሱ ልጆቹን በትኑ
እናንተ ስትጠፉ እነሱ ቀና ብለዉ
ባባታቸዉ እቤት ይሰበሰባሉ
ይህ ነዉ ክርስትና የማይጠፋ ቀለም
በፍጱም ማይጨልም ሁሌ ሚሰጥ ብርሃን
እናማ አርዮስ ቁርጥህን እወቀዉ
ድል ላታደርግ እንደዉ ነብስህን አታስጨንቀዉ
ሃሰት እዉነትን እስኪ የቱጋር ነዉ አሸንፎየሚያቀዉ
ባንድነት ተነሱ የእምነትን ሰይፍ ያዙ
በፍቅር ማርኩና የዲያቢሎስን
በእምነታችሁ ናዱ
በእምነት እንሞላ በጱናት እንቁም
በተስፋ እንዉጣ
ጠላት አፍሮ እንዲቀር መድረሻ እንዲያጣ
የጦር እቃችሁን ልበሱ እንደ ካባ
ዘመቻዉን አጵኑት ቅድስት ምድር
አርዮስ ሳይገባ
የጦርሰልፍ አንሻም ቀስት አንወረዉርም
ደም እያፈሰስን እርሱ የፈጠረዉን እኛ አንገድልም
ቀስትና ጦር ይዘን አንወጣም ዘመቻ
ጠጠርም አንለቅምም አሳዳጁን መምቻ

የአምላክ መገኛ
አንድ እለት አንድ ወጣት
አንድን የበቁ አባት
በማለት ጠየቀ በጣም ፈልጋለሁ አምላኬን ለማየት
ከልብህ ከፈለክ አምላክን ለማግኘት
ልምራህ ወዳለበት ተነስ ተከተለኝ
ታዲያ ግን አደራ ልመለስ አትበለኝ
አምላክን ለማየት ከልብህ ከፈለግክ
እርሱ ወዳለበት ስንሄድ ታየዋለክ
ካሉት በኋላማ ተነሱ በአንድነት ወደ አምላክ ሊሄዱ
ከጠበቀው በላይ ሩቅ ሲሆንበት ወጣቱ መንገዱ
እስኬት ነዉ ምንሄደው አምላክ የት ነው ያለው
እርሱ አምላክ ሳለ በዚህ በበረሃ ለምን ነው ሚኖረው
እኔ ግን አባቴ ልሞት ነው ደክሞኛል
ከምነግሮት በላይ ጉሮሮዬ ደርቋል
አባቴ ይንገሩኝ አምላክ የት ይገኛል
እኔስ ሄድኩ እንበል እርሱ ግን ያውቀኛል
አሁን ተቃርበናል ልንደርስ ነው አምላክ ጋ
እዚሁ ጠብቀኝ እኔ ግን ልሄድ ነው ሚጠጣ ፍለጋ
አሉትና እኚያ አባት ፈጥነው ተራመዱ
ወጣቱም በድካም ተንጋሎ አያቸው በፍጥነት ሲሄዱ
እራሱን ጠየቀ እጅጉን ተገርሞ
እኚህ አባት ጥንካሬያቸውን ኬት አመጡት ደግሞ
እኚያ አባት ሄደው ትንሽ እንደቆዩ
ወጣቱ ዞረበት ምድርና ሰማዩ
አምላኬን ሳላየው ልሞት ይሆን እንዴ
ምነው ግን ቢያቆየኝ እስካገኘው አንዴ
ብሎ ሳይጨርሰው እዚያው ራሱን ሳተ ተንጋሎ ሜዳ ላይ
ልክ እንደ ነቃ ዙሪያ ገባውን ሲያይ
እኚያ አባት ተቀምጠው ይፀልዩ ነበር
እሱም ቀና ብሎ የሚፀልዩትን ይሰማቸው ጀመር
ይስሙኝማ አባቴ
አምላኬን አየሁት ለዚያውም ሁለቴ
ወዴት አገኘኸው እንዴትስ ለየኸው
ባገኘኸው ጊዜስ ምንድን ነበር ያልከው
እኔ ወጣት ሆኜ በድካም ስሰቃይ
እርሶ ግን ሸምግለው ጥንካሬዎትን ሳይ
ያን ጊዜ አየሁት አምላኬን በእርሶ ላይ
ውሃ ጠምቶኝ ደክሞኝ ህሊናዬን ስቼ
ስነቃ ለየሁት ፀሎቶን ሰምቼ
በል አድምጠኝ ልጄ ታዲያ አሁንስ ገባህ
አምላክ ሁሌም አለ በዙሪያ በደጅህ
ይገለፅልህ ዘንድ
የትም ሳትሰደድ
በተስፋ ጠብቀው ልቦናህን ከፍተህ
ይህንን ስትፈፅም ያኔ ታየዋለህ

የህይወት መድሀኒት "


፠፠፠
እንካ እየተባለክ፡የህይወት መድሀኒት:
ምነው መቀለድህ: ጌታህ አዘጋጅቶት
ተቀበለው እንጅ:ምነው ማቅማማት

የዘላለም ህይወት፡ አትፈልግም እንዴ?


