Professional Documents
Culture Documents
Tnbit4 PDF
Tnbit4 PDF
መልዕክት ሦስት
በምድሪቱ ሁሉ ላለህ የሰው ዘር በሙሉ
ተጻፈ በመጋቢት 19 ቀን 2001 ዓ.ም
ይህ መልዕክት የመጨረሻ የአፈጻጸም ውሳኔ ሲሆን የመጀመሪያውንና
የሁለተኛውን መልዕክት ወደ አፈጻጸም የሚቀይር ውሳኔ ነው።
ማስታወሻ
ከፈጣሪየም የተማርኩት ትምክህትን አርቆ ትህትናን መልበስን መልካም ስለሆነ ነው እንጂ ለነገርም ሊታሰብ
የማይችል ስጦታውን ጌታ ለእኔ ለትንሹ ባርያው ሰጥቷአል።ትምክህት ከጨለማ ስለሆነ በመመካት አልናገርም
መግለፅ ግድ ካልሆነብኝ በቀር። የሰው ዘር አድምጥ መሪዎችህ ገዥዎችህ በከፍታ ላይ አቁመህ የምታያቸው
የምትንቀጠቀጥላቸው ጣዖቶችህ ክቡር እከሌ፣አዋቂው ፣ባለሙያው ፣ሊቃውንቱ ፣የጦር ባለሙያው፣ኢኮኖሚስቱ፣
ባለሃብቱ፣ቢሊኒየሩ፣ኢንደስትርያሊስቱ፣ የህክምና ጠበብቱ ፣መሃንዲሱ፣ የአየር ንብረት አዋቂው፣ የጦር አለቃው፣
ተመራማሪው ፣የፖለቲካ ሳይንቲስቱ፣ ኧረ ምኑ ተቆጥሮ የሊቁ፣ የአባይ ጠንቋዩ ፣የጦር ኤክስፐርት ወዘተ እኒህ
ሁሉ ምን ፈየዱ? ምንስ ለወጡ? ምንስ አመጡልህ? በየአገሩ ህዝባቸውን በመግዛት፣ በማስጨነቅ ፣ ወደ ጥፋት
በመንዳት ላይ ያሉ ከመንደር እስከ አገር፣ ክፍለ አህጉር የተኮለኮሉ ገዥዎች መቼ ጊዜ ለፈጣሪ ትዕዛዝ ጀሮ ሲሰጡ
ታየ? የእነሱ ጥፋት ምድርን ሸፍኖ ሰማይን አዳርሷል። የዘመኑን ፊደል ቆጠሩ ሁሉን አዋቂ ሆኑ ። ሰርቆ፣ ነጥቆ ፣
ገሎ፣ አመንዜሮ፣ ዋሽቶ ፣ አታሎ በየትኛውም ቀን ተሰማርቶ ገንዘብን ሰብስቦ ህዝብን አስጨንቆ መኖሩ
ህልማቸውና ደስታቸው ከሆነ ዘመናት አለፈም ተቆጠሩም።
በወቀሳ ፣በማስተማር በመገሰፅ በመለስተኛ ቅጣት መፍታት ቢቻል ኖሮ 7500 ዘመን ሙሉ ጌታ ያለመታከት
በትዕግስት ሸፍኖታል። የሚያዳምጥ ጠፋ እንጂ !
ጊዜን በሰጡ ፣ምክርን በለገሱ የጥፋትንም ስፋት ባሳወቁ ፍርዱንና ፍፃሜውን በገለፁት ሁለት የጌታ መልእክቶች
ማን ተጠቀመ። መጭውን አስከፊ ጠረጋና የከፋ አደጋ ለሰው ሁለ በመግለፅ በኩል በሃገሬ ብዙ ባሕታውያን
መመህራን ከጌታ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ በመቀበል ለማዳረስ ጥረዋል እስከ ህይወት ዋጋም ከፍለዋል። ግን ማን
አስተዋለ? ማንም ተሳለቀ እንጂ
በእኔ በባርያው የአስተላለፈውን የፍጻሜ መልእክት ማንን አስደነገጠ ? በተለይ በትዕቢት በማን አለብኝነት
በአውቃለሁ ባይነት የተወጠሩ የየአገሩ መሪዎች መቼስ ደነገጡ ?
በህዳር 7/1998 እና ግንቦት 27 /2000 የተገለጹት መልእክቶች በሕዝብም በመሪዎችም በተለያየ ባህል፣ እምነት፣
የአገዛዝ ስርዓት ውስጥ ያለ ሁሉ እንዴት ተመለከቱት እንዴትስ አስተናገደት እንየው አራት አይነት ሰዎች
ተከስተዋል። ከእነዙህ ከአራቱ አይነቶች የሚዘል አልነበረም አይኖርምም ይህንን በዝርዝር መግለጫ ውስጥ
የምታዩት ይሆናል።
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 7 ፣ 27-28
የአዳም ልጅ እንግዲህ ገላጋይ ወደሌለበት ወደ ብርቱ የቅጣት መእበል እየተንደረደርክ ነው። ፍጠን አምልጥ፣
ተባልክ ተነገርክ፣ተመከርክ ተዘከርክ፣ ትዕቢትህ የበዛ ነውና መልሰህ ንቀት ትችት በመልእክቱ ከመጠቀም ይልቅ
ስለ መልእክቱ አድርሻ ማንነት ለማወቅ ደከምክ ። አይ የሰው ልጅ ምክንያትህ ምክንያትን እየወለደ ፣ሰበብህ
ሰብብን እየፈጠረ ልትጠቀምበት ይገባህ የነበረውን ቀናቶችና ወራቶች በከንቱ አሳለፈክ። ጥቂቶች ግን ተጠቀሙበት
ወደ ፈጣሪያቸው ጉያ ገቡ ተሸሸጉ። ቅጥራቸውን አጠበቁ አንተስ? በምን ላይ አረፍክ ? አዝናለሁ ጊዛህ አበቃ!
የተከፈተው በር ተዘጋ ! ተከረቸመ ዛሬ በአለም ላይ የሚታየው የቀውስ አይነት ፣የተፈጠሮ አደጋ ብዛት የሕዝብ
ግጭት የአገሮች አለመስማማት የታላላቅ መንግስታቶች ወደ አዘቅት የመውደቅና የመጥፋት ጉዞ ጀምሮ ከ2000
ዓ.ም ማለቂያ ከነኀሴ መጨረሻ ላይ ከዋናው አምላካችሁና ጣዖታችሁ ከአሜሪካ(ባቢልን) በገንዘብ ቀውስ የጀመረ
ሲሆን አድማሱን በማስፋት የኢኮኖሚ መቅለጥ ፣የኢኮኖሚ ቀውስ ወደ ማህበራዊ ቀውስ እየዘለቀ ይገኛል ።
ተስማምቶ የሚፈታ ታቅዶና ተተልሞ የሚተገበር ነገር ከእንግዱህ የማይታይበት ወደ ጨለማ መገስገስ
ተጀምሯል። ሁለንም አዳርሰዋል ይቀጥላል በብርቱም ይከፋል።
በመልእክት ቁጥር 2 እንደተገለፀው (በእንግሉዝኛው) የእስትንፋስ ጊዛ አይሰጥም ። የኢኮኖሚ ቀውስ ፣የገንዘብ
ቀውስ፣የኢንደስትሪ ቀወስ፣ስራ ፈቱ በአጠቃላይ በሁለም ዘርፍ ያለ ቀውስ በከፋ ሁኔታ ይጨምራል። መፍትሄም
አጥታችሁ በልዑል ፊት እስክትወድቁና እስክትንበረከኩ ድረስ። የልዑል ቃል ወጣ አይመለስም እንደ ቃለ
ያደርጋል እንጂ በከፍታ ላይ ያለ መንግስታቶች በሰበሰቡት ገንዘብ ፣ወርቅ፣ ታንክ፣ ጀት፣ኒውክሊየር፤የኢንደስትሪ
ብዛት፣ የህንጻ ውበት፣የጀትና የባቡር የመርከብ ግዝፈትና ርቀት በየቀኑ የሚዘቅጠው ነዲጅ( ዘይት) በማዳበሪያ
በጀነቲክ ኢንጂነሪንግ በፈጠሩት የእህል ዘር የሚመኩበት ደሃን በምጽዋት ደልለው የሚገዙበት ዕቅዳቸው የጨለማ
አገዛዛቸውን የጥፋት የምንዝርና የግድያ ህጋቸውን የሚጭኑበት አካሄዴ የሚቀጥል መስሎቸው አምነውበትም
ነበር።
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 24 በሙሉ
ዛሬ ይህን አደጋ ለማጥፋት ምን ዕቅድ ተነደፈ ምንስ እየተዯረገ ነው ብንል ከመንግስት ካዝና ያለውን ከሕዝብ
የተሰበሰበውን ፌደራል የገንዘብ ክምችት ላይ በመቀነስ መደጎምን ተያይዘውታልሌ።
አሜሪካ/ባቢልን/ በቡሽ ዘመን 700 ቢሉዮን ፤
>> >> በኦባማ ዘመን 879 >>
እንግሉዜ /ትንሿ ባቢልን/ 90 >>
ሲንጋፖር 13.3 >>
ጀርመን 470 >>
ቻይና 570 >>
ፈረንሳይ 18 >>
ራሺያ 28 >>
ደ/ኮርያ 30 >>
አውስትራሊያ 14 >>
ካናዳ መጠኑ ያልታወቀ
ስፔን መጠኑ ያልታወቀ
ሌሎችም እንዲሁ ከ 2 እስከ 10 ቢሉዮን
ከማእከላዊ ባንካቸው ፌደራል ሪዘርቭ በማውጣት ደጉመዋል(ቤል አውት )አድርገዋል። በድጎማ በእቅድ በምኞት
የሚቆሙ መስሎአቸው ይደክማሉ። ከንቱዎች በመልእክት 1 ሆነ 2 እንደተገለፀው ሕልማቸው እቅዳቸው ሁሉ
ቅዠት ይሆናል እንጂ የሚለውጠው ነገር የለም። ሞርጌጅ ባንኮች መሸቃቀጫ ገቢያዎች የሚባሉት ሁሉ በታላቅ
ክስረት እየተመቱ ሲሆን ከመንግስት ካዝና የድረሱልኝ ድጋፍና ድጎማ እየተደረገላቸው ነው። ሆኖም አስር ቦታ
እንደተበሳ እንስራ ውሃ በአናቱ ሲገባ ከስር እንደሚያንዠቀዥቀው ተመልሰው እና መላልሰው በማፍሰስና
በመውደቅ ላይ ይገኛሉ። ታላላቅ የመኪና የኤሌክትሮሊክስ የሸቀጥ ኢንዱስቱሪዎቻቸው በመክሰር ሰራተኞቻቸውን
በማባረር ላይ ይገኛሉ። በታንክና በጠመንጃ የማይፈቱት አደጋንና ጅምር እንጂ መቼ ወደ ካፋው ደርሷል። የእኛ
ብልሆች የኋለኛይቱ ዝንጀሮ በፊተኛዋ ትስቃለች ይባላል። እሱ ነው እሱ ነው ይባባላሉ።
ከንቱዎች ከንቱ የሚያደርጋቸውን እርምጃ ጀመሩ እንጂ ገና መቼ ወደ ከፋ ፍጥነት ገቡ ሲፈጥን ያኔ ሲፈጭህ
ታየዋለህ። እስትንፋስህ ሲዘጋ ቱልቱላህ ሁሉ ይቆማል። ኖኅ መርከብን አዘጋጀ እንደታዘዘው ለዘርና
ለምህረት የታሰቡትን ሰበሰበ እሱም ቤተሰቡም ተጠቃሎ ወደ መዳኛው በእግዚአብሔር እጅ ተጠለሉ።
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 8፣9-10
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 7 ፣13-16
ከአለቃ እስከ ምንዝር በእኔ ላይ በጓደኞቼ ላይ የጥፋት ሥራ ሲሰሩ ሲያስቡ፣በከፍተኛ ወጪ ሲሰልሉ በስጋ
ጥበባቸው ብዙ ሉያደርጉ በያዙት ጠምንጃ ሲመኩ ምንም ያልኳቸው ነገር የለም፣ታገስኳቸው እንጂ። ምክር
ተግሳፅ ከመሰንዘር በስተቀር ከዚያ አልዘለልኩም ፈጣሪን ብጠይቅ ፍፁም በእሳት እንደሚበሉ ነግሬአቸዋለሁ።
ዛሬም ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ ብጠይቅ ተፈፃሚ ነው። በጠረጴዛቸው ላይ ስለ እኔ የሚቀርበው ሪፓርት ዝርዝር
አውቃለሁ። ትምክህት ግን ምን ያደርጋል። አዝንላቸዋለሁ። መልዕክቱ ደርሷቸው ምን እንዳሉ ምን እንደወሰኑ
ሁሉ በግሌ የሚታወቅ ነው። በንቀትም እንደተሳለቁበት እረዳለሁ።
ይሁንና ሳይርቅ ሁሉም ስለሚፈፀም እርምጃቸውን ሁሉ ደግመው ደጋግመው ቢያዩት ለራሳቸው የሚበጅ በሆነ
ነበር። ሆኖም በራሳቸው የስጋ ሩጫ ስለሚያልሙ ከውድቀታቸው አይመለሱም ይበጀናል ብለው የሚወጥኑት ሁሉ
ወደ ከፋ ጨለማ እያወረዳቸው ይገኛል። አሁንም ቢይዙት ሰከንድ ለማትፈጅ እስትንፋሳቸው ይመጻደቃሉ።
የመንፈሳዊን ሰው አይን ንቀው በስጋቸው አይን ሊሰልሉት ይደክማሉ። እስከ ቤቴ ገብተው እንዲሰልሉ
ፈቅጄላቸዋለሁ ከተጠቀሙበት። እውር አይናማውን ሲሰልለው እስቲ አስቡት!
አለም በምን ምጥ ውስጥ እንዳለ ወዴትስ እንደሚጓዝ በፊታቸው ያለው የልዑል መልዕክት ሲለካቸው
ሲመዝናቸው ለፍርድ ሲያዘጋጃቸው በማይታይ የእግዚአብሔር የብርሃን ሰንሰለት ሲጠፍራቸው አያውቁትም
አይረዱትም በህሊና ፣ በስጋ ዕውቀታቸው ዲያብሎስ በሰጣቸው የውሸት ተስፋ ሲመፃደቁ የተሳካላቸው
እየመሰላቸው ሲያከትሙ አይናማው ያያል።እነሱ ግን እንደ ዕውሩ ወደ ገደል ይወድቃሉ። ለምን አያስተውሉምና
በትዕቢት ተሞልተው አያዩምና።
ወደ መንደርደሪያ እንግባና
ስለዚህ መልዕክት ያላችሁን ግንዛቤ መንገድ ለማስያዝ፣ በመልዕክት አንድና ሁለት የታዘዘውን እየተፈፀመ ያለውንና
የሚፈፀመውን ትረዱና ታስተውሉ ዘንድ ይህ መልዕክት የተፃፈ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ተፈፃሚነቱን ብቻ
ሳይሆን ዝርዝር መመሪያውን የሚገልጽ ይሆናል።
ትንቢተ ሕዝቅኤሌ ምዕራፍ 8 በሙሉ
በሦስተኛ ደረጃ እያንዳንዱ የአለም ክፍል ሀገር፣ ክ/አህጉር ሕዝብ፣ ማህበረሰብ፣ የእምነት ተቋም የሚገጥመውን
ሸክም/ቅጣት/ እስከምን እንደሚነድ እንዴት ቅጣቱ እንደሚያበቃ፣ በቅጣቱስ ምን በማድረግ መዳን እንደሚችል
ርዕስ በርዕስ እየተነተነ ይገልፃል።
ይህ መልዕክት ለሁለም የሰው ዘር ሁሉ እንደ ልዑል ትዛዝና ፈቃድ የተዘጋጀ በሁለቱም መልዕክቶች ላይ
መሰረት ያደረገ ዝርዝር የድርጊት መመሪያ ስለሆነ የእግዚአብሔር እውነተኛ አገልጋዮች ፣የታመናችሁ የልዑል
ልጆች በየትኛውም የዓለም ፊት ኑሩ፣ በየትኛውም የህይወት ጎዳና ተሰማሩ ከመልዕክት 1 እስከ 2 እና ይህን ዝርዝር
አመላካች መመሪያ ትጨብጡ ዘንድ ሁሉንም ክንዋኔ ትመዝኑበት ዘንድ በጥብቅ እመክራችኋለሁ። እንደምረዳው
ለበጎ ቀን የተጠበቃችሁ ከጌታ ጋር ግንኙነታችሁ የጠበቀ በእጃችሁ ያለውን ትዕዛዝ ታውቃላችሁ። ፈጣሪ
የሰጣችሁን ምልክት፣ተስፋና ኃላፊነት በማስታዋል በልባችሁ መዝግባችሁ ተጠባበቁ። ልዑል ቃሉን ሊፈፅም
ጥሪው ደርሷችኋልና።
ሁሉንም አካሄዳችሁን መዝኑበት፣ አካባቢያችሁንም፣ የዓለምን ሁኔታ ሁሉ እዩበት ከልዑል የተሰጣችሁ መነፅር
ነውና።
ዕውር ዕውር ነው ዕውርነት ስላችሁ መንፈሳዊ ዕውርነትን ነው። የመንፈስ ዕውር የጌታን የመንፈስ
መነፅር ሊያደርግ አይችልም። ምክንያቱም እንደ ሰውነቱ የተገዛው ለጨለማው መንፈስ ስለሆነ የብርሃን መንፈስን
በደባልነት ሊያጠልቀው አይችልም አጥፊ ነውና።
ዕውር በፍፁም ጠቆረም ነጣ መነፅር ቢያደርግ ዕውርነቱን አይሸፍንለትም በመሆኑም ዕውራን
የዘመናችን ታላላቅ ነን ባይ መንግሥታቶች፣ ሹሞቻቸው፣ የእነዚሁ መንግስታቶች አሽከርና ሎሌ መንግስታቶች
ከነሹሞቻችሁ አንብቡት፣ እንደለመዳችሁት ወርውሩት ናቁት ተሳለቁበት ችግር የለውም የምትከፍሉትን ዋጋ
ከየዝርዝር መግለጫው ስለምታዩት ትሰፈሩበታላችሁ ትጠረጉበታሊችሁ።
የናንተ ጉዞ ረግረግ ላይ እስከ ጉልበቱ ሰምጦ ኳስ እጫወታለሁ የሚልን የዋህ ይመስላል። ስለዚህም ትዕግስቱ
ካላችሁ አንብቡት የጥፋታችሁን ሂደትና ፍጥነት እዩበት።
ለወገኖቼ፣ ለወንድሞቼ፣ ለእህቶቼ፣ ለእናቶቼና አባቶቼ በየትኛውም የምድር ፊት ላላችሁ የእግዚአብሔር
በጎች የሚጠብቃችሁን ክብር፣ በረከት፣ መፅናናትና ደስታ በኔ አንደበት ልገልጽላችሁ ይቸግረኛልና ብቻ ፅኑ
በሚያበጥረው የእሳት ጉዞ ውስጥ ገብታችኋል። እሳቱ እናንተን አይጎዳም ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ አብዲናጎም በልዑል
የታመነ መልአክ ቅ/ ገብርኤል ስለተጠበቁ ምንም እንዳልሆኑ እነሱን ለእሳት የጣሉትን እንደ በላ በምድሪቱ
የበቀሉት የሊባኖስ ዝግባዎች ረዥሙም አጭሩም ልቅም አድርጎ ሲበላ የምትታዘቡ ትሆናላችሁ ለመጭውም
ትውልድ ምስክር ሆናችሁ ትቆማላችሁ እናንተን የሚያስጨንቅ አደጋ አይመጣም።
ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 12 በሙሉ
መላው የሰው ዘር ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ አስተውሉ
ከእኔ ዘንድ የደረሳችሁ መልዕክት 1 እና መልዕክት 2 እና ይህ 3ኛው የመመሪያ የማብራሪያና የአፈፃፀም
የድርጊት ውሳኔ መግለጫ ሁሉ በቸሩ አምላካችን ታዝዤ ያደረግሁት መሆኑን በኔ ዕውቀት ጥበብና ፍላጎት የመጣ
እንዳልሆነ መታወቅ ይገባዋል። እኔ የልዑል አገልጋይ /የሥላሴ ባርያ/ ትዕዛዙን ፈፃሚ እንጂ በራሴ የማመንጨው
አንዲት ነገር የለም።
የክርክር ዘመን አልፏል የእኔ አካሄዴ ትክክል ነው፣የኔ መስመር፣ የኔ እምነት የተሻለ ነው በሚል
ከእውነት መንገድ የወጣም በእውነቱም የተመሰረተ የእምነት ጦርነት ሁሉ በሺዎች ዘመን አስቆጥሯል። ዛሬም
ይኸው ያለና የሚታይ ነው። ግን አበቃ !
