Professional Documents
Culture Documents
ከራፋቶኤል ወርቁ
በዓለማችን በተለይም በሀገራችን ኢትዮጵያ የተደበቀ ሰውር ተሰጥኦ እና ጥበብ ያላቸውን ሰዎች በጅምላ አጸያፊ ስም
በመስጠት የሃበሻ ኮተት ጥንቆላ ወዘተ እያልን እያጣጣልናቸው እነርሱም ሆነ የስራዎቻቸውን ውጤቶች ከማህበረሰቡ
በማግለል ጠቢባን በጥበባቸው እራሳቸውንና ሀገራቸውን ሳይጠቅሙ ባዕዳንን በየዘርፉ እየጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ እዚህ ጋር
አበክሬ ላስገነዝበው የምፈልገው ጉዳይ ይህ ስውር መንፋሳዊ ጥበብ በሁለት መልኩ ለይተን ማየት ይገባናል፡፡ የመጀመርያው
ከፈጣሪ የተለገሰን በተፈጥሮና በመንፈሳዊ ብቃት የምናገኘው መንፈሳዊ ፀጋና ጥበብ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ለስጋዊ ድሎት
በራስ ወዳድነት ሰይጣናዊ ከሆኑ ሃይላት ጋር በመተባበር የሚሰራ ምትሃት ወይም በሀገርኛው አባባል ጥንቆላ ነው፡፡
ታዲያ ከላይ የጠቀስነው መንፈሳዊ የነጠረ የነጠቀ ከስነ ልቦና ሳይንስና ከሌሎች የሳይኪክ ዘርፎች ቀድሞ የተገኘው ስውር
መንፈሳዊ ጥበባት የሀገራችን በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሀብትና ጥበብ ነው፡፡ ነገር ግን
በእጅ የያዙት ወርቅ እንዲሉ ባለን ሀብትና ጥበብ ሳንጠቀምበት ቀርተን በተጨባጩ በሳይንሳዊ መንገድ ብቻ ነው የሚያምኑት
ብለን የምንደሰኩርላቸው ነጮች ከሀገራችን በበዘበዙት መንፈሳዊ ጥበብ በመጠቀም ከቴክኖሎጂው ጫፍ ለመድረስ በቅተዋል
፡፡
ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ይህ መንፈሳዊ ጥበብ የተገለጹባቸውን የጥበብ መጻህፍት ሰርቀው በማሰረቅና በማስተርጎም
ከሳይንሱ ጋር በማጣመር ፓራ ሳይኮሎጂ የሚባል የትምህርት ተም በማም በትላልቅ የዓለማችን ዩንቨርስቲዎችና
ሌሎች ተማት ውስጥ እያጠኑትና እየተመራመሩበት ይገኛል፡፡
ቢሆንም ግን ይህ መንፈሳዊ ጥበብ በነጮቹ አጠራር በሳይኪክ ፎርሙላ ወይም በላብራቶሪ ውስጥ የሚገኝ ባለመሆኑ ነጮች
በጥበቡ መገረምንና የሩቅ ታዛቢ ሆነው መገኘታቸው የሚካድ አይደለም ቢሆንም ግን በተወሰነ መልኩ ተጠቃሚ
መሆናቸውን የማንክደው ሀቅ ነው፡፡
በዚህ ጽሁፍ ማሳየት የምፈልገው ቁም ነገር አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በዚሁ የጥበብ ዘርፍ ለረጅም ጊዜ በላብራቶሪ
ውስጥ እና በትላልቅ የምርምር ተማት ጥናትና ምርምር አድርገው ያልደረሱበትን ውጤት ከሺህ ዓመታት በፊት ግን
የኢትዮጵያ አባቶች ከማወቅም አልፈው ለዚህ ዘመን እንዴት ማድረስ እንደቻሉ ከማስረጃ ጋር ለማሳየት እሞክራለሁ ለዚህም
ይረዳኝ ዘንድ የነርሱን የጥናት ግኝቶች በማብራራት እጀምራለሁ፡፡
ሌላው ደግሞ የሰው ልጅ በተፈጥሮው ሊያየውና ሊሰማው ከሚችልበት ወሰን በማለፍ ያለምንም አጋዥ የቴክኖሎጂ
መሳሪያዎች እርዳታ ማንኛውንም ክስተት ማወቅና መረዳት የሚያስችለው ተሰጥኦ ደግሞ ክሊርቪዮናስ በመባል ይታወቃል፡፡