ሁሌም ዝግጁ ነው፡ ተቀበል ዘመዴ
ና ቅረብ ወንድሜ: መራቅ ምን ያደርጋል?
ከሰዎች ለይቶ: ህይወትን ያመራል

አስብ!
እስኪ ልጠይቅህ?

መድሀኒት ያለው፡ ቢኖር አንድ ዶክተር


ክትባት ልስጥ ቢል ፡በደስታ ዘላለም የሚያኖር
እርሱን ስለማግኘት: አትታገልምን?
በስንት ወርቅ በስንት ብር ፡ትለውጠው ይሆን?

አሀቲ ቃል ተበቅዑ ፡ይሄውልህ ውዴ


ራስክን አረጋግተህ፡ ይችን ስማኝ አንዴ

(የአንድ ደቂቃ ጥሞና)

በነፃ ሰጥቶሀል፡ አርብ ላይ ተሰቅሎ


ለአለም ቤዛ ሆኗል፡ ብሉኝ ጠጡኝ ብሎ
ራስክን አንፃና፡ ነገ ዛሬ ሳትል
የህይወት መድሀኒትን፡ በክብር ተቀበል፡፡

እናማ ወንድሜ ፡ራስክን አዘጋጅተክ


ከአለም ሰው ሁሉ፡ መርጦህ ከተቀበልክ

መንፈስ ቅዱስ ቀርቦህ


ፀጋው ሁሉ ከቦህ
ዲያቢሎስ ተጨንቆ
ከዙሪያህ ርቆ

ፀሎትህ ደርሶልህ፡ ያልከውን አግኝተህ


በድል ትኖራለህ፡ አክሊል ተቀዳጅተህ፡፡

አይጣል ነው አይድረስ "


'
፠ ፠፠
አይጣል ነው፡ አይድረስ
ሰማይ አይታረስ ፡ንጉስ አይከሰስ

የሞት ነገር መቸም ፡ አይሆንልን ዛሬም


ስሙ ሲነሳብን ፡ይቀፈናል ሁሌም፡፡

በዚህ እስካለ፡ ህይወት


ሞትም ፡ከጎኑ ናት፡፡
(ምንም ማድረግ አይቻልም)

"አሁን ብትሞትስ!"ስልህ፡ ምሳሌ ስሰጥህ


ትሰድበኝ ይሆናል፡ "አንት ሟርተኛ"ብለህ
በርግጥም ያስፈራል ፡ወዳላዩት መሄድ
መቸም ቁርጥ ካልሆነ ፡እኔም እንዲዚያ አልወድ፡፡

ምን እናድርግ ?
በተፈጥሮ ህግ!

አይጣል ነው አይድረስ...

ነፍስህ ፡ባንተ አይደለች


በፈጣሪ እጅ ነው፡የተያዘች ያለች
በቤት ውስጥም ሳለህ ፡በመንገድ ጎዳና
በእግርም እየሄድክ፡በአየር መኪና
ልትሞት ትችላለህ ፡አለም ላይ ናትና፡፡

ድንገተኛ አደጋ ፡ምንኛ ሀያል ነው


እዚሁ ከጎናችን ፡በሰፈር ነው ያለው ፡፡
ሀገር ሰላም ብሎ፡ ሰው ከቤቱ ወጦ፣
ከጓደኞቹ ጋ ፡በስርዓት ተቀምጦ፣
የቆመ ግንድ ወድቆ፣
ተባራሪ ጥይት፡ ሌላን ሁሉ ትቶ፣
ሊገድልህ ይችላል ፡አንተኑ ለይቶ፡፡
ምን ይመጣል ብለህ፡ቤትም ብትቀመጥ
ልትሞት ትችላለህ፡በመሬት መንቀጥቀጥ፡፡

(ምን ይታወቃል እያየን ነው)

አይጣል ነው አይድረስ...

