You are on page 1of 10

መናፍቃን 81 /ሰማንያ አሃዱ/ መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉባቸው ምክንያቶች እና እንዲቀበሉ የሚያስገድዳቸው

ምክንያቶችና ማስረጃዎች፡

ክፍል 2

ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት ሰማንያ አንድ መሆኑን ትናገራለች፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ላይ በብዛት
ተሰራጭቶ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ስልሣ ስድስት ነው፡፡

በስልሣ ስድስቱ ውስጥ የሌሉት መጻሕፍት:-

1. ከ ብ ሉ ይ (2 ኛ የቀኖና መጻሕፍት) )

1.መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 2.መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ 3.መጽሐፈ ጦቢት 4.መጽሐፈ ዮዲት 5.መጽሐፈ አስቴር
6.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ 7.መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ 8.መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 9. መጽሐፈ ሲራክ 10.ጸሎተ
ምናሴ 11. ተረፈ ኤርሚያስ 12.ሶስና. 13. መጽሐፈ ባሮክ 14. መጽሐፈ ጥበብ 15. .መዝሙረ ሰልስቱ ደቂቅ 16. .ተረፈ
ዳንኤል 17.መጽሐፈ ኩፋሌ 18.መጽሐፈ ሄኖክ

2.ከሐዲስ ኪዳን

1. ትዕዛዘ ሲኖዶስ 2. ግስው ሲኖዶስ 3. አብጥሎ ሲኖዶስ 4. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶእ 5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ 6.መጽ.
ኪዳን ካልዕ 7. ቀለሚንጦስ 8. ዲዲስቅሊያ

(እነዚህ የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ይህም የሆነው
እያንዳንዳቸው በጣም ትልቅ መጻሕፍት በመሆናቸው ለማካተት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ግን ከ 81 መጻሀፍት መድበን
ነው የምንቆጥራቸው፡፡ሁሉም መጻህፍት በቤተክርስትያኖች ቤተ-መጻሀፍት ውስት እንዲሁም ገዝቶ ማንበብ ይቻላል፡፡
ስለ ይዘታቸው በሚቀጥለው ክፍል እንመለስበታለን፡፡)
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሕፍት ሳታጓድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትቀበላለች፡፡

<<በነገራችን ላይ ከላይ ያሉት መጻሐፍት ሲቆጠሩ ከ 81 በላይ ናቸው፡፡አቆጣጠራቸው እንዴት ሆኖ 81 እንደመጣ


በሚቀጥለው ክፍል እንመለስበታለን.. >>

ዘመናዊ ነን የሚሉ እምነቶች ግን ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌላ የለም ሲሉ ይሰማሉ፣ ለዚህም የሚጠቀሱት ዩሐንስ ራዕይ
መጨረሻው ላይ ያለውን ቃል ነው

‹‹ማን በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መጽሐፍ
ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል›› ፡፡ ራእይ 22‹18

ይህን አባባል በጥሞና ስናጤነው የዩሐንስ ራዕይን ብቻ የሚመለከት ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ “በዚህ በትንቢት መጽሐፍ” አለ
እንጂ ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አላለም፡፡ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “የትንቢት መጽሐፍ” ብቻ ሳይሆን የ”ወንጌል”
፣የመዝሙር፣የመልዕክታት እና የመሳሰሉት መጽሐፍ ነው፡፡

ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው እንደዚሁ አንድ ላይ እንደተጠረዘ ሆኖ የተገኘ አይደለም፡፡ ጻሕፍቱ በተለያየ ዘመን
የነበሩ እንደሆነ ሁሉ ፣መጻሕፍቱም በተለያዩ ዘመናት የተጻፉና በአንድ ወቅት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጸሐፍ
ተጽፈው አልቀው በጥራዝ መልክ እንደወጡ አድርጎ በመውሰድ የዩሐንስ ራዕይን ማጠቃለያ ለሁሉም መጻሕፍት አድርጎ
መውሰድ አለማወቅ ወይንም ተንኮል ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ፡-