ፓራ ሳይኮሎጂ ደግሞ መንፈሳዊ የሳይኪክ ክስተቶችን በሳይንሳዊ መንገድ የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡
ስድስተኛ የስሜት ህዋስ ወይም የቴሌፓቲ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ሌሎች ሰዎች ምን እንደሚያሰቡ እንዲሁም ወደፊት ሊሆን
የሚችለውን ነገር አስቀድሞ መረዳትና ማወቅ የሚችሉ ሰዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ሰዎች እነርሱ በማያውቁት ሁኔታ
ከሌላው ሰው በተለየ መልኩ ድምጾችን መስማትና እንዲሁ ሌሎች ማየት የማይችሉትን ማየት የሚያስችል ተሰጥኦ አላቸው፡፡
ታዲያ በዚህ የሳይኪክ ምንነት ዙሪያ በሳንፎርድ እና በሃርቫርድ እና በሌሎች ዩንቨርስቲዎች ውስጥ በሰፊው ምርምር
የተደረገበት እና እየተደረገበት የሚገኝ ሲሆን የመጀመርያው የሳይኪክ ዩንቨርስቲም በ 1996 ዓ/ም በአሜሪካን ፓራሳይኮሎጂ
ዲፓርትመንት ኦፍ ሳይኪክ በሚል ስያሜ በቨርጂንያ ዩንቨርስቲ በዶክተር አየን ስቴቬንሰን አማካኝነት ተቁሙዋል፡፡
በ 1882 ዓ/ም ፍሬድሪክ ሜየር የተባለ ግለሰብ በእንግሊዝ ውስጥ የሳይኪክ ማህበር እንዲም ከፍተኛ ጥረት በማደረግ
ተሙን መስርቷል፡፡ ይህ የጥናት ማዕከል በዋነኝነት በድንገት ስለሚከሰቱ ነገሮች መንፈሳዊ ስለሆኑ መላምቶች እና ስለዚህ
ስለ ቴሌፓቲ ተሰጥኦ ምንጭ እንዲሁም ስለሌሎች ተጉዋዳኝ ነገሮች መረጃዎችን በመሰብሰብ ለበርካታ ዘመናት ሲያጠና የቆየ
ቢሆንም ውጤታማ ግን አልነበረም ምክንያቱ ደግሞ የሳይኪክ ጥበብን ምንጭ እና መገኛ ላይ መድረስ አለመቻላቸው ነበር፡፡
በ 1898 በፈረንጆቹ አቆጣጠር ቲታኒክ የተባለችዋ ግዙፍ መርከብ ተገንብታ ለጎዞ ከመዘጋጀትዋ ከ 14 ዓመት ቀድም ብሎ
ሞርጋን ሮበርትሰን የተባለ የረጅም ልቦለድ ጸሃፊ ዘሬክ ኦፍ ቲታኒክ በሚል ርዕስ መጽሃፍ አሳትሞ ነበር ፡፡ በመጽሃፉ
የተቀነባበረው ትረካ የገጸ ባህሪያቱ አሳሳል የታሪኩ ሂደትና አጨራረስ በእውነት ከተሰራችው ቲታኒክ መርከብ ጋር በመቶ
ዘጠና ዘጠኙ አንድ አይነት ታሪክ ነበር፡፡ ሌላው አስደናቂ ነገር የመጽሃፉ ቲታኒክ እና እውነተኛዋ ቲታኒክ በባህር ላይ
የሚንሳፈፍ በረዶ ገጭተው የሰጠሙ ሲሆን የመርከብዋ ፍጥነት መጠን የህይወት ማዳኛ ጀልባዎች ብዛት የተሳፋሪዎች ሸክምና
መጠን ከመጽሃፉ ጋር መመሳሰሉ ነበር፡፡
ታዲያ እንደ ቴሌፓቲ ሁሉ ይህ አስቀድሞ የመተንበይ ተሰጥዖም ለፓራሳይኮሎጂስቶች እንቆቅልሽ እንደሆነ ቀርቷል፡፡
ለበርካታ ዘመናት በዘርፉ ጥናትና ምርምር ቢያደርጉም የዚህ ተሰጥኦ ባለቤቶች እንዴት የዚህ ይህን ተሰጥኦ ባለቤት መሆን
እንደቻሉ ተጨባጭ የሆነ ሳይንሳዊ ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም፡፡
የኛ ኢትዮጵያውያን አባቶች ግን የዚህን ተሰጥኦ ምንጭ ከማወቅም አልፎ እንዴት ከትውልድ ትውልድ ማስተላለፍ እንደቻሉ
በሚቀጥለው ክፍል እንመለከታለን፡፡
More Articles...