ይሄ ሞት የሚሉት ፡ምንም ምርጫ አያውቅም፣


ህፃን ሽማግሌ ፡ሴት ወንድ አይለይም፣
ቀጭኑ ወፍራሙንም፡ ረዥሙ አጭሩን
አያውቅም መሰለኝ፡ በያይነት መኖሩን፡፡

(አይመርጤ አሉ)

ብዙዎች ነጎዱ፡ ሳያውቁ ሳይነቁ


እምነት ምን እንደሆን፡ ቅኔ ሰሙ ወርቁ

ቢደርስም ባይደርስም፡ ሁሌ ተዘጋጁ


ሊመጣ ይችላል፡ ሊወስድ ነፍሱን በጁ፣
ይሄኔ ነቃ በል፡ ነጋሪት ሳይጎሰም ሳይነገር አዋጁ፡፡

እና በል ወዳጄ ፡እችን ያዝ እንግዲህ፣


አንድ ቀን ብለይህ፣
ምንም እንዳይመስልህ፣
አይመርጤ አይመርጥልህ!
እውነቴን ስነግርህ!

በል በል አንተ ወዳጄ፣ ጊዜ አትውሰድብኝ


አንዳንድ ስራ ልስራ፣ ሳይወሰንብኝ
መቸም አይቆጨኝም፣ ዝግጁ ከሆንኩኝ፡፡

አይጣል ነው አይድረስ
ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ።

ቸሩ መድህንዓለም ክርስቶስ ለንስሀ ሞት ያብቃን!!! አሜን


ስብሀት ለእግዚአብሔር፡፡
የጅራፍ ንቅሳት
(ኤፍሬምስዩም)
=====//=====
ከጀርባህላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደድህ የዘላለም ምትራት
የፋሬስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ
የጲላጦስ ግርፊያ የሄሮድስ ካባ
ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍ እና እንባ
ላንተ ስቃይ ናቸው ለእኛ ግን ደስታ
መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ
ጅራፍ እና ቡጢ ምራቅና ሃሞት
ለአይን ደስ የማይል የስቃይ ደምግባት
በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
እኒህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
የመዳን አለኝታ የዘላለም ምትራት
ውዴን ያላያችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
ምራቅ ተቀብቷል
ቡጢ ተቀብሏል
ኃጢዓት ተሸክሟል
በቁንዳለው መሃል የደም ጎርፍ ይፈሳል
የፍቅር ንጉስ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ያልሰማችሁ
ፍቅሩን ልንገራችሁ
ዐይኑ ፍቅር ያለቅሳል
ጎኑ ደም ይረጫል
ፅህሙ ተነጭቷል
ልብሱ ሜዳ ወድቋል
በቃሉ ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል
ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለእሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም
ስለሰው መድከሙም ኃይሉን አያወርድም
ስሙ እግዚአብሔር ነው
ስሙ ይቅርታ ነው
ስሙ መሀሪ ነው
የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል
ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል
በ'ሱ ስም ይወድቃል በስሙ ይጣላል
ስሙ ሁሉን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ
ታላቁን የሚጥል ለታናሽ ተዋጊ
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለርሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
እናም ጌታችን ሆይ...
ያመኑትይፅናኑ የወጉህም ይዩህ
በደም የተረጩ ልብሶችህን ለብሰህ
አሜን ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሰህ።

የፀሐይ የእሳት ቀለበት ሥነ ሥርዓት ]


(በመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ለፀሐይ የተጻፈ ግጥም)
በሠኔ ተቃጥረው ኢትዮጵያና ፀሐይ፤
ቀለበት ለማሰር ደስ በሚል ሰማይ።
በፍቅር ሊጓዙ ደግሞም ላይከዳዱ፤
በላሊበላ ላይ ተተከለ ዐምዱ።
ምስክር ለመሆን ሠርጉን ለመታደም፤
ጋበዘችን ፀሐይ የብርሃን ዓለም።
ውለታ ሳትረሣ የካሲዮፕያን፤
ደግሞም የሴፌውስ የነአንድሮሜዳን።
ልታሣየን ክስተት ባለንበት ዘመን፤
ከዓመታት በፊት ተመካክረን ነበር።
በጠፈር የሚሆን ውበቷን ለማየት፤
ወደ ላሊበላ ተጓዝን በአንድነት።
በዚያም እንደደረስን ያየነውን ምስጢር፤
መዝግበን አኖርነው በተገቢው ክብር።
የላሊበላ ጥበብ የሥነ ፈለክም ቁልፎቹ ያሉበት፤
ደሞም ያ ሰሌዳ የሰማይ ሥርዓት የተቀረጸበት፤
በክብር ተቀምጧል ትውልዱ በምስጢር እንዲራቀቅበት።
ደግሞም እስከ ጣሊያን በሚወስደው መንገድ ተገኝቼ በአካል፤
ትክክል መሆኑን በማረጋገጤ የሳይንቲስቶችን ቃል፤
ቤተ ጊዮርጊስ ለካ ምስጢራዊ ነበር የማይገለጽ በቃል።
ሠኔ 12 በቅዱስ ላሊበላ በዕረፍቱ በዓል፤
ገድሉን በመተርጎም ደግሞም በማገልገል፤
ተሳትፌ ዋልኩኝ በረከትን በአካል።
ሠኔ 14 ት መጣ የቀጠሮ ዕለት፤
ሊደገስ ድግሱ በሰማይ ሰገነት።
የአጥቢያ ኮከብ ቬኑስ የጠፈር እንክብል፤
ፀሐይን በመቅደም የጠፈሯን አክሊል፤
ደምቃ ትታይ ነበር በምሥራቁ በኩል።
ቀዝቀዝ ባለው ሌሊት ነፋስ በበዛበት፤
የሰማይ ከዋክብት በዝተው በታዩበት፤
ተራራ ላይ ወጣን ውበትን ለማየት፤
ፀሐይ ቀለበቷን በውል ልታስርበት።
12:10 ላይ ኦርያሬስ ወጣች ደግሞም ቶማስስ፤
ፀሐይ ጀምበራችን ልትኩነሰነስ።
ውበቷ ፈንጥቆ እንዲያ ስትታይ፤
መመሰጥ ጀመርኩኝ በደማቁ ሰማይ።
ለግርዶሽ ለጥሎሽ 12:45 ላይ ጨረቃ ብቅ አለች፤
ብናሴና ኤራዕ ተብላ የተሠየመች።
ሙሽራን መጋረድ ደግሞም መሸፋፈን፤
ወግ ነውና ይኼ ለባህል መታመን።
ጨረቃ ናትና የደማቋ ፀሐይ ዋና ፕሮቶኮል፤
መጋረድ ጀመረች የፀሐይን ክፍል።
የፀሐይን ውበት ደግሞም ዘውድ አክሊሏን፤
ሰንፔር የመሰለ ደማቅ ቀለበቷን።
የሙሽራ ልብሷን ንጹሕ ብርሃኗን፤
ለማየትም ጓጓሁ ያንን ውብ አካሏን።
ሚዜዎቿ መጡ ሁለቱ ፕላኔት፤
ከግራና ከቀኝ አጅበዋት ድንገት።
ተገለጡ ዛሬ በውበት በድምቀት፤
ሜርኩሪና ቬኑስ ለሠርጓ ሥርዐት።
ለሙሽሪት ፀሐይ ለሠርጓ ድግስ፤
ሳተርን፣ ጁፒተርም ደግሞም ቀይዋ ማርስ፤
በክብር እንግድነት ሰመር ሶልስቲስ፤
ጋላክቲክ አላይመንት ሠራ ስካይ ክሮስ።
ትንፋሼ ጨመረ የልቤም ትርታ፤
ተሠርቶም አያቅም እንዲህ ያለ ምስጢር በሰማይ ላይ ካርታ።
በስቶንሄንጅ፣ በጊዛ፣ በማያ ቀመር ላይ፤
የሠኔ 14 ቱ የ 2012 ትም መሠራቱንም ሳይ፤
በአድናቆት በፍርሃት ተዋጥኩኝ በሰማይ።
2 ሰዓት ሆነ ጊዜውም ደረሰ፤
ሰማይ በሮዝ ቀለም ውበት አፈሰሰ።
ለአቀባበሏ አምላክ ለፈጠራት ለዚች ውብ ፍጥረት፤
ለሙሽሪት ፀሐይ ለሠርጓ ዕለት፤
ሁሉም ሰልፉን ሠራ ደምቆ በማብራት።
ብቅ አለች ቶማስስ ዘውዷን ተቀዳጅታ፤
እሳት ቀለበቷን በሰማይ አብርታ።
እልልታው ጩኸቱ ከምድር አስተጋባ፤
ኃይሎጋው ከጠፈር ደምቆ እየገባ።
ድግሱ ቀጠለ ጫጫታው በረታ፤
የአድናቆትን ጮቤ በእግሩ እየመታ።
በሰማይ ላይ ድግስ በዚች ውብ ዕለት፤
የወደፊት ምስጢር ተቀመረባት፤
ያስተዋለ ብቻ ያውቀዋል ድንገት።
3:15 ላይ የሠርጓን ሥርዓት በማጠናቀቅ፤
ለጫጉላ ሽርሽር ጉዞ አደረገች ወደ ሩቅ ምሥራቅ።
እንደዚህ የደመቀ የሠርጓን ሥርዓት አይቼ በዐይኔ፤
ኬክሮሷን ለማወቅ አደረብኝ ወኔ።
ቀጠሮ ያከበረች ሙሽሪት ፀሐይ፤
ንፍገት የለምና በፈለክ ሰማይ።
ኬክሮስ ኬንትሮሷን ጥንተ ኦንን ብመኝ የፀሐይን ሥርዓት፤
ውበቷ ታይቶኝ በሠኔ 14 በሙሽሪት ቀኗ ሰንፔር ቀለበት።