ብሉይ ኪዳን በሐገራችን ቋንቋ በግዕዝ የተተረጎመው ከክርስቶስ ልደት በፊት አንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ሲሆን
ይኸውም በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት ጊዜ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህን ጊዜ ጀምሮ መጻሕፍትን ጠብቃ አቆይታለች፡፡አባቶች ምንም አይነት ጦርነት ቢነሳ ህይወታቸውን
በማስቀደም መጻሕፍትን ጠብቀው አቆይተውልናል፡፡ከምዕራባውያን በፊት ክርስትናን ሆነ የአይሁድ እምነትን
የተቀበለችው ሀገራችን በምዕራባውያን የሌሉ መጻሐፍት መገኛ ብቸኛ ሀገር ናት፡፡

ለዚህም ነው በአይሁድ ዘንድ ሆነ በሮማውያን ዘንድ በነበረው ጦርነት የጠፉ መጻህፍት ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የሚገኙት፡፡
ለዚህም መጽሐፈ ሄኖክ እና መጽሐፈ ኩፋሌ ምሳሌዎች ናቸው፡፡

የመጽሐፈ ሄኖክ ጥቅልል አሁን በቅርቡ በቁምራን ዋሻ ተገኝቷል፡፡የተገኘው ጥቅልልም ሀገራችን ጠብቃ ካቆየችው
መጽሐፈ ሄኖክ ጋር አንድ አይነት ሆነ በመገኘቱ ምዕራባውያን ተርጉመው መጠቀም ጀምረዋል፡፡
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት አይነት የቀኖና ክፍሎችን ያካትታል እነሱም ፕሮቶካኒካል እና ዲዩትሮካኖኒካል ይባላሉ፡፡

(የመጀመሪያ)፡- እነዚህ መጻሕፍት የተሰበሰቡት በካህኑ እዝራ ሲሆን መጀመሪያ በቀኖና መጻሕፍትነት የተመዘገቡ
ናቸው፡፡ 1 ኛ. መቃብያን 2፡10 “ነህምያም የነገስትን መጻሕፍት የያዘ ቤተ መጻሕፍት አቋቁሞ ነበር“

እነዚህም መጻሕፍት በ ሶስት ይከፈላሉ እነሱም ቶራህ (አምስቱ ብሔረ ኦሪት) ፣ ነበኢም (ቀደምት ነብያት እና ደኃርት
ነብያት) እና ከተቢም (ታላላቅ የታሪክ መጽሐፍትና ታናናሽ የታሪክ መጽሐፍትን ያካትታል) ተብለው ይጠራሉ፡፡

እንዲሁም ዲዩትሮካኖኒካል የምንላቸው አይሁድ እንደ ቀኖና መጻሕፍት የማይቀበሉዋቸው ግን እንደ አዋልድ መጻህፍት
የሚቀበሉዋቸው ናቸው፡፡

በነገራችን ላይ አይሁዶች 24 የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ ሲቀበሉ (የመጽሐፋቸው አቆጣጠር ከእኛ አቆጣጠር
ይለያል )ፕሮቴስታንቶች 39 የብሉይ ኪዳን እንዲሁም 27 የሐዲስ ኪዳን ይቀበላሉ፡፡

ካቶሊኮች 46 የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እና 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ሲቀበሉ እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶዎች ግን 46
የብሉይ ኪዳን እና 35 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንቀበላለን፡፡(ከካቶሊኮች ጋር በብሉይ ኪዳን የምንቀበላቸው መጻሕፍት
ላይ የአቆጣጠር እና የመጻሕፍት ልዩነት አለ፡፡እሱን በሚመጣው ክፍል እናብራራዋለን፡፡)