ሁለም ሰው በልዑል ፊት ባመነበት ቆሞ ተሟግቷል፣ ሃሳቡንና እምነቱን ለማስረፅ ከቅድመ አያቶቹ
ጀምሮ ተጉዞበታል። ታዲያ ይኸው ሁኔታ የሚቀጥል መስሎአችሁ ሁላችሁም በተመሰረታችሁበት ቆማችሁ
በየራሳችሁ መነፅር ስታዩ ኖራችኋል። ሁሉም ባመነበት በልዑል ችሎት ተሟግቷል። ውሳኔ ተላልፏል። ይግባኝ
ተሰምቷል። ሌላ ይግባኝ የለም።
በኔ በልዑል ባሪያም የተላለፈውን መልዕክቶች ሁሉ እንደተወለዳችሁበት፣እንዳደጋችሁበት ዛሬም
እንደምትኖሩበት አይንና ሕሊና እያያችሁት መልካም ነው።
ልብ ልትሉት የሚገባው ግን ያ ዘመን አበቃ። ትዕዛዜና ፍርዴ ወጣ የአፈፃፀም መመሪያውም ይኸው
ወጣ። የክርክር ዘመን አለፈ፣ተዘጋ። ከማነው የምትከራከሩት በየትኛው ፍ/ቤት የፍርድ ሂደት ክርክር ይደረጋል።
የፈጀውን ጊዜም ይፈጃል በኋላ በዳኛው ውሳኔ ይሰጣል። በቃ !
እየነገርኳችሁ ያለውን የልዑል ውሳኔ ነው። 1-2 ነግሯችኋል። የዛሬው የውሳኔ አፈፃፀምና መመሪያ ከነሙለ
ማብራሪያው ቀርቦላችኋል። አበቃ !
ትንቢተ ኢሳያስ 43፣8 – 13
ማሳሰቢያ
በዚህ ክልል ውስጥ የሚያርፉ ሰዎች በራሳቸውም ሆነ በቀረቡአቸው ሰውች ዙሪያ የሚያዝ የሚጨብጥ
ባህርይ የሌላቸው ናቸው፡፡ ሁለት እግር ይዘው ሁለት ዛፍ ባንድ ጊዜ ለመውጣት የሚያስቡና የወሰኑ
ናቸው፡
በማናቸውም ጉዳይ ላይ እምነት የማይጣልባቸው ናቸው፡፡ እምነትን ለማመን ከወሰኑም በመምሰል
ለመጓዝ የሚወስኑም ናቸው፡፡ ቆርጠው ባንድ አቋም ፀንቶ ጥቅሙንም ጉዳቱን ለመቀበል የሚችልና
የሚወስን ህሊና የላቸውም፡፡ አላማቸው ያ ብቻ ነውና በማስተማርም የሚመስሉ አይነት አይደሉም ቢጎዱም
ከዋዠቀው አቋማቸው አይወጡም አላማቸው ያ ብቻ ነው፡፡ ጌታ በዮሐንስ ራዕይ ላይ እንደተናገረው
ሙቅነትም ቀዝቃዛነትም የሌላቸው ለብታን የተላበሱ በመሆናቸው ሊተፋቸው ያስጠነቀቃቸው አይነት
ናቸው፡፡ በመላው አለም በቁጥር በዝተው የሚታዩና ለማንኛውም ጉዳይ የማይበጁ ናቸው፡፡ በመልእክት 1
እንዲሁም በመልእክት 2 የተላለፉትን ወቃሽ ፈዋሽና ፈራጅ ገሳጭ መልእክቶች ሰምተው ለጊዜው የመደንገጥ
ምልክት የሚያሳዩ፣ ቆየት ብለው የተሰጣቸውን እድሜ በብልጠት ያገኙት አድርገው በመቁጠር ለከፋው የኑሮ
ገፅታቸው የአለሁበት ማረጋገጫ የሚሰጡ በመሆናቸው ተመልሰው እንደ እርያ ወደ ሃጢያት ጭቃ
የሚመለሱ በመሆናቸው፡፡ በዚህ የፍርድ አፈጻጸም ውስጥ በእሳት የሚበጠሩ ናቸው፡፡ በአብዛኛው የኑሮ
ምቾት የእውቀት ብዛት ያነቃቸው ሩጫቸው ባላቸው ላይ ለመጨመር የሚለፉና ለዚሁ ሁሉ ሌላውን
አሳልፈው የሚሰጡ ናቸው፡፡ በስልጣንም በንግድም በማናቸውም ማህበራዊ ሃላፊነት ቢቀመጡ አታለው
ለመኖር የሚጥሩ የሾማቸውን በከፉ ሰዓት ጥለው የሚጠፉ አምላካቸው ሆዳቸው ብቻ የሆኑም ናቸው፡፡
ስለዚህም አስቸጋሪ ሁኔታ የሚጠብቃቸው መሆኑን ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ፡፡
በሦስተኛው ዘርፍ ያሉ ሰዎች
በዚህ መስፈርት የሚያርፉት ብዘውን ጊዜ የሚያጠፉትን፣ የሚሰሩትን፣ ማናቸውንም ጉዳይ አምነውበት
ይበጀናል ብለው የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ ጥፋትን ሲፈጽሙ ትክክል እንደሰሩ በነሱ እምነት ትክክል እንደሆነ
የሚቆጥሩ ለበዙ ሰው የጋራም ሆነ የግል ተቃውሞና ግሳጼ ቦታ የማይሰጡ የኔ ትክክል ነው ብለው
የሚያምኑና በዚህም እስከ መጉዳት የሚሄዱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ በአለማችን ላይ በእምነት ውስጥ
ለእምነቱ ብርቱ ተሟጋች ሆነው የሚቆሙ የሌላውን ተጻራሪነት በማናቸወም መንገድ ማስወገድ የሚፈልጉ
ሲሆኑ በስልጣን ጫፍ ላይ ከመጡም ሥልጣኑን ለማቆየት ብቻ ሳይሆን በዚያ ስልጣን ላይ መቆየት አለብኝ
ብለው ላመኑበት ምክንያት ጸንተው የሚቆሙ ናቸው፡፡ ከአቅማቸው በላይ የሆነ በግድ የሚያስወግዳቸው
ሁኔታ ሲፈጠር ብቻ አቋማቸውን የሚፈትሹና ከጉዳት በኋላ እውነቱን የሚቀበሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች
በአለም ገጽታ ውስጥ በቁጥር መስፈርት እንደተመለከቱት አይበዙም በእምነት ስንሄድ ሐዋርያው ጳውሎስን
ስናስብ ለፈሪሳዊነቱ ለሕጉ በጽኑ የቆመ ክርስቲያኖችን በማሳደድ እንቅልፍ ያጣ ሐዋርያቶችን እጅግ ያስጨነቀ
ነበር፡፡ ጌታ ሲለውጠው እንኳን በሐዋርያቶች ዘንድ እሱን ለመቀበል ረዘም ላለ ጊዜ የተቸገሩበት ነበር፡፡
ሆኖም አምኖበት ነውና የተለወጠው በክርስቶስ የወንጌል ሥራ ከማንም በላይ ሠርቶ በመስዋእትነት ያለፈ
ጀግና ሐዋሪያ ነው፡፡ የቅርቡን በሥጋው ያለፉትን ብንጠቅስ ደግሞ እነአዶልፍ ሂትለር፣ እነሮማል፣
እነስታሊን፣ ባገራችንም እነበላይ ዘለቀ፣ እነምነግሰቱ ነዋይ፣ እነጀነራል ታሪኩን እጅግ ብዙ ሰዎችን መጥቀስ
ይቻላል፡፡ በዚህ ክልል ለክፉ የሁን ለበጎ፣ በሥጋውም ይሁን በመንፈሳዊ የሚመጡ ሰዎች በግል እጅግ
የሚደንቁኝ ናቸው፡፡ ከነዚህ ክልል ወደፊት በመንፈሳዊ ተልእኮም ሆነ በሥጋው ሥራ ብዙዎችን አያለሁ
ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጥረቱ መስመር እንዲይዙ እውነትን እንዲጨብጡ መጣር ሲሆን ልዑል ከያለበት
ያወጣቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ እነሙሴን፣ እነአብርሃምን፣ እነያእቆብን፣ ሁሉንም ሐዋርያቶች፣ ብንወስድ በዚህ
ክልል የሚያርፉ ናቸው፡፡ ሙሴ ከክብር ወደአመነበት ወደጭቃና ወደወገኖቹ እስራኤላውያን ሲመለስ ቅርም
አላለው የተወው ሕይወት /የግብፅ ሕይወት/ አልናፈቀውም ፈጣሪውን አወቀ በዚያው ጸንቶ ተጓዘ አለፈ፡፡
አብረሃም አባቱን እሱም ቤተሰቡም የሚያምንበትን ጣኦት ትቶ በሰማው የፈጣሪው ድምጽ አምኖ ሁሉን ትቶ
ወደበረሃ በእምነት ወጣ፤ ማንም ያላገኘውን የእምነት ጽናት በሥላሴዎች ታደለ፡፡ ተባረከበት፣ ተቀደሰበት፣
ለሁላችን ተረፈበት፣የዘለአለምን ሕያወት ወረሰበት፡፡ ያእቆብ ጽኑ የእምነት ታጋይ ነበር፤ ከፈጣሪ የብርሃን
መልአክ ጋር ካልባረከኝ አልለቅህም ብሎ ታግሏል ሹልደው ተጎድቶ በጥረቱ የተደነቀው ፈጣሪ በረከቱን
አጎናጽፎታል፡፡ ሐዋርያቶችን ብንወስድ ከተለያዩ ከተናቀ ሥፍራ ጌታ ቢሰበስባቸውም ለቃሉ ታምነው፣
በወንጌል ለኛ ሆነው ለትውልድ ተርፈው በታላቅ መስዋእትነት ለድል በቅተዋል፡፡ በአገራችን አፄ ቴዎድሮስን
እነላሊበላን፣ እነ ዘርአያእቆብን፣ እነ አፄ ዮሐንስን ብናስብ የእምነትም የአገርም መሪና ጀግና ሆነው ባመኑበት
ዋጋ ከፍለው አልፈዋል፡፡ ስለዚህ በስፋት ያሉ ሰዎች ለጥፋቱም እሰከጫፍ የሚሄዱ ለመልካሙም ብርቱ ዋጋ
የሚከፍሉ ናቸው፡፡ በዛሬው አለማችን ባመኑበት የተሰለፉ ብዙ ናቸው፡፡ ዲያቢሎስ ከነዚህ ሰዎች የህሊና
ምርኮኛ ለማግኘት በብረቱ የሚጥርበት ነው፡፡ እስከ ፍፃሜ ባስጨበጣቸው እውነት መሰል ጥፋቱ
ስለሚዘልቁ በብርቱ ይፈልጋቸዋል ይጠብቃቸዋል፡፡
በዚህ በአራተኛው ዘርፍ ያሉ ሰዎች
በዚህ መስፈርት የሚከለሉት ደግሞ እጅግ መጥፎዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በጎን መልካምን ነገር በፍፁም
የማይወዱ፣ በጭካኔያቸው ወደር የማይገኝላቸው ፍፁም ትእቢተኞች ናቸው፡፡ ማንኛውም ነገር የሚለኩት
ለራሳቸው የደስታ ምንጭ ይሆናል አይሆንም ከሚል መስፈርት በመሆኑ ከተጣመመው ፍላጎታቸው ጋር
የሚጋጭ ሁሉ ቢጠፋ እምነታቸው ነው፡፡ እየሞቱም እየተሰቃዩም ቢሆን ከትእቢታቸው፣ ከክፋታቸው፣
መጥፎ ከመስራት የማይመለሱና ባሳለፉት መጥፎ ተግባር መዘከር የሚደሰቱ ስለዚህ ብቻ መስማት የሚወዱ
ናቸው፡፡ ለዚህ ምሳሌ ጌታ ስለኛ በደል በመስቀል ሲሰቀል በመጥፎ ስራቸው ከተሰቀሉት ወንጀለኞች ነፍሰ
ገዳዮች ውስጥ ግራና ቀኝ የተሰቀሉት ፋህታዊ ዘማዊና ፋህታዊ ፀጋምን ነበሩ፡፡ ፋህታዊ ዘማዊ 70 ነፍስ
በመጨረሱ የተፈረደበት ሲሆን ፀጋም እንዲሁ ብዙ ነፍስ ያጠፋ ነው፡፡ ሁለቱም ስለጌታ መከራከር ጀመሩ
በስተቀኝ ያለው ፋታዊ ዘማዊ ስለጌታ ንጹህነት በመመስከር የራሱን ወንጀለንነት በማመን፣ በመጸጸት ለቅጣቱ
አግባብነት ተከራክሮ ጌታ ግን ንጹህ መሆኑን መስክሮ በመንግሥቱ እንዲያስበው ጠየቀ ምህረትም አገኘ፣ ገነት
ከማንም ቀድሞ ከጌታ ጋር ገባ፡፡ በስተግራ የተሰቀለው ፋህታዊ ፀጋምን ግን ጌታን በመዝለፍ ንጉሥ ከሆነ
ራሱን ያድን እያለ በማፌዝ በትእቢት እንደፀና አለፈ ወደ ጨለማው ነጎደ፡፡ በዚህ መስፈርት ያሉ በምንም
መንገድ ቢሏቸው የማይመለሱ በመሆናቸው በፍርድ የሚያገኙትን ቅጣት መቀበል ያለባቸው ናቸው፡፡ ባሁኑ
ዘመን እነዚህ እጅግ በዝተው እናገኛቸዋለን፡፡
የሰው ልጅ ከተፈጠረበት እለት ጀምሮ አክብሮ ሊኖርበት የሚገባ ትእዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ትእዛዝ
ቢጥስ ደግሞ ቅጣት እንደሚከተለው በግልፅ የፈጠረን አምላክ ደንግጓል፡፡ መብትንና ግዴታን መመለሻውን
ድንበርና መሄጃውን መንገድ አመላክቶአል የሰው ልጅ ታዲያ ይህንን የልዑል ትእዛዝ አክብሮ አልኖረም
አባታችን አዳም እናታችን ሄዋን በእባብ ምክር በዲያቢሎስ ጠንሳሽነት ትእዛዝን አፍርሰው ከተሰጣቸው ድንበር
ወጡ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ያስቀመጠውን ትእዛዝ በመጣሳቸው አዘነም ተቆጣ በፍርድ ወንበሩ ላይ
ተቀመጠ የቅጣት ውሳኔውን ከመስጠቱ በፊት ለአጥፊዎቹ ምክንያታቸውን መሳሳት አለመሳሳታቸውን ጠየቀ፡፡
የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ አዳም በሄዋን ሄዋን በእባቡ አመካኙ ዛሬ የሰው ልጅ ሲያጠፋ ብዙ ምክንያት
እንደሚደረድረው ሁሉ አላጠፋሁም ብሎ መከራከር ከራስ ላይ የጥፋትን ሃላፊነት ማሸሽ ተጀመረ፡፡
ትእዛዝ(ሕግ) ሲጣስ ቅጣት አለ፡፡ ከቅጣቱ በፊት ለዳኝነቱ ትእዛዙን ያወጣው ጌታ በችሎቱ ይቀመጣል፡፡
ክርክር ይካሄዳል ቅጣቱ ይሰነዘራል፡፡ አዳም በማዘኑ በልቡ ይግባኝ በማለቱ ቢደመጥም የሞት ቅጣት
ተሰንዝሯል ለአዳም የሰው ዘር እየበዛ ምድርን እየሸፈነ ከመሄዱ በፊት ጌታ ሕግን እንዲጠብቅ በልቡናው ጻፈ
ክፉንና በጎውን እንዲለይ የሚያስችለው ህሊና ቀድሞም ሲፈጥረን ሰጥቶናል፣ በሕገ ልቡና ረዘም ያለ ዘመኖችን
የሰው ዘር ኖረ፡፡ በሕገ ልቦና ሰው ተዳኝቶአል፡፡ የኖህ ዘመንን ማሰብ በቂ ነው፡፡ ሰዶምና ጎሞራን ማስታወስ
ከበቂ በላይ ነው፡፡ በሁለቱም ወቅቶች ጌታ በልባቸው ባስቀመጠው ህገ ልቦና ፍርድ ሰጥቶአል፡፡ ዳኝነት
ተካሂዷል፡፡ ቅጣቱም ተሰንዝሮ ተፈጻሚ ሆኖአል፡፡
ጌታ ሰው በዝቶ ምድርን መሸፈን ከጀመረ በኋላ የግድ የተጻፈ ሕግ ያስፈልገው ዘንድ አየ፡፡ ፈቃዱም ሆነ
በአባታችን ሙሴ ህገ ኦሪት ተደነገገች በዚህም የሰው ልጅ መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ ተደረገ፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት ም2፡ 16 - 17
ኦሪት ዘፍጥረት ም3፡ በሙሉ
ኦሪት ዘፍጥረት ም6. 7 በሙሉ
ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ሰው ሲያጠፋ፣ ሲቀጣ፣ ምህረት ሲጠይቅ፣ ንስሃ ሲገባ፣ ለጥፋት መስዋእት
ሲያቀርብ፣ ምህረትን በይግባኝ ሲያገኝ በየጊዜው ልዑል ዳኝነት ሲሰጥ ዘመናችንም ሲከንፍ አባቶቻችንም
ኖረውበት ሲያጠፉ፣ ሲማሩ፣ ወደ ምህረት ዘመን ተደረሰ፡፡ ጌታ እንደቃሉ ለአዳም እንደሰጠው የይግባኝ መብትና
በዚያም በጨበጠው ተስፋ ከ5500 ዘመን በኋላ ጌታ ላንዴም ለሁሌም የሰውን የሃጢያት እዳ ለመክፈል መጣ፡፡
ቃሉን አከበረ፣ ሕግን ፈፀመ ሰው መፈፀም ያቃተውን ትእዛዙን ፈፀመ፡፡ ለሁሉም የሰው ልጅ ሃጢያት በመስቀሉ
ሻረ፡፡ የዘለአለምን ሕይወት ለኛ አፀና የልጅነት ክብርን አጎናጸፈን፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ አሁንም ቀሊል የሆነውን
ሕግና ትእዛዙን አስቀመጠ፡፡