ይኸው ዛሬም አለ

*
*
አምላኬ አምላኬ!
ተመስገን ጌታዬ ለዚ ላደረስከኝ
በህይወት አኑረህ ዛሬን ላሳየኸኝ
ላልተውከኝ እንዲሁ ምግባሬን አስበህ
ከ ሀፅያቴ ብዛት በኔ ተስፍ ቆርጠህ!።

እኔማ እኔማ!
ምግባረ ከንቱ ነኝ ስሜም አመንዝራ
በሞት አደባባይ ለሞት የምሰራ
ባዶ ነው ኑሮዬ ታሪክ ነው ህይወቴ
ሳልቀበር የሞትኩ ሳልሞት አስቀድሜ
ሻማ የሚበራልኝ በመቃብሬ ላይ ሊከበር ልደቴ!
ኖሬ ማላውቅ አኔ ልታሰብ በሞቴ!!።

ግን ግን አምላኬ ግን!
ይኸው ዛሬም አለ....ልጄ ሆይ እያለ!
ለሀጥአን ነዉ እንጂ ለፃድቃን ያይደለ
ያ የደም መስዋት ላንቺ የተከፈለ
ህይወት አለሽ ልጄ በቃል የታተመ
ነይ ተመለሽ ልጄ...ነይ ወደኔ እያለ!......ይኸው ዛሬም አለ!።

ይኸው ዛሬም አለ....ልጄ ሆይ አያለ!


ተስፋ ላይቆርጥብኝ በራሱ እየማለ
ነይ ወደ አባትሽ ቤት ተመለሸ ወደኔ
ላንቺ ከሰጠሁሽ ከስጋ እና ደሜ
ያዘጋጀሁልሽ የዘላለም ህይወት በዚያ አለ እያለ
..................ይኸው ዛሬም አለ!።

ይኸው ዛሬም አለ!...አሳዝኜው ሳለ!


ይሰማኛል ድምፁ ከበስተሇላዬ ልጄ ሆይ እያለ!
መልካሙ እረኛ የጠፋሁት እኔን እየተከተለ
ፈፅሞ ላይተወኝ በራሱ እየማለ
እጆቹን ዘርግቶ በፍቅር አንደበት ነይ ወደኔ እያለ!
...................ይኸው ዛሬም አለ!።

ይኸው ዛሬም አለ!.....ልጄ ሆይ እያለ!


በሀፅያት ወድቄ በሀጥያት ስዳክር
ህይወት ጨልማብኝ መሄጃ ሲጠፍኝ አዝኖ እያስተዋለ
እኔነቴ ጠፍቶኝ ማንነት አጥቼ እንዲሁ ስባዝን
ውስጤ ተስፋ አቶ የኑሮዬ ክብደት አስጨንቆኝ ሳለ
የካድኩት አባቴ! ዛሬም ከኔ ጋር ነው...ልጄ ሆይ እያለ!

ይኸው ዛሬም አለ!...


በድዬው እያለ ስለኔ ተጨንቆ ልቡ እየቆሰለ
ይሰማኛል ድምፁ ከበስተሇላዬ እየተከተለ
ሸክሜን አውርዶ በፍቅር ሊሸከም ነይ ወደኔ እያለ!
ልጄ ሆይ!...ልጄ ሆይ!...ልጄ ሆይ! ይለኛል በራሱ እየማለ
ይኸው ዛሬም አለ!...ይኸው ዛሬም አለ!...ልጄ ሆይ እያለ!!!
ይመስገን አምላኬ!..ሩህሩሁ አባቴ ከኔጋ ስላለ!!!
 ፌቨን ሰለሞን

You might also like