እዚህ ላይ ከላይ በግልጽ እንደምንረዳው 81 የነበረው የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ብዛት ቀስ በቀስ በሰዎች እየተቀነሰ
እንዲሁም በነበሩት ጦርነቶች መጻሐፍቱ እየጠፉ በመምጣታቸው፣ መጀመሪያ 73 እንዲሆን በመቀጠልም ማርቲን
ሉተር ሲያምንበት ከነበረው የካቶሊክ እምነት ፣ከካቶሊክ መነኮሳት ጋር በነበረው የግል ጸብ እና የፖለቲካ ጸብ (የጀርመን
ዜጋ ስለነበር የአይሁዶች ጥላቻ ስለነበረው) በነበረው ቅራኔ ምክንያት 7 መጻህፍትን በገዛ ፈቃዱ ቀንሶ ዛሬ
በምዕራብውያን ዘንድ በስፋት የተስፋፋውን እና የእኛን ሐገር ጨምሮ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሀይል የሌላቸውን ሀገራት
የተቆጣጠረውን የ 66 መጻሐፍት ሊያስፋፋ ችሏል፡፡

መናፍቃን 81 /ሰማንያ አሃዱ/ መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉባቸው ምክንያቶች እና እንዲቀበሉ የሚያስገድዳቸው


ምክንያቶችና ማስረጃዎች፡-

ይቀጥላል………
22222222222

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት! |

መፅሐፍ ቅዱስ 66 አህዱ ወይስ 81 አህዱ!?

*******★**********★**********★******

#66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ነው! እሱ ብቻ ነው ትክክል! #81 ፩ዱ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ተረት ተረት ነው። ለምትሉ
መናፍቆች ከዚው ከእናንተ ከምታምኑት #66 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ ስንጠይቅ ምን መልስ የሌለው❓ነገር ግን
#81 አሐዱ በደምብ የሚመልስውን ስታዩት ምን ትሉ ይሆን❓

1,✅ #ዘፍ 3፥1-5 እንደተጻፈ እንሰሳትና የሠው ልጆች የሚግባቡበት የጋራ ቋንቋ እንደነበራቸው እባብ ከሔዋን ጋር
ባደረገው ንግግር ይታወቃል ።👈👉ታዲያ ይህ ቋንቋ የት ገባ❓ለምን እንዳይግባቡ ተከለከሉ ❓የሚለውን ጥያቄ ስናነሳ
#ከ 66 ቱ መልስ የሚባል ነገር የለም❓መልሱ ግን #ከ 81 አሐዱ መጽሐፍ ኩፋሌ 5፥1-5 ለምን እንደተከለከሉ ቁጭ ብሎ
አለ።

2,✅ #ዘፍ 4፥17 ላይ ቃየልም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም ሄኖህንም ወለደች ይላል።👈👉አዳምና ሔዋን ቃየልና አቤል
የሚባሉ ልጆችን እንደወለዱ እንጂ #ሴት ልጆችን ወለዱ የሚል አልተጻፈም።👉አዳም ሴቶችን እንደወለደ የተጻፈው
ቃየል ከሚስቱ ሄኖህን ከወለደ በኋላ ነው።👉ታዲያ ቃየልና # ሴት(የአቤል ምትክ) ሚስት ከየት አምጥተው አገቡ❓#66 ቱ
ፍፁም ለዚህ መልስ የለውም። #81 አሐዱ ግን #መጽሐፈ #ኩፋሌ 5፥8-17 አቤልና ቃየል ሲወለዱ መንታ መንታ ሆነው
እንደተወለዱ።የአቤልን መንትያ (አዋንን) ለቃየል የቃየልን መንትያ (አዙራን )ለአቤል እንዳጋበት።ቃየል የአቤልን መንትያ
አግብቶ #ሄኖህን እንደወለደ በደምብ ሙሉ መልስ ይሰጣል።