እንጠብቀው ዘንድ አዘዘ፡፡ ስናጠፋ ንስሐ እንድንገባ እንቢ ብንል በችሎት ቀርበን እንደምንቀጣ አረጋገጠ፡፡ ሰው
ሞገደኛ ነው ሁላችንም በስጋችን ተሸናፊ ነን፡፡ የምናየው ሁሉ፡፡ እኛም እራሳችን ሁሌ እንደፈነጨን የምንጓዝ
ይመስለናል፡፡ በዚህም ትእዛዝን እንጥላለን፡፡ ንስሓ ገብተን በትእዛዝ ጥሰት የሚሰነዘርብንን ቅጣት በይግባኝ
/በንስሐ/ ምህረት ማግኘት ስንችል በትእቢታችን በመግፋት እንጎዳለን፡፡
ጌታ ሁሌም ፍቅሩን በመግለጽ በመታገስ ጊዜ፣ በመስጠት፣ በመውቀስ ቀላል አባታዊ ቅጣት በመሰንዘር ወደ
ትክክለኛው መንገድ እንድንመለስ ሁሌ ያደርጋል ይሁንና ሁሉም ገደብ ስላለው የግድ ብርቱ ቅጣት ይመጣል፡
የሰው ልጅ ሁላችን የጌታን ሕግ ጥሰን የራሳችንን የሥጋ ሕግ የእግዚአብሄር ጠላት የሆነውን የዲያቢሎስ ሕግ
በማጽደቅ የፍቅር ሕጉን ንቀን አታመንዝር ያለውን እንደ መብት በሕጋችን የማመንዘርን ፈቃድ አስቀምጠን፣
አትግደል ያለውን እንገላለን፣ አትዋሽ እንዋሻለን፣ ወንድምህን እንደ ራስህ ውደድ ያለውን ትተን አይ የለም
ወንድም፤ ባልንጀራ ገንዘብ እንላለን፡፡ በሁሉም ትእዛዝ አፈረስን በጭለማ ህግ መመራት ጀመርን፡፡
በዚህም ምክንያት ሲታገስ የቆየው ጌያ በተለያዩ አገልጋዮቹ አማካኝነት ማስጠንቀቂያ ሰጠ፣ መከረ፣ ዘከረ፡፡
መልእክት 1 መልእክት 2 በቃሉ ተመስርቶ በኔ በትንሽ ባርያው ለሰው ሁሉ እንዲዳረስ አደረገ፡፡ ፍርዱን
በመልእክት 1 እንዳሳወቀ የደህንነቱን ትእዛዝ አወጣ ሶስት አመት ታገሶ ይግባኝ ያሉትን ( ምህረት የጠየቁትን )
በምህረቱ አተመ፡፡ የናቁትን፣ ይግባኝ ያላሉትን፣ ፍርዱን ያልተቀበሉትን ወደ አፈጻጸም ውሳኔ በመሻገር ፍርዱን
ለማጽናት ተሻገረ፡፡ የእየአንዳንዳችን መዝገብ ላይ በየ ደረጃው የተካሄደውን የፍርድ ሂደት ጨርሶ ወደ አፈጻጸም
አለፈ፡፡ ተወሰነ አበቃ፡፡ ፍርድ ምን እንደሚመስል ሁላችንም እናውቃለን፡፡
ትንቢተ ኢሳኢያስ ም፡ 53 በሙሉ
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተፈረደ፡፡ ይግባኙ ጠ/ፍርድ ቤት ሄደ፡፡ተወሰነ፤ ከዚያ ወዲያ ወዴት ይኬዳል ወደ አፈጻጸም
ብቻ ይሆናል፡፡
በመሆኑም የዛሬው ይህ የፍርድ አፈጻጸምና መመሪያ ከልዑል ችሎት ወጣ፡፡ ይግባኝየለምጊዜየለም፣ ወደ
አፈጸጸም የሄደ ውሳኔ በአስፈጻሚዎቹ እጅ ገብቷልና፡፡
መልክቶቹና ፍርድ ሂደት አፈጻጸምና ውጤቱ ወንድሞች፣ እህቶች፣ መላው የሰው ዘር በሙሉ፣ ሰማይና ምድርን
የዘረጋ አምላካችን ሲያዝህ፣ ሲመክርህ፣ ሲወቅስህ፣ ለምን አትሰማም? እሱ የፈጠራቸውን እንደፈቃዱ
የሚሽራቸውን፣ የሚሾማቸውን፣ የሥጋ አለቆች ትፈራለህ፡፡ እነሱ ሲሉህ ትደነግጣለህ፤ ሲያዙህ ትታዘዛለህ፣ ፈጽም
የተባልከውን ትፈጽማለህ፤ የአምለክህን ትዕዛዝ ግን ትንቃለህ፣ ታሾፋለህ፣ ታፌዝበታለህ፡፡
ብዙ አገልጋዮች ከልዑል ታዘው መጡ፤ መልእክቱን ተሸክመው፣ ምክርና ግሳጼውን፣ ቁጣውንና ፍርዱን፣
በረከትና ምህረቱን ላንተ ለማድረስ የታዘዘውን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር መልክቶች በመግለጻቸው
ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጸመው በዲያብሎስ በመመራት የጨለማን ህግ ለማጽናት
በመሆኑ በዚህ ድርጊታቸው ገዥዎች ለስልጣናቸው ጥበቃ ሲሉ ሲፈጽሙት የኖሩት ነው፡፡ እነሱ እንደሚሹት
መሆን አለበት ባዮች ናቸው፡፡
ይህን አመጻቸውን ለመግታት በተከታታይ የማሳሰቢያ፣ የመውቀሻ፣ የማስጠንቀቂያ መልአክቶች፣ ከጌታ
በአገልጋዮቹ በኩል ሲፈሱ ኖሩ ይሁንና አለም ናቀ በራሱ ሕግና ደንብ ሰመጠ፣ ፈጣሪን ወግድ አለ ይህንን የሺዎች
ዘመን ትእግስትም ልዑል ጨረሰና በኔ በባሪያው በኩል በ7/3/1998 ዓ.ም. የመጀመሪያውን ምድርና በውስጧ
ያሉትን የሰው ዘር በሙሉ የተመለከተ ውሳኔ ፍርድ አስተላለፈ፣ ተመለሱ አለ 3 ዓመት እያመመው ጠበቀ ሆኖም
ይህንንም አልሰማ ላለው የሰው ልጅ የመጨረሻው ውሳኔ በ27/9/2000 ዓ.ም. በኔው በባሪያው በኩል ተገለጸ፣
ለመሪዎችም፣ ለእምነት ተቋሞችም፣ ለግለሰቦችም፣ ለአለም አቀፍ ተቋሞችም፣ ለመላው አለም አቀፍ የዜና
አታሚዎችም ተሰጠ፡፡
ኦሪት ዘፀአት ም. 32 በሙሉ
ትንቢተ ኢሳኢያስ ም. 3፡ 8 – 15
አስገራሚ ሕዝብ ነው አንድም መሪ ድርጅት፣ አንድም የሃይማኖት ተቋም ትንፍሽ አላለም እንደ ሃላፊነቱ በሚገዛው
በሚመራው፣ በእምነት ስም ለሰበሰበው አልገለጸም መረጃ ለሕዝብ አድራሽ ነኝ የሚል ጋዜጠኛ ማንም
አልተነፈሰም፡፡
በ7/3/1998 የጀመረው የፍርድ ሂደት ቀጥሎ በ27/9/2000 ዓ.ም. ምህረት ለጠየቁትም ለናቁትም ሁሉንም
የይግባኝ የፍርድ ሂደት በልዑል ታየ የመጨረሻው ውሳኔ ጸና፡፡
ዛሬ ደግሞ የፍርድ አፈጻጸምና ሂደቱን ለመግለጽ፣ ለማሳወቅ ይህ ትእዛዝ በልዑል ፈቃድ በኔ በትንሹ ባሪያው እነሆ
ለሰው ዘር በሙሉ ወጣ እንግዲህ አበቃ፡፡
አፈጻጸም ምን ይሆናል በሚል ሁላችንም ልናስብ እንችላለን እጅግ ብርቱ ቅጣትን የሚይዝ ነው፡፡
ትንቢተ ኢሳኢያስ 30፡ 8 – 14
ሹሞቻችን ይፈርዳሉ እንደ ፍርዳቸው ያስራሉ፣ ይቀጣሉ፣ ይገላሉ፣ እነሱም ትላንት ሲፈርዱ ቆይተው
በተራቸው ይፈረድባቸዋል፡፡ እንዳሰሩ ይታሰራሉ፣ እንደ ገደሉ ይገደላሉ፣ ይህ የአለም የህግ ስርአት ነው፡፡
ሁሉም የአለም ስርአት በቆመው ሕግ በየጊዜው በሚመጡ፣ በሚወርዱ አለቃና ምንዝሮች ይዳኛል እሱም ሲወድቅ
በሌላው ተረኛ ይዳኛል፡፡
ፈጣሪ ይዳኛል እንጂ አይዳኝም ፈጣሪ ፈጠረን፣ ሰራን፣ አበጀን፣ በፍቃዱ እስትንፋስ ዘራብን፣ አእምሮ
ሰጠን፣ እኛ ቢሻ የሚያኖረን ባይሻ የሚያተነን ነን፡፡ እኛንና በላይዋ የሃጢያት ማእበል ፈጠረን፤
የምንጨማለቅበትን አለምም በፈቀደው ሰዓት በቃ ቢል ምንተን ነን፡፡
የሰው ጥጋብ ግን ወሰን ያለፈ ነው፡፡ በወንዱም ላይ ሲሰለጥን፣ ሲግል፣ ሲቆርጥ፣ ሲያስር፣ ሲያጠፋ፣ ሲዘርፍ፣
በማይጨበጠው እሳት የሚዳብሰውን ጌታ ያቃልላል፣ ይንቃል፡፡ ጨርሶም በትእዛዙም በመልእክተም ንቀት
ይሰነዝራል፡፡
ይህ የአገራችን መሪዎችና ሹሞች በህሊና ማጣት በትእቢት ሲፈጽሙት እያየን ነው፡፡ የከንቱ ከንቱዎች
ናቸው፡
የእግዚአብሄር የፍርድ አፈጻጸም ሲጀመር አይታይም፣ ሲጨርስም አይዳበስም፡፡ በፈጣሪ ፍርድ የተያዘ
መሪም ተመሪም ሁሉም የተሰጠውን የፍርድ አፈጻጸም ሊያልፍ አይችልም፡፡ የማያስተውል ሕዝብ ይገለበጣል
ይላል የጌታ ቃል፤ እስከ ዛሬ ሲወቀሱ አልሰሙም፣ ሲጠፉም አይሰሙም፡፡ ውጤቱ በልዑል የተወሰነው እውን
መሆን ብቻ ነው፡፡
3. ዓለም በጥቅሉ የሚገጥማት የቁጣ ፍሰት
ትንቢተ ኢሳኢያስ 24፤ 1 – 13
4. ሀ/ ካቶሊክ
ሮም /ጣሊያን/ መቀመጫዋን ያደረገችው ይች እምነት ከተከታዮቿ ብዛት ያላት ናት፡፡ አንድ ቢሊዮን
የሚጠጋ አባል እንዳላት ትናገራለች፡፡ በዚህ እምነት ውስጥ ያሉት ምእመናን በአብዛኛው የሚገኙት በአውሮፓ፣
በላቲን አሜሪካ ነው፡፡ በሌሎች አገሮችም በዋናነት የሚያሰልፍ ቁጥር ባይኖራቸውም በማይናቅ መጠን አሉ፡፡
ካቶሊክ በፖፕ የምትመራ ሲሆን በየሃገሩ እንደየብዛቱ የተሾሙ ጳጳሳት፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ዲያቆናት ወዘተ… አሉት፡፡
ካቶሊክ ማን ናት? ካቶሊክ በመጀመሪያ ልዑል ካስተማረው የተዋህዶ እምነት በ431 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ተገንጥላ
በመውጣት፤ በንስጥሮስ ትምህርት በመወሰድ የክህደት ስራን፣ የመለያየት ተግባር በማጽናት እንደ ድርጅት የቆመች
እምነት ናት፡፡ እስከአሁንም የጨለማ ስራዋን እንደ መልካም የምትዘከር ናት፡፡
በአለም ላይ ያሉ በምስራቅ ኤሽያ በብዛት የሚገኙ ስማዊ ኦርቶዶክሶች፤ ግብራዊ ካቶሊኮች እጅግ ሰፍተው
ይገኛሉ፡፡ በቀጥታም በተዘዋዋሪም በሷ የተጠለፉም አሉ፡፡ ጠንካሮችም አሉ፡፡ በዚህ ፅሁፍ የክርክር ሃሳብ
ለመፍጠር ሳይሆን ፍርድንና አፈጻጸሙን ለመግለጽ የወጣ መልእክት በመሆኑ ከዚህ የሚዘል ሃሳብ አይገለጥም፡፡
ካቶሊክ በሰራዊት ጌታ እንዴት ታየች? ፍርዱስ እንዴት ይታያል የሚለውን እናያለን፡፡ ከ1500 ዘመን በላይ
በልዑል ፊት በአንዲት ተዋህዶ አርቶዶክስ እምነት የክርክር ሂደት ተካሂዷልም፣ አካሂዳለች፡፡ በእምነት ጸንታ
አለምን በወንጌል ታረሰርስ የነበረችን የልዑል ቤት ማፍረስ የጀመረች ካቶሊክ ናት፡፡ እስከ 431 እ.ኤ.አ. በታላቅ
ፈተና እየጸናች፣ ዋጋ እየከፈለች፣ ሐዋርያቶችን፣ ደቀመዛሙርቶቿን እየገበረች የገሰገሰችው የተዋህዶ እምነት
ያልተበገረችለት ጠላት የመረጠው ዘዴ ከሃዲዎችን መፍጠር ነበር፡፡
ወደ እውቀትና ወደ ፍልስፍና ያዘነበሉትን የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ስራን፤ በስጋቸው የእውቀት ትርጉም
የተኩትን ጳጳሳት በመመልመል ለረጅም ጥፋት አነሳስታ ተሳክቶላት የተከለችው አረም በዝቶ አለምን ሸፈነ፡፡
አርዮስን፣ ንስጥሮስን፣ አርጌንስስን፣ መንኪዮስን፣ አብርዮስን፣አፍተክስን፣ አርሲስና መናፍቃንን፣ልዮንን፣
መለካውያን፣ ወዘተ ማንሳት በቂ ማስረጃ ነው፡፡ እነዚህ በክርስትና ሕይወት ላይ የዘመቱ የዲያቢሎስ ምልምሎች
ሲሆኑ ሁሉም የተሰለፉት አንድ ባህርይ፣ አንድ አካል ብላ በምታምነው ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ነበር፡፡ ዛሬም
በነሱ አስተምህሮ ላይ ተመስርተው የቆሙት የዘመናችን ካቶሊኮች፤ ለጥፋት የቆሙ እጅግ ብዙ በጎችን የበሉ፣
ተኩላነታቸውን በለምድ ሸፍነው እያጠፉ ያሉ ናቸው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ብዙ የውስጥ ችግር ቢያንቃቸውም በግብፅ፣ በሕንድ፣ በተለያዩ የኤሽያ አገሮች ከተኩላ ተርፈው ጌታ
ባጸናት ተዋህዶ አርቶዶክስ ጸንተው የቆሙ አሉ፡፡ ይሁንና ጽንሱን ካቶሊክን ከመሳሰሉ አጥፊዎች ዘወትር በፈተና
እንደተጠመዱ ይታወቃል፡፡ እስከ 431 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ድረስ በሮም በሐዋርያው ጴጥሮስ መንበር እየተፈራረቁ
ጳጳሳት በተዋህዶነት ጸንተው የኖሩ ሲሆን ከ431 ዓ.ም. ጀምሮ በልዮን ትምህርት ተለወጠች፡፡ ከዛ በፊት ግን
እውነትን የጸና ተዋህዶን ያቀኑ ሊቃነ ጳጳሳት መሃከል ጥቂቶቹን ባናሳ፤ ቅዱስ ፊሊክስ ሊቀ ጳጳስ፣ ቅዱስ አቡሊድስ
ሊቀ ጳጳስ፣ ቅዱስ አዮክንዲዮስ ሊቀ ጳጳስ፣ ቅዱስ ናጣሊስ ሊቀ ጳጳስ እነዚህን የመሰሉ የተዋህዶ እምነት ጀግኖች
በሮም ጸንተው አልፈዋል፡፡ ወንበር ገልባጮች፣ የዲያቢሎሰ ደቀ መዝሙሮች በልዮን ግንባር ቀደምትነት
እስካፈረሷት ድረስ በአንዲት ተዋህዶ እምነት ልዩነት አልነበራትም፡፡
ዘመቻው ሰፍቶ ዲያቢሎስ ደርጅቶ ከ1500 አመታት በላይ ሲያጠፋ፣ ሲያሳድድ፣ ኖሮ አልጠፋ ብላ፣ አልቆረጥም
ያለችው በኢትዮጵያ የጸናችው ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ብቻ ናት፡፡
የብዙ ሐዋርያት ደም የፈሰሰው የት ነው? የብዙ ነብያት ደም የተረጨው ከማን አገር ነው? ብዙ የወንጌል
አርበኞች የተፈጁት የት ነው? ሮም /ጣሊያን/፣ ሩቅ ምስራቅ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አፍሪካ ስራችሁን ታሪካችሁን
ፈትሹ ! ንጹህ ደም በእጃችሁ አለና፡፡
ኢትዮጵያ ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ የወንጌል ጀግኖችን ተቀበለች እንጂ አላጠፋችም፡፡ ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን
ናቸው፡፡ በሩቅ ሰምታ አመነች ዛሬም ድረስ ቆመች፡፡ ዛሬ ስለእናንተ የጥፋት አለቆች ብዙ መጻፍ ይቻላል፡፡
እናንተን የተዋጉ ኢትዮጵያዊ የተዋህዶ ጀግኖችን ጥቂቶችን ብቻ አነሳለሁ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ የሊቃውንት
ጉባኤ ሰብሳቢ አለቃ አያሌው፣ እነ ንቡረእድ ኤርምያስ፣ እነ አባ ተክለማርያም፣ ከምስከየ ሕዙናን እነ አቡነ