3,✅ #የይሁዳ መልዕክት #1፥14-15👈👉ከአዳም ጀምሮ #7 ኛ የሆነ #ሄኖክ ስለ እነርሱ #እንዲህ ሲል #ትንቢት
ተናገረ።እነሆ እግዚአብሔር በሁሉ ላይ ይፈርድ ዘንድ ከአዕላፋት ቅዱሳን መላዕክት ጋር ይመጣል።👈👉እያለ ሐዋርያው
#ይሁዳ ተናገረ👈👉ይሁዳ ያስተማረውና የጻፈው ሄኖክ።እኔ ምለው መጽሐፈ ሄኖክ የጻፈውና የተናገረው ትንቢት ከሌለ
ይሁዳ ለምን ስለ ሄኖክ ተናገረ❓የተናገረውን የትንቢት ቃል #66 ቱ ውስጥ የለም።ትንቢቱ ተጽፎ ያለው #በ 81 አሐዱ
መጽሐፉ ቅዱስ #ሄኖክ 1፥9 ፍርድን ያደርግላቸው ዘንድ እነሆ ከቡዙ ቅዱሳን ጋር ይመጣል -----እያለ በደምብ ይገልጸዋል
።👈👉እኔ ምለው ታድያ ተረት ተረት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የትኛው ነው❓ሙሉ መልስ የሚሰጠው ነው❓ወይስ
ለእናንተ ሉተር አመናምኖ የሠጣችሁ መልስ የሌለው ቁንፅሉ❓ማንኛው ነው።👉መልስ ሳይኖራችሁ መልስ እንዳለው
አትምሰሉ።እግዚአብሔር ልቦናችሁን ዓይነ ህሊናችሁን ይግለጥ ያብራም።እውነተኛ እና ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ #81
አሐዱ ብቻ እና ብቻ ነው።ለምትጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት #81 አሐዱን መጽሐፍ እንጂ #66 ቱ መልስ
የለውም።ምክንያቱም #15 መጽሐፍ እነ ሉተር፣ጆን ካልቪን እና ክፉ ደቀ መዝሙሮቻቸው አውጥተው እና ቆርጠው
ጥለውታል!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!


መፅሐፍ ቅዱስ 66 አህዱ ወይስ 81 አህዱ!?

*******★**********★**********★******

#66 ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ነው! እሱ ብቻ ነው ትክክል! #81 ፩ዱ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ተረት ተረት ነው። ለምትሉ
መናፍቆች ከዚው ከእናንተ ከምታምኑት #66 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ ስንጠይቅ ምን መልስ የሌለው❓ነገር ግን
#81 አሐዱ በደምብ የሚመልስውን ስታዩት ምን ትሉ ይሆን❓

1,✅ #ዘፍ 3፥1-5 እንደተጻፈ እንሰሳትና የሠው ልጆች የሚግባቡበት የጋራ ቋንቋ እንደነበራቸው እባብ ከሔዋን ጋር
ባደረገው ንግግር ይታወቃል ።👈👉ታዲያ ይህ ቋንቋ የት ገባ❓ለምን እንዳይግባቡ ተከለከሉ ❓የሚለውን ጥያቄ ስናነሳ
#ከ 66 ቱ መልስ የሚባል ነገር የለም❓መልሱ ግን #ከ 81 አሐዱ መጽሐፍ ኩፋሌ 5፥1-5 ለምን እንደተከለከሉ ቁጭ ብሎ
አለ።

2,✅ #ዘፍ 4፥17 ላይ ቃየልም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም ሄኖህንም ወለደች ይላል።👈👉አዳምና ሔዋን ቃየልና አቤል
የሚባሉ ልጆችን እንደወለዱ እንጂ #ሴት ልጆችን ወለዱ የሚል አልተጻፈም።👉አዳም ሴቶችን እንደወለደ የተጻፈው
ቃየል ከሚስቱ ሄኖህን ከወለደ በኋላ ነው።👉ታዲያ ቃየልና # ሴት(የአቤል ምትክ) ሚስት ከየት አምጥተው አገቡ❓#66 ቱ
ፍፁም ለዚህ መልስ የለውም። #81 አሐዱ ግን #መጽሐፈ #ኩፋሌ 5፥8-17 አቤልና ቃየል ሲወለዱ መንታ መንታ ሆነው
እንደተወለዱ።የአቤልን መንትያ (አዋንን) ለቃየል የቃየልን መንትያ (አዙራን )ለአቤል እንዳጋበት።ቃየል የአቤልን መንትያ
አግብቶ #ሄኖህን እንደወለደ በደምብ ሙሉ መልስ ይሰጣል።

3,✅ #የይሁዳ መልዕክት #1፥14-15👈👉ከአዳም ጀምሮ #7 ኛ የሆነ #ሄኖክ ስለ እነርሱ #እንዲህ ሲል #ትንቢት
ተናገረ።እነሆ እግዚአብሔር በሁሉ ላይ ይፈርድ ዘንድ ከአዕላፋት ቅዱሳን መላዕክት ጋር ይመጣል።👈👉እያለ ሐዋርያው
#ይሁዳ ተናገረ👈👉ይሁዳ ያስተማረውና የጻፈው ሄኖክ።እኔ ምለው መጽሐፈ ሄኖክ የጻፈውና የተናገረው ትንቢት ከሌለ
ይሁዳ ለምን ስለ ሄኖክ ተናገረ❓የተናገረውን የትንቢት ቃል #66 ቱ ውስጥ የለም።ትንቢቱ ተጽፎ ያለው #በ 81 አሐዱ
መጽሐፉ ቅዱስ #ሄኖክ 1፥9 ፍርድን ያደርግላቸው ዘንድ እነሆ ከቡዙ ቅዱሳን ጋር ይመጣል -----እያለ በደምብ ይገልጸዋል
።👈👉እኔ ምለው ታድያ ተረት ተረት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የትኛው ነው❓ሙሉ መልስ የሚሰጠው ነው❓ወይስ
ለእናንተ ሉተር አመናምኖ የሠጣችሁ መልስ የሌለው ቁንፅሉ❓ማንኛው ነው።👉መልስ ሳይኖራችሁ መልስ እንዳለው
አትምሰሉ።እግዚአብሔር ልቦናችሁን ዓይነ ህሊናችሁን ይግለጥ ያብራም።እውነተኛ እና ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ #81
አሐዱ ብቻ እና ብቻ ነው።ለምትጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት #81 አሐዱን መጽሐፍ እንጂ #66 ቱ መልስ
የለውም።ምክንያቱም #15 መጽሐፍ እነ ሉተር፣ጆን ካልቪን እና ክፉ ደቀ መዝሙሮቻቸው አውጥተው እና ቆርጠው
ጥለውታል!

33333

፹፩ (81) መፅሐፍ ቅዱስ እና ፷፮ (66)

♦በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ! ♦


★መናፍቃኑ ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የለም ወይም አያስፈልግም እንዳይሉ ማስረጃዎችን
እነሆ፡-

☞በቀላል አማርኛ 66 ቱ መጽሀፍት ጎደሎ ነው አዲስ ኪዳን ላይ የተጻፍት ክርስቶስ የሚያጣቅስባቸው ነገሮች 66 ቱ
ውስጥ የሉም 81 ውስጥ ግን በሙሉ አለ ፡፡እንፈልግም ካላችሁ መቁለጭለጭ ነው ትርፉ ፡፡ለሁሉም ኦርቶዶክስ ጋር
ቅረቡ ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን የጠቀሳቸው በሙሉ እኛ እጅ ላይ አለ፡፡እንደመናፍቃን ጉረኛ ባንሆንም ያልተጋነነ ኩራት
ይሰማናል፡፡፡

☞መናፍቃኑ ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የለም እንዳይሉ እነሱ አምነው የተቀበሉት 66 ቱ
መጽሐፍ ቅዱስ እራሱም ይመሰክርባቸው፡፡

☞ማስረጃ 1.

☞ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ይለናል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ.3፡
23)

- እንግዲህ ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ 30 ዓመቱ በፊት የት ነበረ? ምን እየሰራ ነበረ? ብልን
ስንጠይቅ መልሱን በ 66 መጻሕፍት ውስጥ ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን የትውፊት መጻህፍት ውስጥ እድገቱ ምን
እንደሚመስል በዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን፡፡

☞ማስረጃ 2.