ተክለሃይማኖት /ሃዋርያ/ ብፁዕ አቡነ ባስሊዮስ፣ ከናንተ የወጡት አባ ጴንጤሊዮንን፣ አባ ሊቃኖስ፣ ከናንተው
ፈልሰው በኢትዮጵያ የኖሩትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ትንቢተ ኢሳኢያስ 47፡ 1 – 15
ትንቢተ ኤርሚያስ 17፡ 5 – 8
ኢትዮጵያውያን የወንጌል ጀግኖች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ለዚህ ሃይማኖተ አበውን ማንበብ ይጠቅማል፡፡
ፊት ለፊት የሚቆም ጠላትን መለየት አያስቸግርም፤ መለየት የሚያስቸግረው የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ነው
ብርቱም ጠላት ነው፡፡
የኢት/ተ/ኦርቶዶክስን ለማጥፋት በለምድ ለባሽ ተኩላነት ከተሰለፉት ከካቶሊክ የሚቀድም የለም፡፡ ሌሎቹ የፊት
ለፊት ጠላቶች ናቸው፡፡ ካቶሊክ ፀጋ፣ቅባት፣ እያለች በኢትዮጵያ መለያየትን ለመፍጠር ብዙ የደከመች ናት ዛሬም
ከጥፋቷ ያለተመለሰች ናት ፡፡
ትንቢተ ኢሳኢያስ 5፡ 18 - 25
4. ሐ. እስልምና፡፡
እናንተ የእምነቱ አራማጆች ልብ ብላችሁ አድምጡ በተደጋጋሚ እየገጠማችሁ ያለውን ውድመት
ማስተዋል ተስኗችኋልና፡፡ በዚህ የመጨረሻው የአፈጻጸም ሂደት ምን እንደሚመስል ስሙ ተረዱ፡፡ እስልምና
ፍጹም የተሳሳተ ብዙ ሰዎችን ለጥፋት የዳረገ እምነት ነው፡፡ እስልምና ተረት መሰል የጠላት ዲያቢሎስ ድርሰት
ነው ብንል ከእውነት አንርቅም፡፡
ሰውን አጥፍቶ እኔ እኖራለሁ የሚል፣ በገዛ ወገኑ ሞትን የሚዋጅ፣ ገነት በደም ጨቅይቼ እገባባታለሁ የሚል ፍጹም
የጥፋት እምነት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ላይ ቆሞ ለሰው ጥፋት መሳሪያ ሰብስቦ በዚሁ ሁሉንም እምነት ጨፍልቆ
በራሴ አምሳል ጠፍጥፌ እሰራለሁ የሚል ድርጅት ሲሆን፤ በውስጡም ያሉት ፍጹም የዲያቢሎስ ሰራተኛ የሆኑ
እውነት መስሏቸው ተሳሳቱ፣ እንደ ባህል የያዙ፣ ከዝርያ ጋር አያይዘው የሚያዩ ሱኒ፣ ሺያት፣ በሚል የዘር ሀረግ
የሚፋጁ አንዱ አክራር /ዋህቢያ/ አንዱ ሺያት፣ አንዱ ሱሚ እያለ አንዱ ለአንዱ ሞት እየደገሰ የሚፋጅበት ገንዘብና
እምነቱን በአንድ ሻንጣ አስጨብጦ በደሃ አገሮች ላይ የሚዘምትበት የጥፋት መሳሪያ ነው፡፡
ስለዚህ የዚህ እምነት ተከታዮች በመልእክቱ እንደታየው በሰበሰባችሁት መሳሪያ እራሳችሁ ታልቁበታላችሁ፡፡
እስከምትከስሙ ድረስ፣ ከጥጋብ ተራራ እስክትወርዱ ድረስ፣ አጥታችሁ ነጥታችሁ ትቢያ ላይ እስክትወድቁ ድረስ
የሃብት፣ የመሳሪያ ክምራችሁ በኖ እስኪጠፋ ድረስ፣ ትንፋሽ የማይሰጥ የጥፋት፣ የውድመት እሳት ታዞላችኋል፡፡
ከእናንተ የሚያመልጡት እውነትን ከልባቸው የሚፈልጉ ፈጣሪን ከልባቸው የሚወዱ ቅን፣ የዋህ፣ ትሁት የሆኑ
የጥፋት ስራችሁን የማይወዱ ብቻ ይድናሉ ወደ እውነተኛው የብርሃን መንገድ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን
ይሰበሰባሉ፡፡
ትንቢተ ሕዝቅኤል 22፡ 1 – 5
ይህ እድል የሚገጥማቸው በመጪው የሚያበጥረው እሳት አልፈው የሚድኑት ብቻ ናቸው፡፡
እስልምናን የመንግስት እምነት ያደረጋችሁ አገሮች ሕዝቦች እጣ ፈንታችሁን ከየአገሮቹ ዝርዝር ልታዩ ትችላላችሁ፡
ለዚህም በ1998 ህዳር 7 በተጻፈ መልዕክት ከፈጣሪ እጣ ፈንታዋ ምን እንደሚሆን ተነገራት፣ ከ3 አመት
በኋላ 27/9/2000 የመጨረሻው ማስጠንቀቂያና ፍርድ ተገለጸ እጣ ፈንታዋ ሁሉ በግልጽ ተነገራት፡፡ ይህች አገር
የትእቢት ሁሉ ምንጭ በመሆኗ መልእክቶቹን ከእብድ ቃልና ንግግር አብልጣ አላየችውም፡፡ እኔም መልእክት
አድራሹንም እንደከንቱ ቅዠታም ቆጥራለች ከሷ የተጠፈጠፉት አውሮፓ፣ ኤሽያ፣ አሜሪካ፣ አፍሪካ የኔው አገርም
መሪም ተሳለቁ፣ ይሁንና ቆይታቸው 3 ወር ብቻ ሄደ እንጂ፡፡ በሳቁበት ልክ የአባታቸው የአሜሪካ የሃብት፣
የገንዘብ ክምር በቀውስ ሲታመስ እንደ ሰም ሲቀልጥ ሳቅ ቆመና ሃዘን ሆነ፡፡ እቅድ፣ የአስቸኳይ ስብሰባ፣
የመፍትሔ ብዛት ተደረደረ ሁሉም ተባለ ራስን ደግፎ ምን ይሻላል ማለት ተጀመረ፡፡ እብዱ እኔ እብድነቴ ለናንተ፣
ባለ አእምሮነቴ ህሊና ለሰጠኝ ለእግዚአብሄር፣ ባሪያነቴ ለፈጠረኝ አምላክ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ምጥህ ጀመረ፣ ገና
መቼ ዘለቀ ባቢሎን /አሜሪካ/ አምላክህ አምላክነቷ፣ ጥበቧ፣ ብልሀቷ፣ ምሽግነቷ፣ የሃብታችሁ ምንጭነቷ እነሆ
በከባድ እሳት ይበጠራል፡፡ አምላካችሁ ናትና ከናቃችሁት ጌታ ፍርድ፣ የቁጣ እሳት አታመልጡም፡፡ እናነተም
ሞክሩ ስታመልጡ ልናይ ነው፡፡
በሁለቱም መልእክቶች እንደተጠቀሰው እስትንፋስ የለም፡፡ እቅድ ድርድሩ መላ አደራጁ፣ የዲያቢሎስ
ልጆች መቼም ቢሆን ምላሳችሁ አይሞትም፡፤ አባታችሁ ዲያቢሎስ ባሳደጋችሁ መንገድ በጨለማው
እየተደናበራችሁ ወደ መጨረሻው ሞታችሁ ትዘልቃላችሁ እንጂ መመለስ የለም፡፡
› ከውስጧ የሚወጡ ሰዎች በእሳቱ ሲጤሱና እሳቱ ሲነድ ለአለም ሁሉ ይታያል ለታመኑ ወዳጆቿም ይተርፋል፡፡
› ከውስጡ የሚወጡ ሰዎች ቢኖሩም ለረጅም ጊዜ የፍርሃትና ድንጋጤው ጥላ-አይርቃቸውም፡፡
› ለጥፋት ያሰናዳቸው መሳሪያ ሁሉ የትም ታኑረው የት ወዳጅ ከምትላቸው ጋር አብሮ ይጠፋል፡፡ ምልክቱም
አይገኝም፡፡
› የሰው ዘር፣ ለመግዣ፣ እምቢ ቢል፣ ለመጨፍጨፊያ ያዘጋጀችው/ያዘጋጃችሁት/ ኒክለር፣ ኬሚካል፣ ባዮሎጂካል፣
መሳሪያ ጀት፣ መርከብ፣ ሳተላይት መርዝ ሁሉም ከነአዛዦቹ፣ ከነአድራጊዎቹ፣ ከወሳኞቹ ጋር አብሮ ይጠፋል፡፡
› በዚች በባቢሎን አገር የበቀለ ማንኛውም የትሃጢያት ማጎልመሻ ፣ ማራመጃ፣ የዲያቢሎስ መጠቀሚያ በሙሉ
ይጠፋሉ፡፡ በውስጡ ያሉ ሶዶማውያን አመንዛሪዎች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ በሃብታቸው፣ በእውቀታቸው የሚጨማለቁ
ሁሉ የፈጣሪን ህግ የናቁ ሁሉ የእምነት መሪም ተመሪም ነን የሚሉና እውነትን የናቁ /ካቶሊክ፣ ሙስሊም፣
ፕሮቴስታንት፣ ቡዲሂስት፣ ኮሚኒስት፣ ሌሎችም/ የጦር መሪ ነን፣ የጸጥታ ሃላፊ ነን፣ የምክር ቤት አባል ነን፣
ሴናተር ነን፣ አገረ ገዥ ነን፣ ባለኩባንያ ነን፣ ሊቅ ነን፣ የሚሉ ሁሉ በውስጧ የበቀሉ እሬቶች ሁሉ ይጠረጋሉ
ይጠፋሉ፡፡
› ምድሪቱ ከተሸከመቻቸው ሁሉ አውሬዎች ትጸዳለች ትላቀቃለች፡፡
› ባቢሎን ለሰው ዘር የደገሰችው ሁሉ ለራሷ የምትጋተው ይሆናል፡፡ ቁጣው ሲፈስስ ማን ያመልጣል? ማንም
አያመልጥም እሳቱ ሳይፈትሸው የሚያመልጥ የለም፡፡ በግንባሩ ምልክት ካለው ይድናል፡፡ ከሌለው የለም፡፡
በቁጥር 2 መልእክት እንደተጠቀሰው የሚድኑ ተለይተዋል የሚጠፉም እንዲሁ፡፡
ኢሳኢያስ ም. 24፡ 1 – 13
የዳዊት መዘ. 91/92/ 7 – 8
› እንደ ግለሰብ እንደቡድን እንደተደራጀ አመራርም ቢሆን ከዚች ከባቢሎን እንዴት እድናለሁ የሚል ከሚድኑት
የሆነ ልዑል ያሰበው ካለ ደግሞም ስላለ ይህን ማድረግ ይቻላል፡፡
ሀ/ መዳኛ ኢትዮጵያ ሀገሬ ናት፡፡ አዳኙም በኢትዮጵያ አገልጋዮቹን በዙፋኑ የሚያነግሰው የሰራዊት ጌታ
እግዚአብሄር ነው፡፡
ለ/ እምነቱም የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ነው፡፡
ሐ/ በዚችው በባቢሎን የተሰናዱ መጠለያዎች አሉ፡፡ እነሱም የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸውን
እምነታቸውን ያልጣሉ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገልጋዮች ያዘጋጁት የመድኃኒአለም
የእመቤታችን፣ የገብረኤል፣ የሚካኤል፣ ታቦታት ያረፉበት ቤተ ክርስቲያን ስላለ በዚያ ሄዶ እጅን ሰጥቶ ተዋህዶ
እምነትን መቀበል ብቻ ይቻላል፡፡ ከዚህ በኢትዮጵያ ለሚቆመው የልዑል መንፈሳዊና ስጋዊ አመራር ራስን
ማስገዛትና በተዘረጋው የመገናኛ መንገድ መጠቀምና ትእዛዝ ማክበር የመዳኛ መንገድ ነው፡፡ በዚያ የሚገኙ
የተዋህዶ ልጆች፣ የድንግል ልጆች በትጋት ለሚመለሱ እጅ ለሚሰጡ ማገልገል መርዳት ከዚህ የሚፈሰውን
መንፈሳዊና ስጋዊ አመራር ተግባራዊ ማድረግ ግዴታቸው ነው፡፡
ማንም ኢትዮጵያዊ ለምህረት የታሰበና የዳነ ሁሉ ለሚድኑ ልዑል ለመለሳቸው በትህትና ማገልገል፣
ማጽናናት፣ እውነቱን ማስጨበጥ፣ የልዑልን ቅን ፍርድ ማሳወቅ፣ ለምን ይህ ቅን ፍርድ እንደተፈረደባቸው
ሁሉንም በግልጽና ያለ ሽንገላ ማስረዳት ከፈጣሪ የታዘዘ ግዴታ ነው፡፡
የኢትዮጵያዊነትን ባህል፣ ጨዋነትን፣ ትህትናን፣ ሰውን መውደድን፣ ከውሸት መራቅን፣ ከምንዝርና
ከክፋት ርቆ የልዑልን ትእዛዝ ጠብቆ ሁሉም ፊት የሚበራ ብርሃን ሆኖ ማገልገል ይገባል፡፡ ከሚያበጥረው እሳት
ለመውጣት ሰዎች እንደ ጎርፍ ይመጣሉና አገልጋዮች ሊያደርጉት የሚገባውን ሁሉ ከፈጣሪ ጋር በጸሎት በመነጋገር
መርዳተ ማስረዳት ይገባል፡፡
ከኢትዮጵያ ሀገራችሁ የሚፈሰውን ዝርዝር መንፈሳዊና ስጋዊ መመረያ ለአገልግሎቱም የተመደቡትን
ከዚህ በመነሳት የሚመጡትን በፈጣሪ ፍቅር መቀበልና ጸንቶ ማገልገል፣ መታዘዝ ግዴታ መሆኑን አብሬ
አሳውቃችኋለሁ፡፡
ትንቢተ አሞፅ 9፡ 6 – 7
ስለግንኙነት መስመር ዝርዝሩ በሌሎቹ ርእሶች ስለሚገለጽ በጥንቃቄ ይመልከቱ፡፡
ከባቢሎን/አሜሪካ/ ጋር እጅና ጓንት ሆና የምትጓዘው ካናዳ ለአሜሪካ የተሰናዳውን የቁጣ እሳት
ትጋተዋለች፡፡ በሁሉም ስራቸው ከአሜሪካ የተለየ ምግባር የላቸውምና፡፡ አመንዛሪ፣ ቀጣፊ፣ ዘራፊ፣ የባቢሎን
የቅርብ ታዘዦች ናቸው፡፡ ስለዚህ በሁሉም መስፈርት ከአሜሪካ የማይለይ መለኪያ ይጠብቃቸዋል፡፡
6. ለ. ሜክሲኮ፡-
ይህችም ሀገር የአሜሪካ ደቡባዊ አዋሳኝ ስትሆን ከምንዝርናው ሌላ በእጽ ሱሰኝነት እና ነጋዴነት
የተጠመዱ የሚበዙባት ምንዝርናው እንደ አባትዋ ባቢሎን በምድር ያልታየ ነው፡፡ ወንጀል የበረከተባት ጥፋት
የነገሰባት ናት፡፡ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት ሌሎችም እምነቶች የሚበዙባት ናት፡፡
የዚች አገር ነጻነት በተባበሩት መንግስታት እንደ ነጻ አገር መታወቋ ብቻ ነው፡፡ እንጂ የአሜሪካ 53ኛ
ግዛት እንደማለት ናት፡፡ በመሆኑም ለአሜሪካ የሚደርሰው ሁሉ ለሷም ሳይጎድል ይደርሳታል፡፡
› አሜሪካ /ባቢሎን/ በፊልም እንደምታቀናብሩት ሁሉ በናንተው ላይ በፊልሙ የሚታየው ሁሉ ይፈጸማል፡፡
› የዘረጋችሁት የረቀቀ መገናኛ መሰለያ፣ ማጥፊያ ሁሉ ይጠፋል፡፡
› ይጠብቀኛል ብላችሁ ያሰናዳችሁት ምሽግ ሁሉ መቀበሪየችሁ ይሆናል፡፡
› ለሰው ዘር 200 ዓመት የዘለቀ መጠነ ሰፊ የጥፋት ዘር ዘርታችኋልና እናንተው ታጭዳላችሁ እናንተው
ትቀምሱታላችሁ፡፡
› የናንተ ጥፋት አውሮፓ ያሉ የአውሮፓ ህብረት አባላት የሆኑ ሁሉ በእኩል የሚጋሩት ይሆናል፡፡
› በእናንተ ጥፋት ህንድም፣ ቻይናም፣ ራሺያም እንደየተግባራቸው ይጋቱታል እንጂ አያመልጡም፡፡ አብራችሁ
ነግዳችኋል፣ መክራችኋል፣ አንዱን አንዱን ሊገዛ ሊበልጥ ለሰው ማጥፊያ ኒኩለር ,፣ ኬሚካል፣ ኒትሮን፣
ባዮሎጂካል፣ መሳሪያዎች ሰርታችኋል፡፡ እጅግ የረቀቁ የጥፋት መሳሪያ ባለቤት ሆናችኋል፡፡ በአለም የምትወስኑ
አምስት ሃያላን አገሮች አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ቻይና፣ ራሽያ፣ ፈረንሳይ፣ ከእናንተ በተጨማሪ ህንድ፣ ፓኪስታን፣
እስራኤል፣ ዛሬ ደግሞ ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ ኒክሌር ጨብጠዋል፡፡ ሺ ሰው መግደል ስላነሰ ሚሊዮኖችን በአንዴ
ማጥፋት እንደ ዘዴ ተወሰደ፡፡ ሌሎችም የናንተኑ ፈለግ ለመከተል እየጣሩ ናቸው፡፡
የቀደመውን የኒዩኩለር አሻራ ከጃፓን ሳያጠፉ በ10 ሺዎች የሚቆጠር እጅግ ሀይል ያለው ኒዩክለር
ሰብስባችኋል፡፡ አለም በጦር መሳሪያ ብዛት፣ በተዋጊ ጀት ብዛት፣ በታንክና በሚሳኢል ብዛት፣ በጦር መርከብ
ብዛት፣ በፈንጂ ብዛት የምድር ላይ መጋዘኖች ሁሉ ተጨናንቀዋል፡፡ የዲያቢሎስ ልጆች አስተማሪያቸው ዲያቢሎስ