☞በማቴዎስ ወንጌል 27፡3-10 (በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር
ለካህናት አለቆችና ለሽማግሌዎች መልሶ፦ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን
አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን
አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት
ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ
የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ
ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ። በዚያን ጊዜ የነቢዩ የኤርሚያስ ቃል ተፈጸመ ይለናል ይሁዳ…እንዲህ ያለው
‹‹የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ ሠላሳውን ብር ወሰዱ›› ይህን ቃል የምናገኘው በስድሳ ስድስቱ ውስጥ
ሳይሆን በተረፈ ኤርሚስ 7፣ 2-4 ባለው ላይ ነው፡፡
- ቅዱስ ማቴዎስ ትንቢተ ኤርሚያስን ጠቅሶ ሲጽፍልን 'በነብዩ ኤርሚያስ የተባለው ብሎን ነው፡፡' ምን ተባለ ስንል
ማቴዎስ ''የተባለውን'' ና ''ተፈጸመ'' ያለንን የምናገኘው መናፍቃኑ አንቀበለውም በሚሉት በ 81 መጽሐፍት ውስጥ
ነው፡፡

እንዲህ ይላል ‹‹እስራኤል ልጆች የተስማሙበትን ዋጋ 30 ብር ይቀበሉታል ያንንም ብር ለሸክላ ሰሪ ቦታ ዋጋ አድርገው


ይሰጡታል››

☞ማስረጃ 3.

☞ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፡፡ ‹‹እንፍጠር›› ሲል ከአንድ
በላይ ብዛትን ሲያመለክት 2 ወይም 4 ወይም 10 ሳይሆኑ ስላሴን /ሶስትነት/ ሶስት መሆናቸውን የሚነግረን በሲራክ
2፤22 ሄኖክ 5፤38 ሄኖክ 6፤24 ሄኖክ 13፤14 እዝራ ስቱኤል 4፤56 እዝራ ስቱኤል 12፤48 ሲራክ 44፤10 በግልጽ ስላሴ እያለ
በማሳየት ነው፡፡ ክብር ለቅድስት ስላሴ ይሁን!

☞ማስረጃ 4.

☞በሉቃስ 14:13-14 ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤

የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት 4፣7፡10 የተገኘ ነው ‹‹ከገንዘብህም
ምጽዋት ስጥ ምጽዋትም በመጸወትህ ጊዜ በገንዘብህ አትዘን፣ ከድሃም ፊትህን አትመልስ፤ እግዚአብሔርም ገጸ በረከቱን
ካንተ አይመልስም፡፡››

✿ቁልፍ ቃል

☞ መፅሀፈ ሄኖክ ፣መፅሀፈ ሲራክ . . . የእነዚህ እነና የመሳሰሉትን ከሰማንያአሀዱ የተወጣጡ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች
በዚህ ትምህርት ላይ ይገኛሉ እነዚህን ቃላት በስልካችሁ ባለው 81 ዱ መፅሀፍ ቅዱስ ብታጡት ምዕራፍ ወይም ጥቅሱ
ተሳስቶ ሳይሆን በስልካችሁ ያለው ስለላልተሟላ ነው። ስለሆነም በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት
ቤተመፃህፍት ወይም በቤተክርስቲያን የሚገኙ ሰማንያ አሀዱ መፅሀፍትን በመጠቀም የምታገኙ መሆኑን በትህትና
እገልፃለሁ !

☞ማስረጃ 5.

❀1 ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡2 በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ የእግዚአብሔር
ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት 4፡12 የተገኘ ነው፡፡

☞ማስረጃ 6.

❀በዮሐንስ ወንጌል 10፡22 በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ … ‹‹የመቅደስ መታደስ በዓል›› በሌሎቹ
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አናገኘውም በመጽሐፈ መቃብያን 4 ላይ ብቻ ነው የምናገኘው፡፡

☞ማስረጃ 7.

❀በ ሮሜ 13፡1 ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ
ናቸው። የሚለው ኃይለ ቃል ከሲራክ 17፡14 የተወሰደ ነው፡፡

☞ማስረጃ 8.
❀አዳምና ሔዋን አቤልና ቃየልን ወለዱ፡፡ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ይላል ዘፍጥረት 4፡17 በ 66 ቱ መጽሐፍት ላይ
ስለ አቤልና ቃየል መወለድ እንጂ ሌላ የሰው ዘር በምድር ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አያወራም፡፡ ታድያ ይህቺ የቃየል
ሚስት ከየት መጣች ስለስዋ ምንም አይናገርም በአለም ላይ የነበሩ ሰዎች አራት ብቻ እንደነበሩ ነበር የምናነበው፡፡ የዚህን
መልስ የምናገኘው በኩፋሌ 5፡8-17 ላይ ነው፡፡

☞ማስረጃ 9.

❀- ይሁዳ በመልዕክቱ ‹‹የሄኖክን ትንቢት ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሶ›› ጽፎታል (ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥
ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች
በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ይሁዳ
1፡14-15) መጽሐፈ ሄኖክ ደግሞ በስልሣ ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡ እንግዲህ ያልተጻፈውን ከልቡናው
አንቅቶ ሄኖክ እንዲህ ብሎ ተናገረ ብሎ ዋሸ አይደለም በእውነት መሠከረ እንጂ፡፡

- ይህን ስለ ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረውን ትንቢት ይሁዳ ሲጽፍልን/ሲነግረን ትንቢቱ
ምን እንደነበረ፣ ከመጽሐፈ ሔኖክ / 81 ዱ መጻሕፍት/ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 1፡9፡፡

☞ማስረጃ 10.

❀1 ኛ ቆሮ. 10፡9 ‹‹ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን›› የሚለው
ቃል ከዮዲት 8፡24 የተገኘ ቃል ነው፡፡

✿ቁልፍ ቃል

☞ መፅሀፈ ሄኖክ ፣መፅሀፈ ሲራክ፣መፅሀፈ ጥበብ . . . የእነዚህ እነና የመሳሰሉትን ከሰማንያአሀዱ የተወጣጡ የመፅሀፍ
ቅዱስ ጥቅሶች በዚህ ትምህርት ላይ ይገኛሉ እነዚህን ቃላት በስልካችሁ ባለው 81 ዱ መፅሀፍ ቅዱስ ብታጡት ምዕራፍ
ወይም ጥቅሱ ተሳስቶ ሳይሆን በስልካችሁ ያለው ስለላልተሟላ ነው። ስለሆነም በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ የሰንበት
ትምህርት ቤት ቤተመፃህፍት ወይም በቤተክርስቲያን የሚገኙ ሰማንያ አሀዱ መፅሀፍትን በመጠቀም የምታገኙ መሆኑን
በትህትና እገልፃለሁ !

☞ማስረጃ 11.

✿የዮሐንስ ወንጌል 7፡7 ‹‹ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና እኔን
ይጠላኛል።›› የሚለው የ አምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በጥበበ 2፡13 ላይ ይገኛል፡፡

☞ማስረጃ 12.

✿ት.ኤር. 39፡16 ስለ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ የተነገረው ትንቢት (ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ
በለው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች
ከተማ ላይ አመጣለሁ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል። በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በምትፈራቸው
ሰዎች እጅ አልሰጥህም። ፈጽሜ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፥ በእኔ
ታምነሃልና፥ ይላል እግዚአብሔር፦) የሚለው ትንቢት ፍጻሜውን የምናውቀው በተረፈ ኤርሚያስ ከምዕ.8 ጀምሮ
ስናነብ ነው፡፡
☞ማስረጃ 13

✿1 ኛ ቆሮ. 15፡32 ‹‹ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ።›› የሚለው ቃል
ከጥበብ 2፡6 የተገኘ ቃል ነው፡፡ (ኑ ተድላ ደስታ እናድርግ በህጻንነታችን ወራት ሳለን ከዚህ ይህ ቀረን በማለት
በሰውነታችን ደስ የሚያሰኘንን ስራ እናድርግ)