እዚህ አድርሷችኋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የኤሽያ ህብረት፣ የላቲን አሜሪካ ህብረት፣
የአፍሪካ ህብረት ሁሉም የእናንተን ጉልበተኝነት የተቀበሉ ናቸው፡፡ የስጋ ሰው፣ በመንፈሳዊ አይኑ የታወረ ሰው፣
ፈጣሪውን በስም እንጂ በግብር አያውቅም፡፡ አምልኮቱ የስጋ አምልኮት ነው፡፡ ፈጣሪን ስሙን ይጥራ እንጂ
የሁሉ ነገር ጌታ መሆኑን ልቡና አእምሮው አይቀበልም፡፡ የሚያየውን የሚያምን እንጂ የማያየውን አይቀበልም፡፡
በዚህ ምክንያት አለም የሚያየውን መሳሪያችሁን፣ የጥበብ ርቀታችሁን፣ የሃብት ክምችታችሁን፣ የኑሮ ምቾታችሁን
ያምናል፡፡ ስለዚህ እንደ አምላክ ቆጥሮአችኋል፡፡ የእምነት ተቋሞች ሁሉ ፈጣሪን ስሙን በነጋ በጠባ ይጥሩ እንጂ
አምላካቸው እናንተ ናችሁ፡፡ የምትሉትን ይሰማሉ የምታዟቸውን ይታዘዛሉ፣ ለእናንተ ሰላም የላሉ ለዚህ ደግሞ
የቫቲካኑ ፖፕ፣ የፕሮቴስታንቱ ቄስ፣ የአንጀሊካኑ ጳጳስ፣ የቡድሃ መነኩሴ፣ የሙስሊሙ ሙፍቲ/መሪ/ ሁሉም
ታዛዦቻችሁ ናቸው፡፡
እንግዲህ ይህን ሁሉ የተመለከተ አምላክ፣ ሰማይና ምድርን በፈቃዱ ያጸና አምላክ፣ ሁሉንም የሚሽር
የሚያጸና እግዚአብሄር አብ እግዚአብሄር ወልድ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ትእግስቱ አለቀ
ተሟጠጠ፡፡ በ7/3/1998 ዓ.ም. በችሎቱ ተቀመጠ፣ ወንወጀላችሁ ሁሉ ተመዘነ፣ በጎም ተፈልጎ ጠፋ፣ ምድር ሁሉ
ተፈተሸች በየትኛውም ስፍራ የናንተ ጌታ ዲያቢሎስ የጨለማው ገዢ ፍፁም ወርሶታል፡፡ አንድም ነገር ሳይቀር
ታየ እጣ ፈንታችሁ ተገለጸ፣ ውሳኔውም ተወሰነ/ተፈረደ/ በፍርዱም የሚጠብቃችሁ ሁሉ ተገለጸ፡፡ የይግባኝም
እድል ሰጠ፡፡
በ27/9/2000 ድጋሚ አለም ታየች ተመዘነች አንድም የሚፀፅት ከውስጣችሁ ጠፋ ለሕዝቡ የሚገልጽ
ወደፈጣሪ የሚመለስ ጠፋ፣ በይግባኝም ቢታይ ያው ሆነ ጭራሽ ባሰ፡፡ የመጨረሻው ውሳኔ ጸና እንደ ውሳኔው
ከ3 ወር በኋላ ምልክቱን ማሳየት ጀመረ፡፡ ኢኮኖሚያችሁ ተመታ ምንም አትጸጸቱም፣ ስለዚህ የመጨረሻውን
ውሳኔ ወደ ተግባር የሚለውጠው የአፈጻጸም ውሳኔ ይኸው ወጣ አበቃ ! ይገባኝ የለም ሁሉም ተዘጋ ! እንግዲህ
የታመንክበት ያድንህ ምሽግህ ይከልልህ፣ እውቀትህ ይርዳህ፣ በተጠንቀቅ የቆሙት የልዑል ሃይሎች የአፈጻጸም
ትእዛዛቸውን ተረክበዋል፡፡ አከተመ፡፡
የዳዊት መዝ. 20/21/ ፡ 8 – 13
እንግዲህ አለም በአምላኩ በአሜሪካ የተከሰተውን የመሪ ቀለም መለወጥ እንደ ትልቅ ዜና ሲቀባበለው
አይተናል፡፡ እኝህ ክልስ መሪ ተአምር ይፈጥራሉ እየተባሉ ሰው ሁሉ ወደ አሜሪካ ሲያንጋጥጥ እያየን ነው፡፡ ነገር
ግን በፈጣሪ ውሳኔ ላይ የሚለውጠው የለም፡፡ የሚያመጣውም ነገር የለም የተለዋጩም ሆነ ሌላው ሁሉም
ተጠያቂ የባቢሎን አለቆች ናቸው፡፡
7. ሀ. ኩባ፣ ኒካራጓ፣ ጓቲማለ፣ ኢልሳልቫዶር፣ ኮስታሪካ፣ ሆንዱራስ፣ ጃማይካ፣ ፓናማ፣ ሃይቲ፣ በሃማስ፣
እኒህ ሃገሮች አብዛኞቹ በውሃ የተከበቡ ደሴቶች ናቸው፡፡ በነዚህ አገሮች ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ የሚያንሱት፣
እስላም፣ ሌሎችም የሞሉባቸው ናቸው፡፡ በጃማይካ የሚገኙት የራስ ተፈሪያን አምላኪዎች ሲለዩ በስተቀር፡፡
እነዚህ አገሮች የምንዝር፣ የእጽ ወንወጀሎች ጎልተው የሚታዩባቸው ናቸው፡፡ አብዛኛው ሕዝብ በሃጢያት
ማእበል የሚዋኝ ነው እነዚህም በግለሰብም ይሁን እንደ ቡድን እንደድርጅት እንደ መንግስት ለሌላው የሚሆነው
መስፈሪያ ይሰፈርላቸዋል፡፡ ተሰፍረዋልም፡፡ በእሳት ይፈተሸሉ የሚድነው ይድናል የሚጠፋው ይጠፋል፡፡
እጅግ ደቃቅ የሆኑት ደሴቶች ፤ እነዚህ ደሴቶች ከላቲን ሰሜን ምስራቅ የሚገኙ ናቸው፡፡ ቨረጂን ደሴት
በአሜሪካና እንግሊዝ ስር ያሉ፣ አነጎሊያ/ እንግሊዝ፣ አንቲጉዋ፣ ባርበዶዋ፣ ሴነት ቪትሰነቬስ፣ ጓድላፕ/ ፈረነስይ፣
ማረቲን ኩ/ፈረንሳይ/ባርባዶስ/ ሲነትቪንተስ ግራናዳስ፣ ግሪናዳ፣ ትሪንዳድ እና ቶቤጎ፣ እነዚህ ደሴቶች በእንግሊዝ፣
በፈረንሳይ፣ በአሜሪካ ቁጥጥርና ተጽእኖ ስር ያሉ ናቸው፡፡ በጌታቸው መስፈርት ይዳኛሉ ፡፡ የጌቶቻቸውን
ወንጀል ወርሰዋልና፡፡ በሁሉም መልኩ ይበጠራሉ፡፡
7 - ለ ቬንዝዋላ፣ ኮሎምብያ፣ ሱማትራ፣ ፍሬንች ጊዋና፣ ኤኳዶር፣ ፔሩ፣ ብራዚል፣ ፓራጓይ፣
ቮሊቪ፣ ቺሊ፣ አርጀንቲና፣ ኡራጓይ፣ እነዚህ የደቡብ አሜሪካ አገሮች ናቸው፡፡ እምነታቸው ካቶሊክ የሚበዛ
ነው፡፡ ከዚያ በመቀጠል ፕሮቴስታንት፣ እስላም፣እምነት የለሽም በማይናቅ ቁጥር ያለበት ነው፡፡ ምንዝርና እጅግ
በከፋ መልኩ የሚታይበት ነው፡፡ ወንጀል፣ የሰው ሕይወት ማጥፋት የበዛበት ነው፡፡ ጥንቆላ፣ መተት እንዲሁ
የበዛበት ነው፡፡ ከፊሉ በቀጥታ በአሜሪካ ተጽኖ ስር ሲሆን እንደ ቬንዙዋላ አይነቱ አሜሪካንን የማይደግፍ አለ፡፡
ይሁንና በጥቅሉ ሲታይ ክልሉ ከዋናው አሜሪካ የማያንስ የምንዝርና ሕይወት ስር የሰደደበት ነው፡፡
በመሆኑም እንደ ግለሰብም፣ እንደ ኃይማኖት ተቋምም ፣ እንደ መንግስትም፣ ሁሉም ቅጣቱን ይቀበል ዘንድ
ተለይቶ የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርዱ በእሳት ማበጠሪ መበጠር ይሆናል፡፡
የተጠቀሱት በሙሉ ሰላምን የሚያገኙት ከእሳቱም ማበጠሪያ መውጫው አንድ ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ
የሚጸናውን የብርሃን እምነት ተዋህዶ ኦርቶዶክስና መንፈሳዊና ስጋዊ አገዛዙን መቀበል ብቻ ነው፡፡
8 – 1 ሶርያ ፣ ኢራን-
እኒህ አገሮች በእስልምና ህግ/ የሸሪአ ህግ/ የሚመሩ አገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ አገሮች ከባቢሎን/አሜሪካ/
ጋር የሚጋጩ ናቸው፡፡ እስራኤል ዋና ጠላታቸው ናት፡፡ ሁለቱም የሺአት እምነት የሚከተሉ፣ ያከረሩ አገሮች
ናቸው፡፡ ነዳጅ ዋና የገቢ ምንጫቸው ነው፡፡ እነዚህ አገሮች ከፈጣሪ ህግ ጋር ዘወትር በመጋጨት ላይ ያሉ ናቸው፡
፡ ከእምነታቸው ከንቱነት ሌላ የምንዝርናው፣ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ ተጨማሪ ወንጀላቸው ነው፡፡ እስላሙ
በሚመዛንበት የሚመዘኑ ናቸው፡፡ ከመሰረታቸው ፍፁም የሚጠፉ ናቸው፡፡ የሚተርፉ እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡
ስማቸው ብቻ በነበሩ ይታወሳል፡፡
8 – 2 ሰውዲ አረቢያ፣ ኩዌት፣ ኢምሬትሰ፣ ዱባይ፣ ኳታር፣ ዘማን፣ ባህሬን፣
እነዚህ የ ሱኒ ዝርያ የሚበዛባቸው ሲሆኑ በመንግስት የታወጀ ሌላውን ያገደ እስልምና ሕግ
የሚመራቸው ናቸው፡፡ የእስልምናው መሰረት ከነቢዩ ተብየው መሃመድ መቃብር ጋር በመካ ሳዑዲ ይገኛል፡፡
በአመት በአመቱ ከ 3 – 5 ሚሊዮን እስላም ወደዚያ “ሊባረክ” ይመላለሳል፡፡ ዛሬ አለምን የሚያምሰው
እስልምና መነሻው ከዚሁ ስፍራ ነው፡፡
ትንቢተ ኢሳኢያስ ፡ ም ፡ 33፡ 9 – 12
እነዚህ አገሮች በነዳጅ የከበሩ ናቸው፡፡ ዲብሎስ ዋናው ዙፋኑ ያደረገው በዚህ ነው፡፡ አገዛዛቸውም
የሃብት ምንጫቸውም፣ ዝርያቸውም ለማቸውም ሁሉ አንድ አይነት ነው፡፡ በአገራቸው ምንም አይነት የክርስትና
እምነት አይካሄድም፣ የምንዝርናና የሰካራምነት ቁንጮ ናቸው፡፡
እነዚህ ምን ይገጥማቸዋል? እነዚህ ከውስጣቸው የሚተርፍ ይገኝ ይሆን? ተብሎ ቢታሰብ ይቀላል፡፡
በፍፁም ከምድረ ገጽ የሚጠፉ ናቸው፡፡ ከነአምልኮአቸው ከነ ጣኦታቸው የሚጠረጉ ናቸው፡፡ፍርድ ወጥቷል፡፡
ሃብታቸው ለሚቀረው የእግዚአብሄር ህዝብ ይሆናል፡፡ በነበሩ የሚቀሩ የሚወራ ታሪክ ይኖራቸዋል፡፡ በዐይን
የሚታይ፣ የሚዳሰስ ምልክት አይተውላቸውም፡፡ በሕይወት የሚተርፉት እጅግ የወደቁ ፣የተናቁ፣ ፍፁም ጤና
የራቀው ሕይወት ይመራሉ፡፡
8 – 3 እስራኤል -
ይህች አገር በእግዚአብሄር ፈቀድ የተፈጠረች አገር ናት፡፡ ሕዝቧም ሂትለር ከጨፈጨፈው 6 ሚሊዮን
ያህል የተረፈ ነው፡፡ ይህች አገር ምድሪቱን የወረሳት ልዑል ነው፡፡ የአብርሃም ዘሮች ናቸው ፣ የሙሴ ዘሮችም
ናቸው፣ የታላላቅ ሐዋርያት ዘሮች ናቸው፣ የድንግል ዘሮች ናቸው፣ የጌታም ወገኖች ናቸው፡፡ በእነዚህ ሕዝቦች ላይ
የሚያርፈው ቅጣትም ሆነ ምህረት በልዑል እጅ የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን ከአህዛብ የተማሩትን የሰበሰቡትን ሰው
ዘር ማጥፊያ መሳሪያ ያጡታል፡፡ እንደ አገር እንደ ሕዝብም ይኖራሉ፡፡ ልዑልን ያውቁታል፡፡ ከውስጣቸው
በቀለውን የሰቀሉትን ጌታ የአለምን መድሐኒት መልሰው በታለቅ ፀፀት ይረዱታል፡፡ ለዚህ የሚታደሉ ባይበዙም
ይህ ይሆናል፡፡
8 – 4 ሊባኖስ፣ ኢራቅና ቱርክ፡-
እነዚህ አገሮች እጅግ ብርቱ ፈተና ውስጥ ያሉ አገሮች ናቸው፡፡ ሊባኖስ ኢራእና ቱርክ የጎሪጥ የሚተያዩ
ህብረተሰብ ያቀፉ ናቸው፡፡ በፍፁም ተጠርገው የሚጠፉ ናቸው፡፡
8 – 4ሀ ሊባኖስ፡-
ሱኒ ሙስሊም፣ ሺያት ሙስሊም፣ ፍልስጤም ማሮናይት/ ድሩዝ / ክርስቲያን ያለበት አገር ነው፡፡
መንግስታቸው የነዚህ ቅልቅል ሲሆን በትንሽ ግጭት የሚፈርስ ነው፡፡ ሁሉም እርስ በእርስ የሚፈጁ ናቸው፡፡
ሂዝቦላህ የኢራንና የሶርያ ወዳጅና ተደጋፊ ነው፡፡ ሱኒው በአረቦች/ የአሪሪቡድን ማለት/ የሚደገፉ ሲሆን
በአሜሪካም ይደገፋል፡፡ እስራኤል የጋራ ጠላታቸው ናት፡፡ በእነዚህ ህዝቦች ሌላው በሚታይበት መስፈርት
የሚሰፍሩ ናቸው፡፡ በነዚህም ውስጥ የምንዝርና፣ ግድያ ሀጢያት ስር የሰደደ ነው፡፡ ከክህደታቸው በተጨማሪ
ስለዚህ ብረቱ ማበጠሪያ ያበጥራቸዋል፡፡
8 – 4ለ ኢራቅ፡-
ይህ ህዝብ የሺያት ደጋፊ፣ ሱኒ ደጋፊ፣ የኩርድ ደጋፊ ያለበት ነው፡፡ ተቧድነው የሚፋጁበት አገር ነው፡፡
እስልምና ባሰናዳው መሳሪያ ራሱን ለመፍጀቱ ጥሩ ምሳሌ ሆነው የሚታዩ ናቸው፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮች
ለክርስቲያን የደገሱት መሳሪያ ለራሳቸው መጥፊያ ለመሆኑ ከኢራቅ የበለጠ ማስረጃ የለም፡፡ አሜሪካ ለጥቅሙ ሲል
የገባበት ሲሆን ይህ ህዝብ የሚጠብቀው ቅጣት ከአሁኑ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡
8 – 4ሐ ቱርክ፡-
ይህ ህዝብ ኩርድ ያለበት አብዛኛው የእስልምና ተከታይ የሆነ የምእራብን ሴኩላር አስተዳደር
የሚያራምድ የአሜሪካ የጦር ድርጅት፣ የአውሮፓ የጦር ድርጅት ኔቶ አባል የሆነ አገር ነው፡፡ የዚህ አገር ጥፋት
ከአሜሪካ ከአውሮፓ ጥፋት አይለይም፡፡ ጉዳታቸው እጅግ የሚከብድ ነው፡፡
9 - ኤሽያ፡-
ይህ ሰፊ ክልል ነው በዋናነት ራሽያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ጃፓንን የመሳሰሉ አገሮች የተካተቱበት ነው፡፡
ከዋና ዋናዎቹ እንጀምር፡-
9 – 1 ራሽያ፡-
ይህ አገር ከአሜሪካ ቀጥሎ ወታደራዊ ጉልበት ያለው አገር ነው፡፡ ራሽያ ከ100 ሚሊዮን የማያንስ
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ያለበት ሲሆን እምነቱ በውስጡ ከተዋህዶ የወጣ አካሄድን የሚሄድ በመሆኑ ተዋህዶ
ኦርቶዶክስ እምነትን በተግባር የማይገለጽበት ወደ ካቶሊክ ስርአተ እምነት ያዘነበለ ነው፡፡ በካቶሊኮች ስልታዊ
አካሄድ የተተበተበ ነው፡፡
በሌሎችም በዚሁ በራሽያ ግዛት ውስጥ የነበሩ ተመሳሳይ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ተከታዮች ያሉ ሲሆን ወደ
አውሮፓ በመቀላቀላቸው የካቶሊክ ተገዢ ሆነዋል፡፡
ራሽያ ከ አምስቱ ሃያላን አንዱ ስትሆን ለአሜሪካ በንጽጽር በጉልበቷ የምትመጣጠን ናት፡፡ በኢኮኖሚ
በመበታተኗ ሳቢያና ከባቢሎን ጋር በተደረገ የበላይነት ፍልሚያ የተጎዳችና አሁንም መልሳ በማገገም ላይ ያለች
አገር ናት፡፡ አገሪቱ የኮምኒስቶች/ የከሃዲዎች አገርም ናት/፡፡
በባቢሎን የሚታየው ምንዝርና፣ ሶዶማዊነት፣የተደራጀ ዘረፋ፣ ሌብነት ዕብሪተኝነት፣ የሚታየባት አገር
ናት፡፡ በዚች አገር የእምነት ሰዎች ቢኖሩም በከሃዲዎች የተዋጡ ናቸው፡፡
ይህች አገር እንደ ሌላው ሁሉ የሚያበጥራት እሳት ያገኛታል፡፡ የሰበሰበችውን ኒውክለር፣ ኑውትሮንት፣
ባዮሎጂካል፣ ኬሚካል፣ የጦር መሳሪያ ታንክ፣ የጦር ጀት፣ የጦር መርከብ፣ ፈንጂ፣ ሁሉም ማጥፊያዎች ከባቢሎን
በሁለተኛ ደረጃ ያስቀምጣታል፡፡ በመሆኑም እስክትጥለው ድረስ እሳት ይበላታል፡፡
በአጥቂ ሳተላይቶች፣ በህዋ ላይ የተደራጁ መሳሪያዎች ባለቤትም ናት፡፡ ልክ እንደ ባቢሎን ምድሩ
አንሷት ህዋ ላይ የተሰቀለች አገር ናት፡፡
ሁሉም ጉልበቷ ይወገዳል፡፡ ከዚች አገር ብዙዎች ወደ እውነቱ ወደ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ይመለሳሉ
ይህም የሚሆነው ሁሉም ትምክህቷ ሲጠፋ ብቻ ነው፡፡ ያከማቸችው የጦር መሳሪያ በሙሉ ይጠፋል፡፡ የትም
ይኑር የት እጣው ፈጽሞ መጠረግ ይሆናል፡፡ ይችም አገር ጽዋዋን ጠጥታ የሚተርፈው ወደ ኢት/ተ/ኦርቶዶክስ
እምነትና ወደ መንፈሳዊውም ስጋዊውም ብርሃናዊ አገዛዝ እራስን ሲመልስ ብቻ ነው፡፡ ሰላምን የሚያገኘው፡፡
በእምቢታ ከገፋች ደግሞ ከባቢሎን/አሜሪካ / የማያንስ በትር ይጠብቃታል፡፡ ያገኛታልም፡፡
ከሷ የወጡት ወደ ምእራብ አውሮፓ የተቀላቀሉ እነ ፖላንድ፣ ዩክሬን፣ ቼክ፣ ክሮኤሽያ፣ ቦስንያ፣
ሃንጋሪ፣ ቡልጌሪያ፣ ሮማንያ፣ ሁሉም ለአውሮፓ የሚመጣው መስፈሪያ መስፈሪያዎች ይሆናል፡፡ ፍጹም
ይጠረጋሉ፤ ወደ ትቢያነት ይለወጣሉ፡፡ ከአውሮፓ ጋር ሲቀላቀሉ ከካቶሊክ፣ ከፕሮቴስታንት፣ ከሶዶሞች፣
ከፈላስፎች፣ በእውቀታቸው ከሚታበዩ ጋር እድር ገብተዋል፡፡ መቀበሪያቸው ይሆናል አብረው ይጠረጋሉ
በውስጣቸው ያሉ ቅኖች በፍጥነት እራሳቸውን ወደ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ መመለስ አለባቸው፡፡ ምንም ቀን የለምና፡፡
የማምለጫ ቀዳዳ ሸሽቶ መጠለያ አገሬ ኢትዮጵያ የልዑል የብርሃን አገዛዝ የሚጸናባት ተዋህዶ ኦርቶዶክስ የድንግል
እርስት የሆነችው ብቻ ናት፡፡ ማንም የአለም ክልል መጠለያ አይሆንም በውስጡ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ካለ
ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ብቻ የተጠለለ ይድናል፡፡ ሌላ እንደ አገር ከኢትዮጵያ ውጪ መጠለያ የለም፡፡
9 – 3ሠ በርማ፣ ታይላንድ፣ ካምቦዲያ፣ ቬትናም፣ ላኦስ፣ ሰሜነረ ኮርያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኔፓል
እነዚህ ሕዝቦች ተቀራራቢ ባህል፣ አስተሳሰብና የእምነት አካሄድ ያላቸው ናቸው፡፡ ከሰሜን ኮሪያ
ኮሚንስትነት ውጪ የተቀሩት በሙሉ ጣኦት አምላኪዎች የቡድሃ እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ በደቡብ ኮሪያ ብቻ
ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ በብዛት ያለ ሲሆን በሌሎቹ በመጠኑ አሉ እንጂ እምነታቸው በቻይና የበቀለው ኮነፊሺያን
ትምህርትና ቡድሃ ነው፡፡ በቅርቡ ወሰናቸው ላይ ባለ የቡድሃ መቅደስ በይገባኛል ታይላንድና ካምቦዲያ ጦር
ተማዘውበታል እስካሁንም ያልፈቱት ነው፡፡
9 – 3ረ ጃፓን፡-
ይህች አገር ለኤሽያ በስተምስራቅ ለአሜሪካ በስተምእራብ ያለች ደሴት አገር ነች፡፡ የጃፓን ህዝብ
አኗኗር ከባቢሎን አሜሪካ ምንም ያልተለየ ነው፡፡ ጃፓን ከአሜሪካ ቀጥሎ 2ኛዋ የኢኮኖሚ ሃያል ናት፡፡ በእውቀት
በኢንዱስትሪ እድገት፣ በኤሌክትሮኒክስ፣ በመኪና ምርት፣ በመድሃኒት፣በብዙ የቴክኖኮጂ ምርቶች ያደገች የበለጸገች
ናት፡፡ ሕዝቡ እምነቱ እንደ ጌታዋ አሜሪካ የተመሳቀለ ነው፡፡ አብዛኛውም እምነት የለሽ ነው፡፡
ምንዝርና ግብረሶዶም እጅግ የተንሰራፋበት አገር ነው፡፡ እንደ አሜሪካ ፍጹም የልዑል ጠላት ሆና
የተቀመጠች አገር ናት፡፡
እጣዋ፡-
ይህች አገር ከአሜሪካ በማይተናነስ ቅጣት ትመታለች የታበየችበት ሃብት፣ ንብረት ይጠፋል፡፡
ያከማቸችው ገንዘብ ወርቅ ፍጹም ይጠረጋል፡፡ የሂሮሺማና ናጋሳኪ ጉዳትን በሺ እጥፍ ሆኖ ይመጣባታል እጅግ
ጥቂት ሰው ቢተርፍ ነው፤ ጉዳቷ እጅግ ፈጣንና በዝግታም የሚከናውን ነው፡፡ አውቀው እንዲከስሙ የት ድረስ
ፈጣሪን እንደናቁ እንዲረዱ የሚያደርግ እሳት ይጠርጋቸዋል፡፡
ጃፓን ሃብቴ፣ ጃፓን ቅርሴ፣ የሃይል መሰረቴ ነው የምትለው ሁሉ በእሳት ባህር ይበላል፡፡ የሚወርድባት
ጥፋት የማያቋርጥ ፍጹም የሚያስጨንቅ ይሆናል፡፡ መዳን የሚቻለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው፤ መዳን
የሚቻለው በኢትዮጵያ ለሚቆመው የእግዚአብሄር መንግስት መንፈሳዊና ስጋዊ አመራር እጅ ያለምንም ቅድመ
ሁኔታ በመስጠት ነው፡፡ በዚህም እንደመንግስት፣ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ድርጅት ራስን ማዳን ይቻላል፡፡ ከዚህ
ውጪ የሚመጣ ነገር የለም፡፡
10 – 1 አውስትራሊያ፣ ኒውዚላንድ፣ ፓፓው ጊኒያ፣ ፊጃ፡-
ይህ ክልል ከኤሽያ በስተደቡብ በሰላማዊ ውቅያኖስና በህንድ ውቅያኖስ መሃል ያሉ አገሮች ናቸው፡፡
አውስትራሊያም ሆነ ኒውዝላንድ የእንግሊዝ ዝርያዎች የሚገዙት የሚመሩት አገር ነው፡፡ የመሰረቱ
ዜጎች አቦርጂኖች ተገዢ ናቸው፡፡ ክልሉ በተዘዋዋሪ የእንግሊዝ ቅኝ ነው፡፡
አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድ፣
ያሉበት የጦር ድርጅት አላቸው፡፡ እነዚህ አገሮች ፍጹም የአውሮፓ ተግባር የሚታይባቸው ናቸው፡፡
ምንዝርና ግብረሶዶምነት ከማንም አገር በላይ በግልጽ የሚከናወነወበት ነው፡፡
ትንቢተ ኢሳኢያስ፡ 59 ፡ 3 - 8
እነዚህ ሃገሮች ፍፁም በጣዖት የሚያመልኩ ናቸው፡፡ ፈጣሪ ቀናተኛ አምላክ የሆነውን ሁሌ ሲያስቆጡ የኖሩ
ናቸው፡፡ በመሆኑም በመከራው እጅግ ይበጠራሉ ልዑል የማራቸው ይተርፋሉ፡፡
10-2 ማሌዥያ፣ ኢንዶንዢያ፣ ፊሊፒንስ፣ ታይዋን፣ ሲንጋፖር፡-
እነዚህ ሃገሮች በአብዛኛው በእስልምና እምነት የተሸፈኑ ናቸው፡፡ በብዙ ደሴቶች የታቀፉም ናቸው፡፡
በማእከላዊ የሕንድ ውቅያኖስ የሚገኙ ናቸው፡፡ የአክራሪነት አንዱ ምሽግ እነዚህ አገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ፍፁም
ጣኦት አምላኪዎች ከመሆናቸውም በላይ በእስልምናውና በጣኦቱ አምልኮ፣ ፍፁም ልቅ በሆነ ዝሙት፣ ሰዶማዊነት
የተበከሉ ናቸው፡፡ እነዚህም አገሮች በጌታ የቁጣ እሳት የሚመቱና የሚበጠሩ ናቸው፡፡ ተራፊው ጥቂት ጠፊው
እጅግ ብዙ ነው፡፡
10-3 ህንድ፣ ሲሪላንካ፣
ህንድ በዓለም ሁለተኛውን የሕዝብ ብዛት ከቻይና ቀጥሎ ያቀፈች ናት፡፡ ወደ 1.1 ቢሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ አላት፡፡
ኢኮኖሚዋ እንደ ቻይና በመመንጠቅ ላይ ያለ ሲሆን በሁለቱም መሀል የገበያ ትግል ይካሄዳል፡፡
ህንድ ሂንዱስታን የ2/3 ሕዝብ እምነት ነው፡፡ ወደ 200 ሚሊዮን የሚጠጋ እስልምና እምነት ተከታይ አላት፡፡
ህንድ በግልፅና በማያሻማ መልኩ ጣዖትን ታመልካለች፡፡ የሃዋርያትም ደም በውስጧ አለ፡፡ ህንድ ላምን
እደአምላክ ታያለች አታርድም አትበላም፡፡
ሕዝቡ ፍፁም ለጣዖት ተገዢ ነው፡፡ ምንዝርና በዚህም ሕብረተሰብ አለ፡፡ ኑዪክለርም ታጥቃለች፡፡
ምን ይጠብቃታል፡፡
› በመላው ህንድ ያሉ የጣዖት አምላኪዎች ይጠረጋሉ፡፡
› በውስጧም ያሉ ጣኦቶች ተጠርገው ይጠፋሉ፡፡
›ጉልበቴ የምትለው የጦር መሳርያ ሁሉ ከነአዛዡ እና ከታዛዡ ጋር አብረው ይጠፋሉ፡፡ በህንድ ያለ
የተዋህዶ ኦርቶዶክስ አማኞች ይቀራሉ የተጠለለባቸውም ይድናል፡፡
በዚህ በኢትዮጵያ ያለውን ብርሃናዊ አገዛዝ ስትቀበልና ስትንበረከክ ሰላሟን ታገኛለች፡፡ አለበለዚያ በውስጧ
የሚነደው እሳት ሁሌ ያነዳታል እስክትጠፋም ይጎዳታል፡፡ ይጠርጋታል፡፡
ስሪላንካም በህንድ ያተለየ እጣ ይጠብቃታል፡፡
ትንቢተ ኢሣኢያስ፡ ም 14 በሙሉ
ብዙዎቹ የአውሮፓ አገሮችና የአሜሪካ ግዛቶች ስካንዲኔቪያኖች ሶዶምነትን የፈቀዱ ናቸው፡፡ ውርጃ እንደመብትም
በማጽናት ሴቱን ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ያደረጉ ናቸው፡፡
በመሆኑም እነዚህ አገሮችም የአውሮፓ እጣ ፋንታ ይጠብቃቸዋል፡፡ አውስትራሊያም ሆነ ኒውዚላንድ ሁሉም
በከባድ እሳትና ማዕበል ይጠረጋሉ፡፡ የሚተርፈው እንደሌላው ሁሉ እጃቸውን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤ/ክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ብርሃናዊ አገዛዝ በመስጠት መንበርከክ ግዴታቸው ይሆናል፡፡
11.0 አፍሪካ
ይህ ክልል በሁሉም ነገሩ የተጎዳ ክልል ነው፡፡ 52 የሚሆኑ አገሮችን አቅፏል፡፡ ይህን ክልል አውሮፓውያን
ተቀራምተው ገዝተውታል፡፡ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ፖርቱጋል፣ ስፔን፣ ጀርመን፣ ደች፣ ጣሊያን፣ ቤልጂየም፣
አሜሪካ ተቀራምተው ገዝተዋል፡፡
እንግሊዝ፡- ግብፅን፣ ሱዳንን፣ ሰሜን ሱማሌን፣ የገዛች ሲሆን ስፔኖች፡- እን ሞሮኮን፣ ማውሪታንያን፣ ሲገዙ
ጀርመን፡- ቱኒዝያን፣ ፈረንሳይ፡- ማእከላዊ አፍሪካን በሙሉ፣ ፖርቱጋል፡ እነ ሞዛምቢክን፣አንጎላን ሰለገዙ
ቤልጄም፡- ኮንጎን ገዝታለች፡፡ ጣሊያን፡- ሊቢያን፣ ላጭር ጊዜ ኢትዮጵያን፣ ላጭር ጊዜ ደቡብ ሱማሌን ገዝተዋል፡፡
ደቡብ አፍሪካን ደቾች ገዝተዋል፡፡ ዚምባቡዌና ናሚቢያን እንግሊዝ ገዝታለች፡፡ አሜሪካ ደግሞ ላይቤሪያን
ገዝታለች፡፡
አፍሪካ ፍጹም የነጮች ተገዢ ነበረች፡፡ ለአሜሪካ ርካሽ ጉልበት የተዛቀው ከአፍሪካ ነው፡፡ ከከብት ባነሰ የሚታይ
ህዝብ ነበር፡፡ የባሪያ ንግድ ውጤት ዛሬ አሻራው በአሜሪካ የሚታይ ነው፡፡
11.1 ምዕራብ አፍሪካ
ሞሮኮ፣ ሞውሪታንያ፣ አልጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ኬፕቤርድ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ጊኒ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ አይቬሪ
ኮስት፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጋና፣ ቶጎ፣ ቤኒን፣ እኒህ አገሮች በከፍተኛ ደረጃ የባሪያ ንግድ የተካሄደባቸው ናቸው፡፡
ሞሮኮ፣ ማውርታኒያ፣ አልጄሪያ፣ ሴኔጋል ፍጹም የእስልምና አገዛዝና የእስልምና እምነት የተንሰራፋባቸው ናቸው፡፡
እነዚህ አገሮች ሙሉ በሙሉ የአሜሪካና የአውሮፓ ተገዢዎችና ፖሊሲ አራማጆች ናቸው፡፡ምንዝርና የገነነበት
ወንጀል የተንሰራፋበት አክራሪ የሰፈነበት መንግስታዊ ዘረፋ እጅግ ስር የሰደደበት ፍጹም ውሉ የጠፋ የሁሉ
መራገጫ ክልል ነው፡፡
ይህንን ክልል ብርቱ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ በዚህ ክልል የሚያርፈው የቁጣ በትር ከመካከለኛው ምስራቅ
አገሮች የማያንስ ነው፡፡ ይህ ሕዝብ ምንም የእምነት ጽናት የሌለው ጣኦት የሚያመልክ እስልምናን የሚከተል
ሌሎችም ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት በመጠኑ ያለበት ነው፡፡ ብርቱ ቅጣት እጅግ ከባድ ጥፋት ይገጥመዋል፡፡ ወደ
እውነት ሲመለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ብቻ ሰላምን ያገኛሉ፡፡
11-2 ሰሜን አፍሪካ፡-
ይህ ክልል የአፍሪካ ሰሜናዊት ግዛት ሲሆን በዚህ ውስጥ ግብፅ፣ ሊቢያ፣ ቱኒዚያ የሚገኙበት ነው፡፡ በውስጣቸው
የእስልምና እምነትና አገዛዝ የሰፈነበት ነው፡፡
ይህ ክልል በአፍሪካ የእስልምና እምነትን ተፅዕኖ ለማሳረፍ መንደርደሪያ ሆኖ እያገለገለ ያለ ነው፡፡
11-2-ሀ ግብፅ ፡-
የግብፅ አስተዳደርና ግብፅ ረጅም ታሪክ ያላት አገር ናት፡፡ ህይወቷ ከኢትዮጵያ ምድር የሚፈሰው አባይ ነው፡፡
ለብዙ ሺ አመታት ያጠጣት ያበላት ነው፡፡ በዚች አገር ብዙ አይነት ክንዋኔዎች ተፈጽመዋል ቀድሞ በፈርዖን
ትመራ የነበረችው ግብፅ በራሷ የኢትዮጵያ ግዛት ነበረች፡፡ ንጉሦችዋም የሚሾሙት ከዚህ ከኢትዮጵያ /የኩሽ ግዛተ
መንግስት/ ይባል በነበር አገዛዝ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ለዚህ ለአባይ ውኃ ሲባል ለብዙ ዘመን የተቀናበረ ጥቃት በመሰንዘር ለዛሬው የአገሬ ጥፋት በቁጥር 1
የምትሰለፍ አገር ናት፡፡ ግብፅ በውስጧ ካለው መጠነኛ የተዋህዶ አማኝ በስተቀር እስልምናን የሚከተል አገር
ነው፡፡ በዚች አገር ጥፋት እጅግ ብዙ ዜጎችዋ ይጎዳሉ፡፡ በከፋ የረሃብ፣ የበሽታ፣ የፍጅት መከራ ይመታታል፡፡
እንደመንግስት መቆምም ያቅታቸዋል፡፡ የሰበሰቡት መሣሪያ ከነተጠቃሚው ይጠፋል፡፡ በኢትዮጵያ ተዋህዶ እምነት
አስተዳደር ስር አሜን ብለው ካልተገዙ ጥፋታቸው ፈፅሞ ከምድር የሚያጠፋቸው ይሆናል፡፡
ትንቢተ ሕዝቅኤል 29 ፡ 1
11-2-ለ ሊቢያ
ይህችም አገር በነዳጅ የበለጸገች የእስልምና እምነት ተከታይ አገር ናት፡፡ ከግብፅ ጎረቤቷ ያልተለየ እጣ
ይጠብቃታል፡፡ ትምክህቷ ሁሉ ይጠፋል ተራፊዎች ጥቂት ይሆናሉ፡፡
11-3-ሐ ቱንዝያ
ይህችም አገር ብዙም ባትበለጽግ ሙሉ በሙሉ የእስልምና እምነት ተከታይ ሀገር ናት፡፡ እጣዋም ከግብጽና
ከሊቢያ ያልተለየ ይሆናል፡፡
መ.ነገሥት ካልእ 17 ፡ 7 – 18
12-0 ማእከላዊ አፍሪካ
ይህ የአፍሪካ ማእከል ማእከላዊ አፍሪካን፡- ናየጄሪያን፣ አንጎላን፣ ቻድን፣ ጋቦንን፣ ካሜሩንን፣ ይይዛል፡፡ በዚህ
ክልል ግጭት የሚበዛበት አካባቢ ነው፡፡ እምነቱ የተመሳቀለ ነው፡፡ ካቶሊክ፣ እስልምና፣ ፕሮቴስታንት፣ እምነት
የለሽ፣ የባህል እምነት፣ ዝርያ አዘል ግጭት የሚበዛበት ነው፡፡ እነዚህ ውስጥ ውል ያለው ነገር አይታይም፡፡
ከነጮች የተወረሰ ምንዝርና ሌብነት ግድያ የሰፈነበት ነው፡፡ ተጸጽቶ የሚመለስ ህዝብ እጅግ ጥቂት ነው፡፡ ይህም
ክልል መስፈሪያው እሳት ነው፡፡ የተመካበት ሁሉ ይጠፋል፣ ረሃብ ይነግሳል፣ በሽታ ይስፋፋል፣ ግጭት
ይበረክታል፣ የሚያስተዳድር መንግስትም ይጠፋል፡፡ መናና ከንቱ ባዶ እስከሚሆን ይቀጣል ይጠረጋል፡፡ እንደ
ግለሰብ ለመዳን ለሌላው ሁሉ መፍትሄ የምትሆነው ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ የዚችን አገር መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ
አስተዳደር መቀበል ብቻ ነው፡፡
13-0 ምስራቅ አፍሪካ
በዚች ክልል አገሬ ኢትዮጵያ ትገኛለች፡፡ ስለ ኢትዮጵያ የተጻፈውን መልእክት ለመረዳት በ 13-1 ይመልከቱ፡፡
በምስራቅ አፍሪካ
ከኢትዮጵያ ሌላ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሱማልያ፣ ጅቡቲ፣ ባህረ ነጋሽ /ኤርትራ/፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛንያ
ያሉ ሲሆን እነዚህ አገሮች በታላቅ ፍጅት ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ ክልሉም በድህነቱ የሚታወቅ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ካለው የተዋህዶ እምነት ውጪ ሌላው እስልምና፣ ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ፣ ፓጋን፣ የባህል እምነቶች
የህዝብ ለህዝብ ፍጅትም የሚታይበት ነው፡፡
› ምስራቅ አፍሪካ የልዑል ዙፋን የሚፀናባት በኢትዮጵያ እምብርት ላይ ነው፡፡ ዙፋኑም የሚዘረጋ በመሆኑ እነዚህ
አገሮች ከታላቅ መጠረግ በኋላ እድላቸው የሚወሰን ሲሆን በኢትዮጵያ ፕሮፐር ግዛት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡
ከዚህ በፊት ግን ወንጀላቸው የወለደውን ብርቱ ቅጣት ይጋቱታል ከኤርትራም የሚተርፍ ካለ ድንቅ ይባላል፡፡
13-1 ኢትዮጵያ
ሀገሬ ኢትዮጵያ በስተምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ናት፡፡ አገሬ የምትታወቀው በረሃብ ነው፡፡ ሁሉም አለም ስለረሃብ
ሲነሳ ኢትዮጵያን ምሳሌ ያደርጋታል፡፡ ለ7500 ዘመን በታላቅ የዲያቢሎስ ፈተና የተጨፈጨፈች አገር ኢትዮጵያ
ናት፡፡ በጊዮን የተከበበች አገር ኢትዮጵያ ናት፡፡
ዛሬ አገሬ ኢትዮጵያ ከረሃብ ስሟ ሌላ በተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነቷ ፅናትና ጥንካሬ የምትታወቅ ናት፡፡ሁሉንም
የመጀመሪያቱን የነቢያቶች፣ የሃዋርያቶች እምነት በጌታ ደም ያፀናችውን እምነት በድንግል ምልጃና ባለርስትነት
የፀናችውን ተዋህዶ እምነት የጨበጠች ናት፡፡ አፅንታ በታላቅ የዲብሎስ ውጊያ ፀንታ ለ7500 ዘመን የቆመች አገር
ኢትዮጵያ ናት፡፡
አገሬ ኢትዮጵያ አምልኮን በህገ ልቡና ፣ በሕገ ኦሪት፣ በወንጌል ሕግ አፅንታ፣ በማየት ሳሆን፣ በመስማት ያመነች፣
ላመነችበትም እውነት እስከ አሁን በመላው አለም በሚንተከተከው የገሃነም ደጅ የቆመች አገር ናት፡፡ አገሬ
ኢትዮጵያ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት አንበሶች፣ የእምነት ጀግኖች ሃገር ናት፡፡ የዘመን ፅዋ እስኪሞላ በታላቅ
እሳት የተበጠረች ናት፡፡ አገሬ ቀጣፊ ትውልድ እንደሚያስበው፣ አጥታ፣ ለስራ ሰንፋ የተራበች አይደለችም፣
አልነበረችምም፡፡ የችግሯ ምንጭ የጨበጠችው እውነትና እምነቷ ያስከፈላት ዋጋ ነው፡፡ አባቶቻችን ሁሉም
ክህደትን ፣ ኑፋቄን፣ መለያየትን ሳያስገቡ በአንዲት ተዋህዶ ፀንተው ኖሩ፡፡ አለፉ ፡፡ በጊዜ ብዛት ከወደነጭ የበቀለ
የጠላት አረም በነጩ ዘሪነት በአዝመራችን መሃል ገባ፡፡ዛሬ፣ ፀጋ፣ ቅባት፣ ነኝ የሚል በካቶሊክ ከሃዲዎችበቤ/ክ
ተዘራ ፡፡ እስልምና በእንግድነት ገብቶ ተንሰራፋ፣ ፕሮቴስታንት በስልጣኔ አምጭዎች እንደ ሸቀጥ ወደ አገር ውስጥ
ገባ፡፡ በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ተንሰራፋ ጆሆቫ፣ ጥንቆላ፣ ትብተባ ሁሉም የዲያብሎስ ዘርፈ ብዙ መሳሪያዎች
ይህችን አገር ወረሩ በዚች አገር የወረደው መከራ በዚህ ብቻ አላቆመም እጅግ ዘርፈ ብዙ ሆኖ መጣ፡፡
13-2 እምነትና ውጊያ በኢትዮጵያ
ቀድሞ በነበሩ ዘመኖች ውጊያ ባመኑ ሰዎች መሃል ሆኖ በቃሉ ላይ የተደረገ የጨለማና የብርሃን መንገድ በማፅናት
ላይ የተመሰረተ ፍልሚያ ነበር፡፡ ሁሉም ማለት ይቻላል እምነት አለው፡፡ በአንድ ፈጣሪ ከሚያምኑ ጀምሮ በጉእዝ
ነገር የሚየምን የሞላበት ጊዜ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ጀምሮ እውነትን፣ ተዋህዶ ኦርቶዶክስን ጌታ ስለተከተላት የሚመጡ ነገስታት ስለ
እምነት የቆሙ ነበሩ፡፡ ከጥቂት በስተቀር / እነ ዮዲት ጉዲት፣ እነ ግራኝ መሃመድ/ ከፈጠሩት ቀጥታ የእምነት
ጦርነት ሌላው አብዛኛው የመጣው ውጊያ በእምነት ስም የመጣ ዘመቻና ፀንታ በቆመችው ተዋህዶ መሃል አረም
ለመዝራት በጠላቶች የተሰራ ጥፋት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ጀግኖች የእምነት አርበኞች እጅግ የበረታ የመከላከል
እርምጃ በመውሰዳቸው ተዋህዶ በእሳቱም በማእበሉም ፀንታ እዚህ ደርሳለች፡፡የጥፋት ልጆችም እስከ አሁን
ሊቋቋሟት አልቻሉም ፡፡
ዛሬ ያለው ውጊያ እምነቱን ባልያዘው ትንሽ እውቀት ላይ ባደረገ ውል ባጣ መሰረቱን በማያውቅ፣ ቢያውቅም
በናቀ፣ ከነጭ የተቀበለውን ባህል፣ እምነት፣ የቁስ እድገት፣ እውቀት፣ እንደ አምላክ የሚያይና የሚያመልክ የጠፋ
ትውልድ ጋር የሚካሄድ ትግል ሆኖአል፡፡
ዲያብሎስ ይህንን የጨለመበት ትውልድ በአመራርም በሃብትም በኃይልም እንዲደራጅ ጥሯል፡፡ መንግስት በራሱ
የዲያብሎስ መሳሪያ ሆኖ ይህን የጠፋ ትውልድ ፍፁም እንዲጠፋ ያደርጋል፡፡ እያደረገም ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ
ተዋህዶ እምነት ላይ ያለው ውጊያ በመልእክት 2 እንደተጠቀሰው እምነት አለን በሚሉ ብቻ የሚሰነዘር አይደለም
፤ እምነቱ በሌላቸው በመንግስት፣ በውጪ መንግስታት፣ አለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ባለሃብቶች ጭምር እንጂ፡፡
ሁሉም ይህቺን እምነት ለማጥፋት እስከ አሁን ይሰራሉ፡፡ እየሰሩም ይገኛሉ፡፡ ሁሉን ለመዘርዘር ሰፊ ቦታ ይፈጃል፡
፡ በጠቅላላ በእምነት ውጊያው ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታነት፣ እስላም፣ ጆቫ፣ ሌሎችም ሁሉ በቅንብር በተዋህዶ
ኦርቶዶክስ እምነት ላይ የዘመቱ ናቸው፡፡ ሁሉም ዘማቾች ከውጭ በሚደረግላቸው ቀጥታ የገንዘብና የስልት
የቁሳቁስ ድጋፍ የታጠቁ ናቸው፡፡ በመሆኑም ፍርዳቸው ቀድሞ ወጣ፡፡ አሁን ስለ አፈፃፀሙ በጽሑፍ መጨረሻ
እናየዋለን ፡፡
በኢኮኖሚ፣ በባህል የተደረገ ውግያ ከራሱ ከእምነቱ የማያንስ ነው፡፡ ድሃ እንድንሆን እንድንራብ እንድንበታተን
ከራስ ባህል ይልቅ በምንዝርና፣ በውሸት በእርስ በእርስ መፈጀት እንድናልቅ፣ በሽታ እንድንረግፍ፣ ባለን ሃብት
እንዳንጠቀም፣ በማድረግ ልማታችን ወደ ጥፋት በማዞር እስከ አሁን ሲሰራበት ኖሯል፡፡ በኢትጵያ ላይ በተደረገ
ዘረፈ ብዙ ዘመቻ በጥቂት ግንባር ቀደም የምዕራብ፣ የአረብ፣ አገሮች በመመራት ሁሉም አለም የየበኩሉን ድንጋይ
አቀብሏል፣ ወርውሯል ዛሬ ይከፍልበታል፡፡
እንደ መንግስት ማዳከም መንግስትን የራስ ጥገኛ ማድረግ፣ በተዋህዶ እምነታችን መሐል ተኩላ በውስጧ
በመሰግሰግ ማዳከም፣ መበተን የተደረገ፤ እየተደረገ ያለ ግልፅ ተግባር ነው፡፡
ወገኖቼ በብርሃን ስለምንተያይ በሰፊው ያኔ እንነጋገርበትለን፡፡ በኢትዮጵያ አፈፃፀሙ ምን ይሆናል፡፡ በዚች አገር
ያሉ ሁሉ ደግም ደጋግሞ እንዲያስተውል ተመክሯል ተዘክሯል፡፡
አሁን የወቀሳ፣ የመምከሪያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ተጠናቋል፡፡ ፍርዱ ወደ ፍፃሜ ተሸጋግሯል፡፡ ስለዚህ በልዑል
ያልተመዘገበ ፣ ለምህረት ያልተጻፈ፣ ከነ ድንጋይ ልቡ እያፌዘ ያለ፣ በዚህ አፈፃፀም ፍፁም ይጠረጋል እንጂ
አያመልጥም፡፡
በምንዝርና የተነከረ፣ ከንስሐ ያልደረሰ፣ በትእቢት የጸና በጠመንጃው፣ በሃብቱ፣ በጉልበቱ የሚመካ፣ ውጪ ባለ
ወገኑ የተኩራራ፣ በድሃ ያላገጠ፣ የድሃ ንብረት፣ሚስት የቀማ፣ ጓደኛውን የካደ፣ በውሸት የበለፀገ፣ አገርን የካደ ፣
ተዋህዶን ለማጥፋት የደከመ፣ ንብረቷን የዘረፈ፣ ምእመኑን ለተኩላ የበተነ፣ ለበእድ እምነትና መንግስት የሰለለ
ዋጋም የተቀበለ፣ ምንዝርናን ስራው ያደረገ፣ ንጹሃንን ያሰገደለ፣ የገደለ፣ የእግዚአብሄር አገልጋዮችን የተዋህዶ
ኦርቶዶክስ እምነት አገልጋዮችን ያሳደደ፣ ያሰረ፣ ያሰቃየ፣ በኢትዮጵያ ምድር የምህረትን ዘመን ያለ ቅጣት ያለ ዋጋ
መክፈል ፈጽሞ አያይም፡፡ የሚያየውም ንስሃ የገባውና የተጸጸተው በመጠነኛ ቅጣት የታለፈው ብቻ ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያ ምድር ምንዝርናን በማስፋፋት ሴቶች እጅግ ከፍተዋል፣ ሱሪ ለባሽ ገላዋን ገላጭ፣ በፍጹም የማትመለስ
ነውረኛ ሴት ሁሉ በላያቸው ላይ የሚጠርጋቸው እሳት ወጥቷል፡፡
በኢትዮጵያ ከአንዲቷ ከተዋህዶ እምነት ውጪ ሌላ አይረግጥም፣ አይኖርባትም፣ አይጠለልባትም፡፡ ከዚህ አፈጻፀም
መውጣት በኋላ በኢትዮጵያ በግልም፣ በመንግስትም፣ በኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያንም ፣ በመንግስት
ተቋማትም ስለሚወሰዱት አቋምና እርምጃዎች በቀጣዮች የድርጊት መመሪያዎች ይገለጻሉ፡፡
የዳዊት መዝ 145
መላው አገሬ የኢትዮጵያ ልጆች፣ የተዋህዶ እምነት ልጆች፣ የድንግል ልጆች፣ የገብርኤል የሚካኤል አንበሶች፣
የኡራኤል፣ የሩፋኤል አርበኞች፣ ባጠቃላይ ቅን የዋህ የሆንከው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ፣ ባለህበት ፀንተህ ቁም !
ቅድስናህን ጠብቅ ! አትደንግጥ፣ አትፍራ እራስህን ለፈጣሪ ስጥ፣ ለታላቅ አገልግሎት እራስህን አዘጋጅ ! እስከዛሬ
ከሰራኸው ጥፋት በምህረቱ ሽሮ በቸርነቱ ያሰራህን፣ የኢትዮጵያ አምላክ አስብ፣ አመስግን፡፡ ዝርዝር መመሪያዎችን
በጥንቃቄ አንብብ፣ አስተውለህም አድርግ፡፡ እግዚአብሄር ለክብሩ መር ጦሃልና እራስህን በቅድስናና በትህትና
አንጽ፣ ከክፋትም ሁሉ ራቅ፡፡
14-1 ደቡብ አፍሪካ፡-
ይህ ክልል ደቡብ አፍሪካን፣ ናሚቢያን፣ ዚምባብዌን፣ ሞዛንቢክ፣ ማደጋስካር፣ ሌሴቶ፣ ማላዊ፣ ቦትስዋና፣
ሞሪሺየስ፣ ኮሞሮስን ይይዛል፡፡ ይህ ክልል እጅግ የተጎዳ የቅኝ ተገዢ ነው፡፡ በተለይ በዚህ አገዛዟ መጥፎነት
የምትታወቀው እንግሊዝ እስከዛሬ የምትጫነው ክልል ነው፡፡
ሕዝቡ የጌቶቹን እምነት የወረሰ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ፣ በሞዛምቢክ፣ በዚምባብዌ፣ በናሚብያ ዛሬም ጥቁሩን
እየገዙ እየዘረፉ ያሉት ነጮች እዚያው እንደሰፈሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ክልል እንደ አውሮፓዎች የሚመዘን ነው፡
፡ በዚህ ክልል ምንዝርናው እጅግ የከፋ ነው፡፡ ብዙ እምነቶች አሉ፡- ካቶሊክ፣ አንጀሊካን፣ ፕሮቴስታንት፣
ሙስሊም፣ በስብጥረ ያለበት ነው፡፡
የተሰባጠረ ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡ በእሳትም ይፈተሻሉ የማያቋርጥ እሳት ይበረብራቸዋል፡፡ ለሁሉም ዓለም
እንደሚሆነው እነዚህም ጥቂት የሚተርፍ ስለሚኖራቸው፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስር ሲጠለሉ በኢትዮጵያ
የሚሰፍነውን ብርሃናዊ አገዛዝ ሲቀበሉ ብቻ ሰላማቸው ይመለስላቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ የመፈጠር መፍትሄም ሆነ
ዘዴ አያገኙም፡፡ አይኖርምም፡፡
አሞፅ 2 ፡ 14 - 16
በውስጥ ገፅ የተዘረዘሩት የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሸክም እጅግ ከባድ ከብዙ ጥፋትና ውድመት በኋላ ነው
ለተዋህዶ ኦርቶዶክስ /ለኢትዮጵያ/ አገዛዝ እጃቸውን የሚሰጡት መሰረታቸው ፍፁም ዲያቢሎሳዊ በመሆኑ እሳቱ
እየወረደባቸው ጥቂት እስከሚቀሩ የማይመለሱ ናቸው፡፡
15 አውሮፓ፡- ይህ አህጉር አውሮፓ ሲሆን በዋናነት እነ እንግሊዝ፣ ጀርመንን፣ ፈረንሳይን፣ ስፔንን፣ ዴንማርክን፣
ጣሊያንን፣ ፖርቱጋልንና ሆላንድን ያቀፈ ሲሆን በቅርቡ ከራሽያ ተገንጥለው ወደሱ የገቡት እንደ ፖላንድ፣ ቼክ፣
ላቲቪያ፣ እስቶኒያ፣ ክሮሽያ፣ ቡልጋሪያ፣ ሩማንያ፣ ሃንጋሪን፣ የሰበሰበ የአውሮፓ ህብረት የሚባል ድርጅት ያለ ሲሆን
ኔቶ ከአሜሪካ ጋራ ተጣምሮ አለምን ለመግዛት የሚጥሩና እየገዙም ናቸው፡፡
ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔይን፣ ኦስትርያ፣ እንግሊዝ፣ ሆላንድ፣ ጣሊያንና ፖርቹጋል እነዚህ አገሮች ፍጹም የጥፋት
አገሮች ናቸው፡፡ በውስጣቸው ሁሉም የእምነት አይነት አለ፣ ከተዋህዶ እምነት በስተቀር፣ የምንዝርና ቁንጮ
ናቸው፣ የክህደት አገር ነው፡፡ በኑሮአቸው ምቾት፣ ባላቸው የኢንዱስትሪና የፍልስፍና አካሄድ እጅግ የሚመጻደቁ
ናቸው፡፡ ከእንግሊዝ ቀጥሎ አለምን በቅኝ በመግዛት በሰው ዘር ደም የተጨማለቁ ናቸው፡፡ ሰውን አሽከራቸው
ሃብቱን ንብረታቸው አድርገው ዘምተው ለረጅም አመቶች ደሃን የፈጁ ናቸው፡፡ በእነሱ ውስጥ ያሉት ካቶሊክ
አንጀሊካንና ፕሮቴስታንት እምነቶች ከመንግስታቸው ጋር እኩል ለሰው ጥፋት የዘመቱ ናቸው፡፡ ከእንግሊዝ
አንገሊካን እንደ መንግስት ሆና የመራችም ነች፡፡
አውሮፓ ፍጹም የአለም የጥፋቷ ቁንጮ ነው፡፡ በአውሮፓ ተፈልጎ የሚገኝ አንድም ለምህረት የሚበቃ ነገር የለም፤
በሓዋርያት ደም የታጠበች፣ በብዙ ክርስቲያኖች ሕይወት ያላገጠች የዲያቢሎስ የጥንት ማዘዣ የዛሬው ከአሜሪካን
ቀጥሎ ሁለተኛ ማዘዣ ጣቢያ ናት፡፡
የሚጠብቃት፡-
› አውሮፓ እንደ አህጉርም ሆነ በውስጧ እንዳቀፈቻቸው አገሮች በሙሉ በአንድ ሚዛን ትሰፈራለች
› በዚህ ክልል የአውሮፓ ህብረት አባል የሆኑ 28 የሚጠጉ አገሮች በሙሉ በልዑል የእሳት ማዕበል የሚጠረጉ
ናቸው፡፡
› ከዚህ ክልል የሚተርፉ ቢኖሩ እጅግ ጥቂት ናቸው እንደ አገር ቀርቶ እንደ መንደር መቆም የማይችሉ ናቸው፡፡
› የሰበሰቡት መሳሪያ የራሳቸው መጥፊያ ይሆናል፡፡
› የአውሬ መርቢያ ይሆናል፡፡ ዛሬ እንረዳለን ባዮች ነገ እርዱን የሚሉ ይሆናሉ ከነዚህም የሚተርፍ የታደለ ነው፡፡
ከሚመጣውና ከሚፈሰው የልዑል ቁጣ ከተረፉት መዳን የሚቻለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡
ለኢ. ተ. ኦርቶዶክስ እጅ መስጠት በእምነቱ በአስተዳደሩ እንደ መንግስትም እንደ ቡድንም እንደ ግለሰብም
በኢትዮጵያ ለሚቆመው ብርሃናዊ መንፈሳዊ የልዑል አገዛዝ ፍጹም እጅ መስጠት ብቻ ነው፡፡ እጅም ቢሰጡ
ከልዑል ሲጸናና መታዘዙ ከልብ መሆኑ በልዑል ሲረጋገጥ ነው፡፡
ከውስጣችሁ ለሰው የሚጠቅም ሲቀር ማናቸውም ለጥፋት ሌላውን ለመግዛት ተፈጥሮን ለመጉዳት
ለስግብግብነት ባጠቃላይ ለሰው ዘር ሰላምና ጤና ለምድሪቱም ጤና እንቅፋት የሆነው ሥራችሁ ሁሉ ከመሰረቱ
ተጠርጎ ይጠፋል፡፡
የዳዊት መዝሙር፡ 13 / 14 / 2 – 8
15-1 እንግሊዝ፡-
ይህች ሃገር የአውሮፓ ቀዳሚ መሪ ናት የዚች አገር ወንጀል እና የሃጥያት ጥፋት ከአሜሪካ በምንም መልኩ
የማይለይና በማናቸውም ታሪኳም ሆነ ስራዋ ከባቢሎን የምትመሳሰልና ጠበቃ በመሆኗ ከዚህ በተጨማሪ የክህደት
ፈላስፎች የፈለቁባት የእምነታችን ጠላቶች በትልቅ ደረጃ የተስፋፋባት ለአሜሪካ ልጆቿ እዚህ መድረስ ዋናዋ እሷ
ናት፡፡ እንግሊዝ አለምን በቅኝ የገዛች የጥፋትን ስራ በሁሉም መልኩ ለአለም ያስተማረችና የመራች መሰረት
ያስጨበጠች ናት፡፡ የዚች አገር እጣ ፈንታ በምንም መልኩ ከአሜሪካ እጣ ፈንታ አይለይም፡፡
15-2 ፈረንሳይ፡-
ይህች አገር ከእንግሊዝ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ያላት በአለም ቅኝ ገዥነት ከእንግሊዝ ጋር እኩል ትራመድ የነበረች
ናት፡፡ ከአምስቱ ሃያላን አንዷናት፡፡ የኔቶ ቁልፍ አባል፣ የአውሮፓ ህብረት መስራች ናት፡፡ ፈረንሳይ በአገሬ ጉዳይ
ጣልቃ የገባች ናት፡፡ አገሬን ወደብ አልባ ካደረጉ አገሮች የቅርቡ ተጨባጭ ጠላት ናት፡፡ ጅቡቲን የጦር ስፍራና
መናኸሪያ ያደረገችም ናት፡፡
ለሷ የሚደርሰው ጥፋት እጅግ ብርቱ ነው፡፡ የሰበሰበችው ሃብት ይጠፋል፡፡ ያከማቸችው የጦር መሳሪያ ኒዩክለር፣
ኬሚካል፣ ባዮሎጂካል፣ ሚሳየል፣ ጀት፣ የጦር መርከብ፣ ሰበ መሪን ሁሉም እንደ ጢስ ይተናል፡፡ ዜጎቿ በሙሉ
በእሳት ይበጠራሉ፡፡ አጥቶ መንከራተትን መራብን ያዩታል፡፡ ለነዚህ መንግስት ብርቱ ቅጣት ሳያቋርጥ
ይወርድበታል፡፡ እናንት በኢትዮጵያ ዛሬም እየሰራችሁት ላላችሁት በደል ለፍርድ ትቀርባላችሁ ቶሎ ምህረት
ስለጠየቃችሁም አታገኙም፡፡
ሚኪያስ 2 ፡ 1 – 3
ጣሊያን ትናንት ቅኝ ሊገዛ መጣ ዛሬ የለም፡፡ እናንት ግን ጉልበተኞች ብዙም ሳይርቅ ጅቡቲን ከእናት ምድር
ነጥላችሁ ነፃ ናት አላችሁ፡፡ ጦር ሰፈር አደረጃችሁ፡፡ መቀበሪያችሁ ትሆናለች፡፡ አገራችሁ የሰውን አገር
እንደበተነች ትበታተናለች፡፡ እናንት በኢትዮጵያ ፊት አለፍርድ አትታለፉም ትቢያ ትለብሳላችሁ፡፡ በአውሮፓ
ላሉ አገሮች የከፋ የጥፋት ምሳሌ ትሆናላችሁ፡፡
በመላው አለም ላለህ የሰው ዘር በሙሉ ልብ ብለህ አድምጥ ልትወስደው የሚገባህ እርምጃ ምንድን ነው፡፡
በዚህ የልዑል ውሳኔ ውስጥ የሁሉንም መልእክቶች በሚገባ የተረዳህ ከሆንክ ከዚህ በታች ያሉትን
እንደመጀመሪያው ሁሉ ከዚህም በኋላ ያሉትን የአፈጻጸም ውሳኔዎች አስተውለህ ተረዳ አድርግም፡፡
ይህ መልእክት መላውን አለም የምታይበት የእምነት መነጽርህ ነው፡፡ ከራስህ አትለየው የሚፈጸመውን የልዑል
ውሳኔ አስፈጻሚዎች ሲያከናውኑት ልብ ብለህ አስተውል፡፡ በምድር ሆነ በህዋ፣ በባህርም ውስጥ ሁሉ ሁኑ ይህ
የልዑል መልእክት የማይዳኘው አለም የለምና ፍርዱን እዩ፡፡ ሁሉም የአለም መሪ፣ ሁሉም የአለም ህዝብ፣ ሁሉም
ባለጸጋ፣ ሁሉም ድሃ በብርሃናዊ ፍርድ ይዳኛልና፡፡ ልብ ብለህ አድምጥ፡፡ እምነት የሌለህ ጠማማ ትውልድ
እስከምትጠረግ ጠብቅ፡፡
አለም በውስጧ ብዙ ሕዝብ እንደማቀፏ መጠን የሕዝብን ሃብት ጠቅልሎ በጥቂት ግለሰቦች ሰብስቦ መክተት
ዛሬም የሚታየውን የገብጋቦች አለም እንዲወገድ ያደርጋል፡፡
በተለይ አሜሪካ አውሮፓ ከብዙ ጥፋት ፍሰት በኋላ ስለሚንበረከኩ ጉዳታቸው እጅግ ይከብዳል፡፡
በአለም ያሉ ዛሬ ሲታዩ ትልቆች መሪዎች ባለሃብቶች ሁሉን አድራጊዎች ሊያውቁት የሚገባ ነገር ቢኖር በኢትዮጵያ
በፍትህ አደባባይ ቀርበው ቅን የፈጣሪን ዳኝነት ያገኛሉ፡፡
ሥጋዊ አሰራሮች የእለት ተእለት ክንዋኔዎች ሁሉ ምንዝርናን፣ ሌብነትን፣ ክፋትን፣ ተንኮልን፣ ማታለልን፣
ማጭበርበርን፣ በወንድም ላይ በደል መፈጸምን ከመንፈሳዊ ሕይወት መስመር መውጣትን የሚያስወግድ ፈፅሞም
የማይሸከም ሆኖ ይደራጃል ይዋቀራል፡፡
18 አለም የተሸከመችው የጥፋት መሣሪያ እጣ ፈንታስ
ሀ/ አለም ለረጅም ዘመን ለመፋጂያ መሣሪያን ስታደራጅ ኖራለች የመጀመሪያው የጥፋት መሣሪያ ድንጋይ ነበር፡፡
ቃየል ወንድሙን በዲያቢሎስ ግፊት፣ በቅናት ተነስቶ የገደለው በድንጋይ ነበር፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የጥፋት መሣሪያ
አደራጅቶ ወንድምን መግደል ተዘወተረ፡፡
ለ/ የጥፋት መሣሪያዎች አንድ ሰው መግደል ብቻ በማዘውተራቸው ሰው በጠላት ግፊት የመግደያ መሣሪያዎቹን
እያሻሻለ መጣ ከድንጋይ ወደቀስት ከቀስት ወደብረት እያለ አንድ ሰውን መግደል ተለመደ፡፡ የሰው ስጋ ብርቱ
የጠላት መሳሪያ ነውና በሥጋ ፍላጎቱ የማይረካው ሰው ብዙ የተሻሻሉ መሣሪያዎችን ሠራ፡፡ ከብዙ ዘመን ጉዞ
በኋላ ሰው ታላላቅ የሰውና የንብረት ጥፋት የተደረገበትን 1ኛው የአለም ጦርነትን 2ኛው የአለም ጦርነትን አካሄደ፡፡
አንድ ሰው ከመግደል አልፎ በሰራው ፈንጂ፣ ጀት፣ መድፍና ታንክ በሺና በመቶ መፍጀት ጀመረ፡፡ ይህ መጠን
ያላረካው ዲያቢሎስ ጥበቡን እንደተሞላ ነውና፡፡ የተሻለን የጥፋት መሣሪያ ለሰው አስጨበጠ ኒዩክለር ተሠራ
በጃፓን ተሞከረ ከ300 ሺ ያላነሰ ሰው ፈጀ በዚህ ያልረኩት የዲያቢሎስ አሽከሮች የምድርን ሰው መላልሶ
የሚያጠፋ ኑዩክለር በብዛት ሰሩ ይህ አልበቃቸውም የኬሚካል መሣሪያ ሠሩ ሰውን በጣጥሶ የሚያጠፋ፣ ኒውትሮን
ሰሩ፡፡ ሕይወት ያለውን ብቻ ለይቶ የሚገድል፣ ባዮሎጂካል መሳሪያ ሰሩ በሽታ አምጪ ቫይረሶችን ጨራሽ
አውዳሚ ባክቴሪያዎችን በላብራቶር አደራጁ ስንቴ ሰውን ሊያጠፉት እንዳሰቡ የሚገርም ነው፡፡ ከ9 የማያንሱ
አገሮች ይህንን የኒዩክለር መሣሪያ ተሸክመዋል፡፡
ትንቢተ ሚኪያስ 5፡- 10 - 15
ትንቢተ ኢሣኢያስ 24፡- 1 13
በዚህ አልቆሙም እጅግ ግዙፍና የረቀቁ መርከቦችን፣ ሚሳኢሎችን፣ መድፎችን፣ ታንኮችን፣ አጥቂ
ሳተላይቶችን በጥቅሉ ሰው የማያውቃቸውን የረቀቁ የጥፋት መሣሪዎችን አከማቹ ሰሩ፡፡ ተዘጋጁ ወንድማቸውን
ሊገድሉበት የረቀቁ የጥፋት መሣሪያዎችን አከማቹ ሰሩ ተዘጋጁ ወንድማቸውን ሊገድሉበት እንደ ቃዬል አንዴ
አይደለም መልሰው መላልሰው ሊያጠፉበት አለሙ ዛሬም በዚያው ሕግና አላማ ውስጥ አሉ፡፡ ታላላቅ መንግስታት
ለሃብታቸው ዋስትና ለወንጀላቸው መሸፈኛ ለድሃ መርገጫ ደሃ መንግስትና ሕዝብ ለመዝረፊያ ተጠቅመውበታል
ዛሬም እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ የአለም ዳኛ ነን የሚሉ ታላላቅ ጉልበተኛ መንግሥታት በዚሁ መሣሪያቸው
በሰበሰቡት ሃብታቸው በየቦታው ባደራጁት ተገዥ አሽከሮቻቸው አለምን ወደ ፍፁም ጥፋት እየገፏት ይገኛሉ፡፡
ይህን መሣሪያ የጨበጡት እነዚህ ሀገሮች አሜሪካ ከራሽያ፣ አረብ ከአሜሪካ፣ ኮሪያ ከኮሪያ፣ ሕንድ ከፓኪስታን፣
እስራኤል ከአረብ ከፍልስጤም፣ አንዱ አገር ከአንዱ አገር በቅኝ ገዥዎች በተከለለ ድንበር ሲፋጁ ሲነታረኩ
የሚታዩበት የዘወትር የአለም ድራማ ነው፡፡ የሰው ልጅ ልብ ብለህ አስተውል ጌታ ባይጠብቅህ ዲያቢሎስ
የደገሰልህ ድግሥ ስንቴ ከመቃብር እያወጣ እንደሚገልህ /ቢቻል/ አስብ አሜሪካ 10 ሺ የኒዩክለር አረር፣ ራሺያ
8ሺ የኒዩክለር አረር፣ ቻይና የኒዩክለር በሺ አረር፣ ፈረንሳይ በሺ የሚቆጠር አረር፣ እንግሊዝ በሺ የሚቆጠር አረር፣
ሕንድ፣ ፓኪስታን፣ እስራኤል ከዚያም በመቶ የሚቆጠር የኒዩክለር አረር ተሸክመዋል፡፡ ለአለም ጥፋት የአንዱ
አገር በቂ ነው፡፡ በዚህ አልቆሙም ይህንኑ መሣሪያ ጠፈር ላይ ሰቅለዋል፡፡ ከዚህ በላይ ወንጀለኛ ምን ይምጣ?
ታዲያ ይህ እንዴት ይወገዳል፡፡
ሀ / የተሸከሙትስ መሣሪያ እጣ ፈንታስ?
› ይህ የጥፋት መሣሪያ የተሸከሙ አገሮች ለራሳቸው የደገሱት ነው፡፡
› በእግዚአብሄር የተመረጡ የትም የሁኑ የት ምንም ይፈጠር ምን የሚነካቸው የለም፡፡
› የተሸከሙት መሣሪያ በሙሉ ከምድረ ገጽ ይጠፋል፡፡ ሲጠፋም እነሱኑ የጥፋት አለቆችን ይዞ ይሔዳል፡፡
ትንቢተ ሕዝቅኤል ም 26 /27/ በሙሉ
› እነዚህ አገሮች በኪሳቸው የሚነድ እሳት የከተተን ሰው የመስላሉ፡፡
› አጠፋፉን ሁሉ የሚያየው ስለሆነ መመልከት ለታደሉት ነው፡፡
› የሚጠፉ መልካሙን ሳያዩ ከጥፋት መሣሪያው ጋር አብረው ይበናሉ፡፡
› እንዴት? ያንን ለሃያሉ የሠራዊት ጌታ ውሳኔ አስፈጻሚ የብረሃን መላእክቶች እንተወው፡፡
ለ/ አለም በምን ትመራለች ማእከሉስ የት ይሆናል?
› አለም ከትቢያ በምትነሳው የረሃብ ምሳሌ በሆነችው በአገሬ ኢትዮጵያ ትመራለች፡፡ ትገዛለች፡፡
› ከታላቁ የቁጣ ፍሰት በኋላ አለም በውድም በግድም ይህንን የልዑልን ውሳኔ ይቀበላል፡፡ ተግባራዊ ያደርገል፡፡
ይገዛበታል፡
የአለም አመራር ማእከሉ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ይሆናል፡፡ አለም ቸሩ አምላክ ባነገሠው ንጉሠ ነገሥት ከሱ ጋር
አብረው በሚሾሙ የልዑል አገልጋዮች ትመራለች፡፡ ንጉሡም በታላላቅ ሽማግሌዎች የእግዚአብሄር ሰዎች
ይከበባል፣ ይመከራል፣ ይታገዛል፡ የአለምን አመራር የሚይዘው የልዑል ባሪያ በዙፋኑ ላይ ሲሆን አብረውት
የሚሰሩ በሚሰጣቸው የማእረግ ደረጃ በመሆን ለመንፈሳዊ ጉዳይና ስሰጋዊ ጉዳይ የማማከር ተግባር የሚያከናውኑ
ይኖራሉ፡፡
አለም ቸሩ አምላክ በቀባው አባት በኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አባትና መሪ ከሱም ጋር አብረው በሚቀቡ
በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ በሚመሩ የእምነታችን አባቶች ትመራለች፡፡
መንፈሳዊ አባቶች በመላው አለም ይመደባሉ፡፡ መንፈሳዊና ስጋዊ አሰራሩ ተጣምረው በእግዚአብሄር ፈቃድ
የሚመሩ ስለሆነ እንደየሰው ብዛት እርቀት የአገሩ ስፋት እየታየ የአገልጋዮቹ ምደባ ይፈጸማል፡፡ በየደረጃው
የሚመደቡ ሁሉ የራሳቸው የስልጣን ሽፋንና የመወሰን ጣሪያ ይኖራቸዋል፡፡ የህንንም የሚወስን ሕጋዊ አግባብ
የደራጃል፡፡
በሥጋው ስራና አገልግሎት የሚመደቡት አለምን በሚገዛው የቅድስናና የፅድቅ ሕገመንግሥት ስለሚመራ ከዚህ
ጋር አግባብ ያላቸው ሕጎች እየወጡ በዚያ መስፈርትና ማእቀፍ የመላው አለም የአስተዳደር የአገዛዝ የአመራር
የኢኮኖሚ የገንዘብ፣ የማሕበራዊ አገልግሎት በተያያዥነት ይደራጃል፡፡
በልማድ የደጉ ባህሎችና የአካባቢ አኗኗሮች ከመንፈሳዊና ሥጋዊ አሰራር ጋር የሚስማማው ተዋህዶ
የማይስማማው ተጥሎ የአኗኗር ሁኔታ መሠረት ይይዛል፡፡
ትንቢተ ዘካሪያስ ም፡ 4 /5/ በሙሉ
የዳዊት መዘ. 131 /132/ 6 – 18
19 የአስተዳደር ማእከላት
ተፃፈ -----------------
ቀን 19/7/2001 ዓ.ም.
አመሰግናለሁ፡፡