☞ማስረጃ 14

✿የሉቃስ ወንጌል 16፡9 ‹‹እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ
ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።›› የሚለው ትምህርት በ መጽሐፈ ሲራክ 14፡13 ላይ ይገኛል፡፡ (ሳትሞት ለባለእንጀራህ በጎ
ነገር አድርግ እጅህንም ዘርግተህ የተቻለህን ያህል ስጥ፡፡)

☞ማስረጃ 15

✿በዕለተ ሆሳዕና ዘንባባ ይዘው ጌታችንን የኢየሩሳሌም ሰዎች ሲያመሰግኑት ውለዋል

( ማቴ. 21፡9-15 ‹‹የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤
ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም። ሆሣዕና
ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው። ማር. 11፡9-10 ‹‹የሚቀድሙትም የሚከተሉትም።
ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤
ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ዮሐ. 12፡13 ‹‹የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና። ሆሣዕና፤ በጌታ
ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።)

የዚህ ታሪካዊ ትውፊት አመጣጥ የሚገኘው በዮዲት 15፡12 እና በኩፋሌ 13፡21 ላይ ነው፡፡

☞ማስረጃ 16

✿1 ኛ የጴጥ. 1፡24 ‹‹ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤››
የሚለው ቃል ከሲራክ 14፡18 የተገኘ ነው፡፡ (ቅጠሉ ጭፍቅ ያለ የእንጨት ቅጠል የመጀመሪያው ቅጠል እንዲረግፍ
ደማዊና ስጋዊ ፍጥረት ሁሉ እንዲሁ ነው ይህ ይወለዳል ያ ይሞታል)

እንግዲህ ከነዚህ ማስረጃዎች የምረዳው ሐዋርያት፣ ነብያት፣ ቀደምት አበው ሁሉ ያስተምሩ የነበሩት ከ 46 ቱ የብሉያት
መጽሐፍ እየጠቀሱ እንደነበር ነው፡፡ ለዚያውስ እነሱ (መናፍቃኑ) የተለያዩ የሞት ፍልስፍና የያዙ መጻሕፍትን እያጻፉ
አንብቡ እያሉ ይበትኑስ የለ ታዲያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ መጽሐፍ አታንብቡ ካሉ እነሱ ለምን ሌላ መጽሐፍ እየጻፉ
ያሰራጫሉ ወይስ ትንቢቱ ለኦርቶክሳውያን ብቻ ነው የተነገረው ይሄ ለማጭበርበር ነውና የእግዚአብሔር መንፈስ
ያለባቸውን መጻሕፍት መርምረን እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትን የያዙ ከሆነ አንብበን ልንረዳና ልንመራባቸው
ተፈቅዶልናል፡፡

እንግዲህ ድርሣናትም ሆኑ ገድላት ስለ እግዚአብሔር አዳኝነት ታላቅነት የሚገልጹ ስለሆነ የእግዚአብሔር መንፈስ
ያለባቸው መሆናቸው የተረጋገጠ ነው፡፡ ጳውሎስ ስልሣ ስድስቱን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ተጠቀም አላለም፡፡ ገደብ
ሳያደርግ የእግዚአብሔር መንፈስ ያባቸው በቅዱሳን አባቶችም ሆነ በሌሎቹ ክርስቲያኖች የተጻፉትንም መንፈሳዊ
መጻሕፍት አለ እንጂ፡፡ በዚህም ምክንያት ሃዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተጨማሪ የብሉይኪዳን መጻሕፍትንና
የትውፊት መጻሕፍትን ትቀበላለች ታስተምራለች፡፡

~~~ተፈፀመ~~~

☞ይህንን ለመናፍቃን መልስ የሆነ ትምህርት ስንቶቻችሁ ተከታትላችሁታል ?? ትምህርቱስ ጠቅሞአችኋል ?

ሰብሐት

✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥

✣ ለአብ ✢

✣ ለውልድ ✣

✣ ለመንፈስ ቅዱስ ✣

✥┈┈•◦◈◎❖◎◈◦•┈┈✥

♥ወስብሃት ለእግዚአብሔር♥ ♥ወለወላዲቱ ድንግል♥ ♥ወለመስቀሉ ክቡር♥

አሜን!!

You